አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አይኖቹን ዙሪያውን ሲያሽከረክር በሆቴሉ የተለያዩ ኮሪደሮች የተሠቀሉት ባለሰፋፊ ፍላት እስክሪን ቲቪዎች በጠቅላላ እያሳዩ ያለው የግርማንና የአሮሯን የወሲብ ጫወታ እየመሠለው ነው? በእሱ እይታ ፊት ለፊት ከመንገድ አሻግሮ ያለው ቢልቦርድም እንደዛው የአሮሯ እርቃን ገላ ነው የሞላው...
...ግን ይሄ ሁሉ ከሆነ በኃላ ለምን በእሷ እንዳልተበሳጨ እየገባው አይደለም... አሁንም በውስጡ ያለው ለእሷ የመንሰፍሰፍና የማዘን ስሜት ባለበት እንዳለ ነው...እንደውም ይበልጥ መጠኑን እየጨመረ እየመሠለው ነው....ግርማ በሆነ ድክመቷ ገብቶ እንዳታለላት በሆነ የልጅነት ክፍተቷ ገብቶ ህይወቷን እንዳጨመላለቀባት ነው እየተሠማው ያለው።በዚህ ምክንያት ይበልጥ ግማሽ ልብና ግማሽ ነፍሱ ታመውበታል።አርራ አሳዘነችው።አርራ ናፈቀችው።በዛ ምክንያት ግርማን በተቃራኒው በፊት ከሚጠላው በላይ ጠላው...በፊት ሊያሰቃየው...ሊቀጠቅጠው... ሊቦጫጭቀው ...ሊበቀለው ከሚፈልገው በላይ ለማድረግ  ቸኮለ...።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
41👍18😱3
ልሂድ አልኩት ነፃነቴን እወደው ነበር እንዳሻኝ መብረር ፍላጎቴ ነበር። ፊቱ ላይ ተተንትኖ የማያልቅ ብዙ ስሜት አነበብኩበት...

አወደዋለሁ ከሱ በላይ ግን ነፃነቴን እወደዋለሁ። ለስሜቱ ግድ ሳይሰጠኝ ከእቅፉ ወጥቼ ወዳሻኝ በረርኩ... በ ረ ር ኩ.. ጥቂት ለማይባሉ ጊዜያቶች ያማረኝ የወደድኩት ላይ እያረፍኩ በረርኩ። አምሮኝ ያረፍኩበት ላይ ሁሉ ግን ጎጆዬን መቀለስ አልቻልኩም...

ቋሚ ማረፊያ ፈለግሁ፣ ጎጄዬ ናፈቀኝ፣ ያን ጊዜ ትዝ አለኝ የት ይሆን? ያለው ያስታውሰኝ ይሆን?

ናፈቀኝ... ስለሱ ሳስብ የተዳፈነ ፍቅሩ ተቆሰቆሰብኝ እቅፉ...፣ በስስት የተሞላ አስተያየቱ...፣ ስሜን ሲጠራ ማቆላመጡ(አፉ ላይ ሲያምር እኮ) ብዙ ነገሩ ትዝ አለኝ።

ለምን ነበር የተለየሁት? ምን አድርጎኝ ነበር? በዚያን ጊዜ  እኔን ለማስደሰት ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ በቀስታ እየተንቆረቆሩ ወደ ትውስታዬ መጡ። ከሱ ምን አጥቼ ነው? ምን ነክቶኝ ነው ያን የመሰለ ፍቅር ረግጬ የሄድኩት...ስለሱ ባሰብኩ ቁጥር ናፍቆቱ አንገበገበኝ። 

ልፈልገው ተነሳሁ የት እንዳለ ባላውቅም የጋራ ጓደኛችን ወደነበረው ልጅ ቤት አመራሁ። ሲያየኝ ብዙ መገረም አየሁበት። "ከሳሽ በጣም ተጎሳቁለሻል ታመሽ ነበር" አለኝ። አይ አልኩት መች ነው የተጎሳቆልኩት? ድሮ እንዴት ነበርኩ? አሁንስ ምን የተለየ ነገር ሆንኩ?

ቤቱን በሩቅ አሳይቴኝ በቃ ልመለስ አለ። የድሮ የጓደኝነታችን ወዝ ሙጥጥ ብሎ ጠፍቷል ልክ ለአንድ መንገድ ለጠፋባት ሴት መንገድ አሳይቶ የሚመለስ ሰው ነው የሚመስለው።

ስለሱ ማሰቤን ትቼ ወደ ጠቄመኝ ቤት አመራሁና በሩን አንኳኳሁ ትንሽ ቆይቶ በአንድ ጎልማሳ በሩ ተከፈተ

" አቤት ማንን ፈልገሽ ነው እናትዋ" አለኝ። ቃል አብን ፈልጌ ነበር ይኖራል።

"ጋሼ ሲመሽ ነው የሚመጡ ወይም ስልክሺን ጣፊና ስጪኝ እንዲደውሉብሽ እነግራቸዋለሁ" በቋንቋው ለዛ እየተገረምኩ። እንደማያስፈልግ ነግሬው ወደ ቤት ተመለስኩ

በማግስቱ ወፍ ሳይንጫጫ ውጪ በሩ ስር ቁጭ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ። ቆይቴ በሩ ተከፈተ ወደጎን ሆንኩና የሚወጣውን ሰው መጠባበቅ ጀመርኩ የኔ ቃል የምታምር መኪና ይዟል። ከጎኑ የምታምር ሴት ተቀምጣለች። ከግቢው ከውስጥ " ቻው ዳዲ" የሚል የህፃን ድምፅ ሰማሁ። "ቻው የኔ ልጅ (እጁን ሲያውለበልብ የሚያበራ የጋብቻ ቀለበት አየሁ) ወደ ውስጥ አስገቢያት ብርድ ነው" ላላየኋት ሴት ትዛዝ አስተላለፈ።

ብርድ ነው..... ብርድ ሰውነቴ ተንዘፈዘፈ እንዳያየኝ ፊቴን አዙሬ ትንሽ ተራሙድኩና ጭብጥ ብዬ ተቀመጥኩ። የማስበውን አላውቅም ብዙ ሀሳቦች በፍጥነት ጭንቅላቴ ውስጥ መጥተው ይሄዳሉ?

ምንድነበር የማስበው ያሻኝ ጋ በርሬ ስመጣ ጌጆዬን እንደማገኘው? እንዴት ለሰከንድ እንኳን ስመለስ ጎጆዬን እንደማጣው ሌላ ወፍ ማሳደር እንደሚጀምር ሳላስብ ቀረሁ?

ቀስ ብዬ ተነሳሁናእግሬን እየጎተትኩ መጓዝ ጀመርኩ ሰፈሬ ካለሁበት በጣም ቢርቅም ታክሲ መያዝ አልፈለኩም። እርምጃዌቼ በጨመሩ ቁጥር እኔ አሁን የተሰማኝን ስሜት ድሮ እሱ ሊሰማው ከሚችለው ጋር አነፃፀርኩት። እንዴት አለፈው??

በእውነት የእጄን ነው ያገኘሁት እሱ ግን ተክሷል


አይቀጥልም
ተፃፈበፅዮን


    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍6714😢13
#አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-38
#ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎

አቶ ግርማ ናይትክለቡ ውስጥ በሚገኝ የግል ቢሮው ቁጭ ብሎ እያብሰለሰለ ነው፡፡የአሮራን ነገር መስመር እያስያዘ ነው፡፡ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ወደቱርክ ይልካታል….ከዛ ደግሞ እዛ ባሉ ወዳጆቹ አማካይነት ወደ ሌላ ወደፈለገችው ሀገር እንድትሻገር ይረዷታል..ያንን ካደረገ በኃላ ደግሞ እስከወዲያኛው ይገላገላትና ቀጣይ ህይወቱን በአዲስ መልክ ይጀምራ…ይህቺን  ትእግስት የምትባለዋን  ልጅ  ወዷታል..እናም  ቀጣይ ህይወቱን ከእሷ  ጋር መሞከር ፈልጎል፡፡ስለ እሷ ሲያስብ ናፈቀችው፡፡
ስልኩን አወጣና ደወለላት...፡አልተነሳም ተዘጋበት…ከዛ ወዲያው ሚሴጅ መጣለት።
ꔚꔚꔚ
ግርምሽዬ ..ይቅርታ እማዬ ስሬ ስላለች ስልክህን ማንሳት አልቻልም…ምንም አታስብ..አሁን ስብራቴን  ታሽቼ አልጋዬ ውስጥ ተኝቼ እናቴ የሰራችልኝን አጥሚት  እየጠጣሁ ነው፡፡
ꔚꔚꔚየሚል መልዕክት ላከችለት፡፡
ደስ አለው፡፡
ꔚꔚꔚ
‹‹ደህና መሆንሽን ስለሰማሁ ደስ ብሎኛል…..እኔ ብንከባብሽ በጣም ደስ ይለኝ ነበር፡፡ለማንኛውም ቶሎ ዳኚልኝ…የምትፈልጊው ማንኛውም ነገር ካለ ደውይልኝ ወይም በመልዕክት አሳውቂኝ፡፡ እና ደግሞ እየወደድኩሽ ስለሆነ  ደስ ብሎኛል።
ꔚꔚꔚብሎ ፃፈና ላከላት፡፡
እና ሌላ ስልክ ደወለ።መንግስቱን እንዲያግቱለት ወደቀጠራቸው ሰዎች ነው የደወለው።
‹‹እና እንዴት ናችሁ?››
‹‹አቶ ግርማ እየተከታተልነው ነው፡፡››
‹‹በጥንቃቄ ተከታተሉት…ልጁ ወሮ በላ ስለሆነ አቅልላችሁ እንዳታዩት››
‹‹ችግር የለውም..አንድ ሆቴል ውስጥ ከአንደ ሴትንና ከሌላ አንድ ወንድ ጋር ቁጭ ብለው ውስኪ  እየተጋቱ ነው..ፎቶ አንስቼያቸዋለሁ አሁን እልክልሀለው››
‹‹በዚህ በጠራራ ፀሀይ መጠጥ?››አቶ ግርማ በገረሜታ ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ የሆነ   የምስራች ሰምተው  እያከበሩ ይመስላል››
‹‹አሪፍ ነው …..ሰከር ማለቱ ስራችሁን በተወሰነ መጠን  ያቀልላችኋል…በሉ አድፍጣችሁ ጠብቁና  ከሰዎቹ ሲነጠል አድርጉትና ያሳየዋችሁ ቦታ ውሰዱት ..ከዛ ደውሉልኝ …..››
‹‹እሺ ሀለቃ››
ስልኩ ተዘጋ፡፡ወዲያው መልእክት መጣ፡፡ፎቶ ነው የተላከለት።ከፈተው ድንዝዝ ነው ያለው ፡፡ታማለች ብሎ ሲጨነቅላት የነበረችው ሴት ከቁጥር አንድ ጠላቱ ጋር በደስታ ሆቴል ቀጭ ብላ መጠጥ እየተጋተች ነው…ከዛም በላይ ደግሞ የገዛ ወንድሙም የጠላቶቹን ቡድን ተቀላቅሏል፡፡ማመን አልቻለም..."መጀመሪያውኑስ እንዴት ባለ አጋጣሚ ከየት የት ብለው ተገናኝተው ተዋወቁ....?"ጭንቅላቱን የበላው ትልቅ ጥያቄ ነበር።
‹‹ምን እየተካሄደ ነው ?››ጠየቀ
አሁን ጠላቶቹ አንድ ላይ ተሰብስበው እየጠጡ ያሉት  የት ቦታ እንዳለ ፎቶው ላይ በግልፅ ያስታውቃል… የመሳቢያውን ኪስ ከፈተና ሽጉጡን አወጣ… ውስጡ ሙሉ ጥይት መኖሩን  አረጋግጦ ጎኑ ሸጎጠና ኮቱን ከማንጠልጠያው ላይ በማንሳት እየተንደረደረ ወደ ውጭ ወጣ….መኪና ውስጥ ሲገባ ጋርዱ እየሮጠ ወደእሱ መጣ …ችላ አለውና መኪናዋን አስነስቶ ተፈተለከ…ከናይት ክለቡ ማዶ መኪና ውስጥ ሆነው ሲከታተሉት የነበሩት መንግስቱ የቀጠራቸው ጋንግስተሮች የመኪናቸውን ሞተር አስነሱና ከኃላ ይከተሉት ጀመር ፡፡
በመንገድ መካከል ወደነዳጅ ማደያ ጎራ አለ...
መኪናዋ ቀይ አብርታለች ።በዛ ላይ ፊኛው ወጥሮታል...መኪናውን ለነዳጅ ቀጂው አስተካክሎ  ሲያቆም ከኃላው በመንግስቱ የተቀጠሩት በክንዴ የሚመራው   አጋች ብድን  ከኃላው መጥተው ተከው ቆሙ። አቶ ግርማ  ነዳጅ ከተሞላ በኃላ ቦታውን ለሌላ ተረኛ በመልቀቅ መኪናውን ጠጋ አድርጎ አቆሙና ከፍቶ ወረደ....የመኪናውን በራፍ መልሰው ዘጋና ወደ ማደያው የካፌ መፀዳጃ ቤት ተንቀሳቀሰ..  ክንዴ  መኪናዋን ወደ ጎሮ በኩል  አንቀሳቀሰና የሽንት ቤቱን በራፍ ዘግቶ አቆመው...
"ቶሎ ብላችሁ ውረድ"የሚል ትዕዛዝ ሰጠ።
መኪና ውስጥ ካሉ አራት አጋቾች ሁለቱ ወረድና ተንደርድረው ወደሽንት ቤት ገብ ...እራሱን አስተው መኪናቸው ውስጥ አምጥተው ሲጥሉት ሁለት ደቂቃ አልፈጀባቸውም...ይህንን ሲያደርጉ  ልብ ብሎ ያያቸው ስው እንኳን አልነበረም።ከዛ አንደኛው ከኪሱ ውስጥ  የመኪናውን ቁልፍ አወጣና  ቀጥታ ወደእሱ መኪና  በመሄድ ከፍቶ ገብቶ  በማንቀሳቀስ..ይዞት ወጣ...ጓደኞቹ ከኃላ ተከተሉት።አምስት መቶ ሜትር ያህል ከተጓዙ ብኃላ ሁለቱ መኪኖች የተለያየ አቅጣጫ ያዙ...። የአቶ ግርማን መኪና እየነዳ የወሰዳት በጥንቃቄ ናይት ክለብ አቅራቢያ ወስዶ አቆማትና አሻራው መኪና ውስጥ እንዳይገኝ በጥንቃቄ ካፀዳዳ ብኃላ ማንም ስያየው ከቦታው ተሠወረ ።
ሌሎቹ ደግሞ አቶ ግርማን ይዘው ቀድመው ወዳዘጋጅት ከከተማው ዳርቻ ወደሚገኘው ስውር ስፍራ ወሰድት።
🍎🍎🍎
መንግስቱ  በመጠጥ ከታጀበ ሀሳብ ውስጥ የስልኩ ድምፅ ማሰማት ነው  ያባነነው። ይጠብቀው የነበረ ስልክ ስለነበረ ቁጥሩን እንኳን ሳያይ አነሳው...
"ሄሎ ተሳካልህ.?
"ምኑ ነው ሚሳካው?"
"ወሽመጡ ብጥስ አለ...በንዴት ከተቀመጠበት ተነሳ..."ውቢት አሁን በዚህ ሰዓት ምን ፈለግሽ ደሞ?"
"ሰውዬ ቀስ በል...አጎትህ መምጣቱን ልነግርህ ነው"
"አጎቴ!!! ምን ሊሰራ?"
የማሾፍ ቃና ባለው የድምፅ  ቅላፄ"በፈጣሪ!! አሁን ሰው ወደቤቱ ሲመጣ ምን ሊሠራ ይባላል..?.ናፍቄው ነዋ የመጣው ...ሚስቱ እኮ ነኝ"አለችው
"አንቺ  ስልክሽን ላውድ ላይ አርገሽው እንዳይሆን?"
"አረ እንደመጣ ነው ደክሞኛል ትንሽ ላሳልፍ ብሎ ወደመኝታ ቤት የገባው"
"እና ታዲያ እኔ  ጋር ምን አስደወለሽ...አብረሽው አትተኚም?"አለና ስልኩን ዘግቶ ወደ መቀመጫው ተመለሰ። በጣም ተበሳጭቶል ።በቅርብ እንደሚመጣ ከሳምንት በፊት ሲደዋወሉ ነግሮት ነበር...እንደዚህ በፍጥነት ይመጣል ብሎ ግን ምንም አይነት ግምት አልነበረውም።
"ገደል ይግባ"ሳያስበው ነው ድምፅን ከፍ አድርጎ የተራገመው።
"ማነው ገደል የሚገባው?"በስካር ምክንያት በተኮላተፈ አንደበት የጠየቀችው ትዕግስት ነች።
"አሁን በዚህ ሰአት ማን ገደል እንዲገባለት እንደሚፈልግ አታውቂም?"አላት እዝራ።
"ገባኝ....አዎ ገደል ይግባ"
🍎🍎
በዚህን ጊዜ በድጋሚ  ስልኩ ድምፅ አሰማ..ሚሴጅ ነው ከፍቶ አነበበው።
🍎🍎
ሀለቃ...እቃውን አግኝተን በጥንቃቄ ቦታው ላይ አድርሰናል።በተመቸህ ሰዓት መጥተህ ማየት ትችላለህ"
🍎🍎ይላል።
ፈገግ አለ።ከመቀመጫው ተነሳ።"ሰዎች የሆነች ጉዳይ አለችብኝ ...ልለያችሁ ነው"
"ካስፈለግንህ እንከተልህ?"ትዕግስት ጠየቀች
"አይ የምታስፈልጉኝ ከሆነ ደውላለሁ...በሉ ይመቻችሁ"አለና ብርጭቆ ውስጥ የቀረችውን መጠጥ ጨለጠና በፍጥነት የሆቴሉን ግቢ ለቆ ወጣ።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍11019🥰4😁1
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ምዕራፍ-39
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
መንግስቱ ግርማን አግኝቶ እስኪ ቦጫጭቀው ቸኩሏል፡፡ደግሞ ሲያገኘው ምን ሊነግረው እንደሚችል ሲያስብም ፈርቷል፡፡‹‹ገድያታለው ቢለኝ እና እሬሳዋን የቀበረበት ቦታ ወስዶ ቢያሳየኝስ››ሲል አሰበና ዝግንን አለው፡፡ይሄን በሰማ በደቂቃዎች ውስጥ የግርማን ግንባር በርቅሶ እንደሚገላግለው እርግጠኛ ነው፡፡ጥያቄ ሊሆን የሚችለው ከዛስ የሚለው ነው….? እሷ የሌለችበት አለም እየኖረ እሷ የማትስበውን አየር እየሳበ መቀጠል ይችላል ወይስ እሱም እራሱን አጥፍቶ ይላገላል?፡፡እርግጠኛ መሆን አልቻለም…፡፡መንገድ ጠርዝ አቁሟት ወደነበረችው መኪና መጓዝ ጀመረ፡፡ቀጥታ አሁን ግርማን አግደው ወደአስቀመጡት ቦታ ነው የሚሄደው….ቁልፉን አወጣና ሪሚቱን ተጭኖ  የመኪናውን በራፍ ለመከፍት በሚስብበት ቅፅበት ሁለት ከእሱም የሚገዝፉ ጠብደል ጎረምሶች ልክ እንደ ቅርብ ወዳጅ ከግራና ቀኝ መጥተው ከበቡት፣..በግራ በኩል ያለው እንደውም እጁን ትከሻው ላይ ጣል አደረገበት እና አቀፈው ፡፡መንግስቱ ግራ ገባው…መልካቸውን ተመለከተ ..ካለዛሬም አይቷቸው አያውቅም…ኪስ አውላቂዎች ነበር የመሰሉት… በቀኝ በኩል ያለው ከትልቅ ጃኬቱ እጅን እንደከለለ የሆነ ነገር ወደጎኑ አስጠጋ ..ቆረቆረው፡፡ሹጉጥ መሆኑን አወቀ፡፡
‹‹ነፍሱ ግርግር ሳትፈጥሪ ወደ መኪናው ግቢ ››አለው፡፡
ቀስ ብሎ ገባ ..አንደኛው ቶሎ ብሎ ከኃላ ወንበር ገባ እና ሽጉጡን በስር አሾልኮ ትከሻው  አካባቢ ደቀነበት…ሌለኛው ዘና ብሎ ዞረና ገቢና ገባ፡፡
‹‹በል አሁን ወደ አስኮ ንደው፡፡››
‹‹አስኮ…ለምን?››
‹‹ለሽርሽር…ባክህ አትቀልድ…ወይ ንዳው ካለበለዚያ እዚሁ ደፍተንህ እንሄዳን…ሁለቱም ይመቸናል፡፡››አለው፡፡

መኪናዋን አንቀሳቀሰና ወደአሉት አቅጣጫ አስተካክሎ መንዳት ጀመረ….መንግስቱ ሲጠጣ ከቆየው መጠጥ ጋር ተቀላቅሎ ያጋጠመው ነገር ብዥ እንዲልበት አደረገ…በጣም ነው ግራ የተጋባው..በዚህ ቀን ማን ነው ሊያሳግተው የሚችለው?‹‹አጋቹ ሲታገት›› የሚል ፊልም እየሰራሁ ይሆን እንዴ? ሲል በውስጡ አሰበና ፈገግ አለ፡፡
አጎቱ ትዝ አለው‹‹አጎቴ ነው የላካችሁ?››
‹‹እንዴ አቶ ግርማ አጎትህ ነው እንዴ?›› አንደኛው ጠየቀው፡፡
ክው አለ….‹‹ግርማ ነው ያሳገተኝ?››ጠየቀ…ያሳገተው ሰው በየት በየት ዞሮ ሊያሳግተው እንደቻለ ሊገባው አልቻለም፡፡
‹‹ነፍሱ ዝም ብለሽ ነጂው….ሁሉን ነገር ስትደርሺ ታይው የለ….?ያው እኛ ስራችንን እየሰራን ነው..ነገሩን ፐርሰናል አትድርጊው፡፡››
ሊደራደራቸው ፈለገ‹‹…አይ ችግር የለውም …ስራችሁን እየሰራችሁ እነደሆነም ይገባኛል..ግን ቀጣሪያችሁ ከሚከፍላችሁ እጥፍ ልከፍላችሁ ችላለው…››
‹‹ጥሩ ነበር…. ግን የሞያ ስነምግባራችን አይፈቅድልንም…በዛ ላይ ስራ ያበላሽብናል፡፡››
‹////
ትዕግስት እና እዝራ እዛው በተቀመጡበት ሆነው ሲጠጡ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት  ሆነ…..በተለይ ትዕግስት  በመጠጡ እየተዳከመች ነው …እዝራ ያው ቀኑን ሙሉ የመጠጣት የብዙ አመት ልምድ ስላለው ገና ብዙ የሚቀረው ይመስላል፡፡
‹‹ጋሽ እ…ዝራ››ጠራችው ትዕግስት፡፡
‹‹ወዬ ትእግስት፡፡››
‹‹ወደቤ…ት ወሰደኝ››
‹‹ምነው ደከመሽ እንዴ?››
‹‹አዎ ..በጣም …ነው የደከመኝ…. እዚሁ ጠረጴዛ ላይ ልወድቅ ነው››
‹‹እኔ ደግሞ ገና አልጠገብኩም….››
‹‹ስለዚህ ምን ይሻላል….?እዚህ ተ…ዘርሬ ብወድቅ አላሳዝንህም?››
‹‹በጣም ታሳዝኚኛሽ…ግን እንዲህ ማድረግ እንችላለን…እዚህ ክፍል እንያዝና መጠጣችንን ይዘን እንግባ..አንቺ ትተኛለሽ እኔ ደግሞ  አንቺን እየጠበቅኩ መጠጣቴን ቀጥላለሁ፡፡››
‹‹አይ ጭንቅላት…ሁሌ እኮ እንዳስደመምከኝ ነው››እጇን አውለበለበችና አስተናጋጁን ጠራችው..ሂሳብ ነው የጠየቀችው….የታሰረ እሽግ ብር ከቦርሳዋ አወጣችና ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠቸ…ሂሳብ ከፍለው ከጨረሱ በኃላ ጋሽ እዝራ በአንድ እጁ  እሩብ የቀረለትን የውስኪ ጠርሙስ ይዞ በሌላው እጁ እሷን ደግፎ  ወደ ሪሴፕሽን ሩም ሄዱና አንድ ክፍል ተከራይተው ተያይዘው ገቡ፡ጫማዋን አውልቃ በቁሞ ነው አልጋ ላይ የተዘረረችው፡፡እዝራ በራፉን ዘጋና የመጠጥ ጠርሙሱን ይዞ ክፍል ውስጥ ያለው ደረቅ ወንበር ላይ ተቀመጠ….ከዛ ከኪሱ ውስጥ ሮዝማን ሲጋራውን እና ላይተሩን አወጣና ለኮሰ…መጠጡን እየተጎነጨና ሲጋራውን እያቦነነ በተመስጦ ይመለካታት ጀመር.. ከሴት ጋር አንድ  ክፍል ውስጥ እንዲህ ተፋጦ ሲቀመጥ ስንት አመት አለፈው?፡፡ትዝ አይለውም፡፡
ተኝታለች ብሎ ሲጠብቅ‹‹ጋሽ እ…ዝ…ር››ብላ ጠራችው፡፡
‹‹አቤት››
‹‹ቤቱ እየተገለባበጠብኝ ነው፡፡ሻወር መውስድ ፈልጋለሁ…››
‹‹ብተኚ አይሻልሽም..ስትነሺ ያልፍልሻል››
‹‹አይ መተ…ኛት አይደ…ለም የምፈልገው…እባክህ ደግፈህ ወደ ሻ…ወር ውሰደ…ኝ ፡፡››
ጥያቄዋን ፍላጎቷ ግራ ቢያጋባውም እምቢ ሊላት አልፈለገም..እያጨሰ ያለውን ቁራች ሲጋራ አጠፋና   በእጁ ይዞ የነበረውን ጠርሙስ  አጠገቡ ባለ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠና እራሱን አበረታቷ ተነሳ፡፡ ወደአልጋው ተጠጋ፡፡ክንዷን ያዘና ወደላይ ጎተታት…ተነሳች፡፡ ትከሻው ላይ ተደግፋ እግሯን የመጎተት ያህል እያንቀሳቀሰች ወደሻወር ቤት ተያይዘው ሄዱ…ከፈተና ወደውስጥ ይዟት ገባ፡፡
‹‹ጋሽ እዝራ››
‹‹አቤት››
‹‹ስብ..ር..ብር አልኩ እኮ….››
‹‹እንደአልሽው አሁን ውሀ ሲነካሽ ትጠነክሪያለሽ፡፡››
‹‹እሺ ውሀውን ክፈትልኝ…ቆይ መጀመሪያ ልብሴን ላውልቅ..››
‹‹በቃ እኔ ልውጣልሻ››
‹‹አይ ማውለቁን አግ..ዘኝ እንጂ….አልች…ልም አ…ኮ››
‹‹እርግጠኛ ነሽ››
‹‹ችግር የለውም….አውልቅልኝ…›››
‹‹እሺ ካልሽ….››አለና ያግዛት ጀመረ…ሰውነቷ ላይ ሰማያዊ ፓንት ብቻ ቀረ…
‹‹አሁን በቃ ››ብሎ ሊወጣ ሲል ወደራሷ ጎተተችና ተጠመጠመችበት…እዝራ ግራ ገብቷት ምን ማድረግ እንዳለበት በማሰብ ላይ ሳለ ትእግስት እጆቾን ዘርግታ ውሀው እስከመጨረሻ ከፈተችው….ሁለቱም በውሀው ረሰረሱ…በተለይ እዝራ ከእነልብሱ ነው የረጠበው…ይሄም ጉዳይ ትእግስትን በጣም አዝናናት
‹‹ምንድነው የሰራሽው…?››
‹‹እኔ እንጃ …እንደህ አድርጊ አድርጊ አለኝ…..በቃ አውልቀው..››
ምርጫ ስላልነበረው አወላለቀውና እርቃን ቀረ….እራቅ አለችና አፍጥጣ አየችው‹‹…ጋሽ እዝራ በጣም እንደምወድህ ግን ታውቃለህ››ስትል ያልጠበቀውን ነገር ጠየቀችው፡፡
‹‹አላውቅም….እንዴት ግን እኔን ልትወጂኝ ቻልሽ….?ምርጫሽ ጥሩ አይደለም፡፡››
‹‹ፍቅር የምርጫ ጉዳይ እኮ አይደለም…››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው..ፍቅር የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን መለከፍ ነው…ድንገት በመብረቅ መመታት››
ትዕግስት ውሀው ሰውነቷን ሲያረሰርሳት ይሆን  የእዝራን እርቃን ገላ ማየትና ሰውነቱን ሳሙና እየመታች ስታሸው  በውስጧ ተዝለፍልፎ የነበረውን ጥንካሬዋን ሲያገግምና ሲበረታ ታወቃት….
‹‹ትእግስት….››ጠራት እዝራ፡፡
‹‹ወዬ››
‹‹ለአሮራ ስሟን ያወጣሁላት እኔ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ…?››
‹‹አላውቅም….አንተ ነህ ያወጣህላት? ››
‹‹አዎ እኔ ነኝ ያወጣሁላት… አሮራ ማለት ለመጀመሪያ ጊዜ ብልጭ ስትል የምታያት ልብ ሰንጣቂ  የፀሀይ ብርሀን ማለት ነው…በሌላ ጎኑም ማታ ለመጨረሻ ጊዜ ውስጥሽ በፍራቻ እየተሸበረ እያየች ግን ደግሞ ተሠናብታሽ የምትጠልቀው የመጨረሻዋ የፀሀይ ፍንጣቂ  ማለት ጭምር ነው።ስሙ ኢጣሊያን እያለሁ እስክሞት ድረስ አፍቅሬያት የነበረችው ስፔናዊት ፍቅረኛዬ ስም ነው….እሷ ስትሞትብኝ ነው ሁሉን ነገር ጥዬ ወደሀገር የተመለስኩት ..በዛን ወቅት አሮራ የሁለት አመት ልጅ ነበረች…ሌላ ስም
👍778🤔1
ነበራት እኔ ግን አሮራ አልኳት ከዛ እሱ ጸደቀላት..››
‹‹ያሳዝናል…››
‹‹አዎ ሀያ አንድ አመት ሙሉ አዝኛለሁ…አሁን ልግርሽ የፈለኩት…ይሄ ነገር ይቅርብን ለማለት ነው..››አለና ከውሀውም ከእሷም ራቅ አለ…፡፡
‹‹ለምን ?ደስ አልልህም?››
‹‹አይ….እንደዛ አይደለም..እኔ አንዴ ካፈቀርኩሽ  ላጣሽ አልፈልግም…ፍቅሬ የሞኝ ነው…ብትተይኝ ወይም ጥለሺኝ ብትሂጂ መቋቋም አልችልም.›› አለና ከመስቀያ ላይ ያለውን አንደኛውን ፎጣ ይዞ ሰውነቱን እያደራረቀ ወጣ…..ከዛ ወዲያው ሲጋራውን ከፀረጴዛው ላይ አነሳና ለኩሶ ከሀሳቡ ጋር አንድ ላይ ቀላቅሎ ሟብነን ጀመረ….እሷም ጊዚ አልፈጀችም …፡፡ ለብሳ የነበረው ፓንት አውልቃ ጣለችና  ሌላውን  ፎጣ በማንሳት ሰውነቷን እያደራረቀች   ከሻወር ወጥታ ወደእሱ ሄደች…


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍757
#አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-40
#ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
ከምሽቱ 11 ሰዓት አካባቢ ነው። ትዕግስት ስልኳ ሲጠራ እዝራ ደረት ላይ ተኝታ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷት ነበር። ተንጠራራና ስልኩን አንስቶ ሰጣት።አየችው ።የምታውቀው ቁጥር አይደለም።ግራ በመጋባት ውስጥ ሆና አነሳችው።
"ሄሎ"ነጎድጓዳማ  እና የሚገፋተር ድምፅ  ነው።
"ትዕግስት ነሽ?"
"አዎ ነኝ...ማን ልበል? አላወቅኩህም።"
"አታውቂኝም ክንዴ እባላለሁ...መንግስቱ  ነበር ከቀናት በፊት  ስልክሽን የሠጠኝ....የእኔ ስልክ ካልሰራልህ በእሷ በኩል ታገኘኛለህ ብሎኝ ነበር"
"እሺ ምን ልታዘዝ?"
"ሰባት ሰዓት አካባቢ ደውዬለት ወደአንተ እየመጣሁ ነው ብሎኝ ነበር ።ከዛ ስልኩ ይጠራል አይነሳም አሁን ደግሞ ጭራሽ አይሰራም.....ምን ነካህ እቃውን ይዘን እየጠበቅንህ ነው በይልኝ።"
"ምን? የምን ዕቃ?"
ስልኩ ተቋርጧል።
መኝታዋን ለቃ ወረደችና እርቃኗን ወለል ላይ ቆመች።
"ምንድነው ችግር አለ?"እዝራ ነው ግራ በመጋባቷ ግራ ተጋብቶ የጠየቃት።
"እኔ እንጃ ...በደንብ አልገባኝም"መንግስቱ ጋር ደወለች። አይጠራም።ገስትሀውስ ደወሐለች..በአይን ካዩት   ሶስት ቀን እንደሆናቸው ነገሯት።
"ወይኔ ጉዴ?!!!ልጅ ምን ሆነ? ክንዴ ነኝ ብሎ የደወለላትን ልጅ ጋር ደወለችለት።
"ወንድሜ ይመስለኛል በጠቀስከው ሰዓት እኛ ጋር ነበረ ..ስትደውልለት ወደአንተ ነበር የመጣው"
"ታዲያ ወደእኔ እየመጣ ከሆነ የሰላሳ ደቂቃ አምስት ሰአት ሙሉ ምን ይሰራል?"
"እኔም አልገባኝም"
"እና ምን ላድርግ? እቃውን ልልቀቀው?"
"ምንድነበረ ስምምነታችሁ?"
"መጥቶ ሊያናግረውና ሰውዬውን ተረክቦ ብራችንን ሊከፍለን ነበራ።"
"አሁን የዕቃው ምንነት ገባት።"
"በቃ ሁኔታውን አጣርቼ መልሼ ደውልልሀለው"
"ቶሎ በይ ካልሆነ ዕቃውን ወደቦታው እንመልሰዋለን።"
"አይ...እሱ ካልመጣ, እኔ መጣለሁ..ስንት ብር ነበር የተስማማችሁት።"
"መቶ ሺ ብር ተስማምተናል።ሰላሳ ከፍሎናል።"
"በቃ እስከጥዋት አቆዩት ፤እስከዛ መንጌ እንኳን ባይገኝ እኔ ጥዋት ቦታው ድረስ ብሩን ይዤ እመጣና እቃውን  ትሰጡኛላችሁ"
"እንደዛ ከሆነ አሪፍ ነው...በቃ ቸው የደረሺበትን ደውለሽ አሳውቂኝ"
"እሺ...ዕቃውን ፎቶ አንስተህ በዚህ ቁጥር ትልክልኛለህ?"
"ይቻላል"ስልኩ ሲዘጋ እዝራ ልብሷን ከመታጠቢያ ቤት አምጥቶ  እንድትለብስ እያቀበላት ነበር።
"ያንተስ አልደረቀ?"
"ለበስኩት እኮ...ከጃኬቱ በስተቀር ሌላው ምንም አይልም"
"በቃ ስንወጣ ጃኬት እንገዛለን ...እኔም ፓንቴ ስላልደረቀ ባዶ ቂጤን መሆኔ ነው።"
"አስወልቆ ሚያይሽ የለ ምን ችግር አለው።ለመሆኑ ምን እየተከሰተ  ነው?"
"እኔ እንጃ ።እየሆነ ያለው እኔንም ግራ እያጋባኝ ነው።መንግስቱ እምጥ ይግባ ስምጥ የሚያውቅ ሰው የለም...ወንድምህ ግርማ ደግሞ..."ንግግሯን ሳትጨርስ  ስልኳ ድምፅ አሰማ... ከፈተችው።እና ቀጥታ ለእዝራ አቀበለችው።የወንድሙ የግርማ ፎቶ ነው።እጅና እግሩ ከወንበር ጋር ታስሮ ሲቁለጨለጭ ይታያል።"
"ማነው ያሳገተው?"ጥርጣሬውን ለማረጋገጥ ጠየቃት።
"ማን ይሆናል ?መንግስቱ ነዋ ።የሚገርመው አሳግቶት የት እንደጠፋ ነው?"ለማንኛውም ተነስ እንውጣና እየሄድን ምን ማድረግ እንዳለብን እንነጋገር።"
"እሺ"አለና በሀሳቧ ተስማምቶ ተከተላት።
መንግስቱ ይገኝበታል ብለው የሚጠረጥሩት ቦታ ሁሉ እስከምሽቱ አራት ሰዓት እየተዞዞሩ ፈለጉ...ያቃቸዋል ብለው የሚገምቱት   ሰዎች ጋር ሁሉ እየደወሉ ጠየቁ።አንዳቸውም መንግስቱን እንዳላዩት አረጋገጡላቸው።እሷ ጋም መንግስቱን ፍለጋ የደወሉ ሰዎች ነበሩ።ከካናዳ የተመለሠው አጎቱና ሚስቱ ውቢት በየተራ ደውለውላት መንግስቱ የት እንዳለ የምታውቅ ከሆነ ጠይቀዋት ነበር።እንደማታውቅና ካገኘችው እየፈለጉት እንደሆነ  መልዕክቱን እንደምትነግረው ነግራቸው ነበር...።
"አሁን ከዚህ በላይ ምንም ማድረግ የምንችል አይመስለኝም...ባይሆን ይንጋና ጥዋት ማድረግ የምንችለውን ነገር እናያለን?"
"ትክክል ነሽ"በቃ ወደቤት እንሂዳ አላት እዝራ።ትእግስት ስለእዛ ቤት ስታስብ የሚታያት በደም የተጨማለቀ አንሶላ...ሽጉጥና የአሮራ በጥይት የተበሳሳ ሰውነት ነው።
"አይ እዛ ቤትማ አልሄድም... "

"በቃ  ቤርጎ እንያዛ..."
"እሺ ..ጥሩ ሀሳብ ነው"
"ቆይ እዚህ ሰፈር ያለውን የግርማን ቤት ታውቀዋለህ"
"አዎ አንዴ አይቼው ነበር...ምነው"
"ዘበኛው ካስገባን እዛ እንደር"
"ዘበኛው እኮ እታች ቤት የሚሰራ ነበር...በደንብ ነው የማውቀው"
እና እንሂድ "
"አዎ እንሂድ"ለላደው ቦታውን ነገሩት።ወደእዛው መንዳት ጀመረ።
እዝራ ሲከነክነው የነበረውን  ጥያቄ ጠየቃት"እቤቱን እንዴት አወቅሽው?"
"እንዴ የአሮራን የመጨረሻ ክሊኘ የተቀረፀው እኮ እዚህ ቤት ነው ...ሶስት ቀን አድረናል"
"እ...እንደዛ ነው?"አለ ፈገግ ብሎ።
"አዎ...አይዞህ ከወንድምህ ጋር ምንም የተፈፀመ ነገር የለም....ማለቴ ሙከራው ነበረ ..ግን ሙከራ ብቻ ነው።"
"ይሁን"
ደረሱና ለላዳው ተገቢውን ክፍያው ከፍለው አሰናበቱት እና 
ወደ ጊቢው ተጠጉ።ጭልምልም ብሏል። ከዚህ  በፊት በውጭ መብራት ድምቅምቅ ያለ ነበር።የውጩን መጥሪያ ደጋግመው ተጫኑ።ከደቂቃዎች በኃላ"ማን ነው?"የሚል ድምፅ ከውስጥ ተሰማ።
"ጋረደው እኔ እዝራ ነኝ  ክፈት...ግርማ ልኮኝ ነው?"
የውጩ የብረት በር ወለል ብሎ ተከፈተ...ከፍቹ በበራፉ እራሱን ከልሏል..ትዕግስትና እዝራ ተከታትለው ገብ።በራፍ በፍጥነት ተዘጋ ።ፊት ለፊታቸው ጠብደል ወጠምሻ የሆነ ሰው ሽጉጥ ደቅኖባችዋል።የጠበቁት ጋረደው በቦታው የለም።ደነገጡ።
"ምንድነው...እኔ እዝራ ነኝ የግርማ ወንድ?"
"ሠማሁህ እኮ...አሁን ቀጥሉ ..ወደቤት ግብ"ቆፍጠን ያለ ትዕዛዝ።
እጅ ለእጅ ተያይዘው  እንዳላቸው ወደቤት ተንቀሳቀሱ። ግቢ ውስጥ አራት የሚሆኑ ክላሽ ጭምር የታጠቁ ሰዎች ፈንጠርጠር ብለው በጥንቃቄ ቆመዋል።ሳሎን ሲገብ ወደ ውስጥ (ወደ መኝታ ቤቶች) የሚወስደው  ኮሪደር ላይ ሌሎች ሁለት መሳሪያ  የታጠቁ ሰዎች ይታያሉ።ይዟቸው የመጣው ሰው የደቀነባቸውን  ሽጉጥ  ወደጎኑ መልሶ ሻጠና ወደ ሳፋው በአገጩ እየጠቆመ ተቀመጡና  ለምን እንደመጣችሁ አስረድኝ?"አላቸው።
እንዳላቸው ተቀመጡና በፍራቻ መቁለጭለጭ ጀመሩ።
ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍11312🔥8
አራዳ ተንዶ ፡ መሰረቱ ታየ፣
ገና ብዙ ያያል ፡ ሸገር ላይ የቆየ።
😢51🤔8👍2😁1
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ምዕራፍ-41
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ከበራፍ ተቀብሎ ወደውስጥ በማስገባት ሶፋ ላይ እንዲቀመጡ ያዘዛቸው የአጋቾቹ መሪ የሚመስለው  ሰው ፊት ለፊታቸው ተቀምጦ በዝምታ እየተመከታቸው ነው፡፡አስተያቱ ደግሞ በሁለቱም ውሰጥ ሽብር ነዛባቸው፡፡ ከተቀመጠበት ድንገት ተነሳና…‹‹እስክመለስ ድረስ ለምን እዚህ እንደመጣችሁ እሰባችሁበት ጠብቁኝ››አለና ተነስቶ ወደውስጥ ገባ፡፡
‹‹ምን ማለት ፈልጎ ነው…?ይሄ ሁሉ ሰራዊት እዚህ ቤት ውስጥ ምን ይሰራል…..?ችግር ውስት ገባን ማለት ነው?››ትእግስት ነች ጥያቄዎቾን ደራርባ እዝራን የጠየቀችው፡፡
‹‹አላውቅም…ቆይ እስኪ በፀጥታ ላስብበት…የሆኑ የሆኑ ነገሮች እየተገጣጠሙልኝ  ነው››አለትና አይኖቹን እንደመጨፈን ብሎ በጥልቀት ማሰብ ጀመረ፡፡
እዝራ አእምሮውን ጥልቅ ደረስ ዘልቆ  በረበረ…ስለወንድሙ አካሄድና አንዳንድ ፈላጎቶች አሰበ ..እና እሱን ለመቋቋምና ለሌሎች ሰዎች  ሳይጎዱ እሱ ባጠፋው ጥፋት ልክ ቅጣቱን ማግኘት እንዲቸል ለማድረግ እንዲያስችለው ነገሮችን  በንቃት ማድረግ እንዳለበት ወሰነ ፡፡በንቃት  ላይ ያለ ሠው  ደግሞ አሁን ላይ መገኘት፤እያንዳንዶን ደቂቃና ሰዓት በጥልቀት መኖር፤ነገሮችን ባሉበት ተፈጥሯዊ ይዘት የመቀበል ችሎታ  እና የሌላውን ህመም በጥልቀት መረዳት ብቃት ሊኖረው የግድ ይላል፡፡እና እዝራ ሀሳብን እልባት ሳያበጅለት  አጋቹ መጣና ጥሎት በሄደበት ቦታ ከእነሱ  ፊት ለፊ ቁጭ አለ፡፡
‹‹እሺ..እዚህ ምን እግር ጣላችሁ?አሁን ልሰማችሁ ዝግጁ ነኝ››አላቸው፡፡
እዝራ ከዚህ ትርምስም  እሱንም ሆነ ሌሎችን የሚወዳቸውን ሰዎች በጥበብ ይዞ መውጣት እንደዳለበት ወስኗል ፡፡አዎ አሁን በንዴት ሳይሆን በስሌታ ማሰብ እንዳለበት እራሱን አሳመነ  …..መጀመሪያ የጠረጠራቸው ነገሮች በትክክል የተፈጸሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዳበት ተሰማው… አእምሮውን ለመጠቀም ወሰነ‹‹ከወንድሜ ጋር ወደ እዚህ ቦታ አብረን ለመምጣት ተቃጥረን ነበር፡፡ከዛ ግን ጠፋብኝ…ማለቴ ስልኩ ሁሉ አይሰራም…ሌሎች ቦታዎች  ከፈለኩት በኃላ ምን አልባት በስራ ውጥረት ተዘናግቶ እኔን እረስቶኝ ወደእዚህ መጥቶ ይሆናል ብዬ በመጠራጠሬ ነው የመጣሁት››ሲል ቦታው ላይ የተገኙበትን ምክንያት አብራራለት፡፡
‹‹በዚህ ምሽት  አራት ሰዓት ካለፈ በኃላ?፡፡››ሰውዬው የተናገረውን አንዳላመነው በሚያሳብቅ የድምፃ ቅላፄ ጠየቀው፡፡
‹‹አይገርምም…በጊዜ ከእሷ ጋር ተገናኘተን ትንሽ እየቀማመስን እየተዝናናን ነበር….ከዛ ወደቤት ለመሄድ ላዳ ውስጥ እንደገባን ወንድሜ ጥዋት ወደእዚህ ቦታ እንሄዳለን ብሎኝ እንደነበረ ትዝ አለኝና ላዳው ወደእዚህ እንዲያመጣን ነገርኩት..ይሄው ነው….አሁን ወንድሜ የት ነው?ላናግረው እንደምፈለግ ንገረው፡፡››ማስመሰሉን  ቀጠለበት፡፡
‹‹ወንድምህ እዚህ እንዳለ በምን አወቅክ?››
‹‹ ነገርኩህ እኮ!1ሌላ ቦታ እንደሌላ  አረጋግጬለሁ…እዚህ ካልሆነ ሌላ የት ይሆናል?ብዬ ነዋ››
‹‹እንግዲያው እርምህን አውጣ …ወንድምህ  እዚህ የለም….እኛም ቀኑን ሙሉ ስንጠብቀው ነው የዋልነው››መለሰለት
‹‹ልጁስ ?››እዝራ እንደዋዛ ቀጣዩን ጥያቄ ሰነዘረ፡፡
‹‹የቱ ልጅ?››ኮስተር ብሎ
‹‹መንግስቱ ነዋ…የያዛችሁት ልጅ››
‹‹አለ …ከጀርባ ባለው ክፍል  ነው››
እዝራ በእርካታ ተነፈሰ….ትእግስት በእዝራ ብልጠት ተደመመች‹‹እና ኮሪደሩ ላይ ያሉት ጓደኞችህ ምንድነው የሚጠብቁት?››ስትል ለአጋቹ ሌላ ጥያቄ አቀረበችለት፡፡
‹‹ልጁቷን ነዋ…ስለሷ አልነገራችሁም እንዴ..?እርግጥ እሷን እኛ አይደለንም ያገትናት  ..ቀደም ብላ እዚህ ነበረች›››
‹‹አሮራ ነች?››እዝራ ትንፋሽ በሚያሳጣ ድንጋጤ  ውስጥ ሆኖ ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ ..ዘፋኟ….የገዛ ልጁን ለምን እንዳገታ አልገባኝም….?ምን አልባት ወንድ ላይ እየጠንጠለጠለች አስቸግራው ሊሆን ይችላል…..››የራሱን ግምት በማስቀምጥ ማንነቷን አረጋገጠላቸው፡፡
ሁለቱም ልክ እንደነተነጋገረ ሰው ከመቀመጫቸው በርግገው በመነሳት ወደኮሪደሩ ተንደረደሩ…ጠባቂዎቹ መንገዳቸው ላይ እጃቸውን ሰትረው በመደርደር ግድግዳ ሆነው አገዷቸው…ሲያወራቸው የነበረው ሰው ከኃላቸው መጣና‹‹ሰዎች እሷን ለማነጋር የግድ የግርማ ፍቃድ ያስፈልጋል››አላቸው፡፡
‹‹ግርማ እኮ አሁን እዚህ የለም …መፍቀድ የምትችለው አንተ ነህ››
‹‹አይ አቶ ግርማ እዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን አቋም በግልፅ ነው የነገረኝ …ልጅቷ ያለእሱ ፍቃድ ማንም ሊያናግራት አይችልም…ከቻላችሁ በስልክ አግኙትና ….ያናግሯት  ብሎ ይንገረኝ፡፡››
ትእግስት ስሜቷን መቆጣጠር አቅታት‹‹እንደውም እስከአሁን የነገርንህን ሁሉ እርሳው…ከግርማ ጋር የተነጋርከውን ብር ለማግኘትና ችግር ሳይፈጣር ከዚህ ጣጣ ውስጥ ለመውጣት ከፈለክ ከእኛ ጋር መስማማት የግድ ይልሀል››አለችው ፍጥጥ ብላ፡፡
ሰውዬው ኩስትርትር አለ‹‹አልገባኝም ..ከእናንተ ጋር ምን ይሁንልኝ ብዬ ነው የምስማማው…የቀጠረን ግርማ ነው…ብራችንንም የሚከፍለን እሱ ነው፡፡እስከአሁን እንደውም ለምን እንዳልመጣና እንደዚህ አይነት እርስኪ ያለው ስራ ካሰራን በኃላ እንዴት እንደዚህ  እንዝላል እንደሆነ ገርሟኛል በዛ ላይ እናንተ እኮ በእኔ ቁጥጥር ስር ነው ያላችሁት...አልገባችሁም እንዴ? አሁን እኮ በቃ ታጋቼ ሆናችኋል፡፡››
‹‹እንደዛ እንኳን አይመስለንም …ይሄንን ምንነግርህ ግርማ መምጣት ስለማይችል ነው››አለው እዝራ፡፡
‹‹መምጣት እንደማይችል!! በምን አወቅክ…?አሁን ከጥዋት ጀምሮ ፈልጌ አጣሁት ስትል አልነበረ እንዴ?››
‹‹ዋሽቼህ ነው፡፡››
ሰውዬው ትዕግስቱ ተሞጠጠበትና ሽጉጡን ከሻጠበት መልሶ አውጥቶ ደቀመነባቸው‹‹መቀባጠሩን አቁማችሁ ትክክለኛ እየሆነ ያለውን ነገር ንገሩኝ…ካለበለዛ ግንባራችሁን አፈራርሰዋለሁ፡፡››
ትእግስት‹‹ቆይ›› አለችና ስልኳን በማውጣት ደወለች‹‹ሄሎ ክንዴ››
‹‹ሄሎ ትእግስት መንጌ ተገኘ እንዴ?››
‹‹አይ እስከአሁን እያፈላለኩት ነው…ግን አሁን የደወልኩት እስከጥዋት ተመልሶ ማይማጣ  ከሆነ ጥዋት ሁለት ሰዓት ድረስ ብሩን ይዤ ለመምጣት እንደተዘጋጀው ልነግርህ ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ያስማማናል››
‹‹ከዛ ግርማን ታስረክበኛለህ ››
‹‹ምን ጥያቄ አለው..ዝግጁ ስትሆኚ ደውይልኝ …የእኛ ልጆች ያገኙሽና በጥንቃቄ ..ማለቴ ፖሊስና ሌላም ሰው እንደማይከተልሽ እርግጠኛ ከሆኑ በኃላ ወዳለንበት ያመጡሻል፡፡››
‹‹እሺ አመሰግናለሁ… ቸው››ስልኩ ተዘጋ፡፡
ሽጉጥ የደቀነባቸው የመንግስቱ አጋች‹‹እና አጋቹን ያሳገታችሁት እናንተ ናችሁ ማለት ነው?››ሲል በገረሜታ ጠየቀ፡፡
‹‹አይ ያሳገተው መንግስቱ ነበር..እኛ አይደለንም››ትእግስት መለሰች
ከት ብሎ ሳቀ…‹‹የሚገርም የፊልም እስክሪፕት ይወጣዋል..ታጋቹን አላመንኩትም እንጂ ሊነግረኝ ሞክሮ ነበር..ይገርማል….!!ቆይ አንተም በወንድምህ መታገት እጅህ አለበት?››ወደ እዝራ ዞሮ ጠየቀው፡፡
‹‹የለሁበትም…መታገቱ ግን ይገባዋል ባይ ነኝ..አሁን አስገባንና አሮራን እንያት… ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ዋናው ምክንያት የእሷ ከእይታችን መሰወር ነው…እሷ ጤና መሆኗን እንይና ከዛ ቁጭ ብለን ሁላችሁም ብራችሁን አግኝታችሁ ማንም ሰው ሳይጎዳ ከዚህ ትርምስምስ  የምንወጣበትን እና ወደየህይወታችን  የምንመለስበትን  ሁለታ  ላይ ቁጭ ብለን እንነጋገራለን፡፡››
👍644🥰1😁1🤔1
አጋቹ የእዝራን ንግግር ከሰማ በኃላ ወደትእግስት ዞሮ‹‹አንቺ መንግስቱ ምንሽ ነወ?››ሲል ተየቃት
‹‹ጓደኛዬ››
‹‹ ግርማስ? የት ነው ምታውቂው..?››
‹‹የእሱ ሰራተኛ ነኝ..ማለቴ የአሮራ ረዳት ሆኜ ነው የምሰራው፡፡››
አጋቹ በድጋሜ መገረም ሳቅ   ሳቀ…..‹‹እርስ በርሳችሁ ነዋ እየተጠፋፋችሁ ያላችሁት››

እዝራ‹‹እንደዛ መሰለኝ..ስለዚህ ምንልህን  ስማትና አሁን ወደ አሮራ አስገባንና እንያት ….ከዛ ቁጭ ብለን እናንተም ገንዘባችሁን ሳታጡ..ሌላ ወንጀል ውስጥም ሳይገባ ሁኔታዎችን እናስተካክላለን…በዛ ቃል እንገባልሀለን፡፡››አለው፡፡
እንደማሰብ አለና ‹‹ስልካቸውን ተቀባሏቸውና አስገቧችው››ሲል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ስልካቸው ተቀብለውና ፈትሸው ከመንገዳቸው ዞር አሉላቸው…እዝራና  ትእግስት የመኝታ ቤቱን በራፍ ከፍተው ተከታትለው ወደውስጥ ሲገቡ አሮራ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ነበረ ያለችው…ትእግስት ዘላ አልጋ ላይ ወጣችና ወዘወዘቻት፡፡አሮራ ከእንቅልፏ ባና አይኖቾን ስትገልጥ ትእግስትንና አጎቷን በማየቷ ግራ ተጋባች…‹‹የነቃው መስሎኝ ነበር ህልም ውስጥ ነኝ እንዴ?››ጠየቀች፡፡
‹‹አይደለሽም የእኔ ቆንጆ..የእውነት ነው….አገኘንሽ…በህይወት አለሽ…››ትእግስት መለፍለፏን ሳታቆም እያገላበጠች ትስማት ጀመረ…እዝራም የደስታ እንባ ከአይኖቹ እያረገፈ ግንባሯን ሳመና አልጋውን ተጠግቶ ባለ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡
‹‹እንዴት አገኛችሁኝ …?ጠባቂዎቹ እንዴት ፈቀዱላችሁ…?የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ እንዴ..?ያ የረተረገመ እኮ ዛሬ ወደውጭ ሊልከኝ ነበር..ትኬት ሁሉ ተገዝቶ ነበር…ግን ምን እንደሆነ አላውቅም ቀረ  …እስከመጨረሻው ላጣችሁ ነው ብዬ በጣም ፈርቼ ነበር….›››በማለት ከማያቋርጥ የለቅሶ አጀብ ጋር የሆነውና እና ስላሳለፋቻቸው  የመከራ ቀናት ነገረቻቸው።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍10016👎3👏3🥰2🔥1
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ምዕራፍ-42
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ትእግስት እና  እዝራ ከሁለቱ ወገን አጋቾች ጋር በመነጋገር እና በመደራደር ግርማንና መንግስቱን ፊት ለፊት ለማገናኘት አቅደው ተሳክቶላቸዋል፡፡ከሁለቱም አጋቾች የተውጣጡ ስድስት የታጠቁ  ሰዎች ዙሪያቸውን እየጠበቋቸው አንድ ክፍል ውስጥ እንደበፊቱ እጆቻቸውና እግሮቻቸው ተስረው ሳይሆን ነፃ ሆነው እየተንቀሳቀሱ  ፊት ለፊት ቁጭ ብለው ተፋጠዋል፡፡ከአስር  ለበለጡ ደቂቃዎች ቃል ማውጣት የቻለ አልነበረም፡፡
‹‹በጣም ነው የምታስጠላኝ››አለው መንግስቱ ፡፡
‹‹ያደረኩህን ሁሉ ያደረኩት እኮ በራስህው ስህተት ነው…ሁሌ በመንገዴ ላይ ትሰነቀራለህ…በፊት ያሳሰርኩህም አሁን ያሳፈንኩህም ለዛ ነው፡፡››
‹‹አይ የምጠላህ እኔ ላይ ባደረከው ነገር አይደለም…ለዛ ይቅር ልልህ እችላለሁ…፡፡በአንተ አሻጥር መታሰሬ ብዙ ነገር ቢያሳጣኝም መቼም ለገኛቸው የማልችላቸውን ገራሚ የህይወት ልምዶችንም ያገኘሁበት ቦታ ስለሆነ እራሴን እንደተጎጂ እየተመለከትኩ አንተን ስወቅስ መኖር አልችልም፣..እኔ አምርሬ የምጠላህ አሮራ ላይ ባደረከውና እያደረክ ባለኸው ድርጊት ነው፡፡
ምን አደረኳት…?እንዴት ተንከባክቤ እንዳሳደኳት አታውቅም…?የዝና ጣሪያ ላይ እንድትወጣ መደረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ አድርጌለሁ…ምን በደልኳት?፡፡››
‹‹የሚገርመው ስትበድላት መኖርህ አይደለም….አሁንም በውስጥህ ምንም አይነት ፀፀት አለመኖሩ ነው….እንዴት ከገዛ ልጅህ ጋር ትተኛለህ?››
ግርማ በጣም ደነገጠ…ይሄንን ነገር ማንም ያውቃል ብሎ አስቦ አያውቅም ነበር….‹‹ይሄንን እንዴት ነገረችህ?››
‹‹አይ እሷ አልነገረችኝም…እንደማውቅም አታውቅም…ግን ይሄ ሁሉ ውጥንቅጥ ከመፈጠሩ በፊት አንተን በተወሰነ መጠን ሳሰልል ነበር…እና ከእንጀራ ልጅህ ጋር የጎረምሳ አይነት ወሲብ ስትፈፅም የሚያሳይ የተቀረፀ ቪዲዬ አለኝ…ለአሮራ ባላስብ ያንን ቪዲዬ በኢንተርኔት ነበር የምለቀው….ከዛ በዚህ ወግ አጥባቂ ማህበረሰብ ውስጥ እንዴት አንገትህን ቀና አድርገህ መኖር እንደምትችል አይ ነበር?፡፡ግን እሷን አምርሬ ስለማፈቅራት ..እንደዛ ማድረግ አልቻልኩም››
ግርማ እንደበፊቱ ቆጣ ቆጣ የሚለውን ስሜቱን ገርቶ በተዳከመ ድምፅ ጠየቀ‹‹ሌላ ማን ያውቃል…?››
‹‹ስር ስሮ ስትል ላየኋት ትእግስት አሳይቼታለሁ…ወንድምህ አይቷል….ከዚህ ጣጣ በኃላ ደግሞ ፀባይህ እየታየ ሌሎች ቅርብህ ያሉ ሰዎች እንዲያዩት አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ምን ነካህ ደደብ ነህ እንዴ..?እንዴት ለእዝራ ታሳዋለህ…?እንደልጁ እኮ ነው የሚወዳት …በዛ ላይ እብድ ነው ይገለኛል፡፡››
‹‹ቢገድልህ ደስ ይለኝ ነበር..ግን እንደዛ አይነት የተባረከ ንፅህ ሰው በአንተ ቆሻሻ ደም እንዲረክስ አልፈልግም…ያ  ትክክል አይደለም፡፡አሁን ሁላችንንም ትተወናለህ፡፡››
‹‹ሁላችንንም ስትል?››ጠየቀ ግርማ፡፡
ሁላችንንም…እኔንም ፤አሮራንም ፤ትእግስትንም፤ጋሽ እዝራንም…ሁላችንም ከዛሬ ጀምሮ እኛን አታውቀንም ..እኛም አናውቅህም፡፡ያለንበት አትደርስም አንተ ያለህት አንደርስም..ይሄ ያስማማናል፡፡
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ….?ከአንተ ጋር እሺ በፊትም አሮራ እንጂ ሌላ የሚያገኛኘን ነገረ የለም…በቀላሉ ላለመደራረስ እንችላለን..ሌሎቹ ግን?››
‹‹ሌሎቹ ምን?››
‹‹ለምሳሌ እዝራ ስራ መስራት ካቆመ አመታት አልፈዋል..በሽተኛ ነው…ከእኔ ብር ካለገኘ እንዴት ይኖራል…?ትግስትም ስራዋን ታሳጣታለህ….አሮራንም እየገነነ ያለው የዘፋኝነት ጉዞዋ ላይ እንቅፋት ነው የምትሆንባት ….ለሁሉም አስፈልጋቸዋለው…ለጊዜው ቢበሳጩብኝም ግን እመነኝ ከእኔው ጋር መቀጠል ነው ሚፈልጉት፡፡››
‹‹እንደዚህ ነው የምታስበው…?››
‹‹አዎ…ግልፅ ነው››
መንግስቱ ከመቀመጫው ተነሳና ቆመ…. አቶ ግርማ ተንደርድሮ ሊያንቀው መስሎት አይኑን አፈጠጠ…መንግስቱ ግን  እግሩን ወደበራፉ አንቀሳቀሰ…..እና አንኳኳ…ተከፈተለት፡፡በራፍ ላይ ያለውን ሰው አነጋገረው..እና ወደቦታው ተመልሶ ተቀመጠ፡፡
በመሀከላቸው መልሶ  ዝምታ ሰፈነ….
‹‹እሺ አሁን ምን እናድርግ?››ግር ነው ጠያቂው፡፡
‹‹ቆይ ጠብቅ አለው….››መንግስቱ
በዛው ደቂቃ በራፉ ተከፈተና ትእግስት አንገቷን አስግጋ ቀድማ ገባች፤ከዛ ጋሽ እዝራ የአሮራን እጅ እንደጨበጣ ገባ…መንግስቱ ተነሳና ተቀበላች…ግራና ቀኝ እሱን ከበው ተቀመጡ….ግርማ በእፍረት አንገቱን ወደምድር አቀረቀረ….
መንግስቱ ንግግሩን ጀመረ……‹‹ወዳጆቼ አሁን ከዚህ ሰው ጋር ስለብዙ ነገሮች እየተነጋገርን ነበር….ከዛ በመጨረሻ ከሁላችንም ትርቃለህ..ከእኔም፤ ከትእግስም ፤ ከአሮራም ሆነ ከወንድምህ ከእዝራ አጠገብ አትደርስም…እኛም አንተ ስር አንደርስም…አልኩት …እሱ ግን ከአንተ እርቃለሁ…ከሌሎቹ ከራቅኩ ግን ሚጎዱት እንሱ ናቸው፡፡ትእግስትም ስራዋን ታጣለች…አሮራም የሙዚቃ ህይወቷ ይበላሻል…..ወንድሜም በእኔ ብር ነው የሚኖረው አለኝ…እኔ እናንተን ወክዬ መወሰን ስላቃተኝ ነው ያስጠራዋችሁ…እና ምንድነው ሀሳባችሁ?፡፡
ትእግስት ጀመረች‹‹እኔ እንኳን እሱ ያለበት ቤት ውስጥ እሱ የሚኖርበት ከተማ ውስጥ ባልኖር ደስ ይለኛል….ስሬ እንዳትደርስ››አለችው፡፡
‹‹ለእኔ ሞተሀል….አበባዬን ቀንጥሰህ ነው ያጠወለግከው…አንዴት ይኖራል ?ብለህ አታስብ …መኖር ቢያቅተኝ በክብር ለመሞት ድፍረት ያለኝ ሰው ነኝ፡፡ስለዚህ ስሬ እንዳትደርስ ››አለው፡፡
አሮራ ጉሮሮዋን አፀዳዳችና መናገር ጀመረች….‹‹እኔ ግን አልስማማም…ዝም ብዬ ልተወው አልችልም››አለች፡፡ ሁሉም በድንጋጤ አይናቸው ፈጠጠ….

የግርማ ፊት በፈገግታ  ፈካ…፡፡እና በፈንጠዝያ መናገር ጀመረ‹‹አውቃለሁ የእኔ ቆንጆ ..የእኔ ነገር እንደማይሆንልሽ በደንብ አውቃለሁ…በመሀከላችን ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት አዝናለሁ…ታያለሽ እክስሻለው፡፡ወደ ውጭም እንድትሔጂ ያሰብኩትን ትቼዋለው….እዚሁ ከእኔ ጋር ነው የምትኖሪው…ለዛ ቃል እገባልሻለሁ፡፡››አላት፡፡

አጎቷ እዝራ ባልጠበቀው መልሷ ግራ ተጋብቶ ‹‹ሮሪ እርግጠኛ ነሽ ከዚህ ሰው ጋር ያለሽን ግንኙነት ማሳቀጠል ትፈልጊያለሽ…?ፈርተሸው ከሆነ እኔ አጎትሽ አለሁ፡፡በህይወቴ ጭምር ከእሱም ሆነ ከሌላ አንቺን ሊያጠቃ ከሚያስብ ሰው ጠብቅሻለው፡፡››አላት ፡፡

‹‹አጎቴ እንደዛ እንደምታደርግ አውቀለሁ፡፡ሁላችሁም እኔን ለመጠበቅ እንደማታቅማሙ አውቀለሁ…ለዛምነው ይሄን ሰው ዝም ብዬ በነፃ ልለቀው የማልፈልገው…እሱነ ከህይወቴ ብቻ በማስወጣት በሰላም እንዲኖር ልፈቅድለት አልችልም…..ልጅነቴንና የዋህነቴን ተጠቅሞ አቆሽሾኛል…እሺ እሱን ይቅር ልለው እችላለሁ….እስክሞት ድረስ ደብድቦኝ ለቀናት አግቶኝ ነበር ፤እሱንም ይቅር ልለው እችላለሁ…ግን የእናቴን ነገር እንዴት ችላ ብዬ እተወዋለሁ?፡፡››ስትል ጠየቀች፡፡
ሁሉም ግራ ተጋብተው እርስ በርስ ተያዩ
‹‹ሮኒ እናትሽ ምን?››እዝራ ነው ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቀው፡፡
‹‹እናቴን በእጆቹ የገደላት ይሄ ሰው ነው….ለዛ ሳይከፍል በነፃ ልለቀው አልችልም››


,ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍15014😱3😁2🔥1
(የመጨረሻ ክፍል)
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-43
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
ግርማ ለዘመናት ሸሽጎቸው የነበሩ ሚስጥሮቹ ሁሉ ተዝረክርከውበት  ግራ ተጋብቷል።አሁን የማይፈልጋቸውን ሰዋች ከህይወቱም ሆነ ከአካባቢው እንዴት እንደሚያስወግዳቸው ሳይሆን እራሱን እንዴት ከገባበት ወጥመድና ከእስር ቤት ስጋት ማዳን እንደሚችል ነው እየተጨናነቀ ያለው። በዚህም የተነሳ  አንገቱን ከመድፋት ውጭ  የሚናገረው ነገር አልነበረውም።እዝራ፣አሮራ እና ትዕግስት ፊት ለፊቱ ተቀምጠው  በጥላቻና  በመፀየፍ እየተመለከቱት ነው።
እዝራ  ድንገት አይኖቹን  ወንድሙ ላይ ተክሎ  መናገር ጀመረ"ታላቅ ወንድሜ... በእውነት በዚህ ሶስት ቀናት ውስጥ ስላንተ በሰማሁት ነገር ሁሉ መደነቄን ልደብቅህ አልፈልግም...እንዴት እንዲህ ደፍሪም ፤ገዳይም ..ዘራፊም ልትሆን ቻልክ?ወላጆቻችን እንዴት እንዳሳደጉን  አውቃለሁ? እንዴት እንዲ ፅንፍ የረገጠ ልዩነት በመሀከላችን ኖረ...?ብቻ እናትና አባታችን እንኳንም በህይወት አልኖሩ..?እንዴ እኔ እንዲህ የተሽማቀቅኩብህ እነሱ ኖረው ቢሆን ኖሮ ልባቸው  እንዴት እንደሚሰበር. ሳስበው ዝግንን ይለኛል።"..
ግርማ የወንድሙን ንግግር ችላ አለና  ወደ አሮራ ዞሮ መናገር ጀመረ...
"በቀደም ባቀረብሽልኝ ነገር ተስማምቼያለሁ"አላት።
"ምንድነው የተስማማችሁት?እኛም እንስማዋ።"ጠየቀ መንግስቱ።
"በቀደም   አንድ መኖሪያ ቤት እና  የኤክስካቨተር ማሽን እንድሰጣትና እንድንለያይ ጠይቃኛለች...ምንም ቢሆን ልጄ ነች... ያንን ባደርግላት ብዙም ቅር አይለኝም...ግን ከእሷም የምፈልገው ነገር አለ ...ይሄ  ስለእናቷ ግድያ...ፓሊስ ምናምን ስለምትለው መረጃ ስለሌለው ነገር መቆፈሩን ታቆማለች..."አለ ...
"አንተ የምትላቸው ንብረቶች እኮ የልፋቴ ውጤቶች ናቸው .. እንተሳሰብ ካልን ንብረቴ  ከዚህ በእጥፍ እንደሚበልጥ እርግጠኛ ነኝ።...የማልከስህ ለምትሰጠኝ ንብረት ስል አይደለም...ለአንተም ሀዘኔታ ተሠምቶኝ ፍፁም አይደለም...አንተን ማልከስህና የማላሳስርህ አንድና ብቸኛው ምክንያት ለትንሿ እህቴ ስል ነው።እሷ አባቴ ምን አጥፍቶ ታሰረ ስትለኝ ምን እመልስላታለሁ?ብዬ ስለማስብ ነው"
"ጥሩ ውሳኔ ነው...ግን እንደእኔ እንደኔ ከእሱ የምትረከቢውን ንብረት ቢቀርብሽ እራሡ ደስተኛ ነኝ..."አላት መንግስቱ።
"ለምን ብዬ ሙልጬን ወጣለሁ..?ስጦታ አይደለም እኮ የጠየቅኩት የለፍሁበትን ንብረቴን ነው...እና ደግሞ እህቴም ከእኔ ጋር እንድትኖር ነው  የምፈልገው።. "
"ሙልጭሽን አትወጪም የእኔ እመቤት ...እኔ ምን ያህል እንደማፈቅርሽ ታውቂያለሽ...ፈቅደሽ ብታገቢኝና አብረን ብንኖር ደስ ይለኛል ...ካልሆነም ዛሬውኑ ይሄን ውይይት ጨርሰን  ከእዚህ እገታ ስንላቀቅ አስረክብሻለው።"አላት መንግስቱ
"ምኑን ነው የምታስረክበኝ?።"ግራ በመጋባት ጠየቀችው።
"እኔ ገስት ሀውሱን በስምሽ አዘዋውሬዋለሁ።ያ የ300 ሚሊዬን ብር የሚያወጣው ገስት ሀውስ የእኔም የአጎቴም አይደለም። ያንቺ ከሆነ አንድ ወር አልፎታል።እኔን እሺ ብለሽ አገባሺኝም ብቻሽን ኖርሽም..ወይም ሌላ ሰው አገባሽም  ንብረቱ ያንቺው ነው...ከእሱ ጋር ንብረት መናጠቅ ውስጥ መግባት አያስፈልግሽም"አላት።
እሷ ብቻ ሳትሆን እቤት ውስጥ ያሉት በጠቅላላ በሰሙት ነገር ብዠ ብሎባቸዋል....አሮራ በመገረም ተሞልታ"ለምን ብለህ ነው እንደዛ ያደረከው?"ስትል ጠየቀችው።
"ስለማፈቅርሽ"በአጭሩ መለሠላት።
"እሺ ከወራት በፊት ነው ያደረከው አይደል..ጥሩ በዛን ጊዜ ስለእኔ የነበረህን  ጥሩ ግምት  ነበር  ..ይገባኛል.. ...አሁን ግን ከእዚህ አባት ተብዬ ጋር የነበረኝኝን ግንኙነት አልሰማህም?"
"ሠምቼያለሁ"
"የምታፈቅራት ሴት  የእንጀራ አባቷ መጫወቻ  እንደነበረች ስትሰማ...አልዘገነነህም? "
"አይ አልዘገነነኝም..ግን ደግሞ አልዋሽሽም... አስደንግጦኛልም አበሳጭቶኛልም ።"

"ትክክል እኔም የገመቱኩት እንደዛ ነው ...ከተበሳጨህብኝ ደግሞ በዚህ  ውሳኔህ አትፀናም ማለት ነው"

"አይ ፀናለሁ..ምክንያቱም የተበሳጨሁት በዚህ ሰውዬ እንጂ ፍፁም በአንቺ አይደለም።አንቺ ምን አደረግሽና?"
ሳቀች "እየቀለድክብኝ ነው?"
"ለምን ቀልድብሻለሁ...የምሬን ነው...ለአንቺ ያለኝ ፍቅር  እንዲህ በቀላሉ የሚደበዝዝ አይደለም..."
.ተንደረደረችና ከተቀመጠች ተነስታ ወደእሱ በመሳብ ከንፈሩ ላይ ተጣበቀችበት።ሁሉም ያልጠበቁት ስለነበረ ተገረሙ...አቶ ግርማ ግን በሽንፈትና በንዴት አንጀቱ ኩምሸ አለበት። የሚያደርገው ግራ እስኪገባው ድረስ ባለበት ተንቆራጠጠ..
ከመሳሳም ሲላቀቁ ትዕግስት "አንዴ ለብቻህ ላናግርህ?" አለችው።
ምን ሊፈጠር ነው በሚል ሁሉም እርስ በርስ ተያየ...ትዕግስት ከመቀመጫዋ ተነሳችና  የመንግስቱን ክንድ ይዛ አስነሳችውና   ወደጥግ ይዛው ሄደች።
ከዛ በሹክሹክታ "ምነው ችግር አለ እንዴ?"ሲል ጠየቃት ።
"አጎትህ ከካናዳ መጥቶል ..ጠፍተህበት ምድሩን እያሰሰው ነው..ሰምተሀል?"
"አዎ ሰምቼለሁ።"
"የገስትሀውሱን ስም ማዘዋወርህን እንዴት የሚቀበለው ይመስልሀል?"
"እሱን አኔ እወጣዋለሁ..አንዳንድ የማታውቂያቸው ነገሮች አሉ...ሰውዬው የሀብቱ ሁሉ መነሻ ምን ይመስልሻል ..?ከአባቴ የዘረፈ ብር ነው።ቀን ጠብቄ የሚገባኝን ንብረት ወስጄ ነው ለምወዳት ሴት የሠጠሁት...በዚህ ቅር ብሎት የሚያበሳጨኝ አይመስለኝም።"
"ትቀልዳለህ እንዴ...አጎትህ ለዛ ገስትሀውስ ያለው ፍቅርና ኩራት ቀላል አይደለም...እኔ በማቀው እራሱ ያንን ንብረት ለማፍራት በጣም  ለፍቶል...እና  ከቅሬታ በላይ በሆነ ስሜት ውስጥ ነው የሚገባው"
"እንደዛ ከሆነ  የቀሩትንም ንብረቶች ነጥቀዋለው...እሱ የተሳሳተው ለሁሉም ንብረቶቹ ሙሉ ውክልና የሠጠኝ ቀን ነው።"
"አዎ በዛ እኔም አምናለሁ ..አምኖህ ሙሉ ውክልና መስጠት አልነበረበትም...እኔ የምፈራው እርስ በርስ እንዳትገዳደሉ ነው"
"ዋናው የአሮራ የወደፊት ህይወት ይስተካከል እንጂ የእኛ መገዳደል ብዙም አያሳስብም።"
"የአንድን ሰው ህይወት  ለማስተካከል የሌላውን ማውደም ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው..እሺ ንብረቱን እንተወው ሴቶቹን እንዴት ታደርጋቸዋለህ?"
ያልጠበቀው ጥያቄ ስለሆነ ደነገጠ...ግራ ተጋባም"የትኞቹን ሴቶች?"
"ውሽሞችህን ነዋ ...ሁለቱ የጎትህን  ሚስቶች"
"እንዴ!!! እንዴት እንደዛ ልትይ ቻልሽ ?"
ሁለቱንም ሴቶች አንድ ላይ ስታወጣ አይቼሀለው...እርግጠኛ ነኝ እኚ ሴቶች ነገሩን እንደቀልድ እያዩት አይመስለኝም...እና ጠቅልለህ የአሮራ ልሁን ስትል ዝም ብለው የሚፈቅድልህ ይመስልሀል?"ስጋቷን ጠየቀችው።
"እና ምን ያደርጋሉ?መቼስ ያገባናል ብለው አያስብ"
"ለምን አያስብም...እንደተረዳሁት ከሆነ ሁለቱም አፍቅረውሀል...ያፈቀረች ሴት ደግሞ የትኛውንም አይነት መስዋዕትነት ከፍላም ቢሆን ያፈቀረችውን  ወንድ የራሷ ለማድረግ መጣሯ የተለመደ ነው።"
"አረ ትዕግስት እያጋነንሺው ፤የአጎቴ ሚስቶች ናቸው እኮ"
"አዎ ገባኝ  ...እየተንከባከብካቸው የነበረውም ልክ እንደአጎትህ ሚስቶች ነው...ለማንኛውም ውሳኔህ በጣም  ስሜት የተጫነው መሆኑን እንድታወቅ።የተሠማኝን ተናግሬለው...አሁን ወደ ሰዎቻችን እንመለስና ለውይይታችን እልባት እናብጅለትና ሁለታችሁም በተስማማችሁት መሠረት ለቀጠራችሆቸው አጋቾች  ክፍያቸውን ስጦቸውን ለጊዜውም ቢሆን ከዚህ ግር ግር እንውጣ...ከዛ በሂደት የሚሆነውን እናያለን። "አለችውና ወደነአሮራ ለመመለስ እርምጃ ጀመረች መንግስቱም ስለሰጠችው ጠንካራ ሂስ እያሰላሠለ ከኃላዋ
👍9214👎6🥰5😁2🤔2
ተከተላት።
ታሪኩ ይቀጥላል እኔ ግን አበቃው።
ተፈፀመ

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍44😢12👎9🤔7
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ደሎ  ከተማ በአረና ጥቅጥቅ ደን የተሸፈነች በደቡብ ኦሮሚያ ባሌ ዞን ውስጥ የምትገኝ የወረዳ ከተማ ስትሆን ለሁለት የተከፈለችው ያዶት በሚባል ግዙፍ ወንዝ ነው፡፡ያዶት ወንዝ ለከታማዋ ኑዋሪ ህይወት ነው፣ውበት ነው፣የአይን ማረፊያቸው እና ትምክህታቸው ነው፣ከውጥረታቸው መተንፈሻ ነው፣የሚኮሩበት መዝናኛቸው የሚደምቁበት ጌጣቸው ነው፡፡ ከተማዋ ቆላ እንደመሆኗ መጠን አየሩ በጣም ይሞቃል ፤ በላብ ሚያጥብ ሙቀት፡፡ቀይ  በንፋስ በሚበተን አፈር  እና አቧራ ሲያሰቃየው የዋለው ኑዋሪ ሀብታም ደሀ ሳይል ወደ ያዶት ይነጉዳል፡፡ልብሱን ያወላልቅ እና ወራጅ ወንዝ ውስጥ ይመሰጋል፣እንደ ዓሳ ብቅ ጥልቅ ይላል፣እየተንሳፈፈ ይዋኛል፡፡ ይሄ ትልቁም ትንሹም ወንድም ሴቱም በኩልነት ያለ ልዩነት የሚያደርገው ነው፡፡ሁሉም እርቃኑን በፓንት ብቻ ጎን ለጎን እየተንቧራጨቀ መዋኘት ለእንግዳ ሚያስገርም እና ሚያስደምም ትዕይንት ቢሆንም ለኑዋሪው ተራና የተለመደ የየእለት ደርጊት ነው፡፡

አንድ የዛ ከተማ ኑዎሪ ሌላውን ኑዋሪ ቢያንስ በዓመት አንድ ቀንም ቢሆን እርቃኑን ወይም እርቃኗን የማየት አጋጣሚና ዕድል ይኖረዋል፡፡የደሎ ኑዋሪዎች ዋናተኛ ናቸው፡፡ህጻናት ከ5 አመት ጀምረው ነው ከታላላቆቻቸው ጋር ወደ ያዶት ወንዝ ወረድ በማለት ዋና መማር የሚጀማሩት፡፡ያዶት መዋኛና ከሙቀት አካልን ማቀዝቀዣ ብቻ አይደለም፡፡የከተማው ሰው ሁሉ ልብሱን የሚያጥበው እዛው ወንዝ ነው፡፡ልብሱን በጀርባው አዝሎ ወይ በሻንጣ ሞልቶ ማጠቢያ ሳፋውን ተሸክሞ በመምጣት ወይም ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ በመፈተግ ፅዳቱን ይጠብቃል፡፡ይህ የተለመደና ለከተማዋ እንደባህል የሚታይ እሴት ነው፡፡
በዘመኑ ኑዋሪው ለመጠጥም ሆነ ለምግብ ማብሰያ የሚጠቀሙበትን ውሀ የሚቀዳው ከዚሁ ያዶት ወንዝ ነበር፡፡ውሃው በአብዛኛው ሚመላለሰው በአህያ ጀርባ ነው፡ይሄንን በመስራት የሚታዳደሩ ከሀምሳ በላይ የሚሆኑ ግለሳቦች አሉ፡፡አህያው ላይ የእንጨት ኮርቻ ይጫንና፡፡ኮርቻው ላይ በአንደኛው ሁለት ባለ 25 ሊትር ጄርካን በሌለኛው ወገን እንደዛው ሁለት ጀሪካን በአንዴ አራት ጄሪካን ወይም 100ሊትር ጭኖ ከወንዙ አንድና ሁለት ኪሎ ሜትር በማጓጓዝ ይሸጣል፡፡ለመጠጥ የሚሆን ውሀ የሚቀዳው ግን ገና ሰማይና ምድር እንደተላቀቀ ከ12 ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ባለው ጊዜ  ነው፡፡የዚህ ምክንያት ያዶት ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ተራራዎችን ሰንጥቆ ፤ጫካውን አቋርጦ ስለሚመጣ የሰውና የአውሬዎች ንክኪ ሳይበዛበትና ሳይደፈርስ  የጠራ ውሀ ለማግኘት ነው፡፡
እና በጊዜው  በዚህ ልምድ መሰረት  ለቤቱ የመጠጥ ውሃ መቅዳት እና በለሊት ተነስቶ ወደ ያዶት በሮ በመሄድ የጠራ ውሀ ቀድቶ ቁርሰ ቀማምሶ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የበሻዱ የዘወትር ተግባሯ ነበር፡፡ይሄኛው የበሬዱ ልምድ ከእድሜ ልክ ፍቅረኛዋ ከሆነው ተአምረኛው ፍጡር ጋር የሚያቆራኘው ቀጥተኛ ነገር አለ፡፡
በሬዱ እንደወትሮዋ ከእንቅልፏ ባና ጃሪካኗን አንጠልጥላ ለመያዝ የምትጠቀምበትን ጨርቅ በትከሻዋ ጣል አድርጋለች የቤቱን በራፍ ከፋታ የግቢያቸውን የቆርቆሮ አጥር አልፋ ቁልቁል ወደ ያዶት ወንዝ እየነጎደች ነው፡፡..ግን ከቤቷ ብዙ ከራቀችና ከተማውን ለቃ ወጥታ በወንዙና በከተማው መካከል ያለውን ባዶና  ወጣ  ገባ ስፋራ ከደረሰች በኃላ ነበር የሆነ ትክክል ያልሆነ ነገር እንዳለ  ያስተዋለችው፡፡ከወትሮዋ ፈጠን ብላለች፡፡አዎ ገና ለሊት ነበር፡፡
የተወሰነ ፍራቻ ቢሰማትም ወደ ኋላዋ አልተመለሰችም፡፡ የባህርዛፍ ደን ያለበትን መንገድ ሰንጥቃ ስታልፍም ከነፍራቻዋ ነች፡፡ወደ ኋላዋም ሆነ ወደ ፊት ለፊቷ እየተሸከረከረች ብትገላመጥ ምንም የሚታይ የሰው ዘር  አላየችም፡፡በደን ወደተሸፈነው የወንዙ ዳርቻ ስትደርስ ጉሬዛዎች ከዛፍ ወደዛፍ እየተንጠላጠሉ ሲዘሉ እያየች ቢሆኑም እርምጃዋን አልገታችም፡፡የያዶት ወንዝ ሿሿሿሿ…  ብሎ ሲፈስ ከሩቅ ይሰማታል፡፡ደረስችና ቀሚሷን በመጠኑ ሰብስባ ወደወንዙ አንድ ሜትር ያህል ገባ በማለት ጄሪካኑን መሙላት ጀመረች፡፡

ግማሽ እንደደረሰች ከወንዙ መሀል የሆነ የሚንቦጫረቅ ድምጽ ሰማችና አውሬ መስሏት ጄሪካኗን ጥላ በርግጋ ከወንዙ በመውጣት እራቅ ብላ መመልከት ጀመረች፡፡እሷ ጥላ የወጣችውን ጄሪካን በውሀው ግፊት ወደ መሀል ተምዘግዝጎ አውሬ ወደመሰላት አካል ሲጓዝ ተመለከተች፡፡ ደግነቱ ሰማሁት ያለችው ድምጽ የአውሬ ሳይሆን የሰው ነበር፡፡መጀመሪያ ዕርቃኗን የምትዋኝ ሴት መስሏት ነበር..፡፡
አስተውላና ተረጋግታ ሳታየው ግን ቀይ ጥቅልል ጥቁር ፀጉር ያለውና በውሀው ለስልሶ ግንባሩ ላይ ድፍት ያለበት የሆነ የአማልክት አይነት መልክ ያለው ወጣት የእሷን ጄርካን ይዞ በፍራቻዋ እየሳቀባት  ተመለከተችው፡፡

‹‹ይህን ያህል ፈሪ ከሆንሽ በዚህ ሰዓት እንዴት እዚህ ቦታ ተገኘሽ?››ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፅ አውጥቶ አናገራት፡፡ድምጹ በጆሮዋ እየተንቆረቆረ ወደ ውስጧ ሰርጎ ሲገባ የሆነ በመንፈስ የመሞላት አይነት ግራ አጋቢ ስሜት ተሰማት፡፡
‹‹የነጋ መስሎኝ ነዋ፤አንተስ በዚህ ለሊት እዚህ ቦታ ለዛውም ወንዙ ውስጥ ምን ትሰራለህ?››ስትል መልሳ የራሷን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

‹‹እኔማ አንቺ እንደምትመጪ አውቄ እየጠበቅኩሽ ነው››

‹‹የት አውቀህ ነው የምትጠብቀኝ?››

ከወንዙ መሀል እሷ ባለችበት አቅጣጫ ወደ ዳር ቀረብ እያለ‹‹እርግጥ አላውቅሽም፤ ግን ውሀ ልትቀጂ በለሊት ስትመጪ ሁሌ አይሻለሁ››አላት፡፡

‹‹አንተ ሁል ጊዜ  ለሊት እዚህ ምን ትሰራለህ?››

‹‹እቤቴ እዚሁ ቅርብ ነው፡፡በዚህ ሰዓት መዋኘት ያስደስተኛል፤ከያዶት ጋር በሹክሹክታ ምስጢር የምናወራው በዚህ ሰዓት ነው፡፡እያንዳንዱን አዲስ ቀን በደስታ የምቀበለው እዚሁ ሆኜ ነው፡፡››

‹‹በል እሺ ጄሪካኔን ስጠኝና ዉሀዬን ልቅዳ፡፡›› አለችው፡፡ ከማታውቀው ሰው ጋር በአጉል ሰዓት አጉል ቦታ ሆና አጉል አይነት ወሬ ከዚህ በላይ ማውራት አስፈሪ ቢሆንባትም ጄሪካኑን ግን የእውነት እንዳለችው እንዲመልስላት አልፈለገችም ነበር፡፡ 

..‹‹ልቅዳልሻ…እስከዛ አንቺ አውሪኝ፡፡››ብሎ ጄርካኑን በሁለት እጇቹ ወደታችኛው የውሀው ጥልቃት ደፍቆ… ዷዷዷ በሚል ድምጽ በመታጀብ መሙላት ጀመረ፡፡

ለስለስ ባለ ሰርሰሪ ድምፅ ‹‹አውሪኛ …እስክሞላልሽ›› በማለት በድጋሚ ጠየቃት፡፡
ግራ በመጋባት

‹‹ምን ላውራህ?››ስትል መለሰችለት፡

‹‹አሁን ብጠልፍሽስ?››

‹‹ጠልፈህ ምን ታደርገኛለህ?››

‹‹በሀገራችሁ ተጠልፎ ምንድነው የሚደረገው.? አገባሻለኋ፡፡››

‹‹ሆሆይ…ጠልፎ ማግባት እንዲህ ቀልድ ሆነ እንዴ?አረ ቶሎ ሙላና ስጠኝ ልሂድበት፡፡››

‹‹ቀስ በያ ቆንጆ ስለሆንሽ እኮ ነው ልጥለፍሽ ያልኩሽ፡፡››

ምን አይነት መልስ መመለስ እንዳለባት ግራ ተጋባች ‹‹..ለመሆኑ እቤቴ ቅርብ ነው ምትለኝ እዚህ ቅርብ ከጫካ እና ከጅብ ጉድጎድ በስተቀር ምን ቤት አለ.?››ሲከነክናት የቆየውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

‹‹እውነቴን ነው፡፡የእኔ ቤት እዚሁ ቅርብ ነው፤ግን  በአይን አይታይም፡፡ፀባይ ከላሽ አንድ ቀን ወስድሻለሁ››

‹‹ኸረ ይቅርብኝ››ብላ ከወንዙ አውጥቶ ያቀበላትን ጃሬካን በያዘችው ጨርቅ በጀርባዋ አዝላ ለመሄድ ዝግጁ ሆነች፡፡እንግዳው ሰው ግማሽ አካሉን ወንዝ ውስጥ ግማሽ እርቃን አካሉን ደግም ለእይታ አጋልጦ ለእሷ እያስጎበኘት በአይኖቹ ሸኛት እሷም እየተገላመጠች ወደ ፊት በመንደርደር አመለጥኩ በሚል እፎይታ ግን ደግሞ ትንሽ ብቆይስ? በሚል ግራ አጋቢ ቁጭት ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡

ይቀጥላል
👍17427🥰5🤩5👏2
አትሮኖስ pinned «#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ደሎ  ከተማ በአረና ጥቅጥቅ ደን የተሸፈነች በደቡብ ኦሮሚያ ባሌ ዞን ውስጥ የምትገኝ የወረዳ ከተማ ስትሆን ለሁለት የተከፈለችው ያዶት በሚባል ግዙፍ ወንዝ ነው፡፡ያዶት ወንዝ ለከታማዋ ኑዋሪ ህይወት ነው፣ውበት ነው፣የአይን ማረፊያቸው እና ትምክህታቸው ነው፣ከውጥረታቸው መተንፈሻ ነው፣የሚኮሩበት መዝናኛቸው የሚደምቁበት ጌጣቸው ነው፡፡…»
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///



እቤት ስትደርስ ሰዓቱ ገና ለአስራ ሁለት ሰዓት እሩብ ጉዳይ ነበር‹‹ሁለተኛ ሰዓት ሳላይ እና መንጋቱን ሳላረጋግጥ ንቅንቅ አልልም ..ቅዱስ ሚካኤል ነው ከመአት ያወጣኝ ፡፡››ብላ ስህተቷን ዳግመኛ ለለመድገም  ለራሷ ቃል ገባች፡፡ግን ደግሞ ያለማቋረጥ ስለእሱ ከማሰብ እራሷን ማቀብ አልቻለችም‹‹ይሄ ሰው የሆነ ነገር አድረጎኝ ቢሆንስ ?››ስትል አሰበችና በፍርሀት ራደች፡፡ደግሞ የደሎ መና ኑዋሪ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነች፡፡ምክንያቱም ከተማዋ በሁለት ቀበሌ ብቻ የተዋቀረች በመሆኗ  ኑዋሪዎቹ ቢያንስ በመልክ እርስ በርሱ ይተዋወቃሉ፡፡ ያንን ወንዝ ውስጥ በግማሽ እርቃን ሆኖ ያየችውን ሰው ግን ከዚህ በፊት የትም ቦታ አይታው እንደማታውቅ እርግጠኛ ነች፡፡ የደሎ ህዝብ እርስ በርስ ከመተዋወቁ የተነሳ ለምሳሌ የጉልት ነጋዴዎች በመደዳ አስር ሆነው ቢቀመጡ ምሳ ሰዓት ሲሆን አንዱ ይቀርና ዘጠኙ ምሳ ለመብላት ወደየቤታቸው ይሄዳሉ፡፡አንዱ የሁሉንም ደንበኛ   በታማኝነት ያስተናግዳል፤በታታሪነት ይሸጣል፤ የተቀበለውን ገንዘብ በተገቢው ቦታ ያስቀምጣል፡፡
ቀኑ ተገባዶ መሽቶ ወደ መኝታዋ ስትሄድ እንኳን  ሀሳቧ ያዶት ወንዝ ላይ  እንደተጣበቀ ነበር …ጀርባዋን የጥጥ ፍራሽ ላይ አሳርፋ በተለመደው ሰዓት ብትተኛም እንቅልፏ ሁሉ የተቆራረጠ ..ለሊቱ የረዘመና የተንቀራፈፈ ሆነባት፡፡ክፋቱ ደግሞ አያቷ በኢጣሊያንን ወረራ ለመፋለም አድዋ ዘምተው በድል ሲመለሱ ከጠላት ማርከው ለግላቸው ካስቀሩት አንዱ ብርቅዬ  የእጅ ሰዓት ነበር…ይህ ሰዓት ማሰሪያው ቢበላሽም ዋና ሰዓት ቆጣሪው ግን በትክክል ያለዝንፈት ይሰራል፡፡ይህን የዘመኑ ተአምራዊ ዕቃ አያትዬው ከሞቱ በኋላም ቤተሰቡ ግድግዳ ላይ አንጠልጥለው ይጠቀሙበታል…በሬዱም ማታ ሰዓቱን ከወላጆቾ ክፍል ወደራሷ ክፍል በማዘዋወር ከራስጌዋ ሰቅላው ስለነበር በየሆነ የጊዜ ክፍት አየተነሳች ሰዓቱን ትመለከት ነበር፡፡በወቅቱ ሰዓት ሚባል ተአምራዊ ማሽን በከተማዋ ብርቅ ነበር፡፡ምን አልባትም ይህ ሰዓት በግለሰብ ደረጃ በከተማውም ያለው ብቸኛው ቅርስ  ሳይሆን አይቀርም፡፡ያው በወቅቱ ማህበረሰቡ የጊዜ ልኬትን በተወሳሰበ ማሽን ሳይሆን ሲወርድ ሲዋረድ በመጣ የሰዓት አቆጣጠር ጥበብ ነበር በራስ መንገድ በመስፈር የሚገለገለው፡፡
በሬዱ ግን ዕድሜ ለጀግናው አያቴ እያለች በመሀል ከእንቅልፏ ተነስታ ሰዓቷን ታያለች…ገና 8፡20….መልሳ ለመተኛት ትሞክራለች..ብዙ ከመሰላት ቆይታ በኃላ ሰመመን ከመሰለ እንቅልፏ ትባንንና ብድግ ብላ ፋኖሷን ለኩሳ ሰዓቷን ታያለች 9፡35…‹‹ሰዓቱ ተሳስቶ ይሆን እንዴ?›› የሚል ስጋት በውስጧ ይሰነቀርና በቤታቸው ሽንቁር አጮልቃ ውጩን ትመለከታለች፡፡ ግማሿ ጨረቃ ሰማዮ አናት ላይ በስሱ ስትጓዝ ፤ ከዋክብቶች ደግሞ ሰፊው ሰማይ ላይ ተበትነው ሲደንሱ ታያለች… ወደምድር ስታይ ሁሉ ነገር ጨለማና በፀጥታ የታጠረ ይሆንባታል…ሰዓቱ እንዳልተበላሸ ውስጧን ታሳምንና መልሳ ትተኛለች..
ቆይታ ቆይታ ስትነቃ ምንም የተቀየረ ነገር አይኖረም….ከቤታቸው በአቅራቢ ካለው መስኪድ የመጀመሪያ አዛን  ትሰማለች…በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ የዶሮ ማራኪ ድምፅ እና የወፎች ጥዑም ዝማሬ ይናፍቃታል….ግን ምንም የሚሰማ ነገር የለም…መልሳ ለመተኛት ትሞክራለች‹‹ሰውዬው ምን አይነት አዚም ነው ያስነካኝ?›በራሷ ጥያቄ ውስጧ ራዳ..…ተኝታ ተኝታ ስትባንን የወፎች ብስራት ዜማ ሰማች… በርግጋ ከመኝታዋ ወረደችና ሰዓቷን ተመለከተች 11፡40 ይላል.. ከዛ በላይ ታግሳ መጠበቅ አልፈለገችም..ቀስ ብላ ተነሳችና ቤተሰቦቾን እንዳትቀሰቅስ እየሰጋች ሹክክ ብላ   ጄሪካኗንና ማዘያ ጨርቋን  ይዛ በቀስታ በራፉን ከፍታ ወጣች…

.ያስፈራል፤ከጭለማው ጋር አይኗን እስክታለማምድ ደቂቃዎች ወስደውባት ነበር….በጭራሮ ታጥሮ በጭራሮ በር የተዘጋውን የጊቢያችውን  አጥር መሸንጎሪያ አውጥታ ከፈተችና ወጣች… ግን መቀጠል አልቻለችም… ልቧ ለሁለት ተከፈለ..‹‹ሂጂ ችግር የለውም፡፡››እሯሷን ለማበረታታት ሞከረች፡፡
‹‹..አረ ተይ ሰው አግኝቶ ባይተናኮልሽ እንኳን አውሬስ ቢዘነጥልሽስ…?›ሌላ የፍራቻ ስብከት ከውስጧ በመመንጨት ይረብሻት ጀመር፡፡ ከግቢያችው መሀል ተጋድሞ የነበረው መቻል በጩኸት ያንቧርቀው ጀመር…አንድ ሀሳብ መጣላት፤ተመልሳ ወደ ጊቢ ገባችና ወደ እሱ ሄደች፡፡ቀስ ብላ በሹክሹክታ ልክ እንደልብ አውቃ ጎዳኛ መጮሁን ተወና እግሯ ስር ሽብልል ብሎ ተኛ፡፡
.‹‹አብረን እንሂድ ተነሳ…››አለችውና መንገዷን ይዛ ወደ መውጫው እርምጃዋን  ቀጠለች ..ተከተላት..::
አዎ አሁን ቀለል አላት‹‹…ቢያንስ ካንተ ጋር መሄድ ይሻላል……››ብላ ውሻዋን አስከትላ ጉዞዋን ቀጠለች...ወንዙ ጋር ስትደርስ ገና ጭለማው እንደመግፈፍ እያለ   ነበር፡፡መቻል ከኃላ ከኃላዋ ኩስ ኩስ እያለ ነው፡፡በዛፎቹ ላይ ያሉት ወፎች የለሊት ዝማሬያቸውን ያሰማሉ..እንደደረስች ጄሪካኗን አንከርፍፋ ለአስር የሚሆን ደቂቃ ፈዛ ወዲህና ወዲያ አይኖቾን በማንከራተት የሆነ ነገር ትፈልግ ነበር..፡፡

‹‹እንዴ ምንድነው የምፈልገው….?ጄሪካኑን ይዤያለሁ… የወንዙም ውሀ በእግሬ ላይ እያለፈ ወደ ፊት እየተመመ ነው..እና ለምን ጎንበስ ብዬ  አልቀዳም ..?ለምን በብርድ እንዘፈዘፋለሁ….?›› እያለች ከራሷ ጋር ሙግት በገጠመችበት ቅፅበት ውሻዋ ማንቧረቅ ጀመረ….. ግረ ገብቷት አይኖቾን ስታቁለጨልጭ ከወንዙ መሀል ብልቅ ብሎ ወጣ…፡፡
‹‹የፈጣሪ ያለህ.!!›› ጩኸቷን ለቀቀችው...ደግነቱ  የእሷ ጩኸት ከመቻል ጩኸት ስለማይበልጥ ተውጦ ቀረ…፡፡

"ዛሬም ደነገጥሽ?››
‹‹ምን አይነት ሰው ነህ…..?ቤትህ  ወንዙ ውስጥ ነው እንዴ?››በመገረም ጠየቀችው፡፡
ፈገግታ የተርከፈከፈበትን አንፀባራቂ ፊቱን ወደእሷ አቅጣጫ አዙሮ‹‹አዎ …ከፈለግሽ ነይ ልብስሽን አውልቂና ግቢ ….በዛውም ቤቴን አሳይሻለሁ››አላት፡፡

‹‹ቤትህን ባየው ደስ ይለኝ ነበር… ግን ዋና  አልችልም››አለችውና ለቀልድ ምላሽ ሰጠች፡፡
‹‹የደሎ ልጅ ሆነሽማ ዋና አልችልም ብትይ አላምንም…ደሎዎች እንኳን ሰዎቹ እንስሳቱም ዋናተኛ ናቸው፡፡››

‹‹ቢሆንም ይቅርብኝ ..ባይሆን ሌላ ጊዜ›› እለችና ጎንበስ ብላ ጄሪካኗን ወደ ውኃ ውስጥ ከተተቸው…መቻልም ድምፅን አጥፍቶ በሜትሮች ርቀት መሬት ላይ ለጥ ብሎ ሁለቱንም እየታዘበ ነው፡፡
‹‹እንግዲያው ቀረብሽ ››ብሎ መልሶ ወደ ውሀ ውስጥ እራሱን ደፈቀና ሙሉ በሙሉ በመስመጥ እራሱን ከእይታ ሰወረ…የሆነ ነገሯን ይዞ የሄደ ነው የመሰላት…፡፡
እንዳላት ልብሷን አወላልቃ ወንዙ ውስጥ መግባት እና አብራው መዋኘት በጣም አሰኝቷት ነበር..ግን ፈርታ ነው እምቢ ያለችው፤በዚህ ሰዓት እርቃኗን ወንዝ ውስጥ ከማታውቀው ሰው ጋር…‹‹ግን ምን ችግር አለው…?ባደረግኩት ኖሮ››ስትል ቁጭት ውስጥ ገባች…አንድን ነገር እኩል መፈለግ እና እኩል አለመፈለግ እንዴት ነው የሚቻለው፡፡በዚህ ደቂቃ በእሷ ላይ እየታየ ያለው ስሜት እንደዛ አይነት ነው...በሁለት ጫፍ ወደግራና ቀኝ በእኩል ኃይል መወጣጠር፡
👍1175😁4
ከአሁን አሁን ከሰመጠበት ይወጣል ብላ  ስትጠብቀው ምንም አይነት ምልክት ሳይታይ…ውሀ ውስጥ የደፈቀችው ጄሪካን ሞላ..፡፡ጎትታ ከወንዙ ውስጥ አወጣችውና ዳር ላይ አስቀመጠችው….ጄሪካኗን ተሸክማ ጉዞዋን መቀጠል ነበረባት …ግን እግሯ ሊንቀሳቀስላት አልቻለም...ምትሆነው ግራ ገባት .መጮኸ አማራት…ከነልብሷ ዘላ ወንዝ ውስጥ ለመግትም ፈለገች…ግራ በመጋባት ልቧ እየዋለለ ሳለ ልጅ ብልቅ ብሎ ወጣ….ሳይታወቃት‹‹ተመስገን›› አለች፡፡

ይቀጥላል
👍123😁142👏1
አትሮኖስ pinned «#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// እቤት ስትደርስ ሰዓቱ ገና ለአስራ ሁለት ሰዓት እሩብ ጉዳይ ነበር‹‹ሁለተኛ ሰዓት ሳላይ እና መንጋቱን ሳላረጋግጥ ንቅንቅ አልልም ..ቅዱስ ሚካኤል ነው ከመአት ያወጣኝ ፡፡››ብላ ስህተቷን ዳግመኛ ለለመድገም  ለራሷ ቃል ገባች፡፡ግን ደግሞ ያለማቋረጥ ስለእሱ ከማሰብ እራሷን ማቀብ አልቻለችም‹‹ይሄ ሰው የሆነ ነገር አድረጎኝ…»
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሶስት
፡፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

አይኑን አይታ በመጠኑ ከተረጋጋች በኃላ‹‹ቻው በቃ.. ልሂድ››አለችው፡፡

‹‹አረ ትንሽ ቆይ..እስቲ ስምሽን ንገሪኝ?››

‹‹ምን ያደርግልሀል?››

‹‹ያው የቆንጆ ልጅን ስም ማወቅ ያጓጓል ..ለዛ ነው፡፡››

በንግሩ አፈረችና አቀረቀረች፡፡በጀርባው ተንጋሎ በመዋኘት ወደ እሷ እየተጠጋ…እንደመለመንም እንደማሳዘንም በሚመስል የድምፅ ቅላፄ..፡፡‹‹ንገሪኛ ፡፡››አለት..

‹‹በሬዱ››መለሰችለት፡፡

‹‹አንቺ ቆንጆ ስምሽም ቆንጆ አሪፍ ነው፡፡››አላት፡፡

ፈራ ተባ እየለች ‹‹ያንተስ..?››ጠየቀችው፡፡

‹‹የእኔን ሌላ ቀን ከእነ ትርጉሙ አነግርሻለሁ፡፡››

‹‹እንዴ ሌላ ቀን እንጋናኛለን እንዴ?››በድንጋጤ ጠየቀችው፡፡ጥያቄዋ  ማረጋጋጫ እንዲሰጣት  የመፈለግ አይነት ነው፡፡

የልብ አውቃ ነው‹‹እንዴ !!!ትቀልጂያለሽ እንዴ ..?እኔ እና አንቺ ገና ብዙ ጊዜ ይኖረናል …ብዙ ታሪክ እንጽፋለን፡፡››ሲል ፍርጥም ብሎ መለሰላት፡፡

‹‹የምን ጊዜ…?የምን ታሪክ..?››

‹‹የፍቅር ታሪክ ፡፡››

‹‹የፍቅር ….?ምን አይነት

አይን-አውጣነት ነው…አረ እኔ እንደዚህ አይነት ነገር አላውቅም፡፡››አለችው፡፡

‹‹እንደማታውቂ አውቃለሁ…. እኔም እንዳንቺው አላውቅም ….ግን አብረን እንማረዋለን፡፡››ብሎ ይበልጥ አሳፈራት፡፡

‹‹በል ይበቃሀል አሁን ልሂድ..ብላ የግዷን ጄሪካኗን አንጠልጥላ ተሸከመችና ፊቷን አዞረች፡፡

‹‹በይ ደህና ዋይልኝ..ነገ በዚህን ሰዓት እጠብቅሻለሁ፡፡››

መራመዷን ሳታቋርጥ‹‹አታስበው…..ግን የእውነት እቤትህ እዚሁ ሳይሆን አይቀርም ?›› አለችው ፡፡

‹‹አሳይሻለው ብዬሽ የለ..? አሳይሻለው፡፡››መቶ ሜትር ያህል ከራቀች በኃላ ዞር ብላ አየችው.. ደብዛው የለም‹‹…መልሶ ሰምጦ ይሆን..?ይሄ አፍዛዝ ውበት ያለው ልጅ ሰይጣን ሳይሆን አይቀርም..?የወንዝ ሰይጣን…ግን እንዲህ አይነት ጠንበለል ሰይጣን ካለማ ይገርማል?››ስትል አብሰለሰለች፡፡
ቤተ-ክርስቲያን ግድግዳ ላይ የተለጠፈው ስዕል በቅዱስ ሚካኤል እግር ተጨፍልቆ የሚታየውን አስፈሪው ሰይጣን በምናቧ መጣባትና..ከዚህኛው ጋር አስተያይታ በራሷ አፈረች..‹‹..በስመአብ ይቅር ይበለኝ…››አለች፡፡
///

በተረጋገጠ ሁኔታ ከዛ የወንዝ ዓሳ ፍቅር ያዛት፡፡በቃ ህሊናዋን ማዘዝ፤እርሷን መቆጣጠር እስኪሳናት ድረስ አደጋ ላይ ወደቀች፡፡ የሚገርመው ደግሞ ይሄ የሆነው ከስድስት ወር ግንኙነት በኃላ አይደለም…ሶስት ወርም አይሞላውም….በአንድ ሳምንት ውስጥ ነው ስሜቷ ተርገብግቦ እዚያ ደረጃ ላይ የደረሰው፡፡
ሁኔታዋን እራሷ በራሷ ስትታዘበው የዓይኖቾ ቅንድቦች መገለጥ እሱን ለማየት ባለት ፍላጎት የሚታዘዙ፣የከንፈሯ መሸልቀቅ እና የጥርሶቾ መላቀቅ ለእሱ ንግግር መመሰጧን ለማብሰር የሚውሉ ምልክቶች እንደሆኑ፣የእግሮቾ መንቀሳቀስ እሱ ወዳለበት ለመሄዱ ባላት ፍላጎት  የሚሰሩ እየመሰላት  ከመጣ ቀናቶች አልፈዋል…፡፡አዕምሮዋንማ  በቃ  ሙሉ በሙሉ በምርኮ ተቆጣጥሮታል፤ከእሱ መልክ በስተቀር ሌላ ምንም ምስል የልተለጠፈባቸው  ኦና ሆኖባታል….፡፡

ከተገናኙ በሰባተኛ ቀናቸው  ነው፡፡ሰሞኑን ታደርግ እንደነበው የውሀ መቅጃ ጄሪካኗን ተሸክማ ከለሊቱ  11፡30 አካባቢ ሲሆን ያዶት ወንዝ ደርሳ ወንዙ ጠርዝ በመቆም ከላይ ከጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ እያፏጨና እየተስገመገመ የሚመጣው የውሀው ማዕበል እግሯን እያቀዘቀዘላት  ደንዝዛ ቆማለች፤አይኖቾ ወንዙ ውስጥ ተተክሏል …ፈዛለች….ቡልቅ ብሎ ከወንዙ የሚወጣውን  የፍቅር ዓሳዋን ጥበቃ ፡፡ ሊታክታት ትንሽ ነው የቀራት…..‹‹ግን ጥበቃ እንዴት ይሰለቻል…? በተለይ  ከገነት ወንዝ የተቀዳ የፍቅር ጠበል ይዞ የሚመጣን የልብ ጀግናን መጠበቅ ሲሆን ይከብዳል፡፡››አለች…
ግን ደግሞ አሁንም ጥበቃዋን  ቀጥላለች…5 ደቂቃ ..10 ደቂቃ…. .በቆመችበት  እግሯን ደነዘዛት፤ባፈጠጠችበት አይኖቾን ቆጠቆጣት፤የያዘችውን  ጄሪካን እንኳን አላስቀመጠችም፤ አንከርፍፋ  እንደያዘችው ነበር….፡፡ ሌላ 10 ደቂቃ በጥበቃ ባከነ....ሰማዩ ፈገግ እያለ ለመንጋት እየተግደረደረ ነው…፡፡
‹‹ልጅ የለም...ምን ዋጠው……?.የታበቱ ሄደ?››አእምሮዋን ያጨናነቁባት ጥያቄዎች ነበሩ፡፡በዚህ አይነት ሁኔታ 15 ደቂቃ ከጨመረች  ነግቶ ሰው መምጣት ይጀምራል…ሰው መምጣት ጀመረ ማለት ደግሞ እሱም የመምጣቱ ጉዳይ አከተመ ማለት ነው?እሱ ሰው እንዲያየው  እንደማይፈልግ በውስጧ ታምናለች፡፡ እንደውም አንዳንዴ መንግስት እጅ ላለመግባት በድብቅ ተሸሽጎ የሚኖር ሽፍታ ሁሉ ይመስላታል፡፡  ማስረጃው ደግሞ….ሰለእሱ አንድ የምታወቀው ነገር ቢኖር እሱን ማግኘት ከጀመረችበት  የአንድ ሳምንት ጊዜ  ውስጥ አንድም ቀን በደንብ እስኪነጋ እና ሰው ወደወንዙ መምጣት  እስኪጀምር  አብሯት ቆይቶ አለማወቁና ከወንዝ ውጭ በየትኛውም የከተማው ክልል አይታው አለማወቋ ነው፡፡
በደመነፍስ አንድ ውሳኔ ወስነች፡፡ጄሪካኗን በቁሟ ለቀቀችው፡፡ከድንጋይ ጋር ተጋጭቶ ጓ…ጓ..ጓ የሚል ድምጽ አሰማና  ቦታ ይዞ ተቀመጠ ፡፡ጄሪካኗን ለማዘያም ለብርድ መከላከያም ብላ  ተከናንባ  የነበረውን ፎጣ ከላዮ ላይ ገፈፈችና ስሯ ያለ የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ አንጠለጠለችው፡፡ከዛ ከፍ የሚል ድንጋይ ላይ ወጣች…ቀጥሎ ተወርውራ ወንዙ መሀከል ዳይቨ ሰመጠች……፡፡
ልክ እግሮቾ ድንጋዩን ለቀው በመስፈንጠር አየር ላይ እያለ ነበር ልብሷን ማውለቅ እንዳነበረበረባት ያስታወሰችው‹‹….ምን መሆኔ ነው …?ከነልብሴ መሆኔ አንደኛ እንደልብ ለመዋኘት አያመቸኝም …ሁለተኛ  እርጥብ ልብስ ለብሼ እየተንዘፈዘፍኩ ወደ ቤት ስመለስ ሰው በመንገድ ላይ ሲያገኘኝ ምን ይለኛል…? ቤተሰቦቼስ.…?የራሳቸው ጉዳይ …አሁን አንዴ ገብቼያለሁ…፡፡› በማለት እራሷን ለማፅናናት ሞከረች፡፡
ለአንድ ሁለት ደቂቃ ያህል  እየዋኘች ወደ ላይ ወደታች ተገለባበጠች..ከዛ ወደስር  ወደወንዙ ጥልቅ ሰመጠችና አፏን ዘግታ  ዓይኖቾን ከፍታ ማሰስ ጀመረች፤ግን አልተመቻትም ፡፡ወዲያው ወደ ላይኛው የውሀ ወለል ወጣችና ወደ ዳር ተጠጋች…..
ከወንዙ ሳትወጣ የለበሰችው  ቀሚስ ወደላይ ሞሽልቃ አወለቀችና  ዳር ላይ ከሚገኝ ድንጋይ ላይ በማስቀመጥ በፓንት ብቻ ወደ ውስጥ ተመልሳ በመስመጥ ውስጥ ለውስጥ እንደዓሳ ነበሪ  እየተሹለከለከች መዋኘቷን ቀጠለች፡፡በወንዙ የመሀከለኛ ወለል እየዋኘች ሳለ የሆነ ጠንካራና ፈርጣማ ክንድ ያለው ፍጥረት ከስሯ  በማታስበው  ፍጥነት እና ድንገተኝነት ሰቅስቆ ገብቶ በጀርባው አዝሏት ወደላይ የወንዙ ወለል ይዞት ሲወጣ እሪታዋን አቀለጠችው …

ይቀጥላል
👍19736😁8👏4👎1
#መቃብሬ_ላይ_ሚፃፍ

ጥብቅ ማሳሰብያ ሸክላን ለምትሰሩ
እዚህ መቃብር ላይ ዐፈር አትዘገኑ!!
ሲነድ ሲቃጠል ሲጨስ በመኖሩ፣
ሲቃጠል ለሚኖር፣
ለጀበና መስሪያ አይሆንም አፈሩ።

ኑረዲን ኢሳ
55😢21👍14👏4🔥1