#ሮሜዎና_ዡልዬት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
ለክፋት ፡ ነው ፡እንጂ አልመጣም ፡ በደኅና
እንግዴህ ፡ ልያዘው ፡ ድንገት ፡ ልድረስና ።
(ቀረበ) ።
አንተ ፡ የሞንታግ ፡ ልጅ ፡ዐመፀኛ ፡ መጥፎ
በሰላም ፡ ጸጥታ፡ የተኛውን ፡ ዐርፎ ፡
ምን ፡ ልታደርግ ፡ ነው ፡ ትኵሱን ፡ ሬሳ ፡
ከመቃብሩ ፡ ላይ ፡ በል ፡ እጅህን ፡ አንሣ ፡
ና፡ ወዲህ ፡ ልያዝህ ፡ ከዚህ ፡ ቦታ ፡ ውጣ
ኣሳልፌ ፡ ልስጥህ ፡ በሞት ፡ ለሚቀጣ ።
#ሮሜዎ
አንተ መልካም ወጣት፡ዐርፈህ ሂድ በደኅና
እኔ ፡ ሞገደኛ፡ አጥፊ ፡ ሰው ፡ ነኝና ፡
መዘዜ፡ የበዛ ፡ አሳር ፡ የጐተተኝ፡
ሕይወቴን ፡ የጠላሁ፣ ኑሮ ፡ የታከተኝ፡
ሞትና ፡ መቃብር ፡ ጥፋት ፡ የሸተተኝ ፡
የከፋው ፡ ወንድ ፡ ነኝ ፡ ወደኔ ፡ አትጠጋ ፤ .
ጠብ ፡ አትፈልገኝ' ለሕይወትህ ፡ ሥጋ ።
ቲባልት ፡ እንደዚሁ ፡ ደርሶ : ሳይቸግረው ፡
በመጥፎ፡ ንግግር ፡ ሆዴን ፡ አሳረረው ፡
ሳልፈልግ ፡ ገደልኩት እሱ ባነሣው ፡ ጠብ
አሁን ፡ ደግሞ ፡ አንተ ይብቃህ ፡ አትሳደብ
ነፍሴን ፡ የጠላሁ፡ ሰው ፡ በመሆኔ ፡ ፍራኝ
ሳልወድ ፡ በግዴታ ፡ ዐመፅ ፡ አታሠራኝ ፡
የሚወጣው ፡ ምክር ፡ አሁን ፡ ከመላሴ ፡
አልሠራሁበትም ፡ እኔ ፡ እንኳ ፡ ለራሴ ፡
ስለዚህ ፡ ከራሴ ፡ አብልጬ ፡ ስወድህ ፡
እኔን ፡ አመስግነህ ፡ ይሻላል ፡ መሄድህ ፡
አንድ፡ እብድ ፡ ሰው ዛሬ የሰጠኝን ምክር
ሰምቼ ፡ ድኛለሁ ፡ ብለህ ፡ ይልቅ ፡ ፎክር ።
#ፓሪስ ።
እኔስ ፡ ኣለቅህም ፡ ከያዝኩህ ፡ በኋላ ፤
መስጠት ፡ ትችላለህ ፡ ምክርህን ፡ ለሌላ
#ሮሜዎ
መሞት ፡ ከፈለገህ ፡ እንቢ ፡ ብለህ ፡ በጄ ፡
እንግዲያው ሞክረኝ መልካም፡ነው ወዳጄ
(ይዋጉና'ፓሪስ ፡ ይወድቃል) ።.
ቲባልትና ፣ፓሪስ ፡ እኔን እያስቆጡ ፣
እኔ ፡ ሳልነካቸው ፡ በግድ ፡ እየመጡ፡
በእጄ ፡ እየተወጉ' ክዚህ ፡ ዓለም ፡ ወጡ ።
እንዲህ ፡ መሞታቸው ፡ ተናግረውኝ ፡ ክፉ
ተፈርዶባቸው ፡ ነው ፡ በኔ' እጅ እንዲጠፉ
እንደዚህ ፡ ከሆነ ፡ ፓሪስ ፡ ያንተም ፡ ዕጣ ፡
ጥፋቱ ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ በኔ ፡ እንዳትቈጣ ፡
የዡልዬት ፡ ቁንዥና፡ ደምቆ እንደ ፡ ብርሃን
ጽርሐ አርያም ፡ መስሎ የሰማይ ፡ ውጋጋን
እያንጸባረቀ ፡ ከኮከብ ፡ ሲያበራ ፡
ግርማ፡ተጐናጽፎ፡ በታየበት፡ ስፍራ፡
እንሙት' ወዳጄ ፡ ኣብረን ፡ ከሷ ፡ ጋራ።
(ሮሜዎበዝልዬት፡መቃብር፡ላይየሐዘን ' ንግግር ፡ ያደርጋል)።
ይህችን ፡ ውብ ፡ አበባ ፡ ፍቅር ፡ አሳማሪ ፡
ውሏን ፡ የማትረሳ ፡ ቃል ፡ ኪዳን ፡ አክባሪ ፡
ትወድ ፡ የነበረች ፡ ቁም ፡ ነገር ፡ ጨዋታ፡
እዩልኝ ፡ ከዘመድ ፡ ከሰው ፡ ተለይታ ፡
የኔ ፡ ሆደ፡ ባሻ ፡ ብቻዋን ፡ ተኝታ፡
ተመልከቱት ፡ እጅዋ ፡ ተመልከቱት ፡ ፊቷ ፤
ወዟ ፡ ገና፡ አልጠፋም ። ከሠራ፡ አካላቷ፡
ግንባሯን ፡ ከንፈራን ፡ ተመልከቱ ፡ ጣቷን ፤
ይህን ፡ አበቃቀል ፡ ተክለ ፡ ሰውነቷን ፡
ገላዋ ፡ ያበራል ፡ በደም ፡ ተሸልሞ ፤
ዡልዬት ፡ሞት የነካት፡አትመስልም ፈጽሞ
እባካችሁ ፡ ሰዎች ፡ ሐዘን፡ ተካፈሉኝ፤
ዡልዬት ፡ አልሞተችም ፡ ተኝታለች ፡ በሉኝ
ታውቂ ፡ የነበርሽው ፡ ፍቅራዊ ፡ አቀባበል ፡
ሽቍጥቀጥ ፡እመቤት ባለመልካም ዐመል
ተወዳጁ ፡ ድምፅሽ ፡ ውብ ፡እንደ ፡ ሙዚቃ
በበገናው ፡ ቃሉ ፡ መንፈስ ፡ የሚያነቃ ፡
ዛሬ ፡ ወዴት ፡ ጠፋ? የት ፡ ቦታ ፡ ደረሰ ? .
ደግሞስ ዐይንሽ ፡ ቆቡን ስለ ምን ለበሰ ?
ዡልዩት ፡ ባትሞት ኖሮ፡ በውነት ፡ ባትቀበር
ሮሜዎ ፡ እዚህ ፡ ቆሞ ዝም አትልም ነበር
ባለም ፡ ላይ ፡ ብንሻ ፡ በውነቱ ፡ የት ፡ ኣለ ፡
ጨካኝ አረመኔ ፡ ሞትን ፡ የመሰለ ፡
ጥቂት ፡ አላዘነም ፡ አልሣሣም ፡ ጨርሶ ፡
ይችን ፡ ጽጌ ፡ ረዳ ፡ ሲጥላት ፡ በጥሶ :
ይችን ፡ አሳዛኝ ፡ ልጅ ፡ ትተዋት ፡ ሲሄዱ፡
በሩን ፡ የዘጋ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ቻለ ፡ ሆዱ
እይዋት ይችን ቄንጥ እይዋት ይችን ሎጋ
በባዶ፡ አዳራሽ ፡ በመቃብር ፡ ኣልጋ ፡
ወፍ ፡ በማይዞርበት ፡ ጭር ፡ ባለ ፡ ስፍራ ፡
ብቻዋን ፡ ቀርታለች ፡ አዲሷ ፡ ሙሽራ ።
በመከራ ፡ ቅመም ፡ ባሳር ፡ ተለውሶ :
ዡልዬት፡ ሕይወታችን ፡ መሮን ፡ እንደ ፡ኮሶ
ወጣን ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ያላንድ ፡ ደስታ .
እንግዲህ ፡ እንኑር ፡ እዚህ ፡ በጸጥታ ።
ባለም ፡ ቦታ፡ ጠፍቶ ፡ ለመኖር'ተዋደን ፡
እዚህ ፡ ተገናኘን ፡ ካለም ፡ ላይ ፡ ተሰደን
አይቈጨን እንደዚህ ካለም መውጣታችን
በጣም ፡ ደስ ፡ይበለን ፡ በዛሬው ፡ ዕጣችን
ላለሙ ፡ ደስታ ፡ ለረዥሙም ፡ ዕድሜ ፡
ያው ሞት አይደለም ወይ የሁሉ ፍጻሜ ?
ገላዬን ፡ ከገላሽ ፡ ዐፅምሽን ፡ ካዕፅሜ ፡
ሥጋዬን ፡ ከሥጋሽ ፡ ደምሽን ፡ ከደሜ ፡
ቀላቅሎ ፡ የሚያኖር፡ ከተገኘ ፡ ቦታ ፡
ዡልዬት፡ ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ ምን አለ ፡ ደስታ
ይቅር ፡ ደኅና ፡ ይሁን ፡ ዓለም ፡ ከነቂሙ ፤
እዚህ ፡ እኔና፡ አንቺ ፡ እስከ ፡ ዘላለሙ ፡
መቃብር፡ ሆኖልን ፡ የጸጥታ ፡ ገዳም ፡
ከዛሬ ፡ ጀምሮ ፡ እንኑር ፡ በሰላም ።
ከሚወዱት፡ጋራ፡ እንዲህ ፡ ጐን ፡ ለጐን ፡
ምንኛ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዐፈር ፡ ትቢያ ፡ መሆን ።
(ሮሜዎ ፡ መርዝ ፡ ጠጥቶ ፡ ሞተ ።)
#አባ_ሎራ መብራትና፡ጕጠት፡ ይዞ ፡
ወደ፡መቃብሩ፡ ቦታ፡ መጣ ።
#አባ_ሎራ ።
ስፍራው ፡ አያስኬድም ፡ ሆነና ፡ መቃብር
እያደናቀፈ ፡ ያስቸግራል ፡ ለእግር ፡
አዬ ፡ መከራዬ ፡ በዚሁ ፡ ላይ ፡ ደግሞ ፡
ምንም ፡አይታየኝ ፡ዐይኔ ፡ በጣም ፡ ደክሞ
ማነህ አንተ እዚህ የቆምከው እንደ አጥር ?
#ቤልሻጥር ።
የሚያውቁኝ ፡ወዳጅዎ ፡እኔ፡ ነኝ ቤልሻጥር ።
#አባ_ሎራ ።
እግዚአብሔር ይባርክህ በል ልጄ ንገረኝ ፤
በሩቅ ፡ አላይ ፡ ብሎ ፡ ዐይኔ ፡ አስቸገረኝ፡
እዚያ ፡ በካፑሌ ፡ የመቃብር ፡ ስፍራ ፡
መብራት አይደለም፡ ወይ የማየው ፡ ሲበራ?
#ቤልሻጥር ።
አዎን ፡ ነው ፡ አባቴ ፡ ሄዷል ፡ እዚያ ፡ ቦታ ፡
ወዳጅዎ ፡ ሮሜዎ ፡ የኔ ፡ መልካም ፡ ጌታ
#አባ_ሎራ
ማን ፡ አልከኝ ?
#ቤልሻጥር ።
ሮሜዎ ።
#አባ_ሎራ ።
አዬ ፡ የእግዜር ፡ ቀጣ
ምን ፡ ያኽል ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ እሱ ፡ እዚህ ፡ ከመጣ ?
#ቤልሻጥር ።
ልክ ፡ እኩል ፡ ሰዓት ፡ ነው ።
#አባ_ሎራ ።
ና፡ እንሂድ፡ ወደ ፡ እሱ
#ቤልሻጥር ።
አልችልም ፡ አባቴ ፡ አስጠንቅቆ ፡ ራሱ ፡
ወደ ፡ መቃብሩ፡ እሱ ፡ ወዳለበት ፡
ከቶ ፡ እንዳልጠጋ ፡ ሥራውን ፡ ለማየት ፡
ከልክሎኛልና ፡ በሞት ፡ አስፈራርቶ ፤
ትእዛዙን ፡ ለመጣስ ፡ እኔ ፡አልችልም ፡ ከቶ
#አባ_ሎራ ፡
በል ፡ ተወው፡ ልጄ ፡ ሆይ፡ ሠግቷልና፡ ልቤ
እስቲ ፡ ልመልከተው ፡ ብቻዬን፡ቀርቤ።(አባ፡ሎራሄደ)
#ቤልሻጥር ፡ (ብቻውን ) ።
ዛፍ ፡ ተደገፍኩና ፡ እንቅልፍ ወስዶኝ ፡ ኖሮ
በሕልማ፡ ሮሜዎ ፡ አድርጎ ፡ አምባጓሮ ፡
ውጊያ፡ገጠሙና ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ሲጥል ፡
አየሁ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሲገድል
#አባ_ሎራ ፡(ብቻውን) ።
ይህ ፡ ደም ፡ ከየት ፡ መጣ ? ይህ ሻምላ ፡ ምንድነው?
እዚህ ፡ የወደቀ ፡ ባለቤት ፡ የሌለው ።
(ዡሊዬት ነቃች ፤ አባ ፡ ሎራ፡ ጥግ ፡ ይዞ ፡ ቆመ) ።
#ዡልዬት ።
ሮሜዎ ፍቅሬ ሆይ ማን አምጥቶ ጣለህ ?
ይኸ ፡ ደም ምንድነው ? ፓሪስ ፡ ማ፡ገደለህ ?
ጨርሰው ፡ አይሰሙም ፡ ሞተዋል ፡ እነሱ
ትንፋሽም ፡ የላቸው ፡ አይንቀሳቀሱ ፡
የእንቅልፍ ፡ የመኝታ ፡ የዕረፍት ፡ የጸጥታ :
መሆኑ ፡ ቀረና ፡ ሰላማዊ ፡ ቦታ ፤
ከእንቅልፌ ፡ ስነቃ ፡ አወይ ፡ መቃብሬ ፡
የጦር ፡
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
ለክፋት ፡ ነው ፡እንጂ አልመጣም ፡ በደኅና
እንግዴህ ፡ ልያዘው ፡ ድንገት ፡ ልድረስና ።
(ቀረበ) ።
አንተ ፡ የሞንታግ ፡ ልጅ ፡ዐመፀኛ ፡ መጥፎ
በሰላም ፡ ጸጥታ፡ የተኛውን ፡ ዐርፎ ፡
ምን ፡ ልታደርግ ፡ ነው ፡ ትኵሱን ፡ ሬሳ ፡
ከመቃብሩ ፡ ላይ ፡ በል ፡ እጅህን ፡ አንሣ ፡
ና፡ ወዲህ ፡ ልያዝህ ፡ ከዚህ ፡ ቦታ ፡ ውጣ
ኣሳልፌ ፡ ልስጥህ ፡ በሞት ፡ ለሚቀጣ ።
#ሮሜዎ
አንተ መልካም ወጣት፡ዐርፈህ ሂድ በደኅና
እኔ ፡ ሞገደኛ፡ አጥፊ ፡ ሰው ፡ ነኝና ፡
መዘዜ፡ የበዛ ፡ አሳር ፡ የጐተተኝ፡
ሕይወቴን ፡ የጠላሁ፣ ኑሮ ፡ የታከተኝ፡
ሞትና ፡ መቃብር ፡ ጥፋት ፡ የሸተተኝ ፡
የከፋው ፡ ወንድ ፡ ነኝ ፡ ወደኔ ፡ አትጠጋ ፤ .
ጠብ ፡ አትፈልገኝ' ለሕይወትህ ፡ ሥጋ ።
ቲባልት ፡ እንደዚሁ ፡ ደርሶ : ሳይቸግረው ፡
በመጥፎ፡ ንግግር ፡ ሆዴን ፡ አሳረረው ፡
ሳልፈልግ ፡ ገደልኩት እሱ ባነሣው ፡ ጠብ
አሁን ፡ ደግሞ ፡ አንተ ይብቃህ ፡ አትሳደብ
ነፍሴን ፡ የጠላሁ፡ ሰው ፡ በመሆኔ ፡ ፍራኝ
ሳልወድ ፡ በግዴታ ፡ ዐመፅ ፡ አታሠራኝ ፡
የሚወጣው ፡ ምክር ፡ አሁን ፡ ከመላሴ ፡
አልሠራሁበትም ፡ እኔ ፡ እንኳ ፡ ለራሴ ፡
ስለዚህ ፡ ከራሴ ፡ አብልጬ ፡ ስወድህ ፡
እኔን ፡ አመስግነህ ፡ ይሻላል ፡ መሄድህ ፡
አንድ፡ እብድ ፡ ሰው ዛሬ የሰጠኝን ምክር
ሰምቼ ፡ ድኛለሁ ፡ ብለህ ፡ ይልቅ ፡ ፎክር ።
#ፓሪስ ።
እኔስ ፡ ኣለቅህም ፡ ከያዝኩህ ፡ በኋላ ፤
መስጠት ፡ ትችላለህ ፡ ምክርህን ፡ ለሌላ
#ሮሜዎ
መሞት ፡ ከፈለገህ ፡ እንቢ ፡ ብለህ ፡ በጄ ፡
እንግዲያው ሞክረኝ መልካም፡ነው ወዳጄ
(ይዋጉና'ፓሪስ ፡ ይወድቃል) ።.
ቲባልትና ፣ፓሪስ ፡ እኔን እያስቆጡ ፣
እኔ ፡ ሳልነካቸው ፡ በግድ ፡ እየመጡ፡
በእጄ ፡ እየተወጉ' ክዚህ ፡ ዓለም ፡ ወጡ ።
እንዲህ ፡ መሞታቸው ፡ ተናግረውኝ ፡ ክፉ
ተፈርዶባቸው ፡ ነው ፡ በኔ' እጅ እንዲጠፉ
እንደዚህ ፡ ከሆነ ፡ ፓሪስ ፡ ያንተም ፡ ዕጣ ፡
ጥፋቱ ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ በኔ ፡ እንዳትቈጣ ፡
የዡልዬት ፡ ቁንዥና፡ ደምቆ እንደ ፡ ብርሃን
ጽርሐ አርያም ፡ መስሎ የሰማይ ፡ ውጋጋን
እያንጸባረቀ ፡ ከኮከብ ፡ ሲያበራ ፡
ግርማ፡ተጐናጽፎ፡ በታየበት፡ ስፍራ፡
እንሙት' ወዳጄ ፡ ኣብረን ፡ ከሷ ፡ ጋራ።
(ሮሜዎበዝልዬት፡መቃብር፡ላይየሐዘን ' ንግግር ፡ ያደርጋል)።
ይህችን ፡ ውብ ፡ አበባ ፡ ፍቅር ፡ አሳማሪ ፡
ውሏን ፡ የማትረሳ ፡ ቃል ፡ ኪዳን ፡ አክባሪ ፡
ትወድ ፡ የነበረች ፡ ቁም ፡ ነገር ፡ ጨዋታ፡
እዩልኝ ፡ ከዘመድ ፡ ከሰው ፡ ተለይታ ፡
የኔ ፡ ሆደ፡ ባሻ ፡ ብቻዋን ፡ ተኝታ፡
ተመልከቱት ፡ እጅዋ ፡ ተመልከቱት ፡ ፊቷ ፤
ወዟ ፡ ገና፡ አልጠፋም ። ከሠራ፡ አካላቷ፡
ግንባሯን ፡ ከንፈራን ፡ ተመልከቱ ፡ ጣቷን ፤
ይህን ፡ አበቃቀል ፡ ተክለ ፡ ሰውነቷን ፡
ገላዋ ፡ ያበራል ፡ በደም ፡ ተሸልሞ ፤
ዡልዬት ፡ሞት የነካት፡አትመስልም ፈጽሞ
እባካችሁ ፡ ሰዎች ፡ ሐዘን፡ ተካፈሉኝ፤
ዡልዬት ፡ አልሞተችም ፡ ተኝታለች ፡ በሉኝ
ታውቂ ፡ የነበርሽው ፡ ፍቅራዊ ፡ አቀባበል ፡
ሽቍጥቀጥ ፡እመቤት ባለመልካም ዐመል
ተወዳጁ ፡ ድምፅሽ ፡ ውብ ፡እንደ ፡ ሙዚቃ
በበገናው ፡ ቃሉ ፡ መንፈስ ፡ የሚያነቃ ፡
ዛሬ ፡ ወዴት ፡ ጠፋ? የት ፡ ቦታ ፡ ደረሰ ? .
ደግሞስ ዐይንሽ ፡ ቆቡን ስለ ምን ለበሰ ?
ዡልዩት ፡ ባትሞት ኖሮ፡ በውነት ፡ ባትቀበር
ሮሜዎ ፡ እዚህ ፡ ቆሞ ዝም አትልም ነበር
ባለም ፡ ላይ ፡ ብንሻ ፡ በውነቱ ፡ የት ፡ ኣለ ፡
ጨካኝ አረመኔ ፡ ሞትን ፡ የመሰለ ፡
ጥቂት ፡ አላዘነም ፡ አልሣሣም ፡ ጨርሶ ፡
ይችን ፡ ጽጌ ፡ ረዳ ፡ ሲጥላት ፡ በጥሶ :
ይችን ፡ አሳዛኝ ፡ ልጅ ፡ ትተዋት ፡ ሲሄዱ፡
በሩን ፡ የዘጋ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ቻለ ፡ ሆዱ
እይዋት ይችን ቄንጥ እይዋት ይችን ሎጋ
በባዶ፡ አዳራሽ ፡ በመቃብር ፡ ኣልጋ ፡
ወፍ ፡ በማይዞርበት ፡ ጭር ፡ ባለ ፡ ስፍራ ፡
ብቻዋን ፡ ቀርታለች ፡ አዲሷ ፡ ሙሽራ ።
በመከራ ፡ ቅመም ፡ ባሳር ፡ ተለውሶ :
ዡልዬት፡ ሕይወታችን ፡ መሮን ፡ እንደ ፡ኮሶ
ወጣን ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ያላንድ ፡ ደስታ .
እንግዲህ ፡ እንኑር ፡ እዚህ ፡ በጸጥታ ።
ባለም ፡ ቦታ፡ ጠፍቶ ፡ ለመኖር'ተዋደን ፡
እዚህ ፡ ተገናኘን ፡ ካለም ፡ ላይ ፡ ተሰደን
አይቈጨን እንደዚህ ካለም መውጣታችን
በጣም ፡ ደስ ፡ይበለን ፡ በዛሬው ፡ ዕጣችን
ላለሙ ፡ ደስታ ፡ ለረዥሙም ፡ ዕድሜ ፡
ያው ሞት አይደለም ወይ የሁሉ ፍጻሜ ?
ገላዬን ፡ ከገላሽ ፡ ዐፅምሽን ፡ ካዕፅሜ ፡
ሥጋዬን ፡ ከሥጋሽ ፡ ደምሽን ፡ ከደሜ ፡
ቀላቅሎ ፡ የሚያኖር፡ ከተገኘ ፡ ቦታ ፡
ዡልዬት፡ ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ ምን አለ ፡ ደስታ
ይቅር ፡ ደኅና ፡ ይሁን ፡ ዓለም ፡ ከነቂሙ ፤
እዚህ ፡ እኔና፡ አንቺ ፡ እስከ ፡ ዘላለሙ ፡
መቃብር፡ ሆኖልን ፡ የጸጥታ ፡ ገዳም ፡
ከዛሬ ፡ ጀምሮ ፡ እንኑር ፡ በሰላም ።
ከሚወዱት፡ጋራ፡ እንዲህ ፡ ጐን ፡ ለጐን ፡
ምንኛ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዐፈር ፡ ትቢያ ፡ መሆን ።
(ሮሜዎ ፡ መርዝ ፡ ጠጥቶ ፡ ሞተ ።)
#አባ_ሎራ መብራትና፡ጕጠት፡ ይዞ ፡
ወደ፡መቃብሩ፡ ቦታ፡ መጣ ።
#አባ_ሎራ ።
ስፍራው ፡ አያስኬድም ፡ ሆነና ፡ መቃብር
እያደናቀፈ ፡ ያስቸግራል ፡ ለእግር ፡
አዬ ፡ መከራዬ ፡ በዚሁ ፡ ላይ ፡ ደግሞ ፡
ምንም ፡አይታየኝ ፡ዐይኔ ፡ በጣም ፡ ደክሞ
ማነህ አንተ እዚህ የቆምከው እንደ አጥር ?
#ቤልሻጥር ።
የሚያውቁኝ ፡ወዳጅዎ ፡እኔ፡ ነኝ ቤልሻጥር ።
#አባ_ሎራ ።
እግዚአብሔር ይባርክህ በል ልጄ ንገረኝ ፤
በሩቅ ፡ አላይ ፡ ብሎ ፡ ዐይኔ ፡ አስቸገረኝ፡
እዚያ ፡ በካፑሌ ፡ የመቃብር ፡ ስፍራ ፡
መብራት አይደለም፡ ወይ የማየው ፡ ሲበራ?
#ቤልሻጥር ።
አዎን ፡ ነው ፡ አባቴ ፡ ሄዷል ፡ እዚያ ፡ ቦታ ፡
ወዳጅዎ ፡ ሮሜዎ ፡ የኔ ፡ መልካም ፡ ጌታ
#አባ_ሎራ
ማን ፡ አልከኝ ?
#ቤልሻጥር ።
ሮሜዎ ።
#አባ_ሎራ ።
አዬ ፡ የእግዜር ፡ ቀጣ
ምን ፡ ያኽል ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ እሱ ፡ እዚህ ፡ ከመጣ ?
#ቤልሻጥር ።
ልክ ፡ እኩል ፡ ሰዓት ፡ ነው ።
#አባ_ሎራ ።
ና፡ እንሂድ፡ ወደ ፡ እሱ
#ቤልሻጥር ።
አልችልም ፡ አባቴ ፡ አስጠንቅቆ ፡ ራሱ ፡
ወደ ፡ መቃብሩ፡ እሱ ፡ ወዳለበት ፡
ከቶ ፡ እንዳልጠጋ ፡ ሥራውን ፡ ለማየት ፡
ከልክሎኛልና ፡ በሞት ፡ አስፈራርቶ ፤
ትእዛዙን ፡ ለመጣስ ፡ እኔ ፡አልችልም ፡ ከቶ
#አባ_ሎራ ፡
በል ፡ ተወው፡ ልጄ ፡ ሆይ፡ ሠግቷልና፡ ልቤ
እስቲ ፡ ልመልከተው ፡ ብቻዬን፡ቀርቤ።(አባ፡ሎራሄደ)
#ቤልሻጥር ፡ (ብቻውን ) ።
ዛፍ ፡ ተደገፍኩና ፡ እንቅልፍ ወስዶኝ ፡ ኖሮ
በሕልማ፡ ሮሜዎ ፡ አድርጎ ፡ አምባጓሮ ፡
ውጊያ፡ገጠሙና ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ሲጥል ፡
አየሁ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሲገድል
#አባ_ሎራ ፡(ብቻውን) ።
ይህ ፡ ደም ፡ ከየት ፡ መጣ ? ይህ ሻምላ ፡ ምንድነው?
እዚህ ፡ የወደቀ ፡ ባለቤት ፡ የሌለው ።
(ዡሊዬት ነቃች ፤ አባ ፡ ሎራ፡ ጥግ ፡ ይዞ ፡ ቆመ) ።
#ዡልዬት ።
ሮሜዎ ፍቅሬ ሆይ ማን አምጥቶ ጣለህ ?
ይኸ ፡ ደም ምንድነው ? ፓሪስ ፡ ማ፡ገደለህ ?
ጨርሰው ፡ አይሰሙም ፡ ሞተዋል ፡ እነሱ
ትንፋሽም ፡ የላቸው ፡ አይንቀሳቀሱ ፡
የእንቅልፍ ፡ የመኝታ ፡ የዕረፍት ፡ የጸጥታ :
መሆኑ ፡ ቀረና ፡ ሰላማዊ ፡ ቦታ ፤
ከእንቅልፌ ፡ ስነቃ ፡ አወይ ፡ መቃብሬ ፡
የጦር ፡
👍1
ሜዳ ፡ ሆኖ ፡ ጠብቆኛል ፡ ዛሬ ።
ሮሜዮ፡ ምን ፡ ነካው ? ፓሪስን ማ መታው ?
ይህን ፡ እንቆቅልሽ ፡ማነው ፡ የሚፈታው ?
#ኣባ_ሎራ ።
ይኸውልሽ ፡ ልጄ ፡ እግዜር ፡ አልፈቀደም
እንዳሰብኩት ፡ ሆኖ ፡ ነገሩ ፡ አልሄደም ።
ኣሁንም ፡ ቶሎ ፡ በይ ፡ ውጪ ከዚህ ፡ ቦታ
ሰዎች ፡ መጡ ፡ ከደጅ ይሰማል ፡ ጫጫታ
እንድትገቢ ፡ አድርጌ አንቺን ካንድ ገዳም
እዚያ ፡ ትኖሪያለሽ ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ በሰላም ፡
እባክሽ ቶሎ በይ፡ ሰዎች ወዲህ መጡ፡
#ዡልዬት ።
ከዚህ ፡ እኔ ፡ አልሄድም ፡ እርስዎ ፡ ፈጥነው፡ይውጡ።
(ዡልዬት ፡ ብቻዋን ፡ )፣ ( አባ ' ሎራ' ሄደ)
ደግሞ ፡ ይህ ፡ ኩባያ ፡ እዚህ ፡ ምን ፡ አመጣው ?
ምን ፡ ይሆን ሮሜዎ አግኝቶ የጠጣው ?
አሁን ፡ ገና ፡ ገባኝ ፡ ዐይኔ ፡ ተከፈተ ፤
መርዝ ፡ ጠጥቶ ፡ ነው ፡ ሮሜዎ ፡ የሞተ ።
ጥንቱን ፡ ተፈጥሬ ፡ ለዬዬ ፡ ለለቅሶ ፡
እንዴት ፡ ያለው ፡ ሐዘን ፡ ቈየኝ ፡ ተደግሶ :
እኔ ፡ እሱን ፡ ስጠብቅ ፡ እዚህ ፡ ተቀብሬ ፡
በድን ፡ ሆኜ ፡ ሬሳ ፡ቆየሁ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡
ወይ ፡ አለ ፡ መታደል ፡ መፈጠር፡ ላበሳ ፤
ይኸ ፡ ሁሉ ፡ ድካም ፡ይህ ሁሉ ፡ ግሥገሣ
ለማየት ፡ ኖሯል ፡ ወይ ወድቆ ያንተ ሬሳ፤
ለካ ፡ መልካም ፡ ኖሯል ፡ ብቀር ፡ ሳልነሣ ።
ወደ፡እሱ፡ብመጣ ፡ እኔ አድርጌው ዘመድ፡
እሱስ ቀድሞኝ ሄዷልባላሰብኩት መንገድ
እንዳልቀየመው ፡ የኔ ፡ ከዳተኛ ፡
መጥቶ ፡ ካጠገቤ ፡ እዩት፡እንደ፡ተኛ ።
አወይ ፡ ሮሜዎ ፡ የኔ ፡ ሆደ ፡ ባሻ ፡
አንተ፡ እኔን ፡ ስትፈልግ እኔም አንተን ፡ ስሻ
ብቻህን ፡ ሄደሃል ፡ ሰው ፡ ቀርቶኛል ፡ ሳትል
የጭንቅ ፡ ወዳጅህን ፡ እኔን ፡ ሳታስከትል ፡
አልቀርም ፡ ጠብቀኝ ፡ ባለህበት ፡ ቦታ ፤
ኩባያህ ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ የለውም ፡ ጠብታ ፡
አንተ ፡ ቢስ ፡ ሥሥታም ፡ ንፉግ ፡ መኰንኔ
ጨልጠህ ፡ ጠጣኸው ፡ ሳታስተርፍ ፡ ለኔ
ቆየኝ ፡ ደረስኩብህ ፡ በርሬ፡ እንደ ፡ አሞራ፤
ይኸው ፡መምጣቴ ነው ፡ እኔም ካንተ፡ ጋራ
አልሠራህበትም ፡ አንተ ፡ ባለቤቱ ፡
እስቲ ፡ ልታቀፈው ፡ ይግባ ፡ በስለቱ ፡
አንጀቴ ፡ ለጩቤህ ፡ ይሁነው ፡ አፎቱ ።
(በሮሜዎ ፡ ልቤ ፡ ሆዷን ' ወግታ ፡ ሞተች)
#የመጀመሪያ_ዘበኛ ።
በልምራን ወዴት ነው መንገዱና ስፍራው ?
#የፓሪስ_አሽከር ።
ይኸው እዚህ ነበር መብራት ፡ የሚበራው
#የመጀመሪያ_ዘበኛ ።
ምድሩ ፡ ደም ፡ ብቻ፡ነው፡ምድነው፡ ነገሩ?
እስቲ ፡ ቶሎ ፡ ግቡ ፡ ወደ ፡ መቃብሩ፡
ትልቁ ፡ መኰንን ፡ ፓሪስ ፡ ይኸው ፡ ሞቶ ፡
ቀርቷል ፡ በመሬት ፡ ላይ ፡እዚህ ፡ ተዘርግቶ
ከሁለት ፡ ቀን ፡ በፊት ፡ የቀበሯት፡ ሞታ ፡
ዝልዬትም ፡ ወድቃለች በጨቤ ፡ ተወግታ፡
እዩ ፡ ተመልከቱ ፡ በደም ፡ ተለውሳ ፤
አልብሶት ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ሜዳውን 'ሬሳ ።
ደግሞስ ፡ ሮሜዎ ፡እዚህ ፡ምን አመጣው፤
እሱም ደግሞ ሞቷል ትንፋሽም አይወጣው ።
ቶሎ ፡ ንገሯቸው ፡ መስፍኑ፡ይጠሩ፤
ደግሞም ፡ ግማሻችሁ ፡ ስፍራውን ፡ መርምሩ ፡
ይጠሩ፡ እነ ፡ ሞንታግ ፡ ይምጡ ፡ እነ ፡ ካፑሌ ፤
ፍተሻ ፡ይደረግ ፡ በዚሁ ፡ ቀበሌ ፡
ምስክር ፡ ተገኝቶ ፡ታሪኩ ፡ እስቲሰማ ፡
የተሰወረ፡ ነው፡ ምስጢሩ ፡ ጨለማ ።
💫ይቀጥላል💫
ሮሜዮ፡ ምን ፡ ነካው ? ፓሪስን ማ መታው ?
ይህን ፡ እንቆቅልሽ ፡ማነው ፡ የሚፈታው ?
#ኣባ_ሎራ ።
ይኸውልሽ ፡ ልጄ ፡ እግዜር ፡ አልፈቀደም
እንዳሰብኩት ፡ ሆኖ ፡ ነገሩ ፡ አልሄደም ።
ኣሁንም ፡ ቶሎ ፡ በይ ፡ ውጪ ከዚህ ፡ ቦታ
ሰዎች ፡ መጡ ፡ ከደጅ ይሰማል ፡ ጫጫታ
እንድትገቢ ፡ አድርጌ አንቺን ካንድ ገዳም
እዚያ ፡ ትኖሪያለሽ ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ በሰላም ፡
እባክሽ ቶሎ በይ፡ ሰዎች ወዲህ መጡ፡
#ዡልዬት ።
ከዚህ ፡ እኔ ፡ አልሄድም ፡ እርስዎ ፡ ፈጥነው፡ይውጡ።
(ዡልዬት ፡ ብቻዋን ፡ )፣ ( አባ ' ሎራ' ሄደ)
ደግሞ ፡ ይህ ፡ ኩባያ ፡ እዚህ ፡ ምን ፡ አመጣው ?
ምን ፡ ይሆን ሮሜዎ አግኝቶ የጠጣው ?
አሁን ፡ ገና ፡ ገባኝ ፡ ዐይኔ ፡ ተከፈተ ፤
መርዝ ፡ ጠጥቶ ፡ ነው ፡ ሮሜዎ ፡ የሞተ ።
ጥንቱን ፡ ተፈጥሬ ፡ ለዬዬ ፡ ለለቅሶ ፡
እንዴት ፡ ያለው ፡ ሐዘን ፡ ቈየኝ ፡ ተደግሶ :
እኔ ፡ እሱን ፡ ስጠብቅ ፡ እዚህ ፡ ተቀብሬ ፡
በድን ፡ ሆኜ ፡ ሬሳ ፡ቆየሁ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡
ወይ ፡ አለ ፡ መታደል ፡ መፈጠር፡ ላበሳ ፤
ይኸ ፡ ሁሉ ፡ ድካም ፡ይህ ሁሉ ፡ ግሥገሣ
ለማየት ፡ ኖሯል ፡ ወይ ወድቆ ያንተ ሬሳ፤
ለካ ፡ መልካም ፡ ኖሯል ፡ ብቀር ፡ ሳልነሣ ።
ወደ፡እሱ፡ብመጣ ፡ እኔ አድርጌው ዘመድ፡
እሱስ ቀድሞኝ ሄዷልባላሰብኩት መንገድ
እንዳልቀየመው ፡ የኔ ፡ ከዳተኛ ፡
መጥቶ ፡ ካጠገቤ ፡ እዩት፡እንደ፡ተኛ ።
አወይ ፡ ሮሜዎ ፡ የኔ ፡ ሆደ ፡ ባሻ ፡
አንተ፡ እኔን ፡ ስትፈልግ እኔም አንተን ፡ ስሻ
ብቻህን ፡ ሄደሃል ፡ ሰው ፡ ቀርቶኛል ፡ ሳትል
የጭንቅ ፡ ወዳጅህን ፡ እኔን ፡ ሳታስከትል ፡
አልቀርም ፡ ጠብቀኝ ፡ ባለህበት ፡ ቦታ ፤
ኩባያህ ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ የለውም ፡ ጠብታ ፡
አንተ ፡ ቢስ ፡ ሥሥታም ፡ ንፉግ ፡ መኰንኔ
ጨልጠህ ፡ ጠጣኸው ፡ ሳታስተርፍ ፡ ለኔ
ቆየኝ ፡ ደረስኩብህ ፡ በርሬ፡ እንደ ፡ አሞራ፤
ይኸው ፡መምጣቴ ነው ፡ እኔም ካንተ፡ ጋራ
አልሠራህበትም ፡ አንተ ፡ ባለቤቱ ፡
እስቲ ፡ ልታቀፈው ፡ ይግባ ፡ በስለቱ ፡
አንጀቴ ፡ ለጩቤህ ፡ ይሁነው ፡ አፎቱ ።
(በሮሜዎ ፡ ልቤ ፡ ሆዷን ' ወግታ ፡ ሞተች)
#የመጀመሪያ_ዘበኛ ።
በልምራን ወዴት ነው መንገዱና ስፍራው ?
#የፓሪስ_አሽከር ።
ይኸው እዚህ ነበር መብራት ፡ የሚበራው
#የመጀመሪያ_ዘበኛ ።
ምድሩ ፡ ደም ፡ ብቻ፡ነው፡ምድነው፡ ነገሩ?
እስቲ ፡ ቶሎ ፡ ግቡ ፡ ወደ ፡ መቃብሩ፡
ትልቁ ፡ መኰንን ፡ ፓሪስ ፡ ይኸው ፡ ሞቶ ፡
ቀርቷል ፡ በመሬት ፡ ላይ ፡እዚህ ፡ ተዘርግቶ
ከሁለት ፡ ቀን ፡ በፊት ፡ የቀበሯት፡ ሞታ ፡
ዝልዬትም ፡ ወድቃለች በጨቤ ፡ ተወግታ፡
እዩ ፡ ተመልከቱ ፡ በደም ፡ ተለውሳ ፤
አልብሶት ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ሜዳውን 'ሬሳ ።
ደግሞስ ፡ ሮሜዎ ፡እዚህ ፡ምን አመጣው፤
እሱም ደግሞ ሞቷል ትንፋሽም አይወጣው ።
ቶሎ ፡ ንገሯቸው ፡ መስፍኑ፡ይጠሩ፤
ደግሞም ፡ ግማሻችሁ ፡ ስፍራውን ፡ መርምሩ ፡
ይጠሩ፡ እነ ፡ ሞንታግ ፡ ይምጡ ፡ እነ ፡ ካፑሌ ፤
ፍተሻ ፡ይደረግ ፡ በዚሁ ፡ ቀበሌ ፡
ምስክር ፡ ተገኝቶ ፡ታሪኩ ፡ እስቲሰማ ፡
የተሰወረ፡ ነው፡ ምስጢሩ ፡ ጨለማ ።
💫ይቀጥላል💫