YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 141 ሰዎች ሲሆኑ ከሁለቱ በስተቀር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(81) ሴት(60) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ2 ወር-87 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 58 ሰዎች (44 ከአዲስ አበባ፣ 1 ከትግራይ ክልል፣ 3 ከሶማሊ ክልል፣ 8 ከኦሮሚያ ክልል እና 2 ከደቡብ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1544 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(113)፣ ከኦሮሚያ ክልል(15)፣ከሶማሊ ክልል(2)፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል(1)፣ ከጋምቤላ ክልል(3)፣ ከሀረሪ ክልል(6) እና ከድሬዳዋ(1) በድምር 141 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5175 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 30 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 3 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 81 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የህዳሴው ግድብ ያለስምምነት ከተሞላ “የሮሴይረስ ግድቤን አደጋ ውስጥ ይከትታዋል” ስትል ሱዳን ለጸጥታው ምክር ቤት አቤት አለች

ሱዳን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ባስገባችው ደብዳቤ፤ የህዳሴው ግድብ ያለስምምነት ከተሞላ “የሮሴይረስ ግድቤን ብሎም በተፋሰሱ ላይ የተመሰረቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቼን ህይወት አደጋ ውስጥ ይከታል” ስትል አቤቱታ አቀረበች። ሀገሪቱ ደብዳቤውን ለምክር ቤቱ ያስገባችው ትላንት ረቡዕ ሰኔ 17፤ 2012 ነው።
የሱዳኗ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስማ መሃመድ ለምክር ቤቱ በላኩት በዚሁ ደብዳቤ ላይ በሶስቱ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ስምምነት ባይደረስም ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ሙሌት ለመጀመር እቅድ መያዟ ሀገራቸውን በጥልቀት እንዳሳሰባት ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ለስጋታቸው እንደማሳያ ያቀረቡት ከህዳሴው ግድብ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን የሮሴይረስ ግድብን የህልውና ጉዳይ ነው።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ ፈጣን የኢንተርኔት አቅራቢው በኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት ፍላጎት አሳየ!

የማደጋስካሩ አክሲያን ግሩፕ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ኢንደስትሪ ለመሰማራት ፍላጎቱን አሳየ፡፡ ድርጅቱ ባለፉት ጥቀዊት አመታት ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠውን የኢንተርኔት አገልግሎት በማቅረብ ይታወቃል፡፡በአምስት አፍሪካ አገራት በቴሌኮም ኢንደስትሪ የተሰማራው አክሲያን ለካፒታል ጋዜጣ እንዳለው በኢትዮጵያ ገበያ የመሰማራት እድል ካገኘ በሌሎች አገራት ያስመዘገበውን ውጤት በአገሪቱም እውን ያደርጋል፡፡ከሳምንታት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀውን የዲጂታል ትራንስፎርሜንሽን ስትራቴጂን እውን ለማድረግ ፍላጎት እንዳለውም የማደጋስካሩ ድርጅት ተናግሯል፡፡መንግስት በቴሌኮም ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ ሁለት ድርጅቶች ፍቃድ ለመስጠት የፍላጎት መጠይቅ አውጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡በፍላጎት መጠይቁ የተለያዩ ድርጅቶች መሳተፋቸው የታወቀ ሲሆን ከነዚህም መካከል ሳፋሪ ኮም ይገኝበታል፡፡

#Capital
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየሰጠ ነው በሚል እየተሰራጨብኝ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ብሏል።

ማስተባበያው ቃል በቃል👇👇

የከተማ አስተዳደሩ እያስገነባቸው የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው ለሚገኙ ነዋሪዎች እንጂ ለተለያዩ ክልል ሰራተኞችም ይሁን ግለሰቦች የሚሰጥበት አሰራር የለውም። በ13ኛው ዙር እጣ የወጣላቸውና የወሰን ችግር የሌለባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች እየተላለፉ ሲሆን ከትናንት በስትያ ጀምሮ የቁልፍ ርክክብ እየተካያሄደ ሲሆን በሁለት ሳምንት ውስጥም የቁልፍ ርክክብ የሚጠናቀቅ ይሆናል።ከዚህ ውጪ በየትኛውም መንገድ የእጣ ማውጣት ሂደት የተከናወነ አለመሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን። የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየሰጠ ነው በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀ ነው።የዚህ አይነቱ ፍፁም የሀሰት መረጃዎች የከተማ አስተዳደሩን በተለይ በግዙፍ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ እያሳየ ያለውን እመርታ ለማጠልሸትና ጥርጣሬ ለመፍጠር እንደሆነ እንረዳለን።በመሆኑም ህብረተሰባችን ይህንን ተረድቶ ራሱን ከሀሰት መረጃዎች እንዲያርቅ አደራ ለማለት እንወዳለን።

-የከንቲባው ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 113 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ከእነዚህ ውስጥ 111 አድራሻቸው ከአዲስ አበባ ሲሆን የቀሩት 2 ሰዎች ደግሞ የውጪ ሃገር ዜጎች ናቸው ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3434 ደርሷል፡፡በከተማው ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በህክምና ማዕከል ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ 3 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት 44 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-

👉አዲስ ከተማ 14
👉ቦሌ 14
👉ጉለሌ 21
👉ልደታ 5
👉ኮልፌ ቀራንዮ 25
👉ቂርቆስ 6
👉አራዳ 11
👉የካ 3
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 6
👉አቃቂ ቃሊቲ 3
👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 3

@YeneTube @FikerAssefa
የዋልታ ቴሌቪዥን የምርመራ ዘገባ እንዳይተላለፍ የተጣለው እግድ ተነሳ!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ የፍታብሔር ችሎት ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ ዋልታ ቴሌቪዥን ያዘጋጀው የምርመራ ዘገባ እንዳይተላለፍ አሳልፎት የነበረውን እግድ የፕሬስ ህጉን የሚጣረስ ነው በሚል አንስቶታል፡፡የሚተላለፈው ፕሮግራም ገና ለገና የግለሰብን ስምና ምግባር ያጎድፋል በሚል ከወዲሁ ግምት መውሰድ የማይቻል ከመሆኑም ባሻገር በፕሬስ ህጉ የሰፈረውን የመናገር፣ የመጻፍ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የሚጻረር በመሆኑ ነው ችሎቱ እግዱን ያነሳው፡፡

በመሆኑም የሚዲያ ህጉ በተሰጠው ግዴታና ሃላፊነት የምርመራ ዘገባው ቀጣይ (3ኛ) ክፍል ሊተላለፍ እንደሚችል ወስኗል፡፡በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ዋልታ የፍርድ ቤት እግድ ደርሶት ፕሮግራሙን አስተላለልፏል የሚል ተጨማሪ ክስ ቀርቦበት የነበረ ቢሆንም ከሳሹ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ክሱ ውድቅ ተደርጓል፡፡ፍርድ ቤቱ መልካም ስምና ስነ ምግባርን ከማጥፋት ጋር ተያይዞ የቀረበውን ክስ የክርክር ሂደት ለመስማት ለሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ዘገባው የራሱ የዋልታ ቲቪ ነው
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሩፋኤል ሽፋረ የትግራይ ክልልን ጥያቄ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ "ይቀበላል የሚል ሐሳብ አልነበረንም። ሕገ-መንግሥቱን ለመከተል ብቻ ያቀረብንው ጥያቄ ነበር" ማለታቸውን የትግራይ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል። ሩፋኤል"ምርጫ ቦርድ የፈለገውን ቢወስንም በትግራይ ክልል ምርጫ የማካሔድ ሐሳብን ማንም አይቀይረውም።የክልሉ ሕዝብ ሕገ-መንግሥቱ የሰጠውን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ተጠቅሞ ምርጫ ያካሒዳል። ይኸንን ከማድረግ ማንም ኃይል አያስቆመውም"ብለዋል።ባይቶና፣ ናፅናት እና ሳልሳይ ወያነ ምርጫ ቦርድ የሰጠውን ምላሽ ተቃውመው ክልሉ የራሱን የምርጫው እንዲካሔድ መጠየቃቸው በዘገባው ተጠቅሷል።ፓርቲዎቹ የምርጫ ሕግ እንዲዘጋጅና ተቋም እንዲመሰረትም ሐሳብ አቅርበዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ከታከሙ ህፃናት ሁለቱ ዕድሜአቸው ከአንድ ወር በታች የሆኑ ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ሁለቱም ሙሉ በሙሉ አገግመው ከሆስፒታሉ እንደወጡ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ወረርሽኙ የአለም ግዴለሽነት ያሳየ ነው- የአለም ጤና ድርጅት

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አለም ለጤና የነበራትን የዝግጁነት ማነስ ያጋለጠ ክስተት መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናገሩ።

ዋና ዳይሬክተሩ ይሄን የተናገሩት የአለም ጤና ድርጅት፣ ፈረንሳይና ጀርመን በነበራቸው የሶስትዮሽ ውይይት ላይ ሲሆን የኮቪድ-19 በመቶ አመት አንድ ጊዜ መከሰት አለም ጤናዋን ለመጠበቅ ያሳየችውን ግዴለሽነት ያንጸባረቀ ነው ብለዋል።

ሁላችንም ተባብረን ጤነኛ መሆን ካልቻልን ማንም ብቻውን ተለይቶ ጤነኛ ሊሆን የሚችልበት መንገድ ባለመኖሩ ከክስተቱ ብዙ ልንማር ይገባል ማለታቸውን ሲ ጂ ቲኤን ዘግቧል።

ኮቪድ -19 እስካሁን ከ482 ሺህ በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ መሆኑን የአሜሪካውን ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃን ጠቅሶ የዘገበው ድረገጹ፤ በመላው አለም 9 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎች መጠቃታቸውን አስፍሯል።

አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ወረርሽኙ በአስጊ ደረጃ ለተከታታይ አመታት ሊዘልቅ እንደሚችል ጥናቶች ማመልከታቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤በአለም ላይ በወረርሽኙ የሚያዙ አዳዲስ ተጠቂዎች ቁጥር እጅጉን አሳሳቢ እንደሆነም ተናግረዋል።

ባለፈው አንድ ወር ብቻ 4 ሚሊየን ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው ክስተቱ ምን ያህል አደገኛና ሁሉንም ሊያሳስብ እንደሚገባ የገለጹት ሀላፊው፤ በዚሁ ከቀጠለ ከጥቂት ቀናት በኋላ የተጠቂዎች ቁጥር 10 ሚሊየን ሊደር ይችላል ማለታቸውን መረጃው አስታውሷል።

Via:- EPA
@Yenetube @Fikerassefa
ምንም እንኳ አሜሪካ በኮቪድ-19 የተያዙብኝ ዜጎች 2 ሚሊዮን ተኩል ብቻ ናቸው ብትልም ምናልባት እውነተኛው ቁጥር ከዚህ በብዙ ሊልቅ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

የአሜሪካ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከላዊ መሥሪያ ቤት (ሲዲሲ) እንዳስቀመጠው እውነተኛው ቁጥር አሁን ከሚባለው በአሥር እጥፍ ሊልቅ ይችላል፡፡ይህም ማለት በአሜሪካ በአሁን ሰዓት 20 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል እንደማለት ነው፡፡ይህ መረጃ የወጣው ከአሜሪካ ትልልቅ ግዛቶች አንዷ የሆነችው ቴክሳስ የእንቅስቃሴ ገደብ መላላቱን ለጊዜው እንዲቆይ ከወሰነች በኋላ ነው፡፡ምክንያቱ ደግሞ በቅርብ ቀናት በርካታ ሰዎች በቫይረሱ በመያዛቸው የሆስፒታል አልጋዎች እጥረት ስለገጠመ ነው፡፡

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
"ጣናን እንታደግ" በሚል የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ወደ ባህርዳር ይሄዳሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እንደገለጹት በድንበር ተሸጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት "ጣናን እንታደግ" በሚል ጣና ሃይቅን የወረረውን የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ ከነገ ጀምሮ ለአምስት ቀናት ወደ ባህርዳር ከተማ እንደሚጓዙ ተናግረዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች በጠቅላለው 100 በላይ ልዑካን በድንበር ተሸጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ሃላፊው ገልጸዋል፡፡በጎ ፍቃደኞቹ በቆይታቸው የእንቦጭ አረምን ከማስወገድ በተጨማሪ በባህርዳር ከተማ የጽዳት እና የትራፊክ አገልግሎት እንደሚያከናውኑ አቶ አብረሃም ተናግረዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና በጎፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አስተባባሪነት በድንበር ተሸጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከዚህ ቀደም በአዳማ ፣በደብረብረሃን እና በአንቦ ከተሞች የተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መስጠቱ ይታወሳል፡፡

Via Addis Ababa city PS
@FikerAssefa @FikerAssefa
ፓኪስታን በተጭበረበረ 'መንጃ ፈቃድ' አውሮፕላን ያበረሩ ፓይለቶቿን እያደነች ነው!

የፓኪስታን ዓለም አቀፍ አየር መንገድ 150 አውሮፕላን አብራሪዎችን መንጃ ፈቃዳቸውን ሰርዞባቸዋል፡፡የፓኪስታን አቪየሽን ሚኒስትር ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ይፋ እንዳደረጉት አብዛኛዎቹ የንግድ አውሮፕላን የሚያበሩ የአውሮፕላን 'ሾፌሮች' የማብረሪያ ፈቃዳቸው የተጭበረበረ ነው፡፡ይህ የማጥራት ዘመቻን የቀሰቀሰው ባለፈው ወር በፓኪስታን 97 ሰዎችን ጭኖ ይበር የነበረ አውሮፕላን ለማረፍ ሲቃረብ በካራቺ መከስከሱን ተከትሎ ነው፡፡በዚህ አደጋ ከ2 ተሳፋሪዎች ውጭ በሙሉ አልቀዋል፡፡የመከስከሱ ምክንያት ሲፈተሸም የአብራሪው ብቃት ማነስ እንደሆነ ተደርሶበታል፡፡

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያስገነባውን የኮቪድ-19 መመርመሪያ ማዕከልን በዛሬው ዕለት አሰመረቀ፡፡

በምረቃ መርኃግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ፣ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንግስቱ በቀለ እንዲሁም የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሴ ቁናአ ተገኝተዋል፡፡በቀን 1 ሺህ ናሙናዎችን መመርመር እንደሚያስችለው የተገለጸው ማዕከሉ፣ ለኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል ነው የተባለው፡፡

#Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የ3ተኛው ዙር የ8100A የድጋፍ መርሃ ግብር ግራንድ ሽልማት የመኪና እጣ አሸናፊ ይፋ ተደረገ።

ከሞኢንኮ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የተሰጠው የ2.2 ሚሊዮን ብር ቶዮታ ሃይሉክስ መኪና አሸናፊ ለሆነው የዳውሮ ዞን የጤና ባለሙያ ለአቶ አብርሃም አኔሾ ተሰጥቷል።ሽልማቱንም ያስረከቡት የኢፌዴሪ የንግድ ሚንስቴር አቶ መላኩ አለበል በሽልማት እርክክቡ ወቅት ያለ ኤሌክትሪክ ሃይል የምናስባትን የበለፀገች ኢትዮጵያን መቅረፅ ስለማይታሰብ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገውን ድጋፍ እስከ ግድቡ ፍፃሜ ድረስ አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።የ8100A ሰብስክራይብ የህዳሴ ግድብ የድጋፍ መርሃ ግብር ግራንድ ሽልማት በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በየካቲት ወር 2012 ዓ.ም በይፋ ከተጀመረበት ግዜ አንስቶ 1 ሚሊዮን ቤተሰቦችን አፍርቷል።

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
በጀነራል ሰዓረ መኮንን እና በሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የግድያ ወንጀል ሲካሄድ የነበረው የክርክር ሂደት እንዲቀጥል ተወሰነ!

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 248873 1ኛ የፀረ ሽብርና በህገ-መንግስት ላይ የሚፈፀሙ የወንጀል ችሎት በጀነራል ሰዓረ መኮንን እና በሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የግድያ ወንጀል ሲካሄድ የነበረው የክርክር ሂደት እንዲቀጥል ወሰነ፡፡ ሌሎች ጉዳዮችም እንደነገሩ ሁኔታ በፕላዝማ የክርክር ሂደቱን ለመቀጠል በአመራሩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ፍርድ ቤቶች በከፊል በመዘጋታቸው ክርክሩ ለጊዜው ተቋርጦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የፌ/ጠ/ዐ/ህግ ክርክሩ እንዲቀጥል ያቀረበውን አቤቱታ በመቀበል የምስክር መስማቱን ሂደት ተከሳሽ በማረሚያ ቤት ሆኖ በፕላዝማ እየታገዘ እንዲቀጥል ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡የችሎት ክርክሩ ሂደት ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ቀናት የተጎጂ ቤተሰቦች እና ጉዳዩን መከታተል የሚፈልጉ ውስን ሚዲያዎች ወይም ግለሰቦች ባሉበት እንደሚቀጥል ከችሎቱ ውሎ ለመረዳት ተችሏል፡፡

-የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ የሚተኛበት ስፍራ ደን ምንጣሮ ስራ ትናንት ተጀመረ፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኡንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ በሽር አብዱራሂም እንደገለፁት ክልሉ በኢንተርፕራይዞች አማካኝነት የሚመነጠር 1 ሺህ ሔክታር መሬት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ተረክቦ ትናንት የምንጣሮ ስራው እንዲጀመር አድርጓል።ግድቡ በመጪው ሐምሌ ውሃ ለመሙላት የተያዘውን እቅድ እንዲሳካ ከወዲሁ የደን ምንጣሮ ስራውን ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ 2ሺህ አባላት የያዙ ኢንተርፕራይዞች ወደ ስራው ገብተዋል። ኤጀንሲው የምንጣሮ ስራውን በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወን የቅርብ ክትትል ያደርጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የጤና፣ የጸጥታ እና ሌሎችም ቡድኖች ምንጣሮውን ከሚያካሂዱ ኢንተርፕራይዞች ጋር አብረው ወደ ስፍራው ገብተዋል ብለዋል፡፡ለስራው የሚያስፈልግ በጀት እና ሌሎች ግብአቶች ለኢንተርፕራይዞቹ መቅረቡን አቶ በሽር ተናግረዋል።አጠቃላይ ለምንጣሮ ስራው 32 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት እንደተያዘለትም ከዋና ዳሬክተሩ ገለጻ ለማወቅ ተችሏል፡፡በደን ምንጣሮ ስራው መሳተፍ የጀመሩ ኢንተርፕራይዞች በበኩላቸው ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቀው ለማስረከብ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

#ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በአሰገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የ25 አመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት፡፡

ተከሳሽ ደስታ ገበየሁ የተባለ ግለሰብ ቀኑ ነሀሴ ወር 2011 ዓ.ም ዕድሜቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆነ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ክልል ውስጥ በሚገኝው ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመባቸው በመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዐቃቂ ቃሊቲ ምድብ ፅ/ቤት የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627(1) ተላልፎ በመገኘቱ አራት ክሶችን መስርቶበታል፡፡ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱን ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ ማስረጃ አቅርቦ በማሰማቱ እንዲሁም ተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ ሊያስተባብል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ ነህ በማለት ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ60 አመት እንዲቀጣ የፈረደበት ቢሆንም የተከሰሰበት ድንጋጌ ጣሪያው 25 ዓመት በመሆኑ በ 25 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሴቶችና ህፃናት ወንጀል ጋር ተያይዞ ከመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ 19 የምርመራ መዝገቦች ቀርበው የተጣሩ ሲሆን በ8 መዝገቦች ላይ ክስ ተመስርቶ ለችሎት መቅረባቸውን የአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ጽፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሲሳይ ጎኣ የገለጹ ሲሆን ቀሪዎቹ መዝገቦች በምርመራና በመወሰን ሂደት ላይ እንደሆኑ ምክትል ኃላፊ አብራርተዋል፡፡
በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ድርጊቱ ተፈፅሞ ሲያገኝም በተቻለ ፍጥነት ለፓሊስ ማሳወቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

Via FDRE Attorney General
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ሶስት ወራት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል!

ባለፉት ሶስት ወራት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ከኅብረተሰብ ተሳትፎ መገኘቱን የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገለጸ።ገቢው የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ከተረጋገጠበት ካለፈው መጋቢት እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል።

#Walta
@YeneTube @FikerAssefa
በቦሌ ሚካኤል አየር አንባ ት/ቤት አካባቢ ዛሬ እኩለ ቀን ለደቂቃዎች የቆየ ተኩስ ልውውጥ ተፈጥሮ ነበር፡፡

ከተኩስ ልውውጡ በኋላ ካፒታል ጋዜጣ በቦታው በመገኘት እንደታዘበችው በጥይት ተመቶት የወደቀ ሆኖም በሸራ የተሸፈነ ሰው መኖሩን አረጋግጧል፡፡ እንዲሁም አንድ ግለሰብ መሬት ላይ ተኝቶ ማየት የተቻለ ሲሆን ግለሰቡ እንቅስቃሴ ያሳይ እንደነበር የካፒታል ዘጋቢ ከርቀት ለመታዘብ ችሏል፡፡ባካባቢው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ለካፒታል ጋዜጣ እንዳረጋገጡት የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከዝርፊያ ጋር የሚገናኝ ነው፡፡ በዘራፊነት የተጠረጠሩት ግለሰቦችም የፌደራል ፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ለወንጀል የተሰማሩ የነበሩ ሆኖም አባል ያልሆኑ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡የአይን እማኞች እንደገለፁት የተኩስ ልውውጡ ከሁለቱም ወገን ማለትም ከፀጥታ አካላት እንዲሁም ተጠርጥረው ከሚያመልጡት ወገን እንደነበር አስረድተዋል፡፡ተጠርጣሪዎቹ በመኪና ለማምለጥ ጥረት እያደረጉ እንደነበር የገለፁት የአይን እማኞች መኪናዋ በጥይት ተመትታ ትዛዝ ሆቴል የሚባል አካባቢ ቆማለች፡፡ባካባቢው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉዳዩ ገና በመጣራት ላይ ያለ ነው ሆኖም ከዝርፊያ ጋር የሚገናኝ ነው ብለዋል በቦታው ለነበረው የካፒታል ዘጋቢ፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ገዥዉ ፓርቲ የኢትዮ ቴሌኮምን ከፊል ድርሻ ለመሸጥ እሄደበት ያለውን ጥድፊያ በአስቸኳይ እንዲያቆም ኢዜማ አሳሰበ፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ገዥዉ ፓርቲ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ ለመሸጥ እያደረገዉ ያለዉ ሂደት ግልጸኝነት የጎደለዉና ጥድፊያ የተሞላበት ነዉ ብሏል፡፡የኢኮኖሚ ዘርፎች ተወዳዳሪነት ዋነኛ ሞተር የሆነን የቴሌኮም ኢንደስትሪ እንደ ተራ መረጃ ማስተላለፍያ ብቻ በማየት ለውጪ ድረጅት ለመሸጥ የጀመረው መንገድ ፍፁም አደገኛ እና የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ሲል ጠይቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa