፩ ሃይማኖት
8.91K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና!! ሼር!
""ኢትዮጵያ"" የሚለው የመፅሐፍ ቅዱስ ስም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲወጣ ተደረገ።

@And_Haymanot

ኢትዮጵያ ሀገራችን ከሠሞኑ ሠፊ ምዕመናን(አማኞች) ያሉባት ሀገር ተብላ በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡ ከህገ ልቦና ጀምሮ ለአምላኳ ቦታ ያላት ቅድስት ሀገር ናት፡፡ እንደሚታወቀው በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ""ኢትዮጵያ"" የሚለው ስም ከ40 በላይ ቦታዎች ላይ ተጠቅሷል። ዛሬ ላይ ግን ይህንን ስም ለማጥፍት ዘምነናል፣ አድገናል የሚሉት አውሮፓዊያን (ሉተራዊያን) ቅድስት ሀገር
ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ ከፍተዋል እነሱም የጀርመን ሉተራን ቤተክርስቲያን ናቸው"" #ኢትዮጲያ"" የሚለውን ስም"" #ኩሽ""
እንጂ ኢትዮጵያ አይባልም ብለው ወስነዋል። ለመሆኑ መፅሐፍ ቅዱስን ማንም እንደፈለገው ተነስቶ የሚያስተካክለው መፅሐፍ ነው? እንደራሳቸው ህገ መንግስት ሲፈልጉ የሚፅፉት ሳይፈልጉ የሚፍቁት የህገ መንግስታቸው መፅሐፍ ነው?
@And_Haymanot
ማንም ቢሆን መፅሐፍ ቅዱስ ላይ መጨመርም ሆነ መቀነስም አይችልም
ይህንን መፅሐፍ ቅዱስ በጥብቅ! ያስጠነቅቀናል እንዲህ ሲል የዮሐንስ ራእይ - ምዕራፍ 22÷18 በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ
ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤ 19 ማንምም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል። መፅሀፍ ቅዱስ እንዲህ በጥብቅ እያስጠነቀቀ እና ማነው "ኢትዬጵያ" የሚለውን የመፅፍ ቅዱስ ቃል እንዲፍቁ ስልጣን የሰጣቸው? ለምሳሌ ከተፍቁት ውስጥ መዝሙረ ዳዊት
- ምዕራፍ 68÷31 ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። የሚለው "ኩሽ" በሚል እንዲቀየር ""ኢትዮጵያ""" የሚለው እንዲፍቅ አድርገውታል።ሌላው ትንቢተ ኤርምያስ
- ምዕራፍ 13÷23 በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን
ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? የሚለወን ይህንንም ሀይለ ቃል ፍቀው አውጥተውታል "ኢትዮጵያ" የሚለውን የመፅሐፍ ቅዱስ ስም። እና በግልፅ የኢትዮጵያን ስም ከመፅፍ ቅዱስ ውስጥ
እየተለቀመ እንዲጠፍ ሆነ ተብሎ ለማጥፍት የቴሰረ የነጮች የተለመደ የክፍት ውጤት ነው። በርግጥ መፅሀፍ ቅዱስን አሻሻልን እያሉ ሲጨምሩ እና ሲቀንሱ አሁን የመጀመሪያቸው አይደለም ከዚህ ቀደም ብዙ ምእራፎችን ለራሳቸው
እንደሚመቻቸው ሲደልዙ ኖረዋል። በዚህም ብዙ ህገ እግዚአብሔርን ፍቀዋል ከብዙ በጢቂቱ የሰዶምን ሀጢያት እርኩሰት ቤተክርስቲያን በሚሉት ቦታ ላይ ወንድን ከወንድ ሴትን
ከሴት ቆመው ሲያጋቡ አይተናል ሌላም ብዙ... በዚህ መጨመር መቀነስ ጠንቅም ሰዎች ትክክለኝ እና ሙሉ የመፅሐፍ ቅዱስን ትምህርት እና መልእክት እንዳያገኙ ሆነዋል! በዚህም
ሳቢያ ብዙዎች ባልተረዱት (የፈረንጅ እምነት) ውስጥ ገብተው ሲባክኑ አይተናል።
@And_Haymanot
እኛ ግን እድለኞች ነን የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መፅፍ ቅዱስን ሳይጨመረ ሳይቀነስ
እንደተረከብነው ከቅዱሳን ሀዋሪያት ለትውልድ አስተላልፍልናለች። ክብር ምስጋና ለአባቶቻችን እና ለቤተክርስቲያን ሊቃውንት ይሁን ብራና ፍቀው፣ፊደል ቀርፀው ላይ ታች ብለው.... ሳይነካካ ላቆዩልን። የነጮቹ የተንኮል አላማ ግን እንዲህ በቀላሉ የሚተው አይደለም የኛን ብራና መፃህፍት ስርቀው አውሮፓ አግዘው ተርጉመው ከመጠቀም ጅምሮ እስከ ዶክትሬት ድረስ ትምህርት የሚሰጡባቸው መፃህፍት ናቸው።
የኛን ታሪክ እና እሴት ለማጥፍት ግን ሌት ተቀን እየዳከሩ ነው! ሀገሩን እና ሀይማኖቱን የሚወድ ማንም ኢትዮጵያዊ ሊያወግዘው የሚገባ ድርጊት ነው። ያለንን ንፁህ መፅሐፍ ቅዱስም
ሳይጨመር ሳይቀነስ እኛ እንደተረከብነው ለትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ የሁላችንም ነው። ሼር በማድረግ ሁሉም አውቆ እንዲጠነቀቅ እንዳርግ!! አሁንም እንደቃሉ


ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የቀላል አማርኛው መዘዝ

@And_Haymanot

ተወዳጆች ትላንት ባቀረብንላችሁ መረጃ ሉተራውያኑ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለመፋቅና ኩሽ በሚል እየተኩ እንደሆነ አቅርበንላችኋል [ https://tttttt.me/And_Haymanot/394 ]

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀላል አማርኛ እንዲሁም ለመረዳት ቀላል በሚል ህያው ቃሉን እንደሚመቻቸው ሲቀይሩ አይተናል ለዛሬም ጥቂቶቹን ልናቀርብላችሁ ወደድን
@And_Haymanot

በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ >> ይላል ።
ይህ እንግዲህ ስለ ቅድስት ቤ/ክ ተሚናገር ስለሆነ አልተመቻቸውምና በቀላል አማርኛቸው ላይ
👉🏻 << ዝግዚአብሔር ሲገለጥ ስታዩት ስገዱለት >> ብለውታል ።

ሌላው ቀላል አማርኛ ተብሎ በውጣው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የእመቤታችንን ዘላለማዊ ድንግልና አንቀበልም ለሚለው ክሕደታቸው መግቢያ እንዲሆናቸው
<<ሊገልጣት አልወደደም >> የሚለውን
👉🏻👀 ሊያጋልጣት አልወደደም >> ብለውታል ። ማቴ 1÷19 ።
እንዲሁም ስለ እመቤታችን በመዝ 44÷16 ላይ እንዲህ ተብሉ ነው የተጻፈው፦
<< በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ ፤ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ፤ ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ>> ይላል ።
መዝሙረኛው አሁንም <<መሰረቶቻ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው ሲል ነው የተቀኝው ።

👉🏻👀የተቀደሱ ተራሮች የተባሉት እነ ኖኅ ፣ አብርሃም ፣ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ ••• በካላም ኢያቄምና ሐና ሲሆኑ ሁሉም ቅዱሳን ናቸው።

የእርሷ ቅድስና ግን ከሁሉም በላይ ነውና ቅድስተ ቅዱሳን ትባላለች። እናም
በአባቶችሽ ፍንታ ልጆች ተወለዱልሽ፤ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ>> ሲል የሃይማኖት አባቶቻን እነ አብርሃምን ፣ እነ ዳዊትን ፣ እነ ኢያቄምን መስለው እግዚአብሔርን ደስ የሚያስኙትን ከእርሷ በኋላ የሚመጡትን የሃይማኖት ልጆቻን ካህናት፣ ሊቃውንት ፣ጳጳሳት •••አድርጋ እንደምትሾማቸው ለማስረዳት ነው ቅዱስ ዳዊት ይህን ማለቱ ።
ይህንን የተስጣትን ሥልጣን እነርሱ ይሽሩት ይመስል መናፍቃኑ መሠረቶቻ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው>> የሚለውን ቃል << መስረቶቹ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው >> በማለት ቀይረውታል ።

በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ ፣ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ>> የሚለው ደግሞ👉🏻መናፍቃኑ በ1984 ዓ.ም ባሳተሙት ዳዊትና አዲሱ የ1993 መደበኛ ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በወንድ አንቀጽ አድርገው << በአባቶችህ ፋንታ ልጆች ተወለዱልህ ፤ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርጋህ ትሾማያቸዋለህ ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምህን ያሳስባሉ >> በማለት ነው የለወጠት ።

ይህ ግን ብቅዱስ ቃሉ ላይ ማመፅና ማሾፍ እንጂ ክርስቶስን ማክበር አይደለምና በቃሉ ለሚነግዱ ሁሉ ልብ ይስጥልን እኛንም በአንዲት ሀይማኖቷ በተዋህዶ ያጽናን፡፡
በዚህ ርዕስ ወደፊት በሠፊው እንመለስበታለን
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሰላም ተወዳጆች ብዙዎች ኦርቶዶክሳዊ ይዘት ያላቸው የሚመሥሉ ግሩፖች በተለይም ቻናሎች እየበዙ ነውና ጥንቃቄ እናድርግ፡፡ መልካም የመሠሉንንም ጽሑፎቻቸውን ለሌሎች በላክን ቁጥር የነሱን የምንፍቅና ገጽ እያሥተዋወቅን መሆኑን እንንቃ፡፡
የዛሬው መልዕክታችን ነው
Share
@And_Haymanot
ዛሬም እንላለን
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
❤️መልካም ዕለተ ሰንበት ❤️
@And_Haymanot
ፍትሐት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
@And_Haymanot
ተቃዋሚዎች ጸሎተ ፍትሐት ተገቢ አይደለም በማለት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰማሉ፡፡ ከመጽሀፍ ቅዱስ የማትወጣው ቅድስት ቤ/ክርስትያን እንደተለመደው መጽሀፍ ቅዱሳዊ ምላሽዋ እነሆ፡-
ፍትሐት ማለት ከኃጢአት እስራት መፍታት ወይም መፈታት ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ለሞቱ ሰዎች የሚደረገው ጸሎት ጸሎተ ፍትሐት ይባላል። የሙታን ነፍሳት ከሥጋ እንደተለዩ እስከ እለተ ምጽአት ድረስ በማረፊያ ቦታ ይቆያሉ እንጂ በቀጥታ
ወደ መንግስተ ሰማይ ወይም ወደ ገሃነመ እሳት እንደማይላኩ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውና የምታስተምረው ትምህርት ነው፤ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ የሚቆዩበትም ቦታ ለጻድቃን ገነት ሲሆን ለኃጢአተኞች ደግሞ ሲኦል ነው። የጻድቃን ማረፊያ
ቦታቸው ገነት መሆኑን ለማመልከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በነበረ ጊዜ ንስሐ ለገባው ወንበዴ፡ “በእውነት እልሃለው ዛሬውኑ
ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” ብሎታል። ሉቃስ ፳፫፡ ፵፫። የኃጢአተኞች መቆያ ደግሞ ሲኦል መሆኑን ለማመልከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሀብታሙ
ሰውና በድኻው አልዓዛር ምሳሌ ትምህርቱ ሀብታሙ
ሰው በሲኦል ውስጥ እንደነበረ ገልጿል። ሉቃስ ፲፮፡ ፳፫፡፡ በሙታን ትንሣኤ ጊዜ የምንነሳው በውርደት ወይም ክብር በሌለው ሁናቴ በመሬት ውስጥ
እንደተቀበርነው ሳይሆን፣ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው በክብር፣ በኃይልና በመንፈሳዊነት ነው። ፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፭፡ ፵፪-፵፬። ከዚያም በኋላ ወደ ክርስቶስ የፍርድ ፊት እንቀርባለን። ፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፡ ፲፤ ራዕይ ፮፡ ፱-፲፩፡፡
ይቅርታ በዚሁ ዓለምና በሚመጣውም ዓለም መኖሩን ቅዱስ መጽሐፍ ያስረዳል። ማቴዎስ ፲፪፡
፴፪፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶ ለነበረው ለኦኔሲፎር “በመጨረሻው ቀን ምሕረትን ይስጠው” ብሎ ጸልዮለታል። ፪ኛ ጢሞቴዎስ ፩፡፲፰። ቤተ ክርስቲያንም ይህንኑ ጸሎት ለሞቱ ሁሉ ትጸልያለች።

ለሞቱ ሰዎች መጸለይ ደግሞ በጥንት በዘመነ ብሉይም ነበረ። ጀግናው ይሁዳ መቃብዮስ በጦርነት ለሞቱ ወታደሮቹ የኃጢአት መሥዋዕት ይደረግላቸው ዘንድ ሁለት ሺህ የብር ድራህም
አሰባስቦ ወደ ኢየሩሳሌም ልኳል። ፪ኛ መቃብያን ፲፪፡ ፵፫፤ ዕዝራ ሱቱኤል ፮:፴፭። አይሁድ ለሙታን ሲጸልዩ ዳዊት ይደግማሉ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች በተላከው የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት
ላይ ባደረገው ስብከቱ እንዲህ ብሏል “አንድ ሰው ኃጢአተኛ እንደሆነ ቢሞት የምንችለውን ያኽል ልንረዳው ይገባል። የምንረዳውም በለቅሶና በሐዘን ሳይሆን በጸሎት፣ በምጽዋትና በቁርባን ነው።
የዓለምን ኃጢአት ወደ ተሸከመው የእግዚአብሔር በግ ስለሙታን የምንጸልየው እነርሱ መጽናናትንና እረፍትን እንዲያገኙ ብለን ነው እንጂ በከንቱ አይደለም። ጻድቁ ኢዮብ ስለልጆቹ ያቀርብ የነበረው ቁርባን ጠቀሜታ ከነበረው ስለ ሙታን የምናቀርበው ቁርባን ምንኛ የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረው? ጸሎተ ፍትሐት
የሚደረግላቸው እነ ማን ናቸው ??

ጸሎተ ፍትሐት የሚደረገው ሳይታወቁ ለተፈጸሙ ኃጢአቶች፣ በድብቅ ለተፈጸሙ ኃጢአቶች፣ እንዲሁም ለተረሱ ኃጢአቶችና ኃጢአት ሰሪው ኃጢአት መስራቱ ሳይሰማው የሚሰራቸው
ኃጢአቶች ናቸው። እንደነዚህ ያሉት ኃጢአቶች ከሰው ተፈጥሮ ደካማነት የተነሳ የሚፈጸሙ መሆናቸው ቢታመንበትም በእግዚአብሔር ፍትሕ
በኩል ግን እንዲህ አይደለም። እግዚአብሔር ለሙሴ የነገረው “አንድ ሰው ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ አንዱን ቢተላለፍ በደለኛ ነው” ብሎ ነው፡፡ ዘሌዋ ፭፡ ፲፯። ሰው አፈር የሆነውን ሥጋ የለበሰ እንደመሆኑ መቼም
ቢሆን ሙሉ ለሙሉ ከኃጢአት የነፃ ሊሆን አይችልም። “ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናታልላለን፣ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም” እንዲሉ። ፩ኛዮሐንስ ፩፡ ፰። እግዚአብሔር በንስሐ
የሚመለሰውን ሰው በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ይቀበለዋል። ለምሳሌ በሞት አፋፍ ላይ የነበረውና ከጌታችን ጋር ተሰቅሎ የነበረው ወንበዴ ንስሐው ተቀባይነት ያገኘው በመጨረሻው ደቂቃ ነው።
ስለዚህ ንስሐ የገባ ሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው ማን እንደሆነ ስለማናውቅ ለሁሉም እንጸልያለን። ለሙታን የሚደረግ ጸሎት ወይም ጸሎተ ፍትሐት ዘወትር ጠቃሚ ነው። ወደ ገነት ለመግባት ላልታደሉት ጸሎቱ ዕድላቸውን ከመቃብር በላይ ያደርግላቸዋል። በሰማይ ስማ ሰምተህም ይቅር በል። ፪ኛ ዜና ፮፡ ፳፩። በገነት ላሉትም እንደ ታላቅ ብርሃን እየፈነጠቀ ታላቅ ደስታን ይሰጣቸዋል። በዚህም መሠረት ቤተ ክርስቲያን
በፍትሐት ጸሎት አምና ለልጆቿ ምህረትን ትለምናለች፣ ይህንኑም ታስተምራለች።
ለሙታን የሚደረግ ጸሎት አስፈላጊነት ? ከሞትም በኋላ ቢሆን በሰዎች መካከል የሚኖረው መንፈሳዊ ግኑኝነት በጸሎት አማካይነት ይቀጥላል። ሉቃ ፲፮፡ ፲፱-፴፩። በእምነት የሚደረግ ጸሎት ኃይል
እንዳለው ተራራንም ለማንቀሳቀስ እንደሚያስችል በወንጌል ተገልጾልናል። መጽሐፍ ቅዱስም የአንዱ ሰው ጸሎት ሌላውን እንደሚራዳ ያስተምረናል።
ዮሐ ፬፡ ፵፮-፶፫፤ ማቴ ፲፭፡ ፳፩-፵፰፤ ማር ፱፡ ፲፯- ፳፯፤ ማር ፪፡ ፪-፲፪፤ ማቴ ፰፡ ፭-፲፫፤ ዮሐ ፲፩፡ ፩። ጌታችን ከላይ ከተጠቀሱት ተአምራት በርካታዎቹን
በአካል በቦታው ተገኝቶ ሳይሆን ሳይገኝ በኃይሉ ፈጽሟል። ጸሎት እንደ ብርሃን ነጸብራቅ የሚጓዝና የሚያበራ የፍቅር ውጤት ነው። እግዚአብሔርን
አምነው የሚጸልዩትን ከምድር ጫፍ እስከ ምድር ጫፍም ይሁን የእርሱ አገር እስከ ሆነውም አልፎ ያገናኛል። ጸሎት እኛ የምንኖርባትን ዓለም ከመላእክት፤ ከቅዱሳንና በሞት የተለዩን ወገኖቻችን
ከሚገኙባት ዓለም ጋር ያገናኛል። ሞት በጌታችን ትንሳኤ የተነሳም የቀደመ ኃይሉን አጥቷል። ትንሳኤውም የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ ሆኗል። ሮሜ ፰፡ ፴፰-፴፱። በዚህም የተነሳ እግዚአብሔርን ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም እያልን ሁሉ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እንጸልያለን። ሉቃስ ፳፡ ፴፰።
በዚህ ዓለም የነበሩ ክርስቲያኖች በሕይወት በነበሩበት ዘመን ከቤተ ክርስቲያናቸው ጋር የነበረው ግንኙነት ከአረፉም በኋላ አይቋረጥም። በገነት ከሆኑ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ስለ እኛ ሊጸልዩልን ነጻነት አላቸው። ወደ ሲኦል የወረዱም ከሆኑ በዚያ ሆነው የእኛን ጸሎት ይሻሉ። ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን መሠረቶቿ በምድር ሆነው ጫፎቿ ከሰማይ ጋር የተያያዙ አድርጎ መመሰሉም ይህንኑ ለማስረዳት ጭምር ነው። ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላዕክት፥ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥
ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።; ዕብ ፲፪፡ ፳፪-፳፬። ይህም የሚያመለክተው በሰማይና በምድር ባሉት አብያተ ክርስቲያናት መካከል የማይጠፋ የጠበቀ ግኑኝነት ያለ መሆኑን ነው።
በምንጸልየውም ጸሎት የዘመናት ገደብ ሳይኖርብን የሐዋርያት፤ የሰማእታትና የቅዱሳን ሁሉ ጸሎትም እንዲረዳን
እንጸልያለን።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞_✞_✞
፩ ሃይማኖት
Voice message
👆👆👆👆
የተሃድሶ መናፍቃን ለሚያነሱት ጥያቄ የተሠጠ ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ
በ ፩ ሃይማኖት
ተአምሯን የሰማ ስጋወደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል ...
Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot
በፆም ሰአታችሁ ጊዜም ይሁን አይሁን ሶስት ነገሮችን በህሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችሃለሁ፡፡
@And_Haymanot
እነርሱም፦

👉 ክፉ ከመናገር መከልከልን
👉 ማንንም ሰው እንደ ጠላት ከማየት መቆጠብንና
👉 እንደ ልምድ አድርጋችሁ ከያዛችሁት መሃላ ትርቁ ዘንድ እመክራችሃለሁ።
ፆም የጤንነት እናት፣የፍቅር እህት፣የትህትና ወዳጅ ናት።
ህመሞች አብዛኛውን ጊዜ ያለቅጥ ከመመገብ የሚመነጩ ናቸው።

*(ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ)*
Join
@And_Hayamnot
@And_Haymanot
" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 9:6)
@And_Haymanot
መልካም በአል
ማዕተብ
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴:
@And_Haymanot

ማዕተብ በቤተክርስቲያን ምን ማለት ነው????
ማዕተብ የክርስቲያን ሁሉ ዓርማ

“ማህተብህን በአንገትህ እሰረው ስትሔድ ይመራሃል ስትተኛ ይጠብቅሃል ” ምሳ 6÷21

ማተብ (አተበ፤ አመለከተ ፤ባረከ)

ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ይህም ማለት መታወቂያ ፤ ምልክት ማለት ነው፡፡ይህም ያመኑትንና የተጠመቁትን ካላመኑትና ካልተጠመቁት የሚለይበት የክርስቲያን መታወቂያ ነው፡፡

የዚህ ምልክት መሠረቱና ምሳሌውም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተቀበለው ጸዋትወ መከራ አንዱ በገመድ ታሥሮ መጎተቱ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡

ዮሐ19፤12 ቅዱስ ዳዊትም በመዝ59፤4 ላይ ”ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከከመያምሥጡእምገጸቅስት ፤ ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩ ምልክትን ሰጠሃቸው” ይላል፡፡

አጋንንት የክፋትን ቀስት በዚህ ዓለም በመወርወር የሰውን ልብ ስለሚወጉ ከዚህ ለመዳን ማዕተብን ማድረግ ታላቅ መንፈሳዊ እውቀት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲያስረዱ ሥላሴ ማዕተበ ብርሃን ኃይል ሃይማኖቶሙ ለክርስቲያን፤ሥላሴ ለክርስቲያን ሁሉ የሃይማኖታቸው ጉልበት መታወቂያ የብርሃን ማዕተብ (ምልክት) ናቸው ብለዋል፡፡

ማዕተብ ያላሠረ ኦርቶዶክሳዊ በውግዘት ከቤተክርስቲያኒቱ እንደ መናፍቅ ተቆጥሮ ባይለይም ማዕተብ አለማሠሩ ግን የአባቶቹ ትውፊት እንዳልተቀበለ ያስቆጥረዋል፡፡

በምሳሌያዊ አነጋገርም ሃይማኖት አልባውን ማለትም ክርስቲያን ያልሆነውን ማዕተብ የለሽ ያልተጠመቀ አረምንይሉታል ክርስቲያን በማተቡ መነኩሴ በቆቡ እንዲታወቅ ማዕተብ አልባ መሆን። ደግሞ ክርስቲያን
ይሁን ያልተጠመቀ መሆኑ ለማወቅ ያስቸግራል፡፡

በመለዮዋቸው ሌሎች እንዲታወቁ ክርስቲያን በማዕተቡ ክርስትናውን ሲያሳውቅኖሯል፡፡ በተለመደው አነጋገር እገሌ ማዕተብ አለው ባለማዕተብ ነው ሲባል እገሌ ታማኝ ክርስቲያን ነው።

እውነተኛ :ሐቀኛ ነው የሚል ትርጉምን ይሰጣል “ባለማዕተቢቱ” ሲባል ከአሚን ባሏ የረጋች ከባሏ
ሌላ የማታውቅ እውነተኛ ታማኝ ክርስቲያን የማል ፍች አለው፡፡በዚህ ምክንያት በክርስቲያኑ ኅብረተሰብ የማዕተብ ትርጉም ከፍተኛ ቁም ነገርን አዝሎ ይገኛል፡፡ አንዲት ሀገር ነፃ መሆኗ የሚታወቀው ወይም ራሷን የቻለች የራሷ መንግሥት ያላት ከባዕድ ቀንበር ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣች መሆኗ የሚታ ወቀው በባንዲራዋ ምልክትነት እንደሆነ እንደዚሁም አንድ ክርስቲያን በክርስቶስ አምኖ በጥምቀት ከዲያብሎስ ቁራኝነት ነፃ መውጣቱ ነፃነት ያለው አማኝ መሆኑ የሚታወቀው በማዕተቡ ምልክት ነው፡፡

ለደብዳቤ ለጽሑፍ ዓርማ ማኅተም ፊርማ እንደሚያስፈልገው ያም ለመተማመኛ እንደሚያገለግል ጥቅሙ ታውቆ ይሠራበታል፡፡
የክርስቲያን ማዕተብም በዚሁ አንፃር ብዙ ኃይማኖታዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

መጀመሪያ በልቡ የሚያምነው ሃይማኖት ክርስትናን ሳያፍርበት በአንገቱ ባለው ማተብ መግለጹ በክርስትናው አለማፈሩን ክርስትናህን ካድ ማተብህን በጥስ የሚል ዓላዊ ቢመጣና ያንን ምልክት ዓይቶ
ቢሰዋው የሰማዕትነትን ክብር ያገኝበታል፡፡ ያም ባይሆን በማተቡ ምልክትነት በመናፍቃንና በኢአማንያን የሚቀበለው ዘለፋ ስለ ክርስቶስ መስቀል እንደተሸከመ ያስቆጥረዋል፡፡

ሁለተኛው ከክርስቲያን ወገኖች ጋር
ያለጥርጥርማለትምየክርስቲያንመሆኑታውቆለት በቀላሉ ክርስቲያናዊ ተሳትፎውን ማከናወን ይችላል፡፡ ማተብ ከሌለው ግን ክርስቲያን ይሁን ያልተጠመቀ ስለማይታወቅ በሃይማኖት ዜጎች ዘንድ በቀላሉ ተቀባይነት ማግኘት አይችልምሦስተኛ ከማይታወቅበት ሀገር በአደጋም ይሁን በበሽታ እንደወጣ ሞት ቢደርስበት በማዕተቡ መታወቂያነት የክርስቲያን ሥርዓት ተፈጽሞለት አስክሬኑ ተፈርቶ በቤተክርስቲን ሊቀበር ይችላል፡፡

ማተብ ከሌለው ምስከር በአካባቢው ለክርስቲያንነቱ ማረጋገጫ የሰው ያውም በሰበካው ቤተክርስቲያን የሚታመን ክርስቲያን ከሌለ እንደአልተጠመቀ ተቆጥሮ እንደ አሕዛብ ሥጋው ዱር ከበረሃ ወድቆ ይቀራል፡፡

ዐራተኛ ማተብና መስቀል ያለው ክርስቲያን በውሃ ዋና ወይም በበረሃ ጎዳና በውሃ የሚኖሩ ወይም በበረሃ ያሉ አጋንንት በቀላሉ ሊለክፉት አይችሉም፡፡ ይህምበየጠበሉ ሥፍራ በተአምራት ተረጋግጧል፡፡ አጋንንት የለከፋቸው ሰዎች ማተብና መስቀል አይወዱም፡፡ የሠፈረባቸው ርኩስ መንፈስ ማተብ እንዲበጥሱ መስቀል እንዲጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡

ማተብ በሰይጣን ዘንድ ከተጠላ በአጋንንት ላለመለከፍ የማተቡ መኖር ይጠቅማል ማለት ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች የማዕተብ ሥርዓትን ለመቃወምና ዘመናውያን መስለው ለመታየት “ሃይማኖት በልብ ነው” ይላሉ ተሳስተዋል፡፡ ሃይማኖት የልብ ብቻ አይደለም የጠቅላላው ሕዋሳት ሁሉ ናት እግዚአብሔርን ስንወደውና ስናመልከው በልባችን ብቻ ሳይሆን በአፋችንም በአንገታችንም በጠቅላላው ሰብአዊ ተፈጥሮአችን ሁሉ መሆን ይገባዋል፡፡

ምክንያቱም እግዚአብሔር የጠቅላላው ሰውነታችን አምላክና ፈጣሪ ስለሆነ ነው፡፡ “ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝvሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው
በአባቴ ፊት እክደዋለሁ፡፡ “ማቴ ፲፤፴፪-፴፫በዚህ ቃል
መሠረት በኢአማንያን ዘንድ ክርስቲያን መሆናችንን
የምንገልፀው በልባችን ብቻ ሳይሆን በቃላችንና በሥራችንም ጭምር ነው፡፡

በአንገታችንስ እንዳንመሰክርለት ማን ያግደናል? በአንገታችን ባለው ማዕተብም ለእግዚአብሔር
እንመሰክራለን የስሙን ምልክት በአንገታችን እናኖራለን አናፍርበትም ፡፡ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በጥምቀታችን እንደምንመሰክር የጥምቀታችንንም አርማ በማተባችን እናረጋግጣለን፡፡ (ሮሜ ፲፤፮-፲፫፡፡ ኢዮኤል ፪፤፴፪፡፡ ሮሜ ፮÷፩-፭ ፣ ማቴ ፭÷፲፩-፲፪፡፡ ፩ጴጥ ፫÷፳፩-፳፪ ፩ጴጥ ፬÷፲፪-፲፮)ተመልከት፡፡

የማዕተብ ጥቅም

1. የክርስትናን ማዕተብ በአንገት ማሰር በልብ ያለውን እምነት ሳያፍሩ በኃጢአተኛው ትውልድ መካከል ስለ ክርስቶስ መመስከር እንዲሁም ለሰይፍ ለመከራ መዘጋጀትን ማመልከት ነው፡፡

2. ክርስቲያን ከሆኑ ምእመናን ጋር ሃይማኖታዊ የሆነውን ተሳትፎ በቀላሉ ለማከናወንና በክርስቲያን ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘ

3. በጉዞ ላይ ያልታሰበ አደጋ ቢያጋጥምና ሞት ቢደርስ አደጋው ደርሶበት ያረፈው ክርስቲያን ቤተሰቦቹ ባይገኙ በቅርበት በማዕተቡ ክርስትናው ተረጋግጦ ጸሎተ ፍትሐት ተደርጎለት በእምነቱ ተከብሮ አስከሬኑ በክርስቲያኖች መካነ መቃበር ያርፋል፡፡

ወስበሐት ለእግዚአብሔር!
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
Photo
" ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፥ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ"ሉቃ 3:11 ለድሃ የሚሠጥ ለእግዚአብሔር የሚያበድር ነው፡፡ የተራበን ማብላት የጽድቅ አንዱ መንገድ ነውና የሚሠጥ በልግስና ይስጥ ዋጋው አይጠፋበትምና፡፡
Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ

@And_Haymanot

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ እንመለከታለን፡፡

ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ. 6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30)
@And_Haymanot
ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡

ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)

አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ "የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ አይሹትም ፣ አይደረግምም" የሚለውን በመጥቀስ የሐዲስ ኪዳነ ታቦትን ይቃወማሉ። ቃሉ የተነገረው ለእስራኤል ቤት ሲሆን እስራኤላውያን በእርግጥም የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው አይሹትም። በኦሪት ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃልኪዳን በአዲስ ኪዳን ተተክቷል። ይህ ከሐዲስ ኪዳን መሠዊያ ጋር የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ "አዎ እስራኤል አይሹትም" ብለን እንመልሳለን።
የአሁኑ ታቦት የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት ከቀድሞው አንድ ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው::

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109)

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያ
ከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡

የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡
@And_Haymanot
የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት ‹‹አንዱ ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡
ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡

ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት ደግሞ እኚሁ ጸሐፊና በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡ ‹‹In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice-Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints.

It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡
@And_Haymanot
‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) http://www.stmarkdc.org/coptic-sanctuary ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡

ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡
@And_Haymanot
አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም!
@And_Haymanot
....ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 10 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
*ዐቢይ_ጾም*

@And_Haymanot

ዐብይ ጾም ማለት ምን ማለት ነው?

ዐብይ ጾም ለምን ዐቢይ ተባለ?
ጾም ማለት ፡- ለዘላዓለም ሁሉንም ሕዋሳት ከኃጢአት መከልከል፣ለተሰነ
ጊዜ እህል ከመብላት ዉሃ ከመጠጣት መታቀብ ወይም ለተወሰኑ ወራት
ከጥሉላት ከስጋ ፣ከወተት፣ከቅቤ፣ከእንቁላል፣በአጠቃላይ ከእንሰሳት
ዉጤት መከልከል ነው።
+
#የጾም_ጥቅም ፦ የሥጋ ምኞትን የምታጠፋ የነፍስን ቁስል የምታደርቅ
ለጎልማሶችም ጸጥታንና እርጋታን የምታስተምር ከእንሰሳዊ ግብር ጠባይ
የምትከለክልና ሰው መላእክትን መስሎ የሚኖርባት ደገኛ ሥርዓት ነች፡፡

በብሉይ ኪዳን ብዙ ሰዎች በጾም ተጠቅመዋል እግዚአብሔር የጾምን
ሥርዐት የደነገገው ገና ከጥዋቱ አዳምን በፈጠረበት ወቅት ነው ፡፡ እጸ
በለስን አትብላ ማለት ትዕዛዝ ቢሆንም ትዕዛዙ ግን የጾም ትዕዛዝ ነው
አዳምና ሔዋን ይህን የጾም ሥርዐት በመሻር እጸ በለስን በልተው
በመገኘታቸው ምን እንደደረሰባቸው በቅዱስ መጽሐፍ ላይ የምና ነበው
ነው፡፡
በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳን አበው ጾምን የጸሎት እናት የእንባ ምንጭ
የጽድቅ መሠረት ደገኛ ሥርዐት በማለት ይገልጻሉ፡፡
ጾም በብሉይ ኪዳን ስንመለከት፦
በሕዝብ ላይ የተቃጣውን መከራ ለማቅለል ተጠቅመውበታል መጽ ኢያሱ
7÷6 -9፣ መጽ አስቴር 4÷16 ፣ትንቢተ ዮናስ 1 ፣ መ.ሳሙኤል ካል
12÷17 ዘዳ 9÷9 -18፣ትንቢተ ኢዩኤል 2÷14 ፣መዝ 34(35) ÷ 13
ትን.ዳን 10÷2 መዝ 108÷ 24
ጾም በሐዲስ ኪዳን
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሥራው ሁሉ መጀመሪያ ያደረገው ጾምን
ስለሆነ መሥራቹ ክርስቶስ ነው በሐዲስ ኪዳን ጾም የታዘዘ ስለመሆኑ
የሚከተሉትን ጥቅሶች እንመለከታለን
ማር 2 ÷20 ፣ማር 9÷29 ፣ማቴ 6÷16 ፣ ሉቃ 6÷21 ፣ሐዋ 13÷3
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለጾም ሥርዐትና ደንብ
አውጥታለች በዓመት ውስጥ ሰባት የዓዋጅ አጽዋማት እንዳሉና
ማንኛውም ክርስቲያን እንኝህን አጽዋማት እንዲጾም ታዛለች እነዚህም
አጽዋማት
 ዐቢይ ጾም
 ጾመ ሐዋርያት
 ጾመ ስብከት (ጾመ ነብያት)
 ጸመ ፍልሰታ
 ጾመ ድኅነት
 ጾም ነነዌ
 ጾመ ገሃድ
ከነዚህ አጽዋማት ውስጥ የምንመለከተው ዐቢይ ጾም ነው።
ዐቢይ ጾም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሥርዓት መሰረት የአዋጅ
ፆም የሚባሉ ሰባት አፅዋማት አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም በጊዜው ረዥም
ደግሞም በስያሜው የተለየውን አብይ ጾምን እንመለከታለን፡፡
@And_Haymanot
1. ዐብይ ጾም ማለት ምን ማለት ነው
በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹አበየ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ
የተገኘ ነው፡፡
ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡
2. ዐብይ ጾም ለምን ዐቢይ ተባለ
ዐብይ ጾም ዐብይ የተባለበት ሦስት አበይት ምክንያቶች እንመለከታለን
2.1. ጌታቸን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የጾመው ሥለሆነ ማቴ
4፡2-3
2.2. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት ስለ ሚበልጥ የቀኑ ብዛትም 55
ቀን ነው፡፡
2.3. ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሶስቱ ርዕሰ ኃጢአት
የሚባሉት ትዕቢት፣ስስት ፍቅረ ነዋይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል
የተመቱበት ስለሆነ ይህ ጾም አብይ (ታላቅ) ተብሏል፡፡ ማቴ 4፡3-11
የዐብይ ጾም የተለያየ ስያሜዎች
ዐብይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ ጾሙ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡
+
°#ጾመ ሁዳዴ፡- #ሁዳድ ማለት ሠፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡ ይህም ጾም ደግሞ በቀኑ ብዛት ትልቅ (ሠፊ) በመሆኑ የሁዳዴ ጾም ይባላል፡፡
°#የካሳ_ጾም፡- እንዲህ የተባለበት ምክንያቱ ደግሞ አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሳ ጾም ተብሎሏል
°#የድል_ጾም ፡-ይህም ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡
°#ጾም_አስተምህሮ፡- ይህ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለበት ምክንያት ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የተለያዪ ስያሜዎች አሉት ‹‹የመሸጋገሪያ ጾም፣ ‹‹የስራ መጀመሪያ ጾም ››
+++ @And_Haymanot
#የዐብይ_ጾም_ሳምንታት
ዐብይ ጾም በያዘው በ55 ቀኑ ውስጥ 7 ቅዳሜና 8 እሁዶቸን ይዟል የእነዚህ የስምንቱ እሁዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡
1፣ ዘወረደ
2፣ ቅድስት
3፣ ምኩራብ
5፣ ደብረዘይት
6፣ ገብረ ሔር
7፣ ኒቆዲሞስ
4፣ መጻጉዕ
8፣ ሆሳዕና
+++

ቀደምት ሊቃውንት ሁለት ዓይን የተሰጠን በአንዱ የራሳችን በሌላው
የሌላውን ለማየት ነው፡፡ ሁለት ጆሮ የተሰጠን በአንዱ የራሳችንን
በሌላው የሌላውን ለመስማት ነው፡፡ ሁለት እጅ የተሰጠን በአንዱ
ለመስጠት በሌላው ለመቀበል ነው፡፡ ሁለት እግር የተሰጠን በአንዱ
ወደራሳችን በሌላው ወደ ሌላው ለመሄድ ነው ይሉ ነበር፡፡
፳፩ ፳፩ ፳፩ ፳፩ ፳፩
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም
ቤተክርስቲያን አትታደስም!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም
እንማልዳለን!
(መጽሐፈ ሚስጢር)
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን
መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣
የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ
ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!

†† † † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት
እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም
ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
†† † † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የዝሙት ቀን በኢትዮጵያ !!!
*★★★*

~ ይኽን ሰይጣናዊ በአል የምትጠየፉ ጦማሩን #SHARE ያድርጉት ። የተሰማዎትንም በ #COMMENT መስጫ ሳጥኑ ላይ ሃሳብዎን ያኑሩ ። እስቲ በጉዳዩ ላይ እንወያይ ።

አበቃሁ ። 0911608054 የእጅ ስልኬ ነው ።

ሻሎም.! ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
የካቲት 6/6/2008 ዓም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ~ ብዬ የምጽፍበት ቀን ይመጣል ።

#ETHIOPIA | ~ አዲስ አበባ ~ [ ይኽን ጦማር የዛሬ ፪ ዓመት የካቲት 6/6/2008 ዓም አዱገነት እያለሁ የጻፍኩት ነው ። ይኽ ጽሑፍ በወቅቱ በሸገር ራዲዮ ሲነበብ አስታውሳለሁ ፣ መጽሔቶችም ሲጠቀሙበት ነበር ። ከዚህ ጦማር በኋላ ነው ebs ላይ ይቀርብ የነበረው የበግ ተራ ፕሮግራም የቀረው ።

~ ወቅቱ የጦም ወቅት ነው ። ዛሬ ዕለቱም ረቡዕ ነው ። ይኽ በታላቁ ፍቅር ስም የሚከበረው የዝሙት ቀን እንዲከበር የሚደረገው በዚህ በሱባኤ ወቅት ነው ። እናም ተልዕኮው የ666 የአውሬው ተልዕኮ ነው ። ልንጠየፈው ይገባል ። ጓደኞቼ መልካም ንባብ ።

ይህ ጽሑፍ ቀኑን በፍጹም ቅድስና ህይወት ውስጥ ሆነው የሚያሳልፉትን ፍቀረኛማቾችን አይመለከትም ። አይመለከትም ።

በዕለቱ ክቡር በሆነው " ፍቅር " ስም በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው የተባለላቸውና ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ መልእክቱ 5፣19 ጀምሮ የተናገረላቸው እነ ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ያሉ የሚያደርጉና የእግዚአብሔርን መንግሥት የማያስወርሱ ነውሮች ይፈጸማሉ ።

ለዚህ የጥፋት ቀን በእግሩ መቆም ተጠያቂዎቹ ሁላችንም ነን ።

" የፍቅር " ወይም " የፍቅረኞች " ቀን የተባለ መሰሪና ባንዳ የሆነ መርዘኛ በአል አጀማመሩ በውጪው ዓለም ቆየት ያለ ዘመን እንዳለው ይነገራል ። ይህ በአል በግልጽ ሰይጣናዊ የሆነ የዝሙት ሥራዎች በይፋ የሚተገበሩበትም አሳፋሪና መጤ በአል ነው ። በሃገራችን ደግሞ ካላከበርነው ሞተን እንገኛለን ማለት ከጀመርን ጥቂት ዓመታትን አስቆጥረናል ።

በአሉ ላይ ላዩን ሲያዩትና ሲሰሙት መልካም የሆነ ቢመስልም ፤ ከመልካም ነገሩ ይልቅ ጎጂ ነገሩ እያፈጠጠ መታየት ጀምሯል ።

መቸም የራሳችን የደለቡ፣መላውን ዓለምም የሚያስደምሙና የሚያስደንቁ ታሪኮች ባለቤቶች መሆናችንን ዘንግተን የምዕራቡን ዓለም ግሳንግስ ባህሎችን ሳንመርጥ ማስገባት ከጀመርንም ሰነበትበት ብለናል።

ተው ይኽ ነገር አይጠቅምም ብሎ የሚናገርና የሚያስተምር ሽማግሌ ፣ ለህዝቤ ይህ አይጠቅምም የሚልና ትውልድን ያጠፋል ብሎ ክፉና ጎጂ መጤ ባህሎች እንዳይስፋፉ የሚተጋ መንግሥት ፣ በስነ–ምግባር ታንጸው ማንነታቸውን ለባዕድ ባህል ተገዢ እንዳይሆኑ የሚያስተምሩ የሃይማኖት መምህራን ፣ የሚጠቅመንና የሚበጀንን መልካም ነገሮችን የሚያሰሙን ፣ የሚያሳዩን እና የሚያስነብቡን የሚድያ ተቋማት ስለሌሉን በግላጭ ለባህል ወረራ ተጋልጠናል ።

ስሙን የቀየርነውና እኛ " የፍቅረኞች ቀን " ብለን አታሞ የምንነርትለት ቀን አሁን አሁን በግልጽ በአደባባይ የሚታወቅ "የወሲብ ቀን " ወይም " የዝሙት ቀን " ወደ መሆን ተሸጋግሯል ።

እኔ በበኩሌ ለዚህ ክፉ የባህል ወረራ ተጣያቂ የማደርጋቸው አካላትን ተራ በተራ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ ።

፩ኛ ፦ መንግሥት ፦ መንግሥት የአንድ ሃገር ህዝብ አባትና አስተዳዳሪ አካል ነው ። የሚያስተዳድረውን ህዝብ የሚጎዱ ማናቸውንም አይነት ጠላቶች የመመከትና ህዝቡን ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነትም አለበት ። በድንበር የሚገቡ ጠላቶችን ፣ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ፣ ወዘተ በወታደር ኃይል ቀን ከሌሊት ለአፍታ እንኳን ሳይተኛ ይጠብቃል ። ምን አገባኝ ካለ እሱም እኛም አለቀልን ማለት ነው ።

እንግዲህ በወታደር የማይጠበቁ በተለያዩ ዘዴዎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ጠላቶችን ደግሞ በተለያየ መልኩ ወደ ማኅበረሰቡ እንዳይደርሱና የቆየና ጠንካራ የሆነ ማንነቱን እንዳይሸረሽሩበት በተለያዩ ዘዴዎች ለመከላከል ይሞክራል ። ምክንያቱም ህዝብን ከህዝብ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ ፣ ስርዓት አልበኝነት እንዲነግሥ የሚያደርጉ ከሆነ አደጋው የከፋ ይሆናልና ። አሁን ግን መንግስት ፖለቲካውን ከሚያበላሽበት ነገር ውጪ ያሉትን ህዝብን ገዳይ የሆኑ ነገሮችን ዝም ብሎ በማየት ሆደ ሰፊነቱን ለማሳየት ይሞክራል ። በዚህም በታሪክና በእግዚአብሔር ከመጠየቅ አይድንም ።

የፓኪስታን መንግስት በይፋ ይህ ቀን በሀገሯ እንዳይከበር ማገዷን የዓለም የዜና አውታሮች መግለጻቸውም እየተነገረ ነው ። ለምን ሲባሉ ለህዝባችን የሚያመጣው ጥቅም ስላልታየን በማለት በአጭር ቃል ዘግተውታል ።

ሚዲያው ፦ በየትኛውም ሀገር ያሉ ሚዲያዎች ፈቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱት ከመንግስት ነው ። እያንዳንዱን የሚያዘጋጁትን ፕሮግራም መንግስት ያውቀዋል ። እናም አሁን በኢትዮጵያ የሚገኙ ሚዲያዎች በተለይ በሬዲዮና የቴሌቪዥኑ ዘርፍ እየሰሩ ያሉትን የጥፋት መንገድ ላየ ሰው ወደፊት በዚሁ ከቀጠለ ኡኡ የሚያስብል ነገር እንደሚገጥመን ይጠበቃል ።

ለምሳሌ በEBS ቴሌቭዥን የሚቀርብ አንድ ፕሮግራም አለ ። የፍቅር ምርጫዬ የሚል ኮተታም ፕሮግራም ። በአንደኛው ሳምንት አንድ ወንድ ሦስት ሴቶችን ደርድሮ የሚመርጥበት ፣ በአንደኛው ሳምንት ደግሞ አንዲት ሴት ሦስት ወንድ አስቀምጣ የምትመርጥበት የበግ ተራ የሆነ ፕሮግራም አለ ። ጸያፍና ያልታረሙ ስድ የሆኑ ቃላት የሚደመጥበት ። እንደበግ ከተመራረጡ በኋላም በቀጥታ አልጋ ተይዞላቸው ወይን እና ቢራ ተበርክቶላቸው እንደጀብዱ ዘማዊነታቸው የሚነገርለት ፕሮግራም አለ ። የሰው ልጅን ክብር የሚነካ ፣ በሳምንቱ ሲጠየቁ እንዴት አገኘሃት ሲባል ሆዳም ናት ፣ ወሬኛ ናት የሚልበት እሷም አይኑ አያርፍም ወዘተ ብለው ለሌላ ጊዜ ሌላ እድል እንሞክራለን የሚሉበት የቴሌቭዥን ቡናቤት የሆነ ፕሮግራም አለ ። ይህ ሲሆን መንግስት በደንብ ያያል ። ግን ሆደ ሠፊ ነው ።

ዛሬ የተነሳሁበትን የወሲብ ቀንንም በተመለከተ ከአንድ ወር በፊት ሀገሪቷ ውስጥ የሚነገር ነገር የጠፋ እስኪመስል በተለይ በኤፍ ኤም ራዲዮኖቻችን በኩል የተለየ ቅስቀሳ ሲደረግ ሰንብቷል ። ቅስቀሳው በግልጽ ነው ። ሆቴሎቹ አልጋ አንጥፈው ሽቶ አርከፍክፈው ዝሙቱን እና ድሪያውን በባንድ ሙዚቃና በታዋቂ ዘፋኞች አጅበው እንደሚጥብቋቸው ሲለፍፉ ያልሰማ የለም ። ይህን የሰሙ ጨቅላ ህፃናት ሳይቀሩ ወደ ዝሙት ካምፑ የጎርፋሉ ። በዚያም የሚሆነው ሁሉ ይሆናል ። ይህ ሁሉ ሲሆን በቤተ መንግስትም ፣ በቤተክህነትም ፣ በቤተ መስጊድም ያሉ መሪዎች በደንብ ይሰማሉ ፣ ያያሉም ። ነገር ግን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዚህ ጉዳይ አንዳችም ነገር አይናገሩም ሆደ ሰፊም ናቸው ።

የሚገርመው ከፊታችን የሚመጡት የየካቲት 12 የኢትዮጵያውያን ሰማዕታት በዓልና ነጻ የወጣንበትን ታላቁን የአድዋ በአል እነ ያሬድ ሹመቴ በእግራቸው ከአዲስ አበባ አድዋ ድረስ የሚያደርጉትን የእግር ጉዞ በስሱ ከመናገር በቀር ትንፍሽ አይሏትም ። አይ ጋዜጠኛ !!

የመንግስት ጥቅም ባይገባኝም ዛሬ በዚህ ቀን ላይ የሚጠቀሙ አካላት ግን በእኔ እይታ የሚከተሉት ናቸው ።

፩ኛ፦ የወሲብ ቀንን የቀሰቀሱት ጋዜጠኞችና የሚዲያ ተቋማት ። እነሱ አቅራቢ ደላሎች በመሆን የድለላ ሥራ ነው የሚሠሩት ። የሚደልሉትም ። ለሆቴሎች ፣ ለአስካሪና አደንዛዥ መጠጥ ፋብሪካዎች ፣ ለአበባእርሻ ባለቤቶች
ና ለቀይ በቀይ ወይም ደም በደም አልባሳት ነጋዴዎች ነው የሚደልሉት ። ከሁሉም ስፖንሰር በሚል ሰበብ ያገኛሉ ይከፈላቸዋልም ። ከሆቴሎቹ አልጋም ለአንድ ቀን ይያዝላቸዋል ።

ሆቴሎች ፦ በዚያን ቀን ባለኮከቦቹ ቀደም ተብሎ በሚከፈል ቀብድ አልጋዎቹ በሙሉ የሚያዙ ሲሆን እሱን የሚይዙት ገንዘብ መጣያ ያጡ የአንድ ጀንበር ሃብታሞችና ለዚሁ የወሲብ ቀን የሚመጡ ዲያስፖራዎች ናቸው ።

በየመንደሩ የሚገኙትና ለወትሮው የአይጥና የበረሮ መፈንጫ የነበሩ ሆቴልና አልጋ ቤቶችም ተፈልገው አይገኙም ። እንዲያውም አንዳንዶቹ ሆቴሎች የሰራተኛ ማረፊያና የዘበኛ ቤቶቻቸውን ጭምር ለአገልግሎቱ ያውላሉ ። በወቅቱ ዘማውያኑ ከሚያንቀዠቅዣቸው የዝሙት ዛር መተንፈሳቸውን እንጂ ስለ አልጋው ጥራት የሚያዩበት ጊዜም የላቸውም ።

አንዳንድ ቦታዎች ላይ እንዲያውም አልጋ ከመጥፋቱ የተነሳ ዘማውያኑ ጥንዶች በመዳራት በአንድ ቦታላይ እንደመንጋ ይጠብቁና በተሰጣቸው ቁጥር በወረፋ እየተጠሩ ይገባሉ ። " 10 ቁጥር ! . . .አቤት ! 3 ቁጥር ግቡ ። የሚሰጣቸውን የ30 ደቂቃ ወይም የ1 ሰዓት ጊዜ ካሳለፉም ። በግድ እንዲወጡ ይደረጋሉ ። " አረ ጎበዝ እንተሳሰብ እንጂ ! ለተረኞች እዘኑላቸው እንጂ ! አረ ቶሎ ቶሎ ብላችሁ ጨርሱ ይባላሉ ። አቤት ሲያሳፍር ። ምክንያቱም ሌሎች ዘማውያን እየተቁነጠነጡ ስለሚያስቸግሩ ። በዚያን ቀን ማፈር የሚባል ነገር ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ።

፫ኛ፦ የአበባ ነጋዴዎች ፣ የቀይ በቀይ አልባሳት ነጋዴዎች ፣ የአስካሪ መጠጥ ፋብሪካዎችና ከእነዚህ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ሁሉ ይጠቀማሉ ።

ልጃገረዶች በእለቱ ቀይ ወይን ይጠጡና ፤ በቀይ ምንጣፍ ላይ ተራምደው ፣ በቀይ አልጋ ላይ ቀይ አንሶላ ውስጥ ገብተው ለበአሉ ድምቀት ሲባል የገበሩትንና የሰዉትን ድንግልና ፤ የፈሰሰው ደማቸውን ውጦና እንዳይታይ አድርጎ በሚያስቀር ቀይ በቀይ አልባሳት ተጀቡነው ባዶ ሆነው ወደ ማንነታቸው ይመለሳሉ ።

ከበአሉ ማግስት በኋላ ደግሞ እነ ኤች አይ ቪ ፣ እነ ጨብጥና ቂጥኝን የመሳሰሉ የአባላዘር በሽታዎች የክብር ቦታቸውን ይይዙና ተረኛው ነጋዴዎችና አትራፊዎች የህክምና ተቋማት ይሆናሉ ።

የዘንድሮው በዚህ አይነት ሁኔታ ያልፍና ለሚቀጥለው ዓመት ደግሞ በተሻለ ዝግጅትና ቅስቀሳ ካለፈው ዓመት ጋር እያነጻፀሩ መቀጠል ነው ።

እኛ ግን እንንቃ ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ ይለናል ለሮሜ ሰዎች በላከው መልእክቱ በምዕ. 13 ከቁጥር 11 እስከ 13
----------
11፤ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።

12፤ ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።

13፤ በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን ።

አበቃሁ ። 0911608054 የእጅ ስልኬ ነው ።

ሻሎም.! ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
የካቲት 6/6/2008 ዓም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

+4915217428134 ደግሞ የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶች የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ ።
በቅድሚያ የካቲት 6/2008 ዓም
በአዲስ አበባ ተጻፈ
በድጋሚ ሰኔ የካቲት 6/2010 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ ተለጠፈ ።


#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
https://telegram.me/And_Haymanot