አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እውነቱን_ተናግሮ_አሳደረኝ_ማጣት

“እውነቱን ተናግሮ ፥ የመሸበት ማደር"
እያለ ሲሰብከኝ ፥ የመሸበት ሃገር
ስሰማና ሳምን ፥ ቆይቼ ሰምቼ
በድንገት መሽቶብኝ
አንቺ ጋር ለማደር ፥ ከቤትሽ መጥቼ
እውነቱን ብናገር ፥ ባልሽ ግን ጠመደኝ
እንኳን ሊያሳድረኝ
መዋያ አሳጣኝ ቀን እያሳደደኝ ።
ዳሩ ብሳደድም
እውነት ተናጋሪ
ማደሪያ እንደሚያጣ ፥ ከእንግዲህ አልዘነጋም
እውነቴም አንቺው ነሽ!
ስትሄጂ መሽቷል ፥ ካልመጣሽ አይነጋም።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ሲቀርፁ_መዶልዶም

በጥይት እርሳስ ጫፍ
የተሳተ ስህተት ፥ በላጲስ ባይጠፋም
ቢቀርፁት መዶልዶም
በሆነ የእርሳስ ህግ ፥ ያጥራል እና ተስፋም
ሁለት ምርጫ የለም!
ጨለማ ብርሃኑን
ኑሮኖ አፈሩን ፥ ሰው እኩል አይገፋም፡፡

ዘጠኝ ሞት ቢመጣ ፥ ሰው አንዱን ይመርጣል
ሰው አንድ ሞት ሲመርጥ ፥ስምንት ሞት ያመልጣል
ሁለት ምርጫ የለም
መይ ወድቆ ማንሳት ነው ፥ ወይ ተነስቶ መጣል!

🔘በለይ በቀለ ወያ🔘
#ከእንጃ_ባሻገር

ተራራ የሚያህል ፥ ግዙፍ እምነት አለኝ
ለምንድነው ታዲያ
የሰናፍኝን ቅንጣት ፥ በመግፋት ያልተቻለኝ?
እንጃ!

ክሀሳብ የሰነፉ
ሰፊ መንገድ ኖሮኝ ፊቴ የተሰጣ
ከቶ ለመንድን ነው
ለመሔድ መጋፋው ፥ መርገጫ እስከማጣ ?
እንጃ!

በብርሐን ፍጥነት ፥ መፍጠን የምችል ሰው
ለወንድነው ታዲያ
ቀድሜ ወጥቼ ፥ አርፍጄ ምደርሰው ?
ከቶ ለምንድ ነው
ለጥያቄዬ መልስ ፣ እንጃ የማበዛው?
እንጃ !

ከቶ ለምንድን ነው
ለጥያቄዬ መልስ እንጃ የማበዛው?
እንጃ!

እሺ ለምንድነው ?
ነፃ ያደልኩትን ፣ በውድ የምገዛው ?
እንጃ!
ታድያ ለምን ይሆን
መልስ አልባ ጥያቄ የምፈለፍለው?
እንጃ !
እንጃ!
እንጃ!
ብቻ አንድ እውነት አለኝ እንጃ የማልለው
ከሙሉ ነገር ላይ መጉደል ነው ሚጎድለው።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#የሁለት_ጽንፍ_ዓለም

እጅግ ያስገርማል
የዓለም ልዩነት
አንደኛው በሃብቱ
አንዱ በድህነት
አንደኛው በህመም
አንዱ በጤንነት
አንደኛው በበጎ
አንደኛው በክፋት
አንደኛው ለመኖር
አንደኛው ለመጥፋት
ግን ለምን ተፈጠረች
ዓለም ሆና ሁለት ?

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#ድል

መብትና ነጻነት
ክብርና ማንነት
የነሱ የሆነውን የሚሹ ለማግኘት
ሲገፉ ሲረገጡ
ቁብ እንኳ ሳይሰጡ
መቻል አጠንክሮ .
ጫንቃቸው ካበጡ
ታግለው የደከሙ
ጮኸው ሰሚ ያጡ
ግዜው ምን ቢነጉድ
ቢመሻሽ ሲጨልም
ከድል ደጃፍ ደርሰው
መንጋቱ አይቀርም፡፡
#የቀበቶ_ቅኔ

እንደ ብዙ ወንደች
ከብዙ ሴቶች ጋር ፥ ለዝሙት ተኝቶ
እንዲ እርኩ ማለት
ጀብዱ የሚመስለኝ ፥ እንጎለ ቀበቶ
ለስሜቴ ሳድር ፥ ነፍሴን አዝረክርኬ
ከቀበቶዬ ላይ
ተፅፎ አየሁት ፥ የህይወት ታሪክ።

እዩት ቀበቶዬን
በሴቶች ምሳሌ ፥ ቀዳዳ ተከቦ
እኔ ማለት ያ ነኝ
በቀዳዶች ውስጥ
ገብቶ የሚወጣ ; የቀበቶው ሽቦ፡፡
የማሰቤ ወገብ ፥ ሲቀጥን ሲወፍር
ካንዷ ቀዳዳ ጎን ፥ አንዷን የምቀይር፡፡
የማሰቤ ወገብ ፥ ሲከሳ ሲሰባ
ቀዳዶቹን ትቼ
ሌላ አዲስ ቀዳዳ ፥ ፈልጌ ምገባ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘

(መነሻ ሀሳብ ገጣሚ ደስታ ነጋሽ)
#ይህችን_አታሳጣኝ

የአዳም ዘር በሞላ ታድሞ ከእልፍኝ
ባለው ላይ ሲያተርፍ ካለው እጥፍ ሲመኝ
ከማዶ ሲያማትር አርቆ ከራሱ
ለልጅ ልጅ ሲለፋ ጠግባ አንድ ነፍሱ
ግራ ቀኝ ብፈልግ ውስጤ ፈጥሮ ቅናት
ሀበሻ ወገኔም ካፉ ሲል በአይኔ ልመለከት
መአዱን ሊቋደስ ተራው ከመድረሱ
እፍኝ ቆንጠር አርጎ ባዶ ሆኖ ኪሱ
ሊያመስግን'ሮጠ ሊቆም ከመቅደሱ።

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#ስደት

ቁጥብ ነው
ጭምት ነው
ገራገርም ፍጡር
ግራው ሲነካካ
ቀኙን የሚጨምር
አሳ በመሬት ላይ
አንበሳ በባህር
ዶክተሩ ቢያርስና
ገበሬው ቢቀምር
አይሆንም ግር ይላል
ሊያውም ያደናግር
የሰው ልጅ በሜዳ
በባይተዋር ምድር፡፡

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#አረፍተ_ሀገር

“አበበ” ምንለው ፥ በሶ የሚበላ
ጩቤ እንደጨበጠ ፥ ለምናውቀው ጫላ
ጣሳ እያጠበ ፥ ለሚኖር ጨቡዴ
ሀገርሽ ሀገሬ
አረፍተ ነገርን ፥ ትመስላለች ውዴ።
*
ስልኬ አበበ ነው
በሶ ደሞ ካርዴ ፥ ስትገባኝ ሀገሬ
“ቴሌ ካርድ በላ።”
የሚል ትርጉም አለው ፣ አረፍተ ነገሬ።
*

ጫላ ባለ ስልጣን ፥ ስልጣን ደሞ ጩቤ
የጨበጡት ሁሉ
ሲያቆስሉት የኖሩ ፥ ስጋዬን ከልቤ።
***
ጨቡዴ ሙስና ፥ ጣሳ ደሞ ህዝቡ
እርቃን የሚያስቀሩት
በየ መሥሪያ ቤቱ ፥ ኪሱን እያሰቡ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ማረን_ጌታ

ቅዳሜ ማታ አድረን ማሪንጌቻ
እሁድ ሲነጋጋ ማረን መሰረነሰ ጌታ
እያልነው በቅጥፈት እያልነው በድፍረት
በየት ያርግ መባ በየትይውረድ ምህረት

🔘ኢዛና መስፍን🔘
#እስኪነጋ_ድረስ

ቁርጡን ያወቀ ሰው
መች ያምረዋል ስጋ፣
ያቅልለት እንጅ
የጎመኑን ዋጋ፣
የጨለመው ቀኑ
ቦግ ብሎ እስኪበራ፣
ሀብታም ይቁምበት
የፍየልን ተራ።
#ለመንጋዎች_መንጋ_ግጥም

እኔ ሰው ስለሆንኩ
የግል አእምሮዬን ፥ አሳልፌ አልሰጥም
በመንጋ አስተሳሰብ ፥ ሀሳቤ አይዋጥም
ለመንጋዎችና
ለመንጋ አሳቢዎች ፥ አለኝ መንጋ ግጥም።

#መንጋ_1
ብዙዎች ተስማምተው
በሔዱበት መንገድ
ትክክል ነው ብሎ ፥ አይነሳም እግሬ
ብዙዎች በህብረት
በጠሉት ነገር ላይ ፥ አይቀንስም ፍቅሬ
አመዛዝናለሁ
አስተሳስራለሁ
የግል አእምሮዬን ፥ ከደም ዝውውሬ።
ብዙዎች ሚወዱት
በጥላቻዬ ላይ ፥ ለውጥ አያመጡም
መንጋ አእምሮዎች
ሀሳብን አይወልዱም ፥ በግል አያምጡም
አንዱ የወለደውን
ይዘው ይጮሀሉ ፥ አይደማመጡም።

#መንጋ_2
መንጋ አሳቢዎች
በምላስ ነው እንጂ ፥ በአእምሮ አይቆሙም
ከእረኛቸው እንጂ
በራሳቸው መንገድ ፥ በድፍረት አይተሙም
በቀቀኖች ናቸው ፥ የገደል ማሚቶ
ተቀብሎ መጮህ
ያውቃል ምላሳቸው ፥ አእምሯቸው ሞቶ።

#መንጋ_3
አብሮ መኖር እንጂ
አብሮ ማሰብ ማላው ፥ ሀሳብን አውጠንጣኝ
አእምሮ የቸረኝ ፥ በምላስ ያልቀጣኝ
ፈጣሪ ይመሥገን!
ከባርነት በፊት
ከመንጋ አስተሳሰብ ፥ ነፃ ስላወጣኝ !!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#የተገላቢጦሽ

እህሉን ስናገኝ
ወፍጫችን ደነዘ፣
አልፈጭልን ብሎ
ለግሞ እየፈዘዘ፣
ሌላ ግዜ ደግሞ
አጣንለት መላ፣
እህሉን ስናጣ
ወፍጮው እየሰላ !!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
#የቅርብ_ሩቅ

ፈጣሪን ፍለጋ፤
ስንል ቆላ ደጋ!
ከደብሮች ደብር፤
አሰሳ ስንዳክር!
ሆኖልን ቅንነት፥ የዋህነት ፍቅር፤
እሩቅ የመሰለን
ተቀምጦ ተገኘ ፥ከልቦናችን ስር!

🔘አብርሃም ፍቅሬ🔘
#ለራስ_ነፍስ_ወቀሳ

ለራስ ነፍስ ወቀሳ፣
ላጠራቅም እድሜ፣
በራፌን ከርችሜ፣
መስኮቴ ላይ ቆሜ፣
አልድንአልድን
ወይ
አላድን፣
በድን!

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘
#ማረን_ጌታ

ቅዳሜ ማታ አድረን ማሪንጌቻ
እሁድ ሲነጋጋ ማረን ማረን ጌታ
እያልነው በቅጥፈት እያልነው በድፍረት
በየት ያድርግ መባ በየት ይውረድ ምህረት።

🔘ኢዛብ መስፍን🔘
👍1
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_አንድ


#በክፍለማርያም

መስከረም መጀመሪያ ላይ ነው
ፍፁም ይባላል ወጣት ነዉ ለማስተማር ከተቀጠረበት ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ሊደርስ ጥቂት እርምጃወች ሲቀሩት ወደ ትምህርት ቤቱ የሚገቡ ተማሪዎች ብዛት እና ጫጫታ ለአፍታ አስቆመው።

የመጀመሪያ ቅጥሩ እንደመሆኑ ትንሽ ልቡ የተረበሸ ይመስላል።
''ይቅርታ ሰአትክ ይሰራል?''
አንዲት ዩኒፎርም የለበሰች የደስደስ ያላት ልጅ እጁ ላይ የታሰረዉን ሰአት በአይንዋ እየቃኘች ጠየቀችዉ።
''ሁለት ሰአት''አፉ እየተሳሰረ መለሰላት
''አናቱ ላይ?''
አዎ ለማለት ግንባሩን ከላይ ወደ ታች ሲነቀንቅ
ልጅቷ ''አፍክ አይሰራም!!''እያለች ቆመው ወደ ሚጠብቁዋት
ጉዋደኞችዋ እሮጠች።
እየተገረመ በልቡ"አስተማሪ አልመሰልኳትም" እያለ
መራመዱን ቀጠለ።
ወደ በሩ እየገባ አሁንም ሌላ ልጅ እየሮጠች መጥታ
''ጉዋደኛዬ ካስቀየመችህ ይቅርታ ትንሽ ወሰድ መለስ ስለሚያረጋት ነዉ''
ሌባ ጣትዋን ከአይንዋ አጠገብ ካለው ራስ ቅል
ዙርያ እያሽከረከረች አሳየችዉ
''ምንም አደል''እያለ ጥሏት ወደ ዉስጥ ዘለቀ።
ከመምህራን ማረፍያ ገብቶ የያዘውን ቦርሳ እቃ ማስቀመጫ
ዉስጥ ከቶ ከሌሎች መምህራን ጋር መተዋወቅ ጀመረ ትውውቁን
እንደጨረሰ ከመምህራን ሀላፊዉ ጋር የየእለት አለት የማስተማርያ
መመርያ ለመቀበል ወደ ሀላፊዉ በር ተጠግቶ አንኩዋኩዋ፡፡

''ይግቡ!"
ከዉስጥ ወደ ዉጪ በሰማው ድምፅ መሰረት በሩን ከፍቶ ገባ፡፡

ቢሮዉ ውስጥ ሌላ አንድ መምህር እና ሀላፊዉ
ተቀምጠዋል አስተማሪዉ
''ፍቃዱ እባላለሁ አማርኛ አስተማሪ ነኝ"
ከወንበሩ እንደመነሳት እያለ እጁን ዘረጋለት
"ፍፁም ሂስትሪ መምህር "ሰላም ተባባሉ
የመምህራን ሀላፊዉም
"አረፍ በል ልጅ ፍፁም ከኔ ጋር በቀደም ተዋዉቀናል...ይሄ
ወረቀት ያንተን የማስተማርያ ሰአት እና የምታስተምራቸውን
ክፍሎች የያዘ ነዉ ሌላ የምትጠይቀዉ ነገር ከሌለ
ጨርሰሀል..መልካሙን አመኝልሀለው::"
ከመምህር ፍቃዱ ጋር አንዳንድ ነገር እያወሩ በዛውም
ግቢዉን እና ክፍሎቹን እያስጎበኘዉ ወደ መጀመርያ ትምህርት
ወደ ሚሰጥበት ክፍል ሲደርሱ ቡሀላ ለመገናኘት ተቀጣጥረውተለያዩ፡፡
ወደ ክፍሉ ውስጥ ገብቶ መሀል ላይ ቆመ
በእርስ በእርስ ወሬ ደፍርሶ የነበረው
ክፍል ፀጥ ረጭ አለ ተማሪወቹ በሙሉ አይናቸዉን ተከሉበት
ላለመደናገጥ ልቡን አያደፋፈረ
"ፍፁም ደምሴ እባላለሁ ሂስትሪ ነው
የማስተምራችሁ እንደመጀመራችን ለመተዋወቅ እንዲረዳን
እናንተም በየተራ ስማችሁን ታስተዋዉቁኛላችሁ"
ሁሉም እየተነሳ ስሙን ለፈፁም ማስተዋወቅ ጀመረ
ተራዋ ደርሶ አንዷ
"ቤዛ"አለች ከወንበርዋ ተነስታ
ፍፁም እንዳያያት አንገትዋን ደፍታ
"እንደሌሎቹ ሙሉ ስምሽን ብትነግሪን?"
"ቤዛዊት መለሰ"ቀና ስትል ፊትዋን ለማየት ቻለ
የደሰደስ ያላት ቆንጇ ልጅ ናት ልቡ መምታት ጀመረች
"ከዚህ በፊት አዉቃታለሁ....?እራሱን ጠየቀ
ብዙ ለማሰብ ሞከረ ሲያስታዉስ
ጠዋት ሰአት ጠይቃ የሰደበችዉ ልጅ ናት፡፡

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍5
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በክፍለማርያም መስከረም መጀመሪያ ላይ ነው ፍፁም ይባላል ወጣት ነዉ ለማስተማር ከተቀጠረበት ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ሊደርስ ጥቂት እርምጃወች ሲቀሩት ወደ ትምህርት ቤቱ የሚገቡ ተማሪዎች ብዛት እና ጫጫታ ለአፍታ አስቆመው። የመጀመሪያ ቅጥሩ እንደመሆኑ ትንሽ ልቡ የተረበሸ ይመስላል። ''ይቅርታ ሰአትክ ይሰራል?'' አንዲት ዩኒፎርም የለበሰች የደስደስ…»
አህያ ሁን አለኝ አህያ ሆንኩለት
አሰሱን ገሰሱን እንድሸከምለት
ውሻዬም ሁን ብሎ ሆንኩኝ ላስደስተው
ጭራ እየቆላሁኝ እንዳጨዋውተው
ፈረሴም ሁን ብሎ ፈረሱ አደረገኝ
በየዳገቱ ነው ወስዶ እሚጋልበኝ
እንጃ ግን ሰሞኑን “በግ ነህ” ተብያለሁ
ሊያርደኝ ነው መሠለኝ አሁን ፈርቻለሁ

ተጻፈ፡- ፲፰/፯/፳፻፭ ምሸት ፲፡፳

ከጽሞናና ጩህት የግጥም መድብል
#አቤት_እኔ!

አቤት!
የጎጆዬ ወና - ቅርናቱ!
የነፍሴ ሽንቁር - ስፋቱ!

አቤት!
የአባትነቴ - እጥረቱ!
የአፍቃሪነቴ -ስስቱ!
የዜግነቴ - እጦቱ።

አቤት እኔ!
ከህሊናዬ ጋር ልኖር፣
ያለ እረፍት እንደተዋጋሁ፤
ስንቱ ደዌ ለከፈኝ፣
ስንቴ ሞቼ ተነሳሁ፤
ስንቱ ስሞ ነከሰኝ፣
ስንቱን ካጠገቤ አጣሁ።
አቤትትትት.. . !!

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘
👍1