YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
# "ከተማዋ ትስቃለች" በሚል ሊጀመር የታሰበው አዲስ ፕሮግራም ተቃውሞ ደረሰበት
#በቅርቡ የተምሸረችው አርቲስት ደምዝ ባለመክፈል ቅሬታ ቀረበባት
#የኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች ፕረዘዳንት ለከተማዋ ትስቃለች ፕሮግራም ሂሳዊ ምላሽ ሰጠ.....
#አጫጭር መረጃ እና ሙዚቃ ግብዣዎች...
#ማታ በተርሚነስ ቻናል ይጠብቁን
#update ቤንሻንጉል ⤵️⤵️

#በቅርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በካማሺ ዞን በተከሰተዉ ግጭት ከ70,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉ #ይታወሳል

ተፈናቃዮቹ ወደ ኦሮሚያ ክልል፣ ማለትም፣ በምሥራቅ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች መጠለያ #ማግኘታቸው ተገልጿል።

ለደህንነታቸው በመስጋት ንብረታቸዉን ጥለው ከተፈናቀሉት 70,000 ዉስጥ እስከ ትላንት ማታ ድረስ #ከ28,000 በላይ ወደ ቀየያቸዉ መመለሳቸዉን ፣ የተቀሩትንም ወደ ቀያቸዉ ለመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን የኦዴፓ ጽህፈት ቤት የገጠር አደረጃጀት ኃፊ አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ ጥዋት በፌስቡክ ገፃቸዉ ያሰፈሩት ጽሁፍ አመልክቷል።

ምንጭ ፦ አቶ አዲሱ አረጋ
@yenetube @mycase27
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ የማለፊያ ውጤት #በቅርቡ_ይፋ ይደረጋል። ዘንድሮ ከበፊቱ በተለየ መልኩ ተማሪዎች የሚመርጡት የማህበረሰብ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ብቻ በሚል መሆኑም ተገልጿል። በዚህ መሰረትም ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ "የፍሬሽ ማን ኮርስ" ከወሰዱ በኋላ የሚማሩበትን የትምህርት ዘርፍ የሚመርጡ ይሆናል። በሌላ በኩል በዚህ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከፈለጉ የማህበረሰብ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍን መምረጥ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

Via :- FBC
@YeneTube @FikerAssefa