YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የሲዳማ ብሔር #የሀገር ሽማግሌዎች በሰኔ 8 2010 ዓ.ም በሀዋሳ እና አከባቢው በተከሰተው #ግጭት ሕይወታቸውን ያጡ #የወላይታ ብሔር ተወላጆች ቤተሰብ ላይ ለቅሶ በመድረስ አጽናንተዋል፡፡

ረጅም ዘመናትን የዘለቀው የሁለቱ ህዝቦች ትስስር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የሟች ቤተሰቦች ገልጸዋል፡፡
የሲዳማ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች በሐዋሳና አከባቢዋ በተፈጠረው ግጭት ልጆቻቸውንና ዘመዶቻቸውን በሞት ለተለዩ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ በደረሱበት ወቅት ከሟች ቤተሰቦች አንዳንዶቹ እንደተገለጹት ሁለቱ ህዝቦች ለረጅም ዘመናት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተሳስረው፣ ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው፡፡
በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር የሚቀሰቅሱ አካላት ሊገስጹ ይገባል ብለዋል፡፡

በሰኔ 8 2010 ዓ.ም በሀዋሳ እና አከባቢው በተከሰተው ግጭት የሰው ህይወት በመጥፋቱ እጅግ ማዘናቸውን የሟች ቤተሰቦች ገልፀው እርቀ ሰላም እንዲወርድ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላት፣ አስታራቂ ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እንደተናገሩት የወላይታ እና የሲዳማ ህዝቦች ለዘመናት ተከባብረውና ተቻችለው አብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው፡፡
የሁለቱ ህዝቦች ታሪካዊ ትስስር በአንድ መድረክ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በሁለቱ ህዝቦች መካከል በተከሰተው ግጭት ክቡር የሆነው የሰው ህይወት ከመጥፋቱም በላይ በሰው አካል ላይ ጉዳት ያደረሰ፣ በርካታ ንብረት የወደመበት እና በርካታ ሰው የተፈናቀለበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ይህ ጥፋት ሁለቱንም ህዝቦች የማይወክል ጥቂት ቡድኖችና ግለሰቦች የራሳቸውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት ሆን ብለው ግጭቱ የብሔር ይዘት እንዲኖረውና የህዝቦቹ ትስስር እንዲሻክር ያደረጉት ነው ብለዋል፡፡

የሲዳማ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት በወላይታ ሶዶ በመገኘት ወገኖቻቸውን በሞት ላሰጡ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ ለመድረስና ለማጽናናት የመጡበት ዋናው ዓላማ የሁለቱ ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነታቸውንና አብሮነታቸውን ለማደስ ነው፡፡

የወላይታ እና የሲዳማ ህዝቦች ረጅም ዘመን የቆየው አንድነትና አብሮነት ቀጣይነት አንዲኖረው ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የሀገር ሽማግሌዎቹ አስታውቀዋል፡፡

የሁለቱ ህዝቦች አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ የሟች ቤተሰቦችን የማጽናናት ሥራ በባህላዊ የዕርቅ ስርዓት ተከናውኗል፡፡

በተመሳሳይ በነገው ዕለት ታህሳስ 25 ቀን 2011 ዓ.ም የወላይታ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ሐዋሳ በማቅናት በሲዳማ ብሔር በኩል በግጭቱ ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ በመድረስ እንደሚያጽናኑ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ:- የወላይታ ዞን መንግስት ኮምንኬሽን
@YeneTube @Fikerassefa