አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ከአስር ቀን በኃላ ያሉት ባለስልጣን ከሳምንት በኃላ ደወሉለት..አልጠበቀው ነበር፡፡‹‹ሚካኤል አንድ ጥሩ ዜና አለኝ››

‹‹ምንድነው ጌታዬ?››በጉጉት ጠየቀ፡፡

‹‹ነገ ሰባት ሰዓት ላይ አባትህን እንድታገኝ  ከእስርቤቱ አስተዳዳሪ ፍቃድ አግንቼልሀለው፡፡››

‹‹በእውነት በጣም ነው የማመሰግነው›..እግዜር ይስጥልኝ››

‹‹አዎ በሰአቱ ሂድና…ቀጥታ አሁን በምልክልህ ስልክ እዛ እንደደረስ ደውልለት… አስተዳዳሪው ራሱ ይቀበልህና ሚሆነውን ያደርጋል….ሌሎች ነገሮችን እየሰራሁባቸው ነው….እስከዛው በዚህ ተፅናና…››

‹‹እሺ ጌታ ..በጣም ነው የማመሰግነው››

ስልኩን ዘጋና በደስታ ዘለለ…ልጇን እያጠባች ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው አዲስአለም ..‹‹ምን ተገኘ..ሎቶሪ ወጣልህ እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹በይው…ነገ አባዬን እንድጠይቀው ተፈቀደልኝ››

‹‹በእውነት..በጣም ደስ ይላል››

‹‹አዎ….ምንድነው ይዤለት የምሄደው…..?››ሲል ከፈንጠዝያው ሳይወጣ ጠየቀ፡፡

‹‹አንተ ምን አልባት ቅያሪ ልብስ የላቸውም ይሆናል..ልብስ ምናም አዘጋጅ..እኔ ደግሞ የሚበላ ነገር አዘጋጃለው፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ ..የእኔ ማር በጣም ደስ ብሎኛል….››

‹‹ደስ ይላል..ግን ያው አባትህ እስር ቤት ከገቡ ጀምሮ ልትጠይቃቸው በሄድክ ቁጥር በምን አይነት አቀባበል እንደሚቀበሉህ ታውቃለህ…እንዲህ በመፈንጠዝ ሄደህ በኃላ አላናገረኝም….መጥተህ አትጠይቀኝ አለኝ…ምናምን ብለህ እንዳትበሳጭ››ስትል ስጋቷን ገለፀችለት፡፡

‹‹አረ…የፈለገ ይበል እኔ አይኑን ማየት ብቻ ነው የምፈልገው….ከፈለገ ለምን  ልትጠይቀኝ መጣህ ብሎ በቡጢ  አይነርተኝም ..ግድ አይሰጠኝም››

አሳዘናት…‹‹ሁሉም ሰው ምናለ እንዳአንተ ሰው ወዳጅና ሌላውን የሚረዳ ቢሆን››ስትል በውስጦ አሰበች‹አይ እንደዛ ከተዘጋጀህ ጥሩ››አለችው፡፡

‹‹በቃ ወጣው ….በዛው ለአባዬ የሚሆን ልብስ ገዛዛለሁ››ብሎ ሚስቱን ጉንጯን ልጁን ግንባሩን ሳመና ወጥቶ ሄደ፡፡

ሚካኤል ለአባቱ ልብስና የሚበሉ የተለያዩ ትኩስ  ምግቦችን ተሸክሞ ልክ በተባለው ሰዓት ወህኒ ቤት ጊቢ ደርሶ ስልኩን ደወለ፡፡

‹‹ሄሎ ኩማንደር …ሚካኤል ነኝ…ቀጠሮ ነበረኝ፡፡››

‹‹እ ሚካኤል ….ጥበቃ ላይ ካሉት ፖሊሶች አስርሀለቃ ላቀው በልና ንገረው …ነግሪዋለው ወደእኔ ይዞህ ይመጣል፡፡››የሚል አስደሳች መልስ አገኘ፡፡

‹‹እሺ ኩማንደር አመሰግናለው››
ስልኩን ዘጋና ፊት ለፊቱ ያለውን ፖሊስ ‹አስር ሀለቃ ላቀውን› እንዲያሳየው ጠየቀው….እዛው በቅርብ የነበረ ፖሊስ ጠቆመው፡፡ማንነቱን ለፖሊሱ ነገረና ..ለአባቱ ይዞ የመጣውን እቃ እንዲያስረክ ካደረገ በኃላ ቀጥታ ወደኮማንደር ቢሮ ይዞት ሄዳ፡፡ፖሊሱ ክፉሉን ቆርቆሮ ከፍቶ አስገባውና መልሶ ሄደ፡፡

ሲገባ  የገጠመው ግዙፍና ግርማ ሞገስ ያለው ቢሮ ነው፡፡እዚህ ቀፋፊ ወህኒ ቤት ውስጥ እንዲህ አይነት የሚያምር ቢሮ ይኖራል ብሎ ገምቶ አያውቅም፡፡ፀጉራቸው ሙሉ በሙሉ ቀለሙን ቀይሮ ነጭ የሆነው   ግዙፉ ጠይም ቆፍታምና ሰው ከግዙፉ ጠረጴዛ ኃላ ባለ የቆዳ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጠው ይታያሉ….በጎርናና እና ሻካራ ድምጻቸው ‹‹ግባ አቶ ሚካኤል…..››አሉት

ሄደና ወደእሳቸው ቀርቦ ለሰላምታ እጁን ዘረጋላቸው…በመጠኑ ከመቀመጫቸው እንደመነሳት አሉና እጃቸውን ዘርግተው ጨበጡትና‹‹ተቀመጥ አቶ ሚካኤል›

እሺ ብሎ አንዱን ወንበር ሳበና ተቀመጠ‹‹ኩማንደር ስለአስቸገርኩት ይቅርታ….ያው የቤተሰብ ጉዳይ  ስለሆነብኝ ነው››ሲል  ተናገረ፡፡

‹‹ይገባኛል…እንደውም ጥሩ ልጅ ስለሆንክ መመስገን አለብህ…መቼስ ማረሚያ ቤታችን በአባትህ ላይ የወሰደው አቋም ለምን እንደሆነ ይገባሀል አይደል?አዎ ይገባሀል እንጂ …በእኛ ልትበሳጭ ፍፅም አትችልም፡፡››

‹‹አዎ በትክክል ይገባኛል….››ሲል በአጭሩ መለሰ፡፡

‹‹አሁን ያው ከአንተ ጋር እየተነጋገርን ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን ሁኔታዎችን ለማስተካከል እንሞክራለን….ዋናው አንተ አባትህንን  ምን ያህል ?ማገዝ ትፈልገለህ የሚለው ነው››አሉና ፈገግ ብለው በሲጋራ የበለዘ ጥርሳቸውን አሳዩት፡፡

‹‹ኮማንደር አባቴ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት መሞቻ ቀኑን የሚጠብቅ ሰው ነው…እና ያ ቀን አስኪደርስ ድረስ  በተቻለ መጠን በተመቻቸ ሁኔታ እንዲያሳልፍ ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ ነኝ፡፡አባቴ ይሄንን ቀፋፊ ወንጀል ሰርቶ ወህኒ ቤት ከመግቱ በፊት ለቤተቡ አይደለም ቸገረኝ ላለ ሰው ሁሉ ልብ የሚያዝንና እጁ የሚፈታ መልካምና የተከበረ ሰው ነበር…..ምንም ሆነ ምንም ፍፃሚዊ እንዲህ አሳዛኝ መሆን የለበትም፡፡

‹‹ጥሩ እንደዛ ከሆነ ማድረግ ይምንችለውን ሁሉ እናያለን፡፡››አሉን ወደፊት ተንጠራርተው መጥሪያውን ተጫኑ..አንድ ፖሊስ መጣና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠ…‹‹ሳጂን  ታራሚ ቅጣውን እዚህ አስመጣልን››ሲሉ ትዕዛዝ ሰጡ
ፖሊሱ ትዕዛዙን ተቀበለና ተመልሶ ወጥቶ ሄደ….ከ5 ደቂቃ በኃላ እስከአሁን ያለሳተዋለው በኩማንደሩ መቀመጫ በቀኝ በኩል የምትገኝ ጠበብ የጀርባ በራፍ ተቆረቀረ…ኮማንደሩ ዝርጥት ሰውነታቸው እየከበዳቸው በመከራ  ተነሱና በራፉ ከውስጥ ከፍተው ወደመቀመጫቸው ተመለሱ፡፡ አይኖቹን የተከፈተው በራፍ ላይ እንደተከለ መጠበቅ ጀመረ…ሰው ከማየቱበፊት ብረት ቅጭልጭልታ በጇሮው ሞላ..…ከዛ በተቀመጠበት ደንዝዞ ቀረ..አባቱን ከስድስት ወራት በፊት ነው ያየው…ሰው በስድስት ወር በዚህ መጠና ሊቀየር እንደሚችል ግምቱ የለውም ፡ፀጉሩ ተንጨፍርሮ ተንጨፍርሮ ጉድሮ ሆኖ ግንባሩ ላይ ተደፍቷል…ፂሙ አድጎ ግማሽ ፊቱን ሸፍኖት ያረጀ አንበሳ አስመስሎታል…ከመክሳቱ የተነሳ ሁለቱ ጉንጮቹ አንድ ላይ የተጣበቁ ይመስላል፡፡አይኖቹ ጥልቅ ጉድጓዱ ውስጥ ያሉ ደማቅ አንፖሎች ነው የሚመስሉት…ሚካኤል እንባው ዝርግፍ አለ..ኮማደሩ ከተቀመጡበት ተነሱና ..ለብቻችሁ ጊዜ ልስጣችሁ..አንድሰዓት አላችሁ……በፊት ለፊተኛው በራፍ   ክፉሉን ለቀውላቸው  ወጡና  ከውጭ ቀርቅረውባቸው ብቻቸውን ተዋቸው…
እንደምንም እራሱን አበረታቶ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደአባቱ ሄደ…ልጅ እያለ ባለግርማ ሞገሳሙ አባቱ  ወደ ቤት መምጣቱን የሚያውቀው የመኪናውን ክላክስ ሲሰማ ነበር..ካዛ ከወንድሙ ጋር ሮጠው ከቤት ይወጡና  ወደእሱ ይንደረደራሉ…ከዛ ለልጆቹ የገዛላቸውን ፍራፍሬ ወይም ሌሎች ጣፍጭ  ነገሮች የያዘ ፔስታል ይዞ ከመኪናው ሲወርድ እሱን ጨምሮ ሶስቱም ልጆቹ በሽሚያ አንዱ ቀኝ እግሩን ሌላው ግራ እሩን ያቅፍትና በልዩ ፈንጠዝያ ይቀበሉታል…እሱም ስራቸው ይንበረከክና አንዱን ጉንጩን ሌላዋን ግንባሩን እያሳመና እየዳበሰ ይዞቸው ወደቤት ይገባል…አባትዬው ለልጆቹ እንስፍስፍ የሚባል አባት ነበር..በተለይ  ዬቱ ታላቅ የሆነችውን ሴት ልጁን በልዩነት ንው የሚወዳት…እሷም በአባቷ በምንም አይነት ሁኔታ የማትደራደር  የእሱ ተመራጭ ልጅ ነበረች…እና እንደዛ ኩሩና ሽቅርቅር የነበረው አባቱ አሁን አፅሙ ብቻ ነው ያለው..ሄዶ በፍራቻ ተጠመጠመበት.. ጠረኑ ወደኃላ ይገፋተራል…አባትዬው ምንም አይነት ምላሽ አላሳየውም..እየጎተተ ወደወንበሮቹ ወሰደውና አስቀመጠውና ከፊት ለፊቱ ተቀመጠ፡፡

‹‹አባዬ እንዴት ነህ?››

ለእሱ መልስ ከመስጠት ይልቅ ‹‹ለምን እንደዚህ አደረክ?››ሲል አንቧረቀበት፡፡

‹‹ማለት? ምን አደረኩ?››ምን ስህተት እንደሰራ ባለማወቅ በፍራቻ ጠየቀ፡፡

‹‹ለምን አገኘኸኝ..?እንዴት እንደተቀጣሁና ምን አይነት ቀፋፊ አውሬ እንደሆንኩ ለማየት ነው የመጣኸው?››
👍5512👏1
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////
ሚካኤል ከወህኒ ቤት እንደመጣ ቀጥታ ወደሰፈር ነው ያመራው፡፡ወደቤት ሲገባ አዲስ አለም ከልጇ ጋር እየተዳረቀች ሳሎን ውስጥ ቢያገኛትም ማንኛቸውንም ምንም ሳያናግር ቀጥታ ወደመኝታ ቤት ነበር የተንደረደረው፡፡

‹‹ሚኪ…ምን ሆነሀል.?.ዛሬ ደግሞ ሰላምታ የለም እንዴ?››

‹‹መጣሁ..››ብሎ ብቻ  ወደመኝታ ቤት ገባ…አባቱ የነገሩትን ፎቶ ከግድግዳ ላይ አነሳ ..ከግድግዳው ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ነው…በቀላሉ በእጅ የሚፈረከስ አይነት አይደለም…ከእንደገና ተነደርድሮ ወጣና በጓሮ በኩል ወደ ገራጅ በመሄድ መዶሻ እና መሮ  ይዞ መጣ….‹‹አዲስ አለም ቅዱስን ከወለሉ ላይ አንስታ አቀፈችውና ወደመኝታ ቤቱ ተንቀሳቀሰች…እሷ ከመድረሷ በፊት ሚካኤል ወደውስጥ ገብቶ ከውስጥ ዘጋባት

‹‹እንዴ ሚኪ….ምን እየሆንክ ነው…?ለምንድነው የምትዘጋብን?››

‹‹አዲስ..እባክሽ ጥቂት ደቂቃዎችን ስጪኝ……››ብሎ መሮውንና መዶሻውን በመጠቀም  ግድግዳውን መቆርቆር ጀመረ…ግድግዳ ውስጥ የተቀመጠውን የአባቱን ሚስጥራዊ እቃ ለማግኘት 3 ደቃቃ ያህል ፈጀበት…በላስቲክ በስነሰርአት የተጠቀለለ ነው፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠና የላስቲኩን እሽግ ፈቶ አልጋው ላይ ዘረገፈው፡፡….አምስት የሚሆኑ ፎቶዎች አንድ ሜሞሪ ካርድ  ..አንድ ደብዳቤ ነው፡፡፡

መጀመሪያ ፎቶዎቹን አነሳና ተራ በተራ መመልከት ጀመረ…የመጀመሪያው ፎቶ ላይ  አናትዬው የሆነ ሰው ክንድ ላይ ተደግፋ በፈገግታ ስትፍለቀለቅ ይታያል..ጭንቅላቱን የሆነ መርፌ ነገር ጠቅ አደረገው….ይሄ ሰው በህይወት ዘመኑ አይቶት አያውቅም…የእናቱን ዘመዶች ሁሉንም ያውቃል…ታዲያ ይሄ ማን ነው?፡፡ሁለተኛውን ፎቶ  ገለጠና ተመለከተ…እናትዬው እነሱን ከመውለዷ በፊት ገና ጨቅላ ወጣት ሆና የተነሳቸው ፎቶ ነው..ግን አሁንም ያው ሰው አንገቷ ላይ ተጠምጥሞ በፍቅር ጉንጯን ሲስማት ይታያል…ፎቶውን ገለበጠው…ልቅም ባለ የእጅ ፅሁፍ በአንድ መስመር የተፃፈ ፅሁፍ አለ ‹‹ንጥፍ ወርቅ ፍቅሬ በጣም አፈቅርሻለው….ያንቺው ለሚ በቀለ፡፡››ይላል፡፡
ሁሉንም ፎቶዎች በየተራ እየገለባበጠ ተመለከተው…ተመሳሳይ የሁለቱ ፎቶ ነው…ሲላፉ ሲሳሳሙ….ሲጎራረሱ የተነሱት ፎቶ ነው፡፡
ቤታቸው የወላጆቻቸውን ትዝታ የሚዘክሩ ሁለት ግዙፍ የፎቶ አልበሞች እዳሉ ያውቃል….እናትና እህቱ በአሰቃቂ ሁኔታ ከሞቱ በኃላ በጣም ሲከፋውና ትዝ ሲሉት ለብቻው ክፍል ዘግቶ ተደብቆ  ይመለከት ነበር፡፡እና እዛ አልበም ውሰጥ ዘጠና ፐርሰንት ፎቶ የእሱና የእህትና ወንድሙ ፎቶዎች ፤የበዓል ዝግጅት ፤ የህፃናቱ የልደት በዓል ማስታወሻ ናቸው የሞሉት..እናትና አባቱ በልጆቹ የደስታ ድባብ ውስጥ እንደድምቀት እዚህም እዛም ጣል ተደርገው የተነሱት ነው እንጂ እንዲህ እናቱ ከሌላው ሰውዬ ጋር እንዳደረገችው አይነት አማላይ ፎቶዎች ተነስተው አላየም፡፡

ፎቶውን አስቀመጠና ወረቀቱን አንስቶ አነበበው…
ይድረስ ለምወድሽ ፍቅሬ ንጥፍ ወርቅ …
ይህንን ደብዳቤ ስፅፍልሽ ከአይኖቼ እንባ ሳይሆን ደም እያፈሰስኩ ነው፡፡  ታውቂያለሽ እኔ ከኤለመንተሪ ጀምሮ በጣም ነው የማፈቅርሽ..አንቺም እንደምታፈቅሪኝ አውቃለው፡፡ብዙ አቅድና ብዙ ፕሮግራም ነበረን፡፡በቅርብም ለመጋባት ተነጋግረንና ተማምለን ነበር፡፡አሁን ግን ያንን ቃሌን ማክበር አልችልም፡፡አባዬ ምን ያህል ኃይለኛ እና ጥብቅ ሰው እንደሆነ ታውቂያለሽ  ..አሁን አሜሪካ ካለው ወንድሙ ጋር ተነጋግሮ አሜሪካ እንድሄድ ወስኖ ሁሉም ፕሮሰሶች ጨርሶ ሊልከኛ ነው…ማለቴ… አሁን ይሄ ደብዳቤ ሲደርስሽ ምን አልባት እኔ በርሬም ሊሆን ይችላል፡፡

ይቅር በይኛ…..ያንቺው  ለሚ በቀለ፡፡ይላል
እዛ ደብዳቤ ላይ ብዙ የተንጠባጠቡ የእንባ ጠብታዎች ይታያሉ፡፡ሚካኤል ያየውም ሆነ ያነበበው ነገር  ምንም እየገባው አይደለም..ከውጭ ደግሞ አዲስአለም የመኝታ ቤቱን በራፍ እየቆረቆረች እየረበሸችው ነው፡፡ከተቀመጠበት ተነሳና ሄዶ በራፉን ከፈተ፡፡ በራፉ ላይ ልጇን አቅፋ ተገተትራ በድንጋጤ በድን የሆነችውን አዲስ አለም ላይ አፈጠጠባት፡፡

‹‹አዲስ ምንድነው?››

‹‹እንዴት መኝታ ቤቱን በላይህ ላይ ዘግተህ ምን እያደረክ ነው?››በስጋትና በፍራቻ ተወጥራ ጠየቀችው፡፡

‹‹ኡፍ …ስራ ይዣለሁ ስልሽ አትሰሚም…..ባክሽ አትረብሺኝ››በማለት አንቧረቀና መልሶ ዘጋባት፡፡ከዛ  ወደአልጋው ተመለሰ፡፡አዲስአለም በመጀመሪያ ከደነገጠችውን  በላይ ደነገጠች…ሚካኤል ምንም ባልገባት ነገር እንዲህ አመናጭቋት አያውቅም፡፡

ወደሳሎን ተመለሰችና ፀአዳ ጋር ደወለችላት፡፡
ስታወራ ድምፃ ይንቀጠቀጣል‹‹ሄሎ ፀዲ..አሁኑኑ ወደቤት ነይ››
‹‹እንዴ ምን ሆንሽ..?

ቅዱስ አመመው እንዴ?››
‹‹አይደለም..አባትዬው ነው፡፡››

ፀአዳ በጣም ደነገጠች‹‹እንዴ  ሚኪ ምን ሆነ?››

‹‹እኔ እንጃለት… ቅድም አንቺ ጋር የመጣሁ ጊዜ አባቱን ለመጠየቅ ወህኒ ቤት ሄዶ ነበር…ከዛ ሲመለስ እንደእብድ አድርጎት መኝታ ቤቱ ገባ..ከዛ ወጣና መዶሻና መሮ ይዞ ገብቶ በራፉን ከውስጥ በመዝጋት ግድግዳውን ሲነድለው ነበር…አንኳኩቼ ምን እንደሆነ ስጠይቀው አጓርቶብኝ መልሶ ዘጋው…እህቴ ቶሎ ድረሺኝ…የቀትር ጂኒ ሳያጠናግረው አይቀርም››

‹‹ስለአባቱ መጥፎ ነገር ሰምቶ ይሆን እንዴ?››

‹‹መሰለኝ….ወይ በፈጣሪ ምን አልባት እዛ ሲደርሰ ገድለዋቸው እንዳይሆን ነው የምፈራው..እንደዛ ቢሆንስ በራፍ አስዘግቶ ግድግዳ ያስንዳል እንዴ…?››

‹‹በቃ መጣሁ ..እስከዛው ተረጋጊ››አለቻትና ስልኩን ከመዝጋቷ በፊት ቦርሳውን አንጠለጠለችና መንገድ ጀመረች፡፡

ሚካኤል ሜሞሪውን አነሳና ስልኩ ውስጥ ከተተው፡፡ሁለት ፎልደሮች  አሉት፡፡አንደኛውን ከፈተ ….በምስሉ በቅድሚያ ምትታየው እናቱ ነች፡፡አዎ ቡቲክ ቤታቸው ውስጥ ሆና ልብሶችን ሰታስተካከል ይታያል…ወዲያው አንድ በእሷ እድሜ ያለ ሰው  መጣ …የሰውዬው ጀርባው ነው ሚታዬው እናትዬው ግን በሰውዬው መምጣት ስትደነግጥ ይታያል፡፡

‹‹ለሚ እንዴት መጣህ?››አገላብጣ እየሰማችው ትጠይቀዋለች፡፡

‹‹እንዴት መጣህ ነው እንኳን ደህና መጣህ ነው የሚባለው?እዚህ ስብሰባ ነበረን …ሳላይሽ ተመልሼ መሄድ አልቻልኩም›››

‹‹እንዴ ከሶስት ቀን በኃላ ቀጠሮ ነበረን እኮ…››

‹‹እሱም እንዳለ ነው…ግን እኔ እኮ በየቀኑ ላገኝሽ ነው የምፈልገው…እንደውም ሙሉ በሙሉ የእኔ እንድትሆኚ ነው የምፈልገው፡፡››

‹‹እሱንማ አስረግዘኘኝ  ጥለኸኝ አሜሪካ ከመሄድህ በፊት   ማሰብ ነበረብህ፡፡››

‹‹ይሄንን እኮ ብዙ ጊዜ  ተነጋግረንበት  ሁኔታውን አስረድቼሽ ይቅር ብለሽኛል..አይደል እንዴ የእኔ ፍቅር?››

‹‹አዎ ግን …ይቅር አልኩህ ማለት ለአመታት የገነባሁት ትዳሬንና ልጆቼን በትኜ ወደአንተ ለመመለስ እፈልጋለው ማለት አይደለም፡፡››

‹‹ልጆችሽን በትኚ አልልኩም እኮ ….ባልሽን ፍቺና ልጆቹን ይዘሽ ነይ ነው፡፡›››

‹‹አይ ያንን ሳደርግ ቅጣው እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ ይመስልሀል….?እሱ ምንም እንከን የማይወጣለት ድንቅ አባትና ምርጥ ባል ነው፡፡ልጆቹን እንዴት እንደሚወድ እና እንዴት እንደሚንከባከብ ብታውቅ እንዲህ ለማለት አትደፍርም..በተለይ ትርሲትን በልዩ ሁኔታ ነው የሚወዳት…ሲጠራት እኮ እናቴ ነው የሚላት…እሷስ ብትል..?››

‹‹ግን እውነተኛ ልጁ አይደለችም…ትርሲት የእኔ  ልጅ ነች፡፡››

ሚካኤል በሚሰማው ነገር ሆዱ ሲገለባበጥ ይታወቀዋል…አረ እንደውም ሊያስታውከው እየተናነቀው ነው፡፡

‹‹አረ ድምጽህን ቀንስ..ድንገት ሰው ቢሰማህስ?››
👍6312
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////

ሚካኤልና ፀአዳ አንድ ሬስቷራንት ቁጭ ብለው ተፋጠዋል፡፡ከሁለቱም ፊት ለፊት ተከፍቶ የተቀመጠ ቢራ አለ..አንዳቸውም ግን አንስተው አልተጎነጩለትም፡፡

‹‹ለምን ጊዜችንን ትጨርሳለህ…የሆንከውን ካልነገርከኝ እንደማለቅህ ታውቃለህ››

‹‹ፀዲ..ለምን ችክ ትያለሽ..?ምንም አልሆንኩ የስራ ጉዳይ ነው አልኩሽ እኮ››

‹‹እኮ ግድግዳ በመዶሻ የሚያስነድል ምን አይነት የስራ ጉዳይ ነው?፡፡ሚኪ እኔ እኮ ለአመታት ነው የማውቀው..አንተን የስራ ጉዳይ በዚህ ልክ ሊያበሳጭህ…ኦረዲ አብደሀል እኮ››

‹‹ተይ ፀዲ አታጋኚ››

‹‹አጋነንኩ እንዴ…?የማትነግረኝ ከሆነ …››አለችና እጇን ወደ ሱሪ ኪሷ ሰዳ ስልኳን አወጣች፡፡
‹‹ምን ልታደርጊ ነው?››ግራ በመጋባት ጠየቃት፡

‹‹ብቻዬን አልቻልኩህም..ለአዲስ ደውልላትና ትምጣ..ከዛ ለሁለት እንሞክርሀለን››

‹‹በፈጠረሽ……የእሷን ጭቅጭቅና ለቅሶ የምሸከምበት ትእግስቱ የለኝም››

‹‹እና ንገረኛ››

‹‹እሺ ነግርሻለው››
ስልኩን ጠረጴዛ ላይ ከቢራ ጠርሙሱ ጎን አስቀመጠችና ሙሉ ትኩረቷን ወደእሱ አደረገች፡፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቁዘማ በኋላ እንደምንም አፉን ከፈተ‹‹የአባቴ ጉዳይ ነው››

‹‹እሱንማ አውቄለው…ከዛ ውጭ አንተን በዚህ ልክ ሊረብሽ የሚችል ሌላ ጉዳይ የለም…በዝርዝር ንገረኝ፡፡

‹‹አባቴ እናቴንም ሆነ እህቴን እንዳልገደላቸው ነገረኝ…እኔም አምኜዋለው››

ፀአዳ ክፉኛ ደነገጠች‹‹እና ማን ነው የገደላቸው..?ማለቴ እንዴት ሞቱ?››ተንተባተበች፡፡

‹‹እሱን አላውቅም…አባቴ ግን ከመሞቴ በፊት እናትህንና እህትህን እኔ እንዳልገደልኳቸው በትክክለኛ ማስረጃ አረጋግጥልኝ፡፡ከመሞቴ በፊት ልጆቼ እኔ ንፅህ ሰው መሆኔን ማወቃቸውን ማረጋገጥ እፈልጋለው››አለኝ በማለት ሙሉውን ታሪክ በዝርዝር ነገራት፡፡

‹‹እና አሁን ምን ልታደርግ ነው…?እንዴት አድርህ ማረጋገጥ ትችላለህ?››

‹‹ግድግዳውን የናድኩት ለዛ ነበር..አባቴ እዛ ግድግዳ ውስጥ የደበቃቸው የተወሰኑ ማስረጃዎች ነበሩ..አለና ስልኩን ከፍቶ  በሚሞሪ ያሰቀመጣቸውን ቪዲዬዎች አስደመጣት፡፡ሽምቅቅ አለች፡፡

‹‹በጣም ያሳፍራል አይደል?››አላት፡፡

‹‹በእውነት ምን እንደምልህ አላውቅም››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹አየሽ ክህደት ምን እንደሆነ ምን አይነት ህመም እንደሚያስከትል ከእኔ በተሻለ አንቺ ታውቂያሽ..አባቴ እነዚህን ሁሉ መረጃዎች ካወቀ በኋላ ሚስቱ እሱን ሳይሆን ሌላ ሰው እንደምታፈቅር ከተረዳ በኋላ…በጣም የሚወዳት ቀምጥል ልጁ የእሱ ሳትሆን የሌላ ሰው ልጅ እንደሆነች ካወቀ በኃላ  ….የሁለት መንታ ወንድ ልጆቹ እናት እሱን ጥላ ወደልጅነት ፍቅረኛዋ ልትሄድ ዝግጅት ላይ እንዳለች በግልፅ ካወቀ በኋላ  ምንድነው ማድረግ ያለበት?ይሄንን ሁሉ በደል እንዴት መቋቋም ይችላል…?እና  እሱ ቢቀውስና የእብድ ስራ ቢሰራ ይፈረድበታል?››

‹‹በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው…ግን እኮ አላደረኩትም ብለውሀል….›››

‹‹እሱማ  አዎ እወነቱን እንደሆነ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ….ግን እንዳውቀው ካስቀመጠልኝ መረጃ አንድም እሱ እንዳለደረገው የሚገልጽ ፍንጭ ማግኘት አልቻልኩም..እና መተንፈስ እስኪያቅተኝ ድረስ በጣም ግራ ተጋብቻለው፡፡

‹‹ምን እንደገረመኝ ታውቃለህ?››አለች፡፡

ትኩረቱን በሙሉ ወደእሷ ሰበሰበና‹‹ምን? ››ሲል ጠየቃት፡፡
አባትህ በግድያው ተጠርጥረው ፍርድ ቤት በሚመላሰሱበት ጊዜ ይሄንን አሁን ለአንተ የሰጡህን መረጃዎች ለምን ለፍርድ ቤቱ አላቀረቧቸውም….ቢያንስ እኮ የተፈረደባቸው የሞት ቅጣት ወደእድሜ ልክ ይቀየርላቸው ነበር፡፡››

‹‹አዎ..ትክክል ነሽ…መረጃዎቹን እንዳገኘው እኔም ወደ አእምሮዬ የመጣው የመጀመሪያ ጥያቄ እሱ ነበር..እና ትናንትና ወደወህኒ ቤት ሄጄ አግኝቼው ነበር….ለምን ለፍርድ ቤት እንደመረጃ አድርገህ አላቀረብከውም ስለው…ለእናንተ ስል?››ሲል መለሰልኝ፡፡

‹‹አልገባኝም… እንዴት ለእኛ ስትል ?››ብየየ መልሼ ጠየቅኩት፡፡
‹‹እንዳልከው ይሄንን ለፍርድ ቤት እንደወንጀል ማቅለያ አድርጌ ባቀርብ ኖሮ ይሄኔ እናትም አባትም ነበር የምታጡት፡፡በወቅቱ የእኛ ቤተሰብ ጉዳይ በየጋዜጣውና መፅኄቱ እንዴት እንደሚፃፍ ታውቃለህ..ይሄ ነገር ወጥቶ ቢሆን ኖሮ ስለእናትህ ምን እንደሚፃፍ አስበው…የተፃፈ ነገር ደግሞ ታሪክ ሆኖ ይቀመጣል…የልጅ ልጇቼ ጭምር ስለወንድ እና ሴት አያታቸው ታሪክ ሲያነብ ምን አይነት የልብ መሰበር ያጋጥማቸዋል…የእኛን ማህበረሰብ ለነገሮች ያለውን ብያኔ የምታውቀው ነው..በእኔ ጉዳይ ምን ያህል ፈተና እና መገለል እንደሚገጥማችሁ አውቃለው…ይሄ የእሷ ታሪክ ቢጨመርበት ኖሮ መግቢያ መውጫ ነው የሚያሳጦችሁ››በማለት መለሰልኝ፡፡

‹‹አይገርምም !!ወላጅ መሆን እኮ እዳ ነው..አንዳንዴ የነፍስ ክፍያ ለመክፈል እንኳን የማታመነታበት ምስጢራዊ ፀጋ ነው፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ››

‹‹አሁን አንድ ምርጫ ብቻ ነው ያለን››

በንቃት‹‹ምን ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ሰውዬውን ፈልገን ማነጋገር››

‹‹የትኛውን ሰውዬ?››

ፈራ ተባ እያለች ‹‹የእናትህን ጓደኛ…..››ስትል መለሰችት፡፡

የሚካኤል ደም ስር በንዴት ውጥርጥር አለ‹‹እሱ እኮ ጠላታችን ነው..እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ የከተተን እሱ ነው…ፊት ለፊት አግኝቼ እንድገድለው ነው የምትፈልጊው፡፡››

‹‹የሆነ ፍንጭ ለማግኘት የግድ እሱን ማግኘት አለብን…የግድ አንተ ልታናግረው አይገባም…ቆይ እስኪ››  አለችና ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጠችውን ስልክ አንስታ ከፈተች ..ምን ልታደርግ ነው ብሎ ሲጠብቅ‹‹ስሙ ማን ነበር››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹የማ?››

‹‹የሰውዬው ነዋ››

‹‹ለሚ በቀለ ››

ስሙን ሰርች ላይ ከታ መፈለግ ጀመረች፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ዳይሬክተር ዳይሬክቶሪት ደ/ር ለሚ  በቀለ የሚል ዜና አየች፡፡

‹‹እንዴ ሰውዬው ባለስልጣን ነው እንዴ?››

ምንም አልመለሰላትም..ዜናውን ከፍታ ለማንበብ ሞከራች…ከአምስት አመት በፊት የተፃፈ ዜና ነው፡እሱን ተወችና ….ሌላ ፈለገች ..ሶስት አራቱን ከከፈተች በኃላ በአራተኛው ትኩረት ሚስብ ዜና አገኘች‹‹የግብርና ሚንስቴሬ ዳይሬክተር ዳይሬክቶሬት የሆኑት ዶ/ር ለሚ  በቀለ በጤና እክል ምክንያት መልቀቂያ በማስገባት ስልጣናቸውን ለቀዋል ››ይላል፡፡ከአራት አመት በፊት የተለቀቀ ዜና ነው፡፡

ወደፌስብክ ገባችና በስሙ ፈለገች.. ዲአክቲቬት ከሆነ አመታት አልፈዋል፡፡

‹‹ሰውዬው ጥሩ ሁኔታ ላይ አይመስለኝም….ቆይ ለእኔ ተውልኝ››

‹‹ምን ልታደርጊ አሰብሽ….?››

‹‹ያለን ምርጫ አንድ ብቻ ነው፣ቢያንስ አሁን አንድ ነገር አውቀናል..ከአራት አመት በፊት ግብርና ሚኒስቴር ይሰራ ነበር…ስለዚህ አዛ ሄድና አሁን ሚገኝበትን አድራሻ ጠይቃቸዋለው…ቢያንስ ስልኩን ይሰጡኛል፡፡››

‹‹እስቲ እናያለን››ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡

‹‹አይዞህ ምንም አትጨነቅ..ይሄንን ነገር እንፈታዋለን….የፈለገ መስዋእትነት ያስከፍል የአባትህን ምኞት እናሳካለን….ይሄ ጉዳይ ዘሚካኤልንም ወደቤተሰቦቹ እንዲመለስ ለማድረግ ያግዘን ይሆናል፡፡››

‹‹እኔ እንጇ..ዘሚካኤል እናቱን እንደፈጣሪው ነው የሚወዳት..ለእሱ እሷ እንከን አልባ መልአክ የሆነች ሴት ነች…ይሄንን ሲሰማ ዳግመኛ ይበልጥ  እንዳይሰበር ነው የምፈራው፡፡

‹‹አይዞህ ….ከመሰበር በኃላ ያለ መጠገን ነው እኛን ሞርዶ ሙሉ ሰው የሚያደርገን፡፡ደግሞ እናትህ ጥፋት ያጠፋችው  በሚስትነቷ ነው እንጂ በእናትነቷ  እስከወዲያኛው ምሉ እንደሆነች ነው፡፡››
👍6611🥰1
#አላገባህም


#ምዕራፍ_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁ_ገመቹ

/////

በማግስቱ አቶ ቅጣው እንደተለመደው ጭለማና ድፍን በሆነው የእስር ክፍሉ በሰንሰለት እጅና እግራቸው እንደተጠፈረ  ኩርምት ብለው  በትካዜ ላይ እያሉ  የበራፍ መኳኳት ድምፅ ሰሙ የገመቱት ትንሽዬዋ መስኮት መሳይ ቀዳዳ ተከፍታ የእለቱ የምግብ ኮታቸው ይወረወርልኛል ብለው ነበር …ግን ትልቁ በራፍ ተከፈተ….ወዲያው ብርሀን ሾልኮ ወደክፍሉ ገባና አይናቸው ላይ አንፀባረቀባቸው፡፡አይናቸውን ጨፈኑ..ከዛ ገለጡ… አሁንም ጨፈኑ እንደዛ እያደረጉ ካለማመዱት በኋላ ገልጠው ምን እየተካሄደ እንደሆነ ሲያስተውሉ ከክፍሉ ይዘዋቸው ሊወጡ እንደሆነ ገባቸው..፡፡አንድ ጠባቂ ክላሹን እንዳቀባበለ ውጭ በራፍ ላይ ሲታያቸው አንደኛው ደግሞ እንደተለመደው ወደውስጥ ገባና ሰነሰለቱን ከመሬት ከተቀበረው ብረት ጋር የተያያዘውን ብረት ይፈታል ብለው ሲጠብቁ ከእግራቸው ጋር የተያያዘውን ሰንሰለት ፈታውና አላቀቀው…ከዛ ወደላይ ቀና ብሎ በእጃቸው ላይ የተሳረውን ሰንሰለት በተመሳሳይ ፈታና እዛው ወለሉ ላይ ሲወረውረው የፈጠረው የቅልጭልጭልታ ድምፅ በጆሮቸው ገብቶ አእመሮቸውን አተረማመሰው…‹‹ወደ መገደያዬ ሊወስዱኝ ነው እንዴ?››ሲሉ አሰቡ…..በመጀመሪያ በጣም ቅር አላቸው፡፡ከዛ ግን‹‹እንደውም ግልግል ነው…አሁንስ በህይወት እየኖርኩ ነው ይባላል …?

ከሞት ወደሞት መሄዱ ምኑ ያስፈራል?››ሲሉ አሰቡ፡፡ፊት ለፊታቸው ያለው ፖሊስ ከኪሱ ሌላ የሚያብረቀርቅ ካቴና  ከጃኬት ኪሱ አወጣና እጃቸው ላይ ካደረገላቸው በኃላ

‹‹አቶ ቅጣው..ቀጥል እንሂድ..››አላቸው…፡፡

‹‹ለምን..?ወዴየት?› የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ሳይጠይቅ በዝምታ ፊቱን ወደበራፉ አዞረና እርምጃውን ቀጠለ…ሰውነቱ  የዶሮ ላባ ያህል ቀለለው…ላለፉት ስድስት ወር እንዛ አስጠሊታ ድምፅ ያላቸው የዛጉ ሰንሰለቶች ከእግሩና ከእጁ ጋር ተላቀው ስለማያውቁ በተንቀሳቀሰ ቁጥር እንሱንም ይዞ ይንቀሳቀስ ስለነበረ እንደራሱ አካል ያያቸው ከጀመረ ሰነባብቶል…እና አሁን የሆነ የአካሉን ክፍል ቆርጠው እንዳስቀሩበት ነው የተሰማው..ከክፍሉ ይዘውት ወጡ ፡፡በኮሪደሩ ይዘውት ከተጓዙ በኋላ ለመጀመሪየ ጊዜ ከዛ ቀፋፊና መቀብር መሳይ ህንፃ ሙሉ በሙሉ ይዘውት ወጡና የውጭን ብርሀን እንዲያይ አደረጉት፡፡በመጀመሪያ ጭው አለበት…ከዛ እንደምንም አይኑን አጨንቁሮ አካባቢውን ለመቃኘት ሞከረ..ዛፎች ይታዩታል….አረንጓዴ ሳር የለበሰ ሜዳ ..ከዛፍ ዛፍ እየበረሩ የሚታዩ ወፎች…በግዙፍ አጥር  የተከበበ አነስታኛ ሜዳ…ሜዳውን ሞልተው  ኳስ የሚጫወቱና ስፖርት ሚሰሩ  እናም ደግሞ አፍ ለአፈ ገጥመው የሚያወሩ ቢጫ ቱታ የለበሱ መአት እስረኞች..ከሁሉም በላይ እምክ እምክ የማይልና የማያፍን ንፅህ የተፈጥሮ አየር በአፍንጫው ሲስብ …በቃ ከመቃብር የወጣ አይነት ስሜት ነው የተሰማው….እንባውን ከትሮ ማቆየት ስለተሳነው አለቀሰ…

‹‹እዛ ጨለማና የታመቀ ክፍል ውስጥ በህይወት ከመቆየት እዚህ በተፈጥሮ ፀጋ በተሸሞነሞነ ንፅህ አየር ውስጥ ሞቶ መቀበር ይሻላል››ሲል አሰበ፡፡

ከፊት እየመራው ያለው ፖሊስ‹‹ቀጥል አቶ ቅጣው››ሲል እንዲከተለው አዘዘው፡፡ ሌለኛው ፖሊስ ከኋላ ክላሹን እንደደቀነበት በሁለት ህንፃዎች መካከል ባለች ጠባብ መንገድ እየመራ ወሰደው.. በቆርቆሮ የተሰሩ ብዙ ክፍል ያሉበት ክፍል ጋር ሲደርስ ቆመ …ይሄን የቆርቆሮ ቤት ያውቀዋል….እስረኞች በእያንዳንዱ ክፍል አምስትና ስድስት እየሆኑ በሳምንት አንድ ቀን ሰውነታቸውን የሚታጠቡበት ክፍል ነው፡፡ከበርካታ ወራት በፊት እሱም እንደማንኛውም እስረኛ በሳምንት አንድ ቀን የመታጠብ ወርቃማ እድል ነበረው…አሁን ግን ሰውነቱ ውሀ ከነካው ስድስት ወር ከማለፉ የተነሳ የሰውነቱ ቀለም ሙሉ በሙሉ ተቀይሮል …አካላቱ ላይ የተለደፈው ቆሻሻ በውሀና ሳሙና  ሳይሆን በቢላዋ እየተቀረፈ እየተቀረፈ ካልተነሳ የሚፀዳ አይመስልም፡

አንድ ሌላ ፖሊስ በፔስታል የሆነ ነገር ይዞ በራፍ ላይ እየጠበቃቸው ነበር፡፡መድረሳቸውን ሲያይ አንደኛውን ክፍል ከፈተና ..ይሄው መቀየሬያ ልብሱ እዚህ ውስጥ አለ..ልጅህ ነው ያመጣልህ….ሌላውን ክፍል ድርስ እናመጣልሀለን..ሳሙናም ይሄው አለና›› ለፖሊሱ አስረክቦ ሄደ፡፡

‹‹አቶ ቅጣው ያልሆነ ነገር ለመስራት ፈፅሞ  እንዳትሞክር….ይሄው ሳሙና …  ሰውነትህን ታጠብና ልብስ ቀይር….››አለው

‹‹ለምን ግን?››ሲል መጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ጠየቀ፡፡

ፖሊሱ እጁ ላይ ያጠለቀለትን ካቴና እየፈታ‹‹ለምን ማለት ..ምኑ?››ሲል ጥያቄው እንዳልገባው በሚገልፅ ሁኔታ መልሶ ጠየቀው፡፡

‹‹መታጠቤና ..ልብስ መቀየሬ?››

‹‹ምነው አሁን ያለህበት ሁኔታ ተመችቶሀል እንዴ?ማጥ ውስጥ ሲንከባለል የከረመ ከርከሮ እኮ ነው የምትመስለው …ለማንኛውም ለምን እንድታጠብ እንደተፈቀደልህ አናውቅም…እኛ የታዘዝነውን እያደረግን ነው…ስራችንን እንድንሰራ ተባበረን..እንካ ልብሱንና ሳሙናውን… ይዘህ ግባ››አለው።

እንዳው በግዴለሽነት ተቀበለውና ወደውስጥ በዝግታ ገብቶ በራፉን ከውስጥ ሊዘጋው ሲል…ፖሊሱ ፈጠን አለና‹‹አይ አትዝጋው…..ክፍት ይሁን …ከእይታችን ውጭ መሆን የለብህም››የሚል ትእዛዝ ሰጠው፡፡

በግዴለሽነት በራፉን መልሶ በልቅጦ ወደውስጥ ገባ…ልብስ የያዘውን ፔስታል በአንዱ የግድግዳው ኮርነር ጋር አስቀምጦ ሳሙናውን ብቻ ይዞ ቀጥታ ሻወር ወደላበት ቦታ ሄደ… ውሀውን እስከመጨረሻ  ከፈተውና ውስጡ ቆመ…ውጭ ሆነው በትኩረት እየተከታተሉት ያሉት ሁለት ፖሊሶች በገረሜታ ምን እየሰራነው? ብለው እየተገረሙበት ነበር፡፡ለሀያ ደቂቃ አልተነቃነቀም…ውሀው እየተንፎለፎለ በላዩ ላይ ሲወርድ ከለበሰው ልብስ ላይም ሆነ ከገላው ላይ እየተቀረፈ የሚወርደው ቆሻሻ  ለሚያየው ሰው ይዘገንናል..በኋላ ግራ ሲገባቸው አንደኛው ፖሊስ ወደውስጥ ገባና ወደእሱ ተጠግቶ

‹አቶ ቅጣው ..ቅጣው …››ውሀውን  ዘጋው ሲል ጠየቀው…ከገባበት ጥልቅ ሰመመን የነቃ የሚመስለው ቅጣው‹‹አቤት በቃ ልውጣ እንዴ?››ሲል ጠየቀ፡፡

‹‹አይ እሱ እስከፈለግክ መታጠብ ትችላለህ..ግን በስርአት አድርገው፡››

‹‹በስርአት ማለት?››ተደነጋገረ፡፡

ሳሙናው እኮ በእጅህ እንደያዝከው ሟሙቶ ሊያልቅ ነው..የለበስከውን ቀፋፊ እና ቡትቶ ልብስ አውጥተህ ጣልና ሰውነትህን ሳሙና እየመታህ በትክክል ታጠብ››

‹‹እ..ገባኝ..እሺ›› ብሎ ልብሶቹን አወላለቀና ከእሱ አርቆ በመወርወር ርቃኑን ቆመና ሻወሩን በድጋሚ ከፈተ…ከዛ ከፀጉሩ በመጀመር ሙሉ ሰውነቱን ሳሙና በመለቅለቅ መታጠብ ጀመረ…ምን አልባትም አምስት ስድስት ጊዜ ደጋግሞ ሳሙና በመለቅለቅ ለወራት በሰውነቱ ተጠቅጥቆ የተከማቸውን ቆሻሻ በተቻለው መልኩ ለማስለቀቅ ጣረ… ከዛ…ቧንቧውን ዘጋና ቀጥታ ወደፔስታሉ በመሄድ ውስጡ ያለውን ልብስ ተራ በተራ እያወጣ በመመልከት  ለበሰ…ሁሉም ልብሶች ምርጥና አዲስ ሲሆኑ ለእሱ ግን ሰፍተውታል ….‹‹ምን አልባትም በጣም ከመክሳቴ የተነሳ ለእኔ በልኬ የሚሆን ልብስ ገበያ ላይ ስለሌለ ይሆናል ይሄን ያመጡልኝ››ሲል አሰበና በመጨረሻ ካልሲውንና ጫማውን አድርጎ ወደ ፖሊሶቹ ሄደ….በራፉ ላይ ተቀበሉትና በእጁ ላይ ካቴናውን መልሰው አጠለቁለትና በሌላ አቅጣጫ ይዘውት ሄዱ…አሁንም የወሰዱትን ቦታ ገና እንዳየው ነው ያወቀው›..የእስረኞች ፀጉር ማስተካከያ ቦታ ነው፡፡

‹‹ሽፈራው በል ቆንጆ አድርገህ አስተካክለው››ፖሊሱ ፀጉር አስተካካዩን አዘዘው፡፡

‹‹እንዴ ቅጣው..?እንዴት ነህ..?ሰላም ነህ?››ፀጉር አስተካካዩ በገረሜታ ተቀበለው፡፡
👍6611🥰2🔥1
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

አዲስ አለም በራሷ መኪና ግን ሹፌር እየነዳላት  ከአዳማ ወደአዲስ አበባ እየተጓዘች ነው፡፡

የተቀመጠችው ከኋላ ወንበር ላይ ሲሆን ከግራዋ የራሷ ልጅ ቅዱስ ሲኖር ከግራዋ ደግሞ የፀአዳ ልጅ ምሰር ትገኛለች፡፡

አዲስአለም ወደአዲስ አበባ የምትሄደው እናቷን ለመጠየቅ ነው፡፡ይሄ ቤተሰቦቾ አዳማ ለቀው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ  በወር ወይም በሁለት ወር አንዴ የምታርገው ነገር ስለሆነ ማንም ለምን እንዴት ብሎ የሚጠይቃት የለም፡፡ምስርን በምን ሰበብ አስፈቅዳ ከእሷ ጋር ይዛት እንደምትመጣ ግን ግራ ገብቷት ነበር፡፡ማታ ነበር ፀአዳ ጋር የደወለች፡፡

‹‹እሺ ጓደኛዬ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ ምነው ቀን ተገናኝተን ነበር እኮ..በዚህ መሀከል ምን ትሆናለች ብለሽ አሰብሽ?››.

‹‹አንቺ ደግሞ ከአፍሽ ቀና ነገር ቢወጣ ምን አለበት?››

‹‹በይ አሁን ምን ፈልገሽ ነው ወደገደለው ግቢ….››

‹‹በእናትሽ ነገ እነማዬ ጋር አብረን እንሂድ››

‹‹ነገ ››

‹‹አዎ ነገ››

‹‹ያምሻል እንዴ…?ስንት ስራ እንዳለብኝ  ስነግርሽ ውዬ እንዴት የማልችለውን ነገር ትጠይቂኛለሽ?››

‹‹ውይ ለካ ስራ አለብሽ..ብቻዬን መሄድ እኮ ደብሮኝ ነው››

ብቻሽን መሄድ ከደበረሽ  ታዛዥ እና ጣፋጭ የሆነ ምርጥ ባል አለሽ እሱን አስከትለሽ ሂጂ››

‹‹አንቺ እየሰማሽ እኮ ነው››

‹‹ላውድ ላይ አድርሽ ነው እንዴት የምታወሪኝ… አንቺ እኮ ቅሌታም ነሽ….ለነገሩ ሚኪን በተመለከተ መጥፎ ነገር እንደማልናገር እርግጠኛ ስለሆንኩ እንደፈልገሽ››

‹‹መጥፎ ነገር እንደማትናገሪ እኔም ምስክር ነኝ … ውሸት ግን ትናገሪያለሽ..ምን አልባት እንዳልሺው ጣፋጭ ሊሆን ይችላል ታዛዣ ግን አይደለም..ልክ እንደአንቺው ስራ አለኝ አልችልም የሚል መልስ ነው የሰጠኝ››

‹‹በቃ ከልጅሽ ጋር ሒጂ››

‹‹ወይ እንደውም ተውት ከልጆቼ ጋ ሄዳለው…ምስርን ቆንጆ አድርገሽ አሳምሪያትና ወደስራ ስትሄጂ ይዘሻት ውጭ.. በዛው መጥቼ ወስዳታለው››

‹‹ምን እያልሽ ነው?››ፀአዳ እንደመበሳጨት አለች፡፡

‹‹የራስሽው ምክር እኮ ነው፡፡ልጆቹን ይዤ ሄድና ዘና እንላለን…እናንተም ካለልጆቻችሁ ይድላችሁ…እሁድ ማታ ተመልሰን እንመጣለን፡፡››

‹‹አንቺ እኮ የሆነ መዠገር ነገር ነሽ…እኔ ለራሴ ስንት ስራ አለብኝ..?ገና አሁን እሷን ሰውነቷን ሳጥብ..ፀጉሯን ሰሰራ….››

አላስጨረሰቻትም፡፡‹‹በቃ…ጥዋት ሁለት ተኩል አካባቢ ስራ ቦታሽ እመጣና ወስዳታለው..ደህና እደሪ..እወድሻለው፡፡››ብላት ስልኳን ዘጋችው፡፡እንዳለችውም ጥዋት ስትሄድ ፀአዳ ከነንጭንጯ ልጇን ምስርን አስባና አሳምራ ነበር የጠበቀቻት፡፡

‹‹ውይ ጎደኛዬ ንዴት እንደሸወድኩሽ ስታውቂ እንዴት ትናደጂ ይሆን?›› ብላ አሰበችና ብቻዋን ፈገግ አለች፡፡

ሹፌሩ ጎሮ አካባቢ የሚገኘው የቤተሰቦቾ ቤት ካደረሳት በኃላ  ሚካኤል እንዲገዛለት ያዘዘው ዕቃዎች ስለሉ ወደመርካቶ ለመሄድ ተዘጋጀ….

‹‹በቃ ነገ አስር ሰዓት አካባቢ እዚህ ድረስ ››አለችው አዲስ፡፡

‹‹እዚህ የምትንቀሳቀሺበት አይቸግርሽም?››

‹‹ችግር የለውም..የትም የመውጣት እቅድ የለኝም…ምን አልባት የምወጣም ከሆነ ራይድ እጠቀማለው››አለችና ሸኘችው፡፡

ከዛ ልጆቹን ወደቤት አስገብታ እናቷን በቅጡ እንኳን ሰላም ሳትል ነው ወደጓሮ ሄዳ ስልክ የደወለችው፡፡ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ‹‹እንዴት ነህ ዘሚካኤል?››

‹‹ሰላም ነኝ..ግን አልተሳካልኝም ብለሽ እንዳታበሳጪኝ››

‹‹አረ ተሳክቶልኛል…መጥተናል እማዬ ቤት ነው ያለነው፡፡››

‹‹በጣም ጎበዝ…..በቃ ጎሮ አካባቢ ነው ያልሺኝ፡፡››

‹‹አዎ… ትክክለኛ አድራሻውን በሚሴጅ ልክልሀለው››

‹‹በቃ..በአንድ ሰዓት ውስጥ እመጣለው››

‹‹ጥሩ ነው..እኛም ገና አሁን መድረሳችን ስለሆነ እስከዛ ከእማዬ ጋ እንጫወታለን…በል ቻው››

‹‹አዲስ በጣም አመሰግናለው…ቻው››

ስልኩ ተዘጋ ፣፣እሷ ግን ፈዛ ቀረች…ከዘሚካኤል ጋር በዚህ መጠን መቀራረብ መቻሏ የተአምር ያህል ነው….ለዘመናት ስታልመውና ስትመኘው የነበረ ነገር ነው፡፡ግን በዚህ መንገድ ይሆናል ብላ ፈፅሞ ሀሳብ አልነበራትም..እሱ የእሷን የልብ ጓደኛ አፍቅሮ እሷ ደግሞ እሱን ከሚያፈቅራት ልጅ ጋር ለማቀራረብ ስትጥር….በራሷ ድርጊት ፈገግ አለች፡፡

‹‹ምን አለበት…. ለሚያፈቅሩት ሰው የሚያፈቅረውን ነገር እዲያገኝ መርዳት ትንሽ ህመም ቢኖረውም ግን ደግሞ ደስ የሚል ስሜት አለው፡፡››አለችና ለስሜቷ ድጋፍ ለመስጠት ሞከረች…የባሏ ሚካኤል ምስል በድንገት መጥቶ አየሩን ሞላው‹‹ፍቅሬ ምን እያሰብሽ ነው…?የገዛ ወንድሜን!!!››ብሎ በሀዘን በተሰበረ ስሜት ሲወቅሳት አየች፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ይሄ እኮ ያለፈ ታሪክ ነው….ታውቃለህ እሱን ለማግኘት ስትጥር ነበር ከአንተ ጋር የተቀራረብኩት…ከዛ እሱም ሀገር ጥሎ ጠፋ አንተም ለእኔ ምርጥና ተወዳጅ ሆንክልኝ..እናም  በሙሉ ልቤም ወድጄ አገባሁህ››

‹‹ግን ስታገቢኝ…ወደሽ ነው..ወይስ አፍቅረሺኝ?››

‹‹አይ አንተ ደግሞ ምን ቃላት ትመነዝራለህ….ለማንኛውም..የእሱ ያለፈ የአፍላ የወጣትነት ስሜት ነው..አሁን እየቀረብኩትና እየረዳሁት ያለሁት ያንተ ወንድም ስለሆነ ብቻ ነው››

‹‹እንዴ…!!ምንድነው  ጓሮ ተደብቀሽ ብቻሽን ምታወሪው?››የእናትዬው የመገረም ንግግር ነበር ከገባችበት ቅዠት መሰል ሀሳብ አባኖ ያወጣት፡፡

‹‹አይ እማዬ ..ምንም አይደል ..የሆነ ነገር እያሰብኩ ነበር››

‹‹የሆነ ነገር..ምነው ከሚካኤል ጋር ተጣላችሁ እንዴ?››

‹‹ወይ እማዬ ምንድነው የምታወሪው..?ከሚካኤል ጋር ለምንድነው የምጣለው?››

‹‹ባልና ሚስት ለምንድነው የሚጣሉት?››

‹‹እኔ እንጃ..እኔና ሚኪ ስንጣለ አይተሸን ታውቂያለሽ?››

‹‹እሱ መልካምና ታጋሽ ባል ስለሆነ ነዋ…እንጂማ እንደአንቺ መመነጫጨቅ ቢሆን… ››እናትዬው ነግግሯን ሳታገባድድ አንጠልጥላ ተወችው፡፡

‹‹እማዬ ደግሞ… የእኔ እናት ነሽ  የእሱ?››

‹‹የሁለታችሁም…ባሌ ነው ብለሽ አምጥተሸ ካስተዋወቅሺኝ ቀን ጀምሮ እኮ ልክ እንደአንቺ እሱም ልጄ ሆኗል…በዛ ላይ አሁን ወርቅ የሆነ የልጅ ልጅ ሰጥቶኛል…በይ አሁን ነይ ግቢ ቁርስ ቀርቧል…››አሏትና ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ፡፡ 

ዘሚካኤል እንዳለውም ከአንድ ሰዓት በኃላ በራፍ ላይ ደርሶ ደወለላቸው፡፡ተዘጋጅታ ስትጠብቀው ስለነበረ ወዲያውኑ ነው ልጆቹን ይዛ የወጣችው፡፡ከግዙፉ ሀመር መኪናው ወርዶ በራፍን ከፍቶ ቆሞ እየጠበቃቸው ነበር…የስድስት አመቷ ምስር እንዳየችው ደነገጠች…..መጀመሪያ የት እንደምታውቀው ነበር ግራ የገባት..ከዛ የምትወደው ዘፋኝና ተዋናይ መሆኑን ስታውቅ ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት እየተንደረደረች ወደ እሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ከቆመበት እጆቹን ዘርግቶ ወደእሷ ተንቀሳቀሰ…እቅፉ ውስጥ ወደቀች.. ጭምቅ አድርጎ አቀፋትና በአየር ላይ አንጠለጠላት..የምስርን ድርጊት ያየው ቅዱስ እጆቹን ከእናቱ እጅ አስለቅቆ ኩስ ኩስ እያለ ምስር እንዳደረገችው ወደዘሚካኤል ሮጠ….አዲስአለም በልጆቹ ያልተጠበቀ ድርጊት  በድንጋጤ አፏን ከፈተች ….ሚካኤል ቅዱስ ስሩ ሲደርስ ምስርን ወደአንዱ እጁ አዘዋወራትና ጎንበስ ብሎ ቅዱስን አቅፎ ወደላይ አነሳውና ጉንጮቹን እያገላበጠ ሳመው…..በዚህ ጊዜ አዲስ አለም ከመደነቅ ሳትወጣ ስራቸው ደርሳ ነበር፡፡

‹‹ቆይ ከእነዚህ ልጆች ጋር ከዚህ በፊት ትተዋወቁ ነበር እንዴ?››

ጉንጮቾን እያገላበጠ ሰማት..ትንፋሹ ልክ ሰው ፊት ላይ እደሚበትን አደንዛዥ ዕፅ ኃይል አለው…
👍6617
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ነው፤ የሆነ የሚንጠጣረር ነገር እያደነቆረው ነው፡፡በመከራ ነው ከእንቅልፉ የነቃው…የበራፉ መጥሪያ ድምፅ መሆኑ አወቀ..ስልኩን ከኮመዲኖ ላይ አነሳና ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ይላል፡፡ያልተለመደ ነገር ነው፡፡በዚህ ሰዓት ማን ነው በራፍን መጥሪያ የሚያንጣርረው?፡፡የፅዳት ሰራተኛዋ እንደማትሆን እርግጠኛ ነው፡፡እሷ አንደኛ በዚህ ሰዓት አትመጣም…ብትመጣም የራሷ የሆነ ቁልፍ ስላላት እሱን የምትቀሰቅስበት ምንም  አይነት ምክንያት የላትም….መኝታውን ለቆ ተነሳና ጋዎኑን ደርቦ መኝታ ቤቱን ለቆ ወጣ፡፡፡ሳሎን ደርሶ በራፉን ሲከፍት..እየተመለከተ ያለው  ፈፅሞ በአእምሮው ያልጠበቀውን ነው፡፡ፊቱን በጥፊ ደረቱን በጡጫ እየቀጠቀጠች ገፍትራ ወደውስጥ አስገብታ ትቦጫጭረው ጀመር….‹‹ምን አድርጌሀለው..?እንዴት በልጄ ስሜት እንደዛ ትጫወታለህ..?ምን አይነት አረመኔ ሰው ብትሆን ነው?፡፡››
እንደዚህ አውሬ የሆነች ሴት በእድሜ ዘመኑ አጋጥሞት  አያውቅም፡፡ፊቱን ከብጭሪያ ለመከላከል ሁለቱን  እጆቹን በፊቱ ዙሪያ አድርጎ ለመከላከል ሞከረ፡፡
‹‹አረ ፀዲ ተረጋጊ….››
‹‹አልረጋጋም..እንዲህ አሳብደሀኝ እንዴት ነው የምረጋጋው…..?ልጄን እንዴት እንዳሳደኩዋት ታውቃለህ…?››መደባደቧን እና ጮኸቷን አላቆረጠችም….እንባዋ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ እየረገፈ ነው፡፡ትናንት የሆነውን ከሰማችበት ደቂቃ ጀመሮ ማልቀሷን አላቆረጠችም… ለሊቱን እንቅልፍ ባይኗ ሳይዞር ስትቃጠልና ስትነፈርቅ ስላደረች የእናቱን ሞት አዲስ እንደተረዳ ሀዘንተኛ አይኖቾ ከማበጣቸውም በላይ ክፍኛ ደፍርሰዋል፡፡
ዘሚካኤል መከላከሉ ብቻ እንደማያዋጣ ገባው፡፡እንደምንም አለና ሁለት እጆቾን ያዘና ስቦ ከሰውነቱ ጋር አጣበቃት፡፡
‹‹ልቀቀኝ..ከዚህ ቀፋፊ ሰውነትህ ጋር መነካካት …..››አላስጨረሳትም የተከፈተ አፏን በአፉ ከደነው….በተቻላት መጠን ተወራጨች…ከእሱ ፈርጣማና የዳበረ ጡንቻ ማምለጥ አልቻችም…ከንፈሩን ነከሰችው….ለቀቃትና..ተስፈንጥራ ወደኃላ ልታመልጥ ስትል መልሶ በመያዝ ሙሉ በሙሉ ከስር ገብቷ ተሸከማት……እንደእፃን ልጅ በእግሯም በእጇም ተወራጨች… ወደሶፋው ይዟት ሄደ…ሶፋው ላይ ሊወረውረኝ ነው ብላ ስትጠብቅ እሷን አጥብቆ እንደያዘ እግሩን ዘረጋና ከሳፋው ላይ አንዱን ትራስ ወደወለሉ አወረደ….በፍጥነት ገለበጣትና እንደህፃን አቅፎ ወደታች በጉልበቱ ተንበረከከ እና ወለሉ ላይ አስተኛት…ሾልካ ከስሩ ለማምለጥ ታገለች… በጥንካሬ ጨምቆ ከወለሉ ላይ አጣበቃትና ጭንቅላቱን ቀና አድርጎ ትራሱ ላይ አስደገፋት …እንዳይጨፈልቃት በመጠንቀቅ እላዩዋ ላይ  ተቀመጠ…የለበሰውን ጋወን አውልቆ ወረወረው….
‹‹ምን ልታደርግ ነው?››አይኗቾ በድንጋጤ ፈጠጡ፡፡
ወደታች ጎንበስ አለና የለበሰችውን ቲሸርት ከግራና ከቀኝ ይዞ ወደታች ተረተረው….የመጨረሻውን ንዴት በመናደዷ ምክንያት ደምስሯ ተግተረተረ‹‹ምን እያደረክ ነው? ልትደፍረኝ ነው እንዴ..?እከስሀለው…ስምህን ነው ያማጠፋው….››የቀራት ብቸኛ መከላከያ ምላሷ ብቻ ነበር….ልታስፈራራው ሞከረች ፡፡ተንጠራራና ሌላ ትራስ አምጥቶ ከጎኗ በማድረግ ከላዬ ላይ ወርዶ ከጓና ተኝቶ ወደራሱ ገለበጣትና አቀፋት፡፡
ከታች እሱ በቁምጣ ሲሆን እሷ ደግሞ ልክ እንደወትሮዋ ጅንስ ሱሪ እንደለበሰች ነው፡፡
‹‹በፈጠሪ ስትበሳጪ እንዴት ነው የምታምሪው?፡፡››
‹‹እያሾፍክብኝ ነው?››
‹‹በፍፅም ..አይገባሽም እንዴ ..?ካንቺ ፍቅር ይዞኛል…ላገባሽ እፈልጋለው››
ምትሰማውን ቃል ማመን አቃታት‹‹ይሄ ደግሞ ሌላ ቀልድ መሆኑ ነው?ሕይወት እንደምትተውነው ተውኔት መሰለህ?››
‹‹እሱ እንዳያያዝሽ ነው …እኔ ግን የተናገርኩት ከልቤ ነው…ከፈለግሽ ዛሬውኑ ሄደን መጋባት እንችላለን…እንደማገባሽ እግጠኛ ስለሆንኩ ነው ምስርን ልጄ ነች ያልኩት፡፡››
‹‹እንዴት እሺ ትለኛልች ብለህ አሳብክ?››
‹‹እንደምትወጂኝ አይኖችሽ ውስጥ ስላነበብኩ››
የተፋቀረ ሁሉ ይጋባል ያለህ ማን ነው….ደግሞ እወቅ እኔ ፍቅር አልፈልግም…አሁን ልቀቀኝ ..ከአንተ እስከወዲያኛው መሸሽና መራቅ ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹አይ ከአኔ ሸሽተሸ ማምለጥ  አትችይም፡፡››
‹‹ልቀቀኝ አልኩ..›› ለመመናጨቅ ሞከረች አጥብቆ ያዛትና ከንፈሯ ላይ በድጋሚ ተጣበቀ… ሳላሳ ሰከንድ ያህል ብቻ ነው መታገል የቻለችው..ከዛ ቀስ በቀስ እየለዘበች…  የእጆቾ ጡንቻዎች እየለሰለሱ ..ከንፈሯቾ ለከንፈሮቹ መልስ እየሰጡ መጡ…እሱን ሲቧጭሩ እና ሲደበድብት የነበሩት ጣቶቹ ጀርባውናና መላ ሰውነቱን ማሻሸት ጀመሩ…ከዛ እሱ ቁምጣውን ሲያወልቅ እሷም በገዛ እጇቾ ጅንስ ሱሪዋን እያወለቀች ነበር….እዛ ግዙፍ የሳሎን ወለል ላይ 30 ለሚሆኑ ደቂቃዎች በፍቅር እየተንከባለሉ እና ከኮርነር  ኮርነር እየተሸከረከሩ በጣር የታጅበው ወሲብ ሲሰሩ በራፉ ክፍት መሆኑን እንኳን አላስተዋሉም ነበር፡፡
ከወሲብ በኃላ አርቃኗን ሆና ‹‹አንተ ምን አይነት አዚም ነው ያለህ ግን?››ስትል ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው የፍቅር አዚም ነዋ››
‹‹አይ አይመስለኝም…..የሆነ  የሚያደነዝዝ አይነት መስተፋቅርማ አለህ…አሁን ሻወር ቤቱን አሳየኝ..››አለችው፡፡
ከተዘረረበት ወለል እየተነሳ ወደእሷ ሄዶ ከስር ተሸክሞ ወደምኝታ ክፍሉ ተሸክሟት ገባ….‹‹ያው ግቢና ታጠቢ››
‹‹እሺ…ቲሸርቴን ቀዳደሀዋል….አሁን ምን ልለብስ ነው?››እያለች ገባች፡፡
‹‹አታስቢ አዘጋጅልሻለው….ግን አብሬሽ ሻወር መውሰድ እፈልጋለው፡፡››
‹‹ስርአት ይዘህ የምትታጠብ ከሆነ ትችላለህ›› አለችው፡፡በደስታ እርቃኑን ገባና ተቀላቀላት…መታጠብ ጀመሩ፡፡ ቃል እንደገባው ግን ስርዓት ይዞ አልታጠበም..እሷም በቃላት አውጥታ አትናገር እንጂ ስርዓት የለሽ መሆኑን ፈልጋው ነበር..ከዛ ሻወር ቤት ለመውጣት አንድ ሰዓት በላይ ነበር የወሰደባቸው፡፡ ከዛ ተያይዘው ሲወጡ ሁለቱም ሰውነታቸውን ማዘዝ እስኪያቅታቸው ዝለው ነበር.. ርቃናቸውን ተያይዘው አልጋ ውስጥ ነው የገቡት…ሁለት ሰው መሆናቸውን መለየት እስኪከብድ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተቃቅፈው ለሞት የተቃረበ እንቅልፍ ውስጥ ገቡ፡፡
///
ተመሳሳይ የበራፍ ተደጋግሞ መንጫረር ነበር ከእንቅልፉ ያባነነው..‹‹ዛሬ ደግሞ ምን ጉድ ነው ?››በማለት እየተነጫነጨ…እንደምንም ነቅቶ ስልኩን ሲመለከት..ከ30 በላይ ሚስኮል ነበረው…ሰዓቱን ሲመለከት 7ሰዓት ተኩል ሆኗል…ማመን አልቻለም፡፡ይሄ ሁሉ ሚስኮል ከማን ነው ብሎ ሲያየው አብዛኛው ከአዲስአለም ነው…ስለፀደይ ተጨንቃ እንደሆነ ገመተ ..አልጋውን ለቆ ሲወርድ ፀደይ እራሷን አታውቅም፡፡
ጋወኑን ቅድም ሳሎን ወለል ላይ ትቶት ስለነበረ….ቁምጣ እና ቲሸርት ለበሰና በድኑን እየጎተተ ወደ ሳሎን ሄዶ በራፉን ሲከፍት ክፍኛ የደነገጠችውና አይኗ  የፈጠጠው አዲስአለም በራፉ ላይ ተገትራለች
‹‹እዚህ አልመጣችም…?ወይኔ ጓደኛዬ….›
‹‹አረ ተረጋጊ..ግቢ ››
ወደውስጥ አስገባትና በራፉን መልሶ ዘግቶ ተመለሰ‹‹እሺ የት ሄደች ይባላል ?አንተ ደግሞ ለምንድነው ስልክህን የማታነሳው?››
‹‹አሁን ተረጋጊና ከተቻለሽ ቆንጆ ምሳ ስሪልን››
‹‹ምን እያወራህ ነው?ፀደይ ጠፍታለች እኮ ነው የምልህ››
👍6018
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ


/////
እሱም ጃኬቱን ይዞ  ተከተላት፡፡እራሱ እያሸከረከረ የምትፈልገው መስሪያ ቤት ድረስ ወሰዳት፡፡

‹‹እ…ትጠብቀኛለህ ወይስ ትሄዳለህ?››

‹‹ኸረ በፍፁም.. አብሬሸ እገባለው››

‹‹ተው እዚሁ መኪና ውስጥ ጠብቀኝ..ከአንተ ጋር  የሆነ ቦታ መሄድ እኳ በሴቶች አይን ክፉኛ መገረፍ ነው..ታውቃለህ የሰው አይን ደግሞ ያቃጥላል፡፡››

‹‹አረ ባክሽ…!!!››ሞተሩን አጠፋና ከመኪናው ወረዳ… እሷም ወረደች…ክንዷን ያዘና ወደውስጥ መራመድ ጀመረ..መራመድ አቅቷት እግሯቾ ተሳሰሩባት፡፡ግን ምርጫ አልነበራትም፡፡
ግቢ ውስጥ ገቡና ወደኢንፎሪሜሽን ዴስክ ሲደርሱ እሱን እንግዳ ማረፊያ ወንበር ላይ አስቀጠችውና እሷ ወደዛው አመራች…ከአስር ደቀቂቃ በኃላ ግን አንገቷን ደፍታ ወደእሱ ተመለሰችና ከጎኑ ቁጭ አለች፡፡

‹‹ምነው ፍቅር…አገኘሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አይ ..ጠመሙብኝ …ሰውዬው ከአራት አመት በፊት የዚህ ቢሮ ዳሬክተር ዴሬክቶሬት ነበረ…አሁን የት እንዳለና ቢያንስ ስልኩን እንዲሰጡኝ ነበር የጠየቅኳቸው…››

‹‹ቆይ ሰውዬው ምንሽ ነው?››

‹‹ምኔም አይደለም..ጭራሽም አላውቀውም..ግን ስለአባቴ መረጃ እንዳለው በሆነ መንገድ አውቄለው…እሱን ካገኘው አባቴ ይሙት ይኑር ማወቅ እችላለው፡፡››

የነገረችውን ያለምንም ጥርጣሬ አመናት…አሳዘነችው፡፡‹‹የሰውዬው ስም ማን ነው?››
ሙሉ ስሙን ነገረችው፡፡

‹‹ቆይ እንደውም ተነሽ›› ብሎ እጇን ይዞ ወደኢንፎርሜሽን ዴስኩ መራመድ ጀመረ..እሷ ምን ሊያደርግ እንደሆነ ሳይገባት ዝም ብላ ተጎተተችለት፡፡እንደደረሰ በትንሿ መስኮት ጎንበስ ብሎ ሲመለከት ..ሁለት ልጅ እግር ሴቶች ታዩት

‹‹ጤና ይስጥልኝ?›› ሲላቸው ሁለቱም አፋቸውን ከፍተው ፀጥ አሉት፡፡

‹‹እባካችሁ የሆነ ነገር ላስቸግራችሁ ነበር››

‹‹ምን ፈለክ…?ምን እንርዳህ?››አንደኛዋ ከመቀመጫዋ  ተነስታ በመንሰፍሰፍ ጠየቀችው፡፡

‹‹እሷ እህቴ ነች..ከኃላው ያለችውን ፀአዳን ተመለከተችና‹‹ማንን ነበር ያልሽን?››ስትል  ድጋሚ ጠየቀቻት፡፡

ፀአዳ  ነገረቻት፡፡‹‹ቆይ እስኪ ››አለችና በኋላው በራፍ በመውጣት ወደእነሱ መጣች..እስቲ ተከተሉኝ ጋሽ ይርጋ በደንብ ያውቃሉ፡፡ጋሽ ይርጋ ማለት እዚህ መስሪያ ቤት ለ30አመት የሰሩ የመዝገብት ቤት ሰራተኛ ናቸው፡፡››የምታወራውን እያዳመጡ ከኋላ ተከተሏት‹‹አስቸገርን አይደል..?››አላት፡፡

ወደኃላ ዞራ‹‹‹አረ ችግር የለውም…ለዛውም ላንተ..ባይ ዘወዌ በጣም አድናቂህ ነኝ››አለችው
‹‹አመሰግናለው››ትህትና ባልተለየው የድምፅ ቃና መለሰላት፡፡

ከ10 ደቂቃ በኃላ የሰውየውን ሙሉ አድራሻ ይዘው ከቢሮ ወጡ…መኪና ውስጥ ገብተው መጓዝ እንደጀመሩን‹‹አየሽ አንቺን ሰምቼ ከስርሽ ቀርቼ ቢሆን ኖረ ምን እንደሚያጋጥምሽ ተመልከቺ››አላት በኩራት፡፡

‹‹እሱስ እውነትህን ነው..አድራሻውን እንዲህ በቀላሉ አላገኘውም ነበር›

‹‹እና ሽልማት የለኝም?››

‹‹አለህ..ምን ትፈልገለህ…?መክሰስ ልጋብዝህ?››

‹‹አዎ ግን ቤትሽ››

‹‹ቤትሽ?››ግራ በመጋባት አፍጥጣ አየችው፡፡

‹‹አዎ ምነው ላደርስሽ አይደል…አሁን አስር ተኩልነው… አስራሁለት  ሰዓት ሳይሆን እዛ እንደርሳለን…ከዛ  ቤትሽ መክሰስ ትጋብዢኛለሽ››

‹‹ለምን መክሰስ..እራት ቢሆንልህ አይሻልም….በዛውም ታድራለህ››

በፈገግታ ተሞልቶ‹‹አንቺ እኮ ምርጥ ነሽ…….››ሲል መለሰ

‹‹አረ  አላደርገውም …..ጎረቤቶቼስ ምን ይሉኛል.?.››

‹‹ምንም ይበሉሽ……››

‹‹አይ አይቻልም ከፈለክ ውጭ ልጋብዝህ››

‹‹ውጭ አልፍግም….. ባይሆን እዛ እስክንደርስ አስቢበት››አላት፡

ቀጥታ ወደአዳማ እየነዳ ነው፡፡‹‹አሁን ታዲያ እንዴት ልታደርጊ ነው?››

‹‹ግራ ገብቶኛል..ግን ምን ቢሆን ነው አንድ አመት ሙሉ አማኑኤል ህክምና ላይ የቆየው››

‹‹ያው አማኑኤል ምን ሲኮን ነው የሚቆየው? ጭንቅላቱን አሟት ነዋ….፡፡››መለሰላት፡፡

‹‹ታዲያ ከዛ ሲወጣ ሁሉን ነገር ጣጥሎ ቤተሰቦቹ ጋር ቦንጋ እንደገባ ነው የነገሩን ..እንዴት እንደዛ አይነት ውሳኔ ወሰነ…?ይታይህ በአንድ ወቅት ትልቅ ስልጣን ላይ የነበረ ጉምቱ ባለስልጣን በዛ ላይ ዶ/ር ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ቦንጋ …ከቦንጋም ገጠር  ጠቅልሎ ሲገባ አይገርምም፡፡

‹‹ይገርማል..ግን እደእኔ እንደእኔ የብልህ ውሳኔ ነው የወሰነው ..ይሄ ሰው ጭንቀትና የአእምሮ በሽታ ካለበት ትክክለኛ መረጋጊያ ቦታ ገጠር ነው..ይታይሽ እዚህ አዲስ አበባ እንኳን ለአእመሮ ህመምተኛ ለጤነኛው ሰው ትርምሱና ኳኳታው አስጨናቂ ነው…ይልቅ እኔ ያሳሰበኝ ….አሁን ምን ልታደርጊ ነው?፡፡የሚለው ነው፡፡

‹‹ቦታው ላይ ሄጄ እድሌን ሞክራለው››ስትል በእርግጠኝነት መለሰችለት፡፡

‹‹የእውነት ?››አለ ደነግጦ፡፡

‹‹አዎ….ይሄ እኮ ሲሪዬስ ነገር ነው….››

‹‹አውቃለው ..ግን እዛ ደረስ ሄደሽ ምንም ሊነግርሽ ባይችልስ…..?ማለቴ ከጤናው አንፃር ምንም ነገር ባያስታውስስ?››

‹‹ምንም ይሁን ምን  ሰውዬውን ፊት ለፊት አግኝቼው መሞከር እፈልጋለው….ካለበለዚያ,--እረፍት አላገኝም፡፡››ስትል መለሰችለት፡፡
///
አቶ ቅጣው አዲሱ ክፍሉ በጣም ተመችቶታል…እንደውም በፊት ካለበት ክፍል ጋር ሲነፃፀር ከሲኦል ወደገነት የመዘዋወር አይነት ነው፡፡መኝታ አልጋ ያለው ..በቂ ብርሀን የሚያስገባ ንፁህ ክፍል ነው ያስገቡት፡፡በዛ  ላይ እግሩም ሆነ እጁ ከሰንሰለት እስር ነፃ ስለሆነና ምግብም ሰዓቱን ጠብቆ ስለሚመጣለት ሰውነቱ ተአምራዊ በሆነ መልኩ እያገገመ ነው፡፡ክፍል ውስጥም ቢሆን እንደፈለገው እየተንቀሳቀሰ ቀላል ስፖርቶችን መስራት ችሏል…በዛ ምክንያት መንፈሱም ሆነ አካሉ ልዩ ለውጥ አምጥቷል፡፡
አሁን ቁጭ ብሎ መፅሀፍ ቁዱስ እያነበበ ነው፡፡ይሄንን መፅሀፍ ቅዱስ ከ10 ቀን በፊት ነበር ጠያቂው እና መካሪው መነኩሴ ናቸው አምጥተው የሰጡት፡፡ወዲያው  ግን ማንበብ አልቻለም ነበር…፡፡አይኖቹ ለወራት ጨለማ ክፍል ውስጥ ስለከረሙ በቀላሉ ከብዣታ አገግመው ፊደል እየለቀሙ ለማንበብ ተቸግረው ነበር…ከጥቂት ቀናት ወደዚህ ግን  እንደምንም ለማንበብ ችሏል፡፡
መለኩሴው የመጡ ቀን እንደተለመደው..ጠያቂ አለህ ተብሎ ነበር ከክፍል የተወሰደው፡፡የሚጠብቁት ክፍል ውስጥ ሲገባ እንደወትሮ በሰንሰለት እጅና እግሮቹ ተጠፍሮ የተቀደደ እና የተቦጫጨቀ ልብስ ለብሶ ሳይሆን በተለየ ሁኔታ ነበር፡፡እና በዚህ ሁኔታ ይደነቃሉ ብሎ ጠብቆ የነበረ ቢሆንም መነኩሴው ግን ልክ እንደወትሮ በተመሳሳይ ስሜት ነበር ያተናገሩት
ልጄ ይህ ግንኙነታችን የመጨረሻችን ነው… ልሰናበትህ ነው የመጣውት..›› ሲሉት ከዚ በፊት ተሰምቶት የማያውቀው ብቸኝነት ነው የተሰማው፡፡

‹‹አባ ለምን…?መመላለሱን ሰለቹ እንዴ?››

‹‹አይደለም… ልጄ ልሄድ ነው››

‹‹ወዴት ነው የሚሄዱት?››

‹‹ወደአባቴ…ወደፈጣሪ››

ሌላ ድንጋጤ፣‹‹እንዴ ያሞታል እንዴ?››

ፈገግ አሉ‹‹ አይ ልጄ ወደፈጣሪ ለመሄድ እኮ የግድ መታመም የለብንም…አምላክ በቃ ወደእኔ ና ብሎኛል…የዛሬዋን የመጨረሻ ቀኔ አንተንና ሌሎች ልጆቼን ለመሰናብት ነው የሰጠኝ..መቼስ ፡እሱ ለቸርነቱ ዳርቻ የለው… እኔ ሀጥያተኛውን መሞቻ ቀኔን ነገሮች ለመሰናበቻ ሚሆን ቀን ፈቅዶልኝ…ተመስገን ነው ..ተመስገን፡፡››

መነኩሴው የሚያወሩትን ሊገባው አልቻለም፡፡‹‹አባ እኔ ሞት የተፈረደብኝ ሰው እያለው እርሶ…..››
👍6115😱1
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ዴርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ፀደይና ዘሚካኤል ዶ/ሩን ለማግኘት ቦንጋ ከተማ ይገኛሉ፡፡ይሄ ጉዞ እንደዚህ አልነበረም የታሰበው፡፡ሚካኤልና እሷ ነበሩ ለሳምንታት አብረው ለመሄድ ሲዘጋጁ የነበሩት፡፡ከዛ ዝግጅቱ ሁሉ ተጠናቆ…ሚካኤል ቻርተር አውሮፕላን ተከራይቶ ወደቦንጋ ለመብረር ከአዳማ ተነስተው  አውሮፕላኑ ወደሚገኝበት አዲስ አበባ ሲደርሱ ዘሚካኤል ጠበቃቸው፡፡

ሁለቱም ያልጠቁት ነገር ስለሆነ በጣም ነበር ግራ የተጋቡት፡፡ዘሚካኤል እንደአጋጣሚ ከአዲስአለም ጋር ሲደዋወል ነበር ስለጉዞው የነገረችው፡፡
ለማናቸውም ሰላምታ ሳይሰጥ‹‹ፀዲ ከእኔ ጋር ነው መሄድ ያለብሽ?››አላት፡፡

‹‹ማለት…?ለምን ሲባል?››
‹‹በቃ ካንቺ ጋር መሄድና አብሬሽ መሆን እፈልጋለው››
ሚካኤል እጁን አጣጥፎ በገረሜታ እና በትዝብት እየተከታተላቸው ነው፡፡ፀደይን በተመለከተ እንዲህ ሲሪዬስ በመሆኑ ደስታ ተሰምቶታል፡፡

‹‹አይ…ከሚኪ ጋር ነው የምንሄደው…..አንተን ማስቸገር አልፈልግም››ኮስተር ብላ ተቃወመችው፡፡

እሱም ከእሷ በጠነከረ መኮሳተር‹‹እኔ ደግሞ አልስማማም….በችግርሽ ጊዜ አብሬሽ መሆን እፈልጋለው….የአባትሽን አድራሻ ብታገኚም ባታገኚም አብሬሽ ሆኜ ደስታሽንም ሆነ ሀዘንሽን መካፈል አለብኝ››ብሎ ግግም አለ፡፡

ሚካኤል ፀአዳ ስለ/ዶሩ  እንደዋሸችው ስለሚያውቅ በውስጡ ፈገግ እያለ‹‹ፀዲ አንዴ ላናግርሽ?››አላት፡፡

‹‹ቆይ ጠብቀኝ መጣው››ብላው ከዘሚካኤል ተለየችና ወደሚካኤል ሄደች፡፡

‹‹ፀዲ እሱ አንዴ ከጠመመ እሺ አይልም..››አላት፡፡

‹‹እና ከእሱ ጋር ሄጄ እንዴት ልሆን ነው?››

‹‹አሪፍ ነው እንደውም…ይሄ የእግዚያብሄር የራሱ እቅድ ይሆናል…ሁኔታዎችን እንዳመጣጣቸው ትወጫቸዋለሽ… ከሰውዬው የሆነ ጠቃሚ መረጃ ብናገኝ እንኳን እሱን አስረድቶ ማሳመን ከባድ ነው የሚሆንብን .. በኃላ እንዲህ ነው የተፈጠረው..እንደዛ ነው የሆነው ከምንል ቀጥታ ከፈረሱ አፍ ቢሰማ ነው የሚሻለው››

‹‹አረ ተው ሚኪ..››

‹‹ግድ የለሽም ባንቺ እተማመንብሻለው፡፡››አለና ጉንጮን ስሞ በፈገግታ በመጣበት መኪና ተመልሶ ሄደ፡፡
///
እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነው ሁለቱ  ቦንጋ  ከተማ ሊገኙ የቻሉት፡፡እንደደረሱ ፀደይ ከዘሚካኤል ዞር አለችን የዶ/ሩ ነው ተብሎ በተሰጣት  ስልክ ደውላ ነበር፡፡የዶ/ር ወንድም ነኝ የሚል ሰው ነበር አንስቶ ያዋራት፡፡‹‹ለምን እንደመጣችና ዶ/ርን  ለምን ጉዳይ እንደፈለገችው በአጭሩ ነገረችው፡፡

‹‹ላናግረውና መልሼ ልደውልልሽ ››አለና ስልኩን ዘጋ፡፡ሰውዬው መልሶ እስኪደውል ለሀያ ደቂቃ ተጨንቃ ነበር፡፡‹‹አይ ማግኘት አልፈልግም ቢል ምን አደርጋለው?››የሚልው ሀሳብ ትንፋሽ እስኪያጥራት ድረስ ነበር ያስጨነቃት፡፡ደውሎ ግን አስደሳች ነገር ነው የነገራት፡፡ በፈለጉት ሰዓት መምጣት እንደሚችሉ እና ሊያናግራቸው ፍቃደኛ እንደሆነ ነገራት፡፡ጊዜ ሳያባክኑ ወዲያው ነበር ባጀጃጅ በመከራየት ከከተማው የአንድ ሰዓት መንገድ ወደሚርቅ ገጠር ጉዞ ጀመሩ፡፡

እየሄዱ ሳሉ በገጠሩ ውበት ተደምማ..ዶዶላ ሆኜ አልፎ እልፎ ገጠር ሄድ ነበር..እዛም እንዲህ ውብ ነበር….እና በጣም ነበር ደስተኛ የምሆነው፡፡››

‹‹ገጠር ዘመድ ነበረሽ?››

‹‹አይ የጎደኛዬ ቤተሰቦች ገጠር ነበሩ.. እሱ ነበር ይዞኝ የሚሄደው››

‹‹ጓደኛዬ ስትይ…?››

‹‹የምስር አባት››

ወደራሱ ጎትቶ እያቀፋት‹‹በጣም ነው አይደል የጎዳሽ?››አላት ፡፡

‹‹አዎ!!በፊት በጣም የምጠላውና ባገኘው የምገድለው ይመስለኝ ነበር፡፡››

‹‹አሁንስ?››

‹‹…አሁን ግን  ሙሉ በሙሉ ይቅር ብዬዋለው››አለችው፡፡

‹‹ግን እንዴት በዛ መጠን የምትጠይውን ሰው እንዲህ በቀላሉ ይቅር ማለት ቻልሽ?››ሲል በገረሜታ ጠየቃት፡፡ይህንን ጥያቄ የጠየቃት እሱ በቤተሰቦቹ ላይ የቋጠረውን ቂምና ጥላቻ አሁንም በልቡ ውስጥ ቋጥኝ ሆኖ እያስጨነቀው በመሆኑ እሷ የነገረችውን ነገር ማመን ስላቃተው ነው፡፡

እሷ ግን እርግጠኛ በመሆን ታስረዳው ጀመር….‹‹ምን መሰለህ..በእኔና በእሱ መካከል የተፈጠረው ችገር የዛሬ ስድስት  አመት  የሆነ ነው››

‹‹እና ጊዜ ቁስልን ይፈውሳል በሚለው ብሂል ሄደሽ ነው?››

‹‹አይ እንደእሱ አይደለም…ሳስበው የዛሬ ስድስት አመት የነበረችው ፀደይ አሁን ካለችው ፀደይ ጋር በብዙ ነገር እንደምትለይ ገባኝ..እንደውም አንዳንዴ ያቺ ፀደይ ልክ እንደአንድ የምወዳት ዘመዴ ትናፍቀኛለች…››

እያወራች ያለችው መጀመሪያ ከተነሱበት ሀሳብ ጋር ምንም አልገጣጠም አለው…ቢሆንም በትግስት ማደመጡን ለመቀጠል ወሰነ..
እሷም ቀጠለች‹‹እና አሁን ያለሁት ፀደይ የዛን ጊዜ ባለፍኩበት ሁኔታ ላይ ብሆን ተመሳሳይ ችግር ላይ እወድቃለው..?ብወድቅስ ተመሳሳይ ምላሽ ነው የምሰጠው..?ማለቴ ራሴን ስለማጥፋት አስባለው….?ቤተሰቦቼንና ሀገሬን ጥዬ ወደማላውቀው ከተማ እሰደዳለው…?አንዱንም አላደርግም…፡፡ችግሩን በተለየ መንገድ ነበር የምፈታው…ይሄንን ወደ እሱ ቀየርኩት…አሁን እሱ በህይወት ካለ የሆነች ሴት አፍቅሮ ካስረገዘ በኃላ ደምፁ አጥፍቶ ይሸሻል…?እርግጠኛ ነኝ ቢያንስ እናትዬውን እንኳን ለማግባት ባይፈልግ ልጁን የራስሽ ጉዳይ ብሎ ዞር አይልም፡፡ታዲያ ዛሬ ባገኘውና ጥላቻዬን ባሳውቀው ካዛም አልፌ ልበቀለው ብሞክር ትርጉም ይሰጣል…አይሰጥም..፡፡ምክንያቱም ያ እኔ ማውቀው ልጅ ጠፍቶል… በብዙ ነገር ተቀይሮ በብዙ መከራ ውስጥ አልፎ ብዙ ህይወት ልምዶችን ቀስሞ ሌላ ሰው ሆኖ ነው ማገኘው..እና ሌላ ሰው ባጠፋው ሌላ ሰው የመቅጣት ያህል ነው….ለዛ ነው ይቅር ልለው የወሰንኩት፡፡››

ዘሚካኤል ዝም ነው ያላት…የነገረችውን ጠቅላላ ወደራሱ ህይወት ወስዶ ነው ማሰላሰል የፈለገው…፡፡ከዛሬ ሰባት በፊት የነበረው ዘሚካኤልና አሁን ካለው ዘሚካኤል ፈፅሞ የማይመሳሰል… የተለያየ ፍላጎት ..የተለየ አላማና አመለካከት ያለው ነው ፡፡እና መቶ ፐርሰንት የሚመሳሰሉበት ነገር ቢኖር በስማቸው ነው፡፡እሱንም ቢሆን የአባቱን ስም ስላስቀየረ….መቶ ፐርሰንት ሊባል አይችልም፡፡
//
ከቦንጋ ከተማ የአንድሰዓት እግር መንገድ ሄደው ነው ሰውዬውን ያገኙት፡፡ግዙፉ የሆነ በአረንጎዴ ዛፎችና ተክሎች ተሞላ ውብ ግቢ ነው የገቡት፡፡የሰውዬው ወንድም ነው የተቀበላቸው፡፡ ‹‹ወደማሳ ሄዶል አሁን መምጫው ደርሶል   ግቡና ጠብቁት ››ብሎ ወደግዙፉ የሳር ጎጆ ቤት ይዞቸው ገባ ፡፡ቤቱ ፅድት ያለ ነው፡፡ጥግ ላይ በለአንድ ሜትር የተነጠፈ አልጋ አለ..ከአልጋው አጠገብ ከእንጨት የተሰራ መደርደሪያ አለ..መደርደሪያው ግማሽ በመፅሀፍ ተሞልቷል፡፡ከስር በኩል አንድ መለስተኛ ቴፕ ይታያል፡፡

‹‹ግቡ ››አላቸውን የሚቀመጡበት ወንበር ሰጣቸው፡፡እና መቀመጣቸውን ካረጋገጠ በኃላ ተመልሶ ወጣ፡፡

‹‹አይ ሰውዬው ጥሩ ሁኔታ ላይ ሳይሆን አይቀርም››አላት ዘሚካኤል፡፡

‹‹በምን አወቅክ?››

‹‹አንድ ሰውን እኮ በቤቱ ሁኔታ መገመት ትቺያለሽ..አታይም እንዴ ምንም የቆሸሸ ምንም የትዝረከረከ  ነገር የለም….››

‹‹እንደአፍህ ያድርግልኝ.››አለችው፡፡

ድንገት ዘሚካኤል ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ ተነሳ..ሁኔታው ፀአዳን በጣም አስደነገጣት…እና አብራው ብድግ አለች…የሆነ እባብ ያየ ነው የመሰላት….ተንዳርድሮ ወደአልጋው ተጠጋ ..ከአልጋው በግራ በኩል ባለ መለስተኛ ጠረጴዛ ላይ ብዛት ያላቸው  በፍሬም ያሉ ፎቶዎች ተደርድረውበታል…ቀጥታ ሔደና ተራ በተራ እያነሳ ያያቸው ጀመር….ፀደይ ያልጠበቀችው ነገር ነው ያጋጠማት…ፎቶውን እያየ ወደእሷ ዞረና አፈጠጠባት›

‹‹ይሄ ምንድነው?››
👍509👏2
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///

ዘሚካኤል እንግዳው ላይ አፍጥጦ

‹‹አይ ምንም እየገባኝ አይደለም….?››አለ

ሰውዬውም ዘሚካኤል‹‹ቁጭ በል አስረዳሀለው..››አለና ወደውስጥ ገብቶ ቀድሞ ተቀመጠ…

ፀደይ  ዘሚካኤልን እየጎተተች ይዛው መጣችና አስቀመጠችው…እሷም ተቀመጠችን ስልኳን አውጥታ ሪከርድ ላይ አደረገችና ሰውዬው የሚናገረውን ለመስማት ዝግጁ ሆነች፡፡

‹‹ምን ድረስ ታውቃላችሁ?››

‹‹እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም››ዘሚካኤል በትግስተ የለሽነት መለሰ፡፡

ፀደይ ዝም አለች‹‹ጥሩ ከመጀመሪያው ብጀምርላችሁ ችግር የለውም..እኔ እና እናትህ የልጅነት ጓደኛሞች ማለት ፍቅረኛሞች ነበርን…በጣም ነበር የምንዋደደው…..ምንጊዜም ስለመጋባትና ዕድሜ ዘመናችንን ሙሉ አብሮ ስለመኖር ነበር የምናስበው…ከዛ ድንገት አባቴ ወደአሜሪካ መሄድ አለብህ አለኝ…ብዙ ወንድሞቹ እዛ ስላሉ ሀሳቡን ላስቀይረው አልቻልኩም….አባቴን በጣም ነበር የምፈራው..ከዛ ጥያቄውን ተቀብዬ ወደአሜሪካ ሄድኩ…ለካ እሷ በወቅቱ እህትህን ፀንሳ ነበር..፡፡››

‹‹ፀንሳ ማለት …ከማን?››

‹‹ከማን ይሆናል ከእኔ ነዋ››

‹‹እና እህቴ የአንተ ልጅ ነች…?.ምንድነው የምትቀባጥረው?››

‹‹አልቀባጠርኩም..ከፈለክ አባትህን ጠይቀው …ያውቃል…እናትህ እኔ ጥያት ስለሄድኩ በጣም ተበሳጭታብኝ ስለነበር እና በዛ ላይ አርግዛ ስለነበር…ወዲያው አባትህን አገባችው…ስታገባው..ለልጇ አባት ለማግኘት አንጂ አፍቅራው አልነበረም…እሱም ይወዳት ስለነበረ ተንከባከባት….እህትህም በሰባት ወር እንደተወለደች ነበር ያሰበው…የገዛ ልጁ ነበር የምትመስለው….ስለዚህ ትርሲትን  እንደልጁ አሳደጋት..ከዛ አንተ እና ወንድምህ ተወለዳችሁ፡፡እኔም ከሀያ አመት ቆይታ በኃላ ከአሜሪካ ተመለስኩ፡፡ለእሷ የነበረኝ ፍቅር ከውስጤ ስላልበረደ ፈልጌ አገኘኋት…በጣም ተበሳጭታብኝ የነበረ ቢሆንም ታፈቅረኝ ስለነበረ በሂደት ይቅር አለቺኝ…አባትህን  ፈታ እኔን እንድተገባኝ እጨቀጭቃት ጀመር…እሷም ምንም እንኳን ከእኔ ጋር ለመጋባት በጣም ፍላጎት ቢኖራትም እናንተን መበተን ስላልፈለገች በሀሳቤ ልትስማማ አልቻለችም፡፡

እኔም እሷን ትቼ ሌላ ሴት ማግባት ብሞክርም አልቻልኩም..አቃተኝ…ከዛ በቃ አንቺ እሺ ብለሽ ባልሽን ፈተሸ ማታገቢኝ ከሆነ ቢያንስ ልጄን የማግኘት መብት አለኝ..ለልጄ አባቷ እኔ እንደሆንኩ ንገሪያት እያልኩ በዚህ መጨቃጨቅ ጀመርን፡፡እሷም ያንን ማድረግ አልችልም እያለች መከላከል ጀመረች፡፡በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን በድብቅ እየተገናኘን ፍቅራችንን እንወጣ ነበር…

‹‹ለምን ያህል ጊዜ ከአባቴ እየተደበቃችሁ ..እንደዛ አደረጋችሁ?››ግሽግሽ ባለና ጥላቻ በተጫነው ስሜት ጠየቀው፡፡

‹‹አራት ወይም አምስት አመት››መለሰለት

‹‹እና አባቴ ይሄን ሁሉ ታሪክ ሲያውቅ ነዋ ..ቀልቡን ነስቶት ያንን  ወንጀል የፈፀመው?››

‹‹አይ አይደለም…ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ እስከዛሬ ድረስ ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ  አዝናለው..እመነኝ በጉዳዩ በጣም መፀፀት ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገሬን አጥቼበታለው….፡፡ ስራዬን፤ ጤናዬን …ብዙ ብዙ ነገር…ብዙ ጊዜም ራሴን አጥፍቼ ከልጄ ትርሲት እና ከእናትህ ጎን ለመተኛት ሞክሬ ነበር..ግን በሆነ መንገድ እተርፋለው…መጨረሻ ይሄው እንደምታየኝ የአያቴ መንደር መጥቼ በዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ጀመርኩ..ትንሽም ወደእዚህ ከመጣሁ ነው ጤነኛ የሆንኩት››

‹‹ሰውዬ እኔ ያንተን ፀፀት ለመስማተ  ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም..ስለዋናው ጉዳይ ንገረኝ››

‹‹ትዝ ይለኛል ቀኑ እሁድ ነበር….በእለቱ አባትህ ሞጆ የጓደኛው ለቅሶ ስለነበረ መሄዱን እናትህ ስትነግረኝ..መኪናዬን ከአዲስአበባ አስነስቼ አዳማ ሄድኩ ፡፡እናትህን ተቀጣጥረን ስለነበር ቡቲክ አገኘኋት …እሁድ በዛ ላይ ጥዋት  ስለሆነ የገበያ ግር ግር አልነበረም.. ከዛ የተወሰነ ከቆየን በኃላ የተለመደ ጭቅጭቃችንን ጀመርን‹‹ …ለልጄ አባቷ መሆኔን ወይ ቀድመሽ ንገሪያት ወይ እነግራታለው››አልኳት፡፡

‹‹እሷ ቅጣውን በልዩ ሁኔታ ነው የምትወደው …አባትሽ ቅጣው አይደለም ብላት ልጄ በጣም ነው ምትጎዳው››አለቺኝ፡፡

‹‹ብትጎዳም ለጊዜው ነው…ከውሸት ጋር ለዘላለም ከምትኖር እውነቱን አውቃ ለትንሽ ጊዜ ብትጎዳ ይሻልል››አልኳት
በዚህ ጉዳይ ላይ ለ30 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በከረረ ሁኔታ ስንከራከር ቆየን….ከዛ የስልክ ንግግር ድምፅ ነው  ሁለታችንንም ያነቃን….

እህትህ ትርሲት ከባንኮኒው ማዶ … ፊቷ በእንባ ታጥቦ…አይኖቾ ፈጠውና  አውሬ መስላ ቆማለች..ሱቁ ውስጥ ገብታ እዛ የቆመችበት ቦታ መች እንደቆመች አናውቅም..ምን ያህሉን እንደሳማችንም አናውቅም….ከሁኔታዋ እንደሚታው ግን የሚበቃትን ያህል እንደሰማችን ያስታውቃል…ሁለታችንም በርግገን ጎን ለጎን ተጣብቀን ከተቀመጥንበት ተነሳን….

‹‹ለማን እየደወለች ነው?››ሁለታችንም ግራ ተጋባን፡፡ወዲያው ስልኩ ተነሳላትና ማውራት ጀመረች፡፡

‹‹አባዬ  ….ያንተ ልጅ አይደለሁም እንዴ…?እማዬና ውሽማዋ ሲያወሩ ሰማው…አባዬ እኔ ያንተ ልጅ ካልሆንኩ መኖር አልፈልግም…የሌላ ሰው ልጅ መሆን በጣም ነው የሚቀፈኝ…አይ አልጠብቅህም ..በጣም ነው የምወድህ….››አለችና ስልኩን ግድግዳው ላይ ወርውራ ከሱቁ ወጥታ ተፈተለከች፡፡ልንደረስባት ሞከርን ግን ወዲያው ተሰወረችብን፡፡

‹‹ወይኔ ልጄ….ወይኔ ልጄ…››እናትዬው ተርበተበተች....እኔም የምይዝው የምጨብጠው ግራ ገባኝ….ሱቁን ዘጋንና….

‹‹ወደየት ነው የሄደችው?››ስል እናትህን ጠየቅኳት፡፡‹‹እኔ ምናውቃለው..ወደቤት ከሄደች…ሄጄ ልያት››አለችኝ

‹‹በቃ ነይ መኪና ውስጥ ግቢ››ስላት

‹‹እንዴ ..አንድ ላይ ስንሄድ..?››

‹‹አሁን እኮ ነገሮች ተደበላልቀዋል…ምንፈራው ሳይሆን የምንጋፈጠው ነው››አልኳትና እየጎተትኩ መኪናዬ ውስጥ ይዣት ገባው፡፡በየመንገዱ እየፈለግናት…ልትሄድ ትችልበታለች ብላ እናቷ የጠረጠረችበት  አንድ ሁለት ቦታ አቁመን አይተን መጨረሻ ወደቤት ሄድን…መኪናውን ራቅ አድርጌ እንዳቆም አደረገችኝና…‹‹እኔ ገብቼ ልያትና ካለች እነግርሀለው..ከሌለችም ሌላ ቦታ ሄደን እንፈልጋታለን›› ብላኝ ገባች፡፡እኔም በጭንቀት እየተንቆራጠጥኩ መጠበቅ ጀመርኩ…5 ደቂቃ ..10 ደቂቃ አለፈ..ስልኬን አውጥቼ ስደውል እናትህ ሞባይል አይነሳም…ራሴን መቆጣጠር አቃተኝና የሆነው ይሁን ብዬ ወደግቢው ገባው፡፡ሳሎኑ በራፍ እንደተከፈተ ነበር…ስገባ  ልጄ ኮርኒሱ ላይ ተንጠልጥላለች..እናትህ ደግሞ የገዛ ሆዷን ላይ ቢላዋ ሽጣ ተዘርራለች፡፡ይመስለኛል እናትህ ወደቤት ስትገባ እህትህ ተሰቅላ እራሷ አጥፍታ ስታያት ወዲያው አካባቢው ላይ ያገኘችውን ቢላዋ ሆዷ ውሰጥ የሻጠችው ይመስለኛል፡፡

ከዛ ደንዝዤ የምሆነው ጠፋኝ…ምን ላድርግ ..?ልጄን ከተሰቀለችበት ለማውረድ ገመድ መቁረጫ ለመፈለግ ወደውስጥ ገብቼ መቁረጫ ይዤ ስመለስ አባትህ ከውጭ ከሳሎኑ ሲገባ አየሁት፡፡በደመነፍስ ወደ ጎሮ በራፍ ሄድኩ…ዞሬ ከግቢው ወጣሁና መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ደም እንባ እያለቀስኩ ሁኔታዎችን መከታተል ጀምርኩ፡፡ ከዛ አንተና ወንድምህ አንድ አይነት ሰማያዊ የስፖርት ልብስ ለብሳችሁ ወደቤት ስትገቡ ተመለከትኩ፡፡ ከደቂቃዎች በኃላ ፖሊሶች ሰፈሩን ወረሩት…እናንተንም አባታችሁንም ፖሊሶች ይዘዋችሁ ሲሄድ የእናትህንና የእህትህን አስከሬን በአንብላንስ ሲወሰድ ከመንገድ ማዶ መኪናዬ ውስጥ ተቀምጬ እየተመለከትኩ ነበር፡፡ ሁለቱም እራሷቸውን  እንዳጠፉ እርግጠኛ ነኝ፡፡
👍6519
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡

የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አዲስ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ አንተስ?››

‹‹እኔ በጣም ደህና ነኝ…ሚካኤል ይደውልልኛል ብዬ እየጠበቅኩ ነበር፡፡››

‹‹ይደውልልሀል..አሁን ኩማንደሩ ቀጥሮት ሊያገኘው ሄዶል …ከእሱ እንደጨረሰ እርግጠኛ ነኝ ይደውልልሀል፡፡…አታስብ ኩማንደሩ ደግሞ ያንተ አድናቂ ስለሆነ ከአባታችሁ እንድትገናኙ ሁኔታውን ያመቻቻል….በዛ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው

‹‹ጥሩ ታዲያ አንቺ ሰላም ነሽ?››

‹‹በጣም ሰላም ነኝ…ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ  ነበር››

‹‹ምን?››

‹‹ከፀዲ ጋር እንዴት ናችሁ?››

ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኋላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡

ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››

‹‹ግልፅ ሆነህ ንገረኝ…ስለእሷ ምን ታስባለህ..ማለቴ አሁንም በፊት እንደነገርከኝ ታፈቅራታለህ?››

‹‹እንዴ!እንዴት በአንድ ወር ፍቅሩ ይተናል ብለሽ አሰብሽ? እንደውም ጥሩ ነገር አነሳሽልኝ…የሆነ ቀን አመቻችቼ ካንቺ ጋር መነጋገር እፈልግ ነበር..እኔ ላገባት እፍልጋለው..በቅርብ ቀን..እና እንዴት ጠይቄ ላሳምናት የሚለውን ከእኔ ይልቅ አንቺ ስለምታውቂ እንድታማክሪኝ እፈልጋለው፡፡››

‹‹እንግዲያው እንደዛ ከሆነ ሳይረፍድብህ ፍጠን››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ያንተን ልጅ አርግዛለች..››

የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…

‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››

‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡

በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል  ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ  ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል  ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኋላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››

‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በበቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡

የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ  መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡

ፀአዳ ቤት ሲደርስ በራፏ ዝግ ነበር..ሊደውልላት አልፈለገም ፡፡ሻንጣውን አወረደና በራፏ በረንዳ ላይ አድርጎ እሱ መኪናው ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ጀመረ…ከምሽቱ አንድ ሰአት ስትመጣ እሱ መኪና ውስጥ ሻንጣው በረንዳ ላይ ሆኖ ስታየው ፍፁም ነው ግራ የተጋባችው…ምስር  እሱ መሆኑን ስታውቅ ከእናቷ ተነጥላ ወደእሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ፈጥኖ ከመኪናው ወረደና እጇቹን እንደክንፍ ዘርግቶ ጠበቃት…ተጠምጥማበት በደስታ ጉንጩን ትስመው ጀመር…
ወደቤት እንደገቡ ፀደይ‹‹ምንድነው ጉዱ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምንም ..ለጥቂት ሳምንታት እረፍት ስለሆንኩ እዚህ ከእናንተ ጋር ለመቆየት ወስኜ ነው፡፡››

‹‹እዚህ ከእኛ ጋር?››

‹‹አዎ ከእናንተ ጋር››
ህፃኖ ምስር ‹‹ታድለን…ታድለን›› እያለች መጨፈር ጀመረች፡፡

ፀአዳ ልጇ ምስር ፊት ምንም ማለት አልቻለችም.‹‹እንግዲያው እደቤትህ ዘና በል…እኔ ልብስ ልቀይር ››አለችና መኝታ ቤት ገባች፡፡ከዛ እራት ሰርታ በሉና ከሶስት ሰዓት በኃላ ምስርን አስተኝተው ነበር እንደአዲስ ጭቅጭቁን የጀመሩት፡፡

‹‹ምን እየሰራህ ነው?››

‹‹እንደምታገቢኝ ቃል ገብተሸ ቀለበት እስክታስሪልኝ ድረስ ከዚህ ቤት ወጥቼ ወደቤቴ አልመለስም››ሲል ቁርጡን ፍርጥም ብሎ ነገራት፡

‹‹ጭራሽ ማግባት? እየቀለድክ ነው፡፡››

‹‹በፍፅም …ብቀልድ ነው እንደዚህ አይነት እርምጃ የወሰድኩት፡፡››

‹‹ስማ..እኔ ካንተ ጋብቻ ፍቅር ምናምን አልፈልግም››

‹‹ታዲያ ምንድንው ምትፈልጊው?››

ትኩር ብላ አየችው….
‹‹ንገሪኝ ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው….. ?››

‹‹ካንተ ወሲብ ብቻ ይበቃኛል….ማለቴ እስከአሁን የደረግነውን ለማለት ነው …ደግሞ  አሁንም እናድረግ እያልኩህ አይደለም፡፡››

በንግግሯ ሆድን እስኪያመው ሳቀ…በመሀል ስልክ ተደወለለት ..ከወንድሙ ነበር…በጉጉት አነሳው‹‹እሺ ሚካኤል ደህና አመሸህ?››

‹‹ሰላም ነኝ…ነገ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ አዳማ መገኘት ትችላለህ?››

‹‹ምነው ?አባዬን እንድናገኝ ፈቀዱልን እንዴ?››

‹‹አዎ በጣም ደስ የሚለው ደግሞ አንድ ላይ እንድናገኘው ነው ያመቻቹልን ቅር ካላለህ አዲስንና ቅዱስንም ይዘናቸው እንሄዳለን››

‹‹አረ ቅር አይለኝም ጥሩ ሀሳብ …ግን አባዬ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ የሚሆን ይመስልሀል?››ሰሞኑን ሲብሰለሰልበት የነበረውን ስጋቱን አንስቶ ጠየቀው፡፡

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከመሞቱ በፊት ማግኘት የሚፈልገው ብቸኛ ነገር እኮ አንተን ማናገር ነው…በደስታ  ነው የሚያነባው….እንኳን በአካል አግኝተሀው አባዬ ብለህ ስጠራው ሰምቶ ይቅርና ባለፈው ፎቶህን ሳሳየው እንዴት እያገላበጠ ሲስምና ሲያለቅስ እንደነበረ እኔ ነኝ የማውቀው…በል በዛ እርግጠኛ ሁን..ምንም አትጨናነቅ፡፡››

‹‹ምን ያስፈልገዋል…?ማለት ምን ይዤለት ልሂድ?››

‹‹የሚያስፈልገወን ነገር ሁሉ አዘጋጅተናል…አንተ ደግሞ ሚፈልገውን ነገር እንጠይቀውና በሚቀጥለው ዙር ትወስድለታለህ…ደግሞ ደስ የሚለው ከቦንጋ ያመጣችሁትን ከዶ/ሩ ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ለኩማንደሩ አሰምቼው በጣም ነው ያዘነው..እናም አባዬን ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር ወስነዋል…››

‹‹በጣም የሚያስደስት ነገር ነው እየነገርከኝ ያለሀው..ወንድሜ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንክ ታውቃለህ አይደል… በጣም ነው የምኮራብህ፡፡››

ሚካኤልም እንባ እየተናነቀው‹‹እኔም በጣም ነው የምኮራብህ››አለው

‹‹በቃ እሺ …...ሶስት ሰዓት ነው ያልከኝ አይደል?፡፡››

‹‹አዎ…መድረስ ትችላለህ አይደል…?››

‹‹በደንብ እንጂ ሁለት ተኩል ደርሼ ደውልልሀለው››

‹‹ጥሩ በቃ ደህና እደር››ስልኩን ዘጋ፡፡

ንግግራቸውን ሁሉ በገረሜታ ስትሰማ የነበረችው ፀደይ‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ሁለት ተኩል ትደርሳለህ?››ስትል በፈገግታ አሾፈችበት፡፡

‹‹ትቆጪኛለሽ ብዬ ነው እንጂ እዚህ ነኝ ልለው ነበረ››

‹‹ልፋ ቢልህ ነው ….ግን ለእናንተ ደስ ብሎኛል››

‹‹ማለት?››

‹‹አንተና ወንድምህ እንዲህ እየተደዋወላችሁ በሰላም ማውራት መቻላችሁ ትልቅ ነገር ነው…አረ እንደውም ከመነጋጋርም አልፋችሁ መሞጋገስ ጀምራችኃል››

‹‹እድሜ ለአንቺ ….ባንቺ ቀናነትና ጥረት ነው ለዚህ የበቃነው….››

‹‹እኔን ማሞገሱን እንኳን ለሌላ ጊዜ አቆየው..በነገራችን ላይ የአባትህ ጉዳይ ላይ  ይግባኝ ለመጠየቅ ሚቻል ከአሆነ አንድ ጎበዝ ጠበቃ አግኝኝቼ ሁኔታውን አስረድቼው ነበር….››

‹‹በእውነት ..ታዲያ ምን አለሽ?››
👍6824👎1👏1