የሲዳማ ህዝብ ከዓመታት በፊት ያቀረበዉ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ዘግይቶም ቢሆን ምላሽ ማግኘት በመጀመሩ መላው #የሲዳማ ብሔር #እንዲረጋጋ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ #ሲአን ጠየቀ። የንቅናቄው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ደስላኝ ሜሳ፣ «ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ተቀብሎ ህዝበ ውሳኔ
ለማድረግ መዘጋጀቱን አረጋግጧል።» ብለዋል።
በዚሕም ምክንያት የሲዳማ ሕዝብ የህዝበ ውሳኔውን ሂደት እንዲጠባበቅ ንቅናቄው ጥሪ ማስተላለፉን አቶ ደሳላኝ ለሐዋሳዉ ዘጋቢያችን ለሸዋንግዛዉ ወጋየሁ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አመልከተዋል። ይሁንና አቶ ደሳለኝ እንደሚሉት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ ዉሳኔዉ ሊደረግ ከሚገባዉን ቀን #አዘግይቷል ብሎ ንቅንቄያቸዉ እንደሚያምን ጠቅሰዉ ለዚሕም ቦርዱ፣ ሕዝቡን #ይቅርታ_መጠየቅ_ይገባዋል_ብለዋል።
በሲዳማ ዞን የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ( ሲአን ) ፣ የሲዳማ ሀድቾ ዴሞክራሲያዊ ደርጅት ( ሲሀዴድ ) እና የሲዳማ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ሲብዴፓ )፣ የሲዳማ ህዝብ በክልል ለመደራጀት የሚያስችለው የህዝበ ውሳኔ የሚደረግበትን ቀን መንግሥት በአምስት ቀናት ዉስጥ ይፋ እንዲያድርግ ባለፈዉ ሳምንት መጀመሪያ ጠይቀዉ ነበር። የተቀሩት ሁለቱ ፓርቲዎች አስከ አሁን ሥለ ጉዳዩ በይፋ ያሉት ነገር የለም።
ምንጭ:- DW
@YeneTube @FikerAssefa