YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ጋምቤላ
የጋምቤላ ክልል የፌደራሉ መንግስት በክልሉ የተፈጠረውን አለመረጋጋትና ግጭት ለመግታት እገዛ እንዲደረግለት #ጠየቀ

በክልሉ መንግስት ላይ ያመፁ #ወጣቶች ከፀጥታ ሀይሎች ጋር ተጋጭተው የመርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

📌ክልሉ አሁንም ወደ ሙሉ መረጋጋት አልተመለሰም ።
©wazema
@Yenetube @Mycase27
#update ቡራዩ

#በቡራዩ ተከስቶ ከነበረው ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት 630 ወጣቶች 322 #ተፈቱ

ከዚህ ቀደም በቡረዩ ተከስቶ ከነበረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት 630 ወጣቶች ከተከሰተው ችግር ጋር ግንኙነት ያሌላቸው መሆኑ በምርመራ የተረጋገጠ 322 ወጣቶች ስልጠና ወስደው ተለቀቁ፡፡

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት የምርመራ አስተባባሪ ኮማንደር በቃና ሚደግሳ እንደገለጹት፣ 322 #ወጣቶች በቡራዩና በአዳማ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ነው የተለቀቁት፡፡

የተቀሩት 308 ለተፈጸመው #ወንጀል ተጠርጣሪ በመሆናቸው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ መሆናቸውን ኮማንደር #በቃና ገልጸዋል፡፡

በቡራዩ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር በንብረትና በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽ ቢሮ
@yenetube @mycase27
ሰበር ዜና ‼️ የአርበኞች ግንቦት 7 የባሕር ዳር ውይይት #ተቃውሞ እንደገጠመው ተገለጸ

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በባሕር ዳር ከተማ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የጠራው ሕዝባዊ ውይይት ተቃውሞ እንደገጠመው ተገለጸ፡፡
ንቅናቄው ለውይይቱ ተሳታፊዎችን በማስታወቂያና በመግቢያ ወረቀት መጋበዙን የውይይት ኮሚቴው አባል አቶ ዓለሙ ፈጠነ ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን #ወጣቶች ወደ አዳራሽ በመግባት የሰቀልናቸውን #ጽሑፎች አውርደውብናል፣ የራሳቸውን ጽሑፍ በመስቀልም አውከውናል ብለዋል አቶ ዓለሙ፡፡

ተቃውሞ እያቀረቡ የሚገኙት ወጣቶች በበኩላቸው ግንቦት 7 የአማራን ብሔርተኝት የሚያዳክም፣ በኢትዮጵያዊነት ስም አማራን እንዳይደራጅ የሚያሴር፣ ሀገሪቱ በብሔር ፖለቲካ መወጠሯን እያወቀ አማራ ብቻ ስለኢትዮጵያ እንዲያቀነቅን የሚወተውት ነው እያሉ ነው ፡፡

ምንጭ፡- አማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት
@YeneTube @FikerAssefa