አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

በፊት ፍቅር ማለት....?ብለው ሲጠይቋት በመራቀቅ እና በልበ ሙሉነት ትዘረዝር ነበር::አሁን ከዚህ ልጅ ጋር በአጋጣሚ ከተላተመች በኃላ ግን...ፍቅር ማለት ...?ብለው ሲጠይቋት መልሷ  ረጅም ዝምታ  ነው።እንደዛ ማድረጓ ፈልጋ አይደለም  …ከእሱ ጋር ከተጋራችው ስሜት አንፃር ፍቅርን ለመተንተን ብቁ የሆነ ሀሳቧን የሚመጥን ቃል  በከንፈራ ላይ ስለሌለ ነው።

በቀደም ሜቅዶኒያ በሄድ ቀን በጣም አሪፍ ሚባል ጊዜ ነበር ያሳለፉት…ከአባቱ ጋር አስተዋወቃት…አብረው ከሁለት ሰዓት በላይ አዛውንቶቸን በመንከባከብ የሚሰሩ የበጎ ስራ አገልግሎት ሰራዎችን  ሰሩ፡፡
ይሄ ተግባር  ለቃል  የዘወትር የእለተ እሁድ የግማሽ ቀን ተግባሩ ነው…ለልዩ ግን የመጀመሪያ ኤክስፒሪያንሶ ነበር..እና ከጠበቀችው በተቃራኒ እጅግ አስደሳችና ጭፈራ ቤት አምሽቶ ከመዝናናት በላይ በተሻለ ጥልቅ የሆነ ደስታ የሚሰጥ ተግባር ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡
ስራቸውን ጨርሰው በአባቱ ተመርቀው እና ተሰናብተው ከወጡ በኃላ መንገድ ላይ‹‹ምንም ነገረ ሳይከፈል ምንም ነገር ጥቅም ሳይገኝበት እንዲህ አይነት ፈታኝ ስራዎችን  መስራት የሚገርም ስብዕናን የሚጠይቅ  ነው››አለችው፡፡
‹‹ አይ በነፃ ይመስልሸል እንጄ በነፃ አይደለም…በዚህ ምድር ላይ ያደረግሽው ሁሉ ይመለሰልሻል.አሁን እነዚሀ የአረጋዊያንን ልብስ አጥበሽ በምርቃት ብቻ ተቀብለሽ ስትሄጂ በነፃ ያገለገልሽ መስሎሽ ይሆናል..ግን በሌላ መንገድ ታገኚዋለሽ…ለምሳሌ አሁን አይበለውና መኪናሽ ከሆነ መኪና ጋር ተጋጭታ አደጋ ደርሶብን ሆስፒታል ብንገባ   አንድ የማናውቀው ሰው ለሁለታችንም በናፃ ደም ለግሶን ከሞት ሊያተርፈን ይችላል፡፡ …ያደረግሽው በጎ ነገር ሁሉ ይፍጠንም ይዘግይም ይመለስልሻል…መጥፎውም ነገር እንደዛው›› እንደዛ ነበር ያላት፡፡
ያው እሷ በሰዓቱ ምንም እንኳን በንግግሩ ብትደመምም በትክክለኝነቱ ግን ሙሉ በሙሉ አላመነችበትም..ቢሆንም የሰማችው ግን በፅሞናና በመመሰጥ ነበር…ባለው ነገር ሙሉ እምነት ያልተሰማት ምክንያት ዕድሜያቸውን ሁሉ ክፍ ስራ እየሰሩ ግን ደግሞ በሰላም የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በዙሪያዋ ስለምታውቅ ነው፡፡ለቃል ግን እንዳዛ አላለችውም…፡፡ምን አልባት እንደዛ ብላው ቢሆን ‹‹በሰላም እየኖሩ መሆናቸውን በምን አወቅሽ…? ሰላም ማለት እኮ ትርጉሙ ሰፊ ነው..በህይወታቸው ደስተኛ ናቸው…?ጥሩና ሰላማዊ እንቅልፍ እየተኙ ነው…? አይነት ጥያቄዎችን በመጠየቅ በእጅ አዙር ይመልስላት እንደነበር እርግጠኛ ነበረች፡፡
ከዛን ከሰአት እንጦጦ ሄድ.. በየካፌውና ሬስቶራንቶቹ እየቀያየሩ ድንቁና አረንጓዴ  የሆነውን ወጣ ገባ መልካ ምድር እየጎበኙ ንፅህንና ነፋሻማውን አየር እየማጉ በደስታ ሲፈነጥዙ ዋሉና ማታ አንድ ሰዓት እቤቱ በራፍ ድረስ አድርሳው  ቅር እያላት ወደቤቷ ሄደች…፡፡
ከዛን ወዲህ ሁለት ቀን ተገናኝተው ሻይ ቡና ብለዋል…አሁን ግን ካየችው ሌላ ሁለት ቀን አለፋት ፡፡ናፍቆታል፡፡‹‹
‹‹አይገርምም ..አሁን ናፍቆኛል ስል መድህኔ ቢሰማ ምን ያህል ልቡ ይሰበራል?››ሳታስበው እራሱ ዝግንን አላት…፡፡ቢሆንም  ግን መናፈቋ የማይካድ ሀቅ ነው: አሁን በዚህ ምሽት እያደረገች ያለችው አልጋዋ ላይ እየተገላበጠች ስለእሱ ማሰላሰል ነው..ስለመድህኔ አይደለም…ስለቃል እንጂ ፡፡
‹‹አዎ እስኪ አይኑን ልየው›› አለችና ከመኝታዋ ተነስታ ላፕቶፖን ከተቀመጠበት አመጣች፡፡ ወደቦታዋ ተመልሳ ከፈትችው፡፡
እንዲህ አይነት ስራዎችን በተለያዩ ሰዎች ላይ እንደምትሰራ  የምታውቅ አንድ የትምህር ቤት ጓደኛዋ‹‹ ለምን ግን ደህንነት መስሪያ ቤት ሲርቪስን አታስገቢም፤አንቺ እኮ የተፈጠርሽው ሰላይ ለመሆን ነው፡፡ ብልሀቱንም፤ተንኮሉንም ማስመሰሉንም ተክነሽበታል››ትላት ነበር…፡፡በወቅቱ አስተያየቷን ብትቃወማትም አሁን ሳታስበው ግን እውነቷን ነው ብላ ማመን ጀምራለች፡፡
..ከእሱ መኝታ ቤት የቀበረችው ካሜራ ጋር የሚያገናኘውን ቁልፍ ተጭና እሱ ወደ መኝታ ቤቱ እስኪገባ መጠበቅ ጀመረች፡፡የፊት ለፊቱ ክፍል እንዳለ አውቃለች፡፡ ሙዚቃና አንዳንድ የሚንጋጉ ድምፅች  ከሚቀጠልው ክፍል ውስጥ መኖሩን ያሳብቃሉ…፡፡
መኝታ  ቤቱ ተከፈተ…ቃል ገባና በራፉን ዘጋው…፡፡ትኩረቷን ሰብስባ መከታተል ጀመረች፡፡ወደ ቁም ሳጥኑ ቀረበ፡፡ከፈተ.. ፡፡ቢጃማ አወጣ..፡፡
‹‹ውይ ልብሱን  ሊቀይር  ነው…፡፡››አለች..ግራገባት…ምን ታድርግ..?፡፡
‹‹ለጊዜው ቀይሮ እስኪጨርስ ላፕቶፑን ልዝጋው..ወይስ እኔ ከስሩ ዞር ልበል..?፡፡›› ውሳኔ ላይ ሳትደርስ ከላይ የለበሰውን ሸሚዝ አወለቀና በስነስርአት አጣጥፎ ጥግ ላይ ካለች ጠረጴዛ  ላይ አስቀመጠ..ሲሊፐሩን አወለቀና ባዶ እግሩ ምንጣፍ ላይ ቆመ፡፡ ሱሪውን መዥርጦ አወለቀ…ሰማያዊ ፓንት እየታያት ነው፡፡
‹‹..ወይ ምን እየሰራሁ ነው….?.ሱሪውን በተመሳሳይ አጣጥፎ  አስቀመጠ…፡፡
‹‹እንዴ ሌላ ነገር ሊያወልቅነው እንዴ?›› ስትል እግዜር ይስጠው አልጋው ጠርዝ ላይ አስቀምጦት የነበረውን ፒጀማ አነሳና በየተራ ለበሰ…፡፡መሀል ወለል ምንጣፍ ላይ በጉልበቱ ተንበረከከ… …፡፡
‹‹እንዴ ምን እየሰራ ነው..?ስትል እጁን ወደፊቱ ዘረጋ….ከዛ ድምፅ አውጥቶ ከዚህ በፊት ሰምታው የማታውቀው አይነት አዲስ ፀሎት መፀለይ ጀመረ..‹‹ታድሎ የየትኛው ሀይማኖት ፀሎት ይሆን ..?ምን አልባት አንድ ቀን በደንብ ስንግባባ ጠይቀው ይሆናል..እናም አብሬውም ከጎኑ ተንበርክኬ እጆቹን በእጆቼ ይዤ እፀልይ ይሆናል፡፡››ስትል ተመኘችና ፀሎቱን በጥሞና መከታተል ጀመረች፡፡
///
የውበቶች ሁሉ ድምር ውበት...የሙዚቃዎች ሁሉ ጥቅል ዜማ....የብርሀን ሁሉ  ብርሀን ...የሠው ልጆች ሁሉ ጥምር እስትንፍስ ...እሱ እግዚያብሄር ነው።መላእክቶች ቅርንጫፍ ላይ የበቀሉ ወረቃማ ቅጠሎች ናቸው። ፀሀይ ከልብ አንድ ጥግ መንጭታ  ለአጥናፍ አለሙ ብርሀንና ሙቀት የምትለግስ  የህይወት ምንጭ ነች።  ጨረቃ ከአይኖቹ ብሌን ጫፍ የምትገኝ  የውበት ፈርጥ ነች..ከዋክብቱ ግንባሩ ላይ ልክ እንደፀጉር የተበተኑ  ድንቆች ናቸው ....እኛ የሰው ልጆች  የአእምሮው ህብረሰረሰር ቅንጣት ህዋስ ነን።የእኛ ኢምንት ሀሳቦቻች  ከሱ  እልቆ መሳፍርት ሀሳብ  እየተሸረፍ ሚበተኑ ህልሞቻችን ናቸው። አፅናፍ አለም በእጅ መዳፍ ላይ የተበተኑ የሚነበብና የሚተነተኑ  መስመሮች ናቸው። የምድር ደኖችና ተክሎች  እግሮቹ ላይ የበቀሉ ፀጉሮች ናቸው።  የፍጥረታት ነፍስ ከትንፍሹ የተሸረፈች  የህይወት እርግብግቢት ነች።እግዚያብሄር ሁሉም እና አጠቃላዪ ማለት ነው። ጥልቀቱ ወሰን አልባ ርዝመት የማይደረስበት ...ልኩ ይሄን ያህል ነው የማይባል ...  የነገሮች ሁሉ የመጨረሻው ቅንጣት ኢነርጂ ... በጊዜ የማይገመት በቦታ የማይታጠር   ኤልሻዳይ አምላክ ነው።
/
ከዛ ፀሎቱን እንደጨረሰ ትንፋሽ በጥልቀት ወደውስጥ እየሳበ ከዛ አምቆ ይቆይና ወደውጭ ይለቀዋል…መልሶ ወደውስጥ ይስብና ወደውጭ ይለቀዋል.. ያለመታከትና መሰልቸት ለአስር ያህል ደቂቃ እንደዛ ካደረገ በኃላ...ባለበት ያለምንም እንቅስቃሴ አይኖቹን ጨፍኖ ፀጥ አለ…፡
👍794🔥1
#ህያበ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_ኤርሚ

"እሱን እንዳታስቢው ወይም ራስሽ ፈልገሽ አግኝው... ደግሞ አታገኝውም" አማራጭ የለኝም ሻንጣዬን ይዤ ወደኋላ ተመለስኩ።

"እሺ ውሰደኝ አሁን ውሰደኝ"

"አይ አይሆንም ነገ ነው የምንሄደው" በእሽታ አንገቴን ነቀነኩለት።

ወደቀኝ ገልመጥ ብዬ ሳይ የሰርግ ቬሎዬ ተሰቅሏል። ለራሴ ወደኋላ የለም አልኩ...

"አንደርስም እንዴ ደግሞ እኮ አይኔን በጨርቅ አስረህዋል። የት ነው የምንሄደው ራቀብኝ? ያ ውሻ የት ነው ያለው?"

"አይንሽን ከገለጥሽ ከኔ ጋ ትጣያለሽ ማርያምን የምሬን ነው። ታገሽ ትንሽ ነው የቀረን ደርሰናል" ጥቂት ደቂቃ ከተጓዘ በኋላ መኪናውን አቆመው

"አሁን ጨርቁን ማንሳት ትችያለሽ" ቶሎ ብዬ ፈታሁት... ሰው የሌለበት ቦታ ነው።

"ምንድነው ቢኒ እየቀለድክብኝ ነው" ፊቴን አዙሬ በንዴት አየሁት

"ውረጂ.,. ያውልሽ እዛጋ ይታይሻል...( በወዳደቁ ነገሮች የተሰራች ቤት) እዛ ውስጥ አለልሽ ውረጂና የፈለግሽውን አድርጊው" ሳላቅማማ ወረድኩ። በእልህና ንዴት እየተራመድኩ ወደቤቱ ተጠጋሁ ልገባ ስል

"እባቷ ነኝ ባሏ. ... ሀ ሀ ሀ... ንገሩኝ እስኪ እናቷን አግብቶ ልጁን ያስረገዘ አባት ታውቃላችሁ... አታውቁም? ሙትቻ ለምንድነው የምታፈጡብኝ... መልሱልኝ... ኧረ ተውኝ ኡ ኡ ኡ..." ጩኸቱ አስደንግጦኝ ወደኋላ ተመለስኩ። ትንሽ ተራምጄ ቆምኩና ልጄን አሰብኳት "እገለዋለሁ" ወደ ቤቷ ተመለስኩና ከፍቼ ጎንበስ ብዬ ገባሁ። የቤቱ ጠረን ይገፈትራል ሰው የመጣም አልመሰለው ዝምም ብሎ ልፍለፋውን ቀጥሏል። የማላውቃቸውን ብዙ የሴት ስሞች ይጠራል... ያለቅሳል፣ ይስቃል፣ ይራገማል፣ ድንገት ደግሞ አስደንጋጭ ጩኸቱን ይለቀዋል። ለደቂቃዎች ዝምምም ብዬ ሰማሁት... በብዙው የቤቱ ቀዳዳ በሚገባ ብርሀን አየሁት ከድምፁ ውጪ ምኑም እሱን አይመስልም። ልብሱ ተቀዳዷል፣ ፊቱ ጠቁሮ ከሰል መስሏል፣ ፀጉሩ ተንጨባሯል፣ እላዩ ላይ ተፀዳድቶ መሬቱ ጭምር በሽንትና ሰገራ ተበክሏል። ዮኒ እኔ ልሰጠው ካሰብኩት ሞት በላይ በቁሙ ሞቷል... ልቤን ሽው የሚል የሀዘኔታ ጦር ወጋኝ። ወዲያው ደግሞ ልጄን የከዳኋት መሰለኝ... እየሮጥኩ ከቤቱ ወጣሁ... ልፍለፋው ከኋላዬ ይሰማኛል... እያለቀስኩ መኪናውን ከፍቼ ስገባ

"አደረግሺው ህያብ ገደልሽው" አለኝ

"ሞቷል እኮ ቢኒ የሞተን ሰው ድጋሚ እንዴት እገለዋለሁ" ድፍት ብዬ ተንሰቀሰቅሁ

"ቢኒ እባክህ ምንም ሰላም ሊሰማኝ አልቻለም ዮኒን ሆስፒታል እንውሰደው" ደረቱ ላይ ተኝቼ ለቀናት ከራሴ ጋ ስከራከርበት የነበረውን ሀሳብ ነገርኩት

"እኔ የማውቃትም የምወዳትም ህያብ ይቺ ናት ለጠላቷ ሳይቀር የምትራራ። አታስቢ የኔ ቆንጆ ዛሬውኑ እናደርገዋለን" እዛው ቦታ ተመልን ሄድን። ወደዛች ቤት ገባን አጠገቡ ዳቦ ቁጭ ብሏል። ለነፍሱ ያደረ ሰው እንደሚመግበው ገባኝ። መለፍለፉን አላቆመም እንጂ ተዳክሟል... ይዘናቸው የሄድነው ባለሞያዎች በግድ አንስተው ስትሬቸር ላይ አደረጉት... ከኪሱ የተጣጠፈ ወረቀት ወደቀ፤ ቀልጠፍ ብዬ አነሳሁትና ዞር ብዬ ከፈትኩት በትልቁ ርዕስ "ፀፀት" ይላል። ከስሩ ደግሞ "ለማታዩኝ እኔ ግን በየቀኑ ለማያችሁ ለበደልኳችሁ ሁሉ" ይላል... ትርጉም ያለው ነገር ሊሆን ቢችልም ማንበብ አልፈለኩም... ሌላ ሸክም መሸከም አልፈልግም... እጄ ላይ ያለውን ሶስት ገፅ ወረቀት ቀዳድጄ ዱቄት አደረኩትና ለነፋስ ሰጠሁት ብትትንን... አምቡላንስ ውስጥ አስገብተው ይዘውት ሄዱ። ሰላም ተሰማኝ

አዳራሹ በእንግዶች ጢም ብሎ ተሞልቷል። ቃል የሚያገባቡን ቄስ ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል።

"በሀዘን በደስታዋ በህመም በጤናዋ..." ቢኒ ቃል ገባ እሱ ያለውን መልሰው እኔንም አስባሉኝ።

የጋብቻ ቀለበት ጣቴ ላይ አደረገልኝ እኔም እንደዛው አደረኩለት.....
ገና ወደሰውነት ቅርፅ ያልተቀየረው የአምስት ሳምንት ልጄ ደስ ብሏት/ብሎት ይሆን ሆዴን ዳበስኩት። የልጄ አባት ቢኒ ፈገግ ብሎ አየኝ

"ተመስገን" አልኩ በልቤ የማያልፉ የመሰሉኝ ሁሉ አለፉ... ዛሬ ደስተኛ ነኝ... ነገን አምላክ ያውቃል።

ተ ፈ ፀ መ
👍11249👏2
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

የድባለ አባት ኬድሮንን እንዳያት.. እጁን እንዳንከረፈፈ ከተቀመጠበት ተነሳና‹‹ኬድሮን ምን ተፈጠረ…?ምን ሆንሽ ?›› እያለ ወንበሩን ለቆ ወደእሷ ቀረበ፡፡

ሴትዬዋ መለፍለፏን አላቆመችም….‹‹ምንድነች ማነች…? ታውቃታለህ እንዴ…?ነው ሚስትህ ነች የላከቻት..?››

‹‹አይ  አይደለም…ተረጋጊ የጎረቤት ልጅ ነች.?››

‹ትሁና ..ነይ ውጪልኝ…ቤቴን ማንም እንዲደፍረው አልፈልግም …ከፈለክ ውጭ አናግራት ›› ብላ ክንዷን ይዛ ልትጎትታት ብትሞክርም ንቅንቅ ልታደርጋት አልቻለችም…ሴትዮዋ ግራ ግብቷት እራሷን  አጠንክራ ደግመኛ ሞከረች….ግዙፍ የዋርካ ግንድ የማነቃነቅ  አይነት ነው የሆነባት፡፡
‹‹ምንድነች ይህቺ ጉድ …ውስጧ  ጋንኤል አለ እንዴ?››ስትል የድብአለ አባት በቆመበት ደንዝዞ ሚገባበት ጠፍቶት ኩምሽሽ አለ...የድብአለ  አባት በእነኬድሮን ሰፈር ኬድሮን ከመወለዷ  በፊት የገባ በመሆኑ ስለእሷ ታሪክና ሀሚቶችንም ጨምሮ በዝርዝር ስለሚያውቅ ነው የተጨነቀው…ሴትዬዋ ደግሞ ገና ወደ ደሎ ከተማ ከገባች 6 ወርም ያላለፋት በመሆኑ ስለ እንደዚህ አይነት ታሪክ ምንም ምታውቀው  ነገር የላትም፡፡

‹‹ጋሼ  ለአዲሷ ሚስትህ ስለእኔ አልነግርካትም እንዴ?፡፡››

ሰውዬው ልክ በጣም ሚፈራውን ባለስልጣን እንደሚያናግር ሰው አንገቱን ደፍቶ ዝም አለ፡፡
በጥርጥሬ ልጅቷን አትኩራ እየተመለከተች‹‹ምንድነው ያልነገርከኝ…?ነው ልጅህ ነች…?›ስትል ጠየቀች ፡፡

‹‹አይ የእሱ ልጅ አይደለሁም…እናቴ በሬዱ ትባላለች፡፡ በሬዱ ዲንቃ….አባቴ ደግሞ ዳቢሎሰ ነው…እና ለአዲሱ ባልሽ መልእክት ለመናገር ነው የመጣሁት….ሚስትህ ልጆቾን ይዛ ወደሀገሯ ልትሄድ ነው..እኔ ደግሞ ድባአለ  ጓደኛዬ ስለሆነ እንዲሄድ አልፈልግም…ማለቴ እውነቱን ለመናገር  እኔ እንኳን ቢሄድ ብዙ ግድ የለኝም.. ግን እሱ እኔን ጥሎ መሄድ እንደማይፈልግ እያለቀሰ ነው የነገረኝ…እውነቱን መሆኑን ደግሞ አይኖቹን አይቼ አምኜዋለሁ፡፡ ስለዚህ እንዲሄዱ አልፈልግም…እንዳይሄዱ ደግሞ አንተ እሷን ይቅርታ ጠይቀህ ወደልጆችህ ትመለሳለህ፡

‹‹አንቺ ምን አይነት ጉድ ነሽ…በዚህ  ዕድሜሽ ስለ እንዲዚህ አይነት ነገሮች  ምኑን አውቀሽ ነው ምትዘባርቂው…ይሄኔ ቤተሰቦችሽ ጠፍተሸባቸው እየፈለጉሽ ነው…በይ አሁን ቤቴን ለቀሽ ወደቤትሽ ሂጂ››ሴትዬዋ ተንዘረዘረች …

የድባአለ  አባት ምንም ለመናገር አልደፈረም፡፡

ኬድሮን መናገር ጀመረች..‹‹አንዳልሺው እሄዳለሁ....አሁን ሁለታችሁም ዘና ብላችሁ የጀመራችሁትን እራት ብሉ… ከዛ ስትተኙ ያልኩትን  ባተፈፅሙ ምን እንደሚያጋጥማችሁ ቀድመ ማስጠንቂያ እንዲያሳያችሁ ለዳቢሎሱ አባቴ አሁን ነግሬዋለሁ…እና ምርጫውን  የእናንተ ነው…እርግጠኛ ነኝ የዱብአለ አባት ነገ ለእራት ቆቅ  ወይም ጅግራ አድኜ አመጣና ወደልጆችህ መመለስህን በማስመልከት አብረን እራት እንበላለን….አንቺም ሌላ ሚስት የሌለው ባል እንደምታገኚ እምነቴ ነው.››ብላ ፊቷን አዙራ ስትወጣ ሰውየው ከደነዘበት እንደመባነን ብሎ ‹‹ኬድሮን ልሸኝሽ ?መሽቷል እኮ›አላት፡፡

‹‹አይ ጋሼ እንደማልፈራ ታውቃለህ አይደል? ›

‹‹አዎ እሱስ አውነትሽን ነው፤ደህና እደሪ››ብሎ በቆመበት ሸኛት፡፡
እቤቱን ለቃ እንደወጣች ሴትዬዋ ተንደርድራ በራፏን ከቀረቀረች በኃላ ወደውሽማዋ  ዞራ

‹‹ምን ጉድ ነው ?ማነች ይህቺ ልጅ….?ደግሞ የዳቢሎስ ልጅ ነኝ ትበለኝ እንዴ …?በእሷ  ቤት ማስፈራራቷ  ነው?ወላጆቾ በዳቢሎስ እያሰፈራሩ ነው ያሳደጓት መሰለኝ?››

‹‹እውነቷን ነው…እናቷ ከዳቢሎስ ነው የፀነሰቻት ተብሎ ይወራል›› ብሎ  በመጀመር ሙሉ ታሪኳን ከመጀመሪያው አንስቶ በሚያውቀውና በሰማው መጠን ብትንትን አድርጎ አስረዳት….ሴትዬዋ ይበልጥ በነገራት ቁጥር ይበልጥ በፍራቻ እየተንዘፈዘፈችና እተንቀጠቀጠች ነበር..

‹‹ምን አይነት ጣጣ ውስጥ ነው የገባሁት..?እና ምን ይሻለናል…?››
‹‹ለማንኛውም አሁን እንተኛና..  ነገ የሚሆነውን አይተን እንወስናለን››
አልተከተራከረችውም…እንደቅዱሙ ጩሀቱም ወኔውም ከውስጧ ተሰልቦ ባዶ ሆኗል፡፡ ሹክክ ብላ ወደ አልጋው ሄደች፡፡ እሱም ተከተላትና እንደወትሯቸው ተቃቅፈው ግን ደግሞ በዝምታ ተኙ፡፡

ኬድሮን ቤታቸውን ለቃ ወደቤቷ በድቅድቅ ጨላማው ውስጥ ሰንጥቃ በምታሄደበት ጊዜ‹‹የት እንደሆንክ ማላውቀው አባቴ እንግዲህ ይሄንን ጉዳይ ቀለል ባለ መንገድ እድጨርሰው እርዳኝ….ማለት አሪፍ የሆነ አሳማኝ ህልም እንዲያዩ  አድርግልኝ›.ካልሆነ ግን ታውቃለህ ሌላ ዘዴ እጠቀማለሁ…በዛ ደግሞ የሆነ ሰው ይጎዳል...እኔ እንኳን ማንም ቢጎዳ ብዙም ደንታ እንደሌለኝ ታውቃለህ ግን እናቴ ትከፋብኛለች...ለእሷ ስል ነው ደግና ጥሩ ሰው ለመሆን የምሞክረው እና አግዘኝ›በማለት መልእክት ይሁን ፀሎት ባለየለት ንግግር ነበር መልኩንም ሆነ ማንነቱን በቅጡ የማታውቀው አባቷን ፌበር እየጠየቀች  ወደቤቷ  የተመለሰችው፡፡ኬድሮን ብዙ ጊዜ ስለአባቷ ከሰው ጋር ስታወራ ዳቢሎስ ነው አባቴ ብላ በድፍረት የምትናገረው የእውነት እንደዛ ብላ ስለምታምን ሳይሆን እንሱ እንደዛ ብለው ስለሚያሟትና ከአንደበቷ አውጥታ ስታረጋግጥላቸው በፊታቸው ላይ የምታየውን ድንጋጤና በአካላቸው ላይ የምትመለከተው መንቀጥቀጥ ስለሚያረካት እና በእነሱ ላይ የበለጠ ኃይልና የበለጠ የበላይነት ስለሚያጎናፅፋት ነው፡፡

ይቀጥላል
👍16710👏6😱5👎3
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሁሴንና ሰሎሞን ለመዝናናት ተያይዘው ወጥተዋል፡፡ቦታው ሃያ ሁለት አካባቢ ነው፡፡ ሠዓቱ ከምሽቱ 4፡45 ሆኗል፡፡ ያሉበት ጭፈራ ቤት በጠጪዎችና በቡና ቤት ሴቶች ተሞልቷል፡፡ በዲጄው ፍላጎት በሚለቀቁ ሙዚቃዎች የተወሠኑ ሠዎች ይውረገረጋሉ፡፡ ሠሎሞንና ሁሴን አንድ ጥግ ይዘው መጠጣቸውን ከጨዋታ ጋር እያወራረዱት ነው፡፡

‹‹ቆይ አንተ ጨክነህ እንደ እኔ ወንደላጤ ሆንክ ማለት ነው?›› ሁሴን ነበር ጠያቂው፡

‹‹ኧረ !!ትቀልዳለህ እንዴ! እስከዛሬም የተጃጃልኩት ለልጆቼ ስል ነበር፡፡››

‹‹ቆይ በቤተክርስቲያን ስርዓት አይደል እንዴ ያገባሀት? እና ዝም ብሎ መፋታት ይቻላል…?

ከምትፈራውስ ከፈጣሪ ጋርስ አያቀያይምህም?››

‹‹ዝም ብለህ አትበለኝ፤ዝም ብዬ አይደለም የፈታኋት፡፡ በእኛ ሀይማኖት ፍቺ የሚፈቀዱባቸው ሦስት መሰረታዊ ሁኔታዎች አሉ፡፡ አንደኛው ከተጋቢዎቹ አንዱ ሲሞት፣ ሁለተኛ ከሁለት አንዱ በዝሙት ኃጥያት ከወደቀ ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ የማይድን የአዕምሮ በሽተኛ ሲኮን ነው፡፡››

ሁሴን ከአፉ ተቀበለው፡፡ ‹‹ገባኝ... ገባኝ... ታዲያ እኔ እስከማውቀው ድረስ ያንተዋ አልሞተች ወይም የአዕምሮ ህመምተኛ አልሆነችም የቀረው ዝሙት ያልከው ጉዳይ ደግሞ አንተም እየተንቦራጨክበት ነው፡፡ >>

‹‹ቢሆንም እኮ እኔ ወንድ ነኝ፡፡››

‹‹መፅሀፉ ለወንዶች ልዩ ፍቃድ ይሰጣል ማለት ነው?>>

‹‹ባክህ ነገር አታጣም፡፡ ያው እንደምታውቀው እኔ ሆነ ብዬ ሳይሆን አንዳንዴ ስጠጣና ስበሳጭ የምፈፅመው ስህተት ነው፡፡ ለዛውም ከቡና ቤት ሴቶች ጋር ነው፡፡ አንዴ ያወጣኋትን ሴት መልሼ እንደማልደግማት ታውቃለህ፡፡ ይሄንን የማደርገው ደግሞ ከማንም ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር እንዳይዘኝ ስለምፈራ ነው፡፡ እሷ ግን ሥጋዋንም ልቧንም ጠቅላላ እሷነቷንም ነው ያስረከበችው፡፡ ስለዚህ ለእኔ ምን ይተርፈኛል? ምንም … ፡፡ባዶ በድን ገላና የተራቆተ ልብ...
በቃ፡፡››

‹‹እኔ በበኩሌ ለውሳኔህ ያቀረብከው ምክንያት አላሳመነኝም፡፡ የሀይማኖቱን አላውቅም፡፡ በሞራል በኩል ግን ኢፍትሃዊነት ይመስለኛል፡፡››

ሠሎሞን ተበሳጨ <<አቦ በቃ ጨዋታ ቀይር፤ልዝናና ነው የመጣሁት፤በደስታ ልጠጣበት ፡፡››

ሁለቱም ፊት ለፊታቸው ያለውን የቢራ ጠርሙስ አነሱና ወደ ጉሮሮአቸው ካንቆረቆሩለት በኃላ መልሰው አስቀመጡ፡፡ አዲስ የጨዋታ ርዕስ ለማምጣት የቀደመው አሁንም ሠሎሞን ነበር፡፡

<<ለመሆኑ የመጽሀፉ ሽያጭ እንዴት እየሆነ ነው?>>

‹‹አትጠይቀን ባክህ ... የተአምር ያህል ነው፡፡ በቅርብ ሁለተኛ ዕትም ማሳተማችን የግድ ነው፡፡ በየጋዜጣውና የየሬዲዮ ጣቢያው መነጋገሪያ ርዕስም ሆኗል፡፡ የድርሰቱ ምርጥነት ብቻም ሳይሆን የደራሲዋ ማንነት አለመታወቅ ያልተለመደ ክስተት በመሆኑ መነጋገሪያ እንዲሆን የራሱን አስተዋጽኦ ሳያደርግ አይቀርም፡፡››

‹‹ቆይ ደውላልህ አታውቅም?››

<<ማ? >>

‹‹ጣኦትህ ነቻ...ደራሲዋ?››

‹‹መፅሀፉ ከታተመ ወዲህ አንዴ ደውላልኝ ነበር፡፡ በጣም የሚገርመው ስሜት የለሽ ሆና ነበር ያናገረችኝ፡፡ መቼም አንድ ጤነኛ ሠው የመጀመሪያ ልጁን ሲወልድ እንደሚፈነጥዝ ሁሉ አንድም ደራሲ የመጀመሪያ መፅሐፉ ሲታተምለት በደስታ መፍነክነኩ የሚጠበቅ ነው፡፡ እሷ ግን ደንታም የሠጣት አይመስለኝም፡፡ ስለ ሌላ ነገር ነበር የምታወራልኝ፡፡››

‹‹አሁንም ልታገኝህ አትፈልግም ማለት ነው?››

‹‹እሷን ለማግኘት አንድ አማራጭ ብቻ እንዳለ ነግራኛለች፡፡››

‹‹ምንድነው .. እንዴት አይነት አማራጭ?››

‹‹አልነገረችኝም...ትንሽ ታገስ አለችኝ፡፡››

‹‹አሁንስ አበዛችው…ቆይ እሷ እንደኛው ሠው አይደለችም እንዴ? ነው ወይስ የመላዕክት ዝርያ አለባት ይሆን?... ብቻ እኔን ለማየት አርባ ቀንና ለሊት ፁምእንዳትልህ!››

‹‹ምን ችግር አለው…እጾማለኋ፡፡ ጣኦቴ አይደለች? ሠው ለጣኦቱ ነፍሱንስ ለመስዋዕትነት ይለግስ የለ?››

‹‹ወይ ጉድ!! በሕወቴ ማየት እፈልግ የነበረው አንድ ነገር ያንተን በሴት ፍቅር ተንበርክከህ ስትንገላወድ ማየት ነበር፡፡ አንድ ቀን እንደሚሆን እምነቴ ቢሆንም እንዲህ መላ ቅጡ በጠፋ መልኩ ይሆናል ብዬ ግን ፍፁም ግምቱ አልነበረኝም፡፡ በነገራችን ላይ ይህቺ ደራሲህን ሳስብ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ የመጽሐፍ ምረቃው ቀን ፎዚያን በጣም ስከታተላት ነበር፤ ስታነብ ታሪኩ የራሷ ይመስል ተመስጣ ነበር፡፡››

‹‹አዋ እኔም ያንን ታዝቤለሁ፡፡››

‹‹ቆይ የሥነ ጽሁፍ ችሎታ አላት እንዴ?››

‹‹እኔ እስከማውቀው ድረስ የላትም፤አንባቢ እንደሆነች ግን አውቃለው….ግን ምነው ጠየቅከኝ?››

‹‹አይ የሆነ ጥርጣሬ ነገር በውስጤ ተጭሮ ነው፡፡ >>

ሁሴን ተንከትክቶ ሳቀ፡፡ ‹‹ደራሲዋ ፎዚያ ነች ልትል ነው?››

‹‹ነች አላልኩም፤ ተጠራጠርኩ እንጂ፡፡ አንዳንዴ በዚህ ዓለም ላይ ሊሆን አይችልም የምትለው ነገር ሆኖ ታገኘዋለህ…።››

‹‹እሱ ትክክል ነህ፡፡ ጥርጣሬህ ግን መሰረተ ቢስ ነው …፡፡›ንግግሩን ሳይጨርስ በዙሪያቸው ስትሽከረከር የቆየች አንዲት የ18 ዓመት ውብ ወጣት እጎናቸው ባለው ባዶ ወንበር ላይ ሳታስፈቅድ ተቀመጠች፡፡ እርግጥ ለመቀመጥ እንድትደፍር ያደረጋት የሰሎሞን ዓይኖች ለተደጋጋሚ ጊዜ መላ አካሏቷ ላይ ሲሽከረከር ደጋግማ ስለያዘችው ነው፡፡

በመኮሳተር ንግግሯን ጀመረች፡፡‹‹ቆይ እናንተ የመጣችሁት ልትዝናኑ ነው ወይስ የፓርላማ ውይይት ልታካሂዱ?›› ሁለቱም በአግራሞት አፍጥጠው ቢመለከቷትም መልስ ለመስጠት የቀደመው ግን ሲያፈጥባት የቆየው ሠሎሞን ነՈԸ::

‹‹እስከ አሁን ስትሰልይን ነበር እንዴ?››

‹‹ምን እሰልላችኋለሁ... ገርማችሁኝ እንጂ ፡፡ አሁንም እስቲ በደረቁ አታናዙኝ…ጋብዙኝ፡፡››

‹‹እዘዢ›› ሁሴን ነበር የፈቀደላት፡፡ አስተናጋጁን ጠርታ ቢራ አዘዘች፡፡

ሠሎሞን‹‹ቆንጆ ነሽ፡፡›› አላት ፡፡

ትላልቅ አይኖቿን አንከባለለችበትና ፈገግ ብላ ‹‹ሊበሏት ያሠቧትን ወፍ ጅግራ ነሽ ይሏታል፡፡›› አለ ያገሬ ሠው ስትል›› ተረተች

‹‹እንዴት ማለት?›› አላት ሠሎሞን፡፡

‹‹አይገባህም... ቅኔ አልተማርክም እንዴ?››

‹‹ተይው እሱ ስለ ስሚንቶና ድንጋይ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡›› የሁሴን ንግግር ነበር፡፡


‹‹ግምበኛ ነው እንዴ?›› ከቢራዋ እየተጎነጨች በፈገግታ ጠየቀች፡፡

‹‹ትክክል ነሽ..…የግንበኞች ሀለቃ ነው››

‹‹እሺ አንተስ?››

ሠሎሞን ብድሩን ለመመለስ ተሽቀዳደመ፡፡ ‹‹እሱማ ያው ወሬ ለቃቃሚ ነው ... ወሬ ይገዛል፤ ይሸጣል፡፡››

‹‹ኧረ... እኔ ጋር ብዙ ወሬ አለ፤ ለምን አትገዛኝም.. ? ግን ደስ የምትሉ ጓደኛሞች ናችሁ፤ተረባችሁ ደስ ይላል፡፡››

ሠሎሞን እጁን አንስቶ ጭኗ ላይ በማስቀመጥ ጨመቅ እያደረጋት ወሬውን ቀጠለ ‹‹ተረብ እኮ አይደለም ...እውነቴን ነው የወሬ ነጋዴ ነው ...እሱና መሰሎቹ ግን ለራሳቸው ቆንጆ ስም ሠይመዋል፡፡ ስራችሁ ምንድነው ? ሲባሉ ደረታቸውን ነፍተው ጋዜጠኛ ይላሉ… ።››

ሁሴን ተቀበለው፡፡ ‹‹ልክ እናንተም ስትጠየቁ ኢንጅነር እንደምትሉት ሁሉ፡፡››

‹‹በቃ ይበቃችኋል እኔ ስለማንነታችሁ በቂ መረጃ አግኝቼያለሁ፡፡››

‹‹ኮሚሽን እፈልጋለሁ፡፡›› አላት ሁሴን፡፡

<<ለምኑ?>>

‹‹አያያዙን ሳየው የሚለቅሽ አይመስለኝም፤ ታዲያ ስትደራደሩ ምን ያህል መክፈል እንደሚችል እንድታውቂ መረጃ ሠጥቼሻለሁ፡፡››

‹‹ባክህ ስንት ቀብቃባ ኢንጅነር አይተናል መሰለህ!!>>
👍1029😱3👏1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ፔሩ/አማዞን ወንዝ ላይ

ዳግላስ ሚስቱ የሰጠችውን መድሀኒት ወስዶ ከተኛ ከሁለት ሰዓት በኃላ ነቃ፡፡አይኑን ሲገልጥ የቅንጡ ጀልባዋ መኝታ ቤት ውስጥ ብቻዋን ነው ያለው፡፡ ከነቃም በኃላ አይኑን ብቻ ገልጦ ዙሪያ ገባውን እየቃኘ ባለበት ሆኖ 15 ደቂቃ አሳለፈ፡፡፡ከዛ ተነሳና በራፉን ከፍቶ ‹‹ማሪያ…ማሪያ እያ ተጣራ››ስሙ ሳያስበው ነው አፉ ውስጥ የገባለት፡፡ ሚስቱ ተንደርድራ መጣችን ፊቱ ቆመች፡፡ ወደራሱ ጎትቶ አቀፋትና ደረቱ ላይ ለጥፎ ከንፈሯን ለረጅም ደቂቃ መጠጣት፡፡እሷም እጆቾን ዘርግታ በአንገቷ ዙሪያ አሽከርክራ አቀፈችውና እላዩ ላይ ተንጠለጠለችበት፡፡
‹‹ማሪያ የእኔ ውድ ..አንጀሊናስ?››
‹‹ከእነ ሳንዲያጎ ጋር ነች፡፡እጇን ይዞ እየጎተተ ወደጀልባዋ በረንዳ ወጣ፡፡ሲደርስ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ አስፈሪ ጠባቂዎች ከየተቀመጡበት በድንጋጤ ተነሱና ቀጥ ብለው ቆሙ….አንጀሊና አባቷን ስታይ ወደእሱ ተንደረደረች…በአየር ላይ ቀለባትና ግራና ቀኝ ክንዶን ይዞ አሽከረከራት፡፡ መርከቡ ላይ ያሉት ሁሉ ደስ አላቸው፡፡አሁን እራሱን ዳግላስን ሆኖል ማለት ነው፡፡ከልጁ ና ከሚስቱ ጋር ሀያ ለሚሆኑ ደቂቃዎች በማሳለፍ በመጠኑ ናፍቆቱን ከተወጣ በኃላ እነሱን ወደውስጥ ገብተው እንዲጠብቁት አዞ …ቀጥታ መርከቡ ላይ ካሉት 5 ታጣቂዎች ጋር ስብሰባ ተቀመጠ፡፡
‹‹እሺ እየሰማዋችሁ ነው፡፡››
የታጣቂዎች ሀለቃ የሚመስለው ግዝፍ ሰው አንገቱን እንደደፋ መናገር ጀመረ‹‹ሀለቃ በተፈጠረው ነገር በጣም እናዝናለን፡፡በእውነቱ ችግሩ እንደተፈጠረ ስንሰማ ወዲያው ነበር እርምጃ የወሰድነው››
‹‹እኮ ምን አደረጋችሁ?››
‹‹ያው ብራዚሊያ አየር ማረፊያ ገብታችሁ ነበር… አንተ ወደፕሌኑ ማለፍ ብትችልም አብሮህ የነበረው ፓብሎ ግን በፖሊስ እጅ ወደቀ፡፡አንተን ማሳለፍ ቢችልም እሱ እራሱን ግን ከፖሊሶች እጅ ማስመለጥ አልቻለም፡፡እና ምንም ልንረዳው ባለመቻላችን…ጠበቀ ያለ ምርመራ ሲደረግበት ስለአንተ የሆነ ሚስጥር ሊያወጣ ይችላል ብለን ስለሰጋን እዛው የገባበት እስር ቤት እርምጃ እንዲወሰድበት አድርገናል፡፡
አንተን ወደ ብራዚሊያ ይዛ የሚበረው አውሮፕላን በአየር ፀባይ ምክንያት ኢኩዩቶስ እንደረፈ ስንሰማ እኔ እራሴ ነኝ አንድ ቡድን እየመራሁ በቻርተር አውሮፕላን ወደዛ ያመራሁት፡፡ከዛ ምን አልባት የመንግስት ሰዎች ሆኑ የሲ.አይ.ኤ ሰዎች እጅ እንዳትገባ ተጠንቅቀን ከሆቴል ስትወጣ አፈነንህ ከኢኩዬቶስ አስወጣንህ፡፡
‹‹ጥሩ ስራ ነው….እርግጠኛ ነኝ ምንም ያዝረከረካችሁት ነገር የለም፡፡››
‹‹አረ የለም..ሁሉን ነገር በጥንቃቄ ነው የተከወነው…ግን….››
‹‹‹ግን ምን?››
‹‹አንድ የአንተን ውሳኔ የሚጠብቅ ጉዳይ አለን፡፡››

‹‹ምንድ ነው?››
‹‹ልጅቷን ምን እናድረጋት …?ምን አልባት የምትለው ነገር ይኖራል ብለን..ወደ ዋናው ሳንቺዋሪ እየወሰድናት ነው፡፡አሁን ላቲሲያ ደርሰዋል፡፡ለሁለት ቀን እዛ ቆይተው…ወደሳንቹዋሪ ይዘዋት ይመጣሉ፡፡
‹‹ምንድነው የምታወራው ..?የቷ ልጅ?››
ሰውዬው አንዴ ዳግላስን አንዴ ደግሞ ወደመርከቡ የውስጠኛ በራፍ እያየ ለመናገር ጊዜ ወሰደ‹‹እየጠየቅኩህ እኮ ነው..የምን ልጅ?››
ድምፁን ቀነሰና …‹‹ሆቴል ስናገኝህ ከሆነች አፍሪካዊት ልጅ ጋር ነበርክ….፡፡ ከኤርፖርት አብራችሁ ወጥታችሁ ሆቴልም አንድ ክፍል ነው ያደራችሁት፡፡››ለምን ድምፁ ቀንሶ እንደሚያወራ አሁን ገባው፡፡ከሴት ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ማደሩን ሚስቱ ሰምታ ግርግር እንዳትፈጥር ነው፡፡አሱ ግን ያ ብዙ አላስጨነቀውም፡፡
‹‹እርግጠኛ ነህ..እንደዛ አድርጌለሁ?››
‹‹አዎ እርግጠኛ ነኝ…ምን አልባት ስለአንተ ማንነት ያወቀችው ነገር ይኖር ይሆናል ብለን ስለሰጋን ልንለቃት አልፈለግንም፡፡››
‹‹እና አሁን ወደሴንቸዋሪ ከሚጓዘው ቡዱን ጋር እየወሰድናት ነው እያልከኝ ነው፡፡››
‹‹አዎ፡፡››
‹‹ሽጉጥህን ስጠኝ ፡፡››ኮሰተር ያለ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ሁሉም በያለበት ሽምቅቅ አሉ፡፡ዳግላስ ሽጉጥ ስጠኝ ካለ የሆነ ችግር ሊፈጠር እንደሆነ ሁሉም ያውቃሉ፡፡ሽጉጥ እጁ ከገባ ይተኩሳል፡፡ሲተኩስ ደግሞ አየር ላይ አይደለም..ወይ አንዱ ደረት ላይ ወይ ደግሞ ጭንቅላት ላይ ነው የሚያሳርፈው፡፡በሚንቀጠቀጡ እጆቹ ሽጉጡን ከጎኑ መዞ ሰጠው…ግንባሩ ላይ ደቀነበት፡፡
‹‹እንዴት አንድ ምንነቷን የማታውቃትን መንገደኛ ሴት እየነዱ ወደግዛቴ ይዘዋት እንዲመጡ ትዕዛዝ ታስተላልፋለህ….?ምን ተልዕኮ እንዳላት ታውቃለህ…?ማን እንዳሰማራትስ?››
‹‹ጌታዬ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርገናል…ሙሉ እቃዋን ሆነ ጠቅላላ ሰውነቷን አብጠርጥረን ፈትሸናል፡፡ አታስፈልግም ካልከን አሁን ባለችበት እንዲያስወግዶት ማድረግ እችላለሁ፡፡››በፍርሀት በራደና በሚንቀጠቀት ድምፅ ሊያስረዳው ሞከረ፡፡
‹‹አይ መጀመሪያ አንተን አስወግድህና ትዕዛዙን እራሴ አስተላላፋለሁ፡፡››የሽጉጡን መጠበቂያ አላቀቀ….እጠቱን ምላጩ ላይ አሳረፈ…በዚህ ቅፅበት ልጁ‹‹አባዬ…አባዬ›› እያለች የጀልባውን በራፉ ከፍታ ወደእሱ ተንደረደረች….ቶሎ ብሎ የደቀነውን ሽጉጥ ከሰውዬው ግንባር ላይ አላቀቀና ጠረጴዛ ላይ ወርውሮ ከተቀመጠበት በመነሳት ወደ ልጅ ተንደረደረ፡፡አቃፋትና አባበላት፡፡ዝም ስትል ወደ ታጣቂዎች ዞረና ትዕዛዙን አሰስተላለፈ‹‹ በሉ አሁን ጉዞ እንቀጥል፡፡ እስከአሁን ያባከነው ሰዓት ይበቃል ፡፡ዛሬ ካምፕ ገብተን ማደር አለብን፡፡››
‹‹እሺ ጌታዬ ..ልጅቷን በተመለከተ ትዛዙን ላስተላልፍ?፡፡››
እንደማሰብ አለና‹‹..አይ ያንን ዕድልማ አጥተኸዋል…አሁን እራሴ የሚሆነውን አደርጋለው፡፡››ብሎ ወደውስጥ ገባ…..ጀልባዋም ተንቀሳቀሰችና ጉዞ ጀመረች፡፡
ወዲያው ነበር እጃቸው ላይ ያለችውን ሴት ገድለው ማንም እንዳያገኛት አድርገው እንዲቀብሯት ላቲሲያ ለሚገኙት ገዳዬቹ ትዕዛዝ የስተላለፈው፡፡
ኮለምቢያ
/ላቲሲ(አማዞን ወንዝን ታካ የተመሰረተች በአሳ ምርቶ የምትጣወቅ ከተማ) ካርሎስ  ከገዳይ  አጋሮቹ  ፈንጠር  ብሎ  አንድ  ግዙፍ  ዛፍ  ስር  ቁጭ  ብሎ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ የቀን ውሎውንና ገጠመኞቹን በምጥን ቃላት እያሰፈረ ሳለ በቡድኑ ሀለቃ ተጠራ፡፡ማስተወሻ ደብተሩን አጣጥፎ ጎኑ ያለው የጉዞ ቦርሳው ውስጥ ከተተና መሳሪያውን በአንድ ተከሻው አንጠልጥሎ ቦርሳውን በእጁ ይዞ ወደተጠራበት ቦታ ሄደ፡፡
ቀጥታ ‹‹ግባና ግደላት፡፡››የሚል ትዕዛዝ ነበር የሰጠው፡፡

‹‹ምን ?››ካርሎስ ሀላቀውን በድንጋጤ ጠየቀ፡፡

‹‹ትልቁ ሀለቃችን ትገደል ብሏል…ግባና ግደላት፡፡››ኮስተር ብሎ በድጋሚ ትዕዛዙን አስተላለፈ፡፡
‹‹እርግጠኛ ናችሁ ትገደል ብሏል?››

‹‹ሰውዬ ያምሀል እንዴ? እኔ የተሳሳተ ትዕዛዝ ሳስተላልፈ አይተሀኝ ታቃለህ..?ነው ወይስ ፈራህ?ከፈራህ ግድ የለም ሌላ ሰው በደስታ ያድርገዋል፡፡እኔ እኮ ስለምትወዳት በፍቅር እንድትገድላት እድሉን ልስጥህ ብዬ ነው እንጂ ሌሎች በደስታ የሚፈፅሙት ትዕዛዝ መሆኑን አጥቼው አይደለም …ምንም ቢሆን እሷን እዚህ ድረስ በማጓጓዙ ከአንተ እኩል የለፋ የለም፡፡››
👍627😢6
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

አቶ ለሜቻ ተንሰቅስቀው እያለቀሱ ነው..፡፡የቤቱ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ተሸብሯል…፡፡በፀሎት የምትገባበት ጠፍቷት አብራቸው እንባዋን እያረገፈች ነው፡፡፡ልጃቸው ፊራኦል ላጠፋው ጥፋት አባትዬው ይቅር እንዲሉት በጉልበቱ ተንበርክኮ እየለመናቸው ነው፡፡

‹‹ልጄ ይቅር የምልህ..እያንዳንዱን የገዘኸውን ዕቃ ወይ በየገዛበት መልሰህ ካልሆነም ለሌላ በመሸጥ ገንዘቡን አንድም ሳታጎድል ለልጅቷ ስትመልስ ነው፡፡››

‹‹እሺ አባዬ እንዳልክ አደርጋለው፡፡››

‹‹እኮ ተነስና አድርግ››

‹‹አሁን እኮ መሽቷል….ነገ በጥዋት ተነስቼ እንዳልከው አደርጋለው››

‹‹እስከዛው ላይህ አልፈልግም፣ወይ ቤቱን ለቀህ ውጣ ወይ እኔ ልልቀቅልህ››

‹‹አረ አባዬ… አንተ ምን በወጣህ እኔ ወጣለሁ….››ብሎ ከተቀመጠበት ሲነሳ በፀሎት ከተቀመጠችበት ሆና ጣልቃ ገባች…ጋሼ የሆነው ነገር ሁሉ የእኔ ሀሳብ ነው….ቆርቆሮውም..ሲሚንቶውም ሁሉም የተገዛው በእኔ ሀሳብ ነው፡፡በወቅቱ እሱ እንደማይሆን ነገሮኝ ተቃውሞኝ ነበር..እኔ ነኝ ያስገደድኩት…ስለዚህ ወቀሳውም ቅጣቱም የሚገባው ለእኔ ነው…ለሊሴ ታክሲ ልትጠሪልኝ ትችያለሽ?››

ጥያቄዋ ሁሉንም ሰው አስደነገጠ፡፡

‹‹እንዴ ታክሲ ምን ሊያደርግልሽ?››ለሊሴ ጠየቀች፡፡

‹‹የጋሼን ቅጣት ተግባራዊ ለማድረግ ነዋ…ሆቴል ድረስ የሚወስደኝ ታክሲ ጥሪልኝ…ከቤት መባረር ያለብኝ እኔ ነኝ››

‹‹ተይ እንጂ ልጄ..ለምን ጡር ውስጥ ታስገቢኛለሽ?››አቶ ለሜቻ ለዘብ ብለው ተናገሩ

‹‹ጋሼ ..ይሄ ምንም ጡር አይደለም…ይሄንን እቃ ያስገዛሁት ለራሴ ስል ነው….ያው እንደምታዩት በዚህ አያያዜ ለመዳን ሁለትና ሶስት ወር ይፈጅብኛል ..ከዳንኩ በኋላም ቶሎ የምሄድበት ቦታ ስለሌለኝ ከእናንተ ጋር ቢያንስ ስድስት ወር ኖራለው..ስድስት ወር ሙሉ ደግሞ እንዲህ የለሊሴን መኝታ አስለቅቄ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ከባድ ስለሆነ ነው

ሀሳብን ያመጣሁት..እኔ እንደውም ቤቱን ተረባርበን በአንድ ወር ውስጥ አልቆ እኔ ከእነለሊሴ ጋር እኖርበታለው ብዬ ነው››ስትል አብራራች፡፡

‹‹ልጄ ቢሆንም አግባብ አይለም..በእኛ ላይ ይሄን ሁሉ ብር መከስከስ እኛም አሜን ብለን መቀበል ነውር ነው…ሰውን ተይው …እግዚያብሄሩስ ምን ይለናል?››
‹‹አሁን ልጅህ ለሊሴ ብር አግኝታ እንዲህ ብታደርግ ይሄን ያህል ትበሳጭባታለህ?›› ዝም አሉ
‹‹ገባኝ አትበሳጭባትም….እኔንም እንደልጅህ አድርገህ ከምር ብትቀበለኝ ኖሮ ይሄን ያህል ቅር አትሰኝም ነበር..በቃ ለሊሴ ደውለሽ ታክሲውን ጥሪልኝ››
ለሊሴ  ፈራ  ተባ  እለች…  ስልኳን  ከተቀመጠበት  አነሳችና  ለመደወል  ስትዘጋጅ  ጋሽ ለሜቻ‹‹ልጄ ስልኩን አስቀምጪው..እስኪ ሁላችሁም ተቀመጡና እንረጋጋ…››

‹‹አዎ  ልጆች  ሁላችሁም  ተቀምጡ….ለሊሴ  እስኪ  ሲኒውን  አቀራርቢና  ቢና እናፍላ››እናትዬው ውጥረቱ ረገብ ስላለ ተደስተው የተናገሩት ነበር፡፡
////
በማግስቱ

‹‹…አየሩ በጥላቻ ጥላሸት ጠቁሯል፡፡ከፍቅር ዕጦት በሚመጣ የፍራቻ ግንብ ተከልያለው….በንዴቴ አጥር ስር ተሸሽጌ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡ይበርደኛል..አዎ በጠራራ ፀሀይ ይበርደኛል…ይርበኛል..እየበላው ሁሉ ይረበኛል….፡፡ጉሮሮዬ በጥማት ተሰነጣጥቆል….ግን ከዛ ከጥማቴ የሚፈውሰኝ ውሀም ሆነ ምድራዊ ወይን የለም፡፡››በፀሎት ነች የምታወራው…ፊራኦል ግን ምንም አልገባውም

‹‹አንዳንዴ እንደፈላስፋ ነው የምታወሪው?››

‹‹እንደእኔ ህይወትህን ሙሉ በብቸኝነት በራፍ ዘግተህ ለብዙ ሰዓታት በትካዜና በቁዘማ የምታሳልፍ ከሆነ ወደፈላስፋነት መቀየርህ የግድ ነው፡፡ከሞት ደጃፍ ደርሶ..በቃ አበቃልኝ ብሎ ተስፋ ከቆረጠ በኃላ ወደህይወት ተመልሶ ሁለተኛ እድል የተሰጠው እደእኔ አይነት ሰው ነገሮችን በተለየ መልክ ባያይ ነው የሚገርመው፡፡›››

‹‹አልገባኝም የሞት አፋፍ ላይ መድረስ ስትይ?››

ደነገጠች..አንደበቷን አንሸራቷት ሚስጥር ልታወጣ በመድረሶ እራሷን ወቀሰችና‹‹ማለቴ በዛ ለሊት በሞተሬ ከእዚህ በራፍ ጋር ስለ መጋጨቴ እያወራው ነው…የሞትኩ ማስሎኝ ነበር እኮ››

‹‹እ..እሱ እንኳን እውነትሽን ነው….ግን አሁን ፊትሽ ቁስሉ ደርቆል እኮ …ለምን ቀንና ለሊት በሻርፕ ትሸፍኚዋለሽ…››

‹‹እርግጥ እንዳልከው ድኗል ግን ጠባሳው ያስጠላል..እንዲህ ሆኜ ሰው እንዲያየኝ አልፈልግም ..በተለይ ወንዶች ››
ፈገግ አለ….‹‹ዝም ብለሽ እያካበድሽው ነው እንጂ እርግጠኛ ነኝ ከነጠባሳሽ በጣም ቆንጆ ልጅ ነሽ…እንደውም እንዲሁ አቋምሽን ሳየው የት እንደሆነ የማውቃት አርቲስት ወይም ሞዴል ነገር እየመሰልሽኝ ደነግጣለው፡፡››

‹‹አየህ አንደውም ለዚህ ነው ፊቴን ዘወትር በሻርፕ ምጆብነው››

‹‹አልገባኝም››

‹‹ሙሉ በሙሉ ገልጬልህ ፊቴን በደንብ ካየኸው የትኛዋ ሞዴል ወይ አርቲስት እንደሆንኩ ወዲያው ስለምትለየኝ፣እንደዛ እንዳይሆን ስለፈለኩ ነው››

‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል?››

‹‹ምን ላድርግ ብለህ ነው….በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለ እንደእኔ አይነት ሰው ባይቀልድ ነው የሚገርመው››

‹‹እስኪ እርእሱን እንቀይር ፣ሌላው ስለአንቺ የሚገርመኝ  እስከአሁን ሞባይል ይዘሽ አለማየቴ ነው››

‹‹የለኝም…..ማለቴ ከቤቴ ስወጣ ይዤ መውጣት አልቻልኩም፡፡››

‹‹ታዲያ  ልግዛልሽ…ማለቴ  በራስሽው  ብር  የምትፈልጊውን  አይነት  ስልክ  ልገዛልሽ እችላለሁ፡፡››

ፈገግ አለችና‹‹በራስህ ብር ብትገዛልኝ አይሻልም?››

‹‹ደስ ይለኝ ነበር..ግን አቅሜ ላንቺ የሚመጥን ስልክ ለመግዛት በቂ አይመስለኝም…››

‹‹የእኔ አቅም ምን ያህል ነው..?በምንስ ሚዛን ለካሀው…?ለማንኛውም ለጊዜው አያስፈልገኝም…ስፈልግ ግን ነግርሀለው፡፡››

‹‹ይገርማል… በአንቺ እድሜ ያለች ሴት ስልክ አያስፈልገኝም ስትል አጃኢብ ነው፡፡››

‹‹ምኑ ይገርማል..?ለጊዜው ማንም ጋር ለመደወል እቅድ የለኝም..››

‹‹ሶሻል ሚዲያስ….እንዴት ያስችልሻል፡፡››

‹‹ዕድሜዬን ሙሉ ስልክና ላፕቶፕ ላይ አረ አንቺ ልጅ አይንሽ ይጠፋል እየተባልኩ እስክሪን ላይ አፍጥቼ ነው የኖርኩት…ሶሻል ሚዲያ ከጨለማ ሀሳቦቼ እና ከድብርቶቼ መሸሺጊያ እና መደበቂያ ዋሻዬ  ነበር…አሁን  ግን ችግሮቼን ፊት ለፊት መጋፈጥ  ነው የምፈልገው

….እስከአሁን ከኖሩኩት ህይወት በተቃራኒ ነው መኖር የምፈልገው፡፡ይልቅ ከቻልክ ነገ መፅሀፎች ገዝተህልኝ ትመጣለህ፡፡››

‹‹እሺ ምን ምን መፅሀፍ እንደምትፈልጊ ትንግሪኝና ገዝቼልሽ መጣለው፡፡››

‹‹ጥሩ አሁን ደግሞ ምርጥ አንድ ሙዚቃ ብትጋብዘኝ በጣም ደስተኛ እሆናለው…››
‹‹ጥሩ …አለና ከአጠገቡ ያለውን ክራር አንስቶ ክሮቹን በእጁ እያጠበቀ እና እያላላ ቅኝቱን አስተካከለና‹‹ምን አይነት ዘፈን ይሁንልሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹መቼስ በዚህ ውድቅት ለሊት ስለሀገር ዝፈንልኝ አልልህም…የፍቅር ዘፈን ይሁንልኝ፡፡›› እንደማሰብ አለና ክራሩን መገዝገዝ ጀመረ ..አፏን ከፍታ ነበር የምታዳምጠው…
የነገን ማወቅ ፈለኩኝ … መጪውን አሁን ናፈቅኩኝ.. የፍቅር ምርጫዬ አንቺ ነሽ…ልቤንም መንፈሴን የገዛሽ ወሰንኩኝ ልረታ አስቤ፣አካሌን መንፈሴን ሰብስቤ

በፍቅር ህይወቴን ላኖረው..ላልመኝ ፍፁም ሌላ ሰው የፍቅርን ትርጉም ገልፀሸ አስተማርሺኝ
ካንቺ ደስታ ፣እኔን እያስቀደምሺልኝ ፍቅር ለካ ለራስ …ማለት እንዳልሆነ ስታደርጊው አይቶ… ልቤ በቃ አመነ ከነገርሽ…. ባህሪሽ ማርኮኛል…
👍6321🥰1
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ


ጭንቅ

ደጅ ፣ ደጁን አስሬ እየወጣች ትመለከታለች፡፡ የጣደችውን ቡና እየተንተከተከ ሳታነሳው አራት ሰዓት ሆነው፡፡

በህሊናዋ የተለያየ ሃሳብ እየተመላለሰ ረብሿታል፡፡ ምን ገጥሟቸው ይሆን ? እንዴው መኪና ተገልብጦ ይሆን? ከሰው ተጣልተው ይሆን? ነጋዴው አልመጣላቸው ይሆን ? ጥሩውንም መጥፎውንም ልቧ የገመተውንም ሁሉ እያወጣች እያወረደች ከራሷ ሃሳቧ ትሟገታለች፡፡

ኮሽ ባለቁጥር እየወጣች እየገባች እንቅልፍ የሚባል በአይኗ ሳይዞር ከአሁን አሁን ይመጣሉ እያለች ሌሊቱን ሳታምነው ቁጭ ብላ የማደር ያህል አነጋች፡፡ ጭንቀቱ ውሎም አድሮም አልተፋታትም፡፡

ተመስገንና ያሬድ ወሬያቸው እና ብቅታቸውም ሳይታይ ቀናት ተቆጠሩ፡፡

ተመስገንና ያሬድ ወሬያቸው እና ብቅታቸውም ሳይታይ ቀናት ተቆጠሩ፡፡

አበበች ሃሳብና ጭንቀቷ እየባሰባት ቢሄድም መፍትሄ አላገኘችም፡፡ ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡

የቻለው አባት አለች፡፡ አቶ ጎሹን በበራቸው ላይ ከብቶች ይዘው ሲያልፉ ድንገት አይታ፡፡ ታዲያ አቶ ጎሹን የቻለው አባት ብላ መጣራቷ በልጃቸው ስም ስለምጠራቸው ነበር፡፡

አቶ ጎሹ የቻለው አባት ወደ አለው ድምፅ መለስ አሉ፡፡ "ጠራሽኝ ልበል" ? አሉ ፤ ለአበበች፡፡

አዎ ፤ እኔ ነኝ የጠራዎት፡፡ ብላ ቀኑም እረፍዶ ስለነበር ሰላም አረፈዱ የቻለው አባት" አለች፡፡

"ሰላም አረፈድሽ አበበች፡፡ ምነው ደህና አይደለሽም ኖሯል? አሏት፡፡ አይን አይኗን እየተመለከቱ፡፡

"አይ! እኔ እንኳን ደህናነኝ፡፡ ባለቤቴ ከተመስገን ጋር ውሎ ገባ እንመለሳለን ብለው ወደ ድሬደዋ ሄደው ነበር፡፡ ይኸው ውሎ ገባ ሳይመለሱ ሰነበቱ፡፡ አሁንም ብቅታቸውም ጠፋ፡፡ እንዴው የማደርገው ሲጠፋኝ ነው፡፡ እርሶዎን የጠራዎት" አለች፡፡ መሬት መሬት እየተመለከተች፡፡

አቶ ጎሹ ታዲያ ምን ይሆናሉ ብለሽ ነው፡፡ መኪና አጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም የሄዱበት ሳይሳካላቸው ቀርቶ አድረው ለመምጣት አስበው ይሆናል፡፡ ለማንኛውም ምንም ማሰብ ፣ መጨነቅ የለብሽም፡፡ ደግሞ ወንድ ልጆች ናቸው፡፡ አድረው ይገኛሉ፡፡ ሴት ልጆች ቢሆኑ እንኳን አድረው አይገኙም ይባላል፡፡ ማታ ሊመጡ ይችላሉ ብለው አፅናንተዋት ወደ ከብቶቻቸው ተመለሱ፡፡

አበበች የመለሱላትን የማፅናኛ መልስ በትንሹም ቢሆን ለመረጋጋት ሞክራ መኪና አጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ነጋዴው ሳይመጣ ቀርቶ ሰንብተው ይሆናል፡፡ ብላ በማሰብ ተመልሳ ወደ ቤቷ ገባች ፡፡

አበበች ማታ ይመጣሉ እያለች ስትጠብቅ የሷ ማታ ሳያልቅ ማታና ማታ ተደምሮ አምስት ማታ ቢሆንም እንኳን ያሬድና ተመስገን ሊመጡ አይደለም አየናቸው የሚል ሳታገኝ..ቆየች

ህልምነው ቅዠት ;

"አዎ ፤ ነግቷል ወፍ እየተንጫጫ ነው፡፡ ምነው ሰላም አላደርሽም እንዴ? አሉ፡፡ ቄስ መልካሙ ለባለቤታቸው፡፡ በሌሊት ተነስተው ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ እየተነሳሱ፡፡

"እንዴው ዛሬ ደግሞ ሲያቃዠኝ ነው ያደረው" አሉ ፤ ቄስ

"ኧረ ! እኔንም ሲያቃዠኝ ነው ያደረው፡፡ ያ ተመስገን ደህና አይደል ይሆን? ከያሬድ ጋር የምንሄድበት አለ ብሎኝ ነበር የሄደው፡፡ ማታ ይመጣል ብዬ ጠብቄው ነበር፡፡ ይሄው ሳይመጣ ዛሬ አምስት ቀኑን ያዘ" አሉ፡፡ አይናቸውን በሸማቸው እየጠራረጉ፡፡

"ከያሬድ ጋር ከሄደ ምን ይሆናል ፤ ብለሽ ነው?፡፡ ያሬድ ነጋዴም አይደል ፤ ምን አልባት አብሮት ይዞት ሄዶ ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም እመቤቴ እንደፍቃዷ፡፡ እንግዴህ ቼር ነገር ታሰማን ፡፡ ዛሬ ደግሞ ተረኛ ገቢ ነኝ፡፡ ለቅዳሴ ሳይረፍድብኝ ልሂድ ፤ አንችም ተመስገን ካልመጣ ለከብቶቹ የሚበላ ፤ የታሰሩበት ስጫቸው፡፡ ስመለስ ውሃ አጠጣቸዋለሁ፡፡ ብለው ነጠላቸውን ለባብሰው ፤ ዘንጋቸውን ይዘው ፣ ወደ ጉራንባ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሄዱ፡፡

"እንዴው ዛሬ ደግሞ ምን ልታሰማኝ ይሆን ? ውስጤ የሚረበሸው ፣ እንግዴህ እመብርሃን አንች ታውቂያለሽ ፡፡ ያለዐንች ማን አለኝ እያሉ የጥዋት ፀሎታቸውን በቤታቸው የእንጨት ምሰሶ ስር በፊታቸው ተደፍተው የሚወዷትን የአገራቸውን ታቦት ጥሩ ነገር እንድ ታሰማቸው ተማፀኑዋት፡፡

ከተንበረከኩበት የእንጨት ምሰሶ ስር ተነሱ፡፡ ቤታቸውን በዶዶሆ ቅጠል ጠረግ ፣ ጠረግ አደረጉ፡፡ የሳር ድርቆሽ ከዓውድማ አምጥተው ለከብቶቻቸው ሰጡ፡፡ ሲያቃዣቸው ያደረውን ህልም ይሁን ቅዠት በሃሳባቸው እያወጡ እያወረዱ ለመፍታት ይግተረተራሉ፡፡ አንዴ በጥሩ ፣ አንዳንዴ በመጥፎ ፣ እየፈቱ እንደገና ደግሞ ህልም እንደፈችው ነው እያሉ ከራሳቸው ሃሳብ ጋር ይከራከራሉ፡፡

ታዲያ ወ/ሮ አሰገደች ሳይታወቃቸው ሰዓቱ እረፍዷል፡፡ ቁርስ እንኳን ሳይቀምሱ ባለቤታቸው ከቤተክርስቲያን የመምጫቸው ሰዓት ተቃርቧል፡፡

ቄስ መልካሙ ከቅዳሴ እንደ ወጡ ዛቲ ቀምሰው ለምዕመናኑ አሳርገው ፣ ከብቶቻቸውን ውሃ የሚያጠጣላቸው ስለሌለ ፣ እንዳይረፍድባቸው ሰንበቴያቸውን ቀምሰው ገበታ እንደተነሳ ተነስተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

ከብቶቻቸው ከማሰሪያቸው ሳይፈቱ ደረሱ፡፡ የተሰጣቸውን የሳር ድርቆሽ መብላታቸውን ትተው ቆመዋል፡፡ ያ! ተመስገን አልመጣም ማለት ነው፡፡ ቢመጣ ከብቶቹን ውሃ ያጠጣቸው ነበር እያሉ ወደ ቤት ገቡ፡፡

"ዛሬ ደግሞ ሰንበቴ ሳትገባ ነው እንዴ የመጣኸው"? አሉ ፤ ወ/ሮ አሰገደች፡፡

"አልቆየሁም ፤ እንጅ ደረስ ብያለሁ፡፡ ከቅዳሴም ስንወጣ አረፈድን ፤ ዝክርና ክርስትና ስለነበር ፤ሰንበቴ ቶሎ አልገባንም፡፡ ብለው ተመስገን አልመጣም እንዴ"? አሉ፡፡

"እስከ አሁን አልመጣም፡፡ እኔም አበበች ጋር ሄጀ እጠይቃለሁ ብዬ ነበር፡፡ ከቤትም ሳልወጣ እየተንደፋደፍኩ ምንም የረባ ስራ እንኳን ሳልሰራ አንተም መጣህ"፡፡

ከብቶቹን ላጠጣና እስከምመለስ ካልመጣ አይተን እኔ አበበች ጋር ሄጄ እጠይቃታለሁ፡፡ ብለው ከብቶቻቸውን ከታሰሩበት ፈትተው ውሃ ለማጠጣት ወደ ወንዝ ወረዱ ፤ ቄስ መልካሙ፡፡

ወ/ሮ አሰገደች ባለቤታቸው ከወንዝ እስኪመለሱ ቡና አፍልተው ጠበቋቸው፡፡

ከብቶቻቸውን አጠጥተው ተመለሱ፡፡ የጤፍ ጭድ የሚበላ ሰተው ፈልቶ የጠበቃቸውን ቡና ከባለቤታቸው ጋር እየጠጡ ነው፡፡

እንዴው ያ! ማንደፍሮ የሚሸጥ ባህርዛፍ አለ ብሎኝ ነበር፡፡ ጠዋት ቤተ ክርስቲያን አግኝቸው እጠይቀዋለሁ ብዬ ሳልጠይቀው እረሳሁት፡፡ አሁን ደረስ ብዬ ልምጣ መሰለኝ ፡፡

"እንዴ! ቅድም አበበች ጋር ሄጀ እመጣለሁ አላልከኝም?፡፡ እማንደፍሮ ጋር በሌላ ቀን አይደርስም"? አሉ ፤ ወ/ሮ አሰገደች፡፡

"ምን ያህል እቆያለሁ፡፡ በቁሜ ደረስ ብዬ የሚሸጠውን ባህርዛፍ አይቼ ቶሎ ስመለስ እሄዳለሁ፡፡

ታዲያ ቄስ መልካሙ ባለቤታቸው ያሉትን ለጊዜው ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ተነስተው ወደ ማንደፍሮ ቤት አቀኑ፡፡

ወ/ሮ አሰገደች ከአዳራቸው አንስተው ቀኑን ሁሉ ውስጣቸው ሲረበሽ መዋሉ እረብሿቸዋል፡፡ ልጀ ምን ሆኖ ይሆን ? እንዴው ከቤት እንኳን ወጥቶ አያውቅ፡፡ ከያሬድ ጋር ከተማ መሃል ተጠፋፍተው ይሆን ? ክልብ ክልብ ሲል መኪና ባልገጨብኝ ብቻ፡፡

ለአስር ዓመታት የተለየቻቸውን ብርቅየ የአንጀታቸው ክፋይ የሆነችው ልጃቸውን እድላዊትን ወደ ኋላ፤ ተመልሰው አስታወሱ፡፡ እንባቸው በሁለቱም አይኖቻቸው ግጥም አለ፡፡ ለመመለስ በውስጥ
ቀሚሳቸው ጠራርጉት፡፡ ከአንጀታቸው የመጣ እንባ መመለስ ግን አቃታቸው፡፡ በተቀመጡበት እንደ እንኳይ ኮለል እያለ እንባቸው ይዘረገፍ ጀመር፡፡

ቄስ መልካሙ ቆይተው ለአይን ያዝ ሲያደርግ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡
👍6411👏2
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
ከአመት በኃላ
አላዛር በግንባታው ዘርፍም በፍጥነት እየቀናውና እያደገ ሄዶ  በሁለት አመት  የኮንስትራክሽን ስራው ደራጃ -4 መድረስ ቻለ፡፡በስራ ዓለም ብቻ ሳይሆን እህቶቹንም በማገዝ የተዋጣለት ነበር …አንደኛዋን አህቱን ደግሶ ጥሩ የሚባል ትዳር ሲያሲዛት  ሌለኛዋን ደግሞ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ  እያስተማራት ነው፡፡

…በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ ሰሎሜን አግቢኝ ብሎ ለመጠየቅ በተሻለ ብቃት ድፍረቱን ማሰባሰብ የጀመረው፡፡እንደውም ይሄንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ በጣም ቆይቶል፡፡ከአመት በፊት ሁሴን ጨርቄን ማቄን ሳይል ወደውጭ እንደሄደ ነበር ወዲያው ሊያደርገው የወሰነው፡፡ግን  ቆይ ከዛሬ ነገር ሲል…መጀመሪያ ይህቺን ነገር ላሞላ ብሎ ከራሱ ጋር ሲሟገት ከአመት በላይ ጊዜ ፈጀበት፡፡አሁን ግን አግቢኝ ብሎ ሰሎሜን ለመጠየቅ  ከመቼውም ጊዜ በላይ  ሁኔታዎች ጠቅላላ ለእሱ ያደሉ እየሆኑ ነው ፡፡
እስከአሁን በዋናነት የያዘው ከበፊት ጀምሮ ሰሎሜን ካገባው በኃላ አኖርበታለሁ ብሎ ያልም የነበረውን አፓርታማ እስኪገዛ ድረስ ነበር፡፡ያንን ለማድረግ ለሶስት አመት ያህል ወገቡን አስሮ  ገንዘብ ማጠራቀም ነበረበት ..አሁን ግን ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ገንዘቡም ሞልቶለት ውብ የሆነ አፓርታማ ገዝቶ በእጁ አስገብቷል፡፡
አሁን እዛ ኮንደሚኒዬም ቤት ውስጥ የሚኖረው ከእሷ ላለመለየት ብቻ ብሎ እንጂ በቅርብ የገዛውን አፓርታማ ቤት የሚስተካከለውን ነገር ቶሎ አስተክሎ ወደዛው መዘዋወር ይችል ነበር፡፡ ፡፡ለጊዜው ግን አፓርታማውን ባለበት አቆይቶ  የእሷ ጎረቤት ሆኖ መኖሩን ቀጥሏል፡፡
ሁለተኛ እሷን እንዲጠይቃት ገፊ ምክንያት  ደግሞ ከልጅነቱ ጀምሮ እሷን የራሳቸው ለማድረግ አብረውት ሲፎካከሩት የነበሩት የእሱም የእሷም ምርጥ ጓደኞች በከተማው አለመኖር ነው፡፡
ሁሴን ለትምህርት ከአገር ውጭ የወጣበት አለማየሁ ደግሞ ፖሊስ ሆኖ ተመርቆ የት እንኳን እንደተመደበ የማያውቅበት ጊዜ ላይ ነበር፡፡እናም በዚህ ጊዜ እነዚህ ሁለት ተፎካካሪዎቹ እስከወዲያኛው ከመንገዱ ገለል እንዳሉ እርግጠኛ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡ በእነዚህና ሌሎች ምክንያቶች የእሷ ብቸኛ ጓደኛ ሆኖ የሚገኝበት አጋጣሚ ላይ  በመገኘቱ ክፍተቱን ለመጠቀም ትክክለኛው ጊዜ አሁን እንደሆነ አእምሮውም ሆነ ልቡ በእኩል ተስማምተው እየጨቀጨቁት ነው፡፡

ሌላው እሱ ቢዝነሱ ሁሉ መስመር ይዞ በኢኮኖሚ ጠንክሮ የካማፓኒ ባለቤት እና የብዙ ንብረት ባለቤት  መሆን ችሏል ፡፡  በተጨማሪም  እሷ   ስራ አጥታ  ካፌ በአስተናጋጅነት እየሰራች ብስጭት የምትልበት   ጊዜ ላይ በመሆኗ ግራ ቀኙን አመዛዝኖ እሺ እንድትለው የሚያግዙትን ሌሎች እርምጃዎችን ቀድሞ ለማድረግ  መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡
ሁለት ጥንዶች ወደጋብቻ ከሚገብባቸው ዋነኛው ምክንያት መካከል አንድ   በመካከላቸው የተፈጠረውን ጓደኝነት እድሜ ለመስጠት እና በመካከላቸው የበቀለውንም ፍቅር አድጎና አብቦ ፍሬ እንዲያፈራና እንዲጎመራ ለማድረግ ነው፡፡በዚህ ሰበበ-ምክንያት ጥንዶቹ  ወደጋብቻ ከገቡ በኃላ አንዳቸው ለአንዳቸው ረጅም ጊዜ ይሰጣጣሉ፤ስሜታቸውን በተሻለ ግለት ይጋራሉ፤ በጋራ ስቀው በጋራ ያለቅሳሉ፡፡ለዚህም ሲሉ በጋብቻ እቅፍ ውስጥ አንድ የፍቅር ብሉኮ ለሁለት ለብሰው ህይወት በመደጋገፍ ይስኬዱታል፡፡

ሌላው ጥንዶች ወደጋብቻ የሚገቡበት ሁለተኛው ምክንያት ለህጋዊ ጉዳዬችና ለጥቅማ ጥቅም ሲሉ ነው፡፡ሁለት ጥንዶች ፤ከመንግስት ለሚያኙት ጥቅማ ጥቅም ሲሉ፤ለሚያገኙት ውርስ ሲሉ፤ከፖለቲካ ለሚያገኙት ተርፍና ክብር ሲሉ ወደጋብቻ ሊገቡ ይችላሉ፡፡በሶስተኛ ደረጃ ለጋብቻ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ልጆችና ቤተሰብ ለማፍራት ሲባል ነው፡፡አንዳንድ ተጣማሪዎች በግላቸው በነበራቸው ጉዞ  በህይወት ሁሉ ነገር ይሳካላቸውና ግን ደግሞ ዘራቸውን ተክተው ለማለፍ ወይም ያላቸውንን ንብረት ወይም ሌጋሲያቸውን ሚወርስ ልጅ እንደሚያስፈልጋቸው ትዝ ሲላቸው..ያንን ለማግኘት አቅደው ወደጋብቻ ይገባሉ፡፡ ልጆች ለመውለድና ቤተሰብ ለመሰረት ሲሉ፡፡በአራተኛ ደረጃ እንደምክንያትነት የሚጠቀሰው ደግሞ ለሀይማኖታዊ ወይም ባህላዊ ጉዳዬች ሲባል የሚደረግ ጋብቻ ነው፡፡ሁለት ተመሳሳይ ሀይማኖት ወይም ባህላዊ እሴት የሚጋሩ ጥንዶች ምንም እንኳን በመካከላቸው ወደትዳር አንደርድሮ የሚከት የፍቅር መሳሳብ ባይኖርም በሀይማታዊ ጉዳዬች ምክንያት ወይም በባህላዊ መንገድ በቤተሰቦቻቸው ፍቃድ ብቻ ወይም በጎሳ መሪዎቻቸው ልዩ ትዕዛዝ ወደጋብቻ ሳያቅማሙ የሚገብበት አጋጣሚ አለ፡፡በአሁኑ ዘመን በብት የሚተገበረው አምስተኛው ምክንያት ደግሞ
እራስን ለማሻሻል የሚደረግ የጋብቻ አይነት ነው፡፡ውጥረት በበዛበት በዘመናዊው አለም በተለይ በተጨናነቁ ዋና ከተሞች የሚኖሩ ጥንዶች በመካከላቸው የተወሰነ መግባባት ከተፈጠረ..አስቸጋሪውን የኑሮ ዳገት ተጋግዞ ለመግፋትና ወደፊት ትንሽ ፈቅ ለማድረግ ሲሉ ወደጋብቻ የሚገቡበት አጋጣሚ የተለመደና በቁጥርም ቀላል የሚባል  አይደለም…የቤት ኪራይ ወጪ ለመጋራት…የቤት ውስጥ የስራ ጫናን ለመተጋገዝ፤አብሮ በመረዳዳት ወደተሻለ ህይወት ለመሸጋገር ሲባል በመነጋገርና በመደራደር ወደጋብቻ ተያይዞ ይገባል፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ለጋብቻ ገፊ ከሆኑ ምክንያቶች ውስጥ ዋና ዋኖቹ ናቸው እንጂ ብቸኞቹ አይደሉም..ደግሞም አንድ ሰው ለአንዱ ምክንያት ሲል  ወደጋብቻ ሲገባ ሌሎቹን ፈፅሞ አይፈልጋቸውም ወይም አያገኛቸውም ማለት ሳይሆን ዋና ትኩረቱንና ከጋብቻው ጥምረት በዋናነት ሊያተርፍ የሚፈልገውን ነገርን ለመግለጽ ነው፡፡ለልጆች ብሎ ወደጋብቻ የገባ ሰው..ልጁንም ፤በሂደት ደግሞ ከመቀረረብ ብዛት ፍቅርንም…ከዛም አልፎ ተጋግዞ ከመስራትና ተሳስቦ ከመኖር  ብዛት የተሻለ ህይወትንም ሊያገኝ ይችላል፡፡
አላዛርም ሰሎሜን ሊያገባ የፈለገበት ዋናውና አንገብጋቢው ምክንያት ለእሷ ያለውን ፍቅር ለዘላለም ለመንከባከብና ለመጠበቅ ሲል ብቻ ነው፡፡በዋናነት በአእምሮው ያለው ምክንያት ያ ነው፡፡ቢሆንም ግን ከእሷ ምርጥና ተወዳጅ ልጆችን ማግኘትም ይፈልጋል…እሱ ከቤተሰቡ ያለገኘውን ፍቅርና እንክብካቤ ከእሷ ጋር ለሚመሰርተው አዲስ ቤተሰብ መስጠትና ለልጆቹ  ምርጥና ተወዳጅ አባት ለእሷ ደግሞ ተንከባካቢ እና አፍቃሪ አባወራ  መሆን መቻሉን ማረጋገጥ ይፈልጋል….በኑሮ እንድትረዳውና እንድትደግፈው ፍጽም አይፈልግም…ይልቅ በተቃራኒው ለዘላለም እንደንግስት ሊንከባከባትና ሊያቀማጥላት ነው ምኞቱ፡፡አዎ ሊያነግሳት ነው የሚያገባት፡፡
አዎ በእቅዱ መሰረት ቅድሚያ የሚደረጉ ነገሮችን አድርጎ እንደሚያፈቅራት ነግሯት እንድታገባው ቢጠይቃት .. ምንም እንኳን ለተወሰነ ጊዜ ልታቅማማ ብትችልም ጨክና እምቢ ልትለው እንደማትችል ጠንከር ያለ እምነት አድሮበታል፡፡…

ሰሎሜን ደወለና ቀጠራት፡፡አዲሱ ሰፈራቸው የሚገኝ በብዛት አዘውትረው የሚጠቀሙበት ካፌ ቁጭ ብሎ ስለእሷው እያሰበ ስክትመጣ እየጠበቃት ነው፡፡ከመንገድ ማዶ  በሩቁ ወደእሱ ስትመጣ ሲያያት ነው ውስጡ በደስታ የተተራመሰው፡፡እንደቀረበችው ከመቀመጫው ተነሳና ጉንጭ ለጉንጭ ተሳስመው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ከፊት ለፊቱ ቁጭ አለች፡፡እሷ ፊት ለፊቱ ስትቀመጥ የጥዋት ፀሀይ ወጥታ ሰውነቱን እየዳበሰችው እንዳለ ህፃን መላ ሴሎቹ ይነቃቃሉ፡፡አላዛር  ሰሎሜን ዛሬ እንዲህ አብባ እና አሽታ ሲያያት ይደንቀዋል፡፡እንደልጅነታቸው ሊቀርባት ሊያቅፋት ሊስማት ሁሉ ይመኛል፡፡ግን ደግሞ ይፈራል፡፡በዚህም ረጅም ብስጭት ይሰማዋል፡፡
👍529
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ከአስር ቀን በኃላ ያሉት ባለስልጣን ከሳምንት በኃላ ደወሉለት..አልጠበቀው ነበር፡፡‹‹ሚካኤል አንድ ጥሩ ዜና አለኝ››

‹‹ምንድነው ጌታዬ?››በጉጉት ጠየቀ፡፡

‹‹ነገ ሰባት ሰዓት ላይ አባትህን እንድታገኝ  ከእስርቤቱ አስተዳዳሪ ፍቃድ አግንቼልሀለው፡፡››

‹‹በእውነት በጣም ነው የማመሰግነው›..እግዜር ይስጥልኝ››

‹‹አዎ በሰአቱ ሂድና…ቀጥታ አሁን በምልክልህ ስልክ እዛ እንደደረስ ደውልለት… አስተዳዳሪው ራሱ ይቀበልህና ሚሆነውን ያደርጋል….ሌሎች ነገሮችን እየሰራሁባቸው ነው….እስከዛው በዚህ ተፅናና…››

‹‹እሺ ጌታ ..በጣም ነው የማመሰግነው››

ስልኩን ዘጋና በደስታ ዘለለ…ልጇን እያጠባች ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው አዲስአለም ..‹‹ምን ተገኘ..ሎቶሪ ወጣልህ እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹በይው…ነገ አባዬን እንድጠይቀው ተፈቀደልኝ››

‹‹በእውነት..በጣም ደስ ይላል››

‹‹አዎ….ምንድነው ይዤለት የምሄደው…..?››ሲል ከፈንጠዝያው ሳይወጣ ጠየቀ፡፡

‹‹አንተ ምን አልባት ቅያሪ ልብስ የላቸውም ይሆናል..ልብስ ምናም አዘጋጅ..እኔ ደግሞ የሚበላ ነገር አዘጋጃለው፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ ..የእኔ ማር በጣም ደስ ብሎኛል….››

‹‹ደስ ይላል..ግን ያው አባትህ እስር ቤት ከገቡ ጀምሮ ልትጠይቃቸው በሄድክ ቁጥር በምን አይነት አቀባበል እንደሚቀበሉህ ታውቃለህ…እንዲህ በመፈንጠዝ ሄደህ በኃላ አላናገረኝም….መጥተህ አትጠይቀኝ አለኝ…ምናምን ብለህ እንዳትበሳጭ››ስትል ስጋቷን ገለፀችለት፡፡

‹‹አረ…የፈለገ ይበል እኔ አይኑን ማየት ብቻ ነው የምፈልገው….ከፈለገ ለምን  ልትጠይቀኝ መጣህ ብሎ በቡጢ  አይነርተኝም ..ግድ አይሰጠኝም››

አሳዘናት…‹‹ሁሉም ሰው ምናለ እንዳአንተ ሰው ወዳጅና ሌላውን የሚረዳ ቢሆን››ስትል በውስጦ አሰበች‹አይ እንደዛ ከተዘጋጀህ ጥሩ››አለችው፡፡

‹‹በቃ ወጣው ….በዛው ለአባዬ የሚሆን ልብስ ገዛዛለሁ››ብሎ ሚስቱን ጉንጯን ልጁን ግንባሩን ሳመና ወጥቶ ሄደ፡፡

ሚካኤል ለአባቱ ልብስና የሚበሉ የተለያዩ ትኩስ  ምግቦችን ተሸክሞ ልክ በተባለው ሰዓት ወህኒ ቤት ጊቢ ደርሶ ስልኩን ደወለ፡፡

‹‹ሄሎ ኩማንደር …ሚካኤል ነኝ…ቀጠሮ ነበረኝ፡፡››

‹‹እ ሚካኤል ….ጥበቃ ላይ ካሉት ፖሊሶች አስርሀለቃ ላቀው በልና ንገረው …ነግሪዋለው ወደእኔ ይዞህ ይመጣል፡፡››የሚል አስደሳች መልስ አገኘ፡፡

‹‹እሺ ኩማንደር አመሰግናለው››
ስልኩን ዘጋና ፊት ለፊቱ ያለውን ፖሊስ ‹አስር ሀለቃ ላቀውን› እንዲያሳየው ጠየቀው….እዛው በቅርብ የነበረ ፖሊስ ጠቆመው፡፡ማንነቱን ለፖሊሱ ነገረና ..ለአባቱ ይዞ የመጣውን እቃ እንዲያስረክ ካደረገ በኃላ ቀጥታ ወደኮማንደር ቢሮ ይዞት ሄዳ፡፡ፖሊሱ ክፉሉን ቆርቆሮ ከፍቶ አስገባውና መልሶ ሄደ፡፡

ሲገባ  የገጠመው ግዙፍና ግርማ ሞገስ ያለው ቢሮ ነው፡፡እዚህ ቀፋፊ ወህኒ ቤት ውስጥ እንዲህ አይነት የሚያምር ቢሮ ይኖራል ብሎ ገምቶ አያውቅም፡፡ፀጉራቸው ሙሉ በሙሉ ቀለሙን ቀይሮ ነጭ የሆነው   ግዙፉ ጠይም ቆፍታምና ሰው ከግዙፉ ጠረጴዛ ኃላ ባለ የቆዳ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጠው ይታያሉ….በጎርናና እና ሻካራ ድምጻቸው ‹‹ግባ አቶ ሚካኤል…..››አሉት

ሄደና ወደእሳቸው ቀርቦ ለሰላምታ እጁን ዘረጋላቸው…በመጠኑ ከመቀመጫቸው እንደመነሳት አሉና እጃቸውን ዘርግተው ጨበጡትና‹‹ተቀመጥ አቶ ሚካኤል›

እሺ ብሎ አንዱን ወንበር ሳበና ተቀመጠ‹‹ኩማንደር ስለአስቸገርኩት ይቅርታ….ያው የቤተሰብ ጉዳይ  ስለሆነብኝ ነው››ሲል  ተናገረ፡፡

‹‹ይገባኛል…እንደውም ጥሩ ልጅ ስለሆንክ መመስገን አለብህ…መቼስ ማረሚያ ቤታችን በአባትህ ላይ የወሰደው አቋም ለምን እንደሆነ ይገባሀል አይደል?አዎ ይገባሀል እንጂ …በእኛ ልትበሳጭ ፍፅም አትችልም፡፡››

‹‹አዎ በትክክል ይገባኛል….››ሲል በአጭሩ መለሰ፡፡

‹‹አሁን ያው ከአንተ ጋር እየተነጋገርን ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን ሁኔታዎችን ለማስተካከል እንሞክራለን….ዋናው አንተ አባትህንን  ምን ያህል ?ማገዝ ትፈልገለህ የሚለው ነው››አሉና ፈገግ ብለው በሲጋራ የበለዘ ጥርሳቸውን አሳዩት፡፡

‹‹ኮማንደር አባቴ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት መሞቻ ቀኑን የሚጠብቅ ሰው ነው…እና ያ ቀን አስኪደርስ ድረስ  በተቻለ መጠን በተመቻቸ ሁኔታ እንዲያሳልፍ ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ ነኝ፡፡አባቴ ይሄንን ቀፋፊ ወንጀል ሰርቶ ወህኒ ቤት ከመግቱ በፊት ለቤተቡ አይደለም ቸገረኝ ላለ ሰው ሁሉ ልብ የሚያዝንና እጁ የሚፈታ መልካምና የተከበረ ሰው ነበር…..ምንም ሆነ ምንም ፍፃሚዊ እንዲህ አሳዛኝ መሆን የለበትም፡፡

‹‹ጥሩ እንደዛ ከሆነ ማድረግ ይምንችለውን ሁሉ እናያለን፡፡››አሉን ወደፊት ተንጠራርተው መጥሪያውን ተጫኑ..አንድ ፖሊስ መጣና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠ…‹‹ሳጂን  ታራሚ ቅጣውን እዚህ አስመጣልን››ሲሉ ትዕዛዝ ሰጡ
ፖሊሱ ትዕዛዙን ተቀበለና ተመልሶ ወጥቶ ሄደ….ከ5 ደቂቃ በኃላ እስከአሁን ያለሳተዋለው በኩማንደሩ መቀመጫ በቀኝ በኩል የምትገኝ ጠበብ የጀርባ በራፍ ተቆረቀረ…ኮማንደሩ ዝርጥት ሰውነታቸው እየከበዳቸው በመከራ  ተነሱና በራፉ ከውስጥ ከፍተው ወደመቀመጫቸው ተመለሱ፡፡ አይኖቹን የተከፈተው በራፍ ላይ እንደተከለ መጠበቅ ጀመረ…ሰው ከማየቱበፊት ብረት ቅጭልጭልታ በጇሮው ሞላ..…ከዛ በተቀመጠበት ደንዝዞ ቀረ..አባቱን ከስድስት ወራት በፊት ነው ያየው…ሰው በስድስት ወር በዚህ መጠና ሊቀየር እንደሚችል ግምቱ የለውም ፡ፀጉሩ ተንጨፍርሮ ተንጨፍርሮ ጉድሮ ሆኖ ግንባሩ ላይ ተደፍቷል…ፂሙ አድጎ ግማሽ ፊቱን ሸፍኖት ያረጀ አንበሳ አስመስሎታል…ከመክሳቱ የተነሳ ሁለቱ ጉንጮቹ አንድ ላይ የተጣበቁ ይመስላል፡፡አይኖቹ ጥልቅ ጉድጓዱ ውስጥ ያሉ ደማቅ አንፖሎች ነው የሚመስሉት…ሚካኤል እንባው ዝርግፍ አለ..ኮማደሩ ከተቀመጡበት ተነሱና ..ለብቻችሁ ጊዜ ልስጣችሁ..አንድሰዓት አላችሁ……በፊት ለፊተኛው በራፍ   ክፉሉን ለቀውላቸው  ወጡና  ከውጭ ቀርቅረውባቸው ብቻቸውን ተዋቸው…
እንደምንም እራሱን አበረታቶ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደአባቱ ሄደ…ልጅ እያለ ባለግርማ ሞገሳሙ አባቱ  ወደ ቤት መምጣቱን የሚያውቀው የመኪናውን ክላክስ ሲሰማ ነበር..ካዛ ከወንድሙ ጋር ሮጠው ከቤት ይወጡና  ወደእሱ ይንደረደራሉ…ከዛ ለልጆቹ የገዛላቸውን ፍራፍሬ ወይም ሌሎች ጣፍጭ  ነገሮች የያዘ ፔስታል ይዞ ከመኪናው ሲወርድ እሱን ጨምሮ ሶስቱም ልጆቹ በሽሚያ አንዱ ቀኝ እግሩን ሌላው ግራ እሩን ያቅፍትና በልዩ ፈንጠዝያ ይቀበሉታል…እሱም ስራቸው ይንበረከክና አንዱን ጉንጩን ሌላዋን ግንባሩን እያሳመና እየዳበሰ ይዞቸው ወደቤት ይገባል…አባትዬው ለልጆቹ እንስፍስፍ የሚባል አባት ነበር..በተለይ  ዬቱ ታላቅ የሆነችውን ሴት ልጁን በልዩነት ንው የሚወዳት…እሷም በአባቷ በምንም አይነት ሁኔታ የማትደራደር  የእሱ ተመራጭ ልጅ ነበረች…እና እንደዛ ኩሩና ሽቅርቅር የነበረው አባቱ አሁን አፅሙ ብቻ ነው ያለው..ሄዶ በፍራቻ ተጠመጠመበት.. ጠረኑ ወደኃላ ይገፋተራል…አባትዬው ምንም አይነት ምላሽ አላሳየውም..እየጎተተ ወደወንበሮቹ ወሰደውና አስቀመጠውና ከፊት ለፊቱ ተቀመጠ፡፡

‹‹አባዬ እንዴት ነህ?››

ለእሱ መልስ ከመስጠት ይልቅ ‹‹ለምን እንደዚህ አደረክ?››ሲል አንቧረቀበት፡፡

‹‹ማለት? ምን አደረኩ?››ምን ስህተት እንደሰራ ባለማወቅ በፍራቻ ጠየቀ፡፡

‹‹ለምን አገኘኸኝ..?እንዴት እንደተቀጣሁና ምን አይነት ቀፋፊ አውሬ እንደሆንኩ ለማየት ነው የመጣኸው?››
👍5512👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ



ከወ.ሮ ላምሮት ቤት እንደተመለሱ ቀጥታ ወደራሄል  ወላጇቾ ቤት ነው የሄዱት፡፡ኤልያስ ቤት ድረስ አብሯቸው የመጣው በሁለት ምክንያት ነው…አንድም ሊሸኛቸው ሲሆን ሌላው ግን ጥዋት ከቤት ወጥቶ አብሯቸው ሲሄድ  ሞተር ሳይክሉን እዛው ጥሎ ስለነበረው የሄደው እሱን ለመውሰድ ነው…"ካለበለዚይ ጥዋት ወደስራ ለመግባት ታኪሲ ፍለጋ መጋፋት ሊጠበቅበት ነው…ያ ደግሞ በጣም የሚጠላው ነገር ነው፡፡

ደርሰው  ራሄል መኪናውን ፓርክ አድርጋ እንዳቆመች እሱ ፈጠን ብሎ ወረደና ፀጋን አንስቶ አቀፋት..ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷት ስለነበረ ሲያቅፍት  ልጥፍ አለችበት፡፡ራሄል ቦርሳውን አንስታ አንጠለጠለችና ተከተለቻቸው እና ወደ ግዙፍ ቤት ተከታለው ሲገቡ ጥዋት ተሰምቷት የነበረ ስሜት ተመልሷ ተሰማት…ባሏ… ተወዳጅ ልጇን አቅፎ ወደቤት ሲገቡ….ሀሳቡ የደስታ  ውስጧ በደስታ ስሜት እንዲጥለቀለቅ ስላደረጋት ‹‹እንዴት ደስ ይላል››ስትል በለሆሳሳ አንሾካሾከች፡፡ከፊት ቀደመችና ሳሎኑን ሰንጥቃ እየመራች ወደፀጋ
ክፍል ይዛው ሄደች… ቶሎ ብላ ብርድ ልብሱን ገለጠችለት…ቀስ ብሎ አስተኛትና ተጋግዘው አለባበሳትና ቆመ…ተከትላው ቆመች…በመሀከላቸው ያለው ርቀት ከአንድሜትር አይበልጥም…አንደኛው ሌለኛው ላይ አፍጥጧል….በሚገርም ሁኔታ የትንፋሽ ማጠር አጋጠማት. …ቀስ እያለ ተጠጋትና እጇቹን በወገቧ ላይ አሳረፈ፡፡
ውርር የሚያደርግ ጥሩ ስሜት ተሰማት…ከዛ በምን ፍጥነት እንደሆነ ሳታውቅ ከንፈሮቹ በእሷ ከንፈር ላይ አረፉ …የራሄል አይኖች ተዘጉ፤ እና ለአፍታ ድንጋጤ ተሰማት ፣  እጆቹ በወገቧ ዙሪያ  ተጠመጠሙባት እና ወደራሱ ጎትቶ አስጠጋት። ራሄል ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ  ሙሉ በሙሉ በቀጣይ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር የማወቅ ጉጉት ተሰማት። የበለጠ ልትለጠፍበትና ልትደገፍበት ፈቀደች፡፡ ‹‹ይህ ጥሩ ሥነ ምግባር አይደለም?››በውስጧ ነበር ያሰበችው… በድንገት የከበደውን ከባቢ አየር ማቅለል ፈለገች። ለብዙ ዓመታት ሳትወድቅ ከቆየችበት ቦታ ለመመለስ ተፍጨረጨረች።

‹‹የእህቴን  ሐኪም መሳም ?››ከእቅፉ ሳትወጣ  የሹክሹክታ ድምፅ አሰማች።ወደፊቷ የተደፋውን  ፀጉሯን ወደኃላ በመመለስ አስተካከለላት፡፡ከዚያም ,  ቀስ ብሎ ከከንፈሯም ከአካሏ ተላቀቀ እና እራቅ አለ።

‹‹ ፀጋ ቅሬታ እንደማታቀርብ አምናለው››አለችና  ዓይኗን በእፍረት ደፍች፡፡  ለእሱ ያላትን መስህብ በውስጧ መቅበር እስከቻለች  ድረስ፣ እራሷን ከእሱ ለይታ ማቆየት እስከቻለች ድረስ፣ እነዚህን አዳዲስ እና አደገኛ  ስሜቶች መቋቋም እንደምትችል ታስብ ነበር።አሁን ግን?በጣም ለረጅም ጊዜ የናፈቀችውን ነገር ቀምሳለች። ከንፈሯ ላይ መች ተጠግቶ እንደተጣበቀባት  እንኳን አላወቀችውም። ፍቃዷን እና ሙሉ  ስሜቷን ለዚህ ሰው እስክትሰጥ ቅፅበት ድረስ  ልቧን በኪሩቤል የመቃብር ቦታ ለዘመናት ቀብራው ነበር፡፡ በደረሰባት ኪሳራ ተበሳጭታ ስለነበረ  ራሷን ዳግመኛ እንደዚህ ላለ ሁኔታ ለማጋለጠ ፈፅሞ እንደማትፈቅድ ቃል ገብታ ነበር። አንድን ሰው በጥልቀት ለመንከባከብ መፍቀድ ራስን ነገ በድንገት ለሚመጣ ህመም ማመቻቸት እንደሆነ ህይወት አስተምራታለች።ከዛ ስቃይ ለማገገም እና እንደገና ወደህይወት  ለመመለስ ዓመታት ፈጅቶባታል።

‹‹ይሄ ጉዳይ  በጣም ያስፈራኛል።››አለችው፡፡
አገጯን በአውራ ጣት ዳባበሳት እና ‹‹ምንም አይደለም እኔም  እፈራለሁ:: ግን  ፍርሀታችንን ለማለስለስ ብዙ ጊዜ አለን››አለና ሊያበረታታት ሞከረ፡፡
በረጅሙ ተነፈሰች፣ ከዚያም ፈገግ አለች።

ጭንቅላቷ ላይ ሳማትና ከዚያም በሹክሹክታ ‹‹ባዬ ራሄል››በማለት ክፍሉንም  ቤቱንም ለቆ ወጣ ።ራሄል እስከሳሎን ተከተለችውና  ከኋላው በሩን ዘጋች፡፡ የሞተር ሳይክሉን ድምፅ በመኪና መንገዱ ላይ ሲንደቀደቅ ሰማች። ጭንቅላቷን ቀዝቃዛው  መስታወት ላይ አስደገፈች፡፡ …በድንገት መጸለይ እንዳለባት ተሰማት።‹‹ጌታ ሆይ እሱን ጠብቀው›› አለች ‹‹ራሷን ለሌላ ሰው በዚህ መንገድ እከፍታለው ብላ ፈፅሞ አስባ አታውቅም ነበር? የፀጋ የታፈነ ጩኸት  ተሰማት…ራሷን ከተደገፈችበት  መስታወት  ቀና አደረገች እና ተንቀሳቀሰች…ከዛ ወደ ፀጋ ሄደች። እህቷን ለመከታተል ወደ ደረጃው እየሮጠች ስትሄድ፣ ቀድሞ የነበረባትን ስሜት እየሰመጠ እንደሆነ ተረዳች።
///
ዔሊያስ የቤቱን ዙሪያ ገባ ተመለከተ። ምንም ያማረ ነገር የለም። በራሱ ቤት ውስጥ በራሱ ሶፋ ላይ ተቀምጦ የነበረ ቢሆንም፣ አእምሮው ከአንድ በሰአት በፊትና በተለያት ሴት ላይ ተጣብቆ ነበር።ከአንድ ሰአት በፊት የሳማት ሴት አሁንም ልቡ ውስጥ እየተገላበጠች ነው።እንደዛ ያለ ድንገተኛ እርምጃ እንዲወስድ ያነሳሳው ምንድን ነበር?ቢያስብ ቢያስብ ሊገለፅለት አልቻለም፡፡
እረፍት አጥቶ ከሶፋው በመነሳት ቢንያም ወደተኛበት
ክፍል ተራመደ… ሀሳቡ  ዋና መኝታ ቤቱ በጥቂት ቀናት ውስጥ ማለቅ እንዳለበት ሊነግረው ነበር ። ነገሮች እንዳሰበው ሚሄዱ ከሆነ እና የገንዘብ እጥረት ካላጋጠመው ቤቱ በስድስት ወር ውስጥ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋል። በእቅዱ መሰረት ቤቱን ካጠናቀቀ በኃላ ቀጣዩ እቅዱ አዲስ መኪና መግዛት ነው።  እና ከዚያ ምናልባት ይህንን ንፁህ እና በስርዓት የተቀነበበ  ህይወቱን የምትካፍለው ሴት መፈለግ ይኖርበት ይሆናል። ከአመታ በፊት  እቅዱን  በዚህ መንገድ በቅደም ተከተል ሲያስቀምጥ ሁሉም ነገር እንከን የለሽ እንደሆነ እርግጠኛ ነበር፡፡  ነገር ግን ያ ራሔል ከፊቱ ከመጋረጧ በፊት ነበር ።

የወንዱሙን
ክፍል ለመክፈት እጄታውን ከያዘ በኃላ ሀሰቡን ቀየረ…ራሴ ተረብሼ ለምን እሱን እረብሸዋለው..በማለት ወደኃላ ተመለሰና ወደራሱ መኝታክፍል ገባ፡፡የልብሱን መሳቢያ ከፍቶ ከአሳዳጊ ወላጆቹ ቤት ያመጣውን የስጋ ወላጇቹን የፎቶ ሳጥን አወጣ ፡፡ራሄል ያቀረበችለትን ሀሳብ በድጋሚ አሰበበት።  ምናልባት አሳዳጊዎቹ ይሄንን የወላጆቹን ፎቶ ከእሱ ለማራቅ ጥሩ ምክንያቶች ነበሯቸው።በወላጆቹ ፊት ላይ የራሱን አሻራ ለማግኘት እየሞከረ ፎቶውን አገላብጧ ተመለከተ። አገጩን በእናቱ፣ ዓይኖቹ በአባቱ መልክ ላይ በጨረፍታ የተመለከተ መስሎት ነበር። ወይም ምናልባት ምኞት እንደዛ ስለሆነ ይሆናል፡፡ ፡፡እሱ እንደ አብዛኛው የማደጎ ልጆች ፣ስለ ወላጆቹ  ይበልጥ ለመማር  እና ለማወቅ ፍላጎት ነበረው ።እሱን በተመለከተ  በህፃናት ማሳደጊያ ተቋሙ ውስጥ ያለው ፋይል ውድ የሆኑ ጥቂት መረጃዎችን የያዘ ሲሆን አንዳንድ ነገሮችን እንዲያውቅ አድርገውታል፡፡ታዲያ ለምን መርካት አልቻለም?

ራሄል የማንቂያ ሰዓቱን ላይ ባለማመን አፈጠጠች።እንቅልፍ አልወስዳት ብሎ  ከግራ ወደቀኝ እየተገላበጠች ለአንድ ሰአት ተሰቃየች… የሰዓቱ መንቀርፈፍ የዘለአለም መሰላት። ደጋግማ  ከኤሊ ጋር ስታጫውተው የነበረውን ትዕይንት አዲስ እንደወጣ ተወዳጅ ፊልም ደጋግማ በምልሰት በማሰብ  አጣጣመችው፣ የከንፈሮቹን ንክኪ እንደገና ተሰማት።መላልሳ ባሰበችው ቁጥር በእያንዳንዱ ትውስታ  አዲስ ስሜት ይሰማት ነበር። በቀጣይ ምንድነው የሚሆነው….?እራሷን ትጠይቃለች….አእምሯዋ ለጥያቄዋ መልስ ከመስጠት ይልቅ ግራ መጋባት ውስጥ  አሽቀንጥሮ ይጥላታል፡፡
ያለፈውን የልቧን ጭለማ ጓዝ  እንዴት መልቀቅ እንዳለባት እስከአሁን አላወቀችም፣ አልደፈረችም።
59👍9👏3
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////

ኩማደሩ በቤት ውስጥ ምርጥ የተባለ ውስኪ እያለው በአውራ ጎዳናው ላይ ወደሚገኝ ግርግር ወደሚበዛበት መጠጥ ቤት ገብቶ ለመጠጣት ለምን እንደመረጠ ማወቅ አልቻለም። ምናልባት አዕምሮው ስለተጨናነቀ የተጨናነቀ ቦታ ፈልጎ ሊሆን ይችላል…እሾህን በእሾህ ለማክሰም ።የቡና ቤት አስተናጋጅ መጠጥ እንዲያመጣለት በምልክት ነገረው።ውስኪውን ወደ ብርጭቆው ሲቀዳ እያየ"አመሰግናለሁ" አለ ብቻውን እየቆዘመ ውስኪውን መሳብ ጀመረ፡፡

የጠጣው ውስኪው ቀስ በቀስ በሆዱ ውስጥ እሳት እንዲንቀለቀል እያደረገ ነው። ሲጠጣ ጨጓራውን በጣም ያመዋል….በዛም ምክንያት እርግፍ አድርጎ ለማቆም ሁሌ ይወስናል
..ግን ደግሞ ምክንያት ፈልጎ መጠጣቱን አይተውም…ቢሆንም እስኪሰክር ጠጥቶ አያውቅም በፍጽም የአባቱን ስህተት መድገም አይፈልግም…።ይህ የሌሊቱ የመጨረሻ መጠጥ እንደሚሆን ወሰነ …አዘዘ ፡፡ገና ህጻን ሳለ ነው እንደአባቱ መሆን እንደሌለበት ወስኖ የነበር ።የወህኒ ቤት ወፍ ወይም መነኩሴ፣ የጠፈር ተመራማሪ ወይም የመቃብር ጉድጓድ ቆፋሪ፣ የእንስሳት ጠባቂ ወይም ትልቅ አዳኝ ሆኖ ሊያድግ ይችላል፣ ነገር ግን አንድ መሆን የማይፈልገው ነገር ሰካራም መሆን ብቻ ነበር። ቀድሞውኑ በቤተሰቡ ውስጥ አንዱ ፕሮፌሽናል ጠጪ ነበራቸው እና ያ ደግሞ በጣም በቂ እንደሆነ ያምናል፡፡

"ሂይ ኩማንደር " የሚል ንግግር ከሀሳቡ አናጠበው፡፡

አንገቱን ቀና ሲያደርግ የለበሰችው ጅንስ ሱሪ የጠበባት እና ፊቷን በሚካፕ ያደመቀች ውብ ሴት ፊት ለፊቱ ቆማለች፡፡ይህቺን ሴት ከረጅም ጊዜ በፊት ጀምሮ ያውቃታል….፡፡

‹‹ሰላም ሮዛ።››

"ቢራ ትጋዘኛለህ ብዬ በማመን ነው ከጓደኞቼ ተነጥዬ የመጣሁት?"አለችው በተቃራኒው ኮሪደር ጥግ ከላይ ተቀምጠው ቢራ እየጠጡ ወደ ሚሳሳቁ ሁለት ሴቶች እየጠቆመችው፡፡

"ይቻላል።" አለና እንድትቀመጥ ካደረጋት በኃላ ትዕዛዙን ወደ አስተናጋጁ አስተላለፈ። ትኩር ብላ እያየችው ነው…ብቻውን ከእሷ ጋር መቀመጡ ምቾት ስላልሰጠው..‹‹ከፈለግሽ ጓደኞችሽን ጥሪያቸው››አላት፣ ከአንድ ሴት ጋር ለብቻ ከመሆን ከሶስት ሴት ጋር መሆን የተሻለ መስሎ ስለተሰማው ነው ሶስት ሴቶችን ለመጋበዝ ፍቃደኛ የሆነው፡፡

"አይ እነሱ የሞቀ ጫወታ ይዘዋል …አታስቸግራቸው" አለችው በማሽኮርመም ፡፡

"እየተዝናናችሁ ነው?››

"አዎ..እኛ ሴቶችም አንዳንዴ ወጣ ማለት አያስፈልገንም ትላለህ ?"

"አይ ጥሩ ነው፡፡"

ያዘዘችው ቢራ መጣላትና እየተጎነጨች ማውራቷን ቀጠለች‹‹ከቤት ተያይዘን ስንወጣ ፊልም ቤት ለመግባት ነበር..ግን እንደአለመታደል ሆኖ ፊልሙ ያየነው ስለሆነ ሀሳባችንን ቀየርንና ወደእዚህ ጎራ አልን…እና ደግሞ ደስ የሚለው አንተን አገኘሁህ››

‹‹ጥሩ ነው››ብሎ በአጭሩ መለሰላት፡፡

ሮዛ በቀላሉ የምትተወው አይነት ሴት አልነበረችም። "አይ ኩማንደር ሁል ጊዜ በራስህ ዙሪያ የምትሽከረከር ብቸኛ ፍጡር ነህ።"የሚል አስተያየት ጣል አደረገችበት

" ብቸኝነት ምርጫዬ ነው."ሲል መለሰላት

"አውቃለሁ ግን አሁንም…" እጇን አንቀሳቀሰችና ታፋው አካባቢ አስቀመጠች…በድንጋጤ ግራና ቀኙን አየና..ቀስ ብሎ እጇን  አንሸራቶ ነፃ ወጣ፡፡

"ምናልባት አንተን ማስደሰት እችል ይሆናል፡፡ " አለችው ፡፡ " እስቲ እናያለን››አላት፡፡

"ሰባተኛ ክፍል እያለሁ ጀምሮ በጣም ወድጄህ ነበር። መቼስ ያንን አታውቅም አይደል?"

"አይ ያንን አላውቅም ነበር."

"እሺ አሁን ነገርኩህ ። በወቅቱ አብዬት ፍሬ ትምህርት ቤት እየተማርን እያለ አፈቅርህ ነበር…..ግን ያኔ ተነጠቅኩ። የዚያች ልጅ ስም ማን ነበር? በእነ ጁኒዬር የከብቶች በረት ውስጥ የተገደለችው?"

"ሰሎሜ."

"አዎ. በእሷ ላይ ተመስጠህ ነበር አይደል? ወደሀይስኩል ስንገባም በግልፅ ፍቅረኛማቾች መሆናችሁን በይፋ አሳወጃችሁ…ከዚያም እኔም ተስፋ ቆርጬ አግብቼ ልጆች ወለድኩ." ለንግግሯ ፍላጎት እንደሌለው አላስተዋለችም።

"'በእርግጥ አሁን ባሌ ሞቷል፣ እና ልጆቼም እራሳቸውን ችለው ከቤት ወጥተዋል….አንተ ግን በዚ ሁሉ ዘመን ትራስ ታቅፈህ ታድራለህ…ነው ወይስ ሳልሰማ አገባህ?››

"አይመስለኝም።"

‹‹እስካሁን ››ወደ ፊት ቀረበችው፣

"ምናልባት እኔን እየጠበቅከኝ ይሆናል፡፡››ብላ ወንበሯን አንሸራታ ወደእሱ አቀረበችውና እላዩ ላይ ተለጠፈች፣እሱም ቀኝ እጁን ሰነዘረና"ጡቶቿን በእጁ እያሻሸ ምላሽ ሰጣት፡፡ የጡት ጫፎቿ በቲሸርትዋ ላይ ጠንካራ እና የተለየ ስሜት ፈጠሩበት። የሆነ ሆኖ፣ ግልጽነቷ ልክ እንደ አለም ንፁህ እና ባዶ ጣቶች ከነጭ ጋወን ውስጥ አጮልቆ እንደሚወጣ የሚያማልሉ አልነበረም።
በአለም ነጭ ካባ ስር ምን አለ? ብሎ እንዲያስብ ስለተገደደ አላስደሰተውም። ለምን ብሎ አሰበ።አለም በጣም ቆንጆ ነበረች. ከንፈሮቿ ተከፍለው እርጥብ ነበሩ። ሳይፈልግ ከአለም ከሜካፕ ነፃ ከሆኑ ከንፈሮች ጋር አነጻጽሯቸዋል፣ ነገር ግን አሁንም ሞቃት እና እርጥብ፣ የሚሳም እና ሴሰኛ፣እንደሆኑም እርግጠኛ ቢሆንም ምንም አይነት ሙከራ ሳያደርግ የቢራዋን ዋጋ የሚሸፍን ብር ከጂንስ ኪሱ ውስጥ በማውጣት ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠና

‹‹መሄድ አለብኝ"በማለት ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡

"ግን እኔ ያሰብኩት…."

"ወደ ጓደኞችሽ ብትመለሺ ይሻላል፣ አለበለዚያ ፓርቲው ያመልጥሻል ።"አላት፡፡ ከጓደኞቾ ጋር በፊት ያልነበሩ አራት የሚሆኑ ወንዶች ተቀላለቅለዋቸው ሞቅ ያለ ቡድን መስርተው ነበር….፡፡

‹‹ሮዛ ስለየሁሽ ደስ ብሎኛል›› አለና ኩማንደር ኮፍያውን ዝቅ አድርጎ ፊቱን በከፈል ሸፈነና ወጥቶ ሄደ፣ ፡፡

እና ስለአለም መብሰልሰሉን ቀጠለ..ትናንት ማታ የእናቷ አስከሬን እንደተቃጠለ ሲነግራት ፊቷ ላይ የተመለከተው ሀዘን አሁንም ትዝ ይለዋል፡፡

"ዳኛ ዋልልኝ ያውቅ ነበር?" ስትል ጠየቀችው፡፡

"እነሆ እኔ የማውቀው ነገር ቢኖር እሱ ጠርቶኝ የፈለጋችሁት ነገር የማይቻል ነው ማለቱን ነው፣ "

"የእናቴ አስከሬን መቃጠሉን የሚያውቅ ከሆነ ለምን እራሱ አልነገረኝም?"

"የእኔ ግምት አንቺ ለዜናው የምታሳይውን ትዕይንት ማየት ስለማይፈልግ ይመስለኛል "

"አዎ" ብላ ትኩረቷን ሳትከፋፍል አጉረመረመች፣

"ሁከትን አይወድም። ››

በዝምታ ተመለከተችው። "ቆሻሻ ስራውን እንድትሰራለት ነው አይደል የላከህ ?። ››ነበር ያለችው፡፡

ኩማንደሩ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ጓንቱን አንስቶ አጠለቀ…ኮፍያውንም መልሶ አደረገ ።

"አሁን ደንግጠሻል ..ግን አይዞሽ ደህና ትሆኚያለሽ?"

"ደህና ነኝ።"

"ጥሩ ››

ጥቋቁር አይኖቿ በእንባ ተሞሉ እና አፏ በትንሹ ተንቀጠቀጠ። ድንገት ወደእሱ ተንቀሳቀሰችና እጆቿን ከወገብዋ ጋር አጣበቀች..እና ተሸጎጠችበት። ያን አጥር እንደገና ከመገንባቷ በፊት፣ እጆቹን አንሸራትቶ ወደ እሱ ጎተታት። እሷ ሞቃት ትንፋሽ እና ጥሩ መዓዛ ነበራት በሀዘኗ ውስጥ ደካማ ሆናለች. እጆቿ ሳይጨነቁ ወደ ጎን ተንጠልጥለዋል።

"ኦ አምላኬ እባክህ በዚህ ፈተና ውስጥ እንዳልፍ አታድርገኝ" ስትል በሹክሹክታ ተናገረች እና ጡቶቿ ሲንቀጠቀጡ ተሰማት። እንባዋን ሲንጠባጠብ በልብሱ አልፎ እስኪሰማው ድረስ ጭንቅላቷን ወደ እሱ አስጠጋች። ፀጉሯን የጠቀለለችበት ፎጣ ተንሸራቶ መሬት ላይ ወደቀ። ፀጉሯ እርጥብ ነበር። በወቅቱ እሷን መሳም እንደሌለበት ለራሱ እየተናገረ ነው… ነገር ግን ከንፈሩ ፀጉሯን ከዚያም የአንገቷ ስር ሽታን ወደውስጡ እየማገ ስለሆነ እየደነዘዘ ነበር፡።በዚያን ጊዜ፣ ከባድ የፍትወት ስሜት አቅበጠበጠው፣ እናም በጣም
42👍6