አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ቀለበቱን ከቀረቀረችበት ኪሷ አወጣችና ቀጥታ በድፍረት ወደሰውዬው ጠረጰዛ በመሄድ ፊቱ ቅጭልጭል አድርጌ ስታስቀምጥለት አንዴ ቀለበቱን አንዴ ደግሞ እሷን አንዴ ደግሞ ሴትዬዋ ወደሄደችበት መታጠቢያ ቤት እያፈራረቀ ሲያይ ቆየና እጅን ወደ ኪሱ ሰዶ ፈተሸ..
"አልገባኝም ከየት አገኘሽው?"ሲል ጠየቃት፡፡
"ቅድም መታጠቢያ ቤት ስንጋጭ መሠለኝ ከኪስህ የወደቀው...ከወለሉ ላይ ነው ያገኘሁት...ወዲያው አምጥቼ እንዳልሰጥህ ሴትዬህን ፈራሁ…አልተሳሳትኩም ያንተ ነው አይደል?።››
"አዎ የእኔ ነው ..አመሠግናለሁ..ሲወድቅ ግን እንዴት ድምፅ ሳልሰማ?"
"ምን አልባት ቀልብህ ሴትዬህ ላይ ስለሆነ ይሆናል"አለችውና የእሱን መልስ ሳትጠብቅ ወደ ወንበራ ተመለሰች።
ልዩ በእፍረት እንደተሸማቀቀች ከእዛ ሆቴል ተያይዘው ወጡ …ከቤት ሌላ መኪና ተልኳላት ስለነበረ ቀጥታ ምንም ሳይነጋገሩ በራሷ ፍቃድ ወደእራሱ ቤት ይዛው ሄደች፡፡ ….ከዛ ሁለቱም እሱ አልጋ ላይ በመሀከላቸው መተው ያለበትን ክፍተት አስጠብቀው ጋደም በማለት ማውራት ጀመሩ….እርግጥ እራሷ ነች እንዲያወሩ የመጀመሪያውን የመነሻ ጥያቄ የጠየቀችው….
‹‹ግን ከሌባ ጋር ጎደኛ መሆን አልደበረህም?››ዝም ብላ በውስጧ ስታብሰለስል የቆየችውን ጥያቄ ድንገት የጠየቀችው፡፡
"ሰው ሁሉ እኮ ሌባ ነው"አለት

ገርሟት"እንዴት ማለት?"ስትል ጠየቀችው፡፡

"በየቀኑ አንዳችን የአንዳችንን የህይወት ኃይል ስንዘርፍ ወይንም አስገድደን ስንቀማ ነው የምንውለው"

"አሁንም አልገባኝም"

"እኔ አሁን ብጮህብሽ ባመናጭቅሽ አንቺ መላ አካልሽ ሽምቅቅ ይላል ፤ ሰውነትሽ ይንቀጠቀጣል፤እኔ ጩኸቴንና ስድቤን እየቀጠልኩ ስመጣ አንቺ እየተሸማቀቅሽ በራስ የመተማመንሽ እየወረደ ይመጣል ..ያ ማለት ኃይልሽን እየመጠጥኩና አንቺን ባዶ እያደረኩሽ ነው ማለት ነው…ከዛ ደካማና ሽቁጥቁጥ በማድረግ እኔ በራስ መተማመኔን አሳድጋለሁ ማለት ነው..አየሽ ታዲያ ይሄ እንደውም ረቂቅ ሌብነት ነው፡፡ ››
‹‹እና እቤት ሰራተኞች ላይ ስጮህና ሳንቧርቅባቸው….ሲሸማቀቁና ሲሽቆጠቆጡ..ኃይላቸውን እየሰረቅኩባቸው መሆኑ ነው፡፡››

‹‹አዎ ለዛውም የህይወት ኃይላቸውን…ሰው ተበሳጭቶ ተበሳጭቶ በመጨረሻ ምንድነው የሚሆነው..?ለመኖር ያለውን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ያጣል…፡፡ ያ ማለት ምን ማለት መሰለሽ...ለመኖር የሚያስፈልገው ኃይል ውስጡ የለም ማለት ነው….የት ሄደ…. በዙሪያው ባሉ በተለያዩ ሰዎች ቀስ በቀስ እየተዘረፈ እንዲሞጠጥ ተደርጎል ማለት ነው….እና ትልቁ ሌብነት የሰውን የውስጥ ሰላም ማሳጣት ነው፡፡››

‹‹እና አንተ ለዛ ነው…ለሰው አስተያየት በምትሰጥበት ጊዜ ስሜትህን አብዝተህ ለመቆጣጠር የምትጥረው…?››

‹‹አዎ በተቻለኝ መጠን ከማንም ጋር ቢሆን ሰላማዊ የሆነ፤ከጭቀቅጭቅ የፀዳ፤በቁጣ ያልታጀበ ..በእኩልነት ላይ የተመሰረት ንግግር ማድረግ ነው ምፈልገው..እንደዛ ሲሆን ማለቴ አሁን እኔና አንቺ በጓደኝነት መንፈስ ጎን ለጎን ተቀምጠን ፍትሀዊ በሆነ በእኩልነት ሚዛን ሀሳብ ስንለዋወጥ ኃይልም እንደዛው ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ እየተለዋወጥን ነው....ማለት ከእኔ ኃይል ወደአንቺ ይሄዳልም መልሶ ወደእኔ ይመጣልም …..የሁለታችንም ኃይል በእኩልነት እያደገ ደስተኛና ጤነኛ እየሆንን እንመጣለን..እና አንቺም ሁል ጊዜ ከሰዎች ጋር ያለሽ ግንኙነት እንደዛ እንዲሆን እንድታደርጊ ነው የምፈልገው፡፡››

‹‹እሞክራለሁ..ብቻ በውስጤ ያለውን ክፉ አመል በሆነ አስማታዊ ጨረር የሚያጠፋልኝ የሆነ መላአክ ቢኖር በህይወቴ የተከማቸውን ሀጥያት አንዴ ጥርግርግ አድርጌ በማፅዳት ንጽህ የሆነ ኑሮ ነበር መኖር ምኜቴ ››አለችው…የተናገረቸው ከአንጀቷ ነው…ልክ እንደእሱ አይነት ሰው መሆን ነው የምትፈልገው…

‹‹አይዞሽ.አንቺ ብቻ ከዚህ በፊትም እንደነገርኩሽ እራስሽን ለማከም ዝግጁ ሁኚ.. የልጅነትሽ ወይም የታዳጊነት የህይወት ክፍልሽ ላይ መድሀኒቱ ቁጭ ብሎ እንደሚጠብቅሽ ይሰማኛል….ከአባትሽ ጋር ያለሽ ግንኙነት እሱን በማጣትሽ የተፈጠረብሽ የስነልቦና ክፍተት፤ከእናትሽ ጋር የነበረሽ ግንኙነት…ብቻ በደንብ አስተውለሽ አሰላስይ….ከታሪክሽ የሆነ ጥግ ለምን የስርቆት ልክፍት እንደተፀናወተሸ የሚያስረዳ ምክንያት ይገለፅልሽ ይሆናል...ከዛ ዟምክንያቱን ባወቅሽ ቀን የበሸታሽ መርዝም በራሱ ይከስማል..ትድኛለሽ፡
አይን አይኑን በስስትና በአድናቆት እያየችው፡‹‹እንደቃልህ ይሁንልኝ››አለችው ፡፡
እና በሀሳብ ቁዝዝ አለች‹‹.አሁን እኔ ቃልዬ አንተን በጣም አፈቅርሀለሁ..ካየሁህ ቀንና ሰዓት ጀምሮ አንተን ከማለም ውጭ ሌላ ሀሳብ የለኝም ..ስለዚህ ምንም እንኳን ሴት ብሆንም በድፈረት እንድታገባኝ እየጠየቅኩህ ነውሪ’ዩ ››ልትለው ነው የምትፈልገው …ግን እነዛን ቃላቶች ከአንደበቷ አላቃ ማውጣት በድፍረት ለመጠየቅ ትልቅ እንቅፋት የሆናት እሱ በግልፅ ሚያውቀውን ድክመቷና ደግሞም በየሰው ቤት ካሜራ እየተከለች የሰው ሚስጥር የማነፍነፍ ክፍ በሽታዋ ምክንያት ነው፡፡

ቃል ‹‹.ትንሽ እንተኛ እንቅልፌ መጣ›አለና ወደእሷ በመዞር እጁን ተከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ በማቀፍ አይኑን ጨፈነ…..እሷም በተመሳሳይ ወደእሱ ዞረችና እጅን በትከሻው ላይ አዙራ አቀፈችውና ልክ እሱ እንዳደረገው አይኖቾን ጨፈነች…..ለመተኛት ፈልጋ ወይም እንቅልፍ ተጫጭኗት አይደለም…ፈፅሞ የእንቅልፍ ስሜት የለባትም…እፍረቱ እስከአሁን በደም ስራ እየተሰራጨ ነው..እና ደግሞ የመከራትም ነገር እያብሰለሰለችበትም ነው…

አባቷን ፍለጋ መንቀሳቀስ እንዳለባት ሰሞኑን ወስናለች፡፡ከዚህ በሽታዋ ለመፈወስ ምትችለው ሁለት ነገር ሳታደርግ እንደሆነ ሰሞንኑ ባደረገችው ማሰላለሰል ውሳኔ ላይ ደርሳለች፣..እንደኛው ከቃል ጋር ያለላትን ግንኙነት የሆነ መስመር ማስያዝ ስትችል..ከዛ ቀጥሎ አባቷን ፍለጋ መሰማራት ..ከዛ አባቷን በህይወት ካገኘችት ጥሩ ነው ፤ብዙ ጥያቄዎቼን ይመልስላታል..ቃል እንደሚለውም ምን አልባት የበሽታዋ መድሀኒት ከአባቷ መገኘት ጋር የተሳሰረ ሊሆን ይችላል……ስትል እምነት አድሮባታል..ሞቶም ከሆን የተንጠለጠለች ነፍሷ እርፍ ትልና ስለእሱ ማሰብ ታቆማለች፡፡

የቃልን ጉዳይ በቅርብ መቋጫ ልታበጅለት እንደሚገባ ተሰማት ‹‹….እንደውም ዝም ብዬ ከዛሬ ነገ እያልኩ ባንዛዛሁት ቁጥር ዛሬ እንደሰራሁት አይነት ሌላ ስህተት ፊቱ እሰራና ምንም ነገር ሳይል ከእጄ ሊሾልክብኝና እስከወዲያኛው ላጣው እችላለሁ…እንደውም ነገ ለምን አላደርገውም..አዎ ነገ..››ወሰነች ፡፡ውስጧ የሚጥለቀለቅ ደስታ መሰቃየት ጀመረ….ቃል ነቅቶ እጁን ከላዮ ላይ አነሳ፡፡ ከእንቅልፉ በመባነኑ በጣም ነው ደስ ያላት፡፡ውሳኔ ላይ ከደረሰችበት ደቂቃ ጀምሮ ወደቤት እስክትሄድ ቸኩላለች….ለምን ?ለነገ ለመዘጋጀት….ከአንድ ሰዓት እንቅልፍ በኃላ ሲነሳ ፈጠን ብላ ከአልጋዋ ወረደች፡፡
‹‹ልትሄጂ ነው እንዴ?››
‹‹አዎ እቤት የምሰራው ስራ አለኝ፡፡››
‹‹ልሸኝሽ ታድያ?››አላት.. አልጋውን ለቆ እየተነሳ..
‹‹አይ አልፈልግም…ቃልዬ ነገ ከሰዓት የምትሄድበት ቦታ አለ እንዴ?››ልስልስ ባለ አሳዘኝ ድምፅ ጠየቀችው፡
‹‹አይ ..ምንም ፕሮግራም የለኝም››
‹‹በቃ በጣም ለጥብቅ ጉዳይ እፈልግሀለሁ…ስድስት ሰዓት እዚህ እቤት እመጣለሁ…››
‹‹ከዛ የት ልትወስጂኝ ነው?››
‹‹የትም እዚሁ ነው ምናመሸው..ማለቴ ውለን ምናመሸው…. ነግሬሀለሁ…ስድስትሰ ሰዓት እመጣለሁ..ደግሞ እኔና አንተ ብቻ..ለጥብቅ ጉዳይ ነው የምልግህ››
👍8911🔥1🤩1
​​#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ሰውዬው አሁን ያለበት ቦታ ከዚህ እሷ ካለችበት ብዙም በማይርቅ ሌላ ሆቴል ውስጥ ነው..ግን   እየጠጣ አይደለም..ቤርጎ ውስጥ ሆኖ ነው የሚታያት፡፡ደግሞ ብቻውን አይደለም..አንድ ቅንጥስጥስ ያለች ለጋ ወጣት ክንዱ ላይ ተዘርራ በፀጉር የተሸፈነ ጥቁር ደረቱን እየዳበሰችለት  ነው…..እሱ ከወገቡ በታች ቢጃማ ሱሪ አድርጓል… ልጅቱ ግን በፓንት ብቻ ነች…ደግሞ የሰውነታቸው ቀለም ልዩነት ..እሷ ብጭጭ  ያለች ክልስ  የምትመስል ሴት ነች….ደግሞ ስዕል የመሰለ ውበት ያለት..

‹‹ይህቺን ይዘህ ነው ለካ በእኔ ላይ የጎረርክብኝ?››ስትል አሰበች....እና ይበልጥ የፉክክር መንፈሷ ተነቃቃ…

‹‹የእኔ ፍቅር አሁንም እንደተበሳጨህ ነው?››ልጅቷ ነች የጠየቀችው

‹‹በጣም  እኮ የምታናድድ ሴት ነች..አንተን በዛሬው ቀን  ካላወጣሁ እራሴን አጣፋለሁ ትለኛለች?››

(አሁንም ስለእሷ እያወራ መሆኑን ስታውቅ ውስጧ ሞቀ..የሚበላት አካባቢም ጨመረ)

‹‹ታዲያ ጤነኛ ነች ትላለህ?››

‹‹ጤነኛማ አይደለችም››

‹‹ታዲያ ንቀህ ተዋታ..ለምን  አትረሳትም .... ?መቼስ አሁን እኔ እቅፍ ውስጥ ነህ…መጠጡም እዚሁ ክፍላችን አለ.. እራቱም እዚሁ ነው የሚመጣልን..እኔን የመሰለች ዘበኛ አለህ እንዴት ብላ ከየት ታገኝሀለች..ነው ወይስ  እንደፎከረችው እራሷን ታጠፋለች ብለህ ሰጋህ?››

‹‹ፍግም ትበላ››

‹‹ተው ተው እደዛማ አይባልም…አሁን ለሚሰማህ ሰው አሪፍ ጨካኝ አትመስልም…ሁል ጊዜ እኮ አንደበትህ እና ሆድህ አይገናኝም……….››

‹‹እና እንዴት ነው የሚባለው?››

‹‹አይ ያን ያህል ከወደደችህማ እራሷን ከምታጠፋ አንዴ ብትቸገርላት?››

ገፍትሮ ከደረቱ ላይ አስፈነጠራት  ..
እየሳቀች ‹‹አትበሳጭ.. ቀልዴን እኮ  ነው›› አለችው ወደአስለቀቃት ቦታ እየተመለሰች

‹‹እንዲህ አይት ቀልድ አይመቸኝም ..ካንቺ ውጭ የሌላ ሴት ገላ ከማቀፍ እኔም እራሴን ባጠፋ ይሻለኛል…››

‹‹በቃ የእኔ ጀግና›› ብላ ወደ ደረቱ ተመለሰችና ከንፈሩ ላይ ተጣበቀችበት… ገለበጣትና እላዬ ላይ ተከመረባት…መሳሙን ሳያቆም በአንድ  እጁ የለበሰውን ቢጃማ ከሰውናቱ መዥርጦ አወለቀ..
በንስራ  ታግዛ እያየችው ያለው   ገበናቸው የወሲብ   ረሀቧን  ከምትቆጣጠረው በላይ  እንዲሆንባት አደረገው ፡፡

   እሷ ልትተኛው የፈለገችው ወንድ ከዕጮኛው ጋር በወሲብ ዳንኪራ እየጨፈረ ነው…እናም ደግሞ በራሱ ታማኝነት እንዴት ተመፃዳቂ እንደሆነ ከንግግሩ ለሁለተኛ ጊዜ መስማቷ የቅድሞውን ብስጭቷን  በእጥፍ እንዲጨምር አደረገው…
ሂሳቧን ከፈለችና መቀመጫዋን ለቃ ወደመኪናዋ አመራች ..መኪናዋን  አስነሳችና  ሰውዬዋ ወዳረፈበት ሆቴል ነዳችው… ንስሯም በሰማዩ ላይ ጭለማውን ሰማይ እየሰነጠቀ ከላይ እየተከተላት  ነው፡፡
ንስሯ‹‹ፍቅራቸውን እና መተማመናቸውን አየሽ አይደል…?ተይው በቃ….››የሚል መልዕክት አስተላለፈላት

‹‹አልተውም.. የማታግዘኝ ከሆነ በራሴ እወጣዋለሁ….››መለሰችለት ለንስሯ

‹‹በራስሽማ የበለጠ ጥፋት ታጠፊያለሽ››

‹‹እንግዲያው ዝም ብለህ በቀላሉ ያሰብኩትን እንደሳካ አግዘኛ››
ንስሩ የመስማማት ምልክት አሳያት ..

አሁን ሆቴል ደረሰችና መኪናዋን ቦታ አስይዛ አቆመችና ሞተሩን አጠፋች ….በቀጣይ ምታደርገውን  ነገር ግን ገና አላወቀችውም .. መኪናዋ ውስጥ ሆና ትኩረቷን ስብስባ  እና ከንስሯ እይታ ጋር እይታዋን በማጣመር  ልክ ለስለላ በድብቅ እንደተቀበረ ካሜራ    ክፍላቸውን ወደመቃኘቱ ተመሰች
አሁን ፍቅረኛሞቹ  ስራቸውን ጨርሰው ሻወር ቤት ግብተዋል…እየታጠቡ ነው ፡፡በመታጠባቸው ውስጥ መተሸሻት ..በመተሻሸታቸው ውስጥ ከወሲባዊ  እርካታ በኃላ ያለ ድሪያ አይነት ማሽካካት ይታይባቸዋል…..  ታጥበው ከጨረሱ በኃላ  ሁለቱም ፎጣ አገልድመው ሻወሩን ለቀው በመውጣት አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አሉ….እሱ ተንጠራራና ፊት ለፊታቸው ካለው ጠራጴዛ የወይን ጠርሙሱን በማንሳት የጎደለውን የወይን ብረጭቆ በመሙላት  አንስቶ ሰጣት ..ለራሱም አነሳና ተጎነጨ ….እሷ ግን ጠቀም አድርጋ ተጎነጨችና አፏን ወደእሱ አሞጠሞጠች …ከፈተላት.. በጉንጮቾ ያቆረችውን  ወይን በከፈተላት ጉንጩ ውስጥ ገለበጠችለት››ይሄንን ስታይ የሆነ ምቾቷ እየቀነሰ መጣ….ያልተለመደ አይነት ሆነባት፡፡

‹‹አሁን ሰርጋችን ቀን  መቼ እናድርገው?››እሱ ነው አይን አይኗን በስስት እያያት የጠየቀው፡፡

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹በእኔ በኩል  በጣም በቅርብ መሆን አለበት ባይ ነኝ››

‹‹ቅርብ ስትል? ››

‹‹በሚቀጥለው ወር ውስጥ››

‹‹እርግጠኛ ነህ….?እኔ ግን  ያለችንን ጊዜ እንደዚሁ  በፍቅር ብናሳልፋት ይሻል ይመስለኛል፡፡

‹‹አንቺ ደግሞ ስንት ወር ያወራንበትን ነገር ከእንደገና ወደኃላ ትመልሺዋለሽ ..አድሮ ቃሪያማ አትሁኚ››ኮስተር ብሎ መለሰላት

‹‹የእኔ ፍቀር ላንተው እኮ አስቤ ነው…ከዚህ ጋብቻ  መሳቀቅ ብቻ ነው የሚተርፍህ  ››
ያንን ጥቁር ፊቱን ይበልጥ አጨልሞ ‹‹ግድ የለም ለእኔ አታስቢ..አንቺ ባለችሽ ጊዜ ቶሎ ቶሎ መኖር መቻል አለብሽ ፡፡.ድል ባለ ሰርግ ማግባት …ልጅ ወልዶ ማቀፍና ማጥባት ላንቺ የሚገቡሽ ነገሮች ናቸው››አላት 

‹‹ትቀልዳለህ…..ከዚህ በፊትም ነግሬሀለው …ዛሬም እንደግምልሀለው የማላሳድገውን ልጅ በፍጽም አልወልድም››

‹‹እንግዲህ ነግሬሻለሁ…

ካልወለድሽልኝ አንቺ ጥለሺኝ ስትሄጂ የምጽናናበት ነገር ስለሌለ  ያው ከሸኘሁሽ በኃላ እራሴን በማጥፋት እንደምከተልሽ እና  በምትቀበሪበት ጉድጓድ አብሬሽ እንደምቀበር አትጠራጠሪ››

‹‹ለምን ታስጨንቀኛለህ?››

‹‹እያስጨነቅኩሽ አይደለም…በትክክል የማደርገውን እየነገርኩሽ ነው…አንቺ ስለመሞትሽ ማሰብን  እርሺውና በየቀኑ ማድረግ የምንችለውን እናድርግ.. እንጋባ… ውለጂልኝ..ከዛ በኃላ ያለውን ነገር ለእግዜር እንተወው ..ምን ይታወቃል የሆነ ተአምር ተፈጥሮ በሀኪም ከተቆረጠው የመሞቻ ቀንሽ በፊት ፈውስ የሚሆን መድሀኒት ይገኝ ይሆናል››
ኬድሮን በምሰማው ነገር እየደነዘዘች ነው።

ይቀጥላል
👍1109😱5🥰1👏1😢1
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሁሴን ኢትዬጵያን ለቆ ከሄደ ሁለት ወራት አለፈው፡፡ትንግርት ሙሉ ለሙሉ የስራ አስኪያጅነቱን ቦታ ለመለማመድ ደፋ ቀና እያለች ስለነበር ብቸኝነቱ ብዙም አልከበዳትም፡፡ በዛ ላይ እንደ ጓደኛም እንደ እህትም የምትንከባከባት ፎዚያ ከጎኗ አለችላት፡፡ስራውም ቢሆን አልከበዳትም..፡፡

ሁሴን ትንታግ የሆኑ ጋዜጠኞችን ነው አደራጅቶላት የሄደው ፡፡እነሱን መምራት፤መምራት እንኳን አይባልም ማስተባበር ብዙም አልከበዳትም፡፡

ትንግርት ዛሬ በጥዋት ተነስታ ወደ ቢሮዋ ገብታለች፡፡ የወጪ ሰነዶች፤የተገዙ ዕቃዎች ዝርዝሮች የመሳሰሉትን የቀረቡላትን ሪፖርቶች በጠቅላላ በዝርዝር አየችና የሚፈረመውን ፈርማ የሚሰረዘውን ሰርዛ ጨረሰችና.. በሚቀጥለው ቀን እሁድ ለሚታተመው ጋዜጣ የተዘጋጁ ፅሁፎችን በየደርዛቸው ማንበብ
ጀመረች፡፡ቅር ያለት ቦታ ቆም ትልና መልሳ ታነበዋለች፤ካልተዋጠላት በማስታወሻዋ አስፍራ ወደ ሚቀጥለው ትሸጋገራለች፤ እንዲህ እንዲህ እያለች ጨርሳ ቀና ስትል ሁሉም ሰራተኞች ገብተው የአለት ስራቸውን ተያይዘውት ነበር፤ዋና አዘጋጁን ኤልያስን ጠራችው፡፡ ወደእሷ ተጠጋና ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ፡፡

‹‹ምነው ጥቁርቁር አልሽ ?ሁሴን ናፈቀሽ እንዴ?››

‹‹ገና ሶስት ወር ሳይሞላው እስክጠቁር ድረስ ሚናፍቀኝ ይመስልሀል?››

‹‹ለምን አይመስለኝም፤ የሚያፈቅሩት ሰው ለአንድ ቀንም ቢሆን ከፊት ዞር ሲል ማንገብገቡ የት ይቀራል?››

‹‹ባክህ እሱ ለእንደናንተ ዓይነቱ ነው፡፡ አሁን የሀዋሳውን ልጅ እንዴት እንደምናገኘው ነው ግራ የገባኝ?ባለፈው አይደል ላይ ልጆቹ ሲወዳደሩ ያየሁት እና ትናንትና ድጋሚ በደቡብ ቴሌቨዥን አየሁት ያልኩህን ፤ሁኔታው በጣም ነው ያስደመመኝ፡፡እንዲህም የሚያስብ ሰው አለ እንዴ.?ብዬ እራሴን ደጋግሜ እንድጠይቅ ነው ያደረገኝ፡፡ፈጽሞ ከአዕምሮዬ ላወጣው አልቻልኩም፡፡

‹‹እሱስ እኔም በጣም ነው ያስደመመኝ… የልጆቹ ብቃትማ አፍ ያስከፍታል፡፡››

‹‹አንድ ነገር አስቤያለሁ፡፡››

‹‹ምን አሰብሽ?››

‹‹ታሪኩን በጋዜጣችን መዘገብ፡፡››

‹‹ቴሌቭዥኑን እንደምንጭነት ተጠቅመን?››

‹‹አይደለም... ቦታው ላይ በመሄድ ልጁንም ከነልጆቹ በማግኘትና በጥልቀት በማጥናት፤ቃለ መጠየቅ በማድረግ ፤ዶክመንተሪ በመስራት፡፡››

‹‹እሱ ትክክል ነሽ.. ከፈለግሽ አድራሻውን ላገኝልሽ እችላለሁ፡፡››

‹‹በእውነት ..እንዴት?››

‹‹ኢንተርቪውን የሰራው ጋዜጠኛ የማውቀው ልጅ ነው፡፡ደውዬለት አድራሻውን እንዲሰጠኝ ቀጠሮም እንዲያሲዝልን ማድረግ እችላለሁ፡፡››

‹‹አይ ጭንቅላት ነበረ እኮ!!! ይህቺ ሀገር አልተጠቀመችብህም እንጂ፡፡››በማለት ከአንጀቷ አሞገሰችው፡፡

‹‹ያው ባልሽ እና አንቺ እየተፈራረቃችሁ ጥፍጥፍ አድርጋችሁ እየተጠቀማችሁብኝ አይደል..?››

‹‹በላ አሁንኑኑ ደውልለት፡፡››

<<አሁን??>>

<<አዎ አሁን>>

በገረሜታ ሞባይሉን ከኪሱ አወጣና ደወለለት፤ሁኔታውን በዝርዝር አስረዳው፤ከአደራ ጋር ውለታውን ጠየቀና በመሰናበት ስልኩን ዘጋ፡፡

‹‹ከተሳካ አሪፍ ምሳ ግብዣ አለህ›፡፡›አለችው፡፡

‹‹ለእኔ ሳይሆን ሀዋሳ ስትሄጂ ጓደኛዬን በመጋበዝ ለውለታው ታመሰግኚልኛለሽ፡፡››

‹‹ቃሌን ሰጥቼሀለሁ›› አለችው፡፡

ከሁለት ቀን በኃላ መልሱ መጣ‹‹ተሳክቷል››አላት ኤልያስ ተንደርድሮ ከውጭ ወደ ቢሮ እየገባ ነው የሚናገረው፡፡

‹‹አትለኝም..!!››በደስታ ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡

‹‹አዎ አልኩሽ ሁሉ ነገር ዝግጁ ሆኗል፡፡››

‹‹በጣም ደስ ብሎኛል፡፡››

‹‹እኔም..እና መቼ ልትሄጂ ነው?››

‹‹አይ አብረን ነው የምንሄደው፡፡አንተ ለጋዜጣው የሚሆን ዘገባ ትሰራለህ….እኔ ደግሞ ይሄንን ሰውዬ ገፀ ባህሪ አድርጌ አንድ ምርጥ መፅሀፍ መፃፍ እፈልጋለሁ፡፡ ተዘጋጅ ነገ በጥዋት እንሄዳለን፡፡››

<<ነገ ነገውኑ>>

‹‹አዎ... የሚሰራ ስራ እጅህ ላይ ካለ ለሌሎቹ አስተላልፍ..ለሶሰት ቀን ሀዋሳ ነን፡፡››

‹‹ተቀብያለሁ ኮማንደር ››አላት ቅፅበታዊ ውሳኔዋ አስገርሞት፡፡

በማግስቱ ትንግርት መኪናዋን እያሽከረከረች ከኤልያስ ጋር ከረፋዱ 5 ሰዓት አካባቢ ሀዋሳ ከተማ ደረሱ፤እንደደረሱ የኤልያስን ጓደኛ ጋዜጠኛውን አገኙት፡፡

‹‹እሺ ለመቼ ልቅጠርላችሁ?›› አላት ትንግርትን፡፡

‹‹ከተቻለ አሁኑኑ ባገኘው ደስ ይለኛል፡፡››

‹‹ከተመቸው ልደውልለት >>አለና ሞባይሉን አወጥቶ ታዲዬስ ጋር ደወለለት...

ስልኩ ሲደወል ታዲዬስ እና ዶ/ር ሶፊያ ሰሜን ሆቴል ምሳ እየበሉ ነበር..ዶ/ር ሀዋሳ ለስራ ከመጣች አንድ ሳምንት ያለፋት ቢሆናትም ታዲዬስና ልጆቹ ዙሪያ ስትሽከረከር በራሷ ፍቃድ እስከዛሬ ቆይታለች ..ዛሬ ግን የግድ መሄድ አለባት፡፡ታዲዬስን ለመጨረሻ ጊዜ ልትሰናበተው ነው በስንት ጭቅጭቅ ለዚህ የምሳ ግብዣ በማሳመን አሁን አብራው ያለችው፡፡

‹‹ማን ነው የደወለልህ?››

‹‹ከአዲስአበባ የመጡ እንግዶች ናቸው፤ቢቀላቀሉን ቅር አይልሽም ብዬ ነው እዚህ የቀጠርኳቸው› .አላት፡፡

<<ችግር የለውም..እነሱ እስኪመጡ ካወራን ይበቃናል፤ከዛ ወደማልቀርበት ሀገሬ ጉዞ እጀምራለሁ፡፡››

‹‹ጥሩ ዕቅድ ነው፡፡››አላት፡፡

‹‹በናትህ ግን፤ ቢያንስ በቀን አንዴ መደዋወል አለብን፡፡››

‹‹በቀን አንዴ!!!››

‹‹ምነው ችግር አለው?››

‹‹እንዴ በየቀኑ ተደዋውለን የምናወራው ርዕስ ከየት እናመጣለን?››

<< ደግሞ መደወል እንጂ የሚወራ ርዕስ ይጠፋል?››

‹‹አዎ..እኔ በየቀኑ እየደወልኩ ፍሬ ቢስና ተደጋጋሚ ሀሳብ እያላዘንኩ ያንቺንም የእኔንም ወርቅ ጊዜ አላባክንም..በዛ ላይ ስልኩም በሳንቲም ነው የሚሰራው፡፡››

‹‹እኔ እኮ ነኝ የምደውልልህ?››

‹‹አንቺ ደወልሽ እኔ ምን ለውጥ አለው? ለማንኛውም በሳምንት አንድ ቀን ከተደዋወልን
ወዳጅነታችንን ለማቆየት በቂ ይመሳለኛል፡፡››

‹‹እንዴ!!! በሳምንት አንድ ቀን... ጨካኝ ነህ፡፡››

‹‹ጭካኔን እዚህ ላይ ምን አመጣው?››

‹‹ትቀልዳለህ?ስሜት የለህም እንዴ? ናፍቆት የሚባል ነገር በልብህ አይበቅልም ማለት ነው?>>

‹‹ኧረ ንግግርሽን አጠጠርሽው፡፡እኔ ቀላል ነገር ነው የተናገርኩት፡፡ስልክን አግባብ ለሆነ ነገር በስርዓት መጠቀም አለብን ብዬ የማምን ሰው ነኝ፡፡ምክንያት እየፈጠርን በየሰከንዱ እዚህም እዛም እየደወልን ገንዘባችንንም ጊዜያችንንም ከማባከናችንም በላይ የምንደውልለትንም ሰውዬ ጊዜውን እናባክንበታለን፡፡ደግሞ ሰውዬው የማውራት ፍላጎት አለው ወይ?

ሚመች ቦታ ላይ ላይሆን ቢችልስ?ስራ ላይ ይሆን እንዴ?ትዝ አይለንም፡፡መጫኛ የሚያህል ውል የሌለው ፍሬከርስኪ ወሬያችንን እንተረትራለን..እንዲህ አይነት ነገር አይመቸኝም፡፡ለማንኛውም በሶስት ቀን አንዴ እንደዋወላለን፤ከዛ በላይ የተለየ ነገር ካለሽ በመልዕክት ልትልኪልኝ ትችያለሽ ..በቃ፡፡››

‹‹በየቀኑ ብደውልልህስ?››

‹‹አላነሳልሽም፡፡››

<<እንዴ.!!!>>

በዚህ ጊዜ የታዲዬስ ሞባይል ዳግመኛ ጮኸች፡፡አነሳ፡፡ እንግዶቹ ናቸው እጁን ወደላይ አንጠልጥሎ ያለበትን ቦታ ጠቆማቸው፡፡ ትንግርት፤ኤልያስ እና ጋዜጠኛው ወደእነሱ ተጓዙ፡፡ ዶክተር ሶፊያ ጀርባውን ሰጥታቸው ነው የተቀመጠችው፡፡ደረሱ

‹‹ታዲዬስ›.አለችው ትንግርት ፊት ለፊት የምታየው ፈርጣማ ወጣት በቲቪ ካየችው ምስል ጋር አልገናኝ እያላት ...በዚህ ጊዜ ዶ/ር ሶፊያ ልብን የሚሰነጥቅ አስደንጋጭ ድምፅ ነበር በጆሮዋ የገባው፡፡ በደመነፍስ አንገቷን ጠምዝዛ ዞር አለችና ‹‹ትን..ግር.ቴ.......››አለች፡፡
👍9912😁4👏1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


እሷ እየተንደረደረች ወደቤቷ ገባችና ፎቁን ወጣች መኝታ ቤት ገባች፡፡ የሆነ ነገር አደናቅፎት እንዳትወድቅ እንኳን  መብራቱን  ማብራት  አልፈለገችም።በዳበሳ ከልጋዋ ላይ ወጣችና ጠርዙን ያዘች፡፡ ወደ ኮመዲኖ ተንጠራራች ቀን በጅምር ያቆመችውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳችና ክዳኑን ከፍታ አንደቀደቀችው።

"እስኪ ይሄ ምስኪን ልጅ ምን አደረገኝ?"እራሷን እረገመች። ምነው እግሬን በሠበረው በማለቱ ወደእሱ በመሄዶ እራሷን ወቀሰች፡፡
….////…
ሳባ አሁን በዚህን ሰዓት 80ሺ ብር የተገዛ ባለ 2 ሜትር የተንጣለለ ግዙፍ አልጋ ጠርዝ ላይ ተኝታ  ያቺን ከዛሬ 10 ዓመት በፊት የነበረችዋን  የዋህ  ንፅህ  ጉጉ ተስፈኛ ወጣት አብዝታ እየናፈቀቻት ነው፡፡አሁን ያላትን  ሀብትና  ንብረት  ሁሉ ከፍላ ይቺን ሚስኪን ወጣት ከነሙሉ ክብሯ፤ ንፅህናዋና፤ የዋህነቷ እንዲውም ከሙሉ ተስፋዋ ጋር ቢመልሱላት ዓይኗን ሳታሽ ነበር የምትስማማው፤ ግን ያንን ማድረግ እንደማይቻል ስታውቅት ተስፋ ቆርጣ ይበልጥ አንገት ያስደፋታል፡፡
ደግሞ ይህ ተስፋ መቁረጧ ጫፍ ላይ አድርሶ እርሷን እንድታጠፋ እና ካለችበት ቅዠት እንድትገላገል ቢያግዛት  ደሰተኛ  ትሆን  ነበር፡፡ግን  ህይወትን  በአዲስ መንፈስ አድሳ ከድባቴ እራሷን አላቃ ከሚወቅራት እራስ ምታትና ከሚያኮረማምታት የመንፈስ መሰበር ተላቃ አዲስ ህይወት ለመጀመር የሚያስችላት አቅም ለማግኘት ሆነ እስከዛሬ ባለፈችበት የሀጥያት  መንገድና የተበላሸ የህይወት መስመር የተነሳ እራሷን ተጠይፋ ከህይወት መዝገብ  ላይ በፍቃዷ እራሷን ለማሰናበት የሚያስችል ብቃትና ፅናት ማግኘት አልቻለችም፡፡ያ ደግሞ በአየር ላይ አንገትን በገመድ ታንቆ እንደመንጠንጠል አይነት የሚያቃትት ስሜት ነው እንዲሰማት እያደረጋት ያለው፡፡
አሁን እንደዚህ ምስቅልቅል ባለ ህይወት ላይ ሆና ለሚያያት ሰው ምን ሆነሽ ነው
?ብለው ቢጠይቋት እንዲህ ሆኜ ነው ብላ በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ የምትመልሰው ለሰሚው ሚዛን የሚደፋና ለእሷም እንዲያዝኑላት የሚያደርግ ምንም ምክንያት የላትም… ምክንያቱም ትክክለኛ ምክንያቷን(ነፍስ ገዳይነተዋን)መናገር አትችልም…ብትናገር ማረፊያዋ እስር ቤት ነው፡፡
እነዛን ሚስጥሮች የማያውቁ  ሰዎች ደግሞ‹‹ባፈቀረችውና ልቧን አሳልፋ በሰጠችው ሰው የመከዳት ችግር አልገጠማትም ..የገንዘብ እጥረት ወይም ኪሳራ ፍፅም የለባትም..የሆነ ወንጀል ሰርታ የተከሰሰችበት ጉዳይ ፈፅሞ የለም..የህክምና ምርመራ አድርጋ እንዲህ አይነት ቋሚ የጤና ችግረ አለብሽ ተብሎ አልተነገራት…ታዲያ ምንድነው እንዲህ የሚሰባብራት?›› ብሎ ቢያስብና ቅብጠት ነው ብሎ ፍርድ ቢሰጥ አይገርምም፡፡
እውነታው ግን አሁን በዚህ ወቅት የሳባ መንፈሶ ተሰብሯል ፤የመኖር ጉጉቷ ተንቆሻቁሾል፤በውስጧ ምንም አይነት  የደስታ  ቅመም  መመረት  ካቆመ ሰነባብቷል፡፡ የመኖርም  ሆነ  የመሞት  ፍላጎቷን  አጥታለች፡፡ማፍቀርም  ሆነ መፈቀር ሳይቀር ትርጉመ ቢስ ሆኖባታል፡፡በአጠቃላይ ስሜተ ቢስ እየሆነች ነው፡፡እንደሚታወቀው ስሜት ማለት የሠው  ልጅ  መንፈሳዊ  ወዝ  ነው።  የሰው ልጅ ህይወትን ጣፍጭና ወዝ ያለው የሚያደርገው የስሜቱ ውጣ  ውረድ ነው ። ሰው ሲከፍው ከላለቀሰና ሲደሰት ካልሳቀ ከፍተኛ የስሜት መሠበር እንዳለበትና ጠንካራ ህክምና እንደሚያስፈልገው በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል።ጠንካራ ስሜት ያላቸው ሰዎች ህይወታቸው ደማቅና ከሩቅ ትኩረት የሚስብ ናቸው።ግን ደግሞ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሲሰበሩም በትልቁና በቀላሉ ነው፧፡ለዚህ  ነው  የሠውን ስሜት መስበር አስጠሊታ ሀጥያት የሚባለው።
እለቱ ማክሰኞ እኩለቀን አካባቢ ነው።ሰራተኛዋ አለም የምትሰራውን ሰርታ ወደቤት ለመሄድ ስትወጣ ቀናውን በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ እንደወትሮው ሲያነብ አገኘችው፡፡ኮቴዋን ሲሰማ ቀና ብሎ ‹‹ልትሂጂ ነው?››አላት፡፡
‹‹አዎ ልሄድ ነው….ግን አንድ ነገር ላማክርህ ነበር፡፡›› ከመቀመጫው ተነሳና ፊት ለፊቷ ቆመ‹‹ምንድነበር?››ጠየቃት፡፡
‹‹የዚህች ልጅ ነገር በጣም አሳስቦኛል…ይሄው መኝታ ቤቷ ከተሸሸገች ሁለት ወር ሊደፍናት ነው..ምግብ አትበላ፤ መጠጣትና ..መተኛት ብቻ ነው ስራዋ…፡፡አሁንማ ሰውነቷ አልቆ አልቆ ስንጥር አክላለች..በዚሁ ከቀጠለች በጥቂት ሳምንታት ውስጥ መሞቷ አይቀርም፡››
‹‹የእሷ ነገር እኔንም አሳስቦኛል…..አንቺ ምን አሰብሽ?››
‹‹እንዴ ግራ ገባኝ ..ከቤት መውጣት እምቢ ካለች፤ ህክምናዋና ካቆረጠች፤ መብላትና መጠጣት ካቆመች..እራሷን ቀስ በቀስ እየገደለች እኮ ነው….አንድ ነገር ከሆነች ደግሞ እኔና አንተ መጠየቃችን አይቀርም.. በተለይ እኔ……በጣም አሳስቦኛል፡፡››
‹‹ቆይ ዘመዶች የሏትም እንዴ?››
‹‹አላት …አሰላ ናቸው እንጂ  ዘመዶች  አሏት  ፡፡እሷ  ግን  ያለችበትን  ሁኔታ ለማንም እንዳንናገር በጥብቅ ነው ያስጠነቀቀችኝ…ግን አሁን አሁን ምርጫ የለኝም..ግፋ ቢል ስራውን መልቀቅ ነው፣ እስር ቤት ከመግባት ስራዬን ባጣ ይሻለኛል…እንደምንም የእንጀራ እናቷን ስልክ አግኝቼያለሁ…ልደወልላት ነው፡፡››
‹‹እኔ የሆነ ነገር አስቤ ነበር››አላት ቀናው፡፡

‹‹ምን?››
‹‹አሁን አልነግርሽም…ግን አንድ ሳምንት ይፈጅብኛል..እንደምንም አንድ ሳምንት ጊዜ ስጪኝና ልሞክር… እስከዛ ምንም ለውጥ ካላሳየች እንዳልሺውም ትደውይላቸዋለሽ፡፡››
ለተወሰነ ደቂቃ እንደማሰብ አለችና‹‹..እሺ  ካልክ…እስከዛሬ  ያልሞተች  መቼስ በአንድ ሳምንት ውስጥ አትሞትም ››ብላ ተሰናበተችውና  ወጥታ  ሄደች፡፡ቀናው ወደ ነበረበት መቀመጫ ተመልሶ ተቀመጠና ማሰላሰል ጀመረ..ምን  አድርጎ ቀጣሪው ከገባችበት የመደበት ስሜት ሊያወጣት እንደሚችል አሰበ …ቢያንስ የተወሰነ ቀና ብላ ወደህክምና ክትትሏ እንድትመለስ ማድረግ እንዳለበት ወሰነና ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ግቢውን ቆላለፈና   አነስተኛ ምንጣፋና አንድ መፅሀፍ ይዛ ወደ ትልቁ ቤት ገባ።
የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ውስጡ እየገፋፋው ነበር የከረመው ዛሬ  ደግሞ የአለም ንግግር በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር አስገደደው…እርግጥ ከእሷ የሚያጋጥመውን መልስ ምን እንደሚሆን አያውቅም ግን ምንም ሆነ ምንም ለመጋፈጥ ወስኗል......ሳሎኑን አልፎ ወደፎቅ የሚወስደውን ደረጃ ተያያዘው... መኝታ ቤቷን ቀስ ብሎ ገፍው፡፡ አንገቱን  አሰገገና  ወደ  ውስጥ  ተመለከተ... እንደዚህ ባለ ቅርበት ካያት  ብዙ  ቀናት  አልፈዋል....ፀጉሯ  ተንጨፍርሮና  እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ አስፈሪ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ሆዷ ከጀርባዋ የተጣበቀ ነው የሚመስለው ፤በጣም ከስታለች፤ አይኖቾ ኮርኒሱ ላይ እንደተሰካ ነው ወደ ውስጥ ዘልቆ ገባና መልሶ ዘጋው።በዚህ ጊዜ አይኖቾን አንከባለለችና ወደእሱ ተመለከተች
..የሆነ ነገር እንድትለው ፈልጎ ባለበት ተገትሮ ቆመ...፡፡
ምንም አላለችውም..ወደጥግ ሄደና ግድግዳውን አስጠግቶ ምንጣፉን አነጠፈ... እንደብዲስት መነኩሴ እግሩን አጣምሮ ቁጭ አለ።መፅሀፍን ከፊት ለፊቱ አስቀመጣና እጇቹን አቆላለፈ...ከዛ ልክ እንደእሷ ፀጥ አለ...ልዩነቱ የእሷ ፀጥታ በድንዛዜ ሲሆን የእሱ ፀጥታ በንቃት ነበረ...
👍559🔥1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

ኩማንደሩ ቢሮ ቁጭ ብሎ እያሰበ ነው…የሚያስበው አዲስ ነገር አይደለም፡፡እድሜ ልኩን ሲያስበው ስለኖረው ነገር ነው..ስለ ሰሎሜ፡፡

ጥዋት ላይ አላዛር ከቱርክ ደውሎለት ነበር፡፡ምንም የሚያስደስት ነገር አልነገረውም፡፡ለዛም ነው ቀኑን ሙሉ ሲጨፈግገው የዋለው፡፡
‹‹አሌክሶ እድሜ ለአንተ ሳልፈወስ አልቀርም››የሚለው ንግግሩ ደጋሞ በጆሮዎቹ ላይ እያንቃጨለበት ነው፡፡

‹‹ሳልፈወስ አልቀርም ነው.ወይስ ተፈውሼለው?››

‹‹በቃ  ተፈውሼለሁ ማለት ይቻላል..እርግጥ ቀሪ የአንድ ሳምንት ክትትል አለኝ….ከዛ በኋላ በእልልታ ወደሀገሬ እመለሳለሁ..አዎ እርግጠኛ ነኝ ድኜ እመለሳለሁ››

‹‹በጣም ደስ የሚል ዜና ነው የምትነግረኝ…እንኳን ደስ ያለህ››

‹‹እንኳን አብሮ ደስ ያለን…እንደውም ምን እንደአሰብኩ ታውቃልህ..የእውነትም ድኜ ከሆነ ..አንተና ሁሴን እንደአዲስ ደግሳችሁ ትድሩኛላችሁ፡፡››

‹‹ማለት?››

‹‹የመጀመሪያው ሰርጌ የእናንተ ምርቃት ስለሌለበት ጎዶሎ ነበር..አሁን ግን ሙሉ እንዲሆን እፈልጋለው..መልሳችሁ ከእንደገና ትድሩኛላችሁ››

‹‹አንተን የሚያስደስትህ ከሆነ እናደረርገዋለን..ለመሆኑ ዜናውን ለሰሎሜ ነገርካት፡››

‹‹እንዴት ምን ነካህ …?ለዚህ ጉዳይ እዚህ እንደመጣሁ እኳ ከአንተ ውጭ ማንም ሰው አያውቅም…እንዴት ልነግራት እችላለው…?

ከሳምንት በኃላ ስመጣ በህይወቷ አይታ የማታውቀውን ትልቅ ሰርፕራይዝ ነው የማደርጋት››

‹‹ደስ የሚል ነገር ነው..በቃ የምትመጣበትን ትክክለኛ ቀን ደውለህ አሳውቀኝ››

‹‹እሺ አሳውቅሀለው..ደህና ሁን››

በዚህ ሁኔታ ነበር የስልክ ንግግራቸው የተቋጨው፡፡የአላዛር የምስራችና ፈንጠዝያ ለእሱ ሀዘንና የውስጥ ቅዝቃዜ ነው የፈጠረበት፡፡

‹‹እሺ አሁን ምን ላድርግ?››እራሱን ጠየቀ፡፡አእምሮው‹‹ በህይወትህ ለሁለተኛ ጊዜማ አትሸነፍ…ለፍቅርህ ታገል…አላዛር ከችግሩ ተላቆ መጥቶ ከሰሎሜ ጋር የነበረውን ስንጥቅ ሙሉ በሙሉ ከመድፈኑ በፊት ተንቀሰቀስና የሆነ ነገር አድርግ…ስንጥቁን አስፋውና ሸለቆ ይሁን …ንጠቀውና የራስህ አድርጋት››ይለዋል..፡፡ልቡ ደግሞ ‹‹ተው እንጂ ..አላዛር እኮ ለአንተ በህይወት ውስጥ ከተከሰቱ በጣም መልካም ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ደግሞ ከዚህ በፊትም የእንጀራ አባቱን ሚስት በማማገጥ አባቱ ገዳይ እንዲሆን ምክንያት ሆነሀል…ለዚህ የስንፈተወሲብ ችግር የተጋለጠበት ዋናው ምክንያትም አንተ ከሰራሀው ስህተት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ከበቂ በላይ ጎድተሀዋል..አሁን ደግሞ ሚስቱን ከነጠቅከው ምንድነው የሚሆነው…?በዛ ላይ ለእሷስ ቢሆን አሁን ከእሱ በላይ የተሻለ ባል እሆናታለው ብለህ ታስባለህ…?.በመንግስት ደሞዝ ምን አይነት የተመቻቸ ኑሮ ልታኖራት ነው?የምትወዳት ከሆነ ባለችበት ተዋት››እያለ ይሞግተዋል፡፡

የስልኩ ድምፅ ነው ከሀሳቡ ውስጥ መዞ ያወጣው..አየው ሰሎሜ ነች..ፈጠን ብሎ አነሳው፡››

‹‹ሀይ ቢራቢሮዋ››
‹‹አለሁልህ…..እየመጣህ ነው?››

‹‹አይ ቢሮ ነኝ…ምነው?››

‹‹ለመድኳችሁ መሰለኝ ደበረኝ…ትቆያለህ እንዴ?››

‹‹አይ ..ጨርሼለው፡፡ በቃ መጣሁ….ምነው ግን ሁሴን የለም እንዴ?›

‹‹ፕሮጀክቱን በተመለከተ የሚያገኛቸው ሰዎች ስላሉ ቡራዩ ሄዶል፡፡››

‹‹እሱናማ አውቃለሁ እስከአሁን አልተመለሰም እንዴ.?.››

‹‹አይ  አሁን ደውሎ ስላልጨረስኩ አድራለሁ ብሎኛል…ለዛ ነው የደወልኩልህ››

‹‹በቃ መጣሁ››ስልኩን ዘጋውና ከተቀመጠበት ተነሳ…ቢሮውን ቆልፎ ወጣ..ሞትሩን አስነሳና ወደሰሎሜ መብረር ጀመረ…

‹‹ዛሬ .የመጨረሻ እድሌ ነው….የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ››ሲል በውስጡ ወሰነ…ሲደርስ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ስልኳን እየጎረጎረች ነበር…ስታየው ተነሳችና ጉንጩን አገላብጣ በመሳም ተቀበለችው፡፡

ሊቀመጥ ሲል…‹‹ወደውስጥ እንግባ ..ውጩ ይቀዘቅዛል…እ ››የሚል ሀሳብ አቀረበች፡፡

‹‹እሺ…››አለና ተከተላት…
ሳሎን መሀል እንደደረሱ ‹‹መክሰስ ላቅርብ ..እስከዛ እጅህን ታጠብ››አለችው፡፡

‹‹ምነው ልጅቷ አታቀርብም እንዴ››

‹‹ዛሬ የረፍት ቀኗ ነው…ብቻዬን ስለሆንኩ እኮ ነው የደወልኩልህ››

ልዩ አይነት ደስታ በውስጡ ሲፈስ ታወቀው….እሷም እኔ ያሰብኩትን አስባ ይሆን እንዴ?››ሲል አሰበና እየፈገገ ወደመታጠቢያ ክፍል ሄደ…ታጥቦ ሲመለስ የምግብ ጠረጴዛው በምግብ ደምቆ ነበር…

‹‹የሚጠጣ ምን ይሁንልህ?›

‹‹ወይን ቢሆን ደስ ይለኛል….አንቺ ከጠጣሽ ማለት ነው?››

‹‹እኔ እንኳን ድክምክም እያለኝ ነው..ቢቀርብኝ››
‹‹እንደዛ ከሆነ አልጠጣም››

‹‹ችክ ያልክ ሰው እኮ ነህ..በቃ ትንሽ ጠጣለሁ..ብላ ሔደችና ወይንና መጠጫ ብርጭቆ አምጥታ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች፡፡፡አነሳና ክዳኑን ከፍቶ ለሁለቱም ቀዳ…ከፊት ለፊቱ ተቀመጠችና እራት መብላት ጀመሩ….

‹‹ይሄ ግዙፍ የተንጣለለ ቤት ለብቻ ያስፈራል አይደል?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አረ እንደውም ብዙ ጊዜ ብቻዬን ስሆን ደስ ነበር የሚለኝ..ዛሬ ግን ምን እንደነካኝ አላውቅም ፍርሀት ፍርሀት ይለኛል››

‹‹አይ ምንም ፍራሀት የለም…ናፍቆት ነው››
‹‹ባልሽን ናፍቀሻል እያልከኝ ነው?››

‹‹አይ እኔን ናፍቀሺኝ ነው እልኩሽ ነው››

‹‹ሂድ ጉረኛ….ምን ስለሆንኩ ነው የምትናፍቀኝ?››

‹‹የዘመናት አፍቃሪሽ ስለሆንኩ ነዋ…›

‹‹ታዲያ አፍቃሪዬ ነህ አንጂ አፍቃሪህ አይደለውም ….ልትናፍቀኝ ትችላለህ እንጂ አኔ አልናፍቅህም፡፡››

‹‹ተይ ተይ ..አይኖችሽ ግን እንደዛ አይደለም የሚሉት፡፡››

ከት ብላ ሳቀችና‹‹‹አንተ እያሽኮረመምከኝ እኮ ነው››

ፈራ ተባ እያለ‹‹ሳሎኑ ለሁለት ሰው በጣም ይበዛል…ወደላይ ሄደን ብንጠጣ አይሻልም›› የሚል ሀሳብ አቀረበላት፡፡

‹‹ውይ አንተንም በርዶሀል ማለት ነው…እኔን ብቻ መስሎኝ ኮ ነበር…ተነስ እንሂድ››ብላ ቀድማ ተነሳች…ደስ አለውና ጠርሙሱን ያዘ….‹‹ብርጭቆቹን ልያዛቸው››

‹‹ተዋቸው..እዛ ሌላ አለ›››አለችና ቀድማ ከፊት ለፊቱ መራመድ ጀመረች...በደስታ እየተፍለቀለቀ ተከተላት..‹‹ዛሬ በቃ እድል ሙሉ በሙሉ ፊቷን ወደእኔ አዙራለች…››ሲል አሰበ‹‹አሌክስ ዛሬ ይሄን ወርቃማ እድልህን ተጠቅመህ የሆነ ነገር ካላደረክ በቃ ለዘላለም ሰሎሜን እርሳት››ሲል እራሱን አስጠነቀቀ፡፡ቀጥታ ወደራሷ ክፍል ነው የሄደችው…ልክ እንደህጋዊ ባሏ ያለምንም ማቅማማት ተከተላት..ከፋታ ስትገባ ተከትሎት ገባ..አልጋው ጠርዝ ላይ ስትቀመጥ ጠረጴዛውን ወደእሷ አስጠጋ…ይዞ የመጣውን የወይን ጠርሙስ አስቀመጠ…ብርጭቆውን ካለበት አመጣና ለሁለቱም ቀዳና ወንበሩን አንሸራተተና ወደእሷ በማስጠጋት ተቀመጠ፡፡የፈለገው አልጋው ላይ ከጎኗ በመቀመጥ ሰውነቷን መነካካት ነበር…ግን ደግሞ ያንን ለማድረግ ለጊዜው ድፍረቱን አላገኘም…
ቀለል ያሉ ጫወታዎችን እያወሩ የድሮ ትዝታዎችን እያነሱ እየተጫወቱ ሰዓቱ ገፋ…

‹‹እንቅልፌ መጣ መሰለኝ ››አለችው፡፡

‹‹እና ወደክፍልህ ሂድልኝ እያልሽ ነው››

‹‹ለምን? ከፈለክ እዚህ ማደር ትችላለህ››

በመልሷ ደነገጠ‹‹እርግጠኛ ነሽ?››ሲል መልሷ ጠየቃት፡፡

‹‹ምነው እራስህን አታምነውም እንዴ?››

‹‹አረ አምነዋለው››
👍576👎3😱3