#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
....አንድ ጊዜ የማጠቃለያ እንቅስቃሴዬን ስሰራ፣ ክሪስ እንግዳ ስሜት ፊቱ ላይ እየተነበበ ሲመለከተኝ አየሁ: በቅርቡ አስራ አምስት አመት ልደቱን ያከብራል፡ እንዴት ይሆናል? ትልቅ ሰው እንጂ በጭራሽ ልጅ አይመስልም
ከልጅነት በፍጥነት እየወጣ እንደሆነ የሚናገሩት እነዚያ አይኖቹ ናቸው?ከዚያ ወደ ክሪስ ሄድኩና እጆቼን ወደ እሱ ዘርግቼ “ክሪስ ና ከእኔ ጋር እንደንስ፧ እንዴት እንደሆነ ላስተምርህ?” አልኩት።በመገረም ፈገግ አለና ጭንቅላቱን በመነቅነቅ እንደማይችል ነገረኝ፡ “ባሌት ዳንስ ለእኔ አይሆንም ቫልስ ግን መማር እፈልጋለሁ” አለ፡ አሳቀኝ በዚያን ወቅት የነበረን ብቸኛው የቫልስ ሙዚቃ አሮጌ ነበር፡ ወደ ማጫወቻው እየፈጠንኩ ሄጄ እየተጫወተ የነበረውን አወጣሁና የቫልሱን ከተትኩት ክሪስ ገልጃጃ ሆኖ ነበር የያዘኝ በሚያስቅ አይነት አያያዝ ነበር። በዚያ ላይ ያፈረ ይመስላል ደጋግሞ እየተደነቃቀፈ ሮዝ ቀለም ያለው ሹል ጫማዬ ላይ ይቆማል። ቀላል የሆኑትን እንቅስቃሴዎች ላለመሳሳት ጠንክሮ መሞከሩ ልብ የሚነካ ነበር ተሰጥኦው አእምሮው ውስጥና በጥበበኛ እጆቹ ክህሎት
ላይ እንጂ አንዳቸውም ወደ ቅልጥሞቹና ወደ እግሮቹ እንዳልወረዱ ልነግረው
አልቻልኩም::
በመጨረሻ እናታችን የሚያምሩ ላባዎች ያሉበት ጠባብ ኮፍያ፣ ነጭ ጫማና ቀሚስ ያለበት የዳንስ ልብስ ይዛ በበሩ ስትገባ በከባዱ ተነፈስኩ ፍቅር፣ ተስፋና ደስታ በአንድ ሀምራዊ ሪባን በታሰረበት ትልቅ ካርቶን በኩል
በጣም በሚያስብልኝ አንድ ሰውና ሀሳቡን ውስጧ በከተተው በሌላ ሰው አማካይነት ወደ ፎቁ የመጣ ይመስል ነበር በመጨረሻ ክሪስን ሌሎች ዳንሶችን ላስተምረው ስል ተቃወመኝ፡፡ “እንዳንቺ ሁሉንም የዳንስ አይነቶች መማር አያስፈልገኝም: ምክንያቱም እኔ መድረክ ላይ አልደንስም የምፈልገው ከሴት ጋር የመደነስ አጋጣሚ ቢመጣ መቀለጃ
እንዳልሆን ብቻ ነው:" አለኝ፡
“ክሪስ፣ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ በየአመቱ የዳንስ አይነቶች ልክ እንደ ልብስ ፋሽን ይለዋወጣሉ፡ ስለዚህ ከጊዜው ጋር መሄድ አለብህ አለበለዚያ
ማንም ሴት አታፈቅርህም::”
“ልታፈቅረኝ የምትችል ሴት አትኖርም:”
እንደዚያ አይነት ሰው ፋሽን ያለፈበት ቢሆንም እሱ ግን ማንም ሰው ለራሱ ያለውን ምስል እንዲለውጥ እንዲያስገድደው አይፈቅድም የራሱ ሰው
በመሆኑ እወደዋለሁ የኔ ሰር ክሪስቶፈር
ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ እንደሆንን ወቅቶች ለወጥን፡ የለጠፍናቸውን አበቦች አውርደን በበልግ ቅጠሎች ተካናቸው ክረምት ሲመጣም እዚህ
የምንሆን ከሆነ በረዶ መጣል ሲጀምር የቆራረጥናቸውን ነጫጭ ንድፎች እንሰቅላቸዋለን፡፡
ክሪስ መፅሀፍ በማያነብበት ጊዜ ስዕሎችን በውሀ ቀለም ይስላል በበረዶ የተሸፈኑ ኮረብታዎች፣ የበረዶ ሸርታቴ የሚጫወቱ ሰዎች የሚያቋርጧቸውን ሀይቆች፣ በረዶ ውስጥ የተቀበሩ ቢጫና ሮዝ ትንንሽ ቤቶችና ከጭስ መውጫው ውስጥ የተጥመለመለ ጭስ ሲወጣ የሚያሳይ ይሰራል። ሲጨርስ የመስኮቱን ጥቁር ፍሬም ቀለም ይቀባና ስዕሉን ግድግዳው ላይ ሲለጥፈው ደስ የሚል እይታ ያለው ክፍል ይሆንልናል
አንድ ጊዜ እኔና ክሪስ አሮጌው ፍራሽ ላይ ጎን ለጎን ተጋድመን እያወራን ነበር ነፃና ሀብታም ስንሆን ስለምንኖረው ኑሮ እቅድ ስናወጣ “በዓለም ዙሪያ እንጓዛለን፤ በጣም ቆንጆ፣ አስተዋይና የምትስብ ሴት አገኝና ፍቅር ይይዘኛል። ልጅቷ ታማኝ፣ ቤት አያያዝ ላይ ጎበዝ የሆነች፣ የማትጨቃጨቅ፣የማታማርር፣ የማትጮህ... ትሆናለች” ብሎ ሲናገር የበታችነት እንዲሰማኝ
አደረገኝ የወደፊት ትዳር ጠያቂዎቼን የምመዝንበት ደረጃ እያወጣልኝ እንደሆነ አውቄያለሁ: ታዲያ እንደ ክሪስ ያለ ወንድን ፍላጎት ማሟላት የምችለው እንዴት ነው?
ክሪስ… ይቺ ጎበዝ፣ ማራኪ፣ እውቀት ያላትና ቆንጆ ሴት ያልካት አንድ ትንሽ ጉድለት እንኳን የላትም?”
“ለምን ጉድለት ይኖራታል?”
“ለምሳሌ እናታችንን ውሰድ። ምናልባት ጎበዝ ከሚለው በስተቀር በሁሉም ነገር የምታስባት አይነት ሴት ናት።”
“እናታችን ደደብ አይደለችም!” ተከላከለላት᎓ “በተሳሳተ አይነት አካባቢ ስላደገች ብቻ ነው! በልጅነቷ ዝቅ ተደርጋ ትታይ ነበር። ሴት በመሆኗ ዝቅተኝነት
እንዲሰማት አድርገዋታል"
በበኩሌ ለተወሰኑ አመታት ታዋቂ ዳንሰኛ ከሆንኩኝ በኋላ ለማግባት
ስፈልግ ክሪስ ጋ ወይም አባቴ ጋ ካልደረሰ ምን እንደማደርግ አላውቅም።መልከመልካም እንደሚሆን አውቃለሁ- ምክንያቱም ልጆቼ ቆንጆዎች
እንዲሆኑ እፈልጋለሁና። ጎበዝ እንዲሆን እፈልጋለሁ አለበለዚያ ላላከብረው እችላለሁ የመተጫጫ የአልማዝ ቀለበቱን ከመቀበሌ በፊት ቁጭ እንዲል
አደርግና ጨዋታ እንጫወታለን፡ ደጋግሜ ካሸነፍኩት ፈገግ እልና ጭንቅላቴን ነቅንቄ ቀለበቱን ወስዶ የገዛበት ሱቅ እንዲመልሰው እነግረዋለሁ
ማሰሮ ውስጥ የተተከሉት አበቦቻችን ጠወለጉ ለአትክልቶቻችን የፍቅር
እንክብካቤ እናደርግላቸዋለን እናወራቸዋለን፣መምሰል አቁሙ እንላቸዋለን አንገቶቻቸውን ቀጥ እናደርግላቸዋለን ከሁሉም በላይ በጣም ጤናማ የሆነውን የምስራቅ የጠዋት ፀሀይ ያገኙ ነበር።ቅጠሎቹ ግን እየሞቱ ነበር‥. ቢጫ፡ እየሆኑ ይሄዱ ጀመር ።
እያደር ኮሪና ኬሪ ውጪ ለመውጣት መጠየቃቸውን አቆሙ፡ ኬሪ በትንንሽ
እጆቿ ቡጢ ጨብጣ በሩን መደብደቧን ተወች:: ኮሪ በእግሮቹ መሬቱን መደብደብ አቁሞ ትንንሽ የእግሮቹን ጣቶች የማያጣብቃቸውን ለስላሳ
ጫማዎች ማድረግ ጀመረ
አሁን የሚያገኙት ብቸኛው “ውጪ” ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ የሚገኘው የአትክልት ስፍራ ብቻ መሆኑን ተቀበሉ። ምስኪን መንትዮቹ...ከጊዜ በኋላ በሚያሳዝን ሁኔታ ከዚህ ከተቆለፍንበት ክፍል ውጪ ሌላ አለም ከነመኖሩም ይረሳሉ
ልጆች ለማደግ የፀሀይ ብርሀን ያስፈልጋቸዋል እኛ ማድረግ ያለብን እየሞቁ ያሉትን ተክሎች መመልከትና የጣሪያው ስር ክፍል ውስጥ የአትክልት ቦታችን ላይ ያደረግነውን ነገር መታዘብ ብቻ ነው: ፀሀይዋ እኛ ክፍል
ውስጥ ስለማትገባ ፀሀይ ለማግኘት ፍራሾችን መስኮቱ ስር እንከምርና ላዩ ላይ እንሆናለን
በአጭር ጊዜ ውስጥ ፀሀዩዋ መስኮታችን ጋ ስትደርስ ምንም ሳናፍር ልብሶቻችንን ሁሉ አወላልቀን ፀሀይ እንሞቃለን፡፡ የእያንዳንዳችንን ልዩነት
አየንና ስለነገሩ ብዙም ሳናስብ ያደረግነውን በግልፅ ለእናታችን ነገርናት ምክንያቱም የፀሀይ ብርሀን በማጣት መሞት የለብንምና፡ እናታችን እይታዋን
ከክሪስ ወደ እኔ እያደረገች ደካማ ፈገግታ አሳየችን፡ “ምንም አይደለም ግን አደራ አያታችሁ እንዳትሰማ! ሁላችሁም እንደምታውቁት እሷ በዚህ ደስ
አይላትም” አለች።
መጀመሪያ ክሪስን ከዚያ እኔን እያፈራረቀች ትመለከተን የነበረው ንፁሁነታችንን የሚያሳይ ወይም ስለ ፆታዊ ግንኙነቶች መንቃታችንን የሚያመለክት ምልክት ለመፈለግ መሆኑን አውቄያለሁ መንትዮቹ እርቃናቸውን ሆነው እንደ ህፃናት መጫወት ይወዳሉ አንድ
ቀን ኬሪ “ለምን ክሪስ…?” ብላ ጠየቀች᎓ እሱና ኮሪ ያላቸውና እሷ የሌላትን የሰውነት ክፍል እየጠቆመች። ክሪስ ትክክለኛና እውነተኛ የሆነውን መልስ
ለመመለስ በመሞከር “ሁሉም ወንድ ፍጥረታት የመራቢያ አካላቸው የሚገኘው
ከውጪ ነው: የሴቶች ደግሞ ከውስጥ ስለሆነ ነው። ወላጆቻችን እርቃን ሰውነታችንን ልክ እንደ አይኖቻችንና ፀጉራችን ተቀብለውታል ስለዚህ ባለን
መደሰት አለብን” አላት
“ወንድ ወፎች ደግሞ ልክ እንደ ሴቶች የመራቢያ አካላቸው ያለው ከውስጥ በኩል ነው: አለች ኬሪ
ተገርሜ “እንዴት አወቅሽ?" ብዬ ጠየቅኳት᎓
“በቃ አወቅኩ፡”
“መፅሀፍ ላይ አንብበሽ ነው?”

👍26👏2👎1🥰1😁1
“እና? ታዲያ ወፉን ይዤ
ተመራምሬ ነው?”
“መቼም አያልፍሽም”
“ቢያንስ የማነበው አእምሮዬን ለማሻሻል ነው። ለመዝናናት አይደለም”አንዳንድ ቀናት ፀሀይ ለመሞቅ በጣም ብርዳማ ናቸው: የሚሞቁ ልብሶች ለብሰን እንኳን ካልሮጥን በስተቀር ያንቀጠቅጠናል፡ ወዲያው የጠዋቷ ፀሀይ hምስራቅ ስትሸሽ በደቡብ በኩል መስኮት ቢኖር ብለን እንመኛለን፡ መስኮቶቹ
ግን ተቆልፈዋል
“ምንም አይደል በጣም ጤናማው የጠዋት ፀሀይ ነው” አለች እናታችን፡ ያላስደሰተን ንግግር ነው ምክንያቱም ጤናማው ፀሀይ ውስጥ እየኖሩም አትክልቶቻችን አንድ በአንድ እየሞቱ ነበር።
ህዳር ሲጀምር ጣሪያው ስር ያለው ክፍል እጅግ መቀዝቀዝ ጀመረ። ጥርሶቻችን
ተንቀጫቀጩ፤ አፍንጫዎቻችን ረጠቡ፡ ማስነጠሱ ሲበረታብን ለእናታችን የጭስ ማውጫ ያለው ምድጃ እንደሚያስፈልገን ነገርናት። ምክንያቱም
በመማሪያ ክፍሉ ውስጥ ያሉት ሁለቱም ምድጃዎች ተበላሽተው ነበር።የኤሌክትሪክ ወይም የጋዝ ማሞቂያ እንደምታመጣልን ነግራን ነበር። ነገር ግን የኤሌክትሪክ ምድጃው ከሌሎች ገመዶች ጋር ከተገናኘ እሳት ሊያስነሳ
ይችላል ብላ ፈራች: የጋዝ ምድጃ ደግሞ የጭስ ማውጫ ያስፈልገዋል።
ስለዚህ ወፍራም ልብሶች አመጣችልንና እነዚያን ልብሶች ለብሰን በነፃነት ልንሮጥበትና ከአያትየው አይኖች ልንሸሽበት ወደ ምንችልበት ጣሪያው ስር
ወዳለው ክፍል በየቀኑ መምጣት ቀጠልን አንድ ቀን ድብብቆሽ እየተጫወትን እያለ ኮሪ የተደበቀበትን አጣነው
በአብዛኛው ለመደበቅ የሚመርጠው ክሪስ ተደብቆበት የነበረውን የመጨረሻ
ቦታ ስለነበር እሱን ማግኘት ቀላል ነው: ስለዚህ ቀጥታ ወደ ሶስተኛውና ትልቁ የልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ስንሄድ ኮሪ ወለሉ ላይ ኩርምት ብሎና አሮጌዎቹ ልብስ ስር ተደብቆ እናገኘዋለን ብለን አምነን ነበር- ግን አላገኘነውም፡
“የሚደበቅበት አዲስ ቦታ አግኝቷል ማለት ነው" አለ ክሪስ፡ እውነትም አዲስ መደበቂያ ፈልጎ ከሆነ፣ በዚህ ጣራ ስር ያለ ክፍል ውስጥ ብዙ ጥሩ ጥሩ
መደበቂያ ቦታዎች አሉ
“ኮሪ!” ብዬ ጮህኩ፡ ካለህበት ቦታ ውጣ፣ ምሳ ሰዓት ደርሷል!” አሁን ይሄ ያመጣዋል። በምሳ ቀልድ የለም።
ይሁንና አሁንም መልስ አልሰጠም፡ ክሪስን በቁጣ ተመለከትኩት::"የምትወደው አይነት ምግብ ነው" አልኩኝ ሮጦ እንዲመጣ ሊያደርገው ይገባ ነበር አሁንም ድምፅም፣ ለቅሶም፣ ምንም የለም:
ድንገት ፈራሁ። ኮሪ በዚህ ሰፊ ክፍል ውስጥ ፍርሀቱን አሸንፎ ጨዋታውን በቁምነገር ይወስደዋል ብዬ ማመን አልቻልኩም ምናልባት ደግሞ ክሪስን ወይም እኔን ለመኮረጅ ይሞክር ይሆን? አምላኬ! “ክሪስ! ኮሪን ማግኘት አለብን በፍጥነት” ስል ጮህኩ ድንጋጤዬ ተጋባበትና የኮሪን ስም እየጠራ እንዲወጣና መደበቁን እንዲያቆም እያዘዘ ሮጠ፡ ሁለታችም ኮሪን ደጋግመን እየተጣራን እየሮጥን መፈለግ
ቀጠልን የድብብቆሹ ሰዓት አልቆ አሁን የምሳ ሰዓት ነው! መልስ ግን
የለም ያንን ሁሉ ልብስ ለብሼም በረዶ ሆኛለሁ: እጆቼ ሳይቀሩ ሰማያዊ መስለዋል
“ወይኔ አምላኬ!” ሲል ክሪስ አጉረመረመ: “ምናልባት አንደኛው ሻንጣ ውስጥ ሲደበቅ ድንገት ክዳኑ ተዘግቶበት ይሆን?”
ኮሪ ሊታፈን ይችላል ሊሞት ይችላል!
እንዳበደ ሰው እየሮጥን የእያንዳንዱን ሻንጣ ክዳን እየበረገድን መክፈት ጀመርን፡ ሻንጣዎቹ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ እየበታተንን ፍለጋችንን
ቀጠልን እየሮጥኩና እየፈለግኩ “አምላኬ ሆይ እባክህ ኮሪ እንዲሞት አታድርግ” እያልኩ ደጋግሜ እየፀለይኩ ነበር
ካቲ አገኘሁት!” ሲል ክሪስ ጮኸ፡ ክሪስ ወዳለበት ስዞር ክዳኑ ተዘግቶ ከነበረ ሻንጣ ውስጥ የኮሪን የማይንቀሳቀስ ትንሽ አካል ሲያነሳ አየሁት በእፎይታ
ወደ እነሱ ተጠጋሁና ኦክስጂን በማጣት የቆዳው ቀለም የተቀየረውን የኮሪን ትንሽዬ የገረጣ ፊት ሳምኩ፡ የደከሙት አይኖቹ እያዩ አልነበረም: ራሱን ወደ መሳት ቀርቧል “እማዬ…” አለ በሹክሹክታ “እናቴን እፈልጋለሁ:”
እናታችን ግን ሩቅ ናት የታይፕ
ፅህፈት እየተማረች ነው። ያለችው ሀዘኔታዐያልፈጠረባት አያት ብቻ ናት: እሷንም ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥመን እንዴት እንደምናገኛት አናውቅም ክሪስ “በፍጥነት ሩጪና የመታጠቢያ ገንዳውን በሙቅ ውሀ ሙይው” አለ፡ ግን “በጣም እንዳይሞቅ!” ብሎኝ ኮሪን በክንዶቹ አቅፎ ወደ ደረጃው ተንደረደረ
ቀድሜው ወደ መኝታ ክፍሉ ደረስኩና ወደ መታጠቢያ ቤቱ ፈጠንኩ።ወደኋላ ስመለከት ክሪስ ኮሪን አልጋው ላይ ሲያጋድመው ተመለከትኩ፡፡ ከዚያ ጎንበስ ብሎ የኮሪን የአፍንጫ ቀዳዳ አፍኖ ያዘና ጭንቅላቱን ዝቅ አድርጎ
እንዲተነፍስ ለመርዳት አፉን ኮሪ አፍ ላይ ገጥሞ አየር ሊሰጠው ሲሞክር ልቤ ዘለለች! ሞቷል? መተንፈስ አቁሟል?
ኬሪ ምን እየሆነ እንደሆነ አየች
ስትመለከት መጮህ ጀመረች:
በመታጠቢያ ክፍሉ ውስጥ
ሁለቱንም ቧንቧዎች እስከመጨረሻው ከፈትኳቸው፡ ኮሪ ሊሞት ነው፡ ሁልጊዜ ስለ ሞት ሳልም. ብዙ ጊዜ ህልሜ
እውን ይሆናል፡፡ እና እንደ ሁልጊዜው እግዚአብሔር እንደተወንና ጀርባውን
እንደሰጠን ሳስብ፣ እምነቴን ለመያዝ እዞራለሁ፤ ኮሪ እንዲሞት እንዳይፈቅድ እየጠየቅኩ መፀለይ ጀመርኩ. እባክህ እግዚአብሔር እባክህ እባክህ ...
ልክ ክሪስ እያደረገለት እንዳለው አርቲፊሻል የመተንፈሻ ዘዴ የእኔም የተስፋ መቁረጥ ፀሎት ኮሪን ወደ ህይወት ይመልሰው ይሆናል
“እንደገና መተንፈስ ጀመረ” አለ ክሪስ ፊቱ ገርጥቶ እየተንቀጠቀጠ፡ ኮሪን
ተሸክሞ ወደ መታጠቢያው እየወሰደው “አሁን ማድረግ ያለብን እንዲሞቀው
ማድረግ ብቻ ነው” ወዲያውኑ የኮሪን ልብስ አውልቀን በሙቅ ውሀ የተሞላው ገንዳ ውስጥ ከተትነው ኮሪ ሲነቃ “እማዬ… እማዬን እፈልጋለሁ” አለ
እየደጋገመ በሹክሹክታ እንደዚያ ሲል፣ እጆቼን ጨበጥኩና ግድግዳውን መታሁት: ፍትሀዊ አይደለም! ምን ማድረግ እንዳለባት የማታውቅና
የምታስመስል እናት ሳይሆን ራሷን እናቱን ማግኘት ነበረበት በቃ! ጎዳና ላይ መለመን ቢኖርብኝም እንኳን ከዚህ መውጣት እፈልጋለሁ።
ነገር ግን ክሪስ ቀና ብሎ ተመልክቶኝ በማረጋገጥ ፈገግ እንዲልልኝ በሚያደርግ
ሁኔታ በእርጋታ ተናገርኩ፡ “እኔ እናትህ እንደሆንኩ ለምን አታስመስልም? እሷ የምታደርግልህን ነገሮች ሁሉ አደርግልሀለሁ: ጭኔ ላይ አድርጌ
አቅፍሀለሁ፣ ትንሽ ምሳ ከበላህና ጥቂት ወተት ከጠጣህ እሹሩሩ እያልኩ አስተኛሀለሁ " አልኩት ይህንን ስናገር እኔና ክሪስ ተንበርክከን ነበር እኔ ቀዝቃዛ እጆቹን ለማሞቅ ሳሻሽለት ክሪስ ደግሞ የኮሪን ትናንሽ እግሮች
እያሸለት ነበር፡ የሰውነቱ ቀለም ወደ ነበረበት ሲመለስ ሰውነቱን አድርቆለት የሚሞቅ ፒጃማ ካለበሰው በኋላ በብርድ ልብስ ጠቀለለውና ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ውስጥ ያመጣው የሚወዛወዝ ወንበር ላይ ተቀምጬ ጭኔ ላይ
አስቀመጥኩት። ከዚያ ፊቱን ሁሉ እየሳምኩና ደስ የሚሉ ነገሮች በጆሮው እያንሾካሾኩ እንዲስቅ አደረግኩት።
መሳቅ ከቻለ ደግሞ መብላት ይችላል፡ በትንንሹ እየቆረስኩ ሳንድዊች አጎረስኩት። ለብ ያለ ሾርባና ወተት እንዲጠጣ አደረግኩ። ይህንን ሳደርግ
በአስር ደቂቃ ውስጥ አስር አመት ያህል ያደግኩ መሰለኝ ክሪስ ምሳውን ለመብላት ሲቀመጥ አየት አደረግኩት እሱም ተለውጧል፡ አሁን የፀሀይ ብርሀንና ንፁህ አየር ከማጣት ባሻገር በዚያ ጣራ ስር ያለ ክፍል ውስጥ አደጋ መኖሩን አወቅን፡ እያንዳንዳቸውን አይጦችና ሸረሪቶች የገደልናቸው ቢሆንም እንኳን ሁላችንም ለመኖር ችክ ካሉት ከእነሱ የበለጡ እጅግ የከፉ ነገሮችን ተጋፍጠናል፡

👍34❤3
ክሪስ ብቻውን ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ለመሄድ ወደ ደረጃዎቹ ሲያመራ ኮሪንና ኬሪን ሁለቱንም ጭኖቹ ላይ አስቀምጬ መዝሙር እየዘመርኩላቸው
ወደፊትና ወደኋላ እየተወዛወዝኩ ነበር። ድንገት ሠራተኞቹ ሊሰሙት
የሚችሉት በመዶሻ የሚመታ አይነት ሀይለኛ ድምፅ ከላይ ሲመጣ ሰማን፡
ኬሪ እንቅልፍ እያዳፋት ሳለ ኮሪ “ካቲ እናታችን እዚህ አለመኖሯ ከዚህ በኋላ ደስ አይለኝም” አለ ቀስ ባለ ድምፅ
“አይዞህ እማዬን ታገኛታለህ፤ እኔም ደግሞ አለሁልህ"
“አንቺ እንደ እውነተኛዋ እናቴ ጥሩ ነሽ?”
“አዎ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡ በዚያ ላይ በጣም እወድሀለሁ ኮሪ፤ እውነተኛ
እናት የምታደርገው ደግሞ ያንን ነው:: ኮሪ በትልልቅ ሰማያዊ አይኖቹ አተኩሮ ተመለከተኝ፡ የምሬን መሆኑን ወይም ዝም ብዬ ለማባበል ስል የተናገርኩት መሆኑን ለመለየት የፈለገ ይመስላል። ከዚያ ትናንሽ ክንዶቹ
አንገቴ ላይ ተጠመጠሙና ጭንቅላቱን ትከሻዬ ላይ አሳረፈ: “እንቅልፌ መጥቷል እማዬ፣ ግን መዘመርሽን እንዳታቆሚ፡” አለኝ
ክሪስ ፊቱ ላይ እርካታ እየተነበበበት ተመልሶ ሲመጣ እኔ አሁንም በቀስታ እየዘመርኩ ልጆቹን እንዳቀፍኩ ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተወዛወዝኩ ነበር።
“ሻንጣዎቹ ከዚህ በኋላ ድንገት እንደገና አይዘጉም: ምክንያቱም እያንዳንዱን ቁልፎችና መዝጊያዎች ሁሉ ሰባብሬያቸዋለሁ” አለ፡
በመስማማት ጭንቅላቴን ወዘወዝኩ።.....
✨ይቀጥላል✨

👍32❤12🥰1
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
....ሚስተር ካርላይል ካገባበት ጊዜ ጀምሮ ፍቅርና ቅናት ሁልጊዜ የሚያኝኳት መቆሚያ የሌለው የልብ ሥር ውጋት እሱን ለማግባት የነበራት ምኞትና ተስፋ ከንቱ ሆኖ መቅረትና በዚህም ምክንያት የተሰማት ኃፍረት ሁሉ በአንድነት ተደራርበው ብጥብጥ አደረጓት " የዚያን ቀን ለሚስቱ ሲገልጽላት የነበረው የፍቅር ጭውውትና የነበራቸውንም ደስታ አብራ በማምሸት በዐይኗ ስለ ተመለከተች ልቧን ሰወራት " ሕይወትን ተወዳጅ ሊያደርግ ከሚችል ነገር ሁሉ እንደ ተገለለች ሆኖ ተሰማት የባርባራና የሚስተር ካርላይል ይህን ያል መቀራረብ በእርሷ ላይ ፎቅር ሲያሳድርባት በሱ በኩል ግን እንደ እህቱ እንጂ እንደ ፍቅረኛ አድርጎ አስቧት
አያውቅም እሷ በሐሳብ ማዕበል ስትንገላታና ስትበጠበጥ የዚያ ሁሎ ሁከቷ ምክንያት እሱ መሆኑን ሊገነዘብ ቀርቶ ችግር እንደ ነበረባት ንኳን አላወቀላትም » ስለዚህ እሷ ሲቃ ይዟት ተጨንቃና ተወጥራ እያለ ብሷቷን ባለመረዳት ያልተጨነቀችበትንና ያላሰበችበትን ርዕስ ጣልቃ በማስባት ፡ « አባትሽ ድርቆሹን መች ያስከምሩታል ...ባርባራ?» አላት።
ዝም አለችው " ስሜቷን ለማዳፈን ከራሷ ጋር ስትተናነቅ ሚስተር ካርላይል መልሶ ጠየቃት ባርባራ . . . አባትሽ ድርቆሹን መች እንደሚያስከምሩት ጠይቄሽ ነበር»
አሁንም አልመለሰችለትም መልሶ መናገር አቃታት ጉሮሮዋ ተላወሰ
የአፏ ጡንቻዎች ተኮማተሩ ሰውነቷ ተንሰፈሰፈ ቀጠለችና ጮኻ መንሰቅሰቅ ጀመረች "
« ባርባራ ...አመመሽ እንዴ ? ምንድነው ? » አላት
ፍቅር ንዴት በደልና ጭንቀት አንድነት ተደባልቀው ይፈሉባት ጀመር ብርክ ያዛት እምታደርገውን ማወቅ ተሳናት " ሚስተር ካርላይል በከፊል ተሸክሞ በከፊል እየሳበ ከአጥሩ መወጣጫ ሁለተኛው ደረጃ በክንዱ ደግፎ ይዞ አሳረፋት " በዚያ ጸጥ ባለው የለሊት ሰዓት ረብሻ መፈጠሩ ለምን እንደሆነ የገረማቸው
አንዲት አሮጊት ላምና ሁለት ጥጆች ወደ ስዎቹ በመቅረብ ትክ ብለው ይመለከቷቸው ጀመር ።
ባርባራ ከስሜቷ ግፊት ጋር ባላት አቅም ተናነቀች እንባዋ ተገታ መብረክረኳና የአቅል መሳት ምልክቶቿ ለቀቅ አደረጓት " ደግፎ የያዛትን ክንዱን ወዲያ ገፍታ አጥሩ ላይ በጀርባዋ ተደግፋ ቆመች " ሚስተር ካርላይል ወደ ኩሬው ሮጦ ውሃ ለማምጣት ቃጣው " ነገር ግን ውሃ የሚያመጣበት ከባርኔጣው በቀር ምንም ነገር አልነበረውም ።
« ተሻለሽ ... ባርባራ ? ምን ነክቶሽ ነው? » አላት "
«ምን ነክቶሽ ነው? » ብላ ጮኸችበት « እንዲህ ብለህ ልትጠይቀኝ ትችላለህ ? »
« ነገሩ አልገባኝም " እኔ
የበደልኩሽ ካለ በውነቱ በጣም አዝናለሁ »
«እንዴታ ! አይጠረጠርም ታዝናለህ እንጂ !ለመሆኑ እኔ ነገ ካፈር ብገባ» አለችው መሬቱን በእግሯ እየደበደበች « አንተ ምን ቸገረህ ? እኔ ምንድነኝና አንተ አንደ ሆንክ ሚስትህ አለችልህ ? የኔ መከራ የኔ ሥቃይ ለአንተ ምንህ ሆነና? ስማህ አርኪባልድ ካርላይል ... እኔ የአሁኑን ኑሮዬን ታግሸ ችየው ለመግፋት ከመድከም ሙቸ ብቀበር ይሻለኛል " ያለሁበት ጭንቅ ከምችለው በላይ ነው»
«ነገርሽ ያልገባኝ ለመምሰል አልፈልግም » አላት ብስጭት ብሎ « ግን ባርባራ እኔ ላንቺ ከማስብልሽና ከማከብርሽ የበለጠ እንድታስቢ ያደረግሁት ነገር የሰጠሁሽ ፍንጭ የለም»
«ምክንያት የሚሆነኝ ፍንጭ አልሰጠኸኝም ! .. እንዶ ጥላ እየተከተልhኝ ከቤታችን ስትመላለስ ይኸን አምጥተህ ስትሸልመኝ » ካባዋን ጣል አድርጋ የወርቅ ጌጥ መያዣዋን እያሳየችው « ከወንድም የበለጠ ስትቀርበኝ !
«አይ ባርባራ ቁም ነገሩን አሁን ገና አመጣሽው እኔ ላንቺ
ከወንድምነት በቀር ሌላ ነገር በሐሳቤ መጥቶብኝ አያውቅም » አላት በተለመደው ቀጥተኛ አነጋገሩ።
«እንደ ወንድም ብቻ ሌላ ምንም» አለች ድምጿ በስሜት እየናረ " ልትቆጣጠረው የቻለች አትመስልም « አንተ ስለኔ ስሜት ምን ቸገረህ ? የኔን ፍቅር
ለማግኘት ለምን ብለህ ትቸገራለህ ? »
« ባሮባራ . . ረጋ በዪ እስኪ ትንሽ አስተውዬ በርግጥ ላንቺ ንጹሕ የሆነ ጥልቅ ስሜትና አክብሮት አለኝ " እኔ ያላሰብኩት ስሜት ሊያድርብሽ የቻለውም በዚህ የተነሣ ሊሆን ይችላል " ስለዚህ ለኔ ሳይታወቀኝ በሐሳቤ የሌለ ስሜት ላንቺ እንዲታወቅሽ እንዲሰማሽ በማድረጌ በጣም አዝናለሁ »
ጥቂት በረድ አለላት " እየለቀቃት ሔደ " ሁኔታዎችን አመዛዘነች ፊቷን ወደ ሚስተር ካርላይል ቀና አድርጋ ተመለከተች "
« እሷ ከመኻላች ባትገባ ኖሮ ትወደኝ ኖሮዋል ? »
« እንጃ እንዴት ማወቅ እችላለሁ? እኔ አንቺን እንደ እኅቴ እንደ ንጹሕ ባልንጀራዬ ነበር የማይሽ ስለዚህ ግንኙነታችን ከዚህ ሌላ ምን ሊመስል ይችል እንደ ነበር ለማወቅ አልችልም »
« እኔ ኮ ላንተ እንዳልታወቀህ ሁሉ ለሌላውም ባይታወቀው ኖሮ በቻልኩት ነበር • • •አርኪባልድ »
« በውነቱ በጣም አዝናለሁ - አሁንም ሁሉን ነገር እንደምትረሺው ተስፋ አደርጋለሁ " የዛሬ ማታው ንግግራችንም ከአእምሮሽ ይጥፋ " አሁንም ንጹሕ ባልንጀሮች እኅትና ወንድም እንደሆን እንቀጥላለን " ደግሞ አንቺ የተሰማሽን ግልጽልጽ
አድርግሽ በመናገርሽ ባንቺ ላይ ያለኝን ግምት ምንም አልቀነሰውም »
በግርግሩ አጥር ዘሎ ለመሔድ ያሰበ ይመስል ሊንቀሳቀስ ባርባራ ግን ንቅንቅ አላለችም " እንባዋም ዝም ብሎ ይወርድ ጀመር " በዚህ ጊዜ አንድ ነገር ሰሙ "
« አንቺ ነሽ ሚስ ባርባራ ? »
ባርባራ በጥይት የተመታች ያህል ድርቅ አለች " ከአጥሩ በስተውስጥ የቤታቸው የገረዶች አለቃ የነበረችውን ዊልሶንን አዩዋት ሚስዝ ሔር ጃስፐርን ወደ
ባርባራ ከላከችው በኋላ እሱ እስኪመለስ ድረስ መጠበቅ ስለ አልቻለች እንደገና እሷን ስለላከቻት መምጣቷን ነገረቻቸው " ከዚያ ቦታ ምን ያህል ቆይታ ምን ያህል
ምስጢር እንደ ሰማች አይታወቅም ሚስተር ካርላይል ለራሱ ዐለፈና ባርባራንም
እጅዋን ይዞ አሳለፋት "
« ከዚህ በላይስ መሔድ አያስፈልግህም ይብቃህ ተመለስ» አለችው ቀስ ብላ "
« የለም ከቤት አስገባሻለሁ » ብሎ ክንዱን ሰጣትና ተያይዘው በጸጥታ አዘገሙ " ወደ ማድቤት ከሚያስገባው ከዐጸዱ ጀርባ ካለው በር ሲደርሱ ዊልሰን ቀድማቸው ገባች " ሚስተር ካርላይል ባርባራን እጆቿን ይዞ ደኅና እደሪ ባርባራ » አላት "
ባርባራ ትንሽ አሰበች " ያ ሁሉ ስሜታዊ ንዴት በረደላት የፈጸመችው ነገር ከዕብደት የሚቆጠር አሳፋሪ መሆኑ ታወቃት ሚስተር ካርላይልም ምን
ያህል እንደ ተሰማትገባው
« ይህን ሁሉ ነገር ስናገርህ እውነት አብጀ ነበር መሰለኝ እንጂ በደኅናዬ የነበርኩ አይመስለኝም" አንተ ግን እንዳልተፈጸመ እንዳልተነገረ አድርገሀ ቁጠረው
«ስለዚህ ግድየለሽም ሐሳብ አይግባሽ »
ለሚስትህ አትነግርብኝም ? » አለችው እየቃተተች
«እንዴ ባርባራ ! »
«አመሰግንሃለሁ ደኅና እደር »
እሱ ግን እጁን ይዞ ዝም አለ
«ሰማሽ ባርባራ ፍቅርሽን ከኔ በበለጠ ለመቀበል የታደለ በቅርቡ እንደምታገኝ አምናለሁ።»
«በጭራሽ አልቃጣውም እኔ እኮ በቀላሉ አላፈቅርም ፤ በቀላሎም አልረሳም ከእንግዲህ እስከ ዕድሜ ልኬ ባርባራ ሔር እንደ ተባልኩ እኖራታለሁ እንጂ ባል አግብቼ ሚስዝ እገሌ አልባልም
ሚስተር ካርላይል ስለ ደረሰው ሁኔታ እያሰበ ወደ ቤቱ ገሠገሠ እሷ ባሰበችው መንገድ እሱ ሚስቱን በሚያፈቅራት ዐይነት አይሁን እንጂ ባርበራን ይወዳትና
ያከብራት ነበር " ስለዚህ በባርባራ አነጋገር ኀዘን ተሰማው "

👍19
ባርባራ ሔር ሁና ተወልዳ ስሟን ሳትለውጥ መሞት እንኳን ወጣት ሴቶች ሲበሳጩ የሚናገሩትና ወዲያው የሚረሱት ነገር ነው " ይልቁን ለልቧ ደስ የሚላትን ሰው አግኝታ እኔን እንድትረሳኝ እመኝላታለሁ አለ ለብቻው "
« አርኪባልድ ! »
ከመናፈሻው የመጨረሻውና ከሌሎቹ ሁሉ ለቤቱ ቅርብ ከሆነው ዛፍ ሲደርስ ብቻውን ሲያወጣ ሲያወርድ ከነበረው ሐሳብ ያቋረጠው ድምፅ ከዛፉ ሥር ቁሞ ከነበረው ጥቁር ቅርጽ የወጣ ነበር "
« አንቺ ነሽ እንዴ ፍቅሬ ? »
« ልቀበልህ እኮ ወጥቸ ነው ግን በጣም አልቆየህም ?»
«መሰለኝ ያውም እኮ ገረዲቱን ከመንገድ አግኝተናት ነበር " ግን ዝም ብዬ ቤት ድረስ ሔድኩ »
« ከጀስቲስ ሔር ቤተሰብ ጋር የቅርብ ግንኙነት አላችሁ ? »
« አዎን ኮርኒሊያ እኮ ትዛመዳቸዋለች »
« ባርባራ ቆንጆ ትመስልሃለች ? »
« በጣም ! »
« ታዲያ እንዶዚህ ቅርብ ግንኙነት ካለህ ከሷ ጋር ፍቅር ይዞህ አያውቅም?
ሚስተር ካርላይል ከባርባራ ጋር ሲነጋገሩት የነበረው ትዝ አለውና ሣቀ
«ምን ! ምን አልሺኝ ሳቤላ ? »
« ከባርባራ ሔር ጋር ፍቅር ይዞህ አያውቅም ወይ ? »
« ፍቅር ! ምን ሐሳብ ነው በጭንቅላትሽ የገባው ... ሳቤላ ? እኔ ከአንዲት ሴት በቀር ወድጄ አላቅም ያችንም ሴት ሚስቴ አድርጌያታለሁ»
፡ ፡ ፡ ፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡
ሳቤላና ሚስተር ካርላይል ከተጋቡ ሁለተኛ ዓመታቸውን ያዙ " ሚስ ካርላይልን ባይጥልባት ኖሮ ሳቤላ ደስተኛ ትሆን ነበር " ሌትዮይቱ እስካሁንም ኢስትሊን ላይ ተደላድላ ቁጭ አለችና ጠቅላላ ቤቱን ጤና ነሳችው " ለስሙ የቤቱን ኃላፊነትና ባለቤትነት ለሳቤላ ሰጠች " የእውነቲቱ የቤቱ ባለቤትና አዛዥ ግን ራሷ ሚስ ኮርኒሊያ ካርላይል ሆነች" ሳቤላን ከዕቃ ይህን ያህልም አብልጣ አታያትም ምስኪኗ ሳቤላ በጠራው ጠባይዋና በዐይነ አፋርነቷ ሞገደኛይቷን ሴትዮ
መቋቋም ስለ አልቻለች ከዛ ቤቷ ተጨቁናና ተዋርዳ ተቀመጠች "
ሚስተር ካርላይል ከቤቱ እንደዚህ የመስለ ችግር አለ ብሎ ጠርጥሮ አያውቅም ከቤት የሚገኘው ጧትና ማታ ብቻ ነው ይኸንም ከሥራ ውጭ ሰዓት አብዛኛውን ማንም ሰው ሳይጨምሩ እሱና ሚስቱ አብረው ሲያሳልፉትም እሷ እንዲህ ሆንኩ "ብላ አትነግረውም
በተረፈ የሥራው ብዛት ከጊዜ ወደጊዜ እየበዛበትና እየተጫነው በመሔዱ ከቤት ውስጥ አለመጣጣም መኖሩ አልታየውም
አንድ ቀን ሁለቱ ሴቶች ተጋጩና ነገር ተፈጠረ " በመጨረሻ ሚስ ካርላይል ትእዛዟን ስለአነሣች ሊፈታ ቢቻልም ዐመሏ ከመቸውም የበለጠ ከፋ ሳቤላ አንድ ቀን ለብቻቸው ቢቀመጡ የበለጠ የደስታ ኑሮ እንደሚኖሩ ለባሏ አነሣችለት " ለዚሁም ሚስ ካርላይልን የበደለችና ያስቀየመች መስሏት ከመጨነቋ የተነሣ ልቧ
ይመታ ጀመር " ፊቷ ደም መሰለ ተሣቀቀች እሱም ነገርን መደበቅና ማለባበስ ስለማይችል ለእኅቱ ፍርጥ አድርጎ አስረዳት " እሷ ደሞ በበኩሏ ዘለለች " ጉብ ቂጥ
አለች » በመጨረሻም ምን እንዳስቀየመች ለብዙ የሚበቃ ትልቅ ቤት ይዘው ለምን አንድ ጥግ ሊነፍጓት እንደ ፈለጉ ሳቤላን ጠየቀቻት » ሳቤላም ጠላቷን እንኳን ለማስቀየም ስለማትወድ ወዲያው መልሳ ይቅርታ ጠየቀች » ባሏንም የነገረችውን ሁሉ እንዲረሳው ለመነችው " እሱም ከዚያ ወዲህ ነገሩን አስቦት አያውቅም " ውስጠ ነገር እንደ ነበረባትም አልጠረጠረም። ከእውነተኛው ሁኔታ ትንሽ
ጫፍ ቢይዝ ኖሮ ግን ' ሚስቱን ከሚስ ካርላይል አምባገነን ጭቆና ለማላቀቅ አፍታ
እንኳን አይቆይም ነበር "
አንድ ቀን መታገሥ እንኳን ወግ ነበር “ የሚስተር ካርላይል ጋብቻ ከባድ ድህነት ላይ የሚጥል ወጭ የሚያስከትል እንደሚሆን ሳቤላን በየአጋጣሚው ትጨቀጭቃት ጀመር " ይህም ንግግር ከልክ ያለፈ ልቧን አስጨነቀው በተለይ በወጭ ረገድ እውነትም የሚስተር ካርላይል አጥፊው እንደ ሆነች በአእምሮዋ ተቀረጸ " አንድ ቀን የገና ጊዜ ማውንት እስቨርን ከልጁ ጋር ሆኖ ሊጠይቃቸው መጣ " ሳቤላ በርግጥ ሚስተር ካርላይል ሲያገባት ሌላ ቢያገባ ኖሮ ላይፈጽመው ይችል የነበረ
ውን ነገር አድርጐላት እንደሆነና ይኸን በማድረጉም ያልተጠበቀ ወጭ አስወጥቶት እንደሆነ አስተያየቱን ጠየቀችው » በርግጥ የፈራችው ነገር የደረሰባት መሆኑንና አሁንም ቢሆን የቸርነቱን ወለታ መዘንጋት እንደማይገባት ነገራት " እሷም የተነገራትን በማመን ምክሩን ተቀበለች » ከሚስ ካርላይል ጋርም ምልልስ አቆመች "የባሏን ውለታ ለመመለስ ለሚስ ካርላይል ፈቃድና ፍላጐት ተገዛች ኢስት
ሊን ሲታደስና ዕቃው ሲሟላ ለሚስ ካርላይል ብዙ ገንዘብ አውጥታ ነበር ከነሱ ዘንድ የተደረበችውም ለራሷ ገንዘብ ለማጠራቀም አልነበረም " ገንዘቧን ያወጣችው
ለኢስት ሊንም ሆነ ለሌላ ዙሮ ዙሮ በመጨረሻ ገቢነቱ ለሚስተር ካርላይል ነበር ስለዚህ ሳቤላ ስትገባ ያስወጣችው አንሶ አሁንም ደሞ ኮርንሊያን በማወስወጣት ብዙ ገቢ ልታስቀርበት ደስ አላላትም።
ማንም ሊያስበው ወይም ሊያምነው ከሚችለው በላይ የተፈጥሮዋ ሥጉና ድንጉጥ
የሆነችው ሳቤላ ከቢጤዎቿ የመኳንንት ልጆች የተለየ ከሰዎች ተገልላ የሕይወትን ውጣ ውረድ ልምድ ሳታይ ያደች ስለነበረች ከዓለም ጋር ለመታግል በተለይም ከሚስ ካርላይል ጋር ለመቋቋም የምትችል አልነበረችም " ከአይቷ ጋር አለመቻቻሏን ብቻ ሳይሆን ውለታ የሚለው ነገርም ያለ መጠን ከበዳት አባቷም ያለ
ምንም ቤሳ ጥሏት የሞተ ከካስል ማርሊንግ በቀር ምንም የምትጠጋበት ቤት አጥታ ሰማይ ተደፍቶባት መሬት ጨልሞባት በነበረበት ሰዓት ነበር ካርላይል
ስታየው ሸሽጎ የተወላት አንድ መቶ ፓውንድ ሳይቀር እየተቆላለፉ በአእምሮዋ ተቀርጸው ትዝ እያሏት አፏን አሳርፋ ጻጥ ብላ እንድትቀመጥ ግድ ሆነባት "
የሚስተር ካርላይልን በጎ አድራጊነት ማመስገን እንዳለባት ከልቧ ተስማት
በሷ ምክንያት ከሚችለው በላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣቱን • እሷ የሀብቱ ጠንቅ መሆንዋን በየቀኑ መስማቱ ግን ከማትችለው የሕይወት ምሬት ከተታት ጀፈድፍረት ቢኖራት ኖሮ ከባሏ ጋር በግልጽ ተነጋግራ ' የገንዘብና የሌላም ያለፈ እርዳታ ባለውለታነት የሚባለው የዛች አስተሳሰበ ጠባብ እኅቱ አስተያየት እንጂ የሱ ..አለመሆኑን እሷንም ያገባት | አሁንም የያት ስለሚያፈቅራት ብቻ መሆኑን በአንድ ቃል ሊያረጋግጥላት ይችል ነበር "
እሷ ግን፥ከዚህ ሁሉ ሳትደርስ ሚስ ካርላይል የሚጕተመተም ዐመሏ ሲነሳባት ወይ ዝም ብላ ታዳምጣለች " አለበለዚያ ደግሞ በራስ ምታት የሚሠቃየውን
ራሷን በሁለት እጆቿ መኻል ደፍታ ምንም ሳትመልስ ውስጥ ውስጧን እያረረ በሆዷ መቻል እንጂ ለባሏ ስለ ብሶቷ ገልጻለት አታውቅም።.....
💫ይቀጥላል💫

👍26❤7🤔2
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
....እሷ ግን፥ከዚህ ሁሉ ሳትደርስ ሚስ ካርላይል የሚጕተመተም ዐመሏ ሲነሳባት ወይ ዝም ብላ ታዳምጣለች " አለበለዚያ ደግሞ በራስ ምታት የሚሠቃየውን
ራሷን በሁለት እጆቿ መኻል ደፍታ ምንም ሳትመልስ ውስጥ ውስጧን እያረረ በሆዷ መቻል እንጂ ለባሏ ስለ ብሶቷ ገልጻለት አታውቅም።
አንድ ቀን በየካቲት ወር ውስጥ አሽከሮች አንድ ስሕተት ሠሩ " ኮርኒሊያ ቀጥታ ሳቤላን ሳይሆን አሽከሮችን ስትሳደብ ስትጮህ ቆየችና ዝም አለች ሁሉም ጸጥ አለ " መንፈሷ ተጨንቆ ተስፋ የቆረጠች መስላ ፍዝዝ ብላ ተቀምጣ የነበረችው ሳቤላ ለራሷ የምትናገር መስላ ሚስ ካርላይል ግን እየሰማቻት « አዬ ! ምነው አሁንስ ቶሎ በመሸ » አለች "
« ለምን ቶሎ እንዲመሽ ፈለግሽ ?» አለቻት"
« አርኪባልድ ወደ ቤቱ እንዲመጣ ብዬ»
ሚስ ካርላይል ደስ የማይል ጉርምርምታ አሰምታ «የደከመሽ ትመስያለሽ .ፈእመቤት ሳቤላ» አለቻት "
« በጣም ደክሞኛል»
« አያስደንቅም " እኔ እንዳንቺ ቀኑን ሙሉ ምንም ሳልሠራ ብውል ለሞት የሚያደርስ ድካም ይይዘኝ ነበር " ሳስበው በሕይወቴ የምቆይ አይመስለኝም " "
« የሚሠራ ነገር እኮ የለም » አለቻት ሳቤላ "
«መሥራት ለሚፈልጉ ምን ጊዜም የሚሠራ ነገር አይታጣም " ለምሳሌ ዝም ብለሽ ከመቀመጥ እነዚህን የገበታ መሐረቦች ስቀመቅም ልትሪጅኝ ትችይ ነበር » አለች ኮርኒሊያ ካርላይል "
« እኔ መሐረብ ልቀመቅም ? » አለች ሳቤላ በመገረም "
« ከዚህ የባሰ ትሠሪ ይሆናል . . እሜቴ » አለች ኮርኒሊያ ካፏ ነጠቅ አድርጋ
« እኔ የዚህ ዐይነት ሥራ አይገባኝም » አለች ሳቤላ ረጋ ብላ
« ሌላውም ቢሆን ካልሞከረው በቀር አይገባወም በበኩሌ እጆቼን አጣጥፌ ከመቀመጥ ጫማ ብሠፋና ባድስ ይሻለኛል " ጊዜ ማባከን ወንጀል ነው "
« ዛሬ እንኳን ጤንነት አልተሰማኝም » አለች ሳቤላ »
« አድካሚ ሥራ መሥራት አልችልም»
« እንደሱ ከሆነ ደግሞ እኔ ብሆን በሠረገላ ወጣ ብዬ አየር እቀበል ነበር ሙሉ ቀን ከቤት ውስጥ ሲጠማረሩ መዋል ለስንኩላንም አይበጃቸውም »
«ግን ባለፈው ሳምንት ፈረሶቹ በርግግው ስለ አስነገጡኝ አርኪባልድ ራሱ ካልነዳ በቀር እንድወጣ አይፈቅድልኝም »
« ጆንም ቢሆን ያንቺን ባል ያህል የመንዳት ልምድ አለው " ፈረሶቹ አንድ ቀን የበረገጉ እንደሆነ ሁለተኛ ይበረግጋሉ ማለት አይደለም በይ አሁንም ጆን
ሠረገላውን እንዲያቀርብልሽ ደውይ " የኔ ምክር ይኸው ነው»
ሳቤላ ራሷን ነቀነቀችና «አይሆንም! በዝጉ ሠረገላ ካልሆነ በቀር ያለሱ እንዳል
ወጣ አርኪባልድ ነግሮኛል " እሱ ስለኔ ብዙ ያስባል " ስለዚህ ፈረሶቹ ቢዶፈደነብሩ እንኳን እሱ አብሮኝ ካለ እንደማልደነግጥ ያውቃል»
« አሁንስ በጣም ሆዶ ባሻ እየሆንሽ ሔድሽ መሰለኝ » አለቻት ኮርኒሊያ "
«ለኔም እየመሰለኝ ነው » ብላ መለሰችላት ሳቤላ « ከወለድኩ በኋላ ደኅና እሆናለሁ እንዳሁን አይጨንቀኝም " ብዙ የሚሠራ ነገር ይኖረኛል »
« ለሌሎቻችንም ብዙ ሥራ ይተርፈናል ብዬ አስባለሁ» ብላ አጕረመረመች ቀና ብላ አዬች
«እንዴ ! ምን ሆኖ ይሆን ? አርኪባልድ መጣ በዚህ ሰዓት ምን
አግኝቶት ይመጣል ? »
« አርኪባልድ ! » አለችና ሳቤላም ሒዳ ጥምጥም አለችበት « አንተን ሳይ ፀሐይ የወጣች ነው የመሰለኝ ፍቅሬ ግን ለምን መጣህ ? »
« በሠረገላ ሽርሽር ልወስድሽ » አላት ደወሎን እየደወለ "
« ጧት አልነገርከኝም »
« ምክንያቱም ለመምጣት መቻሌን አላረጋገጥኩም ነበር . . .ፒተር ! የድንክ
ፈረሶቹን ሠረገላ አምጣልኝ " ፈጠን በል እሱን ነው የምጠብቀው »
« ለምንድነው ? ሠረገላውን ለምን ፈለግኸው ? » አለችው ሚስ ካርላይል ሳቤላ ልብሷን ለመቀየር ስትወጣ።
« ለሽርሽር ትንሽ ወጣ ብለን አየር ተቀብለን ለመምጣት »
« ሽርሽር ? »
« አዎን እስቲ ሳቤላን ተመልከቻት እንደዚህ ሁና እያየሁ አምኜ ያለኔ አላስወጣትም »
«እንደዚህ እየተሆነ ነው ሥራ የሚሠራ በቀን እኩሌታ ሥራ እየጣሎ መውጣት»
አለችው ኮርነሊያ "
« በአሁን ጊዜ ከሥራ የሳቤላ ጤንነት የበለጠ ያሳስባል“ ደግሞ ዲልና ሌሎቹ ጸሐፊዎቼ እኔን ተክተው መሥራት እንደሚችሉ ታውቂያለሽ»
« ጆን ካንተ የተሻለ ሠረገላውን ይነዳ የለ ? »
« እሱም ጥሩ ነጂ ነው" ቁም ነግሩ ግን የሱ መቻል ወይም አለመቻል አደለም» ሳቤላ ለባብሳ ጭንቀቷ ሁሉ ለቋት እየተፍለቀለቀች መጣች " ሚስተር
ካርይል ደግፎ ካሳፈራት በኋላ ' ራሱ እየነዳ ሲሔድ ሚስ ካርላይል ቆማ ፊቷን ጭፍግግ አድርጋ ቁማ ትመለከታቸው ጀመር።
ሳቤላን የማያስዶስታት ይኸን የመሳሰሉ ብዙ ሁኔታዎች ነበሩ ነገር ግን ከሚስተር ካርላይል ፊት ክፉ ተናግራት አታውቅም » እሱን ሁልጊዜ ብትወርፈውም የለመደው ነገር ነበር » ሳቤላ ግን ከዚያ ንዝንዝ ውስጥ ድርሻዋን የምትቀበል አይመስለውም ነበር "
ወሩ ሚያዝያ ሰዓቱ ማለዳ ነው " ጆይስ ከእመቤት ሳቤላ ካርላይል መልበሻ ውስጥ እጆቿን በጭንቀት እያፋተገች ዕንባዋን በጉንጮቿ እያወረደች ተቀምጣለች በጣም ፈርታ ነበር
የመታመምን ምንነት ደጋግማ ያየች ይሁን እንጂ እንደ ዛሬው የመሰለ ሕመም ግን አጋጥሟት አያውቅም " ጆይስ ተቀምጣ ትጨነቅበት ከነበረው ክፍል ቀጥሎ ሚስዝ ሳቤላ ካርላይል በሕይወትና በሞት መኻል ሆና
ትስቃያለች "
በመተላለፊያው በኩል የሚያስገባው በር ቀስ ብሎ ተከፈተና ሚስ ካርላይል ገባች " በሕይወቷ ዘመን እንደዚያ ተጠንቅቃ በቀስታ ተራምዳ ታውቃለች ለማለት አያስደፍርም » ተደራርቦ በተጠቀጠቀ መደረቢያ ራሷንና ጆሮዋን ሸፍናለች"
ኩምሽሽ ብላ አንድ ወንበር ላይ ተቀመጠች ጆይስ ቀና ብላ ስታያት ፊቷ ልክ ንጋት ጢስ መስሏል"
« ጆይስ » አለቻት በሹhሹhታ
«ያሠጋል? »
« ኧረ የለም ... እሜቴ አይመስለኝም : ማየቱ እንዲህ ከባድ የሆነ ለደረሰበትማ በጣም አስጨናቂ መሆን አለበት »
« እሱ መቸም የጋራችን እርግማን ነው ጆይስ " አንቺና እኔ ግን ከዚህ ዕጣ ጋር የሚያገናኘን መንገድ ባለ መምረጣችን ዕድለኞች ነን » አለችና ትንሽ ዝምአለች »
«አደራውን ከክፉ ይሰውራት እኔ እሷ እንድትሞት ልፈልግም»
ሚስ ካርላይል በጣም ተጨንቃ ቀስ ብላ ነበር የምትናገር ምናልባት ይች ወጣት አዪቷ የሞተች እንደሆነ ጸጸቱ የዕድሜ ልክ የሕሊና ሸክም ሆኖባት እንዳይቀር ፈርታ ይሆናል " እሷ ብትፈልግ ኖሮ አጭሩ የጋብቻ ዘመኗን የደስታና የእፎይታ ጊዜ ልታደርግላት ትችል እንደ ነበር ከባድና የማይወርድ ሸክም ሹክ ይላት እንደሆነ አይታወቅም : በጣም የፈራችና የተጨነቀች ትመስላለች "
« ጆይስ ... እንዲያው የሚያሠጋ ይመስልሻል ? »
«ለምንድነው ስለ ሥጋት የሚያስቡት? ሌሎች እንዴዚህ ታመው አያውቁም እንዴ”
« አይመስለኝም ... ጆይስ የሷ ለየት ያለ መሰለኝ " ለምንድነው
ዶክተር ማርቲን ቶሎ እንዲደርስ
ቴሌግራም ወደ ሊንበራ የተላከ ?»
ጆይስ ከው ብላ ደነገጠች
«ዶክተር ማርቲን ቶሎ እንዲደርስ ? ማን ላክ
«መቸ ተላከበት ? »
« እኔ የማውቀው መልእክት መተላለፉን ብቻ ነው " ሚስተር ዌይንራይት ከጌታሽ ዘንድ ገብቶ ከወጣ በኋላ ጆንን ወደ ዌስት ሊን የቴሌግራም ቢሮ ጋልቦ እንዲሔድ አዘዘው -ፈረሱ ሲጋልብ ኮቴው እንደዚያ ሲጮህ ጆሮህ የት ነበር ? . .
ሲጋልብ ሰምቸ ለምን እንደሆነ ገባኝ " ስለዚህ ፍራት ፍራት አለኝ ሚስተር ካርላይል ዘንድ ሔጄ ብጠይቀው ደግሞ እሱ ምንም እንደማያውቅ ነገረኝና በሩን እፊቴ
ዘጋብኝ "

👍18
ጆይስ ምንም አልመለሰችላትም " ከመደንገጧ የተነሣ ሰውነቷ ዛለ » ከሚቀጥለው ክፍል ዐልፎ ዐልፎ ይሰማ ከነበረው ድምፅ በቀር ሁሎም ነገር ጸጥ ብሏል“
ሚስ ካርላይል ከተቀመጠችበት ተነሣች " ደኅና አድርጐ ላስተዋላት የምትንቀጠቀጥ ትመስል ነበር "
« እኔ ይህን ሥቃይ መስማት አይሆንልኝም " ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል ስለዚህ መሔዴ ነው
ጆይስ ቡና ወይም ሌላ ነገር ቢፈልጉ ጠይቂኝ እልካለሁ »
ብላ ወጣች "
« እሺ እጠይቃለሁ » አለች ጆይስ የሠራ አካላቷ እየተንቀጠቀጠ "
« ሊገቡ ነው እንዴ ...እሜቴ ?» አለቻት ጆይስ በአግሯ ጣት እየተራመዶች በቀስታ ወደ ውስጠኛው በር ስታመራ አየቻትና ሳቤላም የታየቻት እንደሆነ ደስ
እንደማይላት ገመተች
« እኔን ግን በክፍሉ ሌላ ሰው አያስፈልግም ብለው አስወጡኝ » አለቻት "
«ኧረ እኔ አልገባም ገብቶ የማይረዳ ሰው ከነጭራሹ ባይገባ ይሻላል እኔም የምረዳው ነገር የለም » አለች ኮርነሊያ
« ሚስተር ዌይንራይትም ሲያስወጡኝ ይኸንኑ ነው የነገሩኝ» አለች ጆይስ
ኮርነሊያ ወደ ኮሪደሩ አለፈችና ወጥታ ሔደች "
ጆይስ ተቀመጠች " ጊዜው ማብቂ ያለው አልመስላትም አለ " ትንሽ ቆይቶ ዶክተር ማርቲን ሲገባ ሰማችው " ከዚያ ሚስተር ዌይንራይት ጆይስ ወደ ነበረችበት ክፍል መጣ " ገና ስታየው ምላሷ ከትናጋዋ ተጣጋና · « የሚያሠጋ ይመስልሃል?” የሚለውን ሐረግ ከመተንፈሷ በፊት አልፏት ሔደ"
ሚስተር ዌይንራይት ሚስተር ካርላይልን አገኘዋለሁ ብሎ ወዳሰበቀት ክፍል ገባ " ሚስተር ካርላይል ከዚያ ክፍል ሌሊቱን ሙሎ ሲንጎራደድበት አድሮ ነበር "
ሐኪሙ ሲገባ የገረጣው ፊቱ ቀላ
« ዌይንራይት ... ዶክተር ማርቲን ከገባ ኻያ ደቂቃ ሆነ " ምን ይላል ? »
« እኔ ከተናገርኩት የተለየ ነገር አላገኘም " ምልክቶቹ በጣም አሳሳቢ ናቸው !ቢሆንም ምንም እንደማትሆን ተስፋ አለው » ግን በትዕግሥት ከመጠበቅ በቀር
የሚደረግ ነገር የለም " አሁን እንኳን የመጣሁት ሚስተር ካርላይል ... ቄስ ሊትልን ብታስጠራቸው ብዬ ነው :
ቄስ ሊትል የቤተ ክርስቲያኑ አለቃ ናቸው ሚስተር ካርላይል ቄስ የሚያስጠራ ምን ነገር ተገኘ ብሎ በድንጋጤ ጮኸ "
« እንዴ ለሚስትህ አይደለምኮ » አለ ሐኪም ዌይንራይት ፈጠን ብሎ «ለሚወለደው ሕፃን ነው " ምናልባት በሕይወት ካልቆየ ላንተም ለሚስዝ ካርላይልም
መጠመቁን ስታውቁ ደስ ይላችኋል »
« አይ ደኅና ተባረክ እሺ ይላክበታል » አለው ሚስተር ካርይል "
« አንተ በቃ የቄስ ነገር ሲነሣ የሚስትህ ነፍስ የበረረች መሰለና ደነገጥህ ? ኧረ ፈጣሪ አደራውን ይህ ባያድግ እንኳን ሌሎች ልጆች እንድትተካልህ ዕድሜ ይስጥልህ»
« እስቲ እግዚአብሔር ይስማህ»
ጊዜው ዕኩለ ቀን ነበር » ቄስ ሊትል ሚስተር ካርይልና ሚስ ካርላይል አንድ ትልቅ ባለጌጥ የሸክላ ገበታ መጥመቂያ ውሃ እንደያዘ ከመኻሉ ከተቀመጠበት
ጠረጴዛ ዙሪያ ከበው እንደ ቆሙ ጆይስ አንድ የተጠቀለለ ጨርቅ መሳይ ይዛ ቀረበች "ሚስተር ካርላይል ለሚስቱ ከነበረው ጭንቀት ጋር ሲነጻጸር ለዚህ ጥቅል ጨርቅ አምብዛም አልተጨነቀበትም
« ጆይስ . . እስካሁን ሁሉ ነገር ደህና ነው ? » አለ ሚስተር ካርላይል ሥርዓተ ጸሎቱ ተጀመረ « ይመስለኛል..ጌታዬ » ካህኑ ሕፃኑን ትቀበለ » « ስሙን ማን ትሉታላችሁ ? »
ሚስተር ካርላይል ስለ ስሙ እምብዛም አላሰበበትም ነበር ቢሆንም ምንም ሳያመነታ
«ዊልያም » ብሎ መለሰ
ምክንያቱም ይሀ ስም ሳቤላ የምትወደውና የምታከብረው መሆኑን ያውቅ ነበር።
ካህኑ ጣቶቹን ከውሃው ነከረ ጆይስ ነገሩ ግራ ገብቷት ወደ ጌታዋ እየተመለከተች « ኧረ ሴት ነች እኔ እኮ ቅድም ተናግሬ ነበር » አለችው
ሁሉም ጥቂት ዝም አሉ » ከዚያ
ለልጅቱ ስም አውጣላት » አለ ቄሱ
« ሳቤላ ሉሲ » አለ ሚስተር ካርይል ኮርነሊያ ሥያሜው አስከፋትና አፍንጫዋን ነፋች " ምናልባት በሷ ስም ብትጠራላት ፈልጋ ኖራ ይሆናል " እሱ ግን
አንድ ጊዜ በሚስቱና በናቱ ስም ሠይሞ አበቃ።
ሚስተር ካርላይል ለማየት እስከ ማታ ሳይፈቀድለት ዋለ አሁን ገብቶ ሲያያት ዐይኖቹ አንጸባረቁ " እሷም ስሜቱን ተረዳችና ከትንሽ ፈገግታ በኋላ ከንፈሯን ገርበብ አደረጀቻቸው "
« ጭንቄን መቻል አቃተኝ መሰለኝ... አርኪባልድ ? ቢሆንም በማለፉ አምላካችንን ማመስገን ይገባናል " የሥቃይን መጠን በራስ ደርሶ ካልቀመሱት በቀር
ማንም ሊያውቀው አለመቻሉም ትልቅ መታደል ነው»
« እኔ ደግሞ ማወቅ የሚችሉ ይመስለኛል » አለ ሚስተር ካርላይል "
« እኔ የምስጋናን ምንነት እስከ ዛሬ ቀን ድረስ አላውቀውም ነበር »
« በሕፃኒቱ መትረፍ ነው ? » አለችው ሳቤላ "
« ባንቺ መትረፍ አንጂ . . . ሳቤላ ' ለኔ ተረፍሽልኝ · ዳንሽልኝ እስከ ዛሬ እውነተኛ ጸሎት በጭንቅ የተያዘ ልብ የሚያደርገው ጸሎት አይገባኝም ነበር "
« ሕፃኗን ለምን በኔ ስም ሠየምካት ? »
« ከዚህ ያማረ ስም መስጠት እችል ይመስልሻል ? አልችልም »
« ምነው ወንበር አስመጥተህ ባጠገቤ ብትቀመጥ ? »
ሳቅ አለና ራሱን ግራ ቀኝ ነቀነቀ » « ቢቻለኝ ኖሮ ደስ ይለኝ ነበር ነገር ግን ሐኪሞቹ ካንቺ ጋር እንድቆይ የፈቀዱልኝ ለአራት ደቂቃ ብቻ ነው " ዌይንራይት
ሰዓቱን እያየ ከመዝጊያው ጥግ ቁሞ እየጠበቀኝ ነው "
እውነትም የሁለቱ ጭውውት ከመጀመሩ ሰዓቱ ደረሰ "...

👍34👎1
ሰውን በመፍጠሩ እግዜር የሚጠቀመው
ሰውም በመፈጠር ከእግዜር የሚያገኘው
አንዳች እውነት ባይኖር አንዳች ድብቅ ነገር
ምድሪቱን ለመሙላት ከብት ይበቃ ነበር።
🔘ኤፍሬም ስዩም🔘
ሰውም በመፈጠር ከእግዜር የሚያገኘው
አንዳች እውነት ባይኖር አንዳች ድብቅ ነገር
ምድሪቱን ለመሙላት ከብት ይበቃ ነበር።
🔘ኤፍሬም ስዩም🔘
👍44❤27👏26🥰4🔥3🤔3
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...የምስጋና ቀንና ገና እንደቀረበ ሊያስታውሰን ህያው የቀን መቁጠሪያችን የሆነው የረጅሙ አትክልት አገዳ ትንሽ እምቡጥ ያዘ፡ ያልደረቀው ብቸኛ አትክልታችን እሱ ብቻ ስለነበር በጣም የምንወደው ንብረታችን ነበር᎓ ጣሪያው ስር ካለው ክፍል አንስተን አንድ ሞቃት ምሽት ከእኛ ጋር እንዲያሳልፍ ወደ መኝታ ክፍላችን ወሰድነው: በየማለዳው ገና ሲነጋ ኮሪ ያቺ እምቡጥ ምሽቱን በደህና ማሳለፏን ለማረጋገጥ ሮጦ ሄዶ ይመለከታታል ኬሪም ተከትላው ሄዳ አጠገቡ ትቆምና ሌሎች ሲደርቁ ብቻዋን በመቆየቷ ያቺን ድል አድራጊ ጠንካራ ተክል ታደንቃለች አፈሩ ውሀ የሚፈልግ መሆኑ መንትዮቹ ቢሰማቸውም፣
ግድግዳው ላይ የተሰቀለውን ቀን መቁጠሪያ እየተመለከቱ ቀኑ አረንጓዴ ተሰምሮበት፣ አትክልቱ ውሀ የሚፈልግበትን ቀን እንዲያመለክት ይጠብቃሉ።
ያ ስለማይሆንና በራሳቸው ለማድረግም እርግጠኛ ስለማይሆኑ ወደ እኔ ይመጡና “አትክልቱን ውሀ እናጠጣው? ውሀ የጠማው፦ ይመስልሻል?” ሲሉ ይጠይቁኛል።
ስም የምንሰጠውና የኛ የምንለው ግዑዝም ሆነ ህያው ነገር የለንም
አትክልታችን ብቻ ከኛ ጋር ለመኖር ቆርጧል ኬሪም ሆነች ኮሪ ከባዱን ማሰሮ ይዘው በቅርብ የፀሀይ ብርሃን ወደሚኖርበት ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ለመውሰድ ጥንካሬ አልነበራቸውም፡ ስለዚህ እኔ አትክልቱን እንድይዘው ተፈቀደልኝ ሲመሽ ደግሞ ክሪስ ወደታች ይመልሰዋል በእያንዳንዱ ምሽት ተራ በተራ ቀኖቹን በቀይ ቀለም ምልክት እናደርጋለን፡ እስካሁን መቶ ቀኖች
ላይ ምልክት አድርገናል።
ክረምቱ በመግባቱ ዝናብ መጣ፡፡ ሀይለኛ ንፋስ እየነፈሰ ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ከባድ ጭጋግ የጠዋቷን የፀሀይ ብርሀን ይከልላታል ምሽት ላይ ደግሞ
ነፋሱ የደረቁትን የዛፍ ቅርንጫፎችን ከቤቱ ጋር ሲያስታክካቸው ከእንቅልፌ
ያባንነኝና የሆነ አስፈሪ ነገር መጥቶ የሚበላኝ እየመሰለኝ ትንፋሽ ያጥረኛል በኋላ ላይ ወደ በረዶ ሊለወጥ የሚችል ዝናብ እየወረደ ባለበት ቀን እናታችን
ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ የምስጋና ቀን በዓል እንዲመስልልን ጠረጴዛችንን
የምናስጌጥባቸው የሚያማምሩ የግብዣ ጌጣጌጦች ይዛ ወደ መኝታ ክፍላችን ገባች በተጨማሪም ብሩህ ቢጫ ቀለም ያለው የጠረጴዛ ልብስና ጥልፍ
ያለበት ብርቱካናማ የአፍ መጥረጊያ መሀረቦች ይዛ ነበር።
የያዘችውን ዕቃ በሩ አጠገብ ያለው አልጋ ላይ እያስቀመጠችና ለመውጣት ፊቷን እያዞረች: “ነገ እራት ላይ እንግዶች አሉብን” ስትል አብራራች: “እና አንደኛው ለእኛ ሌላኛው ደግሞ ለሰራተኞቹ የሚሆን ሁለት ዶሮዎች
ይጠበሳሉ፡ ነገር ግን አያታችሁ የሽርሽር ቅርጫት ይዛ በምትመጣበት ወቅት አይደለም ግን አትጨነቁ፣ ልጆቼ በምስጋና ቀን ለቀኑ የሚመጥን ምግብ
ሳይኖራቸው በዓልን አያሳልፉም እንደምንም ብዬ እኛ ከምንበላው ምግብዐለእናንተ የማመጣበትን መንገድ እፈልጋለሁ ለአባቴ ራሴ እንዳቀርብለት እፈልጋለሁ ብዬ ብዙ አዘጋጅና ለእሱ የማቀርበውን ሳሰናዳ በሌላ ትሪ ደግሞ
ለእናንተ ላስቀምጥላችሁ እችላለሁ ነገ ሰባት ሰዓት አካባቢ ጠብቁኝ” አለች።
በትልቅ ሳህን የሚቀርብ ትኩስ የምስጋና ቀን ምግብ ለመብላት በመጠበቅ ደስታ ውስጥ ጥላን ልክ በበሩ በኩል እንደሚገባው ነፋስ ገብታ ወጣች።
“የምስጋና ቀን ምንድነው? አለች ኬሪ።
“ከምግብ በፊት ከማመስገን ጋር አንድ ነው” ሲል ኮሪ መለሰላት በአንድ በኩል ልክ ነው ብዬ አስባለሁ።
ሰባት ሰዓት መጣ፣ ሄደ። ኬሪ ጮክ ብላ አጉረመረመች “አሁን ምሳችንን እንብላ፣ ካቲ!”
“ታገሺ እናታችን ልዩ ትኩስ ምግብ፣ ዶሮና ማባያዎቹ ሁሉ ያሉበት ትሪ ይዛ ትመጣለች ይኼኛው ለእራታችን ነው ምሳ አይደለም” አልኳት: የእኔ የቤት እመቤትነት ስራ ለጊዜው አለቀና በደስታ አልጋው ላይ ጥቅልል ብዬ
ማንበብ ጀመርኩ።
ካቲ ሆዴ ትዕግስት የለውም” አለ ኮሪ፤ ክሪስ በሸርሎክ ሆልምስ ታሪክ ተመስጧል፡ መንትዮቹ ሆዳቸውን ፀጥ እንዲል አድርገው እንደ እኔና እንደ ክሪስ ቢያነቡ ጥሩ አልነበር?
“የተወሰኑ ዘቢቦች ብላ ኮሪ”
“ምንም የተረፈ የለም”
“ለውዝ ብላ”
“ለውዙም ሁሉም አልቋል”
“እሺ ብስኩት ብላ”
“የመጨረሻውን ብስኩት ኬሪ በልታዋለች”
“ኬሪ ብስኩቶቹን ለምን ለወንድምሽ አላካፈልሽውም?”
“የዚያን ጊዜ አልፈልግም ብሎኝ ነው”
ስምንት ሰዓት ሆነ አሁን ሁላችንም እርቦናል። ሁልጊዜም ልክ ስድስት
ሰዓት ላይ ነው የምንበላው፡ እናታችንን ምን አዘገያት? በመጀመሪያ ራሷ ልትበላና ከዚያ ልታመጣልን ነው? ግን'ኮ እንደዚያ አላለችንም ነበር።
ዘጠኝ ሰዓት አለፍ እንዳለ እናታችን በችኮላ ገባች ከላይ በሳህኖች የተሸፈነ ትልቅ ብራማ ቀለም ያለው ትሪ ይዛለች። ሰማያዊ የሱፍ ቀሚስ ለብሳለች። ፀጉሯ ደግሞ ከፊቷ ላይ ተሰብስቦ ኮሌታዋ አካባቢ ዝቅ ብሎ በፀጉር መያዣ
ተይዟል፡ እንዴት ታምራለች! “እንደራባችሁ አውቄያለሁ።" ወዲያውኑ ይቅርታ መጠየቅ ጀመረች: “በመጨረሻዋ ደቂቃ ላይ አባቴ ሀሳቡን ቀይሮ
ተሽከርካሪ ወንበሩን በመጠቀም ከእኛ ጋር ለመብላት ወሰነ።” በመጠኑ ፈገግ አለችልን። “ካቲ ጠረጴዛውን ቆንጆ አድርገሽ አዘጋጅተሽዋል። ሁሉንም ነገር
በትክክል ነው ያደረግሽው: እኔ ግን አበቦቹን ስለረሳሁ ይቅርታ: መርሳት አልነበረብኝም: ዘጠኝ እንግዶች ነበሩብኝ ሁሉም እያዋሩኝና ለብዙ ጊዜ የት
እንደነበርኩ ሺ ጥያቄዎችን እየጠየቁኝ ነበር እና ጆኒ ሳያየኝ የአስተናጋጆቹ ጓዳ ውስጥ መግባት እንዴት ችግር እንደሆነ አታውቁም ያ ሰው ከኋላው
ሳይቀር አይን ያለው ነው የሚመስለው ማንም ሰው እንደኔ ከምግብ ላይ አስር ጊዜ ቁጭ ብድግ ሲል አይታችሁ አታውቁም
“እንግዶቹ ጨዋ እንዳልሆንኩ፣ ወይም ሞኝ እንደሆንኩ ሳያስቡ አይቀርም ግን ያም ሆኖ ሳህኖቻችሁን መሙላትና መደበቅ ችዬ ነበር ከዚያ ወደ መመገቢያው ጠረጴዛ መመለስ፣ ፈገግ ማለትና ሌላ ክፍል ገብቼ አፍንጫዬን
ከማፅዳቴ በፊት ደግሞ አንዴ መጉረስ ነበረብኝ፡፡ መኝታ ክፍሌ ውስጥ ባለው የግል መስመር የተደወሉልኝን ስልኮች መመለስና ማንም እንዳይገምት ድምፄን
መቀነስ ሁሉ ነበረብኝ የዱባ ኬክ ላመጣላችሁ ፈልጌ፣ ጆን ቆራርጦ ሳህኖች ላይ አድርጓቸው ነበር። ምን ማድረግ እችላለሁ? አራት ኬኮች ቢጠፉበት ማወቁ አይቀርም:"በአየር ላይ ሳመችን ደስ የሚል ግን የችኮላ ፈገግታ ሰጠችንና ከበሩ ወጥታ ተሰወረች: አምላኬ ሆይ! እውነትም ህይወቷን አወሳስበንባታል! ለመብላት ወደ ጠረጴዛው ተጣደፍን፡ ክሪስ አንገቱን ዝቅ አድርጎ ጆሮዎች ልብ የሚነካ ምስጋና በሚሰሙበት በዚህ ቀን እግዚአብሔርን ብዙም የማያስደስት የችኮላ ምስጋና አቀረበ፡ “ጌታ ሆይ፣ ስለዚህ ስለዘገየ የምስጋና ቀን ምግብ
እናመሰግንሀለን፡፡ አሜን!”
በክሪስ ቀጥታ ወደ ጉዳዩ የመግባት ባህርይ እየሳቅኩ፣ አስተናጋጃችን እርሱ በመሆኑ ሳህን አቀበልኩትና አንድ በአንድ ምግባችንን ሳህኖቻችን ላይ አደረገልን ምግቦቹ እየቀዘቀዙ ነበር: “ቀዝቃዛ ምግብ አንወድም!” አለች ኬሪ ሳህኗ ላይ የተደረጉላትን ምግብ እየተመለከተች።
የእውነቴን ለእናቴ አዘንኩላት ለእኛ ትኩስ ምግብ ለማምጣት ስትሞክር የራሷን ምግብ በስርዓት ሳትበላ በእንግዶቹ ፊት እንደሞኝ ተቆጥራ፣ አሁን ደግሞ እነዚህ ሁለቱ ሶስት ሰዓት ሙሉ ራበን እያሉ ሲነጫነጩ እንዳልቆዩ
ስለቀዘቀዘ አንበላም ይላሉ… አይ ልጆች!
ክሪስ በየጠዋቱ በሽርሽር ቅርጫት መጥቶ ከሚወረወርልን የችኮላ ምግብ በተለየ በሚጥም ሁኔታ የተሰራውን ምግብ በመብላት በደስታ አይኖቹን ጨፈነ። እውነት ለመናገር አያታችን አንድም ቀን ረስታን አታውቅም።

👍31❤6🥰1
ክሪስ የእውነት ያስደነገጠኝን አንድ ነገር አደረገ፡ ትልቅ ስጋ በሹካ ያዘና
ሙሉውን ወዳፉ ከተተው ምን ነክቶታል!
“እንደዚያ አትብላ ክሪስ። ለልጆቹ መጥፎ ምሳሌ ትሆናለህ” አልኩት።
በአፉ ሙሉ ምግብ እንደያዘ “እነሱ እያዩኝ አይደለምº በዚያ ላይ እርቦኛል።በህይወቴ እንደዚህ ርቦኝ አያውቅም: ምግቡ ደግሞ በጣም ይጣፍጣል” አለ፡
እኔ በመቀማጠል አይነት በትንሹ ቆረጥኩና አፌ ውስጥ ከተትኩ። እግረ መንገዴን በትክክል የሚበላው እንዴት እንደሆነ እያሳየሁት ነበር በመጀመሪያ
ዋጥኩኝና “ለምታገባት ሚስት አዘንኩላት፡ በአመት ውስጥ ትፈታሀለች " አልኩት።
ከመደሰት በቀር ለሁሉም ነገር ዲዳና ደንቆሮ ሆኖ መብላቱን ቀጠለ፡
“ካቲ… ክሪስ ላይ ክፉ አትሁኝበት፤ እኛም ቀዝቃዛ ምግብ ስለማንወድ መብላት ስለማንፈልግ ነው:: አለች ኬሪ
“ሚስቴ በጣም ትወደኛለች፤ የቆሸሹ ካልሲዎቼን ማንሳት ያስደስታታል።
ኬሪ፣ አንቺና ኮሪም ቀዝቃዛ ምግብ ትበላላችሁ:"
ምግቡ አልቆ ጠረጴዛውን ማፅዳት ስጀምር ክሪስ ያግዘኝ ጀመር፡ ላምን አልቻልኩም! በመረታት አይነት ፈገግ አለና ጉንጬን ሳመኝ፡ ከዚያ ወደ እኔ መጥቶ ሳህኖችን ሳጥብና ሳደራርቅ ከማገዙ በፊት ካልሲዎቹን ሳይቀር
አነሳ፡ አሪፍ ምግብ አንድን ወንድ እንዲህ ሊያደርግ ከቻለ፣ ምግብ ዝግጅት መማር ያዋጣል።
ክሪስና እኔ ሁሉንም ነገር አፅድተን በንፁህ ፎጣ ሸፍነን ጠረጴዛው ስር አስቀምጠን ከጨረስን ከአስር ደቂቃ በኋላ መንትዮቹ በአንድ ላይ “እርቦናል ሆዳችንን አመመን፡" እያሉ ጮሁ።
ክሪስ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ እያነበበ ነበር፡ እኔም ጋደም ብዬ ከማነብበት ተነሳሁና ምንም ሳልናገር በለውዝ ቅቤ ሳንድዊች ሰርቼ ሰጠኋቸው።
ወለሉ ላይ ተቀምጠው እየበሉ ሳለ ራሴን አልጋ ላይ ወረወርኩና ግራ በመጋባት ተመለከትኳቸው፡ እንዴት ይህንን የማይረባ ምግብ ወደዱት? ወላጅ መሆን ለካ እገምተው እንደነበረው ቀላል ወይም ደስ የሚል አይደለም።
“ኮሪ ወለሉ በጣም ይቀዘቅዛል ወለሉ ላይ አትቀመጥ።” አልኩት።
በሚቀጥለው ቀን ኮሪን ሀይለኛ ብርድ አመመው: ትንሽዋ ፊቱ ፍም መስላ በጣም ያቃጥላል ሰውነቱን ሁሉ እያመመው እንደሆነ ተናገረ ካቲ እናቴ የታለች? እውነተኛዋ እናቴ?” እናቱን ነው የፈለገው: በመጨረሻ መጣች።
ወዲያውኑ የኮሪን የጋለ ፊት ስትመለከት ፈጠን ብላ የሰውነት ሙቀት መለኪያ አመጣች: ደስ ሳይላት የምታስጠላውን አያታችንን ተከትላ ዞር
አለች::
ኮሪ የሙቀት መለኪያውን አፉ ውስጥ እንደያዘ በጭንቀቱ ጊዜ ልታድነው የመጣች ወርቃማ መልአክ ትመስል እናቱን አተኩሮ እየተመለከተ ነበር።የእናትነት ቦታ ተክታ የነበረችው ግን ተረሳች:
“የምወድህ ውዱ ልጄ” እሹሩሩ ልትለው ከአልጋው ላይ አንስታ አቅፋው የሚወዛወዘው ወንበር ላይ ተቀመጠችና ቅንድቦቹን እየሳመች “አለሁልህ የኔ ልጅ እወድሀለሁ እንከባከብህና ህመምህን እናጠፋዋለን፡ እንደ ጎበዝ ልጅ ምግብህን ብላ፣ የብርቱካን ጭማቂህንም ጠጣ ከዚያ ቶሎ ትድናለህ" አለችው::
እንደገና አልጋ ላይ አስተኛችውና አስፕሪንና ውሀ ሰጥታው እንዲውጥ አደረገች: ሰማያዊ አይኖቿ በእምባ ረጥበዋል። ቀጫጭን እጆቿ በደመነፍስ
ይሰራሉ፡ አይኖቿን ጨፍና ፀሎት የምታደርግ ይመስል ከንፈሮቿ ሲንቀሳቀሱ እያየሁ ነው።
ከሁለት ቀናት በኋላ ኬሪም ከኮሪ አጠገብ አልጋ ላይ ሆነች: እሷም
እያስነጠሰችና እያሳላች የሰውነቷ ሙቀት በሚያስፈራ መጠን ከፍ አለ፡ ክሪስም የፈራ ይመስላል ፍዝዝ ብለውና ገርጥተው ሁለቱም ትልቁ አልጋ ላይ ጎን ለጎን ተኝተዋል።
ከሸክላ የተሰሩ ይመስሉ ነበር፡ ሰማያዊ አይኖቻቸው ወደ ውስጥ እየጎደጎዱ በመሄዳቸው ትልቅ መሰሉ: አይኖቻቸው ስር ጥቁር ጥላ አጠላባቸው እናታችን አጠገባችን በሌለች ጊዜ አይኖቻቸው በፀጥታ እኔና ክሪስ ላይ ተተክለው የሆነ ነገር እንድናደርግና ስቃያቸውን ማጥፋት እንድንችል ይማፀኑናል፡
እናታችን ከትምህርት ቤቷ ተመልሳ ከልጇ ጋር ለመሆን ሳምንት ወሰደባት በጣም ያስጠላኝ ነገር አያትየው እናታችን በመጣች ቁጥር ተከትላ የመምጣቷ አስፈላጊነት ነው ሁልጊዜ አፍንጫዋን በማያገባት ቦታ መክተት፣ የእሷን ምክር የማንፈልግበት ጊዜ ላይ ምክር መስጠት ትወዳለች አስቀድማ
እንዳልተፈጠርን፣ እግዚአብሔር በፈጠራትና እንደሷ ፃድቅና ንፁህ ለሆኑ ያዘጋጃት ምድር ላይ በህይወት ለመኖር መብት እንደሌለን ነግራናለች።
የምትመጣው የበለጠ ልታሰቃየንና እናታችንን ለራሳችን በማድረጋችን ያገኘነውን ምቾት ለመንጠቅ ነው።
የግራጫ ቀሚሷ መንኮሻኮሽ፣ ድምፅዋ፣ የከባድ እግሮቿ እርምጃ ድምፅ፣በአልማዝ ቀለበቶች የተንቆጠቆጡ፣ ቡናማ ነጠብጣብ የሞላባቸው የገረጡ፣
ለስላሳ፣ ወፍራምና ትልልቅ እጆቿ! አምላኬ እሷን ማየት እጅግ ያሰለቻል፡
ከዚያ እናታችን በአብዛኛው እየፈጠነች ትመጣና መንትዮቹን ወደ ጤንነታቸው ለመመለስ የቻለችውን ሁሉ ታደርጋለች: ለመንትዮቹ መጀመሪያ አስፕሪንና
ውሀ፣ በኋላ ደግሞ የብርቱካን ጭማቂና ትኩስ የዶሮ ሾርባ ሰጠቻቸው።
አንድ ጠዋት እናቴ ራሷ ጨምቃ ያዘጋጀችው የብርቱካን ጭማቂ የያዙ ሁለት ትልልቅ ፔርሙዞች ይዛ መጣች: “ከቀዘቀዘው ወይም በቆርቆሮ ከታሸገው ይሻላል፤ በቫይታሚን ሲ እና ኤ የተሞላ ስለሆነ ለብርድ በጣም ጥሩ ነው::” ስትል አብራራችልን፡፡ ከዚያ እኔና ክሪስ ቶሎ ቶሎ የብርቱካን ጭማቂውን እንድንሰጣችው ነገረችን፡
እናታችን ከኬሪ ከንፈሮች ላይ ያነሳችውን የሙቀት መለኪያ ስትመለከት ደነገጠች: “አምላኬ! ወደ ዶክተር ልወስዳት ይገባል፡ ወደ ሆስፒታል!”
አያትየውን አየት አደረግኳት፤ ለዚህ ነገር ያላትን ምላሽ ማወቅ እየሞከርኩ ነው: አያትየው ለእንደዚህ አይነት ከቁጥጥር ውጪ መሆንና መርበትበት
ምንም ትዕግስት አልነበራትም “ሞኝ አትሁኚ ኮሪን: ልጆች ሁሉ ሲያማቸው ትኩሳት ይኖራቸዋል ምንም ማለት አይደለም አሁን ያንን ማወቅ አለብሽ ብርድ በቃ ብርድ ነው” አለች
ክሪስ ከሚያነበው መፅሀፍ ላይ ጭንቅላቱን ቀና አደረገ:፡ መንትዮቹ ኢንፍሉዌንዛ
ይዟቸው እንደሚሆን አምኗል: ያልገባው ቫይረሱን ከየት እንዳገኙት ነው::
አያትየው ቀጠለች “ዶክተሮች ብርድን ስለማዳን ምን ያውቃሉ? እኛ ብዙ እናውቃለን፡፡ ማድረግ የሚያስፈልጉ ሶስት ነገሮች አሉ᎓ አልጋ ውስጥ መቆየት፣
ብዙ ፈሳሽ መጠጣትና አስፕሪን መውሰድ ሌላ ምን ያስፈልጋል? እና እነዚያን ነገሮች ሁሉ አላደረግንም?” በክፉ አይን ተመለከተችኝና “እግሮችሽን
ማወዛወዝ አቁሚ አንቺ! እየረበሽኝ ነው:" አለች እንደገና አይኖቿንም፣
ቃላቶቿንም ወደ እናታችን መለሰች ለእናታችንም “ብርድ ለመያዝ ሶስት ቀን ህመሙ ሶስት ቀን ይቆያል በሶስት ቀን ውስጥም ይለቃል” አለች
“ኢንፍሉዌንዛ ቢሆንስ?” አለ ክሪስ አያትየው ጥያቄውን ችላ ብላ ጀርባዋን አዞረች በጣም አባታችንን ስለሚመስል መልኩን አትወደውም አያትየው እንደገመተችው መንትዮቹ ተሻላቸው፤ ግን በዘጠኝ ቀን ሳይሆን በአስራ ዘጠነኛው ቀን ነበር፡ ደህና የነበሩ ጊዜ ብዙ ጥያቄ የማይጠይቁት
ከታመሙ በኋላ ግን ጥያቄዎች መጠየቅ አበዙ።
የሚያነጫንጯቸውንና የሚያስጨንቋቸውን ነገሮች ሁሉ በቃላት መግለፅ ባለመቻላቸው የፈሩ አይኖቻቸው አስተያየት ልብ የሚያደማ ነበር።
“ለምንድነው ሁልጊዜ እዚህ ፎቅ ላይ የምንሆነው?”
“ምድር ቤቱ ጠፍቷል?"
“ፀሀዩዋ ወደተደበቀችበት ሄዶ ነው?"
“እናታችን ከአሁን ወዲያ አትወደንም?”
“ግድግዳዎቹ ለምንድነው የፈዘዙት?”

👍28🥰1
“ፈዘዋል እንዴ?” በምላሹ ጠየቅኩ
“ክሪስም የፈዘዘ ይመስላል”
ክሪስ ደክሞት ነው::”
ክሪስ ደክሞሀል?”
“ሁላችሁም ጥያቄዎች መጠየቅ አቁማችሁ ትንሽ እንድትተኙ እፈልጋለሁ! ካቲም ደክሟታል እኛም መተኛት እንፈልጋለን” አለ ክሪስ፡
ከዚያ ኮሪን ብድግ አደረገና ወደሚወወዘው ወንበር ወሰደው፡ ኬሪና እኔም ተhትለነው ወንበሩ ላይ ሲቀመጥ እኛም ጭኑ ላይ ተቀመጥን፡፡ ከሌሊቱ ዘጠኝ
ሰዓት ነው፡ ወደፊትና ወደ ኋላ እየተወዛወዝን ታሪክ እናወራላቸው ጀመር።በሌሎቹም ምሽቶች እስከ ሌለቱ አስር ሰዓት ድረስ ተረት እያነበብንላቸው ነበር። እናታቸውን ፈልገው ሲያለቅሱ ክሪስና እኔ እንደ እናትና አባት ሆነን
በቀስታ እሹሩሩ እንላቸዋለን፡፡ ወለሉ ድምፅ እስኪያሰማ ድረስ ወንበሩ ላይ አድርገን እናወዛውዛቸዋለን፡ በእርግጠኝነት ምድር ቤት ያለ የሆነ ሰው
ሊሰማን ይችላል፡
ወዲያው ከኮረብታው በኩል ንፋስ ሲነፍስ ሰማን፡፡ ነፋሱ ሀይለኛ ከመሆኑ የተነሳ በሁሉም መንገዶች ደህንነታችን የተጠበቀ እንዳልሆነ እንድናውቅ
እያደረግን ይመስላል
ከመፍራታችን የተነሳ ጮክ ብለን ማንበብና ብዙ መዘመር ቀጠልን፡፡ እኔና ክሪስ ድምፃችን ከመዘጋቱና ከድካም የተነሳ ራሳችንን በግማሽ ታመምን። ሁልጊዜ ማታ በጉልበቶቻችን ተንበርክከን እግዚአብሔር መንትዮቻችንን እንደገና ደህና እንዲያደርጋቸው በመጠየቅ እንፀልያለን፡፡ “እባክህ እግዚአብሔር በፊት እንደነበሩት አድርገህ መልሰህ ስጠን” እንለዋለን፡፡
ከዚያ ሳሉ የቀነሰበት፣ የአይኖቻቸው ሽፋሎች በእንቅልፍ የከበዱበትና በመጨረሻ በሰላማዊ እንቅልፍ የተዘጉበት ቀን መጣ፡ ወደ መንትዮቹ ተዘርግተው የነበሩት አጥንታማ የሞት እጆች በቀስታ ተሰበሰቡና መንትዮቹ
ወደ ጤናቸው ተመለሱ ሲሻላቸው ግን በፊት እንደነበሩት አይነት ጠንካራ አልሆኑም። ኮሪ በፊትም የሚያወራው ትንሽ ነበር አሁን ደግሞ የበለጠ ያነሰ ሆነ የራሷ የማያቋርጥ ጩኸት የሚያስደስታት ኬሪ አሁን እንደ ኮሪ ዝምተኛ ሆነች፡ ለረጅም
ጊዜ ፀጥታ እንዲኖር የተመኘሁ ቢሆንም አሁን ግን ድምፃቸው ናፈቀኝ፡፡
ምላሷን ሳየው ነጭ የሆነ ይመስላል እየፈራሁ ትራሱ ላይ አጠገብ ለአጠገብ ጋደም ያሉት ሁለቱ ትንንሽ ፊቶች ላይ አተኮርኩ። ለምንድነው እንዲያድጉና ትክክለኛ ዕድሜያቸው ላይ እንዲሆኑ የምፈልገው? ይህ ለረጅም ቀናት የቆየ በሽታ ትልልቅ ሰማያዊ አይኖቻቸው ስር ጥቋቁር ክብ በማድረግ ጤናማ ቀለማቸውን ሰረቀ ትኩሳቱና ማሳሉ ቅፅበታዊ የእድሜ ለውጥ አምጥቶ
ፀሀዩዋ ብትወጣ ባትወጣ ግድ የሌላቸው የደከሙ የአዛውንቶች አይነት እይታ ሰጣቸው አስፈሩኝ፡ አሳዛኝ ፊታቸው ወደ ሞት ህልም ወሰደኝ.....

👍22❤17
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ሕፃኗ በሕይወት መኖሯን ቀጥላለች " እንግዲህም ቢሆን የሚያሠጋት ነገር የሚኖር አይመስለኝም " የሚቀጥለው ሐሳብ ደሞ ሞግዚት መፈለግ ነው ሳቤላ አልጠነከረችም ትኩሳትና ድካም እየተጋገዙ ያጠቋታል " አንድ ቀን ለባብሳ ከምቹ ወንበር ላይ እንደ ተቀመጠች ሚስ ካርላይል ገባ።
«ባካባቢው ካሉት የቤት ሠራተኞች ሁሉ ለሞግዚትነት ትበቃለች የምትባል ታስቢያለሽ ?» አለቻት
« ኧረ እኔ እገሊት ለማለት አልችልም »
« እንዴ ዊልሰን አለች ሚስዝ ሔር ዘንድ የነበረች ከነሱ ጋር ሦስት ዓመት ካምስት ወር ተቀምጣለች አሁን ከባርባራ ጋር ስለ ተጣላች ነው የምትወጣው ትምጣና ታያት ? »
« የምትሆን ትመስላለች ? ጥሩ ሠራተኛ ናት ? »
« በሠራተኛነቷ እንኳን አትከፋም " ሥራዋን አክባሪ ቁም ነገረኛ ናት "
ነገር ግን ከዚሀ እስከ ሊምበራ ' የሚደርስ ምላስ አላት»
« ምላሷ ሕፃኗን አይጐዳትም ግን በደንገጡርነት ስለኖረች የልጅ አያያዝ ልምድ ያጥራት እንዶሆነ ነው እንጂ " »
« ልምዱስ አላት ከሚስዝ ሔር ቤት ሳትገባ ስኳየር ስፒነር ቤት ዋና ሞግዚት ሆና አምስት ዓመት ተቀምጣ ነበር " »
« እንግዲያው ትምጣና ልያት »
« በይ እልክልሻለው ግን ካነጋገርሻት በኋላ ለመልሱ ቀጠሮ ስጫት።
እኔ ከሚስዝ ሔር ዘንድ ሔጀ ስለሷ አጥንቸ ከመጣሁ በኋላ መልሱን ትነግሪያታለሽ”»
አባባሏ ትክክል ነበር ። ሳቤላም ተስማማችና ሠራተኛይቱ ስትመጣ ተነገረላት " የደስ ደስ ያላት ዐይነ ጥቋቁር ረጅም ሴት ገባች ሳቤላ ከሚስዝ ሔር ቤት
ለምን እንደ ወጣች ጠየቀቻት "
« የባርባራን ጠባይ አልችለው ብዬ ነው የወጣሁት ... እመቤቴ " በተለይማ ከዓመት ወዲህ ያመጣችው ዐመል አንዱም ነገር አያስደስታትም " ከዚህ በላይም
ዕብሪቷ ልክ እንዳባቷ ነው " ብዙ ጊዜ ለመውጣት እያሰብኩ መልሸ ስተወው ኑሬ ትናንት ደግሞ ተጣላን " ዛሬ ጠዋት ጨርሸ ወጣሁ " ስለዚህ እርስዎ ሊቀጥሩኝ ከፈቀዱ በደስታ እቀበላለሁ » አለች ዊልሰን "
« ግን እንደ ተረዳሁት አንቺ ከሚስዝ ሔር ቤት የገረዶች አለቃ ነበርሽ እኛ ዘንድ ደሞ አለቃይቱ ጆይስ ናት ምናልባት እኔ ወጣ ብል ወይም ብታመም አዛዧ እሷ ስለሆነች አንቺን የከፋሽ እንደሆነስ ? »
«እኔ ለዚህ ግድ የለኝም ጆይስን ሁላችንም እንወዳታለን ሳቤላ ጥቂት ከጠያየቀቻት በኋላ ለመልሱ ወደ ማታ እንድትመጣ ነግራ ሰደደቻት ኮርነሊያ ወደ ዐጸዱ ሔዳ ስለ ዊልሰን ጠባይ ሚስዝ ሔርን አንድ ባንድ ጠየቀቻት ሚስዝ ሔርም
ዊልሰን በባርባራ አመካኝታ ቸኰላ ከመልቀቋ በቀር ይህ ነው የምትለው ጥፋት እንደሌላት በግልጽ ነግረቻት " ስለዚህ ዊልሰን ተቀጠረች " አዲሱን ሥራዋን በበነጋው ጧት መጥታ እንድትጀምር ተደረገ።
ሳቤላ ከመኝታ ቤቷ ውስጥ የእንቅልፍ ሰመመን ተጫጭኗት ሶፋ ላይ ተጋድማለች።
አዲሲቱ ሞግዚት ጧቱን መጥታ ሥራ ጀመረች በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ ሳቤላ ከመኝታ ቤቷ ውስጥ የእንቅልፍ ሰመመን ተጫጭኗት ሶፋ ላይ ተጋድማለች
የዚህ ዐይነቱ መስለምለም እንዴት እንደሚያደርግ በትክክል የሚያውቁት አንደ ሳቤላ በሰውነት ድካምና ትኩሳት የሚሠቃዩት ብቻ ናቸው ። ከሷ መኝታ ቤት ቀጥሎ ካለው ክፍል ዊልሰን የተኛ ሕፃን ከጉልበቷ ላይ ይዛ ጆይስ ልብስ ስትሰፋ ተቀምጠው ያወጋሉ " በሩ ጎርበብ ብሏል " ሳቤላ በእንቅልፍና በንቃት መካከል ሆኖ ስትስለመለም ስሟ ሲጠራ ድንገት ትሰማና ትነቃለች።
« እንዴት ተደይነዋል ! በጣም የታመሙ ይመስላሉ » አለች ዊልሰን "
« ማን ? » አለቻት ጆይስ "
« እሜቴ » እስከ መቼም በጐ የሚሆኑ አይመስሉም»
« አሁን እኮ በጣም እየተሻላቸው ነው " ባለፈው ሳምንት አይተሻቸው ቢሆን ኖሮና ካሁኑ ሁኔታቸው ጋር ብታነጻጽሪው ገመምተኛ ይመስላሉ አትይም ነበር"
« አሁን አይበለውና እሳቸው አንድ ነገር ቢሆኑ የአንድ ሰው ተስፋ አያንሰራራም ብለሽ ነው ? »
« ወጊጅ ወድያ !ሌላ ወሬ አምጨ»
« አንቺ ያልሺውን ብትይ አይቀርም» ቀጠለች ዊልሰን ።
« ለሁለተኛ ጊዜ እንዲያመልጧት አትፈልግም " በአንድ ጊዜ ነው የምትነጥቃቸው እሷ እንደሆነች ዛሬም ልክ እንደ ድሮዋ ስቅቅ ብላ ነው የምትወዳቸው»
« ይህ ሁሉ የዌስት ሊን ሰው ሥራ ሲፈታ የሚያናፍሰው ወሬ ነው ሚስተር ካርላይል እንደሆኑ ስለሷ ቅንጣት ደንታ የላቸውም»
« ጆይስ አንቺ አታውቂም እኔ ያየሁት ነገር አለኝ " ሲስሟት በዐይኔ አይቻለሁ»
« መንጋ ወሬኛ ! » አለች ጆይስ " « ይኸ እሳቸው እሷን ለማግባት መፈለ?ቸውን አያስረዳም»
« እኔ ያስረዳል አልወጣኝም " ብቻ አሁን የምታስረውን ባለሙዳይ ያንገት ሐብል የሰጧት እሳቸው ናቸው»
« ማናት የምታስረው ? እኔ ስለዚህ ነገር መስማት አልፈልግልም » አለች
« ሚስ ባርባራ እንጂ ደግሞ ማን ! ካንገቷ አውልቃው አታውቅም እኔስ ስትተኛም የምታስቀምጠው አይመስለኝም »
« እሷ አትረባም» አለች ጆይስ "
« እመቤት ሳቤላን ለማግባት ከዌስት ሊን ማለዳ ሊነሡ ማታውን ሚስ ባርባራ
ከሚስ ካርላይል ቤት አምሽታ ስለነበር ሚስተር ካርይል ወደ ቤቷ ይዘዋት መጡ"ገና በመንገድ እያሉ እንዴት እንደሆነ አላውቅም ጃንጥላዋን ሰበሩት ከዋናው
በር ሲዶርሱ የፍቅር ትርዒት ታየ»
« አንቺ ሦስተኛ ሆነሽ አብረሽ ከቦታው ነበሮሽ ? »
« አዎን ሳላስበው እዚያው ተገኘሁ " ያ ገብጋባ አሮጌ ዳኛ አንድም ሰው አስከትለን እንድንገባ አይፈቅድም ካበባ ጐመን የረዘመ አትክልት በሌለው በገላጣው
የማድ ቤት አታክልት ቦታ ውስጥ ማንንም በምስጢር ማነጋገር አይቻልም " ስለዚህ ጠያቂ ወዳጅ ሲመጣ የነበረው ዕድል ወደ ዐጸዱ ገባ ብሎ ለግማሽ ሰዓት ተጫውቶ መመለስ ነው " ያን ዕለት ማታ የምጠብቀው ሰው ስለነበረኝ ወደ ዐጸዱ ወጣሁ።
ወዲያው ሚስተር ካርላይል ሚስ ባርባራ መጡ " እንዲገቡ ብጠይቃቸውም አልፈለጉም ስለዚህ ሁለቱም እዛው ቆሙ ። ስለ መታሰቢያ መያዣው ያንገት
ሙዳይ ጸጉሩን ለማስታወሻ ስለ መስጠታቸው አንዳንድ ነገር ይነጋገሩ ነበር እንዳይሰሙኝ ስለፈራሁ hቆምኩበት አልተነቃነቅሁም የጦፈ የፍቅር ጭውውት ቀጠለ ጠቅላላ አነጋሯ ሁሉ ልክ እንደ ሚስት ነበር ።
« እንቺ ወሬኛ ሊያገቡ ከመሔዳቸው በፊት ማታውን አላልሺም ? »
« እና ቢሆንስ ? እሷ መቸም ዕብድ ሆነች ተሰናብተዋት ከሔዱ በኋላ እጆቿን ወደ ሰማይ ዘረጋች አግብተው እስኪያዩዋት ድረስ ምን ያህል እንደምትወዳቸው ሊገባቸው እንደማይችል ብቻዋን ታወራ ጀመር » አየሽ ጆይስ « በሁለቱ መኻል ብዙ የፍቅር ገድል መፈጸሙን አትጠራጠሪ በመጨረሻ ሚስተር ካርላይል እሜቴን ሲያገኙ ጊዜ በቁንጅናቸውና በትውልዳቸው ማረኳቸው የፊቱ ፍቅር ተረሳ ወንዶች ሲባሉ በተለይ እንደ ሚስተር ካርላይል በመልካቸው የሚመኩ ከሆነ ወረተኝነት ባሕሪያቸው ነው ። »
« ሚስተር ካርይል ወረተኛ አይደሉም ... አንቺ ! »
« አሁንም ሌላ ልንገርሽ » አለችና ጆይስ ማብራራቷን በመቀጠል ሚስተር ካርላይል ማግባቱን ለእኅቱ በጻፌላት ጊዜ ' ኮርነሊያ ለባርባራ ስትነግራት ከመኝታ
ቤቷ ገብታ ያለቀሰችውን ሁሎ እያሳመረችና እየኳኳለች ነገረቻት
« በምንም ለማይወዳት ሰው ይሀን ያህል መጨነቋ ምን ያህል ደንቆሮ ብትሆን ነው ? » አለች ጆይስ

👍21👎1🥰1
« ነገርኩሽ ኮ ... ጆይስ " የማይወዳት መሆናቸውን ማወቅ አትችይም "ዝም ብለሽ እንዶ ዳኛው ሔር ድርቅ አትበይ " በሚስተር ካርላይል ጋብቻ
መልካም ምኞታቸውን ለመግለጽ አባቷ እናቷና እሷ ወደ ኢስት ሊን መጥተው ነበር በትክክል ካስታወስሽ ወላጆቿ ቀድመው ሲሔዱ እሷ ኢስት ሊን እየተጫወተች ለማምሸት ወደኋላ ቀረች "
« አስታውሳለሁ »
« ጃ ስፐር ወጥቶ ስለነበር እኔ እንድቀበላት ተላክሁ ከአጥሩ አጠገብ ስደርስ ምን አየሁ መሰለሽ ? »
ጆይስ ቀና ብላ አየቻት « እንጃ ምናልባት እባብ አይተሽ እንደሆነ ? »
« ሚስ ባርባራንና ሚስተር ካርላይልን አገኘኋቸው " እኔ ከመድረሴ በፊት ምን ያደርጉ እንደነበር እነሱ ይወቁ " እሷ ከአጥሩ ተደግፋ እየተንሰቀሰቀች ታለቅስ ነበር " ሁኔታው ከቀድሞ የተነገራት ነገር እንደ ነበር ለዚያ የወቀሳ መልስ የምትመልስላቸው ይመስል ነበር » እሳቸውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወንድምና እህት ብቻ መሆን እንደሚችሉ ሲነግሯት ሰማኋቸው " እኔም ያዩኝ እንደሆነ ብዬ ፈራሁና ተናገርኩ " ሚስ ባርባራ እንዲመለሱ ነግሬአቸው ነበር " እሳቸው ግን ክንዳቸውን ዘርግተው ክንዷን አቅፈው በጓሮ በኩል እስከ በሩ አብረዋት ወጡ " እኔ በሩን ለመክፈት አልፌያቸው ስሔድ ሁለት እጆቿን ይዘው ራሳቸውን ወደሷ አጐንብሰው አየኋቸው " በመኻላቸው ያለውን ነገር አናውቅም»
« እሷ ግን አሁንም ትወዳቸው እንደሆነ ሞኝ ናት » አለች ጆይስ ቆጣ ብላ "
« በርግጥ ሞኝነት ነው ! ግን ትወዳቸዋለች ሁልጊዜ እሳቸው በነሱ በር አጠገብ በሚያልፉበት ሰዓት እየጠበቀች እንዳያዩዋት ትደበቅና ታያቸዋለች ጆይስ በዚህ ባለፈው ዓመት ባርባራ ጠባይዋ ከዱሮው ተለወጠ " ቁጣ ቁጣ ይላታል ። የዚህ ሁሉ ምክንያቱ ግን በወይዘሮ ሳቤላ ስለምትቀና ብቻ ነው አሁንም ሚስተር ካርላይል እሜቴን ቸለል ቢሏቸው. »
« ዊልሰን » አለቻት ጆይስ ነገሯን አቋርጣ « እባክሽን የምትይውን ዕወቂ። »
« እንዴ አሁን እኔ ምን አልኩ ? ሐቁን ነው ኮ የተናገርኩ " ወንዶች በተለይም ባሎች ከፍቅረኞች የበለጡ ወረተኞች ናቸው " አሁን እሜቴ አንድ ነገር ቢያገኛቸው ሚስ ባርባራ በእግራቸው ጥልቅ ማለቷ የማይቀር ነው»
« እሳቸው ምንም ነገር አይደርስባቸውም» አለቻት ጆይስ
« ለዚች በጭኔ ለታቀፍኳት ምንም ለማታውቅ ሕፃን ሲል ምን ጊዜም እንዳፍሽ ያድርግላቸው " ከክፉ ይሰውራቸው » አለችና ዊልሰን ነገሯን በመቀጠል
« የመጀመሪያይቱ ሚስት ከተጠላች ልጆቿም እንደማይወደዱ የተረጋገጠ ነው
ስለዚህ ሚስ ባርባራ ከገባች ጥሩ የእንጀራ እናት አትሆንም " እንዲያውም ሚስተር ካርላይል እንዲጠሏቸው ታደርጋለች »
« ስሚ ዊልሰን ... ኢስት ሊን ሁነሽ የዚህ ዐይነት ወሬሺን የማታቆሚ ከሆነ ለዚህ ቤት እንደማትስማሚ ለእሜቴ እነግራለሁ»
« አንቺ ደግሞ ጥብቅነቱን ታበዥዋለሽ . . . ጆይስ » አለች ዊልሰን እየሣቀች"
« እኔ ግን ያለውን ነር ተናግሬአለሁ እንግዲህ በቃኝ " ደሞም ይኸንኑ ጉዳይ ለቤትኣሽከሩ ሁሉ የምለፈልፈው አይምሰልሽ »
ሳቤላ የዊልስንን ንግግር ቃል በቃል ልቅም አድርጋ ሰማችው " ጥሩ ጤነኛ ብትሆን ኖሮ ከቁም ነገር አትጽፈውም ነበር " አሁን ግን ሰውነቷ ደከመ የማያቋርጥ ትኩሳት እንደ እሳት ይፈጃታል ከዚህ የተነሣ ዐልፎ ዐልፎ ልቧን እየሳተች ትቃዣለች ይህ አሳዛኝ ሁኔታዋ የሚስተር ካርላይልን ይዞታ እንድትጠራጠር
የተወራውን ነገር አንድታተነትን አስገደዳት " ሚስተር ካርይል ያገባት እውነተኛ ፍቅር ኖሮት ሳይሆን የዝና ፍላጐቱን ለማርካት እንደሆነ አድርጋ አሰበችው
ልቡ ከባርባራ እንጂ ከሷ ጋር እንደሆነ ለማመን አልቻለችም "
በገመምተኛነቷ ላይ ይህን ብስጭት አከለችበትና ይበልጡኑ ደካክማ ተኛች "አእምሮዋን በቅናት በትኰሳት በፍቅር ነገር በጠበጠችው " ሚስተር ካርላይል ሲገባ የራት ሰዓት ተቃርቦ ነበር " ጉንጮቿ ዐመድ ለብሰው በትኩሳት ሲቃጠሉ ዐይኖቿ ተበርዘው ቀልተው ሲያያት ደነገጠ "
« ሳቤላ . . .ዛሬ ደግሞ ብሶብሻል ! » አለ ወደሷ እየተንደረዶረ ሔዶና " ከተቀመጠችበት ሶፋ እንደ መነሣት ብላ እየተርበተበተች ግጥም አድርጋ ያዘችው "
« አርኪባልድ !...አርኪባልድ ! . . . እንዳታግባት - ካገባሃት ከመቃብር
ሁኘም ዕረፍት አላገኝም »
ሚስተር ካርላይል ባነጋገሯ ተገረመና ግራ ተጋባ " ነገሩ ከሰውነት መድከም የመጣና ቶሎ ብሎ እልፍ የሚል ቅዠት መስሎት ሊያረጋጋት ሞከረ " ነገር ግን
ሁኔታዋ በቀላሉ የሚመለስ አልመሰለም " ዕንባዋን እንደጐርፍ እያወረደች ነገሯን ቀጠለች "
“ልጄን ታንገላታብኛለች " ያንተን ፍቅር ለራሷ ወስዳ ለሕፃኗ እንዳታስብ እኔንም እንዳታስታውስ ታደርግሃለች እንደማታገባት ቃል ግባልኝ "
“ አግባብ ላለው ለማንኛውም ነገር ቃል እገባለሁ ” አላት በአነጋገሯ እየተገረመ ።
አሁን የምትዪው ነገር ግን አልገባኝም " እኔ ማንንም የማግባበት ምክንያት የለኝም : አግብቻለሁ ! ሚስቴ አንቺ ነሽ ።
“ የሞትኩ እንዴሆነሳ ? እሞት ይሆናል " ብዙዎቹ ትሞታለች አትተርፍም ይሉኛል " እሷ ያንተ ሚስት መሆኗን ሳስበው ሊገድለኝ የሚችል ሕመም ይሰማኛል "
እሷ በኔ እግር እንዳትግባ "
“የምትያት ሴትዮ ማንም ትሁን ማን ምንም ቢሆን ባንቺ እግር አትገባም ምን ስታልሚ ነበር ? ከጭንቅላትሽ ገብታ እንደዚህ የበጠበጠችሽ ማናት ? ”
“ አርኪባልድ እንዴት ትጠይቀኛለህ ? እኔን ከማግባትህ በፊት የምትወዳት አልነበረችህም ? ምናልባትም እስካሁን ትወዳት ይሆናል ”
“ ስለማን ነው የምትናሪው ... ሳቤላ? አላት ፊቱን ኮስተር አድርጎ
“ ስለ ባርባራ ሔር ”
ሚስተር ካርላይል ግንባሩን ቋጠረ ተበሳጨ ብሽቅ አለ ደግፋት ተቀምጦበት ከነበረው ሶፋ ብድግ አለና ፈንጠር ብሎ ከፊት ለፊቷ ቆመ » ሳቤላ .. በኔና በባርባራ ሔር እንደዚህ ያለ ሐሳብ መኖሩን ኧንዴት አወቅሺው ሊገባኝ አልቻለም እኔ ባርባራ ሔርን በፊትም ሆነ አሁን ለፍቅር ለጋብቻ አስቢያት አላውቅም " ይህሐሳብ እንዴት አድርጎ ከጭንቅላትሽ እንደገባ እንድትነግሪኝ እፈልጋለሁ "
"እሷ ግን ትወድ ነበር "
በዚህ ጊዜ ትንሽ ወላወለ " እንደምትወደው ያውቃል " ይኸንንም እንዴት ሊያውቀው እንደቻለ ያስታውሳል " ነገር ግን ይኸን ሁኔታ ለሚስቱም ሊያምንላት አልቻለም “ እኔ የምትወደኝ መሆኗን አላውቅም " ያንቺ በባርባራ መቅናት ግን በእኅቴ በኮርነሊያ ከመቅናት ለይቸ አላየውም "
ሳቤላ በረጅሙ ተነፈሰች የእፎይታ ትንፋሽ " ትንፋሿም ተስተካከለ ተረጋጋ በአስተማማኝ ሁኔታ አረጋገጠች " ሚስተር ካርላይል ወደሷ ጐንበስ ብሎ በቅሬታና በአዘኔታ አነጋገር “ እኔ ያለፈው ዓመት በከንቱ እንጠጠፋ አድርጌ አላሰብኩትም ነበር ስለ እውነተኛ የልብ ፍቅር አንድ ወንድ ሊሰጠው ከሚገባው ማረጋገጫ ምን አጐደልኩብሽ ?” አላት " ቀና ብላ ስታየው እንባዋ ቅርር አለ " የጸጸት ለቅሶ ተናነቃት " እጁን በሁለት እጆቿ መኻል ያዘችና'' አትቆጣኝ አርኪባልድ እኔ ላንተ ብዙ ባልሳሳና ባልጨነቅ ኖሮ ይህ ሁሉ መጠራጠርና የመንፈስ መረበሽ አይመጣብኝም ነበር "

ሣቅ አለና አሁንም ወደሷ ዝቅ ብሎ''ይህን ነገር ምን ሰይጣን ከጭንቅላትሽ ከተተው ? አላት ።
የሰማችውን ሁሉ ዝክዝክ አድርጋ ልትነግረው አሰበች ! ከዓመት በፊት ሱዛንና ጆይስ የተናገሩዋቸው ጥቂት ቃላትና አሁን የሰማችውን የጆይስን ንግግር ሁሉ ልትገልጽለት ከቆረጠች በኋላ የገረዶች ወሬ ማዳመጡ ውርደት ነው ከቁም ነገር መቁጠሩም የዋህነት ነው” ብላ እንዶገና አሰበችና ተወችው "
አንቺ በኔ የተዛባ አስተሳሰብ እንዲኖርሽ የሚያደርግ ሰው አለ ? አላት
አርኪባልድ .... ማንም የለም " እንዲህ ያለውን ወሬ ማን ደፍሮ ይነግረኛል
እንግዲያ ተኝተሽ ያየሺው ሕልም ስትነቂም አልለቅሽ አለ ?
በርግጥ ከቀትር በኋላ ስተኛ በተለይ በሚያተኩሰኝ ጊዜ ብዙ እንግዳ ሕልሞችን አያለሁ » አንዳንድ ጊዜ ቅዠቱ ልቤን ያጠፋወና እውነቱንና ሕልሙን መለየት ይሳነኛል "
መልሱ የማምለጫ መሆኑ ቢገባውም አጥብቆ አልጠየቃትም "
በይ እንግዲህ ቢቻልሽ እንደዚህ ያለ ሕልም ይቅርብሽ " ላንቺ ደግ አይደለም " ለኔም ያን ያህል ስወድሽና ሳስብልሽ አለስሜ ስም የሚሰጥ ነው እኔ ከአንቺ ጋር በፍቅር በሕግ ማሰሪያዎች ተሳስሬያለሁ " ስለዚህ ልብ በይ ሳቤላ ባርባራ ሔር ይህን አልፋ በሁለታችን መኻል ለመግባት ኃይል የላትም በዚህ ዓለም ቅናትን የሚያህል አሳሳች የማይታመንና ኃይለኛ ነገር አልነበረም አይኖርምም ሚስተር ካርላይል ነገሩ በቅዠት የመጣ እንደ መሰለው ሁሉ አሁንም ይህ ትዝታ እንዶ ቅዠቱ የሚጠፋና የሚረሳ መሰለው ።
ነገር ግን አይደለም ። የባሏን ቃል ወዲያውኑ አመነችበት » ጥርጣሬ ከልቧ በማስገባቷም አፈረችበት " ከዚያ በኋም ይህ ደስ የማይለው ሥጋት እንደገና እንዳያንሰራራባትና እንዳያብታት መጨነቅ ጀመረች በአጉል አጋጣሚ የሰማችው
የዊልሰን ወሬ የሚስተር ካርላይልን ማስተባበያ አሸንፎ በማለፍ ከዐውደ ሕሊናዋ
ገብቶ ይወቃት ጀመረ "።
ሼክስፒር ቅናትን ቢጫና አረንጓዴ ይለዋል እኔ ግን ጥቁርና ነጭ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ይመስለኛል ምክንያቱም ነጩን ጥቁር ጥቁሩን ነጭ አድርጎ ያሳያልና " ሊታመኑ የማይችሉትን ግምቶች የእውነተኝነትን መልክ ያለብሳቸዋል " ፍጹም ሊሆኑ የማይችሉ ነገሮችን ተጨባጭ እውነታዎች አስመስሎ ያቀርባቸዋል " ሳቤላ ለባሏ ሌላ ምላሽ አልሳጠችም የቅናቷን ነገር ስታስበው ባሏን ከምን ጊዜም በበለጠ እንድትቀርበውና ለፍቅሩም እንድትሳሳ አድርጓታል ባርባራ ሔር ግን ከልቧ ልትወጣለት አልቻለችም....

👍17❤7
ሁሌም በየዘመን ፣ ጎልያድ ነን ባዮች በጉልበት ሲነሱ ፣ አይጠፉም ልባሞች
እግዜርን ተማምነው ፣ ጠጠር የሚያነሱ።
እግዜርን ተማምነው ፣ ጠጠር የሚያነሱ።
❤64👍54🥰7👏3