#ሮዛ
👇
👇
የቡና ቤት ሕይወቷን የተመለከቱ
አስገራሚ የዕለት ማስታወሻዎች
ከአዲስ አበባ ቪላዎች እስከ ሙአመር
ጋዳፊ ድንኳን
👉ከ 18 ዓመት በታች ከሆኑ ባታነቡት ይመረጣል ግን እንዲህ ሲባል ያጓጓል አደል እኔ ግን ተናግሬለሁ።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
«ከሾፌር፣ ከሴተኛአዳሪ፣ ከዘበኛእና ከቤት ሰራተኛ የምታመልጥ አንዳቸም የዓለም ሚስጢር የለችም»
#ክፍል_አንድ
፡
#ኮሌጅ_በጠስን
አሁን "ድንግልናዬ ሳይበጠስ ነው ኮሌጅ የበጠስኩት” ብል ማን ያምነኛል?ማንም፡፡ ስለዚህ አላወራም፡፡
አልናገርም፡፡ ዝም፣ ጭጭ፡፡ ኮሌጅ መበጠሴን ራኪ ብቻ ናት የምታውቀው፡፡ ሌሎቹ ባልደረቦቼ መጸሐፍ የማነብ አካባጅ ሸሌ እንጂ ኮሌጅ የበጠስኩ ሸሌ እንደሆንኩ አያውቁም፡፡ ራኪ ለራሷ ሲነሳባት ”…ኡኡቴ ኮሌጅ በጥሶ ሸሌ መሆን ብርቅ ነው እንዴ!” እያለች ካባዬን ታንኳስሰዋለች፡፡ ለነገሩ እውነቷን ነው፣
ምንም ብርቅ አይደለም፡፡ ግቢ ሳለን ከነበርነው ሴት ተማሪች ሲሶ ያህሉ ከወንዶች ጋር ይወጡ የነበረው
ለገንዘብ ሲሉ ነበር፡፡ ስለዚህ መንግስት ባያውቃቸውም ሸሌዎች ነበሩ፡፡ ብዙ ጓደኞቼ እንዳይጫሩ ሲሉ ብቻ ለአስተማሪዎቻቸው ጭናቸውን በልጥጠው ሰጥተዋል፡፡ ገላቸውን መስዋእት አቅርበዋል፡፡ ስለዚህ
ሸሌዎች ነበሩ፡፡ እንዲያሁ የአነጋገር ልማድ ሆኖብን ነው እንጂ ሸሌ ለመባል ቡና ቤት ገብቶ መመናቀር የግድ ነው እንዴ?
ከተመረቅን ስንት ዓመት ሆነን ማለት ነው? ጊዜው እንዴታባቱ ነው የሚበረው?
ኮሌጅ የበጠሱ የኔ ባቾች» እንዳሁኑ ዘመን ተመራቂዎች ሁሉም ኮብልስቶን አንጣፊ አልሆኑም
በባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎችአልጋ አንጣፊ የሆኑም አሉ፡፡ እንደኔ እና እንደ ወይንሸት የተማረ ሸሌ ኾነው የቀሩም አሉ፡፡ እንደ መዲና፣እንደ ራሄል፣እንደ ፎዚያ፣ እንደ ሂዊ፣እንደ ጠይባ አረብ አገር ለግርድና የሄዱም አሉ፡፡እንደ አብዱሰመድ(ወሎዬው) በአካውንቲንግ ተመርቀው የመን አገር ፍየል ለማገድ
የተሰደዱም አሉ፡፡እንደምስኪኑ ሀብትሽ ሰፈር ዉስጥ ጸጉር አስተካካይ የሆኑም አሉ፡፡ ሀብትሽ
« አታካብዱ ያውነው፣ድሮም በጭንቅላቴ ነበር የምሸመድደው አሁንም ጭንቅላት ነው የምከረክመው፤
አሁንም ድሮም ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት ነኝ፣!» እያለ ራሱ ላይ ይቀልዳል፡፡የክላስ ልጆችን ሳስብ እንደ
ሀብትሽ አንጀቴን የሚበላኝ ሰው የለም፡፡ሀብትሽ ለአራት ዓመት «ስፔስ» እየተመላለሰ፣ዓይኑ እየተጨናበሰ፣
እንቅልፍ እንዳያሸንፈው እግሩን በሳፋ እየዘፈዘፈ፣ሌተ ቀን ትምህርቱን ሲሸመድድ ቢኖርም ያቺ ቆሽማዳ
ሕይወቱ ፈቀቅ አላለችም፡፡
የተመረቅን ሰሞን 4ኪሉ ኢንተርኔት ቤት አግኝቼው ሲቪውን ፕሪንት ለማድረግ ሳንቲም ቸግሮት ሰጥቼዋለሁ።እንዴት እንዳሳዘነኝ!! ሀብትሽ ሲቪውን ያላስገባበት የመንግስት መስሪያቤት ቢኖር የአገር ደህንነት ሚኒስትር ብቻ ይመስለኛል፡፡ለህክምና ዶክተር የወጣ ክፍት የሥራ ማስታወቂያ ካየ እሱን
ባይመለከተውም ሲቪውን ከማስገባት ወደኃላ አይልም፤«የሚሆነው አይታወቅም፣አመልካች ሲያጡ
ይጠሩኛል፡፡»ይላል።የሆነ ሰሞንማ ይሄ ልጅ በቃ ለየለት ብለን ነበር፡፡ቁርስ እና እራት መብላት የቻለውም «ፖሊዮ» በሚለው ስራው ነው፡፡ቤት ለቤት ህጻናትን እየዞሩ ማስጠናት፡፡እሱም ቢሆን
ሲናገር ስለሚንተባተብ ትንሽ እንደሰራ ወላጆች ልጆቻችንን ተብታባ ያደርግብናል እያሉ ያበርሩታል፡፡
ሚስኪን ሀብትሽ!!
እንዳለመታደል ሆኖ ለአመታት ሲባዝን አንድም የሚቀጥረው ድርጅትአጣ፡፡ዉልና ማስረጃ ለተላላኪነት የወጣ ክፍት የስራ ቦታ ሁሉ ተወዳደሮ «ኦቨር ኳሊፋይድ ነህ በሚል ስለጣሉት ተስፋ ቆረጠ...ተስፋ ከመቁረጥ ጸጉር መቁረጥ ይሻላል ብሎ ነው መሰለኝ ሰፈር ውስጥ ባለች አንዲት ትንሽ ጸጉር ቤት ተቀጠረ፡፡ለነገሩ «ግቢ» እያለንም እርሱ ነበር የአብዛኛውን ተማሪ ጸጉር የሚላጨው፡፡ሰው በምን እንጀራ እንደሚወጣለት አይታወቅም፣አንዳንዱ በትምህርት ሌላው ደግሞ በሰው አናት ላይ በሚበቅል ጸጉር እንጀራ ይወጣለታል፡፡ይኸው ሀብትሽ አራት አመት ክፍል ገብቶ ከተማረው ትምህርት ይልቅ ስራ ሲፈታ የግቢ ተማሪዎችን ጸጉር በመከርከሙ ዛሬ በልቶ ለማደር በቃ፡፡እኔም ከተማርኩበት ዩኒቨርስቲ ይልቅ የህይወት ስንቅን የሚሰፍርልኝ ያልተማርኩሰት ቡና ቤት ሆነ፡፡
ሀብትሽ ከሁሉ ከሁሉ በማዕረግ መመረቁን ሲያስብ መማሩ የእግር እሳት ይሆንበታል፡፡ከርሱ ባነሰ ውጤት
የተመረቁት ሀፍቶምና ሌሊሳ የህዉሀትና የኦህዴድ ፓርቲ አባልነት ስለተመዘገቡ ብቻ "ዉጭ ጉዳይ" በአሪፍ ብር ተቀጠሩ፡፡ሀብትሽ እባል ሁን ሲባል "ኃይማኖቴ አይፈቅድም” ብሎ ቀለደ፡፡አሁን ይኸው ህይወት በተራዋ የምር ትቀልድበታለች፡፡የሚያሳዝነኝ ግቢ እያለን እናቱን ለመርዳት የነበረውን ጉጉት
ሳስብ ነው፡፡አሁን የማንንም መሀይም ፎሮፎር በሻምፑና ለብ ባለ ዉሀ እያጠበ በወር ዘጠኝ መቶ ብር ይከፈለዋል አሉኝ፡፡
ምስኪን ሃብትሽ፡፡አንዳንዴ ምን አስባለሁ…? “ሴት ኾኖ በተፈጠረና እንደኔ ገላውንም ቢሆን ቸርትሮ ባለፈለት…” እላለሁ፡፡
ምነው ግን ሀብትሽን እንዲህ በስፋት አሰብኩት? በስቅታ መሞቱ ነው ዛሬ፡፡ ለነገሩ ግቢ ሳለን ጀምሮ መጠነኛ «crush» ነበረኝ፡፡ለማንም ግን አልተናገርኩም በወቅቱ፡፡ እሱም የሚያቅ አይመስለኝም፡፡ካፌ የሚገባበትን ሰዓት ጠብቄ ከፊትለፊቱ እቀመጥና የአይኔን ረሀብ አስታግሼ ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ ዶርሜ አቀና ነበር፡፡ለምን እንደሆነ አላውቅም የሆነ ነገሩ ደስ ይለኛል፡፡ብዙዉን ጊዜ ልቅም ያለ ቆንጆ ወንድ አይስበኝም፡፡«ወንድ» በመሰረቱ የሆነ ነገሩ የማያምር እና ኮስታራ ነገር ሲኖረው ነው ወንድ» የሚመስለኝ፡፡
ቬተሪነሪ ዲፓርትመንት የነበረው አኒስ ለምሳሌ የሴት ጓደኛዬ ነበር የሚመስለኝ እንጂ አንድም ቀን እንደ ወንድ ቆጥሬው አላውቅም፡፡ለምን ሱሪ እንደሚታጠቅም እንጂ፡፡መልኩ መካከለኛ ቀይ፣ቁጭን
እና ስስ ከንፈር የነበረው አኒስ የሀረር ቀላዳምባ ልጅ ሲሆን ቤተሰቦቹ አደሬዎች ናቸው፡፡ሰልካካ አፍንጫና
ሉጫ ጸጉር አለው፡፡ግቢ ውስጥ ነጠላ ጫማ መጫማት ያዘወትር ነበር፡፡ክንዱ የተላገ ይመስል ጡንቻ የሚባል ነገር አልፈጠረበትም፡፡በዚያ ላይ ይቅለሰለሳል፡፡እንዴት ይዘገንነኝ አንደነበረ!! ዩኒቨርሲቲ እያለን
አንድም ቀን ብር ቸግሮት አያውቅም፡፡ብዙ ዘመዶች ካናዳ አሉት፡፡የካናዳ ዶላር እየቆነጠሩ ይልኩለታል፡፡
በዚያ ላይ ቤተሰቦቹ የመስጊድ ምንጣፍ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ «non cafe » ስለነበረ አንዳንዴ እኔና የዶርም
ጓደኛዬን ሂንዲያን ልጋብዛችሁ እያለ ከግቢ ይዞን ይወጣ ነበር፡፡የካፌ ምግብ ስለሚያንገሸግሸን ግብዣውን አይናችንን ሳናሽ እንቀበለዋለን፡፡
እኛ ቢራ ስናዝ እርሱ ሚሪንዳ ያዛል፡፡ቅፍፍ ነበር የሚለኝ ሚሪንዳ ሲያዝ፡፡አኒስ በሚሪንዳ አይደራደርም።
ሚሪንዳ የለም ከተባለ ቤት እንቀይር ይላል፡፡ሲያስጠላ!!… አንዳንዴ ሰውነቱ ውስጥ በደም ፋንታ ሚሪንዳ
የሚዘዋወር ነው የሚመስለኝ፡፡ ወንድ ልጅ ወይ ቢራ ወይ ኮካ ነው መጠጣት ያለበት፡፡እንዴት ሚሪንዳ ይዞ ይሟዘዛል!? እኛ ቢራ ስንደግም እሱ ያቺኑ ሚሪንዳ እየተቅለሰለሰ ይጎነጫል፡፡ሂንዲያ ይሄ ባህሪው ስለሚያናድዳት " ..አኒስ ሚሪንዳ ድገም እንጂ.…አንድ ያጣላል
one for the road!» እያለች ሙድ
ትይዝበታለች፡፡እሱ ግን አይገባውም ይስቃል፡፡«ጥርስህ ይርገፍ›› እለዋለሁ በሆዴ፡፡አኒስ ምግብ ሲበላ ጉርሻው ያሳቅቀኝ ነበር፡፡እንደ ሴት እየተቅለሰለሰ ትንንሽ ሲጎርስ ከሂንዲያ ጋር እየተጠቃቀስን እንስቃለን ጥሎበት እይጥና ጸብ በጣምይፈራል፡፡የዶርሙ ልጆች እንደሚያወሩት ከሆነ

👍9❤1