#ሴት_እና_የነገር_ቱባ
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
፡
ቁርሳችንን ለኮፍ ለኮፍ አድርገን ለመውጣት እየተጣደፍን ነው ያለ ቅጥ ረፍዶብናል፡፡
“ብርድ ነው ፀሐይ..? እስቲ ውጣና ዕይልኝ!” አልኩት፡፡ “ሹራብ ልልበስ ሸሚዝ?” በሚል ከተመሣቀለው ቁምሣጥን ልብስ ለመምረጥ
እየተጣደፍኩ፡፡
በቁሙ፧ በግማሽ ልብ ቴሌቪዥን እያየ የሚጠብቀኝ ባሌ፣ መልስ አልሰጠኝም፡
“በረከት!” አልኩት እየጮኽኩ፡፡
“ወ.. ይ...” አለና ከሲ ኤን ኤንዋ ዜና አንባቢ ዐይነን አንስቶ እኔ
ላይ አሳረፈ፡፡
“አትሰማኝም እንዴ?”
“አልሰማሁም...ምን አልሽኝ....?”
“ወይ ጉዴ...! ብርድ ነው ፀሐይ... ውጣና ዕይልኝ... ልብስ እንድመርጥ...”
“ወይ ቆንጂት!... ገና አልለበስሽም እንዴ... ቶሎ ቶሎ በይ እንጂ አለኝ እንደ ነገሩ እያየኝ፡፡
“ወየው.... ከላይ ብቻ ነው የቀረኝ... ዕይልኝ ይልቅ....”
ተበሳጭቻለሁ፡፡
በግብር ይውጣ አካሄድ ወጣና መለስ ብሎ፣ “ደመና ነው... ሹራብ
ያዢ!” አለኝ፡፡
ይሄን ጊዜ ! ከሱሪዬ ጋር የሚሄድ ሹራብ ፍለጋ ቁምሳጥኔን ማተራመስ ጀመርኩ፡፡
“እረ ቆንጂት በፈጠረሽ እንውጣ...! ይቺ ዐሥር ደቂቃ ካለፈች
ታውቂያለሽ የታክሲ ሰልፉ መከራ ነው” አለኝ ቴሌቪዥኑን እያጠፋ፡፡
ሹራብ ፍለጋዬን አቆምኩና ዞር ብዬ ዐየሁት፡፡
ደግሞ ልንጨቃጨቅ ነው፡፡
አሁን አሁን ከምንም ነገር በላይ አብዝተን የምናደርገው ነገር፣
መጨቃጨቅ ነው፡፡
ስለ አለባበሴ እንጨቀጨቃሰን፡፡
ስለ ከጓደኞቹ ጋር ማምሸቱ እንጨቃጨቃለን፡፡
ስለ ገንዘብ አያያዜ እንጨቃጨቃለን፡፡
ስለ ልጆቻችን ጠባይ እንጨቃጨቃለን፡፡
ፐ
ስለ እናቱ እኔን አለመውደድ ጉዳይ እንጨቃጨቃለን፡፡
ስለኔ ታናሽ ወንድም መበላሸት እንጨቃጨቃለን፡፡
ስለምንም ነገር እንጨቃጨቃለን፡፡
ሹራብ ነው የቀረኝ... ታገሰኝ..." ኣልኩት፤ “ዋ ሌላ ነገር ተናገረኝና
ጉድ ይፈላል” በሚል ዓይነት ድምፅ፡፡
ግን ሌላ ነገር ተናገረኝ፡፡
“ስንት ሰዐት እታገስሻለሁ....? ልብስ ለመልበስ አንድ ሰዓት ሊያውም እንዲህ እረፍዶ?”
አሁን በደንብ ልንጨቃጨቅ ነው፡፡
በኔ በረፈደ ሰዐት ላይ ልብስ ለመልበስ መቆየት መነሻነት የተጀመረው ጭቅጭቅ መዳረሻው የት እንደሆነ አላውቅም..
ጭቅጭቃችን የራሱ ቦይ አለው፡፡ ራሱ እየቀደደ የሚፈስበት ቦይ::
ከቀበና ወንዝ ተነስቶ ሜዲትራኒያን የሚገባበት የራሱ ረጅ....ም....ቦይ፡፡
“አንድ ሰዐት አልፈጀብኝም! አታጋንን፤ ማጋነን ስትወድ "አልኩት፣ ሰማያዊውን ሹራቤን አውጥቼ እየለበስኩ፡፡
“እኔው ነኝ አጋናኙ...?” አለኝ ደክሞት ውሎ እንደመጣ ሰው ሶፋው ላይ ተመልሶ እየተቀመጠ፡፡
“ምን ማለት ነው እኔው ነኝ አጋናኙ..? አንቺ ታጋንኛለሽ ለማለት ነው...?” አልኩት ገንፈል ብዬ፡፡
ዝም አለ፡፡
በአሸናፊነት መንፈስ ሹራቤን ለብሼ የቁምሳጥኑ መስታወት ጋር
ሄጄ ከሱሪዬ ጋር ያለውን ቅንጅት አየሁ፡፡
አያምርም፡፡
ሮዙን ሹራብ ባደርግ ይሻለኛል፡፡
ሰማያዊውን ሹራብ አውልቄ አልጋ ላይ ጣልኩና ሮዙን ሹራብ መፈለግ ስጀምር የሆነ ነገር ሲል ሰማሁት፡፡
“ምን አልክ?”
“ምንም አላልኩም ቆንጂት ”
“ለምን ምንም አላልኩም ትላለህ ...? የሆነ ነገር ስትል
አልሰማሁህም አሁን...?” ወደ ሳሎን መጥቼ አፈጠጥኩበት፡፡
“ምንም አላልኩም.... ....... በይ ይልቅ ፤ ትናንት ብፈልገው አጣሁት... የእዚህ ሪሞት አንዱ ባትሪ የት ገባ...? ወድቆ ጠፍቷል” አለኝ፣ መክደኛ የሌለውን የቴሌቪዥናችንን ሪሞት ኮንትሮል
አገላብጦ እያየ፡፡
“ምን እኔን ትጠይቀኛለህ... አንተ ነህ ተሰክተህበት የምትውልበት
ቲቪውን፤ ...ራስህ አትፈልገውም...?” ሹራቤን ፍለጋ እየተመለስኩ መለስኩ፡፡
“እኔ የት እንዳለ ባውቅ አንቺን ምን አስጠየቀኝ?”
“እንጃ! ምናልባት ለሁሉ ነገር ጥፋተኛ የምታደርገው እኔን ስለሆነ”
“ለሁሉ ነገር?”
አዎ! ....ቲቪ ተበላሸ... ቆንጂት ምን አረግሽው...? የቤቱ ግድግዳ
ለቀቀ ፤ ቆንጂት ምን ስትሰሪ እንዲህ ሆነ..? የልጆቹ ፀባይ ተበላሽ
ቆንጂት አንቺ እኮ ነሽ እያቀበጥሻቸው...? አሁን ደግሞ ሚጢጢ ባትሪ ጠፋ እኔኑ ጥፋተኛ...”
ሳላሰበው ሁለመናዬ ሲግል እየተሰማኝ ተናገርኩ፡፡
“በ...ይ ተይው እገዛለሁ... ሆሆ!” ብሎ ሪሞት ኮንትሮሉን ጠረጴዛው ላይ ሲወረውር ተሰማኝ፡፡
ግዛ አንተ ምን አለብህ...! ሽሮ በርበሬ ብዬ የምሣቀቀው እኔ...
አንተማ መዥረጥ አድርገህ ያሻህን ትገዛለህ..." አልኩ።ግለቴ ሳይበርድ፤ ሮዙን ሹራብ እያደረግኩ፡፡
“ታዲያ ከጠፋ ምን አድርግ ትይኛለሽ...? ደሞ ለባትሪ...”
“ደሞ ለዚች እያልክ ነው ገንዘብ የምታባክነው፡፡ ገንዘብ በትንሹ
ካልተቆጠበ ብዙ ይሆናል...?”
“ደሞ አሁን ገንዘብ አባካኝ ሆንኩ..!.”
ድምፁ ይንቀጠቀጣል፡፡ ድምፁ ከተንቀጠቀጠ ተናዷል ማለት ነው፡፡
“አይ ቆጠብክልኝ እንጂ! ቆጠብክልኝ የኔ ጌታ! ይሄ በየማታው የምትጋተው ድራፍት እንኳን ቢደማመር የልጆቹን አስጠኚ የወር ደሞዝ ቀጥ አድርጎ አይችልም....?” አልኩት ድምጼን ከፍ አድርጌ ፤ ወገቤን በነገረኛ ሴት ቄንጥ ይዤ ወደ ሳሎን እየተመለስኩ፡፡
ፊቱ ቀልቷል፡፡
“በየማታው...? እኔ ነኝ በየማታው ድራፍት የምጋተው....? ከቅዳሜ
ውጪ ...ሊያውም ከሁለት ድራፍት በላይ ስጠጣ አይተሸኛል....?
ደሞ ለነገሩስ ለልጆቹ አስጠኚ ይቀጠር ስልሽ... ተወው ፤ ማቲ እየመጣ እንደፈለጋቸው ያስጠናቸዋል' ብለሽ አይደለም የተውነው እንዴ!”
እሱማ ነበር! ....የሚሆን መስሎኝ፡፡ ገንዘብም እንዲቆጠብ ብዬ .. ግን
ምስኪን ወንድሜን በሳምንት ሦስቱ ለሚመጣው እየገላመጥክ
ከቤቴ አራቅከው... አሁን እስቲ ምን አደረገህ ...? ልጆችህን በነጻ ባስጠናልህ...”
አሁን ቅድም እንደ ዋዛ የጣልኩትን የአንገት ልብሴን እየፈለግኩ
ነው፡፡
“ተይ ቆንጂት ግፍ አትናገሪ፡፡ እኔ ነኝ ወንድምሽን ከዚህ ቤት
ያራቅኩት? ራሱ አይደለም፣ ልጆቹ ማቲ ሲጋራ ሲያጨስ እያዩ እንዳይሰላሹ ምከሪው' ስልሽ ሰምቶ እዚህ ቤት አልመጣም ያለው...? እሱ ዱርዬ በሆነው ለልጆቼ ማሰቤ ነው እኔን
የሚያስወቅሰኝ!”
አሁን በማቲ መጣብኝ፡፡ የማቲ ነገር እንደማይሆንልኝ እያወቀ በጠዋቱ በማቲ መጣብኝ፡፡
“በረከት! ማቲ ዱርዬ አልሆነም... ወጣት ነው….. ሊሳሳት ይችላል...
እንደ ታላቅ ወንድም ልትመክረው ሲገባ እንደ እብድ ውሻ ከገዛ እህቱ ቤት አባረርከው... ይሄ ልክ ነው?” አልኩት የአንገት ልብሴን ፍለጋ ትቼ እያየሁት፡፡
“እህ... ተይው... አንቺ ልጄ..... ታክሲው... ይልቅ በናትሽ ለብሰሽ
ጨርሺ አሁን... እንሂድ፡፡” አሁንም ያንን ሪሞት ኮንትሮል እያገላበጠ ያያል፡፡
እንዲህ በነገር እየለበለብከኝ ምኑን ከምኑ አድርጌ ልልበስ.
ስካርፌ ጠፋብኝ” አልኩት ቀዝቀዝ ብዬ፡፡
“ራስሽ በጀመርሽው ነገር መልሰሽ እኔን... ይልቅ አሁን ጨረስሽ..
እንውጣ?” አለኝ ቦርሳውን እንስቶ እያነገተ፤
“ምነው ስታየኝ ያልጨረስኩ እመስላለሁ....?”
ያለ እቅዱ ነገረኛ ድምፄ ተመለሰ፡፡
“ደሞ ይሄ ምን ማለት ነው?”
“የለበስኩ አልመሰልኩም?... ለነገሩ ስታየኝ አይደል የምታውቀው በጠዋት
ቲቪ ላይ እያፈጠጠክ... ሦስተኛ ጡት አብቅዬ ባድርም እስከ ሁለት ወር የሚታይህ አይመስለኝም”
ሣቀ፡፡
እኔ ግን አልሣቅኩም፡፡ እየተጨቃጨቅን ሲስቅ ያናድደኛል።
“ሶስተኛ ጡት...? ምን?” አለኝ አሁንም እየሣቀ፡፡

👍1
ሣቅ አንተ ምን አለብህ! ...እኔ ነኝ የማውቀው... እኔን ማየት ከተውክ እኮ ቆየህ አንተ”
“ቆንጂት.. እንዴት ነው ደሞ ማየት...?”
“ማየት ነዋ ! እንደ ድሮው... እንደ ወንድ፡፡ አይ ወንድ... “ማታ ልሙትልሽ ጠዋት ልግደልሽ አለች ያቺ ዘፋኝ.... ሰለቸሁህ ...በረከት አታየኝም!” ሆድ እየባሰኝ ተናገርኩ፡፡
“ዐይሻለሁ... አሁን እያየሁሽ ኣይደለም?” አለኝ፣ እንደታዘዘ ከላይ
እስከታች በዐይኑ ከከተተኝ በኋላ።
“ድንቄም ማየት እቴ!... እንዴት ነኝ አሁን? ዕየኝ እስቲ... 360ኛ እየተሽከረከርኩ ጠየቅኩት፡፡
ምንም ሳይል እንደገና ዐየኝና ፤
“እ... የላዩ ጥሩ ነው ፀሐይ ወጥቶ በጣም ካልሞቀሽ... ግን ይሄ...
እ... እንይ...! ይሄ የእህትሽ ሱሪ አይደለም እንዴ...?” ከወገቤ በታች በታላቅ አትኩሮት እያየኝ ጠየቀኝ፡፡
እንደ አዲስ ተበሳጨሁ፡፡
“ወይ ጉድ! ይሄ ታየህ?”
“ምነው... ልክ አይደለሁ..?”
ደንግጧል፡፡
“ልክ ነህ አባቴl.ልክ ነህ የኔ ጌታl... የኔ አስተዋይ" አልኩ አሸየጮኹ፡፡
“እህ... ትንሽ ጠቦሻል መሰለኝ...."
ንግግሬ የስላቅ መሆኑ የገባው አልመሰለኝም፡፡
በጣም ፤ በጣም ፤ በጣም ተናደድኩ፡፡
“ወፈርሽ ለማለት ማሽሞርህ ነው..?” አልኩት በቆመበት እየገላመጥኩት፤ እንደ ኳስ አንጥሬ ብለጋው እየተመኘሁ፡፡
“
እንደዛ ማለቴ አይደለም.... እሷ ቀጭን ስለሆነች የሷ ልብስ ላንቺ..”
ወይ ጉድ! ሰፍቷት ሰጥታኝ ነው አረ ቆይ! የትዕግስት መሆኑን በምን አወቅህ ግን...? ካለ አንድ ቀንም አርጋው አልመጣች እዚህ ቤት...” .
እንጃ ቀይ ስለሆነ ዓይኔ ገብቶ ይሆናል እንግዲህ ... እንሂድ እንጂ”
አላ ቦርሳውን እያስተካከለና ወደ በረንዳው እየተራመደ፡፡
ተከተልኩት፡፡
“ቀይ ስለሆነች ዐይኔ ገባች በል እንጂ..ባለጌ!” አልኩት፡፡
“ምን አልሽ...?” አለኝ፡፡
“ገብቶሃል”
“ኧረ ተይ ተይ! ጠምዝዘሽ ጠምዝዘሽ...”
“ምንድነው የምጠመዝዘው ...ፊት ለፊት እየተናገርክ...! ሌላ ነገር ካላሰብክ ...አሁን የእህቴን ሱሪ ምን አሳየህ!”
“...እኔን በእህትሽ...? በስማም... ዛሬስ የሰፈረብሽ ባለቀንዱ ነው...
እኔን በእህትሽ....? ሊያውም በታናሽ እህትሽ...?”
“ምነው... ታላቄ ነበር ያማረችህ...? ሮማንን ፈለግክ ደሞ!”
“በስመ አብ... ኧረ አንቺ ምነው ዛሬ!”
“ድሮም አውቀው ነበር ባክህ... አንሻፈህ ስታያት.... ባለጌ
ልክ ይሄን ስለው የተቋጠረ ምሳ እቃ ይዛ ወደ እኔ የምትመጣው
ሠራተኛችንን አይቼ የድምፄን ከፍ ማለት ሳስብ ደንገጥ አልኩ።
“አንቺ .....አሁንስ በዛ.. ጠነዛ... በጠዋቱ... በስመአብ! በይ እኔ
ልሂድ...”
ሂድ...የለመደብህን...ሂያጅ መሆንህንማ ዐውቃለሁ” አልኩ ድምጼን ለሱ እንዲደርስ ከፍ፣ ለሠራተኛዬ እንዳይደርስ ዝቅ አድርጌ፡፡
እኔ የምሳ እቃዩን በሌላ ኮተት ወደ ተሞላው ቦርሳዬ ለማስገባት
ስታገል ጥሎኝ ሄደ፡፡
ስወጣ የለም፡፡
ያለ ሰልፍ ታክሲ አግኝቶ መሆን አለበት፡፡
እንደተንጨረጨርኩ፣ እየተከፈተ ያስቸገረኝ የጠበበኝን የቀጭኗ
እህቴን ቀይ ሱሪ ዚፕ ወደ ላይ ለመመለስ ስታገልና ቦርጬነሸ እና በረከትን ስራገም ቀኑ አለቀ፡፡
ማታ ቀድሜው ገባሁና በርዝመቱና ጥልቀቱ ጊነስ ላይ ሊመዘገብ
የሚችል ታላቅ ኩርፊያ አኩርፌ ጠበቅኩት፡፡
ከዓመታት የነገር ቱባ አተራተር ልምዴ እንደማውቀው ፣ በረከት
እንደ ጠዋቱ ያለ ጭቅጭቅ በተጨቃጨቅን ዕለት እንዲህ አኩርፌ
ስጠብቀው ፤ ዝምታውና ግልምጫው ከአቅሙ በላይ ሲሆን ፤
ለልጆቹ ሲል፣ ለቤቱ ሰላም ሲል፣ “ቆንጅትዬ...! እሺ በቃ ይቅርታ የኔ ጥፋት ነው...” ይልና ሠርቶ ለተቀጣበትም ፤ ሣይሰራ ስተፈረደበትም ፤ ሠርተሃል ተብሎ ላልገባውና ለተገረፈበት
ኃጥያትም ይቅርታ ጠይቆኝ እንታረቃለን፡፡
ስለዚህ ለዚሁ ተዘጋጅቼ ጠበቀኩት፡፡
መጣ፡፡
ይቅርታ ጠየቀኝ፡፡
ታረቅን፡፡
የእርቃችን ጨዋታ ጣእሙ ሳያልቅ፣ አልጋ ላይ እንደተዘረጋን እናቱ ደወሉ፡፡
እናቱ ከባድ የጭቅጭቅ ማገዶ እንደሚሆኑ ስለሚያውቅ ኣጣድፎ
አነጋገራቸውና ስልኩን ዘጋ፡፡
“ምነው ከመሸ ደወሉ... ምን አሉህ?” አልኩት ተነስቼ ጋቢ እየደረብኩ፡፡
“ምንም...! ለሰላምታ ነው... ስላም ብላሻለች” ድምጹ ውስጥ ሰቀቀን
አለ፡፡
“አይ በረከት... ለምን ትዋሻለህ...? አሁን የአንተ እናት እኔን ሰላም
ለማለት ሲደውሉ ታየኝ! ያንተና የሳቸው ሚስጥር መቼም አያልቅም” አልኩት ጸጉሬን ለመጠቅለል ቢጎዲኖቼን ከመሳቢያ ውስጥ እያወጣጣሁ፡፡
ዐይን ዐይኔን አየኝና፣ “እንደሱ አይደለም፡፡ ጠፋች ደህና ናት ወይ....
ሥራ በዛባት አይደል.... ሠራተኛም ሳይኖራት...... ላንተና ለልጆቹ
ምግብስ መሥሪያ ሰዐት አገኘች ወይ... ምናምን ነው ያለችው ...
አለኝ በተኛበት፡፡
ቢጎዲኑን ጣል አደርጌ ዞር ብዬ ዐየሁትና፤
“ሠራተኛ ሳይኖራት አሉህ?” አልኩት፡፡
“አዎ... ያው ላንቺ አስባ"
አላስጨረስኩትም፧
“እኮ... መች አጣሁት...! ያው እኔን ነው የሚቦጭቁልህ መቼም!
በስተርጅና ሰው መቦጨቅ ....ምግብ አትሠራለትም እና ልጄ በርኀብ
አለመሞቱን ልይ ብለው ነው የደወሉት አይደል..?”
ዝም ብሎ ያየኛል፡፡
“ለምን አገልግል ተሸክመውልህ አይመጡም ነበር?” ብዬ ቀጠልኩ
እምባዬ እየመጣ፡፡ ምንም አላለም፡፡
“በረከት... እሳቸው ግን ለምንድነው እንዲህ ጥምድ ያደረጉኝ..?
ልጃቸውን አግብቼ ሰው ባደረግኩ.. የልጅ ልጅ ባሳምኩ... ንገረኝ እስቲ ምን አደርጌያቸው ነው...?”
ብስጭት እና ፍንጥር ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳና ጥሎኝ ወደ ሳሎን ሄደ፡፡ “በረከት...”
ተከተልኩት፡፡
💫አለቀ💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቅዳሜ። 🙏

#ስም_አነሳት
፡
፡
እኔስ አለኝ እናት
አባትም ባይኖረኝ
እግዜር የካስልኝ
እኔስ አለኝ እናት
ስታመም ከጐኔ
የማትርቅ ሁሌ
እኔስ አለኝ እናት
ከራሷ አሳልፋ
ለኔ የምትለፋ
እኔስ አለኝ እናት
እንባዋ ለፍቅሯ
አይቶኝ የሚያነባ
እኔስ አለኝ እናት
በደሏን ተሸክማ
ለኔ የምትደማ
አዎን ... ነበረችኝ
ፍቅሯ የገረመኝ
ስያሜ አተውላት
በሦስት ፊደላት
እናት ብቻ ብለው
ስሟን ባይቀንሱት
እናትስ ነበረኝ
በቃል የማልገልፃት
የህይወቴ ውበት
የኔነቴ ስምረት፡፡
፡
፡
እኔስ አለኝ እናት
አባትም ባይኖረኝ
እግዜር የካስልኝ
እኔስ አለኝ እናት
ስታመም ከጐኔ
የማትርቅ ሁሌ
እኔስ አለኝ እናት
ከራሷ አሳልፋ
ለኔ የምትለፋ
እኔስ አለኝ እናት
እንባዋ ለፍቅሯ
አይቶኝ የሚያነባ
እኔስ አለኝ እናት
በደሏን ተሸክማ
ለኔ የምትደማ
አዎን ... ነበረችኝ
ፍቅሯ የገረመኝ
ስያሜ አተውላት
በሦስት ፊደላት
እናት ብቻ ብለው
ስሟን ባይቀንሱት
እናትስ ነበረኝ
በቃል የማልገልፃት
የህይወቴ ውበት
የኔነቴ ስምረት፡፡
#ሁቱትሲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
(የመጨረሻ ክፍል)
፡
፡
#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች
፡
#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ
፡
#ድህረ_ታሪክ
፡
፡
#አዲስ_ፍቅር_አዲስ_ሕይወት
አንድ የተሰበረ ልብ ለማገገም ምን ያህል ጊዜ ይወስድበታል ብሎ ለመተንበይ ያዳግታል፤ እኔ ግን ተባርኬያለሁ፡- በእግዚአብሔር እርዳታ ልቤ ከሁለት ዓመት በኋላ ሌላ ለማፍቀር ችሏል፡፡ ስድን ግን የኖርኩት ዝምተኛና አመዛዛኝ ሕይወት ነው ፡፡በተመድ እየሠራሁና ከሳራ ቤተሰብ ጋር እየኖርኩ በትርፍ ጊዜዬ ኪጋሊ በሚገኝ አንድ የእጓለማውታ ማሳደጊያ በደርዘኖች ለሚቆጠሩ የተሸበሩ ብቸኛ ልጆች በታላቅ እህትነት በማገልገል በበጎ ፈቃደኝነት ሥራ አሳለፍኩ፡፡ በፈረንሳይ ምሽግ እንከባከባቸው የነበሩትን ሁለት ወንድማማቾች ሥራዬ ብዬ ብፈልጋቸውም ላገኛቸው አልቻልኩም፡፡ ይሁን እንጂ ሌሎች ብዙ ፍቅር ፈላጊ ወጣቶችን አግኝቻለሁ፡፡ በ1995 መጨረሻ ከኤይማብል ጋር ተገናኘሁ፡፡ ነጻ የትምህርት ዕድል የሰጠው አካል በሩዋንዳ ሰላም ተመልሷል ብሎ ስላመነ ወደ አገሩ የሚመጣበትን የአየር መጓጓዣ ወጪ ሸፈነለት፡፡ ከመምጣቱ በፊት ብዙ ጊዜ ተጻጽፈናል፡፡ ለተወሰኑ ጊዜያትም በስልክ አውርተናል፡፡ በአካል ለመገናኘት ግን በመንፈስ አልተዘጋጀንም፡፡ በአየር ማረፊያው የተገናኘንበትን ሁኔታ መቼም አልረሳውም፡፡ ልቦቻችንን ከክፉ እየጠበቅን ይመስል ስሜታችን ፈንቅሎ በመውጣት ወይም እንባ በመራጨት ፈንታ አቀባበሉ በስሱ ተከናወነ፡፡ ተቃቀፍን፣ ተሳሳምን፤ እኔ የእርሱን፣ እርሱም የኔን ህመም ላለመንካት ግን ተፈራርተን ጥንቃቄ አደረግን፡፡ ዓይን ለዓይን ለመተያየት ተፈራራን፡፡ እውነተኛ ስሜታችን ከወጣ መቆጣጠር እንደሚያቅተን አውቀን ከበደን፡፡ ማልቀስ ከጀመርን ማቆሚያ እንደሌለን ገብቶናል፡፡
ወንድሜና እኔ ከተወሰኑ ጓደኞቼ ጋር ወደ ምግብ ቤት ሄደን ራት እየበላን ስለ እርሱ ትምህርትና ስለኔ ሥራ እያወራንና በጓደኞቼም ቀልዶች እየሣቅን እናስመስል ያዝን፡፡ በዚያ ሌሊት ግን ብቻዬን መኝታዬ ላይ ሆኜ እንባዬን ዘረገፍኩት፡፡ ወንድሜም እንዲሁ እንዳደረገ እርግጠኛ ነኝ፡፡
በቀጣዩ ቀን አብሮ መሆኑ ይበልጥ ቀለለን፡፡ ምንም እንኳን እርስ በርስ መተያየቱ የቤተሰባችንን አሳዛኝ ፍጻሜ አሰቃቂ ትውስታ የሚቀሰቅስብን ቢሆንም በጣም ስለምንዋደድ አንዳችን በሌላችን መኖር ምቾት ተሰምቶናል፡፡ ህመሙን ለመቋቋም የሚያግዘኝን ጥንካሬ እንዳገኘሁ ልነግረውና ላጽናናውም ፈልጌያለሁ፡፡ ይሁን እንጂ የማያጽናኑት ዓይነት እንዳልሆነ ወዲያውኑ ታወቀኝ፡፡ ከአፍታ በኋላም በቤተሰባችን ስለተከሰተው ሰቆቃ ላለማንሳት ሳንነጋገር እንደተስማማን ገባን፡፡ የቤተሰባችንን አባላት ሁሉ በስም ጠቃቀስን፡፡ ያኔም ቢሆን አሁንም በሕይወት እንዳሉ አድርገን ነበር ያወራነው - የምንቋቋምበት ብቸኛው መንገዳችን ይህ ነው፡፡ ለቀጣዮቹም ሁለት ዓመታት በደብዳቤና በስልክ እንደዚያው ስናደርግ ቆየን፡፡ ኤይማብል የእንስሳት ሕክምና የድህረ ምረቃ መርሃ-ግብሩን ጨርሶ ወደ ኪጋሊ ሲመለስም ሁኔታው አልተቀየረም፡፡ በየቀኑ በአካል ብንገናኝም ስለ ዘር ጭፍጨፋው የምናወራው አንድ የሆነ ሰው ላይ የተከሰተ ይመስል እንዲያው በደምሳሳው ነው፡፡ የእማማንና የዳማሲንን መቃብርም ሲያይ እንኳን እንዳካሂደው አልጠየቀኝም፤ ብቻውን ሄደ፡፡ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያው እንዲሁ አለን፡፡ ኤይማብል አሁንም የሚኖረው ኪጋሊ ነው፤ ስኬታማ ሐኪም ሲሆን ቆንጅዬ ሚስትና ልጆች አሉት፡፡ እርስ በርሳችን በጣም እንዋደዳለን፤ ከመቼውም በላይ ቅርርብ አለን፡፡ በየጊዜው እንደዋወላለን፤ ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜም እንጻጻፋለን፡፡ አሁንም ቢሆን ከእነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላም ስለቤተሰባችን ስንነጋገር ‹ነበር› አንልም፡፡ ትዝታቸውን ህያው አድርጎ ማቆያ መንገዳችን ይህ ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡
ብዙ ምሽቶቼን በአቅራቢያዬ ባለና ሁለተኛ ቤቴ ሆኖ በነበረው በጀስዊቶች ማእከል በጸሎትና ተመስጦ ተጠምጄ አሳልፋሁ፡፡ በተደበቅሁባቸው ረጅም ወራት ወቅት ያዳነኝን ከእግዚአብሔር ጋር የነበረኝን የጠበቀ ቁርኝቴን በድጋሚ የጀመርኩት በነዚያ ርጭ ባሉ ስፍራዎች ነው፡፡
ልቤ ቀስ በቀስ ሲያገግምልኝ የወደፊቱን ሕይወቴን አብሬ የሚጋራ አንድ ልዩ የራሴ የምለው ሰውና የምንከባከበው ቤተሰብ ማለም ጀመርኩ፡፡ ግን ሐሳብ ገባኝ … ከዮሃንስ ጋር የነበረኝን ሁኔታ አስታወስኩና በቀላሉ ሊሰበር የሚችለውን ልቤን የትም ለማይደርስና በሚያሳምም መልኩ ለሚቋጭ ግንኙነት ላለመስጠት ወሰንኩ፡፡ ስለዚህ ችግር ወይም ፈተና በሚያጋጥመኝ ጊዜ ሁሉ እንደማደርገው የአምላክን እገዛ ጠየቅሁ፡፡ በገነት የሚሆን ጋብቻ ከፈለግሁ ከአምላኬ በተሻለ የሚኩለኝና የሚድረኝ ከቶ ማን ይኖራል?
መጽሐፍ ቅዱስ ከጠየቅን እንደምናገኝ ይነግረናል፤ በእርግጥም ያንን አደረግሁ፡፡ እግዚአብሔርን የማልመውን ሰው እንዲያመጣልኝ ጠየቅሁት፡፡ ራሴን ማጭበርበር አልፈልግሁም - እግዚአብሔር እንዲልክልኝ የምፈልገው ሰው ምን ዓይነት እንደሆነ በጣም ግልጽ ማድረግ ነበረብኝ፡፡ ስለሆነም ወረቀት ይዤ ተቀመጥኩና ላገባው የምፈልገውን ሰው ፊት ነደፍኩ፡፡ ከዚያም ቁመቱንና ሌሎቹን ገጽታዎቹን ዘረዘርኩ፡፡ ጠንካራ ማንነትና ምቹ ስብዕና ያለው፣ ደግ፣ አፍቃሪና ርህሩህ፣ ተጨዋች፣ ምግባረመልካም፣ ማንነቴን የሚወድልኝ፣ እንደኔ ልጆችን የሚያፈቅርና ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ይሰጠኝ ዘንድ ጠየቅሁ፡፡
ለእግዚአብሔር ቀን አልቆረጥኩለትም፡፡ በዘር፣ በዜግነት ወይንም የቆዳ ቀለም ላይም ምንም ገደብ አልጣልኩ፡፡ በዓለም ላይ ከአምስት ቢሊየን በላይ ሰዎች እንደመኖራቸው - ጌታዬ የሕይወቴን አጋር የሚልክበትና እኔም የምጠብቅበት አግባብ ያለው የቆይታ ጊዜ ስድስት ወራት እንዲሆን አቀድኩ፡፡ አንድ ማስጠንቀቂያንም ጨመርኩ፡- ድንግል ማርያምን እጅግ ስለምወዳት እግዚአብሔር ከእምነቴ ተመሳሳይ የሆነ ባል ቢልክልኝ እንደሚሻል ነገርኩት፡፡ በሃይማኖት ሳቢያ በትዳሬ ምንም ዓይነት ውጥረት እንደማይኖር ማረጋገጥ እንዲሁም ባሌ እግዚአብሔርን እኔ በማመልከው መልኩ እንዲያመልክ ፈለግሁ፡፡
ምን እንደምፈልግ በትክክል ካወቅሁ በኋላ ፍላጎቴን አልመው ጀመር፡፡ ጌታ የተመኘሁትን ባርኮ እንደሚሰጠኝ፣ የልቤ መሻት እንደሚሆንልኝና የጊዜ ጉዳይ ብቻ እንደሆነ አምኜ ሁሉንም ለእርሱ ተውኩት፡፡ ሂደቱን ለማፋጠን የአባቴን ቀይና ነጭ መቁጠሪያ አወጣሁና ባሌ እንዲመጣልኝ መጸለይ ጀመርኩ፡፡ ከሦስት ወራት በኋላም መጣልኝ፡- ከእግዚአብሔር የተላከውና የተመድ የሸለመኝ አቶ ብርያን ብላክ ከአሜሪካ ድረስ ከተፍ አለ! የነገሩ መገጣጠም ደሞ ብርያን ወደ ሀገሪቱ የመጣው የዘር ማጥፋቱን በማቀድ የተሳተፉትን ለፍርድ ለማቅረብ የሚጥረውን የተመዱን ዓለም አቀፍ የሩዋንዳ ፍርድ ቤት በማቋቋሙ ሂደት ለማገዝ ሆኖ እርፍ፡፡ ብርያን ለተመድ ለብዙ ዓመታት ስለሠራ ገዳዮቹን ፍትሃዊ ቅጣት እንዲያገኙ የሚያደርገው የተልዕኮው አካል በመሆኑ ይደሰታል፡፡ በግሌ እርሱ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ተልዕኮ በማስፈጸም ላይ ነው፡፡
ብርያንን ለመጀመሪያ ጊዜ በተመድ ግቢ ሳየው በትክክል እግዚአብሔር እንዲልክልኝ የጠየቅሁትን ሰውዬ መሰለኝ፡፡ በኋላ በአዳራሹ ሳልፈውና በዓይኖቹ የነበረውን ጥልቅ እርጋታ ሳይ እርሱ እንደሆነ እርግጠኛ ሆንኩ፡፡ ግን በእግዚአብሔር እምነቴን ስላደረግሁ ብርያንን ወደኔ እንዲያመጣው ጠበቅሁት አመጣልኛ ብርያን አብረን እንድንዝናና ጋብዞኝ ግሩም ጊዜ አሳለፍን

👍2
በምሽቱ መጨረሻም ሁነኛ ጥንዶች እንደሆንንና የተቀረውን ሕይወቴን አብሬው የማሳልፍ እንደሆነ እርግጠኛ ሆንኩ... ክርስቲያን ቢሆንልኝ! ራሴን አረጋግቼ ትልቁን ጥያቄ ጠየቅሁት፡ ‹‹ሃይማኖትህ ምንድነው?››
‹‹ክርስቲያን ነኝ፡፡››
ዘልዬ እቅፉ ውስጥ ገብቼ ‹‹አምላኬ ምስጋና ይግባህ! ወደ ሕይወቴ እንኳን በደኅና መጣህ - አብረን ኖርናታ!›› ማለት አሰኘኝ፡፡ ግን ያንን ምስኪን ሰው እንዳላስደነብረው ፈራሁ፡፡ ስለዚህ እንዲያውም እጁን ይዤ፣ ፈገግ አልኩና ‹‹እኔም ነኝ›› አልኩት፡፡
ብርያንን በዘር ጭፍጨፋው ወቅት ያለፍኩበትን ነገር ሁሉ በመንገር በፍጹም ባላጨናንቀውም ልቤ በተከፋ ቁጥር ያዳምጠኛል፡፡ ሲያስፈልገኝም ትከሻው ላይ ደገፍ ብዬ እንዳለቅስ ይፈቅድልኛል፡፡
ከሁለት ዓመታት በኋላ ብርያንና እኔ በባሕላዊ የሩዋንዳ የሰርግ ሥነ ሥርዓት ተጋብተን ከተወሰነ ጊዜም በኋላ፣ በ1998፣ ወደ አሜሪካ መጣን፡፡ በፍቅር የተሞላና መተጋገዝ ያለበት ትዳር አለን፤ እግዚአብሔር ሁለት ቆንጆ ልጆችንም ሰጥቶናል - ሴቷ ልጃችንን ኒኬይሻንና ወንዱን ብርያን ትንሹን፡፡ በየቀኑ ከእንቅልፌ ነቅቼ ሁለቱን ትናንሽ መላዕክቴን ሳይ የአምላክን ውበትና ዐቅም በፊታቸው አነባለሁ፡፡ ስለ ውድ ስጦታዎቹ ሁሉ እርሱን ማመስገኔን መቼም አላቆምም፡፡
በማናቸውም ቀንና መንገድ እግዚአብሔር የሕይወቴ አጋር ሆኖ ይቀጥላል፤ የሚያኖረኝ፣ የሚጠብቀኝ፣ የሚያረካኝ እርሱ ነው፡፡ የተሻለች ሚስት፣ እናት ብሎም ሰው ያደርገኛል፡፡ ሥራ እንዳገኝ አድርጎኛል፡፡ ልጆቼን ከወለድኩ በኋላ የሥራ ሕይወቴን መቀጠል ብፈልግም ኒው ዮርክ ከተማ ላይ ሥራ ማግኘት ኪጋሊ ላይ ከዘር ፍጅቱ በኋላ ከነበረው በላይ ፈታኝ ነው - ብዙ ሰዎች፣ ግን በጣም ጥቂት ሥራ፡፡ እግዚአብሔር እንዲመራን ጸለይኩ፤ በማንሃታን፣ በተመድ ውስጥ የምሻውን ሥራም ፈለግሁ፡፡ አንዴ የት መሥራት እንደምፈልግ ካወቅሁ በኋላ እዚያ ሥራ እንዳለኝ አድርጌ አለምኩ - ሁሌ የምጠቀመውን በጎ አሳቢነት መሳሪያ በማድረግ፡- እመኑ ታገኛላችሁ! ወደ ተመድ ድረ-ገጽ ገብቼ የሠራተኞቹን ስምና ማዕረግ የሚዘረዝረውን ክፍል አትሜ አወጣሁና ስሜን በዝርዝሩ ውስጥ ጨመርኩት፡፡ ለራሴ የውስጥ ስልክ መሥመር ሳይቀር ሰጠሁ! የስልክ መዘርዝሩን ግድግዳዬ ላይ ለጥፌ በየቀኑ አየዋለሁ፡፡ ማመልከቻ በእርግጥ ሞልቻለሁ፣ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ሰነዶችን አስገብቻለሁ፣ በስልክም እየደወልኩ ከምን ደረሰልኝ እላለሁ - በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎችም ሰዎች ግን ይህንኑ ያደርጋሉ፡፡ መዘርዝሬን ማየቴንና ሥራው የኔ መሆኑን ማመኔን በመቀጠል በየቀኑ ስልኬ እስኪጮህ እጸልያለሁ፡፡ እንደጠበኩትም ከመቶዎች ሌሎች አመልካቾች ተመርጬ ቃለ መጠይቅ ከተደረገልኝ በኋላ ሥራውን በጄ አስገባሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ኃይል በተግባር በማየቴ መገረሜን በፍጹም አላቆምኩም!
ይህ ወደ ሕይወቴ ቀጣይ ምዕራፍ ለመሸጋገር ወደፊት የሚገፋፋኝ ተመሳሳይ ኃይል ነው፡፡ አምላክ ሕይወቴን ያዳናትና ነፍሴን ያተረፋት ለምክንያት ነው፡፡ ከሞት ያስቀረኝ ታሪኬን ለሌሎች አንድነግርና በተቻለኝ መጠን ለብዙ ሰዎች የፍቅሩንና የምህረቱን የማዳን ኃይል እንዳሳይ ነው፡፡
ትቻቸው የመጣኋቸውና ልረዳቸው የሚገባኝ ሰዎች አሉኝ፡፡ በዘር ፍጅቱ ተራፊዎች በተለይ በእጓለማውታ ልብ ውስጥ ተስፋን መልሶ በማምጣቱ ሂደት ለማገዝ በቻልኩት መጠን ቶሎ ቶሎ ወደ ሩዋንዳ እየተመላለስኩ ለመሥራት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በአሁኑ ወቅት በማናቸውም ስፍራ ያሉ የዘር ፍጅትና የጦርነት ሰለባዎችን በአካል፣ በአእምሮና በመንፈስ እንዲድኑ የሚያግዝ ድርጅት በማቋቋም ላይ እገኛለሁ፡፡
የእግዚአብሔር መልዕክት ድንበር ሳይገድበው የትም ቦታና ከማንም ልብ ውስጥ ይደርሳል፡፡ ማንም በዓለም ላይ ያለ ግለሰብ የጎዳውን ማንንም ሰው እንዴት እንደሚምር መማር ይችላል - ጉዳቱ አነሰም በዛ፡፡ የዚህን እውነትነት በየቀኑ አየዋለሁ፡፡ ምሳሌ ለመጥቀስም ያህል ታሪኬን ያጋራኋት አንዲት አዲስ ጓደኛዬ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ የኔ ታሪክ አንድ ወቅት በጣም ትቀርበው ከነበረና ለዓመታት ካኮረፈችው አጎቷ እንድትታረቅ እንዳነሳሳት ደውላ ነገረችኝ፡፡
‹‹በጣም በመጨቃጨቃችን ስለበገንኩ ከእርሱ ጋር ሁለተኛ አልነጋገርም ብዬ ምዬ ነበር›› ስትል ምስጢሯን አጋራችኝ፡፡ ‹‹ቤተሰብሽን የገደሉትን ሰዎች እንዴት መማር እንደተቻለሽ ከሰማሁ በኋላ ግን ስልኩን አንስቼ ልደውልለት ግድ አለኝ፡፡ ይቅርታ አልጠየቅሁትም - በቀጥታ ልቤን ከፍቼ ማርኩት እንጂ፡፡ ወዲያውኑ በፊት እናወራበት በነበረው መንገድ እናወራ ጀመር - በልዩ በፍቅር፡፡ በኩርፊያ ብዙ ዓመታት እንዳመለጡን ማመን አቃተን›› አለችኝ፡፡
በተመሳሳይ አንድ ከዘር ፍጅቱ የተረፈችና በቅርቡ ወላጆቿ ሩዋንዳ ላይ የተገደሉባት ሰው በስልክ አራጆቹን ለመማር ያደረግኋቸውን ነገሮች ቅደም ተከተል እያለቀሰች ጠየቀችኝ፡፡
‹‹እነርሱን ስትምሪ በልቤ አብዳለች አልኩሽ፣ ኢማኪዩሌ - የእጃቸውን ከማግኘት ስታድኛቸው፡፡ ለ11 ዓመት በልቤ የያዝኩት ሕመምና ምሬት ሊገድለኝ ነው፡፡ ለረጅም ጊዜ ሕይወቴ አሰቃቂ ስለነበር ከአሁን በኋላ የምኖርበት ምንም ዐቅም የለኝም፡፡ ሰዎች ግን አንቺ የቤተሰብሽን ገዳዮች ምረሽ ሕይወትሽን እንደቀጠልሽ ሲያወሩ ስሰማ ቆይቻለሁ … ደስተኛ እንደሆንሽና ባል፣ ልጆችና ሥራም እንዳለሽ! እኔም ጥላቻዬን ለመተው እንዴት እንደምችል መማር ያስፈልገኛል፡፡ እንደገና መኖር መጀመር አለብኝ፡፡ ››
በአምላክ እንዴት እንደምታመን ነገርኳት፤ ምኅረት ለማድረግና ወደ ፊት ለመራመድም ያደረግሁትን ሁሉ ተረኩላት … በዚህ መጽሐፍ ያሰፈርኩትን ነገር ሁሉ፡፡ አመስግናኝ እርሷም ገዳዮቹን እንድትምር እግዚአብሔርን እንዲያግዛት መጠየቋን ነገረችኝ፡፡
ከዚያም በአትላንታ ካቀረብኩት ንግግር በኋላ እያለቀሰች የቀረበችኝን ሴትዮ አስታውሳለሁ፡፡ በሕጻንነቷ ወላጆቿ በናዚ ጭፍጨፋ እንደተገደሉባት ነገረችኝ፡ ‹‹ዕድሜዬን ሙሉ ልቤ በንዴት ተሞልቶ ኖሯል… ሥቃይ ሲሸነቁጠኝ ኖሬያለሁ፤ ስለ ወላጆቼ ለብዙ ዓመታት አልቅሻለሁ፡፡ ያሳለፍሽውን የስቃይ ታሪክና ምኅረት ማድረግ መቻልሽን መስማቴ አነሳሳኝ፡፡ ዕድሜዬን ሙሉ ወላጆቼን የገደሉትን ሰዎች ለመማር ስጥር ኖሬያለሁ፤ አሁን ግን የማደርገው ይመስለኛል፡፡ ንዴቴን ትቼ ደስተኛ ሳልሆን አልቀርም፡፡››
በትምህርታዊ ጉባዔው ላይ የ92 ዓመት ሴት አዛውንት እጃቸውን ጠመጠሙብኝና አጥብቀው አቀፉኝ፡፡ በጣም ስሜታዊ ስለሆኑም መናገር አዳግቷቸዋል፤ ቢሆንም እንደ ምንም ድምፅ ለማውጣት ተችሏቸዋል፡፡ ቃላቸውን አልረሳውም፡- ‹‹ምኅረት ለማድረግ እጅግ ዘገየሁ ብዬ ነበር፡፡ እንዲያው አንድ ሰው አንቺ ያልሽውን ሲል ለመስማት ስጠብቅ - የማይማረውን መማር እንደሚቻል ማወቅ አስፈልጎኝ ነበር፣ ልጄ›› አሉኝ፡፡
የትውልድ ሐገሬን ሩዋንዳን በተመለከተ እያንዳንዱ ሰው የምኅረትን ትምህርት ለመቅሰም ከቻለ ሀገሬ ራሷን ማዳን እንደሚቻላት አውቃለሁ፡፡ በዘር ማጽዳቱ ወቅት የግድያ ወንጀል በመፈጸማቸው የታሰሩት በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከእስር እየተፈቱ ወደ ቀድሞ ከተሞቻቸውና መንደሮቻቸው እየገቡ ነው፡፡ ስለሆነም ከመቼውም ጊዜ በላይ ምኅረት የማድረጊያው ጊዜ አሁን ነው፡፡ ሩዋንዳ መልሳ ገነት መሆን ትችላለች፤ ሆኖም እናት ሀገሬ እንድትድን መላው ዓለም ፍቅሩን ሊሰጣት ይገባል፡

መቼም ያለፈው አልፏል፤ በሩዋንዳ የተከሰተው ግን በሁላችንም በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ በመሆኑ መላው የሰው ዘር በዘር ማጥፋቱ ቆስሏል፡፡ ከአንዲት ልብ የሚመነጭ ፍቅር የልዩነት ዓለምን መፍጠር ይቻለዋል፡፡ በአንድ ጊዜ አንዲትን ነፍስ በማዳን ሩዋንዳን ብሎም ዓለማችንን ማዳን እንደምንችል አምናለሁ፡፡
#ምስጋና
በመጀመሪያ ከሁሉ በላይ እግዚአብሔርን ድንቅ አባት፣ ሁነኛ ጓደኛ፣ እውነተኛው ምስጢረኛ … ብሎም አዳኜ ስለሆነልኝ ማመስገን ግድ ይለኛል፡፡ ጌታ ሆይ፣ በደጎቹም ሆነ በእጅግ መጥፎዎቹ ጊዜያት ቋሚ ባንጀራዬ እንደሆንክ አለህ፡፡ ልቦናዬን ስለከፈትክልኝና እንደገና እንዳፈቅር ስላስቻልከኝ ክበር ተመስገን፡፡ ያላንተ ምንም አይደለሁም፤ ካንተ ጋር ግን ሁሉንም ነገር ነኝ፡፡ ጌታዬ፣ ላንተ እጄን እሰጣለሁ - በሕይወቴ ሙሉ ፈቃድህ ይፈጸምልኝ፡፡ ባንተ ዱካ መራመዴን እቀጥልበታለሁ፡፡ ለተባረክሽው ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ሁሌ አለሁ ለምትዪኝ - ዘወትር ካጠገቤ እንዳለሽ ይታወቀኛል፡፡ ስለ ፍቅርና እንክብካቤሽ ያለኝን ምስጋና ግዝፈት ቃላት አይገልጹትም፡፡ ልቤን ለልብሽ አቅርቢልኝ፣ እናቴ - ሙሉ ታደርጊኛለሽ፤ እስከ ዘላለሙ እወድሻለሁ፡፡ በኪቦሆ ተገልጠሽ ከፊታችን እየመጣ ስለነበረው አደጋ ስላስጠነቀቅሽን አመሰግንሻለሁ … ምነው ሰምተንሽ ቢሆን ኖሮ!
ዶክተር ዌይን ዳየር - ከገነት የተላኩ መልአክ ነዎት፡፡ እግዚአብሔር እርስዎን ወደኔ ሕይወት ስላመጣዎት አመሰግነዋለሁ፣ መንፈሶቻችንም እርስ በርሳቸው ለዘላለሙ እንደተዋወቁ ይሰማኛል! ወደር-የለሹ ደግነትዎ፣ በዕውቀት የተገነባው ምክርዎና አባታዊ ፍቅርዎ ለእኔ እንደ አጽናፍ ዓለም ሰፊ ነው፡፡ እጅግ በርካታ ሰዎች ለምን በእርስዎ ቃል እንደተነሣሱ መገንዘብ ቀላል ነው - እርስዎ የኔ ጀግና ነዎ፣ እወድዎማለሁ፡፡ ስለተማመኑብኝና ወደ ሕልሜ ስለመሩኝ፣ እውነተኛውን የነፍሴን ጥሪም እንዳውቅ ስላደረጉኝ ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡ በተጨማሪም ይህንን መጽሐፍ እውን ስላደረጉልኝና ታሪኬን እንድናገር ስላደረጉኝ ገለታ ይግባዎት፡፡ ስካይ ዳየር፡- ከአባትሽ ጋር ስላስተዋወቅሽኝ እንዴት እንደማመሰግንሽ! እወድሻለሁ!
ለሄይ ሃውስ ድንቅ ቡድን፡- ጂል ክራመር፣ ሻነን ሊትረል፣ ናንሲ ሌቪን፣ ክሪስቲ ሳሊናስ፣ ጃክዊ ክላርክ፣ ስቴሲ ስሚዝና ጃኒ ሊበራቲ - አብረዋችሁ ሲሰሩ ማስደሰታችሁ! ስለ መንገድ ጠቋሚነታችሁ፣ ትዕግሥትና ማበረታቻችሁ ገለታ ይግባችሁ፡፡
ተባባሪዬ፣ ስቲቭ ኤርዊን፣ በዚህ መጽሐፍ ዝግጅት አብረኸኝ ከሠራህ በኋላ ማንም ሰው አንተ የምታውቀኝን ያህል ያውቀኛል ብዬ አላስብም፡፡ አንተ አስገራሚ ሰው ነህ፤ አሁን ለኔ እንደ ወንድም ማለት ነህ፡፡ እንደዚህ ያለህ ጥሩ ሐኪም ስለሆንክልኝ አመሰግንሃለሁ - ስለቤተሰቤ በርካታ ግላዊ ነገሮችን ስትጠይቀኝ ያሳየኸው ሆደ-ቡቡነት ለኔ ብዙ ቁምነገር አለው፡፡ ስለ ተዓምራዊ አጆችህ አምላክን አመሰግናለሁ - ጽሑፍህ ቃላቴንና ስሜቴን ነፍስ ዘርቶባቸዋል፡፡ በተጨማሪ ሁለታችንም እናቶቻችንን ገና ሳንጠግባቸው የማጣትን ሕመም ስለምንጋራ በዚህ መጽሐፍ የገለጽኳቸውን ሁሉንም ስሜቶች ለምትረዳው ለባለቤትህ ለናታሻም ምስጋናዬ ይድረስ፡፡ ናታሻ፣ አንቺ እኮ ለኔ እንደ እህቴ ነሽ!
ቪንሴንት ካዪዡካና ኤስፔራንስ ፉንዲራ፡- ከመጀመሪያው እንዴት እንዳበረታታችሁኝና እንደተማመናችሁብኝ በጭራሽ አልረሳውም፡፡ እወዳችኋለሁ! ለዋሪያራ ምቡጋ፣ ሮበርት ማክማሆን፣ ሊላ ራሞስ፣ አና ኬሌት፣ ቢል በርክሌይና ርብቃ ማርቴንሰን ለእገዛችሁ፣ ለለገሳችሁኝ ሐሳብ፣ ለምክራችሁና አስፈላጊ ማበረታቻችሁ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ
ስማችሁን ያላነሳኋችሁ ግን በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ያገዛችሁኝ በርካታ ውድ ጓደኞቼ፡- አመሰግናችኋለሁ - ሁላችሁም በልቤ አላችሁ፡፡
ተጨማሪ በጣም ልዩ ምስጋና ለሁለት እጅግ ልዩ ቄሶች፣ ለአባ ጋንዛ ዢን ባፕቲስትና ለንስሐ አባቴ ለአባ ዢን ባፕቲስት ቡጊንጎ፡፡
እጅግ ብዙ የፍቅርና የሰቆቃ ትውስታዎችንና ብዙ የማይነገር ሰቆቃ ለምጋራህ ለወንድሜ ለኤይማብል ንቱካንያግዌ፡- ሁቱትሲ ውስጥ ልትጠይቃቸው ላልቻልካቸውና እኔም መልስ ልሰጥህ ላልቻልኳቸው ብዙ ጥያቄዎች ምላሽ ታገኛለህ ብዬ እመኛለሁ፡፡ አንተ በሕይወት ስላለህልኝ አምላክን አመሰግነዋለሁ - አንተ ለኔ ሁሉ ነገር ነህ፡፡ ስለ ሰዎቻችን አትጨነቅ … ደስተኞችና በገነት የኛ ልዩ ጠበቆች ናቸው! ወንድም ጋሼ፣ ግሩም ወንድም ስለሆንክልኝ ምስጋና ይግባህ - ከማስታውሰው ጊዜ ጀምሮ ላሳየኸኝ የማያሰልስ ፍቅር፣ በኔ ላይ ስላለህ እምነትና ሁልጊዜ የቤተሰባችንን ታሪክ እንድጽፈው ስላበረታታኸኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ባያሌው የማመሰግናት ደግሞ ሳውዳ ነች፡፡ ምራቴና ጓደኛዬ ብዬ ስጠራሽ ተባርኬያለሁ - ዘራችንን ስላበዛሽው ምስጋና ይግባሽ፡፡ እንደ ዘር ጭፍጨፋ ተራፊ የታሪክ ተጋሪነትሽ ይህ መጽሐፍ ላንቺ ልዩ ትርጉም ይኖረዋል፡፡ በእጅጉ እፈቅርሻለሁ፡፡ ሾንታል ንዪራሩኩንዶ፣ ኮንሶሊ ንሺምዌና ስቴላ ኡሙቶኒ፡ ትናንሽ እህቶቼ ናችሁ! በዚህ መጽሐፍ ስለተነሣሳችሁ አመሰግናችኋለሁ - ትልቅ መነሳሳትን
አምጥታችሁልኛል፡፡ ለእናንተም መሆኑን እወቁልኝ፤ ስለመዳናችሁ፡፡ ቆንጆዎቹ ልጆቼ ንኬይሻና ብርያን ትንሹ፣ ትንሹ የወንድሜ ልጅ ርያን፡- ውዶቼ፣ እንደ አበቦች ሁሉ ከፈጣሪ ዘንድ የመጣችሁ ትናንሽ መላዕክቴ ናችሁ፡፡ ለፍቅራችሁ ንጽሕናና እንደገና እንድኖር ምክንያት ስለሆናችሁኝ አመሰግናችኋለሁ፡፡ ንጹሃን ነፍሶቻችሁ በጥላቻ በማይጎዱባት ዓለም ብንኖርና የዘር ፍጅትና ጭፍጨፋ የሚሉትን ቃላትም ባትሰሟቸው ምኞቴ ነበር፡፡ ስታድጉ አያቶቻችሁንና አጎቶቻችሁን ሁቱትሲ ገጾች ውስጥ ታገኟቸዋላችሁ - ትውስታዋቻቸው በመጽሐፌ ይኖራሉ፡፡ ለአሁኑ ግን ውድ እጆቻችሁን እኔን ለማቀፍ በኔ ዙሪያ በዘረጋችሁ ቁጥር ፍቅራቸውን አስተላልፍላችኋለሁ፡፡ ሕይወቴ ናችሁ፤ እወዳችኋለሁ፡፡
በመጨረሻም፣ በእርግጠኛነት ግን መጨረሻ ላይ ያደረኩህ ከሌሎቹ አሳንሼህ አይደለም፣ ድንቁ ባሌ፣ ብርያን፣ አመሰግንሃለሁ፡፡ ከብቸኝነት አድነኸኛል፤ በእውነት ግማሽ አካሌ ነህ - ከአምላክ እኔን እንድታሟላ የተላክህ ግማሽ ገላዬ፡፡ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ስለጣርክና ታሪኬን እንድነግር ስለረዳኸኝ፤ በአያሌው ስላበረታታኸኝ፣ አምሽተህ ስለምታነብልኝና ስለምታርምልኝ አመስግኛለሁ፡፡ ለማይነጥፍ ፍቅርህና ከለላነትህ ገለታ ይግባህ፤ እግዚአብሔርን እንደ ወዳጃችን በመቀበልህም ጭምር፡፡ የኔ ፍቅር፣ በሙሉ ልቤና ነፍሴ እወድሃለሁ
#ኢማኪዩሌ
የደራስያኑ ማንነት ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ
ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ በሩዋንዳ ተወልዳ በብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሮኒክና ሜካኒካል ምህንድስና አጥንታለች በ1994 በተፈጸመው ጭፍጨፋ አብዛኛዎቹን የቤተሰቧን አባላት አጥታለች፡፡ ከአራት ዓመታት በኋላም ከሩዋንዳ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተሰዳ በኒው ዮርክ ለተባበሩት መንግሥታት መሥራት ጀመረች፡፡ ሌሎች ከዘር ማጥፋትና ከጦርነት የረጅም ጊዜ ተጽዕኖዎች ይድኑ ዘንድ ለመርዳት የኢሊባጊዛ ፋውንዴሽንን በማቋቋም ላይ ትገኛለች፡፡ ኢማኪዩሌ በሎንግ ደሴት ከባለቤቷ ከብርያን ብላክና ከልጆቿ ከኒኬይሻና ብርያን ትንሹ ጋር ትኖራለች፡፡
💫ተፈፀመ 💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም በድርሰቱ ላይ ያሎትን አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

እንዴት ናቹ #የአትሮኖስ ቻናል ቤተሰቦች እንደሚታወቀው #ሁቱትሲ የተሰኘው ድርሰት በትላንትናው እለት ተጠናቋል ያላችሁንም አስተያየት በውስጥ መስመር እየገለፃችሁልኝ ነው ለዚህም ከብዛቱ የተነሳ ለሁሉም መልስ መስጠት ስላልቻልኩ ይቅርታ እየጠየኩ ባጠቃላይ ግን ሁላችሁንም ከልቤ ማመስገን እፈልጋለሁ። 🙏
ሌላው በቅርብ ቀን ልንጀምረው ያሰብነው
ረጅም ታሪክ አለ ከነዚህም ውስጥ ለጊዜው 3 አሉ ከነዚህ ውስጥ አንዱን መርጦ ለመጀመር የናተ ከፍተኛ ትብብር ያስፈልጋል
መጀመርያ ከታች ከማስቀምጣቻው ምርጫዎች ውስጥ በናተ በከፍተኛ መጠን የተመረጠውን ቅድምያ አቀርባለው
ሌላው #MUTE አድርጋችሁ የምትጠቀሙ የቻናሉ ቤተሰቦች ፅሁፍ ማዘጋጀት በጣም ከባድ ነው አንዳንድ ቻናሎች ላይ እንደምታዩት ሌላ ቻናል ላይ ያሉትን ታሪኮች Cope paste አደለም የማደርገው በተቻለ መጠን አዳዲስ ታሪኮችን ይዤ ለመምጣት እሞክራለሁ ለዚህም ደሞ ለናተ በሚመች መልኩ ለማቅረብ ከፍተኛ ልፋት አለው እንዲህ የተዘጋጀውን ደሞ እናተ ካላያችሁት ልፋት ብቻ ነው የሚሆነው እናም እባካችሁ #UNMUTE አድርጋችሁ ተጠቀሙ እኔም ሳልሰለች ለናተ ምርጥ ምርጥ ታሪኮችን ይዤ እመጣለሁ
ከታች ካሉት ምርጫዎች ቅድምያ ይቅረብ የምትሉትን በመምረጥ ተሳተፉ
💚 #ፍቅር_እስከ_መቃብር
💛 #ሮዛ
❤️ #የአና_ማስታወሻ

#ማሂ_ድንግሏ
፡
፡
ልጃገረድነት ሰልችቶኛል፡፡
ቦይ ፍሬንድ አምሮኛል፡፡
“የኔ ፍቅር” መባል፤ “የኔ ቆንጆ” ተብሎ መጠራት አሰኝቶኛል፡፡እስከ ዛሬ ድረስ “
ትምህርቴን በሥርዓት ለመከታተል”፣ “ከአልባሌ ቦታ ለመራቅ”፣ “መቅደም ያለበትን ለማስቀደም” ፤ የከጀሉኝን
በአልገባኝም እየሸወድኩ፣ የጠየቁኝን እምቢ እያልኩ፣ ስንት የተቀበረ
የወንድ ፈንጂ በጥንቃቄ አልፌ ልጃገረድ ሆኜ ቆይቻለሁ፡፡
ኮሌጅ ከገባሁ ጊዜ አንስቶ ግን ከካልኩለስ በላይ ይሄ እየከበደኝ መጣ፡፡ አብሶ ሦስተኛ ዓመት ስደርስ፤ አብሶ 21 ዓመት ሲሞላኝ፣ አብሶ ጓደኞቼ ሁሉ ወሬያቸው በ“እንትና ደውሎልኝ ፣ በ“እንትና ቴክስት ልኮልኝ” ፣ በ“እንትና ስሞኝ” ሲጀምርና ሲያልቅ፤ እኔ ደግሞ ከወሬው መገለል ስጀምር፡፡
እኔ ስልክ የሚደውልልኝ ታላቅ ወንድሜ ብቻ ነው፡፡ ቴክስት
የሚደርሰኝ ከ8100 ብቻ ነው፡፡ ተስሜ የማውቀው አሥራ አንደኛ
ክፍል እያለን አሳስቶ (ለአራት ወራት) በቀመሰኝ ዮናታን ብቻ ነው፡፡
እነሆ! ድንግል መሆኔን ያወቁት የቅርብ ጓደኞቼ የቀልዶች መጀመሪያ ካደረጉኝ ቆዩ፡፡
አንቺ ልጅ ኧረ ተይ...! ኮርማ አምጥተን እናስጠቃሽ እንዴ...?”
“ቱሪዝም ኮሚሽን ስላንቺ ያውቃል...? ከድንቃድንቅ ቅርሶች መሀል
አስመዝግበው ያስጎብኙሽ እንጂ!”
የሆነ አራት ማእዘን የመስታወት ሣጥን ውስጥ አስቀምጠው ሊመረምሩሽ እንዳይመጡ......”
ልጃገረድነት ሰልችቶኛል፡፡
ቦይፍሬንድ አምሮኛል፡፡
የኔ ፍቅር” መባል፤ “የኔ ቆንጆ” ተብሎ መጠራት አሰኝቶኛል፡፡ግን ቦይፍሬንድ እንዴት እንደሚገኝ፣ ልጃገረድነት እንዴት
እንደሚሰጥ፣ የኔ ፍቅር ለመባል በየት በኩል እንደሚኬድ አጥርቼ
ስለማላውቅ፤ ጓደኞቼ ሲወጡና ሲገቡ ማጥናት፣ አንዳንዴም ጥያቄ
መጠየቅ፣ አንዳንዴም ዝም ብለው ሲያወሩ ከዝባዝንኬው ፍሬ ነገር
መልቀም ያዝኩ፡፡
ልክ ክፍል ውስጥ ገብቼ ደብተሬ ላይ ዋና ዋናው እንደምጽፈው ፤
ከአፋቸው የሚወጡ ነገሮችን፣ ጆሮዎቼን አፋቸው ስር እንደ ባልዲ ደቅኜ መቅዳት ጀመርኩ፡፡
ብዙ ጊዜ የሚጠቅመኝን ነገር የምታወራው ግን ሰምሃል ነበረች::
ሰምሃል እንደ ኤቲኤም ማሽን?” ለወንዶች ሃያ አራት ሰዓት ክፍት ናት፡፡ በተለይ የሚስጥር ኮድዋን ለሚያውቁ::
የሴቶች ቪያግራ ገንዘብ ነው!” የምትለው ነገር አላት ገንዘብ ካገኘች እንደ ሕዝብ ስልክ ማውራት ትጀምራለች፡፡የተጠየቀችውን ታደርጋላች፡፡
አንድ ቀን ዶርም ለብቻችን ስንሆን ድፍረት አጠራከምኩና፤ "ሰሚ ሰምሃል...” አልኳት፡፡
“እንዳትሥቂ ግን...”
“በምን እሥቃለሁ...?”
“በምጠይቅሽ ነገር”
“ምንድነው.....? የሚያሥቅ ነው...?”
“ኦፋ! አትሳቂ አልኩሽ አይደል...?”
“እሺ.. ጠይቂኝ”
የእግር ጥፍሮችዋን ዐይን የሚያደነቁር ቀይ ቀለም እየቀባች ነው፡፡
ጎንበስ ብሎ ለሞከረ ከአውሮፕላን የሚታይ ይመስለኛል፡፡
“እ... ቦይፍሬንድ... ቦይፍሬንድ እንዴት ነው..... የሚያዘው...?
ማለቴ... መጀመሪያ ምን ማድረግ ነው ያለብኝ...?” አልሣቀችም፡፡
ገረመኝ፡፡
“ማሂዬ! የኔ ቆንጆ... ልብስ እንዴት ነው የሚገዛው...?” አለችኝ
ቀለም ቅቡን ትታ ወደኔ እያየች፡፡
ልብስ ስትገዢ ምንድነው ምታደርጊው...?”
"እለካለሁ!”
ወንድም እንደዛ ነው፡፡ ገበያ ትወጫለሽ፤ ያማረሽን ታነሺያለሽ፤
ትለኪዋለሽ፤ ካልጠበበ ወይ ካልሰፋ በልክሽ የሆነውን በዐቅምሽ ትገዣለሽ፡፡”
ብዙ ጊዜ የምትለው ነገር አይጥመኝም ነበር ይሄ ግን ልክ መሰለኝ፡፡
በልክ መግዛት፡፡ በዕቅም መግዛት፡፡ ግን ልኬ ማነው...? ዐቅሜስ
ምን ያህል ነው ? ወንድን “መለካትስ ምን ማለት ነው.....? ስንት
ምሳ ተጋብዤ እመርጣለሁ? ስንት ከንፈር ቀምሼ አውቃለሁ?
ከስንቱ ጋር ተኝቼ እወስናለሁ...? ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች
ነበሩኝ ግን፤
ልጃገረድነት ሰልችቶኛል፡፡
ቦይፍሬንድ አምሮኛል፡፡
“የኔ ፍቅር” መባል፤ “የኔ ቆንጆ” ተብሎ መጠራት አሰኝቶኛል፡፡
ስለዚህ በፈራ-ተባ ቦይ ፍሬንድ ገበያ ወጣሁ፡፡ ምን ያደርጋል!
የምሄድበት ቦታ ሁሉ የኖኅ መርከብ ይመስል ካለ ጥንድ ብቻውን
የቆመ ሰው አጣሁ፡፡ አልፎ አልፎ ብቻውን የቆመ ባገኝም ፤ ለምሳሌ አንዱ መላጣ እና ሾጣጣ ጭንቅላታም ይሆንና፣ “አሁን ይሄ መላጣ፣ ሌላ ፊት አያሰራም?” እያልኩ ስሥቅ የቦይፍሬንድ
ግዢውን እረሳለሁ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያልኩ አቃቂር ሳወጣ ባዶ እጄን እመለሳለሁ፡፡
#ሙከራ_አንድ
ከዕለታት በአንዱ ቀን በሰምሃል አያያዥነት ከአብሥራ ጋር ተዋወቅኩ፡፡ ለነገሩ በፊትም አውቀው ነበር፡፡ “ጓደኝነታችን ሲጠነክርና በግ ተራ እየተቀጣጠርን መገናኘት ስንጀምር፣ የነገሩን አቅጣጫ በመገመት ለሚመጣው መዘጋጀት ጀመርኩ፡፡ የዚያን ጊዜ ነው ሰምሃል የአብሥራም እንደኔ፣ “ልዩና አስደናቂ ወጣት” እንደሆነ የነገረችኝ፡፡ ጎበዝ የማትስ ዲፓርትመንት ተማሪ ስለነበር፣ “በሂደቱ ላይ” ችግር ቢፈጠር መላ መምታት አይከብደውም ብዬ ብዙ አልከፋኝም፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ተከራይቶ የሚኖርበት ቤት ወስዶ፣
“የሚያሳብድ ሙዚቃ” ሊያሰማኝ እንደሚፈልግ ሲነግረኝ በጠዋት
ወጥቼ የውስጥ ሱሪ ገዛሁ፡፡ ቀይ፣ ባለ አበባ፣ የቂጤን አንድ አራተኛ ብቻ የሚሽፍን ሻፋዳ የውስጥ ሱሪ፡፡
እንደ ጎበዝ ተማሪ ባሕሪዬ ፤ ከዚያ በፊት በነበሩት ቀናት ግን ሰምሃልና ሌሎቹ ባሉበት የቅድመ ዝግጅት ጥያቄዬን ልምድ ላካበቱት እነሱ አቅርቤ ነበር፡፡
“ያማል?”
“አዎ ግን አሪፍ ሕመም ነው”
"ካደረግኩ በኋላ ወዲያው መቆምና መራመድ እችላለሁ?”
(ከህብረት ሣቅ በኋላ) “እንዴ! ስልክ እንጨት የምትውጪ መሰለሽ
እንዴ?” ሰምሃል ናት፡፡
ከሱሬ ጋር ካላደረግሽ... ቆመሽ ትሄጃለሽ” ሁሉም ጮኽ ብለው ሳቁ
“ሱሬ ደግሞ ማነው?” ሌላ የማላውቀው ነገር ከጣሪያ በላይ ሲያሥቅ
እኔ ግን መጠየቅ እየሰለቸኝ ጠየቅኩ፡፡
“ሱሬ ቲቪኤስ ነዋ! ሱሬን አታውቂውም?” ሰምሃል ተሽቀዳድማ።
“ሱሬ ማ?”
“ሱሬ ቲቪኤስ!” እንደገና ሣቁ፡፡
“ምንድነው ደሞ ቲቪኤስ?” እያመመኝ ጠየቅኩ፡፡
ሦስቱም በአንድ ጊዜ እንዳጠኑት ሁሉ እኩል “ባለ ሦስት እግር
ተሽከርካሪ!” አሉና እንደገና ሣቁ፡፡
አፍሬም ሥቂም ዝም ብዬ ትንሽ እንደቆየሁ ማክዳ፣ “ለመጀመሪያ
እንኳን ባለማርያም ጣቱን ያድርግልሽ” አለች ከቅድሙ የተረፈ
ይሁን፣ አዲስ ይሆን ያላወቅኩትን ሣቅ ሳታቆም፡፡ ስቄ ዝም አልኩ፡፡
“ባይ ዘ ዌይ..... ክብሩ እንደዛ ነው አሉ!” (ያው እንደምትገምቱት ሰምሃል ናት ይሄን ያለችው)
“ክብሩ..? ክብሩ ሳይኮሎጂ....?” ማክዳ ተሸቀዳድማ ጠየቀች::
“ያ... ሰኒ አብራው አድራ ስትወጣ እንዴት ነበር? ስላት ምን ብትለኝ ጥሩ ነው?”
“ምን አለች?”
“እሱ ኮንዶም ሲያመጣ እኔ ደግሞ ማይክሮስኮፕ ይዤ መሄድ ነበረብኝ!”
እኔ የሌለሁበት ሌላ የኅብረት ሣቅ፡፡

ከእነዚህ ልጆች ሣቅ መደመር አምሮኛል፡፡
የአብሥራ፤ ከላይ ጣራዋን፣ ከታች ወለሏን በማዳበሪያ ኮርኒስ የተለበጠች፤ ከትንሽነቷ ብዛት በስፋት ልኬት ልትጠራ የማይገባት
ቤቱ ይዞኝ ሄደ፡፡ ፍራሽና የሲዲ ማጫወቻ ብቻ ነው ያላት፡፡
“ሙዚቃ ልንሰማ... ሃሃ...ያልተበላ ብላ!” አልኩ በሆዴ፡፡
ፍራሽ ላይ ተጣበን ተቀመጠን፡፡ ካሁን ካሁን ወጣብኝ፣ ካሁን ካሁን
ሴት አደረገኝ፣ ካሁን ካሁን ከተተብኝ ብዬ ስጠብቅ በላዬ ላይ ተንጠራርቶ ማጫወቻው ውስጥ የሆነ ሲዲ ከተተ፡፡
ግርማ ይፍራሽዋን መስማት አለብሽ...! ስሚ የምር ሙዚቃ!” አለና

👍7
ጎታታ የፒያኖ ሙዚቃ ከፈተልኝ፡፡ ዝም ብዬ አየዋለሁ፡፡ በግርማይፍራሸዋ ምስጥ ብሏል፡፡ በቁሙ ምስጥ ይብላውና!
#ሙከራ_ሁለት
ሰምሃል ያጣበሰችኝ ሚኪ እየሳመኝ ነው፡፡ ሲስም እንደ ዮናታን አይደለም፡፡ ዮናታን ሲስመኝ ምላሱን የሚያደርግበት ቦታ ጠፍቶት አፌ ውስጥ ይዘፈዝፈው ነበር፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ጥርሴን ይልስበት
ነበር፡፡ እንደዛ እንደዛ ሲደርግ ሊያስመልሰኝ ይደርስ ነበር፡፡
መሳም ለካ እንዲህ ነው!
“ጎበዝ ነህ... መሳም!” አልኩት፣ የትንፋሽ መሰብሰቢያ ዕረፍት ስንወስድ፡፡ ፈገግ አለና ዝም አለ፡፡
“እንዴት... የት ተማርከው በናትህ?”
“መሳም ስሜት እንጂ ሳይንስ የለውም፡፡”
እንደገና መሳሳም ጀመርን፡፡ ዮናታን እግዜር ይይለት፡፡ ሲስመኝ
ሲስመኝ... ሲስመኝ... ነገራችን ከሰሜን ወደ ደቡብ ቢዘልቅ ተመኘሁ፡፡
ባየው አይወርድም፡፡
ባየው አይወርድም፡፡
ከንፈሬን ሙጭጭ ብሎ ቀረ፡ የትራንስፖርት ወጪ ያለበት ይመስል ሰሜን ላይ ሙጭጭ አለ። አቅበጠበጠኝ፡፡ እጁን በእጄ ይዤ ወደ ደቡብ ተጓዝኩ፡፡ ዋናው ከተማ ላይ ከተመ።
ጎሽ!...
በድንገት ግን ባልጠበቅኩት ፍጥነት ዋና ከተማውን ማተራመስ ጀመረ፡፡ ተናወጥኩ፡፡ ደነገጥኩ፡፡
እሱ ሲቸኩል እኔ አዘገምኩ፡፡
እሱ ሲፈላ እኔ ቀዘቀዝኩ፡፡
“ተው!” አልኩና ሸሸሁ፡፡
“ምነው....?” ድምጹ የሱ አይመስልም፡፡ (ድምፃቸውም ይቀየራል እንዴ)
“ሚኪ...ቨርጂን31 ነኝ”
“አውቃለሁ...”
“እንዴት..? ማለት እንዴት አወቅክ?”
“እነ ኀይለኣብ ሲያወሩ ሰምቼ ነው... ሰምሃል ነግራው ነገረችኝ ብሎ ነገረኝ...”
“ምኑን...?”
“ያው ቨርጂን እንደሆንሽ እና 'ዲስቨርጅ' መደረግ እንደምትፈልጊ....”
ራሴ ዞረ፡፡
“ዲስቨርጅ መደረግ እንደምትፈልጊ” በሚለው አባባል ራሴ ዞረ፡፡
ልክ እንደሚፈለጥ ኮብል ስቶን፣ እንደሚፈታ ሳይመልቲኒየስ
ኤኩዌዥን፣ እንደሚተረተር ቱባ ክር መታየቴ ራሴን አዞረው፡፡
የሰዎች በኔ ጉዳይ ተወያይቶ መወሰን፤ ሴራው፣ ቅንብሩ፣ ድርድሩ አዞረኝ፡፡
ሽሽት አልኩ፡፡ ራሴን ለመታረድ ያቀረብኩ ገራገር በግ የሆንኩ መስሎ ተሰማኝና ሽሽት አልኩ፡፡
“ምን ሆነሻል?”
“ምንም... ሬዲ አይደለሁም... እንሂድ...”
ሙከራ ሦስት አልነበረም፡፡ ከሚኪ በኋላ የተረዳሁት ነገር ከተጨማሪ ሙከራ አቀበኝ፡፡
ልጃገረድነት ሰልችቶኛል፡፡
ቦይፍሬንድ አምሮኛል፡፡
የኔ ፍቅር” መባል፤ “የኔ ቆንጆ” ተብሎ መጠራት አሰኝቶኛል፡፡
ግን ፤ ይሄን ሁሉ ስሞክር የነበረው በመገፋቴ እንጂ፣ በመፈለጌ
አልነበረም፡፡
ይሄን ሁሉ ስሞክር የነበረው ተገፍትሬ እንጂ፣ ተራምጄ አልነበረም፡፡ ይህን ሁሉ ስሞክር የነበረው በይ በይ ተብዬ እንጂ፣
በይ በይ ብሎኝ አይደለም፡፡
ነገም ይሆን የዛሬ ዓመት፣ የዛሬ አምስት ዓመት፣ የዛሬ ዐስር ዓመት (ሃሃ እዛስ ድረስ አልቆይም)፣
ድንግልናዬን ማስወሰድ ሳይሆን መስጠት ነው የምፈልገው፡፡
ድንግልናዬን መገላገል ሳይሆን አሽሞንሙኜ መሸኘት ነው የምሻው።
ድንግልናዬን ማስገርሰስ ሳይሆን መጋራት ነው የምመኘው፡፡
💫አለቀ💫
======:=:::======:==::=======
እንዴት ናቹ ውድ ተከታታዮቼ እንደሚታወቀው ትላንት በናተ ምርጫ በቻናላችን በተከታታይ እንዲቀርብ 3 መፅሀፎች አስመርጠን ነበር በዚህም #ሮዛ ከ230 ሰው በላይ ተመርጧል ከነገ ጀምሮ ይዤ እቀርባለው ከናተ ግን በየክፍሉ ከ 200 በላይ Like 👍 እፈልጋለው ምክንያቱም ስለሚያበረታን እና ምን ያህል ሰው እንደሚከታተለን ለማወቅ ይረዳናል
#ሮዛ ቁጥር_አንድ ነገ 12 ሰዓት ይጀምራል

👍4
#አውቃለሁ_አታውቂም
ስላለፈው ዘመን
መርሳት የተሳነው መከረኛ ልቤን
ባንቺነትሽ ጥጋት
ሴት እየመዘነ የከሰረው ቀልቤን
፡
ያለመሆን ህመም
በመሆንሽ ላይድን ሰርክ እንደባዘነ
በአመታት ስሌት
ከስቃዩ ሳይሽር መንፈሴ እንዳዘነ
፡
አውቃለሁ አታውቂም
አለማወቅ ጠቅሞሽ ላየወጠቅመኝ ማወቄን
ሳታውቂ ባወኩት
የመታመን ብሶት እኔ መሳቀቄን፡፡
፡
ግን እንዴት ላገግም
የህመሜ ምክንያት ሆኖ መዳኒቱ
ስቃዩ በዛብኝ
ልችለው አልቻልኩም ግራ ገባኝ እቱ፡፡
፡
ለዛ ነው ሁል ጊዜ
የጀመርኩት መንገድ ደርሶ ላያደርሰኝ
በዛሬው ዓለሜ
ነገን ብናፍቅም አምና እየታወሰኝ
መኖር የታከተ
ሰቀቀናም ልቤ መሞቻውን ናፍቆ
አመታት ያለፉት
በመኖር እሳቤ ከመሞት እርቆ፡፡
ስላለፈው ዘመን
መርሳት የተሳነው መከረኛ ልቤን
ባንቺነትሽ ጥጋት
ሴት እየመዘነ የከሰረው ቀልቤን
፡
ያለመሆን ህመም
በመሆንሽ ላይድን ሰርክ እንደባዘነ
በአመታት ስሌት
ከስቃዩ ሳይሽር መንፈሴ እንዳዘነ
፡
አውቃለሁ አታውቂም
አለማወቅ ጠቅሞሽ ላየወጠቅመኝ ማወቄን
ሳታውቂ ባወኩት
የመታመን ብሶት እኔ መሳቀቄን፡፡
፡
ግን እንዴት ላገግም
የህመሜ ምክንያት ሆኖ መዳኒቱ
ስቃዩ በዛብኝ
ልችለው አልቻልኩም ግራ ገባኝ እቱ፡፡
፡
ለዛ ነው ሁል ጊዜ
የጀመርኩት መንገድ ደርሶ ላያደርሰኝ
በዛሬው ዓለሜ
ነገን ብናፍቅም አምና እየታወሰኝ
መኖር የታከተ
ሰቀቀናም ልቤ መሞቻውን ናፍቆ
አመታት ያለፉት
በመኖር እሳቤ ከመሞት እርቆ፡፡
❤1👍1
#ሮዛ
👇
👇
የቡና ቤት ሕይወቷን የተመለከቱ
አስገራሚ የዕለት ማስታወሻዎች
ከአዲስ አበባ ቪላዎች እስከ ሙአመር
ጋዳፊ ድንኳን
👉ከ 18 ዓመት በታች ከሆኑ ባታነቡት ይመረጣል ግን እንዲህ ሲባል ያጓጓል አደል እኔ ግን ተናግሬለሁ።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
«ከሾፌር፣ ከሴተኛአዳሪ፣ ከዘበኛእና ከቤት ሰራተኛ የምታመልጥ አንዳቸም የዓለም ሚስጢር የለችም»
#ክፍል_አንድ
፡
#ኮሌጅ_በጠስን
አሁን "ድንግልናዬ ሳይበጠስ ነው ኮሌጅ የበጠስኩት” ብል ማን ያምነኛል?ማንም፡፡ ስለዚህ አላወራም፡፡
አልናገርም፡፡ ዝም፣ ጭጭ፡፡ ኮሌጅ መበጠሴን ራኪ ብቻ ናት የምታውቀው፡፡ ሌሎቹ ባልደረቦቼ መጸሐፍ የማነብ አካባጅ ሸሌ እንጂ ኮሌጅ የበጠስኩ ሸሌ እንደሆንኩ አያውቁም፡፡ ራኪ ለራሷ ሲነሳባት ”…ኡኡቴ ኮሌጅ በጥሶ ሸሌ መሆን ብርቅ ነው እንዴ!” እያለች ካባዬን ታንኳስሰዋለች፡፡ ለነገሩ እውነቷን ነው፣
ምንም ብርቅ አይደለም፡፡ ግቢ ሳለን ከነበርነው ሴት ተማሪች ሲሶ ያህሉ ከወንዶች ጋር ይወጡ የነበረው
ለገንዘብ ሲሉ ነበር፡፡ ስለዚህ መንግስት ባያውቃቸውም ሸሌዎች ነበሩ፡፡ ብዙ ጓደኞቼ እንዳይጫሩ ሲሉ ብቻ ለአስተማሪዎቻቸው ጭናቸውን በልጥጠው ሰጥተዋል፡፡ ገላቸውን መስዋእት አቅርበዋል፡፡ ስለዚህ
ሸሌዎች ነበሩ፡፡ እንዲያሁ የአነጋገር ልማድ ሆኖብን ነው እንጂ ሸሌ ለመባል ቡና ቤት ገብቶ መመናቀር የግድ ነው እንዴ?
ከተመረቅን ስንት ዓመት ሆነን ማለት ነው? ጊዜው እንዴታባቱ ነው የሚበረው?
ኮሌጅ የበጠሱ የኔ ባቾች» እንዳሁኑ ዘመን ተመራቂዎች ሁሉም ኮብልስቶን አንጣፊ አልሆኑም
በባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎችአልጋ አንጣፊ የሆኑም አሉ፡፡ እንደኔ እና እንደ ወይንሸት የተማረ ሸሌ ኾነው የቀሩም አሉ፡፡ እንደ መዲና፣እንደ ራሄል፣እንደ ፎዚያ፣ እንደ ሂዊ፣እንደ ጠይባ አረብ አገር ለግርድና የሄዱም አሉ፡፡እንደ አብዱሰመድ(ወሎዬው) በአካውንቲንግ ተመርቀው የመን አገር ፍየል ለማገድ
የተሰደዱም አሉ፡፡እንደምስኪኑ ሀብትሽ ሰፈር ዉስጥ ጸጉር አስተካካይ የሆኑም አሉ፡፡ ሀብትሽ
« አታካብዱ ያውነው፣ድሮም በጭንቅላቴ ነበር የምሸመድደው አሁንም ጭንቅላት ነው የምከረክመው፤
አሁንም ድሮም ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት ነኝ፣!» እያለ ራሱ ላይ ይቀልዳል፡፡የክላስ ልጆችን ሳስብ እንደ
ሀብትሽ አንጀቴን የሚበላኝ ሰው የለም፡፡ሀብትሽ ለአራት ዓመት «ስፔስ» እየተመላለሰ፣ዓይኑ እየተጨናበሰ፣
እንቅልፍ እንዳያሸንፈው እግሩን በሳፋ እየዘፈዘፈ፣ሌተ ቀን ትምህርቱን ሲሸመድድ ቢኖርም ያቺ ቆሽማዳ
ሕይወቱ ፈቀቅ አላለችም፡፡
የተመረቅን ሰሞን 4ኪሉ ኢንተርኔት ቤት አግኝቼው ሲቪውን ፕሪንት ለማድረግ ሳንቲም ቸግሮት ሰጥቼዋለሁ።እንዴት እንዳሳዘነኝ!! ሀብትሽ ሲቪውን ያላስገባበት የመንግስት መስሪያቤት ቢኖር የአገር ደህንነት ሚኒስትር ብቻ ይመስለኛል፡፡ለህክምና ዶክተር የወጣ ክፍት የሥራ ማስታወቂያ ካየ እሱን
ባይመለከተውም ሲቪውን ከማስገባት ወደኃላ አይልም፤«የሚሆነው አይታወቅም፣አመልካች ሲያጡ
ይጠሩኛል፡፡»ይላል።የሆነ ሰሞንማ ይሄ ልጅ በቃ ለየለት ብለን ነበር፡፡ቁርስ እና እራት መብላት የቻለውም «ፖሊዮ» በሚለው ስራው ነው፡፡ቤት ለቤት ህጻናትን እየዞሩ ማስጠናት፡፡እሱም ቢሆን
ሲናገር ስለሚንተባተብ ትንሽ እንደሰራ ወላጆች ልጆቻችንን ተብታባ ያደርግብናል እያሉ ያበርሩታል፡፡
ሚስኪን ሀብትሽ!!
እንዳለመታደል ሆኖ ለአመታት ሲባዝን አንድም የሚቀጥረው ድርጅትአጣ፡፡ዉልና ማስረጃ ለተላላኪነት የወጣ ክፍት የስራ ቦታ ሁሉ ተወዳደሮ «ኦቨር ኳሊፋይድ ነህ በሚል ስለጣሉት ተስፋ ቆረጠ...ተስፋ ከመቁረጥ ጸጉር መቁረጥ ይሻላል ብሎ ነው መሰለኝ ሰፈር ውስጥ ባለች አንዲት ትንሽ ጸጉር ቤት ተቀጠረ፡፡ለነገሩ «ግቢ» እያለንም እርሱ ነበር የአብዛኛውን ተማሪ ጸጉር የሚላጨው፡፡ሰው በምን እንጀራ እንደሚወጣለት አይታወቅም፣አንዳንዱ በትምህርት ሌላው ደግሞ በሰው አናት ላይ በሚበቅል ጸጉር እንጀራ ይወጣለታል፡፡ይኸው ሀብትሽ አራት አመት ክፍል ገብቶ ከተማረው ትምህርት ይልቅ ስራ ሲፈታ የግቢ ተማሪዎችን ጸጉር በመከርከሙ ዛሬ በልቶ ለማደር በቃ፡፡እኔም ከተማርኩበት ዩኒቨርስቲ ይልቅ የህይወት ስንቅን የሚሰፍርልኝ ያልተማርኩሰት ቡና ቤት ሆነ፡፡
ሀብትሽ ከሁሉ ከሁሉ በማዕረግ መመረቁን ሲያስብ መማሩ የእግር እሳት ይሆንበታል፡፡ከርሱ ባነሰ ውጤት
የተመረቁት ሀፍቶምና ሌሊሳ የህዉሀትና የኦህዴድ ፓርቲ አባልነት ስለተመዘገቡ ብቻ "ዉጭ ጉዳይ" በአሪፍ ብር ተቀጠሩ፡፡ሀብትሽ እባል ሁን ሲባል "ኃይማኖቴ አይፈቅድም” ብሎ ቀለደ፡፡አሁን ይኸው ህይወት በተራዋ የምር ትቀልድበታለች፡፡የሚያሳዝነኝ ግቢ እያለን እናቱን ለመርዳት የነበረውን ጉጉት
ሳስብ ነው፡፡አሁን የማንንም መሀይም ፎሮፎር በሻምፑና ለብ ባለ ዉሀ እያጠበ በወር ዘጠኝ መቶ ብር ይከፈለዋል አሉኝ፡፡
ምስኪን ሃብትሽ፡፡አንዳንዴ ምን አስባለሁ…? “ሴት ኾኖ በተፈጠረና እንደኔ ገላውንም ቢሆን ቸርትሮ ባለፈለት…” እላለሁ፡፡
ምነው ግን ሀብትሽን እንዲህ በስፋት አሰብኩት? በስቅታ መሞቱ ነው ዛሬ፡፡ ለነገሩ ግቢ ሳለን ጀምሮ መጠነኛ «crush» ነበረኝ፡፡ለማንም ግን አልተናገርኩም በወቅቱ፡፡ እሱም የሚያቅ አይመስለኝም፡፡ካፌ የሚገባበትን ሰዓት ጠብቄ ከፊትለፊቱ እቀመጥና የአይኔን ረሀብ አስታግሼ ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ ዶርሜ አቀና ነበር፡፡ለምን እንደሆነ አላውቅም የሆነ ነገሩ ደስ ይለኛል፡፡ብዙዉን ጊዜ ልቅም ያለ ቆንጆ ወንድ አይስበኝም፡፡«ወንድ» በመሰረቱ የሆነ ነገሩ የማያምር እና ኮስታራ ነገር ሲኖረው ነው ወንድ» የሚመስለኝ፡፡
ቬተሪነሪ ዲፓርትመንት የነበረው አኒስ ለምሳሌ የሴት ጓደኛዬ ነበር የሚመስለኝ እንጂ አንድም ቀን እንደ ወንድ ቆጥሬው አላውቅም፡፡ለምን ሱሪ እንደሚታጠቅም እንጂ፡፡መልኩ መካከለኛ ቀይ፣ቁጭን
እና ስስ ከንፈር የነበረው አኒስ የሀረር ቀላዳምባ ልጅ ሲሆን ቤተሰቦቹ አደሬዎች ናቸው፡፡ሰልካካ አፍንጫና
ሉጫ ጸጉር አለው፡፡ግቢ ውስጥ ነጠላ ጫማ መጫማት ያዘወትር ነበር፡፡ክንዱ የተላገ ይመስል ጡንቻ የሚባል ነገር አልፈጠረበትም፡፡በዚያ ላይ ይቅለሰለሳል፡፡እንዴት ይዘገንነኝ አንደነበረ!! ዩኒቨርሲቲ እያለን
አንድም ቀን ብር ቸግሮት አያውቅም፡፡ብዙ ዘመዶች ካናዳ አሉት፡፡የካናዳ ዶላር እየቆነጠሩ ይልኩለታል፡፡
በዚያ ላይ ቤተሰቦቹ የመስጊድ ምንጣፍ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ «non cafe » ስለነበረ አንዳንዴ እኔና የዶርም
ጓደኛዬን ሂንዲያን ልጋብዛችሁ እያለ ከግቢ ይዞን ይወጣ ነበር፡፡የካፌ ምግብ ስለሚያንገሸግሸን ግብዣውን አይናችንን ሳናሽ እንቀበለዋለን፡፡
እኛ ቢራ ስናዝ እርሱ ሚሪንዳ ያዛል፡፡ቅፍፍ ነበር የሚለኝ ሚሪንዳ ሲያዝ፡፡አኒስ በሚሪንዳ አይደራደርም።
ሚሪንዳ የለም ከተባለ ቤት እንቀይር ይላል፡፡ሲያስጠላ!!… አንዳንዴ ሰውነቱ ውስጥ በደም ፋንታ ሚሪንዳ
የሚዘዋወር ነው የሚመስለኝ፡፡ ወንድ ልጅ ወይ ቢራ ወይ ኮካ ነው መጠጣት ያለበት፡፡እንዴት ሚሪንዳ ይዞ ይሟዘዛል!? እኛ ቢራ ስንደግም እሱ ያቺኑ ሚሪንዳ እየተቅለሰለሰ ይጎነጫል፡፡ሂንዲያ ይሄ ባህሪው ስለሚያናድዳት " ..አኒስ ሚሪንዳ ድገም እንጂ.…አንድ ያጣላል
one for the road!» እያለች ሙድ
ትይዝበታለች፡፡እሱ ግን አይገባውም ይስቃል፡፡«ጥርስህ ይርገፍ›› እለዋለሁ በሆዴ፡፡አኒስ ምግብ ሲበላ ጉርሻው ያሳቅቀኝ ነበር፡፡እንደ ሴት እየተቅለሰለሰ ትንንሽ ሲጎርስ ከሂንዲያ ጋር እየተጠቃቀስን እንስቃለን ጥሎበት እይጥና ጸብ በጣምይፈራል፡፡የዶርሙ ልጆች እንደሚያወሩት ከሆነ

👍9❤1
የሆነኝን ቀን በዶርማቸው መስኮት ትንሽዬ እይጥ ገብታ በማየቱ እኒስ ራሱን ስቶ ወደቀ፡፡በስንት ርብርብ ዉሀ ደፍተውበት ከነቃ
በኃላ ለተማሪዎች ዲን ወደ አይጥ የሌለበት ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንዲመደብ የሚጠይቅ ደብዳቤ ማርቀቅ
ጀመረ፡፡ያረቀቀውን ደብዳቤ የዶርሙ ልጆች ኮፒ አድርገው
ካፌ በር ላይ ለጥፈውበት ለአንድ
ሳምንት ሲሳቅበትና የግቢው ሙድ መያዣ ሲሆን ነገሩን እርግፍ አድርጎ ተወው፡፡
እንደ አይጥ ባይሆንም አኒስ ጸብ በጣም ነው የሚፈራው፡፡አንድ ቀን እንደተለመደው እኔና ሂንዲያን
ቢራ ጋብዞን እርሱ ሚሪንዳውን ፉት እያለ ከፊት ለፊታችን የነበሩ ሁለት ጎረምሶች ከአስተናጋጅ ጋር መልስ
« አልሰጠኸንም ሰጥቻለሁ› በሚል ካፌው ውስጥ አምባጓሮ ይፈጠርና ቤቱ ቀውጢ ይሆናል፡፡አኒስ ከመቅጽበት ተሰወረብን፡፡የት እንደገባ አጣነወ፡፡በኃላ አገር ሰላም ሆኖ ነገሩ ሁሉ ከበረደ በኃላ አኒስ ከሽንት ቤት በኩል ሲመጣ አየነው፡፡
«አንተ የት ተሰወርክ፣የፔፕሲ ፍሪጅ ውስጥ ሁሉ ስንፈልግህ ነበር አኮ!» እኛን ጥለህን ትፈረጥጣለህ እንዴ?»አለችው ሂንዲያ፡፡
«እንዴ! … ምን ማለትሽ ነው! በሚሪንዳ ጠርሙስ ጭንቅላቴን ቢሉኝስ…ሞኝ ነሽ እንዴ! » አላት፡፡
ከሂንዲያ ጋር በሳቅ ተንከተከትን፡፡ያን ቀን በጣም ስለሳቅንበት ለጓደኞቹ ነገሩን እንዳንናገርበት ስለፈራ እስከንፈነዳ ድረስ ጥብስና ቢራ ጋበዘን፡፡በሱ ቤት እየደለለን ነው፡፡አፍንጫውን ይላስ፡፡ማታ ጠብቀን ዶርም ለጓደኞቻችን ነገሩን በጣም አጋነን አወራንላቸው……
«አኒስ ፀብ ሸሽቶ የሚሪንዳ ጠርሙስ ውስጥ ተደብቆ ተገኘ» ብለን በስፋት አስወራን፡፡ይህን ወሬ ተከትሎ
ሴቶች ዶርም ለአንድ ሳምንት በአኒስ ዙርያ ብዙ አዳዲስ ጆኮች ተፈበረኩ፡፡
«አኒስ ሲያገባ በሻምፓኝ ፋንታ ሚሪንዳ ነው የሚረጨው…»
«ሰማችሁ.!? አኒስ የተማሪዎች ክሊኒክ ሄዶ «yellow fever» የሚባል ከወባ
የተለየ አዲስ አይነት በሽታ
«ዳያግኖስ» መደረጉን?፡፡የበሽታው ተህዋሲያን የሚራቡት በምን ምክንያት ቢሆን ጥሩ ነው?…Excessive
usage of Mirinada
ከዚያን ቀን በኃላ ግቢ ውስጥ «አኒሳ ማሪንዳ» የሚል ቅጽል ስም ተሰጠው፡፡ ሂንዲያ ደግሞ ግቢ ውስጥ ባየችው ቁጥር
አንተን በሚሪንዳ ጠርሙስ ነበር ግንባርህን ማለት» እያለች ታሾፍበታለች፡፡እየተቅለሰለሰ ይስቃል፣አይገባውም፡፡ዱንዝ!
እንደኔ እንደኔ አኒስን «ዴት» የምታደርግ ሴት ሌዝቦ» መሆን አለባት፡፡ወንድ እንዴት ሚሪንዳ ይጠጣል
አኒስ እኮ ሻይ ቡና ልጋብዛችሁ ለማለት ሲፈልግ እንኳ ሚሪንዳ» ልጋብዛችሁ ነው የሚለው እንዲህ አይነት ወንድ ለምን አንደሆነ አላውቅም turn off ያደርገኛል፡፡አመታትን የኃሊት ተጉዤ ስለ
አኒስ እንዳስብ ያደረገኝ ዛሬ የተዋወቅኩት ዑስማንዘ ፒምፕ» ነው፡፡ ቅላቱና አረብ የሚመስለው ሰውነቱ
የካምፓሱን አኒስን አስታወሰኝ፡፡ወንድሙ እንዳይሆን ሁሉ ሰግቼ ነበር፡፡በመልክ ከመመሳሰል በስተቀር
ኡስማን በሁሉ ምግባሩ ከአኒስ ጋር ፍጹም ተቃራኒ ሰው ሆኖ ሳገኘው ግን ተገረምኩ፡፡
#Usman_the_pimp
ኡስማን ደላላ ነው፤ሴትና እፅ አቅራቢ ደላላ፡፡ዶላር የሚንተራስ ደላላ፡፡ሪያል የሚጫማ ደላላ፡፡ቀሽት የሀበሻ ሴቶችና ወንዶችን ለዜጎች የሚያቀርብ ደላላ፡፡ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ አረቦችን መበቀል
የሚወድ ደላላ፡፡ዑስማን የሴት ብቻ ሳይሆን የቡሽቲ ደላላም ነው፡፡ ጫት የሚሸጥ ነጋዴ አብሮ ስኳርና
ሲጋራ እንደሚሸጠው ሁሉ ኡስማንም ሴት እየነገደ በጎን ቡሽቲ ያሻሽጣል፡፡ ሰዶም የውጭ ዜጎች ወደ
አዲሳባ ሲመጡ ሰዶም ሀበሾችን ያገናኛቸዋል፡፡ “አይደብርህም ግን ከቡሽቲዎች ጋር ስትሰራ” ሲባል
‹‹መብታቸው ነው፣እኔ በነሱ ቂጥ ምናገባኝ» ይላል፡፡ ይቀጥልና ደግሞ «« ጫት ለምሳሌ ጎጂ ነው፣ መንግስት
ግን ይቸበችበዋል…ልክ እንደዛ ማለት ነው» ይላል፡፡ ያዲሳባን ጓዳ ጎድጓዳ የሱን ያህል የሚያውቅ ሰው አላውቅም፡፡አስር ዓመት በ«ቱርጋይድነት ሰርቷል፡፡ደግሞ ዑስማን የልምድ አዋላጅ አይደለም! በግየዳ ሞያ የበቃ፣የነቃ Professional ገያጅ ነው::ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኝ«ሲቲቲአይ ከሚባል ትምህርት
ቤት በምርጥ ውጤት ተመርቋል፡፡እንግሊዝኛን፣ፈረንሳይኛን እና አረብኛን አቀላጥፎ፤ጣልያንኛን ደግሞ
እንደነገሩ ይናገራል፡፡ስድብ የሚቀናው ግን በጣሊያንኛ ነው፡፡‹ጣሊያንኛ ባይኖር ምን ይውጠኝ ነበር!»
ይላል ሁልጊዜ ተሳድቦ ሲጨርስ፡፡እንደ ጣሊያንኛ ለስድብ የሚመቸው ቋንቋ የለም፡፡ሲነሳበት
«ባፋንኩሎስትሮንዞ! ካዞ! ፖርኮ! ታና! ይለናል» እኛ ትርጉሙ ስለማይገባን እንስቃለን፡፡ እሱ ግን
እስኪወጣለት በስድብ ያጥረገርገናል» እኔ ራሴ ‹‹ባፋንኩሎ » የምትለዋን የዘውትር ስድቤን የተማርኩት
ከዑስማን ነው፡፡ እንደዚያ ብዬ ስሳደብ ንዴቴ ይወጣልኝ ጀመር፡፡በተረፈ ዑስማን በጣም ትሁት፣ በጣም
ዘናጭ፣ሽቅርቅርና መልከ መልካም ነው፡፡ርዝመቱና ቅላቱ የተመለከቱ ጓደኞቼ «ከዚህ ክልስ ጋር ደሞ ምን
ጀመርሽ ይሉኛል? ግን እኮ ኡስማን ክልስ አይደለም፡፡ በመጀመሪያዎቹ የምረቃው አመታት አውሮፓዊ እና አሜሪካዊ ቱሪስቶችን ሙርሲ እና ሐመር አንዳንዴም
አልፎ አልፎ ደግሞ ጂንካ በመውሰድ አስጎብኝቷል፡፡ለሶስት ዓመታት ያህል በተለያዩ የመንግስትና የግል
አስጎብኚ ድርጅቶች ውስጥም በአማካሪነት ሰርቷል፡፡ቀጠለና የሚሰራበትን ድርጅት ሳይለቅ በጎን ራሱ
እየተጻጻፈ ቅዳሜና ዕሁድ ለሀብታም ቱሪስቶች ሲቲቱር» መስራትጀመረ፡፡ ለምሳሌ ከሆሊውድ ታዋቂ
ሰዎች ሲመጡ እሱ ነው ሁሉንም ሀላፊነት የሚወስደው፡፡ ከ«ቻናል ኤን እና ከ«ኤም ቲቪ» እንዲሁም
ከ ቢግ ብራዘር አፍሪካ የመጡ ታዋቂ የቲቪ አስተዋዋቂዎች ጋር ሙሉ ኮንትራት ወስዶ እንዳስጎበኘ
ነግሮኛል፡፡ እንደውም ስማቸውን ጭምር ነግሮኝ ነበር ማስታወስ አይሆንልኝም አንጂ፡፡ በዚህም ጠርቀም ያለ ሳንቲም መሰብሰብ ቻለ፡፡በሂደት ግን ሁሉንም ቱሪስቶች አንድ ነገር እንደሚያመሳስላቸው ተረዳ
ሁሉም ወንድ ቱሪስቶች ለሀበሻ ሴት ይሸነፋል፡፡ ብዙ አረቦች ሀበሻ ሴት ሲያዩ ለሀጫቸው ይዝረከረካል
ሌላም ነገር ተማረ፡፡ሁሉም ወንድ ቱሪስቶች ሲመሽ ብቻቸውን ማደር አይፈልጉም፡፡ሌላም ነገር ተማረ
ሁሉም ቱሪስት ሀብታም እንዳይደለ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት ሽማግሌ አውስትራሊያውያን ባልና ሚስት ቱሪስቶችን የአንድ ቀን ሲቲቱር ከሰራላቸው ሰኃላ ዘወትር እንደሚያደርገው የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግብና የቡና ስነ ስርዓት እንዲያዩ በሚል ቦሌ አካባቢ ከሚገኝ «ሕብር የባህል ቤት» ይዟቸው ይሄዳል፡፡በዚያ እንጀራ በዶሮ ወጥ ከተሠገቡ በኃላ የቡና ማፍላት ስነስርዓት ከሚካሄድበት አዳራሽ ይወስዳቸዋል፡፡ስኒ ተደርድሮ የጀበና ቡና እየተፈላ ሳለ ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ፡፡በባህል ልብስ ተውባ ቡና የምታፈላዋ ጠይም ቆንጆ የአውስትራሊያውን
ሽማግሌ ልብ ቀጥ አደረገችው፡፡ሽማግሌው በዉበቷ ተሸነፉ፡፡ “ሰ80 ዓመት ዕድሜዬ ሁሉ እንደዚህ የምታምር ፍጡር የትም አላየሁም” አሉ፡፡ የተደረደሩትን ስኒዎች ፎቶ የሚያነሱ መስለው ልጅቷን በተደጋጋሚ ፎቶ ያነሷት ጀመር፡፡ ኡስማንም ሽማግሌው ቡና በምታፈላዋ ኢትዮጵያዊት መማረካቸውን
አላጣውም፡፡ኾኖም በዚህን ያህል ደረጃ ይሆናል ብሎ በፍጹም አልጠበቀም፡፡እርሳቸው እንደሚሉት እንደዚህ አይነት ስሜት ተሰምቷቸው የሚያውቀው ከ68 ዓመት በፊት የኩዊንስላንድ የሆልቲካልችር የእንደኛ አመት ተማሪ ሳሉ ነው፡፡ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያፈቅሩ የተሰማቸው ስሜት ዛሬ ይሆናል
ብለው ባልጠበቁት ቦታና ሁኔታ ዳግም ኢትዮጵያ ውስጥ ተሰማቸው፡፡ከዚያን ሁሉ ዘመን በኃላ:127 አገራትን ከጎበኙ በኃላ፡፡ ያንኑ ቀን ማምሻውን ኡስማን

👍7❤2
ከሚስታቸው ለይተው በመውሰድ ይህችን ቡና የምታፈላዋን ኢትዮጵያዊትን እንዲያስተዋውቃቸው በጽኑ ይለምኑታል፡፡ኡስማን ልመናቸው ብዙም
አልገረመውም፡፡የሰጡት ጉርሻ ግን በፍጹም በህይወቱ ይሆናል ብሎ ያልጠበቀው ነበር 15ሺ ዶላር
ዑስማን ያን ምሽት እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነጋ፡፡መላ መዘየድ ያዘ፡፡አውስትራሊያው ሽማግሌ
በሀገራቸው ታዋቂ የመካናይዝድ ፋርም ባለቤትና ቢጠሯቸው የማይሰሙ ሚሊየነር ገበሬ እንደሆኑ ስማቸውን «ጉግል በማድረግ ለማወቅ ቻለ፡፡ይህችን ጠይም ቆንጆ ለኚህ ሽማግሌ ቢያስረክብ ሌላ ብዙ እጥፍ የዶላር ጉርሻ እንደሚቀርብለት አላጣውም፡፡ልጅቱን እንዴት ሊያሳምናት እንደሚችል ማውጠንጠን ያዘ
በጠዋት አድራሻዋን ከካሸሪዎች አፈላልጎ ደወለላት፡፡ለጥብቅ ጉዳይ እንደሚፈልጋት ነገራት
ላፓሪዝያን ካፌ ተገናኙ፡፡እንዴት የ80 ዓመት ሽማግሌ አፈቀሩሽ ብሎ ይንገራት?ሲያወጣ ሲያወርድ ቆይቶ
ሌላ መንገድ አልከሰትልህ ሲለው ነገሩን አፍረጥርጦ ነገራት፡፡አራስ ነብር ሆነችበት፡፡ያዋረዳት የናቃት
ያህል ተሰማት፡፡ጥላው ሄደች፡፡ኡስማን ተስፋ አልቆረጠም፡፡ የኔም የሷም ህይወትላንዴና ለመጨረሻጊዜ
መለወጥ አለበት ብሎ ስላመነ ሌላ መላ ዘየደ፡፡ለአይን ያዝ ሲያደርግ ወደ ምትሰራበት «ሕብር ባህል»ቤት
አመራ፡፡እርሱ ካገኘው የ15ሺ ዶላር ውስጥ 5 ሺውን ቢያልሳት አይኗን ሳታሽ እሺ እንደምትለው አምኖ
ነበር ያናገራት፡፡እርሷ እሺ ካለችው ሌላ ብዙ እጥፍ ጉርሻ እንደሚጠብቀው አላጣውም፡፡ሄዶ በድጋሚ
አናገራት፡፡ፊት ነሳችው፡፡የምታፈቅረው ጓደኛ እንዳላት በጨዋ ቋንቋ ልታስረዳው ሞከረት፡፡ሀሳቧን ለማስለወጥ አምስት ሺ ዶላር አቀረበላት፡፡ይህን ጊዜ ስኒ ያለቀለቀችበትን እጣቢ ዉሀ ሰው በተሰበሰበበት ፊቱ ላይ ደፍታ አዋርዳ አባረረችው፡፡በፍጹም ለገንዘብ የማትሸነፍ ሴት ትኖራለች ብሎ አስቦ አያውቅም
ነበር ኡስማን፡፡ደነገጠ፡፡ኾኖም በልቡ አከበራት፡፡
አንድ የመጨረሻ ሙከራ ማድረግ እንዳለበት አመነ፡፡ ቦይ ፍሬንዷን ከየትም እፈላልጎ አገኘው በአንድ ቄራ መብራት ኃይል አካባቢ በሚገኝ ጋራዥ ውስጥ ብሎን መግጠም ነው ስራው 10 ሺህ ብር እጁ ላይ አስቀመጠለት፡፡ ልጁ ሰው የመግደል ግዳጅ ሊሰጠው እንጂ እንዲህ ለቀላል ዉለታ ይህን ያህል ብር
ይሰጠኛል ብሎ በጭራሽ አላሰበም፡፡ ሄዶ ዑስማን በነገረው መሰረት ፍቅረኛውን አበሻቅጦ ተጣላት
..በምን ምክንያት እየተጣላት እንደሆነ ግን አልነገራትም፡፡ በቃ እንደዚህ ጠብሽ እየወገረኝ ካንቺ ጋር
ልቀጥል አልችልም፤ ህይወቴ ሲለወጥ እደውልልሽና ፍቅራችንን እንቀጥላለን አላት፡፡ ክፉኛ አለቀሰች፡፡
"እጠብቅሀለሁ፤ ህይወትህ ሲለወጥ ግን ከኔ ጋር እንደምትቀጥል ቃል ግባልኝ” አለችው፡፡ ደነገጠ፡፡ እሷን
ተስፋ ለማስቆረጥ ያደረገው ሙከራ ያልተፈለገ ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ሲረዳ ነገሩን አፍረጥርጦ ነገራት
የተቀበለውን 10 ሺ ብር አሳያት፡፡ ዑስማንን እሺ እንድትለው በቻለው አቅም ሁሉ ሊያሳምናት ሞከረ፡፡
ነብር ሆነች፡፡ እንዲህ ትወደኛለች ብሎ ከዚህ በፊት አስቦ ስለማያዋቅ በነገሩ ተገረመ፡፡
ኡስማን ለሽማግሌው የሆነውን ሁሉ አረዳቸው፡፡ሽማግሌው ግን ዑስማንን ገሰጹት፡፡ በብር ገዝተህ አምጣት መች አልኩህ ብለው ተቆጡት፡፡ ልጅቷን ደግሞ ይበልጥ አፈቀሯት፡፡ለዘላለሙ ከልቤ ትኖራለች ብለው ከዋሌታቸው ፎቶዋን አውጥተው አሳዩት፡፡በብዙ ነጮች መሐል በስኒዎች ተከባ ቡና ስታፈላ
ያነሷትን ፎቶ ስራዬ ብለው አሳጥበውታል፡፡ኡስማን ተገረመ፡፡ሽማግሌው አማዞን ”ማቹፒቹን” ለማየት
በነገታው ወደ ብራዚልእንደሚበሩ ነገሩት፡፡ከዚያ በፊት ግን አደራ ብለው 10 ሺ ዶላር እና በአውስትራሊያ
የቤታቸው አድራሻ ያለበትን ካርድ ሰጡት፣ለጠይሟ ቆንጆ እንዲሰጥላቸው፡፡ከጀርባው
<<Dear beautiful, I had a crush on you at the age of 80. Do you believe it? Thank you for
making me younger>> ብለው ጽፈውበታል፡፡
የዑስማን የሴት ድለላ ኢምፓየር ለ ልጅቷ እንዲሰጥ አደራ በተባለው 10 ሺ ዶላር ካፒታል ተመሰረተ፡፡
ከሽማግሌው በአደራ መልክ የተሰጠችው ካርድ የመስታወት ፍሬም ተሰርቶላት ዛሬም ድረስ አትላስ ጋ
በሚገኘው በኡስማን ቢሮ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጣ ትታያለች፡፡ኡስማን አደራውን በላ፡፡ከዚህ በኃላ ምንም የሚያስፈራው ነገር የለም፡፡ሁሉም ሰው የሆነ ቦታ በሆነ ሁኔታ አደራውን ይበላል፡፡ቃሉን ያጥፋል፣
ይባልጋል፣ ይዋሻል፡፡ከያንዳንዱ ብልጽግና በስተጀርባ አንድ ወንጀል አይጠፋም፡፡ ከቱሪስት ደንበኞቹ
በየጊዜው የሚማረውም ይሄንኑ ነው::ሚስቶች ይወሰልታሉ፣ባሎች ይባልጋሉ፤አረቦች ሚስቶቻቸውን
በሻሽ ከናንበው እያኖሩ እዚህ መጥተው የሀበሻ ቀሚስ ይገልባሉ፡፡ያመነዘረ ያለ ርህራሄ በድንጋይ ተወግሮ
እንዲገደል የሚፈርደው አረብ አዲሳባ «ገስትሀውስ»ውስጥ ሶስት ሴት ይዞ ያድራል፡፡ሁሉም ሰው አደራውን ይበላል፡፡ቃሉንም ያጥፋል፡፡ በሆነ አጋጣሚ፣ ሀኔታና ቦታ፡፡
ኡስማን ህይወቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተቀየረ፡፡ሴት መደለሉን የሙሉ ጊዜ ስራው አድርጎ ያዘው::
ነገር ግን ተራ ድለላ መሆኑ ቀረ፡፡ ብዙ የዶላር የዲርሃምና የሪያል ልውውጥ የሚካሄድበት ኢንደስትሪ ሆነ
ባለ አምስት ኮከብ ደላላ ሆነ፡፡ በሱ እድገት የሚቀኑበት እሱ "የእምስ ፕሮሞተር ነው” ይላሉ፡፡ ኡስማን
ግን ድንቅ ፕሮፌሽናል ሰራተኛ ነው፡፡ ሁለት የሚፈላለጉ ሰዎችን አገናኝቶ በነሱ ደስታ የሚበለጽግ ታታሪ ሰራተኛ፡፡
ነገርየውን ህጋዊ ሽፋን እንዲሰጥለት ግን የጉዞ ወኪል ቢሮ ከፈተ፡፡የቱሪስቶችን ስነልቦና ቅርጥፍ አድርጎ
በላው፡፡ሁሉም ወንድ ቱሪስት በሀበሻ ሴት ይሸነፋል፡፡አብዛኛው ቱሪስት የላሊበላን ፍልፍል ድንጋይ ለማየት ሳይሆን ሴቶቻችንን ጭን ለመፈልፈል እንደሚመጣ ተረዳ፡፡ አብዛኛው ቱሪስት አክሱምን ከማየቱ በፊት ሴቶቻችንን ሲያይ ወንድነቱ እንደ ሀውልቱ እንደሚቀሰርበት ተረዳ፡፡ አብዛኛው አሜሪካዊ ቱሪስት
ገንዘብ ያለምክንያት እንደማይበትን በጊዜ ሂደት ተማረ፡፡ገንዘብ የሚበትን ህዝብ አረብ እንደሆን አወቀ
አረቦች ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ መስራት ጀመረ፡፡ገስት ሀውሶችን እያደነ መከራየት ያዘ አረብኛን አቀላጥፎ ለማውራት የሚያስችሉ አጫጭር ስልጠናዎችን ወሰደ፡፡ዱባይ ለሁለት እና ሶስት ወራት እየሄደ በመቀመጥ ቋንቋውንም ህዝቡንም በደምብ አጠና፡፡ተሳካለት፡፡አሁን ማንኛውም አስጎብኝ ,
ከሚያስገባው ገቢ በብዙ እጥፍ አንድ ኡስማን ያገኛል፡፡
ዑስማንን ጥሎበት ፈረንጅ አሮጊቶች ይወዱታል፡፡ብዙዎቹ ወደአገራቸው ሲመለሱ የማያልኩለት ነገር የለም፤ዶላር፣ዩሮ፣ፓውንድ፣አይፎን ላፕቶፕ፣ smart phone ለአይን የሚያሳሱ ቅንጡ ሞባይሎችን
እዚህ አገር ለሁለት አመት በአረብ ሊግ ውስጥ በጸሀፊነት የቆየችው ሊባኖሳዊት አሁን የምይዘውን 4wD
ላንድክሩዘር መኪናዋን በስጦታ አበርክታለት ነበር የተሰናበተችው፡፡እሁንም ድረስ ግየዳውንና
ድለላውን የሚያጧጡፈው በዚች የገጠር እና የከተማ ጎርበጥባጣ መንገድ በማይበግራት መኪና ነው፡
እሷ ልታገባው ትፈልግ ነበር፣ ቁርጥ የአጎቴን ልጆች ነው የምትመስለው ትለዋለች፡፡ አፍ አውጥታ አግባኝ
ብላዋለች፡፡ እሱ በጄ አላላትም፡፡ አገሯ ሄደች፡፡
ኡስማንጋር “እምቢ”፣ “አልችልም” እና “የለም” የሚሉት ቃላት በአስማት አይገኙም፡፡ሲበዛ ትሁት ነው
ቱሪስቶቹ “ሀሺሽ ሲያምራቸው ኡስማን ልጅ እግር ደላሎቹን በአንድ የስልክ ጥሪ በማሰማራት ካለበት
ቆፍሮ ያቀርብላቸዋል፣ዜጎቹ ሌዝቢያን ሴት ወይም ቡሽቲ ወንድ ሲፈልጉ በብርሃን ፍጥነት በስልክ ደውሎ
አግኝቶ በመኪናው ያረፉበት ሆቴል፣ወይም ሆስቴል ወይም

👍4❤2
ገስት ሀውስ ድረስ ያቀርብላቸዋል
የፈረሰኩሽና የመሰለች ጨርጫሳ አሮጊትም ትሁን ጨረቃ የመሰለች ዜጋ “አብረን እንዝናና! አብረን እንደንስ!
አብረን እንደር!” ካለችው ታዛዥ ነበር፡፡ አሁን ሀብት ካመጣ በኃላ ተወው እንጂ፡፡ኡስማን በዚህ ትጋቱ
እና ትህትናው እንግዶቹ ይማረኩበታል፡፡አገራቸው ሲመለሱ ለወዳጆቻቸው ስለ ኡስማን ይመሰክራሉ
፡፡ ብዙዎቹ ኡስማን ዘ ኪንግ ይሉታል፡፡ እኛ ደግሞ "ኡስማን ዘ ፒምፕ” እንለዋለን፡፡ ወይም ደግሞ «ኤ»
እያልን እንጠራዋለን፡፡
ኡስማን ቱሪስቶችን የሚያድንበት አሪፍ ድረገጽ እንኳን የለውም፡፡ ድረገጹ ቀደምት ደንበኞቹ ናቸው
የኡስማን አስጎብኚ ድርጅት የሚሰጠውን አገልግሎት በዝርዝርና በጥልቀት በመዘርዘር ይጽፉለታል፤
ይመሰክሩለታል፡፡የኡስማንቢዝነስ «dow Season> ብሎ ነገር አያውቅም፡፡ዓመቱን ሙሉ እንደ ደመቀ
ነው፡፡እርሱ በዓመት ለሁለት ሳምንት ወደ ምስራቅ አውሮፓ እየሄደ የዓመት እረፍት ይወስዳል፡፡ከዚያ ውጭ እረፍት ብሎ ነገር አያውቅም፡፡አትላስ አካባቢ የሚያምር ንጹህ ቢሮ አለው፡፡ሁሉም ሰራተኞቹ ሴቶች ናቸው፡፡እጅግ የሚያማምሩ ሴቶች፡፡ ዘበኛው ብቻ ናቸው ወንድ፡፡ ለሰራተኞቹ በወር ከየትኛውም
NGO ያልተናነሰ ገንዘብ ይከፈላቸዋል፡፡የኡስማን ሞባይል እረፍት አልባ ናት፡፡የጠቅላይ ሚኒስትራትን
_ ስልክ እንኳ የኡስማንን ያህል እረፍት አልባ አትመስለኝም፡፡ኡስማን ከኢትዮጵያ
ንን ያህል እረፍት አልባ አትመስለኝም፡፡ኡስማን ከኢትዮጵያ ውስጥና ከተለያዩ የአለም ጥጎች የሚደወልለትን ስልክ ሲያስተናግድና በትህትና ሲመልስ ይውላል፤በእርጋታ፡፡ድምጹን ዝግ አድርጎ
አንዴ በአረብኛ፣አንዴ በእንግሊዝኛ፣አንዴበፍሬንች ሲያስቀና!
💫ይቀጥላል💫
Like ማድረግ እንዳይረሳ ከ #100 👍
በኋላ ቀጣዩ ክፍል ይቀጥላል
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

👍5