ሰበር ዜና ‼️ የአርበኞች ግንቦት 7 የባሕር ዳር ውይይት #ተቃውሞ እንደገጠመው ተገለጸ
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በባሕር ዳር ከተማ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የጠራው ሕዝባዊ ውይይት ተቃውሞ እንደገጠመው ተገለጸ፡፡
ንቅናቄው ለውይይቱ ተሳታፊዎችን በማስታወቂያና በመግቢያ ወረቀት መጋበዙን የውይይት ኮሚቴው አባል አቶ ዓለሙ ፈጠነ ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን #ወጣቶች ወደ አዳራሽ በመግባት የሰቀልናቸውን #ጽሑፎች አውርደውብናል፣ የራሳቸውን ጽሑፍ በመስቀልም አውከውናል ብለዋል አቶ ዓለሙ፡፡
ተቃውሞ እያቀረቡ የሚገኙት ወጣቶች በበኩላቸው ግንቦት 7 የአማራን ብሔርተኝት የሚያዳክም፣ በኢትዮጵያዊነት ስም አማራን እንዳይደራጅ የሚያሴር፣ ሀገሪቱ በብሔር ፖለቲካ መወጠሯን እያወቀ አማራ ብቻ ስለኢትዮጵያ እንዲያቀነቅን የሚወተውት ነው እያሉ ነው ፡፡
ምንጭ፡- አማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት
@YeneTube @FikerAssefa