#ወይ_አጋጣሚ(አጭር ልብወለድ)
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርስት_በዘሪሁን
==========================
ቢሆንም ቅንዝሬ ያው ቅንዝር ነውና ጆሮው የተደፈነ ነው፤የእኔ እና የእሷን ምክንያት አያዳምጥም ፡፡ስለዚህ እመክረው እመክረውና…ከዛም ደግሞ እለምነው እለምነው እና በቃ ከአቅሜ በላይ ሲሆን እንደነርኳችሁ በወር አንዴ በደሞዝ ሰሞን ወደ አብረቅራቂ መብራት ወደሚንቦገባግባቸው የለሊት ቤቶች ጐራ እላለሁ ፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን ልቤ ለሀይሚ እንዳላዘነ ነው፡፡ዛሬ ግን እፎይ ልገላገል ነው ፡፡ሀይሚ እቤት ለመምጣት ከስድስት አታካች ወራቶች ጭቅጭቅ በኋላ ተስማምታለች፡፡ከቀኑ 8 ሰዓት ነው የምትመጣው፡፡እኔ ግን ከእንቅልፍ የባነንኩት ከለሊቱ 8 ሰዓት ነው፡፡ለዝግጅት፡፡እውነቴን ነው እኮ ፡፡ገና እቤት ማዘጋጀት አለ፣ዕቃ ማጣጠብ አለ፣አልጋ በስርአት ማንጠፍ አለ፣ለፍቅራችን ማጀቢያ ሙዚቃ መምረጥ አለ፣ደግሞ እኔም እንድደፍራት እሷም እንድትደፈርልኝ የሚያግዝ መጠጥ ማዘጋጀት አለ፣አረ ስንቱ….፡፡
ደግሞ አይገርማችሁም ዛሬ ሀይሚ ቤት ልትመጣ ትናንትና ቂጣሟን ማግኘቴ….፡፡ ማግኘቴ ብቻ ሳይሆን እቤቷ ድረስ መከተሌ..ከዛም አልፎ ስልክ ቁጥሯን መቀበሌ..፡፡አሁን ልደውልላት እንዴ….? የሚል ሀሳብ መጣብኝ ፡፡መልሼ ሀሳቤን ውድቅ አደረግኩት ::ለሀይሚ ያለኝን ታማኝነት ዝቅ ማድረግ ነው:: አይደለም መደወል …ቢቻል በምናቤ ተንጠልጥሎ አልወርድ ያለኝን የቂጧን ምስል አሽቀንጥሬ መጣል ብችል ደስ ይለኝ ነበር፡፡እንደቀጠሯችን ምንም ሳታረፍድ ከቀኑ 9 ሰዓት ሀይሚ መጣች..ያው አንድ ሰዓት ዘገየች ማለት አረፈደች ተብሎ መደምደም የለባትም ብዬ ነው፡፡ አለባበሷን ልግለጽላችሁ፣ቡትስ ጫማ፣ጥብቅ ያለ ጅንስ ሱሪ፣በሱሪው ላይ ቁርጭምጭሚቷ ጋር የሚጠጋ ቀሚስ፣በቀሚሱ ውስጥ ደግሞ ሱሪዋ በቀበቶ የተጠፈረ መሆኑን በሚታየው የቀበቶ ቅርፅ ማወቅ ይቻላል፣ከላይ ደግሞ ግብዳ ሹራብ ደርባለች፡፡
ጉንጯን እያገላበጥኩ እየሳምኩ ቢሆንም አይኖቼን ግን ሰማዩ ላይ አንጋጥጬ እያንከራተትኩ ነው፡፡ሀሞቴ ፍስስ ነው ያለው፡፡አሁን እሺ ብላ እንድናደርግ ፍቃዱን ብትሰጠኝ ..ይሄን ጫማዋን ፈትቼ እስካወልቅ አንድ ሰዓት፣ሱሪዋን እስካወልቅ ሌላ አንድ ሰዓት፣ምን አልባት ከሱሪዋ ስር ታይት፣ከታይቱ ስር ደግሞ ሁለት ወይም ሶስት ፓንት ታጥቃ ሊሆን ይችላል..? ታዲያ መሽቶ ነጋ ማለት አይደል?፡፡
ወደ ቤት ዘልቃ ቁጭ አለች፡፡ቁጭ አባባሏ እራሱ ሲያበሳጭ፡፡ ከጓዲያ ወጥቶ ማጅራቷን አንቆ የሚውጣት ዳይኖሰር ያለ ይመስል በራፉ ጥግ የሚገኝ ኩርሲ ላይ ተቀመጠች፡፡ፈርጥጣ ለመውጣት እንዲያመቻት ይመስለኛል፡፡ ደግሞ እሷ ብቻ ሳትሆን እኔም አበሳጫለሁ ፤ ምን አለበት ከመምጣቷ በፊት እቤቴ ያሉትን መቀመጫቸው ሁሉ ሰብስቤ ጓዲያ አስገብቼ ቢሆን ኖሮ ምርጫ ስታጣ አልጋ ላይ መቀመጧ አይቀርም ነበር፡፡
‹‹ሀይሚ ..ምነው በራፍ ላይ….. ?አልጋው አይሻልሽም…?››
‹‹አይ መጣለሁ ብዬህ እንዳልቀር ነው እንጂ …እሄዳለሁ፡፡››
‹‹ወዴት?››
‹‹ወደቤት ነዋ…እናቴ ስራ አዛኝ ነበር ….ተደብቄ ነው የመጣሁት››ብላኝ እርፍ፡፡
ይታያችሁ ሰው አሁን ይህቺን ያፈቅራል...?ከለሊቱ 8 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ፍዳዬን ስበላ ቆይቼ እሷ ግን ገና መጥታ ሳትጨርስ ልሄድ ነው ትላለች፡፡ቀኑን ሙሉ እሷን እያሰበ ሲወጣጠር የዋለውን እንትኔ ወዲያው ልፍስፍስ ብሎ ሲሸበለል ይታወቀኛል፡፡ችላ አልኳት እና ወደ ጓዲያ ገብቼ የሰራሁትን ምግብ በማምጣት ጠረጴዛ ላይ ደረደርኩት፡፡ ወይኑንም አወጣሁ..አሁን የምግብ ጠረጰዛው አልጋውን ተጠግቶ ስለሚገኝ ምርጫ የላትም መጥታ አልጋው ላይ ከጐኔ መቀመጧ አይቀርም ፡፡
‹‹ሀይሚ ነይ ምሳ እንብላ ፣እርቦኛል..እስከአሁን እኮ አንቺን ስጠብቅ አልበላሁም፡፡››
‹‹እኔ እኮ በልቼያለሁ፡፡››አቤት ወሽመጥ ስትቆርጥ፡፡
‹‹ባክሽ አታበሳጪኝ..በስንት ጣጣ መጥተሸ ደግሞ..?›› ተኮሳተርኩ፡፡ እንደመደንገጥ አለችና መጣች፡፡ እንዴት መጣች አትሉኝም…? ኩርሲዋን ይዛ በመምጣት ከአልጋው ራቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ ምርጫ አልነበረኝም፤ እጇን አስታጠብኳት ፤ወይኑን ስቀዳ‹‹ለእኔ እንዳትቀዳልኝ››አለችኝ እየተንዘረዘረች፡፡ መርዝ ልቀዳላት የተዘጋጀው አስመሰለችው፡፡
‹‹አንድ ብርጭቆ ብቻ››ተለማመጥኳት፡፡
‹‹አንድ መለኪያም አልጠጣም..እንድበላ ከፈለክ በውሃ ቀይርልኝ…›› ለወራት ተጨንቆ የቀየሰው የጦርነት እስትራቴጂ ፍርክስክሱ እንደወጣበት የጦር ጄኔራል ሞራሌ ድቅቅ አለበኝ፡፡ለንቦጬን ጣልኩ …ያለችውን አደርግኩ፡፡
እየተጐራረስን በፀጥታ በልተን ጨረስን፡፡እኔ የእሷንም ፋንታ የምጠጣ ይመስል እንደውሃ እጋተው ጀመር ፡፡ እንደጨረስን የተበላበትን ዕቃ አነሳሳሁ..እጇን አስታጠብኳት እና እኔም ታጥቤ ወደ ቦታዬ ተመለስኩ፡፡
ልክ ምሳዋን ለመብላት የመጣች ይመስል…‹‹ልሂድ በቃ፡፡›› አለችኝ፡፡
‹‹ቆይ ማውራት አለብን፡፡››
‹‹ምንድነው የምናወራው?››
‹‹ስለፍቅራችን ነዋ፡፡ ››
እንደመደንገጥ ብላ‹‹ፍቅራችን ምን ሆነ ?››አለችኝ፡፡
‹‹እስከአሁን ምንም አልሆነ …ካላወራንበት እና መፍትሄ ካላበጀንለት ግን መሆኑ አይቀርም.››ወይኑን በደረቁ እየለጋሁት ስለሆነ በድፍረት የመናገር ወኔዬ ሙሉ ነው፡፡
‹‹እሺ ፈጠን በልና እናውራበት››
‹‹ታፈቅሪኛለሽ?››
ግራ በመጋባት‹‹ምን ማለት ነው?››
‹‹ታፈቅሪኛለሽ ወይ?››ደግሜ ጠየቅኳት፡፡
‹‹በጣም አፈቅርሀለሁ፡፡››
‹‹ካፈቀርሺኝ …ዛሬ ፍቅር እንድንሰራ እፈልጋለሁ፡፡››
‹‹ፍቅር እየሰራን አይደል እንዴ?››
‹‹እንደ እሱ አይደለም..ልብስሽን አወላልቀሽ..እኔም ልብሴን አውልቄ… እዚህ አልጋ ላይ ወጥተን ምናምን ማለቴ ነው… በጣም አምሮኛል…ስንት ወር ነው የምሰቃየው…?››ብሶቴን ተረተርኩት፡፡
‹‹እሱማ አይሆንም፡፡››
‹‹ለምን አይሆንም?››
‹‹አፈቅርሀለሁ… ግን ጊዜው አሁን አይደለም…ገና 18 ዓመት እኮ አልሞላኝም፡፡ በዛ ላይ የሃይእስኩል ትምህርቴንም አልጨረስኩም፡፡››
‹‹ስንት ዓመትሽ ነው?››
‹‹17 ዓመት ከ11 ወር…››
‹‹እና ታዲያ ሰው ለሚወደው እንኳን አንድ ወር ይቅርና አንድ ዓመትስ ቢያጭበረብር ምን አለበት?››
‹‹እንደ እናቴ መሆን አልፈልግም፡፡››
‹‹እንዴት እንደ እናትሽ?››
‹‹እሷም 10ኛ ክፍል እያለች ነው እኔን ያረገዘችው፡፡በዛ የተነሳ ትምህርቷን አቋርጣ ብዙ ስቃይ ተሰቃይታለች፡፡ ብዙ ብዙ መከራ ካሳለፍን በኋላ ነው በቅርቡ ህይወታችን የተስተካከለው፡፡››
‹‹እኔ እኮ ብታረግዢም አፈቅርሻለሁ..ማለቴ አገባሻለሁ፡፡››
‹‹አባቴም እሷን እንደዛ ነበር የሚላት…፡፡የእውነት እንዳረገዘች ስትነግረው ግን የራስሽ ጉዳይ ነበር ያላት፡፡››
‹‹እሺ በቃ በኮንዶም እንጠቀም..ህይወት ትረስት፣ሴንሴሽን፣ሜምበርስ ኦንሊ… የፈለግሽው አይነት አለ፡፡››
‹‹እንዴ ዲኬት ነው እንዴ የምትሰራው…? ይሄ ሁሉ ኮንደም ምን ልታደርግ ሰበሰብከው…?››ያላሰብኩትን መስቀለኛ ጥያቄ ጠየቀችኝ፡፡
‹‹ባክሽ አንድ ዲኬት የሚሰራ ጓደኛዬ ነው አምጥቶ ለማንኛውም እያለ ቤቴ የሚያስቀምጠው፡፡››
‹‹ጥሩ…. ግን ድንግል ነኝ… ድንግልናዬን ደግሞ በኮንደም አላስወስደውም፡፡››
‹‹እኔ እኮ ድንግልናውን አልፈልገውም..፡፡››
‹‹……እና አውልቄ ላስቀምጠውና ተጠቅመህ ከጨረስክ በኃላ መልሼ ላጥልቀው?››ንግግሯ ከማበሳጨትም አልፎ አሳቀኝ፡፡
‹‹እና ምንድነው መፍትሄው?››
‹‹ምታፈቅርኝ ከሆነ ጠብቀኝ?››
‹‹እሱማ አፈቅርሻለሁ፡፡››

👍86❤5👏2👎1
#የጣት_ቁስል
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ
ቄስ አሻግሬ
ሔደውልኝ ይሆን? ዛሬ ደግሞ ማርያም ናት፡፡ ቅዳሴ ይኖርባቸው ይሆን? ለነገሩ ቅዳሴ እንኳን ከሰዓት ነው፡፡ ቀኑ ዕሮብ አይደለም ምናልባት ጠዋት ሄደውልኝ ይሆናል፡፡ ለማንኛውም እኔም ማህበር ስላለኝ እዛው ቤተ ክርስቲያን አገኛቸዋለሁ፡፡ ከማህበር ስንወጣ እጠይቃቸዋለሁ፡፡ ብሎ ከሰው ጋር ባይይሆንም ከራሱ ሃሳብ ጋር የተናገረው ነበር፡፡ አቶ ለማ ሽፈራው፡፡
ከቅዳሴ የመውጫ ሰዓት ስለደረሰ ጋቢውን ለባብሶ ተነሳ፡፡ ወደ ጉራንባ ማርያም ቤተክርስቲያን ጉዞውን ቀጠለ፡፡
ቄስ አሻግሬ አማላጅነቱ ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል ባይባልም በተወሰነ መልኩ ተስፋ የሚሰጥ መልስ በማግኘታቸው ተደስተዋል፡፡ ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ከሰዓት ቅዳሴ ስለነበረባቸው ብዙም ሳይቆዩ ተነስተው ወደ ጉራንባ ማርያም ቤተክርስቲያን ጉዞዋቸውን አቀኑ፡፡
አቶ ለማ ከቅዳሴ ሲወጡ ደረሰ፡፡ ቄስ አሻግሬን ለማናገር ከማህበር በኋላ ሊመሽ ስለሚችል ዛቲ እንደቀመሱ ማናገር እንዳለበት አሰበ፡፡ ከዛቲ እንደተበተኑ ካህናት ከቅዳሴ ወጥተው ወደ ተቀመጡበት ቦታ ሔደ፡፡
"ሰላም ዋሉ ቄስ አሻግሬ” ፡፡
"እግዚአብሔር ይመስገን ሰላም ዋልህ?፡፡ ለማ" ብለው አጠፌታ መልስ ሰጥተውት መስቀል አሳለሙት፡፡ "ዛሬ ማርያም መጥተህ ኖሯል፡፡ መሃበር አለህ ለካስ" አሉ፡፡
"አዎ፤ ማህበር አለኝ"፡፡ ብሎ በቀጥታ ለማናገር ወደ ፈለገው ጉዳይ ገባ፡፡ "እንዴው እዛ ጉዳይ ጋር ሔደውልኝ ነበር ?"፡፡
"አዎ፤ ሔጀ ነበር፡፡ ያው! መቼም በአንዴ እሽ እንደማይባል አንተም ታውቃለህ፡፡ ለማንኛውም ለዛሬ አስራ አምስት ቀን ቀጥረውኛል፡፡ ቁርጡ ያኔ ይታወቃል" ::
"ቀጠሮ መስጠታቸውም ጥሩ ተስፋ ነው፡፡ እና እርሶንም በጣም አመሰግናለሁ"፡፡ ብሎ የማህበር ሰዓት ስለደረሰባቸው ወደየ ማህበራቸው ገቡ፡፡
አቶ ለማ ከማህበሩ እንደወጣ ወደ ቤቱ እየሔደ ፤ እንዴው እሽ ባለኝ፡፡ ልጅቷ ጎበዝ ተማሪ እና ጨዋ እንደሆነች መቼም አገር ነው የሚያወራላት፡፡ ፀባይዋም ቢሆን ምንም አይወጣላትም ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ እንዴው በተሳካልኝ፡፡ ሰዎች ስለእድላዊት መልካምነት ሲያወሩ የሰማውን ሁሉ በሃሳቡ እየደጋገመ እና እያወራ ሳይታወቀው እቤቱ ደረሰ፡፡
"ምነው ዛሬ ደግሞ አመሸህ? ማህበሩ ቶሎ አላለቀም እንዴ?" አለ አበበ ላባቱ፡፡
"አዎ፤ ዛሬ ደግሞ ቶሎ ወደ ማህበር አልገቡም ነበር፡፡ ማህበረተኛውም የት እንደ ሄደ እንጃ ፤ጠላውም አላልቅ ብሎን እኔም ይመሽብኛል ብየነው ፤ ሳያልቅ ትቸው ነው የመጣሁት"፡፡
ከዛቲ መልስ ቄስ አሻግሬንም አግኝቻቸው ነበር፡፡ እቄስ መልካሙ ጋር እንደ ሔዱልኝ እና የድጋሜ ቀጠሮውም ለዛሬ አስራ አምስት ቀን እንደቀጠሯቸው ነገሩኝ" አለው፡፡
አበበ ለእድላዊት አማላጅ እንደላከለት ሲነግረው በጣም ወደር የሌለው ደስታ ተሰማው፡፡ ለማግባት የሚያስፈልገውን ነገር ማሟላት እንዳለበት በመወሰን የጀመረውን የቤት ስራ ለመጨረስ እየተጣደፈ ነው፡፡
እድላዊት ግን እሽ ትበለውም አትበለውም ባያውቅም ማድረግ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ባለበት ሰዓት በህሊናው አንድ ሃሳብ ያቃጭልበታል ?
ተመስገን
ሊነጋጋ ሲል የወሰደው እንቅልፍ ተጫጭኖት ቶሎ አልተነሳም፡፡ ለትምህርት ከሚነሳበት ሰዓት አርፍዶ ነው የተነሳው፡፡ የእድላዊት ባል ማግባት እና ከትምህርት መቅረት እውነት ሆኖ ቀረ ማለት ነው?፡፡ እውነት ባይሆንማ ኖሮ ሳትቀሰቅሰኝ ባልቀረች ነበር፡፡ ከራሱ ጋር እያወራ ከመኝታው ተነሳ፡፡ ሽንት ቤት ተፀዳድቶ ተመለሰ፡፡
እናቱን ከቤት ሲወጡ እበር ላይ አገኛቸው፡፡ እንደማይተዋወቅ ሰው የእግዚአብሔር ሰላምታ ሳይለዋወጡ ተላለፉ፡፡ የቤተሰቦቹ ድርጊት እና እርህራሔ የሌለው ውሳኔ ያስከፋው ተመስገን ለማነጋገር አይደለም የሚጨክን አንጀት እና አቅም ቢኖረው ቤተሰቦቹን በደበደባቸው ነበር፡፡
ወደ እድላዊት መኝታ ቤት አመራ፡፡ የቤቱ በር ከውስጥ የተዘጋ መስሎ ገርበብ ብሏል፡፡ እስካሁን ያልተነሳችው አሟት ቢሆን ነው፡፡ የቤቱን በር አንኳኳው፡፡ መልስ የሚሰጥ አላገኘም፡፡ ደጋግሞ በሩን ተመለከተ፡፡ ከነጋ የተከፈተ አይመስልም፡፡
ደግሞ ለማንኳኳት ሰውነቱን ከነከነው፡፡ ውስጡ ፍራት ፍራት ተሰማው፡፡ እጆቹም ተንቀጠቀጡ፡፡ የሚሆነው ሁሉ ጠፋበት፡፡ ከውስጥ አልተዘጋ ይሆን እንዴ? ተጠራጠረ፡፡ በሩን ማንኳኳቱን ትቶ የሞት ሞቱን ገፋው፡፡ መዝጊያው ከውስጥ ምንም የያዘው ነገር ባለመኖሩ ተከፈተ፡፡ በፍርሃት ወደ ውስጥ ገባ፡፡
ከአልጋ በስተቀር እድላዊት አይደለችም ፤ የእድላዊት ልብስ እንኳን አላገኘም ነበር፡፡ የህሊና ፀሎት እንደሚያደርስ ሰው ቆሞ የስልክ እንጨት መሰለ፡፡ ደቂቃዎች አልፈው ከወሰደው የድንጋጤ ሰመመን ባነነ፡፡ በቀጥታ ወደ እናት አባቱ ቤት ሄደ፡፡ እድላዊትን የት ሄደች ? ብሎ እናቱን ጠየቀ፡፡
ወ/ሮ አሰገደች የሚናገሩት ፣ የሚያነሱት ፣ የሚቧጥጡት አጡ፡፡ የት ሔደች? የለችም መኝታዋ ላይ ፤ እንደፎከረችው አደረገችው ማለት ነው፡፡ ወይ ጉዴ! እያሉ ከተመስገን መልስ ሳይጠብቁ ኡኡታቸውን አቀለጡት፡፡
የአካባቢው ሰውና ጎረቤቱ ምን ደረሰባቸው? ምን አጋጥሟቸው ይሆን?፡፡ እየተሯሯጡ ግቢው ሰው በሰው አጥለቀለቁት፡፡ታዲያ የሰው መዓት ቢሰበሰብ እና እሪ እየተባለ ቢጮህም እድላዊት ልትገኝ አልቻለችም፡፡ ኡኡታ
ሰምተው ከመጡት ሰዎች መካከል ወ/ሮ ስንዱ "የት ትሔዳለች ፤ ከዚህ በፊት ከቤት ወጥታ አታውቅም፡፡
ወደ ዘመዶቿ ሔዳ ይሆናል፡፡ ሰው ልኮ ማጠያየቅ ነው" አሉ፡፡
ወ/ሮ አሰገደችን ለማረጋጋት ቢሞክሩም ወ/ሮ አሰገደች ግን የሚረጋጉ አይደለም፤ ጨርቃቸውን ጥለው የሚያብዱ ነበር የሚመስሉት፡፡
ቄስ መልካሙ በድንጋጤ የተነሳ የሚጮኸውን ጩኸት የራሳቸው ችግር አይደለም፤ ለተመለከታቸው ሰው ከነጭራሹም ጩኸቱን የሰሙት አይመስልም ነበር፡፡
ጎረቤት የሆኑት አቶ ማን ችሎት ማን ያዝልሃል፡፡ ቄስ መልካሙን ለማነጋገር እና የተፈጠረውን ለመጠየቅ ቢሞክሩም ቄስ መልካሙ አይናቸውን ከማቁለጭለጭ ውጭ መልስ የሚባል ለመመለስ አይደለም ከነጭራሹም ለመናገር አቅቷቸው ነበር፡፡ ተመስገን ከእናት አባቱ የተሻለ ቢሆንም ሰው የሚጠይቀውን ጥያቄ ግን እሱም መመለስ አልቻለም፡፡
የተሰባሰቡት ሰዎች ሁሉ የሚያደርጉት ጠፋቸው፡፡ ከመካከላቸው አንድ ሰው መኮንን ሃይሌ የሚባል ተነሳ
"አሁን ሁላችንም አብሮ ማጃበሩን እና ማልቀሱ ዋጋ ያለው አይመስለኝም፡፡ እነሱን አረጋግተን መላ ብንፈልግ የሚሻል ይመስለኛል፡፡ ብሎ ሃሳብ ሰነዘረ፡፡ የተሰበሰበው ሰው በሃሳቡ ተስማምቶ ወሮ አሰገደችንና ባለቤታቸውን አረጋግተው እድላዊትን ፍለጋ በየ አቅጣጫው ሁሉም ሰው ተበታተነ፡፡
እድላዊት ግን በዘመዶቿ ቤት አይደለም በዱር በገደሉም ልትገኝ አልቻለችም፡፡ ከጠፋችበት ቀን አንስቶ አየናት፡፡ በዚህ አልፋለች የሚል አይደለም የበላት ጅብ እንኳን ሊጮህ አልቻለም፡፡
ቄስ መልካሙ በልጃቸው መጥፋት ጥልቅ ሃዘን ተሰማቸው፡፡ እድላዊት ትሙት ትኑር ሳያውቁ "አይ! አንተ ሰማይ እና ምድርን የፈጠርህ ጌታ እንደዚህ በቁሜ እንዳዋረደችኝ እና እንዳሰቃየችኝ በቁሟ የሚያዋርድ ይስጣት፡፡ የፈጠሯትን ልጅ አምርረው ረገሟት፡፡

👍73❤6👏3
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
አላዛር አስራሁለተኛ ክፍል ተማሪና ነጋዴ እያለ ነው፡፡ በቀኑ በድካም የዛለ ሰውነቱን ለማሳረፍ ወደአልጋው የሚሄድበት ሰዓት ነው፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት ሆኗል፡፡ቢሆንም ግን ከመተኛቱ በፊት የእለቱን ሂሳብ ቆጥሮና ወጪና ገቢውን መዝግቦ ማጠናቀቅ አለበት..ይሄ ሁል ጊዜ ወደአልጋው ከመሄዱ በፊት መስራት ያለበት የግዴታ ስራው ነው..ግን መዝግቦ ከመጨረሱ በፊት ስልኩ ጠራ፡፡የማያውቀው ቁጥር ቢሆንም ከስራ ጋር የተገናኘ ይሆናል በሚል ግምት አነሳው፡፡
‹‹ሄሎ›
‹‹ሄሎ …አላዛርን ፈልጌ ነበር››ሳግ የተናነቀው የሴት ድምፅ ነው፡፡ግራ ገባው…፡፡በዛ ሰዓት እያለቀሰች እሱ ጋር የምትደውል ሴት ማን ነች..ለመገመት አንኳን አልቻለም፡፡
‹‹አዎ አላዛር ነኝ፡፡ ማን ልበል?››
‹‹በዚህ ምሽት ስለደወልኩልህ ይቅርታ፡፡አስካለ እባላለሁ፡፡››
አስካለ የሚባል ስም ያላት ሴት ቢያስብ ሊመጣለት አልቻለም፡‹‹ይቅርታ አስካለ… አላወቅኩሽም፡፡››
‹‹አታውቀኝም..የአባትህ ባለቤት ነኝ፡፡ ›
‹‹የአባትህ ባለቤት?››
‹‹አዎ ››
ሊገባው አልቻለም፡፡በመጀመሪያ ስለአባቱ ምንም ነገር መስማት አይፈልግም፡፡.ከዛም አልፎ አባቱ ባለቤት እንዳለው አሁን ገና መስማቱ ነው፡፡ከሁሉም በላይ ደግሞ ይህቺ የአባትህ ባለቤት ነኝ የምትል ሴት ለምን እንደደወለችለት መገመት አለመቻሉ ነው፡፡
‹‹እና በሰላም ነው?››
‹‹እኔ እንጃ፣አባት ምን ጠጥተው እንደመጡ አልውቅም…. እራሳቸውን ስተው አረፋ እየደፈቁ ነው፡፡እኔ ለአካባቢውም ለሀገሩም እንግዳ ነኝ፡፡ምን እንደማደርጋቸው አላወቅኩም፡፡ እጄ ላይ እንዳይሞቱ ፈርቼለሁ፡፡እባክህ አንድ ነገር አድርግ››አለችው፡፡
‹‹ለመሆኑ ቁጥሬን እንዴት አገኘሽው?››
‹‹ከአባትህ ማስታወሻ ደብተር ላይ ነው ፡፡ልጄ አላዛር ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ ከዛ ላይ ነው ያገኘሁት፡፡››
ግርም አለው…አንደኛ አባቱ አላዛር የሚባል ልጅ እንዳለው የሚያውቅ አይመስለውም ነበር…ቢያውቅ እንኳን በቁም ነገር የእሱን ስልክ ቁጥር በማፈላለግ በማሳታወሻው መዝግቦ ያስቀምጣል የሚል ቅንጣት ጥርጠሬ እንኳን አልነበረውም፡፡
‹‹እሺ ምን አልከኝ…?በፈጣሪ..ቢያንስ ለእኔ ስትል እርዳኝ፡፡›› ልስልስ እና እንስፍስፍ በሆነ የድምፅ ቃና ተማጸነችው፡፡
አረፋ እየደፈቁ ነው ከተባሉት አባቱ በላይ በሲቃ የምትንሰቀሰቀው የማያውቃት እንጀራ እናቱ አሳዘነችው፡፡ ‹‹እሺ በቃ መጣሁ….እቤቱ ከጠፋኝ ደውልልሻለው… ወጥተሸ ትቀበይኛለሽ፡፡››
‹‹እሺ አመሰግናለው..እባክህ ቶሎ በል፡፡››
ስልኩን ዘጋና ጃኬት ደርቦ ከመሳቢያ ውስጥ ብር አንስቶ ወደኪሱ ጨምሮ ወጣ….መጀመሪያ ጓደኞቹ ጋር ደወለ፡፡
‹‹አሌክስ ተኝተሀል እንዴ?››
በሻከረና በተዳከመ ድምፅ‹‹አዎ!! ምነው በሰላም ነው?››ሲል መለሰለት፡፡
‹የሆነ ችግር አጋጥሞኛል…አንድ ቦታ አብረኸኝ እንድትሄድ ነበር..፡፡››
አለማየሁ ከመኝታ ተነስቶ ልብሱን እየለበሰ‹‹ምነው በሰላም?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ፍጠን …ስትመጣ ነግርሀለው…››ብሎ ስልኩን ዘጋና የሚያውቀው ባለ ላዳ ጋር ደወለ..፡፡ላዳው መጥቶ ውስጥ ገብቶ ሲጠብቅ አለማየሁ ሰሎሜን አስከትሎ መጣ፡፡
‹‹እንዴ !!አንተን ና አልኩህ እንጂ እሷን ይዘህ ና ብየሀለው?››
‹‹ምንድነው ችግርችሁ? የሴት ጉዳይ ነው እንዴ…? ልመለስላችሁ?››አለች ሰሎሜ… በኩርፊያ፡፡
‹‹አረ አይደለም..በዚህ ለሊት በመንገላታትሽ አሳዝነሺኝ ነው››አላት፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ እሱም ጓደኛህ እኔም ጓደኛህ…..እሱ ካስፈለገህ እኔም አስፈልግሀለው ማለት ነው፡፡››
‹‹እሺ ግቡ››
ከኃላ ከፍተው ገቡ..ላዳዋ ልትንቀሳቀስ ስትል አለማየሁ‹‹ቆይ ሁሴንም ደውዬለት መጣሁ ብሏል.. ትንሽ እንጠብቀው››
አላዛር በሰማው ነገር ተበሳጨ‹‹እንዴ ማን ንገረው አለህ…?አሁን ሳምንቱን ሙሉ እንዳላጠና አዘናጋችሁኝ እያለ ሲነጫነች ነው የሚከርመው፡፡››
‹‹ባንነገርው ደግሞ‹እኔስ ጓደኛችሁ አይደለሁም ወይ?› ብሎ ሳምንት ያኮርፈናል››ሲል አለማየሁ መለሰለት፡፡
ሰሎሜ ‹‹እሱ እኮ….››ብላ ሀሳቧን ልትናገር ስትል ሁሴን ደርሶ የኃላዋን የላዳ በራፍ ከፍቶ ተቀላቀላቸው….ላዳዋ ተንቀሳቀሰች፡፡
እነዚህ አራት ጓደኛሞች ከአንድ መሀፀን እንደወጡ መንታ ልጆች ናቸው፡፡በክፉውም ቀን ሆነ በደጉ አብረው ናቸው፡፡
የአራቱ ጓደኝነት መነሻ ምክንያቱ አንድ ሰፈር ውስጥ ተፋፍጎ ከተሰራ ቤት ስለተወለዱ ብቻ አልነበረም፡፡የአራቱም እናቶች ቡና የሚጠራሩ የአንድ ክለብ ተጫዋች አይነት ስለሆኑ ነበር…አንዳችው ቤት ቡና ተፈልቶ ሁሉም እናቶች ሲጠሩ ሁሉም የየራሳቸውን ልጆች ይዘው ይመጣሉ…ከዛ ሁሉም ከእናታቸው እቅፍ ውስጥ እየሾለኩ እርስ በርስ የመጫወት ሙከራ ያደርጋሉ…ያ ደግሞ በተለየ መልኩ ከጮርቃነታችው ጀምሮ በተለየ ሁኔታ እንዲቀራረብ አደረጋቸው፡፡ የእናቶቻቸውን ጡት ሳይጥሉ የጀመረ ጓደኝነት …የእናቶቻችውን መሰባሰብ ሳይጠብቁ በራሳቸው ተጠራርተው በአንዳቸው ቤት በረንዳ ወይም በሆነ ብጣቂ ሜደ መጫወት ተጀመረ…፡፡
ከዛ ትምህርት ቤት የገቡትም አንድ ላይ በአንድ ወቅት ነበር፡፡ሌላው ይቅር አንዳንድ የማይዳረሱ መፅሀፎች አንድ ለሶስት ወይም ለአራት ሲሰጥ ሳይነናጋገሩ ነው የሚቧደኑት፡፡ከመሀከላችን አንድ ሰው ሲጠቃም አንድ ላይ ድንገት አጥቂውን ይወሩታል፡፡ማንም ቢሆን በቁመትም ሆነ በውፍረት ከእነሱ ቢበልጥ እንኳን አራት ሆነው አንደአንድ ለመፋለም ሲከቡት ይፈራል፡፡በዚህም ምክንያት ማንም እነሱን ለመጋፈጥ ድፈረቱ አይኖረውም፡፡
እንዳዛም ሆኖ በህብረት ከሌላው ሰው ጋር ከሚጣሉበት ይልቅ እርስ በርሳችው የሚጣሉበት ጊዜ በብዙ እጥፍ ይበልጥ እንደነበረ ትዝ ይለዋል፡፡የጥላችው 90 ፐርሰንት ምክንያት ግን ሰሎሜ ነች፡፡በመሀከላቸው ያላችው አንድ ብቸኛ ሴት ሁላችውም በሆነ መንገድ ከሌላቸው የተሻሉ ሆነው በሆነ መጠን ወደእራሳቸው የበለጠ እንድታጋድል ስለሚፈልጉ ሁሉ ጊዜ የጥቅም ግጭት በመሀከላችው ይፈጠር ነበር፤እና ሁሉንም እኩል በመቆጣት ጥላችውን አቁመው በስምምነት እንዲከቧት የምታስገድዳቸው እሷው ነች፡፡ሰሎሜ በዛ የጓደኝነት ክበብ ውስጥ ልክ እንደንግስት ንብ አይነት ነበረች፡፡
ንግስት ንብ ትውልድ ከማስቀጠል በተጨማሪ ፌርሞን የተባለ ኬሚካል ታመነጫለች፡፡ፌርሞን ሚስጥራዊ ኃይል ያለው ንጥረ ነገር ሲሆን በአንድ ቀፎ ውስጥ በጋራ የሚኖሩ ንቦችን የውል እና የጋራ ባህሪን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚረዳ ረቂቅ ኬሚካል ነው፡በዛ ኬሚካል አማካይነት ንግስቲቱ በዙሪያዋ ያሉትን እሰከ60 ሺ የሚቆጠሩ የንብ መንጋዎችን ሰጥ ለጥ አድርጋ ትመራለች ፤ ትቆጣጠራለች፡፡ፌርሞን ለንግስቲቱ የአገዘዛ እና የኃይል ምንጭ ከመሆኑም በተጨማሪ በመስክ ስራ ላይ ካሉ ንቦች ጋር መልዕክት የምትለዋወጥበት የመገናኛ አውታር ጭምርም ነው፡፡በተጨማሪ ፌርሞን በአንድ ቀፎ ውስጥ በህብረት ለሚኖሩ ንቦች እንደመታወቂያ ወረቀት ሆኖም ያገለግላል፡፡በአንዷ ንግስት የሚተዳደረው የንብ መንጋ ከሌላው ጋር ይለያል..ያ ማለት አንድ ንብ ከሌላ ቀፎ መጥቶ የተሳሳተ ቀፎ ውስትጥ ገብቶ ከሌሎች 60 ሺ ንቦች ጋር ቢቀላቀል ሰርጎ ገብ መሆኑን በቀላሉ ይለያል ማለት ነው፡፡
እንግዴህ ሰሎሜም ልክ እንደንግስቲቱ ንብ ሶስቱንም የምትቆጣጠርበት እና እንደፈለገች የምታዝበት የራሷ የሆነ ሚስጥራዊ መንገድ ነበራት፡፡

👍61❤20🥰2
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
////
ፀአዳ የ21 ዓመት አዋቂ ሴት ነች፡፡አገላለጹ ይጋጫል አይደል?የ22 አመት ወጣት ሆኖ አወቂ ሴት ነች ሲባል ፡፡አዎ እሷ የ15 አመት እና የ9 ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ድብን ያለ ፍቅር ያዟት ነበር፡፡በ16 ዓመት የልደት በአሏ በሚከበርት ቀን በወቅቱ የ19 ዓመት ጎረምሳና የ11 ክፍል ተማሪ ለነበረው የልቧ ሰው በፍደኝነት ድንግልናዋን አስረከበች፡፡ከሁለት ወር በኃላ ማርገዟን አወቀች… ነገረችው፡፡ከሳምንት በኃላ እሷን ሳይሰነበታት.. ደግሞ ሳይስማት…ደግሞ ቀሚስሽን ላውልቅ ፤ ጡትሽን ልጥባ ሳይላት እሷንም ሆነ ከተማዋን ጥሎ ውትድርና ተቀጥሮ ሄደ…ያንን የመሰለ አስቀያሚ ዜና የሰሚ ሰሚ ከሰው ነው የሰማችው፡፡ያንን የሰማች ቀን ሰማይ ምድሩ ነበር የዞረባት፡ያልጠና ጮርቃ ልቧ ስንጥቅጥቅ አለ….ደነዘዘች…… ፡፡በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ማርገዞን አወቀች…ሰማይ ምድሩ ዞረባት…እና በወቅቱ ሁለት ምርጫ ነበር የታያት ..አንድም በሆነ ዘዴ መርዝ በመጠጠት ወይም በገመድ ተንጠልጥሎ ብቻ በሆነ ዘዴ እራሷን ማጥፋት ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ ብን ብላ ሀገሯን ጥላ ወደማታውቀው ሀገር ሄዳ ህይወት እንዳደረጋቻት መሆን፡፡
….በምን አሳማኝ ምክንያት እንደሆነ ባታውቅም ሁለተኛውን መረጠችና ከተወለደችበትና ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ከሚኖርበት ዶዶላ ከተማ በአንድ አነስተኛ ሻንጣ ልብሷና እና ይጠቅሙኛል ያለችውን ዶክመንት ይዛ ወደአዳማ የሚሄድ መኪና ውስጥ ተሳፈረች፡፡እንግዲህ የህይወት ዘመን ባለውለታዋን የሆነውን ሚካኤልን የተዋወቀችው እዛ መኪና ላይ ነበር፡፡በወቅቱ አጋጣሚ ሆኖ ጎን ለጎን ነበር የተቀመጡት፡፡የተወሰኑ ቃላቶች እየተለዋወጡ ከተግባቡ በኃላ ድንገት ወዳልታሰበ ቁምነገር ያለው ውይይት ውስጥ ገቡ፡፡
‹‹አዳማ ነው የምትሄጂው ወይስ ወደአዲስ አበባ ታልፊያለሽ?
››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አላውቅም…››ስትል በደፈናው መለሰችለት፡፡
‹‹አልገባኝም››
‹‹እኔ እንጃ ..ከተመቸኝ አዳማ እቀራለው…ከለበለዚያ ወደአዲስ አበባ ሄዳለው…እድል እንዳደረገቺኝ ነው የምሆነው››
‹‹ማለት …ቤተሰብ ጋር ነው የምትሄጂው?››ጥያቄውን አሻሽሎ ጠየቃት፡፡
‹‹አይደለም…ስራ ፍለጋ ነው የምሄደው››
‹‹ስራ ፍለጋ….ምን አይነት ስራ?››
‹‹የተገኘውን ስራ፡፡››
‹‹ምነው… ቤተሰቦችሽ የት ናቸው?››
‹‹ዶዶላ ነበር የሚኖሩት …ማለት እናቴ ና እኔ ብቻ ነበር..አሁን እናቴ ስለሞተች ብቻዬን ቀረው…እናቴ የሞተችበት ሀገር ደግሞ ተረጋግቼ መኖር አልቻልኩም..ስለዚህ የእድሌን ልሞክር ብዬ ዝም ብዬ ነው እየተጓዝኩ ያለሁት….››ንግግሯን ተከትሎ ከአይኖቾ እንባዋ እየተንከባለለ ፊቷን በማጠብ ወደታች ይወርድ ጀመር፡
የሚካኤል አይኖቸ እንባ አቀረሩ‹‹በጣም አዝናለሁ….አይዞሽ እሺ››
‹‹አረ ችግር የለውም…መኖር ካቃተኝ መሞት አያቅተኝም››ስትል የበለጠ አስደንገጭ ነገር ነገረችው፡፡እሱ ደግሞ እራስን ማጥፋትን በተመለከት እህቱንና እናቱን በቅርብ ያጣ ሰው ስለነበር በቀላሉ ነው ስሜቱ የተነካው፡፡እና በተቻለው መጠን ሊረዳት ወዲያው ነው በውስጡ ውሳኔውን የወሰነው፡፡
‹ኸረ በፍጽም እንደዛ አታስቢ…ቆይ ትምህርት ተምረሻል?››
‹‹አዎ ግን.. ገና ዘጠነኛ ክፍል ነኝ››
‹‹እንግዲያው ለአንቺ የሚሆን ስራ አለኝ››በማለት ያልጠበቀችውን የሚያስፈነጥዝ የምስራች አበሰራት፡፡ማመን አልቻለችም‹‹እየቀለድክብኝ አይደለም አይደል?››
‹‹አይ እውነቴን ነው…አዳማ ላይ ቡቲክ አለኝ…ፍቅረኛዬ ነች የምትሰራው..ግን በቅርብ ትምህርት ስለምትጀምር የሚረዳት ሰው ያስፈልጋታል…እና ሰው ለመቅጠር እያፈላለግን ነበር››
‹‹በጣም ደስ ይለኝ ነበር…ግን ምንም አይነት ተያዥ እኮ የለኝም..ያለኝ መታወቂያ እንኳን የትምህርት ቤት ብቻ ነው››ስትል ስጋቷን ያለምንም መሸፋፈን በግልፅ ነገረችው፡፡
‹‹ችግር የለውም..እኔ ዋስ እሆንሻለው››ሲል ከስጋቷ ገላገላት፡፡
እንባዋን መገደብ ስላልቻለች ለሁለተኛ ጊዜ ማለቀስ ጀመረች..ያሁኑ ለቅሶ ግን የደስታ ነበር፡፡
‹‹ኸረ አታልቅሺ..በፈጣሪ እኔ ሰው ሲያለቅስ ማየት አልፈልግም››ብሎ ከኪሱ ሶፍት አወጣና አቀበላት…..ተቀበለችና ፊቷን ጠረረገችበት፡፡
እንዳለው አዳማ እንደወረዱ ቀጥታ ይዟት ወደ ቤት ሄደ… ወስዶ ከፍቅረኛው ጋር አስተዋወቃት፡፡በመሰራት ላይ ካለው ጅምር ቤቱ አንድ ክፍል ቤት አስተካከለና ዕቃ አሟልቶ አስረከባት፡፡ሰው ሳይሆን መላአክ መስሎ ተሰማት፡፡እሱም ብቻ ሳይሆን ፍቅረኛው አዲስ አለምም በልዩ ሁኔታ እንደጓደኛ ብቻ ሳይሆን እንደታናሽ እህት ተቀብላ ወደደቻት….በዚህም ፀአዳ ለረጅም ወራቷች ስታማርረው የነበረውን ፈጣሪዋን ይቅርታ ጠይቃ ማመስገን ጀመረች፡፡
በዚህ ሁኔታ ነው ሚካኤል እና ፀአዳ የተዋወቁት..፣ከዛ ብዙም ሳትቆይ ከቤተሰብ ጠፍታ የመጣችበትን ትክክለኛ ምክንያት ለሚካኤል እና ለፍቅረኛው ለአዲስአለም ነገረቻቸው…እንደዛ ያደረገችው ሆዷ እየገፋ ሲሄድ የግድ መጋለጧ የማይቀር መሆኑን ስለተገነዘበች ነው፡፡
ከዛ ልጇን በእጇቸው ላይ ወልዳ ከእሷ እኩል እየተንከባከቡ አሳድጉላት፡፡ዛሬ ላይ እነሱም አንድ ቤት ተጠቃለው መኖር ከጀመሩ አራት አመት ያለፋቸውና የሶስት አመት ልጅ ያላቸው ሲሆን በተለያየ ምክንያት በዚህ ወር ይሁን… በሚቀጥለው አመት እያሉ ሲያዘዋወሩት የነበረው ሰርጋቸውን ለመደገስ አሁን ቀን ተቆርጦ በጀት ተመድቦለት እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡
እና ፀአዳም ይሄንን የወዳጆቾን ሰርግ ልዩ እና በህይወት ዘመናቸው ሙሉ የሚያስታውሱት እንዲሆን ትፈልጋለች፡፡ለዛ ነው ምንም ነገር እንዳይጎድል ለወራት ቀንና ለሊት እንቅልፍ አጥታ ስትለፋ የሰነበተችው ፡አሁን አንድ ነገር ብቻ ይቀራታል፡፡በዚህ ሰርግ ላይ ለሚካኤል ብቸኛ ዘመድ የሆነውን አንድ ወንድሙን እንደምንም አሳምና ሰርጉ ላይ እንዲገኝ በማድረግ ሰርፕራይዝ በማድረግ ደስታውን ሙሉ ልታደርግለት እቅድ አውጥታለች፡፡ሚካኤል ለረጅም ጊዜ አውርቶትና አግኝቶት የማያውቀው ወንድሙ ዘሚካኤል በሆነ ተአምር በሠርጋቸው ላይ እንዲገኝ ለማድረግ ከልቧ ቆርጣ ተነስታለች።
ይህንን ሀሳብ በአእምሮዋ ስታሰላስልና ስትዘጋጅበት ከወር በላይ ነው የቆየችው፡፡በጣም በብዙ ጥረትና በብዙ ድካም መውጫ መግቢያውን ፕሮግራሞቹንና ልምዶቹን ስታጠና ነበር ሰነበተችው፡፡በቋሚነት በሚኖርበት አዲስአበባ እሱን ለማግኘት ፈተና ነው፡፡ በትክክል እንዴት እሱ በሀሳቧ እንዲስማማ ለማድረግ እንደምትችል እስካአሁን ድረስ በትክክል አላወቀችም።ምክንያቱም ዘሚካኤል እንደማንኛውም ሰው በቀላሉ አግኝተውት የሚያናግሩትና የሚያሳምኑት አይነት ሰው አይደለም፡፡እሱ ሚሊዬኖች የሚያብዱለት ከሀገሪቱ ዝነኛ ድምጻዊያን መካከል ከዋናዎቹ አንደኛው ነው፡፡በዛው ልክ ፕሮግራሞቹ የተጣበቡ..አጃቢዎች የበዙ ሰው ነው፡ቢሆንም ይሄንን ማድረግ አለባት፡፡ይሄ ለምትወዳቸው ና የእድሜ ዘመን ባለውለታዋ ለሆኑት ባልና ሚስቶች እንደስጦታ አድርጋ ልታቀርብላቸው ያሳበችው ትልቅ ስጦታ ነው፡፡፡

👍76❤13👏3🔥2👎1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
ፀጋ አባቷ እቅፍ ላይ እንዳለች ፈገግ በማለት የራሄልን ትኩረት ለመያዝ ሞከረች፣ በዚህ ጊዜ እናቷ ጣልቃ ገብታ መናገር ጀመሩ ፡፡
‹‹ራሄል፣ ከዶክተር ኤሊያስን ጋር እንድትተዋወቂ እፈልጋለሁ። እሱ የፀጋ ሐኪም ነው…ዔሊ ይህች ልጃችን ራሄል ናት።››
ዶ/ሩ በስሱ ፈገግ በማለት ‹‹ሰለአንቺ ብዙ ሰምቼያለው ..አንድ ቀን እንደምንገናኝ አምን ነበር›› በማለት እጁን ወደ እሷ ዘረጋ
ጨዋነት ያልጎደለው ፈገግታ ፈገግ አለችለት እና የዘረጋውን እጅን ጨበጠች፡፡ወላጆቿ ከእሱ ጋር አማች ለመሆን እያሴሩ እና እሱንም እያደፋፈሩት እንደሆነ ታውቃለች…ቢሆንም የሱ ጥፋት አልነበረም።
‹‹የሞተር ሳይክሉ ሰው ነህ አይደል?››
‹‹አዎ… ነኝ›› አላት፡፡
እጁ ሞቃታማ፣ ጣቶቹ ረዣዥም ነበሩ፣ እና ሲነካት ለረጅም ጊዜ በእንቅልፍ የመወሰድ አይነት የግንዛቤ ብልጭታ በአእምሯዋ ተንፀባረቆ ነበር….ስሜቱን አልወደደችውም። ‹‹በዛ ፍጥነት ስታበር ገርሞኝ ነበር››አለችው፣ትንፋሽ ወሰደችና ‹‹ደግሞ ዶክተር መሆን እና …..››
‹‹እና ምን?›› ከአንደበቷ ቀልቦ ጠየቃት።
‹‹ከተሸከምከው ሃላፊነት አንፃር ሞተር ማሽከርከር….አንድ ነገር ቢደርስብህስ?››
‹‹ለጊዜው አቅሜ የሚፈቅደው ርካሹ እና ፈጣኑ መጓጓዣ ሞተር ነው. እና ደግሞ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አደርጋለሁ.››ሲል መለሰላት፡፡
ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ‹‹ሁሉም የሚያቀነቅናቸው ታዋቂ የመጨረሻ ቃላቶች ናቸው…ጥንቃቄ አደርጋለው..››አለች በንዴት፡፡
በመጠኑ ደፍረስ ባሉት አይኖቹ በትኩረት ተመለከታት…ከመተዋወቃቸው እየሰጠችው ያለው ጠንከር ያለ አስተያየት ግራ አጋብቷታል…
እናትዬው ፀጋን ከአቶ ቸርነት እቅፍ ወሰድና፡፡‹‹በሉ ወደምግብ ጠረጴዛው እንሄድ….ምሳ ዝግጁ ነው››ሲሉ አወጁ፡፡
ሁሉም ወደምግብ ጠረጴዛው ተከታትለው ሄዱ፡፡ራሄል፣ የተለመደውን ቦታዋ ላይ ተቀምጣለች፣ ዔሊያስ ከእሷ ፊት ለፊት ተቀምጠ።››
አቶ ቸርነት በቀኝ እጇቸው የሴት ልጇቸውን እጅ ግራ እጇቸው ደግሞ በዔሊያስ ትከሻ ላይ ዘረጉና። ‹‹ብዙውን ጊዜ ከምግብ በፊት እንፀልያለን››ሲሉ ለዔሊያስ ገለጹለት።
‹‹እኔ ደስተኛ ነኝ. በቤተሰቦቼ ቤትም ስርዓቱ እንዲሁ ነው.››ሲል መለሰ፡፡አባቷ እጇን ጨምቀው ነበር፣መጸለይ ሲጀምሩ አንገቷን ዝቅ አደረገች።አባቷ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገሩ ማዳመጥ ብትጀምርም ከጸሎቱ ጋር በልቧ መቀላቀል አልቻለችም። እሷ በሀይማኖት ስርዓት ውስጥ ተወልዳ ያደገች ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ከመስመር ወጥታለች። አምላክ በህይወቷ ጣልቃ እንዲገባ አትፈልግም ወይም ደግሞም እሱ ራሱም ለእሷ ደንታ እንደሌለው ታምናለች።ስለዚህ ለምን ትጨቀጭቀዋለች፡፡ ወላጆቿ በዚህ መሳኔዋ ደስተኛ እንዳልሆኑ በደንብ ታውቃለች ቢሆንም ግን ርቀታቸውን በመጠበቃቸው ታመሰግናቸዋለች። እና ምናልባት ወደቀልቧ እንድትመለስ ዘወትር ለእሷ በድብቅ ይፀልዩላት ይሆናል፡፡
ፀሎቱ ተገባዶ በ‹‹አሜን›› እንደተዘጋ እናትዬው ‹‹በሉ እራሳችሁን አስተናግዱ ››አለቻቸው፡፡ሁሉም ፊት ለፊቱ ባለው ሳህን ላይ ፊለፊታቸው ከተደረደሩት በርካታ የምግብ ዓይነቶች የሚፈልጉትን መጠን መውሰድ ጀመሩ፡፡ተ
‹‹ከቻልክ ክትፎውን አቀብለኝ››ስትል ራሄል ወደኤልያስ እያየች አጉተመተመች፣
እናትዬው የራሄልን አስተያየት ውድቅ በማድረግ እጆቿን እያወዛወዘ ‹‹እስኪ እንደአንበሳ ስጋ ማሳደድሽን አቁሚ።››በማለት ገሰፃት፡፡ ቀጠል አደረጉና ‹‹ለሚያገባሽ ሰው አዝንለታለው።››ሲሉ አከሉበት፡፡
‹‹ደህና፣ ደስ ሚለው ነገር ፍቅረኛ የለኝም ››አለች ራሄል፡፡
‹‹እነዚህማ የተለመዱ ቃላቷችሽ ናቸው››
እናቷ በራሄል ንግግር ተከፍተው ‹‹አንድ ቀን ያንን በብቸኝነት የቀዘቀዘ አፓርታማሽን እርግፍ አድርገሽ ጥለሽ እንደ ዶ/ር ኤሊያስ ቤት አይነት ግቢ ወዳለው ቤት ትቀይሪ ይሆናል።››ሲሉ ምኞታቸውን ተናገሩ፡፡
እናትዬው ወደ ዶ/ሩ ዘወር አሉን‹‹ቤትህን በማስተካከል ላይ እንዳለህ ሰምቼያለው?››
‹‹በእውነቱ ወንድሜ ቢንያም ነው እየተከታተለው ያለው። እሱ አናጺ ነው። ስለ ኩሽና አሰራር አንዳንድ ውሳኔዎችን እንድወስን እየጨቀጨቀኝ ነበር, ነገር ግን ዘመናዊ ይሁን ወይም ባህላዊ ጭብጥ ይኑረው የሚለውን ለመወሰን እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም››
አቶ ቸርነት‹‹ራሄልን ይዘሀት ብትሄድ ልትረዳህ ትችል ይሆናል››የሚል ሀሳብ አቀረቡለት። ዔሊያስ የራሔልን መኮሳተር ችላ በማለት እንደ ተወደደ ልጅ ፊቱ እያበራ ነው።
አንቷም ‹‹አዎ የእኔ ልጅ …በኢንቴርዬር ዲዛይን ላይ በጣም ጎበዝ ነች።››ሲሉ የአባትዬውን ሀሳብ ደገፉ፡፡
ራሄል ስለእሷ የተሰጠ ያለው አስተያየት ከየት እንደመጣ አታውቅም። ወላጆቿ አፓርታማዋን በሚጎበኙበት ጊዜ በዕቃዎቾ፤በምንጣፎች እና በመኝታ ቤቷ ቀለም ..ብዙ ብዙ ኔጌቲቨ የሆነ አስተያየት ሲሰጧት እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ እንደውም እናቷ ‹ጥቂት እንኳን ለስሜቷ ሳይጨነቁ ቤቷን መኖሪያ ቤት ሳይሆን ሙዚየም እንዳስመሰለችው ነግረዋት ነበር፡፡
‹‹የምፈልገውን በትክክል አውቃለሁ። ትልቁ ችግሬ ግን ውሳኔዎችን ለመወሰን ጊዜ ማግኘት አለመቻሌ ነው ›› ሲል ኤሊያስ መለሰ።
ራሄል የሆነውን ነገር የተረዳች መስላ‹‹እንድትጨርሰው የምትገፋፋህ ሴት የለችም?››ስትል ጠየቀችው፡፡
አባቷ ራሄልን በግንባራቸው ገፆት ፡፡
ዶ/ሩ ‹‹ለጊዜው አቋሜ ልክ እንደአንቺው ነው….ለሴት ዝግጁ አይደለሁም››ሲል መለሰ።
ራሄል ውይይቱ ወደ መሃል ከተማ የትራፊክ ፍሰት፣ የኑሮው ውድነትና ፣ እና የፖለቲካ ውዥንብር.እና የሰላም እጦት የመሳሰሉት ጉዳዬች ላይ ሲያተኩር እፎይ አለች፡፡
በመሀል ወደ ዶ/ሩ አትኩራ እየተመለከተች ‹‹በቅርቡ የኖብል ፋውንዴሽን አመታዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አለ።በዝግጅቱ ላይ መገኘትህን ማረጋገጥ አለብህ››አለችው፡፡
‹አረ ችግር የለውም..አታስቢ እገኛለው››ሲል ቃል ገባላት፡፡
እናትዬው‹‹ቀኑ ደረሰ እንዴ..?እንግዲህ በስራ ጫና ድራሽሽ ሊጠፋ ነው››ሲሉ ስጋታቸውን ገለፁላት፡፡
ራሄል ‹‹እማዬ ደግሞ ….እኔ ብቻዬን የማደርገውን አስመሰልሺው ። አብዛኛውን ስራ የሚሰሩልኝ ትላልቅ ሰራተኞች አሉኝ እኮ››
‹‹ነገር ግን ለሰራተኞችሽ በቂ ውክልና አትሰጪም።ቅድስትን ለመተካት እነዚያን ሁለቱን ረዳቶች መቅጠርሽን ስሰማ ብዙ የስራ ጫናሽን ያቃልሉልሻል ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን አሁን እንደማየው ከሆነ የበለጠ ስራ ነው ያበዛብሽ፡፡››
‹‹ሰራተኞቹ በጣም አዲስ ናቸው ። ፋይሎቹን ብቻ ሰጥቻቸው ሁሉንም ነገር በራሳቸው እንዲቋቋሙት መጠበቅ አልችልም።››
‹‹ዬኒቨርሲቲ ዲግሪ ያላቸውና …በደንብ የሰለጠኑ ናቸው እኮ።››
‹‹አዎ ትክክል ነሽ..ግን የፋውንዴሽኑን ስራ በተመለከተ ትንሽ ተጨማሪ ልምድ ያስፈልጋቸዋል፣ሁሉም ሰው ወደሆነ አዲስ ስራ ሲሄድ ለተወሰነ ጊዜ ከአሰራሩ ጋር እስኪለማመድ አዲስ ሆኖ መገኘት አይቀርም››ለእናቷ ሌላ የማስጠንቀቂያ እይታ ሰጠቻት። ይህን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በማያውቁት ሰው ፊት መወያየታቸውን አልወደደችውም ።
‹‹ውዴ እወድሻለሁ፣ ግን ደግሞ አውቅሻለሁ።››ሲሉ እናትዬው በአቋማቸው መፅናታቸውን አረጋገጡላት፡፡
የራሄልን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት ‹‹እና ሁሉንም ነገር መቆጣጠር እንደምትችይ ማሰብ ማቆም አለብሽ። አንዳንድ ነገሮችን ለእግዚአብሔርን መልቀቅ አለብሽ።››ሲሉ ንግግራቸውን ደመደሙ፡፡

❤59👍7
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////
ጤና ይስጥልኝ..ከዞኑ ዋና አቃቢ ህግ ቢሮ ክብሩ አቃቢ ህግ አቶ ግርማን ወክዬ ነው የመጣሁት ….ስብሰባው በእኔና እና በእናንተ መካከል ይደረጋል ማለት ነው፡፡››የሚል ያልተጠበቀ አይነት አጭር ማብራሪያ ሰጠች፡፡
ከመሀከለኛው ወንበር የተቀመጡት በእድሜያቸው መጨረሻ ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ሰው"ምንም ችግር የለውም ለአንቺ እና ለሀለቃሽ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኞች ነን…እኔ ዳኛ ዋልልኝ እባላለው፡፡እሱ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኩማንደር ገመዶ ይባላል፡፡ሁለት ሰዎች ተራ በተራ እየጠቆመ። "እሳቸው አቶ ፍሰሀ ይትባረክ ይባላሉ እሱ ደግሞ ልጃቸው ጁኒየር ይባላል።የሶሌ ኢንተርፕራይዝ ዋና እና ምክትል ስራአስኪያጅና ባለቤት ናቸው፡፡የሶሌ ኢንተርፕራይ ማለት ከተማዋ የጀርባ አጥንት የሆኑትን በጣም
በርካታ ድርጅቶችን በጥምረት የሚያስተዳድር ግዙፍ ድርጅት ነው፡፡አቶ ፍሰሀ እና ልጃቸው በከተማዋ እጅግ የተከበሩ እና የተመሰገኑ ግለሰቦች ናቸው፡፡››ሲሉ የማስተዋወቅና የመግቢያ ንግግር አድርገው ከጨረሱ በኃላ ራሷን እንድታስተዋውቅ አይን አይኗን ይመለከቷት ጀመር፡፡
አለምም የዳኛውን ማብራሪያ በፅሞና ስታዳምጥ ከቆየች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህ ከፊት ለፊቷ ያሉትን ዳኛው የዘረዘሯቸውን ሶስት ሰዎች በማየቷ እንግዳ እና ሀይለኛ የማወቅ ጉጉት በውስጧ ሲንተገተግ ተሰማት፡፡በውስጧ ለእነሱ ያዳበረችው ጥላቻም ሲገለባበጥ ይታወቃታል፡፡ እነሱ ስለእሷ እና ስለ ስብሰባው አለማ ለማወቅ እንደጓጉ ሁሉ እሷም እነሱን ለማወቅ ፈልጋለች፣
አለም መጀመሪያ አቶ ፍሰሀን ነው የተመለከተችው….በእድሜ ከዳኛው ብዙም የሚያንስ አይመስልም…ግን እንደዳኛው ግርጅፍጅፍ አላለም፡፡ሰውነቱን በትኩረት ላየ‹‹አሁንም ገና እጅ አልሰጥም ››እያለ የሚፎክር ይመስላል፡፡ፊቱን በትኩረት ስትመለከት መሰላቸቱን ታዘበች፡፡የበጋው የከረረ ጸሀይ እና ፀሀይን ተከትሎ ያለው ሙቀት ያደከመው ይመስላል፣ የማሰብ ችሎታ ያላቸው የሚመስሉ ደማቅ ጥቋቁር አይኖቹ አፈጠጡባት።
አለም ከእሱ አይኗን ነቀለችና ቀጥሎ ወደተቀመጠው ኩማንደር አዘዋወረች፡፡ሙሉ የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ነው፡፡ጭንቅላቱ ላይ ያጠለቀው የፖሊስ ኮፍያ ወደታች አዘቅዝቆ ብድር እንዳለበት ሰው ከፊል ፊቱን እንዲሸፍን አድርጎታል፡፡ እድሜው አርባዎቹ አጋማሽ ላይ እንዳለ ብትገምትም ሰውነቱ ግን አሁንም የጎረምሳ ነው…ከፊቱ ላይ ምንም ማንበብ አልቻለችም ፡፡ቀዝቃዛና ስሜታ አልባ ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡ አካሉ ብቃት ያለው እና ጠንካራ ይመስላል። ማንም ሰው ከእሱ ጋር አካላዊ ፀብ ውስጥ ገብቶ መጣላትን ይጸየፋል። በዛ ላይ ጨካኝና ተንኰለኛ መሆኑን በእይታ እንኳን መገመት ያን ያህል ከባድ አይደለም፡፡ በመጨረሻ ጁኒዬርን ተመለከተች፤በእድሜ ከኩማደሩ ጋር እኩያ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ በሌሎች ነገሮች ግን ተቃራኒ ናቸው፡፡ጁኒዬር ከሁለቱም በተለየ ገራገር ሰው ይመስላል፡፡ፈገግ ሲል ልዩ አይነት መስህብ አለው ። ቀጥ ያሉ ነጭ ጥርሶቹ ብልጭ ድርግም ሲያደርጋቸው ቀልብን ይገዛሉ፡፡ ጥቁር ደማቅ አይኖቹ ከአባቱ በተለየ የጠለቀ ሀዘን ይነበብባቸዋል፡፡ ደግሞ ውብ ነው፡፡የወንድ ቆንጆ፡፡
በሽርፍራፊ ሰከንዶች ሁሉንም ገምግማ ካጠናቀቀች በኃላ ጉሮሮዋን አሟሸችና ስሟን ለመስማት በጉጉት እየጠበቁ ወዳሉት አራት ጥንድ አይኖች እየተመለከተች ።
"እኔ አለም ጎበና እባላለሁ፣ ጎደኞቼ አሌክስ ይሉኛል፡፡የሶሎሜ ሴት ልጅ ነኝ።"አለች
ንግግሯን ተከትሎ በቤቱ ኒዩክሌር ቦንብ የፈንዳ ይመስል በሶስትም ሰዎች ላይ የታየው ድንጋጤ የተለየ አይነት ነበር፡፡ዳኛው ግን ምኑም ስላልገባቸው የሌሎቹ መደንገጥ ድንግርግራቸው እንዲወጣ ነው ያደረገው…ለተወሰኑ ደቂቃዎች በክፍሉ ፍፁም አይነት ዝምታ ተንሰራፋ።
ዳኛው ግራ በመጋባት "ሰሎሜ ማን ናት?"ሲሉ ጠየቁ።
አቶ ፍሰሀ ወንበሩ ላይ እንደ ተሰባበረ አሻንጉሊት ወደ ኋላ ተንሸራተተና
"አንቺ…የሰሎሜ ሴት ልጅ….?
አምላኬ..እኔ አላምንም." አለ፡፡
ጁኒየር በሹክሹክታ" የማይታመን ተአምር።አንድ ሰው ህልም ነው ቢለኝ ደስ ይለኛል?" ሲል ተሰማ፡፡
በጡረታ መውጫው በር ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ዳኛ አሁንም ግራ እንደተጋቡ ነው። ሁሉም ድንጋጤ ውስጥ ስላሉ ለእሳቸው ማንም ትኩረት አልሰጠም።አባትና ልጅ ፊቷን በደንብ ለማጥናት አፈጠጡባት …አይኖቾ ከዘመናት በፊት ከሚያውቋት እናቷ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለቸው በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል።በደንብ ልብሱ ላይ የወታደር ኮፍያ ያጠለቀው ኩማንደር አሁን በትካዜ እግሯቹን እያወዛወዘ እንደሆነ አስተዋለች፡፡
"ከዚህ ሁሉ አመት በኋላ እዚህ ምን ልትሰሪ መጣሽ ?" አቶ ፍሰሀ ነው ያለይሉኝታ የጠየቋት።
‹‹ምን ልትሰሪ መጣሽ ነው..?ወይስ እንኳን ደህና መጣሽ?››በማሽሞጠጥ መልስ ሰጠች፡፡
"ስንት አመት ሆነሽ?" ጁኒየር የጠየቀው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር፡፡
"ሃያ አምስት." አለም ትክክለኛ እድሜዋን ነገረችው፡፡
"አያትሽ እንዴት ነች?"
"በአሁኑ ጊዜ አርጅታለች..በሜቅዶኒያ የአረጋዊያን መንከባከቢያ ተቋም ውስጥ ነው የምትገኘው…የጡረታ ደሞዟን ይዛ እዛ ገብታለች..በካንሰር በሽታ ተይዛ የመሞቻ ጊዜዋን እየተጠባበቀች ነው።
ማለቴ ኮማ ውስጥ ነች።››
"ይህን በመስማቴ አዝናለሁ."አለ ጁኒዬር፡፡
"አመሰግናለሁ።"ስትል በትህትና መለሰችለት፡፡
"ይህን ሁሉ ጊዜ የት ነበር የምትኖሪው?"አቶ ፍሰሀ ነው ጠያቂው፡፡
ህይወቴን በሙሉ አዲስ አበባ ነው የኖርኩት፡፡ቢያንስ እኔ እስከማስታውሰው ድረስ። እዚያው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን አጠናቅቄ ወደ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍልን ተቀላቀልኩ።ከአራት አመት በፊት ነው ግራጅዌት ያረኩት..እና ሶስት አመት እዛው አዲስአበባ አንድ የውጭ ካምፓኑ ውስጥ ተቀጥሬ ስሰራ ነበር..እና አሁን ለዞኑ ምክትል አቃቢ ህግ ሆኜ ከተመደብኩ አንድ ሳምንት ሆነኝ ።"
"የህግ ትምህርት ቤት ተመርቀሽ….እዚ የእኛ ዞን አቃቢ ህግ ። ደስ የሚል ነው››ጁኒየር በፈገግታ ተውጦ ተናገረ ፡፡
በዋናው አቃቢ ህግ ጥያቄ አቅራቢነት ይህንን ስብሰባ እንዲያዘጋጁ የጠየቁትና ያዘጋጁት አዛውንቱ ዳኛ ሁኔታው ምንም አላመራቸውም… ፡፡
"እንደዚህ አይነት ልብ የሚነካ አይነት መገናኘትን እጠላለሁ፣ ግን አሁንም በጨለማ ውስጥ ነኝ..ስለሚካሄደው ነገር ምንም የገባኝ ነገር የለም፡፡››ሲሉ ብሶታቸውን ተናገሩ፡፡
‹‹ሶሎሜ ማለት የእሷ እናት ነች፡፡እሷ ከመወለዷ በፊት የጁኒዬርና የኩማንደሩ የቅርብ ጓደኛ ነበረች፡፡ከዛም አልፏ ቤተሰብ ነበርን….ነፍሷን ይማርና ፈፅሞ የማይለያዩ የልብ ጓደኛሞች ነበሩ…. ››ከዚያም ጥቋቁር አይኖቹ ደመና አጠላባቸውና በሀዘን ራሱን ነቀነቀ..እና ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ "ሞቷ ለሁለችንም ከፍተኛ ሀዘን ያስከተለ ነበር….ክብር ዳኛ … የገዳዩን ችሎት እኮ እርሶ ነበር ያስቻሉት…የእኔ የእርባታ ግቢ ውስጥ አንድ እብድ በቢላዎ ወግቶ ከገደላት በኋላ ራሱን እስር ቤት ውስጥ ያጠፋው…፡፡››
የዳኛው ፊት ሲጠቁር በግልፅ ተመለከተች‹‹እኔ እንጃ ትዝ አላለኝም…የሽማግሌ ነገር ስንትና ስንት ችሎት አስታውሳለው ብለህ ነው?››በማለት ሸፋፍነው ለማለፍ ሞከሩ፡፡
አቶ ፍሰሀ ራሱን ለመቆጣጠር የተወሰነ ጊዜ በፀጥታ አሳለፈና። " ለማንኛውም ስለ አለም ሆነ ስለ አያቷ የሆነ ነገር ስንሰማ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያችን ነው።
ለማናኛውም እንኳን ወደእናትሽ የትውልድ ከተማ በሰላም መጣሽ››አላት፡፡

❤53👍3😢2🔥1