YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጣሊያን ዛሬ ከ6,557 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን 793 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። በአጠቃላይ ጣሊያን 53,558 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ በሀገሪቱ 4,825 ሰዎች ሞተዋል።

የሟቾችና የተጠቂዎች ቁጥር በጣሊያን ዛሬ አሻቅባል ከሌላው ጊዜ በተለየ።
@Yenetube @Fikerassefa
ስፔን ዛሬ ከ3,355 ሰው በቫይረሱ ተጠቅቷል 233 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። በአጠቃላይ ስፔን 24926 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስከ ዛሬ በስፔን 1326 ሰው ሞቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
ኮሮና ቫይረስ ዛሬ ተጠቂ ቁጥር እና ምሟች ሟቾች :-

- ኢራን: 966 አዲስ ተጠቂ ,123 ሰዎች ዛሬ ሞተዋል

- ቤልጂየም: 558 አዲስ ተጠቂ የተገኘ ሲሆን 30 ሰዎች ደግሞ ዛሬ ሞተዋል

- ኦስትሪያ: 278 አዲስ ተጠቂ

- እስራኤል: 178 አዲስ ተጠቂ

- ማሌዢያ: 153 አዲስ ተጠቂ እና የ1 አንድ ሰው ሞት ዛሬ ተመዝግቧል

- ታይላንድ: 89 አዲስ ተጠቂ

- ፊሊፒንስ : 77 አዲስ ተጠቂ

@Yenetube @Fikerassefa
#NewsAlerts

በአለም ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ቁጥር ከ300,000 በለጠ። ዛሬ ብቻ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ቁጥር ከ50,000 በላይ መሆኑም ተነግሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
አምባሳደር ፍፅም አረጋ

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የኮሮና ቫይረስ ረስፖንስ ቲም በዲሲና አካባቢው በማስተባበር በኢትዮጵያ የቫይረሱን ስርጭትን ለመግታት የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ በዓይነት በማሰባሰብ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ ጤና ሚ/ር ተልኳል::

ድጋፉ በተለያየ መልክ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታችን ነው:: ከኤምባሲያችን ራቅ ያለ ቦታ የሚገኙ በየኮሚኒቲው ወይም አመቺ በሆነ መንገድ በማሰባሰብ በዓይነት ቢልኩ ለጤና ሚኒስቴር ለማድረስ ጥረት እናደርጋለን::
@Yenetube @Fikerassefa
#NewsAlert

የኤርትራ ጤና ሚንስቴር ዛሬ ምሽት የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ አስመራ ተገኝቷል ብሏል ግለሰብ የ39 አመት ኤርትራዊ ሲሆን ከኖርዌይ ወደ አስመራ እንደመጣም የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሀውልቲ በቲውተር ገፅቸው ገልጰዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#NewsAlert

ግብፅ ከመቶ ሺ በላይ መስጅዶቿን እና ቤተክርስቲያኖችን እንዲሁም ፒራሚዶቿን ለ2 ሳምንት ዘግታለች።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የግብፅ መንግስት ወቀሳን አስተናግዷል ምክንያቱም ትላንት የሰላት ፕሮግራም መደረጉ ኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ይሆናል በሚል መሆኑን ተመልክተናል።

ግብፅ 285 በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ 8 ሰዎች በዢው ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#NewsAlert

የጁቬንቱሱ የፊት መስመር ተጫዋች ፖውሎ ዲባላ ኮሮና ቫይረስ ተይዟል።

@Yenetube @Fikerassefa
#Newsalert

በኢትዮጵያ ሁሉም ዋና የቢራ ኩባንያዎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሠራተኞችን ሊለቀ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡ ምክንያቱም ስራ ድንገት በመቆሙ ነው።

@Yenetube @FikerAssefa
ምክር አዘል መልክት:- ከእሸት በቀለ

በአራቱም የኢትዮጵያ አቅጣጫዎች የቅዳሜን መሰል ገበያዎች የገጠሩ ሰው ከከተሜ የሚገናኝባቸው ናቸው። ሺህዎች በሚገናኙባቸው የገበያ ቀናት ገበሬ እህል ሸጦ ላምባ እና ጨው ይሸምታል።

ኮሮና በእነዚህ ገበያዎች ሾልኮ ገጠር የገባ ቀን ጉድ ይፈላል።

@Yenetube @Fikerassefa
#Newsalert

ፓውሎ ማልዲኒ እና ልጁ በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#Update የኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊሶች አዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም የምሽት ጭፈራ ቤቶች ተከፈተው ያሉትን በማዘጋት ላይ ናቸው። ትላንት ዶ/ር አብይ አህመድ እንዲዘጉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
14 ቀን ለይቶ ማቆያት የሚጀምረው ሰኞ ነው!!

ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡ ሁሉም መንገደኞች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የ14 ቀናት በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ ሰኞ ከጠዋቱ 12 ጀምሮ መፈፀም ይጀምራል::

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በስካይ ላይት እና ጊዮን ሆቴሎች ለ14 ቀናት ተለይተው ይቆያሉ። ቆይታቸውም በራሳቸው ወጪ የሚሸፈን ይሆናል።

ዲፕሎማቶች በኤምባሲዎቻቸው ተለይተው ይቆያሉ። የትራንዚት ተጓዦችም እስከ ቀጣዩ ጉዟቸው ድረስ በስካይ ላይት ሆቴል ተለይተው የሚቆዩ ይሆናል።

Via:- MoHE
@YeneTube @FikerAssefa
#ምእራብ ኦሮምያ የኮሮና ቫይረስ በቂ መረጃ አያገኙም !!

በኢትዮጰያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች ስለ ኮቪድ19 መረጃ እያገኙ አይደለም ::

በኢትዮጵያ ጥሪ ባደረጉ ቁጥር ስለ ኮሮና ቫይረስ መከላከል ትምህርታዊ መልእክት ያገኛሉ - ግን ጥሪ ማድረግ ከቻሉ ብቻ ነው (ምእራብ ኦሮምያ ተጠቃሚ አይደለ) ፡፡

በምእራብ ኦሮሚያ ውስጥ በመንግስት ለተከታታይ 3 ወራት ጊዜ የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎቶች መዘጋቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የጤናው ስጋት ላይ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ።

አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ያሉትን ማእራብ ኦሮምያን በማሰብ አስፈላጊ ነው
#ReConnectWithMyFamily
#ReConnectWithWestETH

ሰላም እደሩ
ቸር ወሬ ያሰማን
#ሼር
#NewsAlert

ኡጋንዳ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ እንዳገኘች ያሳውቀች ሲሆን ተጠቂው ትናንት ከዱባይ በአዲስ አበባ በኩል ወደ ኡጋንዳ የገባ የ36 አመት ኡጋንዳዊ ግለሰብ እንደሆነ ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካው ምክትል ፕረዝደንት Mike Pence እና ባለቤታቸው ተከታዊት እመቤት Karen Pence ተመርምረው ከኮረና ቫይረስ ነፃ ሆኑ። ምርመራውን ያደረጉት የምክትል ፕረዝደንቱ የስራ ባልደረባ ተመርምሮ ቫይረሱ ስለተገኘበት ነበር።

ቀደም ሲል ፕረዝደንት ትራምፕ ከብራዚሉ ፕረዝደንት(በቫይረሱ ፖዘቲቭ የሆኑ) ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል በሚል ከጋዜጠኞች በቀረበላቸው ተደጋጋሚ ጥያቄ እና ግፊት ተመርምረው ነፃ መሆናቸው ይታወሳል።

Via Maleda Media
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 2 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች የተገኙ ሲሆን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ብዛት 11 ደርሷል ።

@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

ተጨማሪ ሁለት ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

#አንደኛው

- በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሀገር የመጣ የ28 አመት ኢትዮጵያ ሲሆን ቤልጂየም እና ኔዘርላንድ የተጓዘ መሆኑ ተነግሯል።

- ግለሰቡ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ራሱን ለይቶ ማቆየቱ ተገልጿል

#ሁለተኛው

- የ34 አመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን መጋቢት 10 ነበር ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የቫይረሱን ምልክቶች በማሳየቱ ለይቶ ማቆያ ገብቶ በተደረገለት ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘበት ተነግሯል።

--------
ሁለቱም ታማሚዎች በጥሩ ሁኔታ ናቸው እንዲሁም ከዚህ በፊት የተገለፁት 8ቱ በቫይሩ የተጠቁትም ጤናቸው ጥሩ ላይ መሆናቸው ጤና ሚንስቴር ዛሬ በአወጣው መግለጫ አስታውቋል።

Via:- ጤና ሚንስቴር
@Yenetube @Fikerassefa
#መልካም_ሰንበት_ይሁንላችሁ

ከዚህ ፎቶ ብዙ ነገር ትማራላችሁ ሰንበት በትግራይ ክልል አካላዊ መራራቅን ተግብረወል።

@Yenetube @Fikerassefa
ከጃክ ማ ፋውንዴሽን የተላኩ የፊት መሸፈኛ ማስክ እንዲሁም ኮሮና ቫይረስን ለመመርመን የሚያስችሉ የህክምና መሳሪያዎች ዛሬ ቦሌ ኤርፓርት ደርሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በቦታው ተገኝተው በመረከብ ላይ ናቸው።

- ነገር ግን ቫይረሱን ለመከላከል ምንም አይነት የአካላዊ መራራቅ አልተመለከትንም እንዲሁም ምንጫችን እንደነገረን ሰላምታም መለዋወጣቸውን ነው።

#ባለስልጣናት_ለህብረተሰቡ_አርያ_መሆን_አለባችሁ

@YeneTube @Fikerassefa