በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው ወጣቱ ሚስጥሩ ሲሳይ ድረሱልኝ ይላል‼️
#Share_This_if_You_Care
#ሚስጥሩ_ሲሳይ በቴፒ ከተማ ነዋሪ ነው፡፡ ባለፈው ወጣቶችን ለአመፅና ሁከት አነሳስተሃል በሚል ለእስራት ተዳርጎ ነበር፡፡ ከእስር ከተፈታ በኋላ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ የነበረ ሲሆን ወደሚኖርባት ቴፒ ከተማ እየተጏዘ ሳለ #ጅማ ከተማ ላይ ካረፈበት ሆቴል በደቡብ #ልዩ_ፖሊስ ታፍኖ ተወስዷል፡፡ ከዚያን ግዜ ጀምሮ በማሻ ማረሚያ ቤት ታስሮ ይገኛል፡፡ በልዩ ፖሊስ አባላት በደረሰበት ተደጋጋሚ ድብደባ ምክንያት አንድ ኩላሊቱ ከጥቅም ውጪ ሆኗል፡፡ "እዚሁ ትበሰብሳታለህ፣ ምንም አታመጣም!!" እያሉ እስካሁን ድረስ ያለ ምንም የክስ ማስረጃ በእስርና በድብደባ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ የሚመለከታችሁ ወገኖች በሙሉ ስለ #ፍትህ ብላችሁ ለሚስጥሩ ሲሳይ ልትደርሱለት ይገባል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa

በ #ጅማ ዞን በድረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ
በ #ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ ሚርጋኖ በሶ ቀበሌ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ በጣለው ከባድ ዝናብ በድረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።
አደጋው እሁድ ሚያዚያ 26 ቀን 2017 በሚርጋኖ ባሶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ገሬ ኦጎደማ በተባለ ቦታ ላይ ለሌት 6 ሰዓት በጣለው ዝናብ መከሰቱን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ከባድ ዝናብ እና ኃይለኛ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በተለያዩ ንብረቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የሸቤ ሶምቦ ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤቱ አክሎ ገልጿል።
የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ዩሱፍ አባ ማጫ እና የሚርጋኖ በሶ ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ምስጋና ለታ ተጎጂዎችን በመጎብኘት ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል ተብሏል።
ባሳለፍነው አመት ሀምሌ 15 ቀን በ #ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል #ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ250 በላይ ሰዎች ህይወት መለፉም አይዘነጋም።
በተመሳሳይ ወቅት በ #ሲዳማ ክልል በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ 11 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሽኮ ዞንም የአራት ሶዎች ህይወት በመሬት መንሸራተት አደጋ ማለፉም ይታወሳል።
@Yenetube @Fikerassefa

👍12😭6❤4