#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል
....ከቤተሰቦቼ ጋር የነበረኝ ግንኙነት እምብዛም ሳያፈነግጥና ሳይቀርብ፣
ሳይጥምና ሳይሆመጥጥ ቀጠለ የወዲያነሽ አንድ ዓመት ከመንፈቋ እንደ አንድ የደስታ ቀን ፈጥኖ ዐለፈ፡፡ አንድ ቀን እሑድ ከሰዓት በኋላ ከአንድ ጓደኛዬ
የተዋስኩትን መቅረፀ ትርዒት (ካሜራ ወይም ፎቶ ማንሻ ይዤ ወደ ዕጓላ
ማውታ ሄድኩ
ከዚያ ቀደም ሲል ከወሰድኩለት ልብሶች መካከል ጥሩዋን ልብስ አልብሽ አነሣሁትና እንዴት እንደሚደርሳት ቀደም ብዪ ጨርሼ ስለነበር በሳምንቱ እሑድ
የልጇን ፎቶ ይዤ በጉልላት መኪና ወህኒ ቤት ሄድኩ። እንደ ተለመደው !
፣አስጠራኋት፡፡ የአጥሩን አግዳሚ ዕንጨት ተደግፋ ጥቂት አወራራን ድንገት !ሳታስበው ፎቶግራፉን ከኪሴ መዥረጥ አደረግሁና «በይ እስኪ በቃሽ እዪና ጥገቢው፡ ነጋ ጠባ፣ ልጄ! ልጄ ስትይ!...» ብዬ በወታደሪቱ ኣስተላላፊነት
አቀበልኳት፡፡ የወረቀቱን ግራ ቀኝ ጠርዝ በሁለት እጆቿ ይዛ ትኩር ብላ
ተመለከተችው:: ፊቷ ላይ ስታሸበሽብ የቆየችው ኮስማና ፈገግታ ደብዛዋ ጠፋ።
ወዲያው ብርሃኗ በጥቅጥቅ ጭጋግ እንደ ፈዘዘ ጨረቃ ፈዘዘች። እንባዋ
በዐይኖቿ ዙሪያ ግጥም አለ፡፡ አቀረቀረች። በሰንበሌጥ ላይ እየተንኳላላች እንደምትወርድ ጠፈጠፍ እንባዋ ጉንጯን ሳይነካ ከትንሿ ወረቀት ላይ ተንጠባጠበ።
ከሩኅሩኅ የእናትነቷ ባሕሪ የመነጨ የፍቅር ኩልልታ ስለነበር ለመጪው
ጊዜ የሚቀመጥ የትዝታ ጥሪት አስቀመጥኩ፡፡ ደግማ ደጋግማ ሥዕሉን ሳመች።እምብዛም ነገሬ ሳትለኝና እህ! ብላ ሳታዳምጠኝ ተሰናብቻት ተመለስኩ።
ከሌላ ስድስት ወር በኋላ የወዲ ያነሽ ሁለት ዓመት ሞላት።
እሑድ ከሰዓት በኋላ ነበር፡፡ የዕለቱን ጋዜጣ እያነበብኩ እንግዳ መቀበያ
ክፍል ውስጥ ተቀምጬ ሳለሁ የውብነሽ አጠገቤ ተቀመጠች። የያዘችውን
የአማርኛ ሰዋሰው መጽሐፍ እንደተገለጠ አጭሯ ክብ ጠረጴዛ ላይ ዘረጋችው።
ዐይኔ ተወርውራ የጊዜ ተውሳከ ግሥ የሚለውን ርዕስ አየች። ለነገርና
ለወሬ ማነሣሻ ይሆነኝ ዘንድ «ይልቅስ የአኳኋንና የሁኔታን ተውሳከ ግሥ
አታጠኚም» ብዬ መጽሐፉ ውስጥ የማነበው ያለኝ ይመስል አገላብጬ
አስቀመጥኩት። «እኔ የጊዜ ተውሳከ ግሥ አልዘለቅ ብሎኛል። አንተ ደግሞ
ሌላውን ትለኛልሀ» አለችና እጄ ላይ የነበረውን ጋዜጣ ወስዳ የመጀመሪያን ገጽ አርእስቶች በለሆሳስ አነበበች፡፡
«ሥራ አለብሽ እንዴ የውቢ? ከሌለብሽ አንድ ቦታ ደረስ ብለን እንምጣ» ብዬ ጸጉሬን አሻሸሁት፡፡ ጋዜጣውን አጣጥፋ አስቀመጠችው:: «እሺ እንሂድ፡፡ ይህን ማታም ቢሆን ልፈጽመው እችላለሁ» ብላ ከንፈሯን በምላሷ እያራሰች።
«ምንም እንኳ ለጊዜው አሳዛኝ መስሎ እንደሚታይሽ ባውቅም የኋላ ኋላ
ግን ያስደስትሽ ይሆናል» ብዩ ኩራትን ለመግለጽ በሚያስችል ወፍራም ደርባባ
ድምፅ ተናገርኩ። ካንተ ጋር ከሆንኩ ምን ያሳዝነኛል? በመጨረሻ የሚያስደስተኝ
ነገር ሁሉ ደስ ይለኛል፡፡ እንሂድ ካልክ ልብሴን ልቀያይርና እንሂድ» ብላ ተነሣች፡፡ እንዲሁ ገባ እንዳለች ዘርፈጥ ብላ የተቀመጠችበት ቀሚሷ ከበስተኋላዋ
ልሙጥነቱ ጠፍቶ ወደ ልዩ ልዩ አቅጣጫ የተሰበጣጠረ ጭምድ መስመሮች
ሠርቷል። ልብሷን ለመቀያየር ወደ መኝታ ቤት ስትገባ እኔም ጸጉሬን ለማበጠር
ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡
የልብሴን መስተካከል በመስተዋት ከተመለከትኩ በኋላ ጸጉሬን በደረቁ
እበጥሬው ወጣሁ፡፡ ደረጃውን ወርጀ እንደ ጨረስኩ ደረሰችብኝ።
ምንም እንኳ ወዴት እንደምንሄድ ባታውቅም «የምንሔድበት ቦታ ብዙ
ሰዎች አለበት እንዴ?» ብላ ጠየቀችኝ፡፡ «ማንም የለም። የምንሄደው አንድ እሳዛኝ
ሰው ለማየት ነው» ብዬ አለባበስና አረማመዷን እያየሁ መንገድ ገባን፡፡ ደማም ወጣትነቷና እንስታዊ ውብ ቅርጺ ማራኪነት ሰጥቷታል፡፡ ፈገግ ስትል ፍልቅቅ የሚሉት ነጫጭ ውብ ጥርሶቿ ከደም ግባቷ ጋር የአተር አበባ አስመስለዋታል፡፡
እግረ መንገዳችንን ልዩ ልዩ የሚባሉ ነገሮች ገዛሁላት። ዐሥር ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በታክሲ ዕጓለ ማውታ ደረስን፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት
አስከትዩ በመሄዴ ያ ዘወትር ብቻዬን ስመላለስ የሚያየኝ ዘበኛ የውብነሽን
በማየቱ የመገረም ፈገግታ ታየበት።
አብዛኛውን ጊዜ ከቤቱ ታዛ አካባቢ ከብዙ ከልጆች ጋር ተቀምጦ ሲጫወት ከሩቁ የማውቀው በልብሱ ስለነበር ሜዳው መኻል ቆም እያልኩ የቢቶቹን የፊት ዙሪያ ተመለከትኩ፡፡ ብዙ ልጆች ጨዋታቸውንና ልፊያቸውን እየተዉ አዩን፡፡ ወደ መኝታ ክፍሉ ይዣት ገባሁ። እሱኑ ከሚያካክሉ ሁለት ልጆች ጋር ወለሉ ላይ ተቀምጦ እየተኮላተፈ ይጫወታል። ሁለቱ ልጆች መለስ ብለው ካዩን በኋላ ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡ የእኔ ልጅ ዐይኖች ግን እኔ ላይ
ተተከሉ፡፡ ጎንበስ ብዪ አነሣሁት፡፡
አባባና እማማ የሚባሉ ቃላት የማያውቀው፣ የወላጅ ፍቅር ያልቀመሰው
ልጄ እንደ ወፍ ዘራሽ የመስክ አበባ ያምራል። ለምን ወደ ዕጓለ ማውታ እንደ
መጣች ግራ የገባት የውብነሽ በመጠኑ ደንገጥ አለች፡፡ ወደ እርስዋ ዞሬ ትከሻዋን
ቸብ ካደረግሁዋት በኋላ እስኪ ይህን ልጅ ተመልከችው የውብነሽ ቆንጆ ልጅ
አይደለም እንዴ? ብዬ ጠየቅኋት። እ..ብላ ዝም አለች።
ሰውነቷ በጥርጣሬና በሐሳብ የተጠመደ መሰለ፡ ድንገት ከእንቅልፏ ነቅታ ባጋጣሚ ያየችው ይመስል ሁለት እጆቿን ዘርግታ «እውይ እማምዬ ማማሩ! ደስ ማለቱ?» ብላ ከእጁ ላይ ወስዳ ታቀፈችው፡፡
በፊቱ ላይ አንዳችም ሌላ ለውጥ ሳይታይና ፈገግታው ሳይቀንስ ዝርግፍ
ብሉ ወደ እርሷ በመሄዱ በጣም ደስ አለኝ፡፡ እንዲያውም እዚያች ጠባብ ደረቷ
ላይ ልጥቅ አለ፡፡ ነገር ግን ልጄን ለመጀመሪያ ጊዜ ያቺ የማፈቅራትና
የምንሰፈሰፍላት የወዲያዬ ሳትሆን እኅቴ አቅፋው በማየቴ በፋይዳ የለሽ ጥላቻ
ተናደድኩ፡፡ ጉንጮቹን ሳም ሳም ካደረገች በኋላ ፊቷን ወደ እኔ መለስ አድርጋ
<<የማን ልጅ ነው ?» ብላ በጓጓ ስሜት ጠየቀችኝ። የምናገረው እውነተኛና ርግጠኛ እንዲመስል ለመመለስ የማሰላሰያ ጊዜ አልወሰድኩም፡፡ «አንቺ የማታውቂው አንድ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ የዚህ ልጅ አባት ማለቴ ነው። ትዝ እይልሽም ይሆናል እንጂ እኛም ቤት አንድ ሁለት ቀን ያህል መጥቶ ነበር» ካልኩ በኋላ የነገሩን
ድምጥማጥ ይበልጥ ለማጥፋት «ነገር ግን ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት
በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሞቷል፡፡ ልጁ ግን ለጊዜው አሳዳጊ ዘመድ በማጣቱ
ይኸው እዚህ በምታይው ሁኔታ በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ልጅ አባት በጣም
ግሩም ሰው ስለ ነበር እሱን በማሰብና ለልጁ በማዘን ብቻ አልፎ አልፎ ብቅ
እያልኩ እጠይቀዋለሁ፡፡ ጉልላትም አንዳንድ ቀን እየመጣ ያየዋል» ብዬ ዋሸኋት፡፡ግንባሩን ሁለት ጊዜ ያህል ስማ ውብ ዐይኖቹን ባንጸባራቂ ሸጋ ዐይኖቿ ትኩር ብላ ተመለከተቻቸው::
«ምነው አንተም እንዲህ የሚያምርና የሚያስጐመዥ ልጅ በነበረህ» ብላ
እንደ ወይን እሽት የሚያስጐመዡትን ጉንጮቹን ሳመቻቸው:: ንግግሯ ለጊዜው
ረግቶና በርዶ የቆየውን የሕሊናዬን ባሕር በብስጭት ማዕበል አረሰው፡፡
“ምናልባት ሚስት ባገባ ማስቴን በርግዝናዋ ወራት ከቤት አታባርሯት
እንደሆነ ነዋ እንዲህ ያለ ልጅ ማግኘት የሚቻለው» ብዩ በሽሙጥ መለስኩላት።
ድንገተኛው የንግግሬ ይዘት ፊቷን አስቀጨመው:: ልጁን ከሰጠችኝ በኋላ
አንገቷን ስብራ አቀረቀረች። ከጥቂት ዝምታ በኋላ ከወለሉ ላይ ቃላት
እየለቃቀመች ትናገር ይመስል ወለሉን እያየች «ያ ያለፈው ሁሉ ሌላ ጉዳይ
ነው፡፡ የማይገናኙ ነገሮች አታገናኝ እኔን ምን አድርጊ ትለኛለህ? አንተ ከእኔ
የበለጠ ብልህ መሆንህን ዐውቃለሁ አባታችን ቢሰማ ኖሮ በአንተና በእርሱ
መካከል ትልቅ ጠብና ማለቂያ የሌለው

👍4❤1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ስድስት ወራት አለፉ። ጌትነት የስድስት ወር ደሞዙን በላ፡፡ በዚች አጭር ጊዜ ውስጥ ራሱን በብዙ ነገር ቀየረ። አዲስ ልብስም ገዛ፣ ዩኒቨርሲቲ በሶሻል ሳይንስ "አካውንቲንግ ዲፓርትመንት" ትምህርቱን
ጀመረ። በወር ከሚያገኘው ሁለት መቶ ብር ደመወዝ ላይ ለእናቱ ተቆራጭ አድርጎላት ለአባቱ የገባውን የአደራ ቃል ለማክበርና ትምህርቱን በሚገባ በመከታተል በመጀመሪያው ሰሚስተር ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ቻለ። በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ስም ዝርዝር በሚለጠፍበት ሠሌዳ ላይ የጌትነትን ማንነት ለማያውቁት ሁሉ አስተዋወቀ። "እንኳ” ደስ አላችሁ!!" በሚለው ማስታወቂያ ስር ስማቸው ከተዘረዘረው ጥቂት ተማሪዎች መካከል ጌትነት መኩሪያ ግንባር ቀደሙ
ሆነ፡፡ በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች "ኤ" በማገኘቱ ስሙ በግሬት ዲስቲንክሽን ሊስት ውስጥ ተካተተ፡፡ የክፍሉ ተማሪዎች “እሱ ማን ነው?" ብለው ውስጥ ለውስጥ ሲነጋገሩበት ከረሙ:: በኋላም እሱ አንገቱን የደፋው፣ እሱ ትህትና ያልጎደለው፣ እሱ ብቻውን ገብቶ ብቻውን የሚወጣው በመጨረሻ ወንበር ላይ የሚቀመጠው ያልጠበቁት ሰው ሆኖ
አገኙት፡፡ በአብዛኛዎቹ ዘንድ በአድናቆት መታየት ጀመረ። ከሁሉ የበለጠ ስለሱ ማንነት ለማወቅ የተጨነቀችው ግን አማረች ነበረች፡፡ አማረች በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ በሂሳብ ሠራተኛነት ተቀጥራ የምትሰራ በትምህርቱ ጎበዝ የሆነ ስው የምትወድ ቆንጆ ልጅ ናት። ያንን ከፍተኛ ፉክክር ያለበትን የዩኒቨርሲቲ ህይወት ለመምራት ተማሪ እርስ በርሱ
ይፈላለጋል፡፡ በተለይ ጎበዝ ተማሪ አድኖ ለመያዝ ሩጫው ብዙ ነው። ለዚህ ነበር ያንን አመርቂ ውጤት አምጥቶ ለአካውንቲንግ የመጀመሪያ አመት የዲግሪ ተማሪዎች ቁንጮ የሆነውን “እንኳ” ደስ አለህ” የተባለውን የክፍሏን ተማሪ ማንነት ለማወቅ የተጣደፈችው። ብዙ ጊዜ አልወሰደባትም። አወቀችው፡፡አማረች የቀይ ዳማ ናት። ሰውነቷ ሞላ ቁመትዋ ዘለግ ያለ ፀጉርዋ እንደ ስንዴ ነዶ ጀርባዋ ላይ ዘፍ ያለ እንደ ስሟ
መልኳ የሚያምር፡፡ የመጀመሪያው ትምህርት ክፍለ ጊዜ ደርሷል። የዛ
ሬውን 'ሌክቸር የሚስጠው መምህር ዘግይቶ ነበር፡፡ አማረች ሆን ብላ ያንን ጎበዝ ተማሪ፣ ያንን ቁመቱ ዘንከት ያለ የሚስብ ልጅ ልትተዋወቀው ፈለገች፡፡ በቀጥታ ሄደችና ከአጠገቡ ባለው ባዶ ወንበር ላይ ዐይኖቿ” ተከለች።ሌሎቹ ተማሪዎች ደብተሮቻቸውን ገልጠው መምህራቸውን በመጠባበቅ ላይ ነበሩ፡፡
"ሰው አለው?" በጣቷ ባዶውን ቦታ እየጠቆመች በፈገግታ ተጥለቅልቃ
ጠየቀችው፡፡ ቀና ብሎ አያት። ደነገጠ፡፡
"የለው...እ? አለው!" ከሩቁ የሚጠላት ልጅ. በአብዛኛው መልኳ ሸዋዬን
የምትመስለው ልጅ.. ቀድሞውኑ ሲያያት ያልወደዳት ልጅ የምትቀመጥበትን የፊት ወንበር ትታ እሱ አጠገብ ከኋላ ለመቀመጥ መፈለጓ ድንገተኛ ሆኖበት መልሱን ለመስጠት ተደነጋገረው፡፡ የልጁ ሁኔታ አማረችን ገረማት። ሰው የሌለበትን ወንበር አለበት በማለት አሳፈራት። ማንም
እንደዚህ አሳፍሯት አያውቅም፡፡ እየሳቀችና እየተገላመጠች ወደ ቀድሞ
ቦታዋ ሹክክ ብላ ተመለሰች። "እሽ" ብላ አፍራ ምልስ ስትል አሳዘነችውና ተፀፅቶ ራሱን ወቀሰ፡፡ ለምን ያንን ቦታ እንደፈለገችው ገርሞት በዐይኖቹ ተከተላት።
የትምህርቱ ክፍለ ጊዜ አብቅቶ መውጣት ሲጀምሩ አማረች ቀስ ብላ ጭለማውን ተገን አድርጋ የጌትነትን እንቅስቃሴ ትከታተል ነበር። የዩኒቨርሲቲውን ምድረ ግቢ እንደለቀቀ ግራ ቀኝ ሳይል ታክሲውን ይዞ በረረ፡፡ በሚቀጥለውም በወዲያኛው ቀንም ተከታተለችው። ብቻውን እየወጣ ታክሲውን ተሳፍሮ ይከንፋል። ባደረገችው ተደጋጋሚ ጥናት የሴትም ሆነ የወንድ ጓደኛ እንደሌለው አረጋገጠች። አማረች በምቾት ያደገች የሚያምር ተክለ ቁመና ያላት የጠበቃው የአቶ በልሁ ወዳጄነህ
የመጀመሪያ ልጅ ናት። ከሁሉ የበለጠ የሚስበው ውብ ተክለ ቁመናዋ ነው። አነስ አነስ ያሉት ሳቂታ ዐይኖቿ ጉርድ ያለው አፍንጫዋ ከትንሿ ክብ ፊቷ ጋር በህብረት ሲታዩ በትልቅ ሰውነት ላይ የተቀመጠ የህፃን ልጅ ፊት ያስመስላታል፡፡ አማረች ከቁንጅናዋ ይልቅ የደስ ደሷ ከሩቁ ይጣራል። ጉንጮቿ እንጆሪ ይመስላሉ፡፡ ጌትነት እንደዚያ ይጥላት እንጂ ብዙዎቹ ወንዶች ሲያይዋት ጉሮሯቸው እስከሚጮህ ድረስ ምራቃቸውን ይውጣሉ፡፡ አቤት በተለይ ሱሪ ለብሳ የመጣች ዕለት! በዐይኖቻቸው
ሱሪዋን አውልቀው ያንን የሚገላበጥ ዳሌዋን በምናብ እየቃኙ በስሜት
ከወንድነታቸው ጋር ሲታገሉ ይውላሉ። ያያት ወንድ ሁሉ ቢመኛትም አማረች ግን ቁጥብ ነበረች፡፡ በቀላሉ የምትገኝ
አወጣ የተባለ ወንድ ሎተሪ እንደወጣለት ተደርጎ የሚጋነንበት ሁኔታ ነበር፡፡ ሲበዛ ፈታኝ ሰው ነች። ይሄ ሁሉነትዋ ግን በጌትነት ዘንድ ዋጋ አጥቷል። ሰው መስላ አልታየችውም። በሸዋዬነት ውስጥ የበቀለች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ሲል ደምድሟል።ይቺ በመማሯ ሽዋዬ ደግሞ በማይምነቷ መካከል ያለ ልዩነት እንጂ በሴትነት ባህሪያቸው አንድ ናቸው ብሎ የራሱን ድምዳሜ ሰጥቷል። በመልክ በጣም ይቀራረባሉ። በሌላ ፀባያቸውም ያው ናቸው የሚል እምነት ነው ያደረበት፡፡ አማረች አብዛኛው የሀሳብ ክፍሏን ለጌትነት አሳልፋ ሰጠች። ወደ ክፍል ሲገባና ከክፍል ሲወጣ ደጋግማ በስውር ተከታተለችው። ብቸኛ መሆኑን ካረጋገጠች በኋላ "ምን ችግር ቢኖርበት ይሆን?" ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ቀርባ ልታነጋግረውና ስለማንነቱ በሰፊው ለማወቅ ተንስፈሰፈች። ናቅ ስላደረጋት ነው መስል ምን ሲደረግ? የሚል እልህ ተናነቃት። ሌሎች ለሷ ያላቸውን ግምት በሚገባ ታውቃለች። ታዲያ ጌትነት
የምን ትዕቢት ነው? በትምህርቱ ጎበዝ ስለሆነ? መልከ መልካም ስለሆነ?
እኛ ስላለችው? ወይስ ሰው መስዬ ስላልታየሁት? ራሷን በብዙ ጥያቄዎች ዙሪያ በጭንቀት እንድታሽከረክር አደረጋት። ልቧ ዋተተ። እሱ እሷን በሚሸሽበት፣ በሚጠላበት ልክ እሷ ደግሞ እሱን ለመተዋወቅ ልቧ
ሽፈተ።
✨ይቀጥላል✨

👍1
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....በማግስቱ ጠዋት ዘመድ ወዳጁን ሞት የነጠቀው፣ የቆሰለበትና ገና የሆነውን ነገር በውል ያላወቀ የዲላ ነዋሪ ሁሉ ማልዶ ተነሳ፡፡ ማልዶ ወደ
መናኸሪያ ተመመ። ማልዶ ጉዞ ጀመረ፡፡ የተሽከርካሪ ችግር አልገጠመውም። በዲላ ዙሪያ ባሉ መዳረሻዎች ይሰሩ የነበሩ በርካታ ተሸከርካሪዎች ሁሉ ለዕለቱ አስቸኳይ ጉዞ ተመድበዋል። መሄድ የፈለገ ሁሉ ተሳፍሯል፡፡ ሽኝቱ በለቅሶ የተደበላለቀ ነበር፡፡
በልሁም አንዱ ተጓዥ ነበርና በታፈሡ በሔዋንና በርዕድ እየየ እና ጩኸት ተሽኘ፡፡
ገዞው ከወትሮው ፍፁም የተለየ ነበር። ሁሉም ሀዘንተኛ በመሆኑ የተኳረፈ ይመስላል ፀጥ ረጭ ባለ ሁኔታ ይጓዛል፡፡ አብዛኛው ሰው ጋቢና ነጠላ እንዲሁም
ጥቋቁር ልብስ ለብሷል፡፡ የፍተሻ ኬላዎችም ረግበዋል። በየመኪናው ውስጥ ገባ
ብለው ወጣ ከማለት ውጪ ተጓዡን ከመኪና ላይ አስወርደው ሁሉን ነገር በመበርበር ያጠፉት ጊዜ አልነበረም፡፡ ሾፌሮችም የጫኑትን ሕዝብ የውስጥ ስሜት
ያውቁ ነበርና ለከሰል ግዢ የትም ቦታ አልቆመም፡፡ እየተከታተሉ እንዳንዴም እየተሽቀዳደሙ በመብረር እረፋዱ አራት ሠዓት ተኩል ላይ ከዚያ አደጋ የደረሰበት
ቦታ ደረሱ፤ ከዝዋይ ከተማ በስተደቡብ በአሥራ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፡፡
ያ ቦታ ለአየው ሁሉ ይሰቀጥጣል። ወጭ ወራጅ ሁሉ ከሚጓዝበት መኪና ላይ እየ'ወረደ ያለቅስበታል። የተጋጩት መኪኖች ራሳቸው እንደ ሰው ያሳዝናሉ፡፡
ከሞጆ ወደ ሻሸመኔ ስትበር የነበረችው ሊዮንቺን ለዓመታት ስትረገጥ የኖረች ጣሳ መስላ ተጨራምታለኝ፡፡ ሁሉም ወንበሮቿ ሜዳ ላይ እንደ ቆሉ ተበትነዋል። ከዲላ ወደ አዲስ አበባ ይሄድ የነበረው አውቶብስ ደግሞ ፊት ለፊቱ ተቦድሶ ከግራ በኩል ያለው ጎኑ እስከ ኋላ ድረስ ከውጭ ወደ ውስጥ ተጠርምሷል
ከሎንቺኗ በአጠቃላይ፣ እንዲሁም በአውቶቡሰ ግራ በአል ከተቀመጠ ተሳፋሪ መሀል ሰው
ይተርፋል ብሎ ለመገመት እጅግ ያስቸግራል።
መኪኖቹን ተወት አድርጎ የተጋጩበትን አካባቢ መሬት ሲያዩት ደግሞ የባሰ አንጀት ያላውሳል። የአደጋ ሰለባዎች ደም ቦይ ሰርቶ ተንኳሉበታል። ከፈረሱ
ጭንቅላቶች የተበተነ አንጎልን በያለበት ተረጭቶ ዝንቦች ሰፍረውበታል፡፡ የተለያየ
ቅርጽ' ቀለምና መጠን ያላቸው የወንዶችም የሴቶችም ጫማዎች ሚዳው ላይ ተበታትነዋል፡፡ ደም
የተጠረገባቸው ጨርቆችና ስስ ወረቀቶች በየቦታው ተበታትነዋል፡፡
በዚያ ላይ ያ የዲላ ተሳፋሪ ሁሉ ከቦታው ደርሶ ከየመኪናው
እየወረደ፤ እንባ ሲራጭበት ያ ቦታ የባሰውነ መዓት ወረደበት።
በልሁ ትናንት ጠዋት አስቻለውን ሲሸኝ የተቀመጠበትን ቦታ አይቷልና ከመኪና እንደ ወረደ በቀጥታ በፊት በር በኩል ወደ አውቶቡሱ ሮጠ፡፡ በዚያ ቦታ
ላይ ያየው ሁኔታ መሬት ላይ ካለው የባሰ ነው፤ ደም ተጋግርበታል። የሞተሩ ክዳን
ወደ ኋላ ተጨራምቶ ወደ ወንበሩ መደገፊያ በመጠጋቱ ከዚያ ውስጥ ሰው ከነነፍሱ ሊወጣ ይችላል ብሎ መገመት ያስቸግራል። በልሁ በሁለት እጆቹ ራሱን ይዞ በለቅሶ
ሲንሰቀሰቅ ከቆየ በኋላ ድንገት የአስቻለውን የአካል ቁራጭ የሚያገኝ መስሎት ጎንበስ ብሎ በተጨራመተው የሞተር ክዳን ሥር ሲመለከት የአስቻለውን የቀኝ
እግር ቢጫ ጫማ አያት።
ድምጹን ከፍ እድርጎ «ወየው ወየው ወየው ወየው..» ካለ በኋላ
በመኪናው በር በኩል አንገቱን መጣ አድርጎ ጎበዝ ጎበዝ ጎበዝ ድረሱልኝ ጎበዝ ድረሱልኝ!» ሲል ዕርዳታ ጩኸት አሰማ፡፡ በአካባባው የነበሩ ሰዎች ሰምተውት ኖሮ ጠጋ ጠጋ ብለው ምነው? ምነው?» ሲሉት በልሁ እያለቀሰ «የወንድሜ እግር
እዚህ ቀርቷል! ኑ አውጡልኝ! ቶሎ በሉልኝ!» አላቸው።
ሰዎቹ ወደመኪናው ውስጥ ገብተው በልሁ ወደ ጠቆማቸው ቦታ ጎንበስ እያሉ ሲያዩ፡ እውነትም ቢጫ ነገር ታያቸው። ያን የሞተር ክዳን እንደ ምንም ተረዳድተው ወደ ፊት ከመለሱ በኋላ ከመኪና ስፖንዳ ጋር ተጣብቃ የነበረችውን
ጫማ ፈልቀቁኝው በማውጣት ለበልሁ ሰጡት::
በልሁ ያቺን ቢጫ ጫማ ይዞ ከመኪናው ላይ ወረደና ጫማዋን ወደ ላይ ከፍ፡ አድርጎ ለሕዝብ እያሳየ «እዩት ወገኖቼ! እዩዋት የወንድሜን ጫማ! የሆነውን
ነገር በዚህ ገምቱ! ወንድሜ ሞቷል! ወንድሜ ሞቷል! ...» እያለ ይጮህ ጀመር።
አስቸለህኑን የማያውቅ ሁሉ የሆነውን ነገር እየገመተ እንባውን አፈሰስ፡፡
ወዲያው ደግሞ ጥቂት ሰዎች በስቲሽን ዋገን ቶዮታ መኪና አስከሬን ጭነው ከቦታው ደረሱ፤ የጠይሟ ልጃገረድ አስከሬን ኗሯል፡፡ ህዝቡ ሁሉ ግርር
ብሎ፤ ኸደ መኪናዋ ሲሮጥ
በልሁም አብሮ ተጠጋ። ሌላው ሰው ከኋላ ከተሳፈሩት ሰዎች ጋር ሲነጋገር በልሁ ግን የልጅቷን አባት ጋቢና ውስጥ ሆኖ ሲያለቅስ
አየውና ጠጋ ብሎ፡
“አቶ ዘመድኩን!» ሲል ጠራው እንባውን በጉንጩ ላይ እያፈሰስ፡፡
“እንዲህ ሆንኩልህ በልሁ! የድሃ ልጄን ጉድ ተሰራሁ! ስንት ሆኔ ያሳደኳትን የበኩር ልጁን ወይኔ ወይኔ በማለት እያለቀሰ ሀዘኑን ለበልሁ ገለፀ።
«አስክሪን የት አገኘህ?» ሲል ጠየቀው በልሁ አሁንም እያለቀሰ፡፡
ከናዝሪት ውስቢታል ነው የሰጡኝ በልሁ::
«ምናልባት የልጅህን አስከሬን ስታወጣ ልብ ያልከው ነገር ይኖር ይሆን?» ሲል በልሁ ጠየቀው። ዘመድኩን የበልሁ ፍላጎት ገብቶታል።
«ምኑ ይለያል ብለሀ በልሁ? የሬሳ መዓት ተከምሯል፡፡ በያ ላይ እንዳንዱ ምነም ምነም አያስታውቅ፣ ስውነቱ ሁሉ ፈራርሷል። ብታይ እኮ ጉድ ነው
የሚታየው::» አለው ፊቱን በመሀረብ ሞዥቅ አድርጎ እየጠረንገ።
በልሁ አንጀቱ ብጥስ ያለ መስለው፡፡ መቆም አቃተውና ከመኪናዋ ራቅ ብሎ ሜዳው ላይ ቁጭ አለ፡፡ ያቺን የእስቻለውን ጫማ ከፊቱ አስቀምጦ በእግሮች
መሀል እጎንብሶ እያየ ያለቅስ ጀመር፡፡
የጠይሟን ልጃገረድ እስከሬን የጫነችው መኪና ወደ ዲላ ጉዞ ስትጀምር ወደ ናዝሬት የሚሄዱ አዘንተኞችን የጫኑ መኪኖች ሾፌሮችም ወደየመኪናው እንዲገባና ጉዞው እንዲቀጥል ይለምኑ ጀመር። በዚያ ሰዓት ስለ
አደጋው ያጠኑ የነበሩ የትራፊክ ፖሊሶችም መንገድ በማስለቀቅ ሰበብ ሕዝቡ እንዲሳፈር ወደ መኪናው መግፋት ጀመሩ። በልሁንም ደጋግፈው በማንሳት ወደ መቀመጫው ወስደው አስቀመጡት፡፡
ጉዞው ተጀመረ። ማታ እራት በወጉ፣ ጠዋትም ቁርስ ያልበላ ሀዘንተኛ ሁሉ ዝዋይ ሲደርስ እህል ልቅመስ አላለም፡፡ ሾፌሮቹ እንኳ አልከጀሉም፡፡ ዝም ብለው አለፉ፡፡ መቂና አለም ጤና እንዲሁም ቆቃ ከተሞች ታለፉ፡፡ ህዝቡ ደግሞ
አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ አልቅሶ አልቅሶ ደክሞት ስለነበር ጉዞውም ፀጥ ረጭ ያለ ሆነ፡፡ በአብዛኛው የተሳፋሪ እምነት የናዝሬት ሃይለ ማርያም ማሞ ሆስፒታል የአስክሬን መልቀምያ ወይም የቁስለኛ መገኛ ነውና ሁኔታዎች መቀየር የጀመሩት
ሞጆ ከተማ ታልፋ ወደ ናዝሬት ማቆልቆል ሲጀምር ነው፡፡ በተለይ ከናዝሬት መዳረሻ የመጨረሻዋ ዳገት ላይ ሲደርስ ለጥ ባለ ሜዳ ላይ የተቆረቆረችውን የናዝሬት ከተማ ሲያይ ሁሉም ተሳፋሪ ያለቅስ ጀመር፡፡ ከተማ ውስጥ ሲገባ ደግሞ ጫጫታና ኡአታ። ሆስፒታሉ በር ላይ ሲደርስ ደግሞ አገር ቀለጠ፡፡
ሕዝቡ ከየመኪኖቹ ላይ እየተሽቀዳደመ በመውረድ እያለቀሰና እየጮኸ ከሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲገባ ወዴት አቅጣጫ መሄድ እንደነበረበት

👍5
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
“ሺሕ ዓመት ንገሥ።"
ምንትዋብ፣ አፄ በካፋ ወደ መሠሪ እንድትመጣ ሲልኩባት፣ ሕይወቷ
ዳግም ተለወጠ። ለጥቂት ቀናት መሠሪ ሱባዔ ገብተው ስለነበር
ጨርሰው ነው ብላ አስባለች። ከእናቷና ከአያቷ ጋር መሠሪ ስትደርስ፣የበካፋ ታማኝ እልፍኝ አስከልካዮች ቴዎድሮስ፣ ገላስዮስና ድንጉዜ ዐይኖቻቸው ደም መስለዋል። እጅ ነስተዋት ስትገባ መሠሪ ከብዶታል፤
ጨላልሟል። ከወትሮው ጠባብ ሆኖባታል።
አፄ በካፋ ከተኙበት ኣልጋ ራስጌ የነፍስ አባታቸው አባ ዐደራ
መስቀላቸውን ይዘው ቆመዋል። ኒቆላዎስ ከንጉሠ ነገሥቱ ግርጌ
አቀርቅሮ ቆሟል። ምንትዋብ ርምጃዋን ገታ አድርጋ ክፍሉንም
ሰዎቹንም ቃኘች።
ነገሩ አላምር አላት። መንፈሷ ተረበሸ። ሱባዔ ላይ የነበሩት ባሏ ምን እንደደረሰባቸው መገመት አቃታት። ወደ አልጋቸው መራመድ ፈልጋ እግሮቿ አልታዘዝ አሏት፤ ትንፋሽ አጠራት። ልቧ ደረቷን ሲደልቅ እንደ ማጥወልወል አላት። ሐውልት ይመስል ደርቃ ቀረች። ዐይኗ ኒቆላዎስን ኣልፎ ንጉሠ ነገሥቱ ላይ ሲያርፍ፣ ፊታቸው ተሸፍኗል።
ዕለቱ ማክሰኞ፣ ቀኑ መስከረም አስራ ስድስት ዓመተ ምህረቱ 1723 ነው። እኒያ ቅኔ የሚቀኙት፣ መንፈሳዊ መጻሕፍትን የሚፈትሹት፣ አደን የሚወዱት፣ ለሃገራቸው ፊደላት ጥብቅና ቆመው፣ “ፊደል አሳስቶ የጻፈ
እጁ ይቆረጣል” ብለው አዋጅ የጣሉት፣ ሥነ-ጥበብ እንዲዳብር፣ ቃላት እንዲበለፅጉ የጣሩት፣ በወባ ንዳድ ርደው እንደተራ ሰው ባላባት ቤት መደብ ላይ የተኙት፣ ላይ ታች እያሉ ያመጸውን ያስገበሩት፣ ያጠፋውን አይቀጡ ቅጣት የቀጡት፣ እንደ ቀደምት ነገሥታት የሃይማኖት ክርክር
ያከራከሩትና አሻራቸውን ለመተው የራሳቸውን ግንብ የገነቡት አፄ
በካፋ በነገሠ በዘጠኝ ዓመት ከዐራት ወራቸው፣ ምንትዋብን ባገቡ በሰባት ዓመታቸውና በተወለዱ በሰላሳ ሰባት ዓመታቸው ሕይወታቸው
አልፏል።
“ምንድርነው? ጃንሆይ ምን ሁነዋል?” አለች፣ ምንትዋብ፣ ድምጾ ይርበተበታል ።
ተጠጋቻቸውና ቡሉኮውን ከፊታቸው ላይ ገለጥ አደረገችው።አፍንጫቸው ጫፍ ላይ ደም አየች፤ መላ ሰውነቷ ራደ። ኒቆላዎስ ላይ አፈጠጠች።
“ድንገት ነው የሆነው። ባፍ ባፍንጫቸው ደም ፈሰሰ... ምንም ያህል አልቆዩ ዐረፉ” አላት።
ራሷን በሁለት እጆቿ ይዛ “ኡኡኡኡ...” አለች። እናቷና አያቷ
ፈጠን ብለው ግራና ቀኝ ደገፏት።
“ምነው ሳትነግሩኝ? ስለምንስ ከፋችሁብኝ?” እያለች ጮኸች።
መሬት ላይ ተንከባለለች።
ያን ጊዜ እናቷና አያቷ አብረዋት ጮሁ። እንደ እሷ መሬት
ላይ ተንከባለሉ። መሠሪ ጩኸት በጩኸት ሆነ። ዋይታ በረከተ።
ምንትዋብ ለያዥ አስቸገረች። እነግራዝማች ኒቆላዎስ ተጨነቁ፡
ለቅሶው እንዳይሰማ። የቤተመንግሥት ባለሟሎች እንኳን እንዲሰሙ አልተፈለገም።
ምንትዋብ የምትሆነው ጠፋት። ከቶውንም የደረሰውን ማመን
አቃታት። አጎንብሳ፣ “ወዮ እኔ! ይብላኝ ለኔ” እያለች እንባዋን አዘራች።ኒቆላዎስና አባ ዐደራ ግራና ቀኝ እጆቿን ይዘው እንድትቀመጥ ግድግዳ ተጠግቶ ወደ ተቀመጠ ወንበር ሊወስዷት ሞከሩ።
“ተዉኝ... ተዉኝ! ለባሌ ላልቅስ።
ተዉኝ!” እያለች እሪ አለች።
“እቴጌ ባክዎ ለቅሶዎ እንዳይሰማ” አሏት፣ አባ ዐደራ።
“ይሰማ ይሰማ! አገር ይስማ! እኔ አለባል ልዤ አላባት መቅረታችንን...አገር ይስማ... ወዮ እኔ...ወዮ ልዢ ።”
እነኒቆላዎስ እንደ ምንም አባብለው አስቀመጧት። አንዴ ንጉሠ ነገሥቱ የተኙበትን አልጋ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጣራውን ደግሞም ወለሉን እያየች እንባዋ ረገፈ። ሐዘኗ መሪር ሆነ። የደረሰባትን ድንገተኛ ሐዘን
ጫንቃዋ መቋቋም የሚችል አልመስል አላት። ዓለም አስፈሪ ቦታ ሆነችባት። ሕይወቷ ላይ የሐዘን ጥላ አጠላችበት። የመኖር ተስፋዋን ሸረሽረችው። ትናንት ማሾ እያበራች ፈለጓን የተከተለችው መሬትም
ድንገት ጨለመችባት።
አልጋ ባልጋ የመጣው የሕይወቷ መንገድ ፍጻሜው የተቃረበ
መሰላት።
እንደገና ጩኸት ጀመረች። እነኒቆላዎስ ተደናገጡ። የእሷም
ሆነ የእናቷና የአያቷ ጩኸት እንዳይሰማ ፈሩ፤ ለማባበል ሞከሩ፤ አልሆነላቸውም። ምንትዋብን ብዙ ኃላፊነት እንደሚጠብቃት ኒቆላዎስ
ለማስረዳት ቢሞክር አልሰማ አለችው።
“ባሌ ኸሞቱ ገዳም ገብቸ መመንኮስ አለብኝ” አለችው።
እንባዋ ደረቷ ላይ ይወርዳል። ያቺ ፀዳል የመሰለች ሴት ፊቷ ድንገት
ጨለማ ለብሷል። ከመቅጽበት ዕድሜዋ ላይ ዓመታት የተጨመሩ
መስለዋል። ከዐይኗም ከአፍንጫዋም የሚወርደው ፈሳሽ አልቃሻ ሕፃን ልጅ አስመስሏታል።
ኒቆላዎስና አባ ዐደራ ተረበሹ። እናቷና አያቷ ለቅሷቸውን አቋርጠው በድንጋጤ ተመለከቷት።
“አዎ... ኸዝኸ በኋላ ምን ዓለም አለኝ? እኔም እንደ ባለቤቴ መሬት
እስትገባ ዓለሜ ምናኔ ነው። እሳቸው ሙተው እኔ እንዴት ባለም
ኖራለሁ? ልዤን ይዤ ኸዳለሁ” እያለች ጮኸች።
ኒቆላዎስ፣ “የለም የለም፤ እኼማ አይሆንም” አላት፣ ተጠግቷት።
“ደሞስ ምናኔ ማን ያደርስሻል? የጃንሆይ ጠላቶች ወይም ወህኒ
አምባ ያሉ ደጋፊዎች ምንገድ ላይ ጠብቀው አንቺንም ልዥሽንም
ይገድሏችኋል። ባይገድሏችሁ ስንኳ መውጫና መውረጃ የሌለው ወህኒ አምባ ወስደው ያስሯችኋል። ገዳም ብትገቢም ጃንሆይ ቅባት ሃይማኖት
ተከታይ ነበሩ ተብለው ስለሚጠረጠሩ እዚያ ብዙ የተዋሕዶ መነኩሴ ጠላቶች አሏቸው፤ ይጣሉሻል” አላት።
እሷ ግን፣ “በቁስቋሟ ተዉኝ! ተዉኝ” እያለች እጆቿን እያርገበገበች ተማጸነቻቸው።
ያን ጊዜ አባ ዐደራ፣ “እቴጌ መቸም መቀበል እንጂ ምን ማረግ ይቻላል? ኸሞት ሚቀር የለ። አሁን እርስዎ እንደዝኸ ሲሆኑ ሳንዘጋጅ የጃንሆይ መሞት የተሰማ እንደሁ ሁከት ይነሳል። ወህኒ ያሉትም እግረ ሙቃቸውን ፈተው ይመጣሉ። ንጉሥ ሞተ ሲባል ሚሆነውን እናውቃለን። ባክዎ ይጠንክሩልን” እያሉ ተለማመኗት።
ዮልያናም፣ “የኔ ልዥ! ባክሽ ጠንክሪ። እንደዝህ መሆን ደግ ማዶል” እያሉ እንባዋን በነጠላቸው ጠራረጉላት፣ የራሳቸውን ለመግታት
እየታገሉ።
“ልጄ በጡቴ ይዤሻለሁ! በኢያሱ ይዠሻለሁ! በምትወጃት በቁስቋም ማርያም ይዠሻለሁ! በምትወጃቸው ባባትሽ አጥንት ይሻለሁ በርቺልኝ” እያሉ እንኰዬም ሙሾ እንደሚያወርዱ ሁሉ እጃቸውን ወደ ኋላ አድርገው እንባቸውን እያዘሩ ለመኗት።
እሷ ግን እንባዋን መግታት አቃታት፤ አልጽናና አለች።
ኒቆላዎስ አንዴ እንድታዳምጠው ለምኗት የንጉሠ ነገሥቱን ኑዛዜ
ቃል በቃል ነገራት።
“ምን እንደተሰማቸው አላወቅሁም ብቻ እኔን አስጠሩኝ። ኒቆላዎስ...
ዐደራ ምልህ ልዤን... አሉኝ፣ ድምጣቸው እየተቆራረጠ። ልዤን
ኢያሱን እንድታነግሥልኝ። ለነገሥታት ሚደረገውን ሥርዐት ሁሉ... ቅባዓ ንጉሡንም ዘውዱንም... አርገህ እንዲነግሥልኝ። እናቱ ምንትዋብ
ብልህ ናት ትርዳው፤ ኸጎኑ ትሁን። እሷ አገር መምራትና... ማስተዳደር
ትችላለች። አርቆ አስተዋይና እዝጊሃር የባረካት ሰው ናት። አገሬን... አገሬን ኸልዣችን ጋር ሁና፣ ተባህር እስተ ባህር ታስተዳድር። አገሬ.. ምንም ዓይነት በደል እንዳይፈጠምባት። እኔ የዠመርሁትን ሁሉ. አጠናክረሽ ቀጥይ፤ በዐጸደ ነፍስ ኹኜም አልለይሽም በልልኝ። ሁላችሁም ቃሌን ንገሩልኝ…. ዐደራ” ብለው አንቺን እንድንጠራላቸው
ሲጠይቁ፤ ደም ባፍ ባፍንጫቸው ያለማቋረጥ ወረደ። ግዝየም አላገኙ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች።”
ምንትዋብ፣ ተናግሮ ሲጨርስ ሳግ እየተናነቃት ጣሪያውን፣
ግድግዳውን፣ ወለሉን፣ ሁሉንም በየተራ ተመለከተች። እነሱ ምን
እያሰበች እንደሆነ መገመት አቃታቸው። አንዴ እርስ በእርስ እየተያዩ ሌላ ጊዜ እሷን እያዩ ከአፉ የሚወጣውን ለመስማት ተጠባበቁ።

👍11❤1
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
ጥሪ
የሳጥናኤል ኮከብ
የሴሰኝነት ጥሪ
ሲልቪ
እኔና ሲልቪ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ፓሪስ ተጓዝን። በሷ መሪነት
ከፓሪስ ጋር ይበልጥ ተዋወቅኩ። በሲልቪ አስተማሪነት ከቅናት ጋር
ይበልጥ ተዋወቅኩ፡፡ ራሴንም ይበልጥ አወቅኩ ፓሪስ በገባን በሁለት ቀናችን፣ እንደ ልማዷ አንድ ደስ የሚላት ጎረምሳ አየችና አጣድፋ ወደ ሆቴላችን ወሰደችኝ፡፡ መብራቱን አጠፋች፡፡ እንደ “ልማዷ በኔ ገላ ጎረምሳውን ተደሰተችበት፣
አቃሰተች፣ ነገሩ ሊያልቅ ሲል ጮኸች። ተኛን፡፡ ያን ጊዜ እኔም
እሷም አላወቅነውም እንጂ፣ ከኔ ጋር እንዲህ ስትሆንና ስታደርግ
የመጨረሻ ጊዜዋ ነበር ነቃሁ። ጭለማ ውስጥ ነኝ። ምን እንደቀሰቀሰኝ እንጃ:: ከጎኔ
ተንቀሳቀሰች፡፡ በእንቅልፍ ልቧ «“Non! Non! Non!" እያለች
እየተጨነቀች ተፈራገጠች። በጣም የሚያስፈራ ህልም መሆን
አለበት። እየቀሰቀስኳት
«አይዞሽ አይዞሽ፣ ከኔ ጋር ነሽ» አልኳት ራሷን እየደባበስኩ።
በሀይል እየተነፈሰች ተጠጋችኝና
«አንድ ነገር አስደነገጠኝ፡፡ መብራቱን አብራልኝ አለችኝ
አበራሁት። አይኔ ብርሀኑን ከለመደው በኋላ ታየችኝ፡፡ ጥቁር
ረዣዥም ፀጉሯ ጉንጭና አንገቷ ላይ ተጠምጥሟል፣ተለጣጥፏል። ግምባሯ ላይ ላቡ ያብለጨልጫል፡ ጠረግኩላት፣
ፀጉሯን ወደ ኋላዋ ሰበሰብኩሳት
ውሀ» አለችኝ፡፡ ራስጌ ካለው ጠርሙስ አጠጣሁዋት
«ደህና ነሽ?» ስላት፣ ሳቅ ብላ
«አጥፋው» አለችኝ። አጠፋሁት፣ አቀፍኳት
«ቅዠት ነበር፡፡ ኮሙኒስቶች የኢራንን ሻህ መንገድ ላይ
አግኝተውት በጩቤ ሲገድሉት አየሁ፡፡ በኋላ ግን ባህራም ሆነ።
«አይዞሽ ነቅተሻል፡ አይዞሽ» እያልኩ እጄን ጀርባዋ ላይ
ሳንሸራትት ትንሽ ከቆየሁ በኋላ
Tu es plutôt une mére Française qu' un sauvage Africain"
አለችኝ («ፈረንሳዊት እናት ነህ እንጂ አፍሪካዊ አረመኔ
አይደለህም ኮ») ሁለታችንም በሳቅ መንፈርፈር ጀመርን። ታድያ'ኮ ያን ያህል የሚያስቅ አልነበረም፤ ያን ጊዜ መሳቅ ስላስፈለገን ነው
እንጂ፡፡ እየተጠመጠመችብኝ፣ ደስታ ባፈነው ድምፅ
«መኖር እንዴት ጥሩ ነው!» አለችኝ
ካንቺ ጋር ሲሆኑማ!»
የኔ ካስትሮ፣ ይልቅ ካንተ ጋር ሲሆኑ ነው እንጂ፡፡»
እቅፍ አድርጌ ጉንጯን ሳምኳት። በጭለማው ላዬ ላይ ወጣች፡
እንደምትወደው ጀርባዋንና አንገቷን እያሻሸሁ
«ምን ይሰማሻል?» አልኳት
እንደምትወደኝ ይሰማኛል»
«አውቀሻል»
«የተለየ ስጦታህ ምን እንደሆነ ልንገርህ?»
«ምንድነው?»
«የሰላም
ተሰጥዎ ነው ያለህ፡፡ ካንተ ጋር ስሆን ሰላም ይሰማኛል። ካንተ ጋር ስሆን ፀፀትና ንስሀ አያስፈልገኝም፡፡»
«ፀፀትና ንስሀ?»
በተለወጠ ድምፅ
«ቅድም ስለበደልኩህ ገላህን ለጋራ ጥቅማችን ሳይሆን ለግል
ደስታዬ ስላዋልኩት»
ፀፀት ሊጀምራት እንደሆነ ገባኝ፡ አሳዘነችኝ
«የኔ ቆንጆ፡ ቂል አትሁኚ። አንቺ ገላሽን እንድደሰትበት
ትሰጪኝ የለ?» አልኳት
«አዎን»
«ታድያ እኔ ገላዬን እንድትደሰቺበት ብሰጥሽ ምናለበት?»
«ከዚያ ይለያላ»
«አስር ጊዜ ልዩ ይሁን። በናንተ አገር ፍቅር ማለት ምንድነው?
መስጠትና መቀበል አይደለም?»
«ነው»
«ታድያ ገላዬን ብሰጥሽና ተቀብለሽ ብትደሰቺበት ምን ፀፀት
ያስፈልገዋል? እኛ አገር መስጠት ማለት መስጠት ነው። ገላዬን
ከሰጠሁሽ የራስሽ ሆነ ማለት ነው፡፡ የራስሽ ከሆነ ደሞ የፈለግሽውን ልታረጊበት ትችያለሽ ማለት ነው።
«እንደሱ ሆኖ ነው እሚታይህ?»
«ነው እንጂ»
«እንዴት ጥሩ ነህ! እኔ ግን እንዴት መጥፎ ነኝ!»
እንዴት?
«ውሸታም ነኛ!»
«ውሸታም?»
«አዎን፡፡ ለምሳሌ፣ ያን ጊዜ ስትጠይቀኝ የሌላ ሰው ገላ
እያቀፍሽ በሰውየው ገላ ከኔ ጋር ተኝተሽ ታውቂያለሽ ወይ?”
አላልከኝም? እኔ ምን አልኩህ? »
«በጭራሽ አድርጌው አላውቅም አልሽኝ»
«አዎን። ግን ውሽቴን ነበር። ላንተ
መዋሸቴ በጣም ይቆጨኛል፡፡ ስለዚህ አሁን አንድ ውል እንግባ። አንተ ላለፈው ውሸቴ ይቅርታ አድርግልኝ። እኔ ደሞ ለወደፊቱ ሁልጊዜ እውነቱን እነግርሀለሁ፡፡»
«ስሚኝ የኔ ቆንጆ:: ለኔ ምንም ነገር መንገር የለብሽም፡፡»
“አውቃለሁ። ለዚህ ነው ልነግርህ የምፈልገው:: ከዚያም በላይ፣
አንተ ልትረዳኝ ትችል ይሆናል፡፡ እውነቱን ልንገርህ?»
«እሺ»
«አትጠላኝም?»
«በጭራሽ አልጠላሽም»
እሺ፡፡ ያኔ ታስታውሳለህ?»
የኔ ሻህራዝድ የኔ ቆንጆ፣ እንዴት ልረሳው እችላለሁ?»
“ተመስገንን ፍለጋ የምመጣ ይመስልህ ነበር፡፡ እኔ ግን አንተን
ለማግኘት ነበር የምመጣው፡፡ ሳይህ በጣም ደስ ትለኝ ነበር።
ካስትሮን ትመስለኝ ነበር። ስንቀልድ ስንስቅ ጥርስህን አፍህን ሳየው
አንቀህ እንድትስመኝ እመኝ ነበር፡፡ ታድያ አንተ እምቢ አልክ።
ስለዚህ ካንተ ስለይ፡ ተመስገን ጋ እሄድና አይኔን ጨፍኜ አንተን
እያሰብኩ አቅፈው ነበር፡፡»
«ያውቅ ነበር?»
«ምስኪን ተመስገን! እንዴት አርጎ ይወቅ?»
እንጃ፣ ነግረሽው ሊያውቅ ይችላል ምናልባት?»
«እንዲህ አይነት ነገር እንዴት ሊገባው ይችላል?»
»እሺ ቀጥዪ»
«ትጠላኛለህ»
«እንግዲህ ቂል አትሁኚ፡፡ በኔ የመጣ ስለምንም አለመግባባት
አትስጊ። ንገሪኝ፡፡»
«እንዴት አርጌ ልንገርህ?»
«እንደመጣልሽ»
ከነገርኩህ በኋላ ምን እንደሚመስልህ ትነግረኝ እንደሆን»
“Parole d'honneur?'' (የከበሬታ ቃልህን ሰጥተሃል?»)
“Parole d'honneur” («የከበሬታ ቃሌን ሰጥቻለሁ»)
«እሺ። እንዲህ ነው:: አየህ፣ ካንተ ጋር ግብረ ስጋ በጣም
ደስ ይለኛል። ደጋግሜ ነግሬሀለሁ፡፡ ያንተን ግማሽ እንኳ ያህል እኔን ማስደሰት የቻለበት የለም፡፡ ብቻ ምን ልበልህ፣ ታጠግበኛለህ፡፡ ግን
በሽታዬ ይመጣል። ሲመጣ ደሞ መከላከያ የለኝም። ገባህ?»
«ገና አልገባኝም
«እንዳልኩህ፤ ታጠግበኛለህ፡፡ ግን በሽታዬ ይመጣል፡፡ በጣም
ታምረኛለህ፣ በሀይል እመኝሀለሁ
«ታድያ አለሁልሽ አይደለም?»
“እንደሱ አይደለማ የምታምረኝ»
ልቤ መምታት እየጀመረ
“ታድያ እንዴት ነው?» አልኳት፣ ጐሮሮዬም መድረቅ ጀምሯል
በሀይል ታምረኛለህ፣ ምኞቱ ያንገበግበኛል። ግን ስትተኛኝ
በገዛ ገላህ እንዳይሆን ያስፈልጋል። የሌላ ወንድ ገላ ተውሰህ፣ በሱ ገላ አንተ እንድትተኛኝ ፈልጋለሁ። እንደዚህ ያማርከኝ ጊዜ፣ ካንተ
ተለይቼ መሄድ ይኖርብኛል።»
«ወዴት?» ጉሮሮዬ ጨርሶ ደርቋል
“አንተን ፍለጋ፣ ሌላ ወንድ ፍለጋ»
«ታገኚዋለሽ?»
«ምን ይመስልሀል?» ጉሮሮዋ ውስጥ ወፍራም ተንኮለኛ ሳቅ
ተሰማኝ ቅናት ማለት ይሄ ይሆን እንዴ? ታድያ ንዴቱና ብስጭቱ
የታለ? እኔን የሚሰማኝ ጥልቅ የሆነ እሳት የሆነ የሚያቃጥል
ቅንዝር! እንደ ዛሬም አንገብግቦኝ አያውቅ! ተለይታኝ ስትሄድ፣
ወፍራም ዳሌዋን እያወዛወዘች፣ ውብ ኣይኖቿን ክፍት ክድን
እያረገች፣ በፍትወተ ስጋ እስኪፈነዱ ብልታቸውን በሚያሳብጠው ፈገግታዋ የመረጠችውን እድለኛ ወንድ ስትጣራ ታየችኝ። ስጋዬ
አላስታግስ አላስችል አለኝ፣ እላዬ ላይ እንደተጋደመች በጥድፊያ
ገለበጥኳትና ጭኖቿን ፈልቅቄ ስገባ፣ በሙዚቃዊ ፈረንሳይኛዋ፣
በቅንዝር ድምፅዋ
“Ah. cheri, comme tu es sauvage! C'est delicieux"

👍20