YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#NewsAlert

በአሶሳ ከተማ በተለምዶ ጎንድል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ ተጠርጣሪ ግለስብ 9 ሰዎች ላይ በስለት በመውጋት ባደረሰው ጉዳት 4ቱ መሞታቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡በድርጊቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 5 ተጎጅዎች በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ፡፡

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጎንድል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጥር 21 /2012 ዓ/ም ረፋድ ላይ አንድ ተጠርጣሪ ግለሰብ የደረሰውን ጉዳት በማስመልከት መግለጫ የሰጡት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሀመድ ሀመደኒል እንዳሉት በከተማዋ አንድ ግለስብ ጩቤ እና ጦር በመያዝ በ9 ሰዎች ጉዳት ማድረሱና ከእነዚህም ውሰጥ 2 ህጻናትና 2 ወጣቶች ህይዎታቸው ማለፉን ነው የገለጹት፡፡ተጠርጣሪው ግለሰቡ በፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 5ቱ ተጎጅዎች በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና እተደረገላቸው መሆኑንም ኮሚሽነር መሀመድ ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪ ግለሰቡ የጸጥታ አካለት ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል ያሉት ኮሚሽነር መሀመድ ሀመደኒል ተጠርጣሪው የአእምሮ ተማሚ መሆን አለመሆኑም በህክምና በማረጋገጥ አስፈላጊው ምርመራ እንደሚደረግበትም ገልጸዋል፡፡የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ በበኩላቸው ግለሰቡ ሰብዓዊነት በጎደለው ድርጊቱ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ህጻናት እና ሴቶች ላይ ጉዳት በማድረስ ለሞትና ለአካል ጉዳት ዳርጎ በመሽሽ ላይ እያለ ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ አሰሳ በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡም መሰል የወንጀል ድርጊቶች በዜጎች ላይ እንዳይደር ፖሊስ በሚያደርገው የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ አስፈላጊውን ጥቆማ እና ድጋፍ እንዲያደርግም ምክትል ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን የተመኙት ኮሚሽነር መሀመድ በከተማዋ ጫትና ተዛማጅ ሱስ አስያዥ እጾች በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል አዕምሮ እና ስነ ምግባር ላይ እያሳደረ ያለውን ተጽዕኖ ለመቅረፍ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር እንደሚሰራም አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ: የክልሉ ብዙሃን መገናኛ
@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

የኤርትራ ጤና ሚንስቴር ዛሬ ምሽት የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ አስመራ ተገኝቷል ብሏል ግለሰብ የ39 አመት ኤርትራዊ ሲሆን ከኖርዌይ ወደ አስመራ እንደመጣም የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሀውልቲ በቲውተር ገፅቸው ገልጰዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#NewsAlert

ግብፅ ከመቶ ሺ በላይ መስጅዶቿን እና ቤተክርስቲያኖችን እንዲሁም ፒራሚዶቿን ለ2 ሳምንት ዘግታለች።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የግብፅ መንግስት ወቀሳን አስተናግዷል ምክንያቱም ትላንት የሰላት ፕሮግራም መደረጉ ኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ይሆናል በሚል መሆኑን ተመልክተናል።

ግብፅ 285 በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ 8 ሰዎች በዢው ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#NewsAlert

የጁቬንቱሱ የፊት መስመር ተጫዋች ፖውሎ ዲባላ ኮሮና ቫይረስ ተይዟል።

@Yenetube @Fikerassefa
#Newsalert

በኢትዮጵያ ሁሉም ዋና የቢራ ኩባንያዎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሠራተኞችን ሊለቀ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡ ምክንያቱም ስራ ድንገት በመቆሙ ነው።

@Yenetube @FikerAssefa
#Newsalert

ፓውሎ ማልዲኒ እና ልጁ በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#NewsAlert

ኡጋንዳ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ እንዳገኘች ያሳውቀች ሲሆን ተጠቂው ትናንት ከዱባይ በአዲስ አበባ በኩል ወደ ኡጋንዳ የገባ የ36 አመት ኡጋንዳዊ ግለሰብ እንደሆነ ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

ተጨማሪ ሁለት ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

#አንደኛው

- በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሀገር የመጣ የ28 አመት ኢትዮጵያ ሲሆን ቤልጂየም እና ኔዘርላንድ የተጓዘ መሆኑ ተነግሯል።

- ግለሰቡ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ራሱን ለይቶ ማቆየቱ ተገልጿል

#ሁለተኛው

- የ34 አመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን መጋቢት 10 ነበር ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የቫይረሱን ምልክቶች በማሳየቱ ለይቶ ማቆያ ገብቶ በተደረገለት ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘበት ተነግሯል።

--------
ሁለቱም ታማሚዎች በጥሩ ሁኔታ ናቸው እንዲሁም ከዚህ በፊት የተገለፁት 8ቱ በቫይሩ የተጠቁትም ጤናቸው ጥሩ ላይ መሆናቸው ጤና ሚንስቴር ዛሬ በአወጣው መግለጫ አስታውቋል።

Via:- ጤና ሚንስቴር
@Yenetube @Fikerassefa
#NewsAlert

የ2012 ምርጫ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደማይካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የምርጫ 2012 ኦፕሬሽን እቅድ እና የጊዜ ሰሌዳ ላይ የፈጠረውን ችግር ገምግሞ ያሳለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ቦርዱ በተፈጠረው ሁኔታ የተነሳ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምርጫውን ማካሄድ የማይቻለው መሆኑን በመረዳት ያወጣውን የጊዜ ሰሌዳ በመሰረዝ በሰሌዳው መሰረት መከናወን ያለባቸው ተግባራት ለጊዜው እንዲቆሙ መወሰኑን አስታውቋል።

የወረርሽኙ ሥጋት ተወግዶ ሁኔታዎች ሲመቻቹ እንደገና ግምገማ በማድረግ አዲስ የምርጫ ኦፕሬሽን እቅድና ሰሌዳ በማውጣት እንቅስቀሴውን የሚያስጀምር እንደሚሆንም ነው ያስታወቀው።

ቦርዱ ባደረጋቸው ምክክሮችና የዳሰሳ ጥናት ላይ በግልጽ የተለዩ፣ በኮቪድ 19 የማይስተጓጎሉ፣ የቦርዱን የምርጫ አፈጻጸም ዝግጁነት የሚጨምሩ፣ ሁኔታው ተቀይሮ ተቋሙ ወደ መደበኛ ተግባሩ ሲመለስ በተገቢው ሁኔታ ምርጫን ለማስፈጸም የሚያሥችል ሁኔታን የሚፈጥሩ ተግባራትን እያከናወነ መቆየት እንዳለበት ወስኗል፡፡

በህገ መንግስቱ በተቀመጠው መሰረትም በስራ ላይ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስልጣን ጊዜው ከሚያበቃበት አንድ ወር አስቀድሞ ቦርዱ አጠቃላይ ምርጫውን ማድረግ የማይችል መሆኑን ምክር ቤቱ ተገንዝቦ፣ ከዚህ አንጻር የሚሰጠው ውሳኔ ቢኖር ለመነሻነት ያገለግለው ዘንድ ይህ ውሳኔ እንዲሁም ቦርዱ ያደረገው የዳሰሳ ጥናት ሰነድ ለህዝብ ተወካዮች እንዲተላለፍለት ምርጫ ቦርዱ ወስኗል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
#Newsalert

በሳምባ ኢንፌክሽን ዛሬ ማለዳ ህይወታቸው ያለፈው የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮናቫይረስ እንዳልነበረባቸው በላብራቶሪ ምርመራ መረጋገጡ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

@Yenetube @Fikerassefa
#NewsAlert
የቅድመ ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ሳይማሩ እንደማይመረቁ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

ለሳይንስና ከፍትኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑና በስራ ላይ ያሉ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ከመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ማቋረጣቸው ይታወሳል።የሳይንስና ከፈተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፥ በቅድመ-ምረቃ መርሃ ግብር በቴክክኖሎጂ ትምህርት ማስቀጠል ባለመቻሉ ተማሪዎች ሳይማሩ አይመረቁም ብለዋል።“በቴክኖሎጂ የቅድመ-ምረቃ ትምህርት ማስቀጠል ከሞላ ጎደል አልተቻለም፤ እያንዳንዱ ተማሪ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ የሚማረውን እያነበበ፤ ምዕራፍ በምዕራፍ፣ ሞጁል በሞጁል ተምሮ ምዘና እየተደረገለት አልቆየም።

በዚህ ረገድ ያልመጣን፣ የትምህርቱን ይዘት ያላጠናቀቀን ተማሪ ተምሯል ብሎ ወስዶ፤ ይህንን ኮርስ ጨርሰሃል፣ በዚህ መልኩ ተገምግመሃል እና ይህንን ውጤት አግኝተሃል ብሎ ውጤት ሰጥቶ ማስመረቅ በትምህርትም በአሰራርም ወንጀል ነው፤ መሰል አካሄድ አይፈቀድም፤ እንደዚህም አይሆንም!” ብለዋል።የድህረ ምረቃ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪ መርሃ-ግብር በቴክኖሎጂ ማድረስ በመቻሉ ይመረቃሉ ከሚል ድምዳሜ ተደርሷል።ሆኖም የቅድመ-ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ምረቃ በኮቪድ 19 የስርጭት መጠን የሚወሰን እንደሆነ ነው ዶክተር ሳሙኤል የተናገሩት፤ ይህም የምረቃ ዓመታቸውን ተገማች የማያደርገው ነው።

ተጨማሪ ለማንበብ👇👇👇
https://telegra.ph/MoSHEs-statement-on-students-graduation-05-28
YeneTube
የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) አገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል አሉ! የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት አጭር ሪፖርት ኮቪድ-19ኝ መከላከልን ከግምት ውስጥ ያስገባ የምርጫ ስነምግባር፣ ደንብና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ሃገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ማለታቸውን ኢሳት አስታወቀ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ ስርጭት…
#NewsAlert

በኮቪድ 19 ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ አሁን ላይ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ማካሄድ እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ምከረ ሀሳብ አቀረበ!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምኝጃዎች በሚመለከት ለምክር ቤቱ ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።በቀረበው ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነሰ ባይሆንም የቅድመ መከላከል እና ስርጭቱን በመግታት ሂደት ውስጥ በሁሉም ደረጃ አቅም ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሁሉም ክልሎች የተሰራጨ ሲሆን፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ 19 በሽታ ከገተኘባቸው ውስጥ 95 በመቶ የታወቀ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል።እስከ መስከረም 6 2013 ዓ.ም ድረስ 1 ሚሊየን 165 ሺህ 647 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በዚህም 66 ሺህ 224 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን እና 1 ሺህ 45 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉንም አስታውቀዋል።አሁን ላይ የመመርመርም ሆነ ክትትል የማድረጉ አቅም በማደጉ በነሃሴ ወር ብቻ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ቤት ለቤት መጎብኘት መቻሉን እና ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን መለየት እንዲሁም ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ማከናወን መቻሉንም በሪፖርቱ ላይ አብራርተዋል።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን በተሻለ ከማወቅ በተጨማሪ የመከላከል እና የመቆጣጠር አቅምን በከፍተኛ ደረጃ መፍጠር መቻሉንም ገልፀዋል።ከእነዚህ ውስጥ አመራሩ ትኩረት አንዲሰጥ ማድረግ መቻሉ፣ በሚዲያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መከናወኑ፣ የቅኝት ስራ ላይ የሚያስፈልጉ አደረጃጀቶችን ማስፋት መቻሉ እንዲሁም ከ10 ሺህ 500 በላይ የድንገተኛ ምላሽና የበሽታ ቅኝት የሚከናውኑ ቡድኖችን ማደራጀት መቻሉንም አስታውቅዋል።የላቦራቶሪ ናሙና መሰብሰቢያ ቦታዎችን በየወረዳው መስፋት መቻለኩንም በሪፖርታቸው አንስተዋል።

የምርመራ አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል ያሉት ዶክተር ሊያ፥ የጤና ተቋማትና የአልጋ ቁጥር ማሳደግና የቤት ውስጥ ህክምና አገለግሎት ማስጀመር መቻሉንም አንስተዋል።የመመርመሪያ ኪቶች ማምረቻም ማቋቋም እንደተቻለም በሪፖርታቸው ላይ አቅርበዋል።

በዚሁ መሰረት የቀጣይ ወራት ትንብያ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር፣ የሞት ቁጥር እና ወረርሽኙ ከፍተኛውን ጣሪያ የሚደርስበት ጊዜ በዋናነት የሚወሰነው በአካላዊ መራራቅ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምበል በሚተገበርበት ደረጃ ነው ብለዋል።ለምሳሌ ያክል አካላዊ ርቀት 5 በመቶ እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ 50 በመቶ የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ መተግበር ከተቻለ ምንም አይነት እርምጃ ባይወሰድ ሊደርስ ከሚሽለው የበሽታ ስርጭት እና ሞት አንጻር በ92 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ተመላክቷል።

እነዚህና ሌሎችም ነጥቦችን ታሳቢ ያደረጉ በርካታ እርምጃዎች ሲወሰዱ የቆዩ ሲሆን፥ በቀጣይም በተሻለ ደረጃ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።በዚሁ መሰረት ሀገራዊ ምርጫን የማካሄድ ሂደት ውስጥ በርካታ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ምልከታ የተደረገባቸው ሲሆን፥ በአንዳንዶቹ በወረርሽኝ ወቅት ምርጫ ተካሂዷል፤ በአብዛኞቹ ደግሞ እንዲተላለፍ ተደርጓል።

በኢትዮጵያም በሽታውን የመከላከልም ሆነ የመቆጣጠር ዝግጅነቱ ዝቅተኛ በነበረበት ወቅት ምርጫን ማከናወን ስጋቱ የበለጠ የሚያሳድገው በመሆኑ በተላለፈው ውሳኔ እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል።ወረርሽኙ አሁንም የጤና ስጋት ቢሆንም ቀደም ሲል ከነበሩት ለምዶች እንፃር ከፍተኛ አለመሆኑ፣ ኮቪድ 19 በሽታ ረዘም ላለ ጊዜ አብሮን ሊቆይ ሰለሚችልና አንፃራዊ በሆነ ሰዓት ምርጫው ሲራዘም ከነበርንበት ሁኔታ ለስርጭቱ የተሻለ መረጃ ያለን በመሆኑ ቀደም ሲል ከነበረበት በተሻለ የመከላከል ሁኔታዎች በመኖራቸው፣ የህብረተሰቡ ግንዛቤ መሻሻል በማሳየቱ፣ የማስክና የሳኒታይዘር ምርት በሀገር ውስጥ በስፋት በመኖሩ፣ የጤና ተቋማት ዝግጁነት እና ግብአት አቅርቦት መሻሻሉ፣ የምርመራ ኪት ማምረትን ጨምሮ የላቦራቶሪ አቅንም ማገድና የዘርፈ ብዙ ምላሽ በተሻለ ሁኔታ የሚገኝ መሆኑ እንዲሁም የሀራት የምርጫ ተሞክሮን በማየት የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎቸን አማልቶ ሀገራዊ ሁኔታን ማካሄድ ይቻላል።

👉 ከዚህ በፊት ከነበረው የምርጫ ሂደት በተለየ መልኩ ኮቪድ 19ኝ መከላከልን ከግምት ውስጥ ያስገባ የምርጫ ስነ ምግባር ደንብ እና ማስፈጸሚያ ነነሪያዎችን ማዘጋጀትና በተዘጋጁ ዝርዝሮች መሰረት በሁሉም ደረጃ በበቂ ዝግጅቶች ወደ ትግበራ መግባት ያስፈልጋል።

👉 በዚህ ሂደት ውስጥ አንድ አንድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ ስርጭት ከተከሰተ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋል ሲል ሚኒስቴሩ ምክረ ሀሳቡን አቅርቧል።

በቀረበው ሪፖርትና እና መክረ ሀሳብ ላይ የምክር ቤቱ አባላት አስተያየት እየሰጡ ሲሆን፥ ከተወያዩብ በኋላ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

በሀገር አቀፍ ደረጃ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ነገ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ይፋ ይደረጋል ተባለ!

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች በቀጣይ የትምህርት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ውይይት እያካሄዱ ነው።ውይይት እየተካኔደባቸው እና ውሳኔ ከሚያገኙ ጉዳዮች መካከል የመደበኛ ትምሀርት የሚጀመርበት ቀን፣የ8ኛና 12ኛ ክፍል ክልላዊ እና ሀገራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን እንዲሁም በግል ትምህርት ቤቶች ላይ እየቀረቡ ባሉ ቅሬታ ላይ ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን።ከዚህ በተጨማሪም አዲሱ የትምህርት ስርዓት ዝግጅት አካሄድ እና ሁኔታ በውይይቱ ላይ የሚገመገም እና ውሳኔ የሚሰጠው ይሆናል። የጎልማሶች ትምህርት አሰጣጥና አፈፃፀምም በውይይቱ ውሳኔ ከሚያገኙ ጉዳዬች መካከል ነው።በውይይቱ ላይ የተደረሰውን ውሳኔም ነገ በ 9:00 ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።

[MoE]
@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥቅምት 30 በማይካድራ ከተማ የነበረው የሰዎች ግድያ “በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅር እና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን” የተፈጸመ መሆኑን ገለጸ። ድርጊቱንም “ግፍና ጭካኔ የተሞላበት፤ በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል” ሲል ጠርቶታል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛውን አገር አቀፍ የመጨረሻ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ!

የድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 28/2013 ዓም እንዲሆን ተወስኗል።

የጊዜ ሰሌዳው ከላይ የቀረበውን ይመስላል።

@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

በትግራይ ጉዳይ ላይ የተካሄደው የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም/ቤት ስብሰባ ያለስምምነት መጠናቀቁ ተገለፀ!

በአየር ላንድ ጠሪነት ትላንት ማምሻውን በኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ ጫና ለማድረግ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም/ቤት ያደረገው ስብሰባ ያለስምምነት መጠናቀቁን ዲፕሎማቶችን ዋቢ በማድረግ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ። በዚሁ ስብሰባ ላይ የም/ቤቱ ቋሚ አባላት ሩሲያ እና ቻይና እንዲሁም ተለዋጭ አባሏ ህንድ በአገሮች ሉዓላዊነት እና የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት ነው በሚል የታቀደውን የጋራ መግለጫ የማውጣት ፍላጎት መቃወማቸው ተገልጿል።

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️
#NewsAlert

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንትና ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት የቀድሞው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ተነስተው በምትካቸው የአየር መንገዱ ቦርድ አባል የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ ተሹመዋል።አቶ ግርማ ዋቄ ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ መመደባቸውንም ምንጮቹ ገልጸዋል።

አቶ ግርማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመደቡት ለአንድ ዓመት ብቻ እንደሆነና ዋና ተልእኳቸውም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የተረጋጋ የማኔጅመንት ቡድን መገንባት እንደሆነ ታውቋል።በአዲሱ የድርጅቱ አወቃቀር መሠረት፣ ከፕሬዚዳንቱ ስር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈጻሚ ሊኖር እንደሚችል ምንጮቹ ገልጸዋል።

አቶ ግርማን የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አድርጎ የመደባቸው በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል።የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ማሞ ምህረቱ መረጃውን እንዲያረጋግጡ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የአቶ ግርማ ዋቄ ሹመት ከመሰማቱ አስቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን መዘገቡ ይታወሳል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ተወልደ በህክምና ላይ ባሉበት አሜሪካን አገረ ሆነው ለተቋሙ ማኔጅመንት በላኩት የኢሜል መልእክት፣ በገጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በኃላፊነት መቀጠል እንዳልቻሉ ጠቅሰው፣ በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው በጡረታ መገለላቸውን አሳውቀዋል።

አቶ ተወልደ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚነትን የተረከቡት ከአቶ ገርማ ዋቄ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በአየር መንገዱ በተለያዩ ኃላፊነቶች ለ37 ዓመታት አገልግለዋል፡፡በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ አባላት ስብሰባ ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ምንጮቹ ፣ በዚህ ስብሰባ ለአየር መንገዱ አዲስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ምደባ ሊወሰን እንደሚችል ጠቁመዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

በመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪ አካል እንዲወሰን የሚያደርግ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ!


በመኖሪያ ቤቶች የሚደረገው የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ላይ፤ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እንዲሁም በክልሎች በሚቋቋም ተቆጣጣሪ አካል በሚወስነው መሰረት እንዲከናወን የሚያደርግ አዋጅ ዛሬ በፓርላማ ጸደቀ። የተቆጣጣሪ አካሉ “የሀገሪቱን ነባራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች” ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በየዓመቱ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚጸና የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ በአዲሱ አዋጅ ተደንግጓል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ዕለት ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆነው ይህ አዋጅ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደርን ለመደንገግ የተዘጋጀ ነው። በስድስት ክፍሎች እና በሰላሳ ሁለት አንቀጾች የተዋቀረው አዋጁ፤ ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ እና ዋጋ፣ ውል የሚቋረጥባቸውን አካሄዶች፣ የተቆጣጣሪ አካል ስልጣን እና ተግባር እንዲሁም የጥቆማ እና ቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓትን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በውስጡ አካትቷል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
👍56😁86👎5👀1
#NewsAlert

👉በአዲስ አበባ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባቸው ውሳኔ ተላለፈ።

🌟የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

🚧ከውሳኔዎቹ አንዱ ግንባታዎችን የሚመለከት ነው።

በዚህም የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ወጥተዋል።

🖱ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ፦

ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤
ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤
ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት
በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍33😁54👎1
#NewsAlert
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሱሉልታ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ የሆኑት አበበ ወርቁ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት መገደላቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች።

ታጣቂ ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ መሆኑን የገለጹት የዋዜማ ምንጮች፣ ከወረዳ አሥተዳዳሪው ጋር የነበረ የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በቡድኑ ታፍኖ መወሰዱን አስረድተዋል።

ዋና አሥተዳዳሪው፣ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊው እና በርካታ የጸጥታ ኃይሎች ታጣቂ ቡድኑ በስፋት ይንቀሳቀስበታል ወደተባለው "ሞዬ ጋጆ" በተባለው ስፍራ ሲደርሱ አማጺ ቡድኑ ድንገተኛ የእሩምታ ተኩስ እንደከፈተባቸው ተጠቁሟል።
በዚህም ዋዜማ ለጊዜው ቁጥራቸውን ማጣራት ያልቻለችው የጸጥታ ኃይሎች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለው ጫንጮ ሆስፒታል መግባታቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

ከጸጥታ ዘርፍ ኃላፊው በተጨማሪ በርካታ የጸጥታ ኃይሎች በቡድኑ ታፍነው መወሰዳቸውንም ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት መረዳት ችላለች።

ከወራት በፊትም በተመሳሳይ በዚሁ ታጣቂ ቡድን ጥቃት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ለገሰ ሥዩም መገደላቸውን ዋዜማ መዘገቧ ይታወሳል።

ሟቹ አበበ ከሁለት ዓመት በፊት የወረዳው ዋና አሥተዳዳሪ ሆነው ከመሾማቸው በፊት፣ የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ እንደነበሩ ዋዜማ የደረሳት መረጃ ያመለክታል።

[ዋዜማ]
@Yenetube @Fikerassefa
👍33😁7😭62