አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...«ለመሆኑ የትናንቱን ፖሊስ ፍንግል አርገኸው ነበር ለካ
የሮጥከው» አለኝ
«አዎን» አልኩት
«ተነስቶ ቢከተልህስ? እና ካንተ የፈጠነ ሯጭ ቢሆንስ? ወይም
ስትሮጥ ውጋትቢይዝህስ? ወይም ቢተኩስብህስ? ወይ ፊሽካ ቢነፋና
ሌሎች ፖሊሶች ከያለበት ወዳንተ ቢሮጡስ?»

«ታድያ እንዴት ማድረግ ነበረብኝ?» አልኩት
«አታውቅምን ?»
«አላውቅም»
«እንግዲያው ነገ ጧት በአስራ አንድ ተኩል ቤቴ ና....
ከዚያ በኋላ አራት ወር ሙሉ ጧት ጧት ካስራ አንድ ተኩል እስከ
አንድ ተኩል ድረስ የሚያውቀውን ሁሉ አስተማረኝ፡፡ ከሱ እኩል
ከሆንኩ በኋላ፣ አንድ ሌሊት ማጅራት መቺዎች የሚበዙበት
ሰፈር ወሰደኝና እኔ እንግዲህ አላግዝህም፣ ዝም ብዬ ማየት ነው።ይሄ የመጨረሻ ፈተናህ ነው አለኝ

አንድ ቦታ ስድስት ዱርዬዎች ከበቡና ማኑ «ወዲህ በኩል
ያሉት ሁለቱ የኔ ናቹው፣ አራቱን ውሰድ አለኝ በእንግሊዝኛ።
የኔን ሶስቱን አጋደምኳቸው፣ አንዱ ሸሸ። ፈተናዬን አለፍኩ

ግን አንድ ሌሊት አክስ ውስጥ ብቻዬን ስዘዋወር፣ ሶስት
አሜሪካኖች ግድግዳ ላይ ሲፅፍ ይዘውት፣ ሊደበድቡት እንደ ጀመሩ
ድንጋይ በመወርወር አስጥዬዋለሁ። ይህን የአምባጓሮ ችሎታውን ለምን ከነሱ ለማምለጥ አልተጠቀመበትም? ማወቅ ፈለግኩ፣ ግን አልጠየቅኩትም። ከፈለገ እሱ ራሱ እንደሚነግረኝ አውቃለሁ)

ማኑ አንድ ሊላ ነገር አስተኖሮኛል (አለ ባህራም) አየህ፣ ድሮ ሻህ ግርማ ሞገስ ያለው፣ ከነሲሩስ ከነዳርዮሽ የሚስተካከል ንጉስ
መስሎኝ ነበር። እና እየጠላሁትም አከብረው እፈራው ነበር። በማኑ
ቀልድ እየሳቅኩ በማኑ አይን ሳየው ግን ሽህ ምንም ግርማ ሞገስ የለውም። በነዳርዮሽ ዙፋን ላይ ተቀመጠ እንጂ፣ የነዳርዮሽ ደም ወይም ክብር ወይም ጀግንነት የለውም፡፡ የአንበሳ ቆዳ የለበሰ ውሻ ነው

ብኝ እሱን ተወው

አንድ ጊዜ የኮረምሻህር ወደብ ከተማ የሰራተኞች ማርበር
ሰላማዊ ሰልፍና ንግግር ለማድረግ በህግ ተፈቀደለት። የኛ ፓርቲ ላያግዛቸው ወስኖ፣ እኔና ማኑ በባቡር ሄድን፡፡ ስነ ስርአቱ
የሚካሄደው በታጠረ ኳስ ሜዳ ውስጥ ነበር። ቦታ ቦታችንን ይዘን
ንግግሩ የሚደረግበት ሰአት ጥቂት ደቂቃ ሲቀረው፣ ብዙ ብዙ
ፖሊሶች በትልቁ በር ሲገቡ አየሁ። እንደገቡ ፊታቸው ያገኙትን
በዱላ መጨፍጨፍ ጀመሩ
ማኑን «እንሂድ?» አልኩት
«አንተ ሂድ አለኝ
«አንተስ?» አልኩት
«እኔ ደህና ቦታ እንድይዝና ካለቆቻችን ትእዛዝ ካልመጣ
በስተቀር እንዳልለቅ ታዝዣለሁ»
ይህን ጊዜ ሜዳውን ጩኸትና ትርምስምስ ሞልቶታል
“አለቆቻችን የተፈቀደላቸው መስሏቸው ነበር፡፡ ግን ፈቃዱ
ወጥመድ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን እዚህ መቆም ምንም ጥቅም የለውም፡፡
«ና እንሂድ» አልኩት
«አልሄድም፡፡ ኮሙኒስት ነኝ። አለቆቼ ሽሽ ካላሉኝ ልሸሽ
አልችልም» አለኝ
«እዚህ መቆምህ ጥቅም የለውማ!» አልኩት
“ምን ታውቃለህ? ይልቅ ሂድ ፖሊሶቹ እዚህ ሊደርሱ ነው።
በወዲያ በኩል ዝለልና አምልጥ» አለኝ
«አንተ ካልሄድክ አልሄድም» አልኩት
«እኔ አለቆቼን እታዘዛለሁ። አንተም አለቃህን ታዘዝ፡፡ አለቃህ
እኔ ነኝ፡፡ በል አሁን ሂድ። ሂድ!» አለኝ ሄድኩ። አጥሩን ልዘል ስል ዘወር ብዬ አየሁት። ዙሪያውን
ፖሊሱና ሰዉ ሲተራመስ ሲከታከት፣ እሱ ሁለት እጆቹን ደረቱ ላይ አጣምሮ እንደ ሀውልት ቆሟል። በአጥሩ ዘለልኩ
ማኑ ፖሊሶቹ ደብድበውት ሶስት ሳምንት ሙሉ ሀኪም ቤት ተኛ
መሀል ጣቱ ተሰብሮ ቀረ። አሁን ሊያጥፈው ኣይችልም
ማኑ እንዴት ኮሙኒስት እንደሆነ ልንገርህ?
አንድ የትምህርት ቤት ጓደኛ ነበረው። ጓደኝየው በጣም ጥሩ
ልጅ ነው:: ቆንጆ ቆንጆ ግጥሞችን ይደርሳል። ግን ድሀ ብጤ ነው።
ከዚህም በላይ እጅግ የተዋበ!

አንድ ቀን የዚህ ልጅ አባት ታሰሩ። በሽተኛ ሚስት፣ ስድስት
ትንንሽ ልጆች ኣሏቸው። እሱ የመጀመሪያ ልጃቸው ነው። አባትየው ታስረው ልጆቹ ምን ይብሉ? ልጁ ጨነቀው። ያባትየውን ጉዳይ የሚከታተለው የፖሊስ ሹም ቢሮ ሄደና እያለቀሰ የቤቱን ችግር ነገረው። ፖሊሱ ደግ ነበር። የልጁ ችግር ገባው። ጉዳዩ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ፣ አባትህን ዝም ብዬ ነፃ ብለቃቸው፣ የበላይ ሹማምንት ይቀጡኛል፡፡ ብቻ ለማንኛውም ዛሬ ማታ ለእራት ቤቴ ብቅ በልና እንመካከርበታለን» አለው
ሲመሽ ልጁ ፖሊሱ ቤት ሄደ፡፡ እራት ከበሉ በኋላ ፖሊሱ
ልጁን ያሻሽው ጀመር። ልጁ በመጀመሪያ ደነገጠ፤ በኋላ ተቆጣ::ይኸኔ የፖሊሱ ፊት ተለወጠ። ደግ የነበረው በሀይል ክፉ ሆነ፡፡ ረጋ ባለ ድምፅ ልጁን እንዲህ እላው
«አባትህ በኔ እጅ ነው:: ላስገድለውም እችላለሁ፣ ላሳስረውም እችላለሁ፣ ላስፈታውም እችላለሁ፡፡ ስለዚህ አባትህ ባንተ እጅ ነው
ማለት ነው:: እዚህ ከኔ ጋር ካደርክና ካስደሰትከኝ፣ ነገ አባትህ
ለምሳ ቤቱ ይመጣል፣ ተነገ ወዲያ መስሪያ ቤቱ ይሄዳል፣ በስህተት
መያዙን አስመሰክርለታለሁ፡ ቤቶችህ የሚበሉትን ያገኛሉ። እኔን
እምቢ ካልከኝ ግን አባትህ ወየውለት! ትንንሽ ወንድሞችህና
እህቶችህም ምን እንደሚውጣቸው አላውቅም፡፡ ባንተ አጅ ናቸው።
ሁሉም ባንተ እጅ ነው»
ልጁ እሺ እርስዎ እንዳሉኝ አደርጋለሁ አለ። አባትየው ተፈታ።
መስሪያ ቤቱም ተቀበሉት
ልጅየው ውርደቱን ተሸክሞ መጣና የተፈፀመበትን ግፍ
እያለቀሰ ለማኑ አጫወተው። ምን ባደርግ ይሻለኛል? አለው
አየሀ፣ ሲለያዩ ፖሊሱ ምን ብሎታል «እኔ የተገደልኩ ወይም
የተጎዳሁ እንደሆነ፣ ሁለት ሌሎች የፖሊስ ሹማምንት አሉ፤ ጓደኞቼ
ናቸው፡ ኣንተ እንደጎዳኸኝ ያውቃሉ፤
ስለዚህ አባትህን እነሱ
መልሰው ያሳስሩታል። ያን ጊዜስ አባትህን አያርገኝ፣ ቤቶችህን
አያርገኝ! ስለዚህ በኔ ላይ የበቀል ሀሳብ ባታስብ ጥሩ ነው።
ብሉታል። ልጁ ምን ይሁን? የተዋረደ ክብሩን ሊበቀል አልቻለም።
ግን ውርደቱ ሊረሳ የሚችል አይነት አይደለም። ልጁ አልቻለም።
በዛበት፡፡ ከሚችለው በላይ በዛበት፡ አበደ። አበደ በቃ! እብድ ሆነ።
ቤቶቹ በድህነታቸው ላይ ሀዘን ተጨመረጣቸው:: ደግሞስ ማን
ያውቃል? ኢራንም አንድ ታላቅ ደራሲ ባጭሩ ተቀጨባት ማለት
ይሆናል'ኮ
አይ ኢራን! ስንቱን ጉድ ትችያለሽ! ኢራን ውቢቱ! እንዴት
መሰለችህ! አቤት ህዝቡን ብታውቀው! ቋንቋውን ብትሰማው! አይ ህዝብ! እንደ ምንም ብዬ ከሻህና ከጋንግስተሮቹ ነፃ ባወጣው'ኮ የኢራን ህዝብ በደስታ ሊኖር የሚችል ህዝብ ነው። ክብሩን ልመልስለት ብችል፡ ማንንም ሳይፈራ ሰርቶ ለመብላት ቢችል፤ ህግ ካልጣስ ማንም ሊያስረው እንደማይችል እርግጠኛ ለመሆን ቢችል!
ሻህና አሜሪካኖቹ ሀብቱን ባይነጥቁት! ብቻዬን እንዳልመስልህ! በጭራሽ ብቻዬን አይደለሁም፡፡ እኔ ያየሁትን ያዩ፣ እንደኔ የሚቆረቆሩ፣ እንደኔ የተናደዱ፣ እንደኔ ደም ለማፍሰስ ዝግጁ የሆኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ኢራናውያን አሉ። አሉ! አሉ!
የሚመራቸውን ይጠብቃሉ! (አለ ባህራም)
ባህራምና እኔ ከተዋወቅን ጀምሮ እስከተለያየን ድረስ ስለኢራን
ያወራልኝ ነበር። ኢራን፣ ኢራን፣ ኢራን። አልሰለቸኝም ግን ይበዛብኝ ነበር። ይልቁንም የአገሩ መበስበስ ያንገሸግሸኝ ነበር፡፡ ሁሉ ነገር በጉቦ ነው። ፖሊሱ፣ ጃኛው፣ አስተማሪው ሳይቀር ጉቦ ይበላል።
👍17🔥2
#ምንዱባን


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ዣቬር

መሴይ ማንደላይን ከቤቱ ውስጥ የሕክምና እርዳታ የሚሰጥ ክፍል ስለነበረው ፋንቲንን ወደዚያ አስወሰዳት:: የሕክምና እርዳታ የሚሰጡ ሴሮች አልጋ ላይ አስተኝዋት:: በኃይል አተኩሳለች:: ሕሊናዋን ሳታውቅ እንዲሁ እየቃዠች ጥቂት እንደቆየች እንቅልፍ ይዞአት ጭልጥ አለ፡፡

በሚቀጥለው ቀን ወደ ስድስት ሰዓት ገደማ ከእንቅልፍዋ ነቃች
ከአጠገብዋ ሰው እንደቆመ አየች:: መሴይ ማንደላይን ጣራ ጣራውን እያየ ቆሞአል፡፡ ፊቱ በሀዘኔታ ተሞልቷል:: ከንቲባው ጣራውን ሳይሆን ግድግዳ
ላይ ከፍ ብሎ የተሰቀለወን መስቀል ነበር የሚያየው፡፡
ይህ ሰው መልአክ እንጂ ሰው አይመስላትም:: ሰውነቱ በብርሃን
የታነጸ መሰላት፡፡ መሴይ ማንደላይን እየጸለየ ስለነበር ጸሎቱን ላለማቋረጥ ሳትናገር ለረጅም ጊዜ አፍጥጣ አየችው:: በመጨረሻ ግን እየፈራች ቀስ
ብላ ተናገረች::

«ምን እየሠሩ ነው?»

መሴይ ማንደላይን ከዚህ ሥፍራ የፋንቲንን መንቃት እየተጠባበቀ
ለአንድ ሰዓት ያህል ቆሞአል፡፡ እጅዋን ይዞ የልብዋን አመታት ቆጠረ::
«አሁን ምን ይሰማሻል? ደህና ነሽ!»
«በጣም ደህና ነኝ:: እየበረታሁ ነኝ፤ እንቅልፍ ወሰደኝ» አለች ፋንቲን፡፡
«እንግዲያውስ ወደ ጥያቄሽ ልመለስና ምን ትሠራለህ ስላልሽው ስላንቺው ፈጣሪን በመማጠን ጸሎት እያደረስኩ ነበር፡፡»
ያን እለት ማታ ስለፋንቲን የሕይወት ታሪክ ሲጠይቅ አምሽቶ
በሚቀጥለው ቀን ያንኑ ቀጠለ፡፡ ምንም ነገር ሳይቀረው ስለፋንቲን ኑሮ ሁሉንም አወቀ፡፡
«ከመጠን በላይ ስቃይ ተቀብለሻል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ሀዘን አይግባሽ፡፡በዚህ ዓይነት ነው ሥጋ ለባሾች ወደ መስዋዕትነት የሚለወጡት:: ከዚህ
የተለየ መንገድ እንዳለው አላውቅም:: ይህ አንቺ ያለፍሽበት ምድራዊ ገሀነም ወደ መንግሥት ሰማይ የሚወስድ የመጀመሪያ እርምጃ ነው:: ከዚያ መጀመር ግዴታችን ነው::»
ይህን ካለ በኋላ መሴይ ማንደላይን በኃይል ተነፈሰ:: ፋንቲን ጥቂት ፈገግ ስትል ወላቃ ጥርስዋ ታየ::
መሴይ ማደላይን ወደ እነቴናድዬ ደብዳቤ ጻፈ፡፡ በደብዳቤው ፋንቲን
ያለባት እዳ አንድ መቶ ሃያ ፍራንክ እንደሆነ ገልጾ የላከላቸው ግን ሦስት መቶ ፍራንክ መሆኑን ይጠቅሳል፡፡ ብልጫ ገንዘብ የላከላቸው የፋንቲንን
ልጅ ይዘው ወዲያውኑ እንዲያመጡ ነበር:: የልጅትዋ እናት እንደታመመችና
ልጅዋን ለማየት እንደጓጓች ገልጾ ነበር ልጅትዋን ይዘው እንዲመጡ
የጠየቃቸው::
እነቴናድዬ ደብዳቤውና ገንዘቡ እንደደረሳቸው በጣም ተደነቁ::
«ሰይጣን» አለ ሚ/ር ቴናድዬ ለሚስቱ:: «ልጅትዋን አንሰጥም::
ምናልባት አንድ ቂል በውበትዋ ተማርኮ ይሆናል ይህን የመሰለ ደብዳቤ የሚጸፈው::»
ሰውየው ልጅትዋን በመላክ ፈንታ ሂሳቡን በጥንቃቄ አስልቶ ፋንቲን ያለባት እዳ አምስት መቶ ፍራንክ እንደሆነ ገልጾ የመልስ ደብዳቤ
ለመሴይ ማንደላይን ጻፈለት:: ተጨማሪው ሁለት መቶ ፍራንክ ልጅት በታመመች ጊዜ ለመድኃኒት የወጣ መሆኑን አስረድቶ ነበር የጻፈው።

መሴይ ማንደላይን ደብዳቤው እንደ ደረሰው ሦስት መቶ ፍራ
ላከላቸው:: ከገንዘበ ጋር ደግሞ በተቻለ ፍጥነት ኮዜትን ይዘው እንዲመ መልዕክት አከለበት፡፡
«በምንም መንገድ ልጅትዋን አንለቅም» አለ ማ/ር ቴናድዬ::
ፋንቲን በሽታዋ ጠናባት እንጂ ስላልተሻላት አልጋ ላይ ቆየች
መሴይ ማንደላይን በቀን ሁለት ጊዜ ይጠይቃታል፡፡ በጠይቃት
ቁጥር «ኮዜትን ቶሎ በዓይኔ የማያት ይመስሎታል?» ስትል ትጠይቀዋለች።
እርሱም ሲመልስ “ምናልባት ነገ! በማንኛውም ሰዓት ልትደርስ
ትችላለች» ይላታል፡፡
በዚህ ጊዜ የእናተዬዋ የገረጣ ፊት ወገግ ይላል::
«አዬ! እንዴት ደስ ባለኝ!» በማለት ትቆጫለች::
ሕመምዋ እያደር ጠናባት:: አንድ ቀን ሐኪሙ የሳምባዋን አተነፋፈስ
በማዳመጫ መሣሪያ ካዳመጠ በኋላ ራሱን ነቀነቀ::
«እየተሻላት ነው?» ሲል መሴይ ማንደላይን ጠየቀው::
«ዓይንዋን ለማየት የጓጓችላት ልጅ አላት አይደል!» አለ ዶክተሩ
«አዎን፡፡»
«እንግዲያውስ ቶሎ ብታስመጠላት ይሻላል፡፡»
መሴይ ማንደላይን በድንጋጤ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡
«ሐኪሙ ምን አለ?›› አለች ፋንቲን፡፡
መሳይ ማንደላይን ፊቱን ፈገግ ለማድረግ ሞከረ::
«ልጅሽን በቶሎ እንድናስመጣልሽና ይህም በሽታሽን ሊያቃል እንደሚችል ነው የነገረን» ካላት በኋላ ወደ ቢሮው ሄደ፡፡
መሴይ ማንደላይን ከቢሮው ውስጥ ቁጭ ብለ ሥራውን እየሰራ
ሳለ የፖሊስ አዛዥ ዣቬር ሊያነጋግረው እንደሚፈልግ ተገለጸለት።

«ይግባ! » አለ፡፡

ዣቬር ገባ፡፡
ለከንቲባው የአክብሮት ሰላምታ ሰጠ፡፡ ፊቱን ወደ መስኮት አዙሮ
ስለነበር ዣቬር ሲገባ የከንቲባውን ጀርባ ነው ያየው፡፡ መሴይ ማንደላይን ቀና ብሎ ሳያየው ወረቀት ማገላበጡን ቀጠለ፡፡

ዣቬር የክፍሉን ፀጥታ ሳያደፈርስ ቀስ ብሉ ወደፊት ተራመደ፡፡ ፊቱ
ላይ የቆራጥነት ብቻ ሳይሆን የድፍረትም ዓይን በግልጽ ይታያል፡፡ በመጨረሻ ከንቲባው ብዕሩን አስቀምጦ ቀና አለ፡፡
«ታዲያስ፣ ምንድነው ዣቬር? ምን አጋጠመህ?»
ዣቬር አሳቡን ለማሰባሰብ ብሎ ለአጭር ጊዜ ዝም አለ፡፡ ከዚያም
ድምፁን አለስልሶ ሀዘን በተሞላበት አንደበት «ክቡር ከንቲባ፤ አንድ ወንጀል ተሠርታል» አለ፡፡

«የምን ወንጀል?»
«አንድ ግለሰብ አንድን የመንግሥት ባለሥልጣን በስህተት ስለወነጀለ ራሱን ለማጋለጥ ይፈልጋል፡፡ እኔ ደግሞ አሁን የመጣሁት ሥራዬ
እንደመሆኑ መጠን ይህን ለማሳወቅ ነው::»
«ራሱን ለማጋለጥ የሚፈልገው ሰው ማነው?» ሲል መሴይ ማንደላይን ጠየቀው፡፡
«እኔ» አለ ዣቬር፡፡
«አንተ?»
«አዎን፤ እኔ!»
«ማንን በድለህ ነው ራስህን የምታጋልጠው?»
«ክቡርነትዎን፡፡»
መሴይ ማንደላይን ወንበሩን አስተካክሎ ተቀመጠ:: ዣቬር ሳይፈራ አሁንም በትህትና ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«ክቡር ከንቲባ ፧ እኔ አሁን እርስዎን የምጠይቀው ላደረስሁት በደል
ከስራ እንዲያሰናብቱኝና ክስ እንዲመሠርቱብኝ ነው:: »
መሴይ ማንደላይን በጣም ተደንቆ ለመናገር እፉን ከፈተ:: ዣቬር
ቀድሞ ተናገረ፡፡
ስራህን ብቻ ልቀቅ ይሉኝ ይሆናል:: ግን ይህ ብቻ አይበቃም:: በገዛ
ፈቃድማ ሥራ ተመልቀቅ መቻል ክበር ነው:: ጥፋት ስላጠፋሁና በደል ስለሠራሁ ለፍርድ ቀርቤ መቀጣት አለብኝ:: ከስራም መባረር ይኖርብኛል
«እንዴ! በምን ምክንያት?»
«ክቡር ከንቲባ ጉዳዩን ሲያውቁት ይህን ጥያቄ አይጠይቁኝም::
ነገሩ ሁሉ ይገባዎታል፡፡
ዣቬር በኃይል ተነፈሰ፡፡ ሀዘን እየተሰማውና እያፈረ ንግግሩን ቀጠለ
«ክቡር ከንቲባ ከስድስት ሳምንት በፊት ያቺን ሴት በነፃ ከለቀቅዋት
በኋላ በጣም ተናድጄ ከስሽዎት ነበር፡፡»
«እኔን ነው የከሰስከው?»
«አዎን፤ ፓሪስ ድረስ ሄጄ ለፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክሴን አቀረብኩ
ብዙ ጊዜ የማይስቀው መሴይ ማንደላይን ከት ብሎ ሳቀ::
«የፖሊስን ሥልጣን ተጋፋ ብለህ ነው የከሰስከኝ?»
«የለም፧ የጥንት ወንጀለኛ ናቸው ብዬ ነው የከሰስክዎት፡፡»
ከንቲባው ደንገጥ አለ። እንዳቀረቀረ የቀረው ዣቬር ንግግሩን ቀጠሉ
«አልተጠራጠርኩም ነበር፡፡ ለብዙ ጊዜ ጥርጣሬ ነበረኝ፡፡ መልካችሁ
👍18👎1🔥1
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በታደለ_አያሌው

...ረቂቋን የጆሮ ማዳመጫ አዉቆብኝ ኖሯል፤ መንጭቆ አወጣብኝ፡፡
ማደመጫዉን የያዘበትን እጁን ሳይ ተገለጠልኝ ባልቻ በአንድ ወቅት
ከፍተኛ የመንግሥት ደኅንነት ሹሞችን አጠቃላይ መገለጫቸዉን ለጥቂት
የሲራክ፯ አባላት በገለጸልን ጊዜ፣ ስለዚህ ሰዉ ልዩ ምልክት የነገረን አስታዉሼ ይኼን ሰዉ ገመትሁት አወቅሁት የቀለበት ጣቱ ከስሯ ጀምራ የለችም: በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ሰው
እጅ መግባቴን፣ አሁን አወቅሁ ሰዉዬዉ የሀገር ዉስጥ ደንነት ዋና መምሪያ ሹም መሆኑን አሁን ገና፣ ነገሮች ሁሉ ከተጨመላለቀ በኋላ ተረዳሁ። አጠመድሁ ስል እንደ ተጠመድሁ ያወቅሁት፣ አሁን ገና ሁለት እጆቹ ካነቁኝ፣ ድፍርስ ዓይኑ ካፈጠጠብኝ፣ ድርብርብ ጥርሱ ካገጠጠብኝ በኋላ ነበር። መጠርጠር አልነበረብኝም? ነበረብኝ።

«ላም ሆይ ላም ሆይ ሞኟ ላም ሆይ
ሣሩን አየሽና ገደሉን ሳታይ
እልም ካለው ገደል ወደቅሽብን ወይ

እያልሁ፣ መስኮት ቀርቶ ስንጥቅ እንኳን በሌለዉ አመዳም ግድግዳ ላይ
አፍጥጬ በራሴ አላገጥሁበት።

“ጥሩ” አለ የተገለበጠችዋን ወንበር አቃንቶ ራሱ እየተቀመጠባት
“እንተዋወቃ… ማን ብዬ ልጥራሽ?”

ባፍንጫዬ አናፍቼ ብቻ ጭጭ አልሁበት።

“ኦ..ይቅርታ፤ መጀመሪያ ራሴን ማስተዋወቅ ይገባኛል ለካ። ኮሎኔል…"
ብሎ ስለራሱ ሊነግረኝ ሲጀምር ጆሮዬን ያዝሁበት ስሙን እንዲጠራብኝ
አልፈለግሁም አዉቄዋለኋ!

“ማ..ነ..ሽ?” አለኝ በዝግታ፣ በዚያች ኦና ቤት ዉስጥ ብቻ ለብቻ ሲከበኝ
ቆይቶ በዓይኔ እንኳን እንዳልላወስ ከግድግዳዉ ጋር እያጣበቀኝ
ወዲያዉኑ ጆሮዉን ወደ ከንፈሮቼ አምጥቶ ለረዥም አፍታ መልሴን መጠባበቅ ቢጀምርም፣ ትንፋሼን ሳይቀር ዋጥሁበት እንኳንስ ለኮሎኔ ይቅርና፣ ለገዛ እናቴ እንኳን እንዲህ ነዉ ብዬ የማፍረጠርጠዉ ማንነት የለኝ እኔ፡ ዉብርስት እባላለሁ የሲራክ አባል ነኝ የምል መስሎታል? አያዉቀኝማ! አ ያ ዉ ቀ ን ም! ሲራክ.፯ን ጨርሶ አያዉቀንም ማለት ነዉ። የሆነዉ ሁሉ ሆኖም፣ ኮሎኔሉ ከዚህ በላይ
ትዕግሥት የሚኖረዉ አይመስለኝም: ቀጣዩን ጥያቄዉንም እንደዚሁ
ተለሳልሶ እንደማይጠይቀኝ ቁልጭ ብሎ ታይቶኛል።

ስለዚህ አእምሮዬን ማሠራት አለብኝ፡

እኔ ስለማደርገዉ ሳወጣ ሳወርድ፤ እሱ ቀድሞኝ ጆሮዉን ከከንፈሮቼ አንስቶ ከንፈሮቹን ወደ ጆሮዬ አመጣብኝ፡ ይህም ሳያንስ የጥምቀትን ዉርጭ የሚያስመሰግን ቀዝቃዛ ትንፋሹን ለቀቀብኝ ፡ ከዚያ ምላሱን እና
የላይኛዉን ትናጋዉን በማጋጨት መሰለኝ፣ ሦስት ሰቅጣጭ ድምፆች
አከታትሎ አጮኸብኝ በምላስም ማጨብጨብ ይቻላል እንዴ?

“ጣ! ጣ! ጣ!”

ጣዉላ እና ጣዉላ ቢጋጭ ራሱ እንደዚህ መጮሁን እኔ እንጃ በቅጽበት አንድ ጎረምሳ እንደ ሳምሶናይት ያለ ትልቅ ቦርሳ ተሸክሞ ከተፍ አለለት የመጨረሻ ዕድል ሰጥቼሻለሁ፣ የምትነግሪኝ አለ? ማነሽ ለማለት በሚመስል ሁኔታ በጥልቀት ሲያስተዉለኝ ቆይቶ ወደ በሩ አመራ።
በሩን ከፍቶ እንደ መዉጣት ካለ በኋላ፦

“ቶሎ!” የሚል ትእዛዝ ሰጠዉ

“እሺ፤ እንደ ተለመደዉ” ሲል መለሰለት፣ ባለ ሳምሶናይቱ አናዛዥ። እኔና አናዛዡ ብቻ ቀረን፡ በሩን ቀጭ አድርጎ ቆለፈና መክፈቻዉን በኪሱ ወሽቆ ሳምሶናይቱን እዚያች ደረቅ ወንበር ላይ አስቀመጠ። እስኪከፍተዉ ድረስ እሱም ዓይኑን ከዓይኔ፣ እኔም ዓይኔን ከእጁ ላይ አልነቀልንም አንደኛዉን ኪስ ከፍቶ ዘረገፈዉ፡ ሰአሊ ለነ! ያላመጣዉ ምንም የስለት መሣሪያ የለም፡ ትንሿ የብረት መጋዝ ሳትቀር መጥታለች፡ ከሳምሶናይቱ
ሌላኛዉ ኪስም እንዲሁ መርፌዎች እና መርዝ የተሞሉ አራት ብልቃጦች ዘረገፈ፡ ይኼ ሁሉ ለኔ እንዳይሆን ብቻ! ነዉ?

“ቶሎ ምረጭ፣ የቱ ላስቀድምልሽ?”

“እ?” አልሁት፣ ድምፄን ቢከዳኝ በቅንድብ ምልክት፡
“‹ለሞኝ ጉድኋድ አያሳዩትም፣ ቤት ነው ብሎ ራሱ ይገባበታል› ተብሎ ሲተረት ብሰማም፤ የቆንጆም ሞኝ እንዳለዉ ግን አቺን አሁን ገና አየሁ ገና በገዛ'ጅሽ ሰተት ብለሽ እንጦሮጦስ ትወርጃለሽ? ጅል!”

ደም የጠማዉ ነፍሱን በጥርሱ በኩል አሳየኝ፡፡ በኹለቱም ጎኗ ስለት ያላትን ቢለዋ እና ፒንሳ እያጋጨ ወደኔ መጣ፡ ሥራዉ የሰዎችን አካል እያፈረሰ የሚያናዝዝ ሰዉ መሆኑ ያስታዉቃል ለእንደ'ሱ ዓይነት ሰዎች ደግሞ ጥፍር መንቀል፣ የዉሃ ጥም እንደ መቁረጥ ያለ እርካታ ያመጣላቸዋል እንጂ እንዲች ብሎ አይስቀጥጣቸዉም፡ ለምደዉታል:
ርኅራኄ የሚባለዉን ነገር ከዉስጣቸዉ ጨልጠዉ ደፍተዉታል እንዲያዉም ብዙ ጊዜ የሚመረመረዉ ሰዉ ለሐቅም ሆነ ራሱን ለማትረፍ ሲል፣ ገና ሳይነኩት ቶሎ የተናዘዘ እንደሆነ በኃይል ይናደዳሉ ይባላል።

“ጅል ነሽ እንዴ ? ”

እንደ ቅድሙ ባፍንጫዬ አናፍቼ ብቻ ጸጥ አልሁት።

ቁልቁል እያየኝ ከአጠገቤ ቆሞ ነበር። ወደ ኋላ የሚመለስ መስሎ፣ ከመሬቱ ጋር ደባለቀኝ፡ ምኔን በምኑ እንደ መታኝ እንኳን አላየሁትም። ብቻ ብዥ ጭልም ብሎብኝ ቆየሁ።

ነፍሴ ስትመለስ ብልቃጧን ሲያነሳ አየሁት በብልቃጧ ላይ የሰፈረዉን
ስም አሻግሬ ሳነበዉ ሪማሾ-ሚር (Himacio-mir) የሚባለዉ የሰመመን
መርዝ መሆኑን አወቅሁ። ከሚያስቃዠዉ ሰመመን በፊት ጡንቻ የሚያኮማትር እና ሽቅብ ሽቅብ የሚያስብል ንጥረ ነገሮችም አብረዉ እንደ ተቀበመሙበት አዉቃለሁ እሱን የተወጋ ሰዉ ታዲያ እንባ እንደ ዝናብ
እስኪወርደዉ ድረስ ያምጣል እንጂ ወጥቶለት የሚገላገለዉ ነገር
አይኖረዉም፡ ለማስመለስ ጫፍ ይደርስና ይመለሳል። ስለሆነም ጭንቁ አያድርስ ነዉ በጠባብ ጫማ ከመዋልም፣ ሽንት አቋርጦ ከመቋጠርም፣ ሚስማር ላይ ከመቀመጥም ሁሉ ይብሳል

መርፌዉን ተክሎ ሲሪንጁ እስኪሞላ ድረስ ብልቃጧን ምጥጥ አደረጋት።
ሲሪንጁ ጢቅ አለለት: ይኸኔ ጡንቻዎቼን ማነቃቃት ጀመርሁ። ከቀደመኝ አበቃልኝ፡ ልክ እጁን አንከርፍፎ ሲመጣ፣ የፈራሁ መስዬ አንድ ዓይኔን በእጆቼ ጨፈንሁ: ወደ ማጅራቴ መርፌዉን ሲሰድ እጁን
ለቀም አድርጌ ያዝሁትና፣ ፋታ ሳልሰጠዉ ጠምዝዤ ደረቱ ላይ ስካሁለት ዓይኔን እንኳን እስከማርገበግብ አልዘገየም፣ ትዉኪያ ሲያጣድፈዉ ልክ የገማ ጣት እንደ ጎረሰ ሰዉ፣ እንባዉ ዱብ እስኪል ድረስ ሽቅብ ቢለዉም ምንም አይወጣዉ። “ህእእእ!” ይላል በየቅጽበቱ፣ ስቃይ ብቻ! በዚያ ላይ የሠራ አካላቱ እየዛለበት መጣና፣ እንደ አሮጌ ጨርቅ እጥፍጥፍ ብሏል ጊዜ ኖሮኝ ባዘንሁለትማ ደስታዬ ነበረ ግን ለሐዘኔታ የሚሆነዉን ጊዜ የት ልዉለድለት? ይልቅ አሁኑኑ ማምለጥ አለብኝ፡፡ ባይሆን
እያመለጥሁ አዝንለታሁ
ያዉም ከቻልሁ ከኪሱ ባወጣሁት ቁልፍ በሩን ቀስ አድርጌ ከፍቼ አንገቴን ሳሰግግ
በአካባቢዉ ማንም የለም:: ቢሆንም ግን እርግጠኛ መሆን አልቻልሁም:
ያለሁት ዋነኛዉ ቤተ መንግሥት ዉስጥ ነዉ፡ ቤተ መንግሥትን ያህል ግቢ፣ በሚታዩና በሚዳሰሱ ወታደሮች ብቻ ይጠበቃል ማለት ጅልነት
ነዉ። በየሥርቻዉ ካሜራ፣ በየቦታዉ ረቂቅ ዳሳሾች መኖራቸዉ አያጠራጥርም።

“ህእእእ. አህክ እትፍ! ህእእእ አህክ እትፍ!” ይላል አሁንም፣አንጀቱ ከጉሮሮዉ ጫፍ እስኪደርስበት እየሳበዉ፡ ደም ከሚያስንቅ እንባ በቀር ሌላ ምንም ጠብ አይለዉም: መጨከን አለብኝ እንጂ፣ ሁኔታዉ አንጀት ይበላል ያሳዝናል። የሐፍረተ ሥጋዉን መሸፈኛ ብቻ ትቼለት
👍33🥰2
#ሳቤላ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...«ደኅና እኔ እጠራታለሁ » አለና ሚስተር ካርላይል በዚያ ግጥም ብሎ በሞላው ሕዝብ መኻል ዐልፎ ሔደ " በዚያ ሰዓት አንዲቷ የለንደን ተጫዋች አሳዛኝ
ዘፈን ስትዘፍን ስለነበር ተመልካቹ ሁሉም ሚስተር ካርላይልን በክፉ ዐይን ዐየው የሰውን መከፋት ችላ ብሎ አለፈና ከሳቤላ ፊት ቆመ።

"እኔ ደሞ ዛሬ ማታ ወደኔ ትመጣለህ ብዬ አላሰብኰም - በጣም ግሩም ዝግጅት አይዶለም ? እኔን መቸም እንዴት አስደሰተኝ መሰለህ » አለችው .

« እዎን በጣም ደስ የሚል ነው » አላት ፊቱን ጥቁርቁር እያደረገ
« አሁን ግን ስቤላ ( ሎርድ ማውንት እስቨርን እምብዛም ደኅንነት የተሰማቸው አልመሰለኝም " ስለዚህ ሠረገላውን ልከውልሻል »

« ምን ! አባባ ደኅና አይዶለም !! » አለች ከመናገሩ ቀጠል አድርጋ።

«ሳያማቸው አልቀረም ግን እስከዚሀም አይመስለኝም " ሆኖም ወደቤት እንድትመጭ ይፈልጉሻል : እየመራሁ ላሳልፍሽ ? »

«አየ አባባ ... ሁልጊዜ እንዳሰበልኝ አሁንኮ እንዳይሰለቸኝ ስለሠጋ ቀደም ብሎ ሊያላቅቀኝ ፈልጎ ነው " አመሰግናለሁ ... ሚስተር ካርላይል " እስከ ዝግጅቱ መጨረሻ እቆያለሁ »

« የለም የለም ሳቤላ ... እሱማ ስለ ባሰባቸው ነው የላኩብሽ» መልኳ ልውጥ ግንባሯ ቁጥር አለ ግን አልደነገጠችም « እሺ ጥሩ አሁን አዳራሹን አንዳንረብሽ ይህ የተጀመረው ዘፈን ያብቃና እወጣለሁ »

« ጊዜ ባታባክኝ ይሻላል ስለ አዳራሹና ስለ ሕዝቡ ምንም አታስቢ»

ወዲያው ተነሥታ ክንዷን ከሚስተር ካርላይል ክንድ ጣል አደረገች » እሱም ነገሩን ለሚስዝ ዲሊ ገጸላትና ሳቤላን እየመራ ይዟት ወጣ ተመልካቹ በግድ
በመጨነቅ መንገድ እየሰጠ አሳለፋቸው " ብዙ ሕዝብም በዐይኑ ተከተላቸው ከሁሉ የበለጠ የተቅበጠበጠችውና ለማወቅ የጓጓችው ግን ባርባራ ነበረች "
የት ሊወስዳት ነው ? » አለች ሳታስበው
« እኔ ምን ዐውቃለሁ ? » አለቻት ኮርነሊያ « ባርባራ ... ዛሬ ማታ መቁነጥነጥ አበዛሽሳ? ምን ነካሽ? ሰዎችወደዚህ የሚመጡት እኮ ሊያዳምጡ ሊመለከቱ
እንጂ እንደዚህ ሊቅበጠበጡ አይደለም »

የሳቤላ ካባ ከተቀለበት ወርዶ ተደረበላትና ደረጃውን ከሚስተር ካርላይል ጋር ወረደች " ሠረገላው እስከ በሩ ተጠጋላት ። ሠረገላ ነጂው መንገድ ለመጀመር
ልጓሙን ሳብ አድርጎ ተዘጋጅቶ ጠበቃት አንድ ሌላ አሽከር እመቤቲቱን ገና ሲያያት የሠረገላውን በር ከፈተላት ሰውየው ገና ሥነ ሥርዓት ያልተማረ አዲስ ገብ ገጠሬ ብጤ ነበር " ክንዷን ከሚስተር ካርላይል ክንድ አስለቅቃ ወዶ ሠረገላው ልትገባ ስትል ሰውየውን እያየች ትንሽ ቆም አለችና « አባባ በጣም አሞታል እንዴ ? » አለችው "

« አዎን እመቤቴ ሲያቃስቱ ለሰማቸው ያሳዝናሉ " አዩ አንጀት ሲበሉ ! ሰዎችማ ምናልባት ዛሬን ቢያድሩ ነው እንጂ አይተርፉም ይላሉ » አላት።

ምርር ብላ ጮኸችና ከመደንገጧ የተነሣ ልትወድቅ ስትል የካርላይልን ክንድ ግጥም አድርጋ በመያዝ ተረፈች ሚስተር ካርላይል ሰውየውን በቁጣ ገፈተረው ።ከዚያ ድንጋይ ንጥፍ መሬት ላይ በቁመቱ ቢዘርረውም አይረካም ነበር " በጣም
ተናድዶበታል "

«ምነው ሚስተር ካርላይል ለምን አልነገርከኝም ? » አለችው እየተንቀጠቀጠች "

« እኔስ አሁን በመናገርሽም በጣም አዝኛለሁ አሁንም አትደንግጪ ! ሁል ጊዜም እንዴት እንደሚነሣባቸው ታውቂያለሽ " የተለመደው በሽታ ተነሣባቸው
እንጂ ሌላ ምን ይሆናሉ ብለሽ ነው » በይ ይልቅ አሁን ግቢና እንሒድ ምንም ክፉ ነገር እንደማይጠብቀን አምናለሁ»

« አንተም አብረኸኝ ልትመጣ ነው ? »

«አዎን ብቻሽን እንዴት እሰድሻለሁ?» አላት እንዲቀመጥ ፈቀቅ አለችለት "

« ግድ የለም ተይው እኔ ከውጭ እቀመጣለሁ » አላትና በሩ ከተዘጋ በኋላ ከነጂው ጐን ተቀመጠ አሽከሮቼ ከኋላ ተቀመጡ " ሠረገላው ገሠገሠ " ሳቤላ
ከአንድ ጥግ ሽብልል ብላ ተቀምጣ ትንሠቀሠቅ ጀመር "

« ለፈረሶቹ አትዘንላቸው ቶሎ ቶሎ ንዳ አለበለዚያ ሳቤላ በሐሳብ ብቻ ትታመማለች » አለ ሚስተር ካርላይል

« ምስኪን ልጅ መከራዋ አላለቀላትም " ሌሊቱ ከመንጋቱ በፊት ከዚህ የከፋ ነገር ይጠብቃታል " እኔ ከዚህ ቤት ዐሥራ አምስት ዓመቴ ነው ። እሷን ገና ሕፃን ሳለች ጀምሬ ነው የማውቃት »

« ግን ኧርሉን በጣም የሚያሠጋቸው ነው ? »

« አዎን በጣም ታመዋል ሚስተር ዌይን ራይት በሽታው ወደ ልባቸው ተሸጋግሯል ሲሉ ሰምቻለሁ »
« ወትሮምኮ በሺታው ሲነሣባቸው እንዶዚህ ኃይለኛ ነው »

« ዐውቃለሁ የዛሬው ግን የተለየ ነው » ከዚህ ሌላ ዶግሞ » አለ ሠረግላ ነጅው በምስጢር አነጋገር « የሌሊት ወፎቹም በከንቱ አይዶለም የመጡት »

« የሌሊት ወፎቹ ? » አለ ሚስተር ካርላይል "

« አዎን " የነሱ መምጣት ሞት ሰተት ብሎ ወዶቤት መግባት መሆኑን የማያወላውል ምልክት ነው»
« ስለ ምንድን ነው የምታወራው ሚስተር ዌልስ?» አለው ሚስተር ካርላይል
« ዛሬ ቤቱን የሌሊት ወፎች ሲዞሩት አመሹ የት አባታቸው አስቀያሚዎች ናቸው " እኔማ አልወዳቸውም "

« የሌሊት ወፎች ኮ ሌሊት የትም መብረር ይወዳሉ ተፈጥሯአቸው ነው . . .

« ተፈጥሮአቸው ቢሆንም በመንጋ ሁነው እየበረሩ በመስኮት አይገቡም ዛሩ ማታ እመቤቴን ከሙዚቃው ትርዒት አድርሼ ተመለስኩ " ከዚያ ሚስዝ ሜሰን
እንደምትፈልገኝ ነገሩኝና እሷ ወደ ነበረችበት ወደ ቤተ መጻሕፍቱ ስገባ ከተከፈተው መስኮት ቁማ አገኘኋት » ብርድ ስለነበር ለምን መስኮት ከፍታ እንደ ቆመች ጠየቅኳት እሷም ቀረብ ብዬ
እንድመለከት ጠራችኝ እኔም ወደ መስኳቱ ጠጋ ብዬ ብመለከት
ብመለከት በሕይወቴ አይቸው የማላውቀው ጉድ አየሁ" በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የሌሊት ወፎች ዳመና መስለው ክንፎቻቸውን እያማቱ መጡብን ወደ ኋላችን ሸሸት ባንል ኖሮ ፊታችንን ይመቱን ነበር " ከየት እንደ ተጠራቀሙ አላውቅም ከአንድ ደቂቃ በፊት ከደጅ ሳለሁ ለምልክት እንኳን አልነበሩም "

እነዚህ የለሊት ወፎች ምን ነካችው ይህን የሚያህል ክምችት ባንድ ላይ ሆነው አይተህ ታውቃለህ ... ዌልስ ? አለችኝ ሚስዝ ሜሰን “ እኔም ኧረ የለም ደግሞ እንደዚህ ከሰው ሲጠጉም አይቸ አላውቅም እንደዚህ ሆነው ባያቸውም ደስ አይለኝም " ገዱ ደግ አይደለም የክፉ ነገር ምልክት ነው አልኳት ለካስ እሷም በምልክቶችና በሕልመች ከሚስቁት አንዷ ሆናለች በሳቅ ልትፈርስ
እርሶዎም እንደሚያውቁት እሷ እመቤት ሳቤላን ከድሮ ጀምራ ስታስተምር የኖረች ናት እነዚህ የተማሩ ሰዎች በምልክት በሕልም በቀላሉ አያምኑም »

ሚስተር ካርላይል አንገቱን ነቀነቀ

« እንዶዚህ በብዛት መምጣታቸው የምን ምልክት ነው ትላለሀ ... ዌልስ አለችኝ ሚስዝ ሚዞን እያሾፈችብኝ „ “ እኔ እንደዚህ ግጥም ብለው በብዛት ሲመጡ
አይቻለሁ አላልኩም ግን የሌሊት ወፎች እንደዚህ በብዛት ሆነው ወደ ቤት ሲገቡ ብዙ ጊዜ መታየታቸውንና ከገቡበት ቤትም ሰው እንደሚሞት የማያብል
የታወቀ ምልክት መሆኑን ሲነገር ሰምቻለሁ ' አልኳት “ ኧረ ሞትስ በዚህ ቤት አይምጣ” እያለች መስኮቱን ዘጋችው የጌቶች ነገር በሐሳቧ መጣባት መስኮቱ እንደ
ተዘጋ እነዚያ አስቀያሚ ፍጡሮች መስኮቱን በክንፋቸው ይጠፈጥፉት ጀመር ከዚያ ሚስዝ ሜሰን ለአንድ ሦስት ደቂቃ ያህል ስለሌላ ጉዳይ ስታነጋግረኝ ቆየችና ስታበቃ ወደ መስኮቱ ዞር ብዬ ብመለከት አንድም የሌሊት ወፍ አልነበረም“

« ደግሞ ካንዱ ቤት መስኮት ክንፎቻቸውን ሊያርገበግቡ ሔደው ይሆናላ» አለ ሚስተር ካርላይል በነግሩ ባለማመን ።
👍27