አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

....የሎስ አንጀለስ ፖሊስ ዲፓርትመንት መርማሪ ፖሊሶች በሊዛ እና ትሬይ ግድያ ላይ የተገኘውን የዲ.ኤን.ኤ ውጤት ከሰሙ በኋላ ሁሉም አትኩሮታቸው የእነዚህ ግድያ ምርመራዎች ላይ ሆኗል። ምክንያቱም ገዳዬ ወሬ ዞምቢ ነው'
የሚለው ወሬ በመሰራጨቱ የምርመራውን መጨረሻ ለማወቅ ጓጉተዋል።

“ይሄውላችሁ ያለምንም መረጃ ዶክተሯ ላይ ኃጢአቱን መደፍደፋችሁ ትክክል ያልሆነበትን ምክንያት አንድ በአንድ ላስቀምጥላችሁ።

ሀ፦ ኒኪ ሮበርትስ ሁለቱንም ግድያዎችን ለመፈፀም የሚያስችላት አንድም ተጨባጭ ምክንያት የላትም፡፡

ለ፦ የእሷ ቁመት አምስት ጫማ ከሶስት ኢንቺ ሲሆን ክብደቷም ከመቶ ፓውንድ ያነሰ ነው። ትሬይ ሬሞንድ ደግሞ 6 ጫማ ከሁለት ኢንች ሲሆን ክብደቱም 186 ፓውንድ ነው። ሰውነቱም በፈረጠሙ ጡንቻዎች የተገነባ ነው። እና ይህቺ ሴት ናት እሱን በጉልበት ጥላው በጩቤ ወጋግታ የምትገድለው ብላችሁ ነው የምትሞግቱኝ?”

“ምናልባት በወቅቱ የሚያግዛት ሰው አብሯት ነበር::” ብሎ ጆንሰን በመቀጠልም “ምናልባትም ግድያውን ሊያግዛት የሚችል አንድ ሰው
ቀጥራም ሊሆን ይችላል።”

“ያ! ምናልባትም አንጀሊና ጆሊ በድንገት መጥታ እራት ልትጋብዝህም ይሆናል እኮ” ብላ ሀና ባይኔስ ተረበችው እና ቢራዋን እየጨለጠች “ሰው ቀጥራ የሚለው ሀሳብህ በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ ሊያስኬድ ቢችልም በተግባር ግን
የሚሆን አይደለም።” ብላ ስትናገር ፖሊሶቹ በሙሉ ከት ብለው ሳቁበት።
“ሉው ትክክል ነው፡፡ ጆንሰን ይህቺን ሴት ማስረጃ ሳይኖርህ ወንጀለኛ ናት ብለህ ማሰብህ ትክክል አይደለም፡፡” ብላም አና ተናገረችው። ጆንስንም ፍንጥር ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ እና አና ላይ ጣቱን ቀስሮ

“አሁን ላይ ማስረጃ የለኝም፡፡ በቅርቡ ግን ይኖረኛል፡፡ እሷ ነጭ ውሸት ነው እየዋሸች ያለችው፡፡ ስለዚህ ሁላችሁም ገደል መግባት ትችላላችሁ።
ብሎ ከባሩ እየተመናጨቀ ወጣ፡፡

“በእየሱስ ሥም ይሄ ሰውዬ ምን ሆኗል?” ብላ ጉድማንን ጠየቀችው።

“ከእናንተ ጋር የቆየ ወዳጅነት አላችሁ አይደል። እናንተ ለምን ስለእሱ የምታውቁት ነገር ካላችሁ አትነግሩኝም? ሚክ ዶ/ር ሮበርትስን ይሄን ያህል
ለምን አምርሮ እንደሚጠላት ግልፅ ሊሆንልኝ አልቻለም።” አለው ጉድማን፡፡
“ምናልባት እንደዚህ ቢሆንስ?” አላቸው ፓድሬ ሳንቼዝ፡፡

ሳንቼዝ እንደባልደረባው ባይኔስ ለፍላፊ ሳይሆን ብዙ የማያወራ ሰው ነው። ብዙውን ጊዜ አስተያየት መስጠት አይወድም፡፡ አንድ አስተያየት
ሲሰጥም የሚሰጠው አስተያየት ጠብ አይልም፡፡

“ይህቺ ዶክተር ሮበርትስ በየጊዜው የባለሙያ ምስክርነትን እድትሰጥ
ፍርድ ቤቶች ውስጥ ትጠራ ነበር” አላቸው፡፡

“የሳይካትሪክ ምዘናን ትሰጥ ነበር ማለት ነው?” ብሎ ጉድማን ጠየቀ፡፡
“አዎን በተለይ ከአደንዛዥ እፅ ጋር በተያያዘ ሙያዊ ምስክርነትን ትሰጥ
ነበር። እሷ እና ባለቤቷ በአደንዛዥ ዕፅ ለተጎዱ ሰዎች የስነ ልቦና ህክምናን
የሚሰጡ ነበሩ።” አላቸው፡፡

“ሚክ የቀድሞ የአደንዛዥ ዕፅ መርማሪ ነበር ማለት ነው' ብሎ ጉድማን አሰበ “እና በጆንሰን ላይ የተቃዋሚ የባለ ሙያ ምስክር ሆና ቀርባለች ማለት ነው?” ብሎ ሳንቼዝ ጠየቃቸው።

“እኔ ይህን አላውቅም። ለምን ራሱን ጆንሰንን አትጠይቁም? ብቻ ሴትየዋ ለፖሊስ ሀይል ጥሩ አመለካከት እንደሌላት እርግጠኛ ሆኜ ልናገር
እችላለሁ፡፡ እሱ ደግሞ ያው ምን ያህል ቂም ቋጥሮ እንደሚቆይ ታውቃለህ?” ብሎ መለሰለት፡፡

የሳንቼዝን መልስ ከሰማ በኋላ ጉድማን ሃያ ዶላር ባንኮኒው ላይ አስቀምጦ እየሮጠ ወደ ውጭ ወጣ። ሳንቼዝ ከነገረው ነገር ተነስቶም አንድ
ሀሳብ ስለመጣለት ነበር ወደ ውጭ መውጣቱ።

“ሚክ!” ብሎ ጮሆ ተጣራ፡፡
ጆንሰንም ጥሪውን ሰምቶ ዞር አለ። በስልክ የጠራውን የሁበር መኪና
እየጠበቀ ነበር ጉድማን ያገኘው፡፡
ጉድማን ጆንሰን አጠገብ እንደደረስ በቀጥታ ወደ አሰበው ጉዳይ በመግባት “ዶክተር ሮበርትስ በግድያው ውስጥ አለችበት እንበል” አለው

“አለችበት ብቻ? እርግጠኛ ነኝ እንዲያውም።” አለው ጆንሰን በስካር
ምላሱ እየተሳሰረበት፡፡

“ግን አንተ ባልከው መንገድ ሳይሆን እሷ ራሷ ላይ ግድያው ሊፈፀምባት
ታስቦ ቢሆንስ?” አለው ጉድማን፡፡
ጆንሰንም አይኑን እያጉረጠረጠ “ይህንን ነገር ተነጋግረንበት የጨረስን
መሰለኝ በድጋሚ እንድናወራበት አልፈልግም” አለው፡፡

“ሊዛ ፍላንገን የዶክተር ሮበርትስን ረዥም የዝናብ ጃኬት ለብሳ ነበር ያን ምሽት የዶክተሯ ክሊኒክ ቢሮ ከሚገኝበት ህንፃ የወጣችው።”

“እሷ እንደነገረችን ከሆነ ነዋ” ብሎ ጆንሰን እየተንተባተበ መለሰለት እና
በማስከተልም “ይሄውልህ ስለ ጃኬቱ ስትነግረን እኔም ልክ እንደ አንተ
በወቅቱ ተደስቼ ነበር፡፡ ግን ጃኬቱን ልናገኘው አልቻልንም። ስለዚህ ስለ
ጃኬቱ ያለን መረጃ የዚያች ዶክተር ቃል ብቻ ነው።” አለው፡፡

“ግን እሷ እንደዚያ ባለ ነገር ላይ ለምን ትዋሰናለች? እስቲ አስብ” ብሎ
ጉድማን ሞገተው። ጆንሰን ጉድማን የጠየቀው ጥያቄ ትክክል ቢሆንም በውስጡ አጉረመረመ። ጉድማንም ባልደረባው ጆንሰንን ለማሳመን “ጭለማ ነበርበዚያ ላይ ያን ምሽት እየዘነበ ነበር። ከዶክተር ሮበርትስ ቢሮ ስትወጣም
የዶክተሯን የዝናብ ጃኬት ለብሳ ነበር፡፡ የሁለቱም ቁመት እኩል ነው። የፀጉር ስታይላቸውም አንድ አይነት ነው። ስለዚህ ገዳዩ ከኋላ በኩል የቀረባት ከሆነ...”
“እሺ እሺ ገባኝ” አለው ጆንሰን፡፡

“ይሄ ሊሆን አይችልም ትላለህ?” ብሎ ጉድማን ጆንሰንን ይበልጥ ለማሳመን ድምፁን ጠንከር አድርጎ ጠየቀው::
“ልክ ብልሃል ሊሆን ይችላል። ግን ትሬይ ሬይሞንድስ? ከላይ ሊዛ ላይ ያነሳኸው አመክንዮ እሱ ላይ አይሰራም አይደል? የእሱ ቁመት 6 ጫማ ከሁለት ኢንች ነው፡፡ መልኩ ደግሞ ልክ አንተ እንዳደረግከው ባርኔጣ ጥቁር ነው::” አለው፡፡

“ምናልባት ትሬይ የተገደለው ለኒኪ የቅርብ ሰው ስለሆነ ይሆናል” አለ
እና ጉድማን በመቀጠልም “ዶክተር ኒኪ በአደንዛዥ ዕፅ ዙሪያ ላይ በሚካሄዱ
ችሎቶች ላይ የባለሙያ ምስክርነት ትሰጥ አልነበር? ምናልባት
የመሰከረችባቸው ሰዎች እሷን እና ባለቤቷን በጠላትነት እንዲያይዋት
ሊያደርጋቸው ያስችላቸዋል፡፡”
ይህንን የሰማው ጆንሰንም አይኑን አጥብቦ ጉድማንን እየተመለከተው
“እ የባለሙያ ምስክርነትን በየፍርድ ቤቱ ችሎቶች ላይ ትሰጥ እንደነበር ማን ነው የነገረህ?” ብሎ ጉድማንን ጠየቀው፡፡

“እንዴ እንደዚህ አይነት ነገሮችንማ ካላወቅኩኝ ምኑን መርማሪ ሆንኩት?” ብሎ መረጃውን ከሳንቼዝ እንዳገኘ ሳይነግረው ቀረ እና በመቀጠልም
“ምናልባትም በእሷ የምስክርነት ቃል የተፈረደበት የአደንዛዥ ዕፅ አቅራቢ የዶክተር ኒኪን ጃኬት ለብሳ የነበረችውን ሊዛን ዶክተሯ ናት ብሎ ስላስበ በስህተት ገደላት፡፡ ምናልባትም ደግሞ ትሬይ ገዳዩ ማን እንደሆነ ደርሶበት ሊሆን ስለሚችልም ይሆናል እሱም ቢሆን የተገደለው”

ጆንሰንም የማሽሟጠጥ ሳቁን ለቀቀው እና “እና ትሬይ መርማሪ ነው በለኛ?”

“ተው አትድረቅ ሚክ ሀሳቤ ትክክል አይመስልህም?”

ጆንሰንም ዶክተር ኒኪን እንደ አጥቂ እንጂ እንደ ተጠቂ ማየት እንዲጀምር የሚያስገድደውን ሀሳብ ስለቀረበለት ባይወጣለትም ለመረታት ቻለ።

“በዚህ ጉዳይ ላይ ሁላችንም ምንም ነገር አለመደባበቅ እንችላለን?” ብሎ
ጠየቀው፡፡

“እሺ” ግን ግልፅነታችን በሁለታችንም በኩል መሆን አለበት” አለው ጆንሰን፡፡

“ማለት?”

“ማለትም ዶክተር ሮበትስ ከግድያው በስተጀርባ እንዳልሆነች የሚያሳይ
ምንም አይነት ማስረጃ
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

....«እኔ በበኩሌ ብዙ ጊዜ ነግሬሃለሁ። እናትህም ብትሆን ዘወትር እንደ ለመነችህ ነው:: የተማረ ሰው ጥቅምና ጉዳቱን ለይቶ ማወት ያቅተዋል ብዬ አላስብም፡፡ ርግጥ ነው፡ ዐዋቂም ቢሆን መካሪና ነጋሪ ያስፈልገዋል። ግን ሁልጊዜ የሚመከርና የሚነገር ጤነኛ ሰው አይደለም፡፡ በከንቱ ከምታማስነን ይልቅ ዐይንህን የጣልክባትና የወደድካት የጨዋ ልጅ ካለች ንገረኝ። አለበለዚያም እኔ
የምመርጥልህንና ደኅና ሰው ቤት ገብቼ የማመጣልህን ተቀበል፡፡ እኔማ ካነገርኩህ
ይኸው ሁለት ዓመት ዐለፈ፡፡ ምነው የወንድሞችህንና የእኀቶችህን ልብ ቢሰጥ ብሎ መልሴን ለመስማት ትክ ብሎ አየኝ፡፡

«አየህ አባዬ በማለት በተለመደች አጠሪሬ ንግግሬን ጀመርኩ።
“ማንኛውም ሰው የሚያገባው ራሱን ለማስደሰትና ኑሮውን ለመመሥረት እንጂ
ሌላውን ደስ ለማሰኘት አይደለም፡፡ አንተ የምትመርጥልኝን አልቀበልም ለማለት
ሳይሆን ላንተ የምትስማማህና ደስ የምትልህ ለእኔ ደስ አትለኝም ይሆናል።
"ማንኛውም ሰው እለማወት ወይ ድንቁርና ከተገቢዉ በላይ ብዙ እንዲያደንቅና በጠባብ አስተሳሰብ እንዲሠራ በስውርና በግልጽ ሊያስገድዱት ይችላሉ፡፡ እኔ በመጠኑም ቢሆን ከጠባብ አስተሳሰብ ተላቅቄአለሁ። በአጭሩ እንድታውቅልኝና እንድትገነዘብልኝ የምፈልገው ግን ለመግባባት የሚችል ሕሊና እንጂ ከቀን ወደ ቀን የሚለወጥ ሰብአዊ ውበት ብቻውን ጋብቻን ጽኑና ተፈላጊ መሠረት ሊሰጠው አይችልም» ብዬ ረዘም ባለው አነጋገሬ የምን ይለኝ ጅራፍ እየለመጠጠኝ
በመናገር አይኖቼን ወደ ወለሉ ተክዩ ዝም እልኩ፡፡

«ኤድያ! ኤድያ! ደርሶ መንዘባነን ደስ አይለኝ! የዘንድሮ ወጣቶች ሐሳብና መልስ በየቤቱ ይኸው ሆኗል፡፡ ቁም ነገር የሚሠራ ሰው ብዘ አያወራም፡፡ ጋብቻ የጎበዝና የደፋር ሙያ እንጂ ለሰነፍና ለፈሪ የሚታደግ የጠበል ፃዲቅ
ድርሻ አይደለም፡፡ አስተዋይ ልቦና ያለው እንዳቅሙ ይዘላል፡፡ ያለ መቸኮልህስ
ይሁን በጄ! የአቦ ዕለት ሲሉህ የመድኃኔ ዓለም ዕለት ማለት ግን በዛ፡፡ ዛሬን
እንደ ዛሬ ኑረህ ነገን እንደ ነገ መኖርና ነገን መስለህ መገኘት ቁርጥ ዓላማህና
ፍላጎትህ መሆን አለበት፡፡ ዝምታህ እምቢታ መሆኑን ዐውቃለሁ» ብሎ ከጉዳዩ ጋር የተያያዘውንና ያልተያያዘውን ሁሉ ተናግሮ ቆጣ አለ፡፡ ከጊዜያዊ ቁጣው
በኋላ ዝምታ እንዳይጀምር በማሰብ “ምናልባት በሰው ልጅ እኩልነት የምታምን ከሆነ ለምን የትልቅ ሰው ልጅ፡ አጥንተ ጥሩ፣ ባለክብር፣ ባለ ዝና እያልክ
ታማርጣለህ? » ብዬ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅንጣት ድፍረት የተቀላቀለባትን ጥያቄ
ሆዴ በፍርሃት እየተናጠ አቀረብኩኝ።

«አድሮ ጥጃ አለ ያገሬ ሰው ብዙ ጊዜ ነግሬሃለሁ፡ ለምን ነጋ ጠባ
ትጠይቀኛለህ? በማለት ንግግሩን ሲጀምር በቁጣ ትክ ብሎ
የማይሆነውንና የማይገባውን ሁሉ አትመኝ"ሐለሙ ሕልመ ወአልቦ ዘረከቡ"
ተብሏል፡፡ ማንም ሰው ቢሆን የኑሮ ደረጃውን መጠበቅና መመልከት አለበት።
እኔ እባትህ ከትልልቅና ካዋቂ ሰዎች ጋር የምውል ነኝ። አንተም እንደ እኔ
መሆን ይገባሃል።

ዝናና ክብር ቀላል ነገር አይምሰልህ፡፡ ከሜዳ ላይ አይታፈስም። የዘመኑ
ሰዎች ለጤና ያድርግላችሁ እንጂ “አለ "አብልሑ ልሳኖሙ ከመ አርዌ ምድር»
እንዳለው ሆናችኋል። የምታመጣት ልጅ ከጨዋ ቤተሰብ የተወለደች፣ ዘርና
ትውልዷ የታወቀና የጠራ መሆን አለበት። ወይራ ከወይራ ነው፡ ስንዴ ከጓያ
አይቀየጥም፡፡ «ከመልኮስኮስ መመንኮስ» ሲባል አልሰማህም እንዴ? «የማንንም ስድ አደግና ቅሬ ከየትም ለቅመህ ዝናና ክብሬን ብታጠፋት አደባባይ አውጥተሀ የገደልከኝ ያህል እቆጥረዋለሁ፡፡ የደሃ ቀርቀቦ ቢንከባለል ከደሃ ደጅ” ምኞትህ ሁሉ ልክስክስ አይሁን» ብሎ ቁጭቱን ለመግለጽ ያህል ራሱን ነቀነቀ።

ያቺ በስንትና ስንት ጊዜ ውስጥ የምታጋጥመኝ ጭቅጭቅ አይሏት
ውይይት አብዛኛውን ጊዜ ፍፃሜዋ አያምርም። የእኔና የእርሱ ሐሳብ በተቃራኒ አቅጣጫ ስለሚጓዝ ከመከራከርና ከመጨነቅ ይልቅ ሰምቼ መለየትን እመርጣለሁ።

«ማንንና እንዴት ለማግባት እንደምፈልግ ለመግለጽ እስከምችል ድረስ
የመዘጋጃ ጊዜ ቢሰጠኝና ከራሴ ጋር ብመክር ጥሩ ነው:: እኔ ግን ከአንዳንድ
ሁኔታዎች በስተቀር ማንኛውም ሰው በተፈጥሮ ዐይን ሲታይና ሲመዘን እኩል
ነው” በሚለው አምናለሁ» ብዬ እምነቴን ገለጽኩ፡፡ ለመነሣት ሲመቻች ጋብቻን
እንደ አንድ ትልቅ ጦርነት የምትፈራው መስለህ ታይተኸኛል። ጋብቻ ማለት
ሌላ ነገር አይምሰልህ፡ ከአንዲት ከምትወዳት ሴት ጋር ለመኖር የምታደርገው የኑሮ ውል ነው፡፡ ከሆነችህ አብረሃት መኖር፡ እንዲያ ሆነም ምን ውጣ ወረድ አለው፡ ደህና ዋይ ብሉ ማሰናበት ነው:: ከዛሬ ጀምሮ ግን አግባ አታግባ እያልኩ አልነታረክም፡፡ አስቦና የሚሻውን ወስኖ ለማደር ከቻለ አቅመ አዳም ከደረሰ ሰው ጋር ስለ ራሱ ጉዳይ መከራከር ከንቱ ድካም ነው::

«አንተማ በልብህ ግን እንደኔ ማለትህ አይቀርም፣ ንገሩኝ ባይ!»

“ከትንሽ ጅረት ውስጥ የምትንሳፈፍ ቅጠል ከትልቁ ኩሬ ውስጥ ስትገባ
ቁጫጭ አህላ ትታያለች፡፡ ዐወቅሁ ብለህ ሙተሃል፡፡ የሰው ልጅ ክፉ ጠላቱ ደግሞ
በውስጡ የታጎረው ሽካራ ሐሳቡ ነው:: ካንጀቴ ነው:: ራስን ለማረምና ለማሻሻልም እኮ ከሌሎች ሰዎች ስሕተት መማርና መረዳት ካስተዋይነታቸውም መልካም መልካሙን መቅሰም ማለፊያ ዘዴ ነው» ብሎ ፈንጠር ብላ በጸጥታ ነጠላ ወደምትቋጨው እናቴ አሻግሮ አየ። ምንም እንኳ ላቀረበው ሐሳብ ተነጻጻሪና የተሻለ መልስ ቢኖረኝም
እያደር የሚንር ቁጣውን በመፍራት ደጓን ዝምታ ቀጠልኩ።

የተጨማደደውን ግንባሩን እየጠራረገ ከተነሣ በኋላ ሐሳቤን በጠቅላላ
የሚቃወም መሆኑን ለማስረዳት ወለሉን በቀኝ እግሩ ጠፍ ጠፍ እደረገው፡፡
«የሚታየው እኮ እንዴትና የት ማደግህ ብቻ አይደለም፡ ከማን መወለድህም ጭምር እንጂ። መልካም አዝመራ የሚገኘው እንደ ገበሬውና እንደ
መሬቱ ብቻ ሳይሆን እንደ ዘሩም ነው» ብሎ በቀጥታ ወደ መኝታ ቤቱ ሔደ::

ወደ ውስጥ ሰምጣ የነበረችው ለስላሳ መቀመጫ ትንሽ በትንሽ በመሙላት ቅርጿ ተስተካከለ።

«እስኪ አሁን በኪዳነ ምሕረትና በእሑድ ምድር ባትጨቃጨቁ ምን ቸገረሀ ልጄ? ነጋ ጠባ ይነግርሃል፤ እርሱ አይደክመው፣ አንተ አይሰለችህ! መጥኔ እቴ! ወዴት አባቴ ልግባላችሁ ይሆን? በዚያ ላይ ደግሞ ስንተዜ ልንገርህ? ሲሆን
ሲሆን አንተና እኔ ምንና ምን? አንተ በትምርትህም ቢሆን አታጣውም፡ አሁን
በዚህ በአንተ ምልልስ የተነሣ ያ ሰበበኛ የደም ብዛቱ ቢነሣ አበሳው ለኛው ነው፡፡
እሞት አገር አድርሶ እንደሚመልሰው ታውቃለህ፡፡ ከሐኪሙ ቤት የሚያመጣውን አንድ ቁና ኪነን ታያለህ፡፡ እሱ በጦም በጸሉት እያለ ባይዘው ኖሮ ይኸነዩ ጥሪኝ አፈር ሆኖ ነበር። እሱ እንደሁ እሱ ነው: አንተ ግን ሲያመር ሲያመር ከፊቱ ገለል በልለት» በማለት ራቅ ብላ የተቀመጠችው እናቴ ምሬቷን ገለጸች፡፡

አሁንም እንደገና ከእናቴ ጋር የነገር ገበና ለመጫወት ባለመፈለጌ ሰምቼ
ዝም አልኩ። ዐልፎ በልፎ ከሚሰማው ከእናቴ የጉሮሮ ማስሊያ እህህታ በስተቀር
ቤቱ በዝምታ ታመቀ። በሐሳብ ዐውሎ ነፋስ ከወዲያ ወዲህ በመንገዋለል ላይ
እንዳለሁ ጉልላት ከቸች አለ።

እጆቹን ወደ ኋሳ አጥፍቶ እርስ እርሳቸው ካያያዘ በኋላ አንድ እግሩን ትንሽ ቀደም በማድረግ ጎንበስ ብሎ ለእናቴ ሰላምታ አቀረበ፡፡ እናቴ ስለ ጉልላት ስትናገር «እኔ ከሌላው ከሌላዉ ሁሉ የሚያስደስተኝ ትትናውን እጅ አነሳሡ ነው» ትላለች። ከጎኔ ተቀመጠ። ከእናቴ ጋር ልብ ለልብ ተገናኝቼ እንደማላወራ ስለሚያውቅ የጋሪ ወሬ ለመክፈት አልፈለገም፡፡
👍1
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....ሽመልስ በማግስቱ ለአብዱላሂ ስልክ ደወለለት አብዱላሂ ስልኩን አነሳና ጌትነት ያለመኖሩን በድጋሚ አረጋገጠለት። ሽመልስ ተጨነቀ።
“ምን አጋጥሞት ይሆን?" በሚል ሃሳብ ተዋጠ፡፡ ፈተናው የሚሰጠው ከአንድ ቀን በኋላ ነው። ባስመዘገበው ስልክ ተደውሎለት ባይገኝ ደግሞ

ለነአቶ አባይነህ ደስታቸው ነው፡፡ በጣም ተበሳጨ፡፡ ከምሳ ስዓት በኋላ ግን ጌትነት ስለ ሥራው ብቻ ሳይሆን ስለህልውናው ጭምር ጓዙን ጠቅልሎ የሱን ጊዜያዊ ርዳታ ሊጠይቅ ከተፍ አለ።

"እንግዳ ይፈልግሀል ይግባ?"አለች የሽመልስ ፀሐፊ ከውስጥ ስልክ፡፡
"አስገቢው" አላት። እንግዳው ወደ ውስጥ ሲዘልቅ ሽመልስ ዐይኑን ማመን አቃተው፡፡
“ኮንግራጁሌሽን!” አለና ጮኸ፡፡
ጌትነት ያልጠበቀው ዱብ ዕዳ ሆነበት። የሽመልስን ሁኔታ ሲያይ ከደስታው የተነሳ የሆነ ስሜት ስውነቱን ውርር አደረገው፡፡ ሽመልስ አይዞህ ከጎንህ ነኝ እንዳለው አድርጎት ይሆን? እንደመርበትበት እያደረገው የተዘረጋለትን እጅ በደመነፍስ ጨበጠ፡፡
"አረፍ በል እስቲ!"አለና ወንበር ጋበዘው። ጌትነት ከእንግዳ መቀመጫ ወንበሩ ላይ ሄዶ ተቀመጠና በሁለመናው አሰፍስፎ ሽመልስን በጉጉት ይጠባበቀው ጀመር፡፡ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ ሳይወስደው ስላደረ ፊቱ ላይ የመጎሳቆል ምልክት ይታይበታል፡፡

"ለመሆኑ የት ጠፍተህ ከረምክ? በተደጋጋሚ ስልክ ደውዬ ሳጣህ ተስፋ
ወደ መቁረጡ ተቃርቤ ነበር። ትግላችን መስመር እየያዘ የመጣ ይመስለኛል። አንተና ፀሀይ በድጋሚ ፈተና እንድትወስዱ መወሰኑን እና ለፈተናው እንድትዘጋጅ ልነግርህ ነበር የፈለኩህ፡ ከየባለስልጣኑና ከአንዳንድ ሰራተኞች ጋር የተናነቅኩት ለዚህ ነበር። የመጨረሻው ውጤት የሰመረ እንደሚሆን ደግሞ ምንም ጥርጥር የለኝም" ሳቅ አለ።
ጌትነት ከመቀመጫው ዘሎ አቅፎ ሊስመው ከጀለ፡፡ ተንበርክኮ እግሩ
ላይ ሊወድቅ ተመኘ፡፡ ፊቱ በደስታ እንደማሽላ ፈካ፡፡ ፍንድቅድቁ ወጣ፡፡ የእድል ገመዱ ስለለች እንጂ አለመበጠሷን አወቀ፡፡ እንደገና አዲስ
የተስፋ ብርሃን፣ አዲስ የህይወት ምዕራፍ እየሞተ ከሄደው ተስፋው ውስጥ ብቅ ሊል ሲያንስራራ ታወቀው:: ለሱ ለአንድ ምስኪን ተቆርቋሪ ሆኖ በሥራ ህይወቱ ውስጥ ሊጠቅሙትም ሆነ ሊጎዱት ከሚችሉ በርካታ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር ተናንቆ ለዚህ ስላበቃው ሽመልስን የሚያመስግንበት ቋንቋ አጠረው። ሽመልስ ከዚህ ወሳኝ ምዕራፍ
ላይ አድርሶታል፡፡ ፈረስ ያደርሳልንጂ ጦር ይዞ አይዋጋም፡፡ ከዚህ በኋላ የሱ ብርታት ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ይህንን የምስራች ከሰማ በኋላ ከአብዱላሂ ቤት መውጣቱንና ለጊዜው ጎኑን የሚያሳርፍበት ቦታ እንኳ እንደሌለው በፍርሃት ተውጦ ገለፀለት።

"አይዞህ ጌትነት አቅሜ በሚፈቅደው ሁሉ ልረዳህ ዝግጁ ነኝ ስለማደሪያህ ብዙም አትጨነቅ " በማለት ሞራል ሰጠው፡፡
"የናት አባቴ አምላክ" አለና በልቡ ፈጣሪውን አመሰገነ፡፡ ማምሻውን ተያይዘው ወደ ሽመልስ መኖሪያ ቤት ሄዱ።
ቤቷ ሶስት ክፍሎች ያሏት በንፅህና የተያዘች ናት፡፡ ሽመልስ ሶስት ጉልቻ
ሊመሰርት ቅድመ ሁኔታችን በማጠናቀቅ ላይ ያለ ሰው ነው፡፡ ከአስረኛ ክፍል ጀምሮ በጓደኝነት አብራው የቆየችው ኤልሳቤጥን ለማግባት የቤት ዕቃዎችን በሟሟላት ላይ ሲሆን ለጊዜው የሚኖረው በሠራተኛ ነው።
ጌትነት ነፃ ሆኖ ሰውነቱን ታጥቦ የታጠበ ልብስ ቀይሮ ጥሩ በልቶ ጥሩ ጠጥቶ ለፈተናው ሲዘጋጅ አደረ። እኩለ ለሊት ሲሆን የጠዋቱ ተፈታኝ ፈጣሪው በጣለለት ሲሳይ በሽመልስ ላይ ሀሳቡን ጣል አድርጎ በተስፋ የሰላም እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡

“ታዲያስ ጌትነት? አዳር ተመቸህ?" ሽመልስ ቀድሞት ተነስቶ ነበር፡፡

“እግዚአብሔር ይመስገን ጋሼ ሽመልስ፡፡ ነጋ እንዴ? የሶስት ቀን የእንቅልፍ ዕዳዬን ሳወራርድ ነው ያደርኩት። መንጋቱን እንኳ አላወቅኩም ነበር" ከአልጋው ውስጥ ለመውጣት ታገለ።
“እባክህ ይሄንን ጋሼ የምትለኝን ነገር ተወኝ። ሽመልስ እያልክ ጥራኝ።
እንደሱ ስትጠራኝ ነው ደስ የሚለኝ"
"ይሻላል ጋሼ ሽመልስ? መዳፈር አይሆንም? እንዴት ብዬ በአንድ ጊዜ?"

"ተውንጂ! አሁንምኮ ጋሼ እያልክ ነው!"
“እሺ…አንተኮ ወንድሜም ጓደኛዬም አባቴም ነህ። ለኔ ይሄንን ያክል የሚጨነቁልኝ አባቴና እናቴ ብቻ ነበሩ"
“ጌትነት አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ፡፡ እኔ የምታገለው፣ የምጨነቀው ላንተ ብቻ ሳይሆን ፀፀት ሰላሜን እንዳይነሳኝ ለራሴ ጭምር ነው።
በአንተ ላይ የደረሰው በደል በኔም ላይ በተመሳሳይ መልኩ ደርሶብኝ ነበረ፡፡ በነገሩ ይበልጥ እንድገፋበት ያደረገኝ አንዱ ምክንያት ያንን በራሴ ላይ ደርሶብኝ የነበረውን በደል የምዋጋበት አጋጣሚ ሆኖ ስላገኘሁት ነው። ከዩኒቨርሲቲ ተመርቄ ሥራ እንደጀመርኩ በሃላፊነት ላይ
የተቀመጡ ሰዎች ወጣት በመሆኔ ብቻ ለሥራ መደቡ ሊከፈል የሚገባው ደመወዝ እንዳይከፈለኝ ተጽዕኖ አድርገውብኝ ነበር። ሥራውን እንድሠራ ነገር ግን ደመወዙን እንዳላገኝ ሆን ብለው በፈጠሩት ተንኮል ሊጎዱኝ ሞከሩ፡፡ ምን ታደርገዋለህ? በብቃት ሳይሆን በዘመድ የተሾሙ በአድልዎና በጉቦ የነበዙ ከንቱዎች ከዚህ የተሻለ እንዲሰሩ
ቅም፡፡ ተምረህ ሲያዩ ደማቸው ይፈላል። ነገ ቦታዬን ይቀማኛል በሚል ስንኩል ፍርሀት ትንሽ ቀና ስትል በኩርኩም ይገጩሀል።ያሸማቅቁሀል፡፡ ደመወዝ የሚወስነው በሥራ ክብደትና በተሰጠህ ሀላፊነት እንጂ በሥጋህ ወይንም በዕድሜህ ክብደት አይደለም፡፡ አንዳንዶቹ ይሄንን አይገነዘቡትም። ወፍራምና ረጅም ከሆንክ ጥሩ ደመወዝ እንድታገኝ ወጣትና
አጭር ከሆንክ ደግሞ ዝቅተኛ ክፍያ እንዲከፈልህ እስከማድረግ የዘቀጠ
በክብደትና በቁመት ላይ የተመሰረተ የደመወዝ አከፋፈል ሥርአትን
ለመዘርጋት የሚጥሩ ከንቱዎች ናቸው፡፡ እኔም ከዩኒቨርስቲ ተመርቄ ስቀጠር የዚህ የጫጨና የቀጨጨ የድንክ አስተሳሰባቸው ሰለባ ሆኜ ነበር። ወጣት በመሆኔ ብቻ ተመሳሳይ ስራ እየሰራሁ ዝቅተኛ ደመወዝ እንዳገኝ ወስነውብኝ በብዙ ውጣ ውረድና በብዙ ክርክር ነበር መርታት የቻልኩት። ያንተም ጉዳይ ከዚህ የተለየ አይደለም። ወፍራም ጭንቅላት እያለህ እንጀራህን ወፍራም ዘመድ ላለው ሰው አሳልፈው እየሰጡት ነው።ይሄንን ሁኔታ በቸልታ ባልፈው ደግሞ ትናንትና የደረሰብኝን በደል መርሳት፣ እኔነቴን መካድ ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ ጥረቴ ላንተነትህ በሰጠሁት ግምት ብቻ ሳይሆን ለእኔነቴ ጭምር የከፈልኩት ዋጋ
በመሆኑ እንደ ውለታ አትቁጠረው፡፡ ጌትነት አንተም ይህንን ችግርና
ፈተና አልፈህ በድል ስትወጣ የዚህ ሁሉ ችግር ድምር ውጤት ሰው መሆንህን መርሳት የለብህም፡፡ ችግር የሰው ልጅ እንደ እርሳስ የሚቀረፅበት ትምህርት ቤት ነውና ከዚህ ችግር ልትማርበት ይገባል። የህይወትን ጣፋጭነት የበለጠ የምታጣጥመው ከፈተናዋ ውስጥ በድል አድራጊነት ስትወጣ ነውና ለቀሪው ህይወትህ ጥሩ ትምህርት ይሆንሀል። ስለ ሌሎች እንድታስብ ስለ እውነት እንድትከራከር ስንቅ ይሆንሃልና የኔን
ጥረት ብዙም አትጨነቅበት" አለው።

ጌትነት የሽመልስን ምክር አዳምጦ ቁም ነገሩን በልቡ ኣስቀረና አብረው ቁርስ ሊበሉ ተያይዘው ወጡ፡፡ ቁርሳቸውን አብረው ከበሉ በኋላ ሽመልስ
“መልካም ዕድል!" ብሎት ወደ መስሪያ ቤት ሲሄድ ጌትነት ደግሞ በስድስት ሰዓት ለሚሰጠው ፈተና ሲዘጋጅ አረፈደ።

የሰራተኞቹ ሹክሹክታ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ግማሹ ሽመልስን ያደንቃል፡፡ያመስግነዋል፡፡ገሚሱ"ምቀኛ!እርኩስ!”እያለ ይረግመዋል። አቶ
አባይነህም ይደነፋሉ፡፡ “እከካም የድሃ ልጅ ሁላ ትናንትና እከኩን አራግፈንለት ጥብቆ ሲቀይር ጊዜ ማንነቱን ረሳው ቁርስን በልቶ ምሳውን
👍6
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....አስቻለው የተሳፈረበት አንደኛ በራሪ አውቶብስ ከዲላ መውጫ ኬላ ጀምሮ በጩኮ፤ በአፖስቶ በአቢላ እና በአዋሳ ጥቁር ውሃ ፍተሻ ጣቢያዎች ላይ ፍዳውን
ጨርሶ ከሻሽመኔው ኬላ ላይ ከእረፋዱ አራት ሠዓት አካባቢ ደረሰ። የማይቀረው ዕዳ ሊከፈል ተጓዥ ሁሉ ከመኪና ላይ ወረደ:: ከአስቻለሁ አጠገብ በስተግራ በኩል የመስኮት ጥግ ይዘው ተቀምጠው የነበሩት ወይዘሮ ግን አልወረዱም፡፡

ፈታሾች ከመኪናው ዙሪያ እንደ ልማዳቸው ሲጎማለሉ በርካታ ደቂቃዎችን ከአሳለፉ በኋላ ሁለት ፈታሾች ከመኪናው ፊትና ኋላ በር በኩል ገብተው ለመበርበር
ተዘጋጁ ቀድሞ በፊት በር በኩል የነበረው ፈታሽ የመኪናውን በር መወጣጫ ረግጦ ጠልጠል ሲል እኒያ ሴትዮ መኪና ውስጥ ቁጭ ብለው አገኛቸው፡፡

ምንድነው?» ሲል ዓይኑን ፈጠጥ አድርጎ ጠየቃቸው። ፈታሹ አጠር
ጠየም ያለ ነው፡፡ የፊቱ ወዝ ያብረቀርቃል፡፡ ፊቱ ጠፍጠፍ ያለና አፍንጫው ደፍጠጥ ያለው ጎረምሳ ቢጤ ነው፡፡ የመለዮውን እጅጌ ሰቅስቆት የእጁ ጡንቻ ፍርጥም ብሎ ይታያል። ሰንሰስት የሚያህል የወርቅ ሐብል ደረቱ ላይ ተጋድሞ ይንቀለቀላል፡፡

የኔ ልጅ መውጣት መውረዱ ስልችት ብሎኛል ና እዚሁ ፈትሽ ጎሽ!» አሉት ሴትዮዋ በልመና ዓይነት ፈገግ ብለው ፈታሹን እየተመለከቱት፡፡
«ባክሽ ውረጅ! ምን ትቀልዳለች!" አለና ፈታሹ ቆጣ ብሎ በዓይኑም
ገርመም አደረጋቸው።
ሴትዮዋ ፈገግታቸው ድንገት እልም ብሎ ጠፋና ፊታቸው ኮስተርተር፣ ዓይናቸውም ፍጥጥ አለ። ተናደዱ: በተቀመጡበት ወንበር ላይ እንደ መቅበጥበጥ
እያሉ «እንቺ አትበለኝ አንተ ኧረ ይሄ ደፋር!» አሉት፡፡

«ኣ?» አለ ፈታሹ ወደ ወስጥ ገባ እያለ:: እንደገና «ምን አልሽ አንቺ?» ብሎ ቁልቁል ይመለከታቸው ጀመር፡፡አንቺ አትበለኝ አልኩህ!» አሉና ደሞ ምን ያፈጥብኛል?" ብለው
እሳቸውም አፈጠጡበት::

«ቆይ ምንድነሽ አንቺ?» አላቸው ድፍረታቸው ያልተለመደ ሆኖበት።
ሰው! አውሬ እመስላለሁ?» ፈታሹ ለአፍታ ያህል ፍጥጥ ብሎ ተመለከታቸውና ወደ ውጭ እየተመለከተ
«በቃ ይሄ መኪና ተገትሮ ይውላታል እንጂ ይቺ አሮጊት ሳትወርድ አይፈተሽም።»
ብሎ ከመኪናው ላይ ወረደ:: እንዳትገባ!» ሲል በኋላ በኩል ሊገባ የነበረውንም ፈታሽ ከለከለው።

ተሳፋሪው ሁኔታውን ይከታተል ነበርና ግራ የመጋባት ስሜት አደረበት፡፡ሊጉላሉ ነው:: ግማሹ ፈታሹን ይለምን ጀመር፡፡ ሌላው ደግሞ ከመኪና ሌይ እንዲወርዱ ሴትዮዋን፡፡ ሴትዮዋ ግን ፍንክች አልል አሉ። ይልቁንም በሚለምናቸው ተሳፋሪ ላይ ወረዱበት። «መድሐኒዓለም ይለመነኝ ንቅንቅ አልልም!» አሉና አዳሜ አትጨቅጭቀኝ ወዲያ ሄደህ የምትለምነውን ለምን መቼም አንዴ ወኔህን
ተሰልበህ! ልበ ሙት ሁላ ደሞ እኔንም ይዘኸኝ ሙታ!» አሉ ትንፋሻቸው በርክቶ አፍንጫቸው ነፋ ሞሽሽ፣ ነፋ ሞሽሽ እያለ::
በሁለቱም አቅጣጫ ልመና ያልተሳካለት ተሳፋሪ ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነበር፣ ወደ ኬላው ሃሳፊ በመሄድ የተፈጠረውን ሁኔታ ማስታወቅ። በእርግጥም በርካታ ተሳፋሪ ወደ ሃላፊው ቢሮ ተከታትሎ ሄደና አቤቱታውን ማቅረብ ጀመረ፡፡
በዚህ መሀል ግን ብዙ ጊዜ ባከነ፡፡
ከበርካታ ደቂቃዎች በኋላ የኪላው ሃሳፊ ሳይሆን የማይቀር አንድ ፖሊስ የመቶ አለቅነት መለያ ምልክቱን ደርድሮ ከቢሮ ወጣና በለመነው ተሳፋሪ ታጅቦ
ወደ መኪናው አመራ። ቀጠን ያለ ረጅም ነው፡፡ ፈካ ያስ ጠይም ሆኖ ገተር ባለው አፍንጫው ላይ ጥቁር መነጽር አድርጓል። ልክ ከመኪናው የፊት በር አጠገብ
ሲደርስ የተጣላቸውን ፈታሽ ጨምሮ ተሰፋሪው ሀሉ የሚፈጠረውን ሁኔታ ለማየት ዙሪያውን አሰፈሰፈ:: አስቻለውም" ከህዝቡ ፊት ሆኖ ከፈታሾቹ አጠገብ ቆሟል የኬላው ሀላፊ ወደ ውስጥ ሴትየዋን እያየ «ምንድን ነው ችግሩ? » ሲል ጠየቃቸው
«እናቱ እያላችሁ ችግር መች ይጠፋል? ችግር ለመፍጠር አይደል! በየቦታው የተኮለኮላችሁት» አሉ ሴትየዋ ዓይናቸውን አፍጥጠው ቆነጥነጥ እያሉ
«መኪናው አይፈተሽ ነው የሚሉት?»
«እኔ አልወጣኝም፡፡ ስትልጉ መነቃትሩት።» አሉና ሁለመናቸውን አንዘራቸው በል! ስንት አንበሳ የመሳሰለ ጀግና ወልጄ ወልጀ ለወግ ማረግ
ያደረስኩ ሴትዬ አንድ ጓጉንቸር በመሰለ አሽከርህ ልዋረድ!» አሉና ቀሚሳቸውን ቀልጠፍ እያረጉ! ይህ ቅሌታም! አያውቅም እንጂ እኔ አቦነሽ ሃይሌ ስንት ኮረኔል የሚያከብረኝ ሴት ነኝ፡፡ ይህ ባለጌ ባለጌ ያሳደገው! አሉ በማከታተል።
«አሁንም አታርፊ አንቺ አሮጊት!» አላችው ያ መጀመሪያ የተጣላቸው
ፈታሽ በመቶ አለቃው ትክክሻ ላይ አንገቱን ሰገግ አድርጎ ወደ ውስጥ እያየ።ወደ ውስጥ እያየ

ሴትዮዋ እሁንም እየተቅበጠበጡ «አንተ እንደኔ አታረጅ፣ አንት የተረገምክ ዕድሜ እኮ የንጥህና ምልክት ነው። አዳሜን እያስለቀስክ ዛሬ ደረትህ ቢያብጥ
ዘላለም የምትኖር መሰለህ ዛሬ ሰው ቢያቅተው ነገ አንድዬ ይደፋሃል። ምናምንቴ
የምናምንቴ ልጅ! አሉት ወይዘሮ አቦነሽ ሀይሌ። ምናልባት አፍ እላፊ የተናገሩ መስሏቸው ለማካካስ ሳይሆን አይቅርም ከተቀመጡበት ድንገት ብድግ አሉና ግማሽ ጭናቸው እስከሚታይ ድረስ ቀሚሳቸውን እያራገፉ «ቡና ቋጥራለች ብላችሁ
ተሆነ ያው! አቦነሽ ሃይሌ ነጣ!» ብለው ቁጭ እያሉ «ከእንግዲህ ወዲያ አዳሜ ዓይንህን ብታፈጥ የምፈራህ እንዳይመስልህ» አሉ፡፡ እንዳነጋገራቸው የኬላውንም ሀላፊ ነካ እያረጉ ይመስላል።

መቶ አለቃው ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለበት በማሰብ ላይ ሳለ በሴትዮዋ ቆራጥነትና አነጋገር ልቡ ሲነካ የቆየው አስቻለው ጣልቃ ገባ። «እኔ እምልህ መቶ
አለቃ» አለው አጀቹን በደረቱ ላይ አቆላልፎ የኬላውን ሃላፊ ዓይን ዓይኑን እያየ::
«አንተ እምትለኝ» አለው መቶ አለቃው በንቀት ዓይን እያየው::
«የምትፈልጉት ቡና አለማለፉን ወይስ የተሳፋሪውን ከመኪና ላይ
መውረድና መውጣት?» ሲል ኮስተር ብሎ ጠየቀው::
«አንተ ምንድን ነህ?» አለው ያ መጀመሪያ ከሴትዮዋ ጋር የተጣላ ፈታሽ ጣልቃ ገብቶ። ዓይኑንም አፈጠጠበት።
አስቻለው ውስጡ ተቆጣ፡ ቀድሞም ቢሆን መቶ አለቃው በንቀት ዓይን ሲያየው በስጨት ብሎ ነበርና እሁን ደግሞ የባሰ በመናደድ «ምንድነህ?» ሲል
የፈታሹን ጥያቄ ራሱ ደገመው፡፡
«አዎ ምንድነህ?»
አስቻለው ድንገት ሳያስበው አንድ ነገር በአዕምሮው ብልጭ አለበት። በሆዱ የመጣው ይምጣ እያለ «ካኪ አለመልበሴን አይተህ ከሆነ ተሳስተሃል! እኔ ግን
ሙሉ የፖርቲ አባል ነኝ!» ብሎ በመታወቂያ እንደመፈለግ ዓይነት እጆቹን ከአንድ ኪሱ ወደ ሌላው ያራውጣቸው ጀመር፡፡
ቆይ ጓድ!» አለ መቶ አለቃው ፈጠን ብሎ፡፡ የአስቻለውን ሁለት እጆች በሁለት እጆቹ ያዛቸው።
ደሞ ምንድህ ይለኛል እንዴ ይሄl?» በማለት አስቻለው በፈታሹ ላይ ዓይኑን አፈጠጠ፡፡ ያ ፈታሽ በሀፍረትና በፍርሀት ፊቱ ልውጥውጥ አለ።
«የኛ ችግር እኮ - » ብሉ መቶ አለቃው ንግግር ሲጀምር አስቻለው ቶሎ ብሎ አቋረጠው::
“እ! የእናንተ ችግር?»
«አንዱን አስወርደን ሌላውን ስንተው ሕዝቡ አድሎ አደረጋችሁ እያለ» ብሎ ሳይጨርስ አሁንም አስቻለው አቋረጠው፡፡ ፈጠን ፈጠን ባለ አነጋገር፡፡
1