YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በ#ሐረር ከተማ እየተስተዋለ ያለው የመጠጥ ውሃ እጦት #የህግ የበላይነት #ባለመከበሩ ምክንያት መሆኑን የሐረሪ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወልደ አብዶሽ ገለጹ፡፡

ሀላፊው በሰጡት መግለጫ በኤረር ወረዳ ቂሌ አካባቢ ላይ የሚገኘው ውሃ ማሰራጫ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መቋረጡን የገለጹ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች #ከ2 አመት በፊት የተከፈለን ካሳ #በቂ አይደለም በማለት አገልግሎቱን በማቋረጣቸው ነው።

በሀሮማያ የሚገኘው የውሃ ማሰራጫም ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል። ከመቋረጡ ቀደም ብሎ ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚውል 10 #ሚሊየን ብር በ5 ቀናት ውስጥ ይከፈለን የሚል ደብዳቤ በሀሮማያ ኢፈባቴ ቀበሌ 01 ሊቀመንበር በኩል እንደደረሳቸው ሀላፊው ገልጸዋል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa