አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከሌላ ፕላኔት የመጣ ፍጡር ይሆን እንዴ?›› ስል አሰብኩ፡፡ መጨረሻዬም አጓጓኝ፡፡ በዚህ ቅፅበት እጁን ወደ ጃኬት ኪሱ ሲሠድ በጨረፍታ ተመለከትኩ፡፡ ብሞት ግድ የሌለኝ መስሎ ይሠማኝ ነበር፡፡ ይህቺን አለም ገና እንዳልጠገብኳት የተረዳሁት ግን በዚህ ክስተት ነው፡፡የሚያብረቀርቅ ጩቤ አወጣ ፤የራሱን እጅ በጭካኔ ሸረከተው፡፡ ደሙ መስመር ሰርቶ መንጠባጠብ ጀመረ፡፡ የተለያዩ ህብረ - ቀለማት አይኖቼ ላይ ተመላለሱብኝ፤ቀስ በቀስ ከማንነቴ እየተነጠልኩ..እየተፋው ሲሄድ ይታወቀኛል፡፡

ወደ ጥልቅ ገደል እየተንሸራተትኩ ምጓዝ

መስሎ ተሠማኝ፡፡

ለምን ያህል ጊዜ እራሴን ስቼ እንደቆየሁ ትዝ አይለኝም፡፡ አይኖቼን በፍራቻ ስከፍታቸው ባዶ ክፍል ውስጥ ባዶ ሆኜ ብቻዬን ነው ያለሁት፡፡ ዙሪያ ገባውን በጥንቃቄ ቃኘሁ፡፡ የቤቱ ግድግዳ በቀይ ቀለም ተዥጎርጉሯል፡፡ ፅሁፍ ነው፡፡ የሚነበብ ፅሁፍ፡፡ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ‹‹አፈቅርሻለሁ...አምርሬም እጠላሻለሁ›› የሚል ፅሁፍ አነበብኩ፡፡አይኖቼን ወደ ራቁት ሠውነቴ ስመልስ እንደ ግድግዳው በፅሁፍ ሳይሆን በምልክት ተዥጎርጉሯል፡፡ ሁለቱ ጡቶቼ የራይት ምልክት አለባቸው፣ እንብርቴ አካባቢ የኤክስ ምልክት ይታያል፡፡ግራ ገባኝ እስከዛን ግዜ እጆቼ እንደተጠፈሩ አፌ እንደተለጎመ ነበር፤ የተለየው ነገር የአእምሮዬ በመጠኑ መረጋጋት ነው፡፡ እጁን ሲቆርጥ ያየሁትን ምስል ወደ ኃላ ተመልሼ ሳስታውስ ይሄ ሁሉ ግድግዳው ላይና ሠውነቴ ላይ ያቀለመው በራሱ ደም እንደሆነ ገባኝ፡፡ ሠውነቴ ላይ ያረፉት የራይትና የኤክስ ምልክቶች ፍቺ ግን በቀላሉ ሊገለፅልኝ አልቻለም፡፡እንደ ድንገት ወደ ጎኔ ስዞር በቀኝ  በኩል በሚገኘው ግድግዳ ላይ ሌላ ፅሑፍ አነበብኩ፡፡

‹‹40 ፐርሰንት ብቻ ከእሷ ጋር ትመሳሰላለች፡፡ ስለዚህ አትወክላትም... ያበሳጫል...ይቺን መግደል ትርጉም አይሰጥም፡፡›› ይላል... ዳግመኛ አዞረኝ፡፡ የሚገላትን ሴት በመፈለግ ላይ ያለ ወፈፌ ነው ያጋጠመኝ፡፡ የምልክቶቹም ፍቺ ተገለፀልኝ፡፡ ከሚያውቃት ወይም ካስከፋችው ሴት ጋር እያመሳሰለኝ ነበር፡፡ እየተንፏቀኩ ሄጄ በራፉን በደከመ ጉልበቴ ደበደብኩ፡፡ ዘበኛው ሠምቶ ከፈተልኝና ከእስራቴ ነፃ አደረገኝ፡፡እየተንቀጠቀትኩ ልብሴን በመልበስ ላይ ሳለው ቅድም ያለየሁት ሌላ ምልክት ብልቴ አካባቢ አየሁ፡፡ ጥያቄ ምልክት አስቀምጦበታል፡፡ ኮንትራት ታክሲ አስጠርቼ እቤቴ አደረሠኝ፡፡ እቤቴ ስገባ ልክ ከለሊቱ ስምንት ሠዓት ነበር፡፡ ሠውነቴን ታጠብኩ፡፡ከፍራቻዬ ለመገላገል ለሊቱን ሙሉ ስጠጣ አደርኩ፡፡ እያነበበችለት ያለውን ዲያሪ አጥፋ እያስቀመጠች.....ይሄው ነው አለችው፡፡

በጉንጮቹ ላይ ያለ ፍቃድ የወረደ እንባውን እየጠረገ ‹‹ልብ ወለድ ነው እውነት?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ልብ ወለድ በዲያሪ ይፃፋል እንዴ?››

‹‹በቃ ምንም አላውቅሽም ነበር ማለት ነው….? እራሴን አመመኝ ልሂድ፡፡›› በማለት ከመቀመጫው ተነሳና ግንባሯን በመሳም ተሠናብቷት ወጣ፡፡ እሷም በተቀመጠችበት በስስት በሚንከራተቱ አይኖቿ ሸኘችው፡፡

የሠጠችውን ፖስታ ለመቅደድ እቤቱ እስኪደርስ አላስቻለውም፡፡ ከሠፈሩ ትንሽ ወጣ እንዳለ ነበር ወደ አንድ ሆቴል ጎራ በማለት መኪናውን አቁሞ ከውስጥ ሳይወጣ የከፈተው፡፡ የሚያየው ነገር ግራ ገብቶታል፡፡ አንድ ወረቀት እና መዓት ብሮች! ባለ መቶ፤ሃምሳ እና አስር ብር በየመጠናቸው ለየብቻ በብር ላስቲክ ተጠፍንገው እጁ ላይ ተዘረገፉ፡፡ብሮቹን ትቶ ወረቀቱን አነሳና ማንበብ ጀመረ፡፡

‹‹አንተን ከመጀመሪያ ጀምሬ የቀረብኩህ ሸርሙጣ ስለሆንኩ ሳይሆን ስለማፈቅርህ ነው፡፡ ብር የምቀበልህ ከአንተ ፍቅር እንደያዘኝ በፍፁም እንድታውቅ ስለማልፈልግ ነበር፡፡ ቢሆንም ብሩን ተጠቅሜው ቢሆን ኖሮ ፍቅር ሳይሆን ሽርሙጥና ይሆን ነበር… እና ለሁለት ዓመት ደንበኛዬ ነበርክ፡፡ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ አርባ ዘጠኝ ቀን አብረኸኝ አድረሀል፡፡

ከዚህ ውስጥ አስራ አምስቱን ቀን ብር ስላልነበረህ አልከፈልከኝም፡፡

ለዘጠኝ ቀን -> 5ዐዐ ብር ከፈልከኝ  500×19  9500 ብር ይሆናል

አስራ ሁለት ቀን  4ዐዐ ብር ከፈልከኝ  400×12  4800 ብር ይሆናል

ሦስት ቀን  15ዐ ብር ነው የከፈልከኝ 150x3  45ዐ ብር ይሆናል፡፡ እንግዲህ በድምሩ አስራ አራት ሺ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር መሆኑ ነው፡፡ ይሄ ብር እንግዲህ ለመውጫ የምትከፍለውን አርባ.. አርባ ብር አያጠቃልልም፡፡ ቻው፡፡›› ይላል፡፡

አንብቦ ሲጨርስ ወረቀቱን ጨምድዶ አፉ ውስጥ ከተተው፤አኘከው..አደቀቀው  አልተፋውም፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሠዓቱ ከምሽቱ 2፡30 ሆኗል፡፡ ሠሎሞንና ኤደን ቦሌ በሚገኘው ታዋቂው አቢሲኒያ ሬስቶራንት እራት በአክሱማይት ወይን እያወራረዱ በመመገብ ላይ ናቸው፡፡ የተገናኙት በቀጠሮ አልነበረም፡፡ ሁለቱም በጋራ የሚያውቁት ሠርግ ላይ በመታደማቸው ነበር ድንገት የተገጣጠሙት፡፡ ሠሎሞን እንደ ወትሮው ሙሉ ሱፍ ከሠማያዊ ሸሚዝና ጥቁር መደብ ኖሮት በነጭ መስመር ከተዥጎረጎረ ክራባት ጋር ለብሶ ሙሽራ ባይሆንም ሚዜ መስሏል፡፡

ኤደንም ከሱ ባልተናነሰ ሁኔታ ዘንጣለች፡፡ ጥቁር ቀለም ያለው ከጉልበቷ በላይ የሚቀር ጉርድ ቀሚስ ለብሳለች፣ ከላይ ከሠውነቷ ጋር የተጣበቀ ሮዝ ከለር ያለውና የጡቷን ቅርፅ የሚያጎላና ግማሽ የሚሆን የጀርባዋን ክፍል አጋልጦ የሚያሳይ ‹ፓክ አውት›
ለብሳለች፣ጆሮዋ ላይ ያንጠለጠለችው ጌጥ አርቲፊሻል ቢሆንም ለውበቷ የራሱ የሆነ ድርሻ
ነበረው፣በፊትም ጎላ ጎላ ብለው ሚታዩ አይኖቿን በስሱ ተኩላቸው ይበልጥ ቀልብ ሳቢ ሆነዋል፣የፀጉር አሠራሯም ልዩ ነው፡፡

‹‹ቬሎ ስላለበሽ ነው እንጂ ሙሽራዋ እኮ አንቺ መስለሽኝ ነበር፡፡››

‹‹ኧረ ባክህ! ለእንደዛ አይነት ወግማ መች ታደልን፡፡››

‹‹ምን ማለት ነው?›› አላት ሠሎሞን በግራ እጁ አንገቱ ላይ የተሸመቀቀውን ክራባት እያላላ፡፡

‹‹እብድ አፍቅረን ከእሱ ጋር ስንጃጃል ውዱ ጊዜያችን በከንቱ አልፎ በፈነዳንበትም ወቅት የነበረንን አንፀባራቂ ውበት መጠቀም አቅቶን ዛሬ ከጠወለግን በኃላ ካንቀላፋንበት ስንባንን ረፍዶብን አገኘነው...ምን ማድረግ እንችላለን፤ አረጀን! ማን ይፈልገናል፤ ያው ቆመን መቅረታችን ሳይሆን ይቀራል?›› ትካዜዋን
ከቆነጠረችው ምግብ ጋር ወደ አፏ ልካ አላመጠችው፡፡

ሠሎሞን መናገር ጀመረ ‹‹ለመሆኑ ፊትሽን የምትመለከቺበት መስታወት ቤትሽ የለሽም እንዴ? የአስራ ስድስት አመት ልጃገረድ ነኝ ብትይ እኮ ማንም የሚጠረጥርሽ አይኖርም ፤‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆኖ ነው እንጂ› መች ላንቺ የሚሆን ባል ጠፋ ብለሽ ነው ... ለማንኛውም ምግቡን ብይ፡፡››

<<ባክህ በቃኝ::>>

‹‹ምነው?መች ተነካና?››

‹‹ግድ የለህም ይብቃኝ.... ባይሆን ወይኑን እደጋግማለሁ፡፡››

‹‹ኧረ ይቻላል! በስንት ወራችን እኮ ነው የተገናኘነው፤ዛሬማ መላቀቅ የለም፡፡››

‹‹ተስማምቼያለሁ፡፡›› አለች ኤደን የወይን ብርጭቆዋን አንስታ እየተጎነጨችለት፡፡
ሠሎሞን የዘወትር ገረሜታው አሁንም እንደገ አገርሸቶበት የኤደንን ውበት በጎሪጥ እየቃኝ በውስጡ ያብሠለሠላል፡፡
👍8810👎3😁3
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ኮሎምቢያ/አማዞን ደን ውስጥ

ኑሀሚና ካርሎስ አምስት ሰዓት ያለምንም ረፍትና መንቀርፈፍ ነው የተጓዙት፡፡በቀንም ቢሆን እንኳን ፀሀይ የተንጣለሉትን የግዙፍ ዛፎችን ቅርንጫፍ ሰንጥቃ ወደመሬት መድረስ አይሆንላትም፤ ማታ ሲሆን ደግሞ ለጨረቃዋ በጣም ከባድ ስራ ነው የሚሆንባት፡፡ በዚህም ምክንያት በማታ አይደለም በቀንም ከፍተኛ ሀይል ያለው ባትሪ ሳይጠቀሙ መጓዝ አዳጋች እና በቀላሉ ለአደጋ የሚያጋልጥ ስራ ነው፡፡
‹‹አሁን ማረፍ ያለብን ይመስለኛል››አላት ካርሎስ

‹‹ይሻላል ብለህ ነው?››አለችው በዛለና በደከመ ድምጽ፡፡

‹‹አዎ አሁን የተወሰነ የራቅናቸው ይምስለኛል…ባይሆነ ለሊቱን አርፈን ንጊት ላይ በሙሉ አቅም ጉዞችንን እንቀጥላለን፡፡››አላትና ተስማሙ፡፡ቅጠል እየቆረጠች ግዘፉ ግንድ ስር መጓዝጎዝ ጀመረች፡፡
‹‹ምን እየሰራሽ ነው?፡፡››

‹‹መሬት ላይ ከመቀመጥ ቅጠሉ ይሻለናል ብዬ ነዋ፡፡››

‹‹እዚህ የአማዞን እንብርት ላይ መሬት ላይ ተዝናተን መተኛት አንችልም…››

‹‹ለምን? ጃጓር ምናምን ፈርተህ ነው?››

‹‹እሱም አንድ ነገር ነው..ካዛ በላይ ግን ጥቃቅን መርዛማ ነፍሳቶች ናቸው የሚያስፈሩት…..ለምሳሌ የአማዞን ሸረሪት ሰውነትሽን ጥቂት ከጫረችሽ ወይ ከቦጨቀችሽ….በቀጥታ እራስሽን ለሞት ማዘጋጀት መጀመር ነው ያለብሽ፡፡በጣም ብርቱ ከሆንሽ አንድ ሰዓት ብቻ ነው የምትኖሪው፡፡መርዙን አርክሶ ከሞት የሚያድንሽ ምንም አይነት ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ መድሀኒት የለም፡፡እና ይህችን ሸረሪት በቁጥር አንድ ደረጃ ነው የምፈራት፡፡››
ፍራቻው ወደእሷም ተጋባበትና‹‹እና ምን እናድርግ?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ሊያስተኛን የሚችል ዛፍ ነው መፈለግ ያለብን ..››ብሎ አይኖቹን በአካባቢው ወደሉት ግዙፍ ዛፎች ባትሪውና በማብራት መምረጥ ጀመረ…ከዛ ‹‹አዎ ይሄኛው የተሻለ ነው….፡፡››ስል ምራጫውን አሳወቃት፡፡
‹‹እንዴት አድርገን ነው እዚህ ላይ ምንወጣው?››

‹‹እንደምንም መውጣት ነዋ….መቼስ ቢከብድ ቢከብድ የሰው ህይወት ከማጥፋት በላይ አይከብድም፡፡››
በንግግሩ ድንግጥ አለች፡፡እስከአሁን እዛ ለእሷ በተቆፈረው መቃብር አካባቢ ስለሆነው ነገር አንሰተው አላወሩም‹‹ሰው መግደሉን ፈልጌው ወይም ቀላል ሆኖልኝ መሰለህ..?ጨንቆኝና የሞት ሽረት ጉዳይ ሆኖብኝ ነው፡፡››
‹‹እኮ እኔስ ምን አልኩ…?ይሄም የህይወት እና የሞት ትግል ነው፡፡ከዚህ ደን በአውሬ ሳንበላ ወይም በነፍሳት ሳንነደፉ በሰላም ወጥተን የሆነ መንግስት የሚቆጣጠረው ትንሽዬም ቢሆን ከተማ ወይም መንደር እስክንገባ የህይወትና የሞት ሽረት ላይ እንደሆን እንዳትዘነጊ…. በይ ቦርሳሽን ለእኔ ስጪኝና ለመውጣት ተዘጋጂ …እኔ ከኃላ ሆኜ እደግፍሻለሁ፡፡››
የተወሰነ ጊዜ እንደማሰብ አለችና ትከሻዋ ላይ ያንጠለጠለችውን ቦርሳ አቀበለችው፡፡ተቀበላትና ካንጠለጠለው ቦርሳ ጋር አንድ ላይ በቀኝ ትከሻው ደርቦ አንጠለጠለው፡፡በግራ ትከሻው ላይ ክላሽ አለ፡፡
እሷ በረጅሙ ትንፋሽ ወሰደችና ለመውጣት ዝግጁ ሆነች፡፡ቀኝ እግሯን አስቀደመች…ወገቧን ይዞ ደጋፋት፡፡ በእጆቿ ቅርብ ያለውን ቅርንጫፍ ተንጠራርታ ያዘችና ግራ እግሯን አስከተለች፡፡ እንዳዛ እያለች ወደ ላይ መንቀሳቀሷን ቀጠለች፡፡እሱ ከስር ሆኖ ትወድቅ ይሆን በሚል ስጋት በጭንቀት እየተከታተላት ነው፡፡እንደፈራው ሳይሆን እንደውም ይበልጥ አንድ ርምጃ ወደላይ ከፍ ባለች ቁጥር ይበልጥ እየፈጠነችና በራስ መተማመን እየታየባት መጣች፡፡ ለመተኛት ምቹ ነው ብሎ ያሰበበት ቦታ ስትደርስ ‹‹በቃሽ…እዛው ጠብቂኝ›› አላት፡፡እሱም በእፎይታ ወደላይ መውጣት ጀመረ፡፡እሱ ከልጅነቱ ጀምሮ የብዙ አመት ልምድ ስላለው ዛፍ መውጣት ለእሱ በምድር እንደመራመድ ቀላሉ እና ተራ ነገር ነው፡፡
ስሯ ደረሰና ከጎኗ ቁጭ ብሎ የእሷንም የእሱንም ቦርሳ ከአንደኛው ቅርንጫፍ ላይ አሰረው፡፡መሳሪያውንም እንደዛው አንጠለጠለውና በእፎይታ ደገፍ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ካልተመቸሽ እግርሽን በቅረንጫፉ መሀከል አድርጊና ጭንቅላትሽን እኔ ላይ አስደግፊ አላት፡፡››እንዳለት አደረገች፡፡ጭንቅላቷን ደረቱ ላይ ለጥፋ አረፍ ስትል የልብ ምቱ ድውድውታ ተሰማት፡፡
‹‹ልብህ በጣም ይመታል፡፡›› አለችው፡፡

‹‹አንቺን የመሰለች ፀይም መልዐክ ደረቴ ላይ ተኝታ የልብ ምቴ ባይጨምር ነበር የሚገርመው››አላት፡፡
‹‹አይገርምም …የዛሬን አያድረገውና አለቃህም በሰላሙ ቀን ፀይም መልአክ ብሎኝ ነበር››

‹‹እንደዘ በማለቱ እንኳን ተሳስቷል ማለት አልችልም…የእሱም ልብ እንደእኔው በውበትሽ ደንዝዛ ነበር ማለት ነው፡፡››
‹‹በዚህ ጣር ላይ ሆነህ ትቀልዳለህ አይደል?››

‹‹በጣር ላይ ሆንሽ በምቾት ላይ ልብሽ ጉዳዩ አይደለም እኮ …ከተነካ ተነካ ነው..በሲኦሉ ውስጥም ሆነ በገነት እጅ መስጠቱ አይቀርም፡፡››
‹‹ይሁንልህ…ውሀው አለቀች እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡ውሀ ጠምቷት ብቻ ሳይሆን የጀመሩትን የወሬ ርዕስ አቅጣጫ ማስቀየርም ስለፈለገች ነው፡፡የእሱን ልብ አታውቅም የእሷ ልብ ግን በዚህ ጊዜ ነፍሷን ለወንድሟ ስትል ከማትረፍ ውጭ ሌላ ተልዕኮ የላትም፡፡እጁን ወደተንጠለጠለው ቦርሳ ሰደደና ኮዳውን አውጥቶ ሰጣት፡፡ክዳኑን ከፈተችና ተጎነጨችለት፡፡መልሳ ከድና አቀበለችው፡፡ወደቦታው መለሰ፡፡
‹‹አሁን የት ነው ያለነው?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹የአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ነዋ፡፡››

‹‹እሱንእማ እያየሁት ነው…ሀገሩን ነው የጠየቅኩት፡፡
‹‹ብራዚል እና ኮሎምቢያ ድንበር ላይ ነን፡፡››
‹‹እንዴ …!ወደየት ነው እየሄድን ያለነው?››

‹‹ወደብራዚል ነው…››

‹‹ወደኮሎምቢያ ወይም ወደመጣንበት ወደፔሩ የምንሄድ ነበር የመሰለኝ፡፡››

‹‹አይ …ያንን ማድረግ አልመረጥኩም…ከፔሩ ፤ኮሎምቢያ ሜክሲኮ አልፎ አሜሪካ ድረስ ሰውዬው በብዙ ሺ የሚሆኑ ሰዎች አሉት…በየደረስንበት ሁለ ታዳኞች ነው የምንሆነው፡፡ይሄኔ ሁሉም እኛን በደረስንበት ቀጨም አድርጎ ወይ በህይወት ካለሆን ደግሞ እሬሳችንን ለእሱ በማስረከብ እና ደለብ ያለ ሽልማቱን ለመቀበል ቋምጠው እየጠበቁን ነው፡፡››
‹‹ብራዚልስ ሰው የለውም?››

‹‹አይ ብራዚል ተፅእኖው በጣም የሳሳ ነው፡፡በዛ ላይ አሁን እየተጓዝን ያለነው ወደግዙፍ ጥቅጥቅ የአማዞን ደን ነው..በቀደም እንደነገርኩሽ 60 ፐርሰንቱ የአማዞን ደን ያለው ብራዚል ውስጥ ነው፡፡ወደእዛ ጠልቀው ይገባሉ ብሎ ማንም አያስብም፡፡ገብተዋል ብለው ቢያስብ እንኳን ያን ሁሉ ደን ሰንጥቀን ከአውሬዎቹም ከተናዳፊ መራዛማ ነፍሳትም ተርፈን በህይወት የሆነ ቦታ እንደማንደርስ እርግጠኞች ናቸው..ስለዚህ ወደዚህ አይፈልጉንም፡፡ለዛ ነው በጣም ከባዱን መንገድ የመረጥኩት፡፡በህይወት እንዲሳካልሽ አንዳንዴ ቀላሉን መንገድ መምረጥ አዋጪ አይደለም…፡፡››
ፈገግ አለችና‹‹አሳምነኸኛል..ግን አንተስ ከፊታችን እንደፓስፊክ ውቅያኖስ የተዘረጋውን አስፈሪ ጥቅጥቅ ደን ሰርቫይቭ አድረገን ሕይወታችንን እንደምናተርፍ እንዴት ልታምን ቻልክ?፡፡››
‹‹በቀደም በነገርሺኝ ታሪክ ነዋ››

‹‹የትኛው ታሪክ?፡፡››

‹‹የሴትዬዋ… ጨካኝ ንጉስ ያለበት ግዛት ውስጥ ከመኖር አዳኝ ነበር ያለበት ጫካ ውስጥ መኖር እንደሚሻል መምረጦን የነገርሺኝን…››
በጨለማ ውስጥ ፈገግ ብላ‹‹ጥሩ ተማሪ ነህ፡፡››አለችው ፡፡

‹‹አዎ ጥሩ ተማሪ ነኝ..በዛ ላይ ሶስት ነገሮች ያግዙናል ብዬ አስባለው፡፡››

‹‹እስኪ ንገረኝ እነዚሀ ሶስት ነገሮች ምንድናቸው?፡፡››
👍803👎1🥰1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰላሞን የሆነ ሰው እየተጫወተበት እንደሆነ ነው የተረዳው‹‹ግን ማን ነው እንዲህ ያለ ጫወታ ከእኔ ጋር ለመጫወት የሚደፍረው?››በዙሪያው ያሉ ሰዎችን እያሰበ እራሱን እስኪያመው ቢያስጨንቅ በዙሪያው ካሉ ሰዎች እንዲህ መላ ቅጡ የጠፋበት ቀልድ ከእሱ ጋር ለመቃለድ የሚሞከር ሰው ሊመጣለት አልቻለም፡፡

ነገሩ ቀልድ እንዳልሆነ የተረዳው ልክ በተነገረው መሰረት ከሶስት ቀን በኃላ ተመሳሳይ ስልክ ሲደወልለት ነው፡፡በጉጉት አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ..አወቅከኝ?››

‹‹መሰለኝ… አደናጋሪዋ ልጅ ነሽ አይደል?››

‹‹መሰለኝ….የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ?››

‹‹ምን ለማድረግ?››

‹‹በተነጋገርነው መሰረት ስራ ማስጀመሪያ መቶ ሺ ብሩን እንድልክልህ ነዋ››

‹‹እንዴ? ስራው ምን እንደሆነ ሳላውቅ…ልስራው አልስራው መወሰን የምችለው እኮ ስራውን ሳውቅ ነው…መጀመሪያ በአካል ተገናኝነተን ስለስራው ማውራት አለብን››

‹‹ለጊዜው በአካል ላገኝህ አልችልም…ስራው በአባትና እናቴ መካከል ያለውን ችግር መቅረፍ ነው…እናትና አባቴ ያለፉትን 28 አመታት በጋብቻ አሳልፈዋል….እኔ ሀያ አንድ አመቴን ጨርሼ 22 ዓመት ውስጥ ነኝ…በእድሜዬ አንድም ቀን ሰላም ሆነው አይቻቸው አላውቅም…መኝታ  ለይተው  በየራሳቸው  መኝታ  ቤት  ነው  የሚያድሩት….ሁል  ጊዜ
እንደተጣሉና እንደተጨቃጨቁ ነው.ከዛም አልፎ አንዱ ሌለኛውን ለማስወገድም እስከመፈለግ የሚያደርስ ጥላቻ በመካከላቸው አለ..ወይ አይፋቱ ወይ እንደሰው የእውነት አብረው አይኖሩ፣….እና የፈለኩህ ይሄንን የሻገተና የበሰበሰ ጋብቻ የበሰበሰውን ቅጠል ከላዩ አራግፈህ የደረቀውን የጋብቻ ግንድ ቆርጠህ ከስር አዲስ የፍቅር ቅርንጫፍ እንዲያቆጠቁጥ እንድታደርግ ነው…ቢያንስ እንደባለትዳር መልሰው መተቃቀፍ ባይችሉ እራሱ እንደጓደኛሞች እንዲጨባበጡ ማድረግ እንድትችል ነው፡፡ይሄ ጉዳይ የእኔ የህይወቴ ትልቁ አላማ ነው…እባክህ ይሄንን ጉዳይ እንደጉዳይህ ልትይዘው ትችላለህ….?›››

‹‹በእውነቱ ከጠበቅኩት በተቃራኒ የሆነ መሳጭ ነገር እየነገርሺን ስለሆነ ቀልቤን ገዝተሸዋል…የምትይውን በደንብ እየተከታተልኩሽ ነው፡፡፡ለመሆኑ እኔን የምታናግሪው አባትሽ ወክለሽ ነው ወይስ እናትሽን…..?ማለት እኔን ለስራው እንድታናግሪኝ የጠየቀሽ ማን ነው?፡፡››

‹‹በእውነቱ ሁለቱም ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር የለም….›

‹‹ይሄ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ ውስብስብ ያደርገዋል..እሺ ቆይ ለመሆኑ እኔን ለምን…?እንዴት እኔን መረጥሽ?››

‹‹ለጊዜው ማንነቱን ልነግርህ የማልችለው አንድ አንተን የሚያውቅ ሰው ነው ሰለአንተ በሆነ ጉዳይ አንስተን ስንጨዋወት በጋብቻ ጉዳይ ላይ እንደምትሰራና በጉብዝናህም እንደሚተማመንብህ የነገረኝ..እንዳአጋጣ ሚ ሆኖ ደግሞ ያንን ሰው እኔ አምነዋለው…እሱ ጎበዝ ነህ ካለህ ጎበዝ ነህ ማለት ነው…

ተመለሰልህ?፡››

‹‹በከፊል አዎ…ግን እንደነገርሺኝ በወላጆችሽ መካከል ያለው ችግር ለረጅም አመት የተከማቸ የተወሳሰበና ዘርፈ ብዙም ነው፡፡››

‹‹በትክክል ገልፀኸዋል››

‹‹ችግሩ ምን መሰለሽ..በቀደም እንደነገርኩሽ አንድ የጋብቻ አማካሪ በጋብቻ መካከል የተፈጠረ ችግርን ለመፍታት የሚችለው ሁለቱም ተጋቢዎች በመሀከላቸው ችግር እንዳለ አምነው ያንን ለማስተካከል ከአማካሪው ጋር ለመተባበር ሙሉ ፍቃደኛ ሲሆኑ ብቻ ነው…አሁን ያንቺን ጉዳይ ስንመለከት ወላጆችሽ ጉዳዩን እንኳን አያውቁትም..ቢያውቁትም ፈፅሞ ከእኔ ጋር ለመስራት ላይቀበሉት ይችላሉ.››.

‹‹እሱን ለእኔ ተወውና አሁን የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ… ገንዘቡን ትራንስፈር ላድርግልህ››

‹‹ይሄውልሽ ፣እኔ በነገርሺን ታሪክ በጣም ተስቤያለሁ…አንድ ወጣት ሴት በወላጆቾ ግንኙነት ተረብሻ እንዲህ ነገሮችን ለማስተካከል ስትጥር እኔም የበኩሌን እገዛ ለማድረግ ፍጽም ፍቃደኛ ነኝ..እዚህ ላይ ዋናው ገንዘብ አይደለም.. እሱ በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው…አሁን መጀመሪያ አንቺ ራስሽ ወላጆችሽን ከቻልሽ አንድ ላይ አስቀምጠሸ ካልሆነም ለየብቻ ያሰብሽውን ንገሪያቸውና ለማሳመን ሞክሪ..እነሱ ፍቃደኛ ከሆኑ በኃላ ደውይልኝ..ከዛ ፕሮግራም እናወጣና ያለውን ችግር እያየን ለማስተካከል እንሞክራለን፡፡››

‹‹እነሱን በቀጥታ ማናገር አልችልም››

‹‹ለምን?››

‹‹ስሜ በፀሎት ኃይለልኡል ይባላል››

‹‹እሺ በፀሎት…ለምንድነው ወላጆችሽን ማናገር የማትችይው..?እነሱን ማናገር የማትቺይ ከሆነ እንዴት አድርጌ ነው ወላጆችሽን መርዳት የምችለው?››

‹‹ማለት ስሜን የነገርኩህ ስለእኔ የተወሰነ መረጃ እንዲኖርህ ነው..በፀሎት ኃይለልኡል በልና ድህረገፆች ላይ ወይም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፈልግ ..ከ30 ደቂቃ በኃላ መልሼ ደውልልሀለው፡፡››አለችና ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጋችበት፡፡

ስልኩ ቢዘጋም እሱ ግን ስልኩ ላይ እንዳፈጠጠ ነው…የገባው የመሰለው የልጅቷ ሁኔታ መልሶ እየተበታተነበት ነው‹‹…ድህረ-ገፅ ላይ ስለእሷ ምን…?ታዋቂ ሰው ነች ማለት ነው…?››

ጎግል ከፍቶ ››በፀሎት ኃይለመለኮት››ብሎ ሰርች መድረግ ጀመረ..በርካታ መረጃዎች ተዘረገፉ….እውነትም ይህቺ ልጅ ታዋቂ ነች መሰለኝ..ብሎ የመጀመሪያውን ሲያነብ

‹‹የታዋቂ ቢሊዬነሩ የኃይለመለኮት ብቸኛ ወራሽ በውድቅት ለሊት ከቤት ወጥታ ከጠፋች 14 ቀን አልፏታል፡፡››

‹‹ታዋቂው ቢሊዬነር ብቸኛ ልጅ በፀሎት ለምን ከቤቷ ጠፋች?››
‹‹በጸሎት ኃይለመለኮትን ያለችበትን የጠቆመ የ5 ሚሊዬን ብር  ሽልማት እንደሚሸልሙ አባቷ ለፋና ቴልቨዥን በሰጡት መግለጫ አሳወቁ››

በሚያነበው ዜና ሁሉ ደነዘዘ…..ማንበቡን አቆመና..ደወለላት

‹‹ሄሎ ..››

‹‹አሁን በመጠኑ ገባህ?››

‹‹ማለት አሁንም እንደጠፋሽ አይደለሽም አይደል…..?ማለቴ ወደቤት ተመልሰሻል?››

‹‹አይ  አልተመለስኩም…ወደቤት  እንድመለስም  እንደወጣው  በዛው  እንድቀርም የምታደርገኝ አንተ ነህ፡፡››

‹‹አልገባኝም››

‹‹ከእቤት የጠፋሁት የወላጆቼ ጭቅጭቅና የእርስ በርስ ጥላቻ ምርር ብሎኝ ነው….እኔ የእነሱን ሀብታቸውንም ሆነ ውርሳቸውን አልፈልግም፡፡ እኔ የምፈልገው ፍቅራቸውን ነው..ቢያንስ የሁለት ጓደኛሞችን አይነት እርስ በርስ የመግባባት እና የመረዳዳት ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ወደዛ ቤት አልመለስም…እና እቅዴ ምን መሰለህ..ለእነሱ ደብዳቤ ፅፌ ልክልሀለው….በዛ ደብዳቤ ላይ ግልፅ የሆነ ፍላጎቴን አሰፍራለሁ…ማለቴ በግልፅ ከአንተ ጋር ሰርተው በማሀከላቸው ያለውን ግንኙነት ካስተካከሉ…እናም ያንን አንተ ካረጋገጥክልኝ ወደቤት እመለሳለው..ካለበለዚያ በቃ እኔም እነሱን እረሳለው አነሱም እኔን ይረሱኛል ማለት ነው፡፡›

‹‹በተሰቀለው..ነገሩ ካሰብኩት በላይ የተወሳሰበና ..አደገኛም ጭምር ነው፡፡››

‹‹ለዚህ እኮ ነው አምስት ሚሊዬን ብር እንድታገኝ የማደርግህ..ገብቷሀል አይደል አባቴ እኔን ላገኘ ወይም ያለሁበትን ለጠቆመ ሰው የ5 ሚሊዬን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል ..ያ ማለት ነገሮች እንደተሳኩ እርግጠኛ በሆንኩ ጊዜ አንተ እንድታገኘኝና ለቤተሰቦቼ እንድታስረክበኝ አደርጋለሁ…እናም ለሽልማት የተዘጋጀውን ብር ከአባቴ ተቀብዬ ለአንተ አስረክብሀለው፡፡››
👍62🥰123
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

አይንሽን ላፈር

አይ! ሰው ለሰው ሞት አነሰው ብላ የተረተችው ቀበሮ ወዳም አይደለም፡፡ ለካ ለሁሉም የሚተረትለት ችግሩ በቤቱ ሲደርስበት ኖሯል፡፡ ለነሱ ብዬ ስሜ በማንም አፈኛ በየገብያውና በየቤቱ ይነሳል፡፡ እቤት ተዘፍዝፋ ባሏ ዲቃላ ያንጠባጥባል፡፡ ምን አይነት ግፍንት ነች እየተባልኩ የማንም መሳቂያና መተረቻ ልሁን? ከሰውም ጋር ባይሆንም ከራሷ ሃሳብ ጋር ያወራችው ነበር ፡፡

ስሙን ሳነሳሳና ሳማው መጣ እንዴ? ከውጭ በኩል አበበች የሚል የወንድ ድምፅ ሰምታ ተመስገን መስሏት ነበር፡፡ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወጣች፡፡

ግን ተመስገን ሳይሆን ወላጅ አባቷ አቶ አሸናፊ ነበር፡፡

"ደህና አረፈዳችሁ"? አለ ፤ አቶ አሸናፊ፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አረፈድህ አባባ ፤ ግባ ወደ ቤት" አለች፡፡

ወደ እቤት እየገቡ "ያሬድ የለም እንዴ"? አለ፡፡

"የለም፤ በጥዋት መጣሁ ብሎኝ እንደ ሄደ አልተመለሰም፡፡ የሄደበትንም አልነገረኝም፡፡ ምነው ደህና አይደለህም?፡፡

"እኔስ ደህናነኝ፡፡ ከብቶቹ እፀሃይ ላይ ታስረው ሳይ ለምን አልፈታቸውም ብዬ ነው"፡፡

"እኔም ብዬ አሁን ነበር የሚበላ የሰጠኋቸው፡፡ ውሃ ጠምቷቸው ነው መሰለኝ አልበሉትም፡፡ እሱም ውሃ እንዳያጠጣቸው ብቅታውም ጠፋ፡፡ ወይ እቆያለሁ አጠጫቸው እንኳን አላለኝ፡፡ ቶሎ እንደሚመለስ ሰው ሳይነግረኝ መሔዱ አለች፡፡

"መቼ ጉዳይ ብሎ ነው፡፡ ከብት አጠጥቶ የሚያውቀው፡፡ አንዴ ነጋዴ ነኝ ፤ አንዴ ባለጉዳይ ነኝ
እያለ ፤ መንደር ለመንደርና ከተማ ለከተማ እያሽካካና እየዞረ አላት፡፡

"እንዴው እቤት ካለ ብዬ ነው እንጂ ለማጠጣቱማ አዲስ አይደለሁም፡፡ አሁን ለአንተ ቡና ላፍላና አጠጣቸዋለሁ፡፡

"እኔ ቡና አልጠጣም፡፡ አታፍሊ ፡፡

"ለምን አትጠጣም? ምነው ደህና አይደለህም? እንዴ አለችው፡፡ አባቷ ተኮሳትሮ መናገሩ አስፈርቷታል፡፡

አቶ አሸናፊ በሚወራው የሰፈር ወሬ ማንነቱን ያስደፈረው ይመስላል፡፡ ወደ ልጁ ቤት የመጣው እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ለበጎ ሳይሆን ለነገር እንደመጣ በፊቱ ላይ የሚነበበው የመኮሳተር ምልክት የሚያስይ መሆኑ ጥርጥር የለውም ነበር፡፡

"አንቺ ወራዳ ፤ አንቺ ተዋርደሽ እኔንም አዋረድሽኝ፡፡ ባልሽ አንቺን የቤት ገረድ አድርጎ ዲቃላውን በሔደበት ይፈለፍላል፡፡ ከሰማሽ በኋላ፤ እንኳን ጥለሽ መምጣት አቅቶሽ ነው" አለ፡፡ በዱላ እንደ መምታት ያህል በሚሰማ ንግግር፡፡

አበበች የፈራችው አልቀረም፡፡ በትዳሯ ላይ እሳት ሲለኮስ ታያት፡፡ የአባቷ ንግግር ከያሬድ ጋር እንድትቀጥል የሚፈልግ አይመስልም፡፡ ለተመስገን እሽ ያለችበትን ቀን አምርራ ብትረግምም ያቺን ቀን ግን ተመልሳ ልታገኛት አልቻለችም፡፡ መልስ ሳትሰጥ አይኞቿ በእንባ ተሞሉ፡፡

"አሁን ምንድ ነው ሃሳብሽ ? የባልሽ ገረድ ሆኖ መቀጠል ይሻላል?፡፡ ወይስ ለቆ መውጣት ይሻላል?፡፡ መነፋረቁን ትተሸ ተናገሪ አለ፡፡ አሁንም ቁጣና ንዴት በተቀላቀለበት ንግግር፡፡

"አባባ የማታውቀው ነገር ስላለ እኮ ነው ብላ..

"የማላውቀው ምንድ ነው ባክሽ?፡፡ ከቄስ መልካሙ ልጅ ባልሽ መውለዱን ነው፤ የማላቀው? ወይስ በማንም ጨምላቃ አፍ በየቡና ቤቱ ላይ በአንች የተነሳ ስሜ መነሳቱን ነው የማላውቀው?፡፡ ለነገሩ እኔ የተዋረድኩት ዛሬ ሳይሆን አንቺን የወለድሁ ቀን ነው አላት፡፡

ሚስጥሩን ለአባቷ ለመንገር ብትፈልግም አባቷ ግን ምንም አይነት ምክንያት የሚቀበል አይደለም፡፡

"ትዳሬን እንዴት ባልሰራሁት ለቅቄ እሄዳለሁ?

ልጄን ያለ አባት ማሳደግ አልፈልግም፡፡ ነገ እውነቱ ሲወጣ ጥፋተኛ ማን እንደሆነ ያኔ ታውቃለህ አለች፡፡ ደፍራ በመናገሯ አይኑን ላለማየት ወደ መሬት አቀርቅራ፡፡

አቶ አሸናፊ የባሰ በንዴት ቆሽታቸው አረረ፡፡ አንች ወራዳ አታፍሪም ደግሞ ነገ እውነቱ ይወጣል ስትይኝ?፡፡ አንገታቸውን እየነቀነቁ አይ! አለመታደል ይሄ! ልክስክስ ባልሽ ካዋጣሽ ከዛሬ ጀምሮ! ልጄ! አይደለሽም፡፡ ብሞትም እንኳን ከመቃብሬ ላይ እንዳትቆሚ፡፡ ብሏት፤ የወለዳትን ልጅ ረግሞ እንዳልወለዳት ልጄ አይደለሽም ብሎ እያለቀሰች ትቷት ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡

ታዲያ አበበች ስታለቅስ አይን አይኗን እያዬ የሚቁለጨለጨው ልጇ ለተመለከተው ከሷ ለቅሶ ይልቅ የልጇ አይኖች ሲንከራተቱ ያስለቅሱ ነበር፡፡

"ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሽው"? አለ ፤ ያሬድ፡፡ ባለቤቱን ጥዋት ትቷት ሲወጣ ደህና ብትሆንም ሲመለስ ግን እያለቀሰች ስላገኛት፡፡ በምን እንደምታለቅስ ግራ ገባው፡፡ ልጁን ከእቅፏ ላይ አንስቶ ታቀፈው፡፡ ባየው ነገር ሆዱ ባባ፡፡ ከየት መጣ ሳይባል እንባ ከአይኖቹ ተንጠባጠቡ፡፡

የተፈጠረውን ለማውቅ ደግሞ "ምንድ ነው የሆሽው? ለምን አትነግሪኝም? አለ ፤ እንደ መቆጣት ብሎ፡፡

አበበች እንባዋን እየጠራረገች አባባ አሁን መጥቶ ነበር አለች፡፡

"ታዲያ ምን አሉሽ ?፡፡

"ምን ይለኛል፡፡ ያው እየፈራን ላደረግነው ነገር አይንሽን ለአፈር አለኝ፡፡ አንቺ የባልሽ ገረድ ሆነሽ ባልሽ ዲቃላውን ይፈለፍላል፡፡ አሁን ባሌ ይሻለኛል ካልሽ ከዛሬ ጀምሮ ልጄ አይደለሽም፡፡ ብሞት እንኳን ከመቃብሬ ላይ እንዳትቆሚ ብሎኝ እያለቀስኩ አሁን ነው ጥሎኝ የወጣው፡፡

"ሚስጥሩን ነገርሻቸው እንዴ"?፡፡

"እኔ ልነግረው አስቤ ነበር፡፡ እሱ ግን የሚሰማኝ ስላልመሰለኝ አልነገርኩትም፡፡

"ድሮም እግዚአብሔርን ብለን እንጅ ይሄ እንደሚመጣ እያወቅን የገባንበት ነው፡፡ አሁን እውነቱ
እስከሚወጣ ድረስ የምናደርገው ምንም አይኖርም፡፡

ሚስጥሩ መውጣት ያለበት የእነሱም ቤተሰቦች የእኛም ቤተሰቦች ተሰብስበው ነው፡፡ እኔም ትላንትና አልነገርኩሽም እንጅ ከገበያ ስመጣ ወንድምሽ ከመንገድ አድፍጦ ሊገለኝ ሲል እሮጨ ነው ያመለጥኩት፡፡ ሁሉም ነገር ጥፋቱ የእኔ እስከሆነ ድረስ በእነሱ የምይዝባቸው ቂም የለኝም፡፡ ከአሁን በኋላ፤ እናትሽም ቢመጡም ሚስጥሩን እንዳትነግሪ፡፡ ምክንያቱም ወሬው በውጭ ከተወራ ተመስገንና እድላዊት ራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ፡፡ እነሱ ከሌሉ ሁሉም ነገር ጨለማ ለብሶ ሳይገለጥ ተዳፍኖ እንዳይቀር ጥንቃቄ ያስፈልገናል፡፡

ወዶዘማች

ወደ ጠጁ ቤቱ ጎራ አለ፡፡ አንድ ብርሌ ጠጅ አዘዘ፡፡ ሁለት አውቶቢስ አንድ ሚኒባስ ከላይዋ ላይ ድምፅ ማጉሊያ ጭና ከፊት ለፊት ቀድማ ትከንፋለች፡፡ የአስረስ ሽለላና ቀረርቶ በከፍተኛ ድምፅ ተለቋል፡፡ የአረርቲ ከተማን ከዳር እስከ ዳርም አናውጧታል፡፡ ታዲያ ሽለላና ቀረርቶው በጥቂቱ እንዲህ ይል ነበር፡፡

ኧረ ጎራው ኧረ መርዙ፤

ኧረ ጎራው ኧረ መርዙ፤

እንኳን በለው ብለው ልከው ሰደውት፤

ከወገብ ላይ ሆኖ ያኮራል ጥይት፡፡

ኧረ ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ከአፈሙዙ ዘቅዘቅ ከሰደፉ ቀና አድርገው የተኮሱ እንደሆን፤

ጥይት ሰው አይፈራም ምን ደንደሳም ቢሆን፡፡

ኧረ ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ዘሩ የመርዙ ትውልድ፤

አምሶ ይቀብራል እንደ እሳት ሰደድ፤

ኧረ ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ሀገሬ ኢትዮጵያ ኩሪ ይገባሻል፤

የማያስደፍሩ ጀግና ልጅ ወልደሻል፡፡

ኧረ ጎራው ኧረ መርዙ፤

አገሬን ኢትዮጵያ እሳት ይዞረዋል፤

ለመጥፋት ነው እንጅ ምን ይሻገረዋል፡፡

ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ዘራፍ የተጎረፈው በጠመንጃው ፊት ሰው የማያልፈው፤ ሳይነካኳቸው እየደረሱ ይመለሳሉ እየቀመሱ ፤

ታንክ ቢያሽካካ መድፍ ቢያጓራ፤

የሚጋፈጠው በሮ እንደ አሞራ፡፡….

ከአስረስ ሽለላና ቀረርቶ በተጨማሪ ጋዜጠኛ ገረመው ይታያል እሱም እንዲህ ይል ነበር፡፡
👍5211
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////

ሚካኤልና ፀአዳ አንድ ሬስቷራንት ቁጭ ብለው ተፋጠዋል፡፡ከሁለቱም ፊት ለፊት ተከፍቶ የተቀመጠ ቢራ አለ..አንዳቸውም ግን አንስተው አልተጎነጩለትም፡፡

‹‹ለምን ጊዜችንን ትጨርሳለህ…የሆንከውን ካልነገርከኝ እንደማለቅህ ታውቃለህ››

‹‹ፀዲ..ለምን ችክ ትያለሽ..?ምንም አልሆንኩ የስራ ጉዳይ ነው አልኩሽ እኮ››

‹‹እኮ ግድግዳ በመዶሻ የሚያስነድል ምን አይነት የስራ ጉዳይ ነው?፡፡ሚኪ እኔ እኮ ለአመታት ነው የማውቀው..አንተን የስራ ጉዳይ በዚህ ልክ ሊያበሳጭህ…ኦረዲ አብደሀል እኮ››

‹‹ተይ ፀዲ አታጋኚ››

‹‹አጋነንኩ እንዴ…?የማትነግረኝ ከሆነ …››አለችና እጇን ወደ ሱሪ ኪሷ ሰዳ ስልኳን አወጣች፡፡
‹‹ምን ልታደርጊ ነው?››ግራ በመጋባት ጠየቃት፡

‹‹ብቻዬን አልቻልኩህም..ለአዲስ ደውልላትና ትምጣ..ከዛ ለሁለት እንሞክርሀለን››

‹‹በፈጠረሽ……የእሷን ጭቅጭቅና ለቅሶ የምሸከምበት ትእግስቱ የለኝም››

‹‹እና ንገረኛ››

‹‹እሺ ነግርሻለው››
ስልኩን ጠረጴዛ ላይ ከቢራ ጠርሙሱ ጎን አስቀመጠችና ሙሉ ትኩረቷን ወደእሱ አደረገች፡፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቁዘማ በኋላ እንደምንም አፉን ከፈተ‹‹የአባቴ ጉዳይ ነው››

‹‹እሱንማ አውቄለው…ከዛ ውጭ አንተን በዚህ ልክ ሊረብሽ የሚችል ሌላ ጉዳይ የለም…በዝርዝር ንገረኝ፡፡

‹‹አባቴ እናቴንም ሆነ እህቴን እንዳልገደላቸው ነገረኝ…እኔም አምኜዋለው››

ፀአዳ ክፉኛ ደነገጠች‹‹እና ማን ነው የገደላቸው..?ማለቴ እንዴት ሞቱ?››ተንተባተበች፡፡

‹‹እሱን አላውቅም…አባቴ ግን ከመሞቴ በፊት እናትህንና እህትህን እኔ እንዳልገደልኳቸው በትክክለኛ ማስረጃ አረጋግጥልኝ፡፡ከመሞቴ በፊት ልጆቼ እኔ ንፅህ ሰው መሆኔን ማወቃቸውን ማረጋገጥ እፈልጋለው››አለኝ በማለት ሙሉውን ታሪክ በዝርዝር ነገራት፡፡

‹‹እና አሁን ምን ልታደርግ ነው…?እንዴት አድርህ ማረጋገጥ ትችላለህ?››

‹‹ግድግዳውን የናድኩት ለዛ ነበር..አባቴ እዛ ግድግዳ ውስጥ የደበቃቸው የተወሰኑ ማስረጃዎች ነበሩ..አለና ስልኩን ከፍቶ  በሚሞሪ ያሰቀመጣቸውን ቪዲዬዎች አስደመጣት፡፡ሽምቅቅ አለች፡፡

‹‹በጣም ያሳፍራል አይደል?››አላት፡፡

‹‹በእውነት ምን እንደምልህ አላውቅም››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹አየሽ ክህደት ምን እንደሆነ ምን አይነት ህመም እንደሚያስከትል ከእኔ በተሻለ አንቺ ታውቂያሽ..አባቴ እነዚህን ሁሉ መረጃዎች ካወቀ በኋላ ሚስቱ እሱን ሳይሆን ሌላ ሰው እንደምታፈቅር ከተረዳ በኋላ…በጣም የሚወዳት ቀምጥል ልጁ የእሱ ሳትሆን የሌላ ሰው ልጅ እንደሆነች ካወቀ በኃላ  ….የሁለት መንታ ወንድ ልጆቹ እናት እሱን ጥላ ወደልጅነት ፍቅረኛዋ ልትሄድ ዝግጅት ላይ እንዳለች በግልፅ ካወቀ በኋላ  ምንድነው ማድረግ ያለበት?ይሄንን ሁሉ በደል እንዴት መቋቋም ይችላል…?እና  እሱ ቢቀውስና የእብድ ስራ ቢሰራ ይፈረድበታል?››

‹‹በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው…ግን እኮ አላደረኩትም ብለውሀል….›››

‹‹እሱማ  አዎ እወነቱን እንደሆነ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ….ግን እንዳውቀው ካስቀመጠልኝ መረጃ አንድም እሱ እንዳለደረገው የሚገልጽ ፍንጭ ማግኘት አልቻልኩም..እና መተንፈስ እስኪያቅተኝ ድረስ በጣም ግራ ተጋብቻለው፡፡

‹‹ምን እንደገረመኝ ታውቃለህ?››አለች፡፡

ትኩረቱን በሙሉ ወደእሷ ሰበሰበና‹‹ምን? ››ሲል ጠየቃት፡፡
አባትህ በግድያው ተጠርጥረው ፍርድ ቤት በሚመላሰሱበት ጊዜ ይሄንን አሁን ለአንተ የሰጡህን መረጃዎች ለምን ለፍርድ ቤቱ አላቀረቧቸውም….ቢያንስ እኮ የተፈረደባቸው የሞት ቅጣት ወደእድሜ ልክ ይቀየርላቸው ነበር፡፡››

‹‹አዎ..ትክክል ነሽ…መረጃዎቹን እንዳገኘው እኔም ወደ አእምሮዬ የመጣው የመጀመሪያ ጥያቄ እሱ ነበር..እና ትናንትና ወደወህኒ ቤት ሄጄ አግኝቼው ነበር….ለምን ለፍርድ ቤት እንደመረጃ አድርገህ አላቀረብከውም ስለው…ለእናንተ ስል?››ሲል መለሰልኝ፡፡

‹‹አልገባኝም… እንዴት ለእኛ ስትል ?››ብየየ መልሼ ጠየቅኩት፡፡
‹‹እንዳልከው ይሄንን ለፍርድ ቤት እንደወንጀል ማቅለያ አድርጌ ባቀርብ ኖሮ ይሄኔ እናትም አባትም ነበር የምታጡት፡፡በወቅቱ የእኛ ቤተሰብ ጉዳይ በየጋዜጣውና መፅኄቱ እንዴት እንደሚፃፍ ታውቃለህ..ይሄ ነገር ወጥቶ ቢሆን ኖሮ ስለእናትህ ምን እንደሚፃፍ አስበው…የተፃፈ ነገር ደግሞ ታሪክ ሆኖ ይቀመጣል…የልጅ ልጇቼ ጭምር ስለወንድ እና ሴት አያታቸው ታሪክ ሲያነብ ምን አይነት የልብ መሰበር ያጋጥማቸዋል…የእኛን ማህበረሰብ ለነገሮች ያለውን ብያኔ የምታውቀው ነው..በእኔ ጉዳይ ምን ያህል ፈተና እና መገለል እንደሚገጥማችሁ አውቃለው…ይሄ የእሷ ታሪክ ቢጨመርበት ኖሮ መግቢያ መውጫ ነው የሚያሳጦችሁ››በማለት መለሰልኝ፡፡

‹‹አይገርምም !!ወላጅ መሆን እኮ እዳ ነው..አንዳንዴ የነፍስ ክፍያ ለመክፈል እንኳን የማታመነታበት ምስጢራዊ ፀጋ ነው፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ››

‹‹አሁን አንድ ምርጫ ብቻ ነው ያለን››

በንቃት‹‹ምን ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ሰውዬውን ፈልገን ማነጋገር››

‹‹የትኛውን ሰውዬ?››

ፈራ ተባ እያለች ‹‹የእናትህን ጓደኛ…..››ስትል መለሰችት፡፡

የሚካኤል ደም ስር በንዴት ውጥርጥር አለ‹‹እሱ እኮ ጠላታችን ነው..እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ የከተተን እሱ ነው…ፊት ለፊት አግኝቼ እንድገድለው ነው የምትፈልጊው፡፡››

‹‹የሆነ ፍንጭ ለማግኘት የግድ እሱን ማግኘት አለብን…የግድ አንተ ልታናግረው አይገባም…ቆይ እስኪ››  አለችና ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጠችውን ስልክ አንስታ ከፈተች ..ምን ልታደርግ ነው ብሎ ሲጠብቅ‹‹ስሙ ማን ነበር››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹የማ?››

‹‹የሰውዬው ነዋ››

‹‹ለሚ በቀለ ››

ስሙን ሰርች ላይ ከታ መፈለግ ጀመረች፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ዳይሬክተር ዳይሬክቶሪት ደ/ር ለሚ  በቀለ የሚል ዜና አየች፡፡

‹‹እንዴ ሰውዬው ባለስልጣን ነው እንዴ?››

ምንም አልመለሰላትም..ዜናውን ከፍታ ለማንበብ ሞከራች…ከአምስት አመት በፊት የተፃፈ ዜና ነው፡እሱን ተወችና ….ሌላ ፈለገች ..ሶስት አራቱን ከከፈተች በኃላ በአራተኛው ትኩረት ሚስብ ዜና አገኘች‹‹የግብርና ሚንስቴሬ ዳይሬክተር ዳይሬክቶሬት የሆኑት ዶ/ር ለሚ  በቀለ በጤና እክል ምክንያት መልቀቂያ በማስገባት ስልጣናቸውን ለቀዋል ››ይላል፡፡ከአራት አመት በፊት የተለቀቀ ዜና ነው፡፡

ወደፌስብክ ገባችና በስሙ ፈለገች.. ዲአክቲቬት ከሆነ አመታት አልፈዋል፡፡

‹‹ሰውዬው ጥሩ ሁኔታ ላይ አይመስለኝም….ቆይ ለእኔ ተውልኝ››

‹‹ምን ልታደርጊ አሰብሽ….?››

‹‹ያለን ምርጫ አንድ ብቻ ነው፣ቢያንስ አሁን አንድ ነገር አውቀናል..ከአራት አመት በፊት ግብርና ሚኒስቴር ይሰራ ነበር…ስለዚህ አዛ ሄድና አሁን ሚገኝበትን አድራሻ ጠይቃቸዋለው…ቢያንስ ስልኩን ይሰጡኛል፡፡››

‹‹እስቲ እናያለን››ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡

‹‹አይዞህ ምንም አትጨነቅ..ይሄንን ነገር እንፈታዋለን….የፈለገ መስዋእትነት ያስከፍል የአባትህን ምኞት እናሳካለን….ይሄ ጉዳይ ዘሚካኤልንም ወደቤተሰቦቹ እንዲመለስ ለማድረግ ያግዘን ይሆናል፡፡››

‹‹እኔ እንጇ..ዘሚካኤል እናቱን እንደፈጣሪው ነው የሚወዳት..ለእሱ እሷ እንከን አልባ መልአክ የሆነች ሴት ነች…ይሄንን ሲሰማ ዳግመኛ ይበልጥ  እንዳይሰበር ነው የምፈራው፡፡

‹‹አይዞህ ….ከመሰበር በኃላ ያለ መጠገን ነው እኛን ሞርዶ ሙሉ ሰው የሚያደርገን፡፡ደግሞ እናትህ ጥፋት ያጠፋችው  በሚስትነቷ ነው እንጂ በእናትነቷ  እስከወዲያኛው ምሉ እንደሆነች ነው፡፡››
👍6611🥰1
የግዜርየአደራልጅ…


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

ከብዙ ድካምና ልፋት በኃላ የኖብል ፋውንዴሽን አመታዊ የገቢ ማሰባበሰቢያ ቀን ደረሰ፡፡አሁን በግዙፉ እና ነፋሻማው በወላጆቿ ቤት ሁሉም አይነት ዝግጅት ተጠናቆ እንግዶችን በመጠባበቅ ላይ ናቸው‹‹እርግጠኛ ነህ ምንም ነገር የጎደለ የለም?›› ራሔል ሮቤልን ለአራተኛ ጊዜ ጠየቀችው።

በሙሉ የራስ መተማመን‹‹ሁሉ ነገር በቁጥጥር ስር ነው…አንቺ ምንም አታስቢ›› ሲል መለሰላት፡፡
ራሄል የመጀመሪያ እንግዶች በእርሻ ቦታው ላይ በሰዓቱ ሲደርሱ ስትመለከት ተደሰተች። እሷ እንደዚህ ቀደሞቹ ዝግጅቶች ሙሉ ቁጥጥር አልነበራትም። በዚህም ምክንያት በሁሉ ነገር ላይ በቀላሉ  እርግጠኛ መሆን አልቻለችም፡፡
በነገራት ነገር እንዳላመነችው የተረዳው ሮቤል‹‹ ደህና ነን። ነገሮች ጥሩ ናቸው። ሁሉም ሰው በጥሩ ሁኔታ ስራውን እየሰራ ነው። ምንም አትጨናነቂ ዘና በይ …  ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች  ገንዘብ  መሰብሰብ ሲጀመር የፋውንዴሽናችን ካዝና ሞልቶ ይፈሳል፡፡ ››አላት፡፡

ከመጠን ያለፈ በራስ መተማመኑን አልወደደችለትም፡፡ቢሆንም ማድረግ የምትችለው ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ያልታሰብ ችግር እንዳይፈጠር መፀለይ ብቻ ነው፡፡ግን ችግሩ መፀለዩም ለእሷ በቀላሉ መደረግ የሚቻል ነገር አይደለም፡፡

ቀስ በቀስ ግቢው በእንግዶች እየተሞላ መጣ…የቅርቧ ሰዎች ጓደኞቾና ዘመዶቾን ጨምሮ ከዚህ በፊት በዝግጅቷቾ ላይ ተገኝተው የማያውቁ ሚዲያ ብቻ ማታውቃቸው በርካታ ታዋቂ እና ዝነኛ ሰዎች እዚህምእዛም ስታይ በጣም ተገረመች…የሚዲያ ሰዎች በየቦታው እየተሹለከለኩ የመረጡትን ሰው ፎቶ በማነሳትና ቃለመጠየው በማድረግ ተጠምደዋል፡፡

የሚገርም ሁኔታ ቀስ በቀስ  የበለጠ ነፃነት፣ እና ቀላል ያለ  ስሜት እየተሰማት መጣ።ስሯ ያለችው ፀጋ እጇን ስትይዛት ወደቀልቧ ተመለሰች እና ወደታች አጎንብሳ ተመለከተቻት።

በጣቷ ወደ ግራ እየጠቆመቻት‹‹ኤሊ..ኤሊ››አለቻት፡፡ራሄል ጥቆማዋን ተከትላ እይታዋን ወደዛው አዞረች፡፡ዶ/ር ኤልያስ ወደእነሱ እየመጣ ነው፡፡ጥቁር ሙሉ ሱፍ ለብሶ ሽክ ብሏል፡፡ስራቸው ሲደርስ

‹‹ኤሊ. ኤሊ. መጣህ››ትሁት ጮኸች.

የራሄል ልብ ዘለለ፡፡ ዔሊያስ ጎንበስ ብሎ ፀጋን በእቅፉ አስገባትና ስሞ መልሷ አስቀመጣት…። በዚህ ጊዜ ሮቤል ራሄል ጀርባ ደርሶ የሁነ ነገር በሹክሹክታ እየነገራት ነበር፡፡

የኤልያስ የደመቁ ጥቁር ዓይኖቹ ወደ ሮቤል በረሩ፣ ‹‹ኤሊ  ሮቤል ይባላል  … ረዳቴ ነው .››ብላ አስተዋወቀችው፡፡

‹‹ሮቤል እሱ ደግሞ ዶ/ር ኤልያስ ይባላል…››በቀደም  ከንፈሬን የሳመኝ እሱ ነው› የሚለውን ተጨማሪ ንግግር በውስጧ አከለችበት ,፡፡

ዔሊያስ  የሮቤልን እጅ   እየጨበጠው‹‹ስለተገናኘን ደስ ብሎኛል።››አለው፡፡

ሮቤል በደማቅ ፈገግታ ተሞልቶ በቀልድ መልክ  ››ራሔል ስራዎቾን በውክልና ለእኛ አሳላፋ መስጠት እየተማረች ነው። በተቻለህ መጠን ከእኛ አርቀህ ብትይዝልን ደግሞ ነገሮች ከዚህ በላይ እየተሻሻሉ ይሄዳሉ ››አለው

ኤልያስ የሮቤልን ንግግር እያዳመጠ   ዓይኖቹ  ራሔል ላይ ተከለ።

‹‹እንዳልከው አደርጋለው.››አለው ዔሊያስ…ሮቤል ተሰናብቶቸው ወደስራው ተመለሰ፡፡
ብቻቸውን ሲሆኑ ራሄል ቀሚሷን ወደታች እየጎተተች ያስቸገረቻትን  ፀጋን  ወደላይ አንስታ አቀፈቻት እና‹‹በመምጣትህ ደስ ብሎኛል››አለችው ።

‹‹አመሰግናለው››አላት

ፀጋ ፀጉሮሯን እየነጨችና ፊቷን እየቧጨረች አስቸገረቻት‹‹አንቺ ሞኝ  ልጅ ..እረፊ… ፀጉሬን ነቀልሽው እኮ››አለቻት  ራሄል ።

ፀጋ በደስታ ሳቀች ።

‹‹አውርጂኝ ›› ብላ ጠየቀች እና ዔሊያስም እንድታወርዳት ነገራት።እንዳወረደቻት  ለመጫወት ከእነሱ ራቅ ብላ ወደ ሜዳው ኩስ ኩስ እያለች ሄደች፡፡

ራሄል ፀጋ  የበታተነችባትን ፀጉር ለማስተካከል እየሞከረች ‹‹መጀመሪያ ወደ ቤት ሄጄ ፀጉሬን መልሼ መስራት አለብኝ›› አለችው፡፡

ዔሊያስ  ከፀጉሯ ላይ ያረፈች ሳር እያነሳ  ‹‹ባታስተካክይውም ቆንጆ ነሽ ››አላት፡፡

ጉንጯ በእፍረት ቀላ‹‹ አመሰግናለው..ግን እንደምታየው ልብሴንም መቀየር አለብኝ?››

ራሄል አለባበሷ ለስራ ከምትለብሰው ልብስ ጋር ሲነፃፀር የተለመደ ነው ግን ሰሞኑን እቤት ስትውል ከምትለብሳቸው  ልብሰች አንፃር በጣም ያጌጠና ያመረ የሚባል ነው፡፡

የዔሊያስ ተንኮል አዘል ፈገግታ ተፈታተናት፣ እጁ ዘንበል ብሎ አገጯን እየነካካ ‹‹ጸጉርሽን እንዲህ ስትለቂው   ደስ ይለኛል.››ሲላት ለአፍታ ልብን የሚያቆም ፍርሀት ወረራት፡፡

‹‹እንደገና ሊስማኝ  ነው እንዴ?›› ብላ  በውስጧ አሰበች። እንዲያደርገው  ፈለገች።

ፍርሀቷን  በሳቅ ለመሸፈን እየጣረች  ‹‹ፀጋ ሳትርቅ ብንሄድ ይሻለናል››አለችው፡፡
ወደፀጋ ሄዱና እያንዳንዳቸው አንዳንድ እጃን ያዙ. ራሄል ከሩቅ ለሚያያቸው ሰው ልክ ወደ ወ.ሮ ላምሮት ቤት ሲሄድ  እንደነበሩት ቀን  ቤተሰብ እንደሚመስሉ አሰበች። ።ወደጎን   ዞር ብላ ስታየው  ዓይናቸው ተገናኘ። ቢፌ በተደረደረበት ግዙፍ ጠረጴዛ አጠገብ ሲያልፉ  የ ሰላጣ ሳህኖች ባዶ ሆነው አየችና እንደመበሳጨት ብላ‹‹ይቅርታ አድርግልኝ..ይህን ማስተካከል  አለብኝ.››አለችውና ተለይታቸው ልትሄድ ስትል ዔሊያስ  ፈጠን አለና  እጇን በእጁ ያዘ።

‹‹አይ, ይሄ የአንቺ   ስራ አይደለም, ሮቤል እና አዲሷ ረዳትሽ ሁሉንም ነገር በቁጥጥራቸው ስር አድርገውታል…ለእነሱ ተይላቸው.››አላት፡፡ራሄል ፊቷን አኮሰታተረች እና ተቃውሞዋን ልታሰማ ስትል አንዲት ተለቅ ያለች ነጭ ዩኒፎርም  የለበሰች ሴት በላስቲክ የተሸፈነ ሳህን ይዛ መጣችና   ባዶውን የሰላጣ ሳህን ስትሞለ ተመለከተች፡፡

ኤሊያስ ቅንድቡን ከፍ አድርጎ ‹‹አየሽ…ዘና በይ ..ሁሉ ነገር አሪፍ ይሆናል?››ሲል  ተናገረ።ራሄል በራሷ ችኮነት አፍራ ሳቀች።

‹‹እሺ በቃ ዘና እላለሁ ።››አለችና  ረዥሙ ትንፋሽ ሳበች ፣ ዙሪያውን ተመለከተች እና ይህንን እንደምትለምድ ተገነዘበች። የገቢ ማሰባሰቢያ  ዝግጅቱ ብዙ ጊዜ የተጣደፈ ፣ የተቸኮለ  ነበር፣አሁን የምታው ግን የተረጋጋ እና ዘና ያለ ሆኖ ነው ያገኘችው  ፡፡አሁንም እየፈገገ ያለውን ዔሊን ተመለከተች እና ከሰዎች ጋር በቀላሉ መዋሀድ  መቻል እንዴት ጥሩ እንደሆነ አሰበች። ዔሊም እያንዳንዱን እንግዳ ስታናግር  ከጎኗ እንዲሆን ፈለገች።

ራሄል በሳቅ ፈገግታ ተጥለቅልቃ‹‹አስደናቂ ቀን ይሆናል ብዬ አስባለሁ››አለችው ።

ኤልያስም‹‹እንደዛ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ ።››ሲል ተጨማሪ ጥንካሬ ሰጣት።ከዚያም ራሄል ይቅርታ ጠየቀችውና  አዲስ ወደገቡት እንግዶች ሄደች፡፡እሱ ፀጋን እንደያዘ በተወሰነ ርቀት ወደኃላ ቀረ፡፡ እንግዶቹን እያወራች   ትኩረቷ በዔሊ ላይ ነበር። 

ኤልያስ ዙሪያ ገባውን እየቃኘ የራሱን ትዝብት መውሰድ ጀመረ…አዎ እሱም እንደማንኛውም ሰው የራሱ እቅድ ነበረው፣ ነገር ግን ከዚህ ህዝብ ጋር ለመስማማት ትንሽ ከፍ ብሎ ማቀድ፣ ትንሽ መስራት፣ የአምስት አመት እቅድን ቢያንስ ወደ አስር አመት ማስፋፋት ይኖርበታል።እና የዛን ጊዜ በእንደዚህ አይነት ዝግጅት ላይ ከሚሳተፉ ከላይኛው ማህበረሰብ ሰዎች ጋር በደንብ ተቀላቅሎ ዘና ብሎ ማውራት ይችል ይሆናል..እስከዛው ግን   እንደተነጠለ መቆየት መርጧል፡፡

በሀሳብ ተውጦ ሳለ ድንገት ከኋላው መጣችና‹‹ሰላም ነህ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ደህና ነኝ። ትንሽ የመጨናነቅ ስሜት እየተሰማኝ ነው።›› ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ብዙ አዲስ ፊቶች ሲመጡ እያየው ነው›› አለች ራሄል ። ‹‹ግን ከጊዜ በኋላ ታውቋቸዋለህ። ››
75👍2