አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_ሁለት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

#እንደወረደ_ነውና_ለአንባቢ
#የማይመቹ_እኛ_ፀያፍ_የምንላቸው
#ቃላቶች_አሉትና_አሁንም
#በድጋሚ_እንደምናገረው
#የማይመቸው_እንዳታነቡት
#እመክራለሁ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አማንዳ
ለጥቂት ጊዜ


ያን ሰሞን አንዲት ቆንጆ አሜሪካዊት ነበረችኝ፣ አይኗ
ሰማያዊ፣ ፀጉሯ በጣም ንፁህ ቡና አይነት፡፡ እጅግ ደስ ትላለች፣
አልጋ ውስጥ ልብ ታጠፋለች ግን በማልፈልጋት ሰአት ሆቴሌ
እየመጣች አላሰራ ስላለችኝ፤ ቤተ መፃህፍት እየሄድኩ መስራት ግድ
ሆነብኝ፡፡ ሆቴሌ ስታጣኝ ወደ ቤተ መፃህፍቱ መምጣት ጀመረች።

እሷን ለመሸሽና በዚያውም ባህራምን ለማወቅ ስል ሀበሾቹን
እጠጋቸው ጀመር ምግብ ቤት አብሬያቸው እገባለሁ፣ ካፌ
ዶርቢቴል አብሬያቸው ካርታ እጫወታለሁ ከባህራም ጋር ግን ላይ ላዩን እየቀለዱ ለመሳቅ እንጂ፣ የልብ ለመጫወት አጋጣሚ ለጊዜው አላገኘሁም። ይልቅስ ከሀበሾቹ ጋር ግንኙነት በማድረጌ «ሚስቶቻቸውን» በመጠኑ እያወቅኳቸው ሄድኩ፡፡

የነበርንበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሴቶች ከወንዶቹ በጣም ይበዛሉ፡፡
ስለዚህ ለሁሉ ሴት 'ሚዳረስ ወንድ የለም....አሉ ሶስት፣ አራት፣
አምስት 'የሆኑ ወንድ 'ሚያድኑ ልጃገረዶች። ታድያ ወንዱን ቆንጆ
ቆንጆዎቹ ይዘውታል፣ ተጠምጥመውበታል። ነፃ የሆነ ወንድ አይገኝም፣ ቢገኝም ወይ የደስ ደስ የለውም፣ ወይ ጥቁር ነው። ጥቁር ደሞ ምን ቢወዱት አገሩ መመለሱ አይቀርም፡፡ ብልጥ ወይም ውብ ወይም እድለኛ ካልሆኑ፣ ፈረንሳይ ወንድ ማግኘት አይቻልም። ሳያገቡ የማርጀት ፍርሀት በወራቱ ዋሻ ሰአመታቱ ጫካ አድፍጦ
ይጠብቃል.

ጥቁሮቹ ወንዶች ገና እንደመጡ፣ በንግድነት ምክንያት ቆንጆ
ሴት ማጥመዱን ለጊዜው ስለማያውቁበት፣ የተገኘችውን እሺ ብለው ይቀበላሉ። የምትገኘው ደሞ ቆንጆ ያልሆነች ናት፣ ስለዚህ ማቆያ
ናት...

«የሀበሾቹ ሚስቶች» ጎደሎ ብጤዎች ነበሩ፡- እዚህ ቅርፅ
ይጎድሳል፣ እዚያ ድምፅ ይጎድላል፣ እዚያ ጠባይ ይጎድሳል። ብቻ፣ሉልሰገድ እንዳለኝ ሁሉም ያ ነገር ኣላቸው ለጊዜው ሀበሾቹ የፈለጉት እሱን ነው:: መልኩ፣ የደስደሱ፣ ደማምነቱ፣ ጠባዩ፣ በኋላ
ዝግ ተብሉ ይፈለጋል ከሁሉም አስቀያሚ አማንዳ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ድብልብል
አሜሪካዊት ናት፡፡ ወፍራም አንገቷ ዙርያ ስጋው ተጣጥፏል፣ ሽንጥ
ሚሉት የላትም፣ ስትራመድ የሚንቀጠቀጠው ባቷ ረዥም ቂጥ ይመስላል። በጭራሽ ስሜት አትቀሰቅስም። ሉልሰገድ ለምን
እንደያዛት ለጊዜው ሊገባኝ አልቻለም፡፡ የቸገረው እርጉዝ ያገባል ይባላል፣ እሱ ግን አቅፏት ይዞራል። ወገቧ ዙርያ እጁ ስለማይደርስ ትከሻዋን አቅፎ እሷ ወገቡን አቅፋ ሲሄዱ አያቸዋለሁ። የአማንዳ ፈገግታ ደግና ንፁህ ነው፣ ትንንሽ አይኖቿ ንፁሀ ሰማያዊ ናቸው፣ ረዥም ፀጉሯ በጣም ንፁህ ነጭ ሆኖ፣ ጨረቃ ውስጥ ተነክሮ የወጣ ይመስላል። ግን ይህን ሁሉ ውበት ጮማዋ አፍኖ ይዞ እንደሌለ አድርጎታል። ስታያት ውፋሬዋ ነው 'ሚታይህ፣ ስታስታውሳት ጮማዋ ነው ትዝ ሚልህ

ሲልቪ ግን በጣም ቆንጆ ናት። «እጥር ምጥን» ያለች ፈረንሳዊት ሆና፣ ቡናማ ጉልህ አይኖቿ ውስጥና ውብ ሰፊ አፏ
ዙርያ እንደ ነበልባል የሚውለበለበው ፈገግታዋ ልብ ያሞቃል። ወደ ኋላ የተለቀቀው ንፁህ ጥቁር ፀጉሯ ያብለጨልጫል፣ ስትራመድ
ረዥም አንገቷን እያወዛወዘች ስለሆነ፣ ይሄ ጥቁር ሀር ፀጉሯ ዥው ዥው ይጫወታል። ከታች ደሞ አበጥ ያለው ዳሌዋ ያንኑ ያህል ይወዛወዛል። እግሯ በብዙ ጥንቃቄ የተቀረፀ ውብ ፍጥረት ነው::ፍቅርም ምኞትም የምትቀሰቅስ ወጣት ትመስላለች። ተመስገንን በጣም ትወደዋለች ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ይሄ ተመስገን ፈረንሳይ አገር የተስማማው ይመስላል።

ዩኒቨርሲቲውን «ሲቴ» ይሉታል። ሲቴ ውስጥ መኝታ ቤት
ያላቸው ሀበሾች ተመስገን፣ ሉልሰገድ፣ ተካ፣ ሀይለየሱስ ናቸው፡፡
ሌሉቹ እንደኔው የሆቴል ክፍል ወይም የከተማ ቤት ተከራይተው
ይኖራሉ ቆንጆዋን አሜሪካዊት እንዳላገኝ ስፈልግ ከሉልሰገድ ወይም ከተመስገን ቁልፍ ለምኜ መኝታ ቤታቸው ቁጭ ብዬ ሰራለሁ::ሀይለየሱስ ቤት እንዳልሰራ ሰውየውን አልወደውም። ተካ ቤት
እንዳልሰራ ደሞ የተካ ቤት ይገማል። አይ ተካ! እግዜር ይይለት አንዳንዴ እንኳ እግሩን ቢታጠብና እግር ሹራቡን ቢያጥብ ምን ቸገረው ነበር? ዝም ብሎ ብቻ ጥፍሩን እየነከሰ መነጫነጭ ምን ያረግለታል?

ሉልሰገድ ወይም ተመስገን ቤት ቁጭ ብዬ ስስራ አንዳንዴ
ባህራም ይመጣል፡፡ ትንሽ እናወራና ፂሙን ተላጭቶ መልካም ስራ ብሉኝ ይወጣል። ፀጉራም ነው። እጆቹን፣ ደረቱን፣ አንገቱን፣ ፊቱን ፀጉር ወሮታል። ፂሙን ሲላጭ አይኑ፣ አፍንጫውና ጆሮው ብቻ ናቸው መላጨት የሌለባቸው:: ቢሆንም ፀጉሩ አያስቀይምም፡፡ በጣም
ንፁህ ሰው ነው።

አንዳንዴ ደሞ ቁጭ ብዬ ስሰራ ድቡልቡሏ አማንዳ ወይም
ውቢቷ ሲልቪ ይመጣሉ ወዳጃቸውን ፍለጋ፡፡ ቀስ በቀስ እነዚህን ሁለት ልጃገረዶች» እያወቅኳቸው፣ እየወደድኳቸው ሄድኩ፡፡ እነሱም ሊወዱኝ እንደጀመሩ ታወቀኝ። ስለራሳቸው ኑሮ በመጠኑ ይነግሩኝ ጀመር ..

አንዳንድ ቅዳሜ ማታ ሀበሾቹና ጓደኞቻቸው «ሱርፕሪዝ ፓርቲ»
ያደርጋሉ። «ሰርፕሪዝ ፓርቲ» ድንገተኛ ብጤ ነው። ታስቦ የታቀደ
ፓርቲ ሳይሆን፣ ጓደኛሞች ሲገናኙ «ዛሬ ምን እናርግ? ሲኒማ
እንግባ ወይስ ምን ይሻላል?» ይባባሉና ለምን ሰርፕሪዝ ፓርቲ
አናረግም?» ይላሉ፡፡ ያን እለት ማታ ፓርቲው ይደረጋል። የተገኙ
ሰዎች ይጠራሉ፣ የራሳቸውን መጠጥ ይዘው እንደሚመጡ የታወቀ ነው:: አንዱ ቤት ፓርቲው ይደረጋል። ለዚህ ጉዳይ ሀበሾቹን
ባህራም ያገለግላቸዋል
ይጀምራል፤ ወንዶቹን ይጠራል፣ ሴቶቹን ይጋብዛል፣ እዚህ ትእዛዝ
እንደ አውሎ ነፋስ በፍጥነት መዘዋወር ይጀምራል ወንዶቹን ይጠራል ሴቶቹን ይጋብዛል እዚህ ትእዛዝ እዚያ ምክር ይሰጣል፣ ከዚህ ዲስክ ከዚያ ሴት ይዋሳል፣ ፓርቲው ይጀመራል። ተሳታፊዎቹ ወንዶች ኣብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያንና ኢራናውያን ናቸው፣ የሁለቱ አገሮች ማህበር ይመስላል።

እንዲህ አይነት ፓርቲ ውስጥ ነበር ሉልሰገድ አማንዳን ያገኛት። ፓርቲው ውስጥ ጥቂት ሴቶች ብቻ ነበሩ፣ እነሱም ተይዘዋል፡፡ ያልተያዙ አንዲት በጣም ደቃቃ የሆነች የሩቅ ምስራቅ
ልጅና እንዲት አስቀያሚ ድቡልቡል ኣሜሪካዊት ብቻ ናቸው::ምስራቃዊቷ በጣም ደስ ትላለች፣ ግን ሉልሰገድ እሷን ይዞ አልጋ ውስጥ ሲገባ ሊታየው አልቻለም። «ዎ! ብትሞትብኝስ?» ብሎ አሰበ፡፡ ተዋት። ድቡልቡሏ አሜሪካዊት ፈፅማ ደስ አትልም፣ ግን ሙዚቃውና መጠጡ እየገፋፉ ወደሷ ወሰዱት። ተዋወቃት። ስሜ
አማንዳ ነው አለችው፣ አብረው ይደንሱ ጀመር፡፡ በእንግሊዝኛ
እያወሩ ሁለቱም በብሉይ ጠጡ፣ ሞቅ አላቸው:: ስታቅፈው
ስታናግረው በጣም ደስ እያለችው ሄደች ይስማት ጀመር

«ተው እዚህ አትሳመኝ» አለችው

«ምናለበት?» አላት ጆሮዋን እየሳመ አልችልም፡፡ ስሜቴ በጣም ይቀሰቀሳል» አለችው:: ድምፅዋ
በጣም አቆመበት።

ታድያ ምናለበት?» አለ እየተሻሻት

"ያኔ መሳም ብቻ አይበቃኝም» ብላ በሀይል ተጠጋችው::

ሉልሰገድ ቀስ ብሎ ወደ አንዱ መኝታ ክፍል ገብቶ እዚያ
ይሳሳሙ የነበሩትን ሁለት ፈረንሳዮች አስወጣቸው። (መኝታው የማን እንደሆነ እንጃ መብራቱን አጠፋ። ተመልሶ መጥቶ አማንዳን ወደዚህ ጭለማ መኝታ ቤት ወሰዳት፡፡ በሩን ቆለፈ። አልጋው ላይ አጋድሞ ይስማት ጀመር። እየሳመ፣ እያሻሽ ሙታንታዋን አስወለቃት። ጭለማ በመሆኑ አስቀያሚ መልኳ ስለማይታየውና፣አሳሳም ከማወቁም በላይ ወፍራም ገላዋ ምቹ ስለሆነ፣ እጅግ በጣም ተደሰተባት ጠግቦ ከላይዋ ሊነሳ ሲል፣ እቅፍ አደረገችውና እንዳይነሳ ከለከለችው
👍231
#ምንዱባን


#ክፍል_ሁለት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

....አልፎ አልፎ መስመሩን
የሚዘረጋው ጨረቃና ደፋ ቀና የሚሉት ከዋክብተ አካባቢው ጨርሶ ጨለማ እንዳይሆን ረድተዋል :: ስለዚህ የመሬቱን የሰማዩን ያህል አልጨለመም:: ሆኖም አካባቢው በጣም ያስፈራል፡፡.

ከጉብታውና ከተንጣለለው ሜዳ ላይ ከአንድ ቅርጸ ቢስ ዛፍ ሌላ
ምንም አልነበረም፡፡ ዛፉ መንገደኛው ከደረሰበት ሩቅ አልነበረም:: ሁናቴው ስላላማረው መንገደኛው ወደመጣበት ተመለሰ፡፡

ከምሽቱ ወደ ሁለት ሰዓት ገደማ ሆኖአል፡፡ አካባቢውን ስለማያውቅ
መንገድ እንደመራው ብቻ ዝም ብሎ ተጓዘ፡፡ የከንቲባውን ቤት እንዳለፈ ከትምህርት ቤት አካባቢ ደረሰ፡፡ ትምህርት ቤቱን አልፎ እንደ ሄደ ቤተክርስቲያን አጋጠመው:: ገና ቤተክርስቲያኑን ሲያይ እጁን ጨብጦ ዓይኑን ወደላይ አንጋጠጠ፡፡

ከቤተክርስቲያን ፊት ለፊት አንድ ማተሚያ ቤት አለ፡፡ ሰውዬው
ድካም አወራጭቶት ስለነበር ከዚህ የተሻለ ሥፍራ ሳይፈልግ ከማተሚያ ቤቱ አጠገብ ከነበረው የድንጋይ አግዳሚ መቀመጫ ላይ ተጋደመ::

ወዲያው እንደተጋደመ አንዲት አሮጊት ከቤተክርስቲያኑ ወጡ፡፡
«ወዳጄ ከዚህ ምን ታደርጋለህ?» ሲሉ ጠየቁት፡፡

«አየሽ የእኔ አዛኝ፤ መተኛቴ ነዋ!» አሊ በቁጣና በድፍረት የማይሆን
መልስ መስጠቱ ሳይታወቀው:: ክብር የሚገባቸው አዛኝዋና ደግዋ ሴት ማዳም ላ ማርኩዚ ይባላሉ::

«እንዴ! ከድንጋይ ላይ!» አሉ፤ «ሌሊቱን በሙሉ ከድንጋይ ላይ
ተኝተህ ሊነጋልህ አይችልም:: ረሃብ እንዳንገላታህና ብርድ እንዳጠቃህ ሰውነትህ ይመስክራል፡፡ የሚያስጠጋ አላገኘህም?»

«ብዙ ቤት ሞከርኩ፤ የየቤቱን ደጃፍ አንኳኳሁ::»

«እና!»

‹‹ሁሉም ሰው ከበራፌ ሂድ አለኝ::
ደግዋ ሴት የሰውዬውን ጀርባ እየመቱ፡ ከአደባባዩ ባሻገር የሚታየውንና ከጳጳሱ ቤት አጠገብ የነበረውን ቤት ጠቆሙት፡፡
«ያንን ቤት ሞክረሃል?» ሲሉ ጠየቁት::

«አዎን::»

«ከዚያ ማዶ ከሚታየው ቤት አንኳኩተሃል?»

«የለም::»

«እዚያ ሞክር እስቲ፡፡»

እናያ ደገ ጳጳስ ከተማ ወስጥ ሲዘዋወሩ በመቆየታቸው ስለደከማቸው ያን እለት ማታ ከክፍላቸው ሳይወጡ ብዙ ቆዩ:: በተጨማሪም ብዙ ስራ
ስለነበራቸው «ሥራዩን ሳልጨርስ አልነሳም» በማለት አእዚያው አመሹ::

ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲሆን እዚያው ሥራቸው ላይ ነበሩ:: በብጣሽ ወረቀትና በማስታወሻ ደብተር ላይ ጉልበታቸውን እያስደገፉ ሲፅፉ
እንደተለመደው አልጋቸው አጠገብ ከነበረው ቡፌ ከብር የተሠራ ሣህን ለማውጣት መዳም ማግልዋር ይገባሉ:: ሴትዬዋ ከተመለሱ በኋላ ጥቂት
ቆይቶ ገበታ እንደቀረበና እህታቸው እንደሚጠብቋቸው በመገመት ጳጳሱ ወደ ምግብ ቤት ሄዱ:: ምግብ ቤቱ፡ የአራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ዓይነት ሆኖ የእሳት ማንደጃ አለው:: ቢፈለግ ወደ አውራ ጎዳናው የሚያስወጣ በርም አለው:: በአትክልቱ በኩል መስኮት አለ፡፡

ማዳም ማግልዋር ገበታውን ሠርተው ከጨረሱ በኋላ ጠረጴዛውን እያስተካከሉ ከመድምዋዚል ባፕቲስታን ጋር ይጫወታሉ:: ገበታው አጠገብ
ሻማ ከትንሽ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ እየተቀጣጠለ ነው:: ከማንደጃው ውስጥ
የተቀጣጠለው እሳት ፍም ብዛት ስለነበረው ክፍሉ ይሞቃል፡፡ የቤታቸው በር እንዴት መቆለፍ እንዳለበት መዳም ማግልዋር ሲያወሩ ጳጳሰ ይገባሉ፡፡

ማዳም ማግልዋር ለእራት የሚሆን ሸቀጣሸቀጥ ለመግዛት ወደ ገበያ ሄደው ሳለ አንድ መግቢያ ያጣ ማጅራት መቺ ከተማ መግባቱንና ይህ ሰው
በጊዜ ከቤታቸው በማይገቡ ሰዎች ላይ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል ሲወራ ይሰማሉ፡፡ ሁለቱ ሴቶች ስለዚሁ ጉዳይ ሲያወሩ ጳጳስ ስለገቡ «አባታችን
መዳም ማግልግር የሚናገሩትን ይሰማሉ?» በማለት ጠየቅዋቸው::

«የምትሉት ነገር ግልጽ ባይሆንልኝም ሰምቼአለሁ» አሉ ጳጳሱ፡፡ከዚያም ፊታቸውን ወደሚነድደው እሳት በማዞርና እጆቻቸውን ከጉልበታቸው
ላይ በማሳረፍ ሠራተኛቸውን እያዩ

«ታዲያስ ፤ ምንድነው ጉዳዩ? የሚያስፈራ ነገር አለ እንዴ?» ሲሉ ጠየቁ፡፡

ይህን ጊዜ መዳም ማግልዌር ሳያስቡት ታሪኩን በማጋነን አዋሯቸው::
«ያለመጫሚያ ባዶ እግሩን የሚጓዝ ማጅራት መቺ፧ ሌባ፤ ቀማኛ ከተማ ገብቷል» አሉ፡፡ «ክዊን ላባር ሄዶ ማረፊያ ቢጠይቅ ባለቤቱ አልፈቀደለትም::
ከመሸ በኋላ ከተማ ውስጥ ሲዘዋወር ታይታል:: ስልቻውን በገመድ አስርና ተሸክሞ ይዞራል:: መልኩ ደግሞ በጣም የሚያስፈራ ነው::

«እውነትሽን ነው?» ሲሉ ጳጳሱ ጠየቁ፡፡

ጳጳሱ በታሪኩ የተመሰጡና ፍርሃትም ያደረባቸው ስለመሰላቸው

መዳም ማግልዋር ታሪካቸውን በኩራት ይቀጥላሉ:: «አዎን አባታችን፤ እውነት ነው:: ዛሬ ማታ ከተማ ውስጥ አንድ ነገር ይሆናል፡፡ ከተማው ሁሉ ይህንኑ ነው የሚያወራው:: መድምዋዜል ባፕቲስታን ደግሞ እንደምትለው...» በማለት ሴትዬዋ ንግግርዋን ስትቀጥል «እኔ» በማለት የጳጳሱ እህት ጣልቃ ገብተው «ያልኩት ነገር የለም» ይላሉ፡፡

ተቃውሞውን እንዳልሰሙ መስለው መዳም ማግልዋር ልፍለፋቸውን ቀጠሉ፡፡

«የዚህ ቤት ደህንነት ይህን ያህል አስተማማኝ አይደለም:: አባታችን
ቢፈቅዱልኝ ሄጄ ቁልፍ ለሚሠሩት ሰወዬ የድሮዎቹን መቀርቀሪያዎች
መልሰው እንዲገጥሟቸው ልንገራቸው:: መቀርቀሪያዎቹ ስላሉ በደቂቃ ይሰርዋቸዋል፡፡ ለዛሬ ማታ ብቻ እንኳን ባይሆን ለወደፊቱም ጥሩ ነው፤
በራችን ጠንካራ መቀርቀሪያ ይግባለት:: በቀላሉ የሚከፈት በር እጅግ አደገኛና አስፈሪ ነው:: አባታችን እንደሆነ ይቅርታ ቢደረግልኝ እኩለ ሌሊት
እንኳን ቢሆን ቤት ለእንግዳ፤ ይግቡ የማለት ልምድ አለብዎት:: ግን መቼም ለዚህ ፈቃድ መጠየቅ እንኳን አስፈላጊ» ሴትዮዋ አሳባቸውን ሳያጠቃልሉ በር በኃይል ይንኳኳል፡፡ «ይግቡ» አሉ ጳጳሱ፡፡

በሩ ተከፈተ:: ኣንድ ሰው ሰዎቹ ከነበሩበት ክፍል ውስጥ ገባ፡፡
ያ የምናውቀው ማደሪያ ፍለጋ ከቤት ቤት ፤ ከሥፍራ ሥፍራ
ይንከራተት የነበረው መንገደኛ ነበር፡፡ ሰውዬው በሩን መልሶ ሳይዘጋ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራምዶ ቆም አለ፡፡ ስልቻውን በጀርባው ተሽክሞ ዱላውን
በእጁ እንደያዘ ነው:: የእሳቱ ውጋጋን ከፊቱ ላይ ሲያርፍ ሻካራውና ድካም ያጎሳቆለው ፊቱ የጭካኔ ምልክት እንዳለበት አጉልቶታል፡፡ ሆኖም ያ ስሜት ወደ ውስጥ የተቀበረ እንጂ በግልጽ የወጣ ኣልነበረም:: የመናፍስት
በአካል መታየት ነበር የሚመስለው::

ማዳም ማግልዋር ለመጮህ እንኳን አቅም አልነበራቸውም፡፡ እንደቆሙ እየተንቀጠቀጡ አፋቸውን ከፍተው ቀሩ፡፡
መድምዋዜል ባፕቲስታን ዞር ሲሉ ሰውዬው ወደ ውስጥ ሲገባ አዩ፡፡
በፍርሃት ተውጠው ከመቀመጫቸው ብድግ አሉ፡፡ ከዚያም ዝግ ብለው ወደሚነድደው እሳት ዞረው ወንድማቸውን ተመለከቱ፡፡ ፊታቸውን ሲያዞሩ ትንሽ መንፈሳቸው ተረጋጋ፡፡

ጳጳሱ ሰውዬውን በጥሞና ተመለከቱት:: ምን እንደሚፈልግ ሊጠይቁት አፋቸውን እንደከፈቱ ለመናገር እድል ሳይሰጣቸው የያዘውን ዱላ በሁለት
እጁ በመመርኮዝ ከዚያ የነበሩትን ሰዎች አንድ በአንድ ከቃኘ በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ መናገር ጀመረ::

«ተመልከቱኝ! ስሜ ዣን ቫልዣ ይባላል፡፡ የተፈረደብኝ ወንጀለኛ
👍27
#ገረገራ


#ክፍል_ሁለት


#በታደለ_አያሌው

..ማን ቢሆኑ ነዉ? ምን አገባቸዉ?
ዞር ብዬ በቁጣ ላጠናግራቸዉ አሰብሁና፣ መልሼ ተዉሁት፡፡
ካለኝ ልምድ ግን ማንነታቸዉን መገመት እችላላሁ፤ የጠላት ወገን ጆሮ ጠቢዎች ናቸው። ቢሆንም ግን ዓላማቸው አልገለጥልሽ ብሎኛል። ይኼን ጉዳይ እንዲሁ እያውጠነጠንሁ፣ እመዋ የላከችኝንም ከቤቷ አድረሼላት
ታላቁን ቤተ መንግሥት አለፍሁት። ከዚያም በታላቁ የማኅበራችን ሕንጻ ምድር ቤት በሚገኘው መኪና ማቆሚያ ደርሼ መኪናዬን አቆምሁና፣ ሰዓቴን ስመለከት መንገዱ ስድስት ደቂቃዎች ብቻ ፈጅቶብኛል። ሰባት
ኪሎ ሜትር፣ ያውም እናቴ የላከችኝን ጭምር ወደ ቤት አድርሼ፣ ያዉም በአዲስ አበባ መንገድ በስድስት ደቂቃ ብቻ? (እንኳንም እመዋ አላየችኝ
ብዬ አማትቤ፣ የቀረችኝን አንድ ደቂቃ አብቃቅቼ ወደ ዋናዉ የሲራክ፤ ማዕከል ለመግባት ተጣደፍሁ፡፡

ወደ ዐሥራ ስምንተኛው ፎቅ የሚያደርሰኝ አሳንሰር ውስጥ ጥልቅ አልሁ። አሁን ወደ ላይኛው የመጨረሻ ወለል እያቀናሁ ቢሆንም፣ የሲራክ ፯ ዋና ማዕከል የሚገኘው ግን በተቃራኒዉ ከምድር ቤቱ የመኪና
ማቆሚያም በታች ተሠውሮ ነው፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ፣ በቤተ ክርስቲያን ፊት በይፋ የሚታውቁለት የማኅበሩ ብዙ አገልግሎቶች የሚከናወኑት በዚሁ ሕንጻ ሲሆን፣ በምድር ቤት ካለው ሰፊ የመኪና ማቆሚያ እስከ ላይኛው የመጨረሻ ወለል ድረስ የሚገኙ ቢሮዎች ሁሉ፣
ለእነዚሁ አገልግሎቶች በግላጭ የተደለደሉ ናቸው። ለምሳሌ ‹ጥናትና ምርምር የሚባለው አንድ ማዕከል ብቻውን ኹለት ሙሉ ወለሎች ይዟል። ሌሎቹም እንደዚሁ። እያንዳንዷ ቢሮ ደግሞ የራሷ ስም እና ቁጥር ተሰጥቷታል፡፡

የሲራክ፮ን ህልውና ይቅርና፣ ከነጭራሹ ከሕንጻው ምድር በታች ሌሎች ወለሎች እንዳሉ የሚያውቁት እጅግ ጥቂት የራሱ የሲራክ ማዕከል አባላት እና ዋና ዋናዎቹ የማኅበሩ አመራሮች ብቻ ናቸዉ፡፡ ቀድሞ ነገር ለሕንጻዉ ንድፍ ያወጡለትም ሆነ ያሳነጹት በራሳቸዉ በአመራሮቹ
በጥብቅ ምስጢር የተመረጡ ባለሙያዎች ስለሆነ፣ ከእነሱ በቀር የሚያዉቀዉ የለም። እኔም የዚህን ጠመዝማዛ የምድር ቤት መግቢያ ዘልቀው እንዲገቡበትም ሆነ እንዲወጡበት ፈቃድ ካላቸው ጥቂቶች መካከል አንዷ በመሆኔ፣ ከምንም የሚበልጥ ዕድለኛነት መሆኑን አምናለሁ። በመሆኑም የዚህ ማዕከል ኃላፊ የሆነዉ ባልቻ፣ በአስቸኳይ እንድደርስ ወደ ጠራኝ ኮቴ አልባው የሲራክ፤ ማዕከል ለመግባት ወደ
ላይኛው ወለል ደርሼ ከአሳንሠሩ ወርጃለሁ። ከአሳንሠሩ ፊት ለፊት ትንሽ ከተራመድሁ በኋላ ወደ ግራ እጥፍ አልሁ። አሁንም ትንሽ እንደ ሄድሁ ከላይ “ ፲፰፻፴ ከታች ደግሞ “ምክረ ካህን” የሚል ቃል እንደ ነገሩ የተጻፈበት ክፍል ከፍቼ ገባሁ። ቢሮዋ መጻሕፍት በመደርደሪያዎች የታጨቁባት ክፍል ስትሆን፣ ሰዉስጥ በኩል ከበሯ አጠገብ ሁልጊዜም
ካባ የደረቡ አንድ ሽማግሌ ለይስሙላ ይቀመጡባታል። ምናልባትም ግራ የገባዉ ወይም ጥርጣሬ ያደረበት ባይተዋር ሰዉ ወደ ክፍሉ ሲያንኳኳ፣
በማያስጠረጥር ትሕትናቸዉ ከርፈድ ያደርጉና እንደሚሆን እንደሚሆን ሸንግለዉ የሚመልሱት እኒህ በሩ አጠገብ የሚቀመጡት ካህን መሳይ ባለ
ካባ ስዉዬ ናቸዉ፡፡

እጀታዉን በመያዜ ብቻ እኔ መሆኔን በአሻራዬ አውቆ የተከፈተልኝ የዚች ክፍል በር ልክ ወደ ውስጥ እንደ ዘለቅሁ በራሱ ተቆለፈ። በመቀጠል
ወደ ምዕራቡ ግድግዳ ተራመድሁና በመጻሕፍት መካከል እጄን ሰድጄ ግድግዳውን እንደ አዛኝ እናት ስደባብሰው፣ በነጭ ቀለም የደመቀዉ ልሙጥ ግድግዳ ስንጥቅ እየፈጠረ፣ እየሰረገ ሄደልኝ፡፡ ጨርሶ ጥልም ካለ በኋላ ወደ ጎን ተንሸራቶ ጠባብ በራፍ ወጣለት።

አቤት ለመጀመሪያ ጊዜ እዚህ የደረስሁ ጊዜ የተደነቅሁት፤
ወደ ዉስጠኛዉ ክፍል እንደ ዘለቅሁ፣ ይኸኛዉም በር እንደገና ወደ መጽሐፍ መደርደሪያነት ከተመለሰ በኋላ፣ ልክ እንደ መጀመሪያው ሁሉ በራሱ ተቆለፈ። ወደ ነበረበት ተመልሶ ከግድግዳዉ ጋር ለመመሳሰል
ቅጽበትም አልፈጀበት፡፡ ከዚያም ጠበብ ባለችዋ ኮሪደር ትንሽ እንደ
ተራመድሁ፣ በጨረር የታጠረ በር ላይ ደረስሁ። ዝግንትሉ የወጣ ቀይ ክር የሚመስል ኤሌክትሮናዊ ጨረር ከላይ እስከ ታች ተመሳቅሎበታል። ጨረሩ ካልጠፋ በቀር፣ በጭራሽ ማለፍ አይሞከርም። በፍጹም፡፡ ያለበዚያ
ጨረሩን ሊጥሰዉ የሞከረዉን ሁሉ አንጨርጭሮ ሕቅ የማድረግ ጭካኔ አለበት። ከፊት ለፊት ያለዉ ካሜራ ሲያየኝ ስለነበር፣ ለቅጽበት ያህል እንኳን ሳያስጠብቀኝ ጨረሩ ድርግም ብሎ ከሰመልኝ፡፡ ካሜራ መኖሩን ያወቅሁት የኋላ ኋላ ስለመኖሩ ከተነገረኝ በኋላ ነዉ እንጂ፣ በትክክል የት እንዳለ እንኳን ያኔ፣ አሁንም ድረስ አይታየኝም። ብቻ ይኼ እሱ
የሚያየኝ፣ እኔ ግን የማላየዉ ካሜራ አዉቆኝ ጨረሩን አከሰመልኝ፡፡ ከዚያም ወደ ቀኝ ታጥፌ ትንሽ እንደ ተራመድሁ፣ ባለ ኹለት ተከፋች በር አጠገብ ደረስሁ። እሱም ገና ስጠጋው ወለል ብሎ ተከፈተልኝ።
ይህንንም አልፌ አልደረስሁም ገና። ገና ወደ ታች የሚወስደኝ ሥሩ የዉስጥ ለዉስጥ አሳንሰር ይጠብቀኛል። ልክ ወደ አሳንሠሩ እንደ ገባሁ ወደ ታች ይዞኝ ተፈተለከ።

ከመኪናዬ ወርጄ፣ ከዚያ ደግሞ ያንን ሁሉ ተጠንቅቄ፣ እዚህ በምድር ቤት ከሚገኘው የሲራክ ፯ ማዕከል ለመድረስ ኹለት ደቂቃዎች ብቻ ፈጀብኝ።

ልክ እኔ እንደሆንሁት ሁሉ፣ ዕድል ብሎለት ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕከሉን የሚጎበኝ ሰው መደንገጡ አይቀርም። ምክንያቱም መግቢያው
የመንግሥተ ሰማያት፣ ውስጡ ደግሞ ከገጠር ዳስ የማይሻል አዳራሽ ይመስልበታል። የሚከናወንበትን ተአምር እስከሚያውቅ ድረስ የታላቁ
ማኅበር መረጃ ማዕከል፣ ሲራክ፤ ይቺ ናት በቃ?› ብሎ ቢያናንቅ
አልፈርድበትም፡፡ ከፊት ለፊት ከጠፍር አልጋ በማይለዩ መጠነኛ ወንበሮች ላይ ተቀምጠዉ በየኮምፒዉተሮቻቸዉ ላይ ያፈጠጡ ጥቂት ሰዎች
ይታያሉ። ግድግዳዉ ዙሪያዉን ከወገቡ በላይ ዝርግ መከሰቻ ኖሮት ከተለያዩ ሥፍራዎች በሥዉር በተጠመዱ ካሜራዎች የሚቀርጹትን ተንቀሳቃሽ ምስል ሁሉ በመቃን በመቃን ከፋፍሎ ከስቶታል። ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢዉን፣ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ውስጠ ገጹን፣ ብሔራዊ ቤተ መዘክር ውስጡን፣ የአክሱም ጽዮንን ቅጽረ ግቢ፣ የሌሎች ታላላቅ ገዳማትን እቃ ቤቶች፣ የማኅበሩ ጥቂት ቅርንጫፎች ዙሪያ ገባቸዉን
ያለብዥታ ያስመለክታሉ። በነዚህ ሁሉ ማን እንደሚወጣና ማን
እንደሚገባ ያለማቆራረጥ ኩልል አድርገው ያሳያሉ፡፡ ምንም እንኳን ሌላ መጠባበቂያ የመረጃ ማዕከል በሌላ ቦታ እንደሚኖረዉ ብገምትም፣አብዛኛው ከወኪሎች የተሰበሰበው መረጃ ሁሉ የሚተነተነው እና ትርጉም
የሚሰጠው ግን በዚችኛዋ ክፍል ነው፡፡ በውስጧ የተለያዩ ሚናዎች
የተሰጣቸው ሃያ ሦስት የማዕከሉ አባላት በለም አእምሯቸው ቁጭ ብድግ ይሉበታል። ወጣቶች ቢበዙበትም ጥቂት ጎልማሳዎች እና በዕድሜ ጠና ያሉ ሴቶችም አሉበት፡፡

ዕረፍት በቤቱ እምበዛም አትታወቅም፡፡

ሁልጊዜም ወደዚህ ክፍል ስገባ የሚሰማኝ ስሜት አሁንም ተሰማኝ። ወኔዬ ሞቀ። ኩራት ኩራት፣ ደስ ደስ አለኝ፡፡ ልቡናዬ እንደ መሙላት፣ ነፍሴ እንደ መርካት፣ ዓይኔ እንደ መብራት አለልኝ፡፡ በሐቅ ቤት እንዳለሁ
ተሰማኝ፡፡ ከቅኑዓን ጋር እንደ ሆንሁ ታወቀኝ፡፡ ከበጎዎች ወገን መሆኔ መጣብኝ። ሁሉም በየሥራው ተጠምዶ ልብ ያለኝ ባይኖርም፣ ጎንበስ ቀና
ብዬ ለሁሉም የፍቅር ሰላምታ እያቀረብሁ የማዕከላችን የሲራክ፤ ዋና ኃላፊ የሆነዉ ባልቻ ወደሚገኝበት ቀጣይ ክፍል ተራመድሁ።

“ልጅየዋ?” ሲል ተቀበለኝ፣
👍331
#ሳቤላ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

« እረ እባክህ ምንም አይደለም » አለ ጌትዮው ። « ማን አለ መሰለህ ?ከልጄና
ከማርሊንግ ከመጣችው ከሚሲስ ቬን በቀር ሌላ የለብንም።ሚሲስ ቬንል ወደ ግብዣው ይዛት ለመሔድ ነበር የመጣችው። እሷም ብትሆን ከውጭ ራት አለባት ሲሉ የሰማው መስሎኛል እንደተባለው ከሌለች እኛ ብቻችንን እንበላለን እስኪ እሱን ደወል ነካ አድርገው ሚስተር ካርላይል ፡ ይህ መከረኛ እግሬ እኮ አልንቀሳቀስ አለኝ " ደውል ተደወለ። አሽከር ገባ።

« እስኪ ሚሲዝ ቬን ከኛ ጋር ራት ትበላ እንደሆነ ጠይቅ ። »
« ከውጭ ነው የሚበሉት. ...ጌታዬ ። የሚሔዱበት ሰረገላ ከደጅ እየጠበቃቸው ነው።

« መልካም ......... ሚስተር ካርላይል ፡ እንግዲህ እኛው ብቻ ነን ያለን ! አለ የቤቱ ጌታ።

ራት በአንድ ሰዓት ቀረበ ። ዊልያም ቬን በተሽከርካሪ ወንበሩ ሆኖ ወደ ምግብ
ቤት እየተገፋ ሔደ ። ከእንግዳው ጋር በአንዱ በር ሲገቡ ከፊት ለፊታቸው በነበረው በር ደግሞ ሌላ ሰው ገባ ። ለሚስተር ካርላይል የታየው ሰው ይሁን መልእክ ተጠራጠረና ልብ ብሎ ተመለከተ።

በሠዓሊዎች ሐሳብ ከሚታየው በቀር እጅግ ጥቂቶች ብቻ የታደሉት ቁንጅና
ከምንለው የላቀ መልክ ያላት ልጅ ነበረች። ከጫፉ እንደ ቀለበት ጥቅልል ጥቅል ያለው ጥቁር ጸጉሯ ከአንገቷና ከግራ ቀኝ ትከሻዋ ላይ ወርዶ ተቆልሏል ከለስላሳ የልጅ ክንዶቿ ላይ የሉል ጌጥ አስራ ውድ የሆነ ነጭ የዳንቴል ሥራ ቀሚስ ለብሳ ከፊት ለፊታቸው ብቅ ስትልበት መልአክ ትሁን ሰው ለመለየት ተጠራጠረ።

« ልጄ ናት ሚስተር ካርላይል ። እመቤት ሳቤላ ቬን» ብሎ አስተዋወቀው ። ሁሉም ከምግቡ ገበታ ዙሪያ ተቀመጡ ። ዊልያም ቬን የተለመደ የክብር ቦታውን ያዘ ። ልጅቱና ሚስተር ካርላይል ፊት ለፊት ሆነው ቁጭ አሉ ።

ሚስተር ካርላያል ለሴት ልጅ መልክ እደነግጣለሁ ብሎ አያስብም ነበር ።
የዚያች ቆንጆ ልዩ ውበት ግን ጠቅላላ መንፈሱን ማረከው ። ራሱን መቈጣጠር
እስኪሳነው ድረስ አፈዘዘው ። ከሁሉ የበለጠ ያስደሰተው ደግሞ ቅርፆ መልካም ፊቷ ወይም ትከሻዋ ላይ የተኛው ጸጉሯ ወይም የጽጌረዳ አበባ የመሰሉት ለስላሳ ጉንጮቿ ሳይሆኑ የዐይኖቿ አገላለጥ ነበር ። ከዚያ በፊት ያን የመሰለ አጋጣሚ አይቶ ስለማያውቅ ዐይኖቹን ከገጿ ላይ ሊነቅል አልቻለም ።

"ሳቤላ.... ለብሰሻል' አይደለም? » አላት አባቷ ።

« አዎን.....አባባ ። ባልቴቷን ሚሲዝ ሌቪሰን ለሻይ ብዙ እንዳይጠብቁኝ ልሔድላቸው ነው ። እሳቸው ለራሳቸው ሻያቸውን በጊዜ መጠጣት ነው የሚፈልጉ። ቢያመሹ አይወዱም ። ሚሲስ ቬንም ከዚህ ስትነሣ ዐሥራ ሁለት
ሰዓት ዐልፎ ስለነበር ለራት ሳታስጠብቃቸው አትቀርም ። »

« ብዙ እንደማታመሺ ተስፋ አለኝ ሳቤላ » አለ አባቷ ።

« እንደ ሚሲዝ ቬን ሁኔታ ነዋ አባባ እሷ ካላመሸች አላመሽም ። »

"አየ እንግዲያውስ ማምሸትሽ አይቀርም መቼም በዚ በኛ ዘመን ቆነጃጂቱ ሌሊቱን ወደ ቀን እየለወጡት ነው ። ይኸ ደግሞ ለለጋው ዕድሜያቸው ደግ አይደለም ። አንተስ ምን ይመስልሃል ሚስተር ካርላይል ? »

ሚስተር ካርላይል ቀና ብሎ ወደ እሷ ተመለከተ። ጉንጮቿ በበለጠ ደምቀው በቀላሉ የማይጠወልጉ ጽጌ ረዳዎች መስለው ታዩት ።

ራት ተበልቶ እንዳበቃ አንዲት የቤት ሠራተኛ ከሱፍ የተሠራ መደረቢያ ይዛ
ገብታ ከወጣቲቱ እመቤት ትከሻ ላይ ጣል አደረገችላት ። ልጂቱም ወደ አባቷ ቀረብ ብላ «ደኅና አምሽ ......... አባባ » አለችው

"ደና አምሺ........ የኔ ዓለም » አላት ወደሱ ሳብ አድርጎ የሚያምረው ጉንጯን ሳመና « እስኪነጋ ድረስ ውጭ መቆየትሽን እንደማልፈልግ ለሚሲዝ ቪን ንገሪያት " አንቺ ለራስሽ ገና ልጅ ነሽ እስኪ መጥሪያውን ንካው ሚስተር ካርላይል ። ልጄን ከሠረገላው ድረስ መሸኘት እንኳን አቃተኝ። »

« የእርስዎ ፈቃድ ከሆነና እመቤት ሳቤላም ወጣት ሴቶች አስተናግዶ የማያ
ውቅ እንደኔ ያለ ሰው እንዲሽኛት ከተስማማች አሳፍሪያት ብመጣ ደስ ይለኛል »አለ ትንሽ እንደ መደናገጥ ብሎ መጥሪያውን እየደወለ ።

ዊልያም ቬን አመሰገነው ። ወጣቷ እመቤትም ፈገግታ አሳየችው ። ሚስተር
ካርላይልም መብራቱ በተንጣለለበት ደረጃ እየመራ ይዟት ወረደና ከሚያምረው ምቹ ሠረገላ ውስጥ ደግፎ አስገባት ። እጅዋን ዘርግታ ሰላምታ ሰጠችውና ሠረገላው መሽከርከር ሲጀምር ካርላይልም ወደ ዊልያም ቬን ተመልሶ ገባ ።

« ታድያስ ቆንጆ ልጅ አይደለችም : ሚስተር ካርላይል ? »

« ቁንጅና የሚለው ቃል ያንሳታል ። የሷን ያህል ቆንጆ አይቼ አላውቅም ። »

« ባለፈው ሳምንት ከአንድ ግብዣ ሔዳ ነበር ። ሕዝበ አዳም አዳራሹ ውስጥ
ሲያያት ጊዜ ልዩ ስሜት ተፈጥሮ ነበር አሉ እኔማ መቼም ይህ ክፉ ቁራኛ በሽታ
ኮድኩዶ ከቤት አዋለኝና ያንን እንኳን ለማየት ሳልታደል ቀረሁ ። ልጂቱ ልቧም
እንደ መልኳ ነው ፤ እንዲህ አትምሰልህ ፤ ጥሩ ሰው ናት ። »

አባትየው የተናገረው ፡ ልጁ በመሆኗ ለማስወደድ ብሎ ሳይሆን ከልቡ ነበር ።
ሳቤላ ፡ በአስታሳሰብና በትክለ ሰውነትዋ ብቻ ሳይሆን በደግነቷም መስል አልነበራትም ።

ታርማና ተመክራ ነው ያደገችው ። ከቤት ውጭ ምንም ነገር አይታ አታውቅም ። እንደ ዘመኑ ልጆች ቅብጥብጥና ቅንጦት ወዳድ ሳትሆን ፡ ረጋ ያለች ጨዋ ልጅ ነበረች ። እናቷ በሕይወት በነበረች ጊዜ አንዳንዴ ኢስት ሊን፡ አብዛኛው ጊዜ ግን ማውንት እስቨርን ነበር የምትቀመጥ ። ከእናቷ ሞት በኋላ ከአንዲት አስተማሪ ጋር ወደ ማውንት እስቨርን ጠቅላ ገባች ። አባትየው አንድ የሟላ ትንሽ ቤት ሰጥቶ ዐልፎ ዐልፎ ያያቸው ነበር ። ሳቤላ ዐይነ አፋርና በመጠኑም ስሜት ንቁ አደብ የገዛች፡ ለሁሉ አሳቢና ተጨናቂ ነበረች ። አባቷም በጣም ስለሚወዳት መከራ ላይ ወድቃ ከሚያያት እሱ ራሱ ቢገድላት ይመርጥ ነበር ።

የወይዘሮ ሳቤላ ቬን ሠረገላ ጉዞውን ቀጥሎ ከሚስዝ ሌቪሰን መኖሪያ ቤት
አወረዳት ። ሚስዝ ሌቪሰን ጠባይዋ ልዝብ' አንደበቷ ስትር ያለ ሰማኒያ ዓመት
የሚሆናት ባልቴት ነበረች ። ሚሲዝ ቬን እንደ ተፈራው ዘግይታ ደረሰች ባልቴቷ
ለራት ብዙ ስለጠበቀች ተበሳጭታ ኖሮ ፡ ኋላ ደግሞ ሳቤላም የሻይ ሰዓት እስኪያ
ልፍ ስትቆይባት ጊዜ በመናደድ ቆቧን እንጋድዳ ደፍታ ኩፍስ ብላ ተቀምጣ አገኘቻት እውነትም እንደዚህ የመሰለ አሠራር ለአረጋውያን ጤንነትም ሆነ ጠባይ አይስማማም ።

« አስጠበቅሁዎ መሰለኝ » አለች ሳቤላ ወደ ሚስዝ ሌቪሰን እየተጠጋች ,
« ከአባባ ጋር ራት የሚበላ አንድ እንግዳ ስለ ነበረ ነው ትንሽ የቆየሁት »

« ኻያ ኣምስት ደቂቃ አሳልፈሻል » አለች ባልቴቷ ቆጣ ብላ ።

«አሁን ሻይ እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ ።
ኤማ ......... ቶሎ እዘዥልኝ ። »ሚስዝ ቬን ደወለችና እንደ ታዘዘችው ተናገረች ። ይህች ወይዘሮ በመልክ በኩል እንደ ነገሩ ብትሆንም ተክለ ቁመናዋ ያማረ ፡ እና ዕቡይ ከቁመቷ መለስ ያለች የኻያ ስድስት ዓመት ቆንጆ ነበረች ። እናቷ የባልቴቷ የሚሲዝ ሌቪሰን ልጅ ነበረች ፣ ቀደም ብላ ሞታለች ። ሎርድ ( ጌታ)ዊልያም ሼን ወንድ ልጅ አልነበረውምና።ባገሩና በዘመኑ ሕግ መሠረት በወርስ ላገኘው የማወንት እስቨርንን ጉልት ማዕረግና ሀብት ሕጋዊ ወራሽ' የቅርብ ዘመዱ የሆነው ፣ ወንድ ልጅ የርሷ ባል ሬይሞንድ ቬን ብቻ ነበር ።
👍20