አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


ተማሪ አንዱ በአንዱ ላይ እየተንጠራራ ከሰሌዳው ላይ የመለያ ቁጥሩን መፈለግ
ጀመረ።

እነ እስክንድር ግርግሩ መሀል ሲደርሱ እነ ማርታ ውጤታቸውን ለማየት ስለ ተበታተኑ ተሰወሩባቸው ። የአንደኛና የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች ውጤት ብቻ ነበር የወጣው ።

የአራተኛ ዓመቶች ውጤት አልደረሰም እንዴ ? ”
አለው እስክንድር ውጤቱን የለጠፈውን ሰውዬ ሲመለስ አግኝቶት።

"ከሰዓት በኋላ ” ብሎት ሰውዬው እየተደፈ ሐደ ።

“ እስቲ እኔም ጉዴን ልመልከት ”አለ ሳምሶን አስደንጋጭ ድምፁ ስልት አጥቶ እየተንቀጠ።

“ ቆይ ምን አስቸኮለህ ? ግርግሩ ተግ ይበልልህ! ” አለው እስክንድር ።

ሳምሶን አረ ባክህ ! ” ብሎት " ተማሪውን እየገፈታተረ ወደ ልለተኛ ዓመቶች የውጤት ሰሌዳ አመራ።

እቤልና እስክንድር ከግርግሩ መሀል ወጥተው ብቻ ቸውን ቆመው ቀሩ አንዳች ነገር ተጫጭኗቸዋል አይነጋገረም።

ግርግሩን አትረው ይመለከቱ ጀመር » ማንኛውም ነገር ውስጡ ሲሆኑበትና ከውጭ ሲታዘቡት የተለያየ ገፅታ አለው የፈተና ውጤት ግዜ እንዲህ ከሩቅ ሆነው ሲያዩት አሳዛኝ ትርኢት ይታይበታል ውጤቱ የድካም ውጤት ሳይሆን የብሔራዊ ሎተሪ እጣ ይመስላል አንዳንዱ እየሳቀ ሄዶ ውጤቱን አይቶ ሲመለስ ፊቱ ኮሶ ይመስላል በፍርሃት
እየተንቀጠለጠ ሔዶ እየቦረቀ የሚመለስም አለ ውጤቱ አስደንግጦት የቆመበት ዘፍ የሚልም አይታጣም አብዛኛው ተማሪ ስለ ራሱ የነበረው ግምትና አሁን ያገኘው ውጤት እየተራራቀበት ፊቱን አጨማዶ ሲመለስ ነው የሚታየው።
እኔስ ከየትኛው ዐይነት እሆን ? ” ሲል እስክንድር ራሱን ጠየቀ ። የውጤት ጊዜን ሁኔታ እንዲህ በሩቅ ታዝቦ አያውቅም ነበር ።

አንዲት ልጃገረድ በጓደኞቿ ተደግፋ እያለቀሰች በኣጠገባቸው ስታልፍ አይተው የአቤልም የእስክንድርም ልብ
አብሮ አለቀሰ።
አይዞሽ ፡ ዩኒቨርስቲ የሕይወት መጨረሻ አይደለም ” አላት እስክንድር ቀስ ብሎ።

ቀና ብላ አላየችውም ጓደኞቿ ግን ያሾፈባት መስሏቸው ዞረው ገላመጡት ። ግልምጫ ከዐፈር የሚደባልቅ ቢሆን የማይተዋወቁት ሰው ግልጫ ኦሆሆ ! ቶሎ ብሎ ዐይኑን ከአይናቸን አሸሸ ።

ዘወር ሲል ሚስተር ሆርስ ከሶስት ልጆች ጋር ሆኖ ቅልጥሙን እጥፍ እያረገ ፌቱ ፈክቶ ሲያልፍ አየው ።

“ እንዴት ነው ውጤት? ፊትህ ሁሉ ጥርስ ሆኖአል” አለው በሩቁ ከአኳኋኑ ማለፉን ተረድቶ

“ አልሞትንም ፤ ተርፈናል ። የዩኒቨርስቲ ሕይወታችንን አራዝመናል።

« እንኳን ደስ ያለህ ! ” አለውና ፥ “ በቀላሉ የሚደሰት ተፈጥሮ ጥሩ ነው ” አለ በልቡ በድንግት የአቤል ድምፅ አስደነገጠው።

“ ያቻት ትዕግስት"

አቤል ከርቀት ትዕግሥትንና ማርታን ሲያይ ሳያስበው ነው ስሟ ያመለጠው ። በድንጋጤ ስሟን ከመጥራቱ ሌላ
የሚጨምርበት ነገር አልነበረም ።

“ እህ ?” አለው እስክንድርም ደንግጦ "

አቤል ምንም አልመለሰም ። ፊቱ በቅጽበት ተለዋውጦ ከሰል መሰለ ከንፈሩ ተጣብቆ አልላቀቅ አለው ዐይኑ
ፈዞ ቀረ።

እስክንድርም መልስ አልጠበቀም ፥ የአቤልን ዐይን ተከትሎ ትዕግሥትንና ማርታን ተመለከታቸው ውጤታቸውን
አይተው በመመለስ ላይ ነበሩ ። ፊታቸው ዳምኗል ።በኀዘን ተውጠው አንዳችም ቃል ሳይለዋወጡ መሬት መሬት እያዩ ነው የሚሔዱት ። ለእነ አቤል ደግሞ የባሰ
ዳምነውና ተክዘው ታዩአቸው ።

ትዕግሥትና ማርታ እነ አቤልን ሲያዩዋቸውመንገዱቸውን አሳብረው በሌላ በኩል ሔዱ። በማርታ ግፊት ነበር
ይህ የተደረገው። ማንም ሳያያት ወደ መኝታ ክፍሏ መሔድ ነው የፈለገችው ።

አቤል መቆም ኣልቻለም ። ወገቡ የተቀነጠሰ መሰለው። ትዕግሥት ወድቃለች ማለት ነው ? ከዩኒቨርስቲው ልትባረርና ሊያጣት? ስለ ራሱ ውጤት አንዴም አላሰበ መለየት የሞት ያህል ሆኖ ታየው ።

ቃላት መተንፈስ ፈለገ ግን ከንፈሮቹ አልላቀቅ አሉት እርዳታ በሚጠይቅ አመለካከት እስክንድርን አየው ። ከተረታ ወይም ከደከመ ልብ ብቻ ነው የዚያን
ዐይነት እይታ የሚመነጨው።

“ ምን ልርዳህ ? ” አለው እስክንድር ' ሁኔታው ስለ ገባው።

አቤል ምንም ሳይመልስለት ፡ በሚስለመለም ዐይኖቹ እያየው ቀስ ብሎ አጠገቡ ያገኘው ነገር ላይ ቁጭ አለ።

እስክንድር በሐሳቡ አሁን ምን በወቅንና ነው ? ” አለ ። “ ምናልባት እነዚህ ልጆች ሳይወድቁ በዝቅተኛ ማርክ ብቻ እንደሆነስ የተከዙት ? ለምን ተከትዬአቸው ሔጂ አልጠይቃቸውም ? እነሱ ቢሸሹኝ ተናደው ይሆናል። እኔ
ግን ሔጄ ጠይቄአቸው ወድቀውም ከሆነ ማጽናናት አለብኝ ካለዚያ የመተዋወቅ ትርጕሙ ምንድን ነው ? ” አለና አቤልን የተቀመጠበት ትቶት ሔደ ።

ከሁለቱም ከማዘኑ ሌላ የእንድም ቀን የጫዋታ ትዝታ ቢሆን መጥፎ ነውና ከማርታ ጋር የመለያየቱ ነገር እሱንም ቅር ብሎት ነበር ።

ፈጥኖ ሔደ። ሲደርስባቸው ቀድማ ያየችው ትዕግሥት ነበረች ። በደካማ ፈገግታ ሰላምታ ሰጠችው ። ማርታም
እሷን ተከትላ ዘወር ስትል አየችው ። ሰላምታ ልትሰጠው ብትፈልግም ፈገግ ማለት አልቻለችም ።

እስክንድር አጠገባቸው ከደረሰ በኋላ ስለ ውጤታቸው መጠየቅ ፈርቶ ከንፈሩ ይንቀጠቀጥ ጀመር ።

“ እንዴት ነው ? ” አላቸው ፡ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ፥ አንዴ ወደ ማርታ አንዴ ወደ ትዕግሥት እየተመለከተ ።

“ ዩኒቨርስቲያችሁን ለቀቅኩላችሁ እናንተው ኑሩበት!” አለችው ማርታ ቀድማ መንፈሷ ቢደክምም ምላሷ አልሞትም ነበር ።

“ ምነው ? ውጤቱ መጥፎ ነው እንዴ ? ”
ኤጭ ! ”
ከንፈሩን መጠጠና ወደ ትዕግሥት ዞሮ ' “ የአንቺስ ውጤት እንዴት ነው ? ” ሲል ጠየቃት ።

ጥሩ ነው ። በመካከለኛ ውጤት አልፌአለሁ ” አለችው በፈገግታ ።

“ እንኳን ደስ ያለሽ ! ዋናው ማለፍሽ ነው!!” አለና እሱም ፈገግ ብሎ እንደገና ጨበጣት ።

ማርታ ሁለቱንም በቅናት አስተያየት ላጠቻቸው "ዐይን የሚገድል ቢሆን ሁለቱም የቆሙበት ክው ብለው ቀርተው ነበር ።

እስክንድር ደስታና ኀዘን መሐል ገብቶ ወደ የትኛዋ 'እንደሚሆን ግራ ገባው ። “ ግማሽ ፊትን አጥቁሮ፡ ግማሽ ፊትን ማሣቅ ቢቻል እንዴት ጥሩ ነበር !” አለ በልቡ ።

ማርታን ፊት ለፊት ሊያያት አልደፈረም ። ቀስ ብሎ በስርቆሽ ተመለከታት የጠወለገች አበባ መስላለች ለካ ውበት የስሜት ነጸብራቅ ነው?” አለ በሐሳቡ ። ስሜቷ ከውስጥ ሲንድ ፡ሲቃጠል ሲብከነከን ታየው ድርብ የከንፈር ቀለሟ በመጠውለጉ ፊቷ ላይ ጎልቶ ምናምን
የላሰች አይጥ አስመስሏታል ። ቅንድቧ ብቻ እንደ ወትሮው ይርገበገባል ።

እስክንድር የቅንድቧን መርገብገብ አይቶ ወሬ እንደምትፈልግ ዐወቀ ። ግን ምን ዐይነት ወሬ ? በእሷ መውደቅ ምክንያት ተማሪውንና አስተማሪውን ማማት መቦጨቅ ? አይዞሽ ማርታ ዩኒቨርስቲ የሕይወት መጨረሻ አይደለም ” አላትና ፡ አንድ ቀን ያጫወተችውን አስታውሶ : “ ደሞም ከዚህ ወጥተሽ ስኮላርሽፕ መጠበቅ ትችያለሽ ” አላት ።

“እኔ ማርታ ጉዳዬም አይደል ! ብቻ እንኳን ዩኒቨርስቲ የምትሉትን አየሁላችሁ !
እስክንድር በልቡ “ እኛ ደሞ ምን አደረግንሽ ? " ብሎ ጭጭ።

“ የማትስ አስተማንሪኮ ነው ጉድ ያረገኝ ” አለች ትንሽ ቆየችና።

“ እሱ "F" ባይሰጠኝ ኖሮ ሌላ ትምህርት አልጎዳኝም ነበር።

“ ማነው እሱ? ” አላት ያስተዛዘናት መስሎት

“አቶ ኃይሉ የሚሉት አንድ ሽማግሌ አለ " ላውጣሽ ብሎኝ ስለ ዘጋሁት ቁጭቱን ተወጣብኝ ”

“ ያሳዝናል ! ” አለ እስክንድር ፡ ውሸቷ ኮርኩሮት በህዱ እየሳቀ።

ደሞ ከእሱ ጋር ልውጣ እንዴ? ቅሌታም ሽማግሌ ! ”፥

እስክንድር እንደገና ከንፈሩን
1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....አዜብና አንዱአለም አጠገቡ ናቸው፡፡ ከኪሱ ውስጥ የሆነ ነገር አወጣ፡፡ በትንሽ የፕላስቲክ ሳጥን ውስጥ የተቀመጠች..ውድ ነገር:: በመጠን በጣም ትንሽ፤ በቁም ነገር ግን እዚያ እላይ!! ቀለበት. የቃል ኪዳን ቀለበት ... ስለ እውነተኛ ፍቅር የተዘጋጀች ፤ የትዳር መጠንሰሻ:
የቃል መተሳሰሪያ፤ ቀለበት... በምህጻረ ቃል የሱና የሷ ስም የተጻፈበትን
ቀለበት አወጣና......

“በመንፈሰ ጠንካራነትሽ ለሰጠሽኝ ትልቅ ትምህርት፡ ለእውነተኛ ፍቅር ስትይ ለከፈልሽው መስዋዕትነት፣ በታማኝነት ፀንተሽ ኣብረን ለቆየንባቸው ጊዜያቶች ሁሉ ማስታወሻ እንድትሆን፡ ይህቺ ሁለት ዓመት ለቀሪ ህይወትሽ ትምህርት የምታገኝበት፣ እኔ ደግሞ ለሠርጋችንም ሆነ ከሠርጋችን በኋላ የትዳር ህይወታችንን በሰላም ለመምራት እንዲያስችለን የምዘጋጅበት እንዲሆንና፤ የማረፊያ ቤት ቆይታሽ፤ መጪውን ብሩህ
ተስፋ አሻግረሽ የምትመለከችበት የዕረፍት ጊዜ እንዲሆንልሽ በመመኘት፤
ያዘጋጀኋትን ገፀ በረከት፤ ይህችን የቃል ኪዳን ቀለበት፣ እንድትቀበይኝ” አለና ከጉልበቱ በርከክ ብሎ ሽቅብ ተመለከታት፡፡ ከዚያም ፍዝዝ ባለችበት
እንባዋ ጉንጮቿን እያቋረጠ፤ ቁልቁል መውረድ ሲጀምር፤ ቀልጠፍ ብሎ
የግራ እጇንና ቀለበቷን ወደ ላይ ከፍ አደረጋቸው፡፡

ከዚያ የከበበው ሰው በሙሉ በደስታና በሆታ አጨበጨበላቸው፡፡ ዕልልታውን አቀለጠላቸው፡፡ አንዱዓለምና አዜብ ተቃቀፉ፡ ሚስጥሩን የምታውቀው አዜብ ብቻ ነበረች፡፡ ቀለበቱንም የመረጠችለት እሷ ናት።
ለአንዱአለም ግን ሁኔታው ድንገተኛ ነበር፡፡ በፍርድ ቤቱ ቅጽር ግቢ ውስጥ ሌላ ተዓምር፡፡ ቃል ኪዳን ......ከዚያም
ቀለበቷን በጣቷ ውስጥ ሲያጠልቅ፤ አዜብና አንዱአለም በደስታ ሲቃ ተውጠው፤ እልልታቸውን፤ አቀለጡት፡፡
ያቺን ቀለበት በዚህ በዛሬው ዕለት ሊያደርግላት የወሰነበት ምክንያት ነበረው፡፡ ይህቺ የውሣኔ ዕለት፣ ይህቺ የፍርድ ቀን፡ በነፃ የምትለቀቅበት ሳይሆን፡ የህግ እስረኛ ሆና በማረፊያ ቤት እንድትቆይ የሚወሰንበት ዕለት መሆኗን አስቀድሞ ስለሚያውቅ፣ በዚህች ቀን የህግ እስረኛ በመሆንዋ፤ የመገለል ስሜት እንዳይሰማትና፤ የሞራል ውድቀት
እንዳይደርስባት፣ መታሰር ማለት፤ ከዚህ ዓለም መገለል ማለት ያለመሆኑን ተረድታ፤ በጥንካሬና በጽናት የእስር ዘመኗን እንድትጨርስ ለማድረግ፣ በዚያች የውሣኔ ዕለት፤ እስረኛ ብቻ ሳትሆን፤ የታጨች ሙሽራ መሆኗን ጭምር እንድታውቅ፣ የህይወት አጋር ፤የትዳር
ጓደኛው ! ከሷ ሌላ ማንም እንደሌለው ሊያረጋግጥላት፡፡ ሊያበረታታት፡፡
ስለወሰነ፤ የቀለበት ስነ ሥርዓቱን ባልጠበቀችው በዚያ ሁኔታ ሲፈጽምና
ቀለበቷን በጣቷ ላይ ሲያኖርላት፣ በደስታ ሲቃ ተውጣ፣ እስረኛ መሆኗን ፍጹም ረስታ፤ በሳቅ እየተፍለቀለቀች፣ ሻምበልን አንገቱ ላይ ተጠመጠመችበት፡፡ ሻምበል አደራውን ተወጣ! የፈራረሰ በድን አካሏ በወደቀበት ስፍራ በመቃብሯ ላይ ሳይሆን፤ ያቺን ውብ የፍቅር ጽጌረዳ
አበባ፤ አለንጋ በሚመስለው የቀለበት ጣቷ ላይ እና፤ በፍቅሩ ምክንያት ታላቅ ጉዳትና ስብራት በደረሰበት ልቧ ውስጥ በክብር አስቀመጠላት ::
ዶክተር ባይከዳኝ በዚያ በሚያየው ነገር ተደናግጦ እና ተገርሞ አፉን በሰፊው ከፍቶ በመቅረቱ ምክንያት፤ እጆቹን ማራገብ እንኳ ተስኖት!በተከፈተው አፉ
ውስጥ ይመላለሱ የነበሩ ዝንቦች ፤ ያለከልካይ ተዝናኑበት፡፡ ከዚያም እንደምንም ብሎ ከሰመመኑ ሲመለስ፤ የሆነ የቅናት መንፈስ ሰውነቱን ውርር አደረገው :: ያንን ያልጠበቀውን
ትእንግርት እያየ፤ አፉን ከፍቶ በቀረበት ቅጽበት ሌላ ነገር ተደገመ
“እኛ ደግሞ ለዛሬ የወርቅ ቀለበት ያላዘጋጀን ቢሆንም፧ ልክ አንቺ ከማረፊያ ቤት ወጥተሽ፤ የጋብቻ ስነ ስርዓታችሁን ስትፈጽሙ ፤
እኔና አዜቢና ደግሞ፧ የቃል ኪዳን ቀለበታችንን የምናስርበት ዕለት
ለመሆኑ ማረጋገጫው፤ የቃል ኪዳን ማህተሙ፤ ይኸው!” አለና ወንድሟ
አዜብን፡ የምታፈቅራት ጓደኛዋን፡ ወደ ደረቱ ሳብ፤ እቅፍ፤ አድርጉ አንገቷን ቀና በማድረግ፤ ከንፈሯን ግጥም አድርጎ ሲስማት፡ ይህ ሁሉ ተአምር በፍጹም ያልጠበቀችው ነበርና፤ ትህትና ከደስታዋ ብዛት የምትሆነውን አጣች፡፡ ያቺ ከልጅነት እስከ እውቀት፤ በሀዘንና፤ በችግሯ
አንድም ጊዜ ተለይታት የማታውቅ፤ እንደነፍሷ የምትወዳት ጓደኛዋ፤
ይሄውና የወንድሟ ሚስት ልትሆን፡ የሚወልዱዋቸው ልጆች የአክስቴ ፡
የአጎቴ፡ ልጅ ሊባባሉ ነው፡፡ የጓደኝነት ፍቅራቸው ወደ ስጋ ዝምድና ሊሸጋገር ነውና፤ አልቻለችም፡፡እንባዋ በድጋሜ ኮለል ብሎ ሲወርድ አሁንም ህዝቡ
ጭብጨባውን አቀለጠላቸው......

በሚያየው ተደጋጋሚ ትርኢት ተደንቆ፤ በሳቅ እያውካካ ዶክተር ባይከዳኝ ከህዝቡ ፈንጠር ብሎ ቆሞ ነበር፡፡ ያንን ሁሉ ትርኢት ተመልክቶ ካበቃ በኋላ ግን፤ የቅናት ስሜቱ እየተገፈፈ ሄዶ፤በምትኩ የደስታ ስሜት ይሰማው ጀመር፡፡ ምንም እንኳ የዛሬው የሻምበል እድል የሱ እንደነበረ ቢሰማውም፤ በራሱ ጥፋት እድሉን አበላሽቷልና፤ ይህቺ ለሱ ፍቅር ስትል ትልቅ ዋጋ የከፈለች ቆንጆ ልጅ
ከዚያ ሁሉ ችግር በኋላ ከጐኗ ቆሞ አይዞሽ የሚላት አጋር በማግኘቷ
ተደሰተ :: ትህትና ምንም በደል ያላደረሰችበት ልጅ መሆኗን ህሊናው
ደጋግሞ ስለጨቀጨቀው ይቅርታ ሊጠይቃትና እንኳን ደስ አለሽ ሊላት
ፈለገ፡፡ ከዚያም ጠጋ አለና.....
“ለተፈጸመው ስህተት ሁሉ አዝናለሁ፡፡ ላደረስኩብሽ በደልም ከልብሽ ይቅርታ እንድታደርጊልኝ እለምናለሁ :: በሰላም የእስር ዘመንሽን እንድትጨርሺና! መልካም የቀለበት ስነ ስርአት እንዲሆንልሽም ከልብ እመኝልሻለሁ
አላት፡፡
አንተም ፈቃደኛ ሆነህ እዚህ በመገኘትህና እውነቱን በማወቅህ
እኔም በጣም ተደስቻለሁ፡፡ አመሰግንሃለሁ፡፡ ያለፈውን ሁሉ
እረስቼዋለሁ፡፡ላንተም መልካሙ
ሁለ እንዲገጥምህ እመኝልሃለሁ፡፡ አዲስ ቀን ይመጣል : አዲስ ህይወት ይቀጥላል.በማለት አጸፋውን መለሰችለትና፣ ሻምበልን አየችው፡፡ ሻምበልም አያት::ከዚያም ሶስቱም እርስ በርሳቸው ተያይተው ፈገግ ሲሉ፤ አዜብም
ዶክተር ባይከዳኝን እያየች ፈገግ አለች፡፡ ሰራሁልህ ማለቷ ይሆን?

ለጊዜው ቢደብቋትም፤ ውሎ እያደር ለቅሶዋ ቢበዛና ውትወታዋ ቢያስጨንቃቸው፤ እውነቱን ነገሯት፡፡ እንደፈራችውም ልጇ በጤናዋ
እንዳልጠፋች ካወቀች ዕለት ጀምሮ፤ በበሽታዋ ላይ ሌላ በሽታ ተጨመረባት፡፡ ትህትና ከሆስፒታል ድና ብትወጣም እስር ቤት መግባቷን ሰማች፡፡ መርዶ... ትንሹ ልጇ አንዱአለም ደግሞ በእንጭጭነቱ ተለይቷት ለመሄድ መዘጋጀቱን ሰማች፡፡ ሌላ የልብ ስብራት... ያንን የምትወደው ባለቤቷን የነጠቀባት ጦርነት፤ አሁን ደግሞ ሮጦ ያልጠገበ አንድ ፍሬ ልጇን እንዳይነጥቅባት በሥጋት ተውጣ፤
ጠዋትና ማታ እዬዬ ብቻ ሆነ፡፡ሁለቱንም አለኝታዎቿን ከጐኗ ስታጣቸው፤ የወላድ መካን የሆነች መሰላት፡፡ ትህትና ከሆስፒታል ከወጣች በኋላም እቤቷ እንድትገባ ሳይሆን፤ ፍርድ ቤቱ በማረሚያ ቤት እንድትቆይ መወሰኑን ስትሰማ
ከዛሬ ነገ በነፃ ትለቀቅልኛለች ብላ በጉጉት እየተጠባበቀች ጭል፤ ጭል፤ትል የነበረች ተስፋዋ ድርግም ብላ ጠፋች፡፡
ይህ የጨለማ ህይወት ፍጹም ልትወጣው የማትችለው ሆነባት።የቤት ሰራተኛዋ እታፈራሁ የልጅ ያክል ብትንከባከባትና፤ ሻምበል ብሩክና አዜብም ልጆቿን ሊተኩላት ከጐኗ ሳይለዩ
ደፋ ቀና ቢሉም፤ሳይሆንላቸው ቀረ፡፡
ከዚህ በኋላ በሽታው በአንድ ወገን፤ የልጆቿ ናፍቆት በሌላው ወገን ሆነው፤ እየተጋገዙ፤ ስጋዋን እኝከው በመጨረስ፤ የሞት ድግሷን ያፋጥኑት ጀመር..
ትህትና ማረሚያ ቤት በቆየችበት ጊዜ ብቸኝነት፣ መታከት ተስፋ መቁረጥና
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....“ዝግጅቱ በተጀመረ በሦስተኛው ወር ምሥጢሩ አፈትልኮ ተገኘ፡፡ ማን አወጣው? እንዴት አወጣው? የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ብቻ በእንግሊዞቹ
ኦብዘርሸርና በፈረንሳዮቹ አፍሪካን ዲፌንስ ላይ ያዕቅዱ ፍንጭ ታትሞ
ወጣ፡፡ እውነቱን ንገረኝ ካልካ ምሥጢሩን ያወጣው የዕቅዱ ጠንሳሽ እራሱ
ነበር፡፡”

“እንዴት? የዛ ምሥጢሩን ሰምን?”

“ቆይ… ዝም ብለህ ተከተለኝ.… እርግጥ ይህ የእኔ መላምት ነው… ግን ዳር ስንደርስ አንተ እራስህ ተመሳሳይ መላምት ላይ እንደምትደርስ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እንዳልኩህ ምሥጢሩ አፈተለከ፡፡ ይህ እንደተሰማ የተለያዩ የአፍሪካ ባለሥልጣናት ከወዲያ ወዲህ ሲሯሯጡ ሰነበቱ፡፡ ውጤት ወታደራዊ ዝግጅቱ እራሱን በቻለ ምስጢራዊ መልክ እንዲካሄድና በማንኛውም አገር የሚገኝ ቅርንጫፍ ክፍል በቀጥታ ከዋናው ማዘዣ ካልሆነ በስተቀር በሚገኝበት አገር የመከላከያ ሚኒስቴርም ሆነ ሌላ መንግሥታዊ አካል ጣልቃ ገብ ቁጥጥርም ሆነ ተፅዕኖ እንዳይደረግበት ስምምነት ላይ ተደረሱ፡፡

“ዓላማው ዝግጅቱን አንድ ወጥ
በሆነ መልኩ ለማፋጠንና ምሥጢሩም እንዳይባክን ለመጠበቅ ተብሎ የተቀየሰ ነበር፡፡ በሌላ መልኩ ለተመለከተው ደግሞ ስምምነቱ አገሮች በተናጠል በክልላቸው ውስጥ በሚደረገው ወታደራቂ ዝግጅት ላይ መረጃ እንዳያገኙ የሚያግዳቸው ሆነ፡፡ ይህንን ስምምነት ተቃውሞ የሚቆም አገር ደግሞ ቀደም ሲል የተከሰተው አደነት የምሥጢር መዝረክረክ እንደማይፈጠር ማረጋገጫ ማቅረብ ሊኖርበት ሆነ፡፡ የዚህን ዓይነት ዋስትና መስጠት ደግሞ ለማንኛውም አገርዐአዳጋች ነው፡፡ ያም ሆነ ደሀ ምሥጢሩ በጨቅላ ደረጃው በማፈትለኩ ከዛ በኋላ የወታደራዊ አካሉ እቅሰቃሴ ሁሉ ከኣገሮች ቁጥጥር ውጭ በምስጢር
ለመሆን በቃ፡፡ ይሀን ነበር የፈለገው የዕቅዱ ባለቤት-እንቅስቃሴውን ያላታዛቢ
በቀጥታና በምስጢር መምሪት፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላ የአፍሪካ መሪዎች
የሚያጊንት መረጃ ሁሉ ከዋናው ማበዣ በሚተላለፉ በገባዎች ላይ ብቻ
የተወሰነ ሆነ፡፡

በሌላ ቋንቋ የአፍሪካ መሪዎች የሚያውቁት የእንቅስቃሴው መሪ እንዲያውቁ የሚፈቅድላቸውን ብቻ ሆነ:: ይህም እያንዳንዱ አገር አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ ኤምባሲው ባስቀመጠው የወታደራዊ አታሼው
በኩል ብቻ የሚፈጸም ነበር፡፡

“የወታደራዊ አካሉ መረብ እየሰፋና እየተጠላለፈ በመጣ ቁጥር
በየአገሩ የሚገኙ እውቀት ችሎታና ተሰሚነት ያላቸወ የጦር ባለሙያዎች
በጥንቃቄ እየተጠኑና አየተመዘኑ በዚሁ አካል ይዋጡ ጀመር፡፡ ብቻ ምን
ልበልህ..በሁለት ዓመታት ውስጥ እጅግ ጠንካራ፤ እጅግ ሰፊ፧ እጅግ ምስጢራዊ ወታደራዊ አካል አፍሪካ ውስጥ በስውር ተገንብቶ አበቃ:: አልፎ ኣልፎ አንዳንድ ባለስልጣኖች የወታደራዊ ኣካለን አለቅጥ ምስጢራዊ መሆንና መግዘፍ፡ የመቃወም ፍንጭ ሲያሳዩም ያለምንም ምህረት በተናጠል እየተለቀሙ ተወገዱ፡፡ ከዚህ ወዲያ ማንኛውም ምስጢሩን የሚያውቅ ባለሥልጣን ድምፁን ዝቅ እድርጎ መናገርን መረጠ፡፡”

ይህን 'አካል የምትለውን ማነው የሚመራው?” ናትናኤል ጠየቀው፡፡

“በትክክል እነማን እንደሆኑ አላውቅም...ግን ከአፍሪካ አገሮች ሁሉ
የተውጣጡ የጦር አዛዦች እንደሆነ አውቃለሁ፡፡”

“እሺ ቀጥል።”

“ሁኔታው በዚህ ላይ እንዳለ ከሁለት ወር በፊት ወደ አገሬ ተጠራሁ፡፡ አገሬ ውስጥ የቆየሁት ግን ለእራት ሰዓታት ብቻ ነበር፡፡
ሞንሮቪያ እንደደረስኩ ወደ መከላከያ ሚኒስቴር ተወስጀ ስለዚሁ ኣካል
መጠነኛ ገለፃ ከተደረገልኝ በኋላ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ግልጋሎቴን
ለዚሁ አካል እንደምሰጥና ተጨማሪ መመሪያዎችንም ለመቀብል ወደ ሌላ
ስፍራ የምወሰድ መሆኑ ተነገረኝ፡፡

“እንዳልኩህ ሞንሮቪያ ከደረስክ ከአራት ሰዓታት በኋላ በሌላ አነስተኛ አውሮፕላን የሁለት ሰዓታት ጉዞ እድርጌ ከአንድ በረሃማ ቦታ አረፍን፡፡ ቦታው የቶ እንደሆነ ለመናገር ያስቸግራል። እርግጥ ባንዲራ
ተሰቅሉ ይውለበለባል ግን ባንዲራው አንድ ነው፤ የአፍሪካ አንድነት
ድርጅት ባንዲራ “ከአውሮፕላኑ እንደወረድኩ ማረፊያ ቦታ ተሰጠኝ፡፡ ከእኔ ቀደም ብለው የደረሱ ነበሩ፤ እኔ ከገባሁ በኋላም ሌሎች በተከታታይ ከተለያዩ
እገሮች በሄሊኮኘተሮችና በአነስተኛ አውሮፕላኖች እየተጫኑ ገቡ፡፡ በማግስቱ
ፕሮግራሙ ተጀመረ፡፡ በአጠቃላይ አስራ እንድ ነበርን፡፡ በኋላ እንደተረዳሁት
ሁላችንም በአዲስ አበባ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ኤምባሲዎች ውስጥ
እንድንሰራ የተመረጥን ነበርን፡፡ እንደውም አንድ ሁለቱን ኤአዲስ ኣበባ ውስጥ ቀደም ብዬ አውቃቸው ስለነበር እዛ በረሃማ ቦታ በቆየሁባቸው ጥቂት
ቀናቶች ልቀርባቸው ችዬ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ የሞሮኮ ወታደራዊ አታሼ የነበረው መሃመድ ባስሪ እኔ በነበርኩባቸው ቀናቶች እዛው ነበር፡፡ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በወሩ ከጊነው ሰው ጋር ተገድሎ ተገኘ፡፡”

“ምን ላይ ነበር የኘሮግራሙ አትኩሮት?» ናትናኤል ወደፊት አዝምሞ ጠየቀው፡፡

“ዝርዝር ነጥቦች ውስጥ አልገባም፡፡ በአጠቃላይ የቆየነው ለሁለት ሳምንታት ነበር፡፡ በመጀመሪያው ሳምንት በአፍሪካ ወቅታዊ ችግር ላይ ነበር ያተኮርነው፡፡ በሁለተኛው ሳምንት ግን ስለ 'ቆንጆዎቹናሰ ስለዓላማው! ስለእን ቅስቃሴው ነበር በጥቅሉ፡፡ በአጭሩ ከመጪው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ
በኋላ የአፍሪካ መንግሥታት እንደማይኖሩ ነበር የተገለጸልን፡፡››

“ምን ማለት ነው ይሄ?” ናትናኤል ግራ ገባው::
“ነገርኩህ'ኮ ከጥቂት ቀናት በኋላ የምትኖረው አፍሪካ አንድ አፍሪካ
ብቻ ትሆናለች::”

“እንዴት? አልገባኝም፡፡”ናትናኤል የሚያዳምጠው ቅዥት መሰለው፡፡

“የስብሰባው ጊዜ ሲደርስ ጠቅላላ የአፍሪካ መሪዎች ተጠቃለው
አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ ይህ ከተገባደደ በኋላ በመላው አፍሪካ በየአገሩ ያሉ
የአካሉ ቅርጫፍ ክፍሎች በያሉበት አገር ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት
አድርገው ሥልጣን ይጨብጣሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ማንኛውም መመሪያ ከአፍሪካ
አንድነት ድርጅት ይወጣል፡፡ በአዲስ አበባ በየአገሮች ኤምባሲዎች ውስጥ
በሚገኙ ወታደራዊ አታሼዎች አማካኝነት መመሪያዎች እንደአስፈላጊነቱ ለየአገሮች ይተላለፋሉ፡፡ አበቃ::”

“እንዴ! ስንት መፈንቅለ መንግሥት ማለት ነው?” ናትናኤል ካልቨርቶን አተኩሮ ተመለከተው፡፡ ሰውየው ድጋሚ የሰከረ መሰለው፡፡

“ሃምሳ ሦስት፡፡”
“የፈጣሪ ያለህ! ይህ'ኮ እልቂት ነው፤ ሃምሳ ሦስት አገሮች ውስጥ ጦርነት መፍጠር እኮ ማለት ነው::መቼም ሁሉም አሜን ብሎ አይቀበልም:: ጦርነት ይኖራል፡፡”

“እልቂት አይደለም፡፡ ይኽው አካል ተብትቦ ያልያዘው ወገን በዝብዞ
ያላወቀው ምስጢር በየትኛውም አገር አታገኝም፡፡ ውስጥ ውስጡን በየአገሩ
ጠንካራና ተሰሚ ደጋፊዎች አሉት፤ ውስጥ ውስጡን የየአገሩን ደካማ ጎን
አብጠርጥሮ ያውቃል፤እነማን መያዝ መታሰር.መወገድ አለባቸው? እነማን
ሊታመኑ ይገባል? እነማን ባንዳዎች ናቸው? እነማን ዲቃላዎች ናቸው?
እነማን ንፁህ አፍሪካውያን ናቸው? ሁሉ ይታወቃል።”

“አሁጉራዊ መከላከያ የተባለውስ? ማለቴ" ናትናኤል ግራ ገባው::

“ሽፋን ነው:: አየህ... ወታደራዊ አካሉ የአፍሪካ መንግሥታት እያወቁና ሙሉ ድጋፍ እየሰጡት በምስጢር ለመነቃነቅና የዚህን ዓይነት ስፋት ያለው ወታደራዊ ዝግጅት ለማድረግ በየአገሩ የሚገኙትን ከፍተኛ መኮንኖችን በስሩ ለማሰባሰብ አንድ ተቀባይነት ያለው ሽፋን ያስፈልገው
ነበር፡፡ አህጉራዊ የመከላከያ ሃይል ተስማሚ ሽፋን ነበረ፡፡”

“እና የአፍሪካ መንግሥታት ሁሉ ስለእንቅስቃሴው ምንም
አያውቁም ማለት ነው?''

“ያውቃሉ፡፡ዝግጅቱ ሁሉ: ተቀነባብሮ በየአገሩ ያሉ ቅርንጫፍ ኣካላት
👍3
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

...“እየተወዛገብኩኝ ነው መሰለኝ” አለች አኔ ቤታማን፡፡

አኔ ቤታማን ኒኪን እያየች እና በጭንቀት የታችኛውን ከንፈሯን እየነከሰች የኒክ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብላለች፡፡ ያኔ የኮንስርት አዳራሹ ልብስ መልበሻ ክፍል ውስጥ ከተጣሉ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሁለቱ የተገናኙት፡፡ ስለዚህ ነገራቸው ሳይበላሽ በሰላም ማውራት ይፈልጋሉ፡፡

“ስለባሌ ማለቴ የቀድሞ ባሌ” ብላ አስተካከለችው እና “በቃ ምንም
ዓይነት ድምዳሜ ላይ ሳትደርሺ ስለእሱ የምነግርሽን ነገር እንደትሰሚኝ
እፈልጋለሁ፡፡”

“እሺ” አለች ኒኪ የእሷን እና የአኔን ፍርሃት ለማሸነፍ ራሷን እያዘጋጀች፡፡ አኔ የቀድሞ ባሌ' ብላ ማውራቷ ትንሽ ተስፋ ሰጥቷታል።ማለትም አኔ ባሏን ልትፈታው መንገድ እንደጀመረች ስለሚያሳያት ጥሩ
ስሜትን ሰጥቷታል፡፡ የአኔን ጉዳይ እንዴት መያዝ እንዳለባት ኒኪ ውሳኔ ላይ አልደረሰችም፡፡ ዊሊያምስ ስለ አኔ ባል የነገራትን ነገር ለአኔ ትንገራት? ባሏ እሷ እንደምታስበው ዓይነት ሰው እንዳልሆነ ታስጠንቅቃት? በመሃከላቸው ያለው ቅርበትን ደግሞ ይህንን እርግጠኛ ያልሆነችበትን ነገር ነግራ ልታበላሽው አትፈልግም፡፡ ስለዚህ ኒኪ ጊዜው አሁን አይደለም ብላ ዝምታን መረጠች፡፡

“እሺ ስለ እሱ ምንድነው የምትወዛገቢው?”

አኔ በረዥሙ አየር ሳበችና “እሱ እዚህ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ነው የሚገኘው” ይኼ ለእሷ ምን ያህል ያሰጋታል? ፖሊሶቹ እና ዴሬክ ዊሊያምስስ እዚህ እንደሚገኝ ያውቃሉ?

“ዝም በይ ብላ ለራሷ ተናገረች እና “አኔ ራሷ ትናገር እና ወደ እኔ ትምጣ አለች በውስጧ፡፡
እሉ እዚህ የመጣሁት ለቢዝነስ ነው ቢለኝም እኔ ግን አላመንኩትም።
በተቃራኒው እሱ እዚህ የመጣው አኔን አሳምኖ ወደ ቤቱ ለመመለስ
እንደሆነ ነው የሚሰማኝ፡፡”

ጠባኝ አለቻት ኒኪ የተሰማትን የድንጋጤ ስሜት ሳታሳይ እሺ የት ነው ያገኘሽው?”

እኔ እኮ ፈልጌ አይደለም ያገኘሁት” ብላ አኔ ተኮሳተረችና “ከኋላዬ ተደብቆ መጥቶ ነው ያገኘኝ ላዚያውም እዚሁ የአንቺ ቢሮ ከሚገኝበት ሕንፃ ውጪ ነው፡፡ ያኔ ወደ አንቺ ለቴራፒ እየመጣሁ እያለሁ በነበረበት ቀን ላይ ነው ያገኘኝ፡፡”

ኒኪ ይህንን ስትሰማ ኒኪ እላይዋ ላይ ያሉት ፀጉሮች በፍርሃት ተነስተው
ቆሙ። ሮድሪጌዝ እዚህ ቅርቤ ነበር? ቢሮዬ ድረስ መጥቶ ነበር? ይኼ
በእውነት ነገር ፍለጋ ይመስላል።' ብላ አሰበች፡፡

“ያኔ ቀጠሮዬን ስሰርዝ ያልነገርኩሽ...” ብላ አኔ በጭንቀት ጣቶቿን እያቆላለፈች ስታሻቸው ቆየች እና “አንቺ ለእሱ ምን ዓይነት ነገር እንዳለሽ አውቃለሁ። ይህንን ነገርሽን ደግሞ ላባብስብሽ አልፈለግኩም፡፡ በእኛ መካከል ያለውን ነገር እንዳያበላሽ እፈልጋለሁ፡፡”

ኒኪም እጇን ልካ የአኔን እጅ ያዘች እና “እንደዚህ እንድታስቢ ስላደረግኩሽ ይቅርታ፡፡ አኔ ሁሌም አብሬሽ ነኝ፤ ይህንን ደግሞ ታውቂያለሽ አይደል?”

“አውቃለሁ”

“ስለ እሱ ብዙ ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ” አለቻት ኒኪ አኔ ግልጽ ሆና ለመናገር በጥሩ ስሜት ላይ እንዳለች ስላየች፡፡

አኔም በኒኪ ጥያቄ ተገርማ “በእውነት ስለእሱ ምን ምን መስማት ትፈልጊያለሽ?”
ኒኪም ፈገግ ብላ “ማንኛውንም ነገር፡፡ ሙሉ ስሙን እንኳን ነግረሺኝ
አታውቂም፡፡”

“ስሙ ሉዊስ ሮድሪጌዝ ይባላል” አኔ መለሰች፡፡

“ታዲያ ለምንድነው የእሱን ስም ስታገቢው ያልወሰድሽው?”

“ይህንን አስቤበት አላውቅም” አለችና ሳቀች፡፡ በመሃከላቸው ያለው
ነገርም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንዳለ ገምታ ደስ አላት እና እኔ የመድረክ
ላይ ሥራዎቼን ስሠራ ቤታማን በሚለው ተከታይ ስሜ ስለሆነ ይህንን
መቀየር ስላልፈለግኩኝ ነው” አለቻት፡፡
“መልካም፡፡ ሥራው የሪል ስቴት ነው ብለሽኝ ነበር አይደል?”
አኔም “አዎን” አለቻት፡፡
“እሱ ብቻ ነው ሥራው?” ብላ ኒኪ ቀለል አድርጋ ጠየቀቻት፡፡
እኔ እስከማውቀው ድረስ አዎ፡፡ ለዚያም ነው እሱ ለቢዝነስ ብዬ ነው
እዚህ የመጣሁት ያለኝን ነገር ያላመንኩት፡፡ ሁሉም የሪል ስቴት ሥራው
ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ ነው የሚገኙት፡፡ ታዲያ እኔን ለማግኘት ካልሆነ
ለምንድነው እዚህ የሚመጣው?” አለቻት፡፡
በየዋህነትና በንዴት መልሱን የመለሰችበት መንገድን የተመለከተችው
ኒኪ በእርግጥም ዊሊያምስ እንዳለው አኔ ባሏ ሉዊስ ሮድሪጌዝ የሚሠራውን
የአደንዛዥ ዕፅ ሥራን እንደማታውቅ ተረዳች፡፡

“ለማንኛውም እዚህ የአንቺ ቢሮ ሕንፃ ስር ያገኘኝ ጊዜ በጣም ነበር የደነገጥኩት፡፡ ጉልበተኛ ሆኖብኝ ነበር፡፡ ስለዚህም በድጋሚ እንዳገኘው ድርቅ ብሎ ጠየቀኝ፡፡ ሉዊስ በጣም ጠንካራ እና የፈለገውን ነገር እስኪያገኝ ድረስ
እስከጥግ ድረስ የሚታገል ሰው እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ በቃ የፈለገውን ነገር
እስካላገኘ ድረስ የሚያቆም ሰው አይደለም፡፡”

“እሱ አንቺን ይፈልግሻል?” አለቻት ኒኪ፡፡

አኔም ድምጽዋን ወደ ሹክሹክታ ለውጣ “አዎን ይፈልገኛል”

ኒኪም ለሃያ ሰከንዶች ያህል ዝም ብላ ቆየች እና “እሺ አንቺስ? አኔ አንቺስ ምንድነው የምትፈልጊው?” ብላ ጠየቀቻት፡፡

“እኔ ነፃ መሆን ነው የምፈልገው” አኔ እንደዚህ ፍርጥም ብላ ትናገራለች
ብላ በማትጠብቀው ድምፅ ከመለሰችላት በኋላም “ግማሹ ልቤ ሁሌም ይወድደዋል ይኼንን አልክድም፡፡ ግን የራሴን ኑሮ መኖር እፈልጋለሁ።
ጀርባዬን በጥርጣሬ ቀን ከሌሊት እየተገላመጥኩኝ ማየት አልፈልግም፡፡”

“ከእሱ ጋር ለመለያየት ዝግጁ ነሽ?” ብላ ኒኪ ፈገግ ብላ ስትጠይቃት ሰውነቷ ደስታ እየወረረው ነበር፡፡ አኔ ነፃ ሆና እንድትኖር ትፈልጋለች።

እሷም ራሷ ነፃ መሆን ትፈልጋለች፡፡ አዎን ዴሬክ ዊሊያምስ፣ ነፍሰ ገዳዩን ካገኘ በኋላ፣ ስለ ዶውግ ውሽማ ማንነት ካሳወቃት በኋላ ደግሞ እሷም ነፃ
ሆና መኖር ትጀምራለች፡፡


poc camas
“አዎን ዝግጁ ነኝ፡፡ ያንንም ነበር ልነግርሽ የፈለግኩት፡፡ ግን እኔ
እንዲሄድ አስገድጄው ሳይሆን እራሱ አምኖበት እንዲሄድ ነው፡፡ በቃ እህል
ነው የምፈልገው፡፡ ይህንን ግን ማድረግ የሚቻለው እኔና እሱ ጓደኛሞች
ውሃትን እንዳበቃ እና አብረን መኖር እንደማንችል ራሱ አውቆ እንዲተወኝ
ለመሆን ከተስማማን ብቻ ነው::”
“ገባኝ” አለች ኒኪ ይህችን ጠንካራዋን አኔን እያየች፡፡
“ይህንን ነበር ልጠይቅሽ የፈለግኩት” ብላ የኒኪን እርዳታ በሚሻ መልክ
እያየቻትም “ከእሱ ጋር ነገ ማታ በፎር ሲዝን ሆቴል የአደንዛዥ ዕፅ ሱስን
ማስቆም' በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የበጎ አድራጎት ፕሮግራም ላይ እንድገኝ
ስትጋብዘኝ መሄድ ያለብኝ ይመስለኛል።”
ኒኪ ይህንን ነገር ከአኔ ከሰማች በኋላ ውስጧን ሀዘን ተሰማት፡፡
ምክንያቱም በየዓመቱ ከሟች ባሏ ዶውግ ጋር በዚህ ፕሮግራም ላይ ይሳተፉ
ነበር።

“እና ከበፊት ባልሽ ጋር የፍቅር ቀጠሮ አለሻ?” ብላ ኒኪ ጠየቀቻት፡፡
“የፍቅር ቀጠሮማ አይደለም።”
“እና እንደሱ ካልሆነ ለምን ትሄጃለሽ?”
“በመሀከላችን ያለውን ነገር በጓደኝነት ልንቀይረው ስለፈለግኩኝ ነው።
ማለቴ ጓደኛሞች መሆናችንን ላሳየው፣ ያልተጣላንና አንዳችን ላንዳችን ቅርስ
እንደሆንን ነገር ግን በፍቅረኛነት መቀጠል እንደማንችል ላሳየው ስለፈለግኩኝ
ነው።” አለቻት፡፡
አኔ የምታወራው ነገር ሚዛን የሚደፋ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን በኒኪ
አእምሮ ወስጥ የሆነ መጥፎ ነገር ሊፈጠር የሚችል ዓይነት ስሜት
ስለተሰማት ምቾት አልሰጣትም፡፡
“የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን መደገፍ እኔና ሉዊስን የመንፈስ እርካታ
የሚሰጠን ነገር ነው፡፡ ባይገርምሽ እሱ ሜክሲኮ ውስጥ በአደንዛዥ ዕፅ
በሚደርሱ ጉዳቶች በጣም ይጨነቃል፡፡ ታስታውሺ ከሆነ
👍3