ገርበ ጉራቻ አካባቢ ከታገቱት ተማሪዎች ውስጥ 16ቱ ተለቀቁ፤ በታጋቾች ላይ ጾታዊ ጥቃትና ድብደባ ተፈጽሟል ተብሏል‼️
በ #ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን #ገርበ_ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች ከታገቱ ከ167 በላይ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ባለፉት ቀናት 16ቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የማስለቀቂያ ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸው ተገለጸ።
በታጋቾቹ ላይ ግርፋት፣ ድብደባ እንዲሁም ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙን የተማሪዎቹን እገታ ከቤተሰብ ጋር ሆነው በቅርበት እየተከታተሉ ያሉ ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል።
አንድ የታጋች ተማሪ ቤተሰብ “ታጣቂዎቹ በተማሪዎቹ ፊት ሁለት ሰዎችን መግደላቸውን እያለቀሱ ነግረውናል” ብለዋል።
ከ30 በላይ ይሆናሉ የተባሉት ታጣቂዎቹ ‘ፀጉራቸውን የተሰሩ፣ የሲቪል ልብስ የለበሱ እና የተማሩ’ መሆናቸውን ተማሪዎቹ አመልክተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa

😭42👍19