YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሠልፍ #አምስት ሰዎች ሞቱ

ዛሬ ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ #ብሔር ተኮር ጥቃቶችን በመቃወም ሠልፍ ከወጡ ሰዎች መካከል አምስት ሰዎች መሞታቸውንና ሌሎችም መቁሰላቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ለመንግሥት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹የተወሰኑ በቡድን ተደራጅተው የፀጥታ ኃይሎችን መሣሪያ ለመቀማት ሞክረዋል፡፡ አከፖሊስ ጋር ግብግብ የገጠሙትን በአካባቢው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች የማያዳግም ዕርምጃ ወስደው የተወሰኑ ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው ታውቋል፤›› ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሠልፉ ውስጥ #ቦምብ ይዘው የወጡ ግለሰቦች መገኘታቸውንና በሰላማዊ ሠልፉ ተሳታፊዎች ጥቆማ መያዛቸውን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡

በቡራዩና አካባቢውም ሆነ በአዲስ አበባ የተከሰቱትን ግጭቶች አስመልክተው የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ ግርግሩ ሆን ተብሎ የተጀመረውን ለውጥ እንዳይሳካ ለማድረግ ሰፊ የሆነ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የተካሄደ ነበር ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ገንዘብ ተሰጥቷቸው የተሰማሩ ግለሰቦች ብሔር ተኮር ስድብ የታከለበት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር ሲሉም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም ተዘርፈው የተቀመጡ ንብረቶችን ፖሊስ ከጫካ እየሰበሰበ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በቡራዩና በአካባቢው በተፈጸመ ጥቃት የተጠረጠሩ ከ300 በላይ ግለሰቦች ተይዘዋል ብለዋል፡፡

©ሪፓርተር
@YeneTube @Fikerassefa