YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በቡራዩ ከተማና አካባቢዋ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የአካል ጉዳት፣ ዘረፋና ንብረት እንዲወድም ከመስከረም 1 ቀን 2011 ጀምሮ በመቀስቀስ እና ገንዘብ በማከፋፈል ግጭቱ እንዲነሳ በማድረግ የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦችን የፌደራል ፖሊስ ፍረድ ቤት አቀረበ።

በፌደራልና በኦሮሚያ ፖሊስ ለሁለት ተከፋፍሎ የሚከናወነው ምርመራ የቀጠለ ሲሆን፥ ትናንት ከሰዓት በኋላ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምደብ ችሎት 1ኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት ስድስቱ ተጠርጣሪዎች ቀርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀን ጊዜ ጠይቆባቸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ሳምሶን ጥላሁን፣ ዓለሙ ዋቅቶላ፣ ቡልቻ ታደሰ፣ ሀሺም አህሚድ፣ ሽፈራው ኢራና እና ኢሉ ዳንኤል ሲሆኑ፥ ነዋሪነታቸው በቡራዩ፣ ገፈርሳና ከታ አካባቢ ነው።

መርማሪ ፖሊስ ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት በቡራዩና አካባቢዋ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት፣ ንብረት መውደም እና ዘረፋ የተጠረጠሩ ናቸው በማለት መነሻ መረጃ እንዳገኘባቸው አስረድቷል።

ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ድርጊቱን አልፈፀምንም ሲሉ አስረድተዋል።

ክርክራቸውን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራውን በ14 ቀናት ውስጥ አጠናቆ እንዲቀረብ በማዘዝ ለመስከረም 24 ቀን 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው ካሉ ግለሰቦች መካከል 45 ተጠርጣሪዎቹ ትናንት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ዛሬ ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
©fbc
@yenetube @mycase27
#update ቡራዩ

#በቡራዩ ተከስቶ ከነበረው ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት 630 ወጣቶች 322 #ተፈቱ

ከዚህ ቀደም በቡረዩ ተከስቶ ከነበረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት 630 ወጣቶች ከተከሰተው ችግር ጋር ግንኙነት ያሌላቸው መሆኑ በምርመራ የተረጋገጠ 322 ወጣቶች ስልጠና ወስደው ተለቀቁ፡፡

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት የምርመራ አስተባባሪ ኮማንደር በቃና ሚደግሳ እንደገለጹት፣ 322 #ወጣቶች በቡራዩና በአዳማ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ነው የተለቀቁት፡፡

የተቀሩት 308 ለተፈጸመው #ወንጀል ተጠርጣሪ በመሆናቸው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ መሆናቸውን ኮማንደር #በቃና ገልጸዋል፡፡

በቡራዩ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር በንብረትና በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽ ቢሮ
@yenetube @mycase27