*"የህይወት ስንቅ"*
<<>>>::::<<<>>>:
፡ @And_Haymanot
<<>>>::::<<<>>>:
አንድ ወጣት አንድን ታላቅ አባት ጥሩ
ሰው የሚባለው ምን የሚያደርግ ነው ብሎ ቢጠይቃቸው፤
:
*እኚህ ትልቅ አባትም መልሰው ይኸውልህ ልጄ አንተም ብትሆን ጥሩ ሰው ለመሆን ከፈለግክ ሊኖሩህ የሚገቡ ጉዳዮችን ላስቀምጥልህ ልብ ብለህ አድምጠኝ!!*
:
:::---::::---::::---::::---::::
"ፈጣሪን የሚፈራ ልብ ይኑርህ!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ጥሩ ሰው ማለት፡-
:
~►ዘወትር ለኃጢአቱ የሚጨነቅና ይቅርታ የሚጠይቅ፤
፡
~►ዘወትር በሥራና በትጋት የተጠመደ፤
፡
~►ከመናገር ዝምታን ገንዘብ
የሚያደርግ፤
፡
~►የፈጣሪን ትእዛዛቱን የሚጠብቅና እራሱን ዝቅ የሚያደርግ ነው በማለት መለሱለት፡፡
:
ዓሣ ከውኃ ወጥቶ ከቆየ ወዲያው እንደሚሞት ሰውም ከመንፈሳዊ ሕይወቱ ከወጣ እንደዚሁ ይሞታል፡፡
፡
ዓሣው ቶሎ ተምልሶ ወደ
ውኃው ሲገባ እንደሚድን ሰውም በንስሐ ቶሎ ሲመለስ ፈጣሪ የይቅርታውን በር ይከፍትለታል፤
፡
ስለዚህ ንስሐን እንደ ቀላል ነገር አትቁጠረው፤
፡
."መልካምነት ውደድ !"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ከተሰወረ ፍቅር የተገለጠ ዘለፋ፣ ከጠላት መልካም ሐሳብ የወዳጅ ክፉ ምክር፣ ከራቀ ወንድም የቀረበ ወዳጅ ሳይሻል እንደማይቀር አትዘንጋ፤
፡
መልካም ሞት የመልካም ኑሮ ውጤት ነው፤
፡
አንደበተ ትልቅ ውስጠ ቀላል እንዳትሆን ተጠንቀቅ
፡
"በፈጣሪ እንጂ በደጋፊዎች አትተማመን!"
:::---::::---::::---::::---::::
፡
በደጋፊዎች ከተማመንክ ከሰባራ ወንበር ላይ እንደተቀመጥክ ቁጠረው፤
፡
የሰይጣን ደህና ባይኖረውም፣ ብቻውን ካለ ሰይጣን ይልቅ በሰው ላይ ባደረ ሰይጣን ተጠንቀቅ፣ በሰው ላይ ያደረ ሰይጣን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስትለው ከሰውየው ጋር ተጣብቆ ያስቸግራልና፡፡
፡
."ካለፈው ስህተትህ ተማርበት እንጂ አትማረርበት!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ሰዎች በአንተ ላይ ምንም እንዳያወሩ ሥልጣን የለህምና፤ የሚሉህን እየሰማህ ስህተትህን አስተካክል፤
:
."አስፍቶ መረዳትን አዳብር!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ሌሎች እንዴት ማጥቃት እንዳለብህ
የሚነግርህን ሰው ሌላ ጊዜ እሱ ሲያጠቃህ እንዴት መካለከል እንዳለብህ እየነገረህ እንደሆነ ተረዳው።
:
ሌሎችን ቀርበህ እንዴት እንደምትወድ የሚነግርህን ሰው ግን ለፍቅር እድል ስጠው።
:
." ለመታመን ማመን አለብህ!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ሰውን ማመን ቀብሮ ነው የሚለው አስተሳሰብ ስህተት ነው።
:
ለማመን ሰው መቅበር ካስፈለገ
የተቀበረን ለማመንም መቀበር ሊያስፈልግ ነው።
:
ሰውን የማምነው ቀብሬ ከሆነ ሌሎችም እኔን የሚያምኑኝ ቀብረውኝ ነው።
:
መኖር ግዴታ በሆነበት ህይወት ውስጥ ሞት መብት አይሆንም።
:
ማንኛውም ሰው ራሱን በህይወት ማቆየት እንጂ ለመሞት ራሱን መግደል አይችልም።
:
ነገር ግን ራስን ለመግደል ቀላል ዘዴ አለ። :
►መጀመሪያ ማሳብ ማቆም።
:
►ቀጥሎ ማሰብ ያቆምከውን አሳብ መኖር።
:
"ለማድረግ ተዘጋጅ!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ለማድረግ ስታስብ እጥፍ አድርገህ አስብ!"
:
ያሰብከውን ስትተገብር በቁመትህ ልክ አድርግ።
:
ከፍ ባልክ ቁጥር ከፍታህ ቋሚ መድረሻህ አለመሆኑን እወቅ።
:
ወደ ላይ ከፍ ስትል ወደ ታች ተመልከት።
:
በከፍታህ ወቅት ወደታች መመልከትህ ስትወድቅ የምታርፍበትን ምቹ ቦታ እንድትለይ ያደርግሀል።
:
."ለችግር የተሸነፍክ አትሁን !"
:::---:::::---::::---::::---:::::
:
በህይወትህ ችግር ሲያጋጥምህ ችግሩን መለየት የመፍትሄ መጀመሪያ መሆኑን ተረዳ።
:
ችግሩን የመለየት መጀመሪያው ደግሞ አንተ ራስህ በራስህ ችግር አለመሆንህ ለይቶ ማረጋገጥ ነው።
:
ሳያልፍ የመጣ ክፉ ነገር የለምና እስኪያልፍ ታገሥ፤
፡
."ትንሽ ለመስጠት አትፍራ !"
:::---::::---::::---::::---::::
:
የስጦታ ዋጋ በተቀባዩ ስሜት እንጂ በስጦታው ይዘት አይወሰንም።
:
ለሰጪው ትንሽ የሆነ ለተቀባዩ ትልቅ ዋጋ አለው።
:
10."ክብርህን ከምግባርህ እንጂ ከሰው አትጠብቅ !"
:::---::::---::::---::::---::::
:
የምትቀበለው አንተ አስቀድመህ በሰጠኸው ልክ ነውና!
:
ለመከበር ፤ ለመወደድ ፤ ጥሩ ጓደኛ ለማግኘት አንተ አስቀድመህ ሌሎቹን አክብር ፤ ውደድ ፤ጥሩ ጓደኛም ሁንላቸው ምክንያቱም መልካምነት ለራስ ነውና!
:
በህይወታችን ለሰዎች ከክፋት የነጻ
በፍጹም ንጹሕ ልቦና መልካምና ቅን ሆነን እንኖር ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን!
// አሜን 3x///
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን
@And_Haymanot

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
===============
በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
☞ በዘመኑ የሚወዱት ሰዎች ነበሩ፤ የሚጠሉት ሰዎችም ነበሩ፡፡ ዛሬም የሚወዱት ሰዎች አሉ፤ የሚጠሉት ሰዎችም አሉ፡፡
☞ ያን ጊዜ በትሕትና ቀርበዉት ይወዱት የነበሩት ተጠቅመዋል፤ በብዙ ነገር ውስብስብ በኾነ በዚህ ዘመንም ትምህርቱን የሚከታተሉ ኹሉ በቤተ ክርስቲያን ወደብ ያርፋሉ፡፡ ተስፋ የቆረጡት ይነሣሉ፤ ልበ ደንዳኖች ይደነግጣሉ፤ የንስሐ ፍሬም ያፈራሉ፡፡ የማይወዱት ግን በባሕሩ ማዕበል ይሰምጣሉ፡፡
☞ ትምህርቱን ተከታትለው ስፍር ቊጥር የሌላቸው ቅዱሳን ተወልደዋል፤ ብዙ ገዳማት ተመሥርተዋል፤ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ታንፀዋል፡፡ ዛሬም እርሱን ሰምተው የቅድስናን ሕይወት ገንዘብ ለማድረግ የሚጣጣሩ ብዙዎች ናቸው፡፡
☞ ስብከቱን አድምጠው ብዙ ቤተ ሰቦች በቃል ሳይኾን በተግባር ኦርቶዶክሳውያን ኾነዋል፤ ብዙ ልጆች በአፍአ ሳይኾን በኹለንተናቸው ኦርቶዶክሳውያን ኾነው አድገዋል፡፡
☞ አበው ሲናገሩ፡- “ዘወትር የሊቁን ትምህርት የሚያደምጥ ሰው በቀጥታ የክርስቶስ ትምህርትን እንዳደመጠ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የቅዱስ ጳውሎስ አፈ ንጉሥ ነውና፤ ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አፈ ንጉሥ ነውና” ይላሉ፡፡
☞ እንዲህም በመኾኑ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ነው የሚባል ሳይኾን ዛሬም በቃል ኪዳኑ አብሮን ያለ፣ በዚያ ጥዑም አንደበቱ የሚመክረን፣ የሚገሥፀን ቅዱስ አባት ነው፡፡
☞ ያን ጊዜ ሕዝቡ ከትምህርቱ ጣዕም የተነሣ ቆመው ሲያጨበጭቡለት እንዲህ ይላቸው ነበር፡- “እኔ የምፈልገው የእናንተን ምስጋና ሳይኾን የእናንተን ጥቅም ነው፡፡ … እኔ የምሻው የእናንተን ውዳሴና ጭብጨባ ሳይኾን ጥበብን ገንዘብ እንድታደርጉ ነው፡፡” ዛሬም ቃሉ ያው ነው፤ ሕያው ዘኢይመዉት!
✞ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ረድኤት በረከትና ምልጃ አይለየን✞ አሜን ✞✞✞
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
ከወቅታዊ መረጃ ጋር
የሚቀርቡበት፡፡
°ለተሃድሶዎች መልስ የሚሰጥበት°
👉"፩ ሃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡

የመናፍቃን ስሕተትና የእኛ የኦርቶዶስ ተዋህዶ አስተምህሮ፡
@And_Haymanot
ክፍል ፩
(በዚህ ርዕስ በዘመናት የተነሱ የመናፍቃን ሃሳቦች እና ቅዱሳን አባቶች ለኑፋቄአቸው የሰጡት ምላሽ ይዳሰስበታል፡ ይህ ኑፋቄ አሁንም በሌሎች ቤተ እምነቶች የሚገኝ ነውና እውቀትን ሸምተን በትህትና የጠፉ በጎችን እናሳውቅ እንመልሳቸውም)
~ ሰብልያኖስ፡ አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ገጽ ናቸው አለ፡ እኛ ግን ሦስት ገጽ አንድ ኅብረ መልክእ ሦስት አካል አንድ አምላክ ሦስት ስሞች አንድ እግዚአብሔር እንላለን!
~ አቡናርዮስ፡ አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስ ለየራሳቸው ናቸው አለ፡ እኛ ግን አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አንድ ኅብረ መልክእ አንዲት መንግስት አንዲት ፈቃድ ናቸው እንላለን!
~ አርዮስ፡ ክርስቶስ ፍጡር ነው አለ፡ እኛ ግን ፈጽሞ የልተፈጠረ ከአባቱን አኗኗር የጎደለና የተለየ ያይደለ እንደሆነ እንናገራለን!
~ ንስጥሮስ፡ ወልድ ከነቢያት እንደ አንዱ ነው የእግዚአብሔር ልጅ በዮርደኖስ ባደረበት ጊዜ የጸጋ አምላክ ሆነ አለ፡ እኛ ግን ከዘላለም እስከ ዘላለም በመለኮቱ ከአብ ጋር የተከከለ አምላክ ነው እንላለን!
~ ፎጢኖስ፡ የእግዚአብሔር ልጅ ህልውና ከማርያም ከተወለደ ወዲህ ነው፡ ከጥንትም አደለም አለ፡ እኛ ግን ከዘመናትና ከጊዜ ከሰዓታትና ከዕለታት አስቀድሞ የነበረ በኋለኛው ዘመን እኛን
ስለማዳን ያለወንድ ዘር ከድንግል ማርያም ተወለደ እንላለን! ገላ 4፡4
~ አርጌንስ፡ ወልድ ከአብ ያንሳል አይተካከለውም መንፈስ ቅዱስም ከወልድ ያንሳል እርሱን ማየት አይቻለውም አለ፡ እኛ ግን በሥላሴ ዘንድ በማዕረግ ማነሥና መብለጥ የለም
በመለኮት አንድ ወገን ናቸው(አንድ ነው) እንላለን!
~ ቢቱ፡ ለኃጥአን ፍዳን ለመክፈል ለጸድቃንም በጎ ዋጋ ለመስጠት ወልድ ከአባቱ ተለይቶ ይመጣል አለ፡ እኛ ግን አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርዱ በአንድ አደባባይ በአንዲትም መወቃቀሻ ቦታ ይመጣሉ እንላለን!
~ ፀረ ማርያም የሆኑ አንጢዲቆማርያጦስም ማርያም መድሃኒታችንን ከወለደችው በኋላ ከዮሴፍ ተገናኝታለች ይላሉ፡
እኛ ግን ማርያም አምላክን የወለደች ናት ከወለደችውም በኋላ ለዘላለም በድንግልና ኖራለች እንላለን።
~ አውጣኪ፡ የክርስቶስ ስጋ እንደኛ ደካማ ስጋ አደለም መከራንም አልተቀበለም አለ፡ እኛ ግን የክርስቶስ ሥጋ ደከመ ወዛ ተረበ ተጠማ ታመመ ሰው በመሆኑ ሞተ ከብቻቸው
ከሐጢአቶችም በቀር ከሰው ህግ የቀረው የለም እንላለን! ሕዝ
44፡2, ማቴ 4፡3, ሉቃ 1፡32
~ የህንድ ጳጳስ ሳዊሮስ የእለእስክንድርያውም ቴዎዶስዮስ
የእግዚአብሔር ልጅ ያለ ፈቃዱ በግድ ሞተ ይላሉ፡ እኛ ግን በፈቃዱ መከራን ተቀበለ በውዱም ሞተ በመለኮቱም ሃይል ተነሳ እንላለን።
~ አቡርዮስ ፡ የክርስቶስ ሰውነት ልብና ነፍስ የለውም መለኮቱም ስለ ልብና ነፍስ ፋንታ ሆነው አለ፡ እኛ ግን ነፍስ
ነባቢት ልቡና ጠባይዓዊ አለው እንላለን! ዳግመኛም መለኮታዊ ጌትነት አምላካዊም ሁሉን ቻይነት አለው።
~ አፍትኪስ፡ የክርስቶስ ሥጋ ከሰማይ ወረደ አለ፡ እኛ ግን የክርስቶስ ሥጋ እና ነፍስ ከአዳም ባህርይ ብቻዋን ንጽሕት
ድንግል ከምትሆን የገሊላ ሴት ማርያም ያለ ወንድ ዘር የነሳው ነው እንላለን!
~ መንክዮስ፡ የክርስቶስ ሥጋ ምትሐት ነው የሰው ልጅም ሥጋ አይደለም አለ፡ እኛ ግን የክርስቶስ ሥጋ የሥጋን አዳራሽ
የሚያጸና አጥንት በደም ስሮች ውስጥ የምትፈስ ደም ሰውነትን የሚያስሩ ጅማቶች አናትን የሚሸፍን ጠጉርና ቅንድብ የማትታይ ነፍስ የምተስተውልና የምትናገር የሕይወት እስትንፋስ የእጆችና የእግሮች ቡቃያ ጥፍሮች አሉት እንላለን! (መጽሐፈ ምሥጢር በአባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ)
ይቀጥላል....

#ሠለስቱ_ደቂቅን_ያዳናቸው_ማን_ነው?
@And_Haymanot
~► በድርሳነ ገብርኤል ላይ ገብርኤል
~► በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል
~► በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ሩፋኤል ተብሎ መገለጹ ምሥጢሩ ምን ይሆን?
@And_Haymanot
“ታዲያ ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣቸው ማን ነው?” ለሚለው የተሐድሶዎች
ጥያቄ የቀረበ መልስ በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ:
መጀመሪውንም መጽሐፍ ቅዱሱ ገብርኤል ነው አይልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ የሚለው የሚከተለውን ነው፤
‹‹ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም፤ ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት። እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ ›› /ዳን 3 ፤ 24 -25/ ፡፡
-
👉 በዚህ ገለጻ መሠረት አራተኛውን ያየው ንጉሡ ናቡከደነጾር ነው፡፡ እርሱም አየሁ ያለው አራተኛ ሰው ነው፡፡ የጨመረበት ቢኖር አራተኛው የአማልክትን ልጅ ይመስላል የሚለውን ነው፡፡ ለመሆኑ አራተኛውን ሰው እርሱ ብቻ ለምን አየ ? ሌሎቹ ለምን አላዩም ? አንደኛው የጥያቄው ቁልፍ ምስጢር ያለው እዚህ ላይ ነው።
-
እውነቱን ለመናገር ይህ ሰው ጥንቱንም ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እሣት የጣለው ራሱን ምስል አቁሞ ለምስሉ ሕዝቡን በማሰገድ ራሱን አምላክ አድርጎ ሊያስመልክ ነበር፡፡ ታዲያ ራሱንና እርሱን የመሰሉትን አምላክ አድርጎ የሚቆጥር ከሆነ የሚያየውን አራተኛውን ሰው ‹‹ የእኛን ልጅ ይመስላል ወይም እኛን ይመስላል›› ለምን አላለም? ከዚያ ይልቅ አርቆ ሌሎች አማልክትን የሚያመልክ አስመስሎ ‹‹ የአማልክትን ልጅ›› ይመስላል ያለበት ምስጢር ምንድን ነው ? ይህን ያለበት ምክንያቱ ያየው ነገር አራተኛው አካል ከህልውና ያለው በዘር በሩካቤ የተወለደ ሰው እነርሱ ሳያዩት እሳቱ ውስጥ ገብቶ ሳይሆን ነገሩ መገለጥ ስለሆነ ነው፡፡
+
👉 በብሉይ ኪዳን ከተገለጹት ታላላቅ ሦስት የእግዚአብሔር መገለጦች ውስጥ አንዱ ይህ የሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ነው፡፡
አንደኛው በመምሬ የአድባር ዛፍ ሥር እግዚአብሔር ለአብርሃም በሦስት ሰዎች አምሳል የተገለጠው መገለጥ ነው / ዘፍ 18/ ፡፡
ሁለተኛው ደግሞ አሁንም እግዚአብሔር ለአባታችን ለያዕቆብ በጎልማሳ አምሳል ተገልጾ ሲታገለው ያደረበት ታሪክና ያዕቆብንም መጀመሪያ ‹‹ ካልባረከኝ አልለቅህም ›› ከተባረከ በኋላም ‹‹ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው ›› /ዘፍ 32 ፤ 25 - 32/ ያሰኘው መገለጥ ነው፡፡
ሦስተኛው ይህ ለባቢሎኑ አላዊ ንጉሥ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶን እሳት በጣለበት ወቅት ያደረገው መገለጥ ነው፡፡
-
ሦስቱም መገለጦች የሚያመሳስሏቸው ሁለት ጠባያት አሏቸው፡፡ የመጀመሪያው በሦስቱም ጊዜ እግዚአብሔር በሰው መልክና አምሳል መገለጡ ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ደግሞ ቃለ እግዚአብሔር በሥጋዌ ( ሰው በመሆን) ተገልጦ ለሰው ፍጹም ድኅነት የሚሰጥ መሆኑን አስቀድሞ በምሳሌ መግለጽ ነው፡፡ መሠረታዊ መልእክቱ ደግሞ አምላክ ሰው ከሆነ በኋላ የሚያድነው የተስፋውን ዘር እሥራኤልን ብቻ ሳይሆን አሕዛብንም ጭምር መሆኑን ለማሳየትና አሕዛብም የሥጋዌው ነገር ቀድሞ የተገለጸው ለእሥራኤል ብቻ ስለሆነ እኛ ልናምንበት አይገባም እንዳይሉ ለዚህ ደንዳናና ጫካኝ ናቡከደነጾርም ጭምር ገለጸለት፡፡
የእነ ነነዌ ታሪክም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሆኖ የተቀመጠውና እግዚአብሔር ለአሕዛብም ድኅነት ይፈጽም እንደነበር የተዘገበው እግዚአብሔር የእሥራኤል ብቻ ሳይሆን የሁሉም አምላክ የነበረ መሆኑን ራሱ ብሉይ ኪዳንም ምስክር እንዲሆን ነው፡፡ እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ታሪኮችና ምሳሌዎችም በብዛት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ፡፡
ስለዚህ የዚህ በሠለስቱ ደቂቅ ድኅነት ውስጥ የታየው መገለጥ ዋናው ምስጢሩና መልእክቱም የአካላዊ ቃልን ሰው ሆኖ መገለጥና አዳኝ መሆኑንን በሐዲስ ኪዳንም እንደ ሠለስቱ ደቂቅ እሳትና ስለት፣ ሰይፍና ጎራዴ፤ እስራትና ግርፋት የሚቀበሉትን ሰማዕታት ሁሉ የሚያድናቸው እርሱ መሆኑን መግለጽ ነው፡፡
-
ታዲያ ዋናው መልእክቱና ምስጢሩ ይህ ከሆነ ገብርኤልም ሆነ ሌሎቹ መላእክት ለምን አዳኑ ይባላሉ? በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት መሠረት ለሰዎች ከጊዜያዊና ምድራዊ አደጋና ሰዎች ከሚያመጡባቸው መከራ ድኅነት ሲደረግላቸው ድኅነታቸውን የሚፈጽሙላቸው ቅዱሳን መላእክት ማለትም ጠባቂ መላእክቶቻቸው ናቸው፡፡ ምንም አንኳ ይህ መሆኑን አንዳንድ ጊዜ በግልጽ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በምስጢር ቢገለጽም የእግዚአብሔር መላእክት ከሚጠብቋቸው ሰዎች ተለይተው አያውቁም፡፡
ለምሳሌ በሐዋርያት ሥራ ላይ ቅዱስ ያዕቆብን ያስገደለው ሔሮድስ ቅዱስ ጴጥሮስንም ለመግደል ባሰረው ጊዜ በዚያ ወቅት ሊሞት እግዚአብሔር ስላልፈቀደ መልአኩ እንዲያድነው አድርጓል፡፡ ‹‹ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና። ፈጥነህ ተነሣ አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ። መልአኩም። ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ። ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም። የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ። ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ /ሐዋ 12፤ 7 - 11/ ተብሎ እንደተጻፈ ሙት ላነሣውና ስንት ተአምራት ላደረገው ቅዱስ ጴጥሮስ አሁን ግን ይህን ሁሉ የሚያደርግለት መልአኩ ነው፡፡ ይህ መልአክ የቅዱስ ጴጥሮስ ጠባቂ መልአክ እንደሆነ ብዙ ሊቃውንት በትርጓሜያቸው አስተምረዋል፡፡
በዚሁ ታሪክ ላይ ‹‹ ጴጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሉአት አንዲት ገረድ ትሰማ ዘንድ ቀረበች፤ የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ ደጁን አልከፈተችም፥ ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ጴጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች። እነርሱም፦ አብደሻል አሉአት። እርስዋ ግን እንዲሁ እንደ ሆነ ታስረግጥ ነበር። እርሱም፦ መልአኩ ነው አሉ ›› / 13-15 / ተብሎ እንደተጻፈው ውስጥ የነበሩት ጴጥሮስ አይሆንም ‹‹ መልአኩ›› ነው ያሏት እርሱን ሊመስልሽ የሚችለው ጠባቂ መልአኩ ነው ለማለት ነበር፡፡ ይህም የሆነው በጥንት ክርስቲያኖች ዘንድ የጠባቂ መላእክት ጥበቃና መገለጥ በሰፊው ይታወቅ ስለነበረ ነው፡፡
- @And_Haymanot
በመጽሐፈ ጦቢትም ላይ ቅዱስ ሩፋኤል ሰው መስሎ ለጦብያና ለቤተሰበው እንዲሁም ለራጉኤልና ለቤተሰቡ ቀድሞ ጸሎታቸውን በማሳረግ በኋላም ከፈተናቸው በማዳንና ሕይወታቸውን በመባረክ ተገልጾ አይተነዋል፡፡
-
እነዚህ ሁለት ታሪኮች የሚያሰረዱን ጠባቂ መላእክት በድሕነታችን ውስጥ ትልቅ ስፋራ የሚሰጣቸውና በርግጥም እነርሱ የሌሉበት ድኅነት የሌለ መሆኑን ነው፤ ልዩነቱ በአንዳንዶቹ ታሪኮች ላይ መገለጣቸው በአንዳንዶቹ ላይ ደግሞ ተገልጠው ለሰው አለመታየታቸው ብቻ ነው፡፡
-
👉 ጌታችንም በወንጌል ‹‹ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው

👍1
በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና ›› /ማቴ 18 ፤10/ ያለው ስለጠባቂ መላእክቶቻችን ነው፡፡ በእያንዳንዱ ነገራችንና ፈተናችን ላይ ወደ እግዚአብሔር እያመለከቱ የሚጠብቁን የሚያድኑን የሚያስፈርዱልን ወይም የሚያስፈርዱብንም እነርሱ ናቸውና፡፡
+ @And_Haymanot
እንደናቡከደነጾር ያለውን አስፈርደውበት አውሬ አድርገው ሣር ያስግጡታል፤ እርሱም ራሱ አንድ ቅዱስ ጠባቂ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ ብሎ አሁንም አረጋግጧል /ዳን 4 ፤13/ ፡፡ እንደ ሔሮድስ ያለውን ደግሞ ‹‹ ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ ›› /ሐዋ 12 ፤23/ ተብሎ እንደተጻፈው አስፈርደው ይቀስፉታል፡፡ እንደ ዳንኤል፤ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ዮሴፍ፣ ሠለስቱ ደቂቅ ያሉትን ደግሞ ያድኗቸዋል፡፡ ‹‹ ... እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም። በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ። አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ። ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና ፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። ... ›› /መዝ 90 / ተብሎ ተጽፏልና፡፡
-
👉 ጠባቂ መላእክቶቻቸው የሚያድኗቸው ቢሆንም በራእዩ የታየው አንድ ሆኖ ሳለ ሦስቱ ተደርገው በሦስት ድርሳናት ለምን ተገለጸ የሚል ጥያቄም ልናነሣ እንችላለን፡፡
እንዲህ ያሉትን ምስጢራት መረዳት የምንችለው በቅዱሳት መጻሕፍት ያሉትን ተመሳሳይ ታሪኮችና ይህ የሚሆንበትን ምክንያት ስናውቅ ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል የጌታችንን ትንሣኤ አስመልክቶ አራቱም ወንጌላውያን መዝግበውልናል፡፡ አራቱም የመዘገቡበት መንገድ ግን ተቃርኖ ባይኖረውም ልዩነት አለው፡፡ አበይት ልዩነቶቹ ሦስት ነገሮች ላይ ናቸው፡፡ የተገለጹት መላእክት ቁጥር ላይ፤ የመጡት ሴቶች ማንነት ና ሴቶቹ የመጡበትን ሰዓት በተመለከተ የአዘጋገብ ልዩነት አለ፡፡ ለዛሬው ለጉዳያችን ቅርበት ያለው የመላእክቱ ብዛት ላይ እናተኩር፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ‹‹ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ። መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው። እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። ፈጥናችሁም ሂዱና። ከሙታን ተነሣ፥ እነሆም፥ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው /ማቴ 28 ፤2-7/ ሲል ይገልጻል፡፡
ማርቆስ ደግሞ ‹‹ ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ፤ ... ›› /ማር 16 ፤5/ ይላል፡፡
ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ‹‹እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ ›› /ሉቃ 24 ፤4/ይለናል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስም ብዙ ነገር ስለ ትንሣኤው ካተተ በኋላ ‹‹ ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤ ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም በእግርጌ ተቀምጠው አየች / ዮሐ 20 ፤ 11 - 12/ ሲል መዝግቦልናል፡፡
-
እነዚህን አገላለጾች ስናያቸው የአዘጋገብ ልዩነት ቢታይባቸውም ቅራኔና የእውነታ ልዩነት ግን የላቸውም፡፡ ማቴዎስና ማርቆስ ስለ አንድ መልአክ ማነጋገር ቢገልጹም ሌላ መልአክ እንዳልነበረ ግን አላመለከቱም፡፡ እንዲያውም ማቴዎስና ማርቆስ የመዘገቡልን ስለ አንድ መልአክ ይሁን እንጂ ሁለቱም የመዘገቡት ግን ስለተለያዩ መላእክት ነው፡፡ ማቴዎስ ከመቃብሩ ወጭ ድንጋዩን አንከባሎ ስለተቀመጠው ዘግቦ ከመቃብሩ ውስጥ በቀኝ በኩል (በራስጌ ወይም በግርጌ) ስላለው አልመዘገበም፡፡
ማርቆስ ደግሞ ውስጥ ከገቡ በኋላ ስላለው መዝግቦ በውጭ በኩል ስላለው ወይም የመቃብሩ ድንጋይ ላይ ስላለው አልመዘገበም፡፡ ሁለቱም ግን ሌላውን መልአክ አልነበረም አላሉም፤ ‹‹የለም›› በሚያሰኝ መንገድም አልገለጹም፡፡ ሉቃስና ዮሐንስ ደግሞ ሁለቱንም መኖራቸውንና በግርጌና በራስጌ መሆናቸውን ገለጹልን፡፡ ስለዚህ ሁሉም ትክክል ናቸው፡፡ የተለያዩና የማይቃረኑ የተባለው ለዚህ ነው፡፡ ይህም ቢሆን በተዘገበው መንገድ ስለተገለጹት መላእክት ይናገራል እንጂ በትንሣኤው ዕለት ስለነበሩት መላእክት አጠቃልሎና ዘግቶ አይናገርም፡፡ የነበሩትን መላእክትም ሁለት ብቻ ነበሩ ማለት ፍጹም ስሕተት ላይ ይጥላል፡፡
- @And_Haymanot
👉 ወንጌላውያኑ በዚህ በመላእክቱም ቁጥር ሆነ በሌሎቹ ጉዳዮች የተለያዩትስ ለምንድን ነው ስንል ደግሞ አንድ መሠረታዊ መልእክት እናገኛለን፡፡ ይኸውም ስለመላእክቱ የተለያየ ዓይነት መገለጥ የገለጹት ለተለያዩ ሰዎች በትንንሽ የጊዜ ልዩነት የታየውን መገለጥና ለአንዳንዶችም በተቀራራቢ ግን በተለያየ ጊዜ የተገለጠውን ስለመዘገቡ ነው፡፡
ለምሳሌ ቅዱስ ዮሐንስ መግደላዊት ማርያም መመላለሷ ከማሳየቱም በላይ ለእርሷ የተደረገውን የአንድ ጊዜ መገለጥ ብቻ ነው የነገረን፡፡ ሉቃስ ደግሞ ለሌሎች ሴቶች የተደረገውን ( ምክንያቱም ተመላልሰው ያዩም አንድ ጊዜም ያዩ አሉ፤ ብዙ ታሪኮች በውስጡ አሉና) እያሉ ከነጊዜው ስለመዘገቡ እንጂ አንዱን ነጠላ ድርጊት ለያይተውና አሳሰተው መዝግበው አይደለም፡፡ በዚህ መሠረት ቀስ ብሎና በዚህ ጽሑፍ መጀመሪያ ክፍል ላይ እንዳየነው ከመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ተሰጥቷቸውና በጊዜው የነበረውን እውነተኛውን ትውፊት ከሐዋርያትና ከነበሩት ሰምተው ከተረጎሙት ሳይረዳ ልክ እንደዚያ ርኩሳን እንደተባሉት እንስሳት ሳያመሰኳ ወይም እውነታውን ሳይቆነጥጥ ወይም እንደ አሳዎቹ ሐዋርያት የእምነት መከላከያ ጋሸ (ቅርፊት) እና ምስጢራትን የሚረዳበት ክንፈ ጸጋ ሳይኖረው በአመክንዮ (ሎጂክ) ብቻ እረዳለሁም አስረዳለሁም ቢል ይሳሳታል፡፡
---
👉 ስለዚህ የሠለስቱ ደቂቅ ድኅነትን በተመለከተ በድርሳነ ገብርኤል ላይ
ገብርኤል ተብሎ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል ተብሎና በድርሳነ
ሩፋኤል ላይ ሩፋኤል ተብሎ መገለጹ ከላይ በወንጌል እንዳየነው ያለ ትውፊቱን ለያይቶ መዘገብ እንጂ ተቃራኒ ነገር አይደለም፡፡በዚሁ መሠረት ሦስቱን ሕጻናት አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልንም ያዳኗቸው ጠባቂ መላአክቶቻቸው ናቸው፡፡ እነዚህም ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ሩፋኤል ናቸው፡፡ ልክ ሥላሴ ለአብርሃም በተገለጹለት መንገድ ሦስት ሆነው ከሦስቱ ጀርባ ቆመው መታየት ነበረባቸው ካላልን በቀር ከጥንት ጀምሮ በተላለፈው ትውፊት ሦስቱ መላእክት የሦስቱ ሕጻናት ጠባቂ መላእክት ነበሩ፡፡ እንኳን ሰዎቹ ሦስት ሆነው ይቅርና አንድም ሰው ቢሆን ሦስትና ከዚያ በላይ መላእክት ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ዮናታን ወልደ ሳዖል ‹‹ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና›› /1ሳሙ 14 ፤ 6/ እንዳለው በአንድም በብዙ ማዳንም የእግዚአብሔር ፈቃድና ምስጢር እንጂ የማነስና

የመብዛት ጉዳይ አይደለም፡፡ እንዲህ ያለው ነገር እንኳን በመላእክት ቃል ኪዳን ተቀብለው በሚያማልዱና በሚያድኑ ሰማዕታትና ቅዱሳንም ታሪክ ላይ በተደጋጋሚ የተገለጸ መሆኑን ከተለያዩ ገድላት መረዳት ይቻላል፡፡
-
ለምሳሌ አንድ አሣ አስጋሪ ሰው መርምህናም ( ማር ምህናም፤ ቅዱስ ምህናም ማለት ነው) እርዳኝ እያለ ሲጠራ ‹‹ ወበጊዜሃ መጽአ ኅቡረ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወቅዱስ መርምሕናም ተፅኢኖሙ ዲበ አፍራሲሆሙ ....›› ተብሎ እንደተገለጸው ቅዱስ ጊዮርጊስም አብሮ ተገልጾ እንደረዱት የሚነግር ተአምር በገድለ ጊዮርጊስ ተአምሩ ላይ ይገኛል፡፡
ይህ ግን በዋናነት ሊገለጽ የሚችለው በገድለ መርምሕናም እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ በቅዱሳን ዘንድ አንዱ ብቻ ነው እንጂ ሌሎቹ የሉም የሚያስብል ታሪክም ድርጊትም የለም፤ ሊኖርም አይችልም፡፡ ልዩነት ያለ የሚመስለን መገለጦችን የምንረዳበት ሒደት አነስተኛ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
-
ይህ ከሆነ ታዲያ በሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ውስጥ ቅዱስ ገብርኤል ጎልቶ ለምን ይወጣል? በዓል ሆኖ የሚከበረው ለቅዱስ ገብርኤል፤ በሥዕልም ላይ አራተኛው ተብሎ በናቡከደነጾር የተገለጸው ሰው የቅዱስ ገብርኤል ሥዕል ሆኖ የሚሣለው ለምንድን ነው?
+++
👉 ይህም የሆነበት ምክንያት ዝም ብሎ ወይም በአጋጣሚ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሥጋዌውን አስቀድሞ የገለጸው መላእክትንም በሰው አምሳል እንዲገለጹ በማድረግም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ ለሙሴ መጀመሪያ የተገለጠለት በዚሁ መንገድ ነበረ፡፡ ‹‹ የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል ታየው እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ ›› / ዘጸ 3፤2/ ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ይህም ግን ነገረ ተዋሕዶን የሚስረዳ የምስጢረ ሥጋዌ መገለጥ ነው፡፡
እግዚአብሔር ራሱን በመላእክት አምሳል ሲገልጥ ደግሞ ቅድሚያውን ስፍራ የሚይዘው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ምክንያቱም ገብርኤል ማለት ቃለ እግዚአብሔር እንዲሁም ሰውና አምላክ ማለት ስለሆነ ነው፡፡ እመቤታችንን ሊያበስር የተላከውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ለናቡከደነጾር ሥጋዌውን ‹‹ አራተኛ ሰው አያለሁ›› እስኪል ድረስ ሰውነቱን በመገለጥ ያሳየው ከሦስቱ ሊቃነ መላእክት ይህን ምስጢር በስሙም በተልእኮም ቅዱስ ገብርኤል የተሸከመው በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም ሦስቱም ሊቃነ መላእክት በጠባቂ መላእክትነታቸውና ረቂቃን ኃይላት በመሆናቸው ቢኖሩም እግዚአብሔር ሊገልጠው ለፈለገው ታላቅ ምስጢር ተስማሚ የሆነውን (ራሱ ገብርኤል መሆኑ ትርጉምና መልእክት ያለው ነውና) መልአክ በአምሳለ ወሬዛ ኀየል ወይም የነገሥታትን ልጅ በሚመስል መንገድ የንጉሠ ሰማይ ወምድር የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ምሳሌ ሆኖ እንዲገለጽለት አደረገ፡፡
በዓሉ ለእርሱ የተሠጠውና ሥዕሉ የእርሱ የሆነበት ምክንያትም ይኸው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ቅድሰት ተዋሕዶ ይህን ሁሉ ምስጢር እንዲህ ባለ ታላቅ ሥርዓተ በዓል እንዲከበር በሥዕልም እንዲታይ በማደረግ ነገረ ሠጋዌውንም የሕጻናቱን ተጋድሎም የመላእክቱንም ጠባቂነት ስትገልጽበትና ስታስረዳበት ትኖራለች፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን በምልዓት መረዳት ያለው በእውነተኛው የሐዋርያትና የሊቃውንት ትምህርት ትውፊትና ሥርዓተ አምልኮ ጸንታ በምትኖረው ቅድስት ተዋሕዶ ነው፡፡
+
ምንጭ:-
© ይህ ጽሑፍ በቀጥታ ደቀመዝሙር ሸዋፈራው ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ > ነገረ ማርያም - Mariology ገጽ ላይ የተወሰደ ነው። በዲ/ን ብርሃነ አድማስ የቀረበ አስተምሮና ለተሐድሶ የተሰጠ ምላሽ ነው።
♥ ♥ ♥ ♥ ♥
21 21 21
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም
ቤተክርስቲያን አትታደስም!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም
እንማልዳለን!
(መጽሐፈ ሚስጢር)
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን
መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣
የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ
ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
†† † † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት
እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም
ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
†† † † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር

ክፍል ፪
@And_Haymanot
(በዚህ ርዕስ በዘመናት የተነሱ የመናፍቃን ሃሳቦች እና ቅዱሳን
አባቶች ለኑፋቄአቸው የሰጡት ምላሽ ይዳሰስበታል፡ ይህ ኑፋቄ አሁንም በሌሎች ቤተ እምነቶች የሚገኝ ነውና እውቀትን ሸምተን በትህትና የጠፉ በጎችን እናሳውቅ እንመልሳቸውም)
~ አርሲስ የተሰኙ መናፍቃን በነፍስና በሥጋ ወደ ሲኦል ወረደ ይላሉ፡ እኛ ግን መለኮታዊ ቃል ከብቻዋ ከነፍስ ጋር ወደ ሲኦል ወረደ፤ ሥጋን ግን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አወረዱት
በበፍታም ገንዘው በመቃብር ውስጥ አኖሩት እርሷም እስከ ትንሣኤ ድረስ ብቻዋን ያለነፍስ ቆየች፡ መለኮት ግን ከነፍሱ ጋር ነበረ ከሥጋውም አልተለየም በአብም ቀኝ ከአለም አስቀድሞ
እንደነበረ አኗኗሩ በአካል የተለየ ሆነ በሁሉ ስፍራ በሁሉ ዘንድ መልቶ ይኖራልና! ዮሐ 19፡38-42
@And_Haymanot
~ የሮሜ ሊቀጳጳሳት ልዮን ሥጋ ከመለኮት ያንሳል አለ፡ እኛ ግን
ከአንድነት በኋላ የክርስቶስ ሥጋው ከመለኮት አያንስም እንላለን!
~ የኬልቄዶን ማህበርተኞች መለኮትና ሥጋ በሁለት መንገድ በሁለት ሥርዓት ናቸው አሉ። እኛ ግን ከቅድስት ድንግል
ማርያም ሰው የሆነው አምላክ አንድ አካል አንድ ፈቃድ ነው እንላለን!
አንዳንዶች ደግሞ. . .
~ አምሳሉን ወደ መስቀል አወጣ የተቸነከረ እርሱ አይደለም የሚሉ አሉ፡ እኛ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ለብዙዎች መዳን በሊቀ ካህናት አገልጋይ ፊቱን ተጸፋ፤ በጲላጦስ አደባባይ ተገረፈ
በብረቶችም ተቸነከረ በለንጊኖስም ጦር ተወጋ እንላለን! ማቴ 26፡67, ዮሐ 19፡34 (ይህንን የሚሉት ሙስሊሞች ናቸው አልመሲህ ኢሳ አልሞተም አልተሰቀለምም ነገር ግን አምሳያው ተሰቀለ ብለው ያምናሉ፡)
~ አርጌንስ፡ እግዚአብሔር አዳምን እና ሔዋንን ያለበሳቸው ቁርበት እኛ የምንመላለስበት በላያችን ያለ ሥጋ ነው የቁርበት ልብስም አይደለም አለ፡ እኛ ግን ሥጋስ ቀድሞም በተፈጠሩ ጊዜ አላቸው እግዚአብሔር ያለበሳቸው ግን የቁርበት ልብስ ነው ትእዛዙን ስላቃለሉ የነቀፋ ልብስ ነው እንላለን፡ ዘፍ 3፡26
አንዳንዶች ደግሞ. . .
~ ሰማየ ሰማያት የማይወስነው እግዚአብሔር አራት ጎኖቿ ባነሱ በሰው ልጆች እጅ በተሰራች ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዴት ያድራል የሚሉ አሉ፡ ሁለተኛም ኅብስት የክርስቶስን ሥጋ
የምሥጢርም ወይን ደሙን መሆን ይችላልን? ይላሉ፡ እኛ ግን በጽርሐ አርያም ያለ አኗኗሩ ሳይጎድል ይቀድሳት ዘንድ የመለኮት ኃይል በቤተ ክርስቲያን ያድራል። ኅብስትም በመንፈስ ቅዱስ
መውረድ በተቀደሰ ጊዜ ከልማዳዊ ኅብስትነት ሥጋውን ወደመሆን ይለወጣል ወይንም ከልማዳዊ ወይንነት ደሙን ወደመሆን ይለወጣል እንላለን!
~ በወንጌል መምጣት ኦሪት እንደቀረች በሐዋርያትም ስብከት የነቢያት ትንቢት እንደጠፋ ሰንበትም ትንሣኤ በሆነባት በእሁድ እንደተሻረች የሚናገሩ አሉ፡ እኛ ግን ኦሪት በወንጌል ስብከት ከበረች፤ ነቢያትም በሐዋርያት ትምህርት ከፍ ከፍ አሉ፤ አለምን ከመፍጠር የማረፍ ሰንበትም በዓለም አዳኝ ትንሣኤ ዘውድ
ተቀዳጄች እንላለን!
~ ዳግመኛም ስለ ማርያምና ስለመስቀል እንደሚክዱ በጆሮአችን የገባ ወሬ አለ፡ እኩሌቶቹ የወለደችው ማርያም ከመስቀሉ ትበልጣለች ይላሉ እኩሌቶቹም በሕማማቱ ደም የተነከረ መስቀሉ ይበልጣል ይላሉ፡ እኛ ግን ማርያም አምላክን የወለደች እንደሆነች እናምናለን! መስቀሉም መለኮት የተዋሐደው ትስብእት ደም የተቀደሰ የብርሀን ማዕተብ መሆኑን እናምናለን!
~ ፍልብያኖስ የመድኃኒታችን የክርስቶስ መለኮቱና ትስብእቱ ሁለት ገጽ ነው አለ፡ እኛ ግን የአምላከችን የመለኮቱና የትስብእቱ ባሕርይ በአንድ ገጽ በአንድ አካል ያለ ነው እንላለን!
~ መቅዶንዮስ መንፈስ ቅዱስ ፍጡር ነው አብና ወልድ ግን የተከከሉ አንድ ናቸው አለ፡ እኛ ግን መንፈስ ቅዱስም ፈጽሞ ያልተፈጠረ ከአብና ከወልድም ያልተለየ ነው አንድ ኅብረ መልክእ ነው እንጅ የአብና የወልድ የመንፈስቅዱስም ባሕርይ አንድ ነው እንላለን!
~ ሰዱቃዊያንና እንደ እነርሱ ያሉ ትንሣኤ ሙታን የለም ይላሉ፡ እኛ ግን ትንሣኤ ሙታንስ አለ ለኃጥአን ፍዳ ለጻድቃንም በጎ ዋጋ አለ እንላለን! ማቴ 22፡23,ዮሐ 5፡25-29, ሐዋ 23፡8
"አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን
እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤" (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:14፤)

ታቦተ ጽዮን
@And_Haymanot
✞ የእግዚአብሔር ታቦት የገባበት ስፍራ ቅዱስ ነው 2ኛ ዜና 8፥11 ✞
✍ መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች ጥንታውያን መዛግብት እንደሚሉት የቃል ኪዳኑ ታቦት በሚንቀለቀል ብርሃኑና እሳቱ በነቀርሳማ እባጭና በለምጽ የመምታት፣ የማቃጠል፣ ተራሮችን ወደሜዳማነት የመለወጥ፣ ወንዞችን የማድረቅ፣ ታላላቅ ሠራዊቶችን የመደምሰስ፣ ከተማዎችን የማፈራረስ ኃይል አለው።
✔ እነዚህ ምንጮች አክለውም ታቦተ ህጉ የአይሁዶች የእምነት መሰረት እንደሆነና ንጉሥ ሰሎሞንም የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ያሰራው ይህንኑ ታቦት በክብር ለማኖር አስቦ እንደሆነ ይገልጻሉ ይሁንና ከክርስቶስ ልደት በፊት ከአንድ ሺህና ስድስት መቶ አመታት መካከል በነበረው ጊዜ ይህ እጅግ ድንቅና ተአምራዊ ታቦት የትና ወዴት እንደሄደ ሳይታወቅ በመሰወሩ ጉዳዩ ለብዙ ሺህ ዓመታት እንቆቅልሽ ሆኖ ቆይቷል ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት በ587 ዓመተ ዓለም የናቡከደነጾር ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ባቃጠላት ጊዜ ታቦቱ በቦታው አልነበረም በጦርነቱ የተማረኩ እስራኤላውያን ከባቢሎን ወደሀገራቸው ኢየሩሳሌም በ538 ዓመተ ዓለም ተመልሰው ሁለተኛውን ቤተ መቅደስም በሠሩበት ወቅትም ታቦቱ በዚያ አልነበረም ይህም ቀደም ሲል ታቦቱ በባቢሎናውያን አለመዘረፉን ያረጋግጣል።
♦ የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ኤሊየት ፍሬድማን በ1987 ይህን ጉዳይ አስመልክተው ሲጽፉ "የታቦቱ መጥፋት ከመጽሐፍ ቅዱስ አስደናቂ ምሥጢሮች እንደ አንዱ ይቆጠራል" ብለዋል።
❖ "ታቦቱ ወደሌላ ቦታ ስለመወሰዱ፣ ስለመውደሙ (መቃጠሉ) ወይም መደበቁ የተጻፈ ነገር የለም ከዚህ በኃላ ታቦቱ ጠፋ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለም አናውቅም ወይም የት እንዳለ ማንም አያውቅም የሚሉ አስተያየቶች እንኳን አልተጻፉም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዓለም ካሉ ነገሮች ሁሉ ትልቅ ሥፍራ የተሰጠው ክቡር ዕቃ፣ እንደዋዛ ይጠፋል"። [ ግራሃም ሐንኩክ፦ "The sign and the Seal" ወይም "ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ" ገጽ 4 ትርጉም፦በጌታቸው ተስፋዬ ጎጂ]
☞ #የታቦተ_ጽዮን_መኖሪያ_ኢትዮጵያ
✍ ታቦተ ጽዮንን ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ይዞ የመጣው ልዑል ምኒልክ ይባላል ምኒልክ ማለት "የብልህ ሰው ልጅ" ማለት ነው እናቱ ንግስተ ሳባ የጠቢቡ ሰሎሞንን ጥበብ ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም በሄደችበት ወቅት ኢየሩሳሌም ውስጥ ከጠቢቡ ሰሎሞን ብትፀንሰውም ማርገዟን እንዳወቀች ወደሀገሯ ተመልሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የወለደችው ሃያ ዓመቱ ሲሞላ ምኒልክ ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ ከአባቱ ቤተ መንግስት እንደደረሰም የክብር አቀባበል ተደረገለት ይሁንና ለአንድ አመት ያህል ከቆየ በኃላ የእስራኤል ታላላቅ ሰዎች ንጉሱ ሰሎሞን ምኒልክን ከእኛ የበለጠ ያቀርበዋል፣ ይወደዋል በሚል በምቀኝነት ተነሳሱበት ወደሀገሩ ይመለስ ዘንድም አጥብቀው ጠየቁ ንጉሱ ሰሎሞንም የቀረበለትን አቤቱታ ካዳመጠ በኃላ ምኒልክ ወደሀገሩ የሚመለሰው የእስራኤል ታላላቅ ሰዎች የበኩር ልጆች ሁሉ በአጃቢነት አብረውት ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ ከሆነ ብቻ መሆኑን ገለጸላቸው።
❖ በዚህም ተስማሙ ከነዚህም መካከል ከምኒልክ ጋር አብረውት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት መካከል የሊቀ ካህናቱ ሳዶቅ የበኩር ልጅ አዛርያስም ይገኝበታል የቃል ኪዳኑን ታቦት ከቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ደብቆ ያወጣውም እርሱ ነበር ምኒልክ ታቦቱ በድብቅ ወጥቶ ከእርሱ ጋር መምጣቱን ያወቀው ከኢየሩሳሌም ብዙ ርቆ ከተጓዘ በኃላ ነበር ስለሁኔታውም እንደነገሩት ድርጊቱ የተፈጸመው በእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ተገንዝቦ ታቦተ ህጉ ከእነርሱ ጋር መሆን እንዳለበት አምኖ ተቀበለ በዚህ ሁኔታ ነበር ታቦተ ህጉ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው።
✍ በአጠቃላይ ስለ ታቦተ ጽዮን አስር ዓመታት የፈጀ ምርምርና ጥናት በማድረግ የሚታወቀው ግራሃም ሐንኩክ የተባለ እንግሊዛዊ ጸሐፊ "The sign and the Seal" ወይም "ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ" በሚለው መጽሐፉ ገጽ 245 ላይ የታቦተ ጽዮን መኖሪያ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መሆኗን አክሱም ጽዮን ቤተ መቅደስ ሆኖ ሲመሰክር፦ "...ከሲና ተራራ ግርጌ በወርቅ የተሰራው፥ በበረሃ የተጓዘውና የዮርዳኖስን ወንዝ የተሻገረው፥ ወደ ተስፊዪቱ ምድር ለመግባት እስራኤላውያን ያደረጉትን ትግል በድል ያጠናቀቀላቸው፥ በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግስት ወደ እስራኤል የተወሰደው፥ በ955 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ አካባቢ በንጉሥ ሰሎሞን በተሰራው ቤተ መቅደስ ተቀምጦ የነበረው ይህ የቃል ኪዳን ታቦት ነው..." በማለት ነበር የደመደመው።
☞ ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱት የዘመን አቆጣጠር በሙሉ እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ነው።
✞ የእናታችን የአክሱም ጽዮን ረድኤት፣ በረከትንና ምልጃ አይለየን!!!! አሜን!!! ✞

ያጣ ለማኝ
@And_Haymanot
✍ ቀበሮዋ አንድ የበሰለ የወይን ዛላ ተንጠልጥሎ ለመበላትም አስጎምጅቶ ታገኛለች፤ የወይኑ ዛላ ግን ከቁመቷ በላይ በመሆኑ በጣም ካልዘለለች በስተቀር እንደማታገኘው ስለታወቃት እንጣጥ እያለች ብዙ ሞከረች ይሁን እንጂ ወይኑ እንዳሰበችው በቀላሉ የምትደረስበት አልሆነም ወደኋላ ተንደርድራ በጣም ዘለለችና የመጨረሻ ሙከራ አደረገች ይሁን እንጂ ፈጽም ልትደርስበት አልቻለችም ወይኑ በአበሳሰሉ በጣም ልዩ ነው ለዐይን የሚያምር ለመብላትም የሚያስጎመጅ ነው ቀበሮዋ በጣም ተጨነቀች ወይኑን ትታ እንዳትሄድ ያስጎመጃል እንዳትበላው ደግሞ ስትዘል ብትውልም አልደረሰችበትም ስለዚህ "እንደውም ይኼ ወይን አልበሰለም" ብላ ትታው ሔደች።
❖ "ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሔዳል" የሚባለው ለእንደዚህ ዐይነቱ ነው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለመናፍቃን ያልተመቸችው አላዋቂ ወገኖች እንደሚሉት የዶግማና የቀኖና ችግር ኖሮባት ሳይሆን ይህንን መኖርና መፈጸም ስላቃታቸው ብቻ ነው መጾም ያቃቻቸው ጾምን አይስፈልግም ሲሉ ንጽሕናቸውን ያጎደፉና ቆባቸውን የጣሉት ደግሞ ምንኩስና አያስፈልግም ይላሉ ያቃተንና ያልተደረሰበትን ነገር አያስፈልግም ብሎ መንቀፍ የቀበሮ ጠባይ ነው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሥጋዊ ዕውቀት የማትመረመር ብትሆንም ትምህርቷ ግልጽ፤ ተልኮዋም የታወቀ ነው "ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው" እንዲል ፪ኛ ቆሮ ፬፥፫
✞ ለተሃድሶ መናፍቃን የጴጥሮስን እምባ ያድልልን እኛንም ኦርቶዶክሳውያን በሃይማኖት ያጽናን✞ አሜን✞✞✞
ምንጭ፦ ምጥን ቅመም ቁጥር ፫ በዲያቆን ምትኩ አበራ