YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ⤵️⤵️


ፖሊስ #በተስፋዬ ኡርጌ ቢሮ አገኘሁት ያለውን ቦምብ ከሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ቅሪት ጋር ለማመሳከር ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠየቀ።

በሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው የብሄራዊ መረጃ ደህንነት መምሪያ አዛዢ ተስፋዬ ኡርጌ ፖሊስ በቢሮው አገኘሁት ያለወን #ቦምብ መስቀል አደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል ጋር ለማመሳከር ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የጠየቀበትን ምክንያትና የተጠርጣሪውን አስተያየት አዳምጧል።

መርማሪ ፖሊስ ምርመራችንን አጠናቀን ለፌዴራል አቃቢ ህግ ያስረከብን ቢሆንም አቃቢ ህግ መስከረም 15 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት አቶ #ተስፋኤ ኡርጌ ቢሮ ውስጥ ያገኘነውን ቦንብ መስቀል አደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል ጋር በቴክኒክ ለማመሳከር ተጨማሪ ማስረጃ ይቅረብልኝ ማለቱን ተከትሎ ለፌዴራል ፖሊስ ፈንጅ አምካኝ ኦፕሬሽን ዲቪዢን ደብዳቤ ልከናል ሲል አብራርቷል።

ይህንን የቴክኒክ ምርመራ ምላሽ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ብሏል።

ጉዳዩ ያለ አግባብ እየተራዘመ መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በበኩላቸው ፍርድቤቱ አጭር ቀጠሮ ሰጥቶ ለመጨረሻ ትዛዝ ይስጥልኝ ሲሉ #ጠይቀዋል

ፍርድቤቱም በተጠየቀው የጊዜ ገደብ የቴክኒክ ምርመራው ለምን አልተጠናቀቀም የሚል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፥ ፖሊስም ደብዳቤ ልከን ምላሽ ስላልተሰጠ እየጠበቅን ነው ሲል አብራርቷል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድቤት ተረኛ ወንጀል ችሎትም ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ የቴክኒክ ምርመራውን ይዞ እንዲቀርብ ለተጨማሪ ስምንት ቀን ቀጠሮ በመስጠት #ለጥቅምት አራት ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ምንጭ ፦ FBC
@yenetube @mycase27