አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


===============

በሶስተኛው ቀን አለማየሁና ሰሎሜ  ተደዋውለው  ተገናኙ፡፡ማታ አስራሁለት ሰዓት አካባቢ ሆቴል ነው የተገናኙት…ዝንጥ ብላ ነው የመጣችው፡፡በሞቀና በጋለ ሰላምታ ተቀበላት ፡፡ምግብ አዘው በልተው መጠጥ እየተጎነጩ ወሬ ጀመሩ ፡፡
‹‹እሺ እንዴት ነሽ..?ነገሮች እንዴት እየሄዱ ነው?››ሲል ለጫወታ መጀመሪያ የሚሆን አ.ነገር ሰነዘረ፡፡
‹‹ቆይ እስኪ የእኔ ጉዳይ ይቆይ…ለመሆኑ አንተ እንዴት ነህ?››መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹ማለት..እኔ ደግሞ ምን እሆናለሁ?››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ማለቴ በቀደም ሳልጠይቅህ ….አገባህ እንዴ?››
‹‹አረ..በፍጽም፣ባገባ ኖሮ ቢያንስ ለእቴቴ ነግራት ነበር..ለእሷ ከነገርኩ ደግሞ ያው ልጇ ስለሆንሽ አትደብቅሽም ነበር፡፡››
‹‹አውቄዋለሁ….!!››
‹‹እንዴት .?ምኑን ነው ያወቅሽው?››
‹‹አንተ በቀላሉ የምትጨበጥ ወንድ አይደለህማ..አንድ ሴት አንተን አሳምና ወደ ጋብቻ ለመውሰድ በጣም ነው የሚከባዳት፡፡እርግጠኛ ነኝ ለማንም ሴት ከባድ ነው የሚሆንባት ፡፡››
‹‹እንዴ ያን ያህል አስቸጋሪ ሰው ነኝ እንዴ?››እሱን በተመለከተ በሰጠችው  አስተያየት የእውነት ገርሞት  ነው የጠየቃት ፡፡
‹‹አዎ እኔ እስከማውቅህ ድረስ፣ሀሳብህና ፍላጎትህ በደቂቃ ውስጥ  ነበር የሚቀያየረው…መቀሌም  ሞያሌም በአንድ ጊዜ መገኘት የምትፈልግ ለመረዳት አስቸጋሪ አይነት ሰው ነህ፡፡ማለቴ ነበርክ..አላውቅም ምን አልባት ባለፉት አምስት.. ስድሰት አመታት ተቀይረህ ሊሆን ይችላል..እኔ የማውቀው አሌክስ  ግን እንደዛ ነበር፡፡››
‹‹በእውነትን እንደዛ አይነት ሰው መሆኔን አላውቅም ነበር፡፡ደግሞም አንድ እህት ወንድሟን በተመለከተ ይሄንን የመሰለ አስተያየት መስጠት ያልተለመደ አይነት ነው፡፡፡››
‹‹እንዴት  ..ትክክለኛ ባህሪህን እኮ እየነገርኩህ ነው፡፡ለምሳሌ አስራሁለተኛ ክፍል ጨርሰን ማትሪክ እንደወሰድን  አብረን ተማክረን  ተግባረእድ ተመዝግበን  ነበር፡፡ትምህርት ሲጀመር ግን ብን ብለህ ቤቱንም ከተማውንም ለቀህ ጠፋህ .ፖሊስ  ለመሆን ተመዝግበህ  ማሰልጠኛ መግባትህን እንኳን ለእኔ መንገር አልፈለክም..ከእናቴ ነበር የሰማሁት፡፡ሁል ጊዜ የሆነ ነገር አብረን እናቅዳለን..ትግበራው ላይ ግን ድንገት ታፈነግጣለህ፡፡በዚህ በዚህ ሁሴንና አላዛር ካንተ በጣም የተሻሉ ናቸው፡፡እነሱ በቃላቸው ይፀናሉ…በተለይ አላዛር››
‹‹ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ..ለገዛ ባልሽ እያደለሽ ነው..?ለመሆኑ ሁሴን አሁን የት ነው ያለው?››
‹‹ያው ከመሀካላችን የተሻለ ጭንቅላት ያለው እሱ ነበር ፡፡አሁን  እንግሊዝ ሀገር የህክምና ዶክተር ሆኖ እየሰራ ነው…ግን በቅርብ ሳይመጣ አይቀርም፡፡››
‹‹አዎ ውጭ መሄዱንማ ሰምቼለሁ….ለማለት የፈለኩት ትደዋወላላችሁ ወይ ለማለት ነው?››
‹‹ከአላዛር ጋር እስክንጋባ ድረስ እንደዋወል ነበር፡፡ከዛ በኃላ ግን  ደውሎልኝ አያውቅም፡፡.እኔም አንድ ሁለቴ ልደውልለት ሞክሬ ነበር ስልኩን ቀይሮታል መሰለኝ አልሰራ አለኝ፡፡››
‹‹ተበሳጭቶብሽ ነዋ?››
‹‹ምን ያበሳጨዋል?››
‹‹በጣም  ያፈቅርሽ ነበር እኮ…!!››
‹‹ያፈቅርሽ ነበር ወይስ ይወድሽ ነበር?››
‹አንቺ ደግሞ …ሶስታችንም ነበር የምናፈቅርሽ..ይሄንን ደግሞ አንቺም በደንብ ታውቂያለሽ፡፡›.
የመደንገጥና ግራ የመጋባት ስሜት በፊቷ ላይ ተንፀባረቀባት ‹‹ምን እያልከኝ ነው…? እየቀለድክ ነው አይደል?››
‹‹አንቺ ነሽ እንጂ እየቀለድሽ ያለሽው…፡፡ ሶስታችንም ገና ማፍቀር እራሱ ምን እንደሆነ ሳናውቅ በፊት እናፈቅርሽ ነበር፡፡እድሜያችን በሙሉ ማነው በይበልጥ ሚያፈቅራት እያልን ስንፎካከለርብሽ  ነው ያሳለፍነው፡፡››
‹‹እኔ ትምህርት ጨርሰን እስክንበታተን ድረስ አራታችንም እርስ በርስ የምንዋደድ የልብ ጓደኛሞች እንደሆን ብቻ ነበር የማውቀው፣በተለይ አንተ ወንድሜም ጭምር ስለነበርክ  በዚህ መልኩ ላስብህ አልችልም፡፡ ››
‹‹ይሄን አላዛር እስከአሁን እንዴት ሳይነግርሽ…?ለነገሩ ምን ብሎ ይነግርሻል፤ አውቀሽ እሱ እንዳይከፋ በማሰብ ያላወቅሽ መስለሽ እንደምታስመስይ ነው የሚያስበው፡፡››
‹‹እሺ የሁሴንስ ይሁን ..አንተ የእውነት ታፈቅረኝ ነበር?››
‹‹ለዛውም ልክ በሌለው መጠን ነዋ….ለአንቺ ስል የማላደርገው ምን አለ..ቢያንስ የሞዴሱ ታሪክ ትዝ አይልሽም?››
‹‹አንተ ..ደግሞ ታስታውሰኛለህ እንዴ?ስንት አመት ሙሉ አንተ ምትገዛልኝ እየመሰለኝ አንጀቴን ስትበላው ኖረህ…አለችና በሳቅ ፈረሰች..እሱም ተከተላት፡፡
ሁለቱም በምናባቸው ወደኃላ ተጓዙና ትካዜ ውስጥ ገቡ
ሰሎሜ የወር አበባዋ የመጣው በ14 አመቷ ነበር፡፡ያንን ደግሞ ከግሩፑ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቀው አለማየሁ ነበር፡፡የዛም ምክንያት ከሰሎሜ ጋር አንድ ቤት በመኖራቸው ነው፡፡ወር በመጣ ቁጥር ግን ለሞዴስ የሚሆን ብር እናትዬውን መጠየቅ እያሳቀቃት ስትበሳጭ ይሰማና ..ይሄንን ችግር የሚፈታበትን ዘዴ ማሰላሰል ይጀምራል፡፡
ከዛ ፡አላዛር በዛን ጊዜ   ከትምህር ሰዓት ውጭ የሱቅ ስራ ይሰራ ስለነበረ ወደእዛው ነው የሄደው፡፡
‹‹እሺ ቱጃሩ እንዴት ነህ?››
‹‹ያሄው እንደምታየው ነው....ምነው ብቻህን?››
‹‹ማለት?››
‹‹ሰሎሜን ወይም ሁሴንን አስከትለህ ይምትመጣ መስሎኝ ነበር፡፡››
ከሁለቱን ማንን ይዤ ብመጣ ነበር የምትደሰተው?››ሲል መልሱን እያወቀው ጠየቀው፡፡
‹‹ምን ለማለት ነው…?ሁለቱም ጓደኞቼ ናቸው …ለምን መርጣለሁ?››
‹‹ተው እንጂ …አታስመስል፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ…!››ብሎት ዝም አለ
‹‹ቆይ ..ሞዴስ አለህ እንዴ?››
አላዛር ደንግጦ‹‹የምን ሞዴስ?››ሲል ነበር መልሶ የጠየቀው፡፡
‹‹ሞዴስ ነዋ ..ሴቶች የወርአበባ ሲመጣባቸው ሚጠቀሙበት፡፡››ሲል ብራራለት፡፡
‹‹የለኝም፡፡››
‹‹ለምን አታመጣም..ሴቶች አይጠይቁህም?››
‹‹እሱማ አልፎ አልፎ ይጠይቁኛል፡፡››
‹‹እና ለምን አታመጣም?››
‹‹እንዲሁ…ብዙም አስቤበት አላውቅም…ግን አልገባኝም. .እንዴት ልትጠይቀኝ ቻልክ?፡››
‹‹አይ ሰሎሜ እኮ አላዛር ሞዴስ የሚሸጥ ቢሆን እኮ በየወሩ አንድአንድ ይሰጠኝ ነበር…በየወሩ እቴቴን አላስቸግርም ነበር ስትል ሰምቼት ነው፡፡››
በመደነቅ‹‹በእውነት እንደዛ አለች…?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አዎ ብላለች››ሲል  ነበር ፍርጥም ብሎ የዋሸው፡፡
‹‹ግን የወር አበባ ታያለች ማለት ነው?››
‹‹እንዴ ለምን አታይም ሴት አይደለች?››
‹‹ማለቴ ገና ልጅ ነች ብዬ እኮ ነው፡፡››
‹‹ምነው አንተ መርጨት አልጀመርክም እንዴ?››
‹‹አንተ ደግሞ ታበዛዋለህ፡፡››
‹‹እንደውም ቆየች ..ባይሎጂ ላይ አልተማርክም እንዴ ..?አንድ ሴት እኮ ከ12 ዓመቷ ጀምሮ የወርአበባ ልታይ ትችላለች፡፡››
‹‹እሱማ አውቃለሁ…በቃ አሁን አደገች ማለት ነው?››
‹‹አዎ ..በደንብ እያደገችልን ነው፡፡››
‹‹በቃ…ከነገ ጀምሮ አመጣለሁ፡፡››
‹‹ጥሩ ..ለዚህ ወር ተገዝቶላታል..ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ትሰጣታለህ፡፡››
‹‹አዎ..ምንም አታስቢ በላት፡፡››
‹‹እሺ እላታለሁ..የወር አበባዋ የሚመጣው በ22 ወይም በ23 አካባቢ ነው…ስለዚህ በ20 በ20 እየመጣሁ ወስድላታለሁ፡፡››
‹‹ችግር የለውም..ግን እራሷ መጥታ ለምን አትወስድም፡፡››
👍458
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን
===================

ቀለል ያሉ ሌሎች ጫወታዎችን  ሲጫወቱ  አመሹና  እቤቷ ድረስ ሸኝቷት በብዙ ነገር ተወስውሶ  ወደቤት ተመልሶ  ገባና የወንደላጤ ቤቱን ከፍቶ ባዶ ቤት ውስጥ ባዶ አልጋ ላይ ብቻውን ተኝቶ  ማሰላሰል ጀመረ፡፡

ሰሎሜ ደጋግማ እንደጠየቀችው..ከተማውንም ሆነ ሁሉንም ጓደኞቹን ድንገት ጣጥሎ ፖሊስ ማሰልጠኛ  የገባበት የራሱ የሆነ ምክንያት አለው..በቂና ጠንካራ ምክንያት ነበረው::
አለማየው  የፈራረሰና ጣሪያው የዛገ ባለአንድ ክፍል ቤት ውስጥ  ከእናትና አባቱ እና ከታናሽ ወንድሙ እና የሴት አያቱ ጋር የድህነት ግን ደግሞ ጣፋጭ ሳቅና ደስታ የሞላበት ኑሮ ይኖር ነበር፡፡ነበር እንዲህ ህልም ሆኖ አይን ጨፍኖ ሲገልጡ እንደሚበን ማሰብ ይከብደል፡፡ያ ሞቀትና የደመቀ… በፍቅር ሀውልት የተገናባ የቤተሰብ ትስስር በአንድ ወር ውስጥ ነው ድርምስምሱ ወጥቶ የፈረሰው፡፡በወቅቱ እሱ የ13 አመት ወጣት እና የ7 ክፍል ተማሪ ነበር፡፡ድንገት አባትዬው ታመምኩ አለና አልጋ ያዘ፡፡በሶስተኛው ቀን ሰፈር ያለ ጤና ጣቢያ ወሰዱት ፡፡አንድ ቀን አድሮ እስከወዲያኛው አሸለበ፡፡ ያልተጠበቀ ስለነበረ ሁኔታው ጠቅላላ ለቤተሰቡ እንደመቅሰፍት ነበር ፡፡በተለይ ለእናቱ…፡፡አባትዬው በሞተ በማግስቱ ተቀበረ፡፡ከቀብር መልስ እናትዬው ወደ ድንኳን ውስጥ ገብታ በተነጠፈላት የሀዘንተኛ ፍራሽ ላይ ተቀምጣ ሊያስተዛዝኗት የመጣውን የሩቅም ሆነ የቅርብ እንግዶችን በመቀበል ፋንታ ወደቤት ገብታ ከባሏ ጋር ትተኛበት የነበረበት አልጋዋ ላይ ገብታ ጥቅልል ብላ ተኛች፡፡.በሶስተኛው ቀን እስትንፋሷ በውስጧ አልነበረም…፡፡ጉድ ተባለ..፡፡ፍቅር እስከመቃብር….ማለት ይሄ ነው ተባለ…፡፡
የአለማየሁና የወንድሙ እጣ ፋንታ ግን በደካማና እድሜዋ በጋፋ ተጦሪ አያቱ እጅ ነበር የወደቀው፡፡፡ድሮም የድህነት  መቀመቅ ላይ የነበረ ቤተሰብ ውሉ የጠፋበት ሆነ፡፡ ምርጫ አልነበረም፡፡አለማየሁና ታናሹ ለመለያየት ተገደዱ፡፡አያትዬው ጎንደር ለሚኖር ሌለኛው ልጃቸው..‹‹ቢያንስ አንደኛውን ልጅ ውሰድልኝ ››ብለው ተማፀኑት..አጎትዬው ታናሹ ይሻለኛል ብለው መረጡና እሱን  ወሰዱት፡፡አለማየሁና አያትዬው ቀሩ..፡፡ይሄ ሁሉ ሲሆን ግድግዳ ሚጋሩት ቀጥሎ ካለው የቀበሌ ቤት የሚኖሩት ሰሎሜና እናትዬው ከጎናቸው ነበሩ፡፡በማፅናናቱም ካላቸው ላይ ቆረስ እያደረጉ በማጉረሱም አልተለዬቸውም ነበር፡፡ከዛ አያትዬው ሁለመናው ጭልምልም ሲልባቸው.የሰሎሜ እናት እቴቴን ፊት ለፊታቸው አስቀምጠው‹‹ …እኔ በቃኝ፡፡ ለራሴ ማልሆን ሰው የልጅ ልጄን ጠቅመዋለው ብዬ እዚህ  አልቀመጥም…፡፡ጭራሽ ሸክም ነው የምሆንበት፡፡አንቺ ለእናቱ ጎደኛዋ ነበርሽ…አለማየሁንም ልክ ከሰሎሜ እኩል አንቺም አሳድገሽዋል ፡፡..ልጅሽ ነው…፡፡አሁንም አንቺው ነሽ ምታጎርሺን.. ስለዚህ እኔ የልጅ ልጄን ላንቺ ጥዬ ወደ ገዳም መሄዴ ነው…ባይሆን እዛ ሄጄ ፀልይልሻለሁ››በማለት አለማየሁን  ለሰሎሜ እናት ጥለውት ጠቅልለው ገዳም ገቡ፡፡አለማየሁ ብቻውን ቀረ …፡፡
ከዛ ሁሉ ከሞላ ቤተሰብ አመት ባልሞላ ጊዜ ቀስ በቀስ እየበነኑ ጥለውት በመሄዳ ባዶውን አስቀሩት፡፡ በቃ ባዶውን…፡፡ግን ሰሎሜና እናትዬው ከመጠን በላይ እንዲሰበርና አልፈቀዱለትም፡፡ለሰሎሜም እህት ለእሳቸውም ሁለተኛ ልጅ ሆነ ፡፡በመሀከል የሚያዋስናቸውን ግድግዳ ቀደው የውስጥ ለውስጥ በር አበጁለትና አንደኛውን በር ዘጉት፡፡ሁለት የተለያ ክፍል የነበረው ቤት ሁለት  ክፍል ያለው አንድ ቤት ሆነ፡፡
እሱ ከትምህርት ቤት በተረፈው ጊዜ ሰፈር ውስጥ እየተሯሯጠና እየተላላከ በሚያገኘው ብር እራሱን መደጎም ቀጠለ፡፡የሰሎሜ እናት በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የመዝገብ ቤት ሰራተኛ ስለሆኑና ቆሚ ደሞዝ ስላላቸው..ምንም እንኳን የተትረፈረፈ ኑሮ ባይኖራቸውም ለሁለቱ ልጆችና ለእራሳቸው ለለት ጉርስ የሚቸግራቸው አይነት ሰው እልነበሩም…አለማየሁን ከልጃቸው እኩል ለማኖር የእለት ጉርስንና የአመት ልብሱን ለመሸፈን ቸግሯቸው አያውቅም፡፡በዛ ላይ አለማየሁን ከልጅነት ጀምሮ ሚወዱትና ከእናትዬው ጋር ካላቸው ቅርበት የተነሳ ብቸኛ ልጃቸውን ክርስትና የነሳቸው የእሱ እናት ስለሆነች ልጄ ወንድም ይሆናታል  በሚል አመለካከት ከልባቸው ነበር የተቀበሉት፡፡በዛ ላይ ከዚህ በፊት ልጃቸው በህይወትና በሞት መካከል ሆና ሆሲፒታል በገባች ጊዜ ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እሷን ለማትረፍ ያደረጉትን ታሪካዊ ድርጊት መቼም አይረሱትም…እናም ደግሞ ለሌላ ለማንም ሰው የማይነግሩት ተጨማሪ ዋና ምክንያትም ነበራቸው፡፡
.ከዛ ቀስ በቀን ከሰሎሜ ጋር ያለውን ግንኙነት እያላላ ከእናትዬውን ግን በወጉና በስርኣቱ በስልክ እየጠየቀ ስልጠናውን ጨርሶ በምክትል መቶ ሀለቅነት ተመረቀ..ከዛ አዲስ አበባ አካባቢ የመመደብ እድል ቢኖረውም በራሱ ምርጫ ድሬደዋ እንዲመድቡት አድርጎ እርቆ ሄደ፡፡ይሄንን ታሪክ ሰሎሜ ሆነች ሌሎች ጓደኞቹ አያውቁም..አይደለም በዛ ጊዜ ዛሬም እንዲህ ነበር ብሎ ሊነግራትና ሊያብራራላት አይችልም….ከባድ ነው፡፡በሀሳብ ሰውነቱ ስለዛለ ለመተኛት ወደ መኝታ ቤቱ ሄዶ …ድንገት ሳያስበው የአላዛር  ምስል በአእምሮ ተሰነቀረ፡፡

‹‹አሁን አላዛር ህክምናው ባይሳካለትስ…?ሰሎሜ ወደፍርድ ቤት ጉዳዩን ይዛ እንድትሄድ መክራታለው ወይስ ምን አደርጋለው….? ፍርድ ቤቱ እንዲፋቱ ከወሰነስ በኋላ ከእሷ ጋር ያለኝ ግንኙነት እንዴት ነው የሚሆነው…?አሁን ሳይቸግረኝ ሳፈቅራት እንደኖርኩና አሁንም እንደማፈቅራት ነገሬታለሁ…እና በቀጣይ ፡፡ ርቃታለሁ ወይስ የበለጠ ከእሷ ጋር ያለኝን ጓደኝነት አጠናክራለሁ….?እና ከዛስ…አሁን ተራው የእኔ ነው አግቢኝ እላታለሁ? ወይስ ?››..እራሱን አመመው፡፡

ስለምንም ነገር ማሰብ አቁሞ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ለመተኛት በመፈለግ የለበሰውን ልብስ አውልቆ ቢጃማ እየቀያየረ ሳለ ስልኩ  ድምጽ አሰማ..አነሳውና አየው… መልዕክት ነው፡፡ሰሎሜ ነች የላከችው፡፡

‹‹አሌክሶ ..በሰላም እቤት ገባህ..?››ይላል፡፡

‹‹አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለና  መልስ ፅፎ ላከላት‹‹አዎ….ቢራ ቢሮዋ  ሰላም ገብቼለሁ?››

ከልጅቷ ጀምሮ በጣም ቀጭን እና በንፋስ ግፊት በአየር ላይ ተንሳፋ የምትበር ስለምትመስል ቢራቢሮ የሚል ቅፅል ስም አላት…ብዙውን ጊዜ እሱ በዚህ ስም ነው የሚጠራት፡፡

‹‹ጥሩ…ደስ የሚል ምሽት ነበር ያሳለፍነው…አመሰግናለሁ››

‹‹እኔም የልጅነት ጊዜዬን ወደኋላ ተመልሼ እንዳስታውስ ስላደረግሺኝ  ደስ ቢለኝም የተዳፈነ የልጅነት ፍቅሬን ስለቀሰቀሺብኝ ችግር ላይ ነኝ፡፡››ብሎ  ፃፍላና ላከላት፡፡

‹‹አንተ ባለትዳር እኮ ነኝ…ለምን ታሽኮረምመኛለህ?››

‹‹ይቅርታ ምን ላድረግ..?እንደምታውቂው ፍቅር  ይሉኝታ ቢስ ስሜት ነው፤ለማንኛውም አላዛርን ሰላም በይልኝ››

‹‹አይ …እራስ ደውለህ ሰላም በለው፤.ሌላ ነገር እንዲያስብ አልፈልግም…በመጀመሪያ ጉዳዩን ስለነገርኩህ እራሱ በጣም ቅር ብሎታል?፡፡››

‹‹አይ ታዲያ ምን ማድረግ ትችይ ነበር..?እስከመቼ ለብቻሽ በጉዳዩ መሰቃየት ትችያለሽ?››

‹‹አየህ አንተ ከልጅነቱ ጀምሮ የምታውቀው ጓደኛው ነህ.. ሁለታችሁም በጋራ የምታውቋቸው በርካታ ሰዎች አሉ ....ይሄንን ጉዳይ አንተ አወቅከው ማለት ሌሎች እሱንና አንተን የሚያውቁ ሰዎችም የማወቅ እድል ይኖራቸዋል ማለት ነው. .ይሄ ደግሞ ስነልቦናውን ይበልጥ ይጎዳል…..በዛ ላይ እንደምታውቀው የእናንተ የወንዶች ኢጎ ከፍተኛ ነው፡፡››
👍655👏2
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
:
:
#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

‹‹እሺ ቻው ሁሴን…››ስልኩን ዘጋ፡፡ፈጽሞ ያልጠበቀው ነገር ነው፡፡ድብልቅልቅ የሆነ የሚረብሽ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው፡፡ደስታም መረበሽም ….አሁንም ሶስቱም  አንድ ላይ ተገናኝተው  ሰሎሜን ከበው ሲቀመጡ ምን እንደሚሰማቸውና ምንስ ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አልቻለም፡፡

እርግጥ አሁን እንደድሮው አይደለም ሰሎሜ የአላዛር ህጋዊ ሚስት ሆናለች፡፡ግን ደግሞ በመሀከላቸው ያለው ሸለቆ ስምጥና  እሩቅ ነው፡፡እና አላዛር ከበሽታው ማገገም ተስኖት ሁለቱ ከተፋቱ ሰሎሜን መልሶ ለማግኘት ሁለቱ ይፎካከራሉ ማለት ነው…አለማየሁና  ሁሴን…..‹‹ምን አልባት እሱ እስካሁን ባለበት ሀገር አንዷን ወዶና አጭቶ ወይንም አግብቶ ሊሆን ይችላል… እንደዛ ከሆነ ግልግል ››ሲል አሰበና እራሱን እንደምንም ለማረጋጋት ጥረት ማድረግ ጀመረ፡፡
የሁሴንን ድምፅ በስልክ ከሰማ በኃላ  የአላዛርን የህክምና ውጤት ለማወቅ በጣም ነው የጓጓው…ደውሎ ሊጠይቀው አስበና ደግሞ ምን ብሎ እንደሚጠይቀው ስላልገባው  ሀሳቡን ሰረዘ፡፡

…‹‹እራሱን ወይም ልቡን አሞት ቢሆን ኖሮ በቀላሉ ደውዬ የድሮ ጎደኛዬ ልብህን እንዴት ሆንክ ..?አሁን ምን ይሰማሀል…?ምርመራው ምን ውጤት አስገኘ….?ምናምን እያልኩ በዝርዝር እጠይቀው ነበር፡፡››ሲል ተነጫነጨ…ድንገት ብልጭ አለለትና ከተኛበት አልጋ ተነሳና ቁጭ አለ.. ስልኩን ከተቀመጠበት አነሳና ዳታ አበራ…..
ስንፈተ ወሲብ ብሎ ሰርች ሲያደርግ ብዛት ያላቸው መረጃዎች ተዘረገፉለት…የመጀመሪያውን ከፈተ፡፡
ስንፈተ ወሲብ ወይም የወንድ ብልት አለመቆም ችግር ለወንዶች አሳሳቢ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። ይህ ችግር የወንዶችን በራስ መተማመን የሚቀንስና ፍርሃት የሚያሳድር ነው። ስንፈተ ወሲብ ማለት በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የወንድ ልጅ ብልት በደንብ መቆም አለመቻል ነው።
ንባቡን አቆመና ማሰብ ጀመረ..‹‹የእሱ ግን ያለመቆም ችግር ነው እንዴ..?ነው ወይስ ሙሉ በሙሉ ፍላጎት ማጣት…?.››መረጃው ስለሌለው ማሰቡን አቁሞ ንባቡን ቀጠለ፡፡
ስንፈተ ወሲብን ማከም የምንችልባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።
•  ስኳር የበዛባቸው ምግቦች የወሲብ መነሳሳትን ወይም የወሲብ ፍላጎትን ሊቀንሱ ስለሚችሉ ብዙ ስኳርንና ከፍተኛ ካርቦሀይድሬት ያላቸውን ምግቦች ማስወገድ።
•  የኮሌስትሮል መጠናችን ጤነኛ በሚባለው ደረጃ መቆጣጠር።
•  የደም ፍሰትን ለመጨመር ከፍተኛ አሚኖ አሲድ ያላችው ምግቦችን መጠቀም።
•  በዚንክ የበለፀጉ ምግቦችን መጠቀም እንዲሁም የቴስቴስትሮን ሆርሞን እንዲመረት የሚረዱ ሰፕልመንቶችን መውሰድ።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መፍትሄዎች ቀለል ያለ የስንፈተ ወሲብ ችግር ላለባቸው ሰዎች እንደመፍትሄ የተቀመጠ ሲሆን ከዛ ከፍ ያለና አሳሳቢ የሆነ ስንፈተ ወሲብ ችግር ካለብዎ የሜዲካል ህክምና ማግኘት እንደ  ኤክስትራኮርፖራል ሾክዌቭ ህክም ማግኘት ይገባል ይላል፡፡የኤክስትራኮርፖራል ሾክዌቭ ህክምና የታካሚው ብልት ውግት አድርጎ በመያዝ ዝቅተኛ ኢንተንሲቲ ባለው ግፊት ሞገድ ወደ 4000 ሾክ በወንዱ ብልት 4 ቦታ ላይ የብልት የደምስሮችን ለማነቃቃት ይሰጣል። በዚህ ህክምና ታካሚው በሳምንት ከ1-2 ጊዜ በተከታታይ ለ12 ሳምንት ህክምናውን መውሰድ አለበት።
የሚያነበው ነገር ሁሉ ምንም እየገባው አይደለም…ልክ ያንቀላፋ ያለን ልብ በኤልኬትሪክ ሾክ መንጭቆ እንደማስነሳት አይነት ህክምና ይሆን እንዴ..?ልክ እንደዛ በብልት ዙሪያ  የኤሌክትሪክ ንዝረት በመልቀቅ ተመንጭቆ እንዲነሳና እንዲያቆም ማድረግ ይሆን እንዴ….?ተመንጭቆ ተነስቶ አልተኛም ቢልስ?››በራሱ ጥያቄ እራሱ ሳቀ፡፡

እግዚያብሄር ከዚህ አይነት በሽታ አንዲሰውረው  በመፀለይ ስልኩን አጠፋና መልሶ ተኛ፡፡

በሶስተኛው ቀን ከስራ ወደቤት እየተመለሰ  መንገድ ላይ እያለ  አላዛር ደወለለት፡፡

‹‹ሄሎ አላዛር እንዴት ነህ?››

‹‹ምንም አልል ሰላም ነኝ››
ምን ሊነግረው እንደደወለለት  ለማወቅ በከፍተኛ ጉጉት ‹‹አይ ጥሩ ነው…ምነው ፈለከኝ….?.››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹አዎ …ነገ ማታ እራት ብጋብዝህ ብዬ አሰብኩ››

‹‹ይቻላል….የትና በስንት ሰዓት እንደምንገኛኝ ንገረኝ..እገኛለሁ››

‹‹ጥሩ …ቴክስት አደርግልሀለው››

‹‹እሺ እጠብቃለሁ….ግን ሰላም ነው አይደል…?ማለቴ የተነጋገርነው ህክምና በተመለከተ አዲስ ነገር አለ?››በመከራና በጭንቀት ጥያቄውን አፈረጠው…
እስከነገ እንዴት  ብሎ አምቆ ይያዘው…?‹‹የእራት ግብዣው ሙሉ በሙሉ ተፈወስኩ ብሎ የምስራች ሊለኝ ቢሆንስ?.››ሲል አሰበና ተጨነቀ፡፡ የእሱ የምስራች ማለት ለእሱ በተዘዋወሪ  መርዶ ነው….

‹‹አሌክስ  ያው በተነጋገርነው መሰረት ቀናቶች አሉኝ አይደል?››

‹‹አዎ ..20 ቀን አለህ…እንዲሁ ሂደቱ እንዴት እየሄደልህ ነው የሚለውን ለማወቅ ነው››

‹‹ለጊዜው ሁሉ ነገር በሂደት ላይ ስላለ መጨራሻውን በእርግጠኝነት አላውቅም ..ሀኪሞቹም የሚያውቁ አይመስለኝም››

‹‹ጥሩ ..በእኔ በኩል ላግዝህ የምትፈልገው ነገር ካለ ሁሉ ጊዜ አለሁልህ…አሁን መራራቃችንን ሳይሆን የልጅነት ቅርበታችንን  አስበህ ምንም ነገር ልትጠይቀኝ ትችላለህ….ይሄ ነገር ተስተካክሎ ሁለት የልጅነት ጓደኞቼ ደስተኛ የሆነ ትዳራቸውን እንዲያስቀጥሉ እፈልጋለው…ሁለታችሁንም ስል ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አደርጋለሁ››አለው…ንግግሩ ለራሱ  ጆሮ እንግዳ ስሜት ነው የፈጠረበት፡፡
‹‹በእውነት አሌክስ ይህንን መስማቴ ደስ ብሎኛል…በቀደም ቢሮህ ተገናኝተን  በጉዳዩ  ላይ ስንወያይ ንግግርህ ጨከን ያለ ነበር…ይቅርታ አድርግልኝና እንደውም…የሄ ልጅ የእኛን መለያየት ይፈልጋል እንዴ?ብዬ እንዳስብ ነበር ያደረከኝ..ያንን ስሜቴን ደግሞ በእለቱ ነግሬሀለው››ሲል እውነቱን አፍርጦ ነገረው፡፡

እንደዛ ሲለው ዛሬም መደንገጡ አልቀረም….ያን ያህል እስከሚያስታውቅበት እንደዘባረቀ አልተሰማውም ነበር…..ማስተባበሉን ቀጠለ‹‹እንዴ ምን ነካህ ?ለምንድነው እንድትለያዩ የምፈልገው?››

‹‹ያው ታውቃለህ አይደል…..?››

‹‹ምኑን ነው የማውቀው?››

‹‹ያው ልጅ ሆነን ጀምሮ ሶስታችንም ነበር የምናፈቅራት››

‹‹ልጅ ሆነን ነበራ ››

‹‹አሁን እንደውም በይበልጥ ውብና ማራኪ ሆናለች እኮ…እንደውም በበለጠ በፍቅር የምታማልለው አሁን ነው…ማለቴ ስሜቱን በራሴ አውቀዋለው..በየጊዜው ትንሽ ባደገችና እድሜ በጨመረች ቁጥር ውብና ማሪኪ እየሆነች እኔም አምርሬ እያፈቀርኳት ነው እየሄድኩ ያለሁት››

‹‹አላአዛር…አንተ እኮ እንደዛ ቢሰማህ ሚስትህ ስለሆነች ነው…..እኛን በተመለከተ የምታወራው ግን የልጅነትና ያለፈ ታሪክ ነው››

‹‹ለማንኛውም እንደዛ ስላሰብኩህ ይቅርታ…በእውነት ያንተን እገዛና ማበረታቻ በጣም ነው የሚያስፈልገኝ…በዚህ ጉዳይ ላይ ከአንተ በተሻለ የሚረዳኝና የሚያግዘኝ ሰው እደሌለ እኔም  አምናለው››

‹‹አዎ እንደዛ ጥሩ ነው..በል አሁን ቻው …ነገ እንገናኛለን፡፡››
‹‹.ቻው እሺ ..አመሰግናለሁ፡፡››
👍559
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ
================

አለማየሁ በቀጠሮው መሰረት  ከአላዛርና አለማየሁ ጋር ከተገናኘ በኋላ ‹‹እሺ ባላና ሚስቶች ለምንድነው የፈለጋችሁኝ….?ለጥሩ ነገር እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡››ሲል የመጀመሪያ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡

ሁለቱም እርስ በርስ ተያዩ..አንተ ንገረው አንቺ ንገሪው እየተባባሉ የሚገባበዙ ይመስላል አላዛር ቅድሚያውን ወሰደ‹‹በሚቀጥለው ሳምንት ሁሴን እንደሚመጣ ታውቃለህ አይደል?››

ያልጠበቀውን ርዕስ ነው ያነሳበት‹‹ትክክለኛውን ቀን አላውቅም እንጂ  እንደሚመጣ አዎ በቀደም ደውሎልኝ ነበር..››

‹‹ጥሩ እንግዲህ ..እናቱም አባቱም እንደሞቱ ታውቃለህ…..እዚህ ሌላ ዘመድ የለውም ..ከፋም ለማም የልጅነት ጓደኞቹና የቅርቡ ሰዎች እኛ ሶስታችን ነን››

በውስጡ ‹‹የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች›› የሚለውን ተረት  እየተረተበት ‹‹አዎ ትክክል››ሲል መለሰ፡፡

‹‹እና እንዴት እንቀበለው የሚለውን ለመነጋገር ነው፡፡››

‹‹በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው፡፡ይሄ የድሮ ጓደኛችንን የመቀበል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን እኛም መልሰን ለአመታት ተራርቀን ከቆየንበት ለመቀራረብና መልሰን ጓደኝነታችንን ለማደስ ያግዘናል….››አለ
…እንደዛ ሲል በውስጡ ያለው ከአላዛር ወይም ከሁሴን ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ድሮ ጓፈደኛነታችው የመመለስ ጉጉት ኖሮት አይደለም..ከዛ ይልቅ ስለሰሎሜ በውስጡ እያሰበ ነው፡፡

‹‹በጥሩ ሁኔታ ብንቀበለው ደስ ይለኛል…እኔ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ….ዝግጅቱን እኔ ቤት ማድረግ እንችላለን››አለ…

‹‹አይ ከአንተ ቤት የእኛ ቤት ይሻል ይመስለኛል….ማለት የወንደላጤን ቤት ማድመቅ ይከብዳል›› ሰሎሜ  ነች ተናጋሪዋ፡

‹‹እሺ እንዳልሽ…እኔ  ቤት ብንቀበለው በዛውም የራሱን ነገር እስከሚያመቻች አኔ ጋር መቆየት ይችላል ብዬ ነው፡፡››

‹‹እኛ ጋርስ ለመቆየት ምን ይከለክለዋል…?እቤታችን እንደሆነ እንኳን እሱንና  አንተም ብትጨመር በቂ ክፍት ክፍሎች አሉን ….እንደምታውቀው እዛ አፓርታማ ቤት ውስጥ እኔና እሱ ብቻ ነን....ልጅ የለን ምን የለን››

በሰሎሜ ንግግር አላዛር ሽምቅቅ አለ..ሆነ ብላ አስባበት የተናገረችው እንደሆነ   ያውቃል….ግን ዋጥ አድርጎ በትዕግስት ከማሳለፍ ውጭ ምርጫ እንደሌለው ያውቃል፣ያደረገውም እንደዛ ነው፡፡
አለማየሁ‹‹በቃ እሺ እጅ ሰጥቼለው››ሲል በሀሳባቸው ተስማማ፡፡

‹‹ጥሩ  በቃ …እንደዛ ከሆነ በፊታችን እሁድ ቤት ናና ስለዝርዝሩ እንነጋገርበታለን››

‹‹ጥሩ..እንደውም በሰበቡ ቤታችሁን አያለሁ››

‹‹አዎ ››
ከዛ በኃላ ብዙም ያወሩት ነገረ የለም ፡፡ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡

‹‹አላዛር እና ሰሎሜ በአንድ መኪና ገብተው ወደቤታቸው እየተጓዙ ወሬ ጀመሩ‹‹ግን እርግጠኛ ነህ..?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምኑን?››

‹‹ማለቴ  የሁሴን እኛ ቤት ማረፍ….ነው ወይስ አንድ ሁለት ቀን እኛ ጋር ካደረ በኃላ ሌላ ማረፊያ ፈልግ ልንለወው ነው፡?››

‹‹ለምን …አንቺን ካልደበረሽ እቤታቸን ሰፊ ነው…ሁሴን የማናውቀው ሰው አይደለም ….ለሁለታችንም ቅርብ የሆነ ሰው ነው፡፡››

‹‹ገባኝ….በደንብ አስበህበታል ወይ ለማለት ነው…?.እኔማ ደስ ይለኛል..ግን እወቅ እንደነገረኝ ከሆነ እስከሶስት ወር ሊቆይ ይችላል፡፡››

‹‹ችግር የለውም..ታውቂያለሽ የሆነ የእኛ የምንለው ሰው አብሮን እንዲኖር እንዴት እፈልግ እንደነበረ…እህቶቼም ሁለቱም ስላገቡ ወደቤታችን ላመጣቸው አልቻልኩም…የአንቺም እናት  አሻፈረኝ ብላለች..እስኪ አሁን በጓደኛችን እንሞክረው፡፡››

‹‹እማዬ እኮ ከእናንተ ጋር አልኖርም አላለችም..እሷ ያለችው ልጅ ስትወልዱ እሱን ለማሳደግ መጣለሁ…አሁን ግን መጥቼ የእናንተ ሞግዚት መሆን አልፈልግም ነው ያለችው››።

‹‹እና በሞግዚት ኑሪ እንጂ  ሞግዚት ሁኚን  መች አልናት?››

‹‹ተወው አሁን… ለምን የማይሆን ጭቅጭቅ ውስጥ እንገባለን…ቁርጥ አድርጋ አቋሟን አሳውቃለች…መውለድ ስንችል ትመጣለች››

‹‹ይሁን እሺ… ለማንኛውም ስለሁሴን አትጨነቂ… ሁኔታዎች ካልተመቹት እኮ እራሱ አማራጭ ይፈልጋል፡፡››በማለት የተጣመመውን ርእስ እንደምንም ብሎ አቃናው፡፡

‹‹ጥሩ..ለእኛም ከብቸኝነት ጋር ከመታገል በተወሰነ መንገድ ይታደገናል…›› ስትል መለሰች፡፡

‹‹እኔም እሱን አስቤ ነው ››አላት..ግን ሁለቱም ስጋታቸው ሌላ እንደሆነ ግልፅ ነው…ሁሴን ልክ እንደአላዛር ሁሉ የሰሎሜ የልጅነት አፍቃሪዎ እንደሆነ ሁለቱም ያውቃሉ፡፡ለሁለቱም እኩል ጓደኛቸው ቢሆንም ለእሷ ግን በተለየ መልኩ አፍቃሪዋም ጭምር ነው…እና አሁን አንድ ቤት እሱን ጎትቶ ማምጣት ለዛውም አሁን ባልና ሚስቶቹ ባሉበት ሁኔታ ላይ አደጋ እንዳለውና የልታሰበ መዘዝ ሊያመጣ እንደሚችል…ለሁለቱም ግልፅ ነው….እና ሰሎሜ ደጋግማ ስለውሳኔው እርግጠኝነት እየጠየቀችው ያለው..ነገ አንድ ነገር ቢከሰት  ኃላፊነቱን እንዲወስድ በማሰብ ነው፡፡

እሷ ያላወቀችው ግን የእሱን እቅድ ነው…እሱ ሁሴን ወደቤት  እንዲመጣ ሲወስን መዘዙንም አስቦና አስልቶ ነው፡፡ምን አልባት የጀመረው የህክምና ጉዳይ ባይሳካለት ሊያደርግ የሚችለውን እቅድ አስቦና አስልቶ ጨርሷል..በቃ እራስ ወዳድ መሆን እንደሌለበት ገብቶታል…እየወደደም ቢሆን ከሰሎሜን ህይወት ሾልኳ መውጣት  እንዳለበት ወስኗል.. ከህይወቱ ሲሸኛት ግን በተሰበረ ልብ ሆና  ስነልቦናዋ ተጎድቶ መሆን እንደሌለበትም ነው የሚያምነው..ለእሱ መሆን ካልቻለች ከሁለት የልጅነት ጓደኞቾና ከልብ ከሚያፈቅሯት መቼም ቢሆን ሊጎዶት ለማይችሉት ለአንዱ ሊያስረክባት ነው ያሰበው….ለዛም ጥሪጊያ መንገድ ለመፍጠር ሁሴን በእንግድነት እሱ ቤት ማረፍ እንዳለበት ማድረግ እንዳለበት ተሰምቶታል፡፡፡ያንን ካደረገ ደግሞ አለማየሁም በተደጋጋሚ ወደእሱ ቤት ለመመላለስና ከሰሎሜ ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ የመገናኘት እድል ይኖራዋል፣በሂደት ከሁለት አንዱ ከእሷ ጋር በተሻለ መቀራረብ ይፈጥሩና ልቧን ማግኘት ይችሉ ይሆናል….ከዛ አንዱ ያገኛታል ማለት ነው፡፡ከዛ እሱ ሀዘኑን ለብቻው ያዝናል..ማጣቱን በማስታመም ቀሪ የብቸኝነት ዘመኑን ይገፋል…….፡፡እግዚያብሄር ቀንቶት ከተፈወሰ ደግሞ በቃ ምን ይፈልጋል…እና አሁን እያደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት ነው፡፡ይሄ ነው ሰሎሜን ያልገባት፡፡

ይሄ ጉዳይ ደግሞ ከሰሎሜ ይልቅ አለማየሁን ነው ፍፅም ግራ ያጋባው‹‹ሰውዬው ምን እየሰራ ነው?››የሚለው ሀሳብ በውስጡ መጉላላት የጀመረው ገና ከእነሱ እንደተለየ ነው፡፡እና ደግሞ አልተመቸውም….በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ወሳኝ ወቅት የሁሴን ወደሀገር ቤት ተመልሶ መምጣት ደስ አላሰኘውም ነበር፡፡፡በእሱ እምነት አላዛር ካልተሳካለት ቀጥታ ሰሎሜን የእሱ የማድረጉን ትግል በብቸኝነት ለመወጣት ነበር ዕቅዱም ምኞቱም..ሁሴን ደውሎ እንደሚመጣ ከነገረው በኋላ ግን ሌላ ተፋላሚ እየመጣበት እንደሆነ ነው ወዲያው የገባው…እንደውም መምጣቱ እራሱ ያጋጣሚ ነገር ሳይሆን  ሆነ ብሎ የታሰበበት እንደሆነ ነው የሚጠረጥረው…ሰሎሜ አላዛርን ከማግባቷ በፊት ከእሱ ጋር ለረጅም ጊዜ እንደምትደዋወል ነግራዋለች..በእሷ እና  በባሏ መካከል ያለውን ቦንብ ሚስጥር ለእሱ በተገናኙበት በመጀመሪያው ቀን ከነገረችው…ለረጅም ጊዜ ስትደዋወል ለነበረው ለዛውም ከባህር ማዶ ላለው ሁሴን ላትነግረው የምትችልበት ምክንያት ምንም እየታየው አይደለም…እንደጠረጠረው ነግራው ከሆነ ደግሞ በተለይ የሰሞኑን ግር ግር አብራርታለት ከሆነ የሆነ ምክንያት ፈጥሮ አጋጣሚውን ለመጠቀም እንደመጣ ነው የሚያምነው..እና ከእሱ ጋር
👍6014😁4
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ
================

..ፎጣዋን አገልድማ ስትወጣ እሱ ደግሞ ለመግባት እርቃን ሰውነቱን በፓንት ብቻ ሆኖ ወደእሷ አቅጣጫ ሲመጣ አየችው…ዞር ብላ መንገዱን ለቀቀችለት …ቀጥታ ወደውስጥ ገባና የሻወሩን በራፍ ዘጋው…
ባለቤቷን እንዲህ እርቃኑን ስታየው ሁሌ እንደአዲስ እንደገረማት ነው፡፡ሰለብሪቲ አክተር ወይም ታዋቂ ሞዴል እኮ ነው የሚመስለው፡፡እዚህ አካባቢ እንደዚህ ቢሆን የሚባል ቅር የሚያሰኝ የአካል ክፍል የለውም‹‹ሆሆ..ለናሙና የተፈጠረ እኮ ነው የሚመስለው››አለችና ሰውነቷን አደራርቃ በምሽቱ ሶስቱን የእድሜ ልክ አድናቂዎቾና አፍቃሪዎቾ ወንዶችን ያስደምማል ያለችውን አለባበስ ለበሰች፡፡ፀጉሯን አስተካከለች፡፡የተወሰነ ሜካፕ ተጠቀመችና ሽቶ እላዮ ላይ ነስንሳ ወደሳሎን ወጣች፡፡
አለማየሁ ሰማያዊ ቀለም ያለው ሙሉ ሱፍ ለብሶ  ዝንጥ ብሎ  ሳሎን ቁጭ ብሎ እስኪወጡ እየጠበቃቸው ነበር፡፡
እንዳየችው ‹‹እንዴ ኩማንደር….አምባሳደር መስለሀል፡፡›› አለችው፡፡

‹‹የወደፊት እጣ ፋንታዬ ምን አልባት አምባአሳደር ሊሆን ይችላል፡፡››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ምነው አፍጥጠህ አየሀኝ…ልብሱ አልሄደብኝም እንዴ?››ሲል በጥርጣሬ ጠየቃት፡፡

‹‹አረ የሚያስደነግጥ አለባበስ ነው … እንከን አይወጣለትም ..በጣም ያምራል፡፡››

‹‹ልብሱ ብቻ ነው ሚያምረው?››ስትል ልስልስ በሆነ ቅንዝራም ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹ስለአንቺ አላዛር ሲመጣ ይነግርሻል….ያንን አስተያየት የመስጠት መብት ለጊዜው የእሱ ነው፡፡››

ግንባሯን ቋጠረች‹‹ለጊዜው ስትል…?››

‹‹ይሄ ጥያቄ ይዝለለኝ፡፡››

‹‹በጣም ተቀይረሀል ..ድሮ እንደዚህ አልነበርክም››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹ከእኔ ጋር ለምትነጋገረው ነገር ስትጠነቀቅ አይቼህ አላውቅም ..እንደመጣልህ በነፃነት ነበር የምናወራው፡፡ትዝ ይልሀል ..አንተ እኮ ጓደኛዬ ብቻ አልነበርክም….አንድ ቤት ውስጥ አብረኸኝ ያደክ ወንድሜ ነህ፡፡››

‹‹አዎ..በልጆቼን በሞት ሳጣና አያቴም በቃኝ ብላ ገዳም ጥላኝ ስትገባ ..አንተም ልጄ ነህ ..ከልጄ ጋር አሳድግሀለው ብላ የወሰደችኝ እናትሽ እቴቴ ነች፡፡በእውነት ለእሷ በሚገባው መጠን አልተንከባከብኳትም…፡፡››

‹‹ተው ተው..እቴቴንማ በጣም ነው የተንከባከብካት፡፡.በየጊዜው ብር እንደምትልክላት ማላውቅ ይመስልሀል፡፡እዚህ ከተቀየርክ በኃላ  እንኳን እሷን ደጋግመህ አግኝተህ እኛን ግን ለማግኘት ፍቃደኛ አልነበርክም፡፡ካንተ ደግሞ ይልቅ ደግሞ የሚገርመኝ የእሷ ያንተ ተባባሪ ሆና መደበቅ፡፡ …እንደውም አንዳንዴ ከእቴቴ ጋር ስንጣላ እኮ…‹‹ከአንቺ ይልቅ የእኔን እናትነት የተረዳው አለማየሁ ነው…››እያለች ታበሳጨኛለች፡፡እና እሷ በአንተ ደስተኛ ነች…ትንሽ ቅር ሚላት በየጊዜው በአካል ሄደህ ስለማትጠይቃት ነው፡፡በዛ ከአንተ እኔ እሻላለሁ….፡፡››

‹‹ቢሆንልኝ…ለእሷ ምንም ነገር ባደርግ ይገባታል፡፡››

‹‹ለእኔስ…ለስድስት አመት የት እንዳለህ እንኳን ደውለህ አሳውቀሐኝ አታውቅም…አለማየሁ ደወሎ እንዲህ አለ…አለማየሁ ደውሎ በባንክ ይሄንን ላከ ሲባል እንጂ አንድ ቀን ሰሎሜ ሰላም ብሎሻል…?ሰሎሜ አለማየሁ ሰለአንቺ እንዲህ  ያስባል ብሎ የነገረኝ ሰው የለም..ሁል ጊዜ አእመሮዬን እንደበላኝ ነው…‹‹ምን አድርጌዋለው…?መቼ ቀን ነው ያስከፋሁት …?.የቱ ጋር ነው የተቀየመኝ? ብዬ እንደተከዝኩ ነበር..እወነቱን ለመናገር በጣም ተቀይሜህ ነበር ..ባገኝህ እንደማላናግርህ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር..ግን በእንደዛ አይነት ሁኔታ ስንገናኝ…ምንም ማድረግ አልቻልኩም...ተቀይሜህ እንደነበረ ራሱ ከእስር ተፈትቼ ቤቴ ከገባው በኃላ ነው ያስታወስኩት፡፡››

‹‹ጥሩ ነው፣ ቂመኛ አይደለሽም ማለት ነው…አንቺን ያላገኘሁሽ ግን ላላገኝሽ ስላልፈለኩ ሳይሆን ተገድጄ ነው››

‹‹ተገድጄ ስትል?››

‹‹ማለቴ….››ንግግሩን እንዳንጠለጠለ አላዛር ከእነሱ በበለጠ.. ልክ እንደእለቱ ሙሽራ ዝንጥ ብሎ ወደእነሱ ሲመጣ ስለተመለከተ ለንግግር የተከፈተ አፉን መልሶ ዘጋ፡፡

‹‹በሉ…እንሂድና …ቀደም ብለን እዛው አካባቢ ደርሰን ብንጠብቀው ይሻለል፡፡››

አለማየሁ አላዛር መጥቶ ማውራት ከማይፈልገው ነገር ስለገላገለው በመደሰት ‹‹ጥሩ …እንሂድ››አለና ከተቀመጠበት  ተነሳ፡፡ርምጃውን ከአላዛር አስተካክሎ ወደውጭ መራመድ ጀመረ.፡፡ሰሎሜ ከኃላ ሁለቱንም በትኩረት እያየች ተከተለቻቸው፡፡ሁለቱም ፈርጣማና ወንዳወንድ የሚባሉ ናቸው፡፡ግን አላዛር ወደላይ የተሳበ መለሎ ነው፡፡
//
ከ30 ደቂቃ ጥበቃ  በኋላ የተጠበቀው ሁሴን ግዙፍ ሻንጣውን በጋሪ እየገፋ ከተርሚናሉ ሲወጣ ሶስቱም በእኩል አዩት…በደስታና በጩኸት እንዲያያቸው እጃቸውን አውለበለቡለት…ሁሴን ከዛሬ ስድስት   አመት  በፊት እደሚያውቁት አይነት ነው፡፡ እንዳዛው ውልምጭምጭ ቀጫጫ…ባለትልቅ ጭንቅላትና ሉጫ ፀጉር…የህፃን የመሰለ ፍልቅልቅ ፊት…ነጭ ከሩቅ አይን የሚስብ  በረዶ መሳይ ጥርስ ……
ሶስቱም በየተራ እየተጠመጠሙበት ሰላምታ ከሰጡትና ይዘው የመጡትን የእንኳን በሰላም መጣህ ምኞታቸውን የሚገልፅ  አበባ አስታቀፉት፡፡ከዛ በኃላ አለማየሁና አላዘር ሻንጣውን ተቀብለው  ወደመኪናው ወሰዱና ከኋላ ጫኑለት፡፡…በአላዛር ሹፌርነት ሰሎሜ ገቢና ከእሱ ጎን ተቀምጣ አለማየሁና ሁሴን ከኋላ ሆነው ወደቤት ጉዞ ጀመሩ፡፡

ድንገት‹‹ይገርማል…?››አለ ሁሴን፡፡

አለማየሁ‹‹ምኑ ነው የገረመህ?ከተማዋ ልደቷን የምታከብር የቢሊዬነር ብቸኛ ልጅ መሰለችህ አይደል…?››አለው፡፡

‹‹ማለት?››

‹‹አሸብርቃና ተኳኩላ …በደማቅ መብራቷች ተንቆጥቁጣ ስታያት ገርሞህ እንደሆነ ብዬ ነዋ?››

‹‹..አዎ ያልከው ነገር በጣም አስገርሞኛል..ግን እኔ ለማውራት የፈለኩት ሶስታችሁን በአንድነት መጥታችሁ ትቀበሉኛላቹሁ የሚል ምንም አይነት ግምት ስላልነበረኝ በዛ መደነቄን ነው፡፡፡፡›

ልክ እንደሁሴን እሷም ሶስቱም የልጅነት እና የአፍላ ወጣትነት ጓደኞቾ እና አፍቃሪዎቾ ከበርካታ አመታት በኋላ እንዲህ አንድ ላይ ተሰብስበው አይናቸው እሷ ላይ ሲያቁለጨለጩ በመመለከቷ እየተገረመች‹‹ምን ማለት ነው? ሶስታችንም እኩል ጓደኞችህ አይደለንም እንዴ…?ለመሆኑ መጥቶ ይቀበለኛል ብለህ የገመትከው ማንን ነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ያው አሌክስን ነበር፡፡እናንተን በማግስቱ ባገኛችሁ ብዬ ነበር ያሰብኩት፡፡››

‹‹አንተ …ከእኛ ይልቅ አሌክስ ቁምነገረኛ የሆነው ከመቼ ወዲህ ነው…?ነው ሰው ሀገር ከሄድክ በኃላ ፀባያችን ተምታታብህ››አለችው ሰሎሜ በመገረም፡፡

አለማየው በፈገግታ‹‹አንቺ …ሰው ሁሉ ስለእኔ ልክ እንደአንቺ የተሳሳተ ግምት ያለው ይመስልሻል እንዴ?››አላት፡፡

‹‹ተው ተው…ከመሀከላችንማ አንደኛው ቁምነገረኛና ኃላፊነትን የሚወስደው አላዛር ነው…አንተ እንደውም በዚህ ጉዳይ  የመጨረሻው ሰው ነህ››አለው ሁሴን፡፡

‹‹አንተ ዲያስፖራ ለመሆኑ ዜግነትህን ቀይረሀል?››ሲል ጠየቀው፡፡
ያልጠበቀውን ጥያቄ ስለተጠየቀው ግራ ተጋባ‹‹አይ አልቀየርኩም…ግን ለምን ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ ኢትዬጵያዊ ዲያስፖራ ከሆንክ  የሚጮህልህ ኤምባሲ ስለሌለ ለዚህ ንግግርህ የሆነ ሰበብ ፈልጌ ከርቸሌ ልወረውርህ ነዋ….እንደድሮ አለማየሁ ብቻ አይደለሁም..ኩማንደር አለማየሁ ነኝ፡፡››
👍638👎2🔥1🥰1
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///

ዘሚካኤል እንግዳው ላይ አፍጥጦ

‹‹አይ ምንም እየገባኝ አይደለም….?››አለ

ሰውዬውም ዘሚካኤል‹‹ቁጭ በል አስረዳሀለው..››አለና ወደውስጥ ገብቶ ቀድሞ ተቀመጠ…

ፀደይ  ዘሚካኤልን እየጎተተች ይዛው መጣችና አስቀመጠችው…እሷም ተቀመጠችን ስልኳን አውጥታ ሪከርድ ላይ አደረገችና ሰውዬው የሚናገረውን ለመስማት ዝግጁ ሆነች፡፡

‹‹ምን ድረስ ታውቃላችሁ?››

‹‹እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም››ዘሚካኤል በትግስተ የለሽነት መለሰ፡፡

ፀደይ ዝም አለች‹‹ጥሩ ከመጀመሪያው ብጀምርላችሁ ችግር የለውም..እኔ እና እናትህ የልጅነት ጓደኛሞች ማለት ፍቅረኛሞች ነበርን…በጣም ነበር የምንዋደደው…..ምንጊዜም ስለመጋባትና ዕድሜ ዘመናችንን ሙሉ አብሮ ስለመኖር ነበር የምናስበው…ከዛ ድንገት አባቴ ወደአሜሪካ መሄድ አለብህ አለኝ…ብዙ ወንድሞቹ እዛ ስላሉ ሀሳቡን ላስቀይረው አልቻልኩም….አባቴን በጣም ነበር የምፈራው..ከዛ ጥያቄውን ተቀብዬ ወደአሜሪካ ሄድኩ…ለካ እሷ በወቅቱ እህትህን ፀንሳ ነበር..፡፡››

‹‹ፀንሳ ማለት …ከማን?››

‹‹ከማን ይሆናል ከእኔ ነዋ››

‹‹እና እህቴ የአንተ ልጅ ነች…?.ምንድነው የምትቀባጥረው?››

‹‹አልቀባጠርኩም..ከፈለክ አባትህን ጠይቀው …ያውቃል…እናትህ እኔ ጥያት ስለሄድኩ በጣም ተበሳጭታብኝ ስለነበር እና በዛ ላይ አርግዛ ስለነበር…ወዲያው አባትህን አገባችው…ስታገባው..ለልጇ አባት ለማግኘት አንጂ አፍቅራው አልነበረም…እሱም ይወዳት ስለነበረ ተንከባከባት….እህትህም በሰባት ወር እንደተወለደች ነበር ያሰበው…የገዛ ልጁ ነበር የምትመስለው….ስለዚህ ትርሲትን  እንደልጁ አሳደጋት..ከዛ አንተ እና ወንድምህ ተወለዳችሁ፡፡እኔም ከሀያ አመት ቆይታ በኃላ ከአሜሪካ ተመለስኩ፡፡ለእሷ የነበረኝ ፍቅር ከውስጤ ስላልበረደ ፈልጌ አገኘኋት…በጣም ተበሳጭታብኝ የነበረ ቢሆንም ታፈቅረኝ ስለነበረ በሂደት ይቅር አለቺኝ…አባትህን  ፈታ እኔን እንድተገባኝ እጨቀጭቃት ጀመር…እሷም ምንም እንኳን ከእኔ ጋር ለመጋባት በጣም ፍላጎት ቢኖራትም እናንተን መበተን ስላልፈለገች በሀሳቤ ልትስማማ አልቻለችም፡፡

እኔም እሷን ትቼ ሌላ ሴት ማግባት ብሞክርም አልቻልኩም..አቃተኝ…ከዛ በቃ አንቺ እሺ ብለሽ ባልሽን ፈተሸ ማታገቢኝ ከሆነ ቢያንስ ልጄን የማግኘት መብት አለኝ..ለልጄ አባቷ እኔ እንደሆንኩ ንገሪያት እያልኩ በዚህ መጨቃጨቅ ጀመርን፡፡እሷም ያንን ማድረግ አልችልም እያለች መከላከል ጀመረች፡፡በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን በድብቅ እየተገናኘን ፍቅራችንን እንወጣ ነበር…

‹‹ለምን ያህል ጊዜ ከአባቴ እየተደበቃችሁ ..እንደዛ አደረጋችሁ?››ግሽግሽ ባለና ጥላቻ በተጫነው ስሜት ጠየቀው፡፡

‹‹አራት ወይም አምስት አመት››መለሰለት

‹‹እና አባቴ ይሄን ሁሉ ታሪክ ሲያውቅ ነዋ ..ቀልቡን ነስቶት ያንን  ወንጀል የፈፀመው?››

‹‹አይ አይደለም…ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ እስከዛሬ ድረስ ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ  አዝናለው..እመነኝ በጉዳዩ በጣም መፀፀት ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገሬን አጥቼበታለው….፡፡ ስራዬን፤ ጤናዬን …ብዙ ብዙ ነገር…ብዙ ጊዜም ራሴን አጥፍቼ ከልጄ ትርሲት እና ከእናትህ ጎን ለመተኛት ሞክሬ ነበር..ግን በሆነ መንገድ እተርፋለው…መጨረሻ ይሄው እንደምታየኝ የአያቴ መንደር መጥቼ በዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ጀመርኩ..ትንሽም ወደእዚህ ከመጣሁ ነው ጤነኛ የሆንኩት››

‹‹ሰውዬ እኔ ያንተን ፀፀት ለመስማተ  ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም..ስለዋናው ጉዳይ ንገረኝ››

‹‹ትዝ ይለኛል ቀኑ እሁድ ነበር….በእለቱ አባትህ ሞጆ የጓደኛው ለቅሶ ስለነበረ መሄዱን እናትህ ስትነግረኝ..መኪናዬን ከአዲስአበባ አስነስቼ አዳማ ሄድኩ ፡፡እናትህን ተቀጣጥረን ስለነበር ቡቲክ አገኘኋት …እሁድ በዛ ላይ ጥዋት  ስለሆነ የገበያ ግር ግር አልነበረም.. ከዛ የተወሰነ ከቆየን በኃላ የተለመደ ጭቅጭቃችንን ጀመርን‹‹ …ለልጄ አባቷ መሆኔን ወይ ቀድመሽ ንገሪያት ወይ እነግራታለው››አልኳት፡፡

‹‹እሷ ቅጣውን በልዩ ሁኔታ ነው የምትወደው …አባትሽ ቅጣው አይደለም ብላት ልጄ በጣም ነው ምትጎዳው››አለቺኝ፡፡

‹‹ብትጎዳም ለጊዜው ነው…ከውሸት ጋር ለዘላለም ከምትኖር እውነቱን አውቃ ለትንሽ ጊዜ ብትጎዳ ይሻልል››አልኳት
በዚህ ጉዳይ ላይ ለ30 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በከረረ ሁኔታ ስንከራከር ቆየን….ከዛ የስልክ ንግግር ድምፅ ነው  ሁለታችንንም ያነቃን….

እህትህ ትርሲት ከባንኮኒው ማዶ … ፊቷ በእንባ ታጥቦ…አይኖቾ ፈጠውና  አውሬ መስላ ቆማለች..ሱቁ ውስጥ ገብታ እዛ የቆመችበት ቦታ መች እንደቆመች አናውቅም..ምን ያህሉን እንደሳማችንም አናውቅም….ከሁኔታዋ እንደሚታው ግን የሚበቃትን ያህል እንደሰማችን ያስታውቃል…ሁለታችንም በርግገን ጎን ለጎን ተጣብቀን ከተቀመጥንበት ተነሳን….

‹‹ለማን እየደወለች ነው?››ሁለታችንም ግራ ተጋባን፡፡ወዲያው ስልኩ ተነሳላትና ማውራት ጀመረች፡፡

‹‹አባዬ  ….ያንተ ልጅ አይደለሁም እንዴ…?እማዬና ውሽማዋ ሲያወሩ ሰማው…አባዬ እኔ ያንተ ልጅ ካልሆንኩ መኖር አልፈልግም…የሌላ ሰው ልጅ መሆን በጣም ነው የሚቀፈኝ…አይ አልጠብቅህም ..በጣም ነው የምወድህ….››አለችና ስልኩን ግድግዳው ላይ ወርውራ ከሱቁ ወጥታ ተፈተለከች፡፡ልንደረስባት ሞከርን ግን ወዲያው ተሰወረችብን፡፡

‹‹ወይኔ ልጄ….ወይኔ ልጄ…››እናትዬው ተርበተበተች....እኔም የምይዝው የምጨብጠው ግራ ገባኝ….ሱቁን ዘጋንና….

‹‹ወደየት ነው የሄደችው?››ስል እናትህን ጠየቅኳት፡፡‹‹እኔ ምናውቃለው..ወደቤት ከሄደች…ሄጄ ልያት››አለችኝ

‹‹በቃ ነይ መኪና ውስጥ ግቢ››ስላት

‹‹እንዴ ..አንድ ላይ ስንሄድ..?››

‹‹አሁን እኮ ነገሮች ተደበላልቀዋል…ምንፈራው ሳይሆን የምንጋፈጠው ነው››አልኳትና እየጎተትኩ መኪናዬ ውስጥ ይዣት ገባው፡፡በየመንገዱ እየፈለግናት…ልትሄድ ትችልበታለች ብላ እናቷ የጠረጠረችበት  አንድ ሁለት ቦታ አቁመን አይተን መጨረሻ ወደቤት ሄድን…መኪናውን ራቅ አድርጌ እንዳቆም አደረገችኝና…‹‹እኔ ገብቼ ልያትና ካለች እነግርሀለው..ከሌለችም ሌላ ቦታ ሄደን እንፈልጋታለን›› ብላኝ ገባች፡፡እኔም በጭንቀት እየተንቆራጠጥኩ መጠበቅ ጀመርኩ…5 ደቂቃ ..10 ደቂቃ አለፈ..ስልኬን አውጥቼ ስደውል እናትህ ሞባይል አይነሳም…ራሴን መቆጣጠር አቃተኝና የሆነው ይሁን ብዬ ወደግቢው ገባው፡፡ሳሎኑ በራፍ እንደተከፈተ ነበር…ስገባ  ልጄ ኮርኒሱ ላይ ተንጠልጥላለች..እናትህ ደግሞ የገዛ ሆዷን ላይ ቢላዋ ሽጣ ተዘርራለች፡፡ይመስለኛል እናትህ ወደቤት ስትገባ እህትህ ተሰቅላ እራሷ አጥፍታ ስታያት ወዲያው አካባቢው ላይ ያገኘችውን ቢላዋ ሆዷ ውሰጥ የሻጠችው ይመስለኛል፡፡

ከዛ ደንዝዤ የምሆነው ጠፋኝ…ምን ላድርግ ..?ልጄን ከተሰቀለችበት ለማውረድ ገመድ መቁረጫ ለመፈለግ ወደውስጥ ገብቼ መቁረጫ ይዤ ስመለስ አባትህ ከውጭ ከሳሎኑ ሲገባ አየሁት፡፡በደመነፍስ ወደ ጎሮ በራፍ ሄድኩ…ዞሬ ከግቢው ወጣሁና መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ደም እንባ እያለቀስኩ ሁኔታዎችን መከታተል ጀምርኩ፡፡ ከዛ አንተና ወንድምህ አንድ አይነት ሰማያዊ የስፖርት ልብስ ለብሳችሁ ወደቤት ስትገቡ ተመለከትኩ፡፡ ከደቂቃዎች በኃላ ፖሊሶች ሰፈሩን ወረሩት…እናንተንም አባታችሁንም ፖሊሶች ይዘዋችሁ ሲሄድ የእናትህንና የእህትህን አስከሬን በአንብላንስ ሲወሰድ ከመንገድ ማዶ መኪናዬ ውስጥ ተቀምጬ እየተመለከትኩ ነበር፡፡ ሁለቱም እራሷቸውን  እንዳጠፉ እርግጠኛ ነኝ፡፡
👍6519
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡

የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አዲስ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ አንተስ?››

‹‹እኔ በጣም ደህና ነኝ…ሚካኤል ይደውልልኛል ብዬ እየጠበቅኩ ነበር፡፡››

‹‹ይደውልልሀል..አሁን ኩማንደሩ ቀጥሮት ሊያገኘው ሄዶል …ከእሱ እንደጨረሰ እርግጠኛ ነኝ ይደውልልሀል፡፡…አታስብ ኩማንደሩ ደግሞ ያንተ አድናቂ ስለሆነ ከአባታችሁ እንድትገናኙ ሁኔታውን ያመቻቻል….በዛ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው

‹‹ጥሩ ታዲያ አንቺ ሰላም ነሽ?››

‹‹በጣም ሰላም ነኝ…ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ  ነበር››

‹‹ምን?››

‹‹ከፀዲ ጋር እንዴት ናችሁ?››

ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኋላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡

ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››

‹‹ግልፅ ሆነህ ንገረኝ…ስለእሷ ምን ታስባለህ..ማለቴ አሁንም በፊት እንደነገርከኝ ታፈቅራታለህ?››

‹‹እንዴ!እንዴት በአንድ ወር ፍቅሩ ይተናል ብለሽ አሰብሽ? እንደውም ጥሩ ነገር አነሳሽልኝ…የሆነ ቀን አመቻችቼ ካንቺ ጋር መነጋገር እፈልግ ነበር..እኔ ላገባት እፍልጋለው..በቅርብ ቀን..እና እንዴት ጠይቄ ላሳምናት የሚለውን ከእኔ ይልቅ አንቺ ስለምታውቂ እንድታማክሪኝ እፈልጋለው፡፡››

‹‹እንግዲያው እንደዛ ከሆነ ሳይረፍድብህ ፍጠን››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ያንተን ልጅ አርግዛለች..››

የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…

‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››

‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡

በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል  ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ  ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል  ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኋላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››

‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በበቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡

የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ  መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡

ፀአዳ ቤት ሲደርስ በራፏ ዝግ ነበር..ሊደውልላት አልፈለገም ፡፡ሻንጣውን አወረደና በራፏ በረንዳ ላይ አድርጎ እሱ መኪናው ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ጀመረ…ከምሽቱ አንድ ሰአት ስትመጣ እሱ መኪና ውስጥ ሻንጣው በረንዳ ላይ ሆኖ ስታየው ፍፁም ነው ግራ የተጋባችው…ምስር  እሱ መሆኑን ስታውቅ ከእናቷ ተነጥላ ወደእሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ፈጥኖ ከመኪናው ወረደና እጇቹን እንደክንፍ ዘርግቶ ጠበቃት…ተጠምጥማበት በደስታ ጉንጩን ትስመው ጀመር…
ወደቤት እንደገቡ ፀደይ‹‹ምንድነው ጉዱ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምንም ..ለጥቂት ሳምንታት እረፍት ስለሆንኩ እዚህ ከእናንተ ጋር ለመቆየት ወስኜ ነው፡፡››

‹‹እዚህ ከእኛ ጋር?››

‹‹አዎ ከእናንተ ጋር››
ህፃኖ ምስር ‹‹ታድለን…ታድለን›› እያለች መጨፈር ጀመረች፡፡

ፀአዳ ልጇ ምስር ፊት ምንም ማለት አልቻለችም.‹‹እንግዲያው እደቤትህ ዘና በል…እኔ ልብስ ልቀይር ››አለችና መኝታ ቤት ገባች፡፡ከዛ እራት ሰርታ በሉና ከሶስት ሰዓት በኃላ ምስርን አስተኝተው ነበር እንደአዲስ ጭቅጭቁን የጀመሩት፡፡

‹‹ምን እየሰራህ ነው?››

‹‹እንደምታገቢኝ ቃል ገብተሸ ቀለበት እስክታስሪልኝ ድረስ ከዚህ ቤት ወጥቼ ወደቤቴ አልመለስም››ሲል ቁርጡን ፍርጥም ብሎ ነገራት፡

‹‹ጭራሽ ማግባት? እየቀለድክ ነው፡፡››

‹‹በፍፅም …ብቀልድ ነው እንደዚህ አይነት እርምጃ የወሰድኩት፡፡››

‹‹ስማ..እኔ ካንተ ጋብቻ ፍቅር ምናምን አልፈልግም››

‹‹ታዲያ ምንድንው ምትፈልጊው?››

ትኩር ብላ አየችው….
‹‹ንገሪኝ ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው….. ?››

‹‹ካንተ ወሲብ ብቻ ይበቃኛል….ማለቴ እስከአሁን የደረግነውን ለማለት ነው …ደግሞ  አሁንም እናድረግ እያልኩህ አይደለም፡፡››

በንግግሯ ሆድን እስኪያመው ሳቀ…በመሀል ስልክ ተደወለለት ..ከወንድሙ ነበር…በጉጉት አነሳው‹‹እሺ ሚካኤል ደህና አመሸህ?››

‹‹ሰላም ነኝ…ነገ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ አዳማ መገኘት ትችላለህ?››

‹‹ምነው ?አባዬን እንድናገኝ ፈቀዱልን እንዴ?››

‹‹አዎ በጣም ደስ የሚለው ደግሞ አንድ ላይ እንድናገኘው ነው ያመቻቹልን ቅር ካላለህ አዲስንና ቅዱስንም ይዘናቸው እንሄዳለን››

‹‹አረ ቅር አይለኝም ጥሩ ሀሳብ …ግን አባዬ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ የሚሆን ይመስልሀል?››ሰሞኑን ሲብሰለሰልበት የነበረውን ስጋቱን አንስቶ ጠየቀው፡፡

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከመሞቱ በፊት ማግኘት የሚፈልገው ብቸኛ ነገር እኮ አንተን ማናገር ነው…በደስታ  ነው የሚያነባው….እንኳን በአካል አግኝተሀው አባዬ ብለህ ስጠራው ሰምቶ ይቅርና ባለፈው ፎቶህን ሳሳየው እንዴት እያገላበጠ ሲስምና ሲያለቅስ እንደነበረ እኔ ነኝ የማውቀው…በል በዛ እርግጠኛ ሁን..ምንም አትጨናነቅ፡፡››

‹‹ምን ያስፈልገዋል…?ማለት ምን ይዤለት ልሂድ?››

‹‹የሚያስፈልገወን ነገር ሁሉ አዘጋጅተናል…አንተ ደግሞ ሚፈልገውን ነገር እንጠይቀውና በሚቀጥለው ዙር ትወስድለታለህ…ደግሞ ደስ የሚለው ከቦንጋ ያመጣችሁትን ከዶ/ሩ ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ለኩማንደሩ አሰምቼው በጣም ነው ያዘነው..እናም አባዬን ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር ወስነዋል…››

‹‹በጣም የሚያስደስት ነገር ነው እየነገርከኝ ያለሀው..ወንድሜ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንክ ታውቃለህ አይደል… በጣም ነው የምኮራብህ፡፡››

ሚካኤልም እንባ እየተናነቀው‹‹እኔም በጣም ነው የምኮራብህ››አለው

‹‹በቃ እሺ …...ሶስት ሰዓት ነው ያልከኝ አይደል?፡፡››

‹‹አዎ…መድረስ ትችላለህ አይደል…?››

‹‹በደንብ እንጂ ሁለት ተኩል ደርሼ ደውልልሀለው››

‹‹ጥሩ በቃ ደህና እደር››ስልኩን ዘጋ፡፡

ንግግራቸውን ሁሉ በገረሜታ ስትሰማ የነበረችው ፀደይ‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ሁለት ተኩል ትደርሳለህ?››ስትል በፈገግታ አሾፈችበት፡፡

‹‹ትቆጪኛለሽ ብዬ ነው እንጂ እዚህ ነኝ ልለው ነበረ››

‹‹ልፋ ቢልህ ነው ….ግን ለእናንተ ደስ ብሎኛል››

‹‹ማለት?››

‹‹አንተና ወንድምህ እንዲህ እየተደዋወላችሁ በሰላም ማውራት መቻላችሁ ትልቅ ነገር ነው…አረ እንደውም ከመነጋጋርም አልፋችሁ መሞጋገስ ጀምራችኃል››

‹‹እድሜ ለአንቺ ….ባንቺ ቀናነትና ጥረት ነው ለዚህ የበቃነው….››

‹‹እኔን ማሞገሱን እንኳን ለሌላ ጊዜ አቆየው..በነገራችን ላይ የአባትህ ጉዳይ ላይ  ይግባኝ ለመጠየቅ ሚቻል ከአሆነ አንድ ጎበዝ ጠበቃ አግኝኝቼ ሁኔታውን አስረድቼው ነበር….››

‹‹በእውነት ..ታዲያ ምን አለሽ?››
👍6824👎1👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

//
ራሄል የእናቷ የቀዘቀዙ  እጆቿን ይዛ በሆስፒታሉ የእንግዳ መቀበያ   ክፍል ውስጥ ባለው የሶፋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣለች። ቄሱ  በአጠገባቸው ተቀምጦ፣ መዝሙር 46ን ሲያነብ አቶ ቸርነት ከመግቢያው በራፍ ጋር ቆመው በትካዜ ጎብጠው ይታያሉ፡፡


‹‹ እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው፥ ስለዚህ ምድር ብትናወጥ ተራሮቸም ወደምድር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም፡፡
።››ራሄል ቃላቷ በተዳከመ እና በዛለ አእምሮዋ ላይ እንዲያርፍ እየሞከረች ነው፡፡

"ቸርነት  ከእኛ ጋር ትቀላቀላለህ?" ቄሱ ጠየቁ።

አቶ ቸርነት  እንደመባነን አሉና  ጭንቅላታቸውን በአውንታ በመነቅነው ወደእነሱ ተንቀሳቀሱ…ከራሔል አጠገብ ተቀመጡ።ቄሱ የአቶ  ቸርነትን እና የወ.ሮ ትርሀስን  እጅ ያዙ፣ ቸርነት ደግሞ የራሄልንን፣ ራሄል የእናቷን  ያዘች፣ ክቡኑ  ዘጉት ።ቄስ   መጸለይ ጀመሩ። እሱ ፈቃዱ ከሆነ ፀጋን እንዲወስድ ሲጸልይ፣ ራሄል ተቃውሞዋን በጮኸች አሰማች።ግን የእናቷ እና የአባቷ እጆች እጆቿን ሲጨምቋት የተከፈተ አፏን መልሳ ዘጋች፡፡ እግዚያብሄር የሚፈልገው ያንን ከሆነ ፀጋን  መልቀቅ እንዳለባት አወቀች፣ሲጨርሱ፣ ወደ ቄሱ   ቀና ብላ ተመለከተች።

‹‹ አመሰግናለሁ…እዚህ መገኘትዎ በጣም አስፈላጊ ነበር.››አለች፡፡

ቄሱ ፈገግ አሉላት እና‹‹እኛ ቤተሰብ ነን ራሄል ..እርስ በርሳችን እንረዳዳለን።››

‹‹አውቃለሁ እናም ለዚህም አመሰግናለሁ.››

ከሶፋው ተነሳች፣ ድንገት እረፍት ማጣት ተሰማት።እህቷን ማየትም ፈልጋለች። ነገር ግን ኤሊያስና  እና ነርሶቹ ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች አያስፈልጋቸውም። የአይሲዩ ተከፋች በሮች መስኮቱን እየተመለከተች በሩ አጠገብ ቆመች። ከእነሱ ቀጥሎ አንድ  ነርስ በችኮላ ጋሪ እየገፋች ወደ ፀጋ ክፍል ስትሮጥ ተመለከተች፣ እና ልቧ ወርዶ  የጎድን አጥንቷ ውስጥ የተሰነቀረ መሰላት፡፡ …

‹‹ምን እየሆነ ነው?ጌታ ሆይ እባክህ እሷን ከእኛ ጋር አቆይ… እባክህ…ትንሽ እንንከባከባት። ›› ፀሎቷን ሳታቆርጥ   ወደበሩ ቀረበች ።አንገቷን አስግጋ እና አይኖቾን አጨንቁራ በመስኮቱ ወደውስጥ ለማየት ሞከረች..ነገሮች ጥሩ እየሄዱ እንዳልሆነ ያስታውቃል..ሁሉም ከወዲህ ወዳያ ይሯረሯጣሉ….ሚስኪኗን ፀጋን ከበዋታል…

‹‹ቢ.ፒ. እየወረደ ነው›› አለ ‹‹ፈሳሽ ቦልስ ስጧት.›› ሌላ ማሽን ጠፋ።ሌላ ነርስ ‹‹የኦክስጅን መጠን እየቀነሰ ነው›› .ከማሽነቹ የሚወጣው ሲጥሲጥታ ይሰቀጥጣል….ሁሉም ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እንደሆነ ነው የሚያወራው…ራሄል በምታየውና በምትሰማው ነገር እራሷን መቆጣጠር አቅቷት ጩኃቷን ስትለቀው በኮሪደሩ አካባቢው የነበሩ ሰዎች  ሁሉ ትኩረት ወደእሷ ዞረ…ሁኔታውን የተረዳች አንድ ነርስ ፈጠን ብላ መጣችና የመስታወቱን መጋረጃ ከውስጥ በመሳብ ዘጋችው፡፡

…በሁሉም ፊት ላይ  ድንጋጤ እና ተስፋ መቁረጥ ነው የሚነበበው…ከኤልያስ በስተቀር ሌሎች ያከተመ ነገር አድርገው በመውሰድ እጃቸውን ሰብስበዋል…እሱ  ወደጆሮዋ ጎንበስ አለና ‹‹የእኔ ቆንጆ መልአክ …ከእኛ ጋር ቆይ። ራሄል ትፈልግሻለች። ሁላችንም እንፈልጋግሻለን።››አላት..እሱ ሊደርግ ሲገባው ያላደረገው ምንም ነገር ስለሌለ  ..አምላክ ጥንካሬ እንዲሰጠው  ጸለየ፣ ጥበብ ለማግኘት ጸለየ እና ይህች ትንሽ ልጅ እንድትቆይ እንዲፈቀድላት ተማጸነ።ከዛም ወደፀጋ ተመለሰና  በደመነፍስ ሚችለውን ነገር ሁሉ መሞከር ጀመረ…ከ10ደቂቃ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ትግል በኃላ መቆጣጠሪያ ማሽኖቹ ድንገት የምስራች ማሰማት ጀመሩ….ሁሉም ማመን አልቻሉም…

አንድ ነርስ ‹‹ቢ.ፒ. እየወጣ ነው›› አለች.፣ኤሊያስ ቀና ብሎ ማሽኑን   ተመለከተ፣ ትንሽም ቢሆን ምላሽ የመስጠት ምልክት ማሳየቷ የተስፋ ጭላንጭል በልቡ ፈነጠቀ፡፡

በመቀጠልም ‹‹ የኦክስጅን መጠን እየጨመረ ነው››አለች ነርሷ ።

ሁሉም በደስታ ተሳሳቁ…ፀጋ  አምልጣ እንደነበር ሁሉም ባለሞያዎች ተቀብለው ነበር…ተአምሩን በደስታ በመተቃቀፍ ተቀበሉት… እናም እሷን ቀስ በቀስ  ለማረጋጋት አስፈላጊውን ሁሉ አደረጉ፡፡ዔሊያስ የተረጋጋች መሆኗን በደንብ እስኪያረጋግጥ ጥቂት ጊዜ ቆየ። ከዚያም ለራሔልና ወላጆቿ ሊነግራቸው ወጣ።

ፍፅም በድካም ዝሎ እና መላ ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ ነበር…የዛሬው ህክምና በእሱ እውቀት ሳይሆን  በአምላክ ጥበብ  ነው የተሳካው።ምን ተጠቅሞ ምን አድርጎ ከሞት ወደህይወት እንደመለሳት የሪፖርት መዝገቡ ላይ አስታውሶ መፃፍ አይችልም….ብቻ  በመጨረሻ ተቆጣጣሪው እግዚአብሔር  ነበር።ለእሱ ብሎ ሳይሆን ያቺን ሚስኪን ልጅ ተጨማሪ ጊዜ በምድር እንድትኖር ስለፈለገና ለእሷ ሚሆን እቅድ ስላለው ነው..አዎ እንደዛ ነው የገባው፡፡ በኮሪደሩ ላይ ወደ ቤተሰቧ ሲሄድ እያሰበ የነበረው ይሄን ነበር  ፡፡

ራሔል ሲመጣ አይታ ወደእሱ ተንደረደረች… እሱም ወደ እሷ ሮጠ፣

‹‹ደህና ትሆናለች?››

‹‹ጌታ ይመስገን..አስቸጋሪውን ጊዜ አልፈነዋል››

ራሄል ተነፈሰች። ተጠምጥማ አቀፈችው…ከዚያም እንባ አፈሰሰች።ከዛ እህቷን እንድታያት ወደውስጥ ይዞት ገባ ፡፡

የፀጋ  አልጋ ጋር ቆማ ቁልቁል በስስት እያየቻት‹‹ጥሩ ትመስላለች››ስትል በሹክሹክታ ተናገረች። ወላጆቿ ከአንድ ሰአት በፊት ነበር ፀጋ እየተዳከመች ስትሄድ ሞቷን ቁጭ ብለው ላለማየት ወደቤተክርስቲያን ለመፀለይ ተያይዘው የሄዱት፡፡

ራሄል ጸጋ ከኮማዋ እስክትነቃ ድረስ ከአልጋዋ ጎን መነጠል እንደማትፈልግ ተናገረችው..እሱ ግን እንደዛ ማድረግ እንዳማትችልና ለ5 ደቂቃ አይኗን አይታ እንድትረጋጋ ብቻ አስቦ እንደፈቀደላት በትህትና አስረዳት፡፡

ኤሊያስ ከ ጀርባ ቆሞ እጆቹን ትከሻዋ ላይ አደረገ እና ‹‹አሁን ደህና ትሆናለች..አታስቢ ››አለ

‹‹አመሰግናለሁ…አንተ ድንቅ ዶክተር ነህ.››አለችው

‹‹እኔ ዶክተር ብቻ ነኝ…የዳነችው በተአምር ነው›› አለ.

ራሔል ከዔሊ አጠገብ ተነስታ ወደ እኅቷ ቀረበችና  ጎንበስ ብላ ጭንቅላቷን  በስሱ ሳመቻት  ።‹‹ጥሩ እንቅልፍ ተኚ  የእኔ ውድ ››አለች።  ከዚያም ወደ ዔሊ ዞረች።

‹‹እዚህ መቆየት አይቻልም ካልክ… አሁን ለመሄድ ዝግጁ ነኝ.››አለችው…ራሄልን አልፎ ሄዶ የፀጋን  ጉንጭ  በአንድ ጣቱ ነካ።

‹‹ጌታሆይ አመሰግናለሁ››ብሎ በሹክሹክታ አመሰገነ። ከዚያም  አብረው ከክፍሉ ወጡ በኮሪደሩ ላይ ወደ አሳንሰሮች ሄዱ። ሲከፈት ተያይዘው ገቡ፡፡   ድክምክም ብሏታል…ደረቱ ላይ ደገፍ አለችበት፡፡

እጆቹን በደረቷ ዘርግቶ አቀፋትና  ወደታች  ተመለከታት እና ቀስ ብሎ ወደታች ጎንበስ በማለት  ከንፈሯን ሳመ።‹‹ሁሉንም የታካሚዎችህን  ዘመዶች  እንደዚህ ነው የምትስመው?›› ብላ በፈገግታ ጠየቀችው።

‹‹በጣም የሚያስጨንቁኝን እና የምወዳቸውን ብቻ ነው የምስመው››

ራሄል የሚንቀጠቀጡ ጣቶቿን አነሳችና  ጉንጯ  ነካች፣ እይታዋ አሁንም በሱ ተጋርዷል።

‹‹እና እነዚያ ስንት ናቸው?››

‹‹አንድ ብቻ›› አገጮን ቀና አድርጎ  በድጋሜ   ሳማት።መልሳ ሳመችው፡፡

‹‹እወድሀለው  ዶ/ር ኤሊ ። ››

‹‹መቼም ቢሆን እነዚህን ጣፋጭ ቃላት ከአንደበትሽ ታወጪያለሽ ብዬ አስቤ አልውቅም ነበር››በማለት ፈገግ አለና እንደገና ሳማት… እና እንደገና።
56👍8
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

//
ራሄል በወላጆቿ ቤት ከመዋኛ ገንዳ አጠገብ ከእናትና አባቷ ጋር ተቀምጣ የጥዋት ፀሀይ እየሞቀች ነው፡፡

ፀጋ   ‹‹ አበባ ስጪኝ?››ስትል እህቷን ጠየቀች፡፡

ራሄል ከተቀመጠችበት ተነሳችና   የፀሐይ መነፅሯን ወደ ጭንቅላቷ ገፋ በማድረግ   እህቷ የፈለገችውን  አበባ ቀነጠሰችና በትናንሽ እጆቾ ውስጥ አስቀመጠችላት…ፀጋ በደስታ ፈነጠዘች፡፡
ሮቤል እና አዲሷ ረዳት የፋውንዴሽኑን ስራ ከአሰበችው በላይ  በጥሩ ብቃት እየመሩላት እንደሆነ ለሁለት ቀን ወደቢሮ ተመልሳ ባደረገችው የስራ ግምገማ መረዳት ችላለች፡፡
…እህቷን ለማስታመም በሆስፒታል ባሳለፈቻቸው አስር ቀናት ውስጥ ምንም የጎደለ እና ሳይሰራ የተወዘፈ ስራ አልነበረም…እና አሁንም ለሌላ አንድ ሰምንት ታናሽ እህቷ በደንብ እስክታገግም አብራት እንድትሆንና ቀለል ያሉ  ስራዎችን እዛው እቤት ሆና እንድትሰራ ፈቅደውላት እሷም ተስማምታ  ወላጇቾ ቤት ነው ያለችው፡፡

‹‹ኤሊ እመጣለሁ ያለው መቼ ነው?››ወ.ሮ ትርሀስ  መጽሃፏቸውን  ከጎኗቸው  ባለ የመስታወት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ራሄልን  ጠየቋት።

‹‹ከሶስት እስከ  አራት ሰዓት እመጣለሁ ነበር ያለው ፡፡ ››መለሰች…ጸጋ  ራሷ ቀጥፋ የሰጠቻትን አበባ  ፀጉሯ መካከል ሻጠችላት…ራሄል  በፈገግታ እህቷን ወደራሷ ሳበችና ጉንጮን በመሳም‹‹ትንሿ እህቴ ..እንዲህ ስላሳመርሺኝ አመሰግናለው››አለቻት፡፡
በዛው ቅፅበት ወደግዙፉ ግቢ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ተሰማ ፡፡

‹‹የምትጠብቂው ጓደኛሽ  አለ እንዴ?››አቶ ቸርነት ጠየቁ፡፡

‹‹ አይ አይመስለኝም?››ራሄል እርግጠኛ ባለመሆን ጠየቀች፡፡

‹‹እንግዲያው አለም መጥታ ማንነቱን እስክታሳውቀን እንጠብቅ  ?››በማለት እናቷ ሳቁ።

አለም ወዲያው እየተፍለቀለቀች መጣች…‹‹ራሄል  ነይ እንግዳሽን ተቀበይ››

‹‹ማን ነው?››

‹‹አትንገሪያት ተብያለው…እራስሽ መጥተሸ እይው››አለችና ወደኪችኗ ተመለሰች፡፡

ራሄል.‹‹ማነው በወላጆቼ ቤት ከእኔ ጋር እንዲህ አይነት ጫወታ ለመጫወት የደፈረው?››በማለት ተነስታ ፀጋን ይዛ   ሄደች።ራሄል እና ፀጋ  ወደ ግቢው የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ሲሄዴ ኤሊ ወደ ውስጥ ሲገባ ተመለከቱት  ።ራሄል እንዳየችው  በውስጧ የደስታ ማዕበል አጥለቀለቃት።

ባለመኪና ስትጠብቅ ባለሞተር ሰው በማየቷ ተደንቃ ‹‹ሄይ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ? የሞተር ሳይክልህን ድምፅ አልሰማሁም።››አለችው…

ዔሊ ጎንበስ ብሎ በቀስታ ሳማት እና ፀጋን አንስቶ ካቀፋት በኃላ‹‹ሌላ አይነት  የመጓጓዣ ዘዴ ነው የተጠቀምኩት.››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ሞተርህ ተበላሸች እንዴ ?›› አለችና አይኖቾን ወደመኪና ማቆሚያ አዞረች  ከእሷ   ቀይ መኪና  አጠገብ የቆመ ባለ ሰማያዊ ቀለም  መኪና እያየች ግራ ተገባች።

‹‹ ያን መኪና  ከማን ነው የተዋሰከው? ወንድምህ እንደዚህ አይነት መኪና የለውም።››

ዔሊ ተነፈሰ። ‹‹እነሆ፣ ወ.ሮ ራሄል  ሞተሬን ሸጥኩት።››

ራሄል መኪናዋን በድጋሜ  ተመለከተች፣ ‹‹ሞተር ሳይክልህን አስወገድከው !አየህ እኔ ስለ አንተ የምወደው ያን  ነው ። ቆንጆ እና ፈጣን ተማሪ ነህ….ግን ለምን?››

…‹‹ደህና፣ በአንድ ወቅት አንድ ሰው እንዴት አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ለዛውም የህፃናት ሀኪም የሆነ ሰው ሞተር ሳይክል ይነዳል ? የሚል  ጥያቄ ጠየቀኝ። እና ለእሱ መልስ ለመስጠት ብዬ ነው መኪና የገዛሁት፡፡››

ራሄል ወደ መኪናው ሄዳ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ  ትንሽ ነካችው፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለሰች፣ ››

‹‹አስደንቀኸኛል ››አለችው

‹‹ስለሞተር ሳይክሎች ያለሽን ስሜት ስለማውቅ  እናም የፍራቻሽም ምክንያት በከፊል ትክክል መሆኑን ስላመንኩበት  ነው...››

እዛው የሳሎኑ በረንዳ ላይ ካሉ ወንበሮች አንዱን እንዲቀመጥ ሳበችለት ፀጋን በክንዱ እንዳቀፈ ተቀመጠ….ከጎኑ ሌላ ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡

ከዛ ሳታስበውና ምንም ሳትዘጋጅበት ትልቅ  ቁም ነገር ከአንደበቱ አፈትልኮ ወጣ  ‹‹ይህን ሁሉ  በትክክለኛው መንገድ ይፋ   ማድረግ ፈልጌ ነው …ራሄል፣ ላገባሽ እፈልጋለሁ።››አላት፡፡

ጆሮዎቾን ማመን አልቻለችም…ልቧን  ደረቷን ሰንጥቆ እንዳይወጣ የፈራች ይመስል ደግፋ ያዘችው ። በውስጧ የሚንተከተከው ደስታ እና ፍቅር እና ምስጋና መውጫ ለማግኘት እየሞከሩ በአንደበቷ ላይ ተንገዋለሉ….ማልቀስ ብቻ ነው የቻለችው፡፡

‹‹ሄይ እኔ ያን ያህል መጥፎ ነገር አልተናገርኩም….ለምን ታለቅሻለሽ?››

‹‹በጣም ደስ ብሎኝ ነው…..››ስትል በለሆሳሳ መለሰችለት፡፡‹‹እወድሀለሁ ኤሊ›› ወደ እሱ ተሳበችና ጉንጩን ሳመችው..ታፋው  ላይ የተቀመጠችው ፀጋ  በደስታ እጆቿን እያጨበጨበች በሳቅ ተንከተከተች። የእሷ ሳቅና ደስታ ወደ እነሱም ተጋባ፡፡

‹‹መጀመሪያ ዝም ብዬ ለአንቺ ምንም ሳልነገርሽ ወደቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ለመላክ አቅጄነበር …››

‹‹እንዴ የእኔን ሀሳብ ሳታውቅ ሽማግሌ ልከህ እምቢ ብልህስ?››

‹‹ያው ምን አደርጋለው የተሰበረ ልቤን  ይዤ  የብቸኝነት ኑሮዬን ቀጥላለዋ !!››ብሎ ትከሻውን ነቀነቀ።ራሄል ጣቷን ከንፈሩ ላይ አድርጋ ሳቀች።

‹‹ ስለነርከኝ ደስ ብሎኛል፣ደግሞ ስትነግረኝ  ፀጋ በመሀከላችን መገኘት በመቻሏ  ደስታዋ ድርብ  ሆኗል … ለነገሩ እኛን አንድ ያደረገች እሷ ነበረች.››

‹‹እሺ ስላልሽኝ ደስ ብሎኛል…:በዚህ ምክንያት በህይወቴ ለሆነው ነገር እግዚአብሔርን በየቀኑ አመሰግነዋለሁ:: በአንቺ ምክንያት ህይወቴ መሉ ሆኗል››

‹‹አንተ ስጦታዬ ነህ ኤሊ ›› አለችና አቀፈችው።

‹‹አሁን እናትና አባትሽን እንፈልግ።››

ተስማሙና …ተያይዘው በአረንጓዴ ተክሎች ወደተሸፈነው ግዙፉ ጊቢ  ተያይዘው እየተሳሰቁ ሄዱ፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
96👍18
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////
ዶ/ር ኤልያስ ዛሬ ምን አልባትም በህይወቱ ፍፁም የሆነ ደስታ የተሰደሰተበት ቀን ስለሆነ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቷት ጥንቅቅ ብሎ ባለቀ ውብ ቤቱ ውስጥ ከክፍል ክፍል እየተመላለሰ  እንደህፃን እየቧረቀ ነው፡፡ስልኩን አነሳና ደወለ…፡፡ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡

‹‹ውድ ባለቤቴ እንዴት አለሽልኝ››

‹‹አንተ ያንን ቃል መጠቀም የምትችለው እኮ ሰማንያ ፈርመህ ቤትህ ስታስገባኝ ነው››አለችው እየሳቀች፡፡፡

‹‹ያው በይው..ዜናውን አልሰማሽም እንዴ…..?ሽማግሌዎቼ እኮ ወላጆችሽ ልጃቸውን ሊሰጡኝ በደስታ መስማማታቸውን አሁን ነግረውኝ በደስታ እያበድኩ ነው፡፡››

‹‹ከአንተ ቀድሜ ሰማሁ…ምነው ይከለክሉኛል ብለህ አስበህ ነበር እንዴ?››

‹‹እንዴ ምን ይታወቃል…..ምን አልባት ቅድሞ እደጅ እየጠና ያለ  ብረት መዝጊያ አማች ኖሮ ሀሳባቸው ወደእሱ ቢያጋድልስ?››

‹‹እሱስ እውነትህን ነው …ለአሁኑ ግን ተርፈሀል››

‹‹እኔም መትረፍ የምፈልገው ለአሁኑ  ብቻ ነው…የማገባው አንዴ ብቻ እኮ ነው…››ተሳሳቁ፡፡

‹‹እና ይሄንን ደስታ አብረን ማክበር የለብንም ትያለሽ…?››

‹‹አንተ ..ከአሁን ወዲህ እኮ እስከሰርጌ ቀን ድረስ ልታየኝ አይገባም…››

‹‹እንደዛ ከሆነማ ሰርጉን ነገውኑ ደግስ በይኛ››

‹‹አዎ ..ያን ያህል ከቸኮልክ አድርገው››
‹‹እሺ..አስበብበታለው..እውነት ግን በጣም ላገኝሽ ፈልጌለሁ…››

እሷም ከአንደበቷ አውጥታ አትናረው እንጂ በጣም ልታገኘው ፈልጋለች፡፡‹‹ ይቻላል..የትና መቼ?፡፡››

‹‹ምሳ ልጋብዝሽ …ሰባት ሰዓት ስካይ ላይት እንገናኝ፡፡››

‹‹ሰባት ሰዓት ..አሁን እኮ አራት ተኩል ሆኖል…..ለመዘጋጃጀት በቂ ጊዜ አይኖረኝም፡፡››

‹‹አንቺ ደግሞ..እንደውም ምንም መዘገጃጀት አያስፈልግሽም… እዛ ሆስፒታል በነበርሽበት ጊዜ ያለምንም ዝግጅት ምን እንደምትመስዬ እኮ አውቃለው…ለእኔ ብለሽ ለመቆነጃጀት ከሁለት ሰዓት በላይ ማጥፋት የለብሽም…ከዛሬ ወዲህ ባልሽ ነኝ፡፡ማለቴ ለጊዜው እጮኛሽ ነኝ..ግን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡››

‹‹‹ይሁንልህ እሺ…..ግን  ቅር ካላለህ አንድነገር ልጠይቅህ ››

‹‹ምን ጠይቂኝ››

‹‹ጸጋን ይዣት ብመጣ ቅር ይልሀል?››

‹‹አረ በፍፅም   ..እንደውም በተቃራኒው ደስ ነው የሚለኝ …እሷ ከመጀመሪያው ጀምሮ የፍቅራችን ብቸኛ ምስክር ነበረች..ዛሬ መገኘት ይገባታል….ጫጉላ ቀናችን ላይ አብራን ወደመኝታ ትግባ እንዳትይ እንጂ ለዛሬው ደስ ይለኛል››

ስለጫጉላ ሲያወራ እፍረትም ሙቀትም ተሰማት‹‹አንተ ምን እያልክ ነው..?በል ቸው››ብላ ስልኩን ዘጋች፡፡

እሱም ወዲያው ወደሻወር ቤት ገባና ሰውነቱን በፍጥነት ተለቃለቀ…ከዛ ፂሙን ላጨ…ሙሉ ሱፍ ለበሰና ዝንጥ አለ…፡፡ለመውጣት ዝግጁ ሆነ…፡፡ሰዓቱን ሲያይ 5 .ከሩብ ይላል….ከራሄልና ከፀጋ ጋር ወደሚገናኝበት  ቀጠሮ ከመሄዱ በፊት ማግኘት የሚገባው አንድ ሰው አለ…ከአመት በፊት በሆስፒታል አብራው ትሰራ የነበረች የህጻናት ሀኪም ነች ትናንትና ደውላ ላገኝህ እፍልጋለው ያለችው፡፡ለዚህች ዶ/ር የስራ ባለደረባው ነበር…ያለፈውን አንድ አመት ተጨማሪ ትምህርት እድል አግኝታ ኖሩዌይ ነበር ያሳለፈችው፡፡አሁንም ለሁለት ሰምንት ረፍት እንደመጣች እና መመለሻዋ እንደደረሰ እናም ከመሄዶ በፊት አንድ እቃ ልትሰጠው እንደምትፈልግ ነግራው ነው እግረመንገዱን ሊያገኛት የወሰነው፡፡

ሀያ ሁለት ነበር ቀጠሮቸው…እሷም ቸኩላ ስነበረ ቀጥታ ወደጉዳዩ ነበር የገባችው፡፡አንድ የታጠፈ ነጭ ፖስታ አውጥታ እጁ ላይ አደረገች፡፡ግራ ገብቶትም ደንግጦም‹‹ምንድነው ሲል?››ጠየቃት፡፡

‹‹ትዝ ይልሀል ከመሄዴ በፊት አብረን የምንከታተላት አንድ ታማሚ ልጅ ነበረች…እናቷ ከአንተ ጋር ትግባባለች…እንደውም የልጅነት ጓደኛዬ ነበረች ብለሀኛል››

‹‹ኦኬ ትክክል ነሽ..ስለፀጋ ነው…ማለቴ የዛን ጊዜ ስሟ ትሁት ነበር..ስለእሷ ነው የምታወሪው››

‹‹አዎ ስለእሷ ነው…ለመሆኑ እንዴት ነች…?አሁንም በህይወት አለች?››

‹‹አዎ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ነች…ግን ፖስታው ምን እንደሆነ አልገባኝም››

‹‹ፖስታውማ እናትዬው እዛ ሆስፒታል ውስጥ ህጻኗን ጥላ ከመሄዶ በፊት ይህንን ፖስታ ለአንተ እንድሰጥ አደራ ብላ ሰጥታኝ ..ነበር….እርግጥ በወቅቱ ልጇን ጥላ እንደምትሄድ አልገመትኩም እና እሺ ብዬ ተቀበልኮት….ግን በዛው ሰሞን አንተም ለሆነ ስራ ወደክፍለሀገር ወጥተህ ነበር..እኔም  ውጭ ለመሄድ በጣም እየተዋከብኩ ስለነበረ  እቤቴ ወስጄ እንደቀልድ እንዳስቀመጥኩት እረሳሁት እና ሳልሰጥህ ሄድኩ ..በቀደም ነው የድሮ ወረቀቶቼን ሳስተካክል ድንገት አገኘሁት..አድራሻውን ሳነብ ትዝ አለኝ….መጀመሪያ አፍሬ እንደተረሳ ልተወው ነበር›..በኃላ ሳስበው ግን ምን አልባት በጣም አስፈላጊ ነገር ቢሆንስ ብዬ…አይኔን በጨው አጥቤ አግኝቼ ልሰጥህ ወሰንኩ….ይቅርታ እሺ››

‹‹አረ ችግር ለውም…ያው ልጄን አደራ..ተከታተላት ምናምን የሚል መልዕክት ነው የሚሆነው….ያንን ደግሞ እሷ ባትለኝም አደርገዋለው››በማለት ፖስታውን ኪሱ ውስጥ ከተተና  ከእሷ ተሰናብቶ  መኪናው ወደ እስካይ ላይት አዞረ፡፡

ከቀጠሯቸው 10 ደቂቃ ቀድሞ ነበር የደረሰው፡፡ ወንበር ይዞ በጉጉት ይጠብቃቸው ጀመር..፡፡ድንገት ፖስታው ትዝ አለው፡፡ አወጣና አየው…፡፡ከጀርባው  ለማከበርህ ደ/ር ኤልያስ ከፅጌረዳ ይላል፡፡
እነ ራሄል እስኪመጡ ቀዶ ሊያነበው ፈለገ…መቅደድ ከመጀመሩ በፊት ፖስታውን ጠራጴዛው ላይ አስቀምጦ  ስልኩን ከኪሱ አወጣና ተመለከተው…ራሄል ነች፡፡አነሳው፡፡

‹‹እሺ የእኔ ፍቅር››

‹‹ቀድመንህ ደርሰናል መሰለኝ››

‹‹አረ እንዴት ተደርጎ…››አለና ያለበትን ቦታ ነገራቸውና እስኪያዩት ቆሞ ጠበቃቸው…. ራሄልን ሲያያት ልቡ ትርክክ አለ….ወደፊት ተራምዶ  ፀጋን ከእቅፏ ተቀበለና..ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ…. ወደ ጠረጴዛቸው ሄደው ተቀመጡ….ምሳ ታዘዘ እና እስኪመጣ ሞቅ ያለጫወታ ጀመሩ…..ራሄል ድንገት ፊት ለፊቷ የተቀመጠ ፖስታ አየችና በመገረም አነሳችና አየችው…፡፡

‹‹ፅጌረዳ ማን ነች?››ኮስተርተር አለች፡፡

‹‹ቀናሽ እንዴ?››

‹‹በኢንተርኔት ዘመን ፖስታ በምትልክልህ ሴት እንዴት ብዬ ነው የምቀናው?››

‹‹በፖስታው አድራሻ ላይ የተጠቀሰችው ፅጌረዳ ማለት የፀጋ እናት እንደሆነችና ፖስታው ከተፃፈ ከአመት በኃላ እንዴት እንዳገኘው… በእንግሊዘኛ ነገራት››ይሄንን  ያደረገው ፀጋ ፊት ስለእናቷ በምትሰማው ቋንቋ ለማውራት ስላልደፈረ ነው፡፡

‹‹እና..አልተከፈተም እኮ››

‹‹አዎ…አሁን ስለፀጋ እኔን ብቻ ሳይሆን አንቺንም ስለሚመለከት አብረን እናነበዋለን››

‹‹እርግጠኛ ነህ?››

‹‹ አዎ እርግጠኛ ነኝ››

‹‹እና እናንብበዋ››ብላ ልትቀደው ስትዘጋጅ፡፡

‹‹አይ …ይሄንን ጊዜያችንማ ለሌላ ጉዳይ አንጠቀምበትም…››ብሎ ፖስታውን ከእጇ ተቀበለና ከጎኗ ካለው ወንበር ላይ የተቀመጠው የራሷ ቦርሳ ውስጥ ከተተው፡፡

‹‹በቃ አንቺ ጋር ይሁንና ..ሰሞኑን አንድ ላይ ሆነን እናነበዋለን፡፡››ተስማማች…ምሳ ቀረበላቸው በሉ…ከዛ ወጥተው ወደአለም ሲኒማ ጎራ አሉና ፊልም አዩ….አሪፍና ጣፋጭ ቀን አሳለፉ….
53👍3👏1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////

አለም የቢሮውን በራፍ አንኳኳች… የኩማንደሩን ‹ይግቡ› የሚል ሻካራ ቃል እስክትሰማ ድረስ ጠበቀች እና ወደውስጥ ገባች፡፡

"እንደምን አደርክ። ልታገኘኝ ስለፈቀድክ  አመሰግናለሁ።››በማለት ከጠረጴዛው ፊት ለፊት ባለው ወንበር ላይ ተቀመጠች ፡፡
ሳይጠይቃት አንድ ኩባያ ቡና ቀዳላትና ከፊት ለፊቷ አስቀመጠ።ስለቡናው አመሰገነችው። ተሸከርካሪ ወንበሩ ላይ ተቀመጦ፡

"ስለ አያትሽ አዝናለሁ ..አለም" አላት፡፡

"አመሰግናለሁ።"አለች፡፡

አለም የአያቷን የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈፅምና ተያያዝ ጉዳዬችን መስመር ለማስያዝ ለአንድ ሳምንት አዲስአበባ ቆይታ ከመጣች ገና ሁለተኛ ቀኗ ነው ። በቀብሩ ላይ ጥቂት የድሮ ጓደኞቾ እና ከመቅዶኒያ የመጡ አያቷን በቅርበት የሚያውቁ ጥቂት ሰዎች ነበር የተገኙት፡፡… ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በኋላ አለም ወደአረጋዊ ማእከሉ ሄዳ የአያቷን እቃዎች መሰብሰብ ነበረባት…አብዛኛውን እቃዎች እዛው ለሚስፈልጋቸው ሰዎች በመስጠት ነበር ያስወገደችው፡፡
ከዛ ጥልቅ የሆነ ትካዜ ውስጥ ገባችው፡፡ ዳግመኛ ወደ ሻሸመኔ ከተማ መሄድ ይኑርባት ወይም እዛው አዲስአባ ትቅር ግራ ገብቷት ነበር፡፡አሁን አያቷ ሞተዋል….‹‹የእናትሽ ጋዳይ ነሽ››ብሎ እጣቱን የሚጠቁምባት ሰው የለም….ታዲያ ምን አሰቃያታል?፡፡በኋላ ግን ስታስበው እንደዛ ብታደርግ ፈፅሞ የመንፈስ እረፍት እንደማታገኝ ገባት …እንደውም ከበፊቱ በበለጠ እራሷን አጠንክራ ወደሻሸመኔ መመለስ እንዳለባት ወሰነች፡፡ ከህግ አንፃር፣ አሁንም ጉዳዩ በጣም ደካማ ነው…በዛም ምክንያት ፍርድ ቤት መቆም አልቻለችም። ከመካከላቸው የትኛው ለእናቷ ግድያ ተጠያቂ መሆን አለመሆኗቸውን ማወቅ አለባት። በዚህም ምክንያት ወደሻሸመኔ ተመልሳ መጣች።

ከደቂቃዎች ዝምታ በኃላ"እንደምትመለሺ እርግጠኛ አልነበርኩም" ብሎ በግልፅ ነገራት።

‹‹ተስፋ አልቆርጥም አልኩህ እኮ።››

‹‹ አዎ አስታውሳለሁ" አለ በብስጭት፡

"አዲስአበባ ከመሄድሽ በፊት የነጋዴዎች ማህበር አመታዊ ክብረ በአል ላይ ያሳለፍሽው ምሽት እንዴት ነበር?"በማለት ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቃት፡

በመገረም "እዛ ዝግጅት ላይ መሄዴን እንዴት አወቅክ?" ስትል ጠየቀችው፡፡ ዝም አላት፡፡

" ጁኒየር ነው የነገረህ?"

‹‹አይ።"

‹‹እና››

‹‹ምክትሌ በዛን ቀን ማታ …በአውራ ጎዳናው ላይ ከሱ ጋር በመኪናው ውስጥ አይቶሻል።ከፍጥነት በላይ ይነዳ ስለነበረ ቀልቡን ስቦት ነበር››

‹‹አዎ ነበርኩ…. ጁኒዬር ጋብዞኝ ሄጄ ነበር››

‹‹እንዴት ነው ጥሩ ጊዜ አሳለፍሽ?››

"ቆይ ስርጉት የጁኒየር ሚስት እንደነበረች ማንም ያልነገረኝ ለምንድን ነው?"

" አልጠየቅሽም።ደግሞስ ስላልተሳካ የድሮ ትዳር ማወቅ ለአንቺ ምን ይፈይድልሻል ?"

‹‹ሙሽራይቱ የዳኛው ልጅ ሆና መገኘቷ እንግዳ ነገር አይመስልህም? ።" "ይህ በፍፁም እንግዳ ነገር አይደለም."
"የአጋጣሚ ጉዳይ ነው እያልከኝ ነው?."

"አይ አይደለም:: ስርጉት ለመጀመሪያ ጊዜ ጂኒዬርን ካየችበት ቀን ጀምሮ በፍቅር ወይም በፍትወት ውስጥ ነበረች። ሁሉም ያንን ያውቅ ነበር። እሷም ምንም አይነት በደል በማንም ላይ አልፈፀመችም። ሰሎሜ ስትሞት. እድሏን ተጠቀመችበት።››

‹‹እንደዛ ነው የምታስበው››
"በግልፅ…ጁኒየር እንዲወዳት ማድረግ አልቻለችም።ምክንያቱም በየሄደበት እየተንሸራተተ የሚከፈተውን የሱን የሱሪ ዚፕ መዝጋት ለማንም ሴት ቢሆን የሚከብድ ፈታኝ ስራ ነበር።››

"ገመዶ፣ ጥድፊያው ምን ነበር? ጁኒየር ከስርጉት ጋር ፍቅር አልያዘውም ነበር። ታዲያ ለምን ተጋቡ?ነው ወይስ የቤተሰብ ግፊት ነበረባቸው?"

‹‹እነሱኑ ብትጠይቂያቸው አይሻልም?›› ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደ መስኮቱ አመራች፡፡

‹‹ያው አንተም ቤተሰብ ነህ ብዬ እኮ ነው ››

‹‹አዎ…ቤተሰቦቼ ናቸው..ሁል ጊዜ አብረውኝ ነበሩ …››

ወደ እሱ ዞር አለች፣ እሱ ግን ምንም እያያት አልነበረም። ‹‹አባቴ ሲሞት ከመላው የሻሸመኔ ኑዋሪ ለቀብር ሥነ ሥርዓቱ የመጡት አቶ ፍሰሀ እና ጁኒየር ብቻ ነበሩ ። ከቀብር በኃላ አቶ ፍሰሀ  ወደ ሥራ ተመለሰ። ጁኒየር ደግሞ ወደ ትምህርት ቤት ኄደ። እኔ ወደ ቤት ሄድኩ።ብዙም ሳይቆይ ሰሎሜ ወደ ቤቴ መጣች። ትምህርቷን አቋርጣ ነበር የመጣችው። አባቴን በህይወት እያለ ብጠላውም በመሞቱ ግን ብቸኝነት እንደሚሰማኝ ታውቅ ነበር። አልጋዬ ላይ አብረን ተኛን እና እስኪመሽ ድረስ እዚያ ቆየን። ወደ ቤቷ የሄደችው እናቷ እንደምትጨነቅ ስለሰጋች ነበር። ››
ንግግሩን ሲያቆም በክፍሉ ውስጥ ስሜታዊ ፀጥታ ሰፈነ። አለም ምንም እንቅስቃሴ ሳታደርግ በታሪኩ ተመስጣ .. በመስኮቱ አጠገብ ቆማ ነበር። በብቸኝነት የነበረውን ያንን ሚስኪን ወጣት አሰበችና ደረቷ ላይ ህመም ተሰማት።

"ከእናቴ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር የያዘህ በዛን ቀን ነበር?"ስትል ጠየቀችው፡፡

በቀጥታ ወደእሷ ተመለከተ… እና ከወንበሩን ለቆ ወደ እሷ ቀረበ። "የፍቅር ጉዳይ ካነሳሽ… ያንቺ እንዴት ነው?"

‹‹የእኔ ምን?››በንዴት ጠየቀችው

"ከጂኒዬር ጋር…..?ማለቴ….››ሆነ ብሎ ንግግሩን አንጠልጥሎ ተወው

"አንተ ባለጌ ነህ"አለችው

"እንደሞከረ እርግጠኛ ነኝ። እሱ ሁልጊዜም ይሞክራል።››ሲል አከለበት፡፡

"ገሃነም ግባ።"

በእሷን በጁኒዬር መሀከል ስላለው ሁኔታ ለማወቅ ለምን አጥብቆ ፈለገ ?‹‹… አሁን ፊቱ ላይ የሚነበብበት ስሜት ምንድነው ?ምናልባትም ንቀት፣ ወይስ ቅናት….››አሰላሰለች፡፡

"ለምንድነው  ክረምት እናቴ ወደኮፈሌ ስትሄድ የፈቀድክላት…ወደዛ ባትሄድ ኖሮ ከአባቴ ጋር አትገናኝም ነበር….ከአንተ ጋር የነበራችሁ ፍቅርም እክል አያጋጥመውም ነበር››
"ምናልባት  የመልክአ  ምድር  ለውጥ  አስፈልጎት  ይሆናል….ወይንም  ደግሞ  ዘመዶቾ ስለናፈቋት…" ሲል በቁጭት ተናግሯል።

‹‹የቅርብ ጓደኛህ ምን ያህል ይወዳት እንደነበረ ታውቃለህ አይደል?።››
"በትምህርት ቤት ያሉ ሁሉም ወንዶች እናትሽን ያፈቅሯት እንደነበረ አውቃለው እና ደግሞ የከበርቴው ልጅ ከሆነው ጁኒዬር ጋር ስለ ፍቅር ጉዳይ አላወራም ነበር››.

"ጁኒየር እሷ ላይ ባለው ፍቅር ምን እንደተሰማው ታውቃለህ?"

‹‹ነገርኩሽ እኩ…ስለፍቅር ከእሱ ጋር አውርተን አናውቅም››

"እሷን ለማግኘት ምንም ነገር ቢሞክር ትገድለው እንደነበረ ነው የነገረኝ:: የእውነት ሁለቱም ቢከዱህ ትገድላቸው ነበር ?"

"እርግጠኛ ነኝ እንደዛ ያለሽ ንግግሩን ለማሳመር ፈልጎ ነው."አላት፡፡

"ጁኒየርም መልሼ ስጠይቀው የተናገረው ይህንኑ ነው፣ ግን አይመስለኝም" አለች
"ብዙ የሚቀሰቅሱ ስሜቶች ነበሩ። እርስ በርስ ያላችሁ ግንኙነት ተደራራቢ እና ውስብስብ ነው።"

"የምን ግንኙነቶች?"

"አንተ እና እናቴ ትዋደዳላችሁ፣ነገር ግን ሁለታችሁም ጁኒየርን ትወዱታላችሁ።››

"ምንድን ነው የምታወሪው? ከጁኒየር ጋር ፣አልወዳደርም."

"ምናልባት እያወቅክ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን ሌሎች ሰዎች እርስ በእርሳችሁ ያወዳድራችኋል። እና ከመካከላችሁ የትኛው ነው ሁልጊዜ ወደላይ የሚወጣው? አንተ። ያ ያስጨንቅሀል?። ››
"ይሄ የአንቺ የስነ ልቦናህ ጫወታ ነው"

"የእኔ አስተያየት ብቻ አይደለም። ስርጉት በቀደም ይሄንኑ ነገር ነግራኛለች፡፡። ሰዎች ሁል ጊዜ ሁለታችሁን እንደሚያነፃፅሩና ጁኒየር ሁል ጊዜ በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ነግራኛለች።"
42👍6
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

ገመዶ እኩለ ለሊት ላይ ስልኩ ጮኸ….

"ምንድን ነው ነገሩ" በማለት እየተነጫነጨ በተኛበት እጁን ዘረጋና ስልኩን ከኮመዲኖ ላይ አንስቶ ጆሮው ላይ ለጠፈና ‹‹ሄሎ››አለ፡፡

‹‹ኮማንደር መስማት አለብህ ብዬ ነው…ድንገተኛ ነገር ተከስቷል."ምክትሉ ነበር፡፡ ከመኝታው ተነሳና አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡

"…ምንድነው የተፈጠረው?"

"ከእርባታ. ቦታው …ማለቴ የቤተሰቦችህ እርባታ ቦታ፣ከዛ ነው የተደወለልን"አለው…

ከአልጋው ወርዶ ጂንስ ሱሪውን መልበስ ጀምሮ ነበር፡፡ጭንቅላቱ የፍርሀት ቅዝቃዜ ሲፈስ ታወቀው፡፡

"ምን አይነት ድንገተኛ አደጋ ነው?"
‹‹ገና አልተረጋገጠም..ኃይል ወደእዛው ልከናል፡፡›› ያልተቆለፈ ሸሚዙን ከቆለፈ በኋላ ቆሞ ጫማውን አደረገ፡፡

‹‹በቃ ቶሎ አጣርተህ ደውልልኝ…ወደእዛው እሄዳለው፣ይሄው እየወጣሁ ነው… ››ስልኩን ዘጋና ኮቱንና ኮፍያውን አድርጎ ወደ ኮሪደሩ ሮጠ።
/////

አለም በከባድ እንቅልፍ ውስጥ ነበረች፣ ለዚህም ነው የበሯን መንኳኳት በህልሟ መስሎ የተሰማት…።ህልም ውስጥ ነበረች….በመጨረሻ ተከታታይ የሆነው የጥሪ ድምፅ ከእንቅልፏ ቀስቅሷት።

"ተነሺ እና በሩን ክፈቺ."በቁጣ እየጮኸባት ነው፣ ቁጭ አለችና አልጋው ዳር ያለውን መብራት አበራችው… መብራቱ ሲበራ …. ብርሃኑ ዓይኗን አጭበረበራት።

"ገመዶ ነኝ… ክፈቺ?" ጮኸ ። ዝም አለችው፡፡

"በአስር ሰከንድ ውስጥ ካልተነሳህሽ በሩን ሰብረዋለው››

የግድግዳውን ሰዓት ተመለከተች። ከምሽቱ ስምንት ሰዓት ገደማ ነበር።

‹‹ኩማንደሩ ወይ ሰክሯል ወይም አብዷል።››ስትል አሰበች፡፡ ያም ሆነ ይህ አሁን ባለበት ሁኔታ በሯን ልትከፍትለት አልፈለገችም።

"ምን ፈለክ?"

ከእሱ መልስ ስትጠብቅ በራፉ ላይ ፈንጅ የተጣለበት ይመስል ጎጎጎጎ አለና ተከፈተ….ተንደረደረና መኝታ ቤቷ ገባ፡፡በድንጋጤ እየተንቀጠቀጠች አልጋዋ ላይ ቆመች "ምን እየሰራህ ነው?"ብላ ጮኸችበት በቆመችበት አልጋ ልብሱን እየሰበሰበች እርቃኗን ለመሸፈን እየጣረች ነው››

"አንቺን ለማግኘት ነው የመጣሁ ‹‹
ከአልጋው ላይ ጎተተና ወለሉ ላይ አቆማት፣የተጠቀለለችበትን አልጋ ልብስ ከላዬ ላይ ገፎ ወረወረው፣እርቃኗን በፓንት ብቻ ፊት ለፊቱ ቆመች፣ምን ሊያደርጋት እንደሆነ መገመት ሁሉ አልቻለችም፡፡

"ኩማንደር በሬን ገንጥለህ መኝታ ቤቴ ለመግባትህ በቂ ምክንያት እንዳለህ ተስፋ አደርጋለሁ።"

"ማብራሪያ አለኝ።" አለና መሳቢያውን ከፈተ እና ውስጡ ያሉትን ልብሶች ማተረማመስ ጀመረ።

"ንገረኝ ምን እየፈለክ ነው?."አለችና እርቃኗን ወደእሱ ሄዳ ሚያተራምሰውን  የቁምሳጥን በራፍ በዳሌዋ ገፋችና ዘጋችበት ፡፡

"ምን ፈልገህ ነው?"ዳግመኛ ጠየቀችው፡፡
"ልብስ። እንደዚህ እርቃንሽን  መውጣት ካልመረጥሽ በስተቀር  ምትለብሺው ልብስ ያስፈልግሻል››

‹‹ወደየትም አልሄድም››

" ጂንስሽ የት ነው ያለው?›› በ ወፍራም ድምፁ ጠየቀ ። "የትም አልሄድም። ስንት ሰዓት እንደሆነ ታውቃለህ?››

ድንገት ቀና ሲል ከአልጋው አጠገብ ባለው ግድግዳ ልብሷ ተሰቅሎ አየው፡፡ ጂንሱን ከተሰቀለበት ላይ አወረደና ወረወረላት፣ መያዝ ስላልቻለች ወደ ወለሉ ወደቀ።
ከጫማዋቾ ውስጥ አንዱን መረጠና ወደእግሯቾ አቀረበላት፡፡ ዝም ብላ ፈዛ ታየው ጀመር፡፡ "እሺ.. እንዳለብስሽ ትፈልጊያለሽ?"

እሱን ለማስቆጣት ምን እንዳደረገች መገመት አልቻለችም። እርቃኗን እሱ ፊት ቆማ መከራከሩ ስለደከማት ጆንሱን አነሳችና አጠለቀች ፡፡ከላይ ሹራብ ለበሰች….ከኮመዲኖ መሳቢያ ውስጥ አንድ ካልሲ አወጣችና አራግፋ አጠለቀችና ጫማዋን አደረገች፡፡ በመጨረሻም ዞር ብላ አየችው።

"እሺ ይሄው ልብስ ለብሻለሁ …አሁን ምን እየተካሄደ እንደሆነ ንገረኝ ?"

"እየሄድን  እነግርሻለው  ››አለና  እጆቿን  በመያዝ  እየጎተተ  ይዞት  ወጣ  ፡፡በንዴት እየተንቀጠቀጠች ነበር።

‹‹እንዲህ እንድታደርገኝ ማን ነው የፈቀደልህ?››

"አንገትሽን መስበር አለብኝ…..አላደረገውም››በማለት ወደእሷ ተጠጋና ከንፈሯን ሳማት።ያለተቃውሞ ተሳመችለት፡፡ምላሱን ወደ አፏ ውስጥ አስገባ። በዚህ ጊዜ በቁጣ ስሜት መነጨቀችውና እራሷን አላቀቀች፡፡

ኮትዋን ከሳሎን በራፍ አካባቢ ካለው ማንጠልጠያ አነሳችና ያዘች፡፡ ከቤት ይዞት ወጣ " በሩስ?"ብላ ጠየቀችው ።
"የሚጠግን ሰው እልካለሁ።"

"በዚህ ለሊት?"

"በፈጣሪ … በሩን እርሺው..በአካባቢው ቤትሽን በንቃት የሚጠብቁ ፖሊሶች አሉ" ብሎ ጮኸ።

‹‹የሚጠብቁ ነው ሚሰልሉኝ?››

እጇን ጨምድዶ እንደያዛት ስትጠብቀው ወደነበረ ታክሲ ውስጥ ይዞት ገባ፡፡

"በፈጣሪ ገመዶ…ምን እየተፈጠረ ነው……?ነው ወይስ እያሰርከኝ ነው?››

‹‹እያሰርከኝ ..አንቺን……?ምነው ወንጀል ሰርተሸል እንዴ?›› ፡፡

‹‹እና ምንድነው ንገረኛ….?ወደየት እንደምሄድና ለምን እንደምሄድ የማወቅ መብት አለኝ›› ።

"የእርባታ ቦታው እየተቃጠለ ነው."

‹‹የእርባታ ቦታው.?.የነጁኒዬር?››

‹‹አዎ››

‹‹ወይ..ፈረሶችህ ተረፉ?››

ፈረሶቹን ምን ያህል ይወዳቸውና በምን ያህል መጠን ይንከባከባቸው እንደነበረ ስለምታውቅ ነው ቀድማ ስለፈረሶቹ የጠየቀችው፡፡

‹‹አላውቅም…የወደመውንና የተረፈውን ስንደርስ ነው የምናውቀው፡፡››
////
ሲደርሱ እሳቱ ከፈረሶቹ ጋጣ አካባቢ እየተንቀለቀለ ነው…በአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሚገኘው የእንጨት ፋብሪካው ከአደጋ ውጭ ነው፡፡ቢሆንም በንፋስ ታግዞ ወይም በሆነ ምክንያት እሳቱ እዛ ቢደርስ ከፍተኛ ውድመት እንደሚያስከትል የታወቀ ነው፡፡

እንደደረሱ መኪናዋ ስትቆም ኩማንደሩ ከመኪናው ወረደና ወደእሳቱ አቅጣጫ ተንቀሳቀሰ…አለም ከኋላው ተከተለችው፡፡ከአንዱ የፈረስ ጋጣ ጭስ ሲትጎለጎል ይታያል…አለም ሆዷ ተገለባበጠባት። የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች፣ የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው እሳቱን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነበር።ብዛት ያላቸው የእርባታው ሰራተኞችና የአካባቢው ኑዋሪዎች ቅጠለም አፈርም እየተጠቀሙ እሳቱ እንዳይዛመት ለመቆጣጠር እየተረባረቡ ነው፡፡
አንድ ሰው ወደኩማንደሩ ቀርቦ"በጣም ብዙ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ደርሰውበታል" ሲል ነገረው፡፡

‹‹ሰውስ አልተጎዳም?››

‹‹አንድ የተጎዳ ሰው አለ…››የሚል ድምፅ ሰማ፡፡

"ማንው የተጎድቷል?"

‹‹በጣም አሰቃቂ ትዕይንት ነበር።ከፈረስ ተንከባካቢዎች አንዱ ነው… በቂ አየር ወደ ሳምባዋ መሳብ አልቻለችም። ፈረሶችን ለማዳን ሲሯሯት አንድ እግሩም ተሰብሯል››

በዛ ቅፅበት አንድ ፈረስ እየጮኸ ነበር፣ በግልጽ ህመም ላይ እንዳለ ያስታውቃል። አለም እስካሁን ሰምታ የማያውቀው እጅግ አሳቃቂ ድምፅ ነበር የሰማችው። ገመዶ በፍጥነት ወደእዛው አመራ…ከኃላው ተከተለችው….የአቶ ፍሰሀ ቤተሰቦች በጠቅላላ በለሊት ቢጃማቸው በአካባቢው ነበሩ ፡፡መኖሪያ ቤታቸው ከእርባታው ድርጅት ብዙም ሰላማይርቅ እንደሰሙ በእግራቸው ነው ሮጠው ወዲያው ነው የደረሱት፡፡ ሳራ እያለቀሰች ነበር። ፍሰሀ

እራሱን ተቆጣጥሮ በፅናት ቆሞ ይታያል…ጁኒዬር እናቱን አቅፎ ያፅናናል፡፡ ገመዶ ወደ ጎን ገፋቸው እና እሳቱ ጠፍቶ ጭሱ ብቻ ከሚታይበት ጋጣ ውስጥ ገባ ፡፡
48👍4🔥1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////

ከኪሊንኩ ጀርባ ያለው የዶ/ር ኤሊያስ  ቢሮ ምናልባት አለም ከዚህ በፊት ካየቻቸው ቢሮዎች ሁሉ የተዝረከረከ ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡

"ዶክተር ኤሊያስ እኔን ለማየት ስለተስማማህ አመሰግናለሁ።"

"ችግር የለም …ዛሬ ብዙም ስራ አልነበረኝም " ከቀጥታ ከጠረጴዛው አጠገብ ያለውን የእንጨት ወንበር ላይ ያሉትን መጽሔቶችን አስነሳና ጠረጴዛ ላይ በማድረግ ለአለም እንድትቀመጥበት አመቻቸላት፡፡

"አንቺን ሳይሽ ብዙም አልተገረምኩም

"አላት በቅንነት ።

"ለምን?"

"ዋና አቃቢ ህጉ ደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎችን ልትጠይቂኝ እንደምትፈልጊ ነግሮኝ ነበር።"

"ዛሬ ከከተማ ውጭ ያለ መስሎኝ ነበር."

"አይ ከቀናት በፊት ነበር ሰሞኑን ትመጣለች ቡሎ የነገረኝ ።"

"ገባኝ…ለሊት የእሳት ቃጠሎ ቦታው እንስሳቶችን ለመርዳት ስትሯሯጥ ስለነበርክ…ዛሬ እንዲህ ንቁ ሆነህ ቢሮህ አገኝሀለው ብዬ አላሰብኩም ነበር።"

በመደነቅ‹‹እንዴ እዛ እንደነበርኩ በምን አወቅሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹እኔም እንዳጋጣሚ እዛ ነበርኩ…አሁን ጊዜህን ሳልሻማብህ ቀጥታ ወደጉዳዬ ልግባ …የእናቴ የሰሎሜን ግድያን በተመለከተ መረጃዎችን እየሰበሰብኩ ነው….እባክህ አንተ በአቶ ፍሰሀ የእንስሳት እርባታ ድርጅት ውስጥ የእንስሳት ሀኪም ሆነህ እንደመስራትህ የምታውቀው ነገር ይኖር ይሆን ?" ስትል አሳዛኝ በሆነ የድምፅ ቅላፄ ጠየቀችው፡፡

"በእርግጥ እናትሽን አውቃታለው . እሷ በጣም አስደማሚ ሴት ነበረች. በእሷ ሞት ያላዘነ ሰው የለም ››

"አመሰግናለሁ፣ በዛን ወቅት በአቶ ፍሰሀ የእርባታ ድርጅት ውስጥ የእንስሳቱን ጤንነት ሚከታተሉት አባትህ እንደነበሩ ማወቅ ችያለው፡፡ "

" ልክ ነው …በዛን ወቅት አባቴ ነበር….እሱ ከሞተ በኋላ ግን ስራውን እኔ ተረክቤያለሁ." "አባትህ ስለ ሰሎሜ ግድያ ሁኔታ የሆነ ነገር ነግሮህ ይሆን?››

"በቀዶ ጥገና ቢላዋ መገደሏን በሰማ ጊዜ እንደ ሕፃን ነበር ተንሰቅስቆ ያለቀሰው››

"አባትህ እናቴ የተገደለለችበት መሳሪያ ከየት እንደመጣ አውቋል›?›

"አዎ …ያ አባቴ እንስሳቱን ለማከም የሚጠቀምበት መሳሪያ ነበር፣እናቴ ነበረች የሸለመችው የስሙ የመጀመሪያ ፊደል ተቀርፆበት ነበር ፡፡እንዴት አድርጎ ከቦርሳው እንደወደቀበት ነው ግራ የገባው፡፡››

"እንደዛ አይነት ግድ የለሽነት ከእሱ ባህሪ ጋር አይሄድም አይደል?"

"ትክክል ነሽ….አባዬ ለህክምና እቃዎቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያደርግ አይነት ሰው ነው
…በቆዳ በተለበጠ የእንጨት ሣጥን ውስጥ ነበር የሚያስቀምጣቸው…ያ ስለት ከሳጥኑ እንዴት እንደወደቀ ፈጽሞ ማወቅ አልቻለም ነበር, ››

"እናቴ በሞተችበት ቀን አንተ እዚያ ነበርክ?"

"ይህን ቀድመሽ ታውቂያለሽ ብዬ አስባለሁ። አባዬን ለመርዳት ትምህርት ከሌለኝ በስተቀር እዛ እገኝ ነበር …በዛም ቀን  አብሬው ሄጄ ነበር።››

"ገመዶ እዚያ ነበር?"

"በእርግጥ ኩማንደር እዚያም ነበረ።››

"ለሊቱን ሙሉ."

‹‹እሱን እርግጠኛ አይደለሁም…በመሀል አቋርጦ የሄደ ይመስለኛል››

"አባትህ የህክምና ቁሳቁስ የሚይዝበትን ሳጥን የሆነ ቦታ አስቀምጦ ዞር ብሎ ያውቃል?" ኤሊያስ ማሰላሰል ጀመረ … መልስ መስጠት እንደማይፈልግ ነገራት፡፡

‹‹ በዚያ ቀን በዛ አካባቢ ሌላ ማን ነበር?"ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

ለማስታወስ ሲጥር ተመለከተች‹‹‹ጁኒየር፣ ገመዶ፣ ጋሽ ፍሰሀ….እናትሽ….ስርጉት."

‹‹ ማን… ስርጉት ነበረች? ››

‹‹አዎ ነበረች …ከዛ ወደ ቤት መሄድ እንዳለባት ተናገረች እና አካባቢውን ለቃ ሄደች፡፡

‹‹ከግቢው ወጥታ ስትሄድ አይተሃታል….››

‹‹አይ መሄድ አለብኝ ብላ ስታወራ እንጂ ወጥታ ስትሄድ አላየኋትም….›› " ስለ ሊቁ ምን ማለት ይቻላል? እሱ በአካባቢው ነበር?"

‹‹እሱ ሁሌ  በሁሉም ቦታ የሚዞር..በሄድሽበት ቦታ የማታጪው አይነት ንክ ነበር ፣እውነቱን ንገረኝ ካልሺን ግን በዛን ቀን እሱን እዛ ቦታ እንዳየሁት አላስታውስም››

"እርሱን ካላየኸው በሰሎሜ ደም በተሸፈነ ልብሱ በቁጥጥ ስር ሲውል አልተገረምክም?"

‹‹በእርግጥ አልተገረምኩም…. ምን አልባት እኔ ሳላየው ጊቢ ውስጥ ሲዞዞር ከአባዬ ቦርሳ የወደቀውን ቢላዋ እንዳገኘው ገምታለው፣ ከዛ እናትሽን ገድሏታል ብዬ አስባለው.››

‹‹ነገር ግን ከዛ ሁሉ የአባትህ የህክምና መሳሪያዎች መካከል አንድ ቢላዋ ብቻ ሾልኮ መውደቁ ግራ መጋባት ውስጥ አይከትም… ?››

ዝም አላት…..፡፡

ይህ ዶ.ር የሶስቱም ተጠርጣሪዎች ጓደኛ ነው። በዛ ላይ በቋሚነት ለአቶ ፍሰሀ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው፡፡የሚያውቀው ነገር እንኳን ቢኖር በምንም አይነት ተአምር አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደማይፈቅድ አወቀች፡፡ከዚህ በላይ ጊዜዋን ማባከን ፋይዳ እንደሌለው ስላመነች ከመቀመጫዋ ተነሳችና አመስግናው ወደ ሁለተኛ ጉዳዮ አመራች፡፡
///
የእርባታ ድርጅት የእንቅስቃሴ አልባ ሆኗል ። የጽዳት ሠራተኞች ከቃጠሎ የተረፈውን ፍርስራሹን እና አመዱን እየሰበሰቡ እና እየጠረጉ በአካባቢው የቆመው መኪና ላይ እየጫኑ ነው። ኩማንደሩ በአካባቢው ወዲህ ወዲያ እየለ የሚሰራውን እየተመለከተ ነው፡፡ አለም ከመኪናዋ ስትወርድ አይቶታል፣ ነገር ግን እሷን ለማናገር ሲሞክር በአካባቢው የነበረው የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪ ሰለጠራው ወደእዛ ለመሄድ ከተንቀሳቀሰ በኋላ ሀሳቡን ቀይሮ ቆሞ ጠበቃት፡፡ ደረሰችበት…ሰላም ይለኛል ብላ ስትጠብቅ

"እዚህ ምን እየሰራሽ ነው?"ብሎ ጠየቃት፡፡

‹ከሳራ ጋር ሻይ ልጠጣ ነው የመጣሁት።››

በመደነቅ አፍጥጦ ተመለከታ‹‹ከእሷ ጋር ደግሞ ከመቼ ወዲህ ነው ጓደኛ የሆናችሁት?››

“ሃሳብ የእኔ ሳይሆን የእሷ ነበር” አለችው።

"እሺ ተዝናኑ" አለና ፊቱን አዙሮ ሲጠራው ወደ ነበረው ሰውዬ ሄደ፡፡

እሷም ወደማረፊያ ቤቱ ተራመደች..አቶ ፍሰሀ  በቤቱ በረንዳ ላይ ቆሞ ነበር፣ ስትጠጋ ፍርሃቷ እንዳይታይ ለማድረግ ሞክራለች።

"እንዴት ነህ … ጋሽ ፍሰሀ?"

"  ሰዓት  አክባሪነትሽ  የሚደነቅ  ነው…እናትሽም  ልክ  እንደዚህ  ነበረች››አላት፡፡ለምን እንደመጣች እንደሚያውቅ ተረዳች

‹‹አመሰግናለው››አለችው፡፡

‹‹ምንም አይደል››

"ኩማንደሩ እሳቱን ያስነሳውን ሰው  በቁጥጥር ስር እንደሚያውለው  ተስፋ አደርጋለሁ። እኔም ተገቢን ፍትህ እንድታገኙ አስፈላጊውን ሁሉ አደርጋለሁ።"ስትል ቃሏን ሰጠችው፡፡

"አዎ፣ እኔም ተስፋ አደርጋለው… ሁሉንም ነገር ችላ ማለት እችላለሁ። ነገር ግን ያን የመሰለ ተወዳጁን የገመዶን ፈረስ እንዲሞት ያደረገውን ሰው ግን ይቅር አልለውም።ያን ፈረስ በማሳደግና በመንከባከቡ ይሰማው የነበረውን ኩራት እኔ ነበርኩ የማውቀው።"

በዚህ ጊዜ ጁኒዬር ከውስጥ ወጣ…በውብ ፈገግታ ተሞልቶ የሞቀ ሰላምታ ሰጣት፡፡ አለም"ወደ ውስጥ ብገባ ይሻለኛል… እናትህን ብዙ አላስጠብቃት" አለቸው ።
ጁኒየር እጁን ትከሻዋ ላይ ጫነና "እናቴ የትላንት ማታውን ጥፋቷን ማረም ትፈልጋለች። ግብዣዋን ስለተቀበልሽ በጣም ተደስታ ነበር። አንቺን ለማየት በጉጉት እየጠበቀችሽ ነው።››አላት

‹‹ጥሩ››ብላ ወደ ውስጥ ገባች፡፡
አገልጋይዋ በራፉ ድረስ መጥታ ተቀበለቻት።‹‹ግቢ።››ብላ ወደ ውስጠኛው ክፍል እየመራች ወሰደቻትና ከሳራ ጋር አገናኘቻት፡፡

ከሳራ ጋር ተጨባበጡና ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ፡፡
አለም የክፍሉን ዙሪያ ገባ እየተመለከተች"እንዴት የሚያምር ክፍል ነው?!"

"ወደድሽው?።"

‹‹በጣም እንጂ…››
42👍7👏2
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///

"ምንድነው የነገረችሽ?"

"እኔ ዲቃላ መሆኔን ."

የጁኒየር ፊት በድንጋጤ ባዶ ሆነ።

"እውነት ነው አይደል?"
ጁኒየር እጆቹን ዘረጋና እቅፉ ውስጥ አስገባት… እንባዋ በመጨረሻ የዐይን ሽፋኖቿን ሞልተው ያለከልካይ ፈሰሰ።

"ሰሎሜ ከኮፈሌ ተመልሳ መጣች። ከገመዶ ጋር ለመታረቅ ተዘጋጅታ ነበር።ፍቅራቸውን ለማደስ ተስማምተው ነበር …የመጋባት እድል ሁሉ ነበራቸው…በመሀል ግን ለማንኛችንም ሳትነግረን መልሳ ጠፋች….በኋላ ነው አንቺን ማረገዟን ስላወቀች እንደጠፋች ያወቅነው፡፡››ሲል አስረዳት፡፡

በእፍረት ፊቷን በእጆቿ ሸፈነች።
" ኦ አምላኬ በጣም ቢጠላኝ አይገርምም።››

ጁኒየር እጆቿን ከፊቷ ላይ አንስቶ በቅን ልቦና የሚወዳቸውን ጥቆቁር አይኖችን እየተመለከተ።

"ገመዶ አንቺን አይጠላሽም አሌክስ። ማናችንም ብንሆን አንጠላሽም…ያ ከአመታት በፊት ተጋፍጠን በይቅርታ ያለፍነው ጉዳይ ነው››

በንግግሩ በምሬት ሳቀች።‹‹ለምን አያቴ ሁሌ እኔ ላይ ጥብቅ እንደምትሆን እያሰብኩ እበሳጭ ነበር …በስንት ሰዓት ከቤት እንደወጣው? በስንት ሰዓት እንደተመለስኩ..?ከማን ጋር እንደነበርኩ ከአግባቡ ያለፈ ቁጥጥር ታደርግብኝ ነበር…ምክንያቷ አሁን ነው የገባኝ
…ለካ እናቴን ያጋጠማት ነገር እንዳያጋጥመኝ ፈርታ ነው፡፡አሁን ነው የገባኝ፡››

"ይሄ ከሃያ አምስት አመታት በፊት የሆነ ድርጊት ነው ፣ አሌክስ አሁን ስለዛ ማሰብ አቁሚ "

"አያቴ በእውነት እኔን ለምን እንደማትወደኝ የሚያብራራልኝ ታሪክ ነው… የሰሎሜን ህይወት አበላሽቻዋለሁ…እና ለዛ ፈጽሞ ይቅር ሳትለኝ ነው የሞተችው…. ሰሎሜ ገመዶን አጥታለች …ፍቅራቸው እንዳይሆን ሆኖ ተሰባብሯል … እና ሁሉም የሆነው በእኔ ምክንያት ነው››.

‹‹ኦህ፣በእግዚአብሔር !ተረጋጊ እንጂ!"
አለም ከእቅፉ ወጣችና ወደ መኪናዋ ሮጠች…መኪና ውስጥ በመግባት አስነሳችና አካባቢውን ለቀቀች።

."ምንድነው ነገሩ?" አለም ወደ መኪናዋ አቅጣጫ ስትሮጥ ያያት አቶ ፍሰሀ ጠየቀው።

"ሁለታችሁም እሷን ተዋት" ሳራ ከውስጥ እየወጣች ለባሏ መለሰች፡፡

ጁኒየር ወደ እናቱ ዞረና።

"እማዬ እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ? እንዴት ልጅቷን እንዲህ ትጎጂያታለሽ?"

"ልጎዳት አስቤ አይደለም የነገርኳት፡፡››

"ምን ነግራት ነው?" አቶ ፍሰሀ ጠየቀ ፡፡

ጁኒየር “በእርግጥ ጎድተሻታል። ደግሞ አቅደሽበት ነው ያደረግሽው… ለምን ነገርሻት?"

‹‹ምክንያቱም እሷ ማወቅ ስላለባት። አለምን የምትጎዳት እራሱ አለም ብቻ ነች። ሸቅዠቷን እያሳደደች ነው። የምትፈልጋት አይነት ቅድስት የሆነች እናት በሰሎሜ ውስጥ አልነበረችም። ሰሎሜ ምትባል ድንቅ እናት እንደነበረቻት በማይረባ ጭንቅላቷ ደምድማለች። እናቷ ምን ያህል ተንኮለኛ እና ሀጥያተኛ እንደሆነች ልጅቷ ማወቅ አለባት.. እናቷ ስትማግጥ እሷን ዲቃላ እንዳረገዘቻት የማወቅ መብት አላት››

" አንቺ እኮ ጤነኛ አይደለሽም!" አቶ ፍሰሀ ተበሳጨባት፡፡

አቶ ፍሰሀ በጸጥታ ወደ መኝታ ቤት ገባና ከኋላው በሩን ዘጋው፡፡ሳራ በአልጋዋ ላይ ያሉትን ትራስ ደራርባ ተደግፋ መፅሃፏን እያነበበች ነበር…እሱን ስታይ መፅሀፉን ከደነችና አጠገቧ ያለው ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠች ።

ወደአልጋው ቀረበና " ላናግርሸ እፈልጋለሁ።"አላት፡፡

"ስለ ምን?"

‹‹ዛሬ ከሰአት በኋላ ስለተፈጠረው ነገር።››
"ራስ ምታት እየፈለጠኝ ነው…ለእራት ወደታች ያልመጣሁትም ለዛ ነው"

‹‹የሆነ መድሀኒት አልወሰድሺበትም?"

"አዎ ወስጄለሁ…አሁን በመጠኑ እየተሻለኝ ነው ።"የሳራ የራስ ምታት በትዳራቸው ልክ አብሯት የቆየ ህመም ስለሆነ የተለመደ ነው፡፡

በአልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠ እና አቀርቅሮ ሀሳብ ውስጥ ገባ፡፡

" ምንድነው ፍሰሀ ?አሁንም የሚያሰጋን ችግር አለ እንዴ?››ጠየቀች፡፡

"አይ..ሁሉም ነገር ሰላም ነው።"

"ታዲያ ለምን ታስባለህ…?እግዚአብሔር ይመስገን ብቸኛው የሞተው ፈረስ የገመዶ ነው
።››
አቶ ፍሰሀ ምንም አስተያየት መስጠት አልፈለገም ። ሳራ ጆ ለገመዶ ያላት ስሜት ፈጽሞ አይለወጥም፤በዚህ ጉዳይ ከእሷ ጋር መነጋገር ጥቅም አልባ እንደሆነ እርግጠኛ ነው፡፡ከእሷ ጋር ሊወያይ የመጣው ስስ ስለሆነ ጉዳይ ነው። ቃላቱን በጥንቃቄ ለመምረጥ ትንሽ ጊዜ ወሰደበት.

"ሳራ ዛሬ ከሰአት በኋላ -……" "በጣም ተበሳጭቼ ነበር" አለችው፣ ፡፡

" ተበሳጭተሽ ነበር?" ፍሰሀ ትዕግሥተኛ ሆኖ ጠየቃት፡፡ወደ ድምዳሜው ከመዝለሉ በፊት ከእሷ ወገን ያለውን የታሪኩን ገጽታ መስማት ፍልጓል።

"የአለምን ስሜትስ የጎዳሽ አይመስልሽም…?"

"ዲቃላ መሆኗን ስላወቀች ብቻ አይደለም የተናደደችው….እሷ በተፈጥሮዋም ብስጩ ነች:: "

"እኔ በእሷ ቦታ ብሆን አይገርመኝም… ወላጆቼ የጋብቻ ሰርተፊኬት እንዳላቸው በጭራሽ አጣርቼ አላውቅም.., እና ባይኖራቸውም ምንም አይመስለኝም ነበር.››

" ሁሉም ሰው ለነገሮች ያለው ምላሽ የተለያየ ነው››

‹‹ አለም ግን ስሜታዊነት የሚያጠቃት ወጣት ሴት ነች።"

"እሷ ይሄን ታሪክ ለመቀበል የሚያስችል ጥንካሬ እንዳላት አምናለው."ስትል መለሰችለት

"በእርግጥ የምትይውን ያህል ጥንካሬ እንዳላት እርግጠኛ አይደለሁም።በረንዳ ላይ ቆሜ እያየችኝ እኔን እንኳን ሀሳትሰናበተኝ ነው ገፍትራኝ ሮጣ የሄደችው፡፡››

የሳራ ፈገግታ ተሰበረ። "ስለነገርኳት ትወቅሰኛለህ? ስህተት የሰራው  ይመስልሃል?"ስትል ጠየቀችው፡፡

በዛ ልብን በሚሰረስር የግሏ የሆነ ልዩ እይታ ስታየው፣ ልቡ ቀለጠ። ሁል ጊዜም የዚህ አይነት አስተያየት ስታየው የሚሆነው እንደዚሁ ነው። ፍሰሀ በስሱ ይዳብሳት ጀመር፡፡

‹‹ውዴ ስለነገርሻት አልወቅስሽም። ግን የነገርሽበት መንገድ እንደዚህ ባይሆን ጥሩ ነበር፡፡ እንደዛ ከማድረግሽ በፊት ከጁኒዬር እና ከእኔ ጋር መመካከር ነበረብሽ…በህይወቷ ሙሉ ባታውቀው የሚሻል ታሪክ ነበር፡፡››

"አልስማማም" ስትል ሳራ ተከራከረች።
አቶ ፍሰሀም "እናቷ እና አባቷ አብረው ከተኙ በኃላ አለመጋባታቸው ወይ መጋባታቸው በእሷ ልጅነት ላይ አሁን ምን ለውጥ ያመጣል? ይህ በቡዙ ወጣት ሴቶች ህይወት ላይ የሚያጋጥም በጣም የተለመደ ነገር ነው..››አላት፡፡

"ልጅቷ ስለ ሰሎሜ ያላት አመለካከት ላይ ግን ለውጥ ያመጣል። ››

‹‹እንዴት?››

‹‹ሰሎሜ ልጅቷ የምታስባትን አይነት ቅድስት ሴት አይደለችም…ይሄን ማወቋ የእሷን የግድያ ጉዳይ ለማወቅ የምታደርገውን ልፋትና ጥረት ቆም ብላ እንድታይ ያግዛት ይሆናል….ይልቅ ከአሁን በኃላ ሁላችሁም ከአለም ጋር መገናኘቱን እና መወያየቱን ማቆም አለባችሁ፡፡››

"ለምን?"ግራ ገብቶት ጠየቀው፡፡

"ለምን? ምክንያቱም እሷ እኛን ለማጥፋት እየሞከረች ነው…ለዚህ ነው. እሷን ለመፋለም የወሰንኩ…. ያለኝን ጥይት ነው የተጠቀምኩት….አንተን እና ጁኒየርን ለመጠበቅ እየሞከርኩ ነበር."

በእውነቱ፣ ፍሰሀ እንደ አለም ያለ በራስ መተማመን የነበራትን ሴትን ለመጋፈጥ ለሣራ ትልቅ ድፍረት እንደሆነ አሰበ። ያደረገችው ስህተት ቢሆንም ሳራ ያደረገችውን ነገር ያደረገችው ቤተሰቧን ልትጠብቅ እንደሆነ ተረድቷታል። የጀግንነት ጥረቷ ከትችት የተሻለ ነገር ይገባዋል ብሎ አሰበ እና ጎንበስ ብሎ ግንባሯን ሳመ።

ለስለስ ባለ ንግግር" የትግል መንፈስሽን አደንቃለሁ… ግን ማናችንም ያንቺን ጥበቃ አንፈልግም ።"አላት፡፡
46👍3
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ስርጉት እኩለ ለሊት ቢያልፍም ኪችን ውስጥ ስራ እየሰራች ስለነበር አልተኛችም..ድንገት ግን የውጭ በራፍ ሲንጎጎ ስትሰማ እጇ ላይ የነበረውን የሸክላ ሰሀን ለቀቀችውን ወለል ላይ አርፎ ፍርክስክስ ብሎ ተሰበረባት፡፡የበሩ መንኳኳት እንደቀጠለ ነው..ቶሎ ብላ ኪችኑን ለቃ ወጣችና ወደሳሎን ሄደች ...

" በፈጣሪ ማን ነው ?" ጠየቀች፡፡

"ስርጉት… እኔ ነኝ ..ክፈቺ."

የሰማችውን ድምፅ ልታምን አልቻለችም  ….ለማሰብ ጥቂት ሰከንድ እንኳን ሳታቅማማ
ተንደርድራ ወደበሩ ሄደችና ከፈተችው፡፡

በረንዳው ላይ ተገትሯል…ለደቂቃዎች በራፉን አንደያዘች በትኩረት ተመለከተች፣

‹‹በሰላም ነው ጁኒዬር?››

‹‹ሰላም ነው››መለሰላት፡፡

‹‹ግባ …››አለችና ከበራፉ ዞር አለችለት..ሰተት ብሎ ገባ፡፡

"እዚህ ምን እየሰራህ ነው?"

"አንቺ ጋር መጥቼ ነዋ…ክብር ዳኛ ተኝቶ እንደሚሆን እገምታለው››

"አዎ አባዬ በጊዜ ነው የተኛው።››

የቀድሞ ባለቤቷ በዚህ እኩለ ለሊት እሷን ብሎ የሚመጣበት አንድም አሳማኝ ምክንያት ሊመጣላት አልቻለም፡፡ ቢሆንም ግን….ግድ አልነበራትም። እዚህ መገኘቱ በቂ ነበር። አባቷ ካገመሰው ቦድካ በብርጭቆ ቀዳችና ሰጠችው፡፡ተቀበላትና በቆመበት አንዴ ተጎነጨለት፡፡

"ይህ የሌሊቱ የመጀመሪያ መጠጥህ አይደለም አይደል?"

"አይ..አይደለም." ድምፁን ዝቅ አድርጎ መለሰላት ፡፡

"ወደእኔ እንድትመጣ ለወራት ስጠብቅ ነበር ። ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ አሁን ወደእኔ ስትመጣ ደግሞ ለምን የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ እየተመላለሰ ነው፡፡››አለችው፡፡

" ፈልጌ ነበር." አላት፡፡

ለጁኒየር አእምሮ ያ በቂ ምክንያት እንደሆነ ታውቃለች። ሶፋው ላይ ተቀመጠና ጎትቶ ከጎኑ አስቀመጣት።ከበርካታ ደቂቃ ፀጥታ በኋላ " በእርባታ ድርጅቱ ውስጥ ስለተፈጠረው ችግር ሰምቻለሁ" አለችው.

"አሁን ሁሉ ነገር ሰላም ሆኗል….እሳቱ በጊዜው ነው የተደረሰበት…በጣም የከፋ ሊሆን ይችል ነበር."

እያመነታች እጇን እጁ ላይ አሳረፈች፡፡
‹‹አንተ ግን ራስህን ጠብቅ…ንብረታችሁን ለማቃጠል የደፈረ ጠላት በእናንተም ላይ ቀጥታ ጥቃት ከመፈፀም ወደኃላ ላይል ይችላል፡፡››

"አሁንም ለደህንነቴ ትጨነቂያለሽ?"

"ሁልጊዜ።"አለችው፡፡

‹‹ሰሎሜ እንዳንቺ ጣፋጭ ሆኖልኝ አታውቅም። ››

"የደከመህ እና የተቸገርክ ትመስላለህ?።"

"አዎ ደክሞኛል!!።"

ሶፋው ላይ ሙሉ በሙሉ ወጣና ትራሱን ተንተርሶ አረፈ። "በሰሎሜ ግድያ ላይ ያለው ውዥንብር እየበጠበጠን ነው።ሁሉም ነገር እንደ ገሃነም ተስፋ አስቆራጭ ነው።››አላት፡፡ከትራሱ ቀና አለና እሷ ትከሻ ላይ ተንተራሰ"እህ…ጥሩ መዓዛ አለሽ…ይህ ሽታ ናፍቆኝ ነበር. በጣም ንጹህ. ነው፡፡

"ስለዚህ ምርመራ በጣም የሚያስጨንቅህ ምንድን ነው?"

"ምንም የተለየ ነገር የለም። አለም ነች ። እሷ እና እናቴ ዛሬ ተፋጠው ነበር። እናቴ ስለሰሎሜ አንዳንድ መጥፎ ነገሮችን ነገረቻትና በጣም እንድታዝን አደረገቻት… ያ ጥሩ ትእይንት አልነበረም።››

ክንዱ በወገቧ ዙሪያ ላከውና አቀፋት ..እጇን አነሳች እና ጭንቅላቱ ላይ አሳርፋ እንደህፃን ልጅ ታሻሸው ጀመር፡፡

"ዋሻተኋታል እንዴ?"

"የማጣት ፍርሀት የወለደው ውሸት"ጁኒየር ፍላጎት በማጣት አጉተመተመ።

"እናቷ በተገደለችበት ቀን በረንዳ ላይ እንደነበርኩ አልነገርኳትም።ለምን እንደዛ አደረክ ?"

" በተከታታይ ጥያቄዎች እንድታጣድፈኝ አልፈለኩም።አንዳንድ መመለስ የማልችላቸውን ጥያቄዎች ብትጠይቀኝ እንዴት አደርጋለው?›››

‹‹ ጁኒየር ዳግመኛ ችግር ስለፈጠረችብህ ጠላኋት።"

"አለም ሁኔታውን ልትረዳ አትችልም….ያም የእሷ ጥፋት አይደለም.››

ጁኒየር ስለ ሶለሜ ብዙ ጊዜ ተመሳሳይ ነገር ተናግሮ ነበር። የቱንም ያህል ብታበሳጨውም ስለእሷ ጠንከር ያለ ቃል ተናግሮ አያውቅም።ስርጉት በሹክሹክታ

‹‹ይህችን የሰሎሜን ልጅ ልክ እንደእናቷ በጣም እጠላታለሁ››ስትል አንሾካሾከች፡፡

"አሁን ስለዛ አታስቢ። ይህ ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ አያደርግም" አላት፡

እጁን አነሳና እርጥበታማ ከንፈሯ ላይ አሳርፉ ዳበሳት …ከለበሰችው ጋወን ያፈነገጡ ጡቶቾን ተመለከተ።እጁን ከከንፈሯ አነሳና ጡቷ ላይ አስቀመጠ…

‹‹እንደዚህ ሳደርግ ሁል ጊዜ ደስ ይልሽ ነበር ።››

"አሁንም አድርገው።››

‹‹እውነት? ››

"ጡቷን ወደ አፉ አቀረበችለት…ጎረሰው…. እጁን በጭኖቿ መካከል ሰነቀረው፡፡እርጥበት ያለውን ፀጉር እየዳበሰ ወደውስጥ መጓዙን ቀጠለ … ስሙን እየጠራች አቃሰተች።

‹‹ካልፈለግሽ ይገባኛል››አላት

"አይ" አለች በፍጥነት "እፈልጋለው እባክህ።›››ተማፀነችው፡፡፡

"ስርጉቴ ያንቺ በርህራሄ የበለጸገ ፍቅራዊ እንክብካቤ ዛሬ ማታ ያስፈልገኛል። ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ ሁልጊዜም በአንቺ ልተማመንብሽ እችላለሁ።››ሲል ተናዘዘላት፡፡

ጎንበስ አለችና ከንፈሩን ሳመችው፡፡

"ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት እንዴሰማኝ እንደጣርሽ ነው…አይደል እንዴ?" ብሎ ጠየቃት፡፡

"አዎ ።"አለችና አጎንብሳ ተመለከተችው። ልክ እንደ መልአክ ፈገግ አለላት ። እንደዚያ ሲያያት ምንም ልትከለክለው አቅም አይኖራትም በጭራሽ።
///
"ወ/ሪት አለም…ወ.ሪት አለም?አለሽ እንዴ?››

አለም ድክምክም ብላ ተኝታ ነበር። ጥገና የተደረገላት በሯን በተደጋጋሚ ሲንኳኳ ነው ከእንቅልፎ የነቃችው፡፡ ስትነቃ… ደንዛዛ እና ቀዝቃዛ ነበር።ከመተኟቷ በፊት ለረጅም ሰዓት ከማልቀሷ የተነሳ ዓይኖቿ አብጠው ነበር።

"ምን ፈለክ?" ድምጿ ለጩኸት የቀረበ ነበር።

" ክፈቺልኝ እትዬ…መልዕክት አለሽ?።"
እንደምንም ከአልጋው ወረደችና ጋወኗን ለብሳ ወደሳሎን በመሄድ በራፉን ከፈተች፡፡የተከራየችበት አፓርታማ ዘበኛ ነው

"እትዬ ስልክሽ ከአገልግሎት መስጫ ውጭ ነው ይላል?"

"አዎ…ዝግ ነው….ለምን ፈለከኝ?" ግራ በመጋባት ጠየቀችው፡፡

‹‹እኔ አይደለውም…አቶ ግርማ የሚባሉ ሰውዬ መጥተው ነበር›› ደነገጠች‹‹የት ነው..?አሁን አለ?››

‹‹አይ ሄደዋል …መልዕክት ንገርልኝ ብለዋል….ነገ ጥቃት ዝዋይ ስብሰባ ስላለ እንድትገኚ ብለዋል››

‹‹ዝዋይ..?የምን ስብሰባ?››

‹‹አላውቅም እትዬ …ሰውዬው ናቸው ያሉት››

‹‹ማለት ተሳስተህ እንዳይሆን?››

‹‹አይ  ይሄው  ማስታወሻ  ላይ  አስፍሬዋለው…››ብሎ  በተወለጋገደ  ፅሁፍ  የተፃፈውን ማስታወሻ አሳያት፡፡

‹‹እሺ በቃ አመሰግናው››ብላ ሸኘችውና ወደ መኝታ ቤቷ ተመለሰች፡፡ከዛ ስልኳን ፈለግችና አበራችው…ዋናው አቃቢ ህጉ ጋር ደወለች….ስልኩ አይሰራም፡፡፡ስልኳን አስቀመጠችና ጋወኗን አውልቃ ቢጃማ መልበስ ጀመረች፡፡እንደጨረሰች ከእንደገና ስልኳን አነሳችና ደወለች፡፡

"ፖሊስ መምሪያ ነው…ምን እንርዳዎት?."

"እባክህ ኩማንደር ገመዶን ፈልጌ ነበር፡፡"

"እሱ የለም። ሌላ የሚረዳሽ ሰው ጋር እናገናኝሽ?"

"አይ፣ አመሰግናለሁ፣ በቀጥታ ከእሱ ጋር መነጋገር አለብኝ…ምክትል አቃቢ ህግ አለም ጎበና ነኝ።"

‹‹ክብርት አቃቢ ህግ እንዴት ነሽ….አሁን የት ነሽ?፧"

"እቤቴ ነኝ …ለምን ጠየቅከኝ?"

"ኩማንደር ወደአንቺ እየመጣ ነው….እስከአሁን ይደርሳል››

‹‹ምነው በሰላም…..?››መልሱን ሳይመልስላት በራፏ ሲንኳኳ ሰማች‹‹ እሺ …በል ደህና ሁን…ደርሶል መሰለኝ ››አለችና ስልኩን በመዝጋት ወደሳሎን ሄዳ በራፉን ከፈተችለት፡፡

‹‹እሺ ኩማንደር ?››

‹‹ዞር በይልኝ እንጂ ልግባ።››

‹‹መግባትህ አስፈላጊ ነው?››እያለች በራፉን ለቀቀችለት፡፡
83👍15
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
እሱ በራፉን ለመክፈት ሲሄድ አለም ቶሎ ብላ ቦርሳዋ ውስጥ ገባች እና በጣም የሚያምር ውድና ጌጠኛ ብእር አወጣችና ወደቤቱ በራፉ ፊት ለፊት በመወርወር ወደፊት ራመድ ብላ እስኪመለሱ መጠበቅ ጀመረች፡፡

‹‹እ..ሰላም ነው..?ስልክህ አይነሳም፡፡››አቶ ፍሰሀ ነው ተናጋሪው፡፡

‹‹ውስጥ ቻርጅ ላይ እርጌው አላየሁትም…ግባ››ኩማንደሩ መለሰለት፡፡ ወደውስጥ ሲገባ አለምን ስላያት ነገሩ ገባው፡፡

‹‹እንዴት ነህ አቶ ፍሰሀ?››

‹‹ሰላም ነኝ…አንቺስ?››

‹‹አለሁ..››አላችና ‹‹በሉ እንግዲህ መሄዴ ነው››ስትል አከለችበት፡፡

‹‹ምነው ..እኔ ስመጣ ነው እንዴ ምትሄጂው?››

‹‹አይ መጀመሪያውኑም ለመሄድ ስል ነው የመጣሀው…ጉዳዬን ጨርሼለው..ተራውን ለአንተ ልልቀቅ፡፡››አለችና ሁለቱንም ተሰናብታ ወጣች፡፡

ገመዶ እና አቶ ፍሰሀን አስከትሎ ወደውስጥ ለመግባት ሲራመድ በራፉ ጋር ሲደርሱ አቶ ፍሰሀ ጎንበስ አለና አይኑ የገባውን ብዕር አነሳ፡፡

‹‹ይሄን የመሰለ ብዕር ትጥላልህ እንዴ?››ብሎ ወደ ኩማንደሩ ዘረጋለት፡፡ኩማንደሩ ተቀብሎ አገላብጦ ተመለከተውና‹‹ወይ የእኔ አይደለም…የአለም መሰለኝ›››አለና ስልኩን አውጥቶ ደወለላት፡፡

‹‹ሄሎ››

‹‹ ምነው ከአሁኑ ናፈቅኩህ እንዴ?››
‹‹ባክሽ ሌላ ቦታ ጥዬዋለው ብለሽ እንዳትፈልጊ ነው…አንድ ብዕር ጥለሽ ሄደሻል..ካልራቅሽ ተመለሺና ውሰጂው››

‹‹ወይ  እንዴት  ጣልኩት…?ለማንኛውም  በጣም  ከምወደው  ሰው  የተሰጠኝ  ስጦታ ነው…ከኪስህ እንዳይወጣ …ስንናኝ ትሰጠኛለህ››አለቸው፡፡

‹‹እሺ ቻው››አለና ስልኩን በመዝጋት ብእሩን ደረት ኪሱ ውስጥ ሻጠውና ከአቶ ፍሰሀ ጋር ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ….

‹‹ቢራ ልክፈትልህ››

‹‹በጣም ደስ ይለኛል››

ለሁለቱም ቢራ ከፈተና ፊት ለፊት ተቀመጠ፡፡

‹‹መጥፎ ሰዓት ነው እንዴ የመጣሁት?››አቶ ፍሰሐ ጠየቀ፡፡

‹‹አይ እንደውም በተቃራኒው ጥሩ ሰዓት ላይ ነው የመጣሀው..በጣም አደጋ ላይ ነን››

‹‹ማለት››

‹‹ይህቺ ልጅ ከጠበቅኳት በላይ አደገኛ ነች…ሳታጠፋን አርፋ አትቀመጥም….››

‹‹ማለት….አንተ እንዲህ ካልክ ነገሮች ከባድ ናቸው ማለት ነው››

‹‹አዎ…ስለእያንንድ  የሶሌ  ኢንተርፕራይዝ  የአክሲዬን  ድርሻ…ማን  ስንት  ፐርሰንት እንዳለው…አክሲዬኑ መቼ እንዳገኘነው….ዝርዝር መረጀ አላት፡፡››
አቶ ፍሰሀ ልብ ምቱ በደቂቃ ውስጥ ሲጨምር ታወቀው….

‹‹ምን እያልከኝ ነው?››

‹‹አዎ….የእናቴን ሞት ተከትሎ የአንዳችሁ አክሲዬን ተቀንሶ ለሌሎቻችሁ የተጨመረው ለምንድነው ብላ ጠየቀችኝ…?፡፡››

‹‹ይሄ እኮ ወደእውነት እየቀረበች መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡››

‹‹አዎ…አንድ ውሳኔ መወሰን አለብን፡፡››
አቶ ፍሰሀ ወዲያው ስልኩን አወጣ…መጀመሪያ ዳኛ ዋልልኝ ጋር ደወል…አሁኑኑ ወደቤት እንዲመጣ ነገረውና ስልኩን ዘግቶ መልሶ ልጁ ጁኒዬር ጋር ደወለ..ቤት እንደሆነ ነገረው…ሳይወጣ እንዲጠብቀው ነግሮ ዘጋውና‹‹በል ተነስ እንሂድ….አሁኑኑ ተነጋግረን አንድ ነገር ማድረግ አለብን፡፡››
///
ከምሽቱ አራት ሰዓት አራቱ ሰዎች ምድር ቤት በሚገኘው የአቶ ፍሰሀ ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው ፊት ለፊት ተፋጠዋል…በጠረጴዛው መሀከል ሙሉ የውስኪ ጠርሙስ ሲኖር በመሀከላቸው ግማሽ ድረስ የተሞላ ብርጭቆ አለ….

‹‹እኔ  ከመጀመሪያውም  ነግሬችሁ  ነበር..ይህቺን  ሴት  አንድ  ነገር  አድርጓት  ስላችሁ ነበር››ዳኛው በንዴት ደነፉ፡፡

‹‹አሁን ያለፈውን ገር እያነሳን ልንወቃቀስ አይደለም የተገናኘው…አሁን እንዴት አድርገን እናሳቁማት የሚለው ነው ወሳኙ ነገር፡፡››

‹‹ለምን ሁችንም ባለንበት አግኝተናት ይሄንን ጉዳይ እንድታቆም ለመጨረሻ ጊዜ አናሳጠነቅቃትም››አለ ጁኒዬር፡፡

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ….መቼስ ልጅቷን ግትርነት ከአንተ በላይ የሚያውቅ ያለ አይመስለኝም፡፡ እኔ በበክሌ እዚህ እግሯ ከረገጠበት ቀን አንስቶ በሰላምም በማስፈራራትም ይህንን ጉዳይ እንዳታቆም ያልጠየቅኳት ቀን የለም…አንድም ቀን ሽብርክ ስትል አልሰማዋትም…ዛሬም የነገረችኝ ጉዳዩን ከማቆም መሞትን እንደምትመርጥ ነው፡፡››ሲል አስተያየቱን ያቀረበው ኩማንደሩ ነበር፡፡

‹‹እሱማ ትክክል ነህ …እኔም ያልሞከርኩበት ቀን የለም…›አለ ጁኒዬር፡፡

‹‹አዎ…ይሄ ጉዳይ አይሰራም፡፡››
ዳኛው ትእግስት አልባ በሆነ ንግግራቸው‹‹በቃ በንግግር ማስቆሙ ካልሰራ …አስወግዷታ

…መቼስ ይሄንን ስታደርጉ የመጀመሪያችሁ አይደለም››አለ ፡፡

በገመዶና በጂኒዬር ላይ የተከሰተው ድንጋጤ የተለየ ነበር…..እርስ በእርስ ተያዩ….ከዛ ሁለቱም በእኩል ጊዜ ወደአቶ ፍሰሀ ዞሩ….አቶ ፍሰሀ አይናቸው ተጉረጥርጧል…ለመናገር እየፈለጉ እየተናነቃቸው ነው፡፡ከአንደበታቸው ቃል ማውጣት የከበዳቸው መሆኑን ያስታውቃል…ከዛ እንደምንም አሉና መናገር ጀመሩ፡፡

‹‹ይሄንን ለሁላችሁም ነው የምናገረው…ለሁላችሁም….እዚህች ልጅ ላይ የመግደል ሀሳብ አይደለም አንዲት ፀጉሯን ለመንቀል ብታስቡ ቀጥታ ፀባችሁ ከእኔ ጋር ነው፡፡ማንም እጣቱን በእሷ ላይ ሊያነሳ አይችልም፡፡››

ዳኛው አይናቸውን አጉረጠረጡ‹‹ለምን ተብሎ..ለአንድ ዲቃላ ልጅ ሲባል የእኛ ህይወት መመሰቃቀል አለበት፡፡.እናንተ ማድረግ ካልፈለጋችሁ እኔ አደርገዋለው፡፡››

አቶ ፍሰሀ ልክ እንደጎረምሳ ከተቀመጡበት ተስፈንጥረው ተነሳና ከወገቡ ያለውን ሽጉጥ መዞ ሽማግሌው ዳኛ መላጣ ጭንቅላት ላይ ደቀነው፡፡

ገመዶና ጁኒዬር በርግገው ከተቀመጡበት ተነሱ‹‹እንዴ አባዬ ….!ምን እያደረክ ነው?››

‹‹አንተ ፈርሳም ሽማግሌ….ከዛሬ ጀምሮ እንደውም ለልጅቷ ጠባቂ ቀጥረህ እንቅፋት እንኳን እንዳይነካት ብታስጠብቃት ይሻልሀል….በማንም ሆነ በማን አንድ ነገር ገጠማት ሲባል ብሰማ ይሄንን ምላጭ በአንተ ጭንቅላት ላይ ለመሳብ ለሰከንድ እንኳን አላቅማማም፡፡››

‹‹ጋሼ በቃ…..ወደመቀመጫህ ተመለስ..ተረጋጋ…››አለ ገመዶ፡፡

አቶ ፍሰሀ የደቀነውን ሽጉጥ መልሶ ወደ ወገብ ሻጠው እና መደመቀመጫው ተመለሰ

…..ሁሉም በፀጥታ ማሰላሰል ውስጥ ገባ…ገመዶ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደመስኮቱ ተጠግቶ ሲጋራውን ለኮሰና እያጬሰ ማሰብ ጀመረ፡፡ሲጋራውን እንደጨረሰ ወደመቀመጫው ተመለሰና ከውስኪው አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨ በኃላ ‹‹እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ››ሲል የሁሉንም ቀልብ ሳበ፡፡

‹‹ምንድነው እንስማው››ሁሉም ተነቃቁና ኩማንደሩ የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ሆነ፡፡

‹‹የሚቀጥሉት ስድስት ወራት ወሳኝ ጊዜዎች ናቸው..ማለቴ ከጂኒዬር የምርጫ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ይሄ የክስ ጉዳይ ወደፊት ከገፋና እንዲህ አይነት ወሬዎች ህዝቡና ሚዲያው ጆሮ መግባት ከጀመሩ ነገሮች ድብልቅልቃቸው ነው ሚወጣው፡፡እንደእኔ ለተወሰነ ጊዜ ወደሆነ ቦት ዞር አድርገን ብናስቀምጣት፡፡››

‹‹ዞር አድርገን ስትል….?ግልፅ አድርገው?፡፡››

‹‹በቃ ከሰው እያታ ውጭ የሆነ ቤት ወሰድን እዛ ሁሉ ነገር እንዲሞላላት እድርገን ግን ደግሞ ከማንም የማትገናኝበትን ሁኔታ ብናመቻች ጥሩ ይመስለኛል፡፡››

‹‹ጥሩ…እኔም እስከዛ ጡረታ ወጣና ከዚህ ከተማ ዞር እላለሁ››በማለት ዳኛው ቅድሚያ ተስማማ፡፡

አቶ ፍሰሀ ‹‹ጥሩ ሀሳብ ይመስላል….እንደውም ይርጋ ጨፌ የቡና እርሻችን ያለበት ቦታ ብንወስዳት ማንም ሊያገኛት አይችልም……እዛ ሁሉን ነገር እናሟላላታለን…እኛም በየተራ እየሄድን እንጠይቃታለን..መጥፎ ሰዎች እንዳልሆን እንድታምን እናደርጋለን፡፡
51👍8😱2
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ



///
‹‹በተሰቀለው…አሁን ምንድነው የምናደርገው?››

‹‹አላውቅም…ለአባትህ  ደውልለትና  በአስቸኳይ  ይምጣ…እዛ  ይርጋጨፌ  ምንም አያደርግም››

‹‹ደውዬለታለው… እየመጣነው››ሲል መለሰ ጁኑየር

‹‹ዳኛውም እየደወለልኝ ነበር››

‹‹እሱን ተወው ባክህ..ከአሁኑ በልብ ድካም እስከወዲያኛው ማንቀላፋቱ አይቀርም..ለማንኛውም እዚህ ምንም አንሰራም ..ወደቤት እንሄድ›› ተባባሉና ሁለቱም ወደ መኪናቸው በመግባት ተከታትለው ወደእነ ጁኒዬር ቤት መጓዝ ጀመሩ፡፡

በማግስቱ ጥዋት  አንድ ሰዓት በሶሌ ኢንተርፕራይዝ ህንፃ የአቶ ፍሰሀ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው እየተወያዩ ነው፡፡

‹‹ያሰማራናቸውን ሰዎች ምንም ፍንጭ አላገኙም››አቶ ፍሰሀ ናቸው ጠያቂው፡፡

‹‹እዚህ  ከተማ  ውስጥ  ያለች  አይመስለኝም….እያንዳንዱን  ሆቴል  እና  ፔንሲዬን አሳስሼለው….የለችም፡፡››ገመዶ መለሰ፡፡

‹‹ወደ አዲስአበባ ተመልሳ ሊሆን ይችላል?››

‹‹ወደዛም ሰው ልኬለው…..እንግዲህ የሚሆነውን እናያለን፡፡››

‹‹ጥሩ …ዩቲዬብ ባለቤትስ ማግኘት ችለናል…..?››አቶ ፍሰሀ ናቸው ሌላ ጥያቄ የጠየቁት፡፡

‹‹አዎ አናግሬው ነበር…የፈለገውን ያህል ብር እንደምንከፍለውና ቀጣዩን ስራ እንዳይለቅ ጠይቄው ነበር…››

‹‹እና?››

‹‹እናማ…ቀጣዩን አልሰጠችኝም…እራሷ ቀርፃ ነው የምትልክልኝ ….››የሚል መልስ ነው የሰጠኝ፡፡

እንደዛ ከሆነ እኮ አሪፍ ነው…ለልጁ ደህና ብር ስጡትና ቀጣዩን ታሪክ ልታስረክበው ስትቀጥረው ይደውልልን እና እናገኛታለን ማለት ነው››ዳኛው በአዲስ ተስፋ ተሞልተው ተናገሩት፡፡

ኩማንደር ፈገግ አለና‹‹ክቡር ዳኛ….ይሄንን ማሰብ የሚያቅተኝ ይመስልሀል?››

‹‹አይ በፍጹም እንደዛ አላልኩም….ውይይት ላይ ስለሆን የተሰማኝን በግልፅ ነው የተናገርኩት››

‹‹ጥሩ…ለልጁ ይሄንን ሀሳብ አቅርቤለት ነበር….ወዲያው ይሄንን መልእክት አሳየኝ፡፡››

‹‹ምንድነው?››

በዩቲዬብ የተለቀቀውን የወንጀል ታሪካችሁን መንደርደሪያ ስትሰሙ መጀመሪያ ምታደርጉት ወደእዚህ ዩቲዩበሩ ልጅ ጋር ሄዳችሁ በገንዘብም በማስፈራራትም ቀጣዩን እንዳይለቀውና በእሱ አማካይነት እኔን ለመያዝ እንደምትሞክሩ አውቃለው….ለዛም ነው ቀድሜ ይሄንን መልዕክት ልጁ ጋር የተውኩት፡፡አንደኛ ከአሁን በኃላ ቀጥታ ልጁን አላገኘውም .. የተቀረፀውን በሌላ መንገድ ነው ምልክለት፡፡ሁለተኛ ልጅን የምታቆሙት ከሆነ እየተቆራረጠ በአምስት ክፍል ይለቀቅ የነበረውን ለሌላ ዩቲዬበር አንዴ ሰጥቼው በአንዴ እንዲለቀቅና ነገሮች ፍርጥርጥ እንዲሉ አደርጋለው ….ያ ማለት ደግሞ ለማሰቢያ እና የተሻለውን መንገድ መምረጫ ጊዜ ያሳጣችኋላ..እንግዲህ ምርጫው የእናንተ ነው፡፡››ይላል፡፡

‹‹ምን አይነት ጉድ ልጅ ነች?››አቶ ፍሰሀ ነው የተናገረው፡፡

‹‹ብዬችሁ  ነበር..አልሰማ  ብላችሁ  ሁላችንንም  መቀመቅ  ውስጥ  ከተታችሁኝ….በጊዜ ትወገድ ብያችሁ ነበር፡፡››ዳኛው ተወራጩ፡፡

‹‹አንተ  ቀበተት  ሽማግሌ…በዚህ  እድሜህ  አንድ  ፍሬ  ልጅ  ትገደል  ስትል  ትንሽ አይቀፍህም?››አቶ ፍሰሀ በንዴት መለሰ፡፡

‹‹አሁንማ እንድትገደል ብንስማማስ የት እናገኛታለን?በዚህ ሁሉ እድሜዬ አንተንና ኩማንደሩን በእንደዚህ አይነት ጫወታ የበለጠች ብቸኛዋ ሴት እሷ ብቻ ነች፡፡በጣም ብጠላትም በጣም የምትደነቅ ጀግና የሆነች ልጅ ነች››ሲል ዳኛው ተናገረ፡፡

በዚህ ሰዓት ድንገት የኩማንደሩ ስልክ ጠራ ..ከኪሱ አወጣና አየው…..የማያውቀው ቁጥር ነው፡፡አነሳው‹‹ውዴ በጣም ናፍቀኸኛል››
በስልኩ በእግር በፈረስ የሚፈልጋትን የአለም ድምፅ እየሰማ መሆኑን ማመን አልቻለም

‹‹አንቺ…የትነሽ ያለሽው?››

‹‹ቅርብህ ነኝ….ጁኒዬርም አብሮህ ነው አይደል?››

‹‹ምን እያወራሽ ነው?››

‹‹ሁለችሁም ናፍቃችሁኛል?››

‹‹ቀለድሽብን ማለት ነው?››

‹‹አይደለም…መቼስ ሁለታችሁንም እንደምወዳችሁ አትጠራጠሩም አይደል..?ልክ እንደእናቴ… እኔም አፈቅራኋላው፡፡››
ሁሉም አፍጥጠው ይመለከቱት ነበር‹‹እና ምንድነው የምትፈልጊው?፡፡››

‹‹ምፈልገውንማ መጀመሪያ ከተገናኘንበት ቀን አንስቶ መች ደብቄችሁ አውቃለው››

‹‹እና አሁን ምን ይሁን ነው የምትይው?››

‹‹ምንም ….እኔ አሁን እየፈለኩት ስላላው ፍትህ ወይም በቀል ላወራችሁ አይደለም የደወልኩት ..ድምፃችሁን ልሰማ ነው..እባክህ ስልኩን ለጁኒዬር ትሰጠዋለህ፣በጣም ነፍቆኛል…››

‹‹ገደል ግቢ››አለና ስልኩን ጠረቀመው፡፡
‹‹ምንድነው ..ስልኩን ለምን ዘጋህባት?››ጁኒዬር በንዴት ጠየቀው፡፡

‹‹እሷ  ኮመዲ  እየሰራችብን  ነው..እንደናፈቅካት  ተናግራ  ካንተ  እንዳገናኛት  ነው የምትፈልገው››

‹‹ታዲያ ለምን ሳታገኛኘን?››

‹‹ምነው ?አንተም ናፍቃሀለች እንዴ?››

‹‹ተረጋጉ…ሁላችም ወደመቀመጫችሁ ተመለሱ››አቶ ፍሰሀ በመሀከል ጣልቃ ገብተው ሁሉም ወደቀልባቸው እንዲመለሱ አደረጉ፡፡

‹‹ልጆች አይታያችሁም እንዴ..?ይሄ እኮ የበቀሏአንዱ አካል ነው፡፡››

‹‹ማለት..?››ገመዶም ሆነ ጁኒዬር በአንድነት አቶ ፍሰሀ ላይ አፈጠጡ፡፡

‹‹በሁለታችሁ መካከል ቅሬታ በመፍጠር ኃይላችንን ለመበታተን እየጣረች ነው….›› ጁኒዬር ባለማመን ‹‹እንደዛ አስባ ይመስልሀል?፡፡››ሲል በጥርጣሬ ጠየቀ፡፡
‹‹ታዲያ ያንተን ስልክ እያወቀች ለምን ብላ ነው ለገመዶ ደውላ ከጁኒዬር ጋር አገናኘኝ ናፍቆኝ ነው የምትለው?››
‹‹አባዬ እውነትህን ነው….››
///
በተሰጣቸው ሶስት ቀን ውስጥ እሷን አድነው መያዝ አልቻሉም…እሷንም ቀጣዩን ክፍል በተመሳሳይ በዩቲዩብ ገፅ እንዳትለቅ ማድረግ አልቻሉም…ይሄ ሁለተኛው ግን ከመጀመሪያው በበለጠ ጫና ውስጥ ከተታቸው፡፡የከተማው የገዢው ፓርቲ ፅህፈት ቤትም ጁኒዬርን አስጠርቶ በሶሻል ሚዲያው ስለሚዘዋወረው ነገር ማብራሪያ እንዲያቀርብና በአፋጣኝ እየተሰነዘረበት ካለው ክስ ራሱ ነፃ እንዲያደርግ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው፡፡

‹‹አባዬ..ይህ ምርጫ ለምን አይቀርብኝም?››

‹‹ለምን እንደዛ አልክ?››

‹‹የፓርቲው ሰዎች እኮ ቁም ስቅሌን እያሳዩኝ ነው፡፡በአንድ ሳምንት ውስጥ በእኔና በቤተሰቦቼ ላይ እየተነዛ ያለውን ሀሚት ማጥራት ካልቻልኩ በእኔ ጉዳይ ላይ አቋም እንደሚወስዱ ነግረውኛል››

‹‹ምን አይነት አቋም››

‹‹ይመስለኛል..እጩ መቀየር የሚችሉት እስከዚህ ወር መጨረሻ ድረስ ነው፡፡እዚህ ከተማ ላይ በተቃዋሚዎች መሸነፍ አይፈልጉም ..ስለዚህ በሌላ እጩ ሊተኩኝ እያሰቡ ይመስለኛል፡፡››

‹‹ወይ ነዶ..ያን ሁሉ ብር ከስክሰን እንደዚህ ጉድ እንሁን…የክልል ወዳጆቻችንም ለእኔ ደጋግመው እየደወሉልኝ ነው፡፡ልጅቷን መያዝ ካልቻላችሁ እኛ እናግዛችሁ እያሉ ነው፡፡››

‹‹እንዴት አድርገው ነው የሚያግዙን››ጁኒዬር ጠየቀ፡፡

‹‹በአካባቢው ያሉትን የከተማ የፀጥታ አካላት በማነጋገር ፍላጋው ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ ነዋ››

‹‹ታዲያ አሪፍ እድል አይደል?››

‹‹አሪፍ እድል ነው..ግን ደግሞ እገዛቸውን አልተቀበልኩም››

‹‹ለምን?››

‹‹ምክንያቱም እሷን በማደኑ ላይ የመንግስት የፀጥታ አካላት ከገቡበት ድንገት ባልታሰበ ሁኔታ ልትጎዳ ትችላለች…ያንን ሪስክ መውሰድ አልችልም››

‹‹አባዬ..እዚህች ልጅ ላይ የምታሳየው የርህራሄ ስሜት ከእለት ወደእለት እያስደመመኝ ነው፡፡የተለየ ምክንያት አለህ እንዴ?››
51👍7😁1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
እሷ እንደጠረጠረችው…ልክ ግቢዋን ከፍታ እንደገባች በተጠንቀቅ ሲጠብቃት የነበረው ኩማንደር ያስቀመጠው ሰው ወዲያው ነበር ያያት…ስልኩን አንስቶ ኩማንደሩ ጋር ለመደወል ያባከነው ደቂቃ አልነበረም….

ኩማንደሩ ስልኩ ሲደወልለት ዳኛው ቤት ቁጭ ብሎ ማድረግ ስለሚገባቸው አንዳንድ ነገሮች እየተወያዩ ነበር….

‹‹በቃ ታክሲ ያዝና ተከታተላት..ከእይታህ እንዳትሰወር…ያለህበት ድረስ እመጣለው››የሚል ትዕዛዝ ነገረውና ስልኩን ዘግቶ ለዳኛው አለም እንደተገኘች ሲነግራቸው ዳግመኛ እንደተወለዱ አይነት እፎይታ ነው የተሰማቸው…

‹‹.እንዲከተሏት አድርጌያለው…አሁን መሄድ አለብኝ….. ››አለና ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡

‹‹ለምን ሪስክ ትወስዳለህ..?ወዲያው እንዲይዞት ማድረግ ነበረብህ››ሲሉ አካሄዱ ላይ ያላቸውን ተቃውሟ አሰሙ፡፡

‹‹ይዘናትስ….?ምንም የሰራችው ወንጀል የለም እኮ…ዝም ብለን አንጠልጥለን ልናስራት አንችልም››

‹‹እስከዛሬ የምታስሯቸውን ሰዎች ሁሉ ወንጀል ሰርተው ነው?››ዳኛው ስትሰሩ የኖራችሁትን ማላውቅ መሰላችሁ የሚል ቃና ባለው ንግግር ታቃወሙ፡፡
‹‹ልጅቷ እኮ የዞኑ ምክትል አቃቢ ህግ የነበረች የህግ ባለሞያ ነች….ሌላ ሰው ላይ የምናደርገውን ሁሉ እሷ ላይ በቀላሉ ማድረግ አንችልም…በዛ ላይ መከተላችን…የትነው የምትሄደው…?አጋዥ አላት ወይስ ብቻዋን ነች?››የሚለውን ለማጥናት ይረዳናል….ምን
አልባት ከሌሎች ጠላቶቻችን ጋር ህብረት ፈጥራ የምትንቀሳቀስ ከሆነም እሷን ብቻ ነጥለን መያዝ ከምንም አያተርፈንም…..››

‹‹ጥሩ አስበሀል ..እንግዲያው እኔም አብሬህ መሆን ፈልጋለው….››

‹‹አረ በዚህ ምሽት ይቅርብህ…ባይሆን ሁኔታውን በየጊዜው እየደወልኩ አሳውቅሀለው…››

‹‹አረ እኔም ከእናንት ጋር እሄዳለው››

ፎቅ ላይ ሆና ንግግሯቸውን ስታዳምጥ የነበረችው ስርጉት የአለምን መገኘት ዜና ስትሰማ በደስታ ጃኬቷን ደርባ አምርራ የምትጠላትን ሴት መያዝ በቀጥታ በአይኗ ለመከታተል ዝግጁ ሆና ወደእነሱ ስትመጣ ተመለከተ…ብዙ ቢከራከራቸውም ሁለቱም ለመቅረት ፍላጎት ስላላሳዩ ምን አገባኝ በሚል መንፈስ አብረውት እንዲሄዱ ፈቀደላቸው፡፡በኩማንደሩ ሹፌርነት አባትና ልጅ ከኋላ ሆነው አለምን ለመከታል ወጡ ..አለምን የሚከታተላትን ታክሲ አዲሱ መነኸሪያ ካለፈ በኃላ ነበር የደረሱበት…ከዛ የአለምን መኪና ካሳያቸው በኃላ እሱ እንዲመለስ ነገረውና አነሱ የአለምን መኪና መከታተሉን ቀጠሉ..እሷ ቀጥታ ለዛ ምሽት ፈጣን በሚባል አነዳድ የቦሌን የአስፓልት መንገድ ይዛ እየነዳችው ነው፡፡

‹‹ልጅቷ ወደየት እየሄደች ነው?፡፡››ስርጉት ግራ በመጋባት ውስጥ ሆና ጠየቀች፡፡
‹‹ይመስለኛል…ግብረ አበሮቾ ጋር የምትገናኘው ከከተማው ውጭ ነው፡፡››አባቷ የመሰላቸውን ተናገሩ፡፡

‹‹አይመስለኝም››ኩማንደር ነው ተናጋሪው፡፡

‹‹ማለት…ምን አሰብክ?››

‹‹ትዝ ይላችኃላ እናቷ ኮፈሌ ዘመዶች ነበሯት…የአባቷም ዘመዶች እዛው ናቸው..እኛ በማናውቅበት መንገድ ከዘመዶቾ ጋር መገናኘት ጀምራ ነበር ማለት ነው..እና አሁን እነሱን ለማግኘት እየሄደች ያለ ይመስለኛል..››ሲል መላምቱን አስቀመጠ፡፡

‹‹እና ኮፈሌ ድረስ ልንከተላት ነው ማለት ነው?፡፡››

‹‹እንግዲህ ቀድሞውንም አትከተሉኝ ያልኩት ለዚህ ነው…እኔ እንኳን እዚህች ኮፈሌ ድረስ ይቅርና ሱማሌም ድረስ ከነዳችው ከመከተል ወደኃላ አልልም››ሲል ፍርጥም ያለ ውሳኔውን ነገራቸው፡፡
//

አለም መኪናዋን በፍጥነት እያበረረች እንኳን ደጋግማ አቶ ፍሰሀ ስልክ ላይ ከመደወል አልታቀበችም…ግን አሁንም ስልኩ ይጠራል እንጂ አይነሳም…‹‹ይሄ ማለት ሰውዬው ከባድ አደጋ ደርሶበታል ማለት ነው..?››ስትል አሰበችና ዝግንን አላት….በእሱ ላይ በሚደርስ አደጋ እንደዚህ አይነት ሽብር ውስጥ እገባለሁ ብላ አስባ አታውቅም ነበር….እርግጥ እንዲህ በድሎኛል ብላ አንድም ቀን አካላዊ ጉዳቱን ወይም ሞቱን ተመኝታለት አታውቅም
…ቢሆንም ደህንነቱ በዚህ መጠን እንዲህ ያሳስበኛል ብላም ግምቱ አልነበራትም፡፡እና የራሷ ሁኔታ በጣም ነው ያስገረማት፡፡

‹‹ፈጣሪ ሆይ እባክህ..ህይወቱን ጠብቃት››ከልቧ ፀለየች፡፡ለቤተሰቦቹ መሳወቅ እንዳለባት ትዝ ያላት ወደባሌ የሚያመራውን የአስፓልት መንገድ ለቃ ወደቀኝ በመታጠፋ ወደ  ሶሌ ደን የሚወስደውን ጥርጊያ መንገድ ከያዘች በኃላ ነበር፡፡የጂኒዬርን ቁጥር ፈለገችና ደወችለት፡፡

‹‹ሄሎ ጁኒዬር…. አለም ነኝ››

‹‹አለም ..ደህና ነሽ…?የት ነሽ….?እንዴት ነሽ?››የእሷን ድምፅ ሲሰማ የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፋበት፡፡ስልኩ ሲደወልለት ቤት ከእናቱ ጋር ሳሎን ቁጭ ብሎ እየተጫወተ ነበር፡፡እሷ ለእሱ መርበትበት ቁብም ሳትሰጥ ንግግሯን ቀጠለች‹‹ጂኒዬር ልብ ብለህ አድምጠኝ…ከ30 ደቂቃ በፊት ከአባትህ ጋር በስልክ እያወራሁ ነበር…መኪና እየነዳ ሳያስበው ከከተማ እንደወጣ እና ወደሶሌ ደን እየተቃረበ መሆኑንና ከአሁን በኃላ ስለመሸ ወደከተማ እንደማይመለስና ማረፊያ ጎጆ ስላለው እዛው እንደሚያድር እየነገረኝ ነበር፡፡›

‹‹አዎ እዛ አልፎ አልፎ የምናርፍበት ጎጆ አለን….››

‹‹እና..ምን መሰለህ?››

‹‹እያስደነገጥሺኝ ነው..ስለምን ነበር እያወራችሁ የነበረው?››

‹‹እሱ ምን ይሰራልሀል…ለማንኛውም ንግግራችንን ሳንጨርስ አውሬ ገባብኝ የሚል ድምፅ እና ከፈተኛ ፍንዳታ የመሰለ ነገር ሰማው..እና ስልኩ ተቋረጠ.. መልሼ ደጋግሜ ብደውል ስልኩ ይጠራል… አይነሳም..፡፡››

‹‹ወይኔ ፈጣሪ…ምን እያልሺኝ ነው?››አጠገቡ የነበረችው እናቱ ሳራ የልጇ ጭንቀት በእሷም ላይ ተጋብቶባት…ስሩ ቆማ ትንቆራጠጥ ጀመር፡፡.

‹‹ለምንኛውም አሁን ቦታው ላይ እየደረስኩ ነው.. እንዳገኘሁትና ሁኔታውን እንዳየው እደውልልሀለው…ምን አልባት አንብላንስ ያስፈልግ ይሆናል››ስልኩ ተቋረጠ
‹‹ምንድ ነው ልጄ..?ፍሰሀ ምን ሆነ?››ሳራ ጠየቀች፡፡

‹‹አባዬ አደጋ ደርሶበታል መሰለኝ..ሶሌ ያለው ደን ውስጥ ነው…መሄዴ ነው››

‹‹እኔም አብሬህ እሔዳለው››

‹‹እማዬ አንቺ እዚሁ ሆነሽ ጠብቂ….››

‹‹እሔደለው..አልኩህ እሔዳው›› አጉረጠረጠችበት፡፡ምንም አላለም…በክርክር ጊዜ ማባከን ስላልፈለገ ቀጥታ ወደሳሎኑ መውጫ መራመድ ጀመረ… እናቱም ከኃላው ተከተለችው… መኪና ውስጥ ገቡ ..ወደባሌ ጎባ የሚወስደውን የአስፓልት መንገድ ይዘው ወደ ሶሌ ጉዞ ጀመሩ
///
አቶ ፍሰሀ አውሬውን አድናለው ብሎ መሪውን ሲጠመዝ ሙሉ በሙሉ ከመንገዱ ወጥቶ በግራ በኩል ባለው ገደል መሰል ጉድጓድ ውስጥ ነበር ጎማው ተንሸራቷ የገባው…ከዛ ፍሬኑን ለመያዝ ቢሞክርም የመኪናዋን ፍጥነትም ሆነ ባላንስ መቆጣጠር አቅቶት አንድ ዙር ተገለበጠና አንድ የብሳና ዛፍ ተደግፎ ቆመ….ለአምስት ደቂቃ ራሱን አያውቅም ነበር፡፡ከገባበት መደንዘዝ ሲወጣ ወንበሩ ስር ተወሽቆ ነው ራሱን ያገኘው…እንደምንም ታግሎ ቀበቶውን ከአንገቱ አወጣና በራፍን በእግሮቹ ገፍቶ ለመክፈት ሞከር..ቀላል ስራ እልሆነለትም፡፡እግሮቹ  ምን  እንደነካቸው  ባያውቅም  የሚያሰበውን  ያህል  ጥንካሬ
37👍4
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
‹‹ጋሽ ፍሰሀ..አንተ ነህ…?››

‹‹አዎ አለም…እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?››አውሬው ካስደነገጠው በላይ የእሷ በዚህ ሰዓት እዚህ አካባቢ መገኘት አስደነገጠው፡፡

‹‹እንዴ ስልክ እያወራን ነበር እኮ የተቆረጠው….መኪናህ እንደተገለበጠች እርግጠኛ ስለነበርኩ ወዲያውኑ ወደእዚህ የመጣሁት…መኪናህን ቀድሜ ባገኛትም ውስጡ የለህም..ግን የሚንጠባጠበውን ደም እየተከተልኩ ደረስኩብህ››

‹‹ስሩ ደርሳ ደገፈችው››

‹‹አብሮሽ ማን አለ?››

‹‹አረ ማንም የለ….መንገድ ላይ ሆኜ ለጁኒዬር ደውዬለታለው..ይሄኔ እየመጡ ይሆናል፡››

‹‹ይገርማል..የሆነ ነገር ቢያጋጥምሽስ?››

‹‹ሀሳቤ ሁሉ ያንተን ደህንነት ማረጋገጥ ላይ ስለነበር እሱን አላሳብኩትም ነበር…እውነቱን ንገሪኝ ካልከኝ ግን አሁን በፍራቻ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡››

‹‹በጣም ነው ያስገረምሺኝ..አይዞሽ አሁን አምስት ደቂቃ ነው ደርሰናል….እንደውም እዛ መብራት ጭልጭል የሚልበት ቦታ ይታይሻል …?እዛ ነው ጎጆው…በአቅራቢያው የእኔ ሰራተኞች ቤትም አለ…››

‹‹ በአንድ እጇ ደግፋው በሌላ እጇ ደግሞ የስልኳን ባትሪ ከፊት ለፊት እያበራች ወደፊት በዝግታ መራመዳቸውን ቀጠሉ፡፡
አቶ ፍሰሀ ከአውሬው ጋር የነበረው መፋጠጥ አሁንም ከምናብ ሊደበዝዝ አልቻለም… ልቡ ለምን እንዲህ ከመጠን በላይ መታ? ጉዳዩ ምን ነበር? የዱር አውሬው በጣም አስፈርቶት ነው? አይደለም፡፡ እሱ ስለእነሱ አላሰበም። በህይወቱ የበለጠ አስፈሪ ነገሮችን አሳልፎ ያውቃል። ወዲያው ከኃላቸው እየተንሾካሾኩ የሚመጣ የእግር ኮቴ ሰሙ…መንገዱን ለቀቁና ጢሻውን ተከልለው ቆሙ..ሲጠጎቸው ማንነታቸውን በድምፅ ለዩ…‹‹ገመዶ››
ባትሪውን ሲያበራባት ፈጽሞ እዚህ አገኘዋለሁ ብሎ ያላሰበውን አቶ ፍሰሀን በአለም ተደግፋፎ ልክ እንደተወዳጅ ልጁ ስሩ ተሸጉጣ ሲያይ አይኑን ማመን አልቻለም፡፡

ሁሉም ተንደርድረው ከበቧቸው‹‹ጋሼ ምን እየተካሄደ ነው?››

‹‹አይዞችሁ አትደንግጡ… ተርፌለው››

‹‹ተርፌለው ማለት?››ኩማንደሩ በመገረም ጠየቀ፡፡

‹‹የመኪና አደጋ እንደደረሰብኝ ሰምታችሁ አይደለም እንዴ የመጣችሁት?››

‹‹አረ በፈጣሪ..ተርፍክ ታዲያ…?እኛ አልሰማንም..እሷን ከከተማ ስትወጣ አይተን ተከትለናት ነው የመጣናው…ከጠላቶቻችን ጋር ልትገናኝ መስሎን ነበር››

‹‹አይ እሷ እኔን ለማትረፍ ነው የመጣችው››

‹‹እንዴት ከእኛ ቀድማ ልትሰማ ቻለች?..ነው ወይስ በአደጋው ላይ የእሷ እጅ አለበት?››

‹‹እሱን ጎጆው ጋር  ደርሰን ትንሽ ካረፈ በኃላ ብትጠይቀው አይሻልም?››አለችው አለም በንዴት፡፡

‹‹ለምን ወደጎጆ እንሄዳለን? መኪናችንን እኮ በቅርብ ርቀት ላይ ነው ያቆምናት..እዚሁ ጠብቁኝና ይዣት ልምጣ..ቀጥታ ወደከተማ ሄደህ ህክምና ማግኘት አለብህ››

‹‹አይ ደህና ነኝ..አሁን ማረፍ ነው የምፈለገው..ወደጎጆ ውሰዱኝ››

‹‹ተው  እንጂ  ፍሰሀ  ..ሀኪም  ሊያይህ  ይገባል››ዳኛው  ጣልቃ  ገብተው  ለኩማንደሩ ድጋፋቸውን ሰጡ፡፡

‹‹የበለጠ  እያደከማችሁኝ  መሆኑን  ልብ  አላላችሁም  እንዴ..?ወደጎጆ  መሄድ  ነው የምፈልገው›› በማለት የማይቀየር አቋማቸውን አሰሙ፡፡

‹‹ይቅርታ ጋሼ..አንተ ካልክ እሺ ወደጎጆ እንወስድሀለን….እነ ጁኒዬርም አሁን ደውለውልኝ ነበር …መገንጠያው ጋር ደርሰዋል….ከደቂቃዎች በኃላ ይደርሳሉ..››አለና ሄዶ በሌላ ጎኑ አቶ ፍሰሀን ደገፈ….ከ5 ደቂቃ በኃላ ጎጆዋ ደረሱ፡፡ፋኖስ አበሩ፣ መኝታው ተስተካክሎ እንዲተኛ ተደረገና በቅርብ ርቀት ያሉ ሌላ የሳር ቤት ውስጥ ወደሚኖሩት የእነሱ ሰራተኞች ተቀስቅሰው መጡ..እሳት እንዲቃጣጠል ተደረገ…ጁኒዬርና ሳራ የመጀመሪያ ለእረዳታ መስጫ የሚያለግሉ ቁሳቁሶች ይዘው እያለከለኩ ደረሱ…ለተወሰነ ጊዜ ለቅሶና ግርግር በጠባቧ ጎጆ ነገሰ..ከዛ ቀስ በቀስ ወደመረጋጋት ቢመጣም በሰው ብዛት በታፈነችው ጎጆ ውጥረትና ጭንቀት ነግሶ ነበር፡፡

‹‹ቆይ እኔ ያልገባኝ…ምንድነው የሚያስጠብቀን..?ለምንድነው ወደከተማ ይዘነው ሔደን ሀኪማ የማያየው?››ሳራ ነች ግራ በመጋባት ተመሳሳይ አይነት ጥያቄ ለሶስተኛ ጊዜ ያነሳችው፡፡

‹‹ጋሼ አልፈልግም ስላለ እኮ ነው…ጋሼ አሁን ትንሽ አርፈሀል፣ብንሄድ ምን ይመስልሀል?››ኩማንደር ነው ተናጋሪው፡፡

‹‹አይ ዛሬ ማንም ከዚህ አይሄድም…አሁን ሰዎቹን ሸኞቸውና የምንነጋገረው ነገር አለ››ሲል ሁሉም በቀጣይ ምን ሊፈጠር ነው በሚል እርስ በርስ ተያዩ፡፡

ጁኒዬር ከጎረቤት ጎጆ የመጡትን ባልና ሚስቶች ከነልጆቻቸው አመስግኖ ወደቤታቸው እንዲሄዱ ካደረገ በኃላ የጎጆዋ ቤት ተዘጋ፡፡አሁን ስድስት ሰዎች ፊት ለፊት ተፋጠጡ …ሁለቱ ሴቶች እና አዛውንቱ ዳኛ አቶ ፍሰሀ ጎን የተቀመጠችውን አለምን በከፍተኛ ጥላቻን መጠየፍ ነበር የሚመለከቷት፡፡

አቶ ፍሰሀ ከትራሱ ቀና አደረገና አስተካክሎ በመደገፍ መናገር ጀመረ‹‹ዛሬ እየሆነ ያለው ሁሉ ነገር ተአምር ነው…እኔ እቅዴ እንደማንኛውም ቀን ስራ ውዬ ወደቤቴ መግባት ነበር….ነገር ግን የሰሞኑን ውጣ ውረድ እያሰላሰልኩ ሳላስበው ከከተማ ወጣሁና እራሴን እዚህ ሶሌ ደን አካባቢ አገኘሁት..እንዴት እዚህ ልደርስ ቻልኩ? ብዬ እየተገረምኩ ሳለ ያልጠበቅኳት አለም ደወለችልኝ..ከእሷ ጋር እያወራው ሳለ ድንገት ሳላስበው አውሬ ገባብኝና እሱን አድናለው ስል መኪናዬ መንገድ ስታ ተገለበጥኩ…እንደአደጋው መሞት ነበረብኝ..ግን ከተወሰነ ጭረት በስተቀር ምንም አልሆንኩም…እግዜር አሳይቶ ከሞት ደጃፍ መለሰኝ..ከመኪናው ወጥቼ በጫካው እያሳበርኩ ወደእዚህ እየመጣው ሳለ ከጅብ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጥኩ…እሱንም ወደሰማይ ተኩሼ አስበረገግኩትና ሁለተኛውን ፈተና አለፍኩ..ከዛ ወዲያው አለምን ከፊት ለፊቴ አገኘኃት..ወዲያው እነ ገመዶና መጡ…ጎጆው እንደደረስን ደግሞ ልጄና ባለቤቴ መጡ …እኔ ለማናችሁም አደጋ ደረሰብኝ ብዬ አልደወልኩም..በአደጋው ጊዜ ስልኬ ወደየት እንደጠፋም አላውቅም..ግን ሁላችሁም እዚህ ተገኝታችኃላ..ሁላችንን እዚህ ያለነው ለምክንያት ነው፡፡ከአለም ጋር የጀመርነው ድብብቆሽ እዚህ ጋ ማብቃት መቻል አለበት፡፡

‹‹አዎ ማብቃት አለበት …ይህቼ ሴት ከዚህ በፊት ንብረቴ እንዲቃጠል አደረገች… ዛሬ ባለቤቴን ገድላብኝ ነበር….››ሳራ ተንዘረዘረች…ዳኛውና ስርጉት አይናቸውን በማጉረጥረጥ እና በመገላመጥ ለሳራ ያላቸውን እገዛ አሳዩ ፡፡

‹‹ሳራ ተይ ..ዛሬ የምንበሳጭበትና ራሳችንን ሀጥያት ለመሸፈን ሌላ ስው በሀሰት የምንወቅስበት ቀን አይደለም..እኔ አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሁለት ሞት ነው የዳንኩት…ይሄ ያለምክንያት አይደለም..ይህቺን ልጅ ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በድለናታል…ሁላችንም ለእሷ መናዘዝ መቻል አለብን..እውነቱን ልንነግራት ይገባል..ከዛ አመዛዝና ከፈለገች ትበቀለን… ከፈለገች ደግሞ ወደፍትህ አደባባይ ወስዳ ታሰቅለን፡፡

የአቶ ፍሰሀን ንግግር የሰሙት ዳኛው ጫንቃቸውን አላባቸው፡፡ይሄ ሰውዬ በተገበጠበት ወቅት ጭንቅላቱን ተመቶ ማሰቢያው ላልቶ ይሆን እንዴ?››ሲል አሰበና አይኑን ገመዶና ጁኒዬር ላይ አንከራተተ…የሆነ ነገር ብለው የጀመረውን ቅዠት የመሰል ድርጊት እንዲያስቆሙት ነው ፍላጎቱ.
45👍4
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
‹‹ልጄ አንተ እንዲሁ ሰበብ ሆናብህ እንጂ ሰሎሜን የገደልካት አንተ አይደለህም››

‹‹እማዬ አሁን በቃሽ …ባበቃለት ጉዳይ ላይ ምንም ለውጥ ላታመጪ አትድከሚ››

‹‹አይደለም..ሰሎሜን የገደልናለት እኔና ስርጉት ተባብረን ነው.››ስርጉት በተቀመጠችበት ሆና አቃሰተች….ዳኛው መተንፈስ ከበዳቸው፡፡ሳራ ግን ለማናቸውም ግድ አልነበራትም..የእሷ ዋናው ትኩረት ልጇን ከእስር ማዳን ብቻ ነው..እና ንግግሯን ቀጠለች፡፡

‹‹.የዛን ቀን አንተ እኛን ወደቤታችን ከመሸኘትህ በፊት መጠጧ ውስጥ መድሀኒት ጨምረንባት ነበር..ከ30 ደቂቃ በኃላ እንደማሳበድ አድርጓት በአንድ ሰአት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚገድላት መድሀኒት ነበር፡፡እሷ  የተቀየረችብህና ከመስታወት ላይ ግንባሮሯን የከሰከሰችው በመድሀኒቱ ተጽዕኖ ነው…መስታወቱ ሆዷ ውስጥ ቢሻጥ እንኳን  አልሞተችም ነበር…አባትህ መጥቶ ሀኪም ቤት ሊወስዳት መኪናው ውስጥ አስገብቶ መንገድ ከጀመረች በኃላ ነው እስትንፋሷ የተቋረጠው…ያም የሆነው በተወጋችው ውግ ወይም በፈሰሳት ደም ሳይሆን በጠጣችው መርዝ ምክንያት ነው፡፡

‹‹እማዬ ይሄን እንዴት እሰከዛሬ ሳላውቅ…?አባዬ አንተ እንዲህ መሆኑን ታውቃለህ?››ሲል አባቱ ላይ አፈጠጠበት፡፡
አቀርቅሮ የነበረው አቶ ፍሰሀ በከፊል ቀና አለና ‹‹ከአንተ እና ከአለም በስተቀር ይሄንን ጉዳይ እዚህ ቤት ያለው ሁሉም ሰው ያውቃል፡፡››ሲል እውነቱን ፍርጥም ብሎ መለሰለት፡፡

‹‹ምን አረገቻችሁ ቆይ …?ምናችሁ ላይ ደረሰች?››አለም በእንባ ታጥባ እየነፈረቀች ሳራ ላይ አፈጠጠችባት፡፡

ሳራ እሷን ችላ ብላ ወደልጇ እየተመለከተች‹‹አንተን እንዳታገባህ እና ከስርህ እንድትርቅ ለአመታት ለመናት.. አስጠነቀቅናት፤ እሷ ግን ሌላ ሰው አግብታ ወልዳ እንኳን ልትተውህ አልቻለችም…የልጄ ህይወት በእንደዛ አይነት ሁኔታ ሲበላሽ ቆሜ ማየት አልቻልኩም፡፡እኔ ስርጉትን እንድታገባ ነበር ምፈልገው፣ከልቧ በጣም የሚታፈቅርህ ሰሎሜ ሳትሆን ስርጉት እንደሆነች በደምብ አውቃለው..››
ወዲያው ሳራ ንግግሯን እንዳገባደደች ኩማንደር ተቀበላት‹‹ያው እንግዲህ መጠኑ ይለያይ እንጂ በእናትሽ ግድያ ሁላችንን የየድርሻችንን ተወጥተናል…እኔ በእለቱ እስከእራት ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር አብሬቸው የቆየሁት…ከለሊቱ ዘጠንኝ ሰዓት ጋሽ ፍሰሀ ደወለልኝ.. ስመጣ
…እናትሽ ጋሼ መኪናው ውስጥ እጥፍጥፍ ብላና በደም ተበክላ ነበር…ጋሼ የሆነውን በአጭሩ አስረዳኝና የሚሆነውን እንዳደርግ ሀላፊነቱን ለእኔ ሰጠኝ ….ነገሩ ወደህግ ከሄደ ጁኒዬር፤ሳራም ሆነች ስርጉት ዘብጥያ መውረዳቸው አይቀርም …ምን ማድረግ እንዳለብኝ ሳስብ ያ ሊቁ የተባለው እብድ በዛ ውድቅት ለሊት እየለፈለፍ በእርባታ ድርጅቱ ፊት ለፊት ባለው መንገድ ሲያልፍ አየሁት..ወዲያው ሀሳብ ብልጭ አለልኝ..ሮጥኩና ይዤው ወደውስጥ ገባው..ከማታ እራት የተረፈ ምግብና መጠጥ ስለነበረ እሱን ሰጠሁትና ስለማደርገው ነገር መዘጋጀት ጀመርኩ..የምጠቀምበት እቃ ስፈልግ የእንስሳት ዶክተሩ የህክምና ቁሳቁስ የሚይዝበትን ሳጥን በረንዳ ላይ ተቀምጦ ነበር፤አይኔ ውስጥ ገባ፣ ቶሎ አልኩና ከፈትኩት ፡፡ የቀዶ ህክምን ሚገለገሉበትን ቢላዋ አገኘሁና .. በወቅቱ በጣም ተደናግጬ ስለነበረ የማደርገውን ሁሉ የማደርገው በደመነፍስ ነበር….እና ያው ልጅ እንደገደላት እንዲመስል አደረኩና ጥዋት ለፖሊስ ተደወለ.. በኃላ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተጓዙ ሳለ አያትሽ ልጄን የገደላት እብዱ ሳይሆን እነሱ ናቸው… የሚል ወሬ መንዛት እና
አቤቱታ ማሰማት ጀመሩ…ከዛ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሰዎች ዘንድ አንዳንድ ጥርጣሬዎች ብልጭ ማለት ጀመሩ..ሬሳው በደንብ ይመርመር የሚል ግሩፕ ተነሳ…ከዛ ከጋሼ ጋር ተማከርንና የሆስፒታሉ የሬሳ ማስቀመጫ ክፍል እሳት እንዲነሳና እሬሳውም እንዲቃጠል አደረግን..በስተመጨረሻም አያትሽን ይሄንን ሀገር ለቀው ካልሄዱ አንቺን ነጥቀን እስከወዲያኛው እንዳያገኙሽ እንደምናደርግ አስፈራርተናቸው ዝም እንዲሉና ከተማውንም ለቀው እንዲሄዱ አደረግን…እናም በተጨማሪ ስለእናትሽ አሟሟት ሊነግርሽ ነበረውን ሙስጠፋንም የገደልኩት እኔ ነኝ!!የዛን ቀን እኛ ሳናየው እዛ ተደብቆ እያንዳንዱን ነገር ሲያይ ነበር….ይሄን ሁሉ ነገር ግን ፍርድ ቤት ቀርቦ ያምንልኛል ብለሽ እንዳትጠብቂ…››ሲል ንግግሩን አገባደደ፡፡

አለም ደም በለበሱ አስፈሪ አይኖቾን ኩማንደሩ ላይ አፍጥጣ‹‹ቆይ ቆይ እስኪ…ልጁ የገደላት ለማስመሰል ከሞተች በኃላ በዛ የቀዶ ጥገና ቢላዋ ደጋግመህ ወጋሀት አይደል?
…?ከዛ ደሟ ሲንፎለፎል በእጅህ እየዘቅክ እዛ ሚስኪን ልጅ ልብስ ላይ አዳረስከው …እንዳዛ አይደል ያደረከው?በቁሟ እያለች በፍቅር ልብህን ስለሰበራች ልትበቀላት ታስብ ነበር፣ግን ለማድረግ ወኔ አልነበረህም..በዛን ወቅት ግን አጋጣሚው ተመቻቸልህ..ነፍሷ ውስጧ ባይኖርም ደጋግመህ ሰጋዋን በመበሳሳት ንዴትህን ተወጣህባት….ከዛ ሬሳዋ ለምርመራ ሆስፒታል ገባ ..አንዳንድ ጥርጣሬ የሚያስነሱ ነገሮች መፈጠር ሲጀምሩ እራሳችሁን ከማንኛውም አደጋ ጥርጣሬ ለመጠበቅ አስፈላጊ ስለነበረ ጋሼ ፍሰሀ ደግሞ የሆስፒታሉ የሆነ ክፍል በእሳት እንዲያያዝ እና ሬሳዋም እንዲቃጠል እና አመድ እንዲሆነ አደረገ..ከዛ አቶ ዳኛ በዚህ ወንጀል ውስጥ ልጁ ስላለችበት ይህንን ወንጀል እንዳይጋለጥ ባለህ ስልጣን ሁሉ ተጠቅመህ ፋይሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲዘጋ አደረክ…፡፡በትክክል ተረድቼችኋለው አይደል..?እንዲህ ነው ያደረጋችሁት?
‹‹ሁሉም በመሸማቀቅ አንገታቸውን አቀርቅረው ነበር የሚሰሟት‹‹እስከአሁን እንደሰማሁት ከሆነ እኮ ጁኒዬር ብቻ አይደለም ራሱን ለህግ አሳልፎ መስጠት ያለበት …ሁላችሁም ናችሁ..እና እኔ ዳኛ ብሆን በጣም ትንሹን ፍርድ የምፈርደው በእሱ ላይ ነው….እሱ ሳያስበው…በድንገተኛ አደጋ የፈጠረው ወንጀል ነው…ሌለቻችሁ ግን አስባችሁ እና አቅድ አውጥታችሁ ደግማችሁ ደጋግማችሁ እናቴን በነፍስም በስጋም አጥፍታችኃታል….እና ነገ ወደከተማ ስንመለስ ምን እንደምታደርጉ ለማየት በጣም ጎጉቼለው….፡፡››

‹‹መቼስ ሁላችንም ሳታጠፊን እንቅልፍ አይወስድሽም አይደል…?ደስ ይበልሽ ይሄው ተሳካልሽ››አሉ ዳኛው ቅስማቸው ስብርብር ብሎ፡፡

‹‹ደስ ይበልሽ !!….ጭራሽ ደስ ይበልሽ…?.ፍርድን በአደባባይ ሲሸጦት ያዛን ጊዜ ማሰብ ነበረቦት››

‹‹አይ መሬት ያለ ሰው….በእኔ ላይ የደረሰውን ወላጅ ስትሆኚ ነው የምታውቂው….ልጄን ከእስርና ከእንግልት ለማዳን ስል ነው እዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ የገባሁት››

‹‹አይ ልጆትን ከእስር ለማትረፍ ብቻ አይደለም….ከሶሌ ኢንተርፕራይዝም የ10 ፐርሰንት የአክሲዬን ድርሻ በልጆት ስም ማግኘት ችለዋል፡፡››

‹‹ይህ ፍፁም እውነት አይደለም…ያንን አክሲዬን የገዛሁት በራሴ ብር ነው….ከወላጆቼ በውርስ ያገኘሁትን ንብረት በጠቅላላ ሸጬ ነው የገዛሁት…ያንንም ፈልጌው ሳይሆን ኩማንደሩ እና ፍሰሀ አስገድደውኝ ነው፡፡በልጄ አስፈራርተውኝ ነው››

ዳኛው የሚናገሩትን ባለማመን ቀና አለችና ኩማንደሩ ላይ አፈጠጠችበት፡፡
‹‹አዎ..እውነቱን ነው፡፡ይሄንን ወንጀል ዛላለም በመሀከላችን እንደተቀበረ እንዲቆይ እርስ በርስ የበለጠ መተሳሰር አለብን ብለን አሰብን…ከዛ ከጁኒዬር እና ከሳራ ድርሻ ላይ ተቀንሶ በስርጉት ስም አክሲዬን እንዲገዙ አደረግን….ባይሆን እኔ ቀጥታ ጠይቄ ባይሆንም ከእናትሽ ሞት በኃላ የአክሲዬን ድርሻዬ ወደ30 ፐርሰንት እንዲያድግ ሆኗል….››
46👍5😱2