YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የሰኔ_16ቱ የቦንብ ጥቃት⬇️

በሰኔ 16ቱ የመስቀል አደባባዩ ላይ የተወረወረ አይነት ተመሳሳይ #ቦምብ በተጠርጣሪ መኖሪያ ቤት ውስጥ ማግኘቱን መርማሪ ፖሊስ አስታወቀ።

መርማሪ ፖሊስ ዛሬ በተረኛ የጊዜ ቀጠሮን በሚመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት በቀረቡ ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ የደረሰበትን የምርመራ ደረጃ ለፍርድ ቤት ባስረዳበት ወቅት ተመሳሳይ ቦምብ ማግኘቱን አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም መርማሪ ፖሊስ ከሰኔ 16ቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ድጋፍ ሰልፍ ላይ የከቦምብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ተጠርጥራ በአማኒኤል ሆስፒታል ከአይምሮ ህመም በህክምና ላይ የምትገኘውን የህይወት ገዳን ምርመራን ማቋረጡንም በዛሬው ችሎት አብራርቷል።

በችሎቱ በቀዳሚነት የተጠርጣሪ በየነ ቡላና የአብዲሳ መገርሳን የተደረሰውን የምርመራ ደረጃ አዳምጧል።

መርማሪ ፖሊስም በርካታ የምርመራ ስራዎችን ማከናወኑን በመጠቆም ተጨማሪ የኤፍ ቢ አይ የቴክኒክ ምርመራ ውጤትን እና መሰል ማስረጃዎቸን ለመቀበል ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

የተጠርጣሪ አብዲሳ መገርሳ ጠበቃ በበኩላቸው የተጠረጠረበት ጉዳይ ስለፍንዳታው ለግብረ አበሮቹ ሪፖርት አድርገሃል ተብሎ ነው።

ረጅም ጊዜ ምርመራው የሚወስድ አይደለም ጉዳዩም ዋስትና የሚያስከለከል ባለመሆኑ በዋስ ሊወጣ ይገባል ሲሉ የፖሊስን ተጨማሪ ጊዜ ተቃውመዋል።

ተጠርጣሪ በየነ ቡላ በበኩሉ እኔ በፍቼ ነው የተያዝኩት ሆን ተብሎ እኔን ለማጥቃት የሚደረግ ድርጊት ነው በማለት ከዘርና ከፖለቲካ ጋር አያይዘው ላቀረቡት አስተያየት ፍርድ ቤቱ በችሎት ህጋዊ ድርጅትን መዝለፍ አይፈቀድምላይ ሲል ንግግራቸውን አስቁማል።

ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎች የተገኘ ተጨባጭ ማስረጃ እንዳለ መርማሪ ፖሊስ እንዲያበራራ ጠይቋል።

መርማሪ ፖሊስም ከፍተኛ አመራሮች የሚገኙበት የድጋፍ ሰልፍ በመሆኑ በዋናነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ለመግደል እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሰልጣኖች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የታቀደና የተሞከረበት ይህ ድርጊትን በ160 ንጹሃን ዜጎች ላይ የአካል ጉዳትና የሁለት ሰው ሞት እና ቤተሰቦቻቸውን ማሰብ ያሰፈልጋል ብሏል።

ድረስ ይህ የወንጀል ድርጊት ከላይኛው አመራር እስከ ታቸኛው አመራር ተሳትፎ ያለበት መሆኑን ፖሊስ ጠቅሷል።

በየነ ቡላን በተመለከተ ከሌሎች ከተጠረጠሩ ግብረ አበሮች ጋር በመሆን ቦምቡን እንዴት እንደሚያፈነዱ በመነጋገር በማመቻቸት ቦምቡ
እንዲፈነዳ ማስደረጉን የሚጠቁም ማስረጃ እንዳለው ገልጿል።

ሁለተኛ ተጠርጣሪ አብዲሳ መገርሳም ከቦምብ ፍንዳታው በኋላ ፍንዳታው ጉዳት ማን ላይ እንደደረሰና የቦምቡን ጉዳት ሁኔታ ለግብረ አበሮቹ ሪፖርት ማደረጉን የሚያመላከት ማስረጃ አለኝ ሲል ዋስትናቸውንም ተቃውሟል።

የሁለቱንም ጉዳይ የተከታተለው ፍርድ ቤቱ ምርመራው ውስብስብና የወንጀል ድርጊቱ ከባድ ጊዜ የሚጠየቅ መሆኑን በመጥቀስ ለመርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለመጨረሻ እንዲቀርብ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜን ፈቅዷል።

በሁለተኛ ደረጃ ችሎቱ የተመለከተው የእነ አብዲሳ ቀነኔ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማና ባህሩ ቶላን ጉዳይ ሲሆን፥ መርማሪ ፖሊስ ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ጋር አብራ ምርመራ ሲከናወንባት የነበረችው ህይወት ገዳ ጉዳይን ማቋረጡን አስታውቋል።

በተመሳሳይ የምራመራ ስራውን ማከናወኑን በመግለጽ ከኤፍ ቢ አይ የቴክኒክ ምርመራን እና መስል ማስረጃን ለማቀረብ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የአብዲሳ ቀነኔ ጠበቃ በበኩላቸው አብዲሳ የተያዘው ሰው ለመጠየቅ አቤት ሆስፒታል በሄደበት ጊዜ እንጂ ድርጊቱን አልፈፀመም ፖሊስ የድርጊቱ መፈጸምን የሚያሰረዳ ማስረጃ መዝገቡን አቅርቦ ሊያሳይ ይገባል ፖሊስ ምስክር እንዲሆነን የሚያቀርበው ጥያቄ ተገቢ አይደለም ሲሉ በዋስ ሊወጣ ይገባል ሲሉ የፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ ጥያቄን ተቃውመዋል።

በተመሳሳይ ሌሎች ተጠርጣሪዎችም የተጨማሪ ጊዜን በመቃወም ከድርጊቱ ጋር ግንኙነት የለንም በማለት ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም የተጠርጣሪዎቹን የተጠረጠሩበት ድርጊት በማስረጃ መረጋገጡን ፖሊስ እንዲያሰረዳ በጠየቀው መሰረት ፖሊስ ጌቱ ግርማ
መኖሪያ ቤት ውስጥ በሰኔ 16 የመስቀል አደባባዩ የቦምብ ጥቃት ለማድረስ የተወረወረ አይነት ተመሳሳይ ቦምብ መገኘቱን ገልጿል።

አብዲሳ ቀነኔ ባለው የህክምና ሙያ ተጠቅሞ ቦምቡን አፈንድቶ በራሱ ላይም ጉዳት የደረሰበትን ለማስመለጥ አቤት ሆስፒታል ሄዶ በጀርባ በኩል ለማስመለጥ ነርሶችን ሲያግባባ እንደነበርና ለዚሀም ማስረጃ እንዳለው ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሮዎቹ ምንቡን ለማፈንዳት እንዴት፣ የትና በምን ሁኔታ የሚለውን ጉዳይ አስቀድመው መረጃ የተለዋወጡበትን ሆነ ከፈነዳ በኋላ
የተለዋወጡበት መረጃም ሆነ ሌሎች ማስረጃዎች አሉኝ ሲል አብራርቷል።

ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ምርመራው ውስብስብና የወንጀል ድርጊቱ ከባድ ጊዜ የሚጠየቅ መሆኑን በመጥቀስ ለመርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቀርብ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜን ፈቅዷል።

የምርመራ መዝገቡን ከሁለት ቀን በፊት አቀርቦ እንዲያሳይ አዟል።
©FANA
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሠልፍ #አምስት ሰዎች ሞቱ

ዛሬ ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ #ብሔር ተኮር ጥቃቶችን በመቃወም ሠልፍ ከወጡ ሰዎች መካከል አምስት ሰዎች መሞታቸውንና ሌሎችም መቁሰላቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ለመንግሥት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹የተወሰኑ በቡድን ተደራጅተው የፀጥታ ኃይሎችን መሣሪያ ለመቀማት ሞክረዋል፡፡ አከፖሊስ ጋር ግብግብ የገጠሙትን በአካባቢው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች የማያዳግም ዕርምጃ ወስደው የተወሰኑ ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው ታውቋል፤›› ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሠልፉ ውስጥ #ቦምብ ይዘው የወጡ ግለሰቦች መገኘታቸውንና በሰላማዊ ሠልፉ ተሳታፊዎች ጥቆማ መያዛቸውን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡

በቡራዩና አካባቢውም ሆነ በአዲስ አበባ የተከሰቱትን ግጭቶች አስመልክተው የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ ግርግሩ ሆን ተብሎ የተጀመረውን ለውጥ እንዳይሳካ ለማድረግ ሰፊ የሆነ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የተካሄደ ነበር ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ገንዘብ ተሰጥቷቸው የተሰማሩ ግለሰቦች ብሔር ተኮር ስድብ የታከለበት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር ሲሉም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም ተዘርፈው የተቀመጡ ንብረቶችን ፖሊስ ከጫካ እየሰበሰበ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በቡራዩና በአካባቢው በተፈጸመ ጥቃት የተጠረጠሩ ከ300 በላይ ግለሰቦች ተይዘዋል ብለዋል፡፡

©ሪፓርተር
@YeneTube @Fikerassefa
#update ሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ⤵️⤵️


ፖሊስ #በተስፋዬ ኡርጌ ቢሮ አገኘሁት ያለውን ቦምብ ከሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ቅሪት ጋር ለማመሳከር ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠየቀ።

በሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው የብሄራዊ መረጃ ደህንነት መምሪያ አዛዢ ተስፋዬ ኡርጌ ፖሊስ በቢሮው አገኘሁት ያለወን #ቦምብ መስቀል አደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል ጋር ለማመሳከር ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የጠየቀበትን ምክንያትና የተጠርጣሪውን አስተያየት አዳምጧል።

መርማሪ ፖሊስ ምርመራችንን አጠናቀን ለፌዴራል አቃቢ ህግ ያስረከብን ቢሆንም አቃቢ ህግ መስከረም 15 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት አቶ #ተስፋኤ ኡርጌ ቢሮ ውስጥ ያገኘነውን ቦንብ መስቀል አደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል ጋር በቴክኒክ ለማመሳከር ተጨማሪ ማስረጃ ይቅረብልኝ ማለቱን ተከትሎ ለፌዴራል ፖሊስ ፈንጅ አምካኝ ኦፕሬሽን ዲቪዢን ደብዳቤ ልከናል ሲል አብራርቷል።

ይህንን የቴክኒክ ምርመራ ምላሽ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ብሏል።

ጉዳዩ ያለ አግባብ እየተራዘመ መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በበኩላቸው ፍርድቤቱ አጭር ቀጠሮ ሰጥቶ ለመጨረሻ ትዛዝ ይስጥልኝ ሲሉ #ጠይቀዋል

ፍርድቤቱም በተጠየቀው የጊዜ ገደብ የቴክኒክ ምርመራው ለምን አልተጠናቀቀም የሚል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፥ ፖሊስም ደብዳቤ ልከን ምላሽ ስላልተሰጠ እየጠበቅን ነው ሲል አብራርቷል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድቤት ተረኛ ወንጀል ችሎትም ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ የቴክኒክ ምርመራውን ይዞ እንዲቀርብ ለተጨማሪ ስምንት ቀን ቀጠሮ በመስጠት #ለጥቅምት አራት ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ምንጭ ፦ FBC
@yenetube @mycase27
#update news

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ #ቦምብ በማፈንዳት የተጠረጠሩት ግለሰቦች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት #ቀርበዋል፡፡

ፍርድ ቤት ቀረቡት አንደኛ ተከሳሽ #ጌቱ ግርማ ፣ሁለተኛ #ብርሀኑ ጃፋር፣ ሶስተኛ #ጥላሁን ጌታቸው ፣ አራተኛ #ብህሩ ቶላ እና አምስተኛ #ደሳለኝ ተስፋየ ናቸው፡፡

ከአንደኛ እሰከ አራተኛ ያሉት ተከሳሾች በፀረ ሽበር አዋጅ 652/2001 አንቀጽ 3/1 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀት ክስ የመሰረተባቸው #መሆኑ የታወሳል፡፡

ሆኖም ግን ጥቅምት 14 2011 ዓ.ም በነበረ ቀጠሮ ክሱ ላይ ወንጀል #የተፈፀመበት ጊዜና ቦታ ግልፅ አለመሆኑ፣ ወንጅሉን አለመፈፀማቸውን እና መንግስት ያመጣውን ለውጥ ተቀባይ እንጅ ተቃዋሚ አለመሆናቸውን በመቃውሚያ ሀሳብ ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ #ተከሳሾች ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ ሀሳብ መልስ ለመስጠት ዛሬ ችሎት የተገኘ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ #ለህዳር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታውቋል፡፡
ምንጭ ፦ኤፍ ቢ ሲ
@yenetube @mycase27