አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አንድ የመስታወት ቁራጭ ከእንብርቷ በታች ሆዷ ላይ ተሸጦባት ነበር….ትንፋሿን ሳዳምጥ ትንሽ ትንሽ ብን ብን ይላል፡፡በደመነፍስ ስልኬን አውጥቼ ለአባዬ ደወልኩለት… ከዛ በኃላ የሆነውን እኔ አላውቅም….እራሴን ስቼ ቤት ክፍሌ ውስጥ ተዘግቶብኝ በሶስተኛው ቀን ነው የነቃሁት፡፡እና አውቄም ሆነ በድንገት አደጋ እናትሽን የገደልኳት እኔ ነኝ…ነገ ጥዋት ወደከተማ እንደተመለስን አሁን ለአንቺ የነገርኩሽን ጠቅላላ ቃሌን ሰጥቼ ፍርዴን እቀበላለው..በወላጆቼና በሌሎች ሰዎች ላይ የያዝሽውን ቂም ግን በቃ አዚህ ላይ አቁሚ፡፡››አለና በረጅሙ በመተንፈስ ወደኩርሲው ተመልሶ ተቀመጠ፡፡

አለም የጂኒዬርን ኑዛዜ በጥሞና ነው ያዳመጠችው….አንድም ቃል አላሳለፈችም…. እናቷ እንዴት እንደሞተች አሁን በግልፅ አውቃለች….ግን አሁንም ታሪኩ ሙሉ አልሆነላትም…‹‹በምንም አይነት ወንጀለኛውማ ጂኒዬር ብቻ አይሆንም››ስትል በውስጧ አሰበች…እሷ የሆነ ነገር ከማለቷ በፊት….እናቱ ሳራ በድንገት መናገር ጀመረች፡፡
‹‹ልጄ አንተ እንዲሁ ሰበብ ሆናብህ እንጂ ሰሎሜን የገደልካት አንተ አይደለህም››አለችው፡፡
‹‹እማዬ አሁን በቃሽ …ባበቃለት ጉዳይ ላይ ምንም ለውጥ ላታመጪ አትድከሚ››

‹‹አይደለም..ሰሎሜን የገደልናለት እኔና ስርጉት ተባብረን ነው.››

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8228😱23
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
‹‹ልጄ አንተ እንዲሁ ሰበብ ሆናብህ እንጂ ሰሎሜን የገደልካት አንተ አይደለህም››

‹‹እማዬ አሁን በቃሽ …ባበቃለት ጉዳይ ላይ ምንም ለውጥ ላታመጪ አትድከሚ››

‹‹አይደለም..ሰሎሜን የገደልናለት እኔና ስርጉት ተባብረን ነው.››ስርጉት በተቀመጠችበት ሆና አቃሰተች….ዳኛው መተንፈስ ከበዳቸው፡፡ሳራ ግን ለማናቸውም ግድ አልነበራትም..የእሷ ዋናው ትኩረት ልጇን ከእስር ማዳን ብቻ ነው..እና ንግግሯን ቀጠለች፡፡

‹‹.የዛን ቀን አንተ እኛን ወደቤታችን ከመሸኘትህ በፊት መጠጧ ውስጥ መድሀኒት ጨምረንባት ነበር..ከ30 ደቂቃ በኃላ እንደማሳበድ አድርጓት በአንድ ሰአት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚገድላት መድሀኒት ነበር፡፡እሷ  የተቀየረችብህና ከመስታወት ላይ ግንባሮሯን የከሰከሰችው በመድሀኒቱ ተጽዕኖ ነው…መስታወቱ ሆዷ ውስጥ ቢሻጥ እንኳን  አልሞተችም ነበር…አባትህ መጥቶ ሀኪም ቤት ሊወስዳት መኪናው ውስጥ አስገብቶ መንገድ ከጀመረች በኃላ ነው እስትንፋሷ የተቋረጠው…ያም የሆነው በተወጋችው ውግ ወይም በፈሰሳት ደም ሳይሆን በጠጣችው መርዝ ምክንያት ነው፡፡

‹‹እማዬ ይሄን እንዴት እሰከዛሬ ሳላውቅ…?አባዬ አንተ እንዲህ መሆኑን ታውቃለህ?››ሲል አባቱ ላይ አፈጠጠበት፡፡
አቀርቅሮ የነበረው አቶ ፍሰሀ በከፊል ቀና አለና ‹‹ከአንተ እና ከአለም በስተቀር ይሄንን ጉዳይ እዚህ ቤት ያለው ሁሉም ሰው ያውቃል፡፡››ሲል እውነቱን ፍርጥም ብሎ መለሰለት፡፡

‹‹ምን አረገቻችሁ ቆይ …?ምናችሁ ላይ ደረሰች?››አለም በእንባ ታጥባ እየነፈረቀች ሳራ ላይ አፈጠጠችባት፡፡

ሳራ እሷን ችላ ብላ ወደልጇ እየተመለከተች‹‹አንተን እንዳታገባህ እና ከስርህ እንድትርቅ ለአመታት ለመናት.. አስጠነቀቅናት፤ እሷ ግን ሌላ ሰው አግብታ ወልዳ እንኳን ልትተውህ አልቻለችም…የልጄ ህይወት በእንደዛ አይነት ሁኔታ ሲበላሽ ቆሜ ማየት አልቻልኩም፡፡እኔ ስርጉትን እንድታገባ ነበር ምፈልገው፣ከልቧ በጣም የሚታፈቅርህ ሰሎሜ ሳትሆን ስርጉት እንደሆነች በደምብ አውቃለው..››
ወዲያው ሳራ ንግግሯን እንዳገባደደች ኩማንደር ተቀበላት‹‹ያው እንግዲህ መጠኑ ይለያይ እንጂ በእናትሽ ግድያ ሁላችንን የየድርሻችንን ተወጥተናል…እኔ በእለቱ እስከእራት ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር አብሬቸው የቆየሁት…ከለሊቱ ዘጠንኝ ሰዓት ጋሽ ፍሰሀ ደወለልኝ.. ስመጣ
…እናትሽ ጋሼ መኪናው ውስጥ እጥፍጥፍ ብላና በደም ተበክላ ነበር…ጋሼ የሆነውን በአጭሩ አስረዳኝና የሚሆነውን እንዳደርግ ሀላፊነቱን ለእኔ ሰጠኝ ….ነገሩ ወደህግ ከሄደ ጁኒዬር፤ሳራም ሆነች ስርጉት ዘብጥያ መውረዳቸው አይቀርም …ምን ማድረግ እንዳለብኝ ሳስብ ያ ሊቁ የተባለው እብድ በዛ ውድቅት ለሊት እየለፈለፍ በእርባታ ድርጅቱ ፊት ለፊት ባለው መንገድ ሲያልፍ አየሁት..ወዲያው ሀሳብ ብልጭ አለልኝ..ሮጥኩና ይዤው ወደውስጥ ገባው..ከማታ እራት የተረፈ ምግብና መጠጥ ስለነበረ እሱን ሰጠሁትና ስለማደርገው ነገር መዘጋጀት ጀመርኩ..የምጠቀምበት እቃ ስፈልግ የእንስሳት ዶክተሩ የህክምና ቁሳቁስ የሚይዝበትን ሳጥን በረንዳ ላይ ተቀምጦ ነበር፤አይኔ ውስጥ ገባ፣ ቶሎ አልኩና ከፈትኩት ፡፡ የቀዶ ህክምን ሚገለገሉበትን ቢላዋ አገኘሁና .. በወቅቱ በጣም ተደናግጬ ስለነበረ የማደርገውን ሁሉ የማደርገው በደመነፍስ ነበር….እና ያው ልጅ እንደገደላት እንዲመስል አደረኩና ጥዋት ለፖሊስ ተደወለ.. በኃላ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተጓዙ ሳለ አያትሽ ልጄን የገደላት እብዱ ሳይሆን እነሱ ናቸው… የሚል ወሬ መንዛት እና
አቤቱታ ማሰማት ጀመሩ…ከዛ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሰዎች ዘንድ አንዳንድ ጥርጣሬዎች ብልጭ ማለት ጀመሩ..ሬሳው በደንብ ይመርመር የሚል ግሩፕ ተነሳ…ከዛ ከጋሼ ጋር ተማከርንና የሆስፒታሉ የሬሳ ማስቀመጫ ክፍል እሳት እንዲነሳና እሬሳውም እንዲቃጠል አደረግን..በስተመጨረሻም አያትሽን ይሄንን ሀገር ለቀው ካልሄዱ አንቺን ነጥቀን እስከወዲያኛው እንዳያገኙሽ እንደምናደርግ አስፈራርተናቸው ዝም እንዲሉና ከተማውንም ለቀው እንዲሄዱ አደረግን…እናም በተጨማሪ ስለእናትሽ አሟሟት ሊነግርሽ ነበረውን ሙስጠፋንም የገደልኩት እኔ ነኝ!!የዛን ቀን እኛ ሳናየው እዛ ተደብቆ እያንዳንዱን ነገር ሲያይ ነበር….ይሄን ሁሉ ነገር ግን ፍርድ ቤት ቀርቦ ያምንልኛል ብለሽ እንዳትጠብቂ…››ሲል ንግግሩን አገባደደ፡፡

አለም ደም በለበሱ አስፈሪ አይኖቾን ኩማንደሩ ላይ አፍጥጣ‹‹ቆይ ቆይ እስኪ…ልጁ የገደላት ለማስመሰል ከሞተች በኃላ በዛ የቀዶ ጥገና ቢላዋ ደጋግመህ ወጋሀት አይደል?
…?ከዛ ደሟ ሲንፎለፎል በእጅህ እየዘቅክ እዛ ሚስኪን ልጅ ልብስ ላይ አዳረስከው …እንዳዛ አይደል ያደረከው?በቁሟ እያለች በፍቅር ልብህን ስለሰበራች ልትበቀላት ታስብ ነበር፣ግን ለማድረግ ወኔ አልነበረህም..በዛን ወቅት ግን አጋጣሚው ተመቻቸልህ..ነፍሷ ውስጧ ባይኖርም ደጋግመህ ሰጋዋን በመበሳሳት ንዴትህን ተወጣህባት….ከዛ ሬሳዋ ለምርመራ ሆስፒታል ገባ ..አንዳንድ ጥርጣሬ የሚያስነሱ ነገሮች መፈጠር ሲጀምሩ እራሳችሁን ከማንኛውም አደጋ ጥርጣሬ ለመጠበቅ አስፈላጊ ስለነበረ ጋሼ ፍሰሀ ደግሞ የሆስፒታሉ የሆነ ክፍል በእሳት እንዲያያዝ እና ሬሳዋም እንዲቃጠል እና አመድ እንዲሆነ አደረገ..ከዛ አቶ ዳኛ በዚህ ወንጀል ውስጥ ልጁ ስላለችበት ይህንን ወንጀል እንዳይጋለጥ ባለህ ስልጣን ሁሉ ተጠቅመህ ፋይሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲዘጋ አደረክ…፡፡በትክክል ተረድቼችኋለው አይደል..?እንዲህ ነው ያደረጋችሁት?
‹‹ሁሉም በመሸማቀቅ አንገታቸውን አቀርቅረው ነበር የሚሰሟት‹‹እስከአሁን እንደሰማሁት ከሆነ እኮ ጁኒዬር ብቻ አይደለም ራሱን ለህግ አሳልፎ መስጠት ያለበት …ሁላችሁም ናችሁ..እና እኔ ዳኛ ብሆን በጣም ትንሹን ፍርድ የምፈርደው በእሱ ላይ ነው….እሱ ሳያስበው…በድንገተኛ አደጋ የፈጠረው ወንጀል ነው…ሌለቻችሁ ግን አስባችሁ እና አቅድ አውጥታችሁ ደግማችሁ ደጋግማችሁ እናቴን በነፍስም በስጋም አጥፍታችኃታል….እና ነገ ወደከተማ ስንመለስ ምን እንደምታደርጉ ለማየት በጣም ጎጉቼለው….፡፡››

‹‹መቼስ ሁላችንም ሳታጠፊን እንቅልፍ አይወስድሽም አይደል…?ደስ ይበልሽ ይሄው ተሳካልሽ››አሉ ዳኛው ቅስማቸው ስብርብር ብሎ፡፡

‹‹ደስ ይበልሽ !!….ጭራሽ ደስ ይበልሽ…?.ፍርድን በአደባባይ ሲሸጦት ያዛን ጊዜ ማሰብ ነበረቦት››

‹‹አይ መሬት ያለ ሰው….በእኔ ላይ የደረሰውን ወላጅ ስትሆኚ ነው የምታውቂው….ልጄን ከእስርና ከእንግልት ለማዳን ስል ነው እዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ የገባሁት››

‹‹አይ ልጆትን ከእስር ለማትረፍ ብቻ አይደለም….ከሶሌ ኢንተርፕራይዝም የ10 ፐርሰንት የአክሲዬን ድርሻ በልጆት ስም ማግኘት ችለዋል፡፡››

‹‹ይህ ፍፁም እውነት አይደለም…ያንን አክሲዬን የገዛሁት በራሴ ብር ነው….ከወላጆቼ በውርስ ያገኘሁትን ንብረት በጠቅላላ ሸጬ ነው የገዛሁት…ያንንም ፈልጌው ሳይሆን ኩማንደሩ እና ፍሰሀ አስገድደውኝ ነው፡፡በልጄ አስፈራርተውኝ ነው››

ዳኛው የሚናገሩትን ባለማመን ቀና አለችና ኩማንደሩ ላይ አፈጠጠችበት፡፡
‹‹አዎ..እውነቱን ነው፡፡ይሄንን ወንጀል ዛላለም በመሀከላችን እንደተቀበረ እንዲቆይ እርስ በርስ የበለጠ መተሳሰር አለብን ብለን አሰብን…ከዛ ከጁኒዬር እና ከሳራ ድርሻ ላይ ተቀንሶ በስርጉት ስም አክሲዬን እንዲገዙ አደረግን….ባይሆን እኔ ቀጥታ ጠይቄ ባይሆንም ከእናትሽ ሞት በኃላ የአክሲዬን ድርሻዬ ወደ30 ፐርሰንት እንዲያድግ ሆኗል….››
46👍5😱2
ጁኒዬር ከተቀመጠበት ተነሳ፣ ወደኩማንደሩ ቀረበና እየተንዘረዘረ ማውራት ጀመር‹‹ከዛ እኔ ጅሉን አባቷ የሰራሀውን ወንጀል እንዲደብቅልህ እና ወደእስር ቤት እንዳትገባ ልጁን ማግባትና መዛመድ አለብህ ብላችሁ አስፋፈራራችሁኝና..በሰሎሜ ሞት ከደረሰብኝ ሀዘን እንኳን በቅጡ ሳላገግም አግለብልባችሁ ስርጉትን እንዳገባት አደረጋችሁ››ብሎ አፈጠጠበት፡፡
ኩማንደሩ አንገቱን ከማቀርቀር ውጭ ምንም አልመለሰለትም፡፡

‹‹ምን አይነት ጅል ኖሬያለው…አባቴና የልብ ጓደኛዬ እድሜዬን ሙሉ እንደጅል ሲጫወቱብኝ የማላውቅ ሞኝ ››ተንሰቅስቆ አለቀሰ…እናትዬው ከተቀመጠችበት ተነሳችና አቅፋ እያባበለች ወደመቀመጫው መለሰችው፡፡

ከተወሰነ የውጥረት ዝምታ በኃላ‹‹አንድ የመጨረሻ ነገር አለ…››አለ አቶ ፍሰሀ፡፡ የሁሉም አይኖች ወደእሱ ዞረ..

‹‹ከዚህ በላይ ምን ቀረ? አለቀ እኮ… ለመስማት ሳልመው የነበረውን ነገር ሁሉ በዝርዝር አስረዳችሁኝ፡፡››

‹‹ይሄንን ለሁላችሁም ነው የምናገረው..ልጄ ጁኒዬር በዛን ቀን እናትህንና ስርጉትን ሸኝተህ ስትመጣ  ከሰሎሜ  ጋር  ስናወራ  እና  ስንጨቃጨቅ  የነበረው.  ልጄን  አታገቢውማ
..አገባዋለው በሚለው ጉዳይ አይደለም››

‹‹እና ታዲያ በምንድነው?››ጁኒዬር በመገረም ጠየቀ፡፡
‹‹ይሄንን እውነት ስነግራችሁ ሁላችሁም ከህይወታችሁ አንቅራችሁ እንደምትተፉኝ አውቃለው …ይሁን እንጂ በዚህ ለሊት እግዚያብሄር ሁለቴ ከሞት ደጃፍ አድርሶ የመለሰኝ እውነቱን ተናግሬ ንሰሀ እንድገባ ነው….ስለዚህ ነግራችኃላው…የሚያምም ቢሆን ስሙኝ፡፡አለም አንቺ የጎበና ልጅ አይደለሽም…››በቤቱ ሌላ ድንጋጤ..ተበተነ፡፡

‹‹ከዚህ በፊት ዲቃላ ነሽ አላችሁኝ ..አሁን ደግሞ ያንኑ ዲቃላነቴን ልትነጥቁኝ ነው?ይሄስ ምን ማለት ነው?››

‹‹ገመዶ ትዝ ይልህ እንደሆነ አንጃ እሷ በዛን ክረምት ለአንተም ሆነ ለማንም ሳትናገር ወደኮፈሌ ድንገት ብን ብላ ነው የሄደችው…ምክያቱም በማታውቀው ሰው ተደፍራ ነበር፡፡››

‹‹ምን? ማለት?››ዜናው ቤቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁሉ የሚያደነዝዝ ነበር፡፡

‹‹አዎ እኛ ቤት የጁኒዬር የ19 ዓመት የልደት በዓል ዝግጅት ነበር…ትልቅ ድግስ ነበር…ወጣቶች ሲጠጡና ሲጨፍሩ ውለው ሲጨፍሩ ነበር ያመሹት…..እሷ ቤታችን እቤቷ ስለሆነ ጓዲያ ጎድጓዳውን ታውቀዋለች…ለሊት ሰባት ሰዓት አካባቢ ሁኔታው እንዴት እንደሆነ እና የለማና አየጠፋ ነገር እንዳለ ለማየት ከመኝታ ቤቴ ወጣሁና ሳሎን ሄጂ ነገሮችን ተመልክቼ ስመለስ ከእንግዳ ክፍሎች መካከል አንዱን ገርበብ ብሎ ተከፍቷል
..የሆነ ነገር ትኩረቴን ሳበውና ተጠግቼ ገፋ ሳደርገው ተከፈተ፡፡ አልጋው ላይ ከላይ ሰሎሜ ተዘርራ ተኝታ ነበር…በጣም እንደሰከረች ከሁኔታዋ ማየት ይቻላል..ቀሚሷ ወደላይ ተገልቦ ጭኗ ክፉኛ ተጋልጧል…፡፡መልሼ በራፉን ዘጋሁና ወደመኝታ ቤቴ ሄድኩ .የዛን ጊዜ ሳራ ያማት ስለነበረ ለብቻዋ ነበር የምትተኛው፡፡ከዛ የተጋለጠ ጭኖ ከህሊናዬ ሊጠፋ አልቻለም…ስጋለበጥ ከቆየው በኃላ ተመልሼ ሄድኩና ሰው በኮሪደር ላይ አለመኖሩን አረጋግጬ ወደክፍሉ ገባው፣ ከውስጥ ቀረቀርኩት መብራቱን አጠፋው… ከዛ በኃላ
ያለውን ዝርዝሩል ልነግራችሁ አልችልም…ብቻ ማን እንደደፈራት ባታውቅም መደፈራን ግን አውቃ ስለነበረ በብስጭትና በእፍረት በማግስቱ ከተማውን ለቃ ወደኮፈሌ እንደሄደች ሰማው…በእውነቱ ከፊቴ ዞር ስላለች እፎይ ነበር ያልኩት….ከሁለት ነው ከሶስት ወር በኃላ መልሳ መጣች….አሁንም ትንሽ ቆይታ መሄዷን ሳማው..ከዛ ማርገዞን እና ልታገባ መሆኑን ተወራ…ቀኑ ተጠብቆ አንቺ ተወለድሽ ..ቀኑን እስልቼ ስቆጥረው ትክክል ነበር ..የእኔ ልጅ መሆንሽን ባውቅም ለማንም መናገር የምችለው ነገር አልነበረም፡፡የዛን ቀን ልጄ ቀለበት ሊያስርላት መሆኑን ሲነግረኝ ግድ እሷን ከዛ ጋብቻ ላስቆም ብዬ የልጅሽ አባት ጎባና እንዳልሆነ ታውቂያለሽ አይደል?››ስላት

‹‹እኔስ አዎ እናት ስለሆንኩ አውቃለው..አንተ እንዴት ልታውቅ ቻልክ?›› አለችኝ፡፡

‹‹እኔም አባት ስለሆንኩ ነው ላውቅ የቻልኩት ብዬ ታሪኩን በዝርዝር ስነግራት አበደች…በዛ እየተጨቃጨቅን እያለ ጁኒዬር ተመልሶ መጣ ..እንግዲህ ከጠጣችው መርዝ ጋር ከእኔ የሰማችው ዜና ምን ያህል አእምሮዋን እንደሚያስታት መገመት ቀላል ነው…እና እዚህ ዋናው ወንጀለኛ እኔ ነኝ…››

‹‹እና አንተ ..አባቴ…››አለም በተጎተተ ቃላት ከአደበቷ በግድ አወጣች፡፡

‹‹አዎ እኔ አባትሽ….ይሄንንም አሁን ወደእዚህ ከመጣሽ በኃላ በሚስጥር ሳታውቂ እኛ ቤት መጥተሸ የጠጣሽበትን ብርጭቆ በመውሰድ ዲኤንኤ በማሰራት አረጋግጬለው፡፡ እና…››ብሎ ሊቀጥል ሲል አለም ዥው ብላ በተቀመጠችበት እራሷን ስታ ወደኃላዋ ተዘረረች፡፡

‹‹ወይኔ ልጄን..አቶ ፍሰሀ ተስፈንጥሮ ስሯ ደርሶ ደገፋት….ጁኒዬር ተከተለው፡፡ገመዶ ግን ከአቶ ፍሰሀ በሰማው ነገር ደንዝዞ ሰውነቱ ሁሉ እየተንቀጠቀጠበት ነው…‹‹እጅህን ወደጎንህ ላክና ሽጉጥህን መዥረጥ አድርገህ ከአለም በስተቀር እዚህ ቤት ያሉትን ሀጥያተኞች ሁሉ ግንባር ግንባራቸውን በልና ከዛ ራስህንም ገላግለህ ለዚህች ሚስኪን ልጅ ፍትህ አስገኝላት›› የሚል ስሜት ይታናነቀው ነበር፡፡ወዲያው ከጎኑ የነበረችው ሳራ ልክ እንደአለም የሰማችውን ዜና መቋቋም አቅቷት እራሷን በመሳት ከመቀመጫዋ ተንሸራተተችና እላዩ ላይ ተዘረገፈችበት፡፡


ተፈፀመ

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
58👎27🤔11👍9🔥1
ካቲካላ የለም ፤ ከዛሬ ጀምሮ!
               ለምን?
        መለኪያ ተሰብሮ።
               ብለሽ
     ደሞ መሸጥ ቀጠልሽ
             ጥያቄ...
መለኪያሽ ነው እንጂ የተሰባበረው፣ ካቲካላሽማ... በርሜሉን ሙሉ ነው።

             ይሄንን ስትሰሚ
              እንዳትገረሚ።
     መኮመሪያ ቤትሽ መስፈሪያ የጣለ

ባገኘው ይለካል ያገኘውን ኹሉ ልኬት ነው እያለ፡፡
     እረ ያንቺስ እውነት ፣ ልኩን ያሳጣሽው፣
               በምን ለክተሽ ነው...
አንድ አረቄ እያሉ ፣ በርሜል የጨረሽው?
መለኪያሽን ዐየሽ ፣ ንቀሽው ተሰብሮ፤
  በዋጋ ያጣላል ፤ ልክ የሌለው ኑሮ።

              ለዋጋሽ መለኪያ፤
              ለስካር መለኪያ፤
ለማወቅ መለኪያ፤ ጠፍቶሽ እንዳሰምጪ፤
አረቄሽን ዘግተሽ ፣ መለኪያሽን አውጪ።

          ተይ በልክ ቅጂ
          ተይ በልክ ቅጂ
          ተይ በልክ ቅጂ...
ቀጥ ብለው እየገቡ ፣ ሲወጡ በዳዴ፣
በምን ሰጠሻቸው ፣ ሰከሩልሽ ባንዴ።

              የአረቄሽ ሞገስ.…
ሰው እየመሰለው ፣ ዐይኑ ደም ሲቀላ፣
ገዳም ናት ይልሻል ፤ ሰው ቤትሽ ሲሞላ።
  ገድሽ መለኪያሽ ነው! የተሰበረልሽ፤
አትሰሰትም ብሎ ፣ ሰው የሚያመጣልሽ።
ሀገሬው ሀገርሽ ፣ስስት ከመለካት ተደበላልቆበት፣
የሚለካን ኹሉ ስስታም የሚል ስም ወስዶ ለጠፈበት።

            ተይ በልክ ቅጂ
            ተይ በልክ ቅጂ...
ማይለካ አረቄ ፣ እያደልሽው በገፍ፣
ሀገር ሰከረልሽ ፤ በምኑ ይደገፍ?
            ተይ በልክ ቅጂ፣
ጤነኛውስ ይኹን ፤ እብድ አታስብጂ።
           ተይ በልክ ቅጂ!!!

🔘ኤልያስ ሽታሁን🔘
25👏2
#ማበድ_ይሻላል

አእምሮዋን ያማታል፤ ሃና ትባላለች።  በኮሮኮንቹ፣ በአቋራጭ፣ በድልድዩ በኩል አልፋ ቤታችን ትመጣለች፤ ስትመጣ ሰዓት አትመርጥም። የአቅሜን ለማንም ሳልናገር እንድትድን ጥሬያለሁ፤ አልተሳካልኝም እንጂ። መዳኗ በእኔ እንዲሆን አልተመረጠም ወይም ከነጭራሹ እንድትድን አልተፈቀደም።

አንዳንድ ቀን መጥታ በሩን በኃይል ስታንኳኳ ልጄ ከእንቅልፉ ይባንናል። በር የሚከፍት ሲጠፋ በጓሮ ያለውን መስኮት
በድንጋይ ስታንኳኳ መሰለኝ አራት ያህል ጊዜ ሰብራዋለች። በሃኒቾ አልናደድም፤ ይልቅ ይበልጥ ታሳዝነኛለች። ባለቤቴ ግን በእሷ ጉዳይ ሆደ ሰፊነቴ ይገርማታል።

አንድ ዕለት ከእኛ የተረፈ ምግብ ልትሰጣት ስትል ገላምጬ አዲስ ያልተነካካ ምግብ እንድትሰጣት ስነግራት፣ አገለማመጤ ከዚህ በፊት ያላየችው ዓይነት ስለነበር ቅሬታ ልቧ ውስጥ ለሳምንት ያህል ተቀርቅሮባት እንደነበርአስታውሳለሁ።

አንዳንዴ ትክ ብላ ስታየኝ "ሃኒቾ ደህና ነሽ?" ስላት አንገቷን በአዎንታ ትነቀንቃለች። አይኗ ያሳዝናል። አይኗ ሁሉ ነገሯን የሚናገርባት ፍጡር ናት፤ አይኗ ስሜቷን ማንጸባረቂያ መስታወቷ ነውና ሁሉን ከአይኗ አገኘዋለሁ። ሃኒቾን አይቻት ከራባት ቃል ባታወጣ እንኳ አውቃለሁ።

አንድም በልጅነቴ ረሃብን የታናሽ የወንድሜን ያህል በቅርበት ስለማውቀው የራበውን ሰው ትክ ብዬ ማየት አልችልም፤ አጎነብሳለሁ፤ ክፉ ትዝታዬን ይቀሰቅስብኛል። ክፉ ትውስታችንን የሚያስታውሰውን የአእምሮ ክፍል  በሆነ ጥበብ ማደንዝዝ ቢቻለን ብዬ አንዳንዴ እመኛለሁ።

ሁለተኛ ሃኒቾን አውቃታለሁና መራቧን አይቻት ባውቅ አይገርምም።

መንገድ ሳገኛት አሊያም ቤታችን ስትመጣ

"ደህና ነህ እዩ”

“ደህና ነኝ”

“አንቺ እንዴት ነሽ?” ስላት ጭንቅላቷን ደህና ነኝ ለማለት ትነቀንቃለች፤ ከዛ ውጪ ሌላ ምንም አትልም።

ባለቤቴ ሰፈሩን፣ ቤታችንን ጠላችው። በእሷ ጉዳይ ከእኔ ጋ ተያይዞ የሚነዛው ወሬ አወካት፤ በሌሊት እየመጣች እዩ ምግብ ስጠኝ የምትለው፤ በር የሚከፍት ሲጠፋ በጀርባ መስኮት የምትሰብረው ነገር ታከታትና ባልተለመደ ሁኔታ ልትቀና ይቃጣት ጀመር። ባመመው የቀና ሰው ካመመው ሰው በምን ይሻላል እላለሁ በልቤ። ከሚስቴ ጋር በሃኒቾ ጉዳይ ተጎረባበጥን፤ በር በኃይል ስታንኳኳ የልጄን መበርገግ መልመድ አልቻልንም።

አንድ ጠማማ ቀን

ድብርት እንደ ነጭናጫ ሕፃን ልጅ ሱሪዬን ይዞ ሙጭጭያለበትን ውሎ አሳልፌ ቤቴ ገባሁ። ልጄ ባለመተኛቱ መግባቴን እንዳየ አባ እያለ ደስታ ፊቱ ላይ ተጥለቀለቀ። አንድ ቀን እንደ ዘላለም በሆነበት የትግል መንደር ለመውደቅ ጥንጥ ቀርቶኝ እቤት ስደርስ አባ... አባ የሚለኝ የልጄ ቃል ነው እጅ የማያሰጠኝ። የልጄን ጉንጩን፣ ግንባሩን፣ አንገቱን፤ የሚስቴን ጉንጭ ስሜ እራት እንደማልበላ ለሚስቴ ነግሬ ወደ መኝታ በቴ ሳመራ ባለቤቴ ገጼን እያየች “ውሎ እንዴት ነበር?" ስትለኝ ማለት የቻልኩት አድካሚ ነበር ብቻ ነው።

David Darybyshire Bad Day

It's seems on some days

The whole world is against you You feel really down, in a haze
How long do have to feel blue

እንዲል... አንዳንድ ቀን ይደብራል። አውጥተን፣ አውርደን ያቀድነው ይከሽፋል፤ ተስፋ ያደረግነው ይዘምማል። ዕድለኛ ያልመሆን ስሜት ውስጣችን ይርመሰምሳል፤ ኋላ የመቅረት ስሜት ይላፋናል፤ በአጠቃላይ ዛሬ ጥሩ የሚባል ቀን አላሳለፍኩም።

ሹልክ ብዩ አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ በስንት መገላበጥ እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረገኝ፤ በሩ ከዚህ ቀደም ተደብድቦ ከሚያውቀው በላይ በኃይል ተደበደበ። ባንኜ፣ ተንደርድሬ

ሃኒቾ ነች፤ አመድማ፣ ግራ የገባው ፊት እንዳየሁ ፍንትው ብሎልኛል።

በሩን እንደከፈትኩት እያጉረጠረጥኩ ፊቴን አጠይፌ እ ምንድን ነው ሕይወቴን የምታከብጂው? እንዴ......!!!! ካለ እኔስ ሰው አታውቂም? ሁለተኛ እዚህ ቤት እንዳትመጪ..... አልኳት። የሌባ ጣቴን ፊቷ ላይ ደቅኜ እያውለበለብኩባት… ተናግርያለሁ!! እንዳልኩ አስታውሳለሁ።

ትክ ብላ አይታኝ በዝግታ አጎነበሰች። ቀና ብላ አየችኝ፤ ቀና ብላ ስታየኝ አይኖቿ እንባ አርግዘው ነበር። ቀስ ብላ አንገቷን ወደ መሬት ቀብራ፣ መሬት መሬት እያየች በዝግታ ትንሽ ወደፊት እንደተራመደች እሳት ለብሼ ፊቴን አጨፍግጌ ባለቤቴ ከኋላዬ እንደቆመች ዞራ ተመለከተችን አይኗ ያረገዘውን እንባ እያፈሰሰ ነበር።
አስተያየቷ፣ እንባዋ፣ አዟዟሯ ቢያሳዝነኝም ማዘኔን ፊት ነስቼ ፊቴን አዙሬ ወደ ቤቴ ገባሁ። ቀጥታ ወደ አልጋዬ ሄጄ ተመልሼ ተንጋለልኩ። እንደቅድሙ ማሸለብ አልቻልኩም እንጂ። እንባዋ፣ አስተያየቷ፣ አጎነባበሷ አንጀቴን በላው። አንሶላ ውስጥ ገብቼ እንደበደለ ሳይሆን እንደተበደለ፤ እንደጮኸ ሳይሆን እንደተጮኸበት፤ እንዳባረረ ሳይሆን እንደተባረረ ሆኜ አለቀስኩ።

ሃኒቾ ለእኔ ምን እንደሆነች የነበረንን ቁርኝትም የሰፈሩ ሰው ሁሉ በደንብ ያውቃል። ሚስቴ ይሄን  ስለምታውቅ ነው እንደልቧ የማትናገረው፤ ይሄን ስለምታውቅ ነው ሐዘኔታዬ ላይ ቅናት የሚጣባት።

ሃኒቾ ታሪኬ ናት። ዋናው ታሪኬ እሷ ጋ ነው ያለው፡፡ እጮኛሞቾች ነበርን። አንድ ሸበጥ ለሁለት አድርገናል፤ ቤተሰብ  አብሮነታችንን ጠልቶ ሊለያየን ሞክሮ አልሳካ ብሎት ያውቃል፤ በክፉ ካያት ጋ ለእሷ ተቆርቁሬ ተጣልቼላት አውቃለሁ፤ ጎድሎብኝ ሰርቃ ሞልታልኛለች፤ ለምና ተቀብላ ሰጥታኝ ታውቃለች፤ ኪሴ ኪሷ፣ ኪሷ ኪሴ ነበር።

ከእሷ የበለጠ ችስታ ስለነበርኩ ከእኔ በላይ እሷ ለእኔ ሆናልኛለች። ከሁሉ ሰው በላይ ስለምወዳት መንሰፍሰፌን በኩራት ነበር በየአጋጣሚው የምለፍፈው። እሷ ጋ ስሆን ቁጥብነቴ በስሱ ይተናል፤ ፍላጎት እና ገጠመኜን ከሌላው በተለየ እተነፍሳለሁ።

ትዝብት እና ፍርሃቴን አጋራታለሁ፤ እሷ ጋ ሆኜ ስደሰት ፈንጠዝያዬ ማንም እንደሌለ ዓይነት ነበር። ገመናዬን

ነግሬያታለሁ፤ ገመናዋን ነግራኛለች፤
ገበናችንን ተገላልጠናል፤ መተዋወቃችን ነው የሚያገማምተን። አንድ ዕለት አበሳጭታኝ ሁለተኛ አጠገቤ እንዳትደርሺ ስላት ፈገግ እያለች

“በኋላ ስታስሰኝ ትውላለህ“

“አታውቂኝም!!"

በእርግጥ እንዳለችው በቶሎ የዛኑ ቀን  አላሰስኳትም፤ ከሁለት ቀን በላይ ግን : መሻገር  አልተቻለኝም፤ ትዕቢት ተናነቀኝ። ፍቅሬ ከትዕቢቴ ስለሚበልጥ አይኔን በጨው አጥቤ አገኝቻታለሁ፤ ፍቅራችን አይናችን ውስጥ ይጮህ ነበር። እሷን ባለማግኘቴ ምክንያት ተጭኖኝ የነበረው ድብርት በነነ፤ ልትመጣ ስትል እንደመጣሁ መደበቅ አልተቻላትም::

ሃኒቾ ቶሎ ቶሎ ታኮርፍ ነበር፤ እኔ መኳረፍ ጭንቅ የሚለኝ ሰው ነኝ። መለማመጥ ስለማልወድ እንድታዋራኝ ቀልብ ገዝቶ ኩርፊያዋን ለማርገፍ ድራማ ፈጥሬ እተውናለሁ፤ ማኩረፏን ረስታ ቀልቧን ትሰጠኛለች፤ መቅደድ እንጀምራለን።

ደግሞ ትቀና ነበር፤ መቅናቷን በሁኔታዋ ነው የምትገልጸው፤ ትገባኛለች። ሳትጠይቀኝ የቀናችበት የመሰለኝን ጉዳይ አብራራላታለሁ፤ ቀስ ብላ ፍትት ትላለች፤ ፈገግ ስል

“ምን ያስቃሃል?" ትላለች።

ሰውነቷን ለልፊያ እያዘጋጀች የበለጠ አፌን ከፍቼ ስስቅ ትላፋኛለች፤ እላፋታለሁ።
ስስ ነበረች። እሷ በቶሎ ስለምትከፋ እኔም በትንሽ እንዳልከፋባት ይደብረዋል  የምትለውን ነገር ላለማድረግ ትጥራለች።

ትንሽ ነገር ይረብሻታል፤ ሲጨንቃት አቅፋታለሁ፤ እጄን ጸጉሯ ላይ እያንሸረሸርኩ ሁሉም ነገር ይስተካከላል፣ ከባድ አይደለም፤ ደግሞ አምላክ ይረዳናል እላታለሁ፤ እርጋታ ሲያጥለቀልቃት ይሰማኛል።
39👍5🔥2
እንደምትወደኝ ሁኔታዋ ሁሉ፤ እንደምትታመን እንቅስቃሴዋ ሁሉ፤ ከእኔ ጋ መሆን እንደምትፈልግ ሁሉ ነገሯ ያሳብቅባት ነበር!!!

ከነበር በኋላ ምን አለ?

ሃኒቾን የምወዳት በጠይም ቆንጆ ፊቷ አልነበረም፤ የተማረኩት በጥቁር ዞማ ጸጉሯም አልነበረም፤ ያሸነፈችኝ ; በየዋህነቷ ነው። ሃኒቾ ለመድመቅ አለመፍጨርጨሯ ነው። ተፈላጊነቷን ለማሳየት  አትዳክርም፤ ያላትን  ለማጉላት አትታከክም። ምንም የሌለውም ሰው እንደሚወደድ ያሳየችኝ ሃኒቾ ነበረች።

አንድ ቀን ስለ ውሎዋ ስትነግረኝ ትረካዋን ወደ ጎን ትቼ የተዘናፈለ ዞማ ጸጉሯ፣ እርጋታዋ፣ ወዛም ጠይም ፊቷ ላይ ተመስጬ ቆንጅዬ ልጅ እንደሆንሽ ታውቂያለሽ አይደል? ስላት

ዝም ብላ ፈገግ ብላ እያየችኝ ዝም ስትል

የምር አታውቂም?

“እመቤቴን አላውቅም" እመቤቴን ስትል አማማሏ፣ አይኗ ያሳዝናል


"ማልልኝ እስኪ ቆንጆ ነኝ ግን?"

እስቃለሁ። የዋህ ባትሆን ለቆንጆ ነሽ ማልልኝ ትል ነበር?

ሃኒቾ ማለት ይቺ ነበረች በቃ!!! እሷ እመቤቴን ካለች ስለማትዋሽ ሁሉም እንደዛ ነው የሚመስላት፡፡

የሁሉም መለኪያ የልቡ እውነት እና እምነቱ አይደል?

ሃኒቾ ዘመዶቿ ጋ ክፍለሀገር ስትሄድ፣ ስትመጣ፤ እኔም ክፍለሀገር የእናቴ እህት ማሚቱ ጋ ስሄድ ስመጣ አብሮነታችን እየሳሳ እየሳሳ ሌላ መልመድ ጀመርን። ሳንቆሳሰል፣ መራር ቃል ሳንነጋገር ተራራቅን። አብሮነታችን ሳስቶ በሂደት ተለያየን። ክፍለሀገር ለብዙ ጊዜ ኖሬ፣ ትዳርመስርቼ፣ ልጅ ኖሮኝ ተወልጄ ባደግኩባት ከተማ ተመልሼ ያከራየሁትን የቤተሰቦቼን ቤት አስለቅቄ መኖር ጀመርኩ።

ሃኒቾ አግብታ እንደነበር ነገር ግን ከብዙ ንትርክ፤ ከስንት ታርቆ መጣላት በኋላ፤ ከብዙ የጓደኞች፣ የዘመዶች፣ የሽማግሌዎች እና የቤተሰብ ምክር እና ሽምግልና በኋላ አብሮ መሆን አልሆን ብሏቸው እንደተፋቱ፤ ተቆጪዋ፣ መካሪዋ፣ ተቆርቋሪዋ ታላቅ ወንድሟ ሙሉጌታ ሲነዳው የነበረው አነስተኛ መኪና ከከባድ መኪና ጋ ተጋጭቶ ሕይወቱ እንዳለፈ፤ እናቷ እማማ ፀሐይ ታመው አልጋ ላይብዙ ጊዜ እንደማቀቁ፤ ካለመሰልቸት ብቻዋን ታግላ ማትረፍ ባትችልም እንዳስታመመቻቸው ከአብሮ አደጎቻችን ሰማሁ።

ሃኒቾ በሂደት ራሷን ማግለል፣ ብቻዋን መሆን፣ ራሷን አለመጠበቅ፣ ሥራ አለመሥራት፣ ብቻዋን ማውራት፣
ሲያናግሯት ምላሽ አለመስጠት፣ የተዘበራረቀ ነገር ማውራት መጀመሯንም ክፍለሀገር እያለሁ ሰምቼ ነበር።

ለመጀመሪያ ጊዜ ስንገናኝ፤ “እዩ ደህና ነህ?" ብላ እቅፍ አደረገችኝ፤ አስተቃቀፏ እንኳን መጣህልኝ ዓይነት ነበር። እንዳቀፍኳት ደህና ነኝ አንቺ ደህና ነሽ ስላት እንዳቀፈችኝ ቃል ሳታወጣ አንገቷን ነቀነቀች፤ የሆነችውን ሁሉ ብሰማም ባይኔ ስመለከታት ሰውነቴ ብርክ ያዘው...

ያቺ ፍንጣሪ ነጥብ የምታህል ቆሻሻ ልብሷ ላይ ሲያርፍ ደስ የማትሰኝ፣ ጽዳት፣ ማጠብ፣ ማስተካከል ዋነኛ መለያዋ
የነበረው ሃኒቾ ውሃ አይቷት የማያውቅ፣ የተረሳ፣ ሽበት ጣል ጣል ያለበት ጸጉር፤ ጉስቁል፣ ጥቁር ክስት ያለ ፊት፣
የመነቸከ ሽሮ ቀለም ቲሸርት፣ ብዙ እድፍ የተሸከመ ቀለሙ ይሄ ነው የማይባል ሰፊ ሱሪ ለብሳ ባዶ እግሯን አጠገቤ
ስትቆም፣ ስታቅፈኝ ከአጠገቤ ዞር እስክትል እንኳን እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም። ሁኔታዋ፣ ያሳለፍነው ትናንታችን፣
ሳቃችን፣ ገመናችን፣ መተሳሰባችን ሁሉ አንድ በአንድ ቅልብጭ ብሎ ታወሰኝ። ሕይወት እስኪያስጠላኝ ድረስ
ተደበትኩ… ሰው የመሆን ከንቱነቱ ተዳሰሰኝ!! አንዳንድ ስሜት እውነት ካልዳሰስነው አናውቀውም!!

አብሪያት መቆም ስላልቻልኩ ቻው እንገናኘለን ብዬ ጥያት ሄድኩ። አልሆነልኝም እንጂ የዚያን ሰሞን እንድትድን ያልገባሁበት አልነበረም።
በቀን ብዛት ሰውነቴ ለመዳት እና ሲያያት ማመጽም አቆመ።

ሃኒቾ ከሌሎችም ጋ በጣም ትንሽ ብታወራም፤ ከእኔ ጋ ሲሆን አንደበቷ አይታዘዝላትም መሰለኝ

“እዩ ምግብ ስጠኝ"

“እዩ ሳንቲም ስጠኝ"

"እዩ ደህና ነህ” በቀር ሌላ ቃል አትሰነዝረም።

ሃኒቾ አልፎ አልፎ ደህና ነህ ለማለት ብቻ፣ ወይም ሳንቲም ስጠኝ ለማለት ብቻ፣ ምግብ ስጠኝ ለማለት ብቻ ቤታችን ትመጣለች። ደህና ነህ ለማለት የመጣች ቀን ገንዘብም .. ምግብም ብሰጣት እሽ አትልም። በር ስታንኳኳ ከእኔ በቀር ማንም ይክፈት ማንም እዩ አለ? የመጀመሪያ ጥያቄዋ ነው።

ችግሩ በር ስታንኳኳ በኃይል ነው። እንኳን ሕፃን ልጅ ትልቅ ሰው ያስበረግጋል። በስንት መከራ ተባብሎ የተኛውን ልጄን በር በኃይል እያንኳኳች ታባንነዋለች። ቀስ ብለሽ አንኳኪ ብለን እኔም ሆነ ሚስቴ ያልገሰጽናት ጊዜ አልነበረም፤ ለግሰጻችን ምላሿ ፊቷን አመስክና ቅልስልስ እያለች በአይኗ መለመን ብቻ ነው።

ሚስቴ እሷ ስትመጣ ፈገግታዋ ይደበዝዛል።

ሰዓት እላፊ እየመጣች፤ በስንት እሹሩሩ የተኛውን ልጃችንን እያባነነች፤ ባለመኖራችን የበሩን ድብደባ ሰሚ ስታጣ የመስኮት መስታወት እየሰበረች አስመረረችን።

ያ ዱካካም ቀን ለእሷ የነበረኝን ሐዘኔታ አትንኖት እያጉረጠረጥኩ፣ እንዳትመጪ አልኳት። የመጣልኝን እየለደፍኩ

ሄደች።

ሃኒቾ የድሮው እዮብ በልቧ ስላልጠፋ፣ ተካፍለን የበላናት፣ ተበድረን የተካፈልናት፣ የሳቅነው፣ የተጨቃጨቅነው ከውስጧ ስላልጠፋ ልቧን የወጋሁት ያህል ማንባረቄ ያሳመማት ይመስለኛል። ሁሉም እንደሚያባርራት አባረርኳት፤ ሁሉም እንደሚማረርባት ተማረርኩባት።

ሃኒቾ ከቤቴ ቀረች።

መንገድ ላይ ሳገኛት አንገቷን ደፍታ ታልፈኛለች፡፡

በስሜት ተገፍተን የበደልነው ሰው አንገቱን ሲደፋ ከማየት በላይ ያለ ሕመም የትኛው ነው?

ክፋቴን ሁለመናዋ ላይ ተነቅሳው የምትዞር መሰለኝ። ክፉ እንደሆንን የሚመሰክሩብን ተንቀሳቃሽ ሥጋ ለባሽ፣ ተጨባጭ ምስክሮች እንደማየት ያለ ጥፋተኛ ስሜትን በገላችን ውስጥ የሚረጭ ሌላ ምን ዓይነት ክስተት ይኖርይሆን?

ለግንቦት ልደታ ዕለት የሰፈር ልጆች አብዲ ሱቅ ጎን ያለችው ሜዳ ጋ ተሰብስበው ቡና አስፈልተው በስፒከር  ሙዚቃ እያጫወቱ፣ እየጠጡ፣ እየተተራረቡ ሲዝናኑ ሃኒቾ ከሙዚቃውም ከቡናውም ትንሽ ነጠል ብላ ብቻዋን ጽዱ ሥር ለመቀመጫነት ከተቀመጠ ድንጋይ ላይ አይኗን ቡዝዝ አድርጋ ተቀምጣ ሳለች ቀስ እያልኩ አጠገቧ ደርሼ ሃኒቾዬ አልኳት። ሰማይ ላይ ቡዝዝ አድርጋ የተከለችውን አይኗን ወደ እኔ ስታዞር ሃኒቾ አጥፍቻለሁ ይቅርታ አድርጊልኝ ብዬ በአይኔም ጭምር  ለመንኳት። ሌላ ተጨማሪ ነውር
ላለመስማት ይሆን አላውቅም ብቻ የደበዘዘ ትዝብት ለበስ ደረቅ ፈገግታ አሳይታኝ በእርጋታ ተነስታ ሄደች፡፡

ብዙ ሰው ሲያባርራት፣ በር ሲዘጋባት፣ ውሃ ሲደፋበት፣ ሰላም ስትላቸው ሲዘጓት ምንም ያልመሰላት ልጅ የእኔ ሲሆን እንደዋዛ አልተወችውም። ምን አለ ብትሰድበኝ፤ ምን አለ ከአጠገቤ ሂድ ብላ ድንጋይ ለማንሳት ብትሞክር፤ ምን አለ ክፉ ቃል ተናግራ የሠራሁትን ብልግና ብታፈዘው፤ እሷ ጠቢብ ናት፣ ጠላቷን የምትበቀለው ከእብድ በማይጠበቅ ዝምታዋ ነው!!

ዝምታን የመሰለ መሣርያ አልባ መቅጫ ምን አለ?

የሆነ ቀን ጠጥታ፤ የሆነ ቀን እርቧት፤ የሆነ ቀን ልትሰድበኝ፤ የሆነ ቀን ሳንቲም ፈልጋ የምትመጣ መስሎኝ ጠበቅኋት። በራችን በኃይል ሲንኳኳ እሷ እየመሰለችኝ ስሮጥ በሩን እየከፈትኩ ጠበቅኋት። ደህና ነሽ ሃኒቾ ስላት አንገቷን ወደ ላይ እየነቀነቀች ደህና ነኝ እንድትለኝ፤ ሳገኛት አንገቷን እንዳትደፋ ጠበቅኋት፤ ካለ ቀጠሮ መጠበቅ አናዋዥ ነውና አናወዘኝ።
36👍7
ዳግመኛ ለማናገር፣ ይቅርታ ለመጠየቅ ፊቷ መቆም ብፈልግም ፈራኋት። ሳያት የሆነ ሰው በደሌን ተነቅሶ፣ ነውሬን የሚለፍፍ ዓይነት ድብርት ይዳበለኛል። በቀን ብዛት ይሄ ስሜት ድል ይነሳል ብልም አልሆነም። ሁሌም ሳያት የሚሰማኝ ስሜት ትኩስ ድብርት ነው። እኔ ከሚሰማኝ ስሜት እሷን ስበድላት የተሰማት እና ከሚሰማት አይበልጥም ብዬ መደበቴን ታገልኩት። አንዳንድ ቀን ያበድኩት እኔ የበደለችኝ እሷ ብትሆን እያልኩ እስክመኝ ድረስ እረፍት አጣሁ። ትግሌ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ከሃኒቾ ጋር የነበረኝን ትዝታ፣ የበደልኳትን በደል፣ ፊት መንሳቷን፣ ለማምለጥ እሷም ትዝታዋም  አይደርሱበትም ብዬ ወዳሰብኩት ቦታ ለሚስቴ አሳማኝ የሚመስል ሰበብ ደርድሬ ቤታችንን አከራይተን ያን ሰፈር ለቀን ሄድን።

በሽሽት የበዳይነት ሕመሜን ድል አደረገው ከሆነ አየዋለሁ!

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢3919👍1🔥1
አትሮኖስ pinned «#ማበድ_ይሻላል አእምሮዋን ያማታል፤ ሃና ትባላለች።  በኮሮኮንቹ፣ በአቋራጭ፣ በድልድዩ በኩል አልፋ ቤታችን ትመጣለች፤ ስትመጣ ሰዓት አትመርጥም። የአቅሜን ለማንም ሳልናገር እንድትድን ጥሬያለሁ፤ አልተሳካልኝም እንጂ። መዳኗ በእኔ እንዲሆን አልተመረጠም ወይም ከነጭራሹ እንድትድን አልተፈቀደም። አንዳንድ ቀን መጥታ በሩን በኃይል ስታንኳኳ ልጄ ከእንቅልፉ ይባንናል። በር የሚከፍት ሲጠፋ በጓሮ ያለውን መስኮት…»
#ውርስ_ሕይወት

አባቴ ለብዙ ዓመታት ታስሮ ነበር። አስራ አራት ዓመቴ አካባቢ ተፈታ፤ የተወለድኩት ያን ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፤ አባቴ ሲፈታ እኔም ተፈታሁ። አባቴ አስራ አራት ዓመት ድረስ ሳስብ የነበረውን ቀስ እያደረገ ዳመጠው።

አባቴ የላላ፣ የተቆጠበ ማኅበራዊ ግንኙነት ያለው፣ ረጋ፣ ጀንተል፣ ኮስተር ያለ ግለሰብ ነው። ብዙ ሰዓት ዝም ይላል፤ የስሜት መለዋወጥ አይታይበትም፤ ጺሙ በብዙ ሲያድግ በመቀስ በትንሹ ይከረክመዋል፤ ልብሶቹ፣ የሚጠቀምባቸው እቃዎች ስትር ያሉ ናቸው።

ከእስር እንደተፈታ እኖር ከነበረበት ከእናቴ ቤተሰቦች ቤት ወስዶ ተከራይቶ ከነበረው ሰፊ ግቢ ውስጥ መኖር ጀመርን።

ቤታችን ቅዝቅዝ ያለ ነው። ቅዝቅዝ ያለው ብዙ ወንድም እና እህት ስለሌለን ነው ወይስ እናት ስለሌለኝ ነው፣ አልያም ደግሞ አባቴ ከሰው ጋ በደማቁ ስለማይግባባ፤ ምክንያቱን እርግጠኛ ባልሆንም ውጤቱ ግን ቀዝቃዛ ሰፊ ትልቅ ግቢ ውስጥ ነው የኖርነው።

መቀዝቀዙ የገባኝ፣ በየአገጣሚ የትምርት ቤት ጓደኞቼ ጋ ቤታቸው ስሄድ ይሳሳቃሉ፣ ይጨቃጨቃሉ፣ ይካሰሳሉ፤ በዚህም እቀና ነበር። እጦታችን ያወቅነው ዕለት ጉድለት ይሰማን የለ?!

ስሜ ዋሲሁን ቢሆንም አባቴ ዋሴ ነው የሚለኝ፤ ምንም ነገር ሲያስደርገኝ ሆነ ሳደርግ አምኜበት እንዲሆን አድርጎ ሠርቶኛል። ከፍቶኝ ለምቦጬን ከዘረገፍኩ "ዋሴ ማኩረፍ የአቅመቢስነት ማሳያ ነው፤ መጀመርያ የከፋህን፣ ቅር ያለህን በእርጋታ አስረዳ" እያለ የውይይት ባሕል ልቤ ውስጥ እያኖረ ነው ያሳደገኝ።ያምንብኛል። እንደመታመን አበርቺ እጽ እንደሌለ ያወቅኩት ለራሴ ያለኝ በጎ እና የእችላለሁ ወኔ ከብዙ አቻዎቼ መለየቱን እና ምንጩን ስረዳ እና ሲገባኝ ነው።

በጨዋታ መሀል

“ይሄውልህ ዋሴ ሁልጊዜ እሮሮ የሚዘበዝቡ፣ ሁልጊዜ ሰው ማጣጣል ላይ የተመሰጡ ሰዎች፣ ሁልጊዜም አልተሳካልን ዓይነት ደረት የሚመቱ፤ ለውድቀታቸው ሰው የሚወቅሱ ሰዎች፣ ለመውደቃቸው ኃላፊነት ከማይወስዱ ጋ አትወዳጅ" ይላል።

ይሄ ሰውዬ ጓደኛ የሌለው ለውድቀታቸው ኃላፊነት የሚወስዱ አጥቶ ይሆን እላለሁ አንዳንዴ።

ደግሞ በሌላ ቀን እጅግ ብዙ ቆይቶ

“ዋሴ" ይላል። ልገልጸው የማልችለው አጠራር አለው። ሁሉም ሰው ዋሴ ብሎ ቢጠራኝም በእሱ ዓይነት መንገድ የሚጠራኝ ሰው አልገጠመኝም። የሆነ አለኝታዬ ዋስትናዬ የሚለኝ ነው የሚመስለኝ፤ እወድሃለሁ የሚለኝ በአጠራሩ ውስጥ ባለው ድምጸት በኩል ነው።

"ይሄውልህ ዋሴ ሰው አንተ ላይ ስለሚይዘው . አቋም እንዳትጨነቅ፤ ሰው ለማስደሰት ከዳከርክ የራስህ እውነት ሳይኖርህ ታልፋለህ" ይላል።

አባቴ ጥንቅቅ ያለ ሰውዬ ነው፤ ነፍስ እያወቅኩ ስሄድ ነው ለእሱ ያለኝ ፍቅር እና አክብሮት ያየለው።

ብዙ ዝም ስለሚል ሲያወራ ተስገብግቤ ነው የምሰማው፤ እጦትን የመሰለ ነገሮችን ተፈላጊ አድራጊ ያለ አይመስለኝም እኮ::

"ይሄውልህ ዋሴ"

ወዬ አባቴ

“ስንት ዓመት መቀመቅ ያወረደኝ ሐቀኝነቴ ነው፤ ኃላፊነቴን በአግባቡ ለመወጣት ስዳክር፤ ብልሹ ካልኩት አሠራር ጋ ስታገል፣ መደለያቸውን በጄ ስላላልኩ መቀመቅ ውስጥ ወረወሩኝ።

ብቻዬን ቆምኩ!

በእርግጥ እኔ ቆምኩ ልበል እንጂ ለብዙ ሰው ወድቄያለሁ፤ የወደቀ ከሚለው ጋ ማበር የሚፈልግ ማን አለ? ወደቀ ብለው ተዘባበቱብኝ፤ ስንት ዓመት ለመኖር ነው ግን እንዲህ የከፉት እላለሁ፤ ስለ ተቻለ ብቻ አሳማም ጅብም እንዴት ይኮናል?!

ይኸውልህ ዋሴ

ለእራስህ እውነተኛን መሆን የመሰለ የሕሊና እረፍት የለም፤ ከራስ ጋ ሰላም ከመሆን በላይ ምን ሽልማት አለ? ወድቋል ብለው ሲዘባበቱ እኔ ያልሠራሁት መጥፎ ተግባር ምቹ ትራስ ሆኖኝ ከሰላሜ ጋ ነበርኩ።

አንተ እንዲህ የምትወደኝ እኮ፣ አንተ እንዲህ የጎበዝክልኝ'ኮ ለእውነቴ የተሰጠኝ ሽልማት ነው፤ በዚህ ዕድሜ ጤነኛ የሆንኩት እኮ አምላክ ለመታመኔ የሰጠኝ ስጦታ ነው፤ ሰው ሽልማት ጥሬ ገንዘብ ብቻ ይመስለዋል" ይል'ና በስሱ እንደሁሌው ጥርሱን ገለጥ አድርጎ ፈገግ ይላል፤ አሳሳቁ ሞገስ አለው!!

“እኔን ያሳቀሉኝ እኮ በእስተርጅና የሚመታቸው ልጅ፣ የማይወዳቸው ልጅ ኖሯቸዋል፤ ያመኑት ክዷቸዋል፡፡

“እግዚሃር በሚደግሱት ዝክር የሚሸወድ መስሏቸዋል" እያለ አፉን በትንሹ ከፍቶ ጥርሱን እያሳየኝ ፈገግ ይላል።

አባቴ የሚለኝን ሁሉ እየሆነ ያሳየኝ መምህሬ ነው።

“ይኸውልህ ዋሴ ጥቃቅን ነገር ላይ አታተኩር፤ የምትኖርለት መርሕ ይኑርህ፤ እመቀመቅ ድረስ የምትሄድለት ሕልም እና መርሕ ይኑርህ።"

የሚኖርን እውነት ከመስማት በላይ ምን ሐሴት አለ??

ብቻዬን መቆም አስተምሮኝ፣ ጥቂት ቀን ታሞ ጥቂት ቀን አስታምሜው አለፈ። ብዙ ቆይቼ እስር ቤት ሳለ የጻፋቸውን ሐሳቦችን እና ገጠመኞቹን ሳነብ ከዕድሜዬ በላይ አበሰለኝ።

ሕይወቴ ላይ የብስለቱ ዳና ያረፈብኝ የአባቴ ልጅ እኔ ዋሴ ነኝ!!!

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
48👏18
አትሮኖስ pinned «#ውርስ_ሕይወት አባቴ ለብዙ ዓመታት ታስሮ ነበር። አስራ አራት ዓመቴ አካባቢ ተፈታ፤ የተወለድኩት ያን ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፤ አባቴ ሲፈታ እኔም ተፈታሁ። አባቴ አስራ አራት ዓመት ድረስ ሳስብ የነበረውን ቀስ እያደረገ ዳመጠው። አባቴ የላላ፣ የተቆጠበ ማኅበራዊ ግንኙነት ያለው፣ ረጋ፣ ጀንተል፣ ኮስተር ያለ ግለሰብ ነው። ብዙ ሰዓት ዝም ይላል፤ የስሜት መለዋወጥ አይታይበትም፤ ጺሙ በብዙ ሲያድግ በመቀስ…»
#ሊያብብ_ሲል

ሱስ ሳይበላው፣ ሲጋራ መግዣ መለመን ሳይጀምር፤ ጉስቁልና ሳያፈዘው፤ ለልብሱ መቆሸሽ ደንታ ቢስ ከመሆኑ በፊት፤ ሰዎችም ሲጣራ ባልሰማ መሄድ ሳይጀምሩ፤ ቃል አባይ ከመሆኑ በፊት፤ ክብሬ ማለት ሳያቆም፤ ለትንሽ ለትልቁ መላክ ሳይጀምር በፊት… ቆንጆ፣ ተወዳጅ፣ ዘናጭ ነበር። ከጓደኞቹ በላይ ድምቅ ያለ ልጅ ነበር፤ ቆንጆ አማርጦ ይሰክስ ነበር፤ የጸጉሩን ፍሪዝ በመሰታወት አስር ጊዜ እያየ አስር ጊዜ ያስተካክል ነበር።

ሕልመኛ ነበር። እንደ ሁሉም ወጣት ሀብታም መሆን፤ አዋቂ መሆን፤ ቤተሰቦቹን የመርዳት ሕልም ነበረው። የተንሸዋረረ አራድነት አሳስቶት የለኮሳት ሲጋራ፤ ለሳቅ ብሎ የተጎነጫት አረቄ፣ ለሙድ ብሎ የቀነጠሳት የጫት ቅጠል ስትደጋገም አፈዘዘችው፤ ሕልሙን ወጣትነቱን ክብሩን አረገፈችው።

ማንም ብርቱ ነኝ ቢል ታግሎ የማያስመልሳትን ወጣትነቱን ለማያቀው ጣዖት እየሰዋት ነው።

ጥግ ላይ ተቀምጦ ዘመን ሂዶ ዘመን ፤ በመጣ ቁጥር የሚመጡ ለውጦችን ከዳር በትዝብት እየተመለከተ ጊዜው እንዴት ነው የሚሮጠው? የሚል ይመስለኛል።

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
14👍5🔥3
#ባል_ተመኘሁ

አስተዳደጌ ነው የገደለኝ። አስተዳደጌ መጠበቅ እና ማግኘት ነበረበት። አባቴ ሁሌ ቃል ይገባልኛል፣ የሆነ ነገር በጥሩ መልኩ ሳደርግ ይሸልመኛል፣ እናቴ የቤት ሥራ ስሠራ ታመሰግነኛለች፣ ትመርቀኛለች። በምስጋና እና በስጦታ ተንበሽብሼ ነው ያደግኩት፤ ለዛ ነው የጠበቅኩትን ሳጣ የምታመመው ብዬ ሁላ አውቃለሁ፤ ግን በእሱ ብቻም አይደለም!

የማያቸው ሮማንቲክ ፊልሞች እና የማነባቸው መጻሕፍት ናቸው፤ ከፍቅር የሚገኘውን ደስታ እና ሁኔታ ከሚገባው በላይ አጋነው፣ ከቅዱስ የማገኘውን ነገር ሁሉ ያሳነሱብኝ ብዬም አምኜ አውቃለሁ።

ግን እሱ ብቻ አይደለም!

ቅዱስ ራሱ ነው ፍቅረኛሞች እያለን አባቴን መስሎ እና ሆኖ ተንከባክቦ ኑሮ ስንጀምር እርግፍ አድርጎ ትቶኝ የተፈላጊነት ስሜቴን የገደለው።

ኖ በእሱ ብቻም አይደለም!

ገመናዬን፣ ሚስጥሬን፣ ስሜቴን ለሰው ስለማልናገር ነው መፍትሔ ያጣሁት፤ የማይቀለኝ! የሚያብከነክነኝ!

ግን ዋናው ምክንያት ይሄም አይደለም!

ራሴን ከዋናው የሕመሜ ምክንያት፣ የድባቴዬን ምንጭ ለራሴ አልነግር ብዬ ነው።

ቅዱስ አይፈልገኝም። ሲመጣ ባዶ ቤት ቢቆየው ቅር አይለውም። ለስሜቴ ደንታ የለውም። ቆይ ስንት ወራቶች ሞላን ወሲብ እንኳን ከፈጸምን? አልጋ ከለየን ስንት ጊዜ ሆነን? ስንቴ ተዘገጃጅቼ ሊወጣ ሲል፣ ሲገባም ላነሳሳው በሚል አጋጣሚ አስመስዬ ራቁቴን የታየሁት፣ ቀስቃሽ አለባበስ ስንቴ ነው የለበስኩት?

እሱ ግን አያየኝም።

እንዲያዝንልኝ ታመምኩ፤ ኡኡ ነደድኩ፣ ጠዘጠዘኝ፣ ወጋኝ አልኩ፤ ታከሚ ይላል እንጂ አይደነግጥም። ወጣ ብሎ ስልክ ረጅም ሰዓት ያወራል።

መሀላችን ያለው ችግር ቀላል ነው ብዬ አስመሰልኩ... እውነቱ ግን እሱ አይወደኝም።

በመጨረሻ አልፈለግነት ሲጫወትብኝ፣ የድሮ ቦይፍሬንዴ ጋ ሄጄ ተልከሰከስኩ!

እሰይ!! እንኳን ተልከሰከስኩ።

ለሴት ልጅ የአለመፈለግነት ስሜት፣ ለዛውም በእንክብካቤ ላደገች፤ ለዛውም ተለማምጦ፣ ልዕልቴ ናት ብሎ ላገባት፣ ለዛውም መፈለግ እና መውደድ ለምታውቅ ሴት የሚሰማትን የሕመም ስሜት የት ያውቀዋል?!

የምን ጉዝጓዝ፣ ሰበብ፣ ድሪቶ፣ ዝባዝንኬ ነው?!

አለመፈለግ ብቻውን ቀላል ነው?!

ብቻውን ትዳርን መፍታት ብቻ አማራጭ አድርጎ ማሰብ ቀላል ነው?

ብቻውን ወሲብ ማድረግ መፈለግ እና ባል እያለ በፍትወት መቸንከር ቀላል ነው?

ብቻውን ላወራው እየፈለግኩ፣ ስደውልለት ሳያነሳልኝ ሲቀር አያከብረኝም፣ ከምንም አይቆጥረኝም ዓይነት ስሜትስ ቀላል ነው?!

ብቻውን እንዲህ እለዋለሁ ብዬ የሰበሰብኩትን ዓረፍተ ነገር፣ እንዲያዝንልኝ ያጠናሁትን ንግግር፣ እንዲታረቀኝ ያጠራቀምኩትን ቃላት፣ እንዲሳሳልኝ ያከማቸሁትን ሰበብ፣ እንዲረዳኝ የተዘጋጀሁበትን ቃል ፊት ነስቶ ሲያጠፋብኝ ስሜቱ ልብ አይሰብርም??!

ከድሮ ቦይፍሬንዴ ጋር ተንገብግበን፣ ተጠማጥመን ተዋሰብን። ቆንጆ ነኝ ወይ ስለው "ከድሮ በበለጠ” እያለኝ፤ ምኔን ትወድልኛለህ ስለው እያንዳንዱ አካሌን . እየሳመ እያሳየኝ። እየተዟዟርን፣ ቦታ እያማረጥን ተዋሰብን።

ደስስስ አለኝ!!

ለመለምኩ! እየጠወለግኩኝ ነበር።

ያደረግኩት ተግባር ለሌላው፣ ለመንገደኛው፣ ለመርሕ ሰው ሁሉ፣ ለጨዋው ሁሉ፣ ለአማኙ ሁሉ፣ ከዳር ሆኖ ላየኝ ሁሉ፣ ለፈራጅ ሁሉ፣ ለሌባው ሳይቀር ዝሙት ነው!.

ወሲብ ውስጥ ያለውን እፈልግሻለሁ፣ ታምሪያለሽ፣ እወድሻለሁ ሽንገላን መስማት ናፍቆኝ ነበር።

አመሰግንሃለሁ ብዬ አንገቱ ውስጥ ተወሽቄ ሳምኩት። ስለተኛኸኝ አመሰግናለሁ ይባላል? ትዳሬ ላይ ከባለግኩኝ በኋላ ማመስገን ነበረብኝ?

እኔ ግን አመሰገንኩት!

ተሰናብቼው ሳይመሽብኝ ወደ ቤቴ ፈጠን ፈጠን እያልኩ መሄድ ጀመርኩ፤ ቀስ እያልኩ ፍጥነቴን ቀነስኩ፤ እዛ ዱካክ፣ አልፈለግነት የሚበላኝ ቤት መሄድ ፈራሁ። የማይፈልገኝን ባሌን ማየት ሲዖልን የማየት ዓይነት ሆነብኝ፣ የማይናፍቀኝን፣ የማይንከባከበኝ ባሌ ያለበት ቤት መሄድ ጠላሁ፣ ወስልቼበት እንኳን ጸጸት ያልተሰማኝ ባሌ ጋ መሄድ አስጠላኝ።

ለመጀመርያ ጊዜ ልቤን ሰማሁት።

ከእኔ ካልሆነ ሰው ጋር እንድተኛ ያደረገኝ ሰውዬ ጋ ምን አደርጋለሁ??

መሳም እስክናፍቅ ድረስ የገፋኝን፣ መታቀፍን ብርቅ ያደረገብኝን፣ መወደድ እንደሚገባኝ ያሰረሳኝ ሰው ጋ ምን አደርጋለሁ?!

ምን አጠፋሁ? ይቅርታ ለማለት፣ ምን ላድርግልህ እንድለው ትንሽዬ እንኳን ፊት የማይሰጠኝ ሰው ጋ ለመኖር ለምን ወደኋላ ተመለስኩ።

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
37👍4😢1
አትሮኖስ pinned «#ባል_ተመኘሁ አስተዳደጌ ነው የገደለኝ። አስተዳደጌ መጠበቅ እና ማግኘት ነበረበት። አባቴ ሁሌ ቃል ይገባልኛል፣ የሆነ ነገር በጥሩ መልኩ ሳደርግ ይሸልመኛል፣ እናቴ የቤት ሥራ ስሠራ ታመሰግነኛለች፣ ትመርቀኛለች። በምስጋና እና በስጦታ ተንበሽብሼ ነው ያደግኩት፤ ለዛ ነው የጠበቅኩትን ሳጣ የምታመመው ብዬ ሁላ አውቃለሁ፤ ግን በእሱ ብቻም አይደለም! የማያቸው ሮማንቲክ ፊልሞች እና የማነባቸው መጻሕፍት ናቸው፤…»
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ
በሰላም፣በጤና አደረሳችሁ::

መልካም በአል ለመላው የ ክርስትና እምነት ተከታዮች የቻናሉ  ተከታታዮች በሙሉ ::
7👏1
#ምሶሶ_እና_ማገር

ሸክሜን ሳላስተያየው፣ ፍላጎቴን ቸል እያልኩ ከኔ በቀር ማን አለው ለምለው ቤተሰቤ ስል ፍላጎቴን አቀዝቅዤ መናገር የምፈለገውን ሁሉ ሳልናገር እንደ ጓደኞቼ ፋሽን ልከትል ሳልል ኑሮን ለማሸነፍ ስለምባትል ...

የቤታችን ምሶሶ እኔ ነኝ ባይ ነበረኩ!!

ድንገት እናቴ በአስር ቀን ሕመም ተለየችን። ቤታችን በፍጥነት ቀዘቀዘ።

እናታችን የአባቴን ስኳር፣ ደምብዛት እና ኮሌስትሮሉን ያማከለ ምግብ አቀናብራ አቅራቢ ነበረች። ተኝቶ ሳለ ከውጪ ሆነ ከቤት ውስጥ የሚረብሽ የመሰላት ድምጽ ከተተነፈሰ ቀስስ ቀስ ገረመው ተኝቷል ትላለች ድምጿን ለምልክት በቀረበ ማንሻካሾክ። አባታችንም እንዳይረበሽ ድምጽ ቀንስ ለምትለውም ሰው እንዳይቀየም እየተጨነቀች። አባታችን እናታችን ከሌለች ቤት ውስጥ ያገኘውን ሰው 'አልሚ የት ሄዳ ነው? በቃ አንዴ ከወጣች አትመለስም?' እያለ በስሱ ይነጫነጫል። ምቾቱ ሲሰወርበት ማን ዝም ይላል?

የታናሽ ወንድሜ ሱስ ያመጣበትን ግትልትል ብልግና የምትደበቅለት፣ የምትሸሽግለት፣ ብላ እንጂ ገንዘብ የለህ እንደው አንዱ ቦታ ገባ ብለህ የምትጎርስበት፤ እነዛ ጓደኞች እንደሆኑ ሊያጠጡህ ነው የሚፈልጉህ... ደግሞ ሰውነትህ እየቀነሰ ነው... ወይ እንደ ጎረምሳ ጎረስ ጎረስ አድርገህ አትበላ፣ በየትኛው አንጀትህ መጠጡን እንደምትችለው... እያለች ሳትሰለች ግሳጼ እና ምክር እያቀላቀለች ትኩረቷን የማትነግፈው፣  የምትቆረቆርለት፣ ከብልግናው መሀል መልካምነትን አነፍንፋ የምትመሰክርለት እሷ ብቻ ናት።

“ምዕራፌ እኛን እኛን እያልሽ ራስሽን አየበደልሽ እኮ ነው። ጸጉርሽን ተሰሪ እንጂ ደግሞ አማረልኝ እያልሽ ትጎምጂው እና ትጣይኛለሸ! ሴት ልጅ ጸጉሯ ነው ውበቷ..."

ውጪ ስትንገላታ ነው የምትውለው እያለች ታቀብጠኛለች፣ ትመክረኛለች፣ ገመናዬን ትሰማኛለች፣ ትገስጸኛለች፣ ጠዋት ማታ መግባት እና መውጣቴን፣ ሁኔታዬን፣” ገጼን፣ እንቅስሰቃሴን ትከታተላለች።

አደራህን ጌታዬ ከልጆቼ በፊት አድረገኝ፣ የልጅ ሐዘን አታሳየኝ፤ ከጓደኛ በታች አታውላቸው፣ ከክፉ ነገር ጋርዳቸው፤ ለኔ ያደረከውን ለማን አደረክ? ተመስገን፤ ተመስገን አያለች ስታጉተመትም ለሚሰማት ከአምላኳ ጋር የምታወራ አትመስልም፤ ከወዳጇ ጋር እንጂ!! በርግጥ ለታመነ ካምላክ በላይ ወዳጅ ማን አለ!

ምዕራፌ በርቺልን፣ ካላንቺ ማን አለን? አያለች መኖርያ ምክንያት ትለግሰኛለች። ለመመረቅ ሽራፊ. ምክንያት የምትፈልግ ይመስል ላደረኩት ትንሽ ነገር  ስትመርቀኝ ትውላለች።

ለውሻችን ቦቸራ እንኳን በሰዓቱ ምግብ የምትወረውርለት፤ አሞታል እንዴ? ፈዘዘሳ ብላ የምታስተውለው እናቴ ብቻ ናት።

ዘመዶቻችን እንዲመጡ ወትዋች፣ ጠፋችሁ ብላ ወቃሽ፤ ሲመጡ ተንከባካቢ፤ ካልበላችሁ፣ ካልጨመራችሁ፣ ካልቆያችሁ፣ ካላደራችሁ እያለች የምትለማመጥ፤ ሰፈራችን ውስጥ ለቅሶ ሲኖር፣ ሰርግ ሲሰረግ፣ ዝክር ሲዘከር ግንባር ቀደም አጋዥና አድማቂ እናታችን ናት። ለሚውል መዋል፣ ለደግ ደግ መሆን ስለማይከብድ ቤታችን ጉዳይ ሲኖር የሚያግዘን፣ ስንታመም የሚጠይቀን፣ መንገድ ላይ ሰላምተኛችን ብዙ ነው።

ስናጣት ልካችን ተገለጠልን!! እንዴት ይሄን ሁሉ ስትሸከም በዚህ መጠን  አላስተዋልኳትም? ተሸክሞ ሸክምን አለማሳየት ምን ዓይነት ጥበብ ነው?? እናቴን ያሳረፍኳት መስሎኝ ነበር፤ ለካ አሳርፋኝ ነው።

እናቴ ስንት ቀን ፍቅሯ እውነቷን ሲያስደብቃት፤ በድዬ ለእኔ ስታደላ አይቻታለሁ። ልጅ ሳለሁ በንዴት ከገረፈችኝ በኋላ ሲቃ እየተናነቀኝ ጉያዋ ስወሸቅ፣ ተንሰፍስፋ ያባበለችኝ ዕለት ትውስታ ልቤ ውስጥ አለ።

ድከመቴን የማታጎላብኝ፤ መውደዷ · የማይወላውል፣ እንደምወዳት ማስረጃ የማታስስ፤ ተዝረክርኬ ዝንጥ እንዳልኩ የምታሰማኝ፤ ሕመሜ የሚያማት፤ ስኬቴ ከሁሉ በላይ የሚያስፈነድቃት፣ ነገሬን ሁሉ ጉዳዬ ነው የምትል፤ እንደምወደድ እስትንፋሴ ዓለም ላይ ካረፈ ጀምሮ እያሳየች

የመሰከረችልኝ። እምወደድ እንደሆንኩ ልቤ ላይዐያሰረጸችልኝ፤ መወደድን የሚያክል ምንም በረከት እንደሌለ በምርቃት እና በጸሎቷ ያሰማችኝ።

ጥንካሬዋን ፈተና የማይበግረው፣ በደል ሆነ መከፋት የማይሽረሽረው፤ ትሕትና የተላበሰች፣ በየቀኑ ስለ ልጇ ከአምላኳ ጋ የምታወራ  አመስጋኝ፣ ስጉ : ፍጥረት : ናት። እስክንጠግብ የማይርባት፤ አሟት በድካም የምታሳብብ፤ እየረገመችን የምትጸልይልን፣ አንደበቷ ከእውነቷ ጋ የማይገጣጠም ድብቅ ፍጡር ናት። ፍላጎቷን አሽሻ፣ የምትፈልገውን አጣጥላ ለምንወድው ነገር ፍላጎቷን የሰዋች፣ ለልጆቿ ቸር፣ ለራሷ ስስታም ናት።

የልጇን ፊት እንደ ዳዊት ዘወትር የምታነብ፤  ስትናፍቅ፣ ስናረፍድ በስጋት የምትቃዥ እናት፤ የፍጡር ፍቅር ጥግ ናት።

ዋርካችን ሲገነደስ የከለለልን ገበና ገለጠን!

ሞቷ ከእንባ በላይ ነው። አልቅሼ ላውጣው ብል አይወጣም። አንዳንድ ጊዜ አጠገቤ ያለች ይመስለኛል፤ ባትመልስልኝም የልቤን እንዲህ እያልኩ አወራታለሁ።

ለምን የሚወዱሽ ሲያለቅሱ፣ ደረታቸው ሲደቁ፣ ጸጉራቸውን ሲነጩ ዝም ብዬ ፈዝዤ ተመለከትኳቸው?  አቅፈውኝ፣ አዝነውልኝ፣ እያለቀሱ ሲያባብሉኝ ለምን ደነዘዝኩኝ?
ግድ የለም አብሬሽ ሞቼ ነው የሚሆነው። አብሬሽ ሞቼ ባይሆን ድንኳኑ ውስጥ ወዳጅ አዝማድ ተስብስቦ ሲጨዋወት፣ ሲያጽናና እኔ ለምን ብቻዬን ዲዳ ሆንኩኝ?

አብሬሽ ሞቼ ባይሆን

የሚቀርበኝ ጉድሽ ፈላ እያለ ሲመለከተኝ፤ በርቺ አይዞሽ እያለ ማጽናኛ የቃላት ጋጋታ ሲያንጋጋ እንዴት በዚህ ሁሉ መሀል የእንባ ቋቴ አልተረታም? ከሩቅ፣ ከቅርብ ቀዬ ሐዘኔን በአካል ሊጋሩኝ መጥተው አይኔን እያዩ ሲያጨዋውቱኝ፤ ሊያበረቱኝ ሲታገሉ እንዴት ሆድ አይብሰኝም?

አብሬሽ ሞቼ ባይሆን

ቆሌ፣ ቅስሜ፣ ደመነፍሴ፣ ትውስታዬ፣ መጓጓቴ፣ ሕልሜ አብሮ ከአንቺ ጋ ባይቀበር እንዳሁኑ መች እሆን ነበር?

ከዚህ በኋላ አለመኖርሽ አንዴት አያባባኝም?

አንቺ ሞተሽ እኔ አብሬሽ ሞቼ ባይሆን አንድ ዘለላ እንባ እንዴት አልወጣኝም?

ይሁን ሁሉም... አብሬሽ ሞቼ ባይሆን ለምን ምሳዬ አይርበኝም? እንደሁሌው ውሃ ጥሜ ለምን አይታወቀኝም? ቆይ እሺ ለምን አትናፍቂኝም? አብሬሽ ሞቼ ባይሆን፣ ዋርካዬ ሲገነደስ እንዴት ዝም እላለሁ?

ነገሩ ምሰሶው ሲወድቅ ነው ማገር ማንነቱን የሚያውቀው።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
22😢16👍1
#አዎ_እሱ_ጋ_ያመኛል

ትንሽ ስትቀማምስ እና ሞቅ ሲላት “እኔ ጀብራሪት” ስለምትል የሰፈር ጎረምሶች እና ውሪ ሕፃናት ከመንገድ ሲያገኟት ትንሽ

ራቅ ብለጡ ጀብራሪት! ይሏታል

ካልጠጣች ምንም አትልም፤ ሞቅ ካላት ግን ቀኝ እጇን ወደላይ ሰቅላ መዳፏን ጨብጣ “እኔ ጀብራሪት የኩራባቸው ሚስት... የዛ ወንዳወንዱ... የዛ ምሁር!" ትላለች... አንገቷን ወደላይ እያሰገገች፣ አይኗን ፈጠጥ፣ እግሯን ራመድ እንደማድረግ  እያለች፣ ትከሻዋን ወደ ቀኝ እና ግራ እየወዘወዘች ትፎክራለች።

ጀብራሪት የሚሏት ጎረምሳ እና ውሪ ሕፃናት ይዝናናሉ፣ ይፈግጋሉ፤ ሌላው መንገድ ላይ ያላስፎከራት ጀብራሪት ሲላት ስትፎክር ቤቷ ትደርሳለች።

መጠጥ ካልቀማመሰች ትክዝ፣ ቁጥብ፣ ጭምት ማለት መገለጫዋ ነው። ጠይም ገጿ ቀልብ ሰጥቶ ለሚመለከታት እርጅናዋ እና ሐዘኗ ያላደበዘዘው በወጣትነቷ የነበረውን ቁንጅና ከመናገር አይሰንፍም።

አታቲ አክስቴ ናት፤ በልጅነቴ እናቴ ስትሞትብኝ ልታሳድገኝ አምጥታኝ እንደሆነ ተነግሮኛል። እናቴን ሆነ አባቴን አላስታውሳቸውም፤ የማውቀው አታቲዬን እና ጋሽዬን ነው።

የኔ ስም ዕድል ቢሆንም አታቲዬ ዕድሌ ትለኛለች። አንቺ ባትኖሪልኝ የምትለኝ ስለሚመስለኝ ደስ ይለኛል። ጡረታ ከመውጣቷ በፊት ገንዘብ ሚኒስቴር ነበር የምትሠራው፤ የድሮ አስራ ሁለተኛ ክፍል ምሩቅ ናት።

ኩራባቸው የሚባል ባል ነበራት፤ ስድስተኛ ክፍል እያለሁ ሞተብን። ስለ ገዳዮቹ እርግጡን የነገረን የለም። ወደ ቤት ሲመጣ እኛ ቤት መታጠፊያው አስፋልት ጋ ገድለው ጣሉት። ከየትምህር ቤት እየመጣሁ ሳለሁ  ግርግር፣ ጩኸት ተቀበለኝ ለማጣራት ሰው ወደ ተሰበሰበበት ስጠጋ አታትዬ
የወደቀ የኩራባቸው ሬሳ ላይ እየተንከባለለች ትጮኻለች። ሁኔታዋ እስከዛሬ ድረስ መጥፎ ትውስታዬ ውስጥ ተወሽቋል... ከዛ ጊዜ በኋላ ብዙ ደም ሳይ ያዞረኛል፣ እረበሻለሁ። ብዙ ሰው የከበበው፣ ሁካታ ነገር ስመለከት የኔ የሆነ ሰው ጉዳት ደርሶበት፣ ጎድተውት እየተለቀሰ ይመስለኛል። ብርክ ይይዘኛል። ከሰፈሬ፣ ካደግኩባት ከተማ እንኳን ብርቅ ሁካታ፣ የሰው ጋጋታ ክብ ሰርቶ ብመለከት ከመረበሽ ስሜት መላቀቅ አልተቻለኝም።

ማታ ዱዲ ብሎኝ፣ ሱቅ ልኮኝ፣ እራት ስንበላ አጉርሶኝ፣ አደግሽልኝ እያለ በእድገቴ እየፈገገ አምሽተን፤ ጠዋት ጎህ ሲቀድ ተነስተን ቁርሳችንን ተቋድሰን፤ የትምህርት ቤት ክፍያ ሰጥቶኝ፤ ግማሽ · መንገድ ትከሻዬ ላይ መዳፉን አንተርሶ ጥቂት መንገድ የሸኘኝ የእኔ ጋሼ ደም ለብሶና መሬት ላይ ተዘርግቶ የማየው ሰው ነው የሚለውን ነገር በምን መንገድ የልጅ ጭንቅላቴ እንዳመነ ባላውቅም፤ እንጃ ብቻ አፌን ከፍቼ፣ መሬት ላይ ተደፍቼ በደም የጨቀየውን ውሃ ሰማያዊ ሸሚዙን የሙጥኝ ይዤ ተንሰቀሰቅኩ።

ጋሼ ገዘፍ ያለ መካከለኛ ቁመት የነበረው፣ ጺማም ጸጉሩን የሚያጎፍር  አፍሮ ነው። በሽራፊ ሰከንድ ያየው ሰው እርጋታውን፣ የጺሙን ያህል መታየት የሚቻልበት ነበር። ቤታችን ኮርነር ጋ ያለው መጽሐፍ የተደረደረበት መደርደርያ ጋ ያለው ጠረጴዛ እና ወንበር ላይ ተቀምጦ ብዙ ጊዜ ያነባል፣ አንዳንዴ ይጽፋል፡፡

አታቲዬ ጋሺዬ ምንድን ነው የሚያጠናው? ይማራል እንዴ?

ፈገግ ትልና “ጋሼ እኮ ጸሐፊ ነው" ፊት ለፊት ከድርድር መጽሐፉ ጎን የተከማቸውን ጋዜጦች እየጠቆመች “እነዛ ጋዜጦች ላይ ይጽፋል፤ ያኛው ሦስተኛ ድርድር ላይ ለብቻቸው የተቀመጡት መጽሓፍት እኮ የእሱ መጽሓፍት ናቸው" ትለኛለች።

ያ ሁሉ!

“አራት ናቸው እኮ፤ ሦስት ሦስት ቅጂ ተደርጎ ስለተቀመጠ ነው"

ግን እኮ አንዱ ራሱ ወፍራም አይደል እንዴ?

ስስ የተሰሰተ የሚያበረታታ ፈገግታ በጠይም ፊቷ ላይአርብባ

“በእርግጥ አዎ”

“ግን መጻፍ እና ማንበብ ይገናኛል እንዴ?”

“በደንብ እንጂ! ጎበዝ አንባቢ ያልሆነ ጎበዝ ጸሐፊ አይሆንም፡፡ ምናብ ብቻውን ሩቅ አያራምድም፤ ቁንጽል ያደርጋል ይል ነበር የኔ ኩራባቸው”

ዝም ብዬ ያልሽው አልገባኝም፣ አብራሪልኝ ተማጽኖ በሚመስል ሳያት

"ይኼውልሽ ዕድሌ በምትሠሪው ሥራ ታዋቂ፣ ጎበዝ፣ ዝነኛ ለመሆን ሥራው ከሚያስፈልገው ትጋት በላይ ካልኖረሽ በሥራው ላይ ከተሰማሩት የበለጠ ማማ ላይ አትወጪም፤

በእርግጥ ያኔ የነገረችኝ የዛሬን ያህል እውነትነቱ ልቤ ውስጥ አልሰረጸም ነበር፡፡

ተመሳሳይ የቃል እና የሐሳብ ትርጉም በዘመን እና በሁኔታ ጥንካሬው እና ትርጉሙ ይለያይ የለ? አታቲ እና ጋሼ የሚዋደዱ፣ የሚከባበሩ እንደነበር ነፍስ ሳውቅ የበለጠ ተገልጦልኛል። ጋሼ አታቲዬን እንደ ትልቅ ልጁ ነበርየሚንከባከባት፤ እንደ እናት ስትሆን ቆይታ ከውጪ ፌስታል ይዞ ሲመጣ ፈንጠዝ እንደማለት ዓይነት ከተቀመጠችበት አልያ ከቆመችበት ተስፈንጥራ ፌስታሉን ትቀበለዋለች፤ እንደዛ ስትሆን ታላቅ እህቴ ነው የምትመስለኝ፡፡

ከውጪ ሲገባ ወይ ከውጪ ስትገባ ሁሌ ግንባሯን ይስማታል። አንዳንዴ ለእኔ ያኔ የማይገባኝን የጻፈውን በወፍራም ጎርናና ድምጹ በጣም ረጋ ብሎ ቴፑን ለስላሳ ሙዚቃ ከፍቶበት ያነብላታል፤ እኔ እንደማጠና መጽሐፌ ላይተደፍቼ ጆሮዬን ደቅኜ እሰማለሁ።

አታቲ ስትሰማው ትቆይ እና “ፓ አንተ እኮ ምድር ባትመጣ ታጎድላለህ!” ትለዋለች።

አንዳንዴ ደግሞ ሲያነብላት ታጨበጭባለች ወይም ታቅፈዋለች፤ አንብቦላት ያልተደመመችበትን ቀን አላስታውስም።

እጅግ አልፎ አልፎ ጽሁፉን ካነበበላት በኋላ ይሟገታሉ፤ በእርጋታ ይሰማት... ይሰማት እና ያብራራል፤ ትሰማዋለች። ሙግታቸው የጎበዝ አስተማሪ እና የጎበዝ ተማሪ ወይም ደግሞ "ሆነ የሚዋደዱ የታናሽ እና የታላቅ ዓይነት ነው። ያኔ
የሙግታቸው እና የውይይታቸው ኮንተንት  አይገባኝም ነበር፣ ሁኔታቸው ብቻ እንጂ። ከእነሱ ጋ መኖር ያስለመደኝ ነገር  ቢኖር ረጅም ሰዓት መስማት እና ያልገባኝን ነገር ለመረዳት ስል በትህትና መጠየቅን ነው።

አታቲዬ ጋሼ ከሞተብን በኋላ በቀስታ አረቄ ውስጥ መሸገች።

ትንሽ ቀማምሳ እቤት ትመጣና

“ዕድሌ” ትለኛለች ወይ አታቲዬ

“በጣም ጎበዝ፣ በጣም ተንከባካቢ፣ በጣም ጀግና እና ታታሪ እንዳታገቢ እሺ... ድንገት ካጣሺው ትዝታው እና እጦቱ አያራምድሽም”

እሺ አታቲዬ

“ዕድሌ…”

አቤት አታቲዬ

“ስታገቢ ተራ፣ ከሰው የተለየ . ጉብዝና ያላየው፣ የትም የሚገኝ፣ የትም ያለ፣ ከብዙ ሰው የማይለይ፣ መርሕ እና ግብ ያልታጨቀበት አግቢ እሺ፤ ብታጪው እንኳን ማንነትሽ አይናድም... እሺ ዕድሌ”

እሺ...እሺ...አታትዬ

አንድ ዕለት ፀሐይ አዘቅዝቃ ሳለች ንጋት ለምሽት እጅ ለመስጠት በእርጋታ ስትጣደፍ ቤታችን ደረስኩ ቤታችን በትንሹ ገርበብ እንዳለ ነበር፤ የሚያስገባኝን ያህል በቀስታ ገፍቼ ስገባ አታቲ ሽሮ ከለር ዕድሜ ጠገብ አጀንዳ እያነበበች በለሆሳስ ስታለቅስ ደረስኩባት፤ ቀስ ብላ ፊቷን በሌለሁበት አቅጣጫ አዙራ በሻርፕ እንባዋን እንደዳበሰች እንቅስቃሴዋ ነገሮኛል... እንዳላየሁ ሆኜ የኔ አታቲ ደህና ነሽ ስላት?

“ደህና ነኝ ዕድሌ” አለችኝ ምንም ስሜቷን የሚያውክ ሐዘን ውስጥ እንዳልነበረች ለማስመስል እየሞከረች።

ማበስ የማንችለውን እንባ፣ ምንጩን የማናደርቀውን ሐዘንን እንዳላዩ ከማየት በቀር የምንጋፈጥበት ምን አቅም አለን!? በድምጻችን ውስጥ እኔ አለሁልህ/ሽ ከማለት በቀር ምን እናደርጋለን? በሌላ ቀን ቤት በሌለችበት ዕለት ጠብቄ ስታነበው የነበረውን አጀንዳ በሦስተኛ ረድፍ አካፋይከተደረደረው መጽሐፍ ጀርባ ካለው ሁለተኛ ረድፍ ውስጥ ፈልጌ አገኘሁት፤ በሚያምር የጋሼ እጅ ጽሑፍ የተጻፈ ነበር፡፡

አጀንዳውን እንደዘበት ስከፍተው እንዲህ የሚል አገኘሁ...
22👍7
“ምድር ከሰጠችኝ ገጸ በረከት እሷ ዋነኛዋ ነች። ምድር ላይ መቆየት ካማረኝ የሚያምረኝ በእሷ ምክንያት ነው። የሕይወት ተጋድሎዬን ያህል ነው ትርጉም የምትሰጠኝ፤ በዚህ በዝባዥ ስርዓት፣ በእዚህ አምባገነን ስርዓት፤ ሕዝብ ከቁጥር በቀር ትርጉም በማይሰጠው ይህን በዝባዥ አገዛዝ እታገለው ዘንድ እሷ የምትሰጠኝ ተስፋ እና ፍቅር ግዙፍ ነው።

'Socialism እና Karl Marx' እንደማይነጣጠሉ ሁሉ የኖረኝ ክብር እና ዝና ከእሷ ከሚስቴ ጋር ሊነጣጠል እና ካለ እሷ የሚቻል አልነበረም። አይኔን አይታ የምትታዘዘኝ እና የምታዝንልኝ የእኩለ ሌሊት ብርሃኔ እሷ ናት።

እሷ ጠይም የደስታ መግቢያ በሬ ናት። እሷ ሳትኖረኝ ምንስ ቢኖረኝ ምን ያደርግልኛል? ስንት ቀን እሱን ያየ፤ ከእሱ ጋ የቆመ እንደሎጥ ሚስት የጨው ሐውልት ይሆናል ተብሎ ታውጆ እንኳን ምን ቢመጣ ካላንተ ስሆን ከሚሰማኝ አይበልጥም ብላ አብራኝ ነበረች፤ ስንቴስ መቀመቅ ሲያወርዱኝ ከእሷ በቀር ማን አብሮኝ ቆመ?

እሷ የነፍስ ምግብ ጸዳሌ ናት። ምንም ብሆን፤ ምንም ባጣ የማይደንቀኝ ልበ ደንዳና እንደሆንኩ ያለፍኩበት ጨለማ ይመሰክራል፤ እሷ ብቻ ከእኔ ጋ ትሁንልኝ እንጂ።

እሷ ከቀደመችብኝ ያን ዕለት ነው ኩራባቸው መንፈሱ የሚታወከው፤ እሷ ካለችማ ኩራባቸው ልቡ ላይ ሐሴት እንደተመላለሰ የተሰፈረለትን ዘመን ይጨርሳል ..

እሷ የልቤ ብርሃን ናት። ግፍን እቋቋም ዘንድ የተቸረችኝ ጫንቃዬ ናት፤ በንፅሕና ከእውነት ጋ እንድቆም፤ አቋሜ እንዳይሸረሸር፤  መንገዴን፣ አቋሜን  በፍቅር  ከመንገዴ እንዳልሰናከል በትልቁ አቅም ሆናኛለች።

በጠላት፣ በአሰናካይ፣ በቀለብተኛ ተከብቤ : ሳለሁ እንዳላፈገፍግ የምታበረታኝ የደስታዬ ፍላጽ መዓዙን የዓላማዬ ያህል ነው የምወዳት... ይላል። .

ሌላ ገጽ ገለጥኩ

'I will not quit until I make my dreams come true. tius. ኣ"ደምን እንደምን ድምጽ ለመሆን መጥቼ ዝም እላለሁ?

በዜጎች መሀል ግጭትን የሚቸረችር አገዛዝ፤ የማንነታችንን ግንብ የሚሸረሸር ትርክት  የሚያንሸረሽሩ ቀለብተኞች ባሉበት፤ ግፍ ባራኪ፣ ሞራል አልባ አሸከር፣ ፈሪ፣ መርሕ አልባ አለቅላቂ ልሒቃን በተሰባሰቡበት ምድር ተገኝቼ  እስክሞት ዝም አልልም። ደግሞስ ላለመሞት አልመጣሁ፣ ይግደሉኝ እንጂ መቼም እንደማልደለል እኔም፣ መዓዙም፣ እነሱም ያውቃሉ።

እኔ ኩራባቸው ዓለሙ አገር እንድታብብ ከማለም በቀር፤ መነሻ አልባ ትርክት ከማጋለጥ በቀር አንድም ስውር ሕልም እና ግብ ኖሮኝ እንደማያውቅ የልቤን እውነት የምታውቀው መዓዚ እና ሕያው አምላኬ ምስክር ነው እንጂማ ስንቴ በስልጣን ሊደልሉኝ ታከውኝ የለ! እንጂማ በጉቦ ሊጥሉኝስ አላሴሩም? እኔ ኩራባቸው ሳንቲም ግድ የሚሰጠኝ መስሏቸው… ሃሃሃሃሃ የሚታገሉትን ኩራባቸውን አያውቁትም ::

ሌላ ገጽ ገለጥኩ

“አንቺ ግዙፍ ሕልሜን የምታክይ፤ አይበገሬው ልቤን የበገርሽ፣ ኮስታራ ግንባሬን ገንብረሽ ለፈገግታ የራቀውን ፊቴን የምታፈኪ ሚስቴ ሆይ የሕይወት ዘመን ንዑዴ ነሽ። በትንሽ ቀልድ፣ በትንሽ ጨዋታ የምትደሰችልኝ፤ በወደኩበት
በታመምኩበት በታሰርኩበት ሰው ሁሉ ፈርቶ ከእኔ ሲርቅ፣ ከእኔ ጋ ላለመተያየት ሲደበቀኝ በኩራት ፈቅደሽ መርጠሽ ከእኔ ጋ የሆንሽ የእኔ መዓዚ ሕልሜን ልቤ ውስጥ ካስቀመጠው በረከቴ እኩል ባንቺም ተባርኬያለሁ። ባንቺ ምክንያት የምድር ቆይታዬ ከሕልሜ ያላስበለጥኩት የእኔን ያህል መርሄን ስለምትወጅልኝ መስሎኝ...

ጽሑፎቹ እንኳን ለጉዳዩ ባለቤት ለማንም መንገደኛ ትርጉም ይሰጣሉ፤ አጀንዳውን ከተቀመጠበት አኖርኩት፡፡

ጋሼ ታዋቂ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ፣ መንግሥት እንቅስቃሴውን የሚያጠናው፣ መንግሥትም ሆነ መንግሥት የሚቃወሙ አካላት በዛቻ እና በንዋይ ሊደልሉት እንደሚሞክሩ በርካታ ጸሐፊያን በማስረጃ ከትበው አንብቤያለሁ፡፡ እንዲህ እየወደዳት፣ እንዲህ እየተመካባት፣ እንዲህ እየተንሰፈሰፈላት ሲቀጭባት፣ ሜዳ ላይ ሲሞትባት የገዳዩን ማንነት ከመላምት በቀር ገላጭ ሲጠፋ አረቄ ውስጥ ባትደበቅ ከማዘን ውጪ ማጠንከሪያ አቅም እና ሞራል ከየት በኩል ይወለዳል?

ብዙ ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ ሰዎች ስለ ኩራባቸው ዓለሙ ቃለ መጠይቅ እንድትሰጥ ይለምኗታል። አንድም ቀን ግን እሽ ብላ አታውቅም። አንድ ዕለት ስለ ሌላ የባጥ የቆጡን እያወራሁ ሳለ ...

እኔ የምልሽ አታቲ ለምንድን ነው ግን ስለ ጋሼ ምስክርነት፣ እውነት እና የሕይወት ዘመን እንቅስቃሴው የማትናገሪው? ካንቺ በቀርስ ስለሱ ሊያወራ የሚችል ማን ይኖራል? አልኳት...

አታቲ አይኗን ቦዘዝ አድርጋ ጠረጴዛው ላይ ከተቀመጠው ትልቅ ጉርድ ፎቶ ላይ በትካዜ ተክላ

“ይሄውልሽ ዕድሌ ኩራባቸው ምስክርነት አያስፈልገውም። የራሱን ሐውልት ገንብቶ ነው ያለፈው፤ ስለ እሱ ከሥራዎቹ በላይ መናገር የሚቻለው አንድም የለም። ሥራዎቹን መመርመር እና ሥራዎቹን መሞገት ይችላሉ፤ ሕልሙን ጽፎ
አቋሙን ተንትኖ ታግሎ የተሰዋ ሕያው ነው፡፡ ከጻፈው ውጭ የምናገረው፣ ማለት ፈልጎ ያላለው አንድም እውነት የለውም። ከእኔ ጋ ያሳለፍነውን በየሜዳው፣ በየስፍራው ለማንም አላወራም፤ ይነፍስበታል፣ ይቀልብኛል፤ ቀስ እያልኩ እየተረኩ እያዋዛው፣ እያስታወስኩ ራሴ ጋ የማስቀምጠው የሕይወት ዶሴዬ ነው..."

አታቲ ትንሽ ስትቀማምስ ጀግና እንዳላገባ የምትመክረኝ ምክሯ አልሠራም። ከቢልልኝ ጋ ተፋቀርን፤ ቢልልኝ እውነት፣ ከስሜትም፣  ከፍቅርም ይበልጣል የሚል የዘመኑ የማይናወጥ ጀግና ነው።

አታቲ ሞቅ ባላት ቁጥር “ጀግና እንዳትወጂ” ብትለኝም ልቤ ግን ጀግና፣ ባለ ራዕይ፣ ትጉህ እያየ ስላደገ ጀግና ከማፍቀር የታደገው የለም።

ቢልልኝ ኩራባቸው ዓለሙ አሳዳጊ አባቴ እንደሆነ ሲያውቅ የተሰማው ሐሴት ልዩ ነበር። የሰው ማንነት፣ እውነት የተወሸቀው እያየ ባደገው የተበጃጀ ፍጡር ነው ስለሚል የደስታው ምክንያት አልጠፋኝም።

ቢልልኝን አንድ አርብ ዕለት አመሻሽ ላይ ከአታቲ ጋር አስተዋወቅኳቸው። በጋራ እየተጫወትን ሳለ ጨዋታችን ሀገር፤ ትግል፤ እውነት፤ ታሪክ ሆነ። አታቲ የቢልልኝ ሐተታ ምቾት የሰጣት አልመሰለኝም። ስትሰማው ቆየች እና ተቆርቆሪነትህ እና አቋምህ ዋጋ እንደሚያስከፍል ታውቃለህ አይደል? አለችው በፍጹም እናትነት በስስት እያየችው።

ቢልልኝ ትንሽ ዝም ካለ በኋላ እኔ እንደምጠራት “አታቲ" አላት ፊቷ ሐዘን እንደተላበሰ በቀጥልልኝ ዓይነት አየችው
"ክብር አይደለምን ለሚያማኑበት ጉዳይ ዋጋ መክፈል?” ኣላት። ትክዝ ብላ እኔንም እሱንም አፈራርቃ ካየችን በኋላ አቅም አልባነት ፊት እያሳየችን መርዶ እንደሰማ ሰው በእንባ ታጅባ “አዬ መረገሜ” አለች፡፡

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
40
#እንባ_አዳሽ_ነፍሶች

አብረውኝ ከሚሰሩት ለየት ይልብኛል፤ ግሬይ፣ አመድማ፣ ሽሮ ከለር ልብሶች ያዘወትራል። አይዘንጥም፣ ጸጉሩን ስለማይንከባከብ የብርድልብስ ብናኝ በተለይ ጠዋት ላይ ከጸጉሩ አይጠፋም። ጺሙን በቶሎ አያነሳውም፣ ከሰው ጋ አይተራረብም፣ ሰው ሲተረብም አይስቅም። ፖለቲካ ይከታተላል፣ አንባቢ ነው፤ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅን ይወደዋል፤ ጆን ሎክን ይተነትናል፤ አረቄ ነፍሱ ነው።

አንዳንድ ጠዋት የተመሳቀለ ፊት ይዞ ይመጣል። ፊቱ አልኮል ያመሳቀለው ይመስለኛል። ስለ ራሱ አያብራራም፣ ሰው እሱ ላይ ሰለሚይዘው አቋም አይጨንቀውም።

የሚረዳው የለም ብዬ ዋስ ጠበቃ ለመሆን እጋጋጣለሁ፣ ግን ነገሮችን ስለሚመረምር ለራሱ አያንስም።

ሲያወራ፣ ሲሰማ፣ ሐሳብ ሲሰጥ ጥድፍ ጥድፍ አይልም። የዋዛ አንቅስቃሴዎቹ ላይ እንኳን እመለከታለሁ። አስተውሎትን

ሰኞ ዕለት ያሳደገው፣ ያስተማረው አንድ ወንድሙ በመኪና አደጋ ሞተበት። የቢሮ ሰዎች ተሰባስበን ቀብር ላይ ተገኘን። ብሩክ ፍልስፍናው፣ መጀናተሉ ቀሰስ ማለቱ ከእሱ በኖ ጠፋ። መሬት እየተንከባለለ ሲያለቅስ ሳየው አንጀቴ ተንሰፈሰፈ። እንባዬ አካላቴን ሳላወናጭፍ፣ ድምጽ ሳላወጣ ወለል እያለ ወረደ። ብሩክ አቅም አልባነት ሲያጥመለምለው፣ ለብዙ ሰው አለኝታ የነበረውም ወንድሙ ተጀቡኖ ወደ ጉድጎድ ሲወረወር ከንቱነት በላኝ።

በነጋታው ጠዋት ከእነ ዱካኬ ከእንቅልፌ ነቃሁ። ተጣጥቤ፣ ቁርሴን በልቼ ከሥራ መልስ ብሩክ ጋ ለመሄድ ጥቁር ሻርፔን ቦርሳዬ ውስጥ ከትቼ ወደ ቢሮዬ ሄድኩ።

አይኔን አላመንኩትም፤ ብሩክ ወንበሩ ላይ ፋይል ከምሮ አንገቱን ደፍቶ ይሠራል። ሳየው ደነገጥኩ፤ በደመ ነፍሴ ብሩኬ ስለው ኮስተር እንዳለ በማያቀርብ አስተያየት እያየኝ "ሰላም ሊዲያ” አለኝ።

ሁላችንንም ፊት ነሳን። በሌሊት ሥራ ይገባል፣ አምሽቶ ይወጣል፣ ምሳ ብቻውን ይበላል። አይኑ አባብጦ እንባ ያሸበረው ፊት አይበታለሁ፤ ማንም እንዳያጽናናው መንገዱን ዘጋጋው። አለቃችን እንኳን በረታህ ብሎ ሲጀምር አዎ ይልና ከአጠገቡ እብስ ይላል፣ ወይ ደግሞ ወሬ ይቀይራል።

ወንድሙ ካለፈ በአስራ አራተኛው ቀን ላይ ብሩኬ ደህና ነህ? ግን ምነው እራቅከኝ? አልኩት።

"ትንሽ ቀን ነው የምፈልገው ደህና እሆናለሁ፤ ሁሉም ደህና ይሆናል" ብሎኝ ጭጭ አለ።

በቅጡ አንዳላጽናናህ እኮ መንገዱን ዘጋኸው፤ : ሰው በሚያስፈልግህ ጊዜ ነው ከሰው የራቅከው አልኩት። አየኝ፣ አጎነበሰ ቀስ ብሎ ቀና ብሎ እያየኝ ከትንሽ ዝምታ በኋላ...

“ይሄውልሽ ሊዱ ማጽናኛችን የጎደፈ ነው፤ አንዳንዱ ቤትሽ የሚመጣው ለወጉ ነው፤ አይኑ ላይ ምንም እንባ ሳይታይ ወንድሜ፣ ወንድሜ እያለ ድንኳን ውስጥ ይገባል። አጠገብሽ ይመጣና ምን አገኘው? ገጪው ተያዘን ወንድሜ፣ ሰላምተኛዬ፣ ጥሩ ሰው፣ መከታዬ ይላል። ሐኪም ቤት አልወሰዳችሁትም? ጥያቄ በጥያቄ። የሚያስቆጭ፣ ሐዘን የሚፈጥር ጥያቄ፣ የሚያጎላ ጥያቄ። እንዳልታዘበው፣ እንዳልቀየመው ሐዘንህን መጥቻለሁ ፊቶች፣ ፊታቸውን ለማሳየት የሚጋጋጡ ሰዎችን ጋቢ ለብሶ መታዘብ ሕመም ነው።

በጣም ከባድ ነው ሊዱ፤ ሁሉም የሚጽናናበት መንገድ ሊሆን ይችላል እኔ ግን አልቻልኩም፤ የአጽናኞቼን መንገድ የዘጋጋሁት ሆን ብዬ ነው። ለማጽናናት ስለጉዳዩ ማተት የግድ አይደለም እኮ፤ አብሮ መሆን በቂ ነው፤ ማቀፍ በቂ ነው። ጊዜ ኃያል ነው፤ የማያዶለዱመው ሕመም የለም።

ወንድሜ ጋሽዬ ለእኔ ብዙ ነበር። እሱ ነው ያሳደገኝ፤ የምምለው እንኳን በእሱ አይደል? ለቁም ነገር እንድደርሰ ያልሆነልኝ አልነበረም፤ ኃላፊነቱ ነበርኩ፤ የበኩር ልጄ ነው የሚለኝን ወንድሜን ነው ያጣሁት።

ጉዳዬ ከእግዜር ጋ ነው።

እሱ ነው የተመሳቀለውን እጦቴን በመልክ በመልኩ በእግዜርኛ የሚያበጃጅልኝ፤ እንጂማ በፍጡር ሊያውም ማብሸቅ በሚመስል ማጽናኛ አልድንም። ለዚህ ነው ከቀብር ጀምሮ ቤተክርስትያን የማድረው። ከአማኝ ጥቅማጥቅማችን አንደኛው ከአቅማችን በላይ የሆነ ሁነት ሲጋረጥብን እግዜርላይ ሙጥኝ ማለት አይደል? ከትናንት ዛሬ በደንብ እየበረታሁ ነው፤ የታመንኩት አምላክ እያጽናናኝ እያጸናኝም ነው።"

የብሩኬ አወራር፣ ሁኔታው፣ ሕመሙ አንጀቴን አላወሰው። አይኔ ላይ ያቀረረው እንባ አለመውረድ አልቻለም። አንድ ነገር ብቻ አልኩት

እግዜር ያበርታህ ወዳጄ።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏1615😢3
#አርፋጅ

አንድ ሰፈር ነው ያደግነው፡፡ አንድ ዩኒቨርስቲ ተማርን። ብሩክ ፈታ ያለ ነው፣ ጨዋታ ያደምቃል፣ ጨዋታም ያውቃል። እሱ ካለ የሳቅ ድምጽ አይጠፋም። ስድስተኛ ክፍል አልፈልግህም ተብሎ የተላከለትን ደብዳቤ አባቱ አግቶበት
የመታውን ጠረባ፣ ለፍቺም ደርሰህልኛላ እያለ የሚጦልበውን ጡለባዎችን እየቀመመ ሲያጫውት አፉን ከፍቶ የማይስቅ አልነበረም።

ታላቅ ወንድሙ ላይ የሚሠራውን ተንኮል፣ የግድያ ሙከራ የሚመስሉ ድብደባዎችን ኮስተር ብሎ በፌዛም ፊቱ እያወጋ ያዝናናን ነበር። ግሬድ ሲሰቅልም፣ ሲሾቅም ማላገጡ የሚጠበቅ ነው። በዙሪያው የማንጠፋው ፍሬንዶቹ ላይ እንዳይደብረን አድርጎ ለጨዋታ ፐርፐዝ ብቻ ይቀልድብናል።

ብሩክ እንደ ጃካራንዳ ዛፍ በዙሪያው ሚያጅበው አይጠፋም፣ ሰው ይወደዋል። ከሰው ጋ እይጋጭም፣ መከባበር የማይደራደርበት ዋነኛ ፖሊሲው እንደሆነ በደንብ የሚቀርበው ሁሉ ያውቃል፣ የጠበቀ ወዳጅነት ያለን ደግሞ በይበልጥ እናውቃለን።

ብሩክ ለእኔ ወንድሜ ነው የማልለው ባልጀራነትን ማሳነስ ስለሚመስለኝ ነው። ብዙ ሳቅ እና ጭንቀቶችን ተጋርተናል። በድዬ ሳለሁ ለእኔ አግዞልኛል፣ እስከ ድክመቱ ተቀብየዋለሁ፤ ጓደኛዬ ነው፣ ምንም ሳይኖረን ጊዜ ብቻ እያለን ነው ነፍሳችን የተናበበው፤ የጓደኝነት ትርጉም መተንተን ሳንጀምር ነው የተወዳጀነው።

እኔ ታላቅ ወንድሜ የጀመረውን ቢዚነስ ተቀላቅዬ በሂደት ብዙ ሳንቲም ማግበስበስ ጀመርኩ። ብዙ ሀብት ባገኘሁ ቁጥር መፍጨርጨሬ ጠነከረ፣ ነገሮችን በውሎዬ ስለምመዝን እነጫነጫለሁ፣ ብሩክ ነገሮችን ከእሱ አንጻር ስለሚያይ መነጫነጬ አይገባውም።

ብሩክ ቀልደኝነቱ መፍዘዝ ጀመረና መገለጫው ያልሆነ ጨለምተኝነት ወረሰው። ምሬቱን ቀልቤን ሰብስቤ አሰላስዬ አላውቅም፣ መንገዱን ለመደልደል አልጣርኩም። ከእጮኛው ጋ የሚያጋጥመውን ግጭት በምሬት ሲነግረኝ ቀልቤን ሰብስቤ ከጊዜያዊ ስሜት የገዘፈ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም።

የድሃ ልጅ መሆኑ፣ አይዞህ የሚለው አለመኖሩን ሲጠቅስ አብሬው ከማሸብሸብ የዘለለ ጊዜ ሰጥቸው ምን ላግዘው? ከእኔ ምን ይጠበቃል? ብዬ ለአፍታ አሰላስዬ አላውቅም።

እድገት ላይ በመመሰጤ ያሉኝን በረከቶች ለማስተዋል አልተቻለኝም ነበር። ያሉንን እየጣልን የምናመጣው አዲስ ስኬት እንደምን የምንፈልገውን ደስታ ሊያመጣልን ይቻለው ይሆን??

ለሥራ ኔትወርክ የማይሰራበት ቦታ ከርሜ ስመጣ እንድንጠጣ፣ እንድንስቅ ደወልኩለት ግን ስልኩ ዝግ ነው። ደጋግሜ ደወልኩ፤ አሁንም ስልኩ ዝግ ነው። ስልክ ማጥፋት፣ ስልክ አለማንሳት፣ ለብቻው መሆን አዲስ ያመጣው ፋሽኑ መሆን ጀምሯል። ቤቱ ልሄድ ተነሳሁ።

ፀሐዩ ሀሩር ነው፤ ዘንድሮ ፀሐዩን ለማምለጥ እንደዝናብ መጠለል እና መሮጥ መጀመራችን አይቀርም። የድሮ ሰፈሬ ደረስኩ፣ የነ ብሩኬ ደጅ ላይ ድንኳን ተደኩኗል፤ ብሩኬ አያቱ ጠንካራ ሕመም እያንገላታቸው እንደሆነ ነገሮኝ ነበር።

አያቱ በሕይወቱ ደማቅ ስፍራ አላቸው፤ ይወዳቸዋል፡፡ እንደ ወንድሙ ነበር የሚያዋራቸው፣ እንደ ጓደኛቸው ነበር የሚያጫውቱት። ከልጅነት ጀምሮ የምናቀውን ሰው ማጣት ሕመሙ ብርቱ ነው። ድብርት እና ምሬት ሳይጣባው አያቱ ሳይተኙ ለመድረስ ነበር የሚሮጠው።

እርምጃዬን ቀስ እያደረኩ ወደ ድንኳኑ ስሄድ የሰፈራችን ለቀስተኞች አይን እኔ ላይ አረፈ፣ አጎነበስኩ። ቀስ ብዬ የድንኳኑ መግቢያ በር ላይ ያገኘሁት ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ፣ በቀስታ ቀና ብዬ ብሩኬን በአይኔ ሳስሰው ወንበርተደርድሮ በተቀመጠ ፍራሽ ላይ የደከሙ አያቱን አየኋቸው፤ ፍጥጥ ብዬ እንዳየኋቸው አስታውሳለሁ።

ከአጠገባቸው እናቱን አየኋት፣ በጥሩ መንፈስ አላየችኝም፤ አይኔ ወደ ተሰቀለው ፎቶ ተምዘገዘገ። ከዛ ሰዓት በኋላ የሆነውን ብዙ አላስታውስም። ለቀበሌ መታወቂያ ብሎ አብረን ሄደን የተነሳነው የብሩኬ ፎቶ ተሰቅሏል። በጣም እንደጮህኩ አስታውሳለሁ፤ እናቱን ሂሩቴን እየወደቅኩ፣ እየተነሳሁ የሆነውን ለመጠየቅ ፍራሹ ጋ ለመሄድ መሞከሬንም አልረሳሁትም። የሆነውን ሁሉ ፡ አለማወቄ ተገለጸላቸው፡፡ ረጭ ያለው ለቅሶ ቤት ታወከ፤ ሁኔታዬ ያሳዘናቸው ሰዎች አብረውኝ ያለቀሱ ይመስለኛል።

አያቱን አንቄ ጋሽ በላይ ጓደኛዎት የት ሄደ፣ ብሩኬ የት ሄደ? አልኳቸው። በዛለ እጃቸው አቅፈውኝ በትኩስ እንባ ታጅበው እጁን በእጁ በላ አሉኝ። እግሬ አልጸና ያለ ይመስለኛል፤ ብዙ ሰዎች ያዙኝ፤ ክንዴን ክንዴን ብዬ ጮህኩኝ፤ ሰው ለካ እንዲህ ደካማ ነው፤ የቻልኩት መጮህ እና የሆነውን መካድ ነበር።

በቀን ብዛት ተበረታታሁ ያወራነውን ሳሰላስለው ኋላ መቅረት ሲንጠው እንደነበር ገባኝ። ጨለምተኝነቱ ለመኖር ያለውን ፍላጎት ቀድሞ እንደገደለበት ገባኝ። ለካስ ማስተዋል አቅቶኝ ነው እንጂ ሁሉም ነገሩ ይገባ ነበር። አብረን ብንሆንም ለካ ተለያይተን ነበር፤ ለካ እሱ ነበር ጓደኛዬ እንጂ እኔ ጓደኛው አልነበርኩም። አናቱ ላይ በፍጥነት የወረረውን ሽበት ከ"stress"፤ ከመብሰልሰል የተፈጠረ መሆኑን አልጠረጠርኩም ነበር።

ተሳክቶለታል የምባለው እኔ ነገሮች ሲጠሙብኝ፣ አንዳንድ ነገሮች ሲከፉብኝ ይቺ ዓለም እንደምትሰለቸኝ አውርቼው አላውቅም።

ራሴን ልገድለው እንደነበር ነግሬው አላውቅም። ሽራፊ ፈገግታ በሀሩር ፀሐይ ጤዛ እንደመፈለግ ሆኖብኝ ሳለ፣ የሞከርኩት ሙከራዎች ሲከሽፉ፣ ከሰው ሁሉ አነስኩኝ ስሜቴ ሲበላኝ፣ ብቻ መሆን ሲጨፍርብኝ፣ አለመፈለግ ስሜት ሲወዘውዘኝ፣ ያለኝን ነገር ሁሉ ያፈሰስኩበት ተስፋዬ ሲጠፋ፣ ሕልሜ ሰፍቶኝ ስንከላወስ፣ የምሸሸግበት ጥግ ሳጣ፣ በማምነው ሰው ስካድ፣ ዕድለቢስነት እንዳልጠራጠር አድርጎ ሲመሰክርብኝ ራሴን ልገለው ዳድቶኝ ነበር። መዳዳቴን እንዴት ድል እነደነሳሁት ሳልነግረው!

አምላኬ ጋር ሙጥኝ እያልኩ፤

አንዳንዴ በረከቶቼን ፈልፍዬ ለራሴ እየተረኩ፣

አንዳንደ ጭላንጭል ብርሃኔ ላይ ተመስጬ፣

ብሞት የምሰብራቸውን ሰዎች አዝኜላቸው።

አንዳንዴ ክችች ያልኩበትን ጉዳይ እያላላሁ፣ አንዳንዴ ግትርነቱን እየገሰጽኩ፣ አንዳንዴ ሆስፒታል ያሉ አካላቸው የማይታዘዝላቸው ነፍሶችን እየረዳሁ፣ አንዳንዴ እስረኞችን እየጠየቅኩ ነው ራሴ ላይ የራራሁት ሳልለው
ይሄ ትግሌ ለብሩኬ ትርጉም ሊሰጠው እንደሚችል ማሰብ አልተቻለኝም ነበር። የምንወዳቸውን ሰዎች ምን ያህል እንደምንወዳቸው ካለ እጦት እንዴት መረዳት ያቅተናል? ለራስ ሰው አለመድረስን ያህል አርፋጅነት የለም።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
34👍11😢9
ስላንቺ ሳወራ ዋልኩኝ
       አልወዳትም እያልኩኝ፡፡
              ሰልችቶኛል
        መናፈቅ በቅቶኛል፡፡
        እያልኩኝ... ለፈፍኩኝ
ፈሪ ሰው መሆኔ ያዝተኛል ስንቱን?

የወንድ ልጅ ዛቻ ፍጥረቱ ደመና
            የሰነፍ ሽመና

       በቅቶኛል እያልኩኝ
         በቅኔ ነገርኩኝ
        በዜማ ነገርኩኝ።
        ነገርኩኝ በተረት
       የሚሰማኝ የለም።
አደመብኝና ካንቺ ጋራ ፍጥረት፡፡

          ጭራሽ መቀለጃ
          "በቃኝ" መጫወቻ
           ምጸት ነው አቻዬ
  ከመለየት በላይ ያስቃል ዛቻዬ፡፡

                 አንቺዬ...

         "በቃኝ" መጫወቻ
          ምጸት ነው አቻዬ
   ከመለየት በላይ ያስቃል ዛቻዬ፡፡

                  አንቺዬ...
                   በገላ
                  በመላ

ይሄ ንክር ልቤን ስንቱን ያስተማርሽው
ዝም ብሎ መሄድን ምነው ያልነገርሽው?        እሸፍናለሁ ስል ተጋልጥኩኝ ጭራሽ
           አስሬ ስጠራሽ
  መዘበቻ ሆነኩኝ በፉከራ መዘዝ
በገዛ ቃሌ እንኳ አልቻልኩኝም ማዘዝ?

               ታዲያ... ታዲያ
       ይሄን ሁሉ ነገር በሩቁ እያየሽ
               ተለየን ትያለሽ?

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍119