YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አምሓራ ክልል ‼️

በአማሓራ ክልል #ኦሮሞ_ብሔረሰብ አስተዳደርና ሰሜን #ሸዋ ዞኖች በተከሰተ ግጭት የሰው ሕይወት በመጥፋቱ ማዘናቸውን ዶ/ር አምባቸው መኮንን ገለፁ

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች በተከሰተ ግጭት በሰው ሕይወትና ንብረት ጉዳት መድረሱ እንዳሳዘናቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር አምባቸው መኮንን ተናገሩ።

በክልሉ በሁለቱ ዞኖች አንዳንድ ወረዳዎች በተነሳ ግጭት የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ተፈጽሟል።

በጠፋው የሰው ሕይወት እና በደረሰው የንብረት ውድመት የክልሉ መንግሥት ማዘኑን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለፁት።

በክልሉ #የሕግ የበላይነትን፣ ሰላምን እና ልማትን ለማረጋገጥ #እየተሠራ ባለበት ወቅት #ባልተጠበቀ መንገድ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ አሳዛኝ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዶክተር አምባቸው በክልሉ መንግሥትና በራሳቸው ስም #ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል።

የግጭቱን ምክንያት እና ወንጀል የፈፀሙ #ግለሰቦችን በተመለከተ በቀጣይ በማጣራት ለሕዝቡ ይፋ እንደሚደረግ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

የአካባቢውን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በጋራ #እየሠሩ መሆኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በቀጣይም ከፌደራል እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

ኅብረተሰቡም በማኅበራዊ ሚዲያ ተጋነው በሚሰራጩ #አሉባልታዎች መረበሽ እንደሌለበት ርዕሰ መስተዳደሩ አሳስበዋል።

የኅብረተሰቡን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ሕዝቡ ከመንግሥት ጎን እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
#ኦሮሚያ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት የወባ በሽታ እየተባባሰ መሆኑና የጤና አገልግሎቶች መስተጓጓላቸው ተዘገበ

ለማ ተፈራ የተባሉ የምዕራብ ኦሮሚያ አርሶ አደር በአንድ ወር ውስጥ አራት ልጆቻቸውን በወባ በሽታ በሞት መነጠቃቸውን ገልጸው እየተካሄደ ያለው ግጭት ባይኖር ኖሮ አደጋውን መከላከል ይቻላል ብለው እንደሚያምኑ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ ተናግረዋል።

አርሶ አደሩ "በግጭት ምክንያት መንደራችን ውስጥ የወባ መድሃኒት እና ህክምና እንዳልነበርም" ገልጸዋል።

#ኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትና በመንግስት ኃይሎች መካከል በመካሄደ ላይ የሚገኘው ግጭት የጤና አገልግሎቶችን ማቋረጡን በመቀጠሉ ቀውሱ እየተባባሰ መምጣቱን የጤና ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።

የኦሮሚያ ሀኪሞች ማህበር ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር የሆኑት ገመቹ ቢፍቱ "በክልሉ ባለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት የተዘጋጀ ጸረ-ወባ መድሃኒት አቅርቦት ተስተጓጉሏል" ብለዋል።

በአካባቢው የሚገኙ ሐኪሞች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ሪፖርት አድርገዋል። በምዕራብ ወለጋ የሚገኘው የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል ዳይሬክተር ለገሰ ቡልቻ "ከዚህ ቀደም ካለው በተለየ መልኩ አሁንም በድርቅ ወቅት በርካታ ሰዎች በወባ እየተያዙ ነው" ብለዋል። ዳይሬክተሩ በፈረንጆቹ 2023-2024 በሆስፒታሉ ከታከሙ 26,000 ታካሚዎች ውስጥ 70% የሚሆኑት በወባ በሽታ የተያዙ ናቸው ነው ያሉት።

በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥ በሽታው ወደ አዳዲስ አካባቢዎች እንዲሰራጭ ሁኔታዎችን በመፍጠር ቀውሱን እያባባሰው ነው ሲሉም ተናግረዋል።

Via AS
@Yenetube @Fikerassefa
👍23😭92