#የታካሚው_ማስታወሻ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)
ስራ አርፍጄ ገባሁ፡፡ ላለባበሴ ትኩረት መስጠት አቁሚያለሁ።ትንሽ እንደተቀመጥኩ ማሂ ቢሮዬ ገባች፡፡
“እንዴት ነህ?”
“አለሁ፡፡ ምን ልታዘዝ?”
“ማወራህ ጉዳይ አለኝ፡፡ ሻይ ቤት መሄድ እንችላለን?”
“የሚያገናኘን የቢሮ ጉዳይ መሰለኝ፣ እዛ አልሄድም፡፡የምታወሪው ካለሽ፣ እዚሁ ማውራት ትችያለሽ፡፡”
“የቢሮ ጉዳይ አይደለም፡፡ የእኔና ያንተ የግል ጉዳይ ነው።”
“ማለት?"
“ግንኙነታችንን ማቆም ማንችልበት ነገር ተፈጥሯል፡፡ ላወራህ ፈልጋለሁ፡፡” ምን ለማለት እንደፈለገች ገመትኩ፡፡ አዞረኝ። ለቅፅበት በውስጤ ያሰብኩትን እውነት አታድርገው ብዬ ፀለይኩ፡፡ ደሜ ቀዝቅዞ
በድን ስሆን ተሰማኝ፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ፣ ቀስ ብዬ ተነስቼ እንዳለችኝ ሻይ ቤት ሄድን፡፡ ፈንጠር ያለ ቦታ መርጬ ተቀመጥኩና፣
አረገዝኩ ልትዪኝ ባልሆነ...!” አልኳት እንደተቀመጥን፡፡
“አዎ ልልህ ነው፡፡ የወር አበባዬ ከመጣ ወር አልፎታል፡፡ አርግዣለሁ፡፡”
“ስለዚህ ያንተ ነው ልትዪኝ ነው?” ዐይኔ ጨለመብኝ::
“እና ከማን ሊሆን ይችላል? ምን ማለት ፈልገህ ነው? ቆይ ግን አንተ እኔን እንዴት ነው ምታስበኝ?” ተንጨረጨረች፡፡
“ቀስ በይ አትጩሂ! ይኸውልሽ ማሂ፣ አሁን ከማን ነው ሚለውን እንርሳው፣ ያንተ ነው ካልሽኝ ግን፣ እኔ በዚህ ሰዓት አባት
ለመሆን በአቅምም በስነ ልቦናም ዝግጁ አይደለሁም፡፡”
“ስለዚህ?” ብላ አፍጥጣ ተመለከተችኝ፡፡
“ሌላው ቢቀር ያለ አባት ፍቅር ሚያድግ ልጅ ለመውለድ ባታስቢው ይሻላል። አንድ ነገር ብታደርጊ ጥሩ ነው፡፡”
“ምን?! አንተ ሰው መሳይ ሰይጣን ምን አልከኝ? አላደርገውም፡፡አላደርገውም...! የነገርኩህም ሰው መስለኸኝ ነው እሺ፡፡ እንደዚህ አይነት ጭራቅ መሆንህን አላውኩም ነበር፡፡ አባትነትህ እንጦሮጦስ መግባት ይችላል፡፡” ተስፈንጥራ ተነስታ በተቀመጥኩበት ጥላኝ ሄደች፡፡
ወደ ቢሮዬ ተመለስኩ፡፡ በህይወቴ ምን እየሆነ እንዳለ ግራ ገባኝ፡፡ በራሴ ዝርክርክነት፣ አጥምደው እየተጫወቱብኝ ነው። እራሴን ጠላሁት፡፡ እንደዛ በላዬ ላይ ስትጫወት ከርማ፣ አሁን ደግሞ እንዲህ
ትለኛለች፡፡ እውነቷንም ቢሆን፣ ወደዚህች ትርጉም አልባ፣ ጭለማ አለም ሌላ ህይወት ለማምጣት በጭራሽ ምክንያት መሆን አልፈልግም፡፡
ተሰምቶኝ ማያውቅ ጥልቅ ብስጭትና ሃዘን ወረሰኝ፡፡ ቢሮዬን ቆልፌ ወጣሁ።
ወደ ቤት ገብቼ ስልኬን አጥፍቼ፣ ለቀናት ተሸሸግሁ፡፡ ማንንም ማግኘት አልፈልግም፡፡ ወደ ስራ መሄድ ሳስብ አስፈሪ ጭንቀት ይሰማኝ ጀመር። አሁን የሚሰሙኝ ስሜቶች፣ ከዚህ በፊት ስራ ልለቅ ስል የሚሰሙኝ ስሜቶች ናቸው፡፡ መሸሽ፣ መደበቅ፣ መሸሸግ፡፡ ከዚህ ቀደም
ያጠፋሁትን ላለመድገም፣ ለራሴ የገባሁትን ቃል ለመጠበቅ፣ በመከራ
ያገኘሁት ስራ ላለመልቀቅ፣ ስራዬን እንደምንም ለመቀጠል፣ ለቀናት
ከውስጤ ጋር ታገልኩ፡፡ ግን፣ አልሆነም፡፡ አልቻልኩም፡፡ ለአራተኛ ግዜ ስራዬን መልቀቅ ግድ ሆነብኝ፡፡ ቢሮ ሄጄ፣ ቁልፍና ንብረት ለማስረከብ ምትሆን እንጥፍጣፊ ትዕግስት አልነበረኝም፡፡ መልቀቂያ እንኳን
ሳልወስድ፣ ድንገት በብስጭት እንደወጣሁ ቀረሁ፡፡ ለካ ውስጤ፣
ሳይታወቀኝ ሞልቶ ነበር፡፡ እየጠጣሁ እብሰከሰካለሁ። እብከነከናለሁ።
ሁሌም እንደዛ ነበር፡፡ “ለምድን ነው ሁሌም እኔ ላይ እንዲህ ሚሆነው?
ለምንድን ነው ነገር ሚደራረብብኝ፣ በአንዴ ሚጨልምብኝ? ምን ብረገም
ነው?”
ህይወቴን ወደኋላ መለስ ብዬ መመልከት ጀመርኩ፣ ሁሉም ጥቁርና አድካሚ ሆኖ ታየኝ፡፡ በመውጣትና በመውረድ፣ በስቃይ ብቻ የተሞላ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ህይወት በአንዴ ላይ ታወጣኝና መልሳ ከአፈር
ትደባልቀኛለች፡፡ እንደዚህ አይነት ህይወት ሰለቸኝ፡፡ ታከተኝ፡፡ ቢበቃኝ
ይሻለኛል ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡አዕምሮዬ “ከዚህ እስስት ከሆነ ኑሮ ሞት በስንት ጣዕሙ' አለኝ፡፡ ያስፈራል፡፡ ያስጨንቃል፡፡ እንደዛ ማሰብ አልፈልግም፡፡ ማሰቤን ግን ማስቆም አልቻልኩም፡፡ አዕምሮዬ ደጋግሞ በማስረጃ ይሞግተኛል፡፡ መሞት መፍትሄ እንደሆነ ይነግረኛል፡፡ እራሴን
ስለማጥፋት ደጋግሜ አስባለሁ፡፡ ለቀናት ምን ማድረግ እንዳለብኝ አሰብኩ። ከዚህ ከተማ መውጣት፣ መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩ፡፡ ቢሾፍቱን እወዳታለሁ፡፡ የነፍሴ እስትንፋስ ገመድ እዛ የተቋጠረች እስኪመስለኝ ድረስ፡፡ ሲከፋኝም፣ ስደስትም ወደሷ እበራለሁ፡፡ የሀይቆቿ የማይረበሽ፣ የማይናወጥ ውሃ፣ ተረጋግቶ ያረጋጋኛል፡፡ ለግዜውም ተረጋግቼ
ለማስብ፣ ከጥቂት አስፈላጊ ካልኳቸው እቃዎች በስተቀር ያለኝን የቤት እቃ ባገኘሁት ዋጋ ሸጬ፣ ወደ ቢሾፍቱ ለመጓዝ ተነሳሁ፡፡
ከአዳማ ከተማ ወጥቼ ትንሽ እንደተጓዝኩ፣ መንዳት አቃተኝ፡፡
በአይኔ የሞላው እንባ እይታዬን ጋረደኝ፡፡ መኪናዋን ጠርዝ አስይዤ፣ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡ አዳማን ብቻ ሳይሆን ህይወትን ተሰናብቼ እየወጣሁ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ በዚህ ሰዓት እንዲህ እየሆንኩ እንዳለ ሊገምት የሚችል አንድም እንኳ ሰው እንደሌለ ሳስብ፣ ሆድ እቃዬ
እስኪበጠበጥ አለቀስኩኝ፡፡ በቁሜ ለራሴ ለሞተ ሰው እንደሚለቀስ ተንሰቀሰኩ፣ በቀብሩ ማንም እንዳልተገኘ ብቸኛ ሰው ለራሴ አነባሁ፡፡ሲወጣልኝ ተነስቼ ወደ ቢሾፍቱ ሄድኩኝ፡፡ ነገሮችን እስክወስን፣ ቤት መከራየት አልፈለኩም፡፡ መለስተኛ ሆቴል አልጋ ይዤ መቆየትን መረጥኩ፡፡ ሁሉ ነገር፣ ሰልችቶኛል፡፡ አስጠልቶኛል፡፡ ቤተሰቦቼንም ጨምሮ፡፡ አሁን እነ አሌክስንም ማግኘት አልፈልግም፡፡ ስለዚህ ሌላ መዋያ ዱከም ፈልጌ አገኘሁ፡፡ ደብረዘይት ማደሪያዬ ብቻ ሆነች፡፡ ማታ ማታ አብዝቼ እጠጣለሁ፡፡ ስሰክር በለሊት ነድቼ አዲስ አበባ ሄጄ
አጨፍር አድራለሁ። ሲነጋ እንዴት እዛ እንደመጣሁ እንኳ ትዝ እስከማይለኝ፡፡ አንዳንዴም፣ እራሴን መኪና ውስጥ አድሬ አገኘዋለሁ፡፡
አንድ ቀን በመኪና አደጋ ልሞት እንደምችል አስባለሁ፡፡ እሱማ እድል
ነው፣ እንደዛማ ከሆነ እግዜር ይወደኛል እላለሁ፡፡ እራሱን አጠፋ ከምባል፣ በመኪና አደጋ ሞተ መባል በስንት ጣዕሙ ብዬ አስባለሁ፡፡ የመጠጡ ብዛት ጨጓራዬን ነካው፡፡ ስጠጣ ያስመልሰኛል፡፡ ከሚሰማኝ አስጨናቂ ስሜት ለመውጣት ከመጠጣት ውጪ አማራጭ የለኝም፡፡
አላቆምኩትም፡፡ የመጠጥ አይነት እየቀያየርኩ እጠጣለሁ፡፡በየቀኑ ዱከም እየተመላለስኩ እየቃምኩ መንገደኛ ሃሳቦችን ሳስብ እውላለሁ። በምመለከተው ነገር ድንገት በሚመጡ ሃሳቦች እነጉዳለሁ፡፡ ይመለከተኛል፤ ይጠቅመኛል፤ ሳይል አዕምሮዬ ያገኘውን
ያላምጣል። አንዱን አነሳለሁ፤ እጥላለሁ። ሲመሽ እጠጣለሁ። ካደለኝ ክፍሌ ገብቼ እተኛለሁ፡፡ መሽቶ ይነጋል፤ ሌላ ቀን፡፡ አንዳንዴ፣ ለመኖር በሚደረግ ጥረት የሚፈጠር ግርግር ለቅፅበት ቀልቤን ያዝ ያደርገኝና ስለ ኑሮ አስባለሁ፡፡ ሰዎች ለመኖር ይወጣሉ፤ ይገባሉ፤ ይጭናሉ፤
ያወርዳሉ፤ ይመጣሉ፤ ይሄዳሉ፡፡ ይህ ግርግር አንዳንዴ እንደሰመመን ይታየኛል፡፡ነገሮች ላይ ትኩረቴ በጣም ቀንሷል፡፡ እያሰብኩ የነበረውን ሁሉ ቶሎ እረሳለሁ፡፡ ጭንቅላቴ በፍጥነት ወደ ተለመደው፣ አስጨናቂ ሀሳቦች ይመልሰኛል፡፡
ዱከም ቤተኛ እየሆንኩ ነው፡፡ ባለቤቷ ጠፋህ፣ አረፈድክ ማለት ጀምራለች፡፡
ስራ ለቅቄ እዚህ ከመጣሁ ሶስት ሳምንት ሆነኝ፡፡ ማታ ስጠጣ፣ ከነ አሌክስ ጋር እንገናኝ ጀመር፡፡ ስንጠጣ ጨዋታቸው፣ ዘፈኑ፣ ጭፈራው፣ ጭጋጋማ ህይወቴን የብርሃን ጭላንጭል ይፈነጥቅልኛል፣
ቅንጥብጣቢ ደሰታ፡፡ ሲነጋ ግን፣ የተለመደው ከፍተኛ ድብርት፣ ባዶነት፣
ተስፋ ቢስነት ቦታቸውን ይረከባሉ፡፡ ቀኑን እንደምንም አሳልፈውና ማታ እነ አሌክስን እየፈለኩ ድብርቴን እዋጋው ጀመር፡፡ አሌክስ ጨዋታ አዋቂ

👍4
#የታካሚው_ማስታወሻ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)
“አንተ ብቻ አይደለኸም፡፡ ብዙ ሰው እንደዛ ይመስለዋል፡፡እንደውም ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ የእንስሳት ዶክተር ጓደኛዬ
የገጠመውን ልንገራችሁ፤” አለን እየሳቀ፡፡
“እሺ ንገረን፡፡”
“የንሰሃ አባቱ ዶክተር ሲባል፣ የሰው ሃኪም እንደሆነ ይመስላቸው፡፡”
“እሺ፡፡
“እና ንሰሃ ሊገባ እርሳቸው ጋር ይሄድና፣ አባቴ ሃጥያት ሰርቻለሁ፤ ይፍቱኝ ልሎት ነው የመጣሁት፤' ይላቸዋል፡፡ እሳቸውም
'ልጄ፣ ሰው ሆኖ ሃጥያት ማይሰራ ማን አለ? እግዚአብሄርስ ንሰሃን የሰራልን ይህን አውቆ አይደል? በል ንገረኝ ልጄ እፈታሃለው፤ ይሉታል።
አባቴ የኔስ ትንሽ ከበድ ያለ ነው፡፡ ይላል እየተቅለሰለሰ፡፡
አዬ ልጄ፣ ለሰው እንጂ ከብዶ ሚታየው፣ ለእርሱ ምን ይሳነዋል፣ አትፍራ ንገረኝ ልጄ፧' ይሉታል፡፡
“አባቴ ይፍቱኝ፣ ከታካሚዬ ጋር ወሲብ ፈፅሚያለሁ።
'አይ ልጄ፣ እንዳንተ ያሉ ዶክተሮች ሁሉ ሚወድቁበት፣ሚያጋጥም ነውኮ፡፡ አይዞህ ልጄ፣ ንሰሃ እሰጥሃለው፡፡ እግዚአብሄር
ይቅር ባይ ነው ፤ " ሲሉት፣
አባቴ እኔ ግን የእንስሳት ዶክተር ነኝ፣ ታካሚዎቼ... ብሎ ሳይጨርስ ደንግጠው፣
በስመአብ ወወልድ... እያሉ ሲደግሙ፣ እሱም ደንግጦ ወጥቶ ከንስሃ አባቱ በዛው ተቆራርጦ ቀረ፡፡” ካ....ካ... በጣም ሲያስቀን አመሸን፡፡
እነ ሃብትሽ በህይወቴ የቀሩኝ እንጥፍጣፊ ቅመሞች ሆነዋል፡፡ስለ ስራው ሲያወራ፣ የዶሮ እርባታ ስራ ጥሩ እንደሆነና ቢሾፍቱ ለዛ ስራ የተመቸች እንደሆነች ሲያወራ ሰማሁት። አስጨናቂ ሃሳቦቼ የተወሰነ ረገብ ብለውልኛል፡፡ ስልኬን ብዙ ግዜ ክፍት ማድረግ ጀመሪያለሁ፡፡ ሳሚና ማሂ አልፎ አልፎ ይደውላሉ፡፡ ማሂ በአቋሟ
ፀንታለች፡፡ እኔም እንደዛው፡፡ ሳሚ ስለማርገዟ ሰምቶ፣ አስረግዘህ ጠፋህ
አይደል?' እያለ ይቀልዳል፡፡ እስቅና ስለ ሜሪ እጠይቀዋለሁ፡፡ አሁንም ከሼባው ጋር እንደሆነች፣ ኤፍሬም ቦርኮ መንገድ ላይ እንደወጣና እንዳየው፣ በግቢው ያለውን አዲስ ነገር እየሳቀ ያወራኛል።
#እንጥፍጣፊ_መሻቶች...
ያለኝ ገንዘብ አየመነመነ ነው፡፡ አንድ ነገር ካላደረኩ፣ ከዚህ በኋላ ከአንድ ወር በላይ መንቀሳቀሻ ገንዘብ አይኖረኝም፡፡መኪናዬን ለመሽጥ በውስጤ ዝግጅት እያደረኩ ነው፡፡ ለመሸጥ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ ስጠጣ አምሽቼ ተኛሁ፡፡ ከእንቅልፌ ስነቃ የተለየ ስሜት
እየተሰማኝ ነው፡፡ ደስ ሚል ስሜት፣ የፈነደቀ፣ የበራ ውስጠት እየተሰማኝ ነው፡፡ ከአልጋዬ እንደተነሳሁ፤
“ኋት ኤ ብራይት ዴይ ኢዝ ቱዴይ...?”
“ቱዴይ ኢዝ ሳተርዴይ...”
“ኢት ኢዝ ማይ ብርዝ ዴይ...።” ብዬ ሳላስበው ቅኔ ተቀኘሁ፡፡
ወይኔ... ዛሬ ልደቴ ነው እንዴ? እኔኮ አንዳንዴ ሳላስበው በልሳን ምናገረው ነገር አለ፡፡ ልደቴን አላውቀውም። ግን ማን ያውቃል፣ዛሬ ሊሆን ይችላል እኮ..፡፡ ቢያንስ አንድ ሶስት መቶ ስልሳ አምስተኛ
ትክክል የመሆን እድል አለኝ፡፡ ማክበር አለብኝ፡፡
ሻወሬን ወሰድኩኝ፣ ጺሜን ተለጫጨሁ፣ አፍተር ሼቭ፣ ሽቶ ተቀባባሁ። ድንገት እብደቴ እየተነሳ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ ከወራት በኋላ፣ ለመጀመሪ ግዜ ከውስጤ ሳልጠጣ ደስ ሚል ስሜት እየተሰማኝ ነው:: ፈገግ ልል፣ ልስቅ ልጫወት ነው:: እብደቴን አውቀዋለሁ። እወደዋለሁ።
እሱ ይሻለኛል። ዝለል፣ ዝላል፣ ፈንጥዝ፣ ፈንጥዝ ይለኛል። ህይወት የፈካች አበባ፣ ብሩህ ሆና ትታየኛለች፡፡ ቀላልና አጓጊ ያደርግልኛል። ለባብሼ ስጨርስ፣ ምሳ ደርሷል። ወጥቼ ለራሴ ምርጥ ክትፎ ጋበዘኩት።ከምሳ በኋላ መኪናዬን አስነስቼ ዝም ብዬ ነዳሁኝ፡፡ ወዴት፣ ለምን፣
እንደምሄድ አላውቅም፡፡ ብቻ ደስ ብሎኛል። ፍንትው፣ ብርት፣ እንዳልኩ
ሳላስበው እዛው ዱከም ደንበኛዬ ጋር እራሴን አገኘሁት። መሄጃ የለኝም
ገባሁ። ያልተለመደ፣ሞቅ ያለ ስላምታ ሰጠኋቸው። ደስ ሲለኝ መደበቅ
አልችልም:: ፊቴ ያሳብቃል።
“እንዴት ነሽ...? ሰላም ነዉ...?” አልኳት ባለቤቷን፡፡
“አለን፡፡ እንዴት ነህ አንተ? ግባ!።” የቤቱ ባለቤት ወደ ተለመደዉ ቦታዬ እየጠቆመችኝ፡፡
“ዛሬ እምሮብሃል። ፍክት ብርት ብለሃል። ምን ተገኘ?”
“ልደቴ ነው። ዛሬ ከበር መልስ ግብዣ በኔ ነው::”
“እንኳን ተወለድክልን። ልደትህ ከሆነማ፣ እኛ ነን መጋበዝ ያለብን።”
“አመሰግናለሁ። ግን፣ የደስታዬ ቀን ስለሆነ፣ ግብዣው በኔ ነው። ብቻ ዛሬ
ልዩ እንክብካቤ ያስፈልገኛለ፤” ብዬ ጥጌን ይዤ ተቀመጥኩ ብዙም ሳትቆይ ሚያስፈልገኝን ሁሉ አምጥታ
አስቀመጠችልኝ፡፡ ቤተኛ ሆኛለሁ። ሚያስፈልገኝን፣ ልኬን፣ ሁሉን
አውቃለች፡፡ ዛሬ እንደ ከዚህ ቀደሙ፣ ስልኬ ላይ አልተደፋሁም: መሄጃ
ስላጣው እንጂ መቃም ሳይሆን ሰው ነው ያማረኝ፡፡ ለሳምንታት ሰው አስጠልቶኝ ከሰው እንዳልሽሽው፣ ዛሬ ከሰው ማውራት፣ መቀለድና መሳቅ አማረኝ፡፡ ከእነርሱ ጋር እየተጫወትኩ፣ እየቀነጣጠብኩ መቃም ጀመርኩ፡፡ ትንሽ እንደቃምኩ፣ አንድ ጥቁር በጥቁር የለበሰች ረጅም፣ ቁመናዋ የተስተካከለ፣ ቆንጅዬ ልጅ ገባች፡፡ እንዳየኋት ዐይኖቼን
ተክዬባት ቀረሁ፡፡
መጀመሪያ እዚህ ቤት መምጣት የጀመርኩ ሰሞን፣ ባለቤትየዋ እዚህ ከሚመጡ ደንበኞቼ ለየት ትላለህ፤' ያለችኝ ትዝ አለኝ፡፡ ልጅቷ ፅድት ያለች ናት:: ውብና ማራኪ! እኔም እስከዛሬ እዚህ ቤት ሲመጡ ካየኋዋቸው ሴቶች ተለየችብኝ፡፡ ሳሎኑን ተሻግራ፣ በመጋረጃው ጀርባ
ወደ ውስጥ ገባች። ከቤቱ ባለቤት ጋር እንደጓደኛ ሰላም ተባብለው እየተሳሳቁ ያወራሉ፡፡ ቤተኛ ነች፤ ይተዋወቃሉ ማለት ነው? ግን ሲታዩ፣ ፍፁም በተለያየ ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች ይመስላሉ፡፡ባለቤትየው፣ ሱስ ያጎሳቆላት ከሲታና የወየበች ናት፡፡ ይቺ ደግሞ፣ የቆዳዋ ጥራት፣ በታይቷ ውስጥ የሚታየው የተመቸው ሰውነት፣ ሱስ ባለፈበት አልፋ
ምታውቅ አትመስልም። እንዴት ተዋወቁ? ምን አገናኝቸው? ጓደኛማ በፍፁም ሊሆኑ አይችልም:: ከወደ ጓዳ ውስጥ የሚስማውን እንቅስቃሴ እያዳመጥኩ ግንኙነታቸውን ለመገመት እሞክራለሁ፡፡
ትንሽ ቆይታ ልጅቷ መጋረጃውን ከፍታ ወጣች:: በኔ ተቃራኒ ከመጋረጃው ጠርዝ መጅሊስ ላይ ተቀመጠች። ባለቤትየዋ ሺሻ አምጥታ ለኮሰችላት። አሁንም ያወራሉ። ሺሻውን ተቀብላ ማጨስ
ጀመረች፡፡ አትመስልም። በፍፁም ሱስ ባለፈበት ያለፈች አትመስልም።
እንደማያት አንድታውቅ ፈልጌያለሁ። ዐይኔን ተክዬ ቀረሁ:: እጅግ ውብ
ነች፡፡ ፀጉሯ ሉጫነቱ እርዝመቱ፣ ስስ ከንፈሮቿ ከተቀባችዉ ሊፒስቲክ
ጋር እንጆሪ ይመስላሉ። ጉመጣት ጉመጣት የሚል ስሜት ተሰማኝ።
ወተት እንደጠጣች ድመት፣ የራሴን ከንፈር በምላሴ ላስኩት፡፡ የቀይ
ዳማ ናት፡፡ ጥቁር አይኖቿን ሰማያዊ አይ ሻዶው ተቀብታቸዋለች። አማላይ የውበት እመቤት ትመስላለች፡፡
“ከእርሷ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት.
ላፈር አይደለም ወይ የተፈጠርኩት...” የተባለላት ትመስላለች፡፡
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍3