አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ማበድ_ይሻላል

አእምሮዋን ያማታል፤ ሃና ትባላለች።  በኮሮኮንቹ፣ በአቋራጭ፣ በድልድዩ በኩል አልፋ ቤታችን ትመጣለች፤ ስትመጣ ሰዓት አትመርጥም። የአቅሜን ለማንም ሳልናገር እንድትድን ጥሬያለሁ፤ አልተሳካልኝም እንጂ። መዳኗ በእኔ እንዲሆን አልተመረጠም ወይም ከነጭራሹ እንድትድን አልተፈቀደም።

አንዳንድ ቀን መጥታ በሩን በኃይል ስታንኳኳ ልጄ ከእንቅልፉ ይባንናል። በር የሚከፍት ሲጠፋ በጓሮ ያለውን መስኮት
በድንጋይ ስታንኳኳ መሰለኝ አራት ያህል ጊዜ ሰብራዋለች። በሃኒቾ አልናደድም፤ ይልቅ ይበልጥ ታሳዝነኛለች። ባለቤቴ ግን በእሷ ጉዳይ ሆደ ሰፊነቴ ይገርማታል።

አንድ ዕለት ከእኛ የተረፈ ምግብ ልትሰጣት ስትል ገላምጬ አዲስ ያልተነካካ ምግብ እንድትሰጣት ስነግራት፣ አገለማመጤ ከዚህ በፊት ያላየችው ዓይነት ስለነበር ቅሬታ ልቧ ውስጥ ለሳምንት ያህል ተቀርቅሮባት እንደነበርአስታውሳለሁ።

አንዳንዴ ትክ ብላ ስታየኝ "ሃኒቾ ደህና ነሽ?" ስላት አንገቷን በአዎንታ ትነቀንቃለች። አይኗ ያሳዝናል። አይኗ ሁሉ ነገሯን የሚናገርባት ፍጡር ናት፤ አይኗ ስሜቷን ማንጸባረቂያ መስታወቷ ነውና ሁሉን ከአይኗ አገኘዋለሁ። ሃኒቾን አይቻት ከራባት ቃል ባታወጣ እንኳ አውቃለሁ።

አንድም በልጅነቴ ረሃብን የታናሽ የወንድሜን ያህል በቅርበት ስለማውቀው የራበውን ሰው ትክ ብዬ ማየት አልችልም፤ አጎነብሳለሁ፤ ክፉ ትዝታዬን ይቀሰቅስብኛል። ክፉ ትውስታችንን የሚያስታውሰውን የአእምሮ ክፍል  በሆነ ጥበብ ማደንዝዝ ቢቻለን ብዬ አንዳንዴ እመኛለሁ።

ሁለተኛ ሃኒቾን አውቃታለሁና መራቧን አይቻት ባውቅ አይገርምም።

መንገድ ሳገኛት አሊያም ቤታችን ስትመጣ

"ደህና ነህ እዩ”

“ደህና ነኝ”

“አንቺ እንዴት ነሽ?” ስላት ጭንቅላቷን ደህና ነኝ ለማለት ትነቀንቃለች፤ ከዛ ውጪ ሌላ ምንም አትልም።

ባለቤቴ ሰፈሩን፣ ቤታችንን ጠላችው። በእሷ ጉዳይ ከእኔ ጋ ተያይዞ የሚነዛው ወሬ አወካት፤ በሌሊት እየመጣች እዩ ምግብ ስጠኝ የምትለው፤ በር የሚከፍት ሲጠፋ በጀርባ መስኮት የምትሰብረው ነገር ታከታትና ባልተለመደ ሁኔታ ልትቀና ይቃጣት ጀመር። ባመመው የቀና ሰው ካመመው ሰው በምን ይሻላል እላለሁ በልቤ። ከሚስቴ ጋር በሃኒቾ ጉዳይ ተጎረባበጥን፤ በር በኃይል ስታንኳኳ የልጄን መበርገግ መልመድ አልቻልንም።

አንድ ጠማማ ቀን

ድብርት እንደ ነጭናጫ ሕፃን ልጅ ሱሪዬን ይዞ ሙጭጭያለበትን ውሎ አሳልፌ ቤቴ ገባሁ። ልጄ ባለመተኛቱ መግባቴን እንዳየ አባ እያለ ደስታ ፊቱ ላይ ተጥለቀለቀ። አንድ ቀን እንደ ዘላለም በሆነበት የትግል መንደር ለመውደቅ ጥንጥ ቀርቶኝ እቤት ስደርስ አባ... አባ የሚለኝ የልጄ ቃል ነው እጅ የማያሰጠኝ። የልጄን ጉንጩን፣ ግንባሩን፣ አንገቱን፤ የሚስቴን ጉንጭ ስሜ እራት እንደማልበላ ለሚስቴ ነግሬ ወደ መኝታ በቴ ሳመራ ባለቤቴ ገጼን እያየች “ውሎ እንዴት ነበር?" ስትለኝ ማለት የቻልኩት አድካሚ ነበር ብቻ ነው።

David Darybyshire Bad Day

It's seems on some days

The whole world is against you You feel really down, in a haze
How long do have to feel blue

እንዲል... አንዳንድ ቀን ይደብራል። አውጥተን፣ አውርደን ያቀድነው ይከሽፋል፤ ተስፋ ያደረግነው ይዘምማል። ዕድለኛ ያልመሆን ስሜት ውስጣችን ይርመሰምሳል፤ ኋላ የመቅረት ስሜት ይላፋናል፤ በአጠቃላይ ዛሬ ጥሩ የሚባል ቀን አላሳለፍኩም።

ሹልክ ብዩ አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ በስንት መገላበጥ እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረገኝ፤ በሩ ከዚህ ቀደም ተደብድቦ ከሚያውቀው በላይ በኃይል ተደበደበ። ባንኜ፣ ተንደርድሬ

ሃኒቾ ነች፤ አመድማ፣ ግራ የገባው ፊት እንዳየሁ ፍንትው ብሎልኛል።

በሩን እንደከፈትኩት እያጉረጠረጥኩ ፊቴን አጠይፌ እ ምንድን ነው ሕይወቴን የምታከብጂው? እንዴ......!!!! ካለ እኔስ ሰው አታውቂም? ሁለተኛ እዚህ ቤት እንዳትመጪ..... አልኳት። የሌባ ጣቴን ፊቷ ላይ ደቅኜ እያውለበለብኩባት… ተናግርያለሁ!! እንዳልኩ አስታውሳለሁ።

ትክ ብላ አይታኝ በዝግታ አጎነበሰች። ቀና ብላ አየችኝ፤ ቀና ብላ ስታየኝ አይኖቿ እንባ አርግዘው ነበር። ቀስ ብላ አንገቷን ወደ መሬት ቀብራ፣ መሬት መሬት እያየች በዝግታ ትንሽ ወደፊት እንደተራመደች እሳት ለብሼ ፊቴን አጨፍግጌ ባለቤቴ ከኋላዬ እንደቆመች ዞራ ተመለከተችን አይኗ ያረገዘውን እንባ እያፈሰሰ ነበር።
አስተያየቷ፣ እንባዋ፣ አዟዟሯ ቢያሳዝነኝም ማዘኔን ፊት ነስቼ ፊቴን አዙሬ ወደ ቤቴ ገባሁ። ቀጥታ ወደ አልጋዬ ሄጄ ተመልሼ ተንጋለልኩ። እንደቅድሙ ማሸለብ አልቻልኩም እንጂ። እንባዋ፣ አስተያየቷ፣ አጎነባበሷ አንጀቴን በላው። አንሶላ ውስጥ ገብቼ እንደበደለ ሳይሆን እንደተበደለ፤ እንደጮኸ ሳይሆን እንደተጮኸበት፤ እንዳባረረ ሳይሆን እንደተባረረ ሆኜ አለቀስኩ።

ሃኒቾ ለእኔ ምን እንደሆነች የነበረንን ቁርኝትም የሰፈሩ ሰው ሁሉ በደንብ ያውቃል። ሚስቴ ይሄን  ስለምታውቅ ነው እንደልቧ የማትናገረው፤ ይሄን ስለምታውቅ ነው ሐዘኔታዬ ላይ ቅናት የሚጣባት።

ሃኒቾ ታሪኬ ናት። ዋናው ታሪኬ እሷ ጋ ነው ያለው፡፡ እጮኛሞቾች ነበርን። አንድ ሸበጥ ለሁለት አድርገናል፤ ቤተሰብ  አብሮነታችንን ጠልቶ ሊለያየን ሞክሮ አልሳካ ብሎት ያውቃል፤ በክፉ ካያት ጋ ለእሷ ተቆርቁሬ ተጣልቼላት አውቃለሁ፤ ጎድሎብኝ ሰርቃ ሞልታልኛለች፤ ለምና ተቀብላ ሰጥታኝ ታውቃለች፤ ኪሴ ኪሷ፣ ኪሷ ኪሴ ነበር።

ከእሷ የበለጠ ችስታ ስለነበርኩ ከእኔ በላይ እሷ ለእኔ ሆናልኛለች። ከሁሉ ሰው በላይ ስለምወዳት መንሰፍሰፌን በኩራት ነበር በየአጋጣሚው የምለፍፈው። እሷ ጋ ስሆን ቁጥብነቴ በስሱ ይተናል፤ ፍላጎት እና ገጠመኜን ከሌላው በተለየ እተነፍሳለሁ።

ትዝብት እና ፍርሃቴን አጋራታለሁ፤ እሷ ጋ ሆኜ ስደሰት ፈንጠዝያዬ ማንም እንደሌለ ዓይነት ነበር። ገመናዬን

ነግሬያታለሁ፤ ገመናዋን ነግራኛለች፤
ገበናችንን ተገላልጠናል፤ መተዋወቃችን ነው የሚያገማምተን። አንድ ዕለት አበሳጭታኝ ሁለተኛ አጠገቤ እንዳትደርሺ ስላት ፈገግ እያለች

“በኋላ ስታስሰኝ ትውላለህ“

“አታውቂኝም!!"

በእርግጥ እንዳለችው በቶሎ የዛኑ ቀን  አላሰስኳትም፤ ከሁለት ቀን በላይ ግን : መሻገር  አልተቻለኝም፤ ትዕቢት ተናነቀኝ። ፍቅሬ ከትዕቢቴ ስለሚበልጥ አይኔን በጨው አጥቤ አገኝቻታለሁ፤ ፍቅራችን አይናችን ውስጥ ይጮህ ነበር። እሷን ባለማግኘቴ ምክንያት ተጭኖኝ የነበረው ድብርት በነነ፤ ልትመጣ ስትል እንደመጣሁ መደበቅ አልተቻላትም::

ሃኒቾ ቶሎ ቶሎ ታኮርፍ ነበር፤ እኔ መኳረፍ ጭንቅ የሚለኝ ሰው ነኝ። መለማመጥ ስለማልወድ እንድታዋራኝ ቀልብ ገዝቶ ኩርፊያዋን ለማርገፍ ድራማ ፈጥሬ እተውናለሁ፤ ማኩረፏን ረስታ ቀልቧን ትሰጠኛለች፤ መቅደድ እንጀምራለን።

ደግሞ ትቀና ነበር፤ መቅናቷን በሁኔታዋ ነው የምትገልጸው፤ ትገባኛለች። ሳትጠይቀኝ የቀናችበት የመሰለኝን ጉዳይ አብራራላታለሁ፤ ቀስ ብላ ፍትት ትላለች፤ ፈገግ ስል

“ምን ያስቃሃል?" ትላለች።

ሰውነቷን ለልፊያ እያዘጋጀች የበለጠ አፌን ከፍቼ ስስቅ ትላፋኛለች፤ እላፋታለሁ።
ስስ ነበረች። እሷ በቶሎ ስለምትከፋ እኔም በትንሽ እንዳልከፋባት ይደብረዋል  የምትለውን ነገር ላለማድረግ ትጥራለች።

ትንሽ ነገር ይረብሻታል፤ ሲጨንቃት አቅፋታለሁ፤ እጄን ጸጉሯ ላይ እያንሸረሸርኩ ሁሉም ነገር ይስተካከላል፣ ከባድ አይደለም፤ ደግሞ አምላክ ይረዳናል እላታለሁ፤ እርጋታ ሲያጥለቀልቃት ይሰማኛል።
39👍5🔥2