YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በ#ሐረር ከተማ እየተስተዋለ ያለው የመጠጥ ውሃ እጦት #የህግ የበላይነት #ባለመከበሩ ምክንያት መሆኑን የሐረሪ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወልደ አብዶሽ ገለጹ፡፡

ሀላፊው በሰጡት መግለጫ በኤረር ወረዳ ቂሌ አካባቢ ላይ የሚገኘው ውሃ ማሰራጫ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መቋረጡን የገለጹ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች #ከ2 አመት በፊት የተከፈለን ካሳ #በቂ አይደለም በማለት አገልግሎቱን በማቋረጣቸው ነው።

በሀሮማያ የሚገኘው የውሃ ማሰራጫም ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል። ከመቋረጡ ቀደም ብሎ ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚውል 10 #ሚሊየን ብር በ5 ቀናት ውስጥ ይከፈለን የሚል ደብዳቤ በሀሮማያ ኢፈባቴ ቀበሌ 01 ሊቀመንበር በኩል እንደደረሳቸው ሀላፊው ገልጸዋል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
የጤና ሚኒስቴር በድንገተኛ አደጋዎች ላይ ብቻ ህክምና የሚሰጥ ማዕከል በአዲስ አበባ ከተማ ለማስገንባት እቴቴ ከተባለ የኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ተፈራረመ። ማዕከሉ ከ751 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባ ሲሆን ከ550 በላይ አልጋዎች ይኖሩታል።

#በአለርት ሆስፒታል ውስጥ የሚገነባው ማዕከል በሶስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን በቀን #ከ2 እስከ #5 ሺህ ተገልጋዮችን ያስተናግዳል።

@YeneTube @FikerAssefa