YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቤኒሻንጉል #ጉሙዝና በምዕራብ #ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን #ግጭት ለማስቀረት የሚካሄዱ የሰላም ጉባኤዎች ቀጥለዋል። የሰላም ጉባኤው በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ቀሽማንዶ በተባለ ቦታ ሰሞኑን ተካሂዷል።

የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ባለመው በዚህ ስብሰባም ከምዕራብ ወለጋ ቤጊ እና ቆንዳላ ወረዳዎች፤ ከአሶሳ ዞን ደግሞ ባምባሲ እና የማኦ-ኮሞ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን ከአሶሳ ዘጋቢያችን ነጋሳ ደሳለኝ ያላከልን ዘገባ ያስረዳል።

ምንጭ:-Dw
@YeneTube @FikerAssefa