በኮቪድ ምክንያት ከማረሚያ ቤት እንዲለቀቁ ተወስኖላቸው እስካሁን በማረሚያ ቤት የሚገኙ እንዳሉ ታወቀ!
የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጲያ መግባቱን ተከትሎ አንድ ዓመት እና ከዛ በታች የማረሚያ ቤት የቆይታ ጊዜ የቀራቸው እንደሚለቀቁ ከምግስት ወገን ቢነገርም ስም ዝርዝራቸው ተላልፎ እስካሁን ያልተፈቱ ግለሰቦች መኖራቸው ታወቀ፡፡
የታራሚ ቤተሰቦች ለ @addismaleda
እንዳስተወቁት በመንግስት ውሳኔ መሰረት ሁሉም መለቀቅ እየነበረባቸው ሳይለቀቁ የቀሩ እንዳሉ እና ለዚህም ምክንያት ደግሞ ምንድን እንደሆነ በሚጠይቁበትም ወቅት ይቅርታ ቦርድ አላየውም መለቀቅ የሚችሉት ደግሞ ይቅርታ ቦርድ ተቀብሎት ሲፈርምበት ብቻ ነው የሚል ምላሽ ከማረሚያ ቤት እንዳገኙ ለማወቅ ተችሏል። አሁን ደግሞ ይሄን ለማድረግ የይቅርታ ቦርድ አባላቶች መሰብሰብ አለመቻላቸው እንዳይለቀቁ አድርጓቸዋል፤ በማለት ተደጋጋሚ ምላሽ ከማረሚያ ቤቱ እየተሰጣቸው እንደሆነ የታራሚዎቹ ቤተሰቦች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡በመጀመሪያዎቹ የኮቪድ 19 የኢትዮጵያ የገባበት ወቅት ለታራሚዎቹ ተወስኖ የሚለቀቁት ታራሚዎች ስም ዝርዝር የወጣው ከሶስት ወር በፊት እንደሆነ የሚገልጹት ቤተሰቦች ነገር ግን ይለቀቁ ከተባሉት እና ስማቸው ከተላለፉ ሰዎች ውስጥ 17 የሚሆኑት እንዳልተለቀቁ ተናግረዋል፡፡
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወባ በሽታ ስርጭትን ለመከላከል ከ6 መቶ 37 ሺ በላይ የአልጋ አጎበር ስርጭት እና የቤት ለቤት የኬሚካል ርጭት ማካሄድ መጀመሩን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ፡፡የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ከአጋር ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የወባ በሽታ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ በሚታይበት ሸርቆሌ ወረዳ የአጎበር ስርጭቱን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ በክልሉ ወቅታዊ የኮሮና ቫይረስን ከመከላከሉ ስራ ጎን ለጎን መደበኛ የጤና ስራዎችን እየተከናወኑ ነው፡፡
ምንጭ: የክልሉ መንግሥት ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ በክልሉ ወቅታዊ የኮሮና ቫይረስን ከመከላከሉ ስራ ጎን ለጎን መደበኛ የጤና ስራዎችን እየተከናወኑ ነው፡፡
ምንጭ: የክልሉ መንግሥት ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ሊደረግ ነው!
በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮቪድ-19 ክትባት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሊካሄድ እንደሆነ ይፋ ተደረገ። ደቡብ አፍሪካ ለዚህ የክትባት ሙከራ የተመረጠችው በዘርፉ ባሏት ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ያሉባትና ወረርሽኙም በፍጥነት እየተስፋፋባት በመሆኑ ነው።ይህ የክትባት ሙከራ ኦኤክስ1ኮቪድ-19 ክትባት የሚባል ሲሆን የኮሮናቫይረስን የሚያስከትለውን ሳርስ-ኮቪ-2 የተባለውን ቫይረስ ሰዎች እንዳይያዙ ለመከላከል የታለመ ነው።
#BBC

የቀድሞ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ሳንዱካን ደበበ የኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ(CEO) በመሆን መሾማቸው ታውቋል፡፡
በተያያዘ ዜና አቶ ሙሉቀን ቀሬ የኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ ተሹመዋል፡፡
ምንጭ: የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት
@YeneTube @FikerAssefa
በተያያዘ ዜና አቶ ሙሉቀን ቀሬ የኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ ተሹመዋል፡፡
ምንጭ: የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት ከተመነው የሲሚንቶ ዋጋ በላይ በሚሸጡ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
በሲሚንቶ ግብይት ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገበያ ሰንሰለቱ በማሶጣት እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ዋጋ ለማስተካከል የመሸጫ ዋጋ በመተመን ከፍብሪካ አውጥተው የሚያከፋፍሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶችና መመሪየውን አክብረው ለመስራት የተስማሙ የግል ነጋዴዎች ተመርጠው በቅርቡ ወደ ስራ መግባታቸው ይታወሳል፡፡የጥራት የንግድ አሰራርና ሪጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ እሸቴ አስፋው አንደገለጹት መንግስት አላስፈላጊ የሲሚንቶ ዋጋ ንረትን በመቆጣጠርና ዋጋ በመተመን የኮንስትራክሽን ዘርፉ እንዳይዳከም እየሰራነው፡፡
ከፋብሪካዎች ተረክበው የሚሸጡ አከፋፋዮች የሚሸጡበት የአንድ ኩንታል ዋጋ እንደየ ርቀቱ ከ245.60 ብር እስከ 388.10 ብር እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን አከፋፋዮች ግን በተቀመጡ ዋጋ እየሸጡ እንዳልሆነ በተደረገ የመስክ ምልከታ ተረጋግጧል፡፡ፋብሪካዎች የየእለት ምርታቸውን ሪፖርት እያደረጉ በመሆኑ ምርት ማጭበርበር አይቻልም ያሉት አቶ እሸቴ ከሰኔ15/2012 ዓ.ም ጀምሮ አከፋፋዮች የሸጡትን የሲሚንቶ ብዛት፣ የሸጡበትን የዋጋ መጠን እንዲሁም ለማን እንደሸጡና የገዠው አድራሻ የት እንደሆነ በየዕለቱ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባችኋል ያሉ ሲሆን ይህንን የማይፈፅም አከፋፋይ ከተገኘ በሸማቾች ውድድር ባለስልጣን በኩል በቀጥታ ከገበያ ውጪ እንደሚደረግ አስጠንቅቀዋል፡፡
በሌላ በኩል የአቅርቦት ችግሩን ለመፍታት ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትናንት ከሲሚንቶ አከፋፋዮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
- የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ።
አደጋው የደረሰው በትናትናው ዕለት ሲሆን በታራሚዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተገልጿል።አደጋው በትላንትናው ዕለት ከረፋዱ 5፡30 ጀምሮ ቃሊቲ በሚገኘው የአባላት መኖርያ ካምፕ የእሳት ቃጠሎ ደርሶ ነበር፡፡በማረምያ ቤቱ በደረሰው የእሳት አደጋም በህግ ታራሚዎች ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት እንደሌለ ነው ማረሚያ ቤቱ ያስታወቀው፡፡ነገር ግን በእሳት አዳጋው ምክንያት በካምፕ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አባላት ንብረታቸው ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።ቃጠሎው የተነሳበት ቦታም ታራሚዎች ከሚገኙበት ግቢ ውጪ ያለ ቦታ በመሆኑ ከህግ ታራሚዎች ጋር የሚያገኛኘው ነገር እንደሌለም ማረሚያ ቤቱ አስታውቋል፡፡ቃጠሎው በአካካቢው ማህበረሰብ እና በአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ርብርብ በሰው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡የንብረት ጉዳት እና መኖሪያቸው ለተቃጠለባቸው አባላት ሌላ ማረፊያ ቦታ የተዘጋጀ ተዘጋጅቷል ተብሏል።
Via Ethio FM

በሀገር አቀፍ ደረጃ 273 መካኒካል ቬንትሌተሮች ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን ዝግጁ ሆነዋል!
በሀገር አቀፍ ደረጃ 273 መካኒካል ቬንትሌተሮች ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን ዝግጁ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ አስታወቁ፡፡ በሌላ መልኩ 300 መካኒካል ቬንትሌተሮች ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡በተጨማሪም 32 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማዕከላት በሀገሪቱ የሚገኙ ሲሆን ይህን ቁጥር ወደ 51 ከፍ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ አሁን ላይ ያሉት የምርመራ ማዕከላት በቀን እስከ ስምንት ሺህ ናሙና የመመርመር አቅም እንዳላቸውም የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል፡፡
Via ENA/Asham TV

በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 03 ዛሬ ከቀኑ 8:10 አካባቢ ካለሾፌር የቆመ ኤፍ ኤስ አር(FSR)መኪና ተንደርድሮ በመምጣት አንድ ባጃጅ በመግጨቱ የባጃጁ ሹፌር ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።ሾፌሮች መኪና በሚያቆሙበት ጊዜ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አሳስቧል።
መረጃው፦ የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ የሚዲያ ዋና ክፍል ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
መረጃው፦ የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ የሚዲያ ዋና ክፍል ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
ሰርቢያዊው የወቅቱ የአለም ቁጥር 1 የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ኖቫክ ጆኮቪችና ባለቤቱ ጄሌና በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን "Sport klub" የተባለ የሰርቢያ ሚዲያን ጠቅሶ የስፔኑ ኤል ቼሩንጉይቶ ቲቪ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር ተቃውመውታል ተባለ።
የአረብ ሊግ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ በዛሬው እለት በማካሄድ ላይ ይገኛል።የአረብ ሊግ በስብሰባው ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብን ጨምሮ የሊቢያ ጉዳይንም በመመልከት ላይ ይገኛል።በዚህ ስብሰባ ላይም የሊጉ አባል ሀገራት የሆኑት ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር የግብፅን ከታላቁ የውሳኔ ሀሳብን እንደማይቀበሉት አስታውቅዋል።
#FBC

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 185 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3775 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰማንያ አምስት (185) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4848 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3775 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰማንያ አምስት (185) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4848 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 185 ሰዎች ሲሆኑ ከአንዱ በስተቀር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(47) ሴት(138) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ3 ወር-80 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 115 ሰዎች (81 ከአዲስ አበባ፣ 23 ከአማራ ክልል፣ 6 ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ከሐረሪ ክልል፣ 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና 1 ትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1412 ነው።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(160)[105ቱ ተመላሾችና በማቆያ የነበሩ]፣ ከኦሮሚያ ክልል(7)፣ ከአማራ ክልል(2)፣ ከትግራይ ክልል(1)፣ከሶማሊ ክልል(2)፣ ከአፋር ክልል(4)፣ ከደቡብ ክልል(7)፣ ከሀረሪ ክልል(1) እና ከጋምቤላ ክልል(1) በድምር 185 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4848 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 38 ነው።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ ምንም ሞት ያልተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 75 ነው።

የደቡብ ኦሞ ዞን ራሱን ችሎ በክልልነት ለመደራጀት ለመምከር የዞኑ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 5ዓመት 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በነገው ዕለት እንደ ሚያካሂድ ተገለፀ፡፡
ምክር ቤቱ በሚያካሂደው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ የተለያዩ አራት አጀንዳዎችን መሠረት ያደረገ ሲሆን በዋናነት አንደኛ አጀንዳ ሆኖ የቀረበው የደቡብ
ኦሞ ዞን እራሱን ችሎ በክልል የመደራጀት ህገ መንግታዊ ጥያቄ በ2011 ዓ/ም ተቀብሎ በማፅደቅ ለክልሉ ም/ቤት በማቅረብ ምላሹ ያለበትን ደረጃ በመምከር የራሱን አቋም እንደሚገልጽ የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ናኪያ አናኩሲያ ተገልጿል፡፡አክለውም በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ የዞኑ ተወላጅ የሆኑና በደቡብ ክልል ደረጃ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ና የምክር ቤት አባላት በጉባኤው ተሳታፊ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ:የዞኑ መንግሥት ኮምኒኬሽን መምሪያ

የጤና ሚኒስቴር በቀን 15000 ሰዎችን ለመመርመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስተወቀ!
የጤና ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ 19 እለታዊ ምርመራን ወደ 15000 ከፍ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡በአገራችን የኮሮና ቫይረስ መገኘቱ ሪፖረት ከተደረገበት ከመጋቢት 4/ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎችን አስመልክቶ ዛሬ ሰኔ 16/2012 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በተሰጠው መግለጫ እንዳብራራው በየጊዜው ከፍ እያለ የመጣውን የመመርመር አቅም በአሁኑ ሰኣት በብሔራዊ ደረጃ 8000 ማድረስ የቻለ መሆኑን አስታውቋል፡፡ይሁን እንጂ ከወረርሽኙ መዛመት ጋር በተጓዳኝ የምርመራ አቅምንም ለማሳደግ ተገቢ መሆኑን በመታመኑ በቅርቡ 19 ተጨማሪ ምርመራ ጣቢያዎች ወደ ስራ እንደሚገቡ እና የምርመራ አቅምንም በቀን ወደ 15 ሽሕ ከፍ እንደሚያደርገው ታውቋል፡፡

የብሮድካስት ባለስልጣን ለሶስት የሬድዮ ጣብያዎች ፈቃድ ሰጠ!
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለሶስት አዳዲስ የሬድዮ ጣብያዎች ፈቃድ ሰጠ። ፈቃድ ያገኙት ኢትዮ ዋርካ መልቲ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን፣ ትርታ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና አዲስ ኦንላይን የሚዲያና የግብይት ስራዎች ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መሆናቸው ተገልጿል።
ምንጭ: ኢዜአ

የጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ቢመክርም ያለ ውሳኔ ተበተነ!
የህዳሴውን ግድብን አስመልክቶ ትላንት ሰኞ ሰኔ 15፤ 2012 በቪዲዮ ኮንፍረንስ ስብሰባውን ያካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት፤ ግብጽ ባቀረበቸው “የግልጽ ጉባኤ ይካሄድልኝ” ጥያቄ ላይ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ ቀረ። ምክር ቤቱ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ውይይታቸውን እንዲቀጥሉ በማሳሰብ ያለ ውሳኔ ተበትኗል።በትላንቱ ስብሰባ የሰኔ ወር የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንት የሆነችው ፈረንሳይ፤ ሶስቱ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ለምክር ቤቱ የላኳቸውን ደብዳቤዎች ለአባል ሀገራት አቅርባለች። አስራ አምስቱ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት በሶስቱ አገራት መካከል የተጀመሩ የሶስትዮሽ ድርድሮችን በሙሉ ድምጽ መደገፋቸውን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በኒው ዮርክ ያሉ ምንጮቼ ነግረውኛል ብላለች።
Via Ethiopia Insider

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 160 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ከነዚህም ውስጥ 55 ሰዎች አድራሻቸው አዲስ አበባ ሲሆን የቀሩት 105 ሰዎች ደግሞ በአዲስ አበባ በሚገኙ አስገድዶ ማቆያ ውስጥ ከሚገኙ የስደት ተመልሾች መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡በሌላ በኩል በትላንትናው እለት 81 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸው ተገልጿል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 15
👉ቦሌ 5
👉ጉለሌ 19
👉ልደታ 0
👉ኮልፌ ቀራንዮ 2
👉ቂርቆስ 6
👉አራዳ 0
👉የካ 2
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 3
👉አቃቂ ቃሊቲ 2
👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 1
#AMN