#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሦስት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
....“አንድ ጊዜ ከባልቻ ጋር እዚህ መጥታችሁ ነበር አይደል?” አለችኝ እንደ ዋዛ፣ ወደ ታላቁ ቤተ መንግሥት በቅንድቧ እየጠቆመችኝ፡
“አዎ” አልኋት፣ እኔም እንደ ዋዛ፡ “እ?” አልኋት ወዲያዉ፣ ዉሃ ሆኜ ምን ምን? ያለችዉን ነገር እኮ ገና አሁን ነዉ ልብ ያደረግሁበት::
ከማን ጋር ምንድነዉ ያለችኝ? ባልቻ? እርፍ! እንዴት እንዴት ነዉ ነገሩ? በድንጋጤ ተዝለፍልፌ አለመዉደቄ፣ ለራሴ ደነቀኝ፡ መሬቱን ይዤ አረፍ ማለትም አሰብሁ፡ ቢሆንም ግን ቸኩሎ መደናገጥን የሲራክ ፯ ማንነቴ
ስለማይፈቅድልኝ ማስጨረስ አለብኝ፡ ጥርሴን ነክሼ እንደ ምንም ተበራታሁ።
“በዚህ በኩል” አለችኝ፣ ወደ ታዕካ ነገሥት ቤተ መዘክር እያስገባችኝ
ወደ ቤተ መዘክሩ ስመጣ የመጀመሪያዬ ስላልሆነ ብርቅ አልሆነብኝም እንጂ፣ እንደዚህ ማንኛዉንም ሰዉ መንፈሳዊ የሚያደርግ ወደረኛ ቦታ
አለ ቢሉኝ አላምንም ሲጀመር በከተማ ዉስጥ ካሉ ገዳማት እንደዚህ የጸጥታ እና የአርምሞ ገዳም አላዉቅም። በበርሐ ካሉትም የሚስተካከል
ትክክለኛ የገዳም ይዞታ ያለዉ ግቢ ነዉ፡ ዕድሜ በጠገቡ እና ራሳቸዉ ታሪክ በሠሩ ጽዶች የተሞላ ስለሆነ፣ እዚህ ግቢ የገባ ሰዉ ዉጣ ዉጣ አይለዉም እንኳንስ ለአማኝ እና ለተማጻኝ ይቅርና፣ ለማንኛዉም ሰዉ
መረጋጋትን የሚሰጥ ገራሚ ሥፍራ ነዉ።
ቤተ መዘክሩ ዐሥር ብር የከፈለ ማንኛዉም ታሪክ ወዳጅ የሚጎበኘዉ ሕዝባዊ ቤት ቢሆንም፣ የሚገኘዉ ግን በዋናዉ የገዳሙ ሕንጻ ምድር ቤት ነዉ፡ ስለዚህ ወደ ቤተ መዘክሩ ለመግባት የግድ ጫማ አዉል
በቅኔ ማኅሌቱ በኩል ማለፍ ይጠይቃል። በዋናነት የዳግማዊ ምኒልክ፣ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል፣ የእቴጌ ዘዉዲቱ፣ የአቡነ ማቴዎስ
ግብጻዊ የልዕልት ፀሐይ ኃይለሥላሴ ዐጽሞች በየራሳቸዉ ወርቃማ ሳጥን ዉስጥ ተከብረዉ የተቀመጡበት ሲሆን፣ ዓይነተ ብዙ የካህናት እና የነገሥታት ቅርሳ ቅርሶችም አሉበት ከነዚህም መካከል ሮማዊዉ ሊቀ ጳጳስ ለአፄ ምኒልክ የላኩላቸዉ የሚካኤል አንጀሎን ትክክለኛ የእጅ ሥዕል ጨምሮ ብዙ የሚነገርላቸዉ ከሩስያ ከግሪክ ከጣልያን እና ከተለያዩ ሀገራት መንግሥታትን የተበረከቱ ቅርሶች
ሞልተዉ ተትረፍርፈዉበታል። እንዲሁም ንግሥተ ነገሥታት ዘዉዲቱ ለጸሎት ይጠቀሙበት የነበረ ወንበር፣ የእጅ ጽሑፋቸዉ ያለበት ዉዳሴ ማርያም እና ሌሎች የብራና መጻሕፍት እና ለእሳቸዉ የተሰጡ ታሪዊ ስጦታዎች ጭምር አሉበት። ለአድዋ ዘመቻ ሲታወጅ የተጎሰመዉ ነጋሪት፣ አድዋ
ድረስ የዘመተችዋ ድል አድራጊዋ የጃንሆይ መቀመጫ ወንበር ሁሉ
የሚገኙት በሌላ አይደለም፡ እዚሁ ታዕካ ነገሥት ቤተ መዘክር ዉስጥ
ነዉ።
ያም ሆኖ ግን ቤተ መዘክሩን የሚጎበኘዉ ሰዉ በታሪኩ ልክ ብዙ ነዉ ማለት አይቻልም እስከዚህም ነዉ ያን ያህል ንጉሥ ንጉሥም፣ ካህን ካህንም የሚሸት እና ቢናገሩለት የማያልቅ የቅርስ ክምችት እንዳልሞላበት
ሁሉ፣ ጎብኚ ግን ከስንት አንድ ነዉ ብቅ የሚልበት። ያዉም የዉጪ
ሀገር ሰዉ፡ ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ ከነጭራሹ ማንንም አላየሁበትም። አስጎብኚዎቹም እንኳን በአካባቢዉ የሉም
“እና፣ ወደ ቤተ መንግሥቱ ያመጣችሁን ጉዳይ እንደሚሆን እንደሚሆን ከዉናችሁት ልትወጡ ስትሉ ተይዛችሁ ነበር አሉ?” አለችኝ እመዋ፣ በዚያ የዉድ ዉድ እቃዎች ክምር መካከል ለብቻችን ስንዋኝ።
ዝም ብዬ ባዳምጣት ይሻለኛል ምን ልል እችላለሁ? ጭጭ እርጭ ብዬ አዳመጥኋት። ጭራሽ ተዪዛችሁ ነዉ ያለችዉ? በስመ አብ!
“ከዚያ ባልቻ አቺን ደብቆ ራሱን አጋለጠ። አንቺ ይኸኔ የእሱ መጨረሻ እያሳሰበሽ እንደ ምንም ከቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ስታመልጪ ቀድሞሽ ውጪ አገኘሽዉ በምን ተአምር ከእነሱ እጅ እንዳመለጠ ግን እስከ
አሁንም ድረስ ባሰብሽዉ ቁጥር ይገርምሻል አይደለም? በእርግጥም ግን እኮ ይገርማል። የመንግሥት ደኅነቶች ለመያዝ ዘገምተኞች ናቸዉ እንጂ ከያዙ እኮ አይለቁም ይባላል”
እመዋን አላዉቃትም ለካ በእርግጥ ግን ይቺ ሰዉ እመዋ ራሷ ናት ከንግግሩ አነጋገሯ ከአነጋገሯ ሁኔታዋ! እሷ ማለት ለኔ የስልሳ አራት ዓመት አሮጊት፣ ከጾምና ከምሕላ ሌላ የምታዉቀዉ የሌላት ምስኪን
ሃይማኖተኛ ናት፡ እንዲያዉ አዳሯ በገዛ ቤቷ ከመሆኑ በቀር፣ ሙሉ
ሕይወቷ ከመናኝ አይተናነስም፡ በቤተ መንግሥት ዙሪያዉን ባሉ ገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት፣ ለትንሽ ለትልቁ የምትታዘዝ ገዳማዊት ብቻ ናት። በጭራሽ እናቴን አላዉቃትም በቃ።
“በዚህ በኩል” አለችኝ፣ ከሩስያዉ የመጨረሻ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ኒኮላስ ለኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ የተላh መሆኑን የሚያመላክት ጽሑፍ በግርጌ ወደ ሰፈረበት ጽዋዕ እየወሰደችኝ
ከዚህ ቀደም ቤተ መዘክሩን በጎበኘሁ ጊዜ አስጎብኚዉ ስለ ጽዋዉ ያብራራልኝን አልረሳሁትም ከጽዋዉም አልፎ ጽዋዉን ስለላከዉ የሩስያ ንጉሥ ጭምር ገልጾልኛል። ለሃያ ሦስት ዓመታት ገደማ በሩስያ መንገሡን፣ የሩስያ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ድረስ በቅዱስነቱ እንደምታወሳዉ፣ ዝነኛዉ የሀገሩ አብዮት ዘመኑን እንደ ቀጨበት
ያብራራልኝን ከነፊቱ ገጽ አስታዉሰዋለሁ። ስለ ንጉሡ ያልነገረኝ አልነበረም።
ይኼ ሩስያዊ ንጉሥ ለሐበሻዉ ንጉሥ የላከዉ ጽዋዕ አጠገብ ስትደርስ፣እመዋ ፈገግ ብላ አየችኝ። ደግሞ ምን ልትለኝ ይሆን?
“ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም”
ስትል በፊቴ አንጎራጎረች፣ የሩስያዉ ንጉሥ ለአፄ ምኒልክ የላከዉ ጽዋዕ አጠገብ ቆማ ፊቷ የፈገግታ ብርሃን እንደ ፈነጠቀበት
“ዳዊት እደግማለሁ ቆሜ ገረገራ
እመቤቴ ማር ያም ኢትዮጵያን አደራ
ነይ ነይ እምዬ ማርያም”
ከመሬት ተነስታ እንዳልዘመረችዉ ይገባኛል። ምንም እንኳን መዝሙሩ ነባር እና ሕዝባዊ መዝሙር ቢሆንም፣ የእሷን ምክንያት ግን አግኝቼዋለሁ በሲራክ ፯ ማዕከል ዉስጥ ሥራዎቻችንን ጨርሰን ትንሽ
ፋታ ያገኘን እንደሆነ፣ አባላቱ ሁሉ ከበዉ የሚያዘምሩኝ እኔም እንደ
ጸሎት የምቆጥረዉ መዝሙር ነዉ። ከዚህ በላይ፣ ራሷ አፍ አዉጥታ የሲራክ ፯ አባል ነኝ እስከምትለኝ ልጠብቅ ካላልሁ በቀር፣ እናቴ ግን እንደማስባት ዓይነት ሰዉ ብቻ አለመሆኗን በተግባር ጭምር
አሳይታኛለች፡
“ተከተዪኝ” አለችኝ ጽዋዉን ትኩር ብላ ስታይ ቆይታ፣ ዘወር ብሎ
ወዳለዉ ሥዕል ደግሞ እየተራመደች። ልክ ከፊት ለፊቱ ስትቆም፣ ነፋስ የነካዉ ያህል ሥዕሉ መወዛወዝ አመጣ፡ ዓይኔን ተክዬ የሚሆነዉን ሁሉ
ተጠባበቅሁ: አፍታ ያህል ሲወዛወዝ ከቆየ በኋላ፣ የድምፅ ፍጥነትን በሚስተካከል ፍጥነት ተገልብጦ የፊቱ ወደ ጀርባ፣ የጀርባዉ ወደ ፊት ተለወጠ። ሥዕሉ ግን አሁንም ያዉ የቅድሙ ዓይነት ነዉ።
የሆነዉ ሆኖ ሥዕሉ ሥዕል ብቻ፣ እመዋም እመዋ ብቻ እንዳልሆነች
ገብቶኛል።
“አሁን ባልቻ እንዴት እንዳመለጠ ሳይገባሽ አልቀረም” አለችኝ
በፈገግታ።
ወደ ቤተ መንግሥቱ ግቢ የሚዘልቅ የዋሻ መንገድ አለ ማለት ነዉ?አፌን ከፍቼ፣ ዓይኔን በልጥጬ እንዳፈጠጥሁባት ቀረሁ እየቆየ የባሰ እየደነቀኝ፣ ሁሉም ነገር ቅዠት እየመሰለኝ መጣ፡ ጭንቅላቴ በጥያቄ
መዐት ተጠቃ። ሚሊዮን ጥያቄ በዉስጤ እየተዥጎደጎደ፣ አንደኛዉ ከሌላኛዉ ተሽቀዳደመብኝ፡ የሲራክ ፯ አባል ነሽ? እሺ አባል ከሆንሽ ምን

👍21🥰3❤1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሦስት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
..ናንሲ ሌኔሃን የሰውነቷ ክብደት መጨመሩ ታወቃት፡፡ ያለችው
ሊቨርፑል ከተማ አዴልፊ ሆቴል ውስጥ ነው፡፡ ናንሲ አስጠሊታም ቆንጆም
አይደለችም፧ አፍንጫዋ ሰልካካና ጸጉሯ የተዘናፈለ በመሆኑ የደስ ደስ
አላት፡ ደህና ልብስ ስትለብስ ዓይን ትስባለች፡፡ ይሄ ደግሞ የሁልጊዜ
ገጽታዋ ነው፡፡ ኮቷ ስለጠበባት ቁልፎቹ ሲቆለፉ ቀፈት ቢጤ ይወጣባታል:
ይህ የሆነው ሰሞኑን ለአንድ ወር ያህል በፓሪስ ምግብ ቤቶች እየዞረች ምግብ መሰልቀጥ ስላበዛች ነው፡፡ አትላንቲክን በመርከብ ስታቋርጥ ግን ስባት
ያለበት ምግብ ላለመብላት ወስናለች፡፡ ኒውዮርክ ስትደርስ የቀድሞው
ሽንቅጥናዋ ይመለሳል።
ከዚህ በፊት ውፍረት ችግሯ አልነበረም፡፡ ጥሩ ምግብ ብትወድም ብዙ አታግበሰብስም፡፡ አሁን አሁን ውፍረት የእርጅና ምልክት ነው ብላ መፍራት
ጀምራለች፡
ዛሬ አርባኛ አመቷን ደፍናለች፡፡
ሁልጊዜም ሸንቃጣ ነበረች፡፡ ውድ ልብስ ገዝቶ ወይም አሰፍቶ መልበስ ጫማ መግዛት ትወዳለች፡፡ በፋሽን እቃዎች ንግድ ላይ በመሰማራቷ ጥሩ
ነገር መልበስ እንዳለባት ታውቃለች፡፡
ናንሊ የተወለደችው በ1899 ዓ.ም ሲሆን ይህ ወቅት አባቷ የጫማ ፋብሪካ ከፍተው ንግዱን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ ከእንግሊዝ አገር ጥራት ያላቸውን ጫማዎች አስመጥተው አስመስሎ በመስራት በርካሽ ዋጋ ይሸጣሉ፡፡ ሃያ ዘጠኝ ዶላር የሚያወጣውን የለንደን ጫማ አስር ዶላር
ከሚያወጣው የራሳቸው ጫማ ጋር ጎን ለጎን እያስቀመጡ ‹‹እነዚህ
ጫማዎች ልዩነታቸው ምንድን ነው?›› እያሉ ማስታወቂያ ያስነግራሉ፡ ጥሩ ጥሩ ጫማ በማምረት እውቅና እያገኙ ሲመጡ የአንደኛው የዓለም ጦርነት
ሲቀሰቀስ የወታደር ጫማ አቅርቦት ትእዛዝ ጨረታ አሸናፊ ሆኑ።
በ1920 ዓ.ም አሜሪካ ኒው ኢንግላንድ ስቴት ውስጥ በርካታ ሱቆች በመክፈት ራሳቸው የሚያመርቱትን ጫማ ብቻ መሸጡን ተያያዙት፡፡ በ1930 ዓ.ም በተከሰተው የኢኮኖሚ
ድቀት ምክንያት ገበያው
ስለቀዘቀዘ የሚፈበረኩትን የስታይል ዓይነቶች መቀነስ ተገደዱ፡፡ ኢኮኖሚው እያንሰራራ ሲመጣ ለተለያዩ ስታይል ጫማዎች አንድ ዓይነት ዋጋ በመቁረጥ ገበያውን ተቆጣጠሩት፡፡ በዚህ ብልጠታቸው በመጠቀም ሌሎች ነጋዴዎችን ከገበያ
በማስወጣት በትርፍ ላይ ትርፍ ማጋበሱን ቀጠሉ።
የናንሲ አባት ‹‹መጥፎ ጫማ ለመስራት የሚወጣው ወጪ ጥሩ ጫማ ለማምረት ከሚወጣው ወጪ አይተናነስም›› ይሉ ነበር፡፡
ለናንሲ ጥሩ ጫማ ማምረት ጥሩ ቤት ውስጥ መኖር፣ ጥሩ መልበስና ማጌጥ፣ ጥሩ ጥሩ መኪና መንዳትና በየጊዜው መደገስ ማለት ነው፡፡ወንድሟ ሰላሳ ስምንት ዓመቱ ነው፡፡ አባታቸው ለሁለቱ ልጆቻቸው
ለእያንዳንዳቸው 40 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ አውርሰዋቸው ከሞቱ አምስት ዓመት ሞላቸው፡፡ የአባታቸው እህት አክስታቸው 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ሲወርሱ ቀሪው 10 በመቶ ደግሞ በታማኝነት ላገለገሏቸው አዛውንት ጠበቃ ደርሷቸዋል፡፡
ናንሲ አባታቸው ሲሞቱ የኩባንያውን ኃላፊነት ቦታ ለእሷ እንደሚሰጡ
ትገምት ነበር፡ ሴት የኩባንያ ኃላፊነት ቦታ መያዟ ባይለመድም አባቷ
ከፒተር ይልቅ ቢዝነሱን እንድትመራ እሷን ይመርጡ ነበር።
አባቷ ናት ሪጅዌይ የሚባል እሳት የላሰ ምክትል ነበራቸው፡፡ እሱ በበኩሉ የብላክ ቡትስ ጫማ ፋብሪካ ዋና ኃላፊ መሆን ይመኛል።
ፒተርም የኃላፊነቱን ቦታ መከጀሉ አልቀረም፡፡ እሱ ደግሞ የቤተሰቡ ወንድ ልጅ ነው ናንሲ አባቷ ከፒተር ይልቅ ስለሚያቀርቧት ሁልጊዜ ትሸማቀቅ ነበር፡ ፒተር በአባቱ እግር ካልተተካ በጣም እንደሚያዝን ጥርጥር የለውም፡፡ ናንሲም እሱ ከሚያዝን በማለት ኃላፊነቱን እንዲወስድ
ቦታውን ለቀቀችለት፡፡ እሷና ወንድሟ በድምሩ 80 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ
ይዘዋል፡፡
ናት ሪጅዌይ በዚህ ተቀይሞ ኒውዮርክ የሚገኘው ጄኔራል ቴክስታይልስ
የተባለ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ተቀጠረ፡፡ የእሱ ኩባንያውን ለቆ መሄድ
ክስረቱ ለብላክ ቡትስ ብቻ ሳይሆን ለናንሲ ጭምር ነበር፤ አባቷ ሊሞቱ
አካባቢ ከናንሲ ጋር ወዳጅነት ጀምሮ ነበር፡፡
ናንሲ ባሏ ከሞተ ወዲህ ከማንም ወንድ ጋር ወዳጅነት አልመሰረተችም
ነበር፡፡ ናት ፤ደግሞ "በትክክለኛው ጊዜ ነው የደረሰላት ባሏ ከሞተ አምስት ዓመት በኋላ ህይወቷ ሁሉ ስራ ብቻ በሆነበትና የወንድ ፍቅርና የገላ ጠረን እየናፈቃት በመጣበት ዘመን፡፡ በወቅቱ የተወሰኑ ቀናት ራት ጋብዟታል ቴአትር ቤትም ወስዷታል አንድ ቀን ቤቷ ሲሸኛት ምጥጥ አድርጋ
ስማዋለች፡፡ ነገር ግን ይህ ግንኙነት ብዙም ሳይዘልቅ ናት ሪጅዌይ ጥሏት
እብስ አለ፡፡ መሸወዷን ስታውቅ ክፉኛ በሸቀች፡
ከዚያ በኋላ ናት ረጂዌይ
በጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ ታዋቂነትን አትርፎ የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ለመሆን በቃ፡፡ከዚያ በኋላ ከናንሲ አስር ዓመት የምታንስ ቆንጆ ሴት አገባና ናንሲን አሳፈራት፡፡
ፒተር የኃላፊነቱን ቦታ መወጣት አልቻለም፡፡ የኩባንያው ስራ
አስኪያጅነት ቦታ በእጁ በሆነበት አምስት ዓመት ጊዜ የኩባንያው ገቢ
ቁልቁል ወረደ ሱቆቹ በሙሉ ዋናቸውን ከማስመለስ በስተቀር ትርፍ ማግኘት አቃታቸው ኒውዮርክ ውስጥ የሴቶች ጫማ መሸጫ
ቢከፍትም ይህም ሱቅ ከኪሳራ አልዳነም፡፡
ናንሲ የምትመራው ፋብሪካ ብቻ ነው አትራፊ የነበረው:: አገሪቱ የኢኮኖሚ አዘቅት እየወጣች ባለችበት በአስራ ዘጠኝ ሰላሳዎቹ አጋማሽ
ዓመታት ክፍት የሴቶች ሰንደል ጫማ ማምረት ጀመረችና በአንድ ጊዜ
ተወዳጅ ሆነላት፤ ወደፊት የሴቶች ጫማ ገበያ የደራ እንደሚሆን ተገነዘበች
የማምረት አቅሙ ቢኖራት አሁን ከምትሸጠው የጫማ ቁጥር እጥፍ ትሸጥ ነበር፡፡ ነገር ግን እሷ ያመጣችው ትርፍ በፒተር ኪሳራ ስለሚዋጥ ፋብሪካውን ማስፋፋት አልቻለችም፡፡
ናንሲ የጫማ ንግዱን ከኪሳራ ለማዳን አንድ ነገር መደረግ እንዳለበት
ተገነዘበች፡፡
የማስፋፊያ ካፒታል ለመፍጠር የጫማ መደብሮቹ ለኃላፊዎቹ መሸጥ አለባቸው፡፡ ከመደብሮቹ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ፋብሪካውን ለማዘመንና ለማስፋፋት ስራ ላይ ይውላል ፒተር ደግሞ የስራ አስኪያጅነቱን ቦታ
ለእሷ ይለቅና የወጪ ገደብ ጣሪያ ተሰጥቶት የኒውዮርኩን መደብር ብቻ
ያንቀሳቅሳል፡፡
ፒተር የኩባንያውን ሊቀመንበርነት ከነሙሉ ክብሩና ጥቅሙ ይዞ
እንዲቆይ፣ የፒተርን መደብ ከእሷ ኩባንያ ከሚገኘው ትርፍ በገደብ ልትደጉም ሆኖም እውነተኛ ስልጣኑን እንዲለቅ ልታደርገው ፈልጋለች፡
እነዚህን እቅዶቿን ለሌሎች ሳታሳውቅ ለፒተር ለብቻው አቀረበችለት እሱም አስቦበት መልስ እንደሚሰጣት ቃል ገባ፡፡ የኩባንያው ገቢ መቀነስ
በዚሁ ሁኔታ መቀጠል እንደማይገባው በዚህ እቅድ የማይስማማ ከሆነ እሱን
አልፋ ለቦርድ በማቅረብ እሱን አስነስታ ቦታውን እንደምትይዝ በእርጋታ
አስጠነቀቀችው፡፡ ይህን ሳይቀበል ቀርቶ አምባጓሮ ማንሳት ከመረጠ አሳፋሪ
ሽንፈት እንደሚገጥመውና ምናልባትም ከእህቱ ጋር ተቆራርጦ እንደሚቀር
ጥርጥር የለውም
እስካሁንም ምንም ጥቃት አልከፈተም::የተረጋጋ ተቆርቋሪና ተጫዋች መሰለ፡ ፓሪስ ላይ ፒተር ለመደብሮቹ የወቅቱን ፋሽን የተከተሉ ጫማዎች ሲሸምት እሷ ደግሞ ለራሷ ጫማዎች ስትገዛ የፒተርን ወጪ በጥንቃቄ አጠናች፡
ሁሉም እንደሚያደርገው ወንድምና እህት ወደ አሜሪካ መመለስ
እንዳለባቸው ወሰኑ
ቦታው ሁሉ ስለተያዘ በአይሮፕላን ለመሄድ ደግሞ አልተቻለም፡፡
በመጨረሻ ከሊቨርፑል የሚነሳ ውርከብ ቲኬት ገዛች፡፡ ከፓሪስ በባቡር ረጅም ጉዞ ከተጓዙ በኋላ በጀልባ ወደ ለንደን አመሩ፡
ዛሬ በአየር በራሪው ጀልባ ሊበሩ ነው፡፡

👍23❤1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሦስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ከሎ ሆራ በጨርቆሌ ማዝነት በደንብ እየተቀለበ ከቆየ በኋላ ሚዜው ሰውነቱ እንደ ተመለሰ አረጋገጠ። ስለዚህ ከሎ ሆራና ሚዜው
ከተሪ (ዲክ ዲክ) ቆዳ የተተለተለ ቀበቶ መሳይና ኩርኩፋ ይዘው
በደንቡ መሠረት ጎይቲ አንተነህን በድብቅ ማሳደድ ጀመሩ።
ጎይቲ አንተነህ ከሎን አልወደደችውም እሷ ልቧ የጠፋባት ለዚያ ጀግና ለደልቲ ገልዲ ነው" መሬቱን በልበሙሉነት እየረገጠ
ሲንጐማለል፣ የሷንም ልብ እንደ ጠረማመሰው ሁሉ በፍቅር ታቃስታለች።
በኢቫንጋዲ ጭፈራ ወቅት አንዳንዴ መንደራቸው ብቅ ካለ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑትን ሌሎቹን የዳንስ ምቶች ከሌሎች ጋር
ብትጨፍርም ጭንን በጭን የማግባቱ ጊዜ ቀድማ የምትጋብዘው እሱን ነው። ጭኑን በጭኗ ውስጥ ሲያስገባ የአእምሮዋን እንቅስቃሴ ያዛባና በቍጥጥሩ ስር ያደርጋታል" ከወገቧ ልጥጥ ብላ ወንድ ብልቱ ላይ ትለጠፍበታለች" በዚያ ወቅት ስሜት እንደ ቅቤ ይቀልጥና እሱም እሽት፣ እሷም አሽት፣ እሱም እሽት...ሲደራረጉ ይቆዩና
ሁለቱም ሲሸነፉ፣ ውጥረት ሲበዛባቸው ተያይዘው ወደ ጫካ፣ ወደ ልዩው የተፈጥሮ መኝታ ክፍል ጐራ ይላሉ“
ጫካው ውስጥ ወፎች፣ አራዊት፣ እባቦችና ሰዎችም ጭምር ፍቅራቸውን በነፃነት ይለዋወጣሉ ጫካ ውስጥ ትርዒት አቅራቢ እንጂ
ተመልካች አይኖርም። «ሁሉም ለየራሱ…» ብቻ መባባል ነው።
ጎይቲ አንተነህ ታዲያ ያ አራዊትን፣ ሰውን የገደለ ጀግና የፍቅርም ጀግና ሆኖ አግኝታዋለች" ጠምዘዝ አድርጎ በጠንካራ እጆቹ ወደ እሱ እያስጠጋ ትንፋሿ እስኪቋረጥ የሚስማትና እንደ ሕፃን ልጅ አቅፎ የሚያጫውታት ሁሉ ትዝታን ያልፈጠረባት እፎይታን ያልሰጣት ጊዜ የለም።
ከሎ ሆራ፣ ጎይቲ አንተነህን ባየ ቍጥር ከፍቅሩ ፅናት አንፃር ሰውነቱ እየተልፈሰፈሰ ቢርበተበትም ተፈቃሪዋ ግን ኵሩ ሆና ኵሩ ወንድ፣ ጅንን ጀግና፣ ስሙ የገነነ ወንድ ፈላጊ ነበረችና እሱ ለእሷ
ሲል ልብሱን አውልቆ ራቁቱን ቢሄድም፣ ሊያደርገው ያላሰበውን
እንዲያደርግ ፍቅሯ ቢያስገድደውም፣ እሷ ግን ለሱ ቁብ የማይሰማት
ሆነችበት"
የጎይቲ አንተነህ ልብ ያለው ደልቲ ገልዲ ላይ ሲሆን፣ የከሎ ሆራ ልብ የማለለው ደግሞ፣ ለጎይቲ አንተነህ ነው። ቢሆንም ከሎ
ሆራ እሷን የማግኘት ተስፋው አልጨለመበትም" እሱም ሆነ ሽያው
(ሚዜው) ከቀናቸው ጎይቲ አንተነህን ብቻዋን ሰከም ሰከም ስትል ሊያገኟት ይችላሉ።
አንድ ቀን በሬ ጠምዳ ስታርስ፣ አጥማጆቿ በርቀት ቍጥቋጦው ውስጥ ተደብቀው ሲከተሏት ዋሉ። መቼም እንደዚያን ቀን በከፊል የተመቻቸ ቀን ከዚህ በፊት አላጋጠማቸውም" በሬዎችን በጅራፍ ሸንቆጥ በማድረግ፣ ከወገቧ ወደ ጎንና ጎን ለጠጥ፣ ዳሌዎቿን ወጣ ገባ....እያደረገች ስለ ሐመር ጀግኖች፣ ስለ ከስኬ ወንዝ፣ ስለ በልጉ ታንጐራጕራለች። አጠገቧ የአጎቷ ልጅ ብቻ ነው ያለው፤ እሱ ዘወር ካለላቸው ፈጥነው ሊይዟትና የልባቸውን ሊያደርሱ ይችላሉ " እሱ እያለ ግን ምንም መሥራት አይችሉም ጎይቲ የተዘጋጀላትን ወጥመድ በጭራሽ አላወቀችም ዝም ብላ እርሻዋን ታርሳለች። አፍቃሪዋም፣ ከዘምባባው ዙሪያ ካለው ሰንበሌጥ ውስጥ ሆኖ በገዛ ምራቁ ይታነቃል።
አጥጆቿ፣ የኦጎቷን ልጅ ቦርጆ (አምላክ) ከዚያ አካባቢ ዘወር እንዲያደርገው ይመኛሉ" የአጎቷ ልጅ ደግሞ፣ ጎይቲ አንተነህ ልጃገረድ በመሆኗ ብቻዋን ትቷት ቢሄድ ሊደርስባት የሚችለውን
አጋጣሚ አሰበ" ኋላ እሱና ሌሎች ጐረምሳ ዘመዶቿ መጠበቅ ተስኗቸው ጀግንነት፣ ሀብት ከሌለው አንዱ ቢተናኮላት የሌሎች
ልጃገረዶች ማሽሟጠጥና በጓደኞቹ «ፈሪ» ተብሎ መናቁ፣ እሱንና ዘመዶቹን ስለሚያናድዳቸው ብቻዋን ትቷት ለመሄድ አልፈለገም።
ስለዚህ አዳኞች ታዳኟን በቍጥጥር ሥር እንዳያውሉ የአጎቷ ልጅ
«ጕሮሮ አጥንት» ሆኖባቸው ሳይሳካላቸው ቀረ።
በሌላ ቀናትም ውኃ ለመቅዳት ስትሄድ፣ ገበያ ስትመላለስ ትክለ
ቁመናዋን፣ ፈገግታዋን፣ የሚነጥረውን መቀመጫዋን ቀምሶ
ያልጠገበውና እያየ በመሳሳት ላይ ያለው የመንደሯ ጐረምሳ፣ እንደ
ሴት ውሻ ከቦ ስለሚከታተላት በድብቅ ለሚከታተሏት እንቅፋት
ሆኖባቸው ሰነበተ።
ከሎ ሆራ ከሚዜው ጋር ጫካ ለጫካ ሲዞርና ጎይቲ አንተነህን ሲከታተል ጕሮሮው ሲጮህበት ቢውልም፣ እየቆየ ግን መሰላቸት ጀመረ። ፊት ለፊት ሄዶ የደንቡን ለመፈጸም ያስብና ባህሉን ባለማክካበሩ የሚደርስበትን ውግዘትና ቅጣት እያሰበ፣ ሐሳቡን ከሕሊናው አውጥቶ ያሽቀነጥራል"
አንድ ቀን ግን፣ ጎይቲ አንተነህ ደንገዝገዝ ባለ ምሽት፣ ከቤቷ ወጥታ መንገዱን ስትነካው እነከሎ ተከተሏት" ከመንደሯ ዘወር
እንዳለች የመሮጥ ያህል እየተራመደች ወደፊት ገሰገሰች" ከሎ ሆራ፣
«የት እየሄደች ይሆን? ብቻዋን ካለፍርሃት እንዴት ትሄዳለች» በማለት ግራ ገባው ከወሮ ራቅ ብለው ካሉት መንደሮች ለመድረስ
ከመቻሏ በፊት ግን እነሱ ያቀዱትን ከመፈጸም የሚያግዳቸው የለም።
«አቤት ለስንት ጊዜ እንዳለፋን በግላጭ አገኘናት» ተባብለው
ከሎና ሚዜው ተቃቅፈው ደስታቸውን ተገላለጹና ፍጥነት ጨምረው
ለመያዝ ወደ ፊት ሽምጥ ሮጡ" እሷ ዘንድ ከመድረሳቸው በፊት ግን
ሁለቱም ሩጫቸውን ገትተው ቆሙ ከግራር ጥላው ሥር መሣሪያ የያዘና በርኮታው ላየ የተቀመጠ ሰው ያዩ መሰላቸው» አበሸቃቸው፣ ገረማቸውም፣ «ማን ይሆን?» ጠየቀ ከሎ፣ «እንጃ!» አለ ሚዜው። ስለዚህ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ቃጫው ተክል ገባ ብለው አደፈጡ። ጎይቲ አንተነህ ወደዚያ
ሰው እየቀረበች ስትሄድ እየተደነባበረች የሰካራም ጕዞ ጀመረች ሰውየው መጀመሪያ አላያትም ነበር። ዱካዋን ሲሰማ ግን
ከተቀመጠበት ፈንጠር ብሎ ተነሥቶ መሣሪያውን ሲደግን፣ ወደሱ
የምትገሰግሰው ጎይቲ አንተነህ ናት። መሣሪያውን አቃንቶ፣ እጁን ከፍቶ ጠበቃት፤ ያው እንደ ልማዱ እንደ ቀንድ የቆመው ጡቷን
ከሰውነቱ ስታሻሽለት፣ እሱም የኰራውን ዳሌዋን በሁለት እጁ ወደ
እሱ ይበልጥ እየሳበ፣ ትንፋሿ እስኪቈረጥ ድረስ ሳማት። እሷም ሆነ እሱ በተፈጠረው ሙቀት እንደ ቅቤ ቀለጡ።
ከሎ ሆራ፣ ይህን ትርዒት ራሱ እንደሚሠራ ሁሉ፣ እሱም ባለበት ደነዘዘ። ሰውነቱ ሁሉ ባለበት ሲወጣጠር ታወቀው። በእሱ ላይ የተለጠፈችበትና አቅፎ የሚስማት መሰለው። ዋና ተዋናይዎቹ ግን ወደ ዋናው እርካታ ጕዟቸው ለመሄድ አንዱ በሌላው ውስጥ ዘልቆ ሲገባ ከሎ ከሰመመኑ ነቃ። የሚወዳት ጎይቲ አንተነህ ከሱ ጋር
ሳይሆን ያለችው ከሌላ ሰው ጋር ነው። እሱ ያቀፈውና የሳመው ለካ ግንዱን ነው" እሱ ግንድ አቅፎ ሲስም፣ እሷ ሰው አቅፋ
ትቃበጣለች፣ «ዳሚት» አለ ከሎ፣ ሊቈጣጠረው በማይችለው ስሜት ተወጥሮ።
ከሎ ሆራ ሰውዬውን በደንብ ቢያስተውለውም ሊለየው
አልቻለም። ሚዜው ግን ነገረው፣ «አያ ደልቲ ገልዲ ነው» አለው።
"አዎ እሱ ነው ካለሱ እሷን እንዲህ የሚያደነባብራትና
ትንፋሿን የሚያሳጣት ወንድ የለም» በማለት፣ በእልህ ወደ ተዋጠ ሰሜት ውስጥ ገባ" ሚዜው ግን፣ ከርቀት የሚታየው ቅብጠት አፉን
አስከፍቶታል።
ፍቅረኛሞች የፍቅር ጥማቸውን ለማርካት እየደጋገሙ ሲጫወቱ ቆዩና ተለያዩ" ጎይቲ አንተነህ ወደ መንደሯ ስትመለስ ከኋላ የቀረባት ሰው እንዳለ ሁሉ ልቧ ተንጠልጥሎ አልፈጠነችም። መንደሯ

👍22🥰2
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሦስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ሶራ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው በሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ዓመተ ምህረት ነው። ከዚያም በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና በረጂ ድርጅቶች ሰርቷል። ሥራ መቀያየሩ ግን ሆዱን እንደ እንቁራሪት ሆድ ከማሳበጥ በስተቀር ያገኘው የሕይወት እርካታ
የለም። የት ቢሄድ ምን
ቢሆን የህሊና እርካታ እንደሚያገኝ
አያውቅም ዩኒቨርስቲ ውስጥ እያለ ኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንትን የመረጠው በጓደኞቹ ምክርና ግፊት ነው።
"...አትሞኝ! ጥሩ ደመወዝ ለማግኘት አዲሳባ ለመመደብ ዕድልተህ እንዲሰፋ ከፈለግህ" እያሉ የሰማይ ጥገት የሚመኙ ጓደኞቹ እየነዱ ወደ አልተመኘው ዲፓርትመንት
ሃሳቡን አኮላሽተው
አስገቡት።
ከአደገበት· ቀዬ ከተንቦራቸበት የኤርቦሬ ምድርም ዳግመኛ ሳይመለስ የውሃ ሽታ ሆኖ ወደ መጣበት ተመልሶ መግባት የማይታሰብ ገደል ሆነበት። በልጅነቱ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ሊሄድ
ጥብቆ ሲለብስ
ሽማግሌዎችም ሲመርቁት
“…እንደ ጅብ በነጋበት የምትቀር አትሁን። የአያት የቅድመ አያቶችህን ደንብ አክባሪ ለወገንህ ተቆርቋሪ መሆንህን የምታስመሰክር ሁን ብትጠፋ እንኳ የእነሱ ዘር ነው የሚያሰኝህን
ኤርቦሬነትህን አታጥፋ።
ኤርቦሬ ውስጥ ሪስ ፋርቶ ሃልዝጋለች አልሞቅ ሩፍ ህፀንቴ ኤቡሬ ጋሮራ
ጋራንጉዶ ጋርሌ ዲሳ የሚባል ዘር አለ ወደምትሄድበት አገር ስትደርስ የከብት ጆሮ
አበሳሳችሁ እንዴት ነው? ህፃን ልጅ እንደ ተወለደስ መጀመሪያ የምታቀምሱት ምንድን ነው?ብዙ ጊዜ የምትጋቡትስ ከማን
ከማን ጋር ነው?..." ብለህ ጠይቅ።
“...የአንተ ዘር የከብት ጆሮ አበሳስ ታችኛውን የጆሮ ክፍል ከውስጥ ወደ ውጭ በመብሳት ሲሆን! ህፃን ልጅ እንደተወለደ የቡና
ፍሬ ማሽላ የከብት ጥፍር ከህፃኑ ልጅ ሽንት ጋር ተቀላቅሎ ይሰጠዋል። ብዙ ጊዜ ጋብቻ ከቦረናና ፀማይ ጋር ነው። ስለዚህ
ይህን በሄድህበት ሁሉ እየነገርህ ዘርህን ብትጠይቅ ካለጥርጥር
ታገኛቸዋለህ: ከዚያ የቤተስባችሁ አባል ከሌላ አገር ስለመጣ ተቀበሉት ብለው ከዘሮችህ ያደባልቁሃል:
ወደ ሌላ አገር የሄደና የሞተ አንድ ነው እስካልታዩ ድረስ:: ልዩነቱ ያልሞተ ከሄደበት ይመለሳል ! ያኔ ወደ ቤተሰቡ ከመቀላቀሉ በፊት የመንደሩ ሰዎች ማንም ሰው ጠጥቶበት
በማያውቅ ቅል ውሃ ሞልተው ይይዙና ከፊት ለፊቱ ውሃውን እየደፉ መሬቱን በማርጠብ እርጥቡን እግር" ከቤተሰቡ ጋር ይደባልቁታል! ካለበለዚያ ግን ማንም የቤተሰቡ አባል ቢያየውም
ሰላም አይለውም:: እና! አንተም ክሄድክበት ስትመለስ ይኸ ደንብ
እንደሚሰራልህ አትርሳ: ከደንቡ በኋላ ከኤርቦሬ ወንድሞችህ ጋር ጫካ ትወርድና ያገኘኸውን አውሬ ገለህ ስትመጣ ከወላጆችህ በር ፊት ለፊት የእድሜ ጓደኞችህ "ዘውትር ምሽት እየዘፈኑ እያቅራሩ አንዱ የሌላውን ጀርባ ሸፍኖ እየተቀመጠ የአባትህ ቤት የጀግና ቤት መሆኑን እያወደሱ ሲያደምቁት ይሰነብታሉ… ከዚያ ተድረህ ወልደህ ከብደህ ጋንደሩባ ኡላም ሙራል ወይም እጉዴ ትኖራለህ።
“ ኤርቦሬ በአሁኑ ጊዜ ስልጣን የያዘው የኦጌልሻ ሄር ሲሆን ኦጌልሻ ሄር ስልጣነን የተረከበው ከሜልባሳ ሄር ነው።
“በአባትህ ባህል በአርባ ዓመት አንድ ጊዜ አሮጌው ገዥ ሄር በአዲሱ ገዥ ሄር ይተካል:: ይህም ኦቤርሻ ጂም ጊድማ ጂም
ማሮሌ ጂምና ዋተኛ ጂም ሲሆን የመጀመሪያው ጂም ከአስር እስከ አስራ ስምንት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች ሲሆኑ ኦቤርሻ ጂም ይባላሉ: ከዚያ ከጨቅላነት እስከ ዘጠኝ ዓመት ያሉት ህፃናት
አድገው ከአስር እስከ አስራ ስምንት አመት ሲሞላቸው ጊድማ ጂም ይሆናሉ። ያም ማለት ከኦቤርሻ ጂም እስከ ጊድማ ጂም ዘጠኝ ዓመት
ይሆናል ቀጥሎ ደግሞ ከጊድማ ጂም በታች ካሉት ጨቅላዎች እስከ ዘጠኝ ዓመት ያሉት አድገው ከአስር አመት እስከ አስራ ስምንት ዓመት ሲሞላቸው ማሮሌ ጂምን ይመሰርታሉ።
ይህም ዘጠኝ ዓመት
ይፈጃል። ከማሮሌ በታች ያሉት ከጨቅላነት እስከ "ዘጠኝ ዓመት ያሉት አድገው ከአስር እስከ አስራ ስምንት ዓመት ሲሞላቸው ደግሞ ዋተኛ ጂም ይባላሉ።
“ስለዚህ ኦቤርሻ ጂም ዘጠኝ ጊዴማ ጅም ዘጠኝ ማርሌና የአራቱን ጂም
ዋተኛ ጂም እያንዳንዳቸው ዘጠኝ ዘጠኝ ስለሚቆዩ
ለመፈፀም ሰላሳ ስድስት አመት የሚፈጅ ሲሆን አሮጌውን የገዥ ሄር
ከተለያዩ እድሜ ከሴትና ወንድ በእኩል የተሰባሰበውን አዲስ ሄር
አጠቃላይ የኤርቦራ ማህበረሰብ በተሰበሰበበት በተለያዩ ባህላዊ ስነስርዓቶች ስልጣን ከአሮጌው ሄር ይረከብና በጋንደሩባ ኩላም
ሙራልና እጉዴ አንዳንድ ከርነት (ጠቅላይ ሚኒስቴር) ይመረጣል። ከርነት ሆኖ የተመረጠው ሰው ካለ ግልድም በስተቀር ልብስ
አይለብስም። ባህሪውም የተመሰገነ ትሁት... መሆን ይገባዋል። ይህ ሰው የአባት ደንብና አሁን ያለው የኤርቦሬ ህዝብ የአደራ ቀንበር የሚጫንበት በሬ ነው: ጎረምሶችም የራሳቸውን የጦርነት ጊዜ
አዝማች 'መሪናኔት' መርጠው የነብር ቆዳ ያለብሱታል: ይህም ሰው
በጦርነት ጊዜ ስልት አውጭና ደረቱን ለጦር ሰጥቶ ለህዝቡ መከታ
የሚሆን ነው።
“ከዚያ የፖለቲካ መሪ የሚሆኑት አራቱ ከርነቶች
ከመንፈሳዊ መሪዎች (ቃውቶች) የአገር ሽማግሌዎች (ጃላቦች) ጋር
ስልጣናቸውን ለሚቀጥለው ወጣት ሄር ያስረክባሉ። ስለዚህ አንተ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኦጌልሻ ሄር አባል በመሆንህ ቶሎ ተመልሰህ
ማህበረሰብህን መርዳትህን አትዘንጋ: እስከዚያው ግን
ወገኖችህ ፀሐይ ወጥታ እስክትገባ ሳንሰለች እንጠብቅሃለን፡፡ ይህ ኸሊናህ ሳይጎድፍ ተመልሰህ ናና ከማህበረሰብህ ተቀላቀል...” ብለውት ነበር።
አካሉ እያደገ ህሊናው እየበሰለ ሲሄድ ግን ከዘመዶቹ አደራ በላይ የአገሩ የአህጉሩ ባጠቃላይ የሰው ልጆችን የመርዳት አደራ ፕላኔቷን የመጠበቅ ግዴታ... እንዳለበት እንኳን ተረድቶ ነበር። በጎ
አስተሳሰቡን ግን ውሃ በላው። አፍንጫው ጥቅም ውስጥ እየተሰነቀረ
ሆዱ ለእለት ደስታ እየተነጠፈ አስቸገረው መቆፈሪያ አንስቶ
የድህነት ተራራ ለመናድ የማንዴላ እናት አምጣ እንድትወልደው ኃይልን እንድታቀብለው ፈለገ እየቆየ ግን አንድ ሃሣብ በህሊናው
ማውጣት ማውረድ ጀመረ።: ቢያንስ በግሉ አንድ ሆዝብን ሊረዳ
ድርጅት መክፈት። ለዚህም ደግሞ ገንዘብ ያሻዋል። ገንዘብ ያላቸው ሰዎች መዳፍ ገብቶ እንደ ቆሎ እያሹ ጉልበቱን ቆረጣጥመው ምስጥ
እንደበላው ግንድ ገንድሰው እንዲጥሉት ግን አልፈለገም
ነፃ መሆንን መረጠ፡
ለዚህ ግን አልታደለም። ያለበት ዘመን ህይወት በገንዘብ የሚተመንበት የገንዘብ ኃይል ነጋሪት እየተጎሰመ በሚለፈፍበት ጊዜ ነው። ዓላማውን ለማሳካት ግን አንድ አማራጭ አለው: ሰርቶ
የማግኛ ስደት: "ስደት ግን ሽሽት ነው" ብሎ ያምን ነበር: ከዚህ ህዝብ ጋር የበላውን በልቶ የጠጣውን ጠጥቶ ከንፈር እየመጠጡ
ማስተዛኑም ደግሞ ድፍረት እንዳልሆነ ተረዳ። ኤርቦሬ አደራ ይዞ ወጣ፤ አልተመለሰም እና! አደራውን በላ: ከአገሩ ሰርቶ
ለማግኘት ብሎ ሄዶ ፍርፋሬ ቢጥመውስ፤ አዲስ ምኞት ህሊናው ቢያረግዝስ እንደገና ክህደት ሊፈፅም? ስለዚህ ለመወሰን ብዙ
አማጠ ከወሰነ በኋላም ህልሙን እውን ለማድረግ ብዙ ጣረ፤ ግን ተሳካለት። እንደ ደረቀ እንጨት የተለዬ ሆነ እንጂ።

👍21