አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
እግሯ እየተብረከረከ ቀስ ብላ ወደ አልጋው ሄዶች :: ጎንበከ ብላ ፊቱን ዳበስ ፤ ዳበስ አደረገችው ። «ሄይ ማም» አለ አይኑን ገለጥ አድርጐ ማይክ በዚች ዓለም ላይ ለማሪዮን የእነዚያን ቃላት ያህል ውብ ነገር አልነበረም ። የደስታ እንባ አፈሰሰች ፤እየሳቀች ።
«ማይክ በጣም እወድሀለሁ » አለች ።
«እኔም እወድሻለሁ እናት አለም» አላት ። ይህን ሲያይ በሕክምና ዓለም የኖረውና ብዙ ክፉና ደግ ብዙ ሞት ሽረት ያየው ዶክተር ዊክፊልድ ሳይቀር አይኑን እንባ ቆጠቆጠው። ይህን ለጋ ለግላጋ ወጣትና ይህችን ያህል ጊዜ እንቅልፍ ሳያሸንፋት ፤ እህል ሳያምራት የልጀዋን መታመም ስታብሰለስል ከጎኑ ሳትለየው ለመቆየት የቻለች እናት ሲያይ ሐኪሙ እንኳ አላስችል ብሎት እንባው መጣበት ። ስለዚህም ቀሳ ብሎ ትቷቸው ወጣ ። መውጣቱን ሁለቱም አላዩም ።

እቅፍ አድርጋ ይዛው ብዙ ሰዓት ቆየች ። እሱም ጸጉሯን በእጁ እያረሰ «በጣም አትሸበሪ ፤ ማሚ። አሁን ሁሉም ነገር ተስተካክሏል።የክርስቶስ ያለህ ! እንዴት አድርጎ ነው የራበኝ እባካችሁ» አለ ድምፁን ስትሰማ፤ ነፍሱ ተመልሳ «ራበኝ» ሲል ዳነልኝ በቃ የኔ ነው ፣ማንም አይወስድብኝም ፤ ማንም አይቀማኝም ስትል አሰበች ። ደስ አላት ፤ ሳቀች ። «ዊክን እንጠይቀውና ይሁን ካለ በዓለም ላይ ካሉት ቁርሶች ሁሉ የላቀውንና የጣፈጠውን ቁርስ እናቀርብልሃለን » አለች ።
«ዊክ ቢፈልግ ገደል ይግባ ። እኔ በራብ መሞቴ ነው› አለ ማይክል ።
«ማይክል ምናልክ ! » አለች ። ግን ቁጣ ሊሆንላት አልቻለም አትችልምም ። ልትወደው ብቻ ነው እምትችለው ። ቁጣዋ ያሳደረበትን ስሜት ለማየት ፊቱን ስታጤን ልውጥ ሲል ታያት። ቅር ተሰኝቶ አይደለም አልነበረም ። ድንገት አንድ ነገር ያስታወሰ መሆኑ በግልፅ ታይቷታል። ለምን ሆስፒታል ውስጥ እንዳለ የገባው መሆኑ ገብቷታል። የመጀመሪያው አነሳሱ ሌላ ነበር ። በልጅነቱ ቶንሲል አሞት ሰንብቶ ከእንቅልፉ ሲነቃ እንደተሻለው ሲገነዘብ የሚሰማው አይነት ስሜት ነበር ። አይስ ከሬምና እናቱን ብቻ የፈለገው ለዚያ ነበር ። አሁን ግን ፊቱ ላይ ብዙ ነገር አነበበች ። ተነስቶ ሊቀመጥ ሞከረ። ምን እንደሚፈልግ ግራ ገባው እንጂ የሆነ ነገር ሊጠይቅ ፈልጐ ነበር፡፡ ከፊቱ አንድ ነገር ለመረዳት የፈለገ ይመስላል ። ትኩር ብሎ አያት። እስዋም አየችው። እጁን ጭብጥ አድርጋ ይዛ
«የኔ ውድ በቃ ፣፤ ቻለው» አለችው።
«እማዬ . . . ያንለት ሌለት . . ሌሎቹስ! አሁን ትዝ አለኝ» አለ ።
«ቤን ወደ ቦስተን ተወስዷል። ተገጫጭቷል ። ቢሆንም ደህና ነው። ካንተ ይሻላል» አለችው። ይህን ብላ በረጂሙ ተነፈሰች ፤ በጣም ማዘኗን ለመግለፅ ። እና እጁን ጥብቅ አድርጋ ያዘችው ። ቀጥሎ የሚመጣውን ጥያቄ አስቀድማ አውቃዋለች ።መልሱን አስቀድማ ስላዘጋጀች አልተጨነቀችም ።
«ናንሲስ ? » አለ ።«ናንሲ የት አለች ማሚ !?»
ፊታ መልሱን ነገረው ።እንባው ዱብ ዱብ አለ። አጠገቡ ተቀምጣ እጁን ቀስ ብላ እያሻሸች ፤
«በጣም ተጎድታ ነበር ስለዚህ አልተቻለም ። ሕይወቷን ማትረፍ አልተቻለም» አለች ። ቀጥላም… «ሀኪሞች ያልሞከሩት አልነበረም ። አልቻሉም » አለችና ንግግሯን አቋረጠች ። «ዛሬ ጠዋት አረፈች » አለችው ቀጥላ ።
«አየሻት? ሄደሽ አየሻት ?» አለ ፊቷን ትኩር ብሎ ስትዋሽ ውሸቷን ለማንበብ የሚሞክር መስሎ ።
«ትናንት ሌሊት. . . ለጥቂት ጊዜ... አጠገቧ ሄጄ ቁጭ ብዬ ነበር ። »
«ምንው አምላኬ ! ምነው … ናንሲ!ወይኔ ! የኔ ናንሲ» አለ ። ትራሱ ሳይ ተደፍቶ እንደልጅ አለቀሰ ። ማሪዮን ከጀርባው ላይ እጅዋን ጣል አድርጋ ተወችው ። ስሟን እየደጋገመ እያነሳ አለቀሰ ። እስኪደክመውና ድምጹ ተዘግቶ ማልቀስ እስኪ ሳነው። ቀና ብሎ እናቱን አያት ። በዚህ ጊዜም ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው አዲስ ስሜት እፊቱ ላይ አየች ። የናንሲን ስም እየደጋገመ ሲጠራና ሲያለቅስላት ልክ ከውስጡ አንድ ነገር የጠፋ ያህል ነበር ያን ነገር አየችው ። ከውስጡ አንድ ነገር ጐድሎ የእሱ የአካል ክፍል ተነጥሎ እንደሞተ ታያት....

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍14
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...ከዌስት ሊን ተመርጦ የሔደው የሕግ መምሪያ ምክርቤት አባል በጥፋት ከወንበሩ ተባረረ ከሱ በኋላ ደግሞ የዌስት ሊን ሕዝብ ጆን አትሊ የተባለ አንድ በአካባቢው የታወቀ ሰው መርጦ ላከ " እሱም ብዙ ሳይቆይ ሞተና በምትኩ ሌላ እንደ ራሴ መምረጥ አስፈለገ" ማን እንደሚሻል ተመከረበት በአካባቢው የነበሩ ይሆናሉ የተባሉ ሁሉ 'ዳኞችም ሳይቀሩ ተገመገሙ ።

ሚስተር ጀስቲስ ይሻል ይሆን ? እለ · እኔ ያልኩት ይሁን ከማለት በቀር
መተማመን አይሆንለትም ቢሔድም የራሱን ሐሳብ እንጂ የዌስትሊንን ሐሳብ መግለጽ አይችልም። ስኳየር ስፒነርሳ ? እሱ ደግሞ በሕይወቱ በአደባባይ ንግግር አድርጎ አያውቅም " ቀይ ሥር ከማብቀልና ከብት ከማርባት በቀር የሚያውቀው የለውም " ኮሎኔል ቤተል ? ለምርጫው ውድድር የሚያወጣው ገንዘብ አያገኝም » ሰርጆን ዶቢዴ?በጣም አርጅቷል እሱም ራሱ“ከምርጫው ገደብ ኻያ ዓመት አልፏል” ብሎ ሣቀና “ ሁላችንም ብቃት ያላቸውን እየዘለልን በማይሆኑትት ሰዎች ላይ ብቻ ነው ያተኮርነው " ስብሰባችንንኮ ያለዐዋቂዎች ስብሰባ አደረግነው አሁን ከመኻከላችን እንደራሴያችን መሆን የሚችል አንድ ሰው ብቻ ነው ያለን "

“ ማነው እሱ ? አለ ጉባኤው
“ አርኪባልድ ካርላይል ።
ለምን እንደ ረሱት ሁሉም ገረማቸው -ጥቂት ዝም ብለው ከቆዩ በኋላ የድጋፍ
ጉርምርምታ አሰሙ ።

“ እሺ ካለን ነው ” አለ ሰር ጆን ። “ ፈቃደኛ ላይሆን ይችላል ...”

ወዲያው ለጉዳዩ ጊዜ ባይስጡት አንደሚሻል ተስማሙና ተሰባስበው ወደ
ሚስተር ካርላይል ቢሮ አመሩ ። ወደ ቤቱ ሊሔድ ሲል ደረሱበትና በሰፊው እየተወያዩ ብዙ ከቆዩ በኋላ እንዴራሴያችሁ እንደሆን ነው የፈለጋቻችሁኝ ? ለጥቅሜ ሁላችሁንም እሸጣችሁ እንዶ ሆንሳ በምን ታውቃላችሁ ? አላቸው "

ግድ የለም ሚስተር ካርላይል ...እናምንሃለን።

እኔ በአሁኑ ጊዜ ፓርላማ ለመግባት ምንም ሐሳብ አልነበረኝም "

ይኸማ አይሆንም !ይልቁንስ ስምህን ለውድድር እንድናስተላልፍ ፍቀድልን ። ካንተ ሌላ ብቁ ነው የምንለው ሰው የለንም አሁን አንተ እያለህ ከኛ አንዳችንን መምረጥ የማይሆን ነው አውጥን አውርዶን ስናየው ' ከድፍን ዌስትሊን ለዚህ ቦታ አንተን ያህል የሚመጥን ሰው አላገኘንም " ስለዚህ አንተን ለውድድር ለማቅረብ ተስማምተናል ። ነገ ወደ ዌስት ሊን ስትመጣ ግድግዳዎቹ ሁሉ'
ምን ጊዜም ካርላይል በሚሉ መፊክሮች አሽብርቀው ታያቸዋለህ።

እንግዲያውስ ነገሩን ጥቂት እንዳስብበት እስከ ነገ ጊዜ ስጡኝ " ግድግዳዎቹን በመፈክሮች ማስጌጡንም ለአንድ ቀን አዘግዩት '' አላቸው "
“ የለም የለም አሁን ወስንና ንገረን የእሺታ ቃልህን ስጠን።

አሁን ከወሰንኩ በእምቢታዬ እጸናለሁ ይኸ እኮ ጥቂት ማሰብ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው እስከ ነገ ጊዜ ስጡኝ » ምናልባትም ጥያቄያችሁን ለመቀበል እችል ይሆናል
ሰዎቹ ከዚያ የተሻለ።


ሰዎቹ ከዚያ የተሻለ አማራጭ ስለ አልነበራቸው በቀጠሮዉ ተስማምተው
ሔዱ በውይይቱ ጊዜ አብሮ የነበረው ሚስተር ዲል እጆቹን በርካታ እያፋተገና ሚስተር ካርላይልን ዐይን ዐይኑን እያየ ወደ ኋላ ቀረት አለ "

“ዲል ምነው ? በጣም ደስ ያለሀና ስዎቹ የሚሉኝን እንድቀበል የፌለግህ ትመስላለህ …”

"መቀበል አለብህና" .... ሚስተር አርኪባልድ " ደስ ያለኝ ስለመሆኔ ግን እኔ ብቻ ሳልሆን በዌስት ሊን ውስጥ ደስ የማይለው ሴት ወንድ ልጅ አይገኝም

“ ተው ዲል . . . . በጣም እርግጠኛ አትሁን።
“ ስለምኑ ? እንደራሴያችን ስለ መሆንህ ነው ' ወይስ ስለ ሕዝቡ ደስታ ?
“ስለ ሁለቱም አለው ሚስተር ካርላይል ሣቅ ብሎ ።

ከቢሮው ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲሔድ ጉዳዩን ያብላላው ጀመር " ከፊት ጀምሮ ፓርላማ ለመግባት ማሰቡ እርግጥ ነው ‥የሚወዳደርበትን ጊዜ ግን አልወሰነም " ዘመኑን በሙሉ ለግሉ ሙያ ብቻ የሚወስንበት ምክንያት አልታየውም ። ገንዘብ የማጣት ሥጋት የለበትም » በታወቀው የራሱ ሀብት ላይ ባርባራ ይዛው የገባችው
ሲጨመርበት ከአሁኑ ዐይነት አኗኗራቸው ከሚፈለገው በላይ ነው ሥራውን ለመተው ግን አሳብ የለውም ። ምክንያቱም ሥራው : በራሱም ጠንቃቃ አሠራር
ሳቢያ የሚያስከብረው ከመሆኑም በላይ ጠቀምቀም ያለ ገቢ የሚያገኝበትና ከልቡ
የሚወደው ሙያ ነው " ምንም ቢደረግ ሥራ ፈትቶ ለመኖር አይፈልግም " ነገር
ግን ሁልጊዜ ከሥራ ቦታው እንዳይለይ የሚያስገድደው ሁኔታ የለም ። ሚስተር ዲል
የሱን ያህል መምራት ይችላል እንዲያውም ያገልግሎት ዘመንና የሥራ ልምዱ ከተቆጠረ ይበልጠዋል " ስለዚህ ሚስተር ካርላይል ለፓርላማው ሥራ ወደ ለንደን ሲሔድ ኃላፊነቱን ያለምንም ሥጋት ለዲል ቢተውለት በሚገባ ሊያካሒድለት ይችላል " ፓርላማ መግባቱ ካልቀረ ደግሞ የበለጠ ጥቅምና መስሕብ ካለው ከማንኛውም ቦታ ይልቅ ዌስት ሊንን ወክሎ ቢገባ ይመርጣል አሁን ዌስትሊን አንድ አባል ስለሚያስፈልጋት ለሱ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖ ታየው " ጥሩና ብቁ የሕዝብ
አገልጋይ እንደሚሆንም ያምናል " ተሰጥዎው ሰፊ ፡ ንግግሩ አርኪ ነው እውነተኛና ቀና መንፈስ አለው " ወገኖቹን በሙሉ ኃይሉና ችሎታው እንደሚያለግል ያውቃል " እነርሱም ያውቃሉ "

ቅጠላ ቅጠሎቹ ባበቡበት ' ዛፎችና ቁጥቋጦዎች አዲስ ያቆጠቆጠውን ለምለም ቅጠላቸውን በለበሱበት ' በዚያ ደስ በሚለው የጸደይ ምሽት ሁሉም ነገር በተስፋ የተመላ ይመስል ነበር ።

ሚስተር ካርላይልም በቀረበለት ፡ ተስፋ ያለው ዕድል ከልቡ ተደሰተ "

ባርባራ ከሳሎኑ መስኮት ቁማ ትጠብቀው ነበር ሲገባ ደንበክ ደንበክ እያለች ወደሱ ቀርባ በብሩህ ዐይኖቿ ውስጥ የፍቅር ብርሃን እየዋለለ ፊቷን ወደሱ ቀና አደረገች።

'' ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት እንደዚያ ሆና እንደ ቆመች እጆቹን ከወደ ጀርባው
አድርጎ ።

" ምነው ? ደኅና እንዴት አመሸሽ ለማለት አቀበት ከሆነብህ እስከ ሳምንት ድረስ አትስመኝም ልል ሐሳብ አለኝ አርኪባልድ ”

ሚስተር ካርይል በአነጋገሯ ሳማቀና በዚህ የበለጠ የሚቀጣው ማነው ?”
አላት በሹክሹክታ

ባርባራ ለንቦጯን ጣለች እንባዋ ወዲያው በዐይኗ ሞላ “ ባንቺ ይብሳል '
ማለትህ ነው ! ለኔ ደንታ የለህምን አርኪባልድ ?”

በሁለት አጆቹ ጠምጥሞ ይዞ ከደረቱ እቅፍ አደረጋትና መልሶ መላልሶ ሳማት
ላንቺ ማሰብ አለማስቤንማ ታውቂው የለም ? አለት በጆሮዋ "

ይህ ሁሉ ሲሆን ያቺ የፈረደባት ሳቤላ ትመለከት ነበር በዘመኑ ለሷም ሲያደርገው የነበረው ሰላምታ ነው የገረጣው ፊቷ ደም እንደ ለበሰ ልክ እንዳመጣጧ ሹልክ ብላ ሳያዩዋት ወታ ወደ ክፍሏ ተመለሰች " ሚስተር ካርላይል ሚስቱን ወደ መስኮቱ ሳባትና ክንዱን በሽንጧ ሳይ አድርጎ እንደቆሙ “ስሚ እስቲ ባርባራ ካመት ውስጥ ለጥቂት ወሮች ለንደን ብንቀመጥ ምን ይመስልሻል ?

“ ለንደን ? እኔ እዚሁ በደስታ እኖራለሁ " የምን ለንደን አመጣህ ደግሞ ? ለንደን መቀመጥ አማረኝ እንዳትለኝ "

“ እርግጠኛ አይዶለሁም ግን አንድ ነገር ተጠይቄአለሁ ዌስትሊኖች እንደ ራሴያቸው እንድሆን ይፈልጉኛል " ከስሜ ላይ የፓርላማ አማካሪ የሚል ቅጽል ሲጨመርበት ማየቱ ደስ ይልሻል ?

“ጣም ጥሩ ነው ...አርኪባልድ " ሕዝቡ ወትሮም ቢሆን ይወድሃል አሁን ደግሞ የበለጠ ያከብርሃል " ዘለዓለም የገጠር ጠበቃ ሆኖ መኖር ላንተም ደግ አይደለም " ግን አሁን ለዕለት እንጀራህ ስትማስን አያለሁ " ተመርጠህ ብትሔድ ግን
ዌስት ሊን ላይ ለመሥራት አትችልም " ”
👍15
“ ባልችል ኖሮ ጥያቄውን አልቀበለውም ነበር " በዓመቱ ውስጥ ለተወሰኑ
ወሮች ለንደን መቀጥ አለብኝ " ግን ዲል ያለምንም ችግር እኔን ተክቶ መሥራት ይችላል ። እኔም ዐልፎ ዐልፎ ግማሽ ቅዳሜን እሑድንና ግማሽ ስኞን እየመጣሁ ማደር እችላለሁ " ሆኖም ይህ ለውጥ ጥቅምም ብቻ ሳይሆን ጉዳትም አለው አየሽ ከተመረጥኩ ወዲያው ወደ ለንደን መሔድ አለብኝ " አንቺ ደግሞ ቤቱን ትተሽ
አብረሽኝ መሔድ የሚሆንልሽ አይመስለኝም
"
ፊቷ በአንድ ጊዜ ተለዋወጠ ከሚስተር ካርላይል መለየቱ ከብዶ ታያት "

ለዕረፍት እስክትመጣ ድረስ አንተ ለንደን ተቀምጠህ እኔ አዚህ መቆየት አለብኝ ማለት ነው ? ተለያይተን ... አርኪባልድ ? እኔ ካንተ ተለይቼ መኖር አልችልም

“ ታዲያ ምን ማድረግ ይሻላል ? እምቢ ልበል ?

' እምቢ ማለት እንኳን ኢይሆንም ነገሮችን በችግር አኳያ ብቻ ነው የምናያቸው ለአንድ ወር ምናልባትም ለሁለት ወር ያህል አብሬህ ልመጣ እችላለሁ”

የምትችይ ይመስልሻል ?''

እንዴታ በደንብ ግን ልብ በል እማማ ካንተ ጋር እንዳልሄድ እንድትነግረኝ ማድረግ የለብህም” አለችው " ራሷን ከደረቱ ላይ አስደግፋ ደስ የሚለው ፊቷን በልመና መልክ ወደሱ ቀና አድርጋ እየተስለመለመች ንግግሯን ቀጠለች"

" አንተም ብትሆን ይዘኸኝ መሔዱን ትመርጣለህ አይደለም ?

እሱም አንግቱን ዘንበል አድርጎ” ዐይን ዐይኗን እየተመለከተ “ስታስቢው
ምን ይመስልሻል ፍቅሬ ? አላት "

ሳቤላ አሁን ደግሞ ከሌላ መጥፎ አጋጣሚ ላይ ደረሰች " በዚህ ጊዜ ግን ባርባራ ስትገባ ሰማቻትና ከባሏ ፈንጠር ብላ ቆመች " ሚስተር ካርላይልም ዞር ብሎ ማዳም ቬንን አያት ከንፈሯ ዐመድ ለብሶ ድምጿ ስልል ብሎ ወደነሱ መጣች

ወደ ኢስት ሊን ከመጣች ስድስት ወር ሆኗት ነበር እስከዚያ ጊዜ አልታወቀችም ጊዜና መቀራረብ ከአደጋ እንኳን ሳይቀር ያላምዳል የመታወቅ ስጋቷ ለቋታል " ልጆቹ ልክ እሷ እንደምትወዳቸው ወደዋታል " ምናልባትም ለተደበቀው የናትነት ጥያቄዋ ተፈጥሮ ምላሽ መስጠቷ ይሆናል።

ዊልያም ክረምቱን ሁሉ ደኅና ከርሞ ነበር ፀደይ ሲገባ ጀምሮ ግን ሰውነቱ
እንደ ገና አለቀ " ሁልጊዜ ድካም ድካም ይለዋል" ጎኑን ይወጋዋል " ምግብ አያሰኘውም ሚስተር ዌይንራይት ሕመሙን በየዕለቱ ይከታተልለታል - የፊቱ ውበትና የወዙ መሙላት ሲታይ ቀን ቀን በጤናው የዋለ ይመስላል " መልኩን አይቶ ታሟል ብሎ የሚጠረጥረው የለም ወደ ማታ : ጭልምልም ማለት ሲጀምር የበሽታው ምልክቶች በሰውነቱ ላይ ይታያሉ ፊቱ ግርጥት ይላል ለመናገር ይደክመዋል "

ከሁሉ አብልጦ የሚወደው የማረፊያ ቦታ በግራጫው ሳሎን ውስጥ ከእሳት
መሞቂያው ምድጃ ዳር ያለው ምንጣፍ ነው ። ከዚያ ላይ ትራስ ተደርጎለት ዐይኖቹን ገጥሞና በቁመቱ ሙሉ ዟ ብሎ ተዘርግቶ ይተኛል "

'' ልጄ ” ትለዋለች ማዳም ቬን ፤ “ ከሶፋው ላይ ብትሆን ይሻልሃል

“ አይ ይኸው ይሻለኛል ” ይላታል ።

“ወደ እሳቱ ጥቂት ባስጠጋሳ ? እስቲ ሞክረው ... ዊልያም "

አንድ ሁለት ምሽት ከሞከረው በኋላ ' ወደ ወትሮ ቦታው ተመለሰ "
ከዚያ ለመልቀቅ አልፈለገውም አንድ ቀን ማታ ሐና ሻይ ይዛ ስትገባ እንደ ልማዱ ተዘርግቶ አገኘችው " ለአንድ ሁለት ደቂቀ ቁማ ስትመለከተው ጸጥ ብሎ ተጋድሞ
ስለ ነበር እንቅልፍ የወሰዶው መሰላትና ወዶ ማዳም ቬን ዞር ብላ ፡
መቃብሩ እየገሠገሠ ነው ” አለቻት

እናቱ በሐና ንግግር ክው ብላ ደነገጠች " በየዕለቱ አብረን በመዋል በሺታውን እንለምደዋለን " ከለመድነው ደግሞ አሥጊነቱን እምብዛም ጐልቶ አይታየንም ሳቤላም እንደዚህ ነው የሆነችው ። መጀመሪያ ኢስት ሊን እንደ ደረሰች የዊልያምን መልክ አይታ፡ ባትደነግጥም ፡ በመጠኑ አሳስቧት ነበር። በክረምት ሻል ሲለው ከነሥጋቱም ለቀቃት " ፀደይ ሲገባ በልጁ ላይ አንዳንድ ለውጦች መታየት
ጀመሩ " ነገር ግን የተከሰቱት ቀስ በቀስ ስለ ነበር ሁኔታው ሳቤላን አላስደነገጣትም።
ልጁ መከራ የማይችል ደካማ ስለሆነ ጥሩ እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው እንጂ '
ሐና እንደምታስበው ያስፈራዋል ብላ አልጠረጠረችም ።

“ እንዴ ... ሐና ! ” አለቻት በተግሣጽ መልክ "

“ ምነው እማማ ? ሁኔታው ለእርስዎ እንዴት እንደማይታይዎ ገርሞኛል ”
አለቻት ሐና መልሳ ። “ ያልታዴለው ምስኪን ነገሩማ እናት እንዴሌለው የታወቀ
አይደል “ እናቱማ ብታየው ኖሮ ገና በፊት ነበር የሚለቀስለት " ሚስዝ ካርላይል እንደሆኑ የናትነት ያህል ሊሰማቸው አይችልም " ሚስተር ዌይንራይትም የማይገባው ደደብ ነው "

ወቀሳውን የራሷ አድርጋ ተቀበለችው ነገሩ ልቧን ነካት "

“ ምንም የተለየ ነገር የለበትም ... ሐና አቅም ያጥረዋል " ይኽው ብቻ ነው አለቻት ሆኖም እንዲህ ብላ ስትመልስላት በመልሷ አምናበት ሳይሆን ለመhሳከል ያህልና ራሷንም ለማታለል ነበር " ይህን መልስ ስትናግር እንኳን ከፍራቷ የተነሣ ልቧ ያለ መጠን ይደልቅ ነበር

“ ላይተኛ ይችላል እኮ ሐና" ስትናገሪ መጠንቀቅ አለብሽ"

“እኔማ እየሰማ አልናገርም አሁን ግን መተኛቱን ማንም የሚያየው ነው ''
“ ለምንድነው በአደገኛ ሁኔታ ያለ የመስለሽ ?

መምሰል እኮ አይደለም " እንደዚህ እየሆኑ ስለሚሞቱ ልጆች ከዚሀ ቀድሞም አይቻለሁ " "

''በዚህ መኻል ሉሲ ገባችና ሁሉም ዝም አሉ" ሐና ወጥታ ሔደች ሳቤላ በናፍቆትና በጭንቀት ስሜት ትክ ብላ ተመለከተችው » ነጭ ሆነ " ስማያዊ ደም "ሥሮቹ ከፊቱ ቁልጭ ብለው ታዩዋት " ያፍንጫው ቀዳዳዎች በተነፈሰ ቁጥር ይንቀሳቀሱ ነበር ደነገጠች

“ ማዳም ቬን ... ለምንድነው ዊልምን እንደዚህ አድርገሽ የምታይው ? አለቻት ሉሲ "

“ ሐና በጣም አሞታል ትላለች ” ብላ የደመ ነፍሷን መለሰችላት " ሚስተር
ካርላይልን ሲገባ ሰምታው ነበር " የልጁን ሁኔታ ልንገረው እያለች ከራሷ ጋር ስትከራከር ቆየችና ወጥታ ሔደች

በመተላለፊያው ዐልፋ ከሳሎኑ በር ቀስ ኢድርጋ አንኳኳችና ከፍታ ገባች "
ሚስተር ካርላይል ' ከላይ እንዳየነው ሁልጊዜም ውሎ ሲገባ ሚስቱን የፍቅር
ሰላምታ ያቀርብላታል ነበር " አሁንም ልክ በዚያው ዐይነት ሰላምታቸውን ሲለዋወጡ ደረሰች " እሷን ልብ ሰይላይት ተያይዘው እንደ ቆሙ ሰላም መባባላቸውን ቀጠሉ

አንደገና ሹልክ ብላ ወጣችና በጣም እየመታ ያስነቃትን ልቧን በሁለት
አጆቿ ጫን አድርጋ ደግፋ ተመለሰች " ባልና ሚስቱ የፍቅር ንግግር ሲለዋወጡ
በማየቷ ሲቃ ያዛት » ባርባራ የሚስተር ካርላይል ሚስት የፍቅሩ ሕጋዊት ባለመብት መሆኗን ዘንግታ በቅናት ተንገበገበች በፊት የግሏ የነበሩትን የሚስትነት
መብቶች በራሷ ፈርዳ ለባርባራ ለቃላታለች ያበቃለትንና ዳግመኛ የማታግኘውን ነገር እንዳዲስ አስታውሳ በሌላ ሴት ባል ቅናት ያዛት "

ወደ ግራጫው ሳሎን ተመልሳ በምድጃው ራስጌ ከነበረው መደርደሪያ ላይ
ክንዷን አስደግፋ ዐይኖቿን በመዳፏ ውስጥ ሽፍና እንደቆመች ብዙ ቆየች ምን
ያህል ምርር ብላ እንዳዘነች ለሉሲም ተሰማት ።

ሉሲ ራባት » ቀና እያለች ወደሻዩ ጠረጴዛ በጉምዃት ትመለከታለች አስተማሪዋ እስከ መቸ ድረስ በዚህ ዐይነት እንደምትቆይ ጨንቋታል “

“ ማዳም ቬን ሻይ መቅረቡን አላወቅሺም ? አለቻት "

ማዳም ቬን የልጅቱን ጥሪ ስምታ ቀና አለችና ከእግሯ ሥር ወደተኛ ልጅ ተመለከተች » ለጥያቄዋ መልስ ሳትሰጥ እጅዋን ከልጂቱ ትከሻ ላይ ጣል በማድረግ
“ሉሲ ... ብዙ ኀዘን ነው የተሸከምኩት " አለቻት "

“ ሻይ ያጠነክርሻል ደሞም ጥሩ ማርማላታ ቀርቧል ” አለቻት ሉሲ ለማጽናናት "
👍11
እስካሁን የፍቅር ሰላምታቸውን ሳያበቁ አይቀርም እስቲ እንደገና ልሞክር ብላ አሰበችና ሳቤላ ወደ ዋናው ሳሎን ሔደች " የሚስቱን ፊት ከደረቱ አስደግፎ ከንፈርቹን ከግንባሯ ላይ አሳርፎ እንደ ተቀመጡ አገኘቻቸው" በዚህ ጊዜ ስትገባ ሰማት " እሷም ያየችው ሁኔታ ቢዘገንናትም ' ዝም ብላ ቀረበች

« ጌታዬ.. ዊልያምን አንድ ጊዜ ዘልቀው ቢያዩት ” አለችው ሚስተር ካርላይልን

“ እሺ መጣሁ "

“ ለምን ? ” አለች ባርባራ "

" በጣም ያመመው ይመስላል " አስተያየቱ ደስ አላለኝም „

ሦስቱም ወደ ግራጫው ሳሎን ሔዱ ሚስተር ካርላይል እንደደረሰ ልጁን አስተውሎ ተመለከተው "

“ እንዴ ከወለሉ ምን ያደርጋል ? ከሶፋው ይተኛ እንጂ ማዳም ቬን ”
አለች ባርባራ

“ ድንግዝግዝ ሲል ከወለሉ ይተኛና ' ከዚያ በኋ አትንኪኝ ይለኛል " ብለምነው ባባብለው አቃተኝ » እሺ ብሎ አይነሣልኝም ”

ዊልያም ዐይኖቹን ገለጠ ማነው ነው ? አባባ ነህ ?” አለው ።
“ ደኅና አይደለህም እንዴ ዊልያም ?” አለ አባትየው "
“ አይ ኧረ በጣም ደህና ነኝ ብቻ ይደክመኛል "
“ ለምንድነው እሱ ላይ የተኛህው ?
“ ከዚህ መተኛት ደስ ይለኛል ...አባባ ያቺ ቆንጆ ነጭ ጥንቸሌ ኮ ሞተች።
“ እውነት? ተነሥተህ ስላሟሟቷ ብትነግረኝሳ ?
“ እኔም ገና ያወቅሁት ነገር የለም ” አለ ዊልያም ቀስ ብሎ እየተነሣ "
“ሎሲ አሁን ወታ ሳለ ብሌር ነገራት " እኔ ልወጣሁም - እንዳልወጣ ደከመኝ "
ምንድነው የሚያደክምህ ? አለው ሚስተር ካርይል እጁን እየያዝ "
“ እንጃ ሁልጊዜ ይደክመኛል
“ ለሚስተር ዌይንራይት እንደሚደክምህ ትነግረዋለሀ ?

“ የለም ለምን እነግረዋለሁ?እሱስ ያንን ግም ያሣ ዘይት እንድጠጣ ማዘዙን በተወኝ

“ ግን እንዲያጠነክርህ ብሎ” ኮ ነው ...የኔ ልጅ "
“ እንዲያውም ያሳምመኛል " ሁልጊዜ እሱን ከጠጣሁ በኋላ ያመኛል '
አባባ " ማዳም ቬን ግን እርጎ ጥሩ ነው ትለኛለች " ለኔም በጣም ይሻለኝ ነበር

እንደ ዊልያም ዐይነት ሕመም ለታመሙ ብዙ ሲረዳ አይቻለሁ ” አለች

ማዳም ቬንም ሚስተር ካርይል የልጁን አባባል ከሰማ በኋላ ዞር ብሎ ሲያያት

“ ሊሞክር ይችላል ” አለ ሚስተር ካርላይል "

“ እባክሽን ማጻም ቬን ... ለሱ ይጠቅማል የምትይውን ሁሉ ማዘዝ ትችያለሽ ” አለች ሚስ ካርላይል ባሏ ባለው ላይ በማከል “ ስለ ልጆች ከኔ የበለጠ ታውቂያለሽ"

" ሚስተር ዌይንራይት ሲመጣ ምን ይላል ? ” አለ ሚስተር ካርይል ወደ ሚስቱ ዞሮ ዝግ ባለ ድምፅ።

“እኔ ሲመጣ አላየውም
አርኪባልድ " ማዳም ታግኘዋለች ይመስለኛል
አለችው "

“ኧረ ምንድነው ነገሩ ? አለች ሉሲ „ “ ዛሬ ሻይ አንጠጣም ዳቦኖ ማርማላታ እፈልጋለሁ።

ሚስተር ካርላይል'ወደ ሉሲ ዞር ብሎ በፈግግታ ራሱን እየነቀነቀ ትዕግሥት ለትንንሽ ሴት ልጆች ጥሩ ነው ሚስ ሎሲ ትንሽ ዳቦና ማርማላታ ቢስጥህሳ የኔ ልጅ ?”

ዊልያም ራሱን ነቀነቀ ማርማላታ መብላት አልችልም " ውሃ ብቻ ነው
የጠማኝ "

ሚስተር ካርላይል ልጁን ትክ ብሎ ሲያስተውለው ቆየና ወጣ በታመመው
ልጅዋ የተጨነቀችው ሳቤላ ተከትላው ወጣች "
“ በጣም የታመመ ይመስላል...ጌታዬ ? አለችው በሹክሹክታ ድምፅ ሲያዩት ይመስላል ሚስተር ዌይንራይት ምን ይላል ?”

“ ለኔ ምንም አይነግረኝም እኔም ጠይቄው አላውቅም የሚያሠጋ ነገር ይኖራል ብዬም እስከ ዛሬ ማታ አላሰብኩትም ነበር

“ ዛሬ ከበፊቱ የባሰበት ይመስላል ? አላት

ከተለመደው የተለወጠበት ነገር የለም ። ሐና መጥታ ወደ ሞቱ እየተጓዘ
ነው ስትለኝ ነው ያስደነገጠኝ" እሱን ለማትረፍ ምን ማድረግ አንችላለን ?” አለችው።

በጋለ ስሜት ስትናገር እጆቿን አቆላለፈች። አብረው ቆመው ስለ ራሱ ልጅ ስለ ልጃቸው” ደኀንነት ሲነጋገሩ ዛሬ ባሏ ያለመሆኑን የዘነጋችው ትመስል ነበር ያሁኑን አሠቃቂ ሁኔታ ለመርሳት ግን ጨርሶ የሚሆን አልነበረም እንግዲህ እሱም፡ ልጁም በዚህ ዓለም ገንዘቧ ሊሆኑ አይችሉም ።
.
በሚዘንነው ከባድ ጭንቀት እንደ ተዋጠች ጉሮሮዋን እንቅ እንቅ ያደርጋት
ጀመር" በትሕትና እጅ ነሥታው ዞር ስትል ፡ “እስቲ እንደገና የሐኪሙን እርዳታ
አጠይቅለታለሁ
ማዳም ቪን ” ሲላት ስማችው ።

ወይዘሮ ሳቤላ ቬን ተመልሳ ወደ ግራጫው ሳሎን ስትገባ ከሚስዝ ካርላይል
ላይ ተጠምጥሞ ሲለማመጥ ደረሰች “ እማማ እሺ ብትይኝ እኔ የምበላውን ዐውቃለሁ ” ይላታል » እህል መቅመስ እንዳለለት እየነዘነዘች ስላስቸገረችው እንጂ
እውነት አሰኝቶት አልነበረም።

ምን ትበላለህ ?”
ጥቂት አይብ
አይብ ? አይብ በሻይ ? ” አለችና ሳቀች ሚስዝ ባርባራ ካርላይል

“ከሁላት ሳምንት ወዲህ ብዙ ነገር ያምረዋል የበሽተኛ የእህል አምሮት እንደዚሁ ነው " የጠየቀወን ላስመጣለት ግን አንዱንም አይቀምሰውም ” አለች ማዳም ቬን።

አሁን እርግጠኛ ነኝ እማማ ጥቂት አይብ እቀምሳለሁ " አላት "
”ይመጣልሀል አለችው ሚስዝ ካርላይል "
ልትወጣ ዞር ስትል መዝጊያ በኃይል ተንኳኳ " የደጁ መጥሪያ ተደወለ "
ባርባራ በራት ስዓት ምን እንግዳ መጥቶ ይሆን ብላ አሰበች » ወዲያው ሚስ ካርላይል ከንፈሮቿን ነክሳ ግንባሯን ከስክሳ በኮሪደሩ መተላለፊያው ዘለቀች

ኮርኒሊያ እንደዚያ እሳት ጐርሳ እሳት ለብሳ ቸመጣችበት ምክንያት ነበራት እሷ ከቤቷ መስኮት ቁማ ከመንግዱ አንዳንድ ደስ የማይሉ ነገሮች ሲፈጸሙ ትመለከታለች።

ከቤቷ ማዶ የነበረች አንዲት የቤት ሠራተኛ ከዳቦ ጋጋሪው ጋር ትዳራላች
ቁርጥራጭ የለበሱ ስድ ሕፃናት ከቦዩና ከአቧራው እየተሯሯጡ ይወራወራሉ እነዚህን ድርጊቶች እየተመለከተች ግንባሯን እየቋጠረች ዐይኗን እያጉረጠረጠች ትበሽቃለች በዚህ ሁኔታ እንዳለች ዳኞችና ሌሎችም ሰዎች ሆነው ከሚስተር ካርላይል በሮ ሲወጡ አይታ ይገርማታል ከብዛታቸው የተነሣ ኮርኒሊያ አስማተኛ ከባርኔጣ እየመዘዘ የሚጥላቸው አበቦች ትዝ አሏት ወጥተው የሚያበቁ
አልመስሏት አሉ ምንድነው ነገሩ አለች በደንብ ለማየት እንድትችል አፍንጫዋን ከመስተዋቱ ለጥፋ ተመለከተች ።

ሰዎቹ እየወጡ በየአቅጣጫቸው ሔዱ ራት መቅረቡ ቢነገራትም ዝም ብላ ማስተዋሏን ቀጠለች " እነዚህ ሰዎች የተሰበስቡዐትን ምክንያት ለማወቅ በጣም ጓጓች » ወዲያው ሚስተር ካርላይል ከቢሮው ወጣ የቆመችበትን መስኮት በጣቶቿ አንኳኳች አልሰማትም " ዞር አለና ወደ ቤቱ ገሰገሠ " ኮርኒሊያ ጭራቩን እሳት ሆነች

ቀጠሎና ጸሐፊዎች ከሁሉ መጨረሻ ደግሞ ሚስተር ዲል በቅደም ተከተል
ሚስተር ዲል ዝግ ብሎ ይሔድ ስለ ነበር የኮርኒሊያን ምልክት ስምቶ መጣ "

“ በፈጠረህ ! ” አለችው ዲል ትእዛዝዋን አክብሮ ሲመጣላት “ይህ ሁሉ ሰው ከቢሯችሁ ምን እየሠራ ነው ?”

"የእንደራሴነት ምርጫ ነው
“ የምን እንደራሴነት ነው እሱ ?
ሚስተር አርኪባልድን በሚስተር አትሊ ምትክ የፓርላማ አንደራሴአቸው
አድርገው ሊመርጡት ይፈልጋሉ "

“ አህያ ያባብሉ! እና አርኪባልድሳ አይሆንም ብሎ መለሳቸው ?

“ ቀጥታ መልስ ሳይሰጥ እስከ ነገ ጊዜ እንዲሰጡት ለመናቸው " "

“ ምን ማሰብ ያስፈልጋል ? እንደዚህ ያለ ዕብዶት እሱ አይሞክረውም "

“ ለምን .. ሚስ ኮርኒሊያ ? ተመርጦ ከሔደ ኩራት ሊሰማሽ ይገባል ! ''

“ አንተማ ከቀጥተኛው ነገር ይልቅ ጠማማ ነገር ነው የሚያኮራህ ... ሚስተር ጆን ዲል " ያ ደረቱ ላይ የተለጠፈው ሸሚዝህ ትዝ ይልሃል? ምን አደረኸው
“ሽቱ አርከፍክፈሀበት በሳጥን አኖርከው ?
👍16
እንዲያ አድርጌ ሳይሆን ዝም ብዬ ነው ከመሳቢያ ያኖርኩት አንቺ ያን ግዜ
ከተናገርሽኝ ወዲህ ለመልበስ ጠላሁት "

ለምን እሱን በግማሽ ዋጋ ሸጠህ በገንዘቡ ሁለት ጠቃሚ ሸሚዞች አትገዛበትም ይኽን የተሽቀርቃሪዎችን ልብስ ለቂልነትህ ማስረጃ እንዲሆን ከመኖር ይሻላል ምናልባት እሱም እዚያ የሥራ ቶች ማጠራቀሚያ ከሆነው ፓርላማ ከገባ
እንዳንተው የተለጠፈ ሸሚዝ ይገዛ ይሆናል እኔ እዚያ ከምገባ በሰው ጉልበት ከሚሳብ መፍጮ ቤት ብሰራ ይለኛል


“በደንብ ያሰብሽበት አይመስለኝም " ትልቅ ክብር ነው እኮ » እሱም ለዚህ
የበቃ ነው ቢመረጥ ደግሞ ከሁላችን በላይ ከፍ ይላል ደሞም የሚገባው ነው".

“ በል በቃህ ¦ ሰማሁህ አሁን ዘወር በልልኝ " ካንተ በላይ ቀርቶ ከቤትህ
ጉልላት በላይ ስቀለው " አለችውና ጥላው ወደ ፎቅ ወጣች » ደራርባ ለብሳ ተመልሳ ወረደች " በመተላለፊያዉ ዘልቃ ልትወጣ ስትል በጣም ተገርሞ ሊመለከታት
የነበረው ' አሽከሯ “ ራትዎንሳ ' እሜቴ ? አላት ፈራ ተባ እያለ

“ ስለኔ ራት ምን አገባሀ ? የራስህን እንሆነ በልተሃል ”
እየተጐናተርች ሔዶች » ከሚስተር ካርላይል ትንሽ ቆየት ብላ ኢስት ሊን ደረሰች።

“ አርኪባልድ የት ነው ? " አለች ገና ባርባራን ስታያት "
እዚህ ነው " ምነው ደኅና አይደለሽም እንዴ ?

ሚስተር ካርላይል ድምጿን ሰምቶ ብቅ ከማለቱ ወዲያው ጀመረችው "
አዲሰ የዌስት ሊን እንደራሴ ልትሆን ነው ሲባል የምሰማው እንዴት ነው?”
“ የዌስትሊን ፍላጎት ነው " ተቀመጪ እስቲ ኮርኒሊያ

“ ለራስህ ተቀመጥ " እኔ መጀመሪያ ለጥያቄዬ መልስ እፈልጋለሁ " መቸም አል
ተቀበልካቸውም

“ አይ እኔ እንኳን ለመቀበል ቆርለሁ "

“ የሚያስወጣህን ገንዘብ አስበኸዋል ?”

“ በገንዘብም በጊዜም አኳያ አስቤዋለሁ ተወዳዳሪ ከሌለ ወጪው እስከ
ዚህም ነው " ቢኖርም
“ እሺ ቢኖርም ?” አቋረጠ ችውና የሱን ቃል ደገመችው ለዚያው የሚውል ጥቂት መቶ ፓውንድ አላጣም " ”

“እስከ ዛሬ በሕይወት የቆየሁት ይህን ቀን ለማየት ነው?ገንዘብ እንደ ጥራጊ
መቈጠሩ ሲነገር ለመስማት!ለመሆኑ ሥራህሳ እንዴት ይሆናል?ተመራጭ ነኝ አልክ ከዚያ ከተረገመ ከተማ ለንደን ገብተህ ስትንገዋለል ከሥሮ እንዲዘጋ ነው?”

ስለ ስራው ልክ አሁን እንዳለው እኔ ብሞት!ወይም ለሰባት ዓመት ውጭ ብሔድ እንኳን ዲል ቀጥ አድርጎ ይይዘዋል ቢh
ቢስርክም እንኳን ያለሱ መኖር እችላለሁ " ግን አይከስርም ላረጋግጥልሽ

አንቺ ነሽ « ከምርጫው እንዲገባ ያደረግሺው ?” አለቻት ወደ ባርባራ ዙሯ
እሱ የወሰነው ለኔ ከመንገሩ በፊት ይስለኛል " ሆኖም እኔም እንዲቀበል አጥብቄ
ነግሬዋለሁ።

ነው ! ጥሩ አድርገሻል " ለንደን ገብቶ ለብዙ ወሮች እልም ብሎ ሲቀር ከጐንሽ ታገኘዋለሽ l”

ትቶኝ ኮ አይሔድም ” አለች ባርባራ ዐይኖቿ በአንባ እየሞሉ የመቅረት ነገር ስለተነሣ የሆነ መሰላትና ስታስበው ወደ ባሏ ጠጋ አለች ይዞኝ ይሔዳል ”

ተነጋግራችሁ ወስናችኋል ? ” አለች ወደ ሁለቱም በተራ እየተመለከተች “ እንዴታ ! ባልና ሚስት ለማለያየት ትፈልጊያለሽ እንዴ ...አላት እየሣቀ እሷንም ያበረደ መስሎት " ኮርኒሊያ ምንም ሳትናገር ልትሔድ ተነሳች

እራት እኮ እየቀረበ ነው ቁጭ በይና ከራት በኋላ ደግሞ በሰፊው እንነጋገራለን ” አላት "

ያባቴ ልጅ ሥራውን ጥሎ ሰነፍ የፓርላማ ሞልፋጣ ለመሆን ሲያብድ በማየቴ " ለአንድ ቀን የሚቐቃኝን በልቻለሁ „

“ ኧረ ቆይና ራት አብረን እንብላ " ከዚያም ከፈቀድሽልኝ ስለ ምርጫው
ነግር በሰፊው እነግርሻለሁ

“ስለሱ ልትነግረኝ ብትፈልግማ ከቢሮ ስትመለስ በኔ በኵል ታልፍ አልነበር!
“ ነገሩ ትዝ አሳለኝም " ቢሆንም ነገ ጧት መጥቸ ልነግርሽ ነበር : "

አይጠረጠርም ትመጣ ነበር እንጂ አለችውና በማሽሟጠጥ ' 'በሉ ''
ሁለታችሁም ደህና እደሩ ” ብላ ወጥታ ሔደች "...

💫ይቀጥላል💫
👍167
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...ሁለት ሦስት ቀን ቆይቶ ሚስተር ካርላይል ለዌስትሊን ነዋሪዎች ያዘጋጀው ንግግር በአካባቢ ጋዜጦች ወጣ ። ግድግዳዎቹ ሁሉ “ ካርላይልን ምረጡ! ምን
ጊዜም ካርላይል ! በሚሉ ፀባለ ልዩ ልዩ ቀለም ጽሑፎች አጌጡ " ...

ትንግርቶች ማብቂያ የላቸውም ። መገረምም የሰው ልጅ ዕጣ ነው » ሰር ፍራንሲስ ሌቪሰንን የሚያውቁት ሰዎች ሰር ፍራንሲዝ ሌቬሰን ከነበረበት ልማድና ጠባይ ራሱን አላቅቆ እሳት የላስ ፖለቲከኛ ሆነ ሲባል ስምተው እጅግ አድርገው ተደነቁ
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ወደ ፖለቲካ ዓለም የዞረው የጠቅላይ ሚኒስትርነት
ቦታ ተሰጥቶት ወይም ከቁም ነገራም ሰዎች ጋር እንዲሰለፍ ሕሊናው ወቅሶት አይደለም " የገንዘብ ችግር ደረሰበት ። ስለዚህ ደኅና ገንዘብ የሚገኝበት ምንም የማይሠራበት አንድ የሚደገፍበት ነገር አስፈለገው "

የገንዘብ ችግር ! በቅርቡ ከፍተኛ ሀብት የወረሰ ሰው እንዴት ካሁኑ ችግር
ላይ ሊወድቅ ይችላል » የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም " ፍራንሲዝ ሌቪሰን ሚወዳቸውን መዝናኛዎች ለሚወዱ ሁሉ ለክስረት ከዚህ የቀለለ መንገድ አያገኙም " ያጎቱን ማዕረግና ሀብት ሲወርስ እሱ ከጠበቀው የበለጠ ዕዳና ኪሣራ መክፈል ግድ ሆነበት " ሰር ፒተርም በመብቱ ማግኘት ከሚገባው በላይ አንዲት ቤሳ አልተወለትም ዕዳውን በሙሉ ከፍሎ የተረፈውንም ቢሆን በእጁ ከመግባቱ ገና በግራና በቀኝ ይበትነው ጀመረ ጋብቻው ለጥቂት ጊዜ ቢገታውም ተጨማሪ ወጭ ከማስከተሉ በቀር ምንም አላዳነውም " የገንዘብ ዐቅሙን መጥኖ በመኖር ፈንታ እሱና ሚስቱ ከዐቅማቸው በላይ መኖር ጀመሩ ከዚህ ሌላ ከጋብቻው ወዲህ በፈፀረስ
አሽቅድድም በቁማሮችና በልዩ ልዩ ውርርዶች ሁሉ መግባት ጀመረ " ያ ሁሉ
ገንዘብ ያስወጣ ነበር።

በዚህ ዐይነት ጊዜም ሔደ፤ሁኔታዎችም እስኪያቅታቸው ድረስ ተጓዘና ቆሙ።ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን በዚህ ጊዜ ነቃ " የነበረው ገንዘብ አንድ ሺልንግ እንኳን ሳይቀር አለቀ ዕቃው ሁሉ ተያዘ ። በነሱ ምትክ ዕዳና ዕዳ ጠያቂዎች ብቻ ቀሩ።
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ባሮኑ የውርስ ተስፈኛ ከነበረዉ ከተራው ፍራንሲዝ
ሌቪሰን የበለጠ ተጨነቀ

ሥራው ሁሉ እንደ ሟቹ ሎርድ ማውንት እሰቨርን ነበር ነገር ግን ፡ ኧርሉ
የሆነ ብልሃት እየፈጠረ ጉዱን እስከ ጊዜ ሞቱ አለባብሶት ዐለፈ " ይኽኛው ግን ጕዱን ይዞ ከችግርና ካስቸጋሪዎች ጋር ተፋጠጠ የሚያደርገው ሲጠፋው ቁማር ቢጀምርም ዕድል ፊቷን አዞረችበት እንደ ምንም አለና ከፈረስ እሽቅድድም ውድድር
ገባ ነገሩ እንኳን ለጥቂት ቀን ይደግፈው ነበር ሆኖም እሱም አቅጣጫውን ለቀቀና እንዲያውም የተጨማሪ ዕዳ ተጠያቂ አደረገው " በመጨረሻ ብዙ ገንዘብ የሚገኝበት ብዙ የማይሠራበት የመንግሥት ሥራ ለመፈለግ በሕግ መወሰኛ የነበሩትን
ሚኒስትሮችን እንደልቡ ለሚያቀያይረው ለሎርድ
ሄድሎት ጸሐፊ ለመሆን የተስፋ ፍንጭ አገኘ " ተስፋው ግን ተጨባጨጨ ሊሆን የሚችለው ሰወየው በመጀመሪያ ፓርላማ የገባ እንደፀሆነ ብቻ ነው " ከዚያ በኋላ ለተጠየቀ ሥራ ብቁ መሆኑ ይገመገማል " ይህ ሁኔታ ነው ወደ አሁኑ ታሪክ ያመጣን ።

በአንድ ፀሐያማ ድኅረ ቀትር ኢቶን አደባባይ ላይ ከነበረ ቤት በጣም ያማረ ሳሎን
ውስጥ አንዲት መልኳ ስልክክ ያለ መልከ መልካም ልጅ እግር እመቤት ተቀምጣለች " በመልካሙ ፊቷ የቁጣና የኩርፊያ መልክ ይታይባታል " በሚያምረው እግሯ ሥጋጃውን ትመታለች ይህች ሴትዮ የሰር ፍራንሲዝ ሌቪስን ባለቤት ናት።

አንድ ሥራ መልካምም ሆነ ክፉ ይዋል ይደር እንጂ ለሠሪው ፍሬውን አያሳጣወም " ነገሩ ብዙ ዘመን አልፎታል ፍራንሲዝ ሌቪሰን 'ብላንሽ ሻሎነር በተባለች ቆንጆ ልቡ ይጠፋል በፍቅር። ከመኻል ላይ አቋርጦ ለእመቤት ላቤላ ሲል ቸለል ብሏት ይቆያል እንደገና ሳቤላን ጣል አድርጎ ወደ እሷ ተመልሶ የምስጢር ግንኙነት ያደርጋሉ " በምስጢርም ይተጫጫሉ " የብላንሽ እህት ሊዲያ ሻሎነር ትጠራጠርና እኅቷን ትጠይቃታለች ከሌቪሰን ጋር መተጫጨቷን ምላ ተግዝታ ትከዳለች » በዚህ ሁኔታ እንዳሉ ዘመናት ዐለፉ " ምስኪን ብላንሽ በፍቅሯ ማተብ እንደጸናች ጠበቀች ዕዳውን የገንዘብ ችግሩን ቸልታውን ከሳቤላ ካርላይል ጋር ኰብለላውን ሁሉ እያወቀች ትወደው ነበር ከልቧ ታምነው ነበር ውርሱን ካገኘ በኋላ ወደ ለንደን እንደ ተመለሰ የነበረው ወዳጅነታቸው እንደገና ቀጠለ " ግን በሱ
በኩል የነበረው ፍቅር እንደ ወትሮው ሳይሆን ቀዝቃዛና ጭብጥ የሌለው ቢሆንም
ብላንሽ እንደሚያገባት ትተማመን ነበር አሁንም ከሷ ጋር የነበረው ግንኙነት
እንዲያው ያዝ ለቀቅ ነበር » በምስጢር አለሁልሽ አንለያይም እያለ ' ከቤትም እየዘለቀ ይጠይቃት ነበር " ምናልባትም ግንኙነት ማቆሙን ቢነግራት እብድ እንደምትሆንበት በማወቅ ስለ ፈራ ይሆናል " ብላንሽ እንደ ምንም ብላ ጨከነችና ጋብቻው በቶሎ እንዲሆን ጠየቀችው መቸም ቀጣፊዎች ፈሪዎች
ናቸው ሰር ፍራንሲዝም ግልጽ ያለ ነገር እንዳይናገር ጋብቻው በቅርቡ እንደሚሆን ደኅና ሆኖ በማይሰማ አነጋገር እያልጐመጐመ ነገራት "

እኅቷ ሊድያ ሻሎነር ባሏ ሲሞት በተወላት ገንዘብ እየተረዳች ሚስዝ ዌሪንግ
ተብላ ደኅና ኑሮ ትኖር ነበር" ልጆቹ የሙታን ልጆች ስለ ነበሩ እኅቷ ብላንሽ ሻሎነርንም እሷ ያዘቻት ብላንሽ ወደ ሠላሳ ዓመቷ መቃረቧን የሚጠቁሙ አንዳንድ ምልክቶች ይታዩባት ጀመር ዓመቶቹ ሳይሆኑ የማያቋርጡ የተስፋ እንቅፋቶችና
የሐሳብ ጭንቀት ዱካዎች ይታዩባት ጀመር " ጸጉሯ ሳሳ ፊቷ ምጥጥ ሙግግ አለ"
የሚያምረው የሰውነቷ ቅርጽ ጠፋ „ “ ኧረ ወዲያ ደሞ ይችን ነው የማገባ !
አለ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ለራሱ "

አሊሽ ሻሎነር የኻያ ዓመት ቆንጆ የነበረች ታናሽ እኅታቸው ለገና በዓል ልትጠይቃቸው መጣችና ሚስዝ ዌሪንግ ቤት ሰነበተች " በመልኳ ከትልቅ እህቷ ከብላንሽ ሻሎነር በጣም የላቀች ነበረች ገና አንዲት ፍሬ ልጅ ሳለች የተለያት ፍራንሲዝ ሌቪሰን አሁን እንደዚያ አምራና ዳብራ ሲያያት ጊዜ ከሷ ጋር ፍቅር ያዘው ፍቅርም ሲባል ወግ አለው እሱማ ልክ እንደ ጥላዋ እየተከተለ ደስ ደስ የሚሉ የፍቅር ቃላት በጆሮዋ እያንቆረቆረ ልቧን ከማረከ በኋላ ለጋብቻ ጠየቃት " ሳታቅማማ
እሺ አለችው " የጋብቻው ዝግጅት ወዲያው ተጀመረ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን
ዝግጅቱን አጣደፈው እሷም ቶሎ መጋባቱን አልጠላችውም "

ከተራ ጓደኝነት የተለየ በፍቅር በጋብቻ መተሳሰር ለሚባል ነገር ጭራሽ
እንደማያውቅ ነገራት በዚህ ረገድ የሰጣትን ተስፋና የገባላትን ቃል
ጭልጥ አድርጎ ካዳት "

መረጃ ማቅረብ አልቻለችም " ከሱ የተጻፈላት ቁራጭ ወረቀት ወይም አንድ
የፍቅር ቃል ሲተነፍስላት ሰማሁ የሚል የጠላትም ሆነ የወዳጅ ምስክር አልነበራትም እሱ በጣም ተጠንቅቆበታል " እሷም ራሷ ምስጢር የጠበቀች መስሏት ከፍራንሲስ ሌቪሰን ምንም 0ይነት ግንኙነት እንዳልነበራት ለእኀቷ አረጋግጣላት ነበር ስለዚህ ለመዳን ተስፋ በሌለው ሁኔታ በመስጠም ላይ ባለች መርከብ ላይ አንደ
👍14😁2
ተሳፌረች ሆና ተሰማት "
ነርር ግን ድርጊቱን ለአሊስ በመንገር አንድ ጊዜ ዕድሏን ለመሞከር ቆረጠች
ብላንሽ ሻሎነር የሰውየው መጥፎነት ግልጽ ሆኖ ታያት " የሱ ባልነት ለእኅቷ ምንም
እንደማይጠቅማት ዐወቀችው ከዚህ ጋብቻ ከሥቃይ በቀር ምንም እንደማይገኝበት ተረዳችው " ስለዚህ ቢቻላት አሊሲን ቃል ኪዳን ከማሰሯ በፊት ልታድናት ፈለገች " በርግጥ እሷ ልታግባው ነበር " ነገር ግን የሁለቱ ሁኔታ ይለያያል “ ብላ እሱን በመጠበቅ የአፍላነት ዘመኗን አሳልፋለች " ወዟ ጠፍቷል አበባዋ ረግፏል አሊስ ግን ምንም የማታውቅ ልጅ ናት

ቤተሰቡ ሁሉ ተኝቶ ጸጥ ካለ በኋላ ብላንሽ ወደ እኅቷ መኝታ ክፍል አመራች።
አሊስ ልብሷን ማውለቅገና አልጀመረችም " እግሮቿን ከእሳቱ መከላከያ ፍርግርግ
ላይ አሳርፋ ሰር ፍራንሲዝ የጻፈላትን የፍቅር ደብዳቤ በተመስጦ ስታነብ አገኘቻት
“ አሊስ አንድ ተረት ላጫውትሽ ነው የመጣሁት ” አለቻት ብላንሽ “ ትሰሚኛለሽ ?”

ቆይ ጥቂት ተይማ ዝም በይኝ ” አለችና አንብባ ጨረሰች “ እሺ ? ምን
አልሺኝ ብላንሽ ? ... አንድ ተረት አልሽኝ ?

ብላንሽ ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች ከብዙ ዓመት በፊት ሀብታቸው መጠነኛ ከሆነ ቤተሰብ የምትወለድ አንዲት ቆንጆ ልጅ ነበረች " አንድ በሀብቱ የሷ ብጤ የሆነ መኮንን ሲከታተላት ' ሲከታተላት ይቆይና በመጨረሻ በፍቅሩ ትያዛለች እንዳያገባት ሀብት አልነበረውም ስለዚህ ሀብት የሚያኙበትን ዘመን በተስፋ
እየጠበቁ መፋቀራቸውን በምስጢር ቀጠሉ " በተለይ እሷ ' እሱን ስትጠብቀው
ብዙ ዓመቶች ዐለፉ » በተስፋ ደከመች

መቸም አሊስ ... እንዴት ትወደው እንደ ነበር ልገልጽልሽ አልችልም "
ስለሱ ብዙ መጥፎ ነገሮች እየሰማችና እያወቀች እንኳን ልትተወው አልቻለችም ”

ይህቺ የምትያት ወጣት ሴት ማናት? አለች አሊስ አቋርጣ " ተረት ነው ወይስ እውነተኛ ታሪክ ብላንሽ

እውነተኛ ታሪክ ነው " እኔ ዐውቃታለሁ " ያን ሁሉ ዘመን እንድታፈቅረው
እያሽቃበጠ የሚወዳት እንዲመስላት እያታለለ ኖረ " በመጨረሻ በውርስ ከፍተኛ ሀብት አገኘ " የጋብቻቸው እንቅፋት የነበረው ድህነት ተወገደ ይህን ዕድል
ሲያገኝ ውጭ ነበር ወዳገሩ ተመልሶ መጣና ከልጂቱ ጋር የነበራቸው
የፍቅር ግንኝነት ታደሰ"
በመጠበቅ ብዛት መጠውለግ ጀምሮ የነበረው ልቧ እንደገና ሕይወት ዘራ አሁንም ጋብቻው የሚፈጸም አልመሰለውም እሷ ጠየቀችው በቅርቡ መጋባት እንደሚኖርባቸው ነገራት » እሷም በተሰፋ መኖር
ቀጠለች።

“ ቀጥይ ብላንሽ አለቻት አሊስ ታሪኩ ደስ አላትና እሷን እንደሚመለከት
አልጠረጠረችም



“እሺ እቀጥላለሁ“ አሊስ “” ይህን የመጨረሻ ተስፋ ከሰጣት በኋላ አንዲት ልጅ አየና “ ወደድኩሽ' ይላታል ያቺን ብዙ ዘመን በተስፋ ስትጠብቀው የኖረችውን ጥሎ ' አዲሲቱን ለጋብቻ ጠየቃት ከፊተኛይቱ ጋር የነበረው ረጂም የፍቅር ግንኙነት እየደጋገመ የገባላትን ቃል ኪዳን ሁሉ ጨርሶ ካደ።

“ እንዴት የሚያናድድ ነገር ነው ልጄ ? እናስ ተጋቡ ?
“ ሊጋቡ ነው " እንደዚህ ያለ ሰው ደስ ይልሻል ?

እኔ ! ” አለች አሊስ ስለ ተጠየቀች እንኳን የሆነ እየመሰላት አይመስለኝም

“ በይ እንግዲያው ሰውዬው ፍራንሲዝ ሌቪሰን ነው '
“ እንዴት እንደዚህ ደፍረሽ ትናገሪያለሽ ... ብላንሽ ? እውነት አይደለም ! ልጅቱ በድላው እንደሆነሳ ? ለመሆኑ ማን ነበረች ?

“ ምንም አላደረገችውም " ልጂቱም እኔ ነበርኩ ”

“ አሃ ገባኝ እሱ የወደደሽ እየመሰለሽ ስትጃጃይ መኖርሺንና እኔን ስለወደደ
ስሙን ልታጠፊው እንደምትችይ አጫውቶኛል ስትላት ስሜቷን መቆጣጠር
አልቻለችም " እንባዋ እንደ ጉድ እየወረደ ንግግሯን ቀጠለች ።“ አሊስ .. ሰማሽ
እቴ ? ኩራቴ ሁሉ ዐልፎበታል የኔ ፍላጎት አንቺን ለማዳን እንጂ ለማታለል አይደለም " አንቺ ወደዚህ እስክትጪ ድረስ እሱ የኔ እጮኛ ነበር "

አሊስ እኅቷ የነገረቻትን ባለመቀበሏ ብላንሽ ተበሳጨች » ስለ ሰውዬው ክፋት የሰማችውን ሁሉ ወይዘሮ ሳቤላ ካርይልን እንዴት እንዳታለላት ነገረቻት አሊስ እሳት ሆነችባት " በራሷ ላይ ስለ ደረሰው በደል አንድም ቃል ልትቀበላት አልፈለገችም " ስለ ሌላው ያለፈው ድርጊቱ ግን ምኗም እንዳይደል ነገረቻት "

በርግጥ አሊስ ሻሎነር እኅቷ እንደፀዚያ አድርጋ በስሜት እየተገፋች ስትነግራት
አምናት ነበር እሶ ግን ልቧ የተሰቀለው በጌትነቱ በሀብታምነቱ የተደላደለ ጥሩ ኑሮ ለመኖር በመጓጓት እንጂ እንደ እኅቷ እንደ ብላንሽ ፍቅር አልያዛትም " ስለዚህ እሱ የፈለገውን ያሀል ታሪክ ቢኖረው እሷ ብር ያለበት ትዳር በመያዟ ላይ ስላተኮረች ምንም ቢሆን እንዲያመልጣት አልፈለገችም " ብላንሽ ያለችውን ትበል የሆነችውን
ትሁን ብላ አሊስ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን አገባችው ስለዚህ እንደ ዘሩት ማጨድ የማይቀር ነውና ወይዘሮ አሊስ ሌቪሰን በሦስት ዓመት የጋብቻ ዘመኗ ከሰር ፍራን
ሲዝ ሌቪሰን የጠበቀችው የጥሩ ትዳር ተስፋ መሸከ።በሱ ላይ የነበራት እምነት ወደ ጥላቻና ንቀት ተለወጠ " እነሆ አሁን ወለሉን በእግሯ እየቆረቆረች ከሳሎን ተቀምጣ ትተከዛለች "

አንድ የሁለት ዓመት ልጅ ከወለሉ ላይ ይጫወታል “ እናቲቱ ፊቷን ስትቋጥር
ስትፈታ ከንፈሮቿን ስታጣምም ስታኮማትር አንዱን ስታነሣ ስትጥል በሐሳብ ዓለም ተውጣ ልጅዋን ልብ ብላ አላየችውም" ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ፍዝዝ ብሎ
ሲገባ ከያዛት ጥልቅ ሐሳብ ነቃችና በቁጣ አነጋገር ገንዘብ እፈልጋለሁ አለችው

“ ባግኝ እኔም እፈልግ ነበር ” አላት "

በመልሱ ተናደደችና ወለሉን በቁጣ ረገጠችው " አንገቷን በብስጭትና በንቀት ለጋችው „ “ አሁን ገንዘብ ያስፈልገኛል ነው የምልህ በግድ ማግኘት አለብኝ " ትናንትናም ገንዘብ እፈልግ እደ ነበር ነግሬሃለው ሁል ጊዜ አንድም ቤሳ ለላገኝ ጊዜውን እንዲህ ሁኘ የምግፋው ይመስልሃል?

“ አንቺስ ብትሆኚ እንደዚህ መናደዱ ጥቅም የሚስጥሽ ይመስልሻል ? ሳምንት ሙሉ ገንዘብ ገንዘብ ስትይኝ ምንም እንደሌለኝ አልነገርኩሽም አሁንም
ምንም የለኝም እኔን ገንዘብ አምጣ ማለት ይህን ሕፃን ግዘንብ ስጠኝ እንደ ማለት ነው "

“ ምነው ይህ ሕፃን ካንተ ባልተወለደ ” አለች "

በዚህ አነጋገሯ በገጽታዋና በድምጿ ያሳየችው ከፍተኛ ንቀት ሰር ፍራንሲዝን
በጣም አናደደው አጸፋውን ሊመልስላት ሲል አንድ አሽከር ገባ "

“ ይቅርታ እለምናለሁ ሰር ፍራንዝ " ያ ብራወን የሚባለው ሰውዬ በግድ
ጥሶ ከመተላለፊያው ገባና

" ላነጋግረው አልችልም አላነጋግረውም " ብሎ የሚያስፈራ ቃል ሰንዝሮ
የተከተለው ይመስል ወደ ወድያኛው ጥግ ተንደረደረ " ሲያዩት አእምሮውን የሳተ
ይመስል ነበር

እሱን እንኳን በብዙ ትግል አስወጣነው " ግን እሱን ለማስወጣት በሩን
ከፈት አድርገን ስንጨቃጨቅ ሚስተር ረዲት ሰተት ብሎ ዐልፎ ከመጻሕፍት ቤቱ ገባ " ታመውም ሆነ በጤናዎ እርስዎን ሳያይ ንቅንቅ እንደማይል ምሎ ቁጭ
ብሏል "

ትንሽ አሰበና ጥቂት የምሬት ቃላት አጉቶምቱሞ ወጣ አሽከሩም ተከተለው
ወይዘሮ ሌቪሰን ልጁዋን አነሣች "

የኔ ወለላ ” አለችው ፊቷን ከሚሞቀው አንገቱ ቀብራ - “ አንተን እንዳያስቀርብኝ ፈራሁ እንጅ ጥየው በሔድኩ ነበር ”

ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን የባለዕዳዎቹን ፊት ማየት ቸገረውነ በጣም መታመሙን አስወርቶ ከሎርድ ሔድተሉት ቢሮም እንዲሰማ አድርጎ ለሦስት ቀኖች ያህል ተኛ ያን ለት ጧት ብቻ ሁኔታው እንዶ ነገሩ ተጠጋገነና ተነሥቶ ወጥቶ ነበር"
👍14😁3
አንዴ ምን መዓት ነው የሚያወሩብህ ባአክህ ? አንተ እንኳን ልትታመም
ወዝህም ልውጥ አላለም "
ዛሬ በጣም ይሻለኛል ” አለ ሰር ፍራንሲዝ እየሳለ"

“ አንዴት በዚህ ጊዜ ታደፍጣለህ ? ከደጅህ ስንከራተት ሰነበትኩ " ዛሬማ
ቤቱን አፈንድቸ ከፍርስራሹ ጋር አብሬ ልገባ ምንም አልቀረኝ " ለመሆኑ አንተና
እመቤቲቱ ሁለት ሁናችኋል እንዴ ?

ሁለት ? አለ ሰር ፍራንሲዝ "

ትናንት ከሠረገላዋ ስትሳፈር አግኝቻት ስለ ጤንነትህ ብጠይቃት ስላንተም
ሆነ ስል በሽታህ እንደማታውቅ ነገረችኝ " "

እሷ እኮ አንዳንድ ጊዜ ወፈፍ ያደርጋታል " አሁን እኔን ለመፈለግ ምን አስቸኳይ ነገር ገጠመህ?
ሒድተሉት የለም ስለዚያ ምንም የሚሠራ ነገር የለም

"ከዚያ ምንም የሚሰራ አይኑር

ፈፈ እንጂ ከሌላ ቦታ ሞልቷል የአትሊ ወንበር
እኮ በገብያ ላይ ነው።

"እና?".

“ ከምስት አራት ቀን በፌት ወደዚያው መዝለቅ ነበረብህ " ምንም ቢሆን መግባት አለብህ"

“ አልገባም ዌስት ሊን መወከል ደስ አይለኝም : "

“ ዌስትሊን ነው የማይስማማህ ? ለርስትህ ለንብረትህ ቅርብ ነው " ከሱ የተመቸ ቦታ የለም
እንዲያውም

“ ምንም ቢቀርብ እኔ ለዌስት ሊን አልወዳደርም » ”
ሔድተሉት ዛሬ ጧት መጥቶ ነበር ” አለ መረዲት »

“ ሔድተሉን ምን አመጣው

"እየነገርኩህ ... ሌቪሰን ስንት ፍትጊያ አለ መሰለህ " ሔድተሉት ቀድም ብለህ ወደ ዌስትሊን የዘለክ መስሎት ነበር " ሲያጣህ ጊዜ በጣም ተናደደ
በተጨማሪ የምናስቆጥረው እያንዳንዱ የድምፅ ወረቀት በመጠኑ ልክ ወርቅ የሚያስገኝ ነው አሁንም ጊዜ ሳታሳልፍ መጀመር አለብሀ ... ሌቪሰን ”

"አልሔድም”

ጥሩ ተወው ቶርንቶን ለዌስ ትሊን ይወዳደራል። ከሔድተሉት ዘንድ የታሰበልህን ቦታም እሱ ይወስደዋል

“ ሔድትሉት ይኽንኑ ለመንገር ነው ወዲህ የላከህ ?”

“ አዎን ፤እሱኮ ሥራዬ ብሎ ከልቡ ተነሥቶበታል " መቸም እንደሱ ያለ ቅን ሰው አይቸ አላውቅም "

ሰር ፍራንሲዝ በነገሩ ማሰብ ጀመረ አማራጭ ቢያገኝ ኖሮ ዌስትሊንን ወክሎ
ከመቅረብ የሲኦል እንደራሌ ለመሆን ቢወዳደር ይመርጥ ነበር " አሁን ግን ከሚኒስትሩ ከሔድተሉት ዘንድ የታሰበለትን የሥራ ቦታ ዐይኑ እያየ እንዲያመልጠው ካደረገ ደግሞ እንደማይነሣ ሆኖ ይወድቃል " ስለዚህ ወደ ፓርላማ ጠጋ ማለቱ
ከብዙ ፈተና ያድነዋል ።
“ወደ ዌስት ሊን ብቅ ለማለት የጠላህበት ምክንያት ይገባኛል ” አለው ሚስተር መረዲት “ በዚያ .. ባልሳሳት በታወቀው ሥራህ ምክንያት ይመስለኛል "
ግን ከግል ስሜት የሕዝብ ፍላጎት መቅደም ስለ አለበት ' አሁንም ቶሎ መጀመር አለብህ። ሔድተሉትን ያስቆጣውም ቀደም ብለህ ብትገባ ኖሮ ያለ ምንም ተቀናቃኝ ታልፍ ስለ ነበር ነው " አሁን ግን ውድድር ይኖራል

ሰር ፍራንሲዝ ቀና ብሎ አየውና “ ውድድር ?ገንዘቡን ማን ሊችለው ነው?''

ኤድያ ! የገንዘብ እጥረት መሰናክል እንዲፈጥር አናደርግም " ለመሆኑ ተወዳዳሪው ሆኖ የሚቀርበውን ሰው ዐውቀኸዋል ?”

የለም አለው በግድ የለሽነት "
“ ካርላይል ”
“ ካርላይል! ” ብሎ ጮኸ። “ እሱን ልቋቋመው አልችልም
“ አማራጭ እኮ አለን ካልቻልክ ቶርንቶን ይገባል "
“ ምንም ዕድል ላይኖረኝ መሞከር አልፈልግም » እሱ ከገባ ዌስትሊን አይመርጠኝም " የሆነ ቢሆን ዌስት ሊን እኔን የሚፈልገኝ አይመስለኝም "

“ አንተ ደሞ ዝም ብለህ ነው እዚያ ያለንን ጉልበት ታውቃለህ " አትሊን
ያስቀመጠው መንግሥት ነበር ። አንተንም ልክ እንደሱ ብድግ አድርጎ ያስቀምጥሃል ። ስለዚህ እሺ ወይ እምቢ በል ሌቪሰን " "
“ እሺ ” አለ ሌቪሰን "

ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ለአንድ ሰዓት ያህል ወደፊቱ ገሠገሠ ወደ ዌስት ሊን
ሊሔድ ያሰበውን ለውጦ ወደ ስኮትላንድ ያርድ አመራ ከዚያ በኋላ አንድ ሰዓት
ባልሞላ ጊዜ ውስጥ “ "ምስጢር " የሚል ምልክት የተደረጎበት የሚከተለው ቴሌግራም ከዋናው መምሪያ ለዌስት ሊን ፖሊስ አዛዥ ደረሰው

"ኦትዌይ ቤተል ዌስት ሊን ነው? ካልሆነ የት ነው ? ወደዚያ መቸ ይመለሳል ?

ወድያውኑ ኦትዌይ ቤተል ዌስት ሊን ውስጥ የለም። ኖርዌይ ነው ተብሎ ይገመታል መምጫው አልታወቀም የሚል መልስ ተላከ „

አሊስ ሌቪስን ከሚነፍሰው ወሬ ጥቂት ሰምታ ነበር " ሰር ፍራንሲዝ ለጥቂት
ቀኖች ወደ አገር ቤት እንደሚሔድ ለደንቡ ያሀል ሊነግራት ሲሔድ እሳት
ሆነችና ዞረችበት።

“ ትንሽ የኃፍረት ሰሜት ቢኖርህ ኖሮ ልታደርገው ያሰብከውን ለመፈጸም
ወደምትሔድት ቦታ ከመሔድ ይልቅ ራስህን በጥይት ብትገድል ትመርጥ ነበር ”

በሷና በባሏ መካከል ያለው ጠብ እመጨረሻው ደርሷል " ጥላቻውን ከጊዜ
ጊዜ ያከረረው ባያስመርራትና ምክንያት ባይሆናት እንዲህ ደፍራ አትናገረውም ነበር ። ፊቱን ኮስተር አድሮጎ ቁልቁል ተመለከታት "

“የምትሔድበትን ዐውቀዋለሁ ። የሚስተር ካርላይል ተወዳዳሪ ሆነህ ለመቅረብ ነው ኃፍረት የሚያስረሳ ጣጣቴ ካልተተኮስክ እንዲህ ካለው ድፍረት አትገባም ነበር ማንም ሰው ቢሆን ካንተ በቀር አንተ እንደ በደልከው አድርጎ የበደለውን ሰው ከሚያይ መሬት ተከፍታ ብትውጠው ይመርጥ ነበር

“ ምላስሽን አሳርፊ ” አለ ሰር ፍራንሲዝ "

“ ምላሴን ምን ጊዜም አሳርፌው ነው የኖርኩት አንተ ልታሳብደኝ ምንም
ባይቀርህም ባሌ ስለሆንክ በደልህን ችዬ አሳርፌው ኖሬአለሁ " ከእንግዲህ ወዲያ አላሳርፈውም » ጧትም ማታም ጸሎቴ አንድ ነዋ !ካንተ በሕጋዊ መንገድ የምለያይበትን መን?ድ እንዳገኝ ብቻ !ደሞም አገኘዋለሁ !! ”

hዚህ ሁሉ ከብላንሽ ጋር ባትለያዪኝ ኖሮ ይሻልሽ ነበር ” አላት በንቀት
ዐይን ወደሷ እየተመለከተ "
“ ይኸም ቢሆን ያንተ ሌብነት ነው ...ገባህ ?ለካ ዐውቀህ ኖሯል "
ቁጭ አለችና ንዴቷን ለማብረድ ከልቧ እየታገለች ምንጣፉን በእግሯ ትጠበጥብ ጀመር ።
አሁንም ከሚስተር ካርላይል ጋር ለመግጠም ከመነሣትህ በፊት ትንሽ
ተግ ብለህ እንድታስብበት እመክርሃለሁ "

“ ኧረ ካርላይል ላንቺ ምንሽ ነው አታውቂው ”

“ የተከበረ ትክክለኛ ሰው መሆኑን በዝናው ዐውቀዋለሁ " በጓደኞቹ ዘንድ የተወደዶ በትልቁ በትንሹ የተከበረ ሰው ነው " ሕዝበ አዳም ስለ ሚስተር ካርላይል ምን እንደሚያስብ ለማወቅ ያጎትህን ሚስት ጠይቃት ለምሳሌ የሚሆኑ ፍጹም ተቃራኒ ባሕሪ ያላቸው ሁለት ሰዎች ይቅረቡ ቢባል አንተና እሱ ናችሁ ”

ባላጋራዬ ሌላ ሰው ቢሆን ኖሮ ብተወውም ግድ የለኝም ነበር " የኔ ተወዳዳሬ
እሱ መሆኑን ሳስበው ብቻ እስከ መጨረሻው እንድጋጠመው ይገፋፋኛል « እፋለመዋለሁ : አሸንፈዋለሁ ” አላት ።

“ ይልቅ ለሱ ያሰብከው በራስህ እንዳይደርስብህ ተጠንቀቅ ” አለችው አሊስ
ቪሰን „ “ ዕድል ዘለዓለም ለከስካሶችን እንደ ጠበቀች አትኖርም " '

ወይጅ እባክሽን ... ዕድሌን እሞከራለሁ ” ብሎ አንጓጠጣት »....

💫ይቀጥላል💫
👍22
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


ከሳውዝ ሃምፕተን ወደ ፎየንስ (አየርላንድ)


ባቡሩ ጫካውን እየሰነጠቀ ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ሲያመሩ የማርጋሬት
ኦክሰንፎርድ እህት ኤልሳቤት አንድ አስደንጋጭ ነገር ለእህቷ ነገረቻት
የኦክስንፎርድ ቤተሰቦች በአየር በራሪው በተያዘላቸው ልዩ ፉርጎ ውስጥ ተቀምጠዋል፡ ማርጋሬት ፉርጎው መጨረሻ ላይ ተቀምጣ በመስኮት ውጭ ውጩን ታያለች፡፡ አገሯን በችግሯ ጊዜ ጥላት መሄዷ ክፉኛ ቢያበሳጫትም አሜሪካ የመሄዷ ነገር ደግሞ በሌላ በኩል ደስታ አጭሮባታል፡
እህቷ ኤልሳቤት ከቤተሰቡ ነጠል ብላ ወደ ማርጋሬት መጣችና
‹‹እወድሻለሁ ማጊ›› አለቻት።
ማርጋሬት በእህቷ አባባል ልቧ ተነካ፡ በዓለም ላይ የሚካሄደውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነትና ጦርነት መረዳት ከጀመሩ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተቃራኒ አቋም በመያዝ በነገር መጠዛጠዛቸው አራርቋቸው ነበር።ማርጋሬት ይህ የአስተሳሰብ ልዩነት ከእህቷ ስለነጠላት ታዝን ነበር
እንደገና ጓደኛ ቢሆኑ በወደደች፡፡ ‹‹እኔም እወድሻለሁ እታለም›› አለቻትና እቅፍ አደረገቻት፡፡

ትንሽ ቆየችና ‹‹አሜሪካ ከእናንተ ጋር አልሄድም›› አለች ኤልሳቤት ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ደነገጠች ‹‹እንዴት እባክሽ?››

‹‹ለእማማና አባባ እንደማልሄድ በቀጥታ ልነግራቸው ነው፤ ሃያ አንድ
ዓመት ስለሆነኝ ሊያስገድዱኝ አይችሉም››
ማርጋሬት የእህቷ ውሳኔ ትክክል ይሁን አይሁን አላወቀችም ‹‹የት ነው የምትሄጂው?››

‹‹ወደ ጀርመን››

‹‹ሊሆን አይችልም ኤልሲ›› አለች ማርጋሬት በፍርሃት፡፡ ‹‹ትሞቻለሽ››
‹ሶሻሊስቶች ብቻ አይደሉም ላመኑበት ዓላማ የሚሰዉት››

‹‹ግን ለፋሺዝም ብለሽ?››

‹‹ለፋሺዝም ብዬ አይደለም›› አለች
ኤልሳቤት፡፡ ዓይኗ ላይ እንግዳ አመለካከት ይነበባል፡፡ ‹‹በጥቁሮችና በክልሶች የመዋጥ አደጋ ላንዣበበበት ንፁህ ነጭ ዘር ብዬ ነው፡፡››

ማርጋሬትን ያበሳጫት እህቷን ማጣቷ ብቻ አይደለም፡፡ በዚህ ሰይጣናዊ ዓላማ ከእህቷ መለየቷ ነው ያሳዘናት፡ ሆኖም የቀድሞውን ጊዜ የፖለቲካ ጭቅጭቃቸውን አሁን ማንሳት አልፈለገችም፡ አሁን ያስጨነቃት ጉዳይ
የእህቷ ደህንነት ነው፡፡

‹‹እንዴት ትኖሪያለሽ ጀርመን ውስጥ?›› ስትል ጠየቀቻት

‹‹ገንዘብ አለኝ››

ማርጋሬት አያታቸው ሲሞቱ ያወረሷቸውን ገንዘብ አስታወስች፡፡ ገንዘቡ
ብዙ ባይሆንም ያኖራል፡
ማርጋሬት አንድ ነገር በሃሳቧ መጣ፡፡ ‹‹ሻንጣሽ ወደ ኒውዮርክ ተልኳል እኮ››

‹‹ኒውዮርክ የተላኩት ሻንጣዎች የተሞሉት በጠረጴዛ ልብስ ነው::
ልብሴን በሌላ ሻንጣ ሞልቼ ሰኞ ዕለት ልኬያለሁ።››

ማርጋሬት በእህቷ ብልህነት በእጅጉ ተደነቀች፡፡ ኤልሳቤት ሁሉንም
ነገር አቅዳ በትክክልና በምስጢር አከናውናለች፡፡ እሷ ከዚህ ቀደም ያደረገችው የማምለጥ ሙከራ እህቷ ካደረገችው ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል የተውሸለሸለና በሚገባ ያልታቀደ እንደሆነ ተረዳች፡፡ እኔ ምግብ አልበላም እያልኩ ስተክዝ እሷ ግን ለጉዞዋ ቦታ ለመያዝና ዕቃ ለመላክ ትሯሯጥ ነበር፡
እህቷ የያዘችው የፖለቲካ አስተሳሰብ የተሳሳተ ቢሆንም ከእሷ በተሻለ
ሁኔታ መንቀሳቀስ መቻሏ የዝቅተኝነት ስሜት ፈጠረባት፡፡ ወዲያው ደግሞ ከእህቷ ጋር እስከ ወዲያኛው መለያየቷ ገባት፡፡ ምንም እንኳን ብዙም ባይቀራረቡም አብረው አድገዋል፡ ብዙ ጊዜ በሃሳብ ሲከራከሩና አንዷ ያንዷን አስተሳሰብ ስታጣምም ቢኖሩም ማርጋሬት ይሄም ሊቀርባት ነው: በችግር ጊዜ ይረዳዱ ነበር፡፡ ኤልሳቤት የወር አበባዋ በመጣ ቁጥር ህመም ሲሰማት ማርጋሬት አልጋ ላይ አስተኝታት የሚጠጣ ትኩስ ነገርና የሚነበብ መጽሔት ታመጣላታለች፡ የማርጋሬት ፍቅረኛ ኢያን ሲሞት መሪር ሀዘን ላይ ወድቃ የነበረ ጊዜ ምንም እንኳን ኢያንን ባትወደውም ታጽናናት ነበር
ማርጋሬት ዓይኗ በእምባ ተሞልቶ ‹‹ትተሽኝ ልትሄጂ ነው?›› አለቻት እህቷን፡፡

‹‹ግርግር አታብዢ›› አለች ኤልሳቤት ‹‹ገና አልነገርኳቸውም››
ማርጋሬት መነፋረቋን አቆመችና ‹‹መቼ ልትነግሪያቸው ነው?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹ መጨረሻው ደቂቃ ላይ፤ አንቺም እስከዚያው አታስነቂ››
‹‹እሺ እታለም›› ብላ የግድ ፈገግታ አሳየቻት፡
«አይ ማርጊ›› አለች ኤልሳቤት እምባ እየተናነቃት፡፡ ሳጓን ዋጥ
አደረገችና ‹‹እኔ እስከምረጋጋ ድረስ ሂጂና አዋሪያቸው::››

ማርጋሬት የእህቷን እጅ ጨበጥ አደረገችና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች
እናት የፋሽን መጽሔት ያገላብጡና የሚነገር ነገር ሲያገኙ ለአባት ያነባሉ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ደግሞ ለማዳመጥ ፍላጎት የላቸውም፡፡ እናት
ግን ተስፋ ሳይቆርጡ ያነባሉ፡፡ ሎርዱ የንቀት ፊት ይነበብባቸዋል፡ ትልቋ
ልጃቸው የደገሰችላቸውን አያውቁም፡

ለማርጋሬት መንገር አንድ ነገር ነው፤ ለአባቷ መንገር ግን ሌላ ነገር.ነው፡፡ ኤልሳቤት በመጨረሻ ደቂቃ ለመንገር ድፍረት ታጣ ይሆናል፡፡
ማርጋሬትም ከዚህ ቀደም ከአባቷ ጋር እሰጥ አገባ ልትገጥም ነበር በኋላ
እጇን ሰጠች እንጂ፡

ኤልሳቤት ወንድ ወጥቷት ለአባቷ ከነገረች ወደ ጀርመን መሄዷ
የተረጋገጠ ላይሆን ይችላል፡ ሃያ አንድ አመት የሞላትና ገንዘብ ያላት
ብትሆንም እሳቸው ግን አቋመ ፅኑና ያሻቸውን ከማድረግ የማይመለሱ ሰው ናቸው፡ ኤልሳቤት ከፈቃዳቸው እንዳትወጣ ማቆም የሚችሉ ከሆነ
እንደሚያደርጉት ማርጋሬት አትጠራጠርም: በመርህ ደረጃ ኤልሳቤት
የፋሺስት ፓርቲን ብትቀላቀል አይጠሉም፤ ነገር ግን ትዕዛዛቸውን ጥሳና ቤተሰቡን ትታ ብትሄድ ግሥላ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡

ማርጋሬት ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ከአባቷ ጋር ተጣልታለች። ያለሳቸው
ፈቃድ መኪና መንዳት በተማረች ጊዜ ተቆጥተዋታል፡ የእርግዝና መከላከያ ፈር ቀዳጅ የሆነችው የሜሪ ስቶፕስን ንግግር ለመስማት መሄዷን ያወቁ ጊዜ.ፊታቸው በንዴት በርበሬ መስሎ ነበር፡ አባቷ ሳያውቁ ካላደረገች በስተቀር ፊት ለፊት ተጋፍጣ እንደማይሆንላት ታውቃለች፡፡ የአስራ ስድስት ዓመት ኮረዳ ሳለች ከአጎቷ ልጅ ጓደኞች ጋር ትምህርት ቤት ሲዘጋ ሽርሽር ልሂድ
ብላ ስትጠይቃቸው አልፈቀዱላትም፡፡ ያልፈቀዱላት ከሴቶችም ከወንዶችም.እንዳትቀላቀል ነው: ትልቁ ጦርነት የነበረው ትምህርት ቤት ልሂድ ያለች
ጊዜ ነበር፡ ትምህርት ቤት ለመግባት እንዲፈቀድላት ብትለምንም፣ ብታለቅስም ወይም ብታኮርፍም አባት ጆሮ ዳባ ልበስ አሉ፡ ‹‹ትምህርት ለሴቶች ምንም አያደርግላቸውም ሴቶች ቤት ውስጥ አድገው ባል
አግብተው መቀመጥ ነው ያለባቸው›› ነበር ያሏት፡፡

ማርጋሬት እረፍት አጣች፡ አንድ ነገር አገኝ ብላ ተነሳችና ፉርጎው
ውስጥ ተንጎራደደች፡ የሰማይ በራሪው ጀልባ ተሳፋሪዎች ሲታዩ ገሚሶቹ
የተከፉ ከፊሎቹ የተደሰቱ ይመስላሉ፡፡

ከተሳፋሪዎቹ መካከል አንዲት በዓለም የታወቀች አሜሪካዊት ኮከብ የፊልም ተዋናይ ስላለች ሁሉም ስለእሷ በሹክሹክታ ያወራል፡ ሉሉ ቤል ትባላለች፡ ፔርሲ ከሷ ጋር ቁጭ ብሎ ልክ ረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቁ ሁሉ
ያወራታል፡ ማርጋሬት ከተዋናይዋ ጋር ማውራት በወደደች፤ ነገር ግን
ዓይኗን በጨው አጥባ ሄዳ ልታወራት አልደፈረችም፡፡ ፔርሊ ዓይን ቀቅሎ
የበላ ነው፡፡

ሉሉ ቤል በፊልም ስትታይ ወጣት ብትመስልም በአካል ሲያይዋት ግን ያረጀች ትመስላለች፡ አንድ አርባ ዓመት ሳይሆናት አይቀርም ስትል ማርጋሬት አሰበች ምንም እንኳን ፊልሞቿ ላይ ወጣቶችንና በቅርብ ያገቡ
ሴቶች ገጸ ባህሪ ወክላ ብትጫወትም፡፡ ምንም ሆነ ምን አሁንም ውብ
ሽንቃጣና ተግባቢ ናት፡፡

ማርጋሬት ሉሉን ስታይ ፈገግ አለች፡፡ ሉሉም ‹‹ታናሽ ወንድምሽ ያጫውተኛል›› አለች፡፡
👍17🥰2
‹‹መቼም እንዳልረበሸሽ ነው›› ስትል መለሰች ማርጋሬት
‹‹በፍጹም ራሼል ፊሽቤን ስለተባሉት አያታችሁ እያጫወተኝ ነው››
ማርጋሬት በፔርሲ አድራጎት አፈረች፡፡ ለእንግዳ ሰው ውሽት መንገር ብልግና ነው ብላው ነበር፡፡ ምን ይሆን ያላት ለዚች ምስኪን ሴት?› በፔርሊ አድራጎት ብትናደድም ከእናቷ እንደተማረችው የውሸት ፈገግታ ለሉሉ ብልጭ አደረገችላትና አልፋ ሄደች
ፔርሲ ሁልጊዜ ሸር መስራት ይወዳል፡፡ አሁን አሁንማ ደፋር እየሆነ መጥቷል፡ ቁመቱ እየጨመረ ድምጹ እየጎረነነ ነው፡ አሁንም አባቱን የሚፈራ ሲሆን ማርጋሬት ካገዘችው ግን መጋፈጡ አይቀርም፡ ሆኖም ፔርሲ አባቱን ፊት ለፊት የሚቃወምበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ አባታቸው
ሴት ልጆቹን ሲያስፈራሩ ወንድ ልጃቸውንስ ያስፈራሩ ይሆን?› ማርጋሬት
እርግጠኛ አይደለችም::

ፉርጎው መጨረሻ ማርጋሬት በቅጡ
የማታውቃቸው ሰው
ተቀምጠዋል፡ ሰውየው ቁመተ ሎጋ፣ በትኩረት የሚመለከቱ፣ እንደ ቋንጣ
የደረቁ፣ የለበሱት ልብስ ተራና ጨምዳዳ በመሆኑ እዚህ ግሩም ልብስ
በለበሱና ሰውነታቸው ሞላ ባለ ሰዎች መካከል ሲታዩ አለ ቦታቸው የገቡ
መሆናቸው ያስታውቅባቸዋል፡ ፀጉራቸውን ባጭር የተከረከሙ ሲሆን
ሲያዩዋቸው የተጨነቁና ድንጉጥ ይመስላሉ፡፡

ማርጋሬት ሰውየው ላይ ዓይኗ ሲያርፍ እሳቸውም አይዋትና አስታወሰቻቸው፡፡ በአካል አይታቸው ባታውቅም ጋዜጣ ላይ ፎቶግራፋቸውን
አይታለች፡፡ ካርል ሀርትማን ይባላሉ፡ የጀርመን ሶሻሊስት አስተሳስብ
አራማጅና ሳይንቲስት ናቸው፡ እንደ ወንድሟ ደፈር አለችና ከሃርትማ ፊት ለፊት ተቀምጣ ራሷን አስተዋውቃ ወግ ጫረች፡ ሃርትማን ለረጅም ጊዜ የሂትለር ተቃዋሚ በመሆናቸው እንደ ማርጋሬት ባሉ ወጣቶች ዘንድ እንደ ጀግና ይቆጠራሉ፡

‹‹ለዓመት ያህል
የደረሱበት ሲጠፋ ሁሉም
ሰው ክፉ ነገር አግኝትዎታል ብሎ ገምቶ ነበር›› አለች፡ ማርጋሬት ከጀርመን ጠፍተው የሄዱ መስሏት ነበር እንደዛ ከሰውነት ጎዳና ወጥተው ሲታዩ ከገሃነም
ያመለጠ ሰው ነው የሚመስሉት፡፡

የቁም እስር ላይ ብቆይም የምርምር ስራዬን ግን ቀጥዬ ነበር››
‹‹ከዚያስ?››

‹‹አገሬን ጥዬ ወጣሁ›› አሉና አጠገባቸው የተቀመጠውን
አስተዋወቋት፡፡ ‹‹ጓደኛዬን ባሮን ጋቦንን ታውቂዋለሽ?›› አሏት፡፡
ማርጋሬት ባሮኑን በዝና ታውቃቸዋለች፡ ፊሊፕ ጋቦን ፈረንሳዊ የባንክ ባለቤት ሲሆኑ ጽዮናዊነትን ለማራመድ ሀብታቸውን ስለሚያፈሱ በእንግሊዝ
መንግሥት ዘንድ እጅግ የተጠሉ ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜያቸውን በዓለም እየዞሩ አገሮች ከናዚ ጭቆና የሚያመልጡ ይሁዳውያንን በአገራቸው እንዲያስጠልሏቸው ይማጸናሉ፡፡ ማርጋሬት ለሀርትማን
የአይሮፕላን ቲኬት ባሮኑ
እንደከፈሉላቸው ጠረጠረች፡፡ የጋቦንን እጅ ጨበጠችና ትኩረቷን ወደ ሳይንቲስቱ አደረገች፡፡

‹‹ከአገር ወጥተው መሄድዎ በጋዜጣ ላይ አልወጣም››

‹ካርል ከአውሮፓ በደህና እስኪወጣ በምስጢር ይዘነው ነበር›› አሉ ባሮን፡፡

ከባሮኑ አባባል ናዚዎች ሰውየውን እየፈለጓቸው መሆኑን አረጋገጠች፡
‹‹አሜሪካ ውስጥ ታዲያ ምን ሊሰሩ ነው?››
‹‹አሜሪካ ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በፊዚክስ የትምህርት ዘርፍ
ውስጥ ስራ እጀምራለሁ፡፡›› ፊታቸውን ቅጭም አደረጉትና ‹‹አገሬን መልቀቅ አልፈልግም ነበር፡፡ ነገር ግን እዚያ ብቆይ ደግሞ ለናዚ ድል አስተዋጽኦ ማድረጌ አይቀርም ነበር፡፡››

ማርጋሬት ሃርትማን ሳይንቲስት መሆናቸውን ከማወቋ በስተቀር ስለ
ስራቸው ምንም አታውቅም፡፡ እሷን የሚስባት የፖለቲካ አቋማቸው ነበር፡ ‹‹ወኔዎ በብዙ ሰዎች ዘንድ እንደ ምሳሌ ይቆጠር ነበር›› አለች፡፡ ሃርትማን ንግግር ማድረግ በሚፈቀድበት ጊዜ ያደርጓቸው የነበሩትን ንግግሮች
የሚተረጉምላት ኢያን ነበር፡፡ ሳይንቲስቱ የማርጋሬትን ሙገሳ ብዙም ስላልወደዱት ንግግሯን አቋረጡና ‹‹ብቀጥል ኖሮ ደስ ባለኝ›› አሉ ‹‹በጅምር ትቼው መምጣቴ ይቆጨኛል፡››
ባሮን ጋቦንም ጣልቃ ገቡና ‹‹አልተውከውም እኮ ማድረግ ያለብህን ነው ያደረግኸው›› አሏቸው፡፡

ሃርትማን ጋቦን ያሉትን በመቀበል ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡ በኋላም የፓን
አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኛ ምሳ ተዘጋጅቷል የሚቀጥለው
መመገቢያ ፉርጎ ሂዱና ቦታ ቦታችሁን ያዙ›› አለ፡፡

‹‹እንገናኛለን›› አሉ ሃርትማን ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግ ብለው ‹‹ከዚህ በኋላ ሶስት ሺህ ኪ.ሜ ይቀረናል፡››

ማርጋሬት ምግብ መመገቢያ ክፍል ሄዳ ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀላቀለች:
እናትና አባት በአንድ በኩል ሶስቱ ልጆች ደግሞ በሌላ በኩል ተቀምጠዋል ፔርሲ እህቶቹ መካከል ተቀምጧል፡፡ማርጋሬት እህቷን የጎንዮሽ ታያታለች፡፡ መች ይሆን ያንን የቦምብ ናዳ የምታወርደው?

ኤልሳቤት አንድም ቃል ሳትተነፍስ በመስኮት ውጭ ውጪውን
ታያለች፡፡ ማርጋሬት ደግሞ በጭንቀት ትቁነጠነጣለች፡፡ እናት አንድ ችግር እንዳለ ጠርጥረው ኖሮ ‹‹ልጆች ምን ሆናችኋል?›› ሲሉ ጠየቁ።
ማርጋሬት ዝም ስትል ኤልሳቤት የሞት ሞቷን አንድ ነገር
ልነግራችሁ እፈልጋለሁ›› አለች፡

‹‹ምንድነው የኔ ማር›› አሉ እናት፡
ማርጋሬት በጭንቀት ምራቋን ዋጠች፡፡
‹‹አሜሪካ ከእናንተ ጋር አልሄድም›› አለች ኤልሳቤት።
‹‹ምንድነው የምትቀባጥሪው?›› አሉ አባት የሰሙትን ማመን
አቅቷቸው ‹‹ወደሽ ነው ትሄጃለሽ››
‹‹ከእናንተ ጋር አይሮፕላን ላይ አልሳፈርም›› አለች ኤልሳቤት ፈርጠም ብላ፡ ማርጋሬት
የእህቷን ፊት አነበበች ኤልሳቤት ስትናገር ድምጿ ባይንቀጠቀጥም
ፊቷ በጭንቀት መወጠሯን ያሳብቅባታል፡ ማርጋሬት ይህን
ስታይ ለእህቷ አዘነችላት፡፡

እናትም ቀበል አድርገው ‹‹ጅል አትሁኚ አልሲ አባትሽ ትኬት
ገዝቷል›› አሉ፡፡

ፔርሲም ጣልቃ ገባና ‹ካልሄድሽ ገንዘቡን ተመላሽ እናደርጋለን›› አለ
በዘወትር ቀልደኛነቱ፡፡

‹‹ዝም በል አንተ ጅል›› አሉ አባት ተቆጥተው፡
ኤልሳቤትም ‹‹አባባ መቼም በግድ ልትወስደኝ አትችልም፤ አየር
መንገዱም እኔን እየደበደብክ እንድትወስድ አይፈቅድልህም››
‹ኤልሳቤት እንዴት ዘዴኛ ነች? አለች ማርጋሬት በሆዷ አባቷን
በድንገት ምንም ሳያስቡት ምንም ማድረግ በማይችሉበት ጊዜ ያዘቻቸው እሷን በግድ አይሮፕላኑ ውስጥ ማሳፈር እንደማይችሉ ሁሉ ከእሷም ጋለመደራደር ሲሉ ወደ ኋላ መቅረት እንደማይችሉ አውቃለች አባቷ የፋሺስት ፓርቲ አባል በመሆናቸው የእንግሊዝ ፖሊሶች እያደኗቸው ነው።

የምሯን መሆንዋን ቢገነዘቡም አባት ገና አልተረቱም፡፡ ማንኪያቸው
ጣል አደረጉና ‹‹ወደኋላ ቀርተሽ ምን ልታደርጊ ነው?›› አሉ በመረረ
አነጋገር፡ ‹‹ውትድርና ልትገቢ ነው ልክ እንደ ዶሮ ጭንቅላት እህትሽ?››
ማርጋሬት ዶሮ ጭንቅላት በመባሏ ብትበግንም ጥርሷን ነክሳ ዝም
አለች፡፡

‹‹ጀርመን እሄዳለሁ›› አለች ኤልሳቤትም፡፡

አባት በድንጋጤ ምላሳቸው ተያያዘ፡፡

‹‹አላበዛሺውም›› ሲሉ እናት ልጃቸውን ጠየቋት፡

ፔርሲም ጣልቃ ገባና የአባቱን አነጋገር ወስዶ ‹ሜሪ ስቶፕስን ነው
ለዚህ ተጠያቂ የማደርገው›› አለ፡፡
‹‹ዝጋ›› አለችው ማርጋሬት ጎኑን በክርን ጎሸም አድርጋ፡

የምግብ ቤቱ አስተናጋጅ የበሉበትን ሰሃን እስኪያነሳና ጠረጴዛውን
እስኪጠራርግ ድረስ ጠበቁ፡፡ ወንድ ናት አደረገችው› አለች ማርጋሬት በሆዷ እሷ ድሮም ደፋር ናት ታዲያ ሃሳቧን ዳር ታደርሰው ይሆን?›
👍11
ማርጋሬት አባቷ ድንግርግር እንዳላቸው ከፊታቸው አነበበች፡፡ እሷ አገሬ ቆይቼ ፋሺስቶችን እዋጋለሁ ባለች ጊዜ የስድብ ናዳ ለማውረድ ቀላል ነበር፡፡ ነገር ግን ኤልሳቤት የእሳቸውን ሀሳብ አራማጅ ስለሆነች በቀላሉ
ውሳኔዋን ሊያጣጥሉት አልቻሉም፡፡

አስተናጋጁ እንደሄደ ‹‹ይህን በፍጹም አልፈቅድም›› አሉ አባት ይህ.አባባል ንግግራቸውን በሙሉ እንደሚያጠቃልልላቸው ሁሉ።

ማርጋሬት እህቷ ላይ አፈጠጠች፤ ‹ምን ትል ይሆን?› ብላ፡፡
ኤልሳቤትም ፍጹም እርጋታ በተላበሰ ሁኔታ ‹‹አባባ እንዳልሄድ ልትከለክለኝ አትችልም፤ አሁን ሃያ አንድ አመቴ ስለሆነ ያሻኝን ማድረግ እችላለሁ›› አለች፡
‹‹በኔ ስር እያለሽ አታደርጊውም›› አሉ አባት፡፡
‹‹ያንተ እርዳታ አሁን አያስፈልገኝም፤ ትንሽ ገንዘብ አለኝ››
‹‹ያም ሆነ ይህ አልፈቅድልሽም›› አሉ አባቷ፡

ማርጋሬት ኤልሳቤት በዚሁ የሚያበቃላት መሆኑን ማመን ጀምራለች፡፡
ኤልሳቤት አባቷን ማሸነፍ ይሁን ናዚዎችን መቀላቀል የሚያስደስታት ማወቅ አልቻለችም፡፡

ኤልሳቤት በፍርሃት ፊቷ አመድ ቢመስልም ቆራጥነት ይነበብባታል፡፡
ማርጋሬት የእህቷን ዓላማ ባትደግፍም ጽናቷን ታደንቃለች።

‹‹ወደ አሜሪካ የማትሄጂ ከሆነ ባቡር ውስጥ ለምን ገባሽ ታዲያ?››ሲል ፔርሲ ጠየቃት፡፡

‹‹ከሳውዝ ሃምፕተን የሚወስደኝ መርከብ ላይ ለመሳፈር አስቀድሜ
ቦታ ይዣለሁ›› አለች፡

‹‹ከዚች አገር ወደ ጀርመን የሚሄድ መርከብ አታገኚም›› አሉ አባት
በድል አድራጊነት መንፈስ፡፡

ማርጋሬት ደንገጥ አለች አዎ አታገኚም ኤልሲ›› አለች፡፡ በዚህ ምክንያት ውጥኗ ይከሽፍ ይሆን? አለች በሆዷ፡
ኤልሳቤት ረጋ ብላ ‹‹ከሳውዝ ሃምፕተን ሊዝበን (ፖርቹጋል) በመርከብ
እሄዳለሁ፡፡ እዚያ የሚገኝ ባንክ ገንዘብ አስተላልፌያለሁ ሆቴልም ቦታ ይዣለሁ›› አለች።

‹‹አንቺ እርጉም!›› አሉ አባት በንዴት ጮኸው፡፡ በሚቀጥለው ወንበረ
ላይ የተቀመጠው ሰው ጩኸቱን ሰምቶ ወደ እነሱ ዞረ።

ኤልሳቤት አባቷ ያሉትን እንዳልሰማች ሆና ‹‹ሊዝበንከ ከደረስኩ በኋላ
ወደ ጀርመን የሚሄድ መርከብ ላይ እሳፈራለሁ›› አለች።
‹‹ከዚያስ?›› ሲሉ ጠየቁ እናት፡
‹‹ከዚያማ በርሊን ጓደኞች እንዳሉኝ ታውቂያለሽ እማማ››
‹‹አዎ አውቃለሁ›› አሉ እናትም በሲቃ፡
ማርጋሬት ይህን ስታይ እናቷ የፈቀዱ መሰላት፡፡
ሲጮኹ ብዙ ሰዎች ምንድነው?› ምንድነው?› እያሉ ፊታቸውን ወደ እነሱ
አቅጣጫ ዞር ዞር አደረጉ፡፡

‹‹ቀስ ብለህ ተናገር የኔ ውድ›› አሉ እናት ባላቸውን፡፡

አባትም ‹‹ገና በርሊን እንደደረስሽ አፋፍሰው የሚመልሱልኝ ጓደኞች
አሉኝ›› አሉ ድምጻቸውን ዝቅ አድርገው፡፡

ማርጋሬት አፏን ያዘች: አባቷ ኤልሳቤት ጀርመን እንዳትገባ ማስከልከል ይችላሉ፡ በፋሺስት አገር መንግሥት ያሻውን ያደርጋል። ታድያ ኤልሳቤት ወደ ጀርመን ልትገባ ስትል ኬላ ላይ ያለው ተቆጣጣሪ ‹መግባት አትችይም ይላት ይሆን?› ስትል አሰበች ማርጋሬት፡

‹‹ጀርመኖች አይከለክሉኝም›› አለች ኤልሳቤት በሙሉ ልብ፡፡
‹‹እናያለና!›› አሉ አባት፡፡ ማርጋሬት አባቷ ይህን ሲሉ እርግጠኛ እንዳልሆኑ ከድምጻቸው አወቀች፡፡

‹‹አባባ ጀርመኖች እንኳን ደህና መጣሽ ነው የሚሉኝ›› አለቸ ኤልሳቤት፡ ‹‹ከእንግሊዝ አምልጬ እነሱን እንደተቀላቀልኩ ለዓለም በሙሉ ዜናውን ያበስራሉ ልክ የእንግሊዝ ቆሻሻ ፕሬሶች ታዋቂ የጀርመን አይሁዶች ከጀርመን አምልጠው ሲወጡ እንደሚያናፍሱት››

‹‹ስለአያታችን ፊሽቤን ካላወቁ ነው አንቺ የምትይው የሚሰራው››
አላት ፔርሲ፡

ኤልሳቤት ከአባቷ የሚሰነዘርባትን ጥቃት ለመመከት ታጥቃ ተነስታለች፡፡ ነገር ግን የፔርሲ መራራ ቀልድ አንገዳግዷታል፡፡ ‹‹ዝም በል
አንተ ልጅ!›› አለችና ማልቀስ ጀመረች።

አስተናጋጁ ሁለተኛውን ዙር ምግብ አመጣላቸው፤ ኮተሌትና ሰላጣ ቪኖም ቀዳላቸው:፡....

የቀጠላል
👍19🥰2
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ዘጠኝ (9)

የአውሮፕላኑ መስገሪያ ጎማ ከሆዱ ውስጥ ጉጉ ግርር ብሎ ሲወጣ ለናንሲ በደንብ ተሰማት ። እጅዋን ስትዘረጋ ከቦስተን ወደ ሳንፍራንሲስኮ ባደረገችው በዚህ ጉዞ ላይ ያዝ እያደረጉ መቶ ጊዜ ያህል ካፅናኗት ሁለት የተለያዩ እጆች አንዱ ያዝ አደረጋት ። ከሁለቱ ነርሶች አንደኛዋ ነበረች እጅዋን ያዝ አድርጋ ያጽናናቻት ። የነርሷ እጅ እጅዋን ሲቀበል መንፈሷ ተረጋጋ። የትኛዋ ነርስ እንደሆነች ስታውቅ ደስ አላት ። በአያያዛቸው መለየት ጀምራ ነበር ። የአንደኛዋ ነርስ እጅ ቀጭን ሲሆን ልስልስ ያለ ነበር ። የዚች ነርስ እጅ ቀዝቃዛ ቢሆንም አጨባባጧ ግን ጠንካራ በመሆኑ ይህችኛዋ ሴት ስትጨብጣት ፍርሃት ፤ ፍርሃት የሚላት ይተዋትና ልቧ መድፈር ይጀምራል። የሁለተኛዋ ነርስ እጅ ወፍራምና ቡትቡት ያለ ሲሆን ገና ያዝ ስታደርጋት ክብካቤና ፍቅር ያልተለያት እንደሆነ ይሰማታል ። የዚች ነርስ ሞቃት እጅ ፍቅርን ይገልጽላታል ። ያዝ አድርጋ እትከሻዋ አካባቢ እጅዋ መባቀያ ላይ መታ መታ ስታደርጋት የፍቅሯን ጥልቀት ይገልጽላታል ፤ ለናንሲ ። ህመሙ ጠንከር ሲልባት ሁለት ጊዜ መርፌ የወጋቻት ይህችው ነርስ ነበረች ።

ድምጿም የሚያረጋጋ ሀይል አለው። ልስልስ ያለ ነው። ቀጭን እጅ ያላት ሴትዮ ስትናገር ትንሽ ያዝ ያደርጋታል ። ናንሲ ሁለቱንም ሴቶች እየወደደቻቸው ስትሄድ ተሰማት ።

«አሁን ደርሰናል የኔመቤት ። ማረፊያው እየታየኝ ነው» አለች ጠንከር ያለ አያያዝ ያላት ነርስ እጅዋን እንደያዘች ።

ነገሩ እንደተባለው ነበር ። የቀራቸው ሃያ ደቂቃ ያህል ሲሆን፤ ፒተር ግሬግሰን ሰዓቱን በማየት አረጋገጠ ። ፒተር ግሬግሰን በቀጠሮው መሠረት በጥቁሩ አውቶሞቢል ወደ አውሮፕላን ማረፊያው ሲነጉድ ይህን ተገንዝቧል። አምቡላንሱ እዚያው ይጠብቀዋል ። ፒተር ሕክምናውን ከሚያደርግላት ልጅና ከነርሶቹ ጋር በአምቡላንሱ ሊመለስ ወስኗል።ምክንያቱም የልጅቷ ሁኔታና የሚያደርግላት ሕክምና አጓጉቶታል ። አዲስ ፊት መስራት ! አዲስ ውበት መፍጠር ! ይህ 'ቀላል ነገር አይደለም ። በዚያ ላይ ምን አይነት ፊት እንደሚፈጥር ያውቃል ። ፒተር በዚህ ሁኔታ ሀሳቡን ሊቀጥል አልፈለገም ። ስለዚሀም ስለናንሲ ማንነት ማሰብ ቀጠለ ። አራት መቶ ሺህ ዶላር እጅግ በጣም ብዙ ገንዘብ ነው። ልጅቷ ይህን የሚከፍልላት ሰው ማግኘቷ መታደል ነው። ለማሪዮን ሂልያርድ ምኗ ትሆን! ማሪዮን በጣም የምትወዳት ወይም የምታስብላት ሰው መሆን አለባት-። ያለዚያ ይህን ያህል ገንዘብ አታወጣም ነበር። ይህን ያህል አትጨነቅላትም ነበር ።። አራት መቶ ሺህ ዶላር ! ከዚህ ውስጥ ሦስት መቶ ሺህ ዶላር የሱ የአገልግሎት ዋጋ ነው ። ወጭውንና የመሳሰለውን ችሎ ። መቶው ሺህ ዶላር ግን የተከፈለው ለታካሚዋ ነው ። ሕክምናዋን እስክትጨርስ ለመኖር የሚያስፈልጋትን ነገር ለማሟላት የምትጠቀምበት ። በዚህ ገንዘብ የፈለገችውን ሁሉ ለማሟላት ወደ ኋላ አልልም አለ ፒተር ግሬግሰን በሀሳቡ ።

እንደገናም አመት ከመንፈቅ ሙሉ በአይኑ ላይ ውል ሲለው የኖረ ፊት ትዝ አለው ። ያ ፊት ናንሲን አዲስ ሴት ያደርጋታል ። ለአስራ ስምንት ወራት ያረገዘውን ፊት ናንሲ አድርጎ ይወልደዋል ። የናንሲና የእሱን የወደፊት ግንኙነት ሲያስበወ ሲቃ ያዘው። ናንሲ የሙያውን ረቂቅነት የሚያይባት ብቻ አትሆንም ። የእሷና የሱ ግንኙነት ከሐኪምና ታካሚ ግንኙነት ያልፋል ። ከመዋደድም ያልፋል ። ደፋርና በራሷ የምትተማመን ሴት የምትሆንበትን መንገድ ሁሉ ያደርጋል ። ደግሞም ትሆናለች። ይህን ነገር ሲያስብ የሆነ ያህል ሆኖ ተሰማው። በደስታ ሰክረ። ሙያውን ይወደዋል ። አንድ ነገር ሰርቶ ውጤቱ ሲያምር ሁልጊዜም ይደሰታል ። ስለዚህም ምንም እንኳ ነገሩ ግራ ቢመስል ፤ገና ካሁኑ ከናንሲ ጋር ፍቅር ያዘው። ገና ወደፊት ከሚፈጥራት ናንሲ ጋር፤ ካላያት ናንሲ ጋር።

ሰዓቱን እንደገና አየት አደረገ ጊዜው እየታቀረበ ነው። ቤንዚን መስጫውን ተጫነው። መኪናው ተፈተለከ ። የቀጠሮው ሰዓት በመድረሱ ብቻ ሳይሆን ፒተር ግሬግሰን በፍጥነት መንዳት በጣም ከሚያስደስታቸው ሰዎች አንዱ ነው። ይህም ብቻ አይደለም። ፒተር የግል አውሮፕላንም አለው። ያን አውሮፕላን አስነስቶ በጣም ከፍ ብሎ ማብረር ወይም አውሮፕላኑን በፍጥነት ሽቅብ ነድቶ አቅጣጫ ለውጦ ዘቅዝቆ ቁልቁል ማብረር በጣም ያስደስተዋል። ጉራ ወይም ሌላ ነገር አይደለም፣ፒተር አስቸጋሪ ነው የሚባለውን ነገር ሁሉ ማድረግ ይወዳል። አደገኛ ነው ሲሉት ተራራ መውጣት... የመሳሰሉትን ሁሉ በሚገባ እስኪካናቸው ድረስ ያደርጋቸዋል። ፒተር አናቱ ድረስ ያልወጣበት የአውሮፓ ተራራ አይገኝም። ይህ ሁሉ ታዲያ እላይ እንደተገለፀው ካስቸጋሪው ጋር መጋፈጥን በመውደዱ ነው። በዚህ ጠባዩ ነው ይህን የቆዳና የአካል ቅርፅ መፍጠር ቀዶ ሕክምና ሙያው ያደረገው። አስቸጋሪና ብዙ ጥንቃቄ ያሻዋል። ያ ስለሆነ እንዲያውም ሰዎች አንዳንድ ጊዜ እግዜር ልትሆን ትሻለህ? በሚል ተረብ ገረፍ ያዶርጉታል። እሱ ግን ይህ እንዳልሆነ ያውቃል። ይህን አይነት ሕክምና እንዲያደርግ እሱን የሚገፋፋው እልህ ነው ፤አይቻልም ያሉትን ነገር እንዲቻል የማድረግ እልህ። እና አድርጎ ማሳየት ። ፒተር ይኸው ነው። እስከዛሬ ድረስ ያከማቸውን ሰዎች አስታወሰ ። ተሳክቶለታል ። ፒተር ሁልጊዜም ይሳካለታል ። የፈለጋት ሴት እምቢ አትለውም ። ተራሮች ተረትተውለታል። ሰማይን ተጫውቶበታል። ምን ጊዜም አሁንም ይሳካለታል። ናንሲና እሱ ተረዳድተው ሕክምናው ባሰበው መንገድ ይፈጸማል። ዛሬ የአርባ ሰባት አመት እድሜ ያለው ሰው ነው። በዚህ ባሳለፈው እድሜ ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም ። ዛሬም አይሸነፍም

«ሄሎ ናንሲ ፤እንኳን ደህና መጣሽ ጉዞው እንዴት ነበር! አለ ፒተር ግሬግሰን ካውሮፕላኑ እንደወረደች ። ሁለቱን ነርሶች እንዳያቸው ተስማሚ እንደሆኑ ገምቷል ። ለነሱ በጥቅሻ ሰላምታ ሰጠ። ፤ድምጹን ስትሰማ ደስ አላት ።
«ጥሩ ነበር፤ ዶክተር ግሬግሰን » አለች ናንሲ ።ድምጺ እንደደከማት በ.ያመለክትም ስልቸታ ግን አልነበረበትም ።
«ዶክተሬ ነህ-»
«ነኝ። ግን ካሁን ጀምሮ አብረን መሥራታችን እይደለም? ስለዚህ ሚስ ማክኦሊስተር ፤ዶክተር ግሬግሰን ከመባባል ፤ እኔም ናንሲ ብል አንችም ፒተር ብትይ ይበልጥ የሚያቀራርበን ይመስለኛል» አለ ፒተር ። አቀራረቡ ደስ አላት ።
«ልትቀበለኝ ነው እዚህ ድረስ የመጣኸው » አለች።
«አንቺ ብትሆኝ እዚህ ድረስ መጥተሽ አትቀበይኝም ነበር ማለት ነው?» ሲል ጠየቃት ።
«እቀበልህ ነበር እንጂ» አለች ይህን ስትል በሚገርም ሀኔታ ነገሩ እውነት መሰላት። ይህን ያህል ከሰው ጋር ባጭር ጊዜ መግባባት መቻሏ ገረማት «አመሰግናለሁ» አለች ።
«እኔ የመጣሁት ለራሴ ደስ ስለሚለኝ ነበር ። ሆኖም አንችንም ደስ ሲልሽ አየሁ ። ይህ ደሞ ደስታዬን እጥፍ አደረገው እንኳን መጣሁ አሰኘኝ» አለ ።« በማከታተልም «ናንሲ» አለ
«አቤት »
«ናንሲ ከዚህ በፊት ሳንፍራንሲስኮ መጥተሽ ታውቂያለሽ?»
«አላውቅም»
‹‹ደስ እምትል ከተማ ናት ። ፍሬስኮን እንደምትወጃት እተማመናለሁ። ምርጥ የሆነ አፓርታማ እንፈልግልሻለን ። አለቀ ። ብዙ ሰዎች ሳንፍራሲስኮን ከረገጡ በኋላ የተወለዱበትን ፤ የኖሩብትን ቦታ ይረሳሉ። እዚሁ ቅልጥ ብለው ነው የሚቀሩት ። ለምሳሌ የእኔን ነገር ማንሳት እንችላለን ። የዛሬ አሥራ እምስት አመት አካባቢ ከሺካጐ መጣሁ። መጣሁ ቀረሁ። ዛሬ የፈለገው ነገር ቢመጣ ከዚች ከተማ ንቅንቅ አልልም ። አንች የት ነው የነበርሽው?››
‹‹ቦስተን »
👍15🥰1
እንዲህ እያለ በቀላሉ የረጅም ጊዜ ትውውቅ ያላቸው እስኪመስላት ራሱን አላመዳት ። ባንዴ ። ይህን ሁሉ የሚላት ለመቀራረብ ብቻም አልነበረም። በረጂም ጉዞ ላይ ስለነበረች ለጥቂት ጊዜ ያላንዳች እንቅስቃሴና ሀሳብ ስታርፍ ሰውነቷ በቀላሉ ዘና እንደሚል ስላወቀም ነበር ። ነርሶቹም ደስ አላቸው ። እነሱም ከጉዞ ጣመናቸው ማረፍ ያስፈልጋቸው ነበርና ካንቡላንስ ነጂው ጋር እያወጉ ይዝናኑ ነበር። ወደናንሲ አይናቸውን ጣል ሲያደርጉ ዶክተር ግሬግሰን ናንሲን ሲያጫውታት ስላዩ ስውየው ደስ ብሏቸዋል ።
«እኔ ? እኔ እንኳ ያደኩት ኒው ሃምፕሻዬር ነው ። እናትም አባትም አልነበረኝምና እዚያው ባለ የእጓለማውታን ማሳደጊደያ ውስጥ አደኩ ። ወደ ቦተስን የመጣሁት አስራ ስምንት አመት ከሞላኝ በኋላ ነው»
«ይኸማ ልብ የሚሰቅል ታሪክ ነው። ወይስ ማሳደጊያ ቤቱ በቻርልስ ልቦለዶች ውስጥ እንዳሉት ያለ በጭካኔ የተሞላ ነበር» አለ ፒተር ። ናንሲ በፒተር አጠያየቅ ፤ በተለይም ሁሉን ነገር ቀላል አድርጐ በመቀበል ችሎታው ተገረመች የዲክንስ የእጓለማውታ ማሳደጊያዎችን ማሰቡ አሳቃት ።
«ዲክንስ ውስጥ ? በፍጹም ! ያሳደጉኝ መነኩሲቶች በጣም ዶጋጐች ነበሩ ። ደስ የሚሉ። በዚህ የተነሳ እንዲያውም እኔም እራሴ ለመመንኮስ ሀሳብ አድሮብኝ ነበር ። እንደነሱ ለመሆን አለች ናንሲ ።
«አረ የስላሴ ያለህ ! ጆሮ አይሰማው የለ ! ስሚ የኔ እህት» አለ ፒተር ፤ናንሲ ሳቀች ።
«የኔ እህት ልክ ህክምናውን እንደጨረስሽ በቀጥታ ወደ ፊልሙ ከተማ ወደ ሆሊውድ!... ገባሽ?... ነገር ግን... ይህን አይሆንም ብለሽ ቁንጅናሽን ይዘሽ ገዳም ብትገቢ አያድርገውና !... ገዳም ብትገቢ እኔ ምን የማደርግ . . . እኔ ሌላ ምንም አላደርግም ። ወደወደብ ሄጄ፤ አንዱ ቋጥኝ ላይ ወጥቼ፤ ከዚያ ላይ ተወርውሬ ስምጥ ። በቃ ። የለም የለም ፤ እንዲሀ በቀላሉ አንላቀቅም ። እንዲያውም ህክምናዬን ከጨረስኩ በኋላ ቁንጅናዬን አንድ ገዳም ወስጄ ላልደብቅ ለፒተር ግሬግሰን ቃል እገባለሁ ስትይ ማይልኝ፡፡ ይህ ቀልድ ነው ። ሆኖም እንደዘበትም ቢሆን ቃል መገባት ደግ አይደለም ። ይህን ታውቃለች ። ትወቅ እንጂ ቃል ለመግባት ደግሞ አይከብዳትም ። ምክንያቱም እካሏ ይመለሰን እንጂ ወደየት እንደምትሔድ ታውቃለች ። ማይክል አለላት ። በዚያ ላይ ሞግዚቷና እናቷ እንደነበሩት እማሆይ ሜሪ የመሆን ፍላጐቷም አስቀድሞ ጠፍቶ ነበር ። ይህ ሁሉም ሆኖ ትንሽ ጫወታ አይጎዳም በማለት ፣ «እንዲያ ከሆነ እሺ›› አለች
«ምንድነው እሺ ? ቃል ገባሁ ማለችሽ ነው? ቃል በቃል ልትናገሪ ይገባል። ቃል ገብቻለሁ በይ »
«እሺም ቃል ኪዳን ነው። ስለዚህም ቃል ገግብቻለሁ
«ቃል ገብቻለሁ ! ብሎ ነገር ምን ለመሆን ነው ቃል የገባሽው ?»
«መነኩሴ ላለመሆን››
«እፉፉዎዬ ! አሁን ቀለል እለኝ » አለ ፒትር ።

እስካሁን ሰውነቷ ዘና እንደሚል ገባው ። ስለዚሀም ነርሶቹ እንዲወጡ በጥቅሻ ጠራቸው ። በወሬ ብዙ ማድከሙም ደግ እይደለም። ይበቃታል ፤ ሲል እያሰበ ። ሁለቱ ነርሶች ሲመጡ
«ከጌደኞችሽ ጋር ለምን አላስተዋወቅሽኝም ? » አላት ።
«ደግ » አለችና ናንሲ ፤ «ባለሰቀዝቃዛ እጅዋ ሊሊ ትባላለች ። ባለሞቃት እጅዋ ደግሞ ግሬችን ትባላለች» አራቱም በዚህ ንግግር ሳቁ ።
«አመሰግናለሁ ናንሲ » ሊሊ የናንሲን እጅ በማበረታታት መንገድ ጨበጥ አደረገች ። ናንሲ በድንገት ደስ አላት ። እኒህ ሶስት ጓደኞቿ ምንም እንኳ እንግዳ ቢሆኑ የልብን የሚነግሯቸው የሚተማመኑባቸው ጓደኞቿ እንደሆኑ ተገነዘበች ። እነሱ እያሉ ምንም ችግር ይኖራል የሚል ሥጋት አልነበረባትምና ስለአስታማሚና ስለመሳሰሉት ያላትን ሀሳብ አራገፈች ። ይህን አራግፋ ፤ድና ስትወጣ ለማይክል ምን መስላ እንደምትታየው ታሰላስል ጀመር። ፒትር ግሬግሰንን አሰበችው ። የሚቀበሉት ፤ የሚወዱት ሰው ሆኖ አግኝታው ነበርና በህክምናው ተማመነችበት ። ውብ መልክ እንደሚሰጣት ገባት ምክንያቱም ለሰው ፍቅር አለው ። ስለዚህም ይጠነቀቃል ፤ ይጨነቃል ።"

«ወደ ሳንፍራንሲሰኮ እንኳን ደህና መጣሽ ብጥሌ!›› አለ ፒተር ግሬግሰን ። የሊሊ ሚጢጢ እጅ ናንሲን ለቅቋት የፒትር ሰፊ እጅ ያዛት ። ማረፊያቸው እስኪደርሱ ድረስ ማለትም በመንገድ ላይ አምቡላንሰ ውስጥ እጅዋ በእጁ ውስጥ ነበር ። በሚያስገርም አኳኋን ስሜቷን ሁሉ ቀየረው ። እናም የመጣችው ወደማታውቀው ሰፍራ ሳይሆን ወደ ቤቷ፤ ወደትወለደችበት ሀገር እንደሆነ አድርጋ ገመተች......

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍18
Forwarded from Josy Quality Button
❤️የተወለዱበትን ወር ይምረጡ እና ስለ ፍቅር ህይወቶ በጥልቅ ይወቁ❤️
👍3
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሚስተር ካርይልና ባርባራ ቁርስ ላይ እንዳሉ ሚስተር ዲል ሲገባ አዲስ ነገር
ሆነባቸው " እሱን ተከትሎ ጀስቲስ ሔር ጥልቅ አለ » ወዲያው ስኳየር ስፒነር ተከትሎት ግባ " በመጨረሻ ደግሞ ኮሎኔል ቤተል መጣ " አራቱም የመጡት ለየብቻ
ቸው ሲሆን ሁሉም ትንፋሻቸው ቁርጥ ቁርጥ ሲል ማን ቀድሞ እንደሚደርስ የተወዳደሩ ይመስሉ ነበር "

ሁሉም ሲቃ እየተናነቃቸው ሳይደማመጡ ባንድ ላይ ሲናገሩ ሚስተር ካርላይል ሊገባው አልቻለም ።በጣም ተናዶ ይናገር የነበረው የሚስተር ጀስቲስ ሔር
ድምፅ ብቻ ጆሮን ለማደንቆር ይበቃ ነበር ከዚያ ሁሉ ጫጫታ ሚስተር ካርላይል አንድ ቃል ያዘ።

“ ሁለተኛ ሰው ? ተወዳዳሪ ? ይምጣ እንጂ በመጨረሻ ማን እንደሚያሸንፍ ማወቁም እኮ ያስደስታል” አለ ካርላይል በቅን ልቦና "
ሚስተር አርኪባልድ ” አለ ሽማግሌው ማን መሆኑን እኮ አልሰማህም
ዲል “ ከሱ ጋር እኩል ቆሞ መወዳደር ! ” ብሎ ደነፋ ሚስተር ጀስቲስ ሔር ።

“የለም ሰውዬው መሰቀል ይገባዋል” አለ ኮሎኔል ቤተል ከመኻል አቋርጦ"

መዝፈቅ አይቻልም ?” አለ እስኳየር ስፒነር "

ሰዎቹ ተናግረው የሚያበቁ ወይም እየተደማመጡ የሚያወጉ አልመሰለም "
ባርባራ በሁኔታቸው ተገርማ ዐይኗን ካንዱ ወደ ሌላው እያንገዋለለች ታያቸዋለች
“ ይኸ ኃይለኛ ተወዳዳሪ ማነው ? አለ ሚስተር ካርላይል "
ሚስተር አርኪባልድ ” አለ
ዲል ድምፁን ዝቅ አድርጎ " " የቀረበው እጩ ያ ሌቪሰን የሚባለው ሰውዬ ነው ”

ሚስተር ካርላይል ፊቱ ደም ለበሰ ። ባርባራ አንገቷን ደፋች " ዐይኖቿ ግን
በቁጣ ተንቀለቀሉ "

“ ቤንጃሚን ፈረሶቹን ለማንሸርሸር ዛሬ ማለዳ ወደ ከተማ ወጥቶ ነበር '
አለ ጆስቲስ ሔር ከንዴቱ የተነሣ ምላሱ እየተንተባተበ “ ሲመለስ የከተማ
ግድግዳዎች · ሌቪሰን ለዘለዓለም ይኑር ! ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ምረጡ ! በሚሉ ፁሑፎች ተንቆጥቁጠዋል አለኝ “ነደደኝና በጥፊ ላቀምሰው ስል ኧሪ እውነቴን ነው " አንዳንድ ሰዎች አነጋግሬ ነበር ትናንት ማታ ነው አሉ በባቡር ግብቶ ያደረው
አሉኝ "

“ ትናንት ነው በመጨረሻው ባቡር የደረሰው » ያረፈውም ባክስሔድ ሆቴል ነው አለ ሚስተር ዲል " አንድ ወኪል ብጤና አንድ ደግሞ የመንግሥት አባል ነኝ የሚል ሰው አብረውት አሉ ማስታወቂያ አታሚዎቹ ግን ያን ሁሉ ሲያዘጋጁ
ተቀምጠው ሳያድሩ አልቀሩም "

"ገና ሳይጀመር የውድድሩም የድሉም መስክ የኛ ነው እያሉ ጉራቸውን ብትሰሙ
ይገርማችኋል " ሰውየው ግን ራሱን ለውድድር ማቅረቡ ዕብድ ነው?”
አለ ኮሌኔል ቤተል ከዘራውን ወደ መሬት በኃይል በመሰንዘር ።

"ሚስተር ካርላይልን ለመሳደብ ሆን ተብሎ የተደረገ ነገር ነው ” አለ ስፒነር

"ሁላችንን ለማዋረድ ነው እንጂ! ኧረ ቆይ ሲቀልድ እንደገባው ሲቀልድ አይወጣ።

“ በክስ ሔድ ሆቴል ስብሰባ ስለአለ አብሬአችሁ እግኛለሁ” አለ ሚስተር ካርላይል።

“ በክስ ሔድ ሆቴል ነበር ያልከኝ?ይኸን ደግሞ አልሰማሁም” አለ ስፒነር
ባክስ ሔድ እንደነበር መስማቴን ነው የተናገርኩ” አለ ዲል “ እስካሁን ግን
እሱም መሳሳቱንና ዳኞቹ ቢሰሙ ደግሞ እንደሚቀየሙት ነግሬዋለሁ "ዱሮውንም መሳሳቱን ቢያውቅ ኖሮ ይመልሰው እንደ ነበር ካወቀ ወዲ ደግሞ ባጭር ጊዜ
እንደሚያባርረው ግልጾልኛል።

ትንሽ ከተነጋገሩ በኋላ ሰዎቹ ወጡ » ሚስተር ካርላይል ቁርሱን ለመጨረስ ተቀመጠ "

“ አርኪባልድ የዚህ ሰውዬ ደፋር ድርጊት ካሰብከው ፍንክች እንዳያደርግህ”
አለችው ባርባራ "

“ እሱ እኔን ለማጥቃት ገፍቶ መጥቷል " እኔ ደግሞ ከጫማዬ ሥር ካለው
ትቢያ እንኳን አብልጬ አላየውም "

እውነትክን ነው” አለችው ፊቷ በኩራት ቦገግ አለ።

ሚስተር ካርላይል ወደ ዌስት ሊን ሲሔድ አንድ ሰው በሌላው ላይ ሊፈጽመው የሚችለውን የመጨረሻ ታላቅ በደል የፈጸመበትን የዚያን ክፉ ሰው የውድድር ማስታወቂያ ከሱ ማስታወቂያዎች ጋር ጐን ለጐን ተለጥፎ ተመለከተ "

አርኪባልድ ይህን አሳፋሪ ወሬ ሰምተሃል ? አለች ኮርኒሊያ እንደ ጀልባ እየተንሳፈፈች ደረሰችና "

“ ስምቸዋለሁ ኮርኒሊያ ። ባልሰማስ ግድግዳዎቹ ሊነግሩኝ ይችሉ የለ?”

አብዷል ? ደኅና ግድ የለም በፊት ደስ አላለኝም ነበር !አሁን ግን እንዳትለቅለት " ከእፉኝት አብልጠህ እንዳታየው ዌስትሊን በሙሉ ተነቃንቋል እንደዛሬ ሆኖ አያውቅም።

እውነቷን ነበር ድፍን ዌስት ሊን በድጋፍና በቁጣ ተንቀሳቀሰ ገጠሬው ከተሜው ሁሉ ካርላይል ብሎ ተነሣ " ቢሆንም ዌስት ሊን ውስጥ የመንግሥት ትኩረት ከፍተኛ ነው " የግልና የሕዝብ አስተያየት የመሰለ ቢመስልም ለሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን በጣም ብዙ ድምፅ ይመዘገባል።

ያን ዕለት ጧት ባርባራ ባሏን እስከ ግቢው የውጭ በር ድረስ ሽኝታው ስትመለስ ማዳም ቬንንና ሁለቱን ልጆች አገኘቻቸው ዊልያምም ሻል ያለው ይመስል ነበር።ሁልጊዜም ጧት ት ችግር አልነበረበትም "

· እማማ ” አለች ሎሲ “ የሞቀሽ ትመስያለሽ ፊትሽ ተለወጠ ”
አንድ ሰውዬ ከአባታችሁ ጋር ሊወዳዶር ስለ ተነሣ ተናድጄ ነው
ለመወዳደር መብት የለውም እንዴ አባባ ውድድሩ ለሁሉም ክፍት ነው ሲል ሰምቸዋለሁ ” አለ ዊልያም።

“ ለሱ ካልሆነ በቀር ለሌላው ክፍት ነው ” አለች ባርባራ ንዴቷ አስተያየቷን እየቀደመ “እሱ ክፉ · ማንም የሚንቀው ጥሩ የሚባሉ ሰዎች ሁሉ የሚጠሉትና
የማያስጠጉት ሰው ሆኖ እያለ አሁን ከአባታችሁ ጋር ሊወዳደር ቀረበ

“ ስሙ ማን ይባላል ?”

ባርባራ ትንሽ አሰበችና እሷ ባትነግራቸውም ከሌላ መስማታቸው ስለማይቀር
ካመዛዘነች በኋላ '“ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ይባላል ” አለች "

ማቃሰት መደንገጥና መገረም የተቀላቀለበት ድምፅ አሰማች አስተማሪቱ።ባርባራ ዞር ብላ ስታያት አቀርቅራ ፊቷን በመሐረቧ ሸፍና ትስል ስለ ነበር ድንገት ልውጥውጥ ብሎ የገረጣውን ፊቷን ማስተዋል አልቻለችም

አመመሽ እንዴ ? አለቻት ባርባራ "

“ ሕመም እንኳን ደኅና ነኝ " ብቻ አቧራ ብጤ ባፌ ገባ መሰለኝ አሳለኝ። "

ሚስስ ካርላይል ዝም አለች " ሕሊናዋ ግን ዝም አላለም።
ይኸን ስም ስትሰማ ለምን ደነገጠች " ሰውዬውን ታውቀው ኖሮ ይሆን ? የደነጠችው ግን በስሙ መነሣት ነው ? " እያለች ታስብ ጀመር
የሚገርመው ደግሞ ማዳም ቬን የዚያን ለት አላስተማረችም " ስለ ውድድሩ ጉዳይ ቶሎ ከሰሙት አንዱ ሎርድ ማውንት እስቨርን ነበር " ለንደን ውስጥ ከክበቡ
ሆኖ አንድ ማታ ጋዜጣ ሲመለከት ካርላይል ዌስትሊን ” ከሚሉ ስሞች ላይ ዐይኖቹን ያሳርፋል ሚስተር ካርላይል በእጭዎች መቅረቡን ተረድቶ እንዲቀናውም ከልቡ ተመኝቶ ኧርሉ ንባቡን ቀጠለና አንቀጹን አነበበው "

መልሶ መላልሶ አነበበው " ዐይኖቹን አሻሸ " መነጽሩን ወለወለ " በሕልሙ ይሁን በውኑ ለማረጋግጥ ራሱን መረመረ። ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ዌስት ሊን መግባቱን የሚስተር ካርላይል ተወዳዳሪ ሆኖ መቅረቡንና አሁን የፖለቲካ ንግግር የምርጫ ቅስቀሳ በማካሔድ ላይ መሆኑን አነበበ።

“ ይኸ ጋዜጣው ስለሚለው አሳፋሪ ነገር የምታውቀው አለህ ? አለ አብሮት የነበረውን አንዱን ሰውዬ "
“ እውነት ነው » እኔ ከአንድ ሰዓት በፊት ነበር የሰማሁት ሌቪሰን ብዙ
ድምፅ ማግኘቱ አይቀርም "

ድምዕ ! ” ” ኧርሉ በሰውዬው አነጋገር መንፈሱም አካሉም ተሸበረና “በል እንደዚህ አትበል ይህ ወደል ውሻ እንዲያውም መሰቀል ይገባዋል
👍101👎1
ጋዜጣውን ወደ ጐን አኖረና ከቤቱ ተመልሶ ' አንድ የመንገድ ሻንጣ አንሥቶ ልጁን አስከትሎ ' በባቡር ተሳፍሮ ወደ ዌስት ሊን ገሠገሠ ኧርሉ ማውንት እስቨርን • ስለ ምርጫው አስተያየት ለመስጠት ፍላጎት ነበረው "

ጧት ቁርስ በልተው ሲያበቁ ሳቤላ ልጆቹን ይዛ በግቢው የመንሸርሸር ልምድ ነበራት " ከቤቱ ፊት ለፊት ከነበረው ጨፌ እንዳሉ አንድ ሰውዬና አንድ ልጅ መጡ " ሳቤላ ከሎርድ ማውት እስቨርን ፊት ለፊት ግጥም ስትል የምትወድቅ መስሏት ነበር " ኧርሉ ልጆቹን ሰላም ለማለት ቆም ሲል ለእንግዳይቱ ሴትዮም
ባርኔጣውን አነሣላት

“ አስተማሪዬ ናት ማዳም ቬን ትባላለች ” አለች ሉሲ " ማዳም ቬን ምንም ሳትናገር እጅ ነሣችና ፊቷን ወደ ሌላ ዞር አድርጋ ለመተንፈስ ትቃትት ጀመር ጨነቃት "

' አባትሽ ከቤት አለ ... ሎሲ ? አላት ኧርሎ »
“ አዎን ቁርስ ላይ ይመስለኛል ”

ሎርድ ማውንት እስቨርን በሽተኛውን ዊልያም ካርላይልን እጁን ይዞ ወዶ ቤት ሲያመራ የሱ ልጅ ሎርድ ቬን ደሞ ከሉሲና ከማዳም ቬን ጋር ቀረ ከሎሲ ጋር ትንሽ ከተጨዋወተ በኋላ ሉሲ' ኮ . . ማጻም ቬን የኔ ሚስት ልትሆን ነው " አኔመ እስክታድግ አጠብቃታለሁ " እኔ ከማንም የበለጠ እወዳታለሁ ” አላት
አኔም እወደዋለሁ እሱ የሚለው እውነቱን ነው " አለቻት ሉሲም "

ሉሲ ገና ልጅ ነበረች እሱም ቢሆን ይሀን ተናገረ ተብሎ እንደ ቁም ነገር
የሚያዝለት አልነበረም ። የሁለቱም የልጅነት ንግግር ነበር " የተናገሯቸው ቃላት ግን በማዳም ቬን ደም ሥሮች ገብተው ይነዝሯት ጀመር " እንደ ማዳም ቬን ሳይሆን እንደ መከራኛይቱ እናት እንደ ዕድለ ሰባራይቱ እመቤት ሳቤላ ቬን ሆና ስታስበው ከበዳት "

“ ለሉሲ እንደዚህ ብለህ መናገር የለብህም ሊሆን አይችልም” አለችው ሎርድ ቬን ሣቀና ለምን ?አላት

“ አባትህና እናትህ አይስማሙበትም ”

"አባባ እንደሚስማማበት ዐውቃለሁ ፤ ሉሲን ይወዳታል " እማማም ብትሆን ጌታም እመቤትም ካልሆንኩ የምትል አይመስለኝም "

“ አንድ ጊዜ ወደዚያ ቆይማ ሉሲ ከማዳም ቬን ጋር የምንነጋገረው አለኝ አለ”

“ ካርላይል ያንን ሰውዬ በጥይት ገደለው ? አላት ሎሲ እንደ ተባለችው ፈንጠር ስትልለት አባቴማ ስሙን እንኳን ቢያነሣው ከንፈሮቹ የሚቆሽሹበት ይመስል ከደረስን ጀምሮ ምንም ሳንጠይቅ መጣን " እኔንም እንዳልጠይቅ ከለከለኝ ¦ ስለዚህ መናገር እየፈለግሁ ምላሴን እስሬ መጣሁ "

የምን ሰው ? ልትል አሰበች " ነገሩ ግልጽ መሆኑን ስለምታውቅ ቃላቱ
0መፀኞቹ ከንፈሮቿ ላይ ደርሰው ጠፉ ።

ሌቪሰን የት አባቱ ይሀ እርጉም። ካርላይል ሰውነቱን በጥይት ቢበሳሳውና ነፍሱ እስክትወጣ ቢረጋግጠው ዓለም ሁሉ ያጨበጭብለት ነበር እኔ ከጥቂት
ዓመተ በፊት ትልቅ ሰው ሆኜ ብሆን ኖሮ በልቡ ጥይት እከትበት ነበር
እመቤት ሳቤላን ታውቂያት ነበር ?”

አዎን ..የለም ... አዎን” የምትለው ግራ ገባት "

አየሽ የሉሲ እናት ነበረች » እኔ እወዳት ነበር ሉሲንም የምወዳት እናቷን ስለምትመስል ይመስለኛል " ግን የት ነበር የምታውቂያት ? እዚህ ?

"በዝና ነው የማውቃት ” አለች ሳቤላ ትዝታዋ እየመጣባት »

"አሃ በዝና!ካርላይል ውሻውን ገደለው ወይስ እስካሁን ቆሞ ይሔዳል ? "

“እኔ ስለዚህ ጉዳይ ምንም አላቅም ከሌሎች ጠይቀህ ብትረዳ ይሻላል?” አለችው ትንፋሿ እየተናነቃት " ልቧ በጣም እየመታ ወደ ሉሲ ዞሬችና አጅዋን
ይዛት ሔደች » ልጁም መደ ቤት እየሮጠ ገባ "

አሁን የውድድሩ ዘመቻ በይፋ ተጀመረ " የመንግሥት ባለሥልጣን የተባለው የሌቪሰን ደጋፊ ድፊክ የሚባል ተራ ሰውና የግል ጓደኛው ሆኖ ተገኘ « እነሆ ሰር ፍራንሊዝ ሌቪሰን ወኪሉና ድሬክ ሁነው በከተማ እየተሹለከለኩ ዞሩ
ከወንዱም ከሴቱም ብለው ጥቂት ወጣቶች አጅበዋቸዋል " ከሌላው ወግን ደግሞ የገጠር ታላላቅ ሰዎች የከተማው ባለሥልጣኖችና ሎርድ ማውንት እስቨርን ነበሩ
አንዳንድ ጊዜ ሚስተር ካርላይል ከነሱ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ከመካከላቸው ይታያል " ተቀዋሚዎቹ ቡድኖች ሲተያዩና ፊት ለፊት የሚገጠሙ ሲሙስሉ ጀግናው ፍራንሲዝ ሌቪሰን የኋሊት ሙሽሽ ብሎ ይቀርና ከአንዱ አጥር ወደ አንዱ ቅጠል ውስጥ ይገባል " ከሚስተር ካርላይልና እሱን ካጀቡት ዳኞች ጋር ፊት ለፊት ለመተያየት ድፍረት አጣ "

አንድ ቀን ከቀትር በኋላ ሚስዝ ካርላይል ሎሲንና አስተማሬቱን አስከትላ
ወደ ዌስት ሊን ሔደች አካሔዷ ከሱቅ አንዳንድ ነግሮችን ለመግዛት ነበር ሳቤላ ግን የማይሆን ሆኖባት እንጂ' ያ ሰውዬ በከተማ እስካለ ድረስ መውጣቱን ያለ ልክ
ትፈራው ነበር በሕመም እንዳታመካኝ አልታመመችም አልሔድም እንዳትል ታዛዥ ተቀጣሪ ናት " ተነሡና ጃስቲስ ሔር በር ሲደርሱ ሚስ ካርላይልን ከዚያ ስትወጣ አገኙዋት

“ እናትሽ ደኅና አይደለችም ... ባርባራ አለቻት "

“ አመማት ? አለችና ድንግጥ ብላ '“እንግዲያውስ ገብቸ መጠየቅ አለብኝ”

“ ዛሬም ያን የሞኝ ሕልሟን አየሁ ትላለች " አለች ኮርኒሊያ ንግግሯን በመቀጠል » ሎሲንና አስተማሪቱን እንዳሉ ኣልቈጠረቻቸውም

“ ስገባ ስትንቀጠቅጥ አገኘሁዋት " ግድግዳዎቹን እያለፉ መናፍስት የመጡባት ይመስል እንደዚያ እየራደች ዙሪያዋን ትመለከታለች » እኔም እንደ ምንም አግባብቼ አየሁ የምትለውን ሕልም እንድትነግረኝ ብጠይቃት ገልጻ ነገረችኝ እንደ ምትለው ሪቻርድ አንድ ችግር ገጥሞታል ወይም ይገጥመዋል በሕልም የሚመሩ ሰዎች ቦታቸው ከዕብዶች መጠበቂያ ቦታ ነው " የሕልም ተገዥ አትሁኚ ብላት አልሰማችኝም " ትንቀጠቀጣለች ትጨነቃለች

ባርባራ አዘነች " እሷም እንደ ኮርኒሊያ በሕልም አታምንም ግን ከነዚህ
ሕልሞች አንዳንዶቹ በሪቻርድ ላይ ያሳዬዋቸውን ነገሮች መርሳት አልቻለችም
“ እኔ እማማን ልያት ኮርኒሊያ ወዶ ቤት እየተመለስሽ ከሆነ ማዳም ቬን አብራሽ ትሒድና እዚያ ትቆየኝ "

“ እኔ አብሬሽ ልግባ እማማ ” ለመነች ሉሲ "

ባርባራ ሉሲን እጅዋን ይዛ ገባች ሚስ ካርላይልና ወይዘሮ ሳቤላ ወደ ከተማ
አመሩ " ብዙ ሳይሔዱ አንድ መታጠፊያ ላይ ሲደርሱ ኃይለኛ ነፋስ መጣና የሳቤላን ዐይነ ርግብ ይዞት በረረ " እሷም እንዶ ደነገጠች ሳይርቅ ይዛ ለማስቀረት እጅዋን በማርበትበት ስትዘረጋ መነጽሯን ነካችውና ከመሬት ወድቆ ተሰበረ

“ ምን ስታደርጊ ሰበርሺው ? አለቸት ሚስ ካርላይል ።

ፊቷን ወደ መሬት ደፍታ ስብርባሪውን ትመለከት ጀመር " ምን ታድርግ ?
መነጽሩ ተሰብሯል " ዐይነ ርግቧ ከቁጥቋጦው አጥር ላይ ተሰቅሏል " ያን ያልተጋረደ ፊቷን እንዴት አድርጋ ለዓለም ታሳየው ? ፊቷ ልክ እንደ ድሮው የጽጌረዳ አበባ እንደ መሰለ ታየ " ዐይኖቿም ቁልጭ ያሉ ነበሩ ሚስ ካርሳይል ያን ትንግርት ፍዝዝ ብላ ተመለከተችው "

“ወይ ታምር እንዴት ያለ አስገራሚ መመሳሰል ነው ! ስትል ሳቤላ የምትሆነው ጠፋት " ልቧ ድክም አለ " ነገሩ በዚህ ቢያበቃ ደኅና ነበር "
በዚህ ጭንቀት ውስጥ እንደ ሰጠመች ከነሱ ጥቂት እርምጃዎች ራቅ ብሎ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ሲመጣ አየችውና እንዳያውቃት ፈራች "....

💫ይቀጥላል💫
👍18👎21
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


...."አስተናጋጁ ሁለተኛውን ዙር ምግብ አመጣላቸው፤ ኮተሌትና ሰላጣ ቪኖም ቀዳላቸው:

አባትም የቀረበላቸውን ምግብ በሹካ እየወጉ አፋቸው ውስጥ ከተው
በንዴት ያኝካሉ፡፡ ማርጋሬት የአባቷን ፊት ስታይ ከንዴታቸው በስተጀርባ
የግራ መጋባት ሁኔታ ይነበብባቸዋል፡ እንደዚህ ድንብርብራቸው ሲወጣ
አይታ አታውቅም፡፡ ሰማይ እንደተደፋባቸው ተገንዝባለች ይህ ጦርነት
ራዕያቸውን ሁሉ ድባቅ መቶባቸዋል፡፡ የእሳቸው ፍላጎት የእንግሊዝ ህዝብ
ፋሺዝምን በእሳቸው መሪነት እንዲቀበል ነበር፤ ጭራሽ እንግሊዝ በፋሺዝም
ላይ ጦርነት አውጃ እሳቸውን ለስደት ዳረገቻቸው፡

የተመኙት የፖለቲካ ሁኔታ አፈር መብላቱ ሳያንስ ልጆቹ ደግሞ እያመጹ አስቸገሩ: ፔርሲ ይሁዳዊ ነኝ እያለ ይቀባጥራል፤ ማርጋሬት
ልትጠፋ ሞከረች ከሁሉም በላይ የእሳቸው አስተሳሰብ ተከታይና የአመለካከታቸው ተጋሪ የነበረችው ኤልሳቤት ደግሞ ትዕዛዛቸውን ጣሰች፡

ማርጋሬት ለመብላት ብትሞክርም የጎረሰችው አልዋጥልሽ አላት፡፡
እናትም ‹‹በርሊን ፍቅረኛ አለሽ?›› ሲሉ ጠየቋት፡፡

‹‹የለኝም›› አለች ኤልሳቤት፡ ማርጋሬት አምናታለች። ማርጋሬት እንደምታውቀው ኤልሳቤት ጀርመንን የምትወደው በሚከተሉት የፖለቲካ አመለካከት ብቻ አይደለም፧ እነዛ ጸዳ ያለ ዩኒፎርም የሚለብሱትና
የሚያብረቀርቅ ጉልበት የሚደርስ ቦት ጫማ የሚያጠልቁት ዘንካታና ጸጉረ ነጭ ወታደሮች ልቧን ሰልበዋታል፡፡ ኤልሳቤት እንግሊዝ ውስጥ መልከ ጥፉ ተብላ ብትቆጠርም ጀርመን ውስጥ ግን የጀርመንን ናዚዝም የሚያደንቅና የሚደግፍ የእንግሊዝ ባላባት ልጅ ናት ተብላ ትከበራለች፡፡ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት መቀስቀሻ ላይ አገሯን ከድታ የመጣች መሆኗ ዝነኛ ያደርጋታል፡፡ እዚያ ‹‹አንበሳ›› ነው የምትባለው፡ከቀናትም አንዱን ወጣት
መኮንን ታፈቀርና ወይም ስልጣን በስልጣን ላይ የጫነ የናዚ ፓርቲ አባል
ታገባና ጸጉረ ነጭ ልጆች ትወልድለታለች፧ ልጆቹም ጀርመንኛ እየተነጋገሩ
ያድጋሉ፡፡

‹‹አሁን ልታደርጊ ያሰብሺው ነገር አደገኛ ነው የኔ ማር፤ አባትሽ እና እኔ የተጨነቅነው ለደህንነትሽ ነው›› አሉ እናት፡፡

ማርጋሬትም አባታችን የኤልሳቤት ደህንነት ያስጨንቀው ይሆን?›
ስትል አሰበች፡፡ እናታቸው ያስጨንቃቸዋል፤ አባታቸው ግን የተናደዱት ኤልሳቤት ትዕዛዛቸውን ባለማክበሯ ነው፡፡ በእርግጥ ከቁጣቸው በስተጀርባ የሩህሩህነት ጭላንጭል ይታያል፡፡ ድሮ እንዲህ ጨካኝና ክፉ አልነበሩም፤ አንዳንዴም ልጆቹን ያጫውቷቸው ነበር፡ ይህ ሁሉ በሃሳቧ መጣና አዘነች።

‹‹አደገኛ እንደሆነ አውቃለሁ, አለች ኤልሳቤት ‹‹የወደፊት እጣ ፈንታዬ በዚህ ጦርነት ላይ የተመሰረተ ነው፤ በይሁዳውያን ባለሃብቶችና
በቆሻሻ ኮሚኒስት የሰራተኛ ማህበራት የተሞላ ዓለም ውስጥ ከምኖር ሞቴን
እመርጣለሁ››

‹‹ታዲያ ከኛ ጋር ሂጂያ
አሜሪካ ጥሩ አገር ነው›› አሉ እናት፡፡

‹‹የአሜሪካ የባንክ ቢዝነስ ማዕከል (ዎል ስትሪት) በይሁዳውያን እጅ
ነው ያለው›› አለች ኤልሳቤት፡፡

‹‹ይሄ መቼም ተጋኗል›› አሉ እናት ፈርጠም ብለው የባላቸውን አይን እየሸሹ፡፡ ‹‹በእርግጥ በአሜሪካ የቢዝነስ ስራ ውስጥ በርካታ ይሁዳውያንና
ብልሹ ሥነ-ምግባር ያላቸው ሰዎች መኖራቸው እርግጥ ነው፡፡ አያትሽ
ደግሞ የባንክ ባለንብረት እንደሆኑ አትዘንጊ፡፡››

‹‹በሁለት ትውልድ ከቀጥቃጭነት ወደ ባንክ ባለንብረትነት መለወጣችን
የሚደንቅ ነው›› አለ ፔርሲ፡፡ ሆኖም ማንም ጆሮ የሰጠው የለም፡፡

እናትም ቀጠሉና ‹‹በፖለቲካ አመለካከትሽ እኔም እስማማለሁ፤ አንቺም
ይህን ታውቂያለሽ ነገር ግን በአንድ ነገር ስላመንሽ ለእሱ ስትይ ህይወትሽን
ትሰውያለሽ ማለት አይደለም›› አሉ
ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ደነገጠች፤ እናታቸው የፋሺስት አስተሳሰብ
ህይወት የሚሰዉለት አላማ አይደለም እያሉ ነው፤ ይህም በአባታቸው ዘንድ
ክህደት እንደመፈጸም ይቆጠራል፡ እናታቸው እንደዚህ አባታቸውን ፊት
ለፊት ሲቃወሙ ማርጋሬት አይታ አታውቅም፡፡ ኤልሳቤትም የእናታቸው
አነጋገር ገርሟታል፡፡ ሁለቱም አባታቸውን ገርመም አደረጓቸው፤ ‹ምን ይል ይሆን?› በማለት፡፡ እሳቸው ግን ፊታቸው በርበሬ ከመምሰሉና በመጠኑ ከማጉረምረም በስተቀር በንዴት አልጮኹም፡፡

ቡና ለተሳፋሪዎች ሲታደል ማርጋሬት ከሳውዝ ሃምፕተን ከተማ ጥግ
መድረሳቸውን ተገነዘበች፡፡ ባቡር ጣቢያ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ
ይደርሳሉ፡ ኤልሳቤት እንደ ፎከረችው ታደርግ ይሆን?›
ባቡሩ ፍጥነቱን ቀነሰ፡፡
ኤልሳቤትም አስተናጋጁን ጠራችና ‹‹የሚቀጥለው ጣቢያ ላይ ወራጅ
ነኝ›› አለችው፤ ‹‹የሚቀጥለው ፉርጎ ውስጥ እመቤት ኤልሳቤት ኦክሰንፎርድ የሚል የተጻፈበት ሻንጣ አለልህ ይዘኽልኝ ና››

‹‹እሺ እመቤት›› አለ አስተናጋጁ፡

ማርጋሬት አባቷን ታያቸዋለች፡ ምንም ቃል ባይተነፍሱም ፊታቸው
በታመቀ ንዴት መወጠራቸውን ያሳብቅባቸዋል፡ ሚስታቸው እጃቸውን እባላቸው ጭን ላይ አስቀመጡና ‹‹እባክህ ሰው እንዳይሰማ ዝም በል፣ የኔ ውድ›› አሏቸው፡፡ ባላቸው ግን መልስ አልሰጡም፡፡

ባቡሩ ጣቢያው ጋ ደርሶ ቆመ::

ኤልሳቤት የተቀመጠችው በመስኮቱ በኩል በመሆኑ ማርጋሬትን አየት ስታደርጋት ማርጋሬትና ፔርሲ መንገድ ለቀቁላት፡፡ አባትም ቆሙ
ተሳፋሪው በሙሉ በአባትና በልጅ መካከል የተከሰተውን ፍጥጫ እንደ ትንግርት ያያል፡፡
ኤልሳቤት ተገቢውን ጊዜ መርጣለች፡ በዚህ ሁኔታ አባቷ ኃይል ተጠቅመው እንደማያስቀሯት አውቃለች፡፡ በፍርሃት ሰውነቷ እየራደ
ቢሆንም፤ ከሞከሩም ሌሎች ተሳፋሪዎች አይፈቅዱላቸውም።

አባቷ ፊታቸው በንዴት ቀልቷል፡፡ ዓይናቸው ተጎልጉሎ ሊወጣ የደረሰ
ይመስላል ኤልሳቤት በፍርሃት ብትንቀጠቀጥም ፈርጠም እንዳለች ነው፡፡

‹‹ከዚህ ባቡር ብትወርጂ ዳግም አይንሽን አላይም፤ መቃብሬም ላይ
እንዳትቆሚ›› አሏት።

‹‹እባክህ አባባ እንዲህ አትበል›› ስትል ማርጋሬት አለቀሰች፡ አባት አንድ ጊዜ ብለውታል፡፡ የተናገሩትን መልሰው ሊውጡት አይችሉም፡፡

እናት ይነፋረቃሉ፡

ኤልሳቤትም ‹‹ደህና ሁኚ እንግዲህ›› አለቻት እህቷን፡
ማርጋሬት እህቷ አንገት ላይ ተጠመጠመችና ‹‹መልካሙን ሁሉ
እንዲገጥምሽ እመኝልሻለሁ እታለም!››

‹‹ለአንቺም እንዲሁ›› አለችና ጀርባዋን መታ መታ አደረገቻት፡

ኤልሳቤት የወንድሟን ጉንጭ ሳመችና ወደ አባቷ ዞራ ድምጿ እየተንቀጠቀጠ ‹‹አባባ አትሰናበተኝም?›› ብላ እጇን ዘረጋች፡

አባትም ፊታቸው በጥላቻ ተጀቡኖ ‹‹ልጄ ከእንግዲህ ሞታለች፤ ልጄ አይደለሽም፧ ክጄሻለሁ›› አሏት፡

እናት ይሄን ሲሰሙ በተስፋ መቁረጥ እዬዬያቸውን አቀለጡት፡

የቤተሰቡ ውዝግብ እንዴት እንደሚጠናቀቅ ለማየት ተሳፋሪው በሙሉ
ትንፋሹን ውጦ ይጠባበቃል፡፡

ኤልሳቤት ፊቷን አዙራ ወደ በሩ አመራች፡፡

ማርጋሬት የአባቷ አድራጎት አበሳጭቷታል፡ ለአንዴ እንኳን እንዴት አይረታም! ስትል አሰበች፡፡ ኤልሳቤት ልጅ አይደለችም። እድሜ ልኳን አባት እናቷ የሚሉትን ሁሉ አሜን ብላ ስትቀበል አትኖርም፡ አባቷ ዕድሜ
ልካቸውን ሊቀጧት መብት የላቸውም፡፡ በቁጡ ባህሪያቸው ቤተሰቡን
ለያዩት፡ እዚያ በንዴት ጦፈው እንደ አበያ በሬ እንደተገተሩ ‹‹የተረገምክ!›፣
ጨቋኝ!›፣ ደደብ›፣ ብትላቸው በወደደች፡ ነገር ግን እንደልማዷ ከንፈሯን
ከመንከስ በስተቀር ምንም ቃል አልወጣትም፡፡
👍19
ኤልሳቤት ቀይ ሻንጣዋን ይዛ መንገዷን ቀጠለችና በሩጋ ስትደርስ ዞር
ብላ አይኗ በእምባ ሞልቶ ቤተሰቡን በሙሉ ደህና ሁኑ በማለት እጇን አውለበለበች ማርጋሬትና ፔርሲ እጃቸውን አንስተው ባይ ባይ አሏት፡፡
አባት ፊታቸውን ሲያዞሩ እናት ደግሞ ድምጽ ሳያሰሙ አነቡ፡፡

አባት የሚያደርጉትን አጥተው ቁጭ አሉ፡፡ ማርጋሬትም እንዲሁ፡፡

ባቡሩ ደውሉን አሰማና ቀስ ብሎ ጉዞውን ጀመረ። መላው ቤተሰብ ኤልሳቤትን በዓይኑ ፈለገ፤ እሷም ባቡሩ እስኪያልፍ ቆማለች፤ ፊቷ ላይ የሀዘን ጥላ አጥልቷል፡

ባቡሩ ፍጥነት ሲጨምር ኤልሳቤት እስከወዲያኛው ከዓይናቸው ተሰወረች፡፡ ማርጋሬትም እህቷን ‹ወደፊት አገኛት ይሆን?› ስትል አሰበች::

ሌዲ ኦክሰንፎርድ በያዙት መሀረብ ዓይናቸውን ለማበስ ቢጥሩም
ስሜታቸውን መቆጣጠር
እምባቸውን ሊገቱት አልቻሉም፡፡ እንደዚህ
አቅቷቸው አያውቅም፤ ማርጋሬት እናቷ እንደዚህ ሲያለቅሱ አይታ አታውቅም፡ ፔርሲ ድንጋጤ እንደወረረው ያስታውቅበታል ማርጋሬት
ምንም እንኳን እህቷ ለዚህ የማይረባ ዓላማ ስትል ብትለያቸውም ነፃነቷን
ማወጇ ግን አስደስቷታል፡፡ ኤልሳቤት ወንድ ናት፤ ያለችውን አደረገችው::
የአባቷን ትዕዛዝ አሻፈረኝ ብላ በውሳኔዋ ፀናች፡ አባቷን ፊት ለፊት ተጋፍጣ
ረታቻቸው፤ ጥላቸውም ሄደች፡፡

ኤልሳቤት ይህን ማድረግ ከቻለች እሷስ ይህን ማድረግ ምን ያቅታታል!›

ማርጋሬት የባህሩ መዓዛ አፍንጫዋን አወዳት፡፡ ባቡሩ ወደ ወደቡ ተጠግቶ መጓዝ ጀመረ፡ የወደብ ክሬኖችና ባህር አቋራጭ መርከቦች በሰልፍ ቆመዋል፡፡ ምንም እንኳን ከእህቷ መለየቷ ቢያሳዝናትም ነፃ ለመውጣት መቃረቧን ስታስበው ልቧ በደስታ ይደልቃል፡

ባቡሩ ኢምፔሪያል ሃውስ የሚል ፅሁፍ ያለበት ትልቅ ህንፃ ጋር ሲደርስ ቆመ:፡ የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ እንደሌሎቹ ተሳፋሪዎች ሁሉ ሻንጣቸውን አንግበው ከባቡሩ ወረዱና የጉዞ ፎርማሊቲ ለማጠናቀቅ ህንፃው ውስጥ ገቡ፡፡ ዕቃ ያጨቁባቸው ሻንጣዎቻቸው ከባቡሩ ወደ አይሮፕላኑ
ተዛወሩ፡፡

ማርጋሬት በሃሳብ ደነዘዘች: በዙሪያዋ ያለው ዓለም በፍጥነት ተለዋውጧል፡፡ ቤቷን አገሯን ትታ ልትሄድ ነው:፡ አገሯ ጦርነት እሳት
ውስጥ ተማግዳለች፡፡ እህቷን ተነጥቃለች። ወደ አሜሪካ ልትሄድ ነው፡፡

‹‹አባት ለፓን አሜሪካን የበረራ መኮንን ኤልሳቤት እንደማትሄድ ሲነግሩት ‹‹ችግር የለም ቲኬቷን ለመግዛት የሚፈልግ ሰው አለ፡፡ ስለዚህ እሱን ለኔ ተዉልኝ›› አላቸው፡፡

ማርጋሬት ፕሮፌሰር ሃርትማን አንድ ጥግ ይዘው በሰላም ማጣት ሲጋራቸውን ሲያቦኑ አየቻቸው፡፡ ካሁን አሁን ተያዝኩ እያሉ ሲበረግጉ ነው የዋሉት፡፡ ያሉበት ሁኔታ ድንጉጥ አድርጓቸዋል፡፡ ‹እንደ እህቴ ያሉ ሰዎች ናቸው ፕሮፌስሩን ለዚህ ያበቁት ስትል አሰበች ማርጋሬት። ፋሺስቶች ከአገራቸው አባረዋቸው በቁሙ የሚባንን ሰው አደረጓቸው፡፡ ከአውሮፓ ለመውጣት ልባቸው መቆሙ አይፈረድባቸውም:፡

ፔርሲ በእንግዳ ማስተናገጃው ሳሎን ውስጥ ሆኖ አይሮፕላኑን ማየት ስላልቻለ ማየት የሚችልበት ቦታ መፈለግ ጀመረ፡፡ ሲመለስም በርካታ መረጃ ይዞ መጣ፡፡ አይሮፕላኑ በፕሮግራሙ መሰረት በስምንት ሰዓት እንደሚነሳ፤አንድ ሰዓት ተኩል እንደሚወስድበት፣ አየርላንድ ከእንግሊዝ ጋር ተመሳሳይ የሰዓት አቆጣጠር ስለምትጠቀም እዚያ የሚደርሰው ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ መሆኑን፣ ነዳጅ ለመሙላትና ለጉዞ
አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማመቻቸት ለአንድ ሰዓት እንደሚቆም እና አስር
ሰዓት ተኩል ላይ ጉዞ እንደሚጀምር ነገራቸው።

እዚህ ሳውዝ ሃምፕተን ወደብ ውስጥ ማርጋሬት ባቡሩ ላይ ያልነበሩ
አዳዲስ ሰዎችን አየች፡ አንዳንዶቹ ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ቀጥታ ዛሬ ጠዋት
የመጡ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ትናንት መጥተው ሆቴል ያደሩ ናቸው።
ከዚያም አንዲት ይህ ቀረሽ የማትባል ቆንጆ ሴት ከታክሲ ስትወርድ ታየች፡፡
ይቺ ዕድሜዋ ሰላሳ ቤት ውስጥ የሚገመት ፀጉረ ነጭ ሴት የለበሰችው
ልብስ ክሬም ሆኖ ላዩ ላይ ቀይ ነጠብጣብ አለበት፡፡ አንድ ተራ አለባበስ
የለበሰ ሰው አብሯት አለ፤ ሲያዩዋቸው ደስተኞች ይመስላሉ፤ ሰው ሁሉ
እነሱን ነው የሚያየው፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ አይሮፕላኑ ተሳፋሪዎቹን ለማሳፈር ዝግጁ መሆኑ
ተነገረ፡፡ ከዚያም ወደቡ ጥግ በተገነባ ቀጭን መተላለፊያ ላይ አልፈው አንድ በአንድ ወደ ሰማይ በራሪው ጀልባ ገቡ፡፡ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ቆሞ በባህሩ እንቅስቃሴ ወደ ላይ ወደ ታች ይላል፡፡ የተቀባው ብርማ ቀለም ጸሃይ ሲያርፍበት ያብረቀርቃል ግዙፍ ነው፡

ማርጋሬ እንዲህ አይነት ግዙፍ አይሮፕላን አይታ አታውቅም፡ የትልቅ ቤት ያህል ከፍታ ያለው ሲሆን ርዝመቱ ሁለት የቴኒስ ሜዳ
ያክላል፡ በሾጣጣ አፍንጫው ላይ የአሜሪካ ባንዲራ ተስሎበታል፡፡ ክንፎቹ ከፍ ብለው በጎንና ጎኑ ተሰክተዋል አራት ትላልቅ ሞተሮች ክንፎቹ ላይ የተገጠሙ ሲሆን ሞተሮቹ ጫፍ ላይ ረጃጅም አየር ቀዛፊ መዘውሮች
(ተርባይኖች) ይታያሉ፡፡

‹እንደዚህ አይነት ነገር እንዴት ሊበር ይችላል!

‹‹በሰማይ መብረር ከቻለ ቀላል ነው ማለት ነው?›› ስትል ጠየቀች ማርጋሬት፡፡

‹‹አይሮፕላኑ 92 ቶን ይመዝናል›› አለ ፔርሲ ካፏ ነጥቆ ‹‹ልክ ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ በሰማይ መብረር ማለት ነው፡፡››
እመቤት ኦክሰንፎርድ ወደ አይሮፕላኑ የሚወስደው ተንሳፋፊ መንገድ ላይ ከጎንና ከጎን ያለውን የብረት መደገፊያ ይዘው በፈራ ተባ ይራመዳሉ፡፡ባህሩ ውስጥ እወድቃለሁ ብለው ሰግተዋል፡፡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ደግሞ
ሁለቱንም ሻንጣዎች ይዘው ከኋላ ይከተላሉ፡ ሁሉም ወደ ሰማይ በራሪው
ጀልባ ገቡ፡፡

የአይሮፕላኑ ወለል ምንጣፍ የለበሰ ሲሆን ግድግዳው ግራጫ ቀለም ነው፡፡ ላያቸው ላይ የኮከብ ቅርጽ ፈንጠቅጠቅ ያለባቸው ሰማያዊ ሶፋዎች
ተገጥግጠዋል ከላይ ክብ ቅርጽ ያላቸው መብራቶች አሉት፡ በመጋረጃ የተጋረዱ አራት ማዕዘን ቅርጽ ያላቸው ትላልቅ መስኮቶች የሚታዩ ሲሆን የመስኮቶቹ ቅርጽ ቤት ውስጥ ያሉ እንዲመስሎት ያደርጋሉ፡ ከፊት ሁለት በሮች ይታያሉ

ኒኪ የተባለ የአይሮፕላኑ አስተናጋጅ እነ ማርጋሬትን ቀን ቀን ለመቀመጫ በመኝታ ጊዜ ደግሞ እንደ አልጋ የሚዘረጋ ሶስት ሰዎች የሚያስቀምጥ ሶፋ ወዳለው ቦታ ወስዶ አስቀመጣቸው: ሶፋዎቹ ትይዩ የተቀመጡ ሲሆን መሃከላቸው ላይ ጠረጴዛ ተኮፍሷል፡ ከመተላለፊያ በግራ በኩል ደግሞ እንደዚሁ ሁለት ሁለት ሰው የሚያስቀምጡ መሀከላቸ
ትንንሽ ጠረጴዛዎች ያሉባቸው ሶፋዎች ተደርድረዋል፡

አይሮፕላኑ ባህር ላይ ሆኖ
ከፍ ዝቅ ይላል፡ ልክ በተረት
እንደሚወራው እንደሚበረው ምንጣፍ ነው::ሞተሮቹ ይህን ግዙፍ ‹‹ቤት›› አየር ላይ እንዲንሳፈፍ ማድረጋቸው
ማርጋሬትን ገርሟታል።

ፔርሲ ከመቀመጫው ተነሳና ‹‹እስቲ ዞር ዞር ብዬ ልይ›› አለ፡፡

‹‹ቁጭ በል!›› ሲሉ አባት ደነፉ፡ ‹‹እዚህ እዚያ ስትንከወከው የሰው
መንገድ ትዘጋለህ››

ፔርሲ ደንግጦ ቁጭ አለ፡፡ አባት በቤተሰቡ ላይ ያላቸው የበላይነት
አሁንም እንዳለ ነው፡

እናት ፊታቸውን በፓውደር ያባብሳሉ፡ አሁን ለቅሶዋቸውን አቁመዋል፡

ማርጋሬት አንድ የአሜሪካውያን ያነጋገር ቅላጼ የሚናገር ሰው ‹‹ፊት
👍11
ብቀመጥ ይሻለኛል›› ሲል ሰማችና ዞራ ተመለከተች፡ ኒኪ ይህንን ሰው
የሚቀመጥበትን ቦታ እያሳየው ሲሆን ሰውየው ጀርባውን የሰጣት ስለሆነ ማን እንደሆን አላወቀችም፡፡ ሰውየው ጸጉረ ነጭ ሲሆን ሰማያዊ ሱፍ ልብስ ለብሷል ኒኪም ‹‹ደህና ሚስተር ቫንዴርፖስት ያሉት ቦታ መቀመጥ ይችላሉ፡

! ሰውየው ዞር ሲል ከማርጋሬት ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉ።ስሙ ቫንዴርፖስት አይደለም ሰውየውን ከዚህ ቀደም ታውቀዋለች፡
አሜሪካዊም አይደለም፡ ሄሪ ለማስጠንቀቅ ገልመጥ አደረጋት ሆኖም ዘግይቷል፡፡

‹‹ወይ እግዚአብሔርl›› ስትል ለራሷ አጉተመተመችና ‹‹ሄሪ ማርክስ!››
ስትል ተጣራለች፡....

ይቀጥላል
👍10😱3
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሚስ ካርይልና ወይዘሮ ቬን በዚያ በሚግለበለበው ነፋስ መኻል ከመንገዱ መታጠፊያ ቆመው ነበር። ሳቤላ ተደናግጣና ግራ ተጋብታ የመነጽሯን ስብ
ርባሪ ስትለቃቀም 'ሚስ ኮርኒሊያ ደግሞ ተገርማ ያን ነፋስ የገለጠውን ፊት ትመለከታለች። በደንብ የምታውቀው መልክ ነበር " ሆኖም ትኰረቷን የሰር ፍራንሲዝ መዝለቅ ለወጠው።

ፍራንሲዝ ሌቪሰን ወደ እነሱ ተጠጋ " ሚስተር ድሬክ ... ሁለተኛው ጓደኛውና ሌሎች
ጥቂት አዳማቂዎች አብረውት ነቀሩ እሱና ኮርኒሊያ ፊት ለፈት ሲገናኙ የመጀመሪያቸው ነበር " የጥላቻ ግንባሯን ቋጥራ በኩራትና በመራራ ንቀት
ተሞልታ ጠበቀችው እሱ ግን ከነሱ ዘንድ ሲደርስ ለትሕትና ብሎ ይሁን ወይ
ስለ ተደናገጠ ወይም ለማሾፍ አልታወቀም ባርኔጣውን ብድግ አደረገላቸው "

ለሚስ ካርላይል ግን ሊያሾፍ ያደረገው መሰላት ከንዴቷ ተነሣ ከንፈሯ
ዐመድ መሰለ "

“ እኔን ነው እንደዚህ የምትሰድበኝ . . . ፍራንሲዝ ሌቪሰን ? ''

" በመሰለሽ ተርጉሚው ? አላት እሱም ጅንን ብሎ "

አንተ ለኔ ባርኔጣ ልታነሣልኝ ትደፍራለህ ? እኔ ሚስ ካርላይል መሆኔን ረስተኽዋል ?”

“ አንቺን አንድ ጊዜ ያየሽ መቸ በቀላሉ ይረሳሻል” አላት በግልጽ እያሾፈ
አብረውት የነበሩት ሁለት ጓዶኞቹ ምን ማለት እንደሆነ ነገሩ አላምር ብሏቸው ይመ
ለከታሉ "

ሳቤላ ፊቷን እንዳያይባት ለመሸሸግ የሚቻላትን ስትሞክር የነሱ' የነገር ምልልስ የሰበሰባቸው ተመልካቾች ደግሞ ሥራዬ ብለው ከበው ያዳምጣሉ " ከነዚያ ተመልካቾች ውስጥ ጥቂት የስኳየር ስፒነር አራሾች ነበሩባቸው "

አንተ የተናቅህ ትል ጮኽችበት ኮርኒሊያ „ “ በማናለብኝነት በዌስት
ሊን እንደምትዘባነንበት በኔም የምትችል ይመስልሃል ? ደፋር መጥፎ አሁን ያዙት ! ብላ ስትጮህ ለሰውየው ፈጣን ቅጣት የሚስጥ አለ ብላ አስባ አልነበረም ከቦ የነበረው ሕዝብ ተዘጋጀቶ ይጠብቅ ኖሯል " ሚስ ካርላይል ደግሞ የፈለገው
0ይነት ጥፋት ቢኖራትም አካባቢው በጣም ያከብራት ነበር " እሁንም እንዲህ በሷ
አነጋገር ተነሣሥተው ይሁን ወይም የነሱ ጌታ እስኳየር ስፒነር ኢስት ሊን መጥቶ
ሳለ ያወሳውን የማድፈቅን ነገር ጠቁሟቸው ይሁን ወይም ከገዛ ስሜታቸው ተነሣሥተወ አይታወቅም እነዚያ ጫንቃ ሰፋፊ አራሾች እንቅስቃሴ ጀመሩ “ድፈቁት " ብሎ ኣንድ ድምፅ ሲጮሀ ሌሎች ያን ቃል እየተቀባበሉ ' ' ድፌቁት ድፈቁት ! ኩሬው ከዚህ ነው ! ማግኘት ከሚገባው ትንሽ እናቅምሰው ይህ ገፋፊ ሚስተር ካርላይልን ለመወዳደር ነው ዌስት ሊን የመጣው ? በእመቤት ሳቤላ የፈጸመው ነገር ምን ነበር ይህን ሥራውን እኛ ዌስት ሊኖች በቀላሉ አናየውም ዌስት ሊን
አይፈልገውም
" ዌስት ሊን እንደሱ
ያለውን ቀጣፊ አይፈልግም
ፊቱ ነጣ ስወነቱ በድንጋጤ ተናጠ " እንደሱ ያሉ ጥቅመ ቢሶች ብዙ ጊዘ ፈሪዎች ናቸው " ወይዘሮ ሳቤላም ስሟ ሲነማ ሰምቲ እንደሆነ እንጃ እንደሱ ትንዘፈዘፍ ጀመር " የዳር አጫፋሪዎቹን ሳይጨምር ኸያ ጥንድ የሚሆኑ ጠንካራ ሸካራ
እጆች ተረባረቡበት በርግጫ በጡጫ ቀጉሽምት ያዋክቡት ጀመር እዚያ የነበረው የቁጥቆጦ አጥር ተጠረማመሰ እሱን ከዚያ ላይ እየጎተቱ መሰዱት ከሚስተር ዴሪክና አብሮት የመጣው ጠበቃው ሁለተኛው ሰው ጠበቃ ነበር ድረገሐቱን ለመግታት ምንም አቅም አልነበራቸው ለመገላገል አስበው አንደኛው መናገር ሲጀምር
የማያርፉ ከሆነ እነሱንም መጨር ነው የሚል ምላሽ ሰሙ አጭር ወፍራም የነበረው ጠበቃ አድራጎቱ ሕገ ወጥ ረብሻ መሆኑን አልጎምጉሞ ካምባጓሮው ቦታ ውልቅ ብሎ ወጣ ሚስ ካርላይል በግርማ ሞገስ ቀጥ ብላ ቁማ ድርጊቱን ትመለከት ጀመር " ለማገላገል ፍላጎት ኖሯት እንደሆነ አልታወቀም
እንጂ መኻል ገብታ ልታላቅቀው ብትሞክርም ኖሮ ሰሚም ተቀባይም አታገኝም ነበር።

እያዳፉ እያንገላቱ ወደ አረንጓዴው ኩሬ ጠርዝ ወሰዱት ልብሱ ብዙ ከመቀዳደዱና ከመዘነጣጠሉ ሌላ የኮቱ ጅራትም ተቆርጦ ሔዶ ነበር " አንዱ ወደፊት ሲጎትተው ሌላው ከበስተኋላው ሲገፈትረው ' ሌላው አንገትያውን ይዞ ሲያንዞረው
የቀሩት ደግሞ በኩርኩም በጥፊ በቁንጥጫ በጉሽምታ መዓታቸውን
አወረዱበት "

“ ክተቱት ጎበዝ !”

ማሩኝ ! ማሩኝ !” አለና ጮኸ ጉልበቶቹን አጥፎ ጥርሶቹን እያንቀጫቀጨ።
“ ስለ ፈጣሪ ብላችሁ ማሩኝ ስለ ፈጣሪ ” አለ " ውሃው ተንቦጫረቀ ፍራንሲዝ
ሌቪሰን አረንጓዴ ከለበሰው ባሕር ውስጥ ተዘፈቀ » የልዩ ልዩ ነፍሳት መኖሪያና
መራቢያ ከሆነው ቁሻሻ ውሃ ሳይወድ እየጠጣ የደመ ነፍሱን ተፍጨረጨረ
ሰዎቹ እሱን ከተው ሲያበቁ ከዳር ቁሙው እየሣቁ አፌዙበት " ከበው የነበሩት
አዳማቂ ሕፃናት እየጨፈሩ እያጨበጨቡ ኰሬውን ዞሩ።

ነፍሱን ጨርሶ ከመሳቱ በፊት አወጡት » ኩምሽሽ ብሎ የከፋ ነጭ ፊቱ
የሚንዘፈዘፉት እግሮቹና ከመቀደዳቸውም በላይ ከኩሬው ተዘፍቀው ከወጡት ልብሶቹ ጋር ባጠቃላይ ሲታይ ከውሃ ገብታ ከሞተች አይጥ የበለጠ ያስከፋ ነበር "
ገበሬዎቹም የሠሩትን ሠርተው ሔዱ ይጨፍሩ የነበሩት ልጆቹም ከአካባቢው ጠፉ ፤ ሚስ ካርላይልም ሳቤላን አስከትላ መንገዷን ቀጠለች

መከራኛይቱ ሳቤላ
መንቀጥቀጡ አልለቀቃትም
ሚስ ካርላይል ምንም ሳትናገር አንገቷን ቀጥ አድርጋ ወደፊት ገሠገሠች "
ዐልፎ ዐልፎ ብቻ ዞር እያለች የማዳም ቬንን ፊት ታይና '' ይገርማል !ወይ መመሳሰል ... በተለይ ዐይኖቿ' ብላ እያሰበች ከአንድ መነጽር ቤት አጠገብ ደረሱ "
“ መነጽሬን እንዲሠሩልኝ ሰጥቻቸው ልለፍ ” ብላ ጎራ ስትል ሚስ ካርይል
ተከትላት ገባች
መነጽሩ እንዴት ሆኖ መሠራት እንደሚገባው አሳይታ አስረከበችው " ሌላ
ለመማዛት ብትፌልግ ከነጭ በቀር አንድም ባለ ቀለም አልነበረም " ተፈልጎ ተፈ
ልጎ • ከብዙ ዘመን በፊት አንድ ሰው ለማሠራት አምጥቶት ሳይወስደው የቀረ አንድ ጠርዙ አረንጓዴ የሆነ አስቀያሚ መነጽር ተገኘላትና አሱን አደረገች ኮርኒሊያ አሁንም ዐይን ዐይኗን ታያታለች

"ለምንድነው መነጽር የምታደርጊው ? አለቻት ገና ከቤቷ ሲገቡ።

" 0ይኖቼ ይደክብኛል ” አለች ጥቂት አስባ "

“ሲታዬ ጤነኛ ይመስላሉ "ነጩ ለሁሉም ሊያገለግል ይችላል !ለምንድነው
ባለ ቀለም የምትመርጪው ?”

“ ባለቀለም ስለ ለመድኩ ዛሬ ነጭ ለማድረግ ደስ አይለኝም "

ኮርነሊያ ዝም ብላ ቆየችና “ የክርስትና ስምሽ ማነው ማዳም ? አለቻት "

“ ጄን” አለች ሳቤላ ።

“ ኧረ ምን ነገር ነው ? ያ ምንድነው ?

በመንገዱ የሕዝብ ጮኽት ተሰማ ኮርኒሊያ ወደ መስኮቱ ተንደረደረች ሳቤላ
ተአተለቻት " ከሁለቱ ተቃራኒ አቅጣጫ ወደ አንድ መኻል የሚመጡ ይመስሉ ነበር። ባንድ በኩል ቀይና ወይን ጠጅ ዐርማ ያደረጉ የሚስተር ካርላይል ደጋፊዎች ዘለቁ ሎርድ ማውንት አስቨርንና ሚስተር ካርላይል ፊት ፊት ይመሩ ነበር "

የሌላው ወገን ባለ ብጫ ምልክት ሲሆን አመጣጡ
ስርአት የለሽ ትርምስምስ
ያለ ነበር ውሃ የገባች አይጥ የመሰለውን የሕዝቡ ግምባር መሪ አድርገው ጠበቃውና ሚስተር ድሬክ ደግፈው ይዘውት ዘለቁ " ጸጉሩ በሁሉም በኩል ተንዘርፍፎ እግሮቹ እየተንገዳገዱ ጥርሶቹ እየተንቀጫቀጩ ልብሱ ተሸረካክቶና ተዘነጣጥሎ ወደፊት ሲጓዝ መንገዱን አስከ ጫፍ ሞልተው የያዙት
ብዙ ሰዎች የማሾ ፋና የማናናቅ ጩኽትና ፉጨት እያስተጋቡ ተከትለውት ሲጓዙ ኮረሊያና ሳቤላ
ቁመው ተመለከቱ ።
👍13