YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሠልፍ #አምስት ሰዎች ሞቱ

ዛሬ ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ #ብሔር ተኮር ጥቃቶችን በመቃወም ሠልፍ ከወጡ ሰዎች መካከል አምስት ሰዎች መሞታቸውንና ሌሎችም መቁሰላቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ለመንግሥት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹የተወሰኑ በቡድን ተደራጅተው የፀጥታ ኃይሎችን መሣሪያ ለመቀማት ሞክረዋል፡፡ አከፖሊስ ጋር ግብግብ የገጠሙትን በአካባቢው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች የማያዳግም ዕርምጃ ወስደው የተወሰኑ ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው ታውቋል፤›› ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሠልፉ ውስጥ #ቦምብ ይዘው የወጡ ግለሰቦች መገኘታቸውንና በሰላማዊ ሠልፉ ተሳታፊዎች ጥቆማ መያዛቸውን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡

በቡራዩና አካባቢውም ሆነ በአዲስ አበባ የተከሰቱትን ግጭቶች አስመልክተው የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ ግርግሩ ሆን ተብሎ የተጀመረውን ለውጥ እንዳይሳካ ለማድረግ ሰፊ የሆነ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የተካሄደ ነበር ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ገንዘብ ተሰጥቷቸው የተሰማሩ ግለሰቦች ብሔር ተኮር ስድብ የታከለበት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር ሲሉም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም ተዘርፈው የተቀመጡ ንብረቶችን ፖሊስ ከጫካ እየሰበሰበ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በቡራዩና በአካባቢው በተፈጸመ ጥቃት የተጠረጠሩ ከ300 በላይ ግለሰቦች ተይዘዋል ብለዋል፡፡

©ሪፓርተር
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ  በአዉሮፕላን አደጋዉ የሞቱትን ሰዎች የመለየቱ ስራ አስከ #አምስት_ቀን ሊፈጅብኝ ይችላል አለ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ አስራት በጋሻዉ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት የሟቾቹን ማንነት ሙሉ ለሙሉ ለማወቅ ቢየንስ እስከ አምስት ቀን ሊቆዩ  እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ትላንት በቢሾፍቱ አካባቢ በደረሰዉ የአዉሮፕላን አደጋ የ35 ሀገራት ዜጎች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉ ይታወቀል፡፡

-Arts TV
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው የባሌ ሮቤ ከተማ ለጀዋር መሐመድ ድጋፍ ከተደረገ ሰልፍ በኋላ በተቀሰቀሰ ግጭት ቁጥራቸው በወል ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።

የባሌ ሮቤ ነዋሪዎች የሐይማኖት መልክ ይዟል ባሉት ግጭት ሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች እና ሻይ ቤቶች መቃጠላቸውን የዐይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ሶስት የከተማዋ ነዋሪዎች ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ ባሌ ሮቤን ከሌሎች አካባቢዎች የሚያገናኙ መንገዶች፣ የግብይት መደብሮች፣ የመንግሥት እና ማኅበራዊ ተቋማት መዘጋታቸውን አስረድተዋል። ጀዋር መሐመድ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ካሰራጨው መልዕክት በኋላ ትናንት ጠዋት በአብዛኛው ወጣቶች የተሳተፉበት ሰልፍ መካሔዱን የገለጹት ነዋሪዎች በሒደት መልኩን እየቀየረ ወደ ግጭት እና ጥቃት መቀየሩን ተናግረዋል።

«ትናንትና ቄሮ በሚለው ስም የተደራጁ የባሌ ወጣቶች ተነስተው ባንድነት ከተማው ውስጥ እየዞሩ ነበር» ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የባሌ ሮቤ ነዋሪ እማኝታቸውን ሰጥተዋል። ወጣቶቹ «ጀዋር ነው የሚመራን፤ በጀዋር ሥር ነው የምንኖረው፤ ጀዋር ማለት የቄሮ አባት ነው የሚሉ መፈክሮች ያሰሙ ነበር» ብለዋል።በባሌ ሮቤ የሚገኝ አንድ ቤተ-ክርስቲያን ለማቃጠል ጥረት ተደርጎ እንደነበር የሚጠቅሱት የከተማዋ ነዋሪ ጉዳዩን ወደ ሃይማኖት ግጭት ለመውሰድ እየተደረጉ ስላሉ እርምጃዎች አብራርተዋል። በቤተክርስቲያን ተሰቅሎ የነበረን ባንዲራ ወጣቶቹ አውርደው ማቃጠላቸውን እና ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ላይ ጥቃት እያደረሱ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

«የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ንብረት የሆኑ መጠጥ ቤቶች ይሔዱና ያፈርሳሉ። እቃቸውን ውጪ አውጥተው ማንደድ፤ የእሳት አደጋ ማድረስ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ነው ያሉት» ሲሉ የወጣቶቹን እርምጃዎች ዘርዝረዋል።አንድ ሌላ የባሌ ሮቤ ነዋሪ በበኩላቸው ሆቴሎችን ኢላማ ጥቃት መፈጸሙን ገልጸዋል። ዘርፌ ግርማዬ፣ ባላገሩ እና መስቀል የሚባሉ ሆቴሎች መውደማቸውን የሚናገሩት እኚሁ ነዋሪ በሐረር ሆቴል ላይም ጥቃት መፈጸሙን ተናግረዋል። የሮቤው ነዋሪ እንደሚሉት ጥቃት የደረሰባቸው ግለሰቦች የበቀል እርምጃ ሲወስዱ ተመልክተዋል። ከዚህው ጋር በተያያዘ ንብረትነቱ የሙስሊሞች የሆነ «ዌልመል» የተባለ ካፌ ትላንት ምሽት መውደሙን ጠቁመዋል።የዐይን እማኙ ቢያንስ #አምስት ሰዎች ተገድለዋል የሚል ወሬ በከተማዋ መሰማቱን ቢናገሩም ዶይቼ ቬለ ጉዳዩን ከገለልተኛ ወገን ማረጋጥ አልቻለም። «ጠዋት ሰው በጦር መሳሪያ ተመትቶ በቃሬዛ ይዘዋቸው ሲሔዱ አይቻለሁ። በከተማው ጥቃት ሲደርስ ታያለህ» የሚሉት የከተማዋ ነዋሪ ሁከቱን ወደ ሃይማኖት ግጭት የመቀየር አዝማሚያ እንዳለ ገልጸዋል። «በጣም የሚያሳዝነው ነገር መከላከያ፤ የከተማ ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ያንን ነገር ለማርገብ ምንም አይነት እርምጃ እየወሰዱ አይደለም» ሲሉ በጸጥታ ኃይሎች በኩል የተመለከቱትን ቸልተኝነት ተችተዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa