፩ ሃይማኖት
8.91K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
video-2018-02-02-07-40
*እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ*

*ለተሃድሶአውያን የተሠጠ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽ*

💕በዲያቆን ቴዎድሮስ

*"በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።"*
(ወደ ሮሜ ሰዎች 3:24)
@And_Haymanot
*👉ጸጋ ምንድን ነው?
👉 ስንት አይነት ጸጋ አለ?*
@And_Haymanot
አስማተ መለኮት(የመለኮት ስሞች) እውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉምን?

@And_Haymanot

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በዕብራይስጥ፥ በግሪክና በግዕዝ ልሳን ስመ አምላክ መጥራቷ፤ ድርሳናቷ ጥንቆላ አስተምህሮዋ ፀረ-ወንጌል
ያስብላታል???
+++ ተወዳጆች ሆይ! ሃይማኖተ ክርስቶስ በሆነች ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነታችን የሚያምን ሁሉ ትክክለኛውን አስተምሕሮ በጥንቃቄ ቀርቦና ጠልቆ ሊረዳ ይገባዋል:: እስቲ ዛሬ አንዳንድ አብዳን(ሰነፎች) የሚስቱበትን አስማተ መለኮት(የመለኮት ስሞች) እንይ::
@And_Haymanot
ድርሳነ ሚካኤል ላይ ከመጽሐፈ ሄኖክ የተወሰዱ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ የተጻፉ ኅቡዕ ስሞችን እናገኛለን::
✞ 1ኛ.አህያ ሸራህያ ("ህ" ላልቶ ይነበብ!) በዕብራይስጥ ኤህዬ አሼር ኤህዬ ይባላል:: በግዕዝ ደግሞ እሄሉ
ዘእሄሉ ወይም እከውን ዘእከውን ሲባል በአማርኛ "ያለና የሚኖር" ማለት ነው:: ዘፀ.3፥14 ላይ እናገኘዋለን::
✞ 2ኛ.አግዮስ የሚለው በጽርዕ(በግሪክ) አጊዎስ ይባላል:: ቅዱስ፥ ክቡር፥ ምስጉን ማለት ነው::
✞ 3ኛ.አካዕ በግሪክ አካይዖ ሲባል አምላክ ከሃሊ(አምላክ ሁሉን ቻይ) ማለት ነው:: "ወአንበሮ ለዝ መሐላ አካዕ በእዴሁ ለሚካኤል" እንዲል:: ሄኖ.20፥1-5::
✞ 4ኛ.ቤቃ ማለት ቀዳሜሁ ቃል
(በመጀመሪያ የነበረ ቃል) ማለት ነው::
✞ 5ኛ.አውሎግዮስ ጌርዮስ የሚለው ደግሞ በግሪክ ኤፍሎጊቶስ ኪሪዮስ ይባላል:: ቡሩክ እግዚአብሔር ማለት ነው::
✞ 6ኛ.ጌርዮስ
በግሪክ ኪርዮስ ሲባል እግዚእ(ጌታ)፥ እግዚአብሔር ማለት ነው::
✞ 7ኛ.ፓንዋማንጦን በግሪክ(በጽርዕ)
ፕኔፍማቶን ይባላል:: መንፈስ(ቅዱስ) ማለት ነው::

ታዲያ በዕብራይስጥ፥ በግሪክና በግዕዝ ልሳን ስመ አምላክ መጥራቷ፤ ድርሳናቷ ጥንቆላ አስተምህሮዋ ፀረ-ወንጌል
ያስብላል??? ለመሆኑ እነዚህ ስሞች ለእግዚአብሔር ብቻ የሚያገለግሉ አይደሉምን??? ካልተማረ መናፍቅ
ይጠብቀን!!!
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
🙏1
( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )
።።።።።።።።።።።።።።።።።።፡፡፡
@And_Haymanot
።።።።።።።።።።።።።።።።።።፡፡፡
አንተ ሰው ! ቃለ እግዚአብሔርን ተማር
ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር ! ሁልግዜ ተማር ! ላትስተካከል ትችላለህ ላትለወጥ ትችላለህ ግን ተማር! ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትሆን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት አቅም ታገኛለህ ። ካልተማርክ ግን ራስህን
እንኳን መውቀስ የምትችልበት አቅም አታገኝም ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስሰራ ራስህን እየወቀስክ
ትሰራለህ ይህች የንስሃ በር ትሆንሀለች አንድ ቀን ወደ ንስኃ ትመራሀለች !!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
‹‹መዳንም በሌላ በማንም የለም›› የሐዋ 4፥12

@And_Haymanot

«መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ከሰማይ በታች ሌላ የለም» የሐዋ 4፥12 ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ከእርሱ በቀር አዳኝ አምላክ የለም። ኢሳ 45፡21 ከኢየሱስ ውጪ አዳኝ የለም ስንል ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ማለታችን ነው ምክንቱም ከእግዚአብሔር ውጪ የሚያድን ስለሌለ ነገር ግን አምላካችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ለአመኑትን #የጸጋ_የማዳን_ስልጣን_ለቅዱሳን ሰጥቶአቸዋል። መጽ መሳፍ 3፡9 የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብን የታናሽ ወንድሙን የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን አስነሣላቸው። መጽ መሳፍ 3፥15 የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ናዖድን ግራኙን ሰው አዳኝ አስነሣላቸው የእስራኤልም ልጆች በእርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎም ግብር ላኩ።
የያዕቆብ ወንድም የይሁዳ መል ቁጥር 22 እንዲ ይላል "አንዳንዶች ተካራካሪዎችንም ዉቀሱ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ" የጌታ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቃል መፅሀፍ ቅዱስ የተናገረውን መካድ የክርስቲያን ጠባይ አይደለም። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ፍጥረታቱ ሁሉ በደሙ ከሐጢአታችን አንጽቶናል። ይህን ስራ ማንም ሊያደርገው አይችልም። ነገር ግን ሰዎች ከሐጢአት መንገድ መመለስ አንዱ የማዳን ሥራ ነው። ሐጢአት መስራት በራሱ ሞት ነውና። ከዚህ ከሐጢአት ሞት ሰዎችን በመመለስ በህይወት እንድኖሩ ማድረግ ለቅዱሳን ሰዎች የተሰጠ ስልጣን ነዉ። ስለ ሰው ሐጢአት መጸለይ የማዳን ስራ ነው። ሰዎች ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ማድረግን የማዳን ስራ ነው። ነገር ግን የአዳምን በደል በሞቱ ያጠፋው ጌታችን አባታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ብቻ በመስቀል ዲያቢሎስን ድል በመድረግ አዳነን። ለአንዴና ለመጨረሻ በእርሱ ተፈጸመ።
@And_Haymanot
ዛሬ ግን እርሱ በየቀኑ አይሞትልንም እኛ ሞቱን ስለበደላችን እንደሆነ እንመሰክራለን። በጌታ የሚያምኑ ቅዱሳን ሰዎች ለሌሎችን ሐጢአት ይጸልያሉ ከሐጢአት ሞት በጸሎት ያድናሉ።ያዕ5፡16ሐዋርያዉ ቅዱስ ጰዉሎስም እንኳን እንዲህ በማለት ተናግሮአል 'ወንድሞቼ ሆይ ስለ እኛ ጸልዩ" ወደ 1ኛ ተሰሎ 5 ፡ 25
የያዕቆብ መል 5፤20 ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን፥ የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ። በዚህ የእግዚአብሔር ቃል ላይ የማዳን ስልጣን የተሰጠው ለቅዱሳን ነው። የእነ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ ብዙ በሽተኖችን አድኗል።ሐዋ5፡15 በሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ ልብስ ብዙዎች ድነዋል።ሐዋ19፡11 እራሱ ጌታችን እንዲህ በማለት የተናገረው ቃል አለ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ያደርጋል ከእኔም የበለጠ ያደርጋል በማለት ታላቅ ሥልጣንን ሰጥቶአቸዋል።ዮሐ14፡12 ጌታችን ኢየሱስ አዳኝነት የባህሪ ገንዘቡ እንደሆነ ሁሉ በርሱ ያመኑ ቅዱሳንም ይህ ጸጋ ይሰጣቸዋል ፡፡ቅዱሳን የጸጋ ማዳን ስልጣን በመጽሐፍ ቅዱስ አላቸው። ቅድሰት ቤተ ክርስቲያናችን የጌታ የባህሪ ብቸኛ አዳኝነት ታምናለች። ለቅዱሳንም የጸጋ ማዳን ስልጣን ትቀበላለች።እንደ ጌታችን ቅዱስ ቃል ትመራበታለችም። ቅዱሳን ይህ ቃል የተሰጣቸው እርሱን ተጠግተው ነው።ቃሉን ሰምተው የተሰጣቸው ልዩ ስጦታ ነው። እንደውም እርሱን ለመቀበል የመጀመሪያው መስፈርት አድርጎታል፡፡ሐዋርያው መዳን በሌላ በማንም የለም ሲል የክርቶስን ማዳን ማንም አይተካዉም፣ የሚተካውማ ቢኖር ወደዚህ ምድር ምን አስመጣው??? በኦሪቱ ብዙ መስዋት ተሰውቷል፡ ብዙ ነብያትም ነበሩ፡ አልቻሉም ምክንያቱም አዳማዊ ሀጢያት በደማቸው ስለ ነበር፡ አካላዊ ቃል፣ በርሱ ፈቃድ በአባቱ ፈቃድ እንዲሁም በባሕሪ ህይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ወደዚህ ምድር መጣ። እኛን ሊያድን። አዳነን ነጻም አወጣን ። ስለዚህ ይህ ድኅነት በማንም አልነበረም ወደፊትም አይኖርም፡፡ ስለዚህም ከአዳም ሀጢያት መዳን የሚቻለው #የባህሪ_አዳኝ_በሆነው_በኢየሱስ እንጂ በሌላ በማንም እንዳልሆነ በዚህ እንረዳለን ፡፡
@And_Haymanot
አሁንም ማዳን የሚችለው እርሱ ኢየሱስ ነው እርሱ ግን በፈለገው አድሮ ያድናል። እግዚአብሔርን አሰራር ማን ይከሳል። አቤሜሌክን አብርሃም ይጸልይልህና እኔ ልማርህ ያለ አምላክ ነው። የዛሬዎችን አይነት ሰዎች እንደሚሉት ቢሆን ኖሮ ለምን መንገድ ያረዝማል? ራሱ ማዳን እየቻለ እርሱ ይጸልይልህ እንዴት ይላል? ለሶስቱ ሰነፎች ኢዮብ ይጸልይላችሁና ላድናችሁ እንዴት ይላል? ራሱ በቀጥታ ማዳን ሲችል። ይህ ሁሉ እግዚአብሔር እንዲከበር ነው። ደግሞም የወዳጆቹን ክብር እግዚአብሔር መግለጥ ደስ ያሰኘዋል። በእውነት እግዚአብሔር ምስጢሩን ከአብርሃም ይሰውራልን እንዳለው ራሱ ጌታ እግዚአብሔር። እግዚአብሄር ቅዱሳንን ስለሚያደርገው አስቀድሞ ይገልጣል አማክሮም ያውቃል፡ እርሱ ምክር የሚፈልግ ሆኖ አይደለም እግዚአብሔር የቅርብ አምላክ መሆኑን መግለጥ ስለፈለገ እንጂ። እግዚአብሄር የቅርብ አብሮን ያለ ነው። ለበረከቱና ለስጦታው ወሰን የሌለው ነው። ለቅዱሳን የሰጣቸው ክብር ከዚህ አንጻር የምናየው ነው። እርሱ ፈቃዱ ስለሆነ የቅዱሳንን ስም እንጠራልን፡ እርሱ በእነርሱ አድሮ ስለሚያድን አድኑን ብለን አንማጸናቸዋልን። የእግዚአብሔርን ሐሳብ ያልተረዱ ደግሞ እግዚአብሔርን ለማስተካከል መንገዱን ጠመዝማዛ አደረግኸው አስተካክል ብለው ከጌታ ጋር ይሟገታሉ። ጌታ ግን አሰራሩ ድንቅ ነው። አዳኛችን ኢየሱስ ለማዳን የበረታ ጌታ ሁላችንንም በቸርነቱ ያድነን አሜን ! የቅዱሳኑ ምልጃ እና በረከት ይደርብን !! አሜን !
ይቆየን
______፩ ሃይማኖት_____
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን
@And_Haymanot
#______አትታደስም______!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
============================
፩ ጌታ
፩ ሃይማኖት
፩ ጥምቀት ኤፌ4:5
🙏1
ኃጢአትን ለንስሓ አባት/ለካህን መናዘዝ/

@And_Haymanot

ተወዳጆች የተሀድሶ መናፍቃን ምዕመናንን ከንስሃ ህይወት ለማራቅ ሃጢአትን ለንስሃ አባት መናዘዝ አያሥፈልግም በማለት ሀጢአትን ለካህን መናዘዝን ይቃወማሉ፡፡ እናት ቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታሥተምራለች
@And_Haymanot
ካህን የእግዚአብሔር ምሥጢራት አስፈፃሚ ስለሆነ ኃጢአትህን ንገረው ። ይህን ቅዱስ ጳውሎስም አስረግጦ ጽፎልሃል ። " እንዲሁ ሰው እኛን እንደ እግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ይቁጠር ።" 1ቆሮ 4*1
አስቀድሞም በነቢዩ ሚኪያስ ያደረው እግዚአብሔር ሲናገር "ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነው "ይላል ።

ኃጢአትህን ለካህን በምትነግርበት ጊዜ የሚሰማህን ኃፍረት መሸማቀቅ ሁሉ ችለህ የመመለስን ምሥጢር እንዲያስፈጽምልህ ስትጥር እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ድርጊትህን እንደ ታላቅ መሥዋእትነት ቆጥሮልህ ኃጢአትህን ሁሉ ይደመስስልሃል ።/ ዩሐ 20*21*23/ ማቴ 18*18

ካህኑ ክርስቶስ በሰጠው በዚህ ሥልጣን መሠረት ከኃጢአት እሥራት መፈታትህን ያረጋግጥልሀል ። ሕይወት ለሚሆነው ሥጋና ደሙ እንድትበቃም ያደርግሃል ።/1ቆሮ 11*27/

በሕይወትህ ውስጥ የሚታዩትን ጉድለቶች (መንፈሳዊ ድክመቶች )እየተመለከተም እንዴት አሸናፊ መሆን እንደምትችል የሚመክርህ መንፈሳዊ መሪህ ካህን የንስሓ አባት መሆኑንም አትዘንጋ ።

ለካህን ኃጢአትን መናዘዝህ በራሱ የሚያተርፍልህ ነገር አለው ። ኃጢአትን መልሰህ ስትናገረው ለአንተ ለራስህ ምን ያህል አሳፋሪ እንደሆነ ይሰማሃል ። ይህም ዳግም እንዳትመለስበት ታላቅ ትምህርት ይሰጥሀል ። መጽሐፍ ቅዱስም የሚለው ይህንኑ ነው ። " እርስ በእርሳችሁ ኃጢአታችሁን ተናዘዙ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ሰው ስለሌለው ይጸልይ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ።" /ያዕ 5*16 /

ምንጭ @pope_shenouda
@pope_shenouda
___፩ ሃይማኖት_______
ላልደረሳቸው እናዳርስ
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን
@And_Haymanot
#______አትታደስም______!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
============================
፩ ጌታ
፩ ሃይማኖት
፩ ጥምቀት ኤፌ4:5
🙏1
ቤተክርስቲያንን መሳለምና መስገድ

@And_Haymanot

የተሃድሶ መናፍቃን ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች አንዱ ቤተክርስቲያን መሳለምን እንዲሁም በመቅደስ መስገድን ይቃወማሉ እኛም ጥያቄ ለሚነሳባቸው ምዕመናን በማለት አቅርበነዋል የበለጠውን ከአባቶች እንጠይቅ ለማለት እንወዳለን ኦርቶዶክስ መልስ አላትና፡፡
+ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ማደሪያ ናት፤ ዘጸ፡፳፰፥፰። “አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ
፥ጆሮቼም ያደምጣሉ።
አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ፥ ቀድሻለሁም፥ ዓይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።”ያለ እግዚአብሔር ነው። ፪ኛ ዜና፡፯፥፲፭- ፲፮። በሙሴ ዘመን እግዚአብሔር፡-ታቦቱ ባለበት ድንኳን ላይ በደመና በሚወርድበት ጊዜ ሕዝቡ በግልጥ ያዩ ነበር፤እየተነሡም በቤተ መቅደሱ በር ይሰግዱ ነበር። ዘጸ፡33 ቁ.7። እሳት ሲወርድ፥ቤተ መቅደሱም በብርሃን ሲሞላ ያዩ ነበር በዚህን ጊዜም በወለሉ ላይ በግምባራቸው ተደፍተው ይሰግዱ ነበር ፪ኛ ዜና፡፯፥፫። ወደ ቤተክርስቲያን ዞረን የምንሳለመውና የምንሰግደው ለዚህ ነው። ቅዱስ ዳዊትም፡-“እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።.... በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ፥ ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ።”ብሏል። መዝ፡፭፥፯፣ መዝ፡፻፴፯፥፪። ተሃድሶዎቹ ግን እንደ አባቶቻቸው እንደ ፕሮቴስታንት “እስከ መቼ ነው ለድንጋይ የምንሰግደው?” እያሉ ያደናግራሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ “የአባቴ ቤት” ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት “ድንጋይ” ይላሉ። ሉቃ፡2 ቁ.49። እኛ ግን በድንጋዩም ድንቅ ስራውን የሚሠራ ጌታ ነውና ያለን አናፍርበት ያመንነውን እናውቀዋለንና በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንገዛለታለን
ይቆየን
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾችን ለማግኘት
👉 @And_Haymanot
🙏1
" የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።"
1ኛቆሮ 1:18
@And_Haymanot
መልካም ዕለተ ሰንበት
ጫማ ማውለቅ፤

@And_Haymanot
Share
ተቃዋሚዎቹ፡-“ከእግረ ነፍስ ላይ የኃጢአትን ጫማ ማውለቅ እንጂ ከእግረ ሥጋ ላይ ጫማን ማውለቅ ጥቅም የለውም፤”ይላሉ። ነገር ግን ሙሴ፡- በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሲያወልቅ ያየነው የእግሩን ጫማ ነው፤“ ወደዚህ አትቅረብ፥አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን አውልቅ፤”ብሎታል። ዘጸ፡፫፥፭። የእግዚአብሔርም መልአክ ኢያሱን፡-“ጫማህን አውጣ፤”ብሎታል። ኢያ፡
፭፥፲፭። በዚህ ዓለም ስንኖር ለእግዚአብሔር የምንገዛው በሥጋም በነፍስም ነው። ስንዘምር በሥጋም በነፍስም እንዘምራለን እንጂ፥ልባችን ከዘመረ ይበቃል ብለን አፋችንን አንዘጋም። ስንሰግድም በሥጋም በነፍስም እንሰግዳለን እንጂ፣ልባችን ከሰገደ ይበቃል ብለን በጉልበታችን ከመስገድ አናቋርጥም። ቅዱስ ጳውሎስ፡-“በሥጋችሁ እግዚአብሔርን
አክብሩ፤”ያለው ለዚህ ነው ፩ኛ፡ቆሮ፡፮፥፳። ስለዚህ
ወደተቀደሰችው ስፍራ ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንገባ፥ ከእግረ
ሥጋችን ጫማን፥ከእግረ ልቡናችን ደግሞ ረቂቁን የኃጢአት ጫማ በንስሐ ማውለቅ ይገባል።
ይቆየን
👉 @And_Haymanot
🙏1
ነጭ መልበስ

@And_Haymanot

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡- በታቦር ተራራ ላይ አምላካዊ ክብሩን በገለጠ ጊዜ፥ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቷል፤ ልብሱ ደግሞ እንደ ብርሃን ነጭ ሆኗል። ማቴ፡፲፯፥፪።በጌታ መቃብር ዙሪያ የተገኙ ቅዱሳን መላእክትም ልብሳቸው ነጫጭ ነበር። ማቴ፡፳፰፥፫ ማር ፲፮፥፭ ሉቃ ፳፬፥፬ ዮሐ ፳፥፲፪። ጌታችን ባረገበት ጊዜም ነጫጭ ለብሰው ታይተዋል። የሐዋ፡ ፩፥፲። በወዲያኛውም ዓለም የሚጠብቀን ነጭ ልብስ ነው “ከሊቃናቱም አንዱ ተመልሶ፡- እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ? አለኝ። እኔም ጌታ ሆይ አንተ ታውቃለህ አልሁት። እርሱም፡-እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው ፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ (በኢየሱስ ክርስቶስ) ደም አነጹ።” ይላል። ራዕ፡7 ቁ.13-14። ነጭ መልበስ የቤተክርስቲያን ሥርዓት የሆነው ለዚህ ነው።
ይቆየን
👉 @And_Haymanot
ዕጣን ማጠን

@And_Haymanot

ሥርዓተ ዕጣንን ለሙሴ ያስተማረው እግዚአብሔር ነው።“በቀማሚ ብልሃት እንደ ተሠራ ፥በጨው የተቀመመ
ንጹሕና ቅዱስ ዕጣን አድርገው።..... ከዚያም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። እርሱም የቅዱሳን ቅዱስ ይሁንላችሁ። እንደ እርሱ የተሠራ ዕጣን ለእናንተ አታድርጉ፥በእናንተ ዘንድም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን። ሊያሸትተውም እንደ እርሱ
የሚያደርግ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።”ብሎታል። ዘጸ፡፴፥ ፴፬-፴፰። በብሉይ ኪዳን ዘመን ካህኑ አሮን በጽንሐ አድርጐ ያጠነው ዕጣን ሕዝቡን በሞት ከመቀሠፍ አድኖአቸዋል። ከዕጣኑ
በፊት ፲፬ሺ፯፻ ሰው ተቀሥፎአል፥ከዕጣኑ በኋላ ግን መቅሠፍቱ ቆመ። ዘኁ፡፲፮፥፵፮-፶። ጸሎት የሚያርገው(ወደ ላይ የሚወጣው) በዕጣን ነው።
ቅዱስ ዳዊት፡-“ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፤”ያለው ለዚህ ነው። መዝ፡፻፵፥፪። በአዲስ ኪዳ ንም
ጌታችን በተወለደ ጊዜ ሰብአ ሰገል ከወርቅና ከከርቤ ጋር ዕጣን ገብረውለታል ማቴ፡፪፥፲፩።
ጻድቁ ካህን ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ውስጥ እየጸለየ በሚያጥንበት ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦለት መልካም የምሥራች ነግሮታል። “ዘካርያስ ሆይ፥ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ፥ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፤”ብሎታል። ሉቃ፡ ፩፥፰-፳፫። ሥርዓተ ዕጣን በሰማይም አለ፤“ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው። የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።” ይላል ራዕ፡፰፥፩-፭ በመሆኑም ዕጣን ምዕራገ ጸሎት ነው፡፡
@And_Haymanot
እግዚአብሔር፡-“ዕጣን በእኔ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤”ያለበት ጊዜ አለ። ይህም ዕጣን በራሱ የሚያጸይፍ ነገር ኖሮት አይደለም። የአቅራቢውን ሰውነት የሚመለከት ነው። ዕጣን ብቻ
ሳይሆን ማንኛውንም ከኃጢአት ባልተለየና ከበደል ባልራቀ ሰውነት የሚቀርብ፥ ጸሎት፣ ጾም፣ መሥዋዕት፣ ቍርባን፣መብዓ፣ ጉባዔ፣በዓል ወዘተ... ፈጽሞ እንደማይቀበል ተናግሯል። ምክ
ንያቱን እና ምን ማድረግ እንደሚገባቸውም ሲነግራቸው፡-“እጆ
ቻችሁ በደም ተሞልተዋል። ታጠቡ፥ሰውነታችሁንም አንጹ
የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ ክፉ ማድረግን ተዉ፥ መልካም መሥራትን ተማሩ ፍርድን ፈልጉ የተገፋውን አድኑ ለደሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።”
ብሏል። ኢሳ፡፩፥፲-፲፯። የተነገረውም በሰዶምና በገሞራ ግብር ለጸኑ፥ ለሰዶም አለቆችና ለገሞራ ሕዝብ ነው።
ይቆየን....
"ባለንበት ጸንተን እንቁም"
👉 @And_Haymanot
🙏1
ዋሽንት የወንጌል ምሳሌ ነው፥ስድስቱ ቀዳዳዎች ደግሞ የስድስቱ ቃላተ ወንጌል ምሳሌዎች ናቸው። ከዋሽንት የሚወጣ ድምፅ ልብን ደስ እንደሚያሰኝ፥የወንጌልም
ቃል ነፍስን ደስ ይሰኛል።
…~ በቀሲስ ደጄኔ ሽፈራው
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በሰሙነ ሕማማት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምና የትከሻ ሰላምታ መለዋወጠን አይፈጽሙም፡፡
@And_Haymanot
ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት፣ አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማክሰኞ መከሩ አልሠመረላቸውም፡፡ ምክራቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ አያንሾካሾኩ “ እንስቀለው … አንግደለው ” ብለው ይማከሩ ነበር፡፡ ያንን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ መስቀልም አንሳለምም፡፡ ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሰላምታ የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ ይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ “እኔ የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት” ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት
አይደለም፤ ተንኮል የተሞላበት እንጂ፡፡ የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሔዋንን “ ሰላም ለኪ” ብሎ ነው ያታለላት፣ የዲያቢሎስ እና የይሁዳ ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ
ሕማማት ሰላምታ ልውውጥ የለም፡፡ ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኸው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ሥርወ መሠረቱ ይህ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል ይቀጥላልም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot
🙏1
ዜማ

@And_Haymanot

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፡-በቅዱስ ያሬድ በኩል ከእግዚአብሔር የተሰጣት ዜማ አላት። ዜማው ሦስት ዓይነት ሥልት አለው፥ግዕዝ፣ዕዝል፣አራራይ በመባል ይታወቃሉ ። እነዚህም ለአብ፣ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ምሳሌዎች ናቸው።
የመዝሙሩ፥የማኅሌቱ፥የቅዳሴውና የሰዓታቱ ዜማ ከእነዚህ ከሦስቱ አይወጣም። ዜማው የራሱ ምልክት(NOTA) አለው። ቤተክርስቲያን ለ፩ሺ፮፻ ዓመታት ስታገለግል የኖረችው፥ወደፊትም የምታገለግለው በዚህ ዜማ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ድርሰት በመሆኑ በምንም የሚለወጥና የሚተካ አይደለም። የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ከብሉይ ኪዳን ከአዲስ ኪዳን፣ከመጻሕፍተ ሊቃውንት እና ከመጻሕፍተ መነኮሳት የተውጣጣ ነው።
ተሀድሶዎቹ እየታገሉ ያሉት ይኸንን መንፈሳዊ ጸጋ ለማጥፋት ነው። የፕሮቴስታንቱን የዘፈን ሥልት እያመጡ በመበረዝ ላይ ናቸው። ይህም የመናፍቃኑን እያመጡ ካለማመዱ በኋላ ሕዝቡ በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት መካከል ያለው ልዩነት እንዲጠፋበት ነው።መናፍቃኑ የእኛኑ ሰዎች መልምለው አሰልጥነው በገዛ ሜዳችን እየወጉን ነው። እነ ዲያቆን እገሌ እነ ቀሲስ እገሌ እነ መሪጌታ እገሌ እነ ዘማሪ እገሌ እነ ሰባኬ እገሌ ውስጠ ፓስተር ሆነው ተገኝተዋል።
@And_Haymanot
ጌታ በወንጌል፡-“ከፍሬያቸው ታውቋቸ ዋላችሁ።” በማለት አስቀድሞ እንደነገረን ከፍሬያቸው (ከአሰባበካቸው፥ ከአዘማመራቸው ከኑፋቄአቸው)
አውቀናቸዋል። ማቴ ፯፥፲፮። ስብከታ ቸው ከፕሮቴስታንት ስብከት ጋር አንድ ነው፥የሚያዘጋጁት ከፕሮቴስታንት መጻሕፍትና የስብከት ካሴቶች ነው። መዝሙራቸ ውም እንደዚሁ ነው። ዜማው ሥጋዊ ስሜትን ለማርካት የተደረሰ የዘፈን በመሆኑ ግንጥል ጌጥ ነው። ነገር ግን እንኳንስ መንፈሳዊውን ስጦታ፥ ሥጋዊውን ስጦታ እንኳ እግዚአብሔር ሠርቶ ካስቀመጠው ውጪ መለወጥ አንችልም። ለምሳሌ፡-ሁለቱ ዓይኖቻችን ከፊት ከሚሆኑ አንዱን ከኋላ እናድርገው ማለት አይቻልም።

የዜማ መሣሪያዎች፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዜማ መሣሪያዎች መሠረታቸው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ከአገልግሎታቸው በተጨማሪም በምሳሌነታቸው
ሃይማኖታዊ ትርጉም አላቸው።
@And_Haymanot
በገና፡- ከጥንት ጀምሮ ለመንፈሳዊ አገልግሎት የዋለ የመጀመሪያው የዜማ መሣሪያ ነው። ዘፍ ፬፥፳፩። ሌዋውያን
ካህናት በበገና ይዘምሩ ነበር። ፩ኛ፡ዜና፡፲፭፥፳፩፣፪ኛ፡ዜና፡
፳፱፥፳፭-፳፯። ቅዱስ ዳዊት፡-“አሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት፤..... እግዚአብሔርን በበገና አመስግኑት፤” ብሏል። መዝ፡፴፪፥፬፣ መዝ፡፩፻፶፥፫። ቅዱስ ዳዊት በገና በሚደረድ ርበት ጊዜም በሽተኞች ይፈወሱ፥ከአጋንንት ቁራኝነትም ይላቀቁ ነበር። ፩ኛ፡ሳሙ፡፲፮፥፲፮። የበገና ሁለቱ ምሰሶዎች የብሉይ እና የአዲስ ምሳሌዎች ናቸው፤አሥሩ አውታር (ገመዶች) የአሠርቱ ትእዛዛት ምሳሌዎች ናቸው፤ብርኩማው (ሣጥኑ) ደግሞ የሲና ተራራ ምሳሌ ነው። በገና በሰማይም አለ፥ቅዱሳን መላእክት በገና
እየደረደሩ ይዘምሩለታል። ራዕ፡፭፥፰።
@And_Haymanot
መሰንቆ፡-እንደ በገና ከጥንት ጀምሮ የነበረ የዜማ መሣሪያ ነው። የሚውለውም ለእግዚአብሔር ምስጋና ነው። መዝ፡ ፩፻፶፥፫። መስንቆን እና ሌሎችንም መንፈሳዊ መሣሪያዎች
መዝፈኛ ያደረጉ ሰዎች በነቢያት አንደበት በእግዚአብሔር ተወቅሰዋል። ኢሳ፡፶፫፥፲፪፣ኢሳ፡፳፫፥፲፮። አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው እመቤታችንን በመሰንቆ መስሏታል። የመስንቆ ገመድ ያማረ
ድምፅ የሚሰጠው በዕጣን ሲታሽ ነው፤ዕጣን የጌታ ምሳሌ ነው፥የመሰንቆ ድምፅ ማማር ከዕጣኑ እንደሆነ ሁሉ የእመቤታችንም ክብሯ በዕጣን የተመሰለ ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷ ነው። መሰንቆ የተለያየ ብዙ ድምፅ እንደሚያወጣ ሁሉ የእመቤታችንም
ምስጋናዋ ብዙ ነው። እንኳን የአምላክ እናት፥አምላኩ እግዚአብሔር የሆነ ሕዝብ የተመሰገነ ነው። ቅዱስ አትናቴዎስ
ደግሞ በቅዳሴው፥ ሰማዕታት ገን ዘብ ያደረጓትን ሃይማኖት በመሰንቆ መስሏታል። በመሰንቆ ጫፍ ላይ የመስቀል ምልክት ስላለው የመስቀልም ምሳ ሌ ነው። የመሰንቆ መምቻ ደጋኑ
ደግሞ የኖኅ ቃል ኪዳን ምልክት የቀስተ ደመናው ምሳሌ ነው። ዘፍ፡፱፥፲፩-፳።
@And_Haymanot
ጸናጽል፡-“ጸንጸለ - መታ”ከሚለው ከግዕዝ ቃል የተገኘ ነው። ቅዱስ ዳዊት፡-“እግዚአብሔርን ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤”ብሏል። መዝ፡፩፻፶፥፩። በኦሪቱ ድንኳን በታቦቱ ፊት የተሾሙ ካህናት በጸናጽል ያመሰግኑ ነበር። ፩ኛ ፡
ዜና፡፲፭፥፲፮፣፪ኛ፡ዜና፡፳፱፥፳፭።ጸናጽል፡- ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግታ ላያት መሰላል ምሳሌ ነው። ሲጸነጸል ድምፅ የሚያሰሙት ሻኩራዎች፥ በመሰላሉ ላይ ሲወጡ
ሲወርዱ ለታዩት መላእክት ምሳሌዎች ናቸው። ሻኩራዎቹ አምስት ከሆኑ፥የአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት፤ስድስት ከሆኑ፥የስድስቱ ቃላተ ወንጌል ምሳሌዎች ናቸው። ሻኩራዎቹን የሚሸ ከሙት፥ጸናጽሉን መሰላል የሚያስመስሉት ሁለቱ ቀጫጭን ብረቶች ደግሞ የፍቅረ እግዚአብሔር እና የፍቅረ ቢጽ ምሳሌዎች ናቸው። ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል ለእመቤታችንም ምሳሌ ናት። መሰላሏ ሰማይና ምድርን እንዳገናኘች፥የሰማዩን አምላክ እና መሬታዊውን ሰው በተዋህዶ
ያገናኘች መሰላል እመቤታችን ናት።ምክንያቱም አምላክ በተዋህዶ ሰው የሆነው በእርሷ ነውና። ዘፍ፡፳፰፥፲።
@And_Haymanot
ከበሮ፡-ከጥንት ጀምሮ የነበረ መንፈሳዊ መሣሪያ ነው።እስራኤል
ከግብፅ የባርነት ቤት ወጥተው ዮርዳኖስን በደረቅ በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔርን በከበሮ አመስግነውታል። ዘጸ፡፲፭፥፳። ቅዱስ
ዳዊትም፡-“ዝማሬውን አንሡ፥ከበሮንም ስጡ፤.....በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት፤....በከበሮና በመዝሙር
አመስግኑት፤”ብሏል። መዝ፡፹፥፪፤፩፵፱፥፫፤፩፻፶፥፬። የከበሮ
ሰፊው ክፍል የመለኰት፥ጠባቡ ክፍል ደግሞ የትስብእት (የሰውነት) ምሳሌዎች ናቸው።ሰፊው ክፍል፡-የመለኰትን
ስፋትና ምልዓት ሲገልጥ፥ጠባቡ ክፍል ደግሞ የሥጋን ጠባብነት እና ውሱንነት ያስተምራል። ከበሮው የለበሰው ቀይ ጨርቅ፥ጌታ በዕለተ ዓርብ ለለበሰው ቀይ ከለሜዳ ምሳሌ ነው።ማቴ፡፳፯፥፳፰። በከበሮው አፎች ላይ የተሸፈኑትን ቆዳዎች፥ ዙሪያውን ወጥሮ የያዘው ጠፍር (የቆዳ ገመድ) ጌታ ሲገረፍ በአካሉ ላይ ለታዩት የሰንበር ምልክቶች ምሳሌ ነው። ከበሮውን አንሥተን
ለመምታት፥አንገታችን ላይ የምናንጠለጥልበት ገመድ፥ጌታ
ለተገረፈበት ጅራፍ ምሳሌ ነው። በተጨማሪም እጆቹንና አንገቱን
አስረው ጐትተውት ነበርና የዚያም ምሳሌ ነው።
@And_Haymanot
መቋሚያ፡-ለያዕቆብ በትር ምሳሌ ነው፤ያዕቆብ የመስቀል ምልክት ያለበትን በትሩን ከፊቱ አቁሞ ይሰግድ፥ይጸልይ ነበር። ዕብ፡፲፩፥፳፩።በትረ ያዕቆብም፥መቋሚያም የመስቀል ምሳሌዎች ናቸው።ጌታ መስቀሉን በት ከሻው እንደተሸከመ፥ መቋሚያውን
በትከሻችን ተሸክመን እንዘምራለን። መቋሚያውን የምንደገፈው፥ መስቀል ኃይላችን መሆኑን ለመግለጥ ነው። በቤተክርስቲያን የመዝሙር አገልግሎት፡-ወደ ግራ፥ወደ ቀኝ፣ወደ ፊት፥ ወደ ኋላ እየተደረገ በመቋምያ ይዘመማል። ይህም ጌታ መስቀል ተሸክሞ ለመንገላታቱ ምሳሌ ነው። ሙሴም ብዙ ተአምራት ያደረገባት
በትር የመስቀል ምሳሌ ናት። ሙሴ በበትሩ የኤርትራን ባሕር ከፍሎ ሕዝቡን እንዳሻገረ፥ ጌታም በመስቀሉ የሲኦልን ባሕር ከፍሎ ነፍሳትን ወደ ገነት አሻግሯል። ሙሴ በትሩን በትከሻው
ተሸክሞ እንደዘመረ፥መቋሚያውን በትከሻችን ተሸክመን እንዘምራለን። ዘጸ፡፲፬፤
@And_Haymanot
ዋሽንት፡-ከሸንበቆ የሚሠራ የትንፋሽ የዜማ መሣሪያ ነው፥ስድስት የድምፅ ማውጫ ቀዳዳዎች አሉት። ዳን፡፫፥፭-፲
፣፩ኛ፡ቆሮ፡፲፬፥፯።
🙏1
እውነት ስለሆነ
@And_Haymanot
እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ዋለ በአደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ
የሐሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው
ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድን ነው
አዝ--------------------------//
ከቃሉ እብለትን ባያኙበትም
ዝምታውን አይተው አላዘኑለትም
ባላወቁት መጠን ጠሉት ካለበደል
ጥፋቱ ምን ይሆን የሚያደርስ ከመስቀል(፪)
አዝ-----------------------//
የልቡን ትህትና ፍቅሩን ሳያስተውሉት
ቸሩ ጌታችንን አቻኩለው ሰቀሉት
እሩህሩሁን ጌታ ቸንክረው ሰቀሉት
ሞትን አስወግዶ ቢሰጣቸው ህይወት(፪)
አዝ-----------------------//
ስለቸርነቱ ስድብን ከፈሉት
ስለ ርህራሄው የእሾክ አክሊል ሰጡት
ሀሞት እና ከርቤ ሆምጣጤ ደባልቀው
መራራ አስጎነጩት ጨክኖ ልባቸው(፪)
አዝ------------------------//
ፈውስን ለሰጣቸው ልባቸውን ሞልተው
አሉት ወንበዴ ነው ስቀለው ስቀለው
ከእጁ በረከትን የተሻሙ ሁሉ
ይጮሁ ነበረ ይገደል እያሉ(፪)
@And_Haymanot
እንኳን አደረሳችሁ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
🙏1
ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ ዮሐ 19:30
https://tttttt.me/And_Haymanot/438
እንኳን አደረሳችሁ