#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
ሲልቪ
ላይ ላዩን
..ተመስገን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ ስሰራ አንዳንዴ ውቢቱ ሲልቪ ትመጣና «Salut Castro noire» ትለኛለች። («ሰላም፣ ጥቁር ካስትሮ») (ፂም ስላለኝ ነው፡፡)
«Que la paix soit avec toi Scheherazade Blanche» እላታለሁ
(«ሰላም ላንቺ ይሁን፣ ፃእዳይቱ ሻህራዝድ ሆይ»)
ትስቃለች። በምስራቃውያን አነጋገር እንቀጥላለን። ቀልድ
ነው። ከሲልቪ ጋር ሁልጊዜ ቀልድ ነው:: እውነተኛ ፈረንሳዊት ናት፣ ስለምንም ነገር ቢሆን «Moi je men fous!» ነው የምትለው
(«እኔ ስለዚህ ነገር ደንታ የለኝም»)
ታድያ ደስ ትላለች። ሰፊ አፏ
ሳሙኝ ሳሙኝ ይላል፡፡ አብረሀት ስትሆን ሳቅ ቀልድ ታበዛለህ፣
«ዠማንፉቲዝሟ» ይጋባብሀል፤ ስለምንም ነገር ደንቴ አይኖርህም
አንድ ቀን ግን
«ምንድነው ሁልጊዜ ስትፅፍ የማገኝህ?» አለችና ደብተሬን
አየችው:: የምን ፅህፈት ነው ይሄ? ያገራችሁ ነው?» አለችኝ
«አዎን»
«ምኑም አይገባም»
«ቀላል ነው፡፡ ሁለት መቶ አርባ የሚሆኑ ፊደላት አሉት»
«Quel horreur! (ኧረ የጉድ ያለህ!) እንግዲያው አታስረዳኝ
ይቅርብኝ .. ምንድነው ምትፅፈው?»
«ምንም አይደለም»
«ልብወለድ ነው?»
«ብጤ ነው»
«እንዴት ማለት ብጤ?»
«እንዴት ልበልሽ? ልብወለድ ነው፣ ግን ፈጥሬው አይደለም፣
ያየሁትን የሰማሁትን ነገር ሰብስቤ ቅርጹን እለዋውጣለሁ እንጂ፣
ላንባቢ እንዲጥም»
«ቆይ ቆይ፡፡ አሁን መፃፍ አለብህ ወይስ ለጊዜው ልትተወው
ትችላለህ»
«ልተወው እችላለሁ»
«እንግዲያው ከዚህ እንሂድና ቡና ልጋብዝህ:: እና ስለድርሰት
እናውራ። ይስማማሀል?»
«በደምብ ነዋ! ቆንጆ ሴት ቡና ስትጋብዘኝ ሁልጊዜ
ይስማማኛል»
«Malin Castro noir va!» («ሂድ ወድያ! ፎሌ ጥቁር ካስትሮ!»)
Deux Chevaux መኪናዋ ውስጥ ከገባን በኋላ
«ኤክስ ውስጥ የምወደው ካፌ የለኝም፡፡ ማርሰይ እንሂድ?»
አለችኝ
እየቀለድን እየሳቅን ደጋግማ «Moi, u sais je m en fous!»
እያለች፣ በሆዴ ውበቷን እያደነቅኩ፣ ማርሰይ ደረስን፡፡ የንግድ ሳይሆን የግል የመደሰቻ ልዩ ልዩ አይነት ጀልባዎች ከተደረደሩበት ወደብ አጠገብ አንድ ካፌ ገብተን ቢራ ካዘዝን በኋላ፣ ጉልህ ሰማያዊ
አይኖቿ በፈገግታ እያዩኝ
«ንገረኛ ስለምትፅፈው» አለችኝ
«ምን ልንገርሽ?»
«ስለሰዎቹ፣ ስለጊዜው፣ ስለግንኙነታቸው፣ ማን ማንን እንደ
ሚወድ፣ ማንስ ማንን እንደሚጠላ፣ መፅሀፍህ አንዴት እንደ ሚጀመር፣ አሁን የት እንደደረሰ፣ በኋላ እንዴት እንደሚያልቅ፣
ምን ምን ነገር እንደሚያስቸግርህ፣ መፅሀፍህ ምን እንዲል እንደ
ምትፈልገው፣ ሁሉን ንገረኝ
ቆንጆ ስለሆነች ይሁን፣ አጠያየቁን ስላወቀችበት ይሁን ወይ ሌላ ያልተገለፀልኝ ምክንያት ይኑር እንጃ፣ ስለመፅሀፌ ሁሉን
ነገርኳት። ለማንም ነግሬ የማላውቀውን ለሷ አጫወትኳት፡፡ ችግሩን ደስታውን፣ ብስጭቱን፣ የድል አድራጊነት ስሜቱን፣ ምንም
ሳልደብቅ አዋየኋት። ፈረንሳይኛው ሲያስቸግረኝ ልክ ልናገረው
የፈለግኩትን ቃላት ታቀብለኛለች፣ ምክንያቱም ሀሳቤ ቃላቱን
ቀድሞ ደርሷት ይቆያል። አንዳንድ ቦታ አንድ ሀሳብ ተናግሬ
ጨርሼ ሌላ ሀሳብ አልመጣልህ ሲለኝ አንድ ጥያቄ ትጠይቀኛለች
እሱን ጥያቄ ስመልስ፣ ሌላ ሀሳብ ይመጣልኝና እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ ብዙ ካወራሁ በኋላ
«ይገርምሻል፣ ይህን ለማንም ነግሬ አላውቅም» አልኳት
«Jen suis lattee» አለችኝ (ክብር ይሰማኛል።)
«እኔ እውነቴን ነው»
«እኔም እውነቴን ነው»
«አሁን ተራሽን አውሪልኝ
«ቆይ» አለችና ከያዘችው የመፃህፍት ቦርሳ አንድ አስር የሚሆኑ ባንድ በኩል ብቻ በታይፕ የተፃፈባቸው ነጠላ ወረቀቶች ሰጠችኝ።
አንብበው አለችኝ፡፡ አነበብኩት፡፡ አጭር ልብ ወለድ ታሪክ ነው።
ስጨርስ ምን ይመስልሀል?» አለችኝ
«አንቺ ነሽ የፃፍሽው?» አልኳት
«አዎን» አለችኝ
«አዝናለሁ። ጥሩ ታሪክ አይደለም»
«ምንድነው የጎደለው?»
«እርግጠኛ አይደለሁም። አየሽ፣ አንድ ሰው የሚወዳትን ሴት
ሊገድል ይችል ይሆናል፡፡ ግን ባስር ገፅ ውስጥ ይህን መናገር
የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሁለት መቶ ገፅ
ያስፈልገዋል»
«ይህንንም አንብብ እስቲብላ ሌላ አስራ ሶስት ገፅ ሰጠችኝ።
አነበብኩት። ግሩም ታሪክ ነበር፡፡
«ይህንንም አንቺ ነሽ የፃፍሽው?»
«አዎን»
«ታሪክ ይሉሻል ይሄ ነው! ይህን ጊ ደ ሞፓሳን ራሱ ነው የፃፈው ቢሉኝ አምናለሁ» አልኳት
ጉልህ ሰማያዊ አይኖቿ ልዩ አስተያየት ሰጡኝ፣ እንደማቀፍ ያለ
አስተያየት፣ ሙቀት ያለው አስተያየት
«Merci»አለችኝ
«Je ten prie (ኧረ ምንም አይደለም) ይህን የመሰለ ለመፃፍ
ስትችዪ፣ እንዴት አርገሽ የቅድሙን ፃፍሽው?» አልኳት
መሳቅ ጀመረች (ጥርሶቿ ትክክል ሆነው ነጫጭ ናቸው። ነጭ
የፈረንጅ ጥርስ ብዙ እይታይም) «እኔ እንጃ አለችኝ «በምፅፍበት
ሰአት ሁሉም እኩል ጥሩ ሆኖ ይሰማኛል። ካንድ ሁለት ወር በኋላ
ሳነበው ነው እውነተኛው ዋጋው የሚታየኝ»
«ይሄ መጥፎው መቼ ነው የተፃፈው?»
«ካንድ አመት ተኩል በፊት
«እንግዲያው መጥፎ መሆኑ
ድሮ ገብቶሻል። ለምን
እስነበብሽኝ?»
«ላውቅህ ስለፈለግኩ። ማንም ሰው ቢሆን፣ እንደምፅፍ ካወቀ
ወይም እንዲያውቅ ከፈለግኩ፣ መጀመሪያ መጥፎ ታሪኬን
አስነብሰዋለሁ። አንብቦት ጥሩ ነው ካለ በቃው። ሁለተኛ እኔ
የፃፍኩትን አያነብም። እስካሁን ለአንድ ስምንት ሰው አስነብቤያለሁ።
አንተና አንድ የፓሪስ ጓደኛዬ ብቻ ናችሁ መጥፎውን መጥፎ
ያላችሁት። ስለዚህ ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ ጥሩውን ያነሰሳችሁ»
«ሌላ የፃፍሽው አለ?»
«ሃያ ሶስት አለኝ፡፡ አስራ አንዱ ጥሩ ይመስሉኛል። ሰባቱ
በጣም መጥፎ ነው:: አምስቱ ግን ጥሩም አይደል፣ መጥፎም
ኣይደል እንደኔ እስተያየት። ስለዚህ አንተ እነዚህን አምስት
አንብበህ ምን እንደሚመስልህ ብትነግረኝ፣ ተስፋ የሌለውን
እጥለውና ተስፋ ያለውን እየመከርከኝ አሻሽለዋለሁ»
«ክብር ይሰማኛል፣ ግን ልመክርሽ መቻሌን እንጂ
«ትችላለህ። ታግዘኛለህ? »
«ከቻልኩማ በደስታ! አሁን ስለራስሽ ንገሪኝ፡፡ ቅድም እኔ
እንደነገርኩሽ»
ነገረችኝ፡፡ የምንፅፍበት ቋንቋ ተለያየ 'ንጂ ሙከራችን፤
ችግራችን፣ አስተያየታችን በጣም ይመሳሰላል፡፡ ስንወያይ መሸ፡፡
«እማውቃት ጥሩ ርካሽ ምግብ ቤት አለች» ብላ ሳን ሻርል
ባቡር ጣቢያ አጠገብ ወስዳ እራት ጋበዘችኝ። በፈረንሳይ ደምብ ከምግቡ ጋር አንድ ጠርሙስ ወይን ጠጣን፡፡ ሲኒማ ላስገባሽ አልኳት፡፡ ሁለታችንም እንደዚህ ልንጨዋወት የምንችልበት ጊዜ
መቼ ተመልሶ እንደሚመጣ አይታወቅም አለችኝ፡፡ እውነትሽን ነው አልኳት
ወደ ወደቡ ተመልሰን በእግር እየተዘዋወርን ወሬያችንን ቀጠልን። በተርታ የቆሙ ጀልባዎች የሚወዛወዙበት ውሀ ውስጥ የማርሰይ መብራት ይጫወታል። የባህር ሽታ ይዞ ከባህር በኩል የሚመጣው ነፋስ ቅዝቅዝ ያለ ሆኖ ይለሰልሳል። እንደኛው እያወሩ
የሚዘዋወሩ ሰዎች አሉ፤ አብዛኛዎቹ ተቃቅፈዋል፡፡ መንሽራሽር ሲበቃን አንድ ካፌ ገብተን ቁጭ ብለን ቢራ አዘዝን

👍27❤1👏1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
...ለአሥራ ዘጠኝ ዓመት እስር ቤት ውስጥ ሲቀመጥ ኣንድ ቀን እንኳን እንባ አልወጣውም::
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከቤተክርስቲያን አናት ላይ የተሰቀለው ሰዓት ስምንት ሰዓት ሲደውል ዣን ቫልዣ ከእንቅልፉ እንደገና ነቃ፡፡ ከአራት ሰዓት በላይ ጥሩ እንቅልፍ ወስዶት ተኝቷል፡፡ ድካሙ ሁሉ ወጣለት:: ለዚህን ያህል ጊዜ የእረፍት ሰዓት ኣግኝቶ አያውቅም፡፡ ዓይኑን ገልጦ በአካባቢው በሰፈነው ጨለማ
ዘልቆ ለማየት ሞከረ፡፡ ለማየት ባለመቻሉ እንደገና እንቅልፍ እንዲወስደው ዓይኖቹን ጨፈነ፡፡
ቀኑን ሙሉ አእምሮ በብዙ ነገሮች ተበጥብጦ ከዋለና የተለያዩ ነገሮች ከተመላለሱበት አንድ ጊዜ እንጂ ሁለት ጊዜ እንቅልፍ ሊወስድ እንደማይችል
ሁሉ ዣን ቫልዣንም ሊወስደው አልቻለም:: እንቅልፍ መጀመሪያ ሲመጣ ያዳፋል፡፡ ሁለተኛ ግን ቢለማመጡትም በዓይን አይዞርም:: እንደገና እንቅልፍ
ሊወስደው ስላልቻላ ማሰብ ጀመረ::
ብዙ ዓይነት አሳብ ከኀሊናው ውስጥ ገባ፡፡ ግን ሌሎቹን ሁሉ እየዋጠ እርሱ ብቻ እየተመላለሰ ያስቸገረው አንድ አሳብ ነበር፡፡ እነዚያ መዳም ማግልዋር ከጠረጴዛው ላይ የደረደሩዋቸው የሚያማምሩ ስድስት ከብር
የተሠሩ ሣህኖችና ትልቅ የብር ጭልፋ በዓይኑ ዞሩ፡፡ በጣም ወዷቸዋል:: አጠገቡ ከጳጳሱ ትራስጌ በኩል ቡፌ ውስጥ ሴትዬዋ ሲያስቀምጧቸው
አይቶአል፡፡ ከብር የተሠሩ ጥንታዊ ቅርስ በመሆናቸው ከነጭልፋው እስካ 200 ፍራንክ እንደሚያወጡ ያውቃል፡፡
ኅሊናው ከወዲያ ወዲህ እየዋለለ አንድ ሰዓት አለፈ፡፡ በአሳብ እየዋተቱ አንድ ሰዓት ማሳለፍ፤ ያውም ሌሊት በጨለማ ምን ያህል ረጅም እንደሆነ
የደረሰበት ያውቀዋል፡፡ የቤተክርስቲያኑ ሰዓት ደወል ዘጠኝ ሰዓት መሆኑን አበሰረ:: ዓይኑን በድንገት ገልጦ ከአልጋው ዘልሉ ወረደ:: ስልቻውን በእጁ
እየዳሰሰ ፈለገና እንደያዘው ከአልጋው ጠርዝ ቁጭ አለ፡፡ ሳያውቀው ብዙ ተቀመጠ፡፡ ሰዓቱ በየአሥራ አምስት ደቂቃና ግማሽ ሰዓት ደወል እየደወለ ባይቀሰቅሰውማ እስኪነጋ ድረስ በተቀመጠ፡፡ ደወሉ «አይዞህ፣ በርታ» የሚለው መሰለው::
ተነስቶ ቆመ፤ ለመራመድ ግን አመነታ:: አንድ እርምጃ ወደፊት
ተራምዶ አዳመጠ፡፡ ሁሉም ነገር ጸጥ ብሎአል:: ቀስ ብሎ በጥንቃቄ ወደ መስኮቱ ተጠጋ፡፡ ሌሊቱ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ የተዋጠ ኣልነበረም:: ጨረቃ
በሩቁ ትታያለች:: ሆኖም ደመና ዞሮባታል፡፡ ደመና ጨረቃዋን በጋረዳት ቁጥር ቤቱ ትንሽ ጨለም ይላል፡፡ ውጪው በደምብ ሲታይ እቤት ውስጥ ግን ያንገዳግዳል፡፡ መስኮቱ አጠገብ ደርሶ መስኮቱን ሲመለከት በቀላሉ
እንደሚከፈት ስለተገነዘበ ከፈተው:: ሆኖም ኃይለኛ ብርድ ስለገባ መልሶ ዘጋው:: መስኮቱ መስታወት ስለነበር እንደተዘጋ ግቢውን ቃኘ፡፡ ግቢው
በአነስተኛ ግምብ መከለሉን ተመለከተ:: ከግምቡ ውጭ ረጃጅም ዛፎች ነበሩ፡፡ በሁለት ዛፎች መካከል ያለውን ርቀት ሲያጤን ርቀታቸው ተመሳሳይ
ሆኖ ስላየው ምናልባት ማዘጋጃ ቤቱ የተከላቸው ዛፎች መሆናቸውን በመገመት ከአጥሩ ውጭ ያለው መንገድ አውራ ጎዳና መሆን አለበት ብሎ ደመደመ::
ወደ ውሳኔ አሳብ እንደደረሰ ሰው በቆራጥነት ወደ አልጋው ተመለሰ፡፡ አቆማዳውን አንስቶ ከፈተውና ከውስጠ ምናምን ፈለገ፡፡ ኣንድ ነገር አውጥቶ
አልጋው ላይ አስቀመጠ፡፡ ጫማውን ኪሱ ውስጥ ከተተ፡፡ ኣልጋው ላይ ካስቀመጠው እቃ ሌላ የተቀሩትን እሳስሮ ትከሻው ላይ አኖረ፡፡ ቆቡን አጠለቀና ዱላውን ፈልጎ ከያዘ በኋላ ያሰረውን እቃ ከመስኮቱ ሥር
አስቀመጠው:: ወደ ኣልጋው ተመልሶ ያስቀመጠውን እቃ አነሳ:: እቃው ከአንድ ጫፍ እንደ ጦር የሾለ፣ ከሌላው ጫፍ ቋር ያለው ወፍራም ብረት ነበር፡፡ በዚያ ጨለማ ብረቱ ለምን ሥራ እንደተዘጋጀ ለመለየት አስቸጋሪ
ነበር፡፡ ዱላ ነው ወይስ እቃ ማንሻ? አይታወቅም:: ቀን እንኳን ቢሆን
የማዕድን ሠራተኞች መቆፈሪያ ነው ለማለት ያስችላል፡፡ በዚያን ጊዜ ቱሉን ከተባለ ቦታ አካባቢ በሚገኙ ከፍተኛ ኮረብታዎች ላይ ድንጋይ እንዲፈልጡ
የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ይቀጠሩ ነበር፡፡ ወንጀለኞቹ ብዙውን ጊዜ የዚያን ዓይነት ብረት የመሰለ መፍለጫ ይይዛሉ፡፡
ዣን ቫልዣ ያን ብረት በቀኝ እጁ ያዘ፡፡ ትንፋሹን ውጦ በዝግታ
ተራመደ:: ወደ ጳጳሱ መኝታ ቤት አመራ:: ወደ በሩ ሲጠጋ አለመቀርቀሩን ተመለከተ፡፡ «አባታችን በራቸውን ሳይቆልፉ ነው የሚተኙት» አለ በልቡ፡፡
ዣን ቫልዣ ጆሮውን አቅንቶ አዳመጠ፡፡ ድምፅ የሚሉት ነገር
የለም:: በሩን ከፈት አድርጎ ሲፈራ ሲቸር በጣቶቹ ጫፍ ቀስ ብሎ ገፋው::ጥንቃቄው ከድመት ይበልጣል:: በሩ ምንም ድምፅ ሳያሰማና ለመንቀሳቀሱ
እንኳን በሚያጠራጥር ሁኔታ በዝግታ በመገፋቱ ከመጀመሪያው ይበልጥ ጥቂት ከፈት አለ፡
ለጥቂት ጊዜ ከበሩ አጠገብ ቆም አለ፡፡ አሁን ግን በይበልጥ ድፍረቱ
ስለተሰባሰበለት ከቀድሞ በበለጠ ጉልበት በሩን ገፋ አደረገው:: በዚህ ጊዜ የበሩ ማያያገዥ የዛገ ብረት ረዘም ያለ የሚሰቀጥጥ ድምፅ አሰማ፡፡
ልቡ የተሰነጠቀ መሰለው:: እንደ እንጨት ደርቆ ከቆመበት ሐውልት
ይመስል ሳይንቀሳቀስ ለጥቂት ጊዜ ተገተረ:: ለመነቃነቅ አቅም አነሰው ድፍረትም አልነበረውም:: ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ:: በሩ ወለል ብሎ ተከፍቷል:: ወደ ክፍሉ ተመለከተ:: የተንቀሳቀሰ ነገር የለም:: አዳመጠ፤ የሚንቀሳቀስ ወይም ድምፅ የሚሰጥ ነገር አሁንም ከጆሮው ኣልገባም::
የበሩ ድምፅ ማንንም አልቀሰቀሰም ማለት ነው::
የመጀመሪያው አደጋ አለፈ:: ልቡ ግን በጣም ፈርቷል ፤ ሆኖም
አላወላወለም:: የፈለገውን ቶሎ ለመጨረስ ቁርጥ አሳብ አደረገ፡፡ በአንድ እርምጃ ከክፍለ ውስጥ ገባ፡፡ ክፍሉ ውስጥ ጸጥታ ሰፍኖበታል፡፡ ዣን ቫልገዣ ከወንበርና ጠረጴዛ ጋር እንዳይጋጭ እየተጠነቀቀ ወደፊት ተራመደ::ጳጳሱ ክፍለ ውስጥ ጥግ ይዘው ተኝተው በኃይል ሲተነፍሱ አዳመጠ፡፡በድንገት ቆም አለ:: ከጳጳሰ አልጋ አጠገብ ደርሷል፡፡
ቶሉ የደረሰ መሰለው::አንዳንድ ጊዜ ተፈጥሮ የምንሠራውን ሥራ ለማራገብ ከእኛ ጋር ታብራለች:: ለግማሽ ሰዓት ያህል ደመና ጨረቃን በመጋረድዋ አካባቢው
ጨልሞ ነበር፡፡ አሁን ግን ልክ እንደተማከረ ሰው ዣን ቫልዣ ከጳጳሱ አልጋ አጠገብ እንደቆመ ደመና ለጨረቃ ቦታዋን ለቀቀች:: የጨረቃ ብርሃን በመስኮት በኩል ዘልቆ በመግባት ከጳጳሱ የገረጣ ፊት ላይ አበራ:: ጭልጥ
አድርጎ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። የሌሊቱ ብርድ ከባድ ስለነበር ወፈር ያለ የሌሊት ልብስ ለብሰው በጀርባቸው ተዘርረው ነው የተኙት፡፡ ስንት ደግ ሥራ የሠራው ታማኙና ነዳያን የሳሙት እጃቸው ካልጋው ጠርዝ አልፎ ወደመሬት ተንጠልጥሎአል፡፡ ሌላው እጃቸው ከደረታቸው ላይ በማረፉ
የጵጵስና ቀለበታቸው ያበራል፡፡ እዚያ ተጋድመው ሲያይዋቸው መላ አካላቸው የተስፋ ፣ የደስታና የእርካታ ማኅደር እንደሆነ ይናገራል:: በቃላት ለመግለጽ የሚያዳግት የማይታይ ብርሃን ከግንባራቸው ላይ አርፎአል፡፡
የጨረቃው በሰማይ ላይ መንጣለል፤ የምድር በከፊል የተኛች መምሰል ፤ የግቢው አትክልት እርጭ ማለትና የቤቱና የዚያች ሰዓት ፀጥታ እኚህ መለኮት የቀረባቸውን ሰው «አክብሩ አትድፈሯቸው» የሚያሰኝ
ነበር፡፡ ዓይናቸውን ጨፍነው እንደተኙ የነበራቸው ግርማ ሞገስና ለተስፋ ምንጭ የሆነውና በጨርቅ ያልተሽፈነው ግንባራቸው ሲያዩት በፍርሃት የሚያርበደብድ ነበር፡፡

👍19❤1
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
“እንዴት ነህ ጃ?” አልሁት፣ ከተንጋለልሁበት መነሳት የእረጥብ አራስ ያህል እያቃተኝ፡፡ ያቆላመጥሁት ራሱ አልመሰለኝም ማን ብዬ ነዉ ግን የጠራሁት? እንደ እህት ጃ ነዉ ወይስ እንደ ቀበሌ ጃሪም ብዬ? እንጃልኝ
ብቻ።
“ጭራሽ አልጋዬ ላይ?”
"በይ አልጋዬን ልቀቂልኝ ያለ በሚመስል ዓይኑ ጠቅ አድርጎኝ ሲቆም፣ ብድግ ብዬ ከአልጋዉ ላይ ወርጄለት ወደ ራሴ ክፍል ሄድሁ። ምን እንዳለኝ እንኳን ልብ ያልሁት በኋላ ሻንጣዎቹን ወደ ዉጪ ማመላለስ ሲጀምር ነበር።
የእመዋ ቤት ጎስቆል ያለች ብትሆንም፣ አሠራሯ ሁልጊዜም
ያስገርመኛል። ክብ አይሏት፣ አራት ማዕዘን አይሏት፣ የግንብ አይሏት፣
የጭቃ አይሏት፣ ብቻ ግን ሁሉንም ትመስላለች። በዚያ ላይ የሞቀች
ናት፡፡ እኔም፣ ምንም እንኳን ከቤተሰባችን ጋር አባታችንን እየተከተልሁ በዞርሁበት ክፍለ ሀገር የኖርሁባቸዉ ቤቶች ሁሉ የነበረኝ ትዝታ ባይለቀኝም፣ በቅጡ ነፍስ ያወቅሁባት ቤት ናትና እንደዚችኛዋ የሚሆንልኝ ቤት ግን የለም፡፡ ጠባብ ብትመስልም ለእኛ ግን ጠብባን አታዉቅም። በዚች ቤት ሁላችንም የየራሳችን ክፍል አለን፡፡ በእርግጥ በዚች ቤት ያለንን ክፍል መጀመሪያ የያዝነዉ እንደ ዋዛ፣ በሽሚያ ነበር።
ትዝ ይለኛል፤ መጨረሻ ከነበርንበት ከተማ ቀይረን ወደ'ዚች ቤት ልንገባ ደጁን የረገጥነዉ ኅዳር 29፣ ሐሙስ ቀን ነበር።
“በሉ እንግዲህ” አለችን እመዋ፣ ልክ ወደ'ዚች ቤት በራፍ
ከመድረሳችን፣ ቤቷ ወዳሏት ክፍሎች እየለቀቀችን፡፡ “መቼም እንግዲህ አድገናል ብላችኋል። ለየብቻ ማደሩን ከሆነ የጓጓችሁለት ይኸዉ እንዳሻችሁ ሞክሩት ደግሞ። በሉ፤ ኮተቶቻችሁን በየክፍላችሁ አስገቡ”
“በየክፍላችሁ?” አልሁኝ እኔ፣ እንክት ብዬ፡ ያደግነዉ አንድ ሰፊ
ምንጣፍ መሀል ወለሉ ላይ አንጥፈን፣ ተቃቅፈን እየተኛን ነዉ። እየተኛን አልሁ እንጂ፣ የሌሊቱን እኩሌታ እንኳን የምናሳልፈዉ እንዲሁ እንዳዉካካን ነበር። ለወጉ መብራቱን እናጠፋፋና፣ ልብሳችንንም ለዋዉጠን በዚያ ሀገር በሚያህለዉ ምንጣፍ ላይ በጎን በጎናችን እንሆናለን። ከዚያ ተረቡ፣ አሽሙሩ፣ ቀልዱ፣ ተረቱ፣ እንቆቅልሹ፣ እንካ ስላንቲያዉ፣ መሳሳቁ፣ መላፋቱ ይመጣል። ያልሆነዉ ምን አለ? ዛሬ ተረኛ እኔ የሆንሁ እንደሆነ፤ አንዴ በቃል ተረብ፣ ቀጥለዉ በልፊያ፣
ቀጥለዉ ቁንጥጫ ሁሉም ይረባረቡብኛል። ታዲያ ያሉኝን ቢሉኝስ ወንድሞቼንና እህቶቼን ላኮርፋቸዉ? ኧረ በጭራሽ! እንዲያዉም አሁን አሁን ሳስበዉ፣ ተረባቸዉን እና ልፊያቸዉን ሁሉ ለመከላከል አደርገዉ
የነበረዉ መፍጨርጨር ሁሉ ሳይጠቅመኝ አልቀረም። ቢያንስ ቢያንስ ንግግሬ እና ጡንቻዬን አዳብሮልኛል። በዚያም ላይ እኮ እኔ በተራዬ የቀመስኋትን ሁሉ፣ እነሱም በየተራቸዉ ይቀምሷታል።
“በየክፍላችሁ? አረ ምን ዓይነት፣ የማን ሐሳብ ነዉ ግን ይኼ?” አልኋት እመዋን፣ ሆዴን ባር ባር እያለዉ።
“ቀርፋፎ! ይልቅ ተመርጦ ሳያልቅብሽ ክፍልሽን አትመርጪም?” አለችኝ
ኣንደኛዋ እህቴ፣ የራሷን ክፍል መርጣ ማንም እንዳይነካባት ቆልፋዉ ወደኔ እየተመለሰች።
ብቻዬን እንደ ቀረሁ አስተዋልሁ። ሁሉም ይሻለኛል የሚለዉን ክፍል
ተሻምቷል። እኔ እዚህ በትዝታ ወዲያ ወዲህ ስል፣ እንደ ዱሯችን
እንድንተኛ እንድመካከራቸዉ እንኳን የሚሆን አፍታ ሳይታገሱኝ መስኮት ያላቸዉን እና በመስኮት በኩል አሻግሮ ለማየት የሚያመቹትን ክፍሎች ሁሉ ተሽቀዳድመዉባቸዋል፡፡ በተለይ የጃሪም ደግሞ ልዩ ነዉ፡፡ ከመስኮት በተጨማሪ፣ በዚህ በኩል ወደ ዋናዉ ሳሎን የሚያስገባ እና በዚያ በኩል
ደግሞ ወደ ዉጪ የሚያስወጣ በር ያለዉን፣ ሰፊዉን ክፍል ነዉ ተሻምቶ የያዘዉ።
ምንም አማራጭ ስላጣሁ እነሱ ያያዟቸዉን ክፍሎች እየተዟዟርሁ
ስመለከት ቆይቼ፣ ያሉኝን ኮተቶች ሁሉ እየጎተትሁ ወደ ተተወችልኝ
ምራጫ ክፍል አስገባሁባት። ያም ሆኖ ግን እምብዛም አልከፋኝም ነበር። ምክንያቱም፣ ዞሮ ዞሮ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ናቸዉ። ለስሙ ክፍሉ የየራሳቸዉ ቢባልም፣ መቼም በፈለግሁት ክፍል እንዳላድር የሚከለክለኝ
አይኖርም፡፡ እነሱም ለጊዜዉ መስሏቸዉ ነዉ እንጂ፣ በዚህ ምርጫቸዉ እንደሚጸጸቱ ገምቻለሁ። ለአንድ ወይም ላኹለት አዳር ለየብቻ ከሞከሩት
በኋላ ወደ መሀል ወለል መጥተዉ እንደ ዱሯችን አብረን እንተኛ
ማለታቸዉ አይቀርም፡፡ ይኼን ይኼን ሳስብ ትንሽ ቀለል ብሎኝ የነበረ ቢሆንም፣ ዉሎ አድሮ የሆነዉ ግን እንደ ጠበቅሁት አይደለም።
ይኼዉ በእንደዚያ ያለ ሁኔታ የያዝነዉ ክፍል አሁንም ድረስ ድርሻችን እንደሆነ አለ። የኋላ በኋላም ቢሆን፣ ጨክነን የየራሳችንን ቤት ስላልሠራን፣ በዚሁ ቤት ያለዉ ክፍላችን እንደ ተጠበቀ አለ። በርግጥ ገሚሶቹ ወንድሞቼ ወጣ ገባ እያሉ የኪራይ ቤት ኑሮ የሞካከሩ አሉ።
የሆነዉ ሆኖ፣ አሁን የየራሳችንን ሥራ ከያዝን እና የየራሳችን ኃላፊዎች ሆነናል ካልን በኋላም የምንኖረዉ እዚሁ ግቢ ነዉ። ቀን የየራሳችንን ሥራ ስንከዉን ዉለን አዳራችንም በየራሳችን ክፍል፣ በየራሳችን አልጋ ሆኗል። በእርግጥ እኔ ከሌሎቹ በተለየ መልኩ፣ ክፍት ባገኘሁት አልጋ
ሁሉ ነዉ የምተኛዉ። እንዲያዉም ብዙ ጊዜ ክፍት ሳይሆንም ጭምር፣ ጠጋ በሉልኝ ብዬ አብሬ የምተኛበት ጊዜ አለኝ። እያየኋቸዉም እንኳን
ደርሰዉ ንፍቅ በሚሉኝ ሰዓት ስስቴን የማስታግሰዉ፣ እነሱን እቅፍ አድርጌ ትንፋሻቸዉን ስምግ ያደርሁ እንደሆነ ብቻ ነዉ። እንደ ነፍሴ በምሳሳላቸዉ እህቶቼ እና ወንድሞቼ አልጋ ላይ ብተኛ፣ ነዉሩ ምን ላይ እንደሆነ አሁንም አይገባኝም፡፡ በእርግጥ ማንም ከልክሎኝ አያዉቅም ነበር። እኔ እንዲያዉም ደስ የሚላቸዉ ነበር የሚመስለኝ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ማጉረምረም አመጡ፡፡ አንዳንዶች እንደ ጨዋታ እያስመስሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ የሆነች የጀመሯት ነገር አልሳካ ያለቻቸዉ
እንደሆነ፣ ቀድመዉ የሚያላክኩት ወደኔ ሆኗል። የእነሱ ማለት የእኔም ነዉ እያልሁ ባደረስኝ ክፍል ሁሉ ስንት እና ስንት ልብስ እና ጌጣጌጥ ያኖርሁ ቢሆንም፣ አሁን ግን እሱን ጭምር ብላሽ አስቀርተዉብኛል።
“ምነዉ ሻንጣህን ሸካከፍህ፣ ንብረት እያሸሽህ ነዉ'ንዴ ወንድሜ?” አልሁት፣ በእኔ ቤት ቀልጄ ሞቼ ልቤ ዉልቅ እያለ፡፡ ይኼም አልበቃ ብሎኝ እኮ ጥርሴን ለፈገግታ አግጥጨዋለሁ ሳላስበዉ ነፍሰ ጡር እንደሆንሁ፣ ሕይወቴ ምስቅልቅሉ እንደወጣ፣ የእሱ የወንድምነት ምክር
እንደሚያስፈልገኝ ልነግረዉ በልቤ ወስኛለሁ። በመሆኑም የመጨረሻ
ሻንጣዉን አንጠልጥሎ ወደ በሩ ሲጣደፍ ተከተልሁት። ለካንስ ሌላ
ደልዳላ ሰዉ ደግሞ ከበሩ በእዳሪ ሆኖ እየተቀበለ ወደ መኪናዉ
እያጓጓዘለት ኖሯል። ልብ ባልለዉ እንጂ፣ ከልብሶቹ ሌላም የእኔ ናቸዉ የሚላቸዉን እቃዎች ከሳሎን ሳይቀር ለቃቅሞ በመኪናዉ ቀርቅቦ አስጭኖ ጨርሷል። አልጋዉን ራሱ ከምን ጊዜዉ እንዳወጣዉ አላየሁትም።
“ምን እያደረግህ ነዉ አንተ?” አልሁት፣ ልሳቅ አልሳቅ በሚል ቃና።
“ቻዉ!” አለኝ፣ ጥያቄዬን እንዳልሰማ ሁሉ የመኪናዉን የጋቢና በር ከፍቶ እየገባ፡፡
“አንተ ጃሪም! ቆይ እንጂ ወዴት ... ምን እየሆንህ ነዉ?” አልሁት፣
ተንደርደሬ ከፊት ለፊቱ መንገዱን ዘግቼ እየቆምሁበት።
“አይበቃንም ብለሽ ነዉ?”
“ምኑ ነዉ የሚበቃን?”
“ዉሽቱ ሁላ! ለጥቅማችሁ ስትሉ ጠብ እርግፍ አላችሁ እንጂ፣ እኔ እኮ ከዚህ ቤተሰብ አይደለሁም። እናትሽም እናቴ፣ አንቺም እህቴ፣
ዘመዶችሽም ምኔም አይደላችሁም በቃ”
“ምንድነዉ የምታወራዉ?”

👍34❤2
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
... ሚሲዝ ሔር እሳቷን አስነድዳ ወንበሯን አስጠጋችና አግሮቿን ከምድጃውጠርዝ ዘርግታ ስትሞቅ ባርባራ ግን አሁንም ሐሳቧ እንደ ተበተነ ልቧ እንደ ተሰቀለ ነበር " በመጨረሻ ከልብስ መስቀያው አንድ የሱፍ ያንገት ልብስ አውርዳ ከትከሻዋ ደረበችና ወጥታ ሔደች የግቢውን የአግር መንገድ ይዛ በቀጥታ ሔዳ ከብረቱ በር ስትደርስ ቆም ብላ ወደ ሕዝቡ ጐዳና ትመለከት ጀመር " ነገር ግን ያ ጐዳና በዚያ ሰዓትና ቦታ፡እንደ ሌላው ጊዜ ሕዝብ አልነበረበትም!ጸጥ ብሎ ነበር
የግንቦት መጀመሪያ ላይ ስለ ነበረ በጣም ቀዝቃዛ ይሁን እንጂ ጸጥ ያለ አስደሳች የጨረቃ ምሽት ነበር።
“ ከቶ መቸ....ይመለስ ይሆን ? አለች ባርባራ ከበሩ ተደግፋ ብቻዋን ስታወራ (እሱ የሌለበት ሕይወት ምን ሕይወት ነው ! አሁን በነዚህ ጥቂት ቀኖች ውስጥ ምን ያህል ተጨነቅሁ ? እንደ ኮርኒሊያ አባባል ከሆነ ለአንድ ቀን ብቻ ነበር የሔደው " ለመሆኑ ወደዚያ ምን ጉዳይ ቢኖረው ነው የሔደው ?
የእግር ዳና ከጆሮዋ ጥልቅ አለ በዚያ ሰዓትና ቦታ ማንም መንገደኛ እንዲያያት አልፈለገችም ስለዚህ ወደ ኋላዋ ምልስ ብላ ከዛፎቹ ጥላ ሥር ተከለለች "
የኮቴው ድምፅ እየቀረበ ሲመጣ ከዚያ በፊት የምታውቀው አረጋጥ መሆኑን ለየችው ስሜቷ ተለዋወጠ ዐይኖቿ በሩ ጉንጮቿ ፍም መሰሉየደም ሥሮቿ
ከደስታዋ ብዛት ነዘሩ እንዳትታይ ተጠንቅቃ በበሩ ቁልቁል ስትመለከት አንድ ረጅም ሰውዬ ከወደ ዌስት ሊን ሲመጣ አየች " የኋሊት ሽሽት አለች እውነተኛ
ፍቅር ድንጉጥ ነው " የባርባራ ሔር ሌሎች ተስጥዎች ያፈቀደውን ቢባሉም ፍቅሯ
ግን ልባዊና ጥልቅ ነበር ከበሩ ሲደርስ ይገባል ብላ ስትጠብቀው ዐልፎ የሚሔድ ይመስል ወደ በሩ እንኳን ዞር ብሎ አላየም " ባርባራ ሐሞቷ ፍስስ አለ እንደገና
ወደበሩ ተጠግታ ፍዝዝ ብላ በጕጒት መመልከት ጀመረች።
በርግጥም ስለሷ ምንም ሳያስብ ወደሷ ዘወር ሳይል ዐልፎ ወደፊቱ ሲገሠግሥ ስታይ በዚያች ቅጽበት በመጣበት የስሜት ግፊት «አርኪባልድ» ብላ ጠራችው።
« ባርባራ ... ሌቦችና ሕገ ወጥ አዳኞች እንዳይቡ እየጠበቅሽ ነው እንዴ ? እንደምነሽ ? » አለ
«እንደምነህ?» አለችው በአንድ በኩል በሩን ከፍታ ይዛ ስታስገባው በሌላ በኩል ደግሞ ከሱ ጋር እጅ ለእጅ ስትጨባበጥ እየገነፈለ ያስጨነቃትን ስሜት ለማመቅ ከራሷ ጋር እየተናነቀች » « መቸ መጣህ ? » አለችው " « አሁን በሁለት ሰዓቱ ባቡር መድረሴ ነው " ላንዳፍታ ከቢሮ ገባሁና አሁን ደግሞ ሚስተር ቦሻምን ለአንድ ጉዳይ ስለምፈልገው ወደሱ እየሔድኩ ነው " በይ ስመለስ እገባ ይሆናል " አሁን ግን ቸኩያለሁ አመሰግናለሁ " »
አዬ አባባና ሚስተር ስፒርነርም ከዚያ ስለአሉ ' ከነሱ ጋር ቆይተው ወደዚህ ለመምጣት በጣም ይመሽብሃል “ እነሱ እንዶሆኑ ከአምስትና ከስድስት ሰዓት በፊት
አይላቀቁም " »
« እነሱ እዚያ ካሉስ ከሚስተር ቦሻም ጋር ያለኝ ጉዳይ የግል ስለሆነ ለነገ ማስተላለፌ ነው » የያዘችውን በር ተቀብሎ ዘጋውና ክንዷን በክንዱ ይዞ ወደቤት
አመሩ እሱ ይህን ያህል የሚቀርባትና የሚይዛት በምንም ስሜታዊ ግፊት ሳይሆን
ከልማዳዊው ትሕትና በመነሣት ማክበሩ ነበር ባርባራ ሔር ግን ክንዷን ከክንዱ አቆላልፋ ጐን ለጐን ሆነው እያነጋገራት ሲሔዱ ኤደን ገነት ውስጥ እንደ ገባች ሆና ሀይሰማት ነበር "
«ታዲያስ ባርባራ ... ... ... በነዚህ ጥቂት ቀኖች ውስጥ እንዴት ሰነበታችሁ?
« መሔድህን ሳንሰማ ምን ነገር ነው ድንገት ብድግ አድርጎ የወሰደህ ? »
« ተናርሺው እኮ ባርባራ!...... ... አንድ ያልታሰበ የሥራ ጉዳይ ተፈጠረ ሔድኩ »
« ኮርኒሊያ ግን ለአንድ ቀን ብቻ መሔድን ነበር የነገረችኝ»
« አለችሽ እንዴ ? ለንደን ከደረስኰ በኋላ ብዙ የምፈጽማቸው ነገሮች
ገጠሙኝና ቆየሁ " ሚስዝ ሔር እንደምን ስነበቱ ? »
« እሷ ያው ናት እኔስ ግማሾቹ በሽታዎቿን በሐሳቧ የፈጠረቻቸው ይመስሉኛል " አሁን በግድ እየተነሣች ብትንቀሳቀስ ይሻላት ነበር " ምንድነው ከሱ ጠቅለህ የያዝከው ? »
« ሚሲዝ ሔርን እንጂ አንቺን ስለማይመለከት አትጠይቂኝ " »
« ለእማማ ያመጣህላት ነገር ነው ማለት ነው አርኪባልድ ? »
« አዎን ' አንድ ገጠሬ ለንደን ከደረሰ ለወዳጆቹ ምን ስጦታ ይዞላቸው እንደሚመለስ ነው የሚያስበው " የጥንት ወጉ ይኸ ነበር " »
« እና አሁን በርግጥ ለእማማ ያመጣህላት ነው? »
« ምነው እየነገርኩሽ …. ባርባራ ላንቺም እንድ ነገር አምጥቼልሻለሁ»
« ምን አመጣልኝ ? » አለችው ፊቷ እንዳመሉ እየቀላ ቀልዱን ይሁን እውነቱን እስክታውቅ ድረስ ሐሳቧ በጕጒት እየተንጓለለ "
« ቀስ በይ እኮ አትቸኩይ !ምን እንደሆነማ ልታይው አይደል » አላትና የያዘውን ጥቅል አጠገባቸው ከነበረ ከአንድ ያትክልት ቦታ ወንበር ላይ አስቀመጠና ኪሶቹን ሁሉ ቢዳብስ አጣ "
« ባርባራ ... ካንዱ ሳልጥለው ቀረሁ ብለሽ ? » አለና እንደገና
ኪሶቹን ሁሉ ፈለገ አራገፈ " በመጨረሻ አንድ ያልታሰበ ኪስ ውስጥ አንድ ነገር ጐረበጠው
«አይ እዚህ አለ መሰለኝ ። ግን እዚህ ምን አመጣው ? » አለና አንዲት ትንሽ ሣጥን አውጥቶ በመክፈት ከውስጧ አንድ ረጂም የወርቅ ሐብል አንሥቶ ባንገቷ አጠለቀላት ከሐብሉ ጋር ባንድ በኰል ጌጥ በሌላ በኩል የጥቃቅን መታስቢያዎች ለመያዣ የሚያገለግል ትንሽ የወርቅ ሙዳይ ተያይዞ ነበር ።
ልቧ በኃይል ሲመታ የፊቷ ቅላት እንደ ልቧ አመታት ቦግ እልም ይል ጀመር አንዲት የምስጋና ቃል እንኳን መተንፈስ አልቻለችም " ሚስተር ካርላይል ያኖረውን ጥቅል አንሥቶ ወደ ሚስዝ ሔር ዘንድ ገባ። ሻማ ባይያያዝም በክፍሉ ሲነድ የነበረው እሳት ቦግ ብሎ በርቶ ነበርዠ።
« መቸም እንዳይሥቁብኝ» አለ ያመጣውን ጥቅል እየፈታ እስከዚህም የረባ ስጦታ አይደለም ብቻ ብዙ ጊዜ ሲመኙት እሰማ ስለ ነበር ከአንድ ሱቅ መስኮት ላይ አይቼ በአየር የሚሞላ መከዳ ነው ያመጣሁለዎ » ብሎ ሰጣት » በመጋደምና በመቀመጥ ሰውነቷ ያለቀው ሚሲዝ ሔር እንደዚያ ያለ ዕቃ ለንደን እንደሚገኝ
ከመስማቷ በቀር ከነማየቷም አታስታውሰውም እንደ ጓጓች ተቀበለችውና በምስጋና ትክ ብላ ተመለከተችው "
« አንዴት ብዬ ነው የማመሰግንህ? » አለችው የደስታ ዕንባ እየተናነቃት
« አስበህ ስለ አመጣሀልኝ አመሰግንሃለሁ»
« አሁን ለባርባራ ስነግራት ነበር " ወደ ለንደን ከሔድን ለወዳጆቻችን ምን ይዘን መመለስ እንደሚገባን ማሰብ እንጀምራለን ባርባራንስ እንዴት እንዳሳመርኳት አዩዋት አይደል ? » አላት ሚስተር ካርላይል "
ባርባራ ሐብሉን ካንገቷ ቶሎ አወለቀችና ከናቷ ፊት አኖረችው "
«አቤት እንዴት ያምራል ልጄ!መቸም ለዚህ ያወጣኸው ገንዘብ ልክ አይኖረውም»
« ኧረ እሱስ ጥቂት ነው ፍሬም የለው» አለ ሚስተር ካርላይል እንደ መሳቅ ብሎ " « እንዴት እንደገዛሁት ላጫውታችሁ የጅ ስዓቴ ማሰሪያ እየተፊታ አስ
ቸገረኝና ወደ አንድ ወርቅ ሠሪ ዘንድ ጎራ ብዬ ነበር በዚያ ብዙ አይነት ሐብሎች ተሰቅለው ሳይ ኮርነሊያና ባርባራ አብረውኝወደ ሊንቦራ ሔደው በነበረ ጊዜ ባርባራ የጠፋባትን ሐብል አስታወሱኝ " ስለዚህ ለባርባራ አንገት የሚስማማውን መርጬ

👍23