አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ከተሸከርካሪው ጀርባ የሚመጡት ያለማመንና የፍርሃት ጩኸቶች እየቀረቡን የመጡትን ገዳዮች ትኩረት የበለጠ ሳቡ፡፡ አንዱን ኢንተርሃምዌ ዓይኑን ትኩር ብዬ አይቼ አትኩሮቱን ያዝኩበት፡፡ እንደኔ ዓይነት ሰው እንደሆነና በእውነት መግደል እንዳልፈለገ ልቤ ነግሮኛል፡፡ መቁጠሪያዬን ይዤ ለእርሱ የፍቅር መልዕክት ለመላክ ቁርጠኝነቴን ሁሉ ሰበሰብኩት፡፡ አምላክ ገዳዩን በፍቅሩ ኃይል እንድዳስሰው እንዲጠቀምብኝ ጸለይኩ፡፡
ዓይኖቼን አልጨፈንኳቸውም … እናም ያንድ ሰው ዕድሜ ለመሰለኝ ያህል ጊዜ ተፋጠጥን፡፡ በመጨረሻም ገዳዩ ሳፈጥበት እይታውን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዞረ፡፡ ሰይጣን ሰውነቱን ትቶት እንደሄደ ሁሉ ጀርባውን አዙሮ ገጀራውን አሽቀንጥሮ ጣለው፡፡ በአንጻሩ ሌሎች ብዙ ዲያብሎሶች የእርሱን ስፍራ ለመተካት ተዘጋጅተዋል፡፡ ቢያንስ 15 ኢንተርሃምዌዎች ከተሸከርካሪው የተወሰኑ እርምጃዎች ርቀት ላይ ገጀራ ይዘው ፊታቸውን ተኮሳትረው ቆመዋል፤ እየተከሰተ ያለውን ነገር ምንነት በማጤን ከጓደኞቼ አንዳቸው እንኳን ለመውረድ አለመድፈራቸውን ያዩ ይዘዋል፡፡ ከመውጣት ውጪ ምንም አማራጭ የለንም፡፡ ሰላሳችንም እዚያ ገዳዮቹን ተጋፍጠን እስክንቆም ድረስ ጓደኞቼ አንድ በአንድ እየዘለሉ ወረዱ፡፡ ሁሉም ወርዶ እንዳለቀ ሁለት የፈረንሳይ ወታደሮች አሎይዜን አወረዷት፤ ልጆቿንም ኬንዛንና ሳሚን ከጎኗ አደረጉላት፡፡ ወታደሮቹ ተሳፈሩና ተሽከርካሪው በአቧራና እርግጠኝነት እጦት ደመና ውስጥ ትቶን በከፍተኛ ፍጥነት ነጎደ፡፡
አንደኛው ገዳይ ‹‹እነዚህን ሁሉ ቱትሲዎች እዩዋቸው›› ሲል በመገረም ተናገረ፡፡ ‹‹እንዴት ነው እስካሁን በሕይወት ሊኖሩ የቻሉት?››
‹‹የፈረንሳይ ወታደሮች ከለላ ሰጥተዋቸው የነበሩት በረሮዎች ናቸው›› አለ ሌላኛው፡፡ ‹‹እስኪ አሁን ማነው የሚያድናችሁ? በረሮ ሁላ!››
ጓደኞቼ በጣም ስለፈሩ መንቀሳቀስ እንኳን ተሳናቸው፡፡ ለጨካኝ ገዳዮች መላ በመዘየድ ባለሙያ የሆንኩ ይመስል ጎሰም አድርገው ምን ማድረግ እንደሚገባን ጠየቁኝ፡፡ ፍሎሬንስና ቤተሰቧ ገዳዮቹ ቆራርጠው እስከሚገድሏቸው ተራቸውን እየጠበቁ በቤተክርስቲያን የተቀመጡችበትን ታሪክ እያስታወስኩ ፊቷ ላይ ያለውን የገጀራ ጠባሳ አየሁት፡፡ ያበጠው ይፈንዳ እንጂ እኔማ ቆሜ የምታረድበትን ተራ አልጠባበቅም፡፡
‹‹እንሂድ›› አልኩ፡፡ ‹‹ወደ ሩአግ ምሽግ በእግራችን እንሄዳለን - ወታደሮቻቸው ቅርብ ናቸው፡፡››
ገዳዮቹ ሩአግ ስል ሲሰሙኝ ጊዜ ተናደዱ፡፡
መንቀሳቀስ ብንጀምርም ብዙም መሄድ አልቻልንም፡፡ መንገዱን የድንጋይና የሰው አስከሬን በጣም ስለሞላው የአሎይዜን የመቀመጫ ተሸከርካሪ መግፋቱ አስቸገረን - አንዱ ጎማው በተቀረቀረ ቁጥር ሁላችንም እንቆማን፡፡ የአሎይዜ ልጆችም እያለቀሱ የእናታቸውን ክርኖች ያዙ፡፡
ጓደኞቼን ዢን ፖልንና ካሬጋን ከቡድኑ ነጥዬ ወሰድኳቸው፡፡ ‹‹እናንተ ሁለታችሁ ከኔ ጋር ኑ - ሌሎቻችሁ ከአሎይዜ ጋር ትቆያላችሁ… እና ደግሞ ጸልዩ፡፡ ቱትሲ ወታደሮቹን ፈልጌያቸው እመጣለሁ፡፡ ከዚህ ስፍራ አትሂዱ፤ ያለዚያ በዚህ የሁቱ ጎርፍ መካከል ላገኛችሁ አልችልም፡፡›› አሎይዜ በጥርጣሬ እያየችኝ ‹‹እውነት መሄድሽ ነው? በእርግጠኝት ይገድሉሻል! ይልቅ ወንዶቹ ቢሄዱ ይሻላል›› ስትል ለመነችኝ፡፡
‹‹አይሆንም እኔ ነኝ የምሄደው … እናንተ ብቻ በጸሎታችሁ ላይ አተኩሩ፡፡›› ያን ካልኩ በኋላ ፈረንሳውያኑ ትተውን ከመሄዳቸው በፊት ይዘውን ይሄዱ የነበረበትን አቅጣጫ ተከተልኩ፡፡ ስንሄድ ከአምላክ ጋር በሙሉ ልቤና ነፍሴ እያወራሁ በመቁጠሪያው ጸሎት አደርስ ጀመር፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ! እውነት በሞት ፈፋ ውስጥ እየሄድኩ ነው - እባክህ ድረስልኝ፡፡ በፍቅርህ ኃይል ከልለኝ፡፡ ይህን የምሄድበትን መንገድ ፈጥረኸዋል፤ ስለዚህ እባክህ እነዚህን ገዳዮች የልጅህን ደም እላዩ እንዲያፈሱት አታድርጋቸው፡፡››
ከትልቁ ቡድን ተነጥለን ስንሄድ ሦስት ኢንተርሃምዌዎች ተከተሉን፤ አንዱ እንዲያውም እኔን ዐወቀኝ፡፡ ‹‹ይህችን በረሮ አውቃታለሁ›› አለ፡፡ ‹‹የሊኦናርድ ልጅ እኮ ነች - ለወራት ስንፈልጋት ቆይተናል! አስካሁን አለች ብዬ አላምንም… ሌሎቹን ገድለናቸዋል፤ ግን ይቺ ደቃቃ በረሮ አምልጣናለች!››
በቻልኩት መጠን ፈጥኜ እየተራመድኩና የአባቴን መቁጠሪያ በእጄ አጥብቄ ይዤ ‹‹ጌታ ሆይ›› ስል ጸለይኩ፡፡ ‹‹አንተ ታድነኛለህ፡፡ ፈጣሪዬ እንደምትንከባከበኝ ቃል ገብተህልኛል፣ እንግዲህ አለኝታነትህን አሁኑኑ እፈልጋለሁ፡፡ በጀርባዬ ሰይጣኖችና የሎሶች አሰፍስፈዋል፡፡ አምላክ … እባክህ ጠብቀኝ፡፡ ከነዚህ ሰዎች ልብ ውስጥ ሰይጣኑን አስወጣው፤ ጥላቻቸውንም በቅዱስ ፍቅርህ አሳውረው፡፡›› ድንጋይ ወይንም አስከሬን እንዳያደናቅፈኝ ሳልጠነቀቅ፣ እምነቴን በጌታዬ ላይ ጥዬና ደኅና ወደምሆንበት ስፍራ እንዲመራኝ እግሮቼን እንኳን ማየቴን ትቼ ተራመድኩ፡፡ የምንጓዘው በጣም በፍጥነት ነው፤ ቢሆንም ግን ገዳዮቹ ገጀራዎቻቸውን በአየር ላይ እያወናጨፉ ከበውናል፡፡ ማንም ከለላ የሚሆነን የለም፡፡ ታዲያ ለማጥቃት ምንድነው የሚጠብቁት?

‹‹ከገደሉኝ፣ እግዚአብሔር፣ እንድትምራቸው እለምንሃለሁ፡፡ ልባቸው በጥላቻ ታውሯል፤ ለምን ሊጎዱኝ እንደሚፈልጉም አያውቁትም፡፡››
ግማሽ ኪሎሜትር በዚያን ዓይነት ሁኔታ ከሄድን በኋላ ዢን ፖል ‹‹እዪ ሄደዋል…ሄደዋል!›› አለኝ፡፡
ተመልሼ ሳይ እውነት ኖሯል - ገዳዮቹ ትተውን ተመልሰዋል፡፡ ዢን ፖል በኋላ ላይ ምናልባት የሩአግ ወታደሮች በቅርብ እንዳሉ ስላወቁ ይሆናል ቢልም ትክከለኛውን ምክንያት ግን አውቄዋለሁ፤ በዚያ መንገድ ላይ ሕይወታችን ስላተረፈልን እግዚአብሔርን ማመስገኔን አላቆምኩም!
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በአንድ የሩአግ ኬላ ብዙ ደርዘኖች ረጃጅም፣ ቀጫችንና ኮስታራ የቱትሲ ወታደሮችን ዘበኝነት ቆመው አየን፡፡ በለየለት ሩጫ ሄጄ እፊት ለፊታቸው ተንበረከክሁ፡፡ ዓይኖቼን ጨፍኜ የምስጋና መዝሙር ዘመርኩላቸው፡፡
‹‹ተመስገን አምላኬ፣ ተመስገን ጌታዬ፣ ድነናል! ተመስገን አምላኬ፣ ደረሳችሁልና፡፡ ተባረኩ፤ ሁላችሁም ተባረኩ! አይ፣ ያለፍንበትን ብታዩልን፡፡ እናመሰግናለን ለ - ››
አስደንጋጭ ቀጭ ቀጭ የሚል የጠመንጃ መሳቢያ ሲሸለቀቅ የሚያሰማው ድምፅ ስላቋረጠኝ የጀመርኩትን ንግግር ለመጨረስ አልቻልኩም፡፡ ዓይኖቼን ገልጬ ሳይ የጠመንጃው አፈሙዝ ፊቴ ላይ ተደግኗል፡፡
ወይ አምላኬ፣ ይህን የቅዠት ሕይወት ይበቃል የምትለው መቼ ይሆን?
ወደ ጠመንጃው አፈሙዝ ቀና ብዬ ካየሁ በኋላ ክፋት ወደሚነበብባቸውና ወደ ቁጡዎቹ የቱትሲው ወታደር ዓይኖች አማተርኩ፡፡ ሃያ ከማይሞሉ ደቂቃዎች በፊት ያፈጠጥኩባቸውን የገዳዩን ዓይኖች አስታወሱኝ፡፡
የዘር ፍጅቱ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ከመአት ይሰውሩናል ብለን ተስፋ ስናደርግባቸው የቆየነው የሩአግ ወታደሮች እነዚህ ከሆኑ አሁን ለኔ ትክክለኛው የመሞቻ ሰዓቴ ነው፡፡ ጎረቤቶቼ ከድተውኛል፣ ገዳዮቹ እንደዚያ ሲፈልጉኝ ከርመዋል፣ ፈረንሳውያኑ ትተውኛል፣ አሁን ደግሞ ቱትሲ ወገኖቼ ጭንቅላቴን ሊያፈርሱት ቃጥቷቸዋል፡፡
ያንተው ድርሻ ነው፣ እግዚአብሔር፣ ስል በውስጤ ጸለይኩ፡፡ ያንተን ፍቃድ እየፈጸምኩ እስከሆነ ድረስ ኖርኩም ሞትኩ ለኔ ምንም ችግር የለውም፡፡ እዚህ አምጥተኸኛል - መወሰኑ እንግዲህ ያንተው ድርሻ ነው፡፡
👍2
ቀስ ብዬ እጆቼን በአየር ላይ እያነሳሁ ሁለቱ ጓደኞቼና እኔ ቱትሲዎች መሆናችንን እያብራራሁ ለመቆም ሞከርኩ ‹‹ፈረንሳውያኑ ወታደሮች መንገድ ላይ ጥለውን ሄዱ … የጭፍጨፋው ሌሎች ተራፊዎች ከኋላችን በገዳዮች ተከበዋል፡፡ እባካችሁ እጅግ ከመዘግየቱ በፊት ልትረዷቸው ይገባል፤ ኧረ ድረሱላቸው፡፡››
‹‹አፍሽን ዝጊና መሬቱ ላይ ቁጭ በይ!›› ወታደሩ በጠመንጃው እየጎሰመኝ ጮኸ፡፡
‹‹ቱትሲዎች ከሆናችሁ እንዴት ነው እስካሁን ልትኖሩ የቻላችሁት?!›› ሌላው ጠመንጃውን በኔ ላይ ደግኖ ጮኸ፡፡ ‹‹ሁሉም ሞቷል፣ ሁሉም! እናንተ ራሳችሁ ገዳዮች ናችሁ… የሁቱ ሰላይ ሁላ! ጆሮ ጠቢዎችን ምን እንደምናደርግ ታውቃላችሁ? አርፋችሁ ተቀመጡ፤ እንዳትንቀሳቀሱ - አንዲትም ቃል እንዳትተነፍሱ፤ ዋ ቀስቀስ ትሉና! እያንዳንድሽ ቱትሲ ነኝ፣ ጂኒ ጃንካ ብትዪ የሚሰማሽ ያለ አይምሰልሽ!››በቁጡ ወታደሮች ስለተከበብን ማውራት ፍሬ አልነበረውም፡፡ አፌን ዘግቼ ዕጣ ፈንታዬ ያስቀመጠልኝን እጠብቅ ገባሁ፤ ደቂቃዎች አለፉ፡፡ በቃሌ ጸንቼ ወታደሮቹን እንዲያድኗቸው እንድልክላቸው የሚጠብቁትን አሎይዜንና ሌሎቹን በገዳዮቹ የተከበቡትን አሰብኳቸው፡፡ እንግዲህ እግዜር ይሁናቸዋ፤ ሌላ ምን እላለሁ?

በኋላ ላይ የአማጽያኑ ወታደሮች አዛዥ ሊመረምረን መጣ፡፡ ይጠብቁን የነበሩት ወታደሮች ሰላምታ ሰጡት፤ ‹‹ሻለቃ›› እያሉም ይጠሩታል፡፡ ረጅም፣ እንደዱላ የቀጠነና በሕይወቴ ካየኋቸው ሰዎች ሁሉ የተረጋጋ የሚመስል ነው፡፡ ቤቱን ሰብረን ስንገባ የተያዝን ሌቦች እንደሆንን ሁሉ ገረመመን … የፈረንሳይ ወታደሮች የኢንተርሃምዌውን ሰላይ እንደያዙ በፊታቸው ላይ ይታይ የነበረው ዓይነት ገጽታ ይታይበታል፡፡ ያ ሰው ምን ዕጣ እንደገጠመው አስታውሼ አማተብኩ፡፡ ሻለቃው ከዘር ፍጅቱ የተረፍን መሆናችንን አለማመኑ ያስታውቃል፡፡ ይህንንም በማየቴ በመንገድ ዳር ስለተውናቸው ምስኪን ነፍሶች እጸልይ ጀመር፡፡
በዚች ቅጽበት እግዚአብሔር ለእኛ በድጋሚ ጣልቃ ገባልን፡፡
‹‹ኢማኪዩሌ? ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ?›› ከሻለቃው ጎን የተቀመጠ ወታደር ስሜን እየጠራ ባለማመን አፈጠጠብኝ፡፡ ‹‹ኢማኪዩሌ! አይ፣ አንቺማ አትሆኚም፣ እንዲያው ትሆኚ ይሆን ? አንቺ ነሽ?››
‹‹ባዚል?››
‹‹አንቺ ነሽ!›› ጠመንጃውን አስቀመጠና ተንበርክኮ አቀፈኝ፡፡ ባዚል ቱትሲ አማጽያኑን ደግፎ ለመዋጋት የዘመተ ሁቱ ጎረቤታችን ነው፡፡ ከትምህርት ቤት ጀምሮ እንተዋወቃለን፡፡ እናቴ ለረጅም ዓመታት ተሰጥኦ የነበረውና ጎበዝ ተማሪዋ ስለነበር ትወደዋለች፡፡ እማማ ለእርሱ የተለየ ፍቅር ስለነበራት እቤት ብዙ ጊዜ ስለምትጋብዘው ‹‹የመምህርት ብርቅዬ የቤት እንስሳ›› እንለዋለን፡፡
‹‹ይቺን ልጅ ታውቃታለህ?›› ሻለቃው ባዚል አቅፎኝ ሲጨርስ ጠየቀው፡፡
‹‹እንዴ አዎን አብረን ነው የተማርነው፡፡ ወላጆቿ በመንደራችን እጅግ የተከበሩ ቱትሲዎች ነበሩ - በጣም ጥሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ምንም ችግር የለባትም ሻለቃ … ሰላይነቱ አይነካካትም፡፡ ኢማኪዩሌ የምትለው ሁሉ ፍጹም ሃቅ ነው፡፡›› ባዚልን በምፈልግበት አፍታ ስለላከልኝ አምላኬን በቶሎ አመሰገንኩት፡፡ ወታደሮቹ የደገኗቸውን ጠመንጃዎች ዝቅ አደረጉ፤ ሻለቃውም እጃቸውን ዘርግተው ሰላምታ አቀረቡልኝ፡፡ ‹‹ሻለቃ ንትዋሊ እባላለሁ›› አሉኝ፡፡ ‹‹ስለ ግርታው ይቅርታ፤ በእርግጥ ሰላዮችም በየስፍራው አሉ፡፡ እዚህ አካባቢ አሁንም በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ግን ከኛ ጋር ከሆናችሁ ዘንዳ ሐሳብ አይግባችሁ፡፡ ለእናንተ ጦርነቱ አልቆላችኋል … ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ከማናቸውም ጥቃት እንከላከላችኋለን፡፡››
‹‹አመሰግናለሁ ሻለቃ፤ እጅጉን የእርስዎን ከለላ የሚፈልጉት ግን ጓደኞቼ ናቸው›› ስል ወዲያውኑ ነገርኳቸው፡፡ ‹‹ፈረንሳውያኑ ወታደሮች የተዉን በኢንተርሃምዌዎቹ መሐል ነው፤ በመሆኑም በመንገዱ ወደ ግማሽ ኪሎሜትር ወርዶ 30 የቱትሲ ርዝራዦች በገዳዮች ተከበው ይገኛሉ፡፡ እስካሁን ድረስ በሕይወት መኖራቸውንም አላውቅም፡፡ እባክዎን …››
ተናግሬ እንኳን ሳልጨርስ ሻለቃው የተወሰኑት ወታደሮች አሎይዜንና ሌሎቹን እንዲያመጧቸው ለአንዱ ምልክት ሰጡት፡፡ ‹‹ስለጓደኞችሽ አትጨነቂ፡፡ እንደርስላቸዋለን፡፡››
‹‹አመሰግናለሁ… ፈጣሪ ይባርክዎ! አዬ፣ ሌላ ምን እላለሁ!›› ወታደሮቹ ሌሎቹን ለማገዝ ሲሄዱ ባዚል ከጎኔ ተቀምጦ በሥጋት የጥያቄ መአት አወረደብኝ - ‹‹ይኸው እቤት ከሄድኩ ስንት ወሬ … የሰፈራችንን ወሬ ሰምተሻል? መምህርት እንዴት ናቸው - እናትሽን ማለቴ ነው? አልበረቱም? ስለ ወላጆቼ፣ ወንድሞቼና እህቶቼስ የሰማሽው ነገር አለ? ለመጨረሻ ጊዜ በጠየቅኋቸው ጊዜ አገሪቱን ለቀው ሊሄዱ እየተዘገጃጁ ነበር… ወጡ እንዴ?››
እጄን በባዚል ክርኖች ላይ ጣል አደረግሁ፡፡ ልቀሰቅስበት የምችለው ሕመም ይታወቀኛል፤ ስለሆነም በተቻለኝ መጠን ረገብ ለማለት ሞከርኩና ‹‹ስለዚህ ጉዳይ እንዴት እንደምነግርህ አላውቅም፣ ባዚል፣ እውነቱን ከመናገር በቀር፡፡ ሁሉም ሞተዋል - የኔም፣ ያንተም ቤተሰብ … በመንደራችን ያለ ቱትሲና ለዘብተኛ ሁቱ ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ በሞት ጎዳና ተከታትለው ሄደዋል - አዬ! ደመ-ከልብ ሆነው ቀርተዋል ወንድሜ›› ብዬ አረዳሁት፡፡
መናገር እንደረሳ ሁሉ ብቻ ዝም ብሎ ያስተውለኛል፤ ከዚያም በእግሮቼ ስር ጥቅልል ብሎ ደረቱ ትር ትር እያለ በጠመንጃው ሰደፍ ላይ ያነባ ጀመር፡፡ ምስኪን ባዚል… ወላጆቹን፣ አራት ወንድሞቹንና ሦስት እህቶቹን አጣ፡፡ ውይ አንጀት ሲበላ!
እንደደረስን በዚያን ዓይነት ጥርጣሬ ለምን እንዳስተናገዱን አሁን ገባኝ፡፡ ከእነዚህ ወታደሮች አብዛኞቹ ከዩጋንዳ ድረስ እየተዋጉ ስለመጡ በመንገዳቸው ስለቤተሰቦቻቸው ምንም ወሬ አልሰሙም፡፡ አሁን ሲመለሱ ቤተሰቦቻቸውን በሕይወታቸው ሙሉ ባመኗቸው ሰዎች፣ በጎረቤቶቻቸው፣ ታርደው ያገኟቸዋል፡፡ በአማጽያኑ ምሽግ ቁዘማ ነግሷል፡፡
እኔም ብዙም ደስታ አልተሰማኝም፡፡ ባዚልን በማርዳቴ ተጸጽቻለሁ፤ ደቂቃዎችም ባለፉ ቁጥር አሎይዜንና ቡድኗን የሚፈራው ነገር ገጥሟቸው እንዳይሆን በመስጋት ስለደህንነታቸው በጣም እየጸለይኩ ሳለ የደስተኛዋን ጓደኛዬን የተለመደ ሣቅ እየመጣ ካለው የሩአግ ተሽከርካሪ ሰማሁት፡፡
‹‹ኢማኪዩሌ፣ ይህ የምትጸልዪው ጸሎት ምንም ዓይነት ይሁን ምን መጸለይሽን እንዳትተዪ›› ስትል አሎይዜ እየሳቀች ነገረችኝ፡፡ ‹‹እነዚያ ገዳዮች እኮ ሊቆራርጡን ቢፈልጉም መንቀሳቀስ እንደተሳናቸው ነው እይታቸው የሚያሳየው … እዚያው ባሉበት እንደ በረዶ እኮ ነው የሆኑት! በአንበሶች ጉድጓድ እንደተጣለው እንደ ዳንኤል ነበር እኮ የሆንነው … በአንበሶች ጋጣ እንደተጣለው ዳንኤል ልጄ!›› አሎይዜ ልጆቿን ሳብ አደረገችና ጠበቅ አድርጋ አቀፈቻቸው፤ ከዚያም እንባ በጉንጮቿ እስኪወርድ ድረስ በሣቅ ትንከተከት ገባች፡፡ ልቤ ተነሣሳችና ‹‹አምላክ ከእንግዲህ ከገዳዮቹ ጋር ድጋሚ አያገጣጥመንም፡፡ ይህችን ደፍሮ ለማለት ያደርሰኝ እንደሆነ ካሁን በፊት አላውቅም ነበር፤ ለማንኛውም አሁን ጭፍጨፋው አብቅቷል - እግዚአብሔር አትርፎ አዲስ ሕይወት ሰጥቶናል፡፡ አምላክ ይመስገን! እናመሰግንሃለን ፈጣሪ!›› አልኩ፡፡
አሎይዜ ሣቅ ብላ ‹‹ይሁን ይደረግልን፣ ኢማኪዩሌ… ይሁና!›› አለችኝ፡፡

የአሎይዜ ሳቂታነትና ነጻነት ያለበት መንፈሷ ያዘኑትን
👍1
ወታደሮች አስደሰታቸው፡፡ በምሽቱ ባሳለፍናቸው የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሰዓታት እስካሁን ስላገኘቻቸው ዝነኛ ሰዎች የተለያዩ ነገሮችን በማውጋት ስታዝናናቸው ቆየች ከሁሉም በላይ የተማረኩት ግን በማይናወጠው አዎንታዊ ምኞቷ ነው - በሕይወቷ ስለገጠማት ዕጣ በፍጹም አታማርርም - እያንዳንዷንም ቅጽበት በተቻላት መጠን ትጠቀምባታለች አሎይዜና እኔ በጣም ስለተግባባን ሻለቃ ንዋትሊ እናቴ እንደሆነች ጠየቁኝ፡፡ ‹‹አይደለችም›› ስል መለስኩለት፤ ግን እንደ ልጇ ነው የምታየኝ፡፡ ወላጆቼና ሁለቱ ወንድሞቼ በእርግጥ የጭፍጨፋው ሰለባዎች ናቸው - ሌሎቹም ዘመድ አዝማዶቼ እንዲሁ፡፡
‹‹ይቅርታ›› አሉ ሻለቃው ‹‹ትወቅሱናላችሁ?››
‹‹ምን ማለትዎ ነው?›› ስል ጠየቅኋቸው በጥያቄያቸው ተደናግሬ፡፡
‹‹በተከሰተው ነገር ብዙዎቹ ወታደሮቼ ራሳቸውን ይወቅሳሉ፡፡ የራሳቸውን ቤተሰብ ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቱትሲዎች ሲገደሉ ኪጋሊን ለመቆጣጠር ስንዋጋ ብዙ ጊዜ እንደፈጀን ያስባሉ፡፡ እዚህ ለመድረስ ረጅም ጊዜ እንደወሰድን ይሰማቸዋል፡፡››
‹‹እንደዚያ ማሰብ የለባቸውም ሻለቃ - የእናንተ ችግር አይደለም፡፡ እኛን ለማዳን ነው እኮ የተዋጋችሁት … ዲያብሎስን ነው የተፋለማችሁት፡፡ አሁን ተመሳሳይ ጦርነት እንዳይመጣብን መጣር አለብን፡፡ መግደልን አቁመን እንዴት ምኅረት ማድረግ እንዳለብን እንማር፡፡››
ባለመስማማት ራሳቸውን ነቀነቁብኝ፡፡ ‹‹ስለ እግዚአብሔር ወይንም ስለ ዲያብሎስ አታውሪልኝ - ይህን ማን እንዳደረገው አውቃለሁ፡፡ ለምትፈልጊያቸው ሁሉ ምኅረት ማድረግ ትችያለሽ፣ ኢማኪዩሌ፡፡ አንቺ ግን ምናልባትም እኔ ያየሁትን ያህል የጅምላ መቃብሮች አላየሽም፡፡ እነዚያን መቃብሮች የሞሉት ሰዎች አሁንም እዚያው ናቸው፤ እና እመኝኝ ገዳዮቹ ምኅረትሽ የሚገባቸው አይደሉም፡፡ መገደል አለባቸው፤ ስለሆነም እኔ የእጃቸውን መስጠትን እመርጣለሁ፡፡ ባይሆን ገድዬ ይቅር እላቸዋለሁ፡፡
ሻለቃው በቅርብ ያለ የባፕቲስት ቤተክርስቲያንን አመለከቱን፡፡ ‹‹ሌሎች ከግድያው የተረፉ ሰዎችን እዚያ ታገኟቸዋላችሁ፡፡ ስለናንተ ምን እንደምናደርግ እስክንወስን ድረስ እዚያው ሁኑ፤ ደግሞ እንዳትዟዟሩ፡፡ አስታውሱ፣ አሁንም ቢሆን በጦርነት ቀጣና ውስጥ ናችሁ፡፡ ጥቂት ኢንተርሃምዌዎች ቢያገኟችሁ እናንተ እንደምትምሯቸው አይምሯችሁም፡፡››
የኔ ቡድን ከሌሎች አንድ መቶ ከሚሆኑ ሌሎች የተረፉ ቱትሲዎች ጋር በቤተክርስቲያኑ ቆየ፡፡ በዚያ ስፍራ አልጋም ሆነ ብርድልብስ የለም፡፡ ከራሳችን በላይ ጣራ በመኖሩ ግን ደስተኞች ነን፡፡ በዚያም ላይ በእግዚአብሔር ቤት መሆናችን አስደስቶናል፡፡ ባዚል ምግብ ስለሰጠን እኔ አዘገጋጅ ጀመር፡፡ ውጪ ላይ እሳት ለማያያዝ ስሞክር አንዳች መጥፎ ሽታ አጥወለወለኝ፡፡
‹‹በፈጣሪ ስም ይህ ሽታ ምንድነው?›› ስል አንደኛውን እኛን እንዲጠብቅ የተመደበውን ወታደር ጠየቅሁት፡፡ እጄን ይዞ ምንም ሳይናገር ወደ ቤተክርስቲያኑ ጓሮ ወሰደኝ፡፡ ከሲዖል የመጣ ምስል ነው ማለት ይቻላል - በመቶዎች የሚቆጠር ሬሳ በሬሳ ላይ እንደ ግንድ ተከምሯል፡፡ ላዩን ደግሞ ጥቁር የዝንብ ምንጣፍ ሸፍኖታል፤ አሞራም ላይ ላዩን ይራኮትበታል፡፡ አንድ ሽማግሌ ሰውዬ በክምሩ ዳርቻ ቆመው ውሾችን በዱላ ያባርራሉ፡፡
አፌን ሸፈንኩ፤ ዓይኖቼም በመሸበር ፈጠጡ፡፡ ከዚያም ወታደሩ ከክምሩ አለፍ ብሎ 30 ሜትር ርዝመትና 20 ሜትር ጥልቀት ያለውን ጉድጓድ አመለከተኝ፡፡ በአሥር ሺዎች በሚቆጠር አስከሬን የተሞላ ነው፡፡ ራሴን አዞርኩ፣ አስመለሰኝና ወደ ቤተክርስቲያኑ ግቢ ፊተኛ ክፍል እየተንገደገድኩ ሄድኩ፡፡ ወታደሩም ምንም ሳይተነፍስ ተከተለኝ፡፡
‹‹የዚህ አካባቢ ሰው ነህ?›› ስል ጠየቅሁት፡፡ ራሱን በአዎንታ ስለነቀነቀልኝ በዚያ እየበሰበሰ ባለ የሰው ክምር ውስጥ አንድ ቦታ ቤተሰቡ እንዳለበት ገባኝ፡፡ ሰቀቀኑ ቃላት ከሚገልጹት በላይ ነው፡፡
ከስንት ዓመት፣ ከስንትስ ትውልድ በኋላ ይሆን ሩዋንዳ ከዚህ አሰቃቂ ድርጊት የምታገግመው? የቆሰሉ አንጀቶቻችንስ በምን ያህል ጊዜ ይሽሩ ይሆን? የደደሩት ልቦቻችን በምን ያክል ጊዜ ይመለሳሉ? ለኔ ረጅም ጊዜ ሆኖ ታየኝ፡፡ የወታደሩን ዓይኖች ሳይ ሩዋንዳን ለቅቄ መሄድ እንዳለብኝ ገባኝ፡፡
ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜ የዚህችን ሀገር ሰቆቃና ሥቃይ ትቼ መሄድ አለብኝ፡፡ እግዚአብሔር ሌሎች ጉዳተኞች እንዲድኑ አግዝ ዘንድ ይህን አንዳደርግ እንደፈቀደ ስለማውቅ ጊዜና ቦታ ብቻ የሚፈቅዱልኝን በማመዛዘን የምወስንበት ሁኔታ ያስፈልገኛል፡፡ መጀመሪያ ራሴን ማዳን አለብኝ ሌሎቹን ለማገዝ - በፈረንሳውያን ምሽግ ያሉትን ወላጅ አልባዎች፣ ልባቸው በቀል የተሞላውን ሻለቃ፣ አሁንም መግደል በዓይናቸው ላይ የሚነበብባቸውን አራጆችና ሐዘኑ ነፍሱን ያፈነችበት ከፊት ለፊቴ የቆመው ወታደር - ሁሉንም፡፡
እሄዳለሁ፣ ግን ገና ጊዜ መጠበቅ አለብኝ፡፡ መጀመሪያ ብዙ ማድረግ ይኖርብኛል፤ በተጨማሪም ምንም ሥራ፣ ገንዘብም ሆነ ራእይ የለኝም፡፡ ያለኝ ብቸኛው ነገር የለበስኳቸው ልብሶችና በኪሴ ያለው የአባቴ መቁጠሪያ ነው፡፡ ጓደኞቼና እኔ አብዛኛውን ጊዜያችንን ያለ ምንም ገንዘብ ወደ ኪጋሊ እንዴት መሄድ እንደምንችል በማሰብ ከአማጽያኑ ታጋዮች ጋር ለተወሰኑ ቀናት ቆየን፡፡ አንዴ እዚያ ከደረስን አሥራ ሁለታችንም አሎይዜ ቤት ልንቆይ እንችላለን፣ አሁንም ቢሆን ግን አስቸጋሪውን የአምስት ሰዓት ጉዞ ማድረግ የምንችልበት ምንም መንገድ አልነበረንም፡፡ በግሌ ለቀናት ጸልዬበት ሁሉም አንደኔ እንዲጸልዩ ጠየቅሁ፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሔር በምላሹ ሻለቃ ንትዋሊን ከነመፍትሔው ላከልን፡፡ ሻለቃው አሎይዜ በር ላይ የሚያደርሰን የጭነት ተሸከርካሪ ከነዘዋሪው ሰጡን፡፡ ያ ብቻ አይደለም፤ ተሸከርካሪው ላይ ወጥተን ስናበቃ ብዙ ኬሻ ሩዝ፣ ዱቄት፣ ስኳር፣ ባቄላ፣ ቡና፤ የቆርቆሮ ወተትና ዘይት አስጫኑልን፡፡ ለረጅም ጊዜ ካየሁት ምግብ ሁሉ በላይ ሲሆን ለወራት ሊያቆየን ከሚችለውም የበለጠ ነው፡፡ ደኅና ሁኑ በማለት እጆቻችንን ስናውለበልብና ወደ ኪጋሊ ስናመራ ሻለቃውን ለችሮታቸው ደጋግመን አመስግነናቸዋል፡፡
ከተወሰኑ ወራት በፊት ቢሆን ወከባ የበዛበት የሥራ ቀን ይሆን በነበረ ዕለት ቀትር ላይ ከዋና ከተማዋ ደረስን፡፡ ወደ አስፈሪው ከተማ ገባን፡፡ መንገዶቹ አልፎ አልፎ ከሚመጣው የተመድ የጭነት ተሸከርካሪ ወይም መንገድ ውር ውር ከሚሉት ከሩአግ አነስተኛ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በስተቀር የሚንቀሳቀስ አልነበረባቸውም፡፡ ያሉትም እነዚህ ተሽከርካሪዎች በመንገዶቹ ያሉትን የሰው አስከሬኖች ወይንም ወታደሮቹ እነዚህን አስከሬኖች እንዳይበሉ በጥይት መትተው የገደሏቸውን ዉሾች ላለመዳጥ ተጠንቅቀው ይሄዳሉ፡፡ አየሩ ሞት ሞት ይሸታል፤ ንፋሱም ሰው በሌለባቸው ቤቶች ውስጥ ከሰው ላይ እንደተነሡ መናፍስት ሲሄድ ይሰማኛል፡፡ እጅግ ብዙ ሕንጻዎች በጥይትና በአዳፍኔ ተኩስ ተቃጥለውና ተበሳስተው ፈራርሰው ወድቀዋል፡፡ የሱቆች በሮች ከማጠፊያዎቻቸው ተገነጣጥለዋል፣ የዕቃ መጋዘኖችም ተዘርፈዋል፡፡ አልፎ አልፎም በርቀት ፍንዳታዎች ይሰሙናል፡፡ በአሥራዎቹ ዕድሜዬ ላይ ሆኜ ደማቅ ሰማያዊ መብራቶቿና በሰው የሚጨናነቁት መንገዶቿ ያስደመሙኝን ውቧን ከተማ በዚህ ወቅት ላውቃት አልቻልኩም፡፡
ዘዋሪው ‹‹ተጠንቅቃችሁ ተጓዙ›› ሲል አስጠነቀቀን፡፡ ‹‹በየሄዳችሁበት ፈንጂዎች ተቀብረዋል … የት የት እንደቀበርና
👍2
እንደቀበርናቸው አናስታውስም፡፡ እዚህ አካባቢ ልትላወሱ ወጥታችሁ እግራችሁን በአንድ አፍታ ልታጡ ትችላላችሁ፡፡››
የአሎይዜን ባለቤት፣ ፋሪን፣ እናገኘው እንደሆነ ብለን በቀጥታ ወደ ተመድ ዋና ጽሕፈት ቤት ነዳን፡፡ ‹‹ከኛ ቤት እስከ ተመድ በእግር የሚያስኬደው አሥራ አምስት ደቂቃ ነው፡፡ ኮርኒሳችን ውስጥ ተደብቆ ከዳነ ሊመጣ የሚችለው እዚህ ነው፡፡ ይህ ኪጋሊ ውስጥ በጣም ሰላም ያለበት ስፍራ ነው›› አለች አሎይዜ፡፡ በትልቁ የብረት በር ፊት ለፊት ቆመን አሎይዜን አወረድናት፡፡ ተንቀጠቀጠች - ካገኘኋት ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ መንፈሷ ተናወጠ፡፡ ‹‹ፋሪን ገድለውት ከሆነ እንዴት እንደምኖር አላውቅም›› ስትል እውነቱን ተናገረች፡፡ ‹‹ነፍሴ፣ ሁሉ ነገሬ ነው፣ ጥንካሬዬንም የማገኘው ከእርሱው ነው፡፡ በሕይወት እንዲኖርልኝ በጣም ስጸልይ ቆይቻለሁ… አምላክ ያንቺን ጸሎት እንደሚሰማ ሁሉ የኔንም በሰማኝ፣ ኢማኪዩሌ፡፡›› አምላክ እውነትም አሎይዜን ሰምቷት ኖሯል፡፡ ተናግራ ሳትጨርስ ያን ዓይኗ ማየት የለመደውን ሰው በግቢው ሲንቀሳቀስ አየችው፡፡ ‹‹ወይ አምላኬ … እሱው ነው! እርግጠኛ ነኝ እሱው ነው - አካሄዱን የትም ቢሆን እለየዋለሁ፡፡ ጥሩት፤ አንድ ሰው ይጥራልኝ!››
አንደኛውን የተመድ ዘበኛ ሮጦ አሎይዜ የጠቆመችበትን ሰውዬ እንዲያመጣልን ለመንነው፡፡ ሰውዬው አሎይዜን እስኪያያት ድረስ ወደኛ በቀስታ መጣ … በቻለውም መጠን ሮጠ፡፡ ዋናውን በር አልፎም በጉልበቶቹ ወደቀና ይስማት ገባ፡፡ ‹‹የኔ ውድ›› አላት፡፡ ትንንሾቹ ልጆች ኬንዛና ሳሚም ክርኖቹ ላይ ወደቁና በማቀፍና መሳም ብዛት አፈኑት፡፡ ይህ በሕይወቴ ካየኋቸው የቤተሰብ አባላት መልሰው የተገናኙባቸው ክስተቶች አንዱና እጅግ አስደሳቹ ነው፡፡ ይህ የሆነው ግን ፋሪ፣ ‹‹ሕጻኗስ?›› ብሎ እስኪጠይቅ ድረስ ብቻ ነው፡፡
የአሎይዜ ዓይኖች በእንባ ተሞሉ፡፡ ‹‹ፈጣሪ ወሰዳት›› ስትል አቃሰተች፡፡ ‹‹ትኩሳት ነበረባት፤ አልችል አለችው፡፡››
ፋሪ ራሱን በአሎይዜ ጭኖች ላይ አድርጎ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ያህል አለቀሰ፤ ሌሎቻችን በበኩላችን ተሳቀን እርስ በርሳችን እየተያየን ቆምን፡፡ አንዳችንም አሎይዜ በፈረንሳውያኑ ምሽግ ከመድረሷ በፊት ልጅ እንደሞተባት አላወቅንም፡፡ በጥንካሬዋ ተገረምን፡፡
በኋላም ፋሪ ቀና ብሎ ስለኛ ማንነት ጠየቃት፡፡ ‹‹በስደተኞች መጠለያው ልጆቼ
አድርጌ የተቀበልኳቸው እጓለማውታ›› ስትል አሎይዜ ነገረችው፡፡ ‹‹ከኛ ጋር ይቆያሉ፡፡››
‹‹እንኳን ደኅና መጣችሁልኝ›› አለ ፋሪ፡፡
‹‹ያች ረጅሟ የሮዝና የሊኦናርድ ልጅ ነች … ሁለቱም ወዳጆቻችን አርፈዋል፡፡››
‹‹ወይኔ›› አለ ፋሪ ተነሥቶ እጄን ይዞ፡፡ ‹‹ቁርጥ ወላጆችሽን የኔ ቆንጆ፡፡ ጠንክሪ - እናትና አባትሽ ቆንጆዎችና ደጋጎች ነበሩ፡፡ አንቺን አምላክ ለዓላማ ነው ያተረፈሽ… ያ ዓላማ ምን እንደሆነ እስክታውቂው ድረስ እኛ ጋ መቆየት ትችያለሽ፡፡››
‹‹አመሰግናለሁ›› ከማለት በስተቀር ምን እንደምልም አላውቅም፡፡

ወደ ተሸከርካሪው እንደገና ወጥተን ወደ አሎይዜ ቤት ሄድን፡፡ በመንገድም ላይ ሳለን ፋሪ ላለፉት አራት ወራት ቤቱን ትቶ በተመድ እንደኖረ ነገረን፡፡ ‹‹አሎይዜ ከልጆቹ ጋር ባትመለስልኝ ኖሮ›› አለ ‹‹በጭራሽ አልመለስም ነበር፡፡ ቤት እኮ ያለ ፍቅር እስር ቤት ነው፡፡››
ስፍራው ተተረማምሷል፤ መስኮቶቹ ብትንትናቸው ወጥቷል፤ ግንቡ በጥይት ተበሳስቶ፣ የጣራውም ግማሽ ክፍል ተገልጧል፡፡ ግን ሁላችንም ተረባርበን መጪውን ሳምንት ቤቱን ስንጠግንና ስናጸዳ አሳለፍን፡፡ በጥረት፣ የግንባታ እቃዎች ከተለያዩ የፈራረሱ ቤቶች ተፈልገው ስፍራው እንደገና ቤት መሰለ፡፡ ዢን ፖልና ሌሎቹ ወንዶች የራሳቸው ክፍሎች ሲደርሷቸው ፍሎረንስና እኔ በአንዷ ክፍል ተዳብለን ተቀመጥን፡፡ የወላጆቼን ቤት ከለቀቅሁ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አልጋ ላይ ተኛሁ፡፡ ሁላችንም ገነት ገባን!
ሻለቃ ንዋትሊ የሰጡን ምግብ ቢኖረንም ምንም ገንዘብ የለንም - ልብሶቻችን ለወራት በመለበሳቸው ነታትበዋል፡፡ ወደ ባዶ ቤቶች እየሄድን ጫማና አዳዲስ የሚለበሱ ነገሮች እንፈልግ ያዝን፡፡ በአንድ ቤት ጥንድ የወርቅ የጆሮ ጌጥ አገኘሁ፡፡ ይህን ሁሉ ካሳለፍኩ በኋላ ጥሩ እንዲሰማኝ የሚያደርግ አንድ ቆንጆ ነገር እንደሚገባኝ ራሴን አሳመንኩና ኪሴ ውስጥ አደረግኋቸው፡፡ በአሎይዜ ቤት በመስታወቱ ፊት ስሞክራቸው ግን የማየውን ምስል ልቋቋመው አልቻልኩም፡፡ የሚታየኝ የዚህ ጌጥ ባለንብረት የነበረችው ሴትዮ ፊት ብቻ ሆኖ አረፈው፡፡ የጆሮ ጌጦቹ የኔ አይደሉም፤ ምንም ትውስታዎቼም የሉባቸው፤ ሌላ ሰው እነዚህን ለማግኘት በርትታ ሰርታለች ወይንም እንደ ፍቅር ስጦታነት ተቀብላቸዋለች፡፡ በሌላ ሰው ሕይወት ውስጥ ሳይፈቀድልኝ እንደገባሁ ተሰማኝ፡፡ ለፍቼ ያላገኘኋቸውንና የማይገቡኝን ንብረቶች አልፈለኩም፤ ስለዚህ በመጭው ቀን ጌጦቹን ወዳገኘሁበት ወስጄ መለስኳቸው፡፡
በኋላም በጆሮዬ አንድ ድምፅ ያንሾካሹክ ገባ፤ በሰማሁትም በመስማማት ራሴን ነቀነቅሁ፡ ለመንቀሳቀስ ሰዓቱ አሁን ነው፡፡ ሥራ ማግኛ ጊዜዬ አሁን ነች፡፡



💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3
አትሮኖስ pinned «#ሁቱትሲ ፡ ፡ #ምዕራፍ_አስራ_አምስት ፡ ፡ #የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች ፡ #ትርጉም_በመዝምር_ግርማ ፡ ፡ #ወደ_አማጽያኑ_የሚወስደው_መንገድ ፡ ፡ በነሃሴ መጨረሻ በአንድ ሞቃት ከሰዓት በኋላ የፈረንሳዩ መኰንን ምሽጉን ለቀን ልንሄድ እንደሆነ ነገረኝ፡፡ ዘመቻ ቱርኮይዝ ተጠናቀቀ፣ ስለሆነም ፈረንሳውያኑ ከሩዋንዳ ለመውጣት ይዘገጃጃሉ፡፡ ‹‹ምሽጋችንን ዛሬ እንዘጋለን›› አለኝ፡፡ ‹‹በሁለት ሰዓታት…»
#ሴትነቴ

አዎ. . . እንቢታ ነው
መልስህን አውቃለሁ
ብዙ ፈላጊ አለህ
ምን ተስፋ አደርጋለሁ
ግን ውዴ. . .

መውደዴን ነገሬ
ማፍቀሬን ተንፍሼ
ከራስህ አንደበት
እንድሰማ እንቢታ
እንድመዘገብም
ከአፍቃሪዎችህ ተርታ
ውስጤን ተናግሬ
ልቤ 'ኳ ቢረጋ
እባክህ. . .
. . . ላንዳፍታ
ድፍረትን አውሰኝ
እንዳገኝ እፎይታ።
#ስልጣን

ሁሉም እኩል ሊሆን
ዝና ሁሉ ሊርድ
ነፍስም ቀኗ ሲደርስ
ወደ ሰማይ ልትሄድ
ጠፊ ስልጣን ይዘህ
እውነትን ላትገድላት
በሀብት በጉልበት
በዛሬ መመካት
ለማንም አይጠቅም
ጎበዝ አትሳሳት።
#ሁቱትሲ


#ምዕራፍ_አስራ_ስድስት


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#የጌታዬ_ሥራ

ሰዎች በመንገድ ላይ ለመዘዋወር እንኳን በሚፈሩበት ከተማ ሥራ የት እንደማገኝ የሚያውቀው አምላክ ነው፡፡ ውድቅዳቂ ፈንጂዎች የኪጋሊን መንገዶች ሞልተዋቸዋል፤ ለመሥራት ከፈለግሁ ግን በነዚህ ጎዳናዎች ሥራን እያነፈነፍኩ መኳተን ይኖርብኛል፡፡ የሕዝብ ማጓጓዣ ተሸከርካሪዎች መንቀሳቀሳቸውን ትተዋል፤ ለአነስተኞቹም ማጓጓዣዎች የምከፍለው ምንም ገንዘብ አልነበረኝም፡፡
ፋሪን በቤቱ አቅራቢያ ያሉ ክፍት የሥራ ቦታ ያላቸውን ድርጅቶችን ያውቅ እንደሆነ ጠየቅሁት፡፡ ‹‹አሁን ማንም እየቀጠረ ስላልሆነ አማራጮችሽ በጣም ውሱን ናቸው›› ሲል መለሰልኝ፡፡ ‹‹ያለው ብቸኛ አማራጭ የተመድ ነው … እዚያ ለመግባት ግን እንግሊዝኛ መናገር ያስፈልጋል፡፡››
በአእምሮዬ የሆነ ነገር ብልጭ አለልኝ፡፡ በእርግጥ! እግዚአብሔር በመታጠቢያ ክፍሉ እንግሊዝኛ እንዳጠና ያደረገኝ ዋነኛው ምክንያት እኮ የተመድ ነው፡፡ በተመድ የመሥራት ሕልምም ነበረኝ፡፡
በዚያን ምሽት ልብሶቼን በሚገባ አጥቤ አምላክ በተመድ ሥራ እንዳገኝ ያግዘኝ ዘንድ ጸለይኩ፡፡ በመጨረሻ እንግሊዝኛዬን በሥራ ላይ የማውልበት መሆኑን አስቤ በጣም ተደስቼ አብዛኛውን የሌሊቱን ጊዜ መስታወት ሳይና ራሴን በራሴ ያስተማርኳቸውን ሐረጋት ስለማመድ ቆየሁ፡፡
‹‹እንደምን አደራችሁ››
‹‹እንዴት ነዎት?››
‹‹ሥራ ፈልጌ ነው፡፡›› ስሜ ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ ነው፡፡››
‹‹ሩዋንዳዊት ነኝ፡፡››
‹‹ቡታሬ ባለው ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ አጥንቻለሁ፡፡››
‹‹ሥራ ፈልጌ ነው፡፡››
አቤት! እንዴት ደስ ይላል! ትክክለኛ የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮችን መናገር ጀምሬያለሁ፤ ነገ በአዲስ ቋንቋ እነጋገራለሁ … ከዚያም አዲሱን ሥራዬን እሠራለሁ! ተመስገን አምላኬ!
ልክ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ በተመድ ሕንጻ በር ፊት ለፊት ሄጄ ቆሜያለሁ፡፡ ጋናዊ ዘበኛ እንግሊዝኛ በሚመስል ቋንቋ ሞቅ አድርጎ ሰላምታ ሰጠኝ፡፡ ‹‹እንደምን አደርሽ፣ ምን ልርዳሽ?›› ያለኝ ይመስለኛል፡፡ እኔ የሰማሁት ግን ‹‹ታታታ ታታታ ታታታታ?›› ዓይነት ነገር ነው፡፡ ምንም እንዳለ አንዳች ፍንጭ ባላገኝም የገባኝ አስመሰልኩ፡፡ ራሴን ከፍ፣ አገጬን ወጣ አድርጌ ‹‹እንዴት ነዎት? ስሜ ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ ነው፡፡ ሥራ ፈልጌ ነው›› አልኩ በእንግሊዝኛ፡፡
ውይ፡፡ የዓይኖቹ አኳኋን አነጋገሬ እንዴት አስቂኝ እንደሆነበት ነገረኝ፡፡ ቢሆንም ግን እንደገና ሞከርኩ፡፡ ይህን ሁሉ ርቀት የመጣሁት ተመለሽ ለመባል አልነበረም፡፡ ‹‹እንዴት ነዎት? ስሜ ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ ነው፡፡ ሥራ ፈልጌ ነው››
‹‹አሃ! ሩዋንዳዊት ነሽ… የምትችይው ፈረንሳይኛ መሆን አለበት›› አለኝ፡፡ ፈገግ ብዬ በአዎንታ ራሴን ነቀነቅሁ፡፡ ዋናውን በር ከፍቶልኝ ሌላ ዘበኛ ወደ አንዲት ትንሽ የእንግዳ መቀበያ ክፍል ወሰደኝ፤ ብዙ ቅጻቅጾችን ሞልቼ እንድጠብቅ ተነገረኝ፡፡ ጠበቅሁም … ጠበቅሁ… ጠበቅሁ … ጠበቅሁ፡፡ የተመድ ሠራተኞች ማታ ከሥራ ሲወጡ እንግዳ ተቀባይዋን ሥራውን እስካገኝ ምን ያክል መጠበቅ እንዳለብኝ ጠየኳት፡፡
‹‹ረጅም ጊዜ ትጠብቂያለሽ ውዴ … ሥራ የለም፡፡››
ወደ ቤቴ ተበሳጭቼ ግን ተስፋ ሳልቆርጥ ሄድኩ፡፡ በተመድ መሥራት ዕጣ ፈንታዬ - የማልመውና ቆርጬ የተነሣሁበት ጉዳይ ነው፡፡ ፈጣሪ እዚያ እንድሠራ ከፈቀደ ከግቤ ከመድረስ ምንም አያስቆመኝም፡፡
በቀጣዩም ቀን ተመለስኩ፣ እነዚያኑ ቅጾች ሞላሁና ከሰዓቱን ጠበቅሁ፡፡ በቀጣዩም ቀን ይህንኑ አደረግሁ፤ በቀጣዩም፤ በቀጣዩም፡፡ ቅጾችን ስሞላና ስጠብቅ ከሁለት ሳምንታት በላይ ፈጀሁ፡፡ በየቀኑ ወደ ቤቴ ስሄድ እንግዳ ተቀባይዋ ‹‹እኔ አንቺን ብሆን ተመልሼ አልመጣም ነበር ውዴ፡፡ ምንም ሥራ እኮ የለም›› ትለኛለች፡፡ በሁለተኛው ሳምንት መጨረሻ ተስፋዬ እየተሟጠጠ መጣ፡፡ ሥራ ሳላገኝ ወደ አሎይዜ ቤት መሄድ አስፈራኝ፡፡ ስለሆነም ለራሴ አዝኜ በቤታችን ሰፈር በፈራረሱ መንገዶች እዞር ገባሁ፡፡ በራሴ ዐቅም ላይ ለማተኮር ከአምላክ ጋር ጸጥታ የተሞላበት ተግባቦት እያደረግሁ ለመቀመጥ ፈለግሁ፤ ለዚያ ተመስጦ ግን የአሎይዜ ቤት በጣም ረብሻ የሚበዛበት ነው፡፡ እርስዎ አመኑኝም አላመኙኝ ከአምላኬ ጋር ለሰዓታት ያለማቋረጥ የማወራበትን በቄሱ መታጠቢያ ክፍል ያሳለፍኩትን ወቅት ናፈቅሁ፡፡ በነዚያ ረጃጅም ጸጥ ያሉ ጸሎቶቼ ወቅት ልቤን የሞላበትን ደስታና ሰላም አስታወስኩ
- ከዚያ በኋላ አገኝ የነበረውን የአእምሮ ንጽሕናም ጭምር፡፡
ከአሎይዜ ቤት ሁለት ግቢ አልፎ ወደተቃጠለ ቤት ፍርሥራሽ ሄድኩ፡፡ በጉልበቶቼ በተቃጠለው ፍርሥራሽና በተሰባበረው መስታወት ላይ ተንበርክኬ ጸሎቶቼን ጀመርኩ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ጴጥሮስ ሌሊቱን ሙሉ ዐሳ ለማጥመድ ቢሞክርም ምንም ሳይዝ ቀርቶ ተስፋው ቢሟጠጥ፤ አንተ ግን በዚያው ቦታ ላይ ሄዶ እንዲያጠምድ ነገርከው - እናም ብዙ ዐሳ አጠመደ! በጣም ደስተኛም ሆነ! እኔንም ታዲያ ወደ ተመድ ስለመራኸኝ እስካሁን ይህን ሁሉ ቀን ሥራ ‹እንዳጠመድኩ› አለሁ፡፡ ግን ምንም ዓሶች እዚህ የሉም፡፡ እግዚአብሔር፣ ምን እንደማደርግ አላውቅም፡፡ ገንዘብ የለኝም፤ ልብሶቼ እየተበጣጠሱ ነው፤ ሥራም አያስገኙኝም፡፡ ስለዚህ እገዛህን እፈልጋለሁ፡፡ እነዚህን የተመድ ሰዎች እንዲያዩኝና ጥሩ የጽሕፈት ቤት ሥራ እንዲሰጡኝ አድርግ፤ አንተ እንደምፈልገው ታውቃለህ፡፡ አግዘኝ፤ እኔም በበኩሌ ራሴን አግዛለሁ! ይሁን ይደረግልኝ፡፡››

ራሴን አጸዳድቼና የፈራረሰውን ቤት ትቼ በታደሰ የራስ መተማመን ሄድኩ፡፡ እግዚአብሔርን እገዛውን ጠየቅሁት፤ የምፈልገው አሁን እንዲከሰት ማድረጉ የራሴ ድርሻ እንደሆነ ታውቆኛል፡፡ በተመድ መሥራት የምፈልገውን በአእምሮዬ መቅረጽ ጀመርኩ - ማስታወሻ መያዝ፣ ስልክ መመለስና ጠቃሚ ውሳኔዎች ሲደረጉ ማገዝ፡፡ ወደ ቤት ስሄድ የተመዱን ሥራዬን አንዴ ካገኘሁ በኋላ ስለሚያስፈልጉኝ ነገሮች ሳስብ ቆየሁ፡፡ የተወሰኑ ለሰው ፊት የሚቀርቡ ልብሶች ሊኖሩኝ ይገባል፤ እናም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀኩበት ምስክር ወረቀትና ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ዓመታት መከታተሌን የሚያረጋግጥ መረጃ ያስፈልጉኛል፡፡ ያለመታደል ሆኖ ሁሉም ንብረቶቼ አራት ሰዓት በተሽከርካሪ በሚያስነዳው ቡታሬ በሚገኘው በትምህርት ቤት የመኝታ ክፍሌ ናቸው፤ እንደሚታወቀው ወደዚያ ለመሄድ ደግሞ የምከፍለው ገንዘብ የለኝም፡፡
በሐሳብ በጣም ተውጬ አንድ ተሸከርካሪ በአጠገቤ አልፎ ነጂው ስሜን ሲጣራ ልብ አላልኩትም ማለት እችላለሁ - በዩኒቨርሲቲዬ መምህር የሆነው ዶክተር አቤል፡፡ ‹‹መች አወቅሁሽ ኢማኪዩሌ›› አለኝ፡፡ በጣም ከስተሻል! በመትረፍሽ በጣም ተደስቻለሁ … እንዲያው ምግብስ እየበላሽ ነው? የምትኖሪበትስ ቦታ አለሽ?›› ዶክተር አቤል የህክምና ዶክተር በመሆኑ ስላለፍኩበት ሁኔታና ስለጤናዬ ጉዳይ ጠየቀኝ፡፡ ለማገገም እንዲያግዘኝ ከእርሱ፣ ከሚስቱና ከቤተሰቡ ጋር ቡታሬ እንድኖር ቢጋብዘኝም አመስግኜው የምቆይባቸው ቤተሰብ እንዳሉኝ ነገርኩት፡፡ በቅርቡ ግን ቡታሬ የሚሄድ ከሆነ እንዲወስደኝ ነገርኩት፡፡
‹‹ምን ችግር አለ? በእርግጥ ነገ ሂያጅ ነኝ፡፡››
እንደገና የዕድል ገጠመኝ ነው ብዬ ባሰብኩት በዚህ ጉዳይ የአምላክን
👍4
እጅ አየሁት፡፡ በቀጣዩ ቀን ዶክተር አቤል በዱሮ ዩኒቨርሲቲዬ የፊት በር ጋ ጣለኝ፡፡ ትምህርት ቤቱ ተዘርፎ፣ ወታደሮች በበሩ ስር ተቀምጠው አገኘሁት፡፡ ጠባቂዎቹ ወደ መኝታ ክፍሌ አናስኬድም አሉኝ፡፡ ‹‹ትምህርት ቤቱ ከነጭራሹ ተዘግቷል›› በማለት፡፡ ይባስ ብለው ወደ ኪጋሊ እንድመለስ ነገሩኝ፡፡
እግዚአብሔር እንዴት ወደ ግቢው እንደሚያስገባኝ እስኪያሳየኝ እየጠበቅሁ በመንገዱ ዳር ተቀምጬ በአባቴ መቁጠሪያ ጸለይኩ፡፡ በአሥር ደቂቃ ውስጥ የወታደሮቹን አለቃ ኮሎኔል የጫነች ተሽከርካሪ ዋናው በር ጋ ቆመች፡፡ ለኮሎኔሉ ወታደሮቹ ሰላምታ ለማቅረብ ሲራኮቱ እኔም ሄጄ ተዋወቅሁ፡፡
‹‹እዚህ ምን እያደረግሽ ነው ሚጡ?›› ሲሉ መለሱልኝ፡፡ ‹‹ወላጆችሽ የት ናቸው? እዚህ ብቻሽን መሆንሽ አደገኛ እኮ ነው፡፡››
ሃያ አራት ዓመቴ ቢሆንም በጣም ከመክሳቴ የተነሣ የ12 ዓመት ልጅ መስያለሁ፡፡
‹‹ጌታዬ ወላጆቼማ ሞተዋል፡፡ ከተቀረው ቤተሰቤ ጋር በዘር ጭፍጨፋው ነው የተገደሉት፡፡ በዓለም የቀረኝ ነገር መኝታ ክፍሌ ብቻ ነው፤ ወታደሮችዎ ወደ ትምህርት ቤቱ አናስገባም አሉኝ እንጂ፡፡ ሊያግዙኝ ይችላሉ?›› ስል በተቻለኝ መጠን ተሸቆጥቁጬ ጠየቅኋቸው፡፡
ኮሎኔሉ በሩን ከፍተውልኝ ከአንደኛው ወታደር ጋር ገባሁ፡፡ በበሩም ገብተን ወደ መኝታ ቤቴ አሳዛኙንና አጭሩን ጉዞ አደረግን፡፡
ብዙ አስደናቂ ትዝታዎቹ ያሉብኝና ግሩም ጓደኞችን ያፈራሁበት ውቡ ትምህርት ቤቴ እንዳልነበር ሆኗል፡፡ በየቦታው የቆሻሻ ክምር ይታያል፤ ብዙዎቹ ሕንጻዎችም ጋይተዋል፤ ፈራርሰውማል፡፡ የተማሪዎችን የትምህርት ማስረጃ በግቢው ሙሉ ደርቆ እንደረገፈ ቅጠል ነፋስ ያንገላታቸዋል፤ ከእነዚህ ሁሉ ሳምንታት በኋላም እንኳን አሁንም መሬት ላይ እጅግ ብዙ አስከሬኖች ይታያሉ፡፡ የሳራንና የሌሎቹን የሴት ባልንጀሮቼን አስከሬን እንዳላይ ፈርቼ ደፍሬ ማየት አልቻልኩም፡፡ ከተዝናናሁባቸው የትምህርት ቤት ጭፈራዎች አንዱን፣ የተሳተፍኩባቸውን ተውኔቶችና ከዮሐንስ ጋር ያደረኳቸውን የፍቅር ሽርሽሮች ለማስታወስ ሞከርኩ፡፡ ግን ሁሉም አስቀድሜ ባየሁት የወዳጆቼና የንብረቶቻቸው በየቦታው መውደቅ ሰበብ ጠፉ፡፡ ኮሎኔሉ መኝታ ቤቴ ጋ አውርደውኝ ተሟጦ ወደተዘረፈው መኝታ ክፍሌ ስሄድ ወታደራቸው ተከተለኝ፡፡ በሩ በመጥረቢያ ተገንጥሎ እያንዳንዷ የነበረችኝ ነገር ተወስዳለች - ቦርሳዎቼን፣ ልብሶቼን፣ ጫማዎቼንና ፍራሼን ሳይቀር ዘርፈዋቸዋል፡፡ ይመስገነው፤ የተወሰኑ የወላጆቼ ምስሎች - የአብሮነት ሕይወታችን ብቸኞቹ ማስታወሻዎቼ - በግንቡ ላይ እንደተሰቀሉ አሉ፡፡ ከወለሉ ላይ የተወሰኑ የተበታተኑ የደብዳቤ ኪስ ወረቀቶችን ብለቃቅምም ወታደሩ ከእጄ እየመነጨቀ ያነባቸው ያዘ፡፡
ከትከሻው ጠመንጃውን አውርዶ በማስፈራራት፣ ‹‹ኤይማብል ማነው?›› በማለት ጠየቀኝ፡፡
መሣቅ ስጀምር አስገረምኩት፡፡ ከዘር ጭፍጨፋው መትረፌ አስቆኛል፣ ግን ባዶ የመኝታ ክፍሌን በመዝረፍ ሰበብ በቱትሲ ወታደር በጥይት ተመትቼ ሊያበቃልኝም ይችላል፡፡
‹‹ኤይማብል ወንድሜ ነው፡፡ ያ ደብዳቤ እርሱ ከሚኖርበት ከሴኔጋል የተላከ ነው›› አልኩት፡፡ አያጉረመረመ ደብዳቤዎቼን ሊያነብ ወደ አዳራሹ ገባ፡፡ መሬት ላይ ያሉትን ሌሎች የተወሰኑ ወረቀቶች ሳስተካክል ያየሁትን አላመንኩም፡፡ እዚያ በአንድ ትልቅ ኪስ ወረቀት የሁለተኛ ደረጃ ምስክር ወረቀቴ፣ የዩኒቨርሲቲ ውጤቴና ትምህርት ቤቱ በትምህርት እድሉ ሰበብ ሰጥቶኝ የደበቅሁት ወደ 30 የሚጠጋ ዶላር አለ፡፡ በድንገት ሃብታም ሆንኩ … ከዚያም በኋላ ይህን የተገኘውን ማስረጃ ተጠቅሜ የተማርኩ መሆኔን ማስረዳት እችላለሁ ማለት ነው!
ከትምህርት ቤቱ ግቢ ወዲያውኑ ወጥቼ ከአሜሪካ ዶላሮቼ አንዱን ወደ ኪጋሊ ለመመለስ ተጠቀምኩበት፤ አንድ ሌላ ጸሎቴን ስለመለሰልኝ እቤት እስክደርስ እግዚአብሔርንም አመሰገንኩት፡፡ በእውነት ቃሉን ጠብቆ እንደ ልጁ ተከታትሎኛል፡፡ በከተማው የተወሰኑ ሱቆች ስለተከፈቱ የተወሰኑ ልባሽ ጨርቆችን፣ አዳዲስ ጫማዎችንና ሽቶ ገዛሁ፡፡ ከዚያም በአምስት ወራት ለመጀመሪያ ጊዜ ጸጉሬን ተሠራሁ፡፡ መልሶ ሴትነት እየተሰማኝ ወደ ቤት ሄድኩ፡፡ አሎይዜ ለባብሼና አምሮብኝ ከክፍሌ ብቅ ስል ስታየኝ የልብ ድካም የተነሣባት ያህል አደረጋት፡፡
‹‹ምንም ነገር እንድታገኚ ስትጸልዪ እኔም ትንሽ እንዳገኝ እስኪ ጸልዪልኝ›› አለች ካንጀቷ እየሳቀች፡፡ በተረፈኝ ገንዘብ የገዛሁትን ለአንድ ሌላ ወር የሚበቃንን መጠጥ ሳሳያትማ ይበልጥ ሳቀች!
በቀጣዩ ቀን ጠዋት ሥራ ፍለጋዬን እንደገና ለመቀጠል ወደ ተመድ አመራሁ - አምሮብኝ፣ አልባብ አልባብ እየሸተትኩ፣ የትምህርት ማስረጃዬን ይዤ ሙሉነት ተሰምቶኝና በራሴ ተማምኜ፡፡ በአዲሱ ዓለሟ ስፍራዋን ለመያዝ የተዘጋጀች ሥራዋን የምታስቀድም ሴት ወጥቶኛል፡፡
ጋናዊው የጥበቃ ጓድ በዚህ ወቅት በሩ ጋ አላስቆመኝም፤ በእርግጥ ያለ ምንም ጥያቄ ሳልፍ ፈገግ ብሎ ስላስገባኝ ያወቀኝም አልመሰለኝ፡፡ ሕንጻው ጋ እንደደረስኩ ወደ ሰው ኃይል ኃላፊው ክፍል አቅንቼ በሩን አንኳኳሁና ኃላፊውን በወሬያቸው መካከል አቋረጥኳቸው፡፡
‹‹ምን ልርዳሽ እህቴ?›› ሲሉ በፈረንሳይኛ ጠየቁኝ፡፡
‹‹ሥራ ፈልጌ ነው ጌታዬ›› አልኩ በእንግሊዝኛ … ወይንም ያልኩ መሰለኝ፡፡ ተምታታባቸው፡፡ ‹‹ሥራ እፈልጋለሁ ነው የምትዪው?››
‹‹አዎን ጌታዬ፣ ልክ ነው - ሥራ ፈልጌ ነው›› ስል በፈረንሳይኛ መለስኩ፡፡ እንግሊዝኛዬ የሆነ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው አያጠራጥርም፡፡
‹‹አሃ … እስኪ አንዴ እዚሁ ጠብቂኝ›› አሉኝና ወደ ክፍሉ ገቡ፡፡ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ጸሐፊያቸው ልታነጋግረኝ መጣችና ከላይ እስከ ታች ምንጥር አድርጋ አየችኝ፡፡ ሩዋንዳዊት ነች፡፡ ብቻ በሆነ ምክንያት ገና ስታየኝ ዓይነ-ውኃዬን አልወደደችውም፡፡ ‹‹ወደዚህ ሕንጻ እንዴት ልትመጪ ቻልሽ? ምንድነው
የምትፈልጊው?›› ስትል በኪንያሩዋንዳ ቋንቋ ጠየቀችኝ፡፡
‹‹ሥራ ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹ምን ልምድ አለሽ?››
‹‹ኤሌክትሮኒክ ምህንድስናና ሒሳብ ሳጠና በዩኒቨርሲቲ ነው የቆየሁት፡፡››
‹‹እዚህ ያሉት ሥራዎች የጽሑፍ ሥራዎች ናቸው - ያም የሚሆነው ደሞ ሥራው ሲኖረን ነው፡፡ መቀምር መጠቀም ወይንም እንግሊዝኛ መናገር ትችያለሽ?››
‹‹የጽሕፈት ሥራ ሰርቼ አላውቅም፣ ግን ትንሽ ትንሽ እንግሊዝኛ እሞካክራለሁ፡፡››
‹‹አሃ›› አለች እንደዋዛ፡፡ ‹‹እንግዲህ ምንም ሥራ የለንም - ምናልባት በሦስትና አራት ወር ውስጥ ካለ ነው፡፡ ግን ባለሽ ክህሎት ምንም ሥራ የምናገኝልሽ አይመስለኝም፡፡ እባክሽ ስትወጪ በሩን ዝጊው፡፡››
ክፍሉን ለቅቄ ስወጣ በጣም ስለተበሳጨሁ ወደ ጓሮ በሚያስወጡት ደረጃዎች ማንም ሳለቅስ እንዳያየኝ ብዬ እየሮጥኩ ወረድኩ፡፡ የተወሰኑትን ደረጃዎች እንደወረድኩ አንድ በመካከለኛ ዕድሜ ላይ ያሉ ሰውዬ በፈረንሳይኛ ጠሩኝ፡
‹‹ጠብቂኝ! አንዴ ቆይ እህቴ! ላናግርሽ?››
ሩጫዬን ለመቀጠል ብፈልግም ለታላላቆቼ አክብሮት ስላለኝ ምላሽ መስጠት አለብኝ ብዬ ቆምኩ፡፡ እንባዬን ወዲያውኑ ጠራረግሁና ‹‹አቤት?›› አልኩ፡፡ሰውዬው ሲያዩኝ አኳኋናቸው ከሆነ እንግዳ መንፈስ ጋር ግጥምጥም እንዳሉ ሁሉ አስመሰላቸው፡፡ ‹‹እም… እ… እዚህ ምን እንዳመጣሽ አልገባኝም?››
ዘበኛ ሊጣሩ ነው
1👍1
ብዬ ባስብም ‹‹ሥራ ጌታዬ … ሥራ ፈልጌ ነው›› ስል መለስኩላቸው፡፡
‹‹የሰው ኃይል ኃላፊውን አናገርሽው?››
የደረጃ ላይ ጥያቄያቸው ቢያበሳጨኝም እንደገና በአክብሮት መለስኩላቸው፡፡ ‹‹አዎን ጌታዬ፣ አናግሬያቸዋለሁ፡፡ ግን ምንም ሥራ እንደሌለ ተነግሮኛል፡፡››
‹‹እ … እንግዲህ እንደዚያ ካለ›› ብለው በአድራሻ ወረቀታቸው ላይ የሆነ ነገር ጻጽፈው ሰጡኝ፡፡ ‹‹ነገ ጠዋት ዋናው በር ላይ ይህንን አሳይተሽ ግቢ›› አሉ፡፡ ‹‹አራት ሰዓት ላይ እኔ ሥራ ቦታ እንድትመጪ፡፡ ሥራ እንድታገኚ ማድረግ የምንችለውን ነገር እስቲ እናያለን፡፡››
ምን እንደምል አላወኩም፤ ብቻ እርሳቸው ደረጃውን ሲወጡ በሰጡኝ ወረቀት ላይ አፍጥጬ ቆየሁ፡፡ ጽሑፉ ሳነበው አንዲህ ይላል፡- ፒየር ሜሁ ቃል አቀባይ፣ ዩናሚር የተመድ የሩዋንዳ አጋዥ ተልዕኮ
ቃል አቀባይ ምን እንደሆነ ምንም የማውቀው ነገር የለም፤ ሲያዩት ግን ትልቅ ነገር ይመስላል፡፡ ዩናሚር ከጦርነቱ በፊት የተቋቋመው በሩዋንዳ የተሻለ የመንግሥት አሠራር ለማምጣት ነበር፡፡ ምን አልባት ባልደረባው ልሆን እችል ይሆናል!
በቀጣዩ ቀን ጠዋት ከአቶ ሜሁ ጋር ስገናኝ በዋዜማው በደረጃው ላይ እንዳዩኝ በጣም የሚወዷት ከጦርነቱ በፊት ሠራተኛቸው የነበረችውን ወጣት ሩዋንዳዊት መስያቸው እንደነበር ነገሩኝ፡፡ በዘር ጭፍጨፋው ወቅት ከነቤተሰቧ ነው አሉ የተገደለችው፡፡ ከዚያ በኋላ ታሪኬን አንድነግራቸው ጠይቀውኝ ነገርኳቸው፡፡
‹‹እንዲያው ወርሃዊ ገቢሽ ስንት ነው?›› ሲሉ ጠየቁኝ፡፡
‹‹ምን?››
‹‹ምን ያህል ገንዘብ ታገኛለሽ በወር?››
‹‹ምንም፡፡ ለዚያ ነው እኮ እዚህ የመጣሁት፡፡››
‹‹እስኪ እንግዲህ … ግን የለንም፡፡ ያው መቼም ሥራ እንድታገኚ አግዝሻለሁ፡፡ ወላጆችሽ በደንብ እንዳሳደጉሽ ያስታውቃል፡፡ ወላጅ-አልባ የምትሆኚው መሆን ከፈልግሽ ብቻ እንደሆነ እወቂ፡፡ ከአሁን ጀምሮ የተመድ ቤትሽ ነው፤ እኔንም እንደ አባትሽ ቁጠሪኝ፡፡››
እስኪያመኝ ድረስ ፈገግ አልኩ - እግዚአብሔር በእውነት የሚንከባከቡኝ
መላዕክት በመላክ ቃሉን ጠብቋል፡፡
‹‹በእርግጥ ሁሉንም ፈተናዎች መፈተን ይኖርብሻል›› አቶ ሜሁ ቀጠሉ፤ ‹‹ይህን ትምህርትሽን ይዘሽ ግን ያ አያዳግትሽም፡፡ የመቀምር ጽሑፍና የእንግሊዝኛ ክህሎትሽ እንዴት ነው?››
‹‹መተየብ ባልችልም በመታጠቢያ ቤቱ እንደተደበቅሁ ግን ራሴን እንግሊዝኛ አስተምሬያለሁ፡፡››
‹‹እንደዚያ ከሆነ እንግዲህ …. አስቸኳይ የአጭር ጊዜ ትምህርት ያስፈልግሻል፡፡›› አቶ ሜሁ ከጸሐፊያቸው ከዣኒ ጋር አስተዋወቁኝ፤ እርሷም መቀምር አጠቃቀም፣ ቃለ - ጉባኤ አያያዝና የአቀማመጥ ዝርዝሩን ሁሉ አሳየችኝ፡፡ በመቀምሩ ላይ ያሉትን ሁሉንም ቁልፎች ማስታወስ ቻልኩ፡፡ በተጨማሪም የመጻፊያ ሰሌዳውን ትክክለኛ አምሳል በቁራጭ ክላሴር ላይ ሣልኩት፡፡ በመቀምሩ ላይ ሦስት ቀናት በመፍጀት ሦስት ሌሊቶችን ሙሉ ሳልተኛ አድሬ በእጅ በተሳለው ሰሌዳዬ ላይ ስጽፍና ስለማመድ ቆየሁ፡፡
እግዚአብሔር ጣቶቼን መርቷቸው ሳይሆን አይቀርም፤ በአራተኛው ቀን የተመድን የትየባ ፈተና በአጥጋቢ ውጤት አለፍኩ፡፡ ከተወሰኑ ቀናት በኋላም የእንግሊዝኛውን ፈተና አለፍኩና በተመድ ለመሥራት ብቁ ነሽ ተባልኩ፡፡ በአእምሮዬ ስዬው፣ አልሜው፣ ጸልዬበት ነበረና አገኘሁት!
ለጊዜው ባይነገረኝም የመዝገብ ቤትን ሥራ ቀጥ አድርጌ ይዤው ኖሯል፡፡ ወዲያውኑም ሁሉንም ከውጪ ወደ ሩዋንዳ የሚገቡ የተመድ አቅርቦቶች የመከታተል ኃላፊነት የኔ ሆነ - ከአዳዲስ አነስተኛ ተሸከርካሪዎች እስከ ግዙፍ የምግብ አቅርቦቶች፡፡ ወሳኝ ሥራ ስለሆነ ከተወሰኑ ወራት በፊት እሞት እድን ሳላውቀው በአንድ ሌላ ሰው ትንሽ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ቁጢጥ ብዬ እንደነበር ላምን አልቻልኩም፡፡
ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ የሆኑት የጸሎትና የአዎንታዊ አስተሳሰብን ዐቅም ቋሚ ማሳያ ነኝ፡፡ አምላክ የሁሉም አዎንታዊ አስተሳሰብ ምንጭ ነው፤ ጸሎትም የእርሱን ዐቅም ለማጉረፍ ሁነኛው መንገድ ነው፡፡
አምላክ ከመታጠቢያ ቤቱ ስንትና ስንት መንገድ አምጥቶኛል፤ ይህን መንገድ ስጓዝም እያንዳንዷን እርምጃ አብሮኝ ተጉዟል፡፡ ከገዳዮች አድኖኛል፤ ልቤን በይቅር ባይነት ሞልቶታል፣ እንግሊዝኛ እንድማርም ረድቶኛል፣ ወደ ደህንነትም መርቶኛል፤ ጓደኞች፣ መጠለያና ምግብ ሰጥቶ፤ በመጨረሻም አቶ ሜሁንና የማልመውን ሥራዬን አስተዋውቆኛል፡፡ ባለፉት ብዙ ወራት ያለፍኩበት ምንም ይሁን ምን እግዚአብሔር ከአጠገቤ አልተለየም፤ ብቻዬንም አልሆንኩም፡፡
አዲሱን ሥራዬን ወድጄዋለሁ፤ እያንዳንዷ ቀን ካለፈው የበለጠ አስደሳች ነች፡፡ በተመድ ብዙ የተለያየ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ስላሉ በገዛ አገሬ ጎብኝ የሆንኩ ያክል ተሰማኝ፡፡ አዳዲስ ክህሎቶችን በተከታታይ ስማር፣ ሰዎችን ስተዋወቅና እንግሊዝኛዬን ሳሻሽል ቆየሁ፡፡
ያለኝ የእግዚአብሔር ቡራኬ ብቻ ሳይሆን ደሞዜም ጭምር ነው! ወዲውያኑም ለአክስቶቼ ገንዘብ መላክና አሎይዜና ልጆቿን ላደረጉልኝ ነገር ሁሉ ለማመስገን ምግብና አዳዲስ ልብሶች መግዛት ቻልኩ፡፡ ቤትና ቤተሰብ በጣም በፈለግሁበት ወቅት ሰጥተውኛል … ግን የመሄጃ ጊዜዬም እንደተቃረበ አውቄያለሁ፡፡ በጥቅምት መጀመሪያ ሁሉም ከፈረንሳይ ምሽግ የመጡት ጓደኞቼ የአሎይዜን ቤት ለቀው ስለሄዱ በአቅራቢያዬ ያለው ሁሉም ነገር መቀያየር ጀምሯል፡፡ በ1959ኙና 1973ቱ የዘር ጭፍጨፋዎች ያመለጡ የነበሩ ከሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ቱትሲ ስደተኞች ከዓለም ዙሪያ ልጆቻቸውን፣ የልጅ ልጆቻቸውንና ያላቸውን አዲስ የባህል ቅርስና እንግዳ ቋንቋዎች ይዘው መመለስ ጀማምረዋል፡፡ የሀገሪቱንም ገጽታ እየቀየሩት ነው፡፡ አንድ ሚሊዮን ስደተኛ ተመለሰ፡፡ በዘር ፍጅቱ የተፈጀውን ያህል ቱትሲ መሆኑ ነው - ልረዳው የማልችለው ቁጥር፡፡
ቱትሲዎቹ ሲመለሱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሁቱዎች የበቀል ግድያዎችን ፈርተው ሩዋንዳን ለቀው ተሰደዋል፡፡ አብዛኞቹ በሌሎች አገሮች ባሉ ቆሻሻ የስደተኞች መጠለያዎች መሰቃየት ዕጣቸው ሲሆን ብዙዎች በበሽታና በምግብ እጥረት ሞተዋል፡፡ በየስፍራው ሥቃይ ነግሷል፡፡ አንድ ቀን ብዙ እንዳወቅሁና በቂ ገንዘብ እንዳጠራቀምኩ በሀገሬ ሆኜ የተሸከምኩትን ብስጭት ትቼው ርቄ እሄዳለሁ፡፡ ለአሁኑ ግን የማደርጋቸው ትናንሽ ለውጦች አሉኝ፡፡ ሕይወት በሩዋንዳ እየተለዋወጠ ስለሆነ እኔም አብሬው እለዋወጥ ይዣለሁ፡፡
አምላኬን በፍቅርና በበጎ ስሜቶች የምከበብበትን አዲስ ቤት እንዲሰጠኝ ለመንኩት፡፡ በዚህ ወቅት የአሎይዜን ቤት የፊት በር ስከፍት የራሴን ጸሎት ራሴው እንድመልስ አደረገኝ፡፡ ውድ ጓደኛዬና አንድ ክፍል በኮሌጅ አብራኝ ትማር የነበረችው ሳራ በሩ ላይ ቆማ እኔን በማግኘቷ በደስታ ታነባለች፡፡ ስትፈልገኝ ቆይታ ነው ያገኘችኝ፤ ሁለታችንም ተጯጩኸን ተቃቀፍን፡፡ ለሰዓታት ስለነበረው ነገር ሁሉ እንዲሁ ስንጠያየቅና እንባችንን ስናዘራ ቆየን፡፡ ቄሱ ወንድሞቻችንን ኦገስቲንንና ቪያኒን እንዴት አድርገው በሌሊት እንዳባረሯቸውና ልጆቹ እንዴት አብረው እንደሞቱ ስነግራት ልቤ እንደገና ተሸበረች - በጣም እንወዳቸው ስለነበሩት

ስለወንድሞቻችንና ስለተቀረው ቤተሰቤ በጣም ተላቀስን - ሳራ ሁሉንም ታውቃቸዋለች፤ ትወዳቸውማለች፡፡
‹‹ሁሌም ቢሆን እኛ
👍3
ቤተሰብሽ እንሆናለን›› አለች ሳራ፡፡ ‹‹ነይ እኔ ቤት ኑሪ… መልሰን እህቶች እንሆናለን!›› ሳራ ለኔ እጅግ ልዩ ስለሆነችና ችሮታዋንም ስለምፈልገው ወዲያውኑ ተቀበልኩት፡፡ በዚያኑ ቀን እቃዎቼን አስሬ ወደ ወላጆቿ ቤት ሄድኩ፡፡ አሎይዜ የሳራ ቤት ከቤቷ አምስት ደቂቃ ራቅ ብሎ ስለሚገኝ መሄዴ ምንም አልመሰላት፤ ቶሎ ቶሎ እንደምጠይቃትም ቃል ገባሁላት፡፡
በወቅቱ ከሳራ ቤት የበለጠ ሰላማዊና ፍቅር የሞላበት ቤት አልተመኘሁም፡፡ በዕድሜ የገፉት ወላጆቿ ለ55 ዓመታት ያህል በጋብቻ ኖረዋል፤ እርስ በርሳቸው ግን አሁንም በአሥራዎቹ ዕድሜ ያለን ነን እያሉ ይቀላለዳሉ፤ ይኩራሩማል፡፡ አጥባቂ ክርስቲያኖች ሲሆኑ በየቀኑ ጠዋት አብረው ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ይጸልያሉ፡፡ ቤታቸው ከእግዚአብሔር ጋር የነበረኝን የግል ግንኙነት መልሶ ለመገንባት ትክክለኛው ስፍራ፣ ስለ ቤተሰቤም ለማልቀስና ራሴን መልሼ ለማዳን ሁነኛው ቦታ ነው፡፡ ቀስ በቀስ የቆሰለው ልቤ እነ ሳራ ቤት አሁንም እንኳን ወረቀት ላይ ላሰፍራቸው የማልችላቸውን ቃላት እንድናገር ብርታቱን አገኘ፡፡ በዚያን ወቅት ሴኔጋል ሆኖ ልኑር ልሙት ለማያውቀው ለወንድሜ ለኤይማብልም የምጽፍበት ሰዓቱ ደረሰ፡፡ በከፊል ምንም የመላላኪያ አገልግሎት ባለመኖሩና በዋነኛነት ቃላቱን ካላየኋቸው እነዚያ አሰቃቂ ተግባራት በእውነት እንዳልተከሰቱ አስባለሁ በማለት ይህን አስቸጋሪ ተግባር በይደር አቆይቼዋለሁ፡፡ ችግሮቹ ግን ያው ተከስተዋል - እውንም ናቸው፡፡ ስለሆነም መጨረሻ ላይ መቀበል ጀማመርኩ፡፡
የአባቴን መቁጠሪያ በአጠገቤ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጬ መጻፉን ተያያዝኩት፡- የኔ ውድ ኤይማብል፣ ይህ በሕይወቴ የጻፍኩት እጅግ አሳዛኙ ደብዳቤዬ ነው፣ አንተም የምትቀበለው እጅግ ዘግናኙ …

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «#ሁቱትሲ ፡ ፡ #ምዕራፍ_አስራ_ስድስት ፡ ፡ #የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች ፡ #ትርጉም_በመዝምር_ግርማ ፡ ፡ #የጌታዬ_ሥራ ፡ ሰዎች በመንገድ ላይ ለመዘዋወር እንኳን በሚፈሩበት ከተማ ሥራ የት እንደማገኝ የሚያውቀው አምላክ ነው፡፡ ውድቅዳቂ ፈንጂዎች የኪጋሊን መንገዶች ሞልተዋቸዋል፤ ለመሥራት ከፈለግሁ ግን በነዚህ ጎዳናዎች ሥራን እያነፈነፍኩ መኳተን ይኖርብኛል፡፡ የሕዝብ ማጓጓዣ ተሸከርካሪዎች…»
#ዕውነቴን_የበሉ

ጠግቤአለሁ ብለህ

ሰልፍ ውጣ ቢሉኝ
መፈክሬን ይዤ

በድንገት አዛጋኝ
እነሱም መለሱ

እውነቴን አበሉ
እርቦት አይደለም

እንቅልፍ ነው አሉ።
#ይህች_ሀገር

#ትላንት
ሀገሬ ኢትዮጵያ መመኪያዬ እያለ
የጠቀማት መስሉት ስንቱን ሰው ገደለ፤

#ዛሬ
ይህች ሀገር እንዳለ ስሟን ሳያነሳ
ክብር ተሸለመ በስሟ ሲወሳ ፤

#ነገ
ሰብሳቢ ከጠፋ ደርሶ የሚያድናት
ኢትዮጵያዬ ብለን በስሟም አንጠራት!!
#ሁቱትሲ


#ምዕራፍ_አስራ_ሰባት


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#ሙታኑን_ስቀብር


‹‹ወላጆችሽ የት ነው የሚኖሩት?›› ይህ ጥያቄ በተመድ ሥራዬን ከጀመርኩ ከጥቂት ወራት በኋላ የቀረበልኝ፡፡
‹‹ልቤ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር በሕይወት የሉም›› በማለት በትዕግሥት መለስኩ፡፡
‹‹በዘር ፍጅቱ ተገድለዋል፡፡››
የተመድ ሰቆቃዬን ለመርሳት የምችልበት ስፍራ አይደለም፡፡ እዚያ የሚሰሩት አብዛኞቹ ከሀገሪቱ ውጪ የመጡ ስለሆኑ የቤተሰቤን ዕጣ ፈንታ ሲያውቁ የዘውጌ አባላት አብዛኞቹ በተገደሉበት ሁኔታ እኔ እንዴት ልተርፍ አንደቻልኩ ለማወቅ በጣም ይጓጓሉ፡፡
‹‹ይቅርታ›› አሉኝ እያዋሩኝ ያሉት ሰውዬ፡፡ ‹‹አላወቅሁም፡፡ እንዳላበሳጨሁሽ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡›› ስማቸው ኮሎኔል ጉዬ ሲሆን ወደ ሩዋንዳ አገሪቱን በማረጋጋቱ ተግባር ለማገዝ የመጣው የተመድ ሰላም አስከባሪ ጦር አዛዥ ሴኔጋላዊ ናቸው፡፡ እኔን ስለማበሳጨት እንዳይጨነቁ ለኮሎኔሉ ነገርኳቸው፡፡ ጥያቄ መጠየቅ ያለፍኩትን ሁሉ ከግምት ውስጥ ሳስገባው ከሚያሳስቡኝ ነገሮች በጣም ዝቅተኛውን ደረጃ ነው የሚይዘው፡፡ አሁንም ቢሆን ከጦርነቱ ወዲህ ባላያቸውም አክስቶችና በመጣሁበት ኪቡዬ ክፍለሀገር የሚኖር አጎት እንዳለኝ አሳወቅኋቸው፡፡
‹‹አሃ፣ ኪቡዬ … እዚያ የሰፈሩ የተወሰኑ ወታደሮች አሉኝ›› በማለት መለሱልኝ፡፡ ‹‹ዘመዶችሽን መጠየቅ ካስፈለገሽ ላጓጉዝሽና ራሴ ላጅብሽ እችላለሁ፡፡ ጓደኛም ከፈልግሽ ማምጣት ትችያለሽ፡፡››
በሀገሪቱ መዘዋወር ያን ጊዜም ቢሆን አስቸጋሪና አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ የእርሳቸው ግብዣ ትልቅ ችሮታ ነው፡፡
‹‹በእውነት? መቼ እንደሆነ ይንገሩኝና እንሄዳለን ኮሎኔል፡፡›› ከሁለት ሳምንታት በኋላ ሳራና እኔ ወታደራዊ ጠያራ ላይ በቀበቶ ታስረን አንዳችን የሌላችንን እጆች እየያዝንና በደስታ እየሣቅን በሩዋንዳ አረንጓዴ ተራሮች ላይ እንበር ጀመር፡፡ ሁለታችንም በአየር በርረን ስለማናውቅ ኮሎኔሉ የመብረር እድሉን ሲሰጡን እውነት አልመሰለንም ነበር!
ውቧን አገሬን ቁልቁል ሳያት የዘር ጭፍጨፋውን አስቀያሚ እውነታ ማመን አስቸገረኝ፡፡ በነዚያ ጨለማ ቀናት ምን ያህል ጊዜ ነው ወፍ ሆኜ በተወለድኩ ብዬ የተመኘሁት? ምን ያህልስ ጊዜ ነው ከመታጠቢያ ቤት እስር ቤቴ ወጥቼ ከአሰቃቂው ሰቆቃ በላይ ርቄ መብረርን ያለምኩት? እና አሁን እዚህ ወንጀሉ የተፈጸመበትን ስፍራ ተመልሼ ለመጎብኘት ይኸው እበር ይዣለሁ፡፡ ከማታባ አምልጬ ኪጋሊ ለመድረስ ስንት ጊዜ ፈጅቶብኝ እንደነበር አውርቼልዎታለሁ - ለመመለስ ይኸው 30 ደቂቃ ብቻ ፈጀብኝና አረፈው፡፡
ኤይማብል ከኔ ጋር ቢሆን ብዬ ተመኘሁ፤ ግን አልተቻለም፡፡ የመልዕክት መላላኪያ አገልግሎቱ ገና ቀርፋፋ ሲሆን፤ በዚያም ላይ ከእርሱ የመልስ ደብዳቤ እንኳን ለማግኘት ሳምንታት ፈጅቶብኛል፡፡ ከኔ ይህ ደብዳቤ ስለደረሰውና በሕይወት መኖሬን በማወቁ በጣም ደስተኛ ስለሆነ ስሜቱን ለመግለጽ ቃላት ሊያገኝልኝ እንዳልቻለ ገልጾ ጻፈልኝ፡፡ በዘር ፍጅቱ ወቅት የዜና ዘገባዎችን ይከታተል ስለነበር ሁሉም የቤተሰባችን አባል ከሌላው ሩዋንዳ ውስጥ ካለ ሁሉም ቱትሲ ጋር ወድሟል ብሎ አምኖ ተስፋ ቆርጦ ነበር፡፡ ለመገደል ካልሆነ በቀር በዘር ፍጅቱ ወቅት ወደ ሀገሪቱ የሚመለስበት ምንም መንገድ አልነበረውም፡፡
ለመምጣት ችግር የሆነበት ደግሞ በወቅቱ ለመመለስ ወጪውን መሸፈን አለመቻሉ ነው፡፡ ተማሪ ስለሆነ ገቢ የለውም፣ የሚኖረው 5 000 ኪሎሜትር ርቆ በሴኔጋል ነው፡፡ የአየር መሳፈሪያ ወጭው ብቻ 2 000 የአሜሪካን ዶላር ይፈጃል፤ ይህም የማይታሰብ ነው! ሙሉ ወጭውን ሸፍኖ የሚያስተምረው የአውሮፓ ድርጅትም ሩዋንዳ በጣም አደገኛ የጦርነት ቀጠና ስለሆነ ወደዚያ የምትሄድበትን ክፍያ አልከፍልልህም ይለዋል፡፡ ወንድሜ ትምህርቱን አቋርጦ መጥቶ ከኔ ጋር ለመኖር ቢፈልግም እማማንና አባባን የሚያኮራበት ሁነኛ መንገድ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት መጨረስ እንደሆነ ነገርኩት፡፡ በየሳምንቱ ለመጻጻፍ፣ ለወደፊቱ ለመጠያየቅና ገንዘብም ለማጠራቀም ተስማማን፡፡ እናም አሁን ወደ ማታባ ላገኘሁት የነጻ የአየር ጉዞ ምስጋና ይግባውና ቤታችንን ያለ ብቸኛው ቀሪ ወንድሜ እጎበኛለሁ፡፡

ትንሿ ወታደራዊ ጠያራ መሬት ላይ ካረፈች በኋላ ኮሎኔል ጉዬ ትራኦሬ ለሚባል ብርቱ ወጣት መኰንን አደራ ብለው በወታደሮቹ ምሽግ አስቀምጠውን ይሄዳሉ፡፡ እርሱም ለእያንዳንዱ ወታደር የኮሎኔል ጉዬ ልጆች ናቸው ብሎ አስተዋወቀን፡፡ ከዚህን ጊዜ በፊት በነበሩኝ የወታደር ምሽግ ቆይታዎቼ አግኝቼው የማላውቀውን አገኘሁ - ሳራና እኔ የየራሳችን ክፍል፣ የምንተኛባቸው አልጋዎች፣ ምርጥ ምግብ ብሎም የእያንዳንዱ ወታደር አክብሮትና እገዛ ተቸረን፡፡ እንዲያውም እስከ ንጋት ድረስ ባህላዊ የሴኔጋል ዘፈኖችን ሲዘፍኑና እርስ በርሳቸው ሲቀላለዱ አብረን አነጋን፡፡ ሳራ በአቀባበሉ ደስ ከመሰኘቷም በላይ ደኅንነት ሲሰማት እኔም አገሬ በመግባቴ ደስ ተሰኘሁ፡፡
በማግስቱ ወደ መንደሬ ለመሄድ ስምንት ኪሎሜትር የሚርቀውን የእግር መንገድ ለመጓዝ ስዘገጃጅ መኰንን ትራኦሬ ስለደህንነታችን ያለውን ሥጋት ይናገር ጀመር፡፡ የዘር ፍጅቱ ቢያበቃም በሀገሪቱ ግልጽ የሆነ ጥላቻ ስለነገሰ በዚያን ወቅትም ግድያ ይፈጸማል፡፡ መኰንኑ በትጥቅ አጀብ ሊልከን ወሰነ - አጀቡም ከሁለት ደርዘን ያላነሱ ወታደሮችንና አምስት ብረት-ለበስ ተሸከርካሪዎችን ያጠቃልላል፡፡ ማታባ በጀግና ኩራት እንገባለን እንጂ እንደ ተመላሽ ስደተኛ አንሹለከለክም፡፡ በዚያች መንደር ያን ያህል ጊዜ በፍራቻና ሥጋት ተሸሽጌባታለሁ፤ አሁን ግን ራሴን ቀና አድርጌ መሄዴ መልካም ነው፡፡
በልጅነቴ በጣም በማውቀው ሰማይ ስር ተሸከርካሪዎቻችንን ስንነዳ ስሜቴ በፍጥነት ወደ ኃይለኛ ብስጭት ተለወጠ፡፡ ወንድሞቼና እኔ ብዙውን ጊዜ እንሄድበት ወደነበረው መንገድ ስንገባ ማልቀስ ጀመርኩ፤ ከዚያም በወቅቱ ጭር ባለው እናቴ ታስተምርበት በነበረው ትምህርት ቤት አልፈን አባታችንን ተከትለን በጠዋት ኪቩ ሐይቅ ወርደን ልንዋኝ በምናልፍበት መንገድ ቁልቁል ወረድን፡፡ ሳራ እጇን በትከሻዬ አድርጋ ልታጽናናኝ ብትሞክርም አልሆነም - መጽናናት የምችል አልነበርኩም፡፡ በፈራረሱ መስኮቶችና በተዘጉ የውጪ በሮች አጮልቀው የሚያዩን ፊቶች ጥላ ይታየኛል … ብዙ ወገኖቼን አሳደው የገደሉ ጽንፈኛ ሁቱዎች ፊቶች፡፡ ብዙዎቹን የቱትሲዎችን ቤቶች ራሳቸው ካቃጠሉ በኋላ አሁን ብቻቸውን ቆመው ያሉትን ብቸኛ ቤቶች በንብረትነት ይዘዋቸዋል፡፡ ከዚያም የራሴ ቤት ጋ ደረስን፡፡
ጣራ የለ፣ መስኮት የለ፣ በር የለ፤ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡ ገዳዮቹ ለጭፍጨፋቸው ሲዘገጃጁ እኛ ለቀናት ሬድዮ ስናዳምጥበት የነበረውን የተቃጠለውን መሬት የተወሰኑ ከፊል ግንቦች እየጠበቁት ዘብ ቆመዋል፡፡ አንድ ወቅት የወላጆቼ ሕልም የነበሩትን ባዶ ክፍሎች እየቃኘሁ በድንጋይ መዋቅሩ ውስጥ ተዟዟርኩ፡፡ የተጎዱ የቤት እቃዎችም ሆኑ የተቃጠሉ ልብሶች አሻራ የለም - ማንም ሊገምት እንደሚችለው ቤቱ ከመጋየቱ በፊት ንብረታችን ተዘርፏል፡፡
ብዙ በሕይወት የተረፉ ቱትሲ ጎረቤቶቻችን ወታደራዊ አጀባችንን አይተው ሰላም ሊሉኝ መጡ፡፡ በተደበቅኩባቸው ጊዜያት ስለተከሰቱት መጥፎ ነገሮች ነገሩኝ፤ እናቴ በተቀበረችበት ቦታ ላይ ሆነንም እምዬ እናቴ አንዴት እንደተገደለች ያስረዱኝ
👍1
ገቡ፡፡ የተወሰኑ የዳማሲን ጓደኞች ሊያገኙ የቻሏቸውን የሰውነቱን ክፍሎች በችኮላ ወደቀበሩባት አነስተኛ ጉድጓድ ወሰዱኝ፡፡ ዘበኛችን የነበረው ካሩቡ ወንድሜ ሲገደል ስላየ ንግግሩን ቃል በቃልና እያንዳንዷ ጥቃት ስትሰነዘርበት የነበረውን ክስተት ነገረኝ፡፡
ዘግናኞቹ ትውስታዎች፣ ጭካኔ የተሞላባቸው አረመኔያዊ ዝርዝሮቹ በዝተው ከምችለው በላይ ሆኑብኝ፡፡ ከሃዘኑ ገና ማገገሜ ስለሆነ ቁስሎቼ እንደገና በዚህ አሰቃቂ እውነታ ምክንያት በግድ ሲቀረፉ ተሰማኝ፡፡ ጎረቤቶቼንና ወታደሮቹን ለእናቴና ለወንድሜ የሚገባቸውን ቀብር እንዳደርግላቸው እንዲያግዙኝ ለመጠየቅ ፈለግሁ፤ መናገር ግን አቃተኝ፡፡ በጉሮሮዬ የተፈጠረው እብጠት ድምጼን ስላቆመው ለወታደሮቹ መልሰው ወደ ምሽጉ እንዲወስዱኝ በእጄ ምልክት ሰጠኋቸው፡፡ እማማንና ዳማሲንን ከሸፈነው ምልክት-አልባ የአቧራ ክምር አልፈን ከቤቴ ርቀን እየነዳን ሳለን በአፌ መራራ፣ ቆሻሻ የጥላቻ ጣዕም በአፌ መጣብኝ፡፡ በመልስ ጉዟችን ወቅት ስናልፍ አጨንቁረው የሚያዩንን ፊቶች አየሁና እነዚያ ሰዎች በእጃቸው ደም እንዳለባቸው በሙሉ ልቤ ታወቀኝ - የጎረቤቶቻቸው ደም … የቤተሰቤ ደም፡፡ ወታደሮቹ ማታባ ላይ ነዳጅ አርከፍክፈውልኝ ወደ አመድነት የሚቀይራትን ክብሪት ጭሬ እንድለኩስባት እንዲያደርጉኝ ፈለግሁ፡፡
ምሽጉ ጋ ስንደርስ ከማንም ጋር ሳላወራ በቀጥታ ወደ መኝታዬ ሄድኩ፡፡ ነፍሴ ከራሷ ጋር ተጣላች፡፡ ምኅረት ለማድረግ በጣም ብሟሟትም ይህን በማድረጌ እንደተታለልኩ ተሰማኝ፤ ጭላጭ ምኅረት እንኳን አልቀረኝም፡፡ የቤቴን መፈራረስ ማየቴና የምወዳቸውን ሰዎች የተተዉና ብቻቸውን የቀሩ መቃብሮች መጎብኘቴ መሃሪዋን መንፈሴን አስጨነቃት:: ጎረቤቶቼ የቤተሰቤን አሰቃቂ የግድያ ወሬ በጆሮቼ ሲያሠራጩት ከነፍሴ አስወግጄዋለሁ ብዬ ያሰብኩት የጥላቻ ስሜት ከማንነቴ ጥግ በታደሰ ጉልበት በግድ ተስፈንጥሮ ወጣ፡፡ ልቤ በቀልን ተርባ በውስጤ በገንኩ፡፡
እነዚያ ክፉ እንስሳት! አራዊት ናቸው፣ አራዊት፣ አራዊት፣ አራዊት!
ለሰዓታት መኝታዬ ላይ ተገላበጥኩ፡፡ ዲያብሎስ እየፈተነኝ እንደሆነ ታውቆኛል - ከእግዚአብሔር ብርሃን፣ ከምህረቱም ነጻነት አርቆ እየወሰደኝ አንደሆነ፡፡ የአሉታዊ ሐሳቦቼ ክብደት በጨለማው እየመራ ካመጣኝ ብርሃን ሲነጥለኝና ሲጎትተኝ ይታወቀኛል፡፡ በዚያ ሌሊት እንደተሰማኝ ዓይነት ብቸኝነት ፈጽሞ ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ እግዚአብሔር እውነተኛው ባልንጀራዬ ነው፤ እነዚህ ስሜቶች በመሀላችን እንደ ግንብ ቆመዋል፡፡ ሐሳቦቼ እንዳሳመሙት አወቅሁ፤ ይህም አሰቀቀኝ፡፡ ከአልጋዬ ወርጄ ተንበረከክሁ፡፡ ‹‹ስለ ርኩሳን ሐሳቦቼ እግዚአብሔር ሆይ ማረኝ›› ስልም ጸለይኩ፡፡ ‹‹እባክህ … ሁልጊዜ እንዳደረከው ይህን ህመም ከኔ አርቀህ ልቤን አንጻልኝ፡፡ በፍቅርህና በምኅረትህ ኃይል ሙላኝ፡፡ እነዚያን አሰቃቂ ነገሮች ያደረጉት አሁንም ቢሆን ልጆችህ ናቸው፡፡ ስለዚህም ልርዳቸው፤ አንተም እንድምራቸው
አግዘኝ፡፡ ኧረ አምላኬ፣ እንድወዳቸው እርዳኝ፡፡››
ሳንባዎቼን ድንገተኛ የአየር መአት ሞላቸው፡፡ በከባድ የእፎይታ ትንፋሽ አቃሰትኩ፤ ራሴንም ትራሱ ላይ እንደገና አሳረፍኩት፡፡ ሰላሜን እንደገና አገኘኋት፡፡ አዎን፣ ተበሳጭቼ፣ በእጅጉ በግኜም ነበር፤ ብስጭቴ ግን ለበጎ ሆነ፡፡ እንዲቆጣጠረኝ የፈቀድኩለት ይህ ብስጭት ንጹሕ መሆኑን አወቅሁ፡፡ ምሬት ወይንም ጥላቻ የሚባል ነገር የሌለበት፡፡ ቤተሰቤን በእጅጉ ብናፍቅም እንደ ግርሻ ወጥሮ ይዞኝ የነበረው ንዴቴ ግን ለቆኛል፡፡
ቤተሰቤን የጎዱት ሰዎች እንዲያውም ራሳቸውን በበለጠ ጎድተዋል፤ በመሆኑም ላዝንላቸው ይገባኛል፡፡ በሰብዓዊነትና በእግዚአብሔር ላይ ለፈጸሟቸው ግፎች መቀጣት እንዳለባቸው ማንም ጥርጥር አልነበረውም፡፡ ተጠያቂ የሚሆኑትን ለመያዝ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቋቋም በተመድ ውይይት ተጀምሯል፤ ይህም እንዲከሰት፣ ርህራሄም እንዲኖር ጸልዬአለሁ፡፡ እግዚአብሔርን የጥላቻን ዑደትና ጽንፍ የረገጠን ጥላቻ የሚያቆመውን ምኅረት እንዲለግሰን ጠይቄዋለሁ፡፡ ልቤና አእምሮዬ ሁሌ ንዴት ሊሰማቸው እንደሚዳዳቸው አውቄዋለሁ - ውንጀላንና ጥላቻንም እንደሚፈልጉ፡፡ አሉታዊ ስሜቴ ሲመጣብኝ ይህን ችግር ፈታሁት፤ እንዲያድግ ወይንም እንዲባባስ አልፈለግሁም፡፡ የሁሉም እውነተኛ ኃይል ምንጭ ወደሆነው ወዲያውኑ ፊቴን እመልሳለሁ፡፡ ወደ እግዚአብሔር እዞራለሁ፤ ፍቅሩና ምህረቱም ከለላና ድኅነት ይሆኑኛል፡፡
ራሴን ቀና ሳደርግ ጨረቃ እንደወጣች አየሁ፡፡ ወታደሮቹ ሲስቁና ሲዘፍኑ ስለሰማኋቸው ወደ ውጪ ወጣሁ፡፡ ሳራና እኔ እርስ በርሳችን ተሣሣቅንና እንደገና እዚያ ባሉት በሁሉም ላይ ፈገግ አልኩ፡፡ ወታደሮቹ እየተዝናኑ ስለሆነ እኔ በጣም ደስ ያለኝ መስዬ ስቀላቀላቸው ተገረሙ፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ሲጨፍሩ ሳራና እኔ ታዳሚ በመሆን ስናደማምቅላቸው ቆየን፡፡

በቀጣዩ ቀን እናቴንና ወንድሜን እንደ ደንቡ ለመቅበር መኰንኑ መልሶ ወደ መንደሩ ይወስደኝ እንደሆን ጠየቅሁት፡፡ በዋዜማው የገባሁበትን ሐዘን አስቦ በእውነት አስፈላጊው ጥንካሬ እንዳለኝ ጠየቀኝ፡፡ ጥንካሬው እንዳለኝም አረጋገጥኩለትና ወደ መንደሩ ያለፈውን ቀን የሚያህል የወታደር አጀብ ፈቀደልኝ፡፡ መንገዳችን ላይ በድሮው ቤታችን አቅራቢያ የሚኖሩትን አክስቶቼን ዣኒንና ኢስፔራንስን ለመጠየቅ ቆምን፡፡ ከፈረንሳውያኑ ምሽግ ከወጣን ወዲህ አልተገናኘንም፡፡ ሁለቱም ከሰቆቃቸው ሙሉ በሙሉ ባያገግሙም (እንዳያያዛቸውማ መቼም የሚያገግሙ አይመስሉም) በወቅቱ ግን ቢያንስ በጣም በተሻለ ሁኔታ ላይ ነበሩ፡፡ ስሜት በተቀላቀለበት ሁኔታ በመንገድ ዳር መልሰን ተገናኘን፣ እኔ ግን ልቤን ወደፊት ለሚጠብቀኝ ጽኑ ግዳጅ በደኅና አቆየሁት፡፡ የእማማና የዳማሲን ቀብር ላይ የሚገኙ ሰዎችን እንዲፈልጉና አሮጌው ቤቴ ጋ እንዲያገኙኝ ነገርኳቸው፡፡
አብዛኞቹ በመንደሬ ያሉት ቱትሲ የዘር ፍጅት ተራፊዎችና የተወሰኑ ሁቱ ወዳጆቻችን ተገኙ፡፡ አንድ ካይታሬ የተባሉ ሽማግሌ የቤተሰቤ ወዳጅ ሁለት የሬሳ ሣጥን፣ አንድ ሌላ ሰው ደግሞ አካፋና መጽሐፍ ቅዱስ አምጥተው ሁላችንም አስከሬናቸውን ፍለጋ ሄድን፡፡ በመጀመሪያ ዳማሲንን ፍለጋ ተቆፈረ፤ የተወሰኑ ጎረቤቶቻችን እንዳላይ ለመከለል ከበቡኝ - ቀስ ብለው የተገኘውን የአካሉን ክፍል እንዳላይ ከለከሉኝ፡፡
ተጋፍቼ አለፍኳቸው፡፡ ‹‹ወንድሜ አይደል እንዴ - ማየት አለብኝ›› ብዬ አስቸገርኩ፡፡ አስከሬኑን በዓይኔ ባላይ ኖሮ ዳማሲን ሞቷል ብዬ መቼም የማምን አይመስለኝም፡፡ ከዚያ አካፋው ከአጥንት ጋር ሲጋጭ ሰማሁት፤ ከዚያም አየሁት … የጎድን አጥንቶቹን አየሁ፡፡ መጀመሪያ ያየሁት ምንም ልብስ እንዳልለበሰ ነው፤ ከመግደላቸው በፊት ምን ያህል ክብሩን ሊገፉት እንደሞከሩም አስታወስኩ፡፡
‹‹አትዪ›› አለችኝ ኢስፔራንስ፡፡ ግን ግድ ይለኛል - የጎድን አጥንቶቹን እንጂ ምንም አላየሁም፡፡ ከታትፈውታል - ክርኖቹን፣ ራሱን … ወይኔ፣ እግዚአብሔር፣ የኔ ውድ ዳማሲን፣ ምንድነው ያደረጉህ? ስል እንደ እንስሳ ግሳት ዓይነት ድምፅ አወጣሁ፡፡ አንድ ሰው ወደ መቃብሩ ጎንበስ ብሎ የወንድሜን የራስ ቅል በእጁ ይዞ ቀና አለና ወደኔ ዞረ፡፡ መንጋጭላው ወጣ ብሎ ጥርሱን አየሁት … በጥርሱ አወቅሁት፡፡ ጥርሱ ከአማላይ ፈገግታው የቀረው ብቸኛው ነው፡፡ እኔ ላይ በአሰቃቂና አስፈሪ ፈገግታ አተኩሮብኛል፡፡ አይ ዳማሲንዬ! እንዲህ መጨረሻህ
ሳያምር ይቅር!
‹‹እንዴ አይሆንም! … እንዴ ዳማሲን! … ወይኔ! ቅድስት ማርያም! የአምላክ እናት!›› መሬቷ ወደኔ ሮጠችና ራሴንም ድንጋይ መታው፣ ከዚያማ በቃ ጽልመት ብቻ፡፡
ራሴን እስታለሁ ብዬ ባልጠበቅም አእምሮዬ በመጨረሻ የወንድሜን ሞት ሲያምን ከዓለም የምንተነፍሰው አየር ተመጦ እንዳለቀ ተሰማው፡፡ ዘመዶቼና ጎረቤቶቼ እንድነቃ አድርገው ደጋግፈው በእግሮቼ አቁመውኝ የዳማሲንን አስከሬን ወደ ሣጥን አስገብተን ደግሞ የእማማን ፍለጋ ይዘነው እንዞር ገባን፡፡ አንዴ ለጉድ ጎልቶኝ! ሰዎቹ በዚህን ሰዓት የሰውነቷ ክፍሎች አይለዩም፤ ደግሞ በጣም አፈር ስለበላው እጅጉን ያበሳጭሻል ብለው አስቸገሩኝ፡፡ የሕመሜ ወሰን ላይ ስለደረስኩም ተስማማሁ፡፡ ምንም ያህል ልቤን ባጠነክረውም እናቴን በእንደዚያ አይነቱ ሁኔታ ማየቱ ለአፍቃሪ ዓይኖቼ መቻል ከሚችሉት በላይ ይሆንባቸዋል፡፡ አስከሬኗን ሳላይ ለመቅበር ተስማማሁ፡፡ ይልቅ በሕይወት እንደነበረችው ባስታውሳት ይሻለኛል … ዘላለም በልቤና በህልሞቼ እንደምትኖረው ሁሉ፡፡
አንድ ሰው እናቴ ባለችበት ሣጥን ክዳን ላይ ሚስማር ሲመታ የጓደኞቼንና የዘመዶቼን ፊቶች አየሁ - የተሸበሩ ሕይወቶችን የሚያንጸባርቁ የተሸበሩ ፊቶች፡፡


ሶስቱ ልጆቿ እፊቷ ሲታረዱ እንድታይ የተገደደችው የአክስቴ ልጅ፤ በሚወዳት ሚስቱና በሰባት ልጆቹ ሞት ከበፊቱ ማንነቱ ጥላው ብቻ የቀረው በአንድ ወቅት የሚንቀለቀል ቁርጠኝነት የነበረው አጎቴ ፖልና ባሎቻቸው ሞተውባቸው ልጆቻቸው መዳን በማይችሉበት ሁኔታ ታመው ያሉት አክስቶቼ ሁሉ ቆመዋል፡፡ ከተራራ የከበደ ሐዘን የተሸከሙ ፍጡራን!
በመንደሩ ላይ የወረደውን ትካዜ ሁላችንም እንጋራዋለን፣ ግን በዙሪያዬ የተሰበሰቡት ሰዎች ከኔ በላይ ብዙ ሰው እንደተነጠቁ አውቄያለሁ፡፡ እምነታቸውን አጥተዋል - በዚያም ተስፋ አጥተዋል፡፡ በእናቴና ወንድሜ አስከሬኖች ላይ አፍጥጬ አስከሬኖቻቸውን ላገኘው የማልችላቸውን አባቴና ቪያኒን አሰብኩ … አምላክንም አመሰገንኩት፡፡ ሁሉንም ባጣም እምነቴን ግን ጠብቄያለሁ፤ እሱም ያጠነክረኛል፡፡ አበርትቶኛል፤ አሁንም ሕይወት ዓላማ እንዳላት አሳውቆኛል፡፡
‹‹የት እናድርጋቸው በይ? የት እንቅበራቸው?›› እጆቹን በጽድ ሳጥኖቹ ላይ ወዲያና ወዲህ እያላወሰና እያነባ አጎቴ ፖል ጠየቀኝ፡፡
‹‹እቤት›› አልኩት፡፡ ‹‹እቤት ወስደን እናሣርፋቸው፡፡››
የእናቴንና የወንድሜን አስከሬኖች ይዘን ወደ ቤታችን ፍርሥራሽ ወሰድንና በአንድ ወቅት ሣቅና ፍቅር የሚያስተጋባበት የነበረው አንደኛው ቤት በነበረበት ስፍራ ወለል ላይ ትልቅ የመቃብር ጉድጓድ ቆፈርን፡፡ በመንደሩ ያሉ የቀሩ ምንም ቄሶች ስለሌሉ ራሳችን የደንቡን አደረግን፡፡ እማማ ትወዳቸው የነበሩ የተወሰኑ መዝሙሮች ዘመርን፤ ብዙ ጸሎትም አደረስን፡፡ እግዚአብሔርን ቤተሰቤን ወደራሱ አቅርቦ እንዲይዝልኝና ንጹሕ ነፍሶቻቸውን በገነት ባለህ እንዲልልኝ ጠየቅሁት … ከዚያም ደኅና ሁኑ አልኩ፡፡
‹‹በቃ መሄጃችን ሰዓቱ አሁን ነው ሳራ - ኪጋሊ መሄጃችን ደርሷል›› ስል ለውዷ ባልንጀራዬ፣ በማደጎ ተቀብላ ለምታኖረኝ እህቴ ብሎም አዲስ ቤተሰብ ለሰጠችኝ ለሳራ አንሾካሾክሁ፡፡
ወዲያውኑም ተመልሰን በደመና ውስጥ ገብተን ከመንደሬ በላይ ከፍ ብዬ እበር ጀመር፤ ሕይወታችንን ካጨቀዩት ሰቆቃዎች በላይ … በጣም ከፍ በማለቴም የእግዚአብሔርን ፊት መንካት የምችል መሰለኝ፡፡

ቤተሰቤ በገነት እንዳለ ማወቄ እነሱን የማጣቴን ሕመም አላቀለለልኝም፡፡ አሟሟታቸው በታሰበኝ ቁጥር ልቦናዬን የሚቆጣጠረውን ሰንካዩን ሰቀቀን ላራግፈው አልተቻለኝም፡፡ እንቅልፍ ከሚነሳኝና ቀን ከሚያስቸግረኝ ሥቃይ ለመገላገል በየምሽቱ ጸልያለሁ፡፡ የተወሰነ ጊዜ ወሰደብኝ፣ ግን እንደሁሌው እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማኝ፡፡ በዚህ ወቅት ይህን ያደረገው እስከዚያን ጊዜ አይቻቸው ከነበሩት የተለየ ሕልም በማሳየት ነው፡፡
በቤተሰቤ ቤት ላይ በወታደራዊ ጠያራ እየበረርኩ ሳለሁ ጥቁር ደመና ከበበኝ፡፡ እማማን፣ አባባን፣ ዳማሲንንና ቪያኒን ከኔ በላይ ከፍ ብለው በሰማይ ቆመውና ጸጥታን በሚያንጸባርቅ ልዩ፣ ነጭ ብርሃን ተጥለቅልቀው ታዩኝ፡፡ ብርሃኑ የሸፈነኝን ጥቁር ጨለማ እስኪገፈው ድረስ በሰማይ ላይ ተንሠራፋ፡፡ በድንገትም እንደገና ከቤተሰቤ ጋር ተገናኘሁ፡፡ ሕልሙ በጣም እውን ስለሆነ በእጄ ተንጠራርቼ የሰውነታቸውን ሙቀትና የንክኪያቸውን ሃያልነት ተረዳሁ፡፡ በጣም ደስ ስለተሰኘሁ በአየሩ ላይ ዳንኪራ ረገጥኩ፡፡
ዳማሲን አዲስ፣ ንጹሕ፣ ምርጥ ነጭ ቲሸርትና ሰማያዊ ሱሪ ለብሷል፡፡ በደስታ በፈካ ፊት ካየኝ በኋላ ፈገግ አለ፡፡ ከኋላው እማማ፣ አባባና ቪያኒ እጅ ለእጅ ተያይዘው እኔን ሲያዩ በደስታ ፈክተው ቆመዋል፡፡ ‹‹ታዲያስ ኢማኪዩሌ፣ አሁንም አንቺን ለማስደሰት መቻላችንን ማየታችን መልካም›› አለ መልከ ቀናው ወንድሜ፡፡ ‹‹ይህን ሁሉ ጊዜ ደብቶሻል፤ ለቅሶሽን መተው አለብሽ፡፡ ያለሽበትን ድንቅ ስፍራ እስኪ እዪ … እንዴት ደስ እንዳለን አታዪም? በሥቃይ ላይ እንዳለን በማመንሽ ከቀጠልሽበት ትተነው ወደሄድነው ህመም እንድንመለስ ታስገድጅናለሽ፡፡ ምን ያህል እንደምትናፍቂን አውቃለሁ፣ ቢሆንም ግን … ተመልሰን መጥተን እንድንሰቃይ ትፈልጊያለሽ?››
‹‹አይሆንም፣ አይሆንም፣ ዳማሲን!›› ስል ጮህኩ የደስታ እንባ ከዓይኖቼ እየወረደ፡፡ ‹‹እዚህ አትምጡ! እዚያው ጠብቁኝ፤ ስመጣ ሁላችሁንም አገኛችኋለሁ፡፡ አምላክ በዚህ ሕይወቴ በቃሽ ሲለኝ ወደናንተ እመጣለሁ፡፡››
‹‹እዚሁ እንጠብቅሻለን እህት ዓለም፡፡ አሁን ልብሽን ፈውሺ፡፡ ማፍቀር አለብሽ፤ በኛ ላይ የተላለፉትንም መማር አለብሽ፡፡››
የቤተሰቤ አባላት ቀስ በቀስ ወደ ሰማይ እያፈገፈጉ መንግሥተ-ሰማያት ውስጥ ተደበቁ፡፡ ከዚህ ክስተት በኋላም በቤቴ ላይ እያንዣበብኩ ቢሆንም ከጨለማው ደመናና ከምበርበትም ጠያራ ወጥቻለሁ፡፡ በመንደሬ ላይ እንደ ወፍ በረርኩባት፤ በቄሱ ቤትና በፈረንሳዮቹ ምሽግ ላይ፣ በውድ ሀገሬ ሁሉም ወንዞችና ፏፏቴዎች በላይ
- በሩዋንዳ ላይ አንዣበብኩባት፡፡
ከሐዘንና ከመሬት ስበት በጣም ነጻ ስለወጣሁ በደስታ መዘመር ጀመርኩ፡፡ ከልቤ ዘመርኩ፤ ቃላቱ በደስታ ከአፌ ጎረፉ፡፡ መዝሙሩ ‹‹ምዋሚ ሺሚርዋ›› የሚል ሲሆን በኪንያሩዋንዳ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ ከአእምሮ በላይ ለሆነው ፍቅርህ አመሰግናለሁ›› ማለት ነው፡፡
እኩለ ሌሊት ስለሆነ ዝማሬዬ ቤተሰቡን በሙሉ ከእንቅልፉ ቀሰቀሰው፡፡ የሳራ እናት ወይ አመማት ወይ ትኩሳት ያዛት ብለው በመሥጋት ወደ ክፍሌ ሲሮጡ መጡ፡፡
ከዚያን ምሽት በኋላ እንባዬ መድረቅና ሕመሜም መቀነስ ጀመረ፡፡ ስለቤተሰቤ ዕጣፈንታ አስቤ ድጋሚ በፍጹም አልተሰቃየሁም፡፡ ሁሌም አለቅስና እናፍቃቸዋለሁ ብዬ ባምንም አንዲትም ቀን ስላዩት ሥቃይ ስጨነቅ አላሳልፍም፡፡ አምላክ የቤተሰቤ አባላት ሥቃይ ካለበት ስፍራ ርቀው ወዲያ ማዶ እንዳሉ በሕልም አሳየኝ፡፡ ወደ መንደሬ ሌላ ጉዞ ማድረግ እንዳለብኝም አሳይቶኛል፡፡

ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ኮሎኔል ጉዬ እንደገና ወደ ሀገር ቤት የመሄድ ዕድል ሰጡኝ፣ በዚህ ጊዜ ግን የነዳነው በሀገር አቋራጭ ነው፡፡ የአገሬ መልከዓ-ምድር በዚያን ወቅት አላበሳጨኝም፤ እንዲያውም በዙሪያዬ ባሉት ትዕይንቶችና ድምጾች ሰበብ በሚነሳሱት ትኩስ ትዝታዎቼ ተነቃቅቻለሁ፡፡ በእናቴ የሙዝ ልማትና በተራራ ጥግ
👍2
በሚገኘው የአባቴ የቡና ማሳ ውስጥ ከጓደኞቼ ጋር ተዘዋውሬያለሁ፡፡ ለአክስቶቼ ዱር መሄድ ካልፈሩ የአትክልቶቹን አላባ እንዲጠቀሙበትና ኑሯቸውን እንዲደጉሙበት ነግሬያቸዋለሁ፡፡
አክስቴ ዣኒ ስለመፍራቱ እንዳላስብ ነገረችኝ፡ ጠመንጃ በቅርቡ ስለምታገኝ አተኳኮስም ትማራለች፡፡ ‹‹ለወደፊቱማ ዝግጁ እሆናለሁ›› አለች፡፡ ለወደፊቱ በማለት፣ በጣም ተንፍሼ አሰብኩ፡፡
እማማንና ዳማሲንን ለመጠየቅ ወደፈራረሰው ቤታችን አቀናሁ፡፡ በመቃብሮቻቸው አጠገብ ተንበርክኬ ለመጨረሻ ጊዜ ካየኋቸው በኋላ የተከሰተውን ሁሉ ነገርኳቸው፡፡ በተመድ ስላገኘሁት ሥራና ወደፊት ምን ለማድረግ እንዳሰብኩ ነገርኳቸው፡፡ ፊቶቻቸውን ማየትና ድምጾቻቸውን መስማት ስለናፈቀኝ አለቀስኩ፡፡
የዚያን ሰዓቱ እንባዬ ግን የነጻነት እንጂ የሰቆቃ አይደለም፡፡
ከዚያ በኋላ ላደርግ የመጣሁትን ነገር ማድረጊያው ጊዜ ደረሰ፡፡

ከሰዓት በኋላ ዘግየት ብዬ ማረሚያ ቤት ስደርስ አዲሱ የኪቡዬ አስተዳዳሪ ሴማና ተቀበለኝ፡፡ ሴማና ከዘር ፍጅቱ በፊት መምህር፣ የአባቴ የሥራ ባልደረባና ጥሩ ጓደኛ ሲሆን፤ እኔ ደግሞ እንደ አጎቴ አየው ነበር፡፡ ከስድስት ልጆቹ አራቱ በእርዱ አልቀዋል፡፡ ስለሆነም እኔ ልጆቹ ከእግዚአብሔር ጋር እንደሆኑ እምነቱ እንዲኖረው ነገርኩት፡፡
‹‹ዓለም ምን ያህል እንደተቀየረች ማየት ቻልኳ፤ ልጆች ወላጆቻቸውን ያጽናናሉ›› በማለት በሆድ ብሶት መለሰልኝ፡፡
እንደ አስተዳዳሪነቱ ሴማና አካባቢያችንን ያሸበሩትን ገዳዮች የማሰሩንና በቁጥጥር ስር የማቆየቱን ሥራ የሚሠራ ትልቅ ዐቅም ያካበተ ፖለቲከኛ ሆኗል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢንተርሃምዌዎችን ስለመረመረ ከማንም በተሻለ የትኛው ገዳይ ማንን እንደገደለ ያውቃል፡፡
በመሆኑም ለምን ጉዳይ እንደመጣሁ አውቋል፡፡ ‹‹እናትሽንና ዳማሲንን የገደለውን ቡድን የመራውን ማግኘት ትፈልጊያለሽ?››
‹‹አዎን ጋሼ፣ እፈልጋሁ፡፡››
በጽሕፈት ቤቱ መስኮት ስከታተል ሴማና ግቢውን አቋርጦ ወደ ወንጀለኞች ማቆያው ክፍል ደርሶ ሲመለስ አየሁት፡፡ ሁሉ ነገሩ የቆሻሸሸና የሚያነክስ ሽማግሌ እየነዳ ተመለሰ፡፡ እየቀረቡኝ ሲመጡም ወዲያውኑ ሰውዬውን ስላወቅሁት በድንገት ወደ ሰማይ ዘለልኩ፡፡ ይህ የተሳካለት ሁቱ ነጋዴ አያ ፌሊሲን ነው፡፡ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስማር ከልጆቹ ጋር እጫወት ነበር፡፡ ረጅም፣ መልከ መልካም፣ ሁሌ ውድ ሱፍ ልብሶች የሚለብስና ለንጽሕናው ጥንቁቅ ነበር፡፡ ገዳዮቹ ወደ ቄሱ ቤት መጥተው ሲፈልጉኝ ስሜን እየተጣራ ሲፈልገኝ ድምጹን ስለሰማሁት ተንቀጠቀጥኩ፡፡ ፌሊሲን ሊገድለኝ ሲያድነኝ ሰንብቷል፡፡
ሴማና ፌሊሲንን ወዳለሁበት ክፍል ሲገፈተረው በጉልበቱ ወደቀ፡፡ ከወለሉ ቀና ብሎ የምጠብቀው እኔ መሆኔን ሲያስተውል አመዱ ቡን አለ፡፡ ድንገትም እይታውን ወደ ሌላ አቅጣጫ መልሶ መሬቱ ላይ አፈጠጠ፡፡
‹‹ተነሥ፣ አንተ ነፍሰ-በላ!›› ሲል ሴማና ጮኸበት፡፡ ‹‹ቆመህ ለዚህች ልጅ ቤተሰቧ ለምን እንደሞተ ንገራት፡፡ እናቷን ለምን እንደገደልክና ወንድሟን ለምን እንዳረድክ አብራራላት፡፡ ተነሥ ብያለሁ! ተነሥና ንገራት!›› ሴማና የበለጠ ጮክ ብሎ ተናገረ፤ የተጎዳው ሰውዬ ግን ተነሥቶ ዓይኔን ማየቱ በጣም አሸማቆት እንደተንበረከከና እንዳቀረቀረ ቀረ፡፡ ቅስሙ ተሰብሯል፡፡
አዳፋ ልብሱ በመነመነው ሰውነቱ ላይ ተቀዳዷል፡፡ ቆዳው ከመገርጣቱ፣ ከመቆሳሰሉና ከመሸብሸቡም በላይ ዓይኖቹን አንዳች ነገር አድርቶባቸዋል፡፡ ፊቱ በአዳፋና ጎፍላላ ፂም ተሸፍኗል፡፡ ጫማ የናፈቃቸው እግሮቹም ቆሳስለዋል፡፡ ሁኔታውን ሳይ አነባሁ፡፡ ፌሊሲን ዲያብሎስ ልቡ ውስጥ እንዲገባ ፈቅዷል፤ ርኩሰትም ሕይወቱን እንደ ነቀርሳ ሆኖ አበላሽቶበታል፡፡ አሁን በሥቃይና በጸጸት እንዲኖር የተፈረደበት የተጠቂዎቹ ተጠቂ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ሰውዬ የተሰማኝ የመራራት ስሜት ጎዳኝ፡፡
‹‹የወላጆችሽን ቤት ዘርፏል፤ የማሳቸውን አላባ ጠቅሎ ወስዷል፣ ኢማኪዩሌ፡፡ የአባትሽን የእርሻ ማሽኖች እቤቱ አግኝተናቸዋል፣ አላገኘንም እንዴ?›› ሴማና ፌሊሲን ላይ ጮኸበት፡፡ ‹‹ሮዝንና ዳማሲንን ከገደለ በኋላ አንቺን መፈለጉን ቀጥሎ ነበር … ንብረትሽን ለመውሰድ ሲል አንቺ እንድትሞቺለት ፈልጎ ነበር፡፡ አልፈለግህም አንት አሳማ?›› ሴማና በድጋሚ አምባረቀበት፡፡
ድንገት ሳላስበው ሴማና ሲያየኝ ጊዜ ወደ ውስጥ በረጅሙ ተንፍሼ ወደ ኋላዬ ሸሸት አልኩ፡፡ ሴማና ባሳየሁት ምላሽ ተደናግጦና በፊቴ ላይ በሚወርደው እንባ ግራ ተጋብቶ አየኝ፡፡ ፌሊሲንን የሸሚዙን ኮሌታ ይዞ በጡጫ መታው፡፡ ‹‹ምን የምትላት አለህ? ምን የምትነግራት አለህ ለኢማኪዩሌ?››
ፌሊሲን አለቀሰ፡፡ ሐፍረቱ ተሰማኝ፡፡ ለአፍታ ቀና ብሎ ቢያየኝ ዓይኖቻችን ተገጣጠሙ፡፡ ተንጠራርቼ እጁን ነካሁና ልናገር የመጣሁበትን በፍጥነት ተናገርኩ፡፡
‹‹ምሬሃለሁ›› ስለው ልቤን ወዲያውኑ ቀለል አለኝ፡፡ ሴማና ወንጀለኛውን በሩን አሳልፎ ወደ ግቢው ከማስወጣቱ በፊት በፌሊሲን ትከሻ የነበረው ጭንቀት ሲቀል አየሁት፡፡ ከዚያም ሁለት ወታደሮች ፌሊሲንን አንጠልጥለው ወደ ማረፊያ ክፍሉ እየጎተቱ ወሰዱት፡፡ ሴማና ሲመለስ እንደተናደደብኝ አየሁ፡፡
‹‹ምን ማለትሽ ነው፣ ኢማኪዩሌ? ይህ እኮ ቤተሰብሽን የጨረሰው ሰውዬ ነው፡፡ ያመጣሁት እኮ በጥያቄ እንድታፋጥጪው … ከፈለግሽ እንድትተፊበት ነበር፡፡ ግን አንቺ ማርሽው! እንዴት እንደዚያ ታደርጊያለሽ? ለምን ማርሽው?›› እውነቱን ነገርኩት፡ ‹‹የምሰጠው ነገር ምኅረት ብቻ ነው መሆን ያለበት፡፡ ››


💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
አትሮኖስ pinned «#ሁቱትሲ ፡ ፡ #ምዕራፍ_አስራ_ሰባት ፡ ፡ #የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች ፡ #ትርጉም_በመዝምር_ግርማ ፡ ፡ #ሙታኑን_ስቀብር ፡ ፡ ‹‹ወላጆችሽ የት ነው የሚኖሩት?›› ይህ ጥያቄ በተመድ ሥራዬን ከጀመርኩ ከጥቂት ወራት በኋላ የቀረበልኝ፡፡ ‹‹ልቤ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር በሕይወት የሉም›› በማለት በትዕግሥት መለስኩ፡፡ ‹‹በዘር ፍጅቱ ተገድለዋል፡፡›› የተመድ ሰቆቃዬን…»
#እጠብቅሻለው

ዝምታሽ ሲበዛ
እንቢታ እንደሆነ ለኔ ቢጠባኝም
ማፍቀሬን ከልቤ
መሆኑን ባታምኚም
ብዙም አይደንቀኝም
ብቻ የኔ ልዕልት. . .
ላንቺ መፈጠሬን
ዘግይተሽ ስታውቂ
ማፍቀሬን ተረድተሽ
ኋላ ስትቆጪ
ሰማይ ቤትም ቢሆን
ልብሽ ከፈለገኝ
ተስፋዬ ነሽና መልሱን እንድትኘግሪኝ።