#ተአምረተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
ሰሚራ ለዚህ ሀሳብ ውል ሳታበጅለት ማደር አልፈለገችም….. ቦርሳዋን አንጠልጥላ ተመልሳ ወደስራዋ ቦታ ተመለሰች….መመለሷ ምን እንደሚጠቅማት ለራሷም አልገባትም ..ግን በቃ ተመለሰች..እንደደረሰች ቀጥታ መላኩ ወደተኛበት ክፍል ነበር የገባችው…በሽተኛው የተኛበት ክፍል ውስጥ የተኙ ሌሎች ሶስት ታካሚዎችና እነሱን የሚያስታሙም አስታማሚወች ነበሩ…
ቀጥታ ወደተኛበት አልጋ ተጠግታ አስተዋለችው…አይኖቹ እንደተጨፈኑ ናቸው… ጥቁር ፊቱ ላይ የሰላምና የመረጋጋት መንፈስ አርብቦበታል…በታዋቂ ቀራፂ በጥንቃቄ የተቀረፀ የሚመስለው አፍንጫው ለፊቱ ውበት አጎናጽፎት ትልቅ ግርማ ሞገስ ሆኖታል…የዓይኖቹ ሽፋ ሽፍቶች ድምቅ ያሉና የተለየ ስሜት የሚያጭሩ ሆነው ነው ያገኘቻቸው..
‹‹እንዴ እስከዛሬ ለምን እንደዚህ እትኩሬ አላስተዋልኩትም…..?›› ስትል እራሷን ጠየቀች ….እስከዛሬ ባለ እይታዋማ ከማንኛውም በሽተኛ የተለየ ምንም ነገር አልነበረውም….አሁን ግን ሁኔታዎች ተቀያይሩባት..አሁን ስሩ ቆማ የምታየው ጥቁር ቆንጆ ወጣትን ለመግደል ግማሽ ሚሊዬን ብር ተቀብላለች…ስለዚህ አሁን ለእሷ ዝም ብሎ ሰው አይደለም….‹‹ደግሞ እንዴት አባቱ ነው የሚያምረው ….…..?››አለችና ክፍሉን ለቃ ወጣች …
ወደ ዶክተር እስክንድር ቢሮ …ዶ/ር እስክንድር በእሷ እድሜ ክልል የሚገኝ አስተዋይ ወጣትና ጓደኛዋ ነው ..ይሄንን ነገር በምትፈልገው መጠን ሊረዳት እንደሚችል ያሰበችው እና ሚስጥር ጠባቂ ነው ብላ ያመነችው እሱን ነው፡፡እሱን ብቻ፡፡
ቢሮው ብቻው ቁጭ ብሎ የበሽተኞችን ፋይል እየመረመረ ነበር ያገኘችው….
‹‹እንዴ ወደቤት የሄድሽ መስሎኝ?››
‹‹ሄጄ ነበር››
‹‹ታዲያ ምን ገጠመሽ እና ተመለሽ…?››
‹‹ታአምር ተፈጥሮ››
‹‹እስቲ ቁጭ በይ እና ተአምሩን ንገሪኝ .››
በድካም ስሜት ከፊት ለፊቱ ያለውመን ወንበር ስባ ቁጭ አለች….
‹‹እሺ አጫውቺ……..?ምን ተፈጠረ…..?››
‹‹እንድታግዘኝ ነው የመጣሁት… በጣም እርዳታህን እፈልጋለሁ…››
‹‹አልገባኝም ምንድነው የምረዳሽ…..?››
‹‹ልናግር አይደል››
‹‹እያዳመጥኩሽ ነው››አላት ትኩረቱን ሰብስቦ ተመቻችቶ እየተቀመጠ
ከሰዓታት በፊት ያጋጠማትን እና እያበረረ ወደእሱ ያስመጣትን ጉዳይ ከመጀመሪያው አንስታ በዝርዝር አስረዳችው…በገረሜታ አፉን ከፍቶ አዳመጣት…ስትጨርስ
‹‹ወይኔ ጉዳችን.!!!.እንዴት ቼኩን ትቀበያለሽ…..?››
‹‹አልቀበልም ብል ዝም ሚሉኝ ይመስልሀል…ሚስጥራቸውን እንደማጋልጥባቸው ስለሚጠረጠሩ ሊያጠፍኝ ይችላሉ ብዬ ፈራኋ…››.
‹‹እሱስ ትክክል ነሽ …ለገዛ ዘመዳቸው ያላዘኑ ላንቺ አይመለሱም…..እና ምን እናድርግ›መልሶ እሷኑ ጠየቃት፡፡
‹‹እርዳኛ››
‹‹እኮ እንዴት ልርዳሽ…?››
‹‹እኔ እንጃ››
ትኩር ብሎ በጥርጣሬ አይን አይኗን እየያያት ቆየና‹‹…ልጅን እንዲሞት ትፈልጊያለሽ እንዴ….?ማለቴ በመግደል እንዳግዝሽ ነው የምትፈልጊው…..?››ሲል ጠየቃት
‹‹አረ በአላህ…..!!እንዴት እንደዛ አሰብክ..…..?››
‹‹እኔ እንጃ… ምን አልባት ብሩ ብዙ ስለሆነ….››ንግግሩን አላስጨረሰችውም
‹‹የፈለገ ብዙ ብር ቢሆን ይህን ለግላጋ ጥንቅሽ ወጣት ለመግደል ጭካኔውን ከየት አመጣለሁ…..?››
‹‹እንዴ ለግላጋ ወጣት ነው ያልሺኝ..…..? ቆንጆ ነው እንዴ..…..?››
ከንግግሩ ተነስታ የተናገረችውን ነገር በምልሰት ስታስታውስ እፈረት ተሰምቷት ‹‹….አንተ ደግሞ በዚህ ሰዓት እንዲህ አይነት ቀልድ ይቀለዳል…..?››አለችው
‹‹ቀልድ እኮ አይደለም ..አንቺው ስላልሽ ነው…ለግላጋ ባይሆን እንዲሞት ትፈቅጂ ነበር ማለት ነው.…..?ንግግርሽ እኮ እንደዛ የምትይ ነው የሚመስለው››
‹‹ይሁንልህ እስቲ አሁን እንዴት እናድርግ….…..?››
አምስት ለሚሆኑ ደቂቆዎች ሁለቱም በየፊናቸው አሰብ …ከዛ ደ/ር እስክንድር ከሀሳቡ ባኖ በፈገግታ መናገር ጀመረ‹‹…አሪፍ ሀሳብ መጣልኝ ››
‹‹ምን አይነት ሀሳብ ንገረኝ……..?.››
‹‹አሁን አልነግረሽም… መጀመሪያ እራት ጋብዢኝ››
‹‹ንገረኝና ጋብዝሀለሁ…..?››
‹‹እዚህ አልነግረሽም… በዘመናችን ምንም በነፃ የሚሰጥ ነገር የለም….ሁሉም ነገር ያስከፍላል…ስለዚህ ጋብዢኝና ልንገርሽ ወይም ደግሞ ይቅርብሽ››
‹‹ይሁንልህ እሺ … አሪፍ ምክር ይሁን እንጂ በደስታ ጋብዝሀለሁ››
‹‹አይ አንቺ ብዙ ቀን ጋብዢኝ ብዬሽ አሻፈረኝ ብለሽ ነበር..ዛሬ እጄ ገባሽ›››
‹‹ስለተሳካልህ እንኳን ደስ ያለህ››አለችውና ተያይዘው ወጡ
እራት በልተው እንዳጠናቀቁ ያሰበውን ይነግራት ጀመር
‹እንግደለው››
‹‹ምን አይነት ብሽቅ ሀሳብ ነው››
‹‹ማለቴ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሞተ እንዲመስል እናደረግና መሞቱን አይተው እንዲያምኑ እናድርግ››
ከቁጣዋ መለስ ብላ‹‹ከዛስ?››ስትል በጉጉጉ ጠየቀች፡
‹‹‹ከዛማ በቃ ሳጥን አምጡ እንላቸውና የሆነ ነገር አሽገን እንሰጣቸዋለን….››
‹‹ከዛስ…?››
‹‹ከዛማ ሰውዬውን የሆነ ቦታ ወስደን እስኪድን እንጠብቅና ለምን ሊገድሉት እንደፈለጉ ከራሱ እናጣራለን…ከእሱ በምናገኘው መረጃ የሆነ ነገር እናደርጋለን…ወይም እራሱ ሲድን የሆነ ነገር ያደርጋል››
ተነስታ ተጠመጠመችበት ‹‹..እንዲት ይህ ሀሳብ መጣልህ?››
‹‹እድሜ ለሆሊውድ ፊልም …ሊዚህ ለዚህ ካልተጠቀምንበት ለምን ይጠቅመናል?››
‹‹እና መቼ እናድርገው…››
ነገ ተነጋግረን የሚሆነውን እናደርጋለን››
✨ይቀጥላል✨

👍129❤17😁5😱2👎1
#ተአምረተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
በማግስቱ….
ከምሽቱ 1 በሰዓት አካባቢ ነው ሰሚራም ሆነች ዶ/ር እስክንድር የእለቱ የማታ ተረኛ ሆነው ስራቸው ላይ ተስማርተዋል፡፡
ሰሚራ ለመላኩ ዘመዶች ደወለችላቸው…ሰሎሞን ነበር ስልኩን ያነሳው
‹‹ሄሎ››
‹‹ሄሎ..ሰላም ነሽ?››
‹‹አዎ ሰላም ነኝ …እንድትመጡ ፈልጌ ነው››
‹‹ማን…..? ››
‹‹እናንተ ናችሁ…. ሁለታችሁም››
‹‹ለምን…..? ምን ተፈጠረ…..?››
‹‹ላደርገው ነው…ማድረግ የምፈልገው ደግሞ እያያችሁ ነው..እናንተ ባላችሁበት››
‹‹አረ ችግር የለውም ..ሁሉን ነገር ካጠናቀቅሽ በኃላ ብትደውይልን ይሻላል››
‹‹እንደዛ አላደርግም…በቃ አሁን በነፍስ ነው ብዬ እንደደወልኩላችሁ አስቡትና እቤትም ሆነ መንገድ ላይ ለገኛችሁት ሰው እንዲሁም ለሌሎች ዘመዶቻችሁ እየደወላችሁ በነፍስ ነው ተብሎ ተደውሎልናል እያላችሁ ንገሩ ፣እናንተም በ20 ደቂቃ ውስጥ ድረሱ›
‹‹አዎ… በቃ ገባኝ እንመጣለን..ትክክል ነሽ››ስልኩ ተዘጋ
ሁለቱ ብቻ ሳይሆኑ በሌሎች ከስድስት በማያንሱ ሰዎች ታጅበው ለመምጣት ከ15 ደቂቃ በላይ አልፈጀባቸውም…..ሰላም ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሆስፒታሉን አተረማመሰችው….ሰሎሞንም እንባውን እየዘራ ወንድሜን እያለ በማጎራት ግቢውን መዞር ጀመረ…
ለስድስት ቀን በኮማ ውስጥ የሰነበተው መላኩ ምን እንደነካው ከዶክተሩና ከሰሚራ ውጭ ማንም በማያውቀው ምክንያት በጣር ነፍስ ጊቢ ነፍስ ውጭ እያቃተተ ነው…ዶ/ር እስክንድር ሲስተር ሰሚራ እና ሌሎች ሁለት ነርሶች ዙሪያውን ከበው ሊረዱት እየሞከረ ነው..
‹‹ሲስተር ሰሚራ ቶሎ ብለሽ ይሄንን መድሀኒት ውጊው ››ብሎ በወረቀት ላይ የመድሀኒቱን ስም ጽፎ ሰጣት… እሷም ተቀብላ ቶሎ ብላ ወጥታ ሄደችና በሶስት ደቂቃ ውስጥ ይዛ መጣች… መዳሀኒቱን በተንጠለጠው ግሉኮስ ከረጢት ውስጥ በስሪንጅ መጣ ለቀቀችበት ..ቀስ እያለ በቱቦ ውስጥ በመንጠባጠብ ከደም ስሩ ተቀላቀለ…. ከደቂቃዎች በኃላ የበሽተኛው ጣር እየቀነሰ …መንፈራገጡም እያቆመ መጣ….ከዛ ፀጥ አለ …ሰው ሲሸነፍ ወይም ሲያፈገፍግ ፀጥ ይል የለ….ዶ/ር እስክንድር በማዳመጫ ትንፋሹ አዳመጠው…እጆቹና እያወናጨፈ አንገቱና ቀብሮ በብስጭት ክፍሉን ለቆ ወጣ …ኮሪደር ላይ እነ ሰሎሞን እና አጃቢዎቻቸው ከበቡት.
‹‹ዶክተር..እንዴት ነው በሽተኛው…..?››
‹‹ዶክተር ይሻለዋል ..ፍቅሬ ይድናል…..?››
ለበራካታ ሰከንዶች ተገትሮ ሰላምን አፍጦ ከማየት ውጭ ምንም መናገር አልቻለም፣‹‹….….ይቺን ላየ ሰው እነ ሰላም እና መሀደር ምኑን አክተር ተባሉት ?››ሲል በውስጡ አሰበ…መለስ ብሎም ስለራሱ አሰበ …ወየው ጉድ እኔም ለካ ሌላ ተዋናይ ሆኜያለሁ…አለም ሰፊ መድረክ እኛም ኑሪዎቾ ተዋናዬች ነን ያለው ማን ነበር …..? ለካ እውነት ነው…›አለና ወደቀልብ በመመለስ ለእነሱ ጥያቄ መልስ መስጠት ጀመረ
‹‹አዝናለሁ የተቻለንን አድርገናል…ግን አልተሳካልንም..አርፏል ››ብሎ በተገተሩበት ጥሎቸው እግሮቹን አንቀሳቀሰ … ግቢውን በጩኸት እና በለቅሶ ሲያደበላልቁት በውስጡ እየተጠየፋቸው እና እየረገማቸው ጥሎቸው ወደ ቢሮው ሄደ
ሰላም…
..ፍቅሬ ፍቅሬ…
እንጋባለን ብለሀኝ አልነበረ ወይ…
ሙሽራዬ ነሽ አላልከኝም ነበር ወይ..
ለማን ተውከኝ..ለማን ተውከኝ
ሰሎሞን……
ወንድም ጋሻዬ ….ወንድም ጋሻዬ
የእኔ ብቸኛ..የእኔ ብቸኛ
የአባቴ ምትክ ..የአባቴ ምትክ
የዓይን ማረፊያዬ….
/////
ከደቂቃዎች በኃላ ሬሳው እየተገፋ ተመላካቹን በእንባ በሚያራጭ እንግሩጉሮአዊ ዜማ እና አንጀት በሚበላ ሁኔታ በሚያለቅሱት እና ኩርምት ጭብጥ በሚሉት በወንድሙ ሰሎሞን እና በፍቅረኛው ሰላም መካከል አልፎ ወደሬሳው ክፍል ተወሰደ…..ሰሚራም እየተንቀጠቀጠች እና እየዘገነናት እራሷን ለማረጋጋት በትርምሱ መሀል ተሹለክልካ ከሁሉም ነገር በመሸሽ ቢሮዋ ገብታ ተሸጎጠች
እስከአሁን የሰራችው ስራ እና የፈጠረችው ተግባር ትልቅ ድንጋጤ ውስጥ ከቷት እየተንቀጠቀች ነው..የሚገርመውና ይበልጥ የሚጨንቀው ግን ከአሁን በኃላ የምትሰራው ስራ ነው…
በበቀልም ሆነ በጥላቻ ተነሳስቶ ሰውን ድፍት አድርጎ መግደል በጣም ቀላል ነው…ሳያስበው በሆነ ብረት ማጅራቱን መጠቅለል እና ዝርግፍ ብሎ ሲወድቅ ጭንቅላቱን በድልዱም ብረት መድገም ነው…አዎ እንደዛ ማድረግ ቀላል ነው… የሚከብደው ከገደሉት በኃላ ያለው ነገር ነው፡፡ሬሳውን ምን ላድርገው…?ግቢው ውስጥ ቆፍሬ ልቅበረው..….?ረሀብ ያንገላታው ውሻ ቆፍሮ አውጥቶ ቢያጋልጠኝስ…?በጆንያ አድርጌ ከከተማ አውጥቼ ራቅ ያለቦታ በመውሰድ ጫካ ውስጥ ልጣለው…?.መንገድ ላይ ፖሊስ ለፍተሻ ቢያስቆመኝስ……..?እንደዛ ሳደርግ ሰው ቢያየኝስ……..?ስቃይ ነው….በዛን ቅጽበት ከሟቹ በላይ ገዳዩ ያሳዝናል…በተለይ ገዳዩ እንደእሷ አማትር ገዳይ ሲሆን ......ሁኔታው እንደቅዣት ሆኖባት፤ በውስጧ ስትብሰለሰል ስልኳ ተንጫረረ….
ከፈጣሪ የተደወለባት ነው የመሰላት….በርግጋ ከተቀመጠችበት በመነሳት ተፈናጥራ ቆመችና የደዋዩን ማንነት ለደቂቆች አትኩራ ተመለከተች…. በፈራ ተባ ስሜት አነሳችው
‹‹አቤት››
‹‹የት ገባሽ…..?››
‹‹አለው ፈርቼ ቢሮዬ ቁጭ ብዬ ነው››
‹‹ምን ያስፈራሻል.…..?.››
‹‹እንዴ ድመት እኮ አይደለም ሰው ነው ያስገደላችሁኝ…..››
‹‹ማለቴ መግደልሽን ማን ያውቃል..…..?እንደውም ስትፈሪና ስትንቀጠቀጪ የስራ ባለደረቦችሽ እንዳይጠረጥሩሽ…በተለይ ዶክተሩ እንዴት ሞተ ……..?ይሞታል ብለን አልገመትንም ነበር ሲል ሰምቼዋለሁ››
‹‹እ!! እንደዛ አለ እንዴ…..? ››
‹‹አዎ ብሏል…ለማንኛውም አሁን ምን እናድርግ.››
‹‹ምን ለማድረግ አሰባችሁ?››
‹‹ሬሳውን አሁኑኑ ብትሰጡንና በጥዋቱ ቶሎ ብለን ብንቀብረው ጥሩ ነው፡፡››
‹‹ሬሳውንማ ላሰጣችሁ አልችልም …ጥዋት ነው መውሰድ የምትችሉት››
‹‹አይ አሁኑኑ መውሰድ አለብን… አሁን ሬሳ ሳጥን ገዝተው እንዲመጡ ሰዎች ልኬያለሁ…አንቺ ብቻ ደክተሩን አሳምነሽ እንዲፈርምልኝ አድርጊ…››
‹‹ዶክተሩ እኮ መሞቱን ብቻ ነው የሚያረጋግጥልህ….ሬሳውን በዚህ ምሽት እንድታወጣ የመፍቀድ ስልጣን ያላቸው ግን ሌሎች ናቸው››
‹‹ሌሎቹን ተያቸው ..ዶክተሩ ብቻ ካስፈረምሽልኝ ካንቺ ምንም አልፈልገም…..ወደቤትሸ ሄደሽ ተረጋግተሸ በድል መተኛት ትችያለሽ…የስራ ኮንትራታችንን እዛ ላይ ይጠናቀቃል….››
‹‹እዛ ላይማ አይጠናቀቅም … መቶ ሺ ብር ጨምርልሻለው ብለኸኝ ነበር››
‹‹ሀይለኛ ብር ወዳድ ልጅ ነሽ… አይዞሽ አረሳሁትም ግን እንደምታይኝ አሁን ሀዘን ላይ ነኝ ፡፡ ከሶስት ቀን በኃላ ያው እንደምንም መጽናናቴ ስለማይቀር አቀብልሻለሁ…››
‹‹ዋ እንዳትረሳ››
‹‹አረሳም አሁን ያልኩሽን ጨርሺና ደውይልኝ››
ስልኩ ተዘጋ……

👍122❤13👎9👏4🔥1🥰1
#ተአምረተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
አንቺ ወደሬሳ ማቆያው ቀድመሽ ሂጂና ሁኔታውን አመቻቺ… እኔ ቀስ ብዬ በጓሮ በኩል ሄጂ የግቢውን መብራት አጠፋለሁ…ጄኔሬተሩንም አቶማቲኩን ስላበላሸሁት ሄደው አስተካክለው እስከሚያበሩት 10 ደቂቃ ይኖረናል..በዛ ጊዜ ውስጥ ይዘነው እንሄዳለን››
‹‹እሺ ግን ተጠንቀቅ…. ሰው እንዳያይህ››
‹‹እጠነቀቃለሁ..እንቺ ልክ መብራቱ እደጠፋልሽ ቶሎ አዘጋጂውና ከጋሽ ተካ ጋር ይዛችሁት በጎሮ በኩል መኪና መቆሚያው ድረስ ይዛችሁት ኑ..እኔ የመኪናዬን ሞተር አስነስቼ ዝግጁ ሆኜ እጠብቃችኋለው…››
ተስማምተው እሱ ወደጎሮ መብራቱን ሊያቆርጥ እና ግቢውን በጨለማ እንዲዋጥ ሊያደርግ እሷ ደግሞ በሽተኛውን ልትረከብ ወደሬሳ ማቆያ ክፍል ሄደች
መብራቱም ጠፍቶ እነሱም ሬሳውን(በሽተኛውን ) ይዘው በመምጣት በመኪና ውስጥ አድርገው የውጭ ጥበቃዎችን በጥበብ አልፈው ግቢውን ለቀው ለመውጣት 8 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀባቸው..
ደ/ር እስክንድር ቀጥታ የነዳው ለዚሁ ጉዳይ ታስቦ ወደተዘጋጀ ዛሬ ጥዋት ወደተከራዩት አፓርታማ ነበር….ይህን ቤት የተከራዩበት ዋና ምክንያት የሰሚርን ቤት የበሽተኛው ዘመዶች ያውቁታል..እሱ ቤት እንደይወስዱት ደግሞ ከቤተሰቦቹ ጋር ነው የሚኖረው…. በዚህ ምክንያት የግድ ማንም የማያውቀው እና ሰወር ያለ ቦታ ቤት መከራየት ነበረባቸው….
እንደደረሱ….ያው እንደሬሳ ድርቅርቅ ያለውን በሽተኛ ለሁለት እንደምንም ተጋግዘው ከመኪናው አወረዱትና ከሆስፒታል ባመጡት ተሸከርካሪ ጋሪ እየገፉ ወደቤት አስገቡትና …መኝታ ቤት የሚገኝ አልጋ ላይ ዘረሩት….
ይሄንን ሁሉ እስኪያደርጉ በመካከላቸው በስሜት ከመግባባት እና በምልክት መልእክት ከመለዋወጥ ውጭ ቃላት አልወጣቸውም ነበር….ሁለቱም በተመሳሳይ ሁኔታ በድን ሆነዋል
‹‹በይ ቶሎ መድሀኒቶቹን አምጪልኝ…››ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ዓ.ነገር ነበር
ሮጣ ሄደችና ካስቀመጠችለት በማምጣ ፊቱ ያለው ጠረጵዛ ላይ ዘረገፈችለት…
ሁለት መድሀኒቶችን ቀላቅሎ በመርፌ ክንዱ ላይ ወጋው….እና ከጎን ያለ ወንበር ሳብ በማድረግ አልጋውን ተጠግቶ በመቀመጥ የሚሆነውን መጠበቅ ጀመረ..ሰሚራ ተገትራ አይኖቾን የተዘረረው ሬሳ ላይ እንደሰካች ነው…ዶክተርም ቁና ቁና እየተነፈሰ በየሰከንዶች ልዩነት ሰዓቱን እያየ ይቁነጠነጣል..ሰዓቱ ደግሞ መንቀርፈፉ….
‹‹ምነው ዝም አለ…..?››ሰሚራ ጠየቀች
‹‹እኔ እንጃ …መድሀኒቱ በመላ ሰውነቱ እስኪሰራጭና እስኪሰራ 5 ደቂቃ ይወስድበታል››
‹‹ታዲያ ከሰጠሀው እኮ ቆየ…..?››
‹‹መስሎሽ ነው …ገና ሁለት ደቂቃ ነው››
‹‹ሁፍ!!! ሁለት ደቂቃ ማለት ግን ስንት ነው…..?››
‹‹ሁለት ደቂቃ ማለትማ ያው ሁለት ደቂቃ ነው..ግን አንዳንዴ እንደዚህ ይበረክታል››አላት በደመነፍስ
…አይደርስ የለ 5 ደቂቃ ሞላ በሽተኛው ንቅንቅ አልል አለ….
‹‹ምን ይሻላል..…..?የሆነ ምልክት ማሳየት ነበረበት››ደ/ር እስክንድር ነው ግራ በመጋባት ለራሱ ይሁን ለሰሚራ በማያስታውቅ ስሜት ያወራው
‹‹አረ የሆነ ነገር አድርግ..ወይኔ ተዋረድን››
‹‹ቆይ እስቲ ተረጋጊ …ይበልጥ ግራ አታጋቢኝ..››አለና ፊት ለፊቱ ካለ ጠራጴዛ ላይ ከተዘረገፉት መድሀኒቶች ውስጥ አንዱን መርጦ በፊት ከወጋው በተቃራኒ ባለው ክንዱ ላይ ወጋውና በተመሳሳይ ሁኔታ ውጤቱን መጠበቅ ጀመረ….
አንድ ደቂቃ..ሁለት ደቂቃ…ሶስት ደቂቃ…ምንም የለም..በድን ሬሳ…
‹‹ወይኔ ተበልተናል…ምንድነው የተሸወድኩት…..?››
‹‹እኔ ምን አውቃለሁ…መድሀኒቱ አስተማማኝ ነው …አውቀዋለሁ ብለህኝ ነበር…..?››
‹‹አዎ ብዬሽ ነበር..ግን አልሆነም››
‹‹ግን አልሆንም ትለኛለህ እንዴ……?ስለሰው ህይወት እኮ ነው እያወራን ያለነው..ገና አለምን በቅጡ መኖር ስላልጀመረ ወጣት››
‹‹መቼስ ይሄ እንዲሆን ፈልገን አይደለም..እንደውም በተቃራኒው የእሱን ህይወት ለማትረፍ ነው እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ የገባነው..ሞክረናል ግን አልቻልንም››
‹‹መቻል ነበረብን …››ከ20 ደቂቃ በላይ ተገትራ ከቆመችበት ቦታ ተነቃነቀችና ወደእሱ ቀረበች ….እሱም ምን ሊፈጠር ነው በሚል ስጋት ከተቀመጠበት ተነሳና ፊት ለፊቷ ቆመ
እንባዋን እያዘራች….‹‹ልታድነው ይገባ ነበር …መሞት አልነበረበትም…ከባድ ስህተት ነው የፈፀምነው…››ደረቱን እየመታች በመንሰቅሰቅ እቅፉ ውስጥ ገባች፡
‹‹አንቺ ምን አደረግሽ..…..?ከምትችይው በላይ ልትረጂው እየሞከርሽ ነበር›››
‹‹አይ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ነበር መሄድ የነበረብኝ…የማይሆን ነገር ነው የሞከርኩት …..››
‹‹የት ነው ያለሁት…..?››ያልታሰበ ከሩቅ የሚመስል ድምጽ ተሰማ…. ሁለቱም በድንጋጤ ፈዘው ወደአልጋው መመልከት ጀመሩ ....መላኩ በተኛበት እልጋ ላይ አይኖቹን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገ ዙሪያ ገባውን ሲቃኝና በጥያቄ አስተያየት ሲያይ ተመለከቱት
‹‹ወይኔ በአላህ ነቃ ..አደረከው ..አደረከው..››ደ/ር ላይ ተጠመጠመችበት….ለቅሶዋን ማቋረጥ አልቻለችም….ከሳቅ ጋር የተቀላቀለ የደስታ እንባ
‹‹የት ነው ያለሁት…..?››በሽተኛው ጥያቄውን ደገመው
‹‹አይዞህ… እኔ ሲስተር ሰሚራ እባላለሁ…እሱ ደግሞ ጎደኛዬ ነው ዶ/ር እስክንድር ይባላል…ያንተን ጤንነት የምንከታተለው እኛ ነን››
‹‹ምን ሆኜ ነው…..?››
‹‹አይዞህ ጥቂት ጉዳት ደርሶብህ ነበር.. አሁን ተርፈሀል….››
‹‹ሰላሜስ…..?ሰላምን ጥሪልኝ..››
‹‹አይዞህ ጠራታለሁ .አሁን ራስህን አታድክም .››
‹‹ጥሩ…ልኝ..››እያለ ወደ እንቅልፍ አለም ገባ
‹‹መተኛቱ ጥሩ ነው….ይገርማል የሰጠነው መድሀኒት ከሞት ብቻም ሳይሆን ሰሞኑንም ከነበረበት ኮማ ጭምር ነው መንጭቆ ያወጣው….እንዲህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር….ግን አሁን መልሶ ከእንቅልፉ ሲነቃ ስለፍቅረኛው እና ስለወንድሙ እንዴት ታስረጂዋለሽ…..?››
‹‹አታስብ ዋናው ወደ ህይወት መመለሱ ነው… ሌላው እዳው ገብስ ነው… የሆነ ዘዴ አላጣም..አንተ ግን ድንቅ ሰው ነህ››
‹‹አረ ድንቅነት በአፍንጫዬ ይውጣ ..ሁለተኛ እንዲህ አይነት ቅብጠት አይዳዳኝም …እንዴ ነፍሴ በአፍንጫዬ ልትወጣ እኮ ነበር››
‹‹ይቅርታ አጨናነቅኩህ አይደል…..?››
‹‹አጨናነቅኩህ ብቻ..ልትውጪኝ እኮ ነበር…ይሄ ልጅማ እንዲህ በቃላሉ ከዚህ ቤት የሚወጣ አይመስለኝም››
‹‹ምን ማለት ነው…..?››
‹‹እኔ እንጃ አይነ ውሀሽ አላማረኝም…ለማንኛውም በየስድስት ሰዓት ልዩነት ይሄንን መድሀኒት ስጭው…ችግር ካለ ደውይልኝ አሁን እኩለ ለሊት ከማለፉ በፊት ወደቤቴ ልሒድ››
‹‹ስላደረክልኝ ነገር በጣም አመሰግናለሁ..ና ልሸኝህ››
‹‹አረ ግድ የለም….ነገ መቼስ ስራ አትመጪም››
‹‹አረ የዓመት ፍቃድ እጠይቃለሁ..እስኪሻለው ለማን ጥዬው እሔዳለሁ…?››
…ፈገግ ብሎ እየሳቀባት ቤቱን ለቆላት ሄደ
.በደንብ እስኪሻለው 15 ቀን ፈጀበት..የሆነውን ነገር እና ፍቅረኛውና ወንድሙ ምን እንዳደረጉት የነገረችው እቤቷ በወሰደችው በ3ተኛ ቀን ነበር..የመከዳቱን ነገር ከሰማ በኋላ ለቀጣዬቹ ሶስት ቀናት ህመሙ አገርሽቶበት ለምን ነገርኩት…..? ብላ እስከምትፀፀት ድረስ ነበር እንዲቆጫት ያደረገት..በኋላ ግን ቀስ በቀስ እያገገመ መጣ ..ሲቆይ በእሷ እንክብካቤ እና ማበረታታት ተሻለው….

👍92❤18🥰5😁4
#ተአምረተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
በ25ኛው ቀን ጥዋት ቁርስ ከበሉ በኃላ
‹‹ዛሬማታ ልሄድ ነው››
‹‹የት ነው የምትሄደው…..?››ደንገጥ ብላ ጠየቀችው ሰሚራ
‹‹ከከተማ ወጣ ብዬ ትንሽ ራቅ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማሰብ እፈልጋለሁ….››
‹‹ስለምንድነው የምታስበው..…..?ክፉ ነገር አይደለም አይደል…..?››
‹‹እኔ እንጃ …ለጊዜው ምንም የመጣልኝ ነገረ የለም..እንደገደሉኝ ልግደላቸው…ወይስ ይቅር ልበላቸው …..?የማውቀው ነገር የለም…ገንዘቤን ግን ልጅነቴን የሰዋሁበትና ብዙ ፈተና ያየሁበት ስለሆነ ሰባራ ሳንቲም እንደማልተውላቸው እርግጠኛ ነኝ..ምን አልባት እስከዛው በደንብ ቢደሰቱበት ጥሩ ነው››
‹‹እንዴት አድርገህ ታስመልሳቸዋለህ……..?አሁን እኮ ንብረትህ በእነሱ እጅ ነው..በህይወት መኖርህን ካወቁ ባለ በሌለ ኃይላቸው ነው አሳደው የሚያስገድሉህ››
‹‹አይዞሽ አታስቢ… እጠነቀቃለሁ….ለዛም ነው ከዚህ ከተማ ራቅ ብዬ በጽሞና ምን ማድረግ እንደምችል ማሰብ አለብኝ የምልሽ››
‹‹ካልክ እሺ ..ቆይ መጣሁ›› ብላ ከነበሩበት ሳሎን ተነስታ ወደመኝታ ቤቷ ከሄደች ከ5 ደቂቃ በኃላ ተመልሳ መጣችና ቼክ እጁ ላይ አስቀመጠችለት፣..ግራ ገብቶት አንዴ የሰጠችውን ቼክ አንዴ ደግሞ እሷን በማፈራረቅና በመገረም ሲያያት ከቆየ በኃላ
‹‹ምንድነው ይሄ…..?››ጠየቃት
‹‹የራስህ ብር ነው..አንተን እንድገድልላቸው የከፈሉኝ ነው…ሁኔታዎችን እስቲስተካከሉልህ ለመንቀሳቀሻ ይሆንሀል››
‹እንዴ ምን አይነት ሰው ነሽ….?እንዲህ አይነት ሰው እኮ በዚህ ጊዜ አይገኝም››
‹‹አይ እንደምታስበኝ ደግ ሴት ሆኜ አይደለም..ለአንተ ብቻ ነው እንዲህ የሆንኩት..››
በንግግሯ ውስጡ ተነካና‹‹ለእኔ ለምን…..?››ጠየቃት
‹‹እኔ እንጃ….. ›አለችው
..ከተቀመጠበት ተነሳና ስሯ ተንበረከከ..ደነገጠች፡፡ አቀፋት …አንገቷ ሰር ገብቶ ሳማት…. ውርርር አደረጋት፣..አላቆመም… ወደታች አስጎንብሶ ግንባሯን …አይኖቾን… ጉንጮቾን በመጨረሻ ከንፈሯ ላይ ተጣበቀባት…አይኗን ከመጨፈን እና ከንፎሯን ከማነቃነቅ ውጭ ምንም ተቃውሞ አላሰማችም…ደስ የሚሉ እልፍ መሰል ሁለት ደቂቆች አለፉ….
የሚያደርገውን አድርጎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሲቆም እሷ አፍራ አቀረቀረች…
የሰጠችውን ቼክ መልሶ ጉልበቷ ላይ እያስቀመጠላት..ይሄ ምን አልባት እኔን ለገደልሽበት ቢከፍሉሽም.. አንቺ ግን እኔን ለማዳን ለህክምና ይሄን ቤት ለመከራየት ላወጣሽው ወጪ መሸፈኛ ይሁንሽ…ውለታሽ ግን በዚህ ብር የሚመለስ ወይም የሚጣጣ ፍጽም አይደለም…በሕወቴም ጭምር ከፍዬ አልጨርሰውም››
‹‹ህይወትህን ስፈልግ ያኔ ትከፍለኛለህ …አሁን ግን ከእኔ ይልቅ አንተ ነህ ችግር ላይ ያለህው … ደግሞ ከራሴ ገንዘብ ምንም ያወጣሁት ነገር የለም…ከዚህ በተጫማሪ መቶ ሺ ብር ቦነስ ብለው ሰጥተውኝ ነበር…እርግጥ ከላዩ ላይ አንተን ለማሸሽ እና የሬሳ ሳጥኑን ቀይረው ለሰጡኝ አቶ ተካ 50 ሺ ብር ከፍያለሁ..ሌላውን 50 ሺብር ደግሞ እስከአሁን እየተጠቀምኩበት ነው ፡፡››
‹‹አይዞሽ ለእኔ አትስቢ አልኩሽ እኮ …እነሱም ሆነ ማንም የማያውቀው 5 ሚሊዬን ብር ባንክ አለኝ…..በዛ እጠቀማለሁ፡፡››
‹‹ግን ባረብሽህ ምትሄድበት ይዘህኝ ብትሄድ …..?››
‹‹አረ ደስ ይለኛል..ስራሽን ብዬ እኮ ነው…..?››
‹‹ስራው ይደርሳል››
‹‹በያ ተዘጋጂ….መኪና እንከራይ ››
‹‹ወደየት ነው ግን ምንሄደው…..?››
‹‹እግራችን ወደመራን….››

👍112❤9👎5👏2
#ተአምረተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
የጊቢዋ አጸድ ውስጥ ባለ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ የወፎችን ዝማሬ እና የዛፎችን ሽውሽውታ እየታዘበች በሀሳብ እየናወዘች ነው፡፡ያው በህይወቷ አዲስ ክስተት ተከስቷል … አንድ ሰው ላይ ለቀናቶች ሀሳቧ እንደተጣበቀ ነው….ያ ባሪያ ልጅ ልቧን ቅልጥ ሀሰቧን ውስውስ ነው ያደረገባት፡፡ሰሚራ ከምትባለው ፍቀረኛው ጋር ያለውን ታሪክ እና የፍቅር ትስሰር ሙሉውን ታሪክ ለመጨረስ እራሱ አቅም አነሳት...ስለሱ ከማሰብ የሚያሰንፋት መስሎ እየተሰማት ነው….‹‹ለማንኛውም እስቲ ታሪኩን ልጨርስ›› ብላ ተቀመጠች …ግን ታሪኩን ለመጨረስ ንስሯ ያስፈልጋታል..እንደምታየው ደግሞ አሁን ጊቢ ውስጥ ንስሯ አይታያትም …ብዙም ሳያስጠብቃት ከሄደበት ተመልሶ መጣ
ቀጥታ ወደዛ ወደተለከፈችበት ታሪክ አመራች …አእምሯዋን ከንስሯ አዕምሮ ጋር በተለመደው መንገድ አቆራኘችው..አዎ አገኘዋቸው…ከከተማ እንውጣ ብለው ላንጋኖ ነው የሄድት …በሀይቁ ዳር በታነፀ ላውንጅ የተዘጋ መኝታ ክፍል ውስጥ ናቸው፡፡
//////
ህይወት ልክ እንደካርታ ጫወታ ነች…ይበወዝና ተጫዋች ለሆኑት ኗዋሪዎቾ የሚታደል ዕጣ ፋንታ በሚሉት ምናባዊ ሀዲድ የምትሸረብ…አጋጣሚ በተባለ የህይወት ሰንሰለታማ ጉዞ ላይ በትክክለኛው ቦታ በትክክለኛው ጊዜ አንዱ ካንዱ በመገጣጠም መላተም እና በሌላ ገጽ ላይ በሰከንድ ሽርፍራፊ ሰከንድ መዘግየት ተፈጥሮ ተፈላልጎም ሳይገናኙ መተላለፍን በውስጧ የያዘች….
በጣርነው መጠን ማናገኝባት…ባመረትነው መጠን ማንሰበስብባት…በተመኘነው መንገድ ማንጓዝበት..እንደሎተሪ ዕጣ ብዙዎቻችን የምንከስርባት…የተወሰነው በማስተዛዘኛ የምንፅናናባት..ጥቂቶች ደግሞ እንደው ጠብታ ላባቸውን በአልማዝ ተመንዝሮ እጃቸው ላይ የሚቀመጥላቸው …ውጥናቸውን አለም ጠቅላላ ተረባርቦ ከግብ የሚያደርስልቸው ከእርጥብ እድል ጋር የተፈጠሩ…ንግግራቸውን በደቂቃ አለም የሚያደምጥላቸው…እነሱ ለተከዙት አለም ተንሰቅስቆ የሚያለቅስላቸው …እንዲሁ መርቆ የፈጠራቸው አሉ፡፡ … እና ህይወት የካርታ ጫወታ ነች…የጫወታውን ህግ ግን ተፈጥሮዊ ብቻ አይደለም..ሰው ሰራሽም ጭምር ነው …
ይሄንን ሀሳብ ያሰበችው ሰሚራ ነች ..ፍቅረኛዋ መላኩ ደረት ላይ ጋደም ብላ እያሰላሰለች የምትገኘው፡፡እንዴት እንዲህ ልሆን ቻልኩ....?እንዴት ከበሽተኛዬ ጋር ፍቅር ውስጥ ገባሁ…...?አጋጣሚው ነው ወደዛ የገፋኝ ወይስ እራሴ ነኝ ፈቅጄ እና አስቤ ወደዚህ ደረቱ ላይ ወደተጋደምኩት ልጅ ልብ ውስጥ የገባሁት…...?
‹‹ምን እያሰብሽ ነው..?››ድንገት በጠየቃት ጥያቄ ለውስጥ ጥያቄዋ መልስ ሳታገኝ አቋረጠችው፡፡
‹‹መቼ ጥለህኝ እንደምትሄድ እያሰብኩ ነው››አለችው…ለምን እንደዛ እንዳለችው ለራሷም አልተገለጸላትም… ..ምክንያም እያሰበች ያለችው ያንን እንዳልሆነ እሷና እግዚያብሄር ያውቃሉ….ሳታስብ ከንፈሯ ላይ የመጣላት ድንገታዊ መልስ የእውነት ስጋቷ አይደለም ማለት ግን አይቻልም…
‹‹የት ነው ጥዬሽ የምሄደው..?››
‹‹ወደኑሮህ ነዋ››
‹‹ኑሮ ማለት እኮ የህይወት ደስታሽ የሚመረትበት ቦታ ነው….ማንም ሰው በህይወቱ የሚባክነው ያንን ቦታ ፍለጋ ነው…የደስታው ምንጭ የሚፈልቅበትን ጥግ ለማግኘት …የሰው ልጅ ስኬትም የሚለካው በዚህ ነው…እና እኔ እድለኛ ነኝ .ብዙም ሳለፋ በተዐምራዊ አጋጣሚ አንቺን አግኝቼያለሁ….እንዳገኘውሽ ያወቅኩት ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በቃ ስትስቂ ልቤ ትቀልጣለች…ትንፋሽሽን ወደውስጤ ስስበው በሰውነቴ ውስጥ በስብሰው ያበቃላቸው ሴሎቼ እንኳን መልሰው ህይወት ሲዘሩ ራሱ ይታወቀኛል…..ከጎኔ መኖርሽን ሳይ ዓለም ጠቅላላ ተሰብስባ ከእጄ የገባች ይመስለኝና ልቤ በኩራት አብጣ ልትፈነዳ ትደርሳለች..እና ከአንቺ ተለይቼ መሄድ ማለት ወደባዶነት ሸለቆ ተወርውሮ መከስከስ ማለት እንደሆነ ሚጠፋኝ ይመስልሻል …...?አሁን ባለሁበት ሁኔታ ከንቺ ውጭ ኑሮ ማለት ሲም ካርድ የሌለው ባዶ የሞባይል ቀፎ መሆን ማለት ነው…..››
ከትከት ብላ ሳቀች..ኪ…ኪ..ኪ…እንዴ ‹‹ነገሩን ሁሉ እኮ ስነጽሁፋዊ አደረከው…ከእኔ ከመገናኘትህ በፊት ነጋዴ ነበርኩ ብለሀኝ አልነበር እንዴ..?››
‹‹አዎ በጣም ጎበዝ ነጋዴ ነበርኩ…ምን ተፈጠረ..?››
‹‹አይ ንግግርህ የደራሲ እንጂ የነጋዴ አልመሰለኝ አለኛ…..››
‹‹አታውቂም እንዴ..? ፍቅር እና ችግር ያፈላስፋሉ እኮ….!!!››
‹‹አይ ጥሩ….ለማንኛውም የቀልድህንም ቢሆን በሰማሁት ነገር ደስ ብሎኛል….ምነው በተናገረው መጠን ሊያፈቅረኝ በቻለም ብዬ ተመኝቼያለሁ››
ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ አነሳትና እሱም ከተጋደመበት ቀና ብሎ ተቀመጠ… ወደእሷ ዞሮ አይን ዓይኗን እያየ‹‹አላመንሺኝም እንዴ ..? የምሬን ነው የተናገርኩት….በጣም ነው ያፈቀርኩሽ ..ወደፊት ማግባት የምፈልገው አንቺን ነው….የልጆቼ እናት ላደርግሽም እፈልጋለሁ….. ››
አንገቷን ወደእሱ ዘንበል አድርጋ እጆቾን በመዘርጋት ተጠመጠመችበት ..‹‹በጣም ነው የማፈቅርህ አንተን ስላገኘው እድለኛ ነኝ››
…..
‹‹እሺ አሁን ወጣ ብለን ቢች ዳር ዘና እንበል…..››አላት በሀሳቡ ተስማማችና ተያይዘው ወጡ…
ላንጋኖ ሀይቅ ላይ ያረፈችው የማታዋ ጀንበር ልዩ ህብረቀለም እየረጨች ስትታይ ለአካባቢው ልዩ ውበት አልብሳዋለች…. ቢች ዳር ኳስ የሚጫወቱ አሉ..ሀይቅ ውስጥ ገብተው የሚዋኙን የሚንቦጫረቁም ጥቂት አይደሉም…… በአካባቢው ደስታ ተመርቶ የሚታደል ወይንም ከንፋሱ ጋር ተቀላቅሎ አየሩን እየሞላው በስፍራው ያለው ሰው ሁሉ እየማገው የሚፈግና የሚደሰት ይመስላል፡፡
‹‹ትዋኚያለሽ …..?››
‹‹አረ ይቅርብኝ …ዝምብለን እዚህ ሳሩ ላይ ቁጭ እንበልና በማየት እንደሰት..ባይሆን ቆይቶ ከነሸጠኝ አብረን እንገባለን›› አለችውና ቁጭ አለች ..ተከትሎት ከጎኗ ቁጭ አለ…….

👍129👎15❤14👏6😁2🔥1
#ተአምረተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
ለዓመታት ጎብጦ እና አጎንብሶ የነበረ ትከሻቸው ቋቋቋቋቋ የሚል ድምጽ እያሰማ በመላቀቅ መቃናት ጀመረ…የተጨማደደ እና ተኮመታትሮ የነበረ ቆዳቸው ልክ የሽማግሌ ገፃ-ባህሪ ለመጫወት ጭንብል አጥልቆ እንደነበረ አክተር ከፊታቸው ተሞሽልቆ በመነሳት መሬት ወደቀ…
ወዲያው መለስተኛ አውሎ ንፋስ ተነሳና እየተሸከረከረ መጥቶ እዚህም እዛም በዙሪያችን የወደቀውን የፕሮፌሰሩን የተወገደ አካል ከአካባቢው ጠራርጎ በአየር ላይ ተሸክሞ ሄደ ..
ከዛ…. ሁሉ ነገር እንዳሰበችው እንደሆነ ካረጋገጠች በኃላ እጆቾን ከጭንቅላታቸው አነሳችና…ወደመቀመጫዋ ተመልሳ ተቀመጠች…
አየቻቸው‹‹…..እንዴት አባቱ የሚያምር ጎረምሳ ሆኖል›ስትል እራሷ በሰራችው ተአምር እራሷ ተደነቀች …‹‹ውይ እነዛ የአባቴ ዘመዶች መተው ሚወስዱኝ ባይሆን ኖሮ ይሄን ፊት ለፊቴ የተቀመጠውን ቆንጅዬ ጎረምሳ አግብቼ መኖር ነበር….›ስትል የምፀት ፈግታ ፈገግ አለች፡
ፕሮፌሰሩ ቀስ እያለ ከሰመመኑ ነቃ…
‹‹ወይ ልጄ ምድነው ያደረግሺኝ…….?ራስ ምታቴ እና ጭንቀቴ እኮ ለቆኝ ሄደ››
‹‹አሞህ ነበር እንዴ…….?››
‹‹ምን አልሽኝ…….?››ግራ ተጋብተው
‹‹ ይቅርታ አሞት ነበር እንዴ…….? ለማለት ፈልጌ ነው››
‹‹አንቺን አልረብሽሽም ብዬ ነው እንጂ እንደምትሄጄ ከሰማሁበት ቀን አንስቶ ጤናም የለኝ ነበር..››
‹‹አይ እንኳን ተሸሎት››
‹‹አረ መሻል ብቻ አይደልም …››ንግግራቸውን ሳይጨርሱ አይናቸው እጃቸው ላይ አረፈ..ተጨማዶ ና ተሸብሽቦ የነበረ እጃቸው አሁን በለግላጋ ጣት እና ለስላሳ ቆዳ ተሸፍኖ ሲያዩት ማመን አልቻሉም… ግራ በመገባት እና ባለማመን በጃኬታቸው ሸፈኑት..መልሰው ገለጡ…
‹‹ቆይ መጣሁ›› ብለው….ትተዋት ወደቤት በፍጥነት መራመድ ጀመሩ…ከኃላ ተከተለቻቸው…ቀጥታ ወደመኝታ ቤታቸው ሄደው የቁምሳጥናቸው መስታወት ፊት ለፊት ነው የቆሙት….
‹‹የምን ታአምር ነው.…….?.እኔ የት ሄድኩ……….?ማን ነው ይሄ..…….?እኔ ማነኝ…….…….? ››ፊታቸውን እየዳበሱ ለፈለፉ…
መልስ መስጠት ጀመረች‹‹አሁን የ30 ዓመት ወጣት ሆነዋል..ማለት ሆነሀል፡፡…የሚፀፀቱበት ምንም ነገር የለም..ቀጣይ 45 ዓመት ተሰጥቶታል …. ስዚህ ቅድም እንዳሉት ሚዛናዊ ኑሮ ይኑሩበት..ማለቴ ኑርበት…››
‹‹ምን ጉድ ነው….…….?እኔ ወጣት…አንደገና መወለድ እኮ ነው…….?››
‹‹አዎ ነው..ልክ እንደንስር እንደገና የመታደስ ዕድል..››አለቻቸውና ቤታቸው ለቅቄ ወደራሴ ቤት አመራሁ ..ወደ እናቴ ለመሄድ ልዘጋጅ
////
ንጋት ላይ ነው ጉዞ የጀመሩት፡፡የንጋቱን ቀዝቃዛ አየርን እየማጉ ሰማዩን ሰንጥቀው ቁልቁል የኢትዬጵያን ደቡባዊዉን መልካ ምድር እየቃኙ እየተጓዙ ነው፡፡እስኪ ትንሽ ከላይ ሆነው ቁልቁል ወደታች ሳያዩ ከፊል ኢትዬጵያ ምን እንደምትመስል አብረናቸው እንመልከት፡
ኢትዬጵያ 12 ታሪካዊ ቅርሶችን በዩኒስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት አስመዝግባለች፡፡እነዚህም፤ የአክሱም ሀውልቶች፣ የላሊበላ አብያተክርቲያናት፣ የጎንደር ፋሲል ቤተመንግስት፤የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ፣ የኮንሶ ሰው ሰራሽ መልካዓ ምድር፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣የታችኛው አዋሽና የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ የመስቀል ደመራ፣ የሲዳማ ፊቼ ጨንበላላ፣ የኦሮሞ የገዳ ሥርአት ናቸው። ሌሎችም ለማስመዝገብ ላይ ያለ አሉ በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ በእቅድ ደረጃ የተያዙ ቅርሶችም እንደ የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ፣ የድሬ ሼክ ሁሴን መስጊድ፣ የሶፍ ኦመር ዋሻ፣ የጌዲዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መልከዓምድር፣ የመልካ ካንቱሬ የአርኪዮሎጂ ስፍራዎች ናቸው። በማይጨበጥ ባህላዊ ቅርስነት ደግሞ የአማራና የትግራይ የሻዳይና የአሸንዳ በዓላት የጥምቀት በዓል ይጠቀሳሉ።
ኢትዬጳያ ግን ለቱሪስት ኢነደስትሪው ግብአት የሚሆኑ ሀብቶቾ እነዚህ ብቻ አይደሉም…ሀገሪቱ እራሱ ሙሉ በሙሉ በዩንሰኮ ቅርስነት ብትመዘገብ አያንስባትም…ግን በዛ መጠን የሚያስብ በዛም መጠን የሚሰሩ ልጆች ወልዳ አለማሳደጎ በጣት የሚቆጠሩትን ብቻ ማስመዝገብ ችላለች፡፡
ይገርማችኋል ይህቺ ሀገር ሙሉ ነች፡፡ሙሉ ስላችሁ ለምሳሌ አየር ፀባዮ ደጋ ጥቂት ፈቅ ስትሉ ወይና ደጋ ..ብዙም ሳትርቁ ቆላ ታገኛላችሁ፡፡ይሄ ድንቅና መድሎ ያለበት የተፈጥሮ ስጦታ ነው…መልካ ምድሯን ስንመለከት ለጥ ያለ ሜዳ…ደግሞ ቀጥ ያለ ተራራ..እሱ ሲገርማችሁ ጭው ያለ ገደል…በሌላ ጎኑ እንደጣባ አህያ የተራቆተ መሬት…እንደ ደብረብርሀን የሱፍ በግ ጥቀጥቅ ያለ ጫካ…ኩሬ ሀይቅ ወንዝ….አቤት እነዛ አሜሪካኖቹ ይሄን መልካ ምድር ከዚህ የተመጣጠነ ምግብ ከሆነ አየሯ ጋ ቢያገኙት.. አቤት ይሮፖዎች ያ በቆፈን የሚያኮራምት በረዶ ገላግሎቸው እንዲህ ሚዛኑን የጠበቀ አየር ቢያድላቸው ምን ያህል ተአምራዊ ህይወት ይኖሩ ነበር.. ተፈጥሮ ሚዛኗን የምትጠብቅበት የራሷ ቀመር አለት መሰለኝ ለእነሱ ሀብት ከቆፈን ጋር ስታድል ለእኛ ምርጥ አየር ከችጋር ጋር.. ያስቃል….እነሱ በቱሪስት ሆነው መልካምድሯን አይተው ለመደሰት እና አይሯን ምገው ሀሴት ለማድረግ ምቾት ባለው አይሮፕላን መጥተው ገንዘባቸውን ከስክሰው ከረምረም ብለው ይመለሳሉ..እኛ በስደት መልክ ከችግር ለመላቀቅ በእግር ተጉዘን በባህር ተጉዘን ሀገራቸው እንገባና ጉልበታችንን አንጠፍጥፈን አንገታችንን ደፍተን ስንባዝን ስንባዝን እንኖርና በዛው የውሀ ሽታ ሆነን እንቀራለን የእነሱ አንድ ነፍስ በእኛ ስንት ነፍስ እንደሚመነዘር ስሌቱ አይታወቅም ..ምን አልባት የብራችን ምንዛሬ ወይም ዋጋ ልዩነትን ያህል የነፍሳችንም ዋጋ ልዩነት ይኖረው ይሆናል…
….ይሄን ሁሉ ይምታስበው.ይሄን ሁሉ የምትመኘው በአየር ላይ ሆና ንስሯ ጀርባ ላይ ተጣብቆ ነው እየተጓዙ ያሉት…
ያው ሰው በተፈጥሮ በመጨረሻው የህይወቱ ማብቂያ ሰዓት ቁጭት ውስጥ መግባቱ እና ፀፀቱን መናዘዙ ተለመደ አይደል..እሷም ያው በግማሽም ሰው በመሆኗ መጠን ከሰውም ኢትዬጵያዊ ስለሆነች ያው ያ ደግሞ ክርስቶስም ለስጋው አደላ የእንደሚባለው ለእሷም ለዘመዶቿ ተቆጭታ ነው እንጂማ የእሷ የአባቷ ዘመዶች በምድራዊ ዕውቀት የማይመዘን ብቃት እንዳላቸው ታውቃለች፡፡
ለማንኛውም አሁን ደሎ ደርሰዋል…ግን ቀጥታ ወደእናቷ ቤት መሄድ አልፈለገችም ..በመጀመሪያ ያደገችበትን ጫካ ልትሰናበት ፈለገች..መቼስ የደሎመና ጫካ ጫካ ብቻ አይደልም …ውስጡ የቡና ተክል የተሰገሰገበት ነው..ልጅ ሆነው እንጨት ለቀማ ከእኩዬቾ ጋር ስትሰማራ ከቡናው ተክል ድፍኑን ሸምጥጠውን ይመጡት ነበር..የቡና ተክል ጥሬ ሆኖ ድፍን አረንጓዴ ነው …እየበሰለ ሲሄድ ቢጫ እየሆነ ይመጣል በስተመጨረሻ ሙሉ ብስል ሆኗል የሚባለው ሙሉ ቀይ ሲሆን ነው..ታዲያ በዛን ጊዜ ፍሬውን ቀፈው ይመጣሉ…ቀዩ የቡና ገለፈት በወስጡ የያዘው ፈሳሽ ልዩ ጣዕም አለው….ሌላው የሚገርማት ይሄ አሁን ከላይ ወደታች የማታየው የደሎ ጫካ ወይም ሀራና ደን የመንግስት ነው…በውስጡ ከደኑ ጋ ተሰባጥሮ ሚገኘው የቡና ተክል ደግሞ የግለሰብ ነው….የኢትዬጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲህ ተዋህደው በስምም ሲጠቀሙ በዚህ ደን ብቻ ነው ያየችው፡፡

👍70❤10😢2😁1🤔1