YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የመከላከያ ሠራዊት በአብዛኛው ከአንድ አካባቢ በመጡ ሰዎች የተሞላ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ በመከላከያ ሠራዊት ሁሉም አዛዦች የትግራይ ተወላጆች እንደነበሩም አስታውቀዋል፡፡መከላከያና ደህንነት የነበሩ ሰዎች ለሥራ አመች ሜዳ የማይፈቅዱ እንደነበሩ ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ በመንግሥት ውስጥ ያሉ መንግሥታት ማንሳት አስፈላጊ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙንና የደህንነት ሹሙን በአንድ ጊዜ ማንሳታቸውን ነው ያስታወሱት፡፡ የደህንነት ሹሙ ከስልጣን ሲነሱ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ሰርቀው ወደ መቀሌ መሄዳቸውንም ነው የተናሩት፡፡

የተሰረቀው መሳሪያ የታወቀውም ከሰኔ 16 የግድያ ሙከራ በኃላ በተደረገ የተቋሙ ፍተሻ እንደሆነም አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ቢያንስ መሳሪያውን ይመለስ በሚል ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር መወያዬታቸውንም ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ ፈታኝ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመከላከያ ተቋሙን፣ የደህንነት ተቋማት፣ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኅንነት ተቋም፣ የፖሊስ፣ የገንዝብ ደኅንነት ተቋማትን መለወጥ እንዳስፈለገም አስታውሰዋል፡፡

በመከላከያ ተቋም ባለ አራት ኮከብ ጄኔራሎች ከትግራይ ክልል 60 በመቶ፣ ከቀሪው ኢትዮጵያዊ 40 በመቶ ብቻ ነበሩ ነው ያሉት፡፡ ሌትናል ጄኔራል ደግሞ 50 በመቶ ከትግራይ ክልል የነበሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ሜጄር ጄኔራል 45 በመቶ፣ ብርጋዴል ጄነራል 40 በመቶ፣ ኮሎኔል 58 በመቶ፣ ሌትናል ኮሎኔል 66 በመቶ፣ ሺሕ አለቃ 53 በመቶ ከአንድ አካባቢ የመጡ እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡ በዚህ አካሄድ መከላከያውን ሚዛናዊ የሆነ ተቋም ለመፍጠር አስቸጋሪ እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡

መከላከያውን አመራር የሚሰጠው ኃይል 80 በመቶው የሚሆነው ከትግራይ ክልል የመጣ እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡ በሀገሪቱ የነበሩ እዞች ዋና አዛዥና ምክትል አዛዥ ሙሉ በሙሉ ከትግራይ እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡ከሰሜን እዝ ውጭ በሌሎቹ እዞች ሎጂስቲክና የሰው ኃይል ከሌሎች ክልሎች የተውጣጡ ነበሩበት፡፡ በሰሜን እዝ ግን አዛዥ፣ ምክትል አዛዥ፣ ሎጂስቲክስና ሰው ኃይል አስተዳደር አራቱም ከትግራይ የመጡ መሆናቸውን ነው ያስታወሱት፡፡

የኢትዮጵያ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር መቶ በመቶ ከትግራይ ክልል የሆኑ እግረኛ ክፍለ ጦር ደግሞ 80 በመቶ ከትግራይ እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡ ሜካናይዝድ ብርጌዶች 85 በመቶና እግረኛ ብርጌድ 80 በመቶ ከትግራይ እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡የመካለከያ ተቋም ስልጠና ተቋማት 85 በመቶ በትግራይ ተወላጆች ሲመራ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ ይህን የተዛባ አካሄድ የትግራይ ህዝብ ሆነ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ እንዳለበትና መደገም እንደሌለበትም ነው ያስገነዘቡት፡፡

የሙያ ብቃት እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉም በሚገባው መውሰድ እንደሚገባው ነው ያሳሰቡት፡፡ ኢትዮጵያን የሚመስል መከላከያ መገንባት ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ካሁን ቀደም የተገነባበት ስርዓትም የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል ለመወሰን የሚያስቸግር እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የደህንነት እና የመከላከያ ተቋም ስሪት ለበርካታ ግጭቶች መነሻ እንደነበሩም ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለተከሰቱት ግጭቶች መነሻው ትግራይ ክልል ውስጥ የመሸጉት ቡድኖች እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡ እነዚህ የቡድን ስብስቦች የሀገር ውስጥ ብጥብጥ ከመፍጠር ባለፈ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ለማጋጬት ብዙ ሙከራ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡ከለዉጡ በኃላ የመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ማሻሻያ እንደተደረገበትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ ወታደሩ የህዝብ እንጂ የብልጽግና እንዳይሆን መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡

AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ በሆኑት በመተከል እና በአዊ ዞን በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይ ላይ በመምከር አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት ጥምር ኮሚቴው ውይይት እያካሄደ ነው።

ውይይቱ የአዊ ዞን አዋሳኝ በሆነው የመተከል ዞን በተደጋጋሚ ለሚስተዋለው የጸጥታ ችግር እልባት ለመስጠት ያለመ መሆኑም ተገልጿል።እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት እየተስተዋለ ያለውን የሰዎች ሞት፣ መፈናቀልና የንብረት መውደም ለመታደግና መፍትሄ በማስቀመጥ የጋራ ስምምነት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል መባሉን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።በውይይቱ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የጸጥታ አካላት እና ቀጠናውን በኮማንድ ፖስት የሚመራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አዛዦች መገኘታቸውን የመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሮኬት ክምችት ላይ ጥቃት ባለማድረስ ህዝብን ከጥፋት መታደግ ተችሏል። -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

በመቀሌና አድዋ ከተሞች የሚገኘውን የሮኬት ክምችት ባለ ማጥቃት ህዝብን ከጥፋት መታደግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።በመቀሌና አድዋ ከተሞች በጠላት እጅ ወድቆ በነበረው ከፍተኛ የሮኬት ክምች ላይ ጥቃት ቢደረግ ከሚያስከትለው ጥፋት አንጻር መንግስት ሮኬቶቹን ከማውደም መቆጠቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።በዚህም ሊከሰት የሚችለውን ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ጥፋት መታደግ መቻሉን ነው የገለጹት።የጥፋት ቡድኑ ከዚህ ቀደም ላሰበው የጥፋት ተልዕኮው እንዲሆን አብዛኛውን የመከላከያ የጦር መሳሪያ በሰሜን እዝ ብቻ እንዲሆን ማድረጉንም አስታውሰዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ስደተኞችን በሳምንት ውስጥ እንደሚቋቋሙ ተገለጸ!

በለውጥ ሂደት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆሩ ሰዎች ተፈናቅለው መልሰናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በሱማሌ እና በሌሎች ክልሎችም ስደተኞችን የመመለስ በቂ ልምድም አለን ሲሉ ተናግረዋል።ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥራቸው ወደ 30 ሺህ ገደማ ሰዎች እንደተሰደዱ ሪፖርቶች ያመላክታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፤ ስደተኞችን በሳምንት ውስጥ እናቋሙማለን ብለዋል።

ከተባበሩት መንግስታት አና ከሱዳን መንግስት ጋር ስደተኞችን ለማስመለስም በራችን ክፍት ነው ሲሉም ገልጸዋል።ግን አንድ ችግር አለ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ፤ ከስደተኞቹ ውስጥ ሴቶች የሉም ሕጻናት የሉም ወጣት ብቻ ነው ስደተኛ የተባለው ይህ ወጣት ማነው የሚለው ጉዳይ ጊዜ የሚመልሰው ይሆናል ብለዋል።አክለውም ‹‹ማይካድራ ላይ አርዶ ሄዶ ከሆነና ማስረጃ እና መረጃ ከተገኘበት በሕግ ይጠየቃል›› ያሉ ሲሆን ንጹሃን ዜጋ ለመመለስ ፍላጎት ላለው በራችን ክፍት ነው ሲሉም ተናግረዋል።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ኅዳር 21/2013 6ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ተኛ ልዩ ስብሰባ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽ ሰጥተው መርሃግብሩም ተጠናቋል።

Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ዶ/ር ደብረጽዮን ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል መባሉን አስተባበሉ!

የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል «ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል» ተብሎ የተነገረዉ ዘገባ «ሐሰት ነው» በማለት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።ደብረጽዮን «አሁንም በመቀሌ ከተማ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር እየተዋጋን ነው።»ብለዋል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ባለፈው ቅዳሜ የመቀሌ ከተማን መቆጣጠሩን አስታውቋል።በወቅቱ ደብረጽዮን የመቀሌ ከተማን ለቀው መውጣታቸውን ለሮይተርስ በላኩት አጭር የጽሁፍ መልዕክት አረጋግጠዋል።የሕወሓቱ መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ወደ ደቡብ ሱዳን ሸሽተዋል የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ በሰጡት መልስ« ከትግራይ ክልል አልወጣሁም» ሲሉ ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ቃል አቃባይ ቢለኔ ስዩም በበኩላቸው «የፌዴራል መንግሥት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን በማረጋጋት ስራ ላይ ተጠምዷል፤ ተበታትኖ ላለ ወንጀለኛ ንግግር መልስ መስጠት ጉዳያችን አይደለም» ሲሉ ደብረጽዮን «በመቀሌ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር ውግያ ቀጥለናል» ብለው መናገራቸውን ያጣጣሉበትን ሃሳብ ለሮይተርስ ነግረዋል።

[Reuters/DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ከ3 ሺህ በላይ በ'ጁንታ'ው ቡድን ታፍነው የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና አልዋጋም ብለው ያመለጡ የጁንታው ልዩ ሀይል አባላት በደባርቅ ከተማ አቀባበል ተደረገላቸው!

በበየዳና ጠለምት መስመሮች የመጡ 3 ሺህ በላይ በ'ጁንታ'ው ታፍነው የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና አልዋጋም ብለው ያመለጡ ጁንታው ያደራጃቸው ልዩ ኃይል በደባርቅ ከተማ አቀባበል ተደረገላቸው።የሠሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያየአለም ፈንታሁን እንደተናገሩት ከበየዳና ጠለምት ወረዳ ከተሞች ጀምሮ ሕብረተሠቡ አቀባበል በማድረግ የደከሙትን በማዘልና በመመገብ ደባርቅ እንዲደረሱ አድርገዋል ተብሏል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ለ2012 ዓም ተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ አደረገ!

የወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ #MoSHE ከዛሬ ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ዩንቨርስቲዎች ጥሪ እንዲያደርጉ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ህዳር 24 እና 25/2013 ዓም የምዝገባ ጊዜ መሆኑን አስታውቋል። ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ደግሞ ህዳር 28 መሆኑን ጨምሮ አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የመጀሪያው የጨረር ህክምና መሳሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

በኢትዮጵያ የመጀሪያው የጨረር ህክምና መሳሪያ (radio therapy) ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ::በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀደም ሲል የካንሰር የጨረር ህክምና ይሰጥ የነበረ ቢሆንም አሮጌ በመሆኑ የካንሰር ህመምተኞች መስተጓጐል እንደነበር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሎጅ ዲን ዶክተር ዳዊት ወንድማገኘው ተናግረዋል፡፡የጨረር ህክምና ለማግኘት ወረፋ በመጠበቅ ላይ እያሉም ህይወታቸው የሚያልፉ የካንስር ህመምተኞች ብዙ መሆናቸውን የጠቆሙት ዶክተር ዳዊት አሁን የተመረቀው የካንሰር የጨረር ህክምና መሳሪያ ቀደም ሲል ይከሰቱ የነበሩ ችግሮችን ይቀርፋል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሆስፒታሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ ትኩረት አድርገው መስራት አለባቸው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡የካንሰር ህክምናን ማእከላት ለማስፋፋት መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የጠቆሙን የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ የተመረቀውን የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጨምሮ በቀጣይ በጅማ፣ ጎንደር፣ ሀዋሳ እና ሀረሪ ሆስፒታሎች አገልግሎቱን ለመጀመር መታሰቡን ተናግረዋል፡፡ከካንሰር ህክምና ማእከል በተጨማሪ ህክምናውን የሚሰጡ ባለሙያዎች እየጨመረ ሲሆን በቀጣይም በተለያዩ የሙያ እርከኖች ባለሙያዎች የማስተማር ስራ ጤና ሚኒስቴር ይሰራል ብለዋል፡፡

[ኤፍ ቢ ሲ]
@YeneTube @FikerAssefa
ከሰሞኑ በኮንሶ ዞን፣ አማሮ፣ ዴራሼ፣ አሌና ቡርጂ ወረዳዎች ባሉ ግጭቶች የተጠረጠሩ 137 ሰዎች ተያዙ።

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ እንዳሉት ህዝቡ እርስ ችግር ባይኖርበትም ነባር ጥያቄዎችን ሰበብ በማድረግ እነዚህ የጥፋት ሀይሎች አማካኝነት በ17 ቀበሌዎች በተነሳ ግጭት የ66 ሰዎች ህይወት አልፏል።እንዲሁም በዚህ ግጭት ሳቢያም 39 ሰዎች የአካል ጎዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ130 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ ከሚኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለዋል ብለዋል።በአካባቢው የህወሃትና ኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት ባላቸው አካላት የተፈጸመውን ጥቃት በመፍራትም ከ130ሺ በላይ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን አስረድተዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ለእነዚህ ወገኖች አሰቸኳይ የእለት እርዳታ እየቀረበላቸው መሆኑንም ሀላፊው ይናገራሉ፡፡ህግን የማስከበር ስራ 4 የምርመራ ቡድኖች ተቋቋመው መረጃዎች እየተሰባሰቡ መሆኑንም ተናግረዋል። የክልሉ እና የወረዳዎቹ ነዋሪዎች ባደረጎት ከፍተኛ ጥረትም ግጭቱ እንዲነሳ ተሳትፎ ያደረጉ 137 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ቀሪዎቹን የጥፋት ቡድን አባላት ህግ ፊት የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ዜጎቿን መልሳ ለማቋቋም እየሰራች ነው ሲሉ አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ!

መንግስት በስደት ሱዳን የሚገኙ ዜጎችን በትግራይ ክልል መልሶ የማቋቋም ስራ እየሰራ መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብርሃ ገለጹ።አቶ ዛዲግ በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከጀርመን ድምጽ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ህወሃት በትግራይ ቴሌኮምን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማቶችን በማውደም የትግራይ ህዝብን ከተቀረው አለም ጋር እንዳይገናኝ ስለማድረጉ አብራርተዋል።የሀገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌ መግባቱን ተከትሎ ባለሙያዎች #የስልክ_መስመሮችን ለማስተካከልና ግንኙነቱን ለማስጀመር እየተሰሩ መሆኑንም አብራርተዋል።የህወሃት ቡድን በክልሉ ኤርፖርትን ጨምሮ መንገዶችንና ድልድዮችን ማፈራረሱን ገልጸዋል።

አሁን መንግስት እነዚህን መሰረተ ልማቶች መልሶ እየገነባ ነው ሲሉ ገልጸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ነገሮች በግልጽ የሚያደርግና ምንም የሚደበቅ ነገር እንደሌለው ነው ያስረዱት።አለምአቀፍ ስደተኞችን በማስተናገድ ኢትዮጵያ ከአለም ሶስተኛዋ ሃገር በመሆኗ ሰብአዊ እርዳታዎችን እንዴት ማሰራጨት እንዳለባት ጠንቅቃ ታውቃለች ብለዋል።የተበላሹ መሰረተ ልማቶችን በማስተካከል ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀደመ ኑሯቸው ለመመለስ ቀንና ሌሊት እየተሰራ ነው ብለዋል።ህወሃት በመረጠው ወታደራዊ አማራጭ የተሸነፈ በመሆኑ ድርድር ማድረግ የሚባለው የማይሆን እንደሆነ ነው ያስረዱት።አቶ ዛዲግ አብርሃ የትግራይ ህዝብ በህወሃት አስተዳደር የተማረረ በመሆኑ በድርድር ሰበብ ህወሃት ተመልሶ እንዲረግጠው አይፈልግም ብለዋል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የባንክ እና ቴሌኮም አገልግሎቶች ወደ ቀድሞ አገልግሎታቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ።

ኮሚሽኑ የመልሶ ማቋቋም ተግባራት በሰብአዊ መብቶች የሚመሩ መሆን አለባቸውም ብሏል።ቀደም ሲል በኢሰመኮ የቀረቡ፣ በተለይም በሲቪል ሰዎች ላይ ማንኛውም አይነት ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ እንዲደረግ አጽንዖት የሚሰጡት ምክረ ሃሳቦችንና ጥሪዎችን በማስታወስ፣ በቀጣይ የሚደረጉ የመልሶ ማቋቋምና መልሶ ግንባታ ተግባራት በፌዴራል መንግሥቱ ሰብአዊ መብቶችን የማክበርና የመጠበቅ ግዴታ የሚመራ እንዲሆን አሳስቧል።የተጠፋፉ ቤተሰቦች እንዲገናኙና ተገቢው ሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን የተቋረጡ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ ውሃና ኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ሰጪ አካላት አገልግሎት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ማሳሰቡን ኮሚሽኑ በላከው መግለጫ ገልጿል።

እንዲሁም በግጭቱ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ሰዎች ወደ መደበኛ መኖሪያቸው እንዲመለሱ እና የተጠፋፉ ቤተሰቦች እንዲገናኙ የሚያስችል አስፈላጊ የሆነው የሎጂስቲክስና የሰብአዊ እርዳታ መሰረተ ልማት እንዲደራጅም ጠይቋል።ተጠያቂነትን ለማረጋገጥና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና ያስከተለውን ሰብአዊ ቀውስ የሚመመረምር ገለልተኛና ግልጽ የሆነ አሰራር ከወዲሁ እንዲተገበር፣ ተዓማኒና አካታች የሆኑ የእርቅና የፍትሕ ሂደቶች በጊዜ ሊደራጁ ይገባልም ብሏል።በተጨማሪም ኢሰመኮ በትግራይ ተወላጆች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረገ መድሎዎና መገለል ስለመድረሱ የሚቀርቡለት ቅሬታዎች በከፍተኛ ደረጃ እያሳሰበውና እየተከታተለው መሆኑን ገልጿል።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
አክሱም ተያዘና አውሮፕላን ተመታ መባሉን መንግሥት ሐሰት ነው አለ!

የህወሓት ኃይሎች ትላንት [እሁድ] ምሽት አክሱም ከተማ መልሰው እንደያዙና የፌዴራል መንግሥት ንብረት የሆነ ተዋጊ ጄት መትተው መጣላቸውን ገልጸው ነበር።ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በህወሓት በኩል ተባሉት ነገሮችን "ነጭ ውሸት" ሲሉ አጣጥለውታል።ሚኒስትር ዛዲግ ጨምረውም "የህወሓት የመጨረሻ ይዞታ የነበረችው መቀሌ ናት፤ ይህንን ሊያደርጉ አይችሉም" ሲሉ ተናግረዋል።ከሦስት ሳምንት በላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ውስጥ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ዋና ከተማዋን መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መከላከያ "ሕግ የማስከበሩ ዘመቻ" መጠናቀቁን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከመቀለ መያዝ በኋላ ለሮይተርስ ዜና ወኪል በአጭር የጽሁፍ መልዕክት እንደገለጹት በውጊያው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።በተጨማሪም የቡድኑ ኃይል መቀለ ከተማ አቅራቢያ ውጊያ እያካሄደ ነው ሲሉ ተናግረዋል።ይህንን በተመለከተ ህወሓት የሽምቅ ውጊያ እያካሄደ እንደሆነ በቢቢሲ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ዛዲግ አብረሃ ሲመልሱ "የህወሓት አመራሮች በአሁኑ ጊዜ ሕይወታቸውን ለማዳንና በሕግ ከመጠየቅ ለማምለጥ እየሸሹ ነው እንጂ ውጊያ ላይ አይደሉም" ሲሉ መልሰዋል።ትናንት ምሽት ከየት ቦታ እንደሆነ ካልታወቀ ስፍራ ከህወሓት በኩል ወጣ በተባለ መግለጫ ላይ የቡድኑ ተዋጊዎች ከሳምንት በፊት በፌደራሉ ኃይሎች የተያዘችውን የአክሱም ከተማን መልሰው እንደተቆጣጠሩና አንድ ተዋጊ አውሮፕላን መትተው መጣላቸውን ገልጸዋል።

አቶ ዛዲግ አብርሃ ግን ተመትቶ የወደቀ የጦር አውሮፕላን እንደሌለና የአክሱም ከተማ "መያዝም በፍፁም ከእውነት የራቀ ነው" ብለው፤ "ህወሓት በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት ወታደራዊ አቅም የለውም፤ ሚሊሻውም ሆነ ልዩ ኃይሉ እጅ እየሰጠ ነው" ሲሉ ከቢቢሲ ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።ሚኒስትሩ አክለው በክልሉ ያለውን ሁኔታ ለጋዜጠኞች ክፍት ለማድረግ በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች በርካታ መሠረተ ልማቶች በህወሓት ኃይል በመውደማቸው እነሱ ከተጠገኑ በኋላ ጋዜጠኞች ወደ ሥፍራው ሄደው ሁኔታውን ማጣራት ይችላሉ ሲሉ የመገናኛ መስመሮች አለመኖራቸውን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር ወቅት ከዓመታት በፊት አባይ የተባለ ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያለው የመገናኛ ብዙሀን ተቋም መኖሩን ጠቅሰዋል።የተጠቀሰው ተቋም በዩቲዩብ ሥራውን በመከወን ላይ ከሚገኘው እና በቅርቡ የቴሌቪዥን ስርጭት ከሚጀምረው #አባይ_ሚዲያ ጋር አንድነት እንደሌለውና ሁለቱ ተቋማት የተለያዩ እና ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ከነገ ጀምሮ ያበቃል!

በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ከነገ ኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም በህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ከነገ ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም።
የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታኅሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወቅቱ መግለጹ ይታወሳል።ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምስረታ ላይ የሚገኘው የአማራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጩን አጠናቀቀ፡፡

የአማራ ባንድ አክሲዮን ማህበር በምስረታ ሂደት ላይ በቆየበት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ160 ሺህ በላይ አክሲዮኖችን በመሸጥ ከሰባት ቢሊዮን በላይ ብር መሸጡን አስታውቋል፡፡እንዲሁም ከአምሰት ቢሊየን በላይ ብር ደግሞ በካፒታል መሰብሰቡንም ገልጿል።በዚሁ ወር መጨረሻ ደግሞ ከባለአክሲዮኖች ጋር ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
#REMINDER!!

በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ዛሬ ያበቃል!

በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ከዛሬ ኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም በህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ከዛሬ ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም። የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታኅሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወቅቱ መግለጹ ይታወሳል።ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአልጀርስ ከዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ጋር ውይይት ተካሄደ!

በአልጀርስ የሚገኘው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት /IOM/ ኃላፊ ፓውሎ ካፑቶና የኘሮጀክት ኃላፊ ከሆኑት ፍላቪያ ጂኦርዳኒ ጋር ዜጐቻችን IOM ድጋፍ ማግኘት በሚችሉበትና በወቅታዊው የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግ ማስከበር ዙሪያ የተወሰዱ እርምጃዎችን አስመልክቶ ኀዳር 21 ቀን 2013 በኢፌዲሪ ኤምባሲ ጽ/ቤት ውይይት ተካሄዷል። አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ አልጄሪያ በተለያየ ምክንያት በስደተኝነት የመጡ ኢትዮጵያውያን ክብራቸው ተጠብቆና ተገቢው ድጋፍ ተደርጐላቸው ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ በዓለም ዓቀፉ ስደተኞች ድርጅት አልጄሪያ ቢሮ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ሚስተር ፓውሎ ካፑቶ በበኩላቸው ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የአዲስ አበባው ዓለምዓቀፍ በስደተኞች ጽ/ቤት በኃላፊነት መስራታቸውን በማስታወስ ተቋማቸው በስደትና ስደት ተመላሾች ጉዳይ ዙሪያ ምንግዜም ቢሆን ዜጐች ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንዲሁም ህገ-ወጥ የሠዎች ዝውውርን ለማስቀረትም የተለያዩ ሥራዎችን እንደሚሠሩ ገልፀዋል። አምባሳደር ነብያትም በውይይቱ የፌደራል መንግስት ሕግንና ሥርዓትን በማስከበር እንቅስቃሴው አጥፊው ቡድንና ሕወሃት የተቆጣጠረውን የትግራይ ክልል ዜጐች ለጉዳት ሳይጋለጡ በኃላፊነትና በጥንቃቄ በአጭር ጊዜ ነፃ ለማውጣት መቻሉንና በግጭቱም ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት እንዲመለሱ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

[በአልጀርስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ]
@YeneTube @FikerAssefa
የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያልተገባ 1.5 ሚሊዮን ብር ለስልክ ከፈለ!

የመሥሪያ ቤቱ ላልሆኑ ስልኮች 271 ሽሕ ብር መክፈሉ በኦዲት ተረጋግጧል።የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በ2011 በጀት ዓመት ተገቢ ያልሆነ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ለስልክ ክፍያ መፈጸሙን በኦዲት ግኝት መረጋገጡ ታውቋል፡፡

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መርሃ-ግብር:

ረቡዕ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ፣
• በሻሌ ሆቴል፣ በወሰን ግሮሰሪ፣ በቆሼ፣ በወለቴ እና አካባቢዎቻቸው፣

በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ፣
• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒያለም፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ፣ በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ በፊልም ማዕከል፣ በራስ ካሳ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤ/ክ፣ በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤ/ክ፣ በሳሪስ አቦ ቤ/ክ፣ በቦሌ ቡልቡላ ኮንደሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞርያ፣ በክሬሸር እና አካባቢዎቻቸው፣

ሐሙስ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 6:30 ድረስ፣
• በአደይ አበባ፣ በሳሪስ አዲስ ሰፈር፣ በአዋሽ ቆዳ ፋብሪካ፣ በቦሌ ሚካኤል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማህበር እና አካባቢዎቻቸው፣

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:00 ድረስ፣
• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒያለም፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ፣ በለገሃር፣ በቴሌ እና አካባቢዎቻቸው፣

በመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa
ፌስቡክ በአዲሱ ዓመት ታላቋ ብሪታኒያ ውስጥ ለሚገኙ ዜና ሰሪ አውታሮች ክፍያ መክፈል ሊጀምር ነው።

ለዚህም የፌስቡክ መተግበሪያው ላይ ራሱን የቻለ የዜና መጠቆምያ ነቁጥ ይበጅለታል ተብሏል።ይህ አገልግሎቱን በአሜሪካ ከወዲሁ ሥራ ጀምሯል ተብሏል። በታላቋ ብሪታኒያ ደግሞ ከአንድ ወር በኋላ በአዲሱ ዓመት ይጀምራል።ፌስቡክ ክፍያ የምፈጽምላቸው የዜና አገልግሎቶች ዜናውን በራሳቸው ገጽ ያላተሙ ከሆነ ብቻ ነው ብሏል።ይህም ማለት የዜና አገልግሎቶቹ በፌስቡክ እንዲከፈላቸው ከፈለጉ ዜናውን ለፌስቡክ ብቻ የሚጽፉት ይሆናል።በራሳቸው ድረገጽም ሆነ በጋዜጦቻቸው ላይ ሊያትሙትም አይችሉም።ፌስቡክ ላይ እንጂ የትም ላልታተሙና የይዘት ደረጃቸው ከፍ ያሉ ናቸው ለሚባሉ የዜና ዘገባዎች ብቻ ክፍያ እፈጽማለሁ የሚለው ድርጅቱ የዜና ዘገባዎችንና ስርጭትን ያለምንም ክፍያ ለደንበኞቹ ሲያጋራና ሲጠቀምበት ነበር፥ በዝባዥ ሆኖ ቆይቷል በሚል ሲተች ነበር።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa