YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ቤንሻንጉል ⤵️⤵️

#በቅርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በካማሺ ዞን በተከሰተዉ ግጭት ከ70,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉ #ይታወሳል

ተፈናቃዮቹ ወደ ኦሮሚያ ክልል፣ ማለትም፣ በምሥራቅ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች መጠለያ #ማግኘታቸው ተገልጿል።

ለደህንነታቸው በመስጋት ንብረታቸዉን ጥለው ከተፈናቀሉት 70,000 ዉስጥ እስከ ትላንት ማታ ድረስ #ከ28,000 በላይ ወደ ቀየያቸዉ መመለሳቸዉን ፣ የተቀሩትንም ወደ ቀያቸዉ ለመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን የኦዴፓ ጽህፈት ቤት የገጠር አደረጃጀት ኃፊ አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ ጥዋት በፌስቡክ ገፃቸዉ ያሰፈሩት ጽሁፍ አመልክቷል።

ምንጭ ፦ አቶ አዲሱ አረጋ
@yenetube @mycase27
#update ህገ-ወጥ ወታደራዊ ስልጠና #በጫካ ውስጥ ሲሰጡ የነበሩ 10 አሰልጣኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው #ተገለፀ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ግለሰቦችን በመመልመል በጫካ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ 10 አሰልጣኞች መያዛቸውን ፖሊስ ገለጸ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ እንደገለፁት፥ በሕገ ወጥ መንገድ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩት አሠልጣኞች ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር የዋሉትም ከኅብረተሰቡ በደረሰ #ጥቆማ መሆኑ ነው የተገለፀው ፡፡

ግለሰቦቹ የሚያሰለጥኗቸውን አካላት ከአሶሳ ዞን መንጌ፣ አሶሳና ኦዳቢልድግሉ ወረዳዎች በመመልመል ሲያሰለጥኑ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ በግለሰቦቹ ላይ የተጀመረው የምርመራው ውጤት በፍጥነት አጠናቆ ለህግ ለማቅረብ ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለፁት ኮማንደሩ የምርመራ ውጤቱንም በየጊዜው ለሕዝቡ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡

ኅብረተሰቡ በሕገ ወጥ ድርጊት ላይ የተሰማሩትን ግለሰቦች ጉዳይ በማሳወቅ ትብብሩን #እንዲቀጥል ምክትል ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።

በክልሉ ህዝብ ላይ ጥፋት ለመፈጸም በአሶሳ ወረዳ ገንገን ቀበሌ በጫካ ውስጥ ህገ-ወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 51 ተጠርጣሪዎች በቅርቡ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው #ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ኢዜአ
@yenetube @mycase27
የፈተናዎች ኤጄንሲ ⬆️

ውድ የዩኒቨርስቲ መግብያ (12ኛ ክፍል) ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችና የተፈታኝ ተማሪ ወላጆች ነሐሴ 1/2011 ዓ.ም የተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና ውጤት ዛሬ ነሐሴ 5/2011 ዓ.ም ይለቀቃል ብለን መረጃ መስጠታችን ይታወሳል፡፡ ኤጀንሲው በገጠመው ችግር ምክንያት በዛሬው እለት ውጤቱን መልቀቅ አለመቻሉን እየገለጸ ለተፈጠረው መዘግየት ይቅርታ እየጠየቀ ውጤቱን ከሁለት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የምንለቅ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡ ውድ የዩኒቨርስቲ መግብያ (12ኛ ክፍል) ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችና የተፈታኝ ተማሪ ወላጆች ነሐሴ 1/2011 ዓ.ም የተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና ውጤት #ዛሬ_ነሐሴ 5/2011 ዓ.ም #ይለቀቃል ብለን መረጃ መስጠታችን #ይታወሳል፡፡

ኤጀንሲው በገጠመው ችግር ምክንያት በዛሬው እለት ውጤቱን መልቀቅ አለመቻሉን እየገለጸ ለተፈጠረው መዘግየት ይቅርታ እየጠየቀ ውጤቱን ከሁለት ቀን #ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የምንለቅ መሆኑን #በትህትና እንገልጻለን፡፡


@Yenetube @FikerAssefa